#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...መቼም ባልቻን በግልፍተኛነት የሚያማዉ አይገኝም የጃሪምን ግልምጫ ከምንም ሳይቆጥር ፈገግ ብሎ አሳለፈዉና፣ ወደኔ መጥቶ አቀፈኝ፡ እሱን
እዚህ መሆኔን እንዴት አወቀ አይሉትም፡ እኔም በችኮላ ተንከረፈፍሁ እንጂ የትም ብሄድ ከሲራክ ፯ ማምለጥ እንደማልችል ማስተዋል ነበረብኝ፡ እንኳንስ እንደዚህ ተንዘላዝዬለት ይቅርና! የንዝህላልነቱ ንዝህላልነት ደግሞ በገዛ ስልኬ ለሸዊት ስልክ መደወሌ፡ በዚህ ስሕተቴ
እንኳንስ የሲራክ ፯ቱ ባልቻ፣ የተናቀ የመንደር ደመኛ እንኳን ሊያገኘኝ ይችላል።
ባልቻ ከመግባቱ አፍታ ሳይቆዩ እሸቴ እና ሸዊት ተከታትለዉ ገቡ።
“አንቺ?” ስል ተቀበልኋት፣ ከእሸቴ ኋላ መጥታ ለሰላምታ ስታቅፈኝ፡
“እንዲያዉ እስካሁን እያለቀሰችም ቢሆን ገና አሁን ነው የምትደርሽልኝ ማለት ነዉ?” አልኋት፣ ለቂሜ መወጫ ጠበቅ አድርጌ እያቀፍኋት።
የአሁኑ መተቃቀፋችን ትርጉሙ የትየለሌ ነዉ: አንድም በሆስፒታል
ቆይታዬ ዓይንሽን ለአፈር ብያት የነበረዉን ኩርፊያ ጨርሼ ረሳሁላት፣አንድም ለቱናት አምጭልኝ ያልኋትን ወተት ያዉም የሚሆናትን መጠጫ ጡጦ ጭምር ስላመጣችልኝ አመሰገንኋት፣ አንድም ነባሩ
ሰላምታችን እንደዚህ ነዉ፡ እንደገና እቅፍ አድርጌ ጨመቅኋት።
"እ?"
“ኧረ እኔስ ወዲያዉ ነበር የደረስሁት”
“አዎ” አለ ባልቻ፣ ክንዱን ትከሻዋ ላይ እየጫነ፡ “ወተቱን ብቻ ይዛ
ስትመጣ አግኝቻት፣ እኔ ነኝ ጡጦም ጨምራችሁ አምጡ ብዬ ከእሸቴ ጋ መልሼ የላክኋቸዉ። መቼም ምን ዶክተር ብትሆን፣ በዕድሜ ታናሼ ስለሆነች፣ በዚህ ቅር የምትሰኝብኝ አይመስለኝም”
“ኧረ በጭራሽ!” አለች፣ ወተቱን እና የጡጦ እቃዉን እያቀበለችኝ:
“ኧረ ስሚኝማ ዉቤ” አለች፣ የመደነቅ ፊቷን እየገለጠችልኝ፡፡
“ምን”
“ወንድምሽን እኮ ሊፍቱ ጋ አግኝቼዉ አሁን''
“ማንን?” አልኋት ለወጉ፣ ማንን ማለቷ እንደሆነ ባላጣዉም፡፡
“ጀሪምን ነዋ”
“እሺ”
“ምን እሺ ትይኛለሽ? ሰላምታ ከልክሎኝ ሄደ እኮ”
“ኧረ?” አልኋት፣ ከእሽጉ ዉሃ ከፍቼ ወደ ጡጦዋ እየቀነስሁ ዉሃዉ መቼ እንደ ተቀመጠልኝ ግን አላወቅሁም: ከአጠገቡ ሶፍት፣ ፎጣ እና ሌሎች አልባሌ ነገሮችም መኖራቸዉን ሳይ ማረፊያ ክፍሉን ከመያዜ
በፊትም ተቀምጠዉ እንደነበር ገባኝ፡፡
“አይገርምሽም? መቼስ ረስቶሽ ነዉ አትዪኝም ጃሪም እኔን ሊረሳ? ጉድ እኮ ነዉ! ያኔ እንዲያ …” ብላ፣ ተገርማ ቀረች፡፡ እየቆየ እንደገና በኃይል ከነከናት፡ ምክንያቷን አላጣሁትም፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሳለን ለአንድ ዕረፍት እኛ ቤት በነበርንበት ጊዜ፣ ጃሪም ዓይን አብዝቶባት ነበር
እንዲያዉም ደጋግሞ ወድጃታለሁ እንዳለኝ አስታዉሳለሁ ስሜቱን በግልጽ ለእሷ እንደ ነገራት ግን አላውቅም፡ ከአሁኑ ሁኔታዋ
እንዳስተዋልሁት ከሆነ፣ መንገር ብቻም ሳይሆን እሞትልሻለሁ› ጭምር ሳይላት እንዳልቀረ ገመትሁ ያ ሁሉ ቀርቶ አሁን ግን እንደማያዉቃት ከሆነባት፣ ባይገርማት ነበር የሚገርመኝ፡ ያዉ፣ የእኔ ጓደኛ አይደለች?
በእሱ ቤት እኮ አሁን፣ የእኔ የሆነ እና እኔ የነካሁት ሁሉ ርኩስ
ሆኖበታል።
“አጀብ ነዉ አለ ጅብ? የሆነዉስ ይሁንና በምን ዝም አሰኘሻት?” አለች፣ ቱናትን ገለጥ እያደረገቻት፡ ከጀርባዋ አጥንት ላይ ላለዉ ቁስል ጥንቃቄ አድርጋላት፣ አቀፈቻት እና ልትቀመጥ ብትፈልግ መቀመጫ አጣች: ገና
ይኸኔ ነዉ የሆቴል ማረፊያ ክፍል ዉስጥ መሆኔ ራሱ ትዝ ያላት:
የጃሪምን ፊት መንሳት ማመን አቅቷት ዋናዉን ጥያቄዋን እንደ ረሳችዉ ልብ አደረገች፡፡
“ቆይ ቆይ፣ አንቺ ግን እዚህ ምን ትሠሪያለሽ? ከእመዋ ቤት ያዉም ያን ድግስ ጥለሽ? ያዉም ይቺን ጨቅላ ይዘሽ? ምን ልትሆኚ እዚህ መጣሽ በይ?”
ይኸዋ! እንደ ፈራሁት የማርያም መንገድ እንኳን ሳታስቀርልኝ ጥያቄዋን አመጣችዉ ያልሰማሁ መስዬ ዝም ልላት ፈልጌ ነበር፡ ነገር ግን እሷን ሽሽት ዓይኔን የጣልሁበት ባልቻም ከእሷ በላይ አፈጠጠብኝ፡፡ ለራሱ ጉዳይ
ቢሆን፣ ሽንቱ እንኳን የፈለገ ወጥሮ ቢይዘዉ የሲራክ ፯ ጉዳይ ፋታ
እንደማይሰጠዉ እያወቅሁ፣ ለእኔ ሲል ነዉ አትረፍርፎ የሚሰጠኝ። እኔ ግን እንደ ደመኛ ተደብቄዉ እዚህ ሲያገኘኝ ማዘን ይበቃዉ ይሆን? እንኳን ማኩረፍ ሌላም ቢያደርግ እዉነት አለዉ፡ ግን እሱ ነዉና ሰዉዬዉ፣ መተዉ ያዉቅበታል፡ ያም ቢሆን ግን ጥያቄዋን ተጋርቷታል።
እንድመልስላት ከእሷ እኩል እየተቁለጨለጨብኝ ሳለ እሸቴ በሩን ከፍቶ ገባ፡፡ መቼ እንደ ወጣ ግን አላየሁትም ነበር፡፡ ለካንስ እመዋ ደዉላለት፣ እሷን ለማነጋገር ወጥቶ ኖሯል።
“እመዋ ናት የደወለችልኝ። (ልምጣ ወይ እያለች ነዉ፣ ትምጣ እንዴ?" አለ፣ ሳይታወቀዉ በሸዊትና
በባልቻ ከተፋጠጥሁበት ጥያቄ
ሲያስመልጠኝ፡ ባልቻ ቅር እንዳለዉም ቢሆን ቸለል አለልኝ፡ ሸዊትም እንዲሁ ቱናትን እንዳቀፈቻት ከአልጋዉ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ወተቱን ለማጥባት ሞከረች::
“እናንተ?” አለች፣ ወተቱን ልታጠጣት ሞክራ ሞክራ እንዳልሆነላት ስታዉቅ ተስፋ እየቆረጠች። “ቱናት የተለየ ልምምድ ሳያስፈልጋት
አይቀርም: ከተወለደች አንስቶ ኹለቱን ወር ሙሉ የከረመችዉ ግሉኮስ ተተክሎላት ስለነበር፣ ከጡትም ሆነ ከጡጦ ምግብ ስትሞክር ይኼ የመጀመሪያዋ ነዉ። ስለዚህ፣ እንደኔ እንደኔ አሁኑኑ ወደ ሆስፒታል ተመልሳ መግባት ያለባት ይመስለኛል” አለች፣ እኔ ደግሞ እንድሞክራት
እያቀበለችን፡ “ለጊዜዉ ጉሉኮሱም ቢሆን ማግኘት አለባት” አታዩትም
አተነፋፈሷንስ? የባሰ ሲር ሲር እያለ እኮ ነዉ። ለመሆኑ የቀጣይ
ሕክምናዋን ጉዳይ አማክራ ችሁበታል ወይ?”
“ማንን፣ ይኼዉ አንቺ አለሽል አይደል? አንቺዉ ምከሪን እጂ” አለ ባልቻ፣ እኔም እንደዚሁ ልላት ስል ቀድሞኝ፡፡
ይኼ ሙያዬ አይደለም: ስለዚህ እኔ በቅጡ ከምፈተፍት፣ ጉዳዩን ይሁነኝ ብለዉ የተማሩት
ባለሙያዎች ስላሉ ወደ እነሱ መሄድ ይኖርብናል”
«የት ናቸዉ እነሱ ታዲያ?”
“ምን እሱማ ባላውቃቸውስ በአብዛኛዉ ሆስፒታሎች አይጠፉም ነበር:: ግን የመሣሪያዎች ዉስንነት አለ: ለጊዜዉ ሕክምናዉ በኹለት
ሆስፒታሎች ብቻ እንደሚገኝ ነዉ የማዉቀዉ”
“በስመ አብ!” አለ ባልቻ፡ “ወረፋዉ አያድርስ ነዉ በይኛ''
“በጣም!”
ከመንግሥት ሆስፒታሎች መካከል ይኼን ሕመም ጉዳዬ ብሎ በብቸኝነት ሕክምና ወደሚሰጠዉ ዘዉዲቱ ሆስፒታል ሄድን፡፡ አቤት ወረፋዉ! ያሉት
አልጋዎች ዉስን ናቸዉ፤ ተመዝግቦ ተራዉን የሚጠባበቀዉ ግን የትየለሌ! እንዲያዉም የኋላ ኋላ እንደ ሰማነዉ ከሆነስ፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ብቻ ከሃያ ሺ የሚበልጡ ሕጻናት የቱናት ዓይነት እክል ያጋጥማቸዋል አሉ፡ ቁጥሩን አሰብሁት ስንት የሚወራላቸዉ
ወረርሽኞችም እኮ ከዚህ የከፉ አይደሉም
የቱናንት ሁኔታ አጣዳፊ መሆኑን ልናስረዳ ብንልም፣ የሚሰማን
አላገኘንም: አብዛኛዉ እዚህ የመጣዉ ሰዉ ሁሉ ቱናት ካለችበት የሚተናነስ አለመሆኑን አምነን ተቀበልን፡፡ ሆኖም ሕክምናዉን በተመለከተ እስከሚወሰንልን ድረስ፣ ባይሆን በረኀብ እንዳትሞትብን በሚል ግሉኮስ ተፈቅዶልን አንድ ጥግ ላይ ተተከለላት:: በረንዳ ላይ:
መኝታ ክፍልማ የሚታሰብም አይደለም፡
“በቃ እናንተ ሂዱ እጂ” አልኋቸዉ፣ ለግማሽ ሰዓት ያህል እንደዚሁ
እንደ ቆየን፡፡ እሳቱ የማይበርድ ችግር እየተጠባበቃቸዉ ሳለ፣ የሦስቱም እዚህ መቀመጥ ከቱናት ሕክምና ባልተናነሰ አሳስቦኛል ሸዊትም ፋታ የለሽ ሐኪም ናት፣ ባልቻም ባልቻ ነዉ፣ እሸቴም ያዉ ነዉ፡፡ “ሂዱ አረ! ሂዱ” አልሁኝ፣ እንደማግባባትም እንደማጣደፍም እያደረግሁ::
“መጨረሻዉን ሳንሰማ?” አለ ባልቻ፣ ስልክ ስልኩን ሲያይ እንዳልነበር ሁሉ፡

👍38❤1👎1🔥1
“ግድየለም፤ዉሳዉን ሰምቼ እጠራችኋለሁ: አሁን ግን ምም
አታደርጉልኝም። ወደየሥራችሁ ሂዱልኝ''
አላመኑኝም: ቅድም ለመጥፋት ያደረግሁትን አድራጎት አስታዉሶ
መሰለኝ፣ በተለይ ባልቻ ጥሎኝ ለመሄድ አልጨከነም:: ግን ደግሞ መሄድ አለበት: እስከ አሁንም የማይቻለዉን ነዉ የቻለልኝ፡፡ የጋመ ሚስማር ላይ ቆሞ ከጎኔ እንዳለ አዉቅለታለሁ፡ ለቅጽበት እንኳን ፋታ የማይሰጠዉን የሲራክ፯ ኃላፊነቱን ትቶ አብሮኝ እንዳለ ይገባኛል። እንኳንስ ግማሽ ቀን፣ እሱ በግማሽ ደቂቃ ምን ተአምር እንደሚያደርግባት
አዉቀዋለሁ፡
“እእእ...እኛ እንበቃለን፣ እናንተ ሂዱ” አለ እሸቴ፣ የኹለቱንም ማቅማማት ሲመለከት ቆይቶ፡
“ይሻላል?” አለች ሸዊት' ሰዓቷን አሁንም አሁንም ስታይ ቆይታ
“አዎ፤ እንዲያዉም እሽቴና እኔ እንበቃለን። በሉ ባይሆን እናንተ ሂዱ”
“አደራ ታዲያ!” አለ ባልቻ ችሎያለፈዉን ቁጣዉን እያሳየኝ
“የማይሆ ነገር አደርጋለሁ ትይና ወዮልሽ! ማርያምን ነዉ የምልሽ፣
ቅድም ያደረግሻት ዳግመኛ ሞክሪያትና አንቺን አያርገኝ! ማርያምን ብያለሁ !”
“ቃል እገባለሁ”
«እንዳትሞክሪያት!»
“አታስብ”
ሽዊትን እና ባልቻን እንደ ምንም ገፋፍተን ከሸኘናቸዉም በኋላ፣ ባልቻ መለስ ብሎ እሸቴን ጠራዉ፡ ራመድ ብሎ ሲቀርበዉ የሆነ ነገር
አንሾካሾከለት ከዓይኑ እንዳልሠወር በንቃት እንዲከታተለኝ ሳይነግረዉ
እንዳልቀረ ከመገመት በቀር በትክክል ምን እንደ ተባባሉ እሸቴም ሊነግረኝ አልፈቀደም: ከዚያ የቀረነዉ እኔና እሸቴ ፎጣዎች ደራርበን ቀዝቃዛ ሊሾ
ላይ ያስተኛናትን ልጃችንን ከበን ተቀመጥን፡፡ ለካንስ እሱ ገና አሁን ነዉ ልጁን በአካል የሚያያት፡፡ የማይንቀሳቀሱ እግሮቿን እና ሁለመናዋን በፍቅር ደባበሳት፡ ሊያጫዉታት፣ ሊያስቃት የማይሆነዉ የለም አሁንም
አሁንም ያለ አቅሟ የተሸከመችዉን የራስ ቅሏን ይለካዋል አሁንም አሁንም ይስማታል፡ ይነሳና በትራስጌዋ በኩል፣ ከዚያ ይነሳና በጎኗ
በኩል፣ ከዚያ ደግሞ ይነሳና በግርጌዋ በኩል ይቀመጣል ግማሹ የዓይኗ ጥቁር ክፍል በላይኛዉ ሽፋሽፍቷ ተሸፍኖ፣ እንደ ምንም ወዲያ ወዲህ ከምትለዉ ዓይኗ ትይዩ ዓይኖቹን ያንከራትታል
አንጀቴን በላዉ፡
ሆኖልኝ ሀገር ጥዬ ብጠፋ ኖሮ ለካ ይኼንንም ኖሯል የምነፍገዉ፡ እሱ
ቱናትን፣ እኔ እሱን እያየን ሰዓቱን ገፋነዉ፡፡ ሰባት ሰዓት… ተኩል
ስምንት ሰዓት… ከሩብ… ተኩል… ሩብ ጉዳይ… ዘጠኝ እያልን ቆጥረን እንደ ምንም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ደረስን፡፡ ሲፈርድብኝ ቅድም እመዋ ቤት በስስት ከሰለቀጥኋት ገንፎ በቀር፣ ቀኑን ሙሉ ምግብ የሚባል
አልቀመስሁም: ዉርጭ እና ረኀብ ተከታትለዉ መጡብኝ፡፡ በጨለማ
መንገድ ዝናብ ተጨምሮ አሉ? እኔ እንዲህ ከተንሰፈሰፍሁ፣ ቱናትስ
የዉርጩን ነገር እንዴት ችላዉ ይሆን? እንዲህ አድርጉላት እንኳን
እንዳንል፣ ማንን? የቦዘነ ሰዉ የለም ሆስፒታሉ የሥራ ቤት ነዉ፡
ነርሶቹ፣ዶክተሮቹ ተላላኪዎችና የጽዳት ሠራተኞች ሳይቀር
በአንዳቸዉም ዘንድ ዕረፍት የሚባል አላየንባቸዉም የሚያዋልዱት ለማዋለድ፣ ሕይወት የሚያተርፉት ለማትረፍ፣ ነፍስና ሥጋ እጃቸዉ ላይ የተለያየባቸዉ ሬሳ ለመሸኘት፣ ሌሎቹም እንደየምድባቸዉ ይባክናሉ እንጂ የተቀመጠ የለም፡ ታዲያ በዚህ ቤት ማን ይወቀሳል? ማንም!
ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሲያልፍ፣ እመዋ መጣችልን፡
“ምግብ ይዞ መግባት አይቻል እንደሆነ ብዬ ባዶዬን መጣሁ፤ በሉ እስኪ ወጣ ብላችሁ ቀማምሱ” አለችን፣ ግራና ቀኝ እንደኛ ኩርምት ብለዉ
የተደረደሩትን ሌሎች አስታማሚዎች አይታ ከንፈሯን እየመጠጠች:የሁሉም ሰዉ ሁኔታ ልብ ይነካል፡ ልጆቻቸዉን ለማዳን ጥሪታቸዉን ሁሉ አሟጠዉ ሸጠዉ ከዳር ሀገር ድረስ የመጡ አሉ፡ ያዉም ከባህሉ አምልጠዉ፡ እንኳንስ እንዲህ ያለዉን ይቅርና የጥርስ ፍንጭት ሳይቀር
እንደ ርግማን ታይቶ አየሽዉ አየኸዉ› እየተባለ መጠቋቆሚያ የሆነበት ባህል ስላለን፣ ለዚህ የሚሸነፉት ብዙ ናቸዉ፡ ስንትና ስንት እናት ከሰዉ አፍ ፍራቻ፣ ከወለደችዉ ጀምራ ልጇን ደብቃ ሞቱን እንደምታይ ቤቷ
ይቁጠረዉ።
“እንደም አለሽ የኔ ልጅ?” አለቻት እመዋ፣ አንደኛዋን ደርባባ ሴት::
ከመጣን ጀምሮ እንዲችዉ ኹለት እግሯን በኹለት እጇ አቅ
እንደተቀመጠች ናት ፊቷን ብቻ አይቼ፣ ዕድሜዋን በአርባዎቹ
መጀመሪያ ገደማ ገመትሁት።
“እግዚአብሔር ይመስገ”
“ምነዉ ምን አገኘሽ?”
“ልጄን”
“ምን አገኘብሽ ልጅሽን?''
“ኧረ ይተዉኝ” አለች፣ በቁጭት። “ይተዉ ኝማ! ይተዉማ! እህህ….
በገዛ ልፋቴ፣ ማስኜ ኳትኜ በሠራኋት ቤት ተመቅኝቶ አስመትቶብኝ ይኼዉ ልጄን እንዲህ አርጎብኝ ቀረ እንጂ! ያዉም የሩቅ ሰዉ መሰለዎ?
የመጀመሪያ ባሌ እኮ ነዉ። በወጣ በገባ ቁጥር ደቁሶ ደቁሶ ጤና ቢነሳኝ፣ እህል ዉሃችሁ ካልገጠመማ ከምትጋደሉ ተለያዩ ብሎ ሽማግሌ አፋታን
ጥሎ አይጥሉ ጌታ ባወቀ፣ ብዙም ሳልቆይ ሌላ ትዳር መጣልኝና አሁን ወዳለሁበት ባል ገባሁ: እዉነትም ይኸኛዉ ትዳሬ ደህና ሆነልኝና፣ ኹለት ልጆች ወለድሁ: ንብረትም ደህና አፈራን ይኸ ጊዜ የቀድሞዉ ባሌ ምቀኝነት አመጣላችኋ! እንዴት እኔ ሳልወልድ፣ የእኔ ከብቶች ሳይረቡ ቅብጥርሴ እያለ አላስቀምጥ አላስኖር አለኝ: በጠበጠኝ። ከዚያ ቀድሞ ላጋቡንም ኋላ ላፋቱንም ሽማግሌዎች 'አቤት' ብዬበት፣ ትንሽ አድቦልኝ ሳለ ይሄኸኛዉን ልጄን በሆዴ መያዝ! ሲፈርድብኝ እሱ ወትሮዉንም
አልተኛልኝም፣ ማርገዜን ሲያዉቅማ ጨርቁን ጣለ። በየመተተኛዉ መዞር
ጀመረ። በእሱ የተነሳ፣ ልጄን ስወልደዉ እንደዚህ ሆኖ አረፈዉ።ተሳካለት። የተመኘዉ ሆነለት። መተቱ ሠራለት። የማለዳ ዕድሌ ወስዶ ጥሎኝ፣ በአሣር በመከራ እንጂ ከሰማይ የሸመጠጥሁት ይመስል በምቀኝነት ተጫወተብኝ! ወንድም የላትም ብሎ። ሰዉ የላትም ብሎ! ልጄን አጉል አስቀረብኝ። እህህህ!”
እኔ ከእሷ ተሽዬ ሞቼ አዘንሁላት ሐዘኔታዬን ተከትሎ ደግሞ እምነቷ ልክ
አለመሆኑን ልነግራት አፌን በላኝ፡ በዚህ ዘመን በመተት ማመኗ ገርሞኛል። ከእሷ ይልቅ በጣም የደነቀችኝ ደግሞ እመዋ ናት። ልክ አለመሆኗን እያወቀች ዝም አለቻት: ለነገሩስ እንኳን የሰዉ ሰዉ ላይ፣
እኔ ልጇ ላይ እንኳን ቁልጭ ያለ ስሕተት ብታይብኝ፣ አይባልም ብላኝ
አታዉቅም ስሕተቴን የምታርምባት ብልሃት ግን ሁልጊዜም በእመዋ
ልብ ዉስጥ አለች፡ ለዚች ምስኪንም አንድ ነገር ሳታስብላት አትቀርም
“አሁን ታዲያ እንዴት ነዉ? እየዳነልሽ ነዉ?”
“ቀድሞ ነገር መቼ ታየልኝና?”
“ዛሬ ነዋ የመጣሽዉ እንደኛ?”
“ወይ ዛሬ! ወር ደፈንሁ እንጂ”
“ምን? ወር?” አልን ሦስታችንም እኩል፣ ሐሞታችን ፍስስ እያለብን፡
“እንዳልሄድ ሀገሬ ሩቅ ነዉ: እንዲህ ሆኖ ወስጄ ብመልሰዉ መኪናዉ ገጭ አጓ ባለ ቁጥር የልጄን ሰበበኛ ጀርባ ይነካብኛል ብዬ ፈራሁለት።እና ከዛሬ ነገ ተራሽ ደርሷል ይሉኛል እያልሁ ይኸዉ አንድ ወሬ እዚህ''
“ሰአሊተ ምሕረት! እና ማን አብሮሽ አለ?” አልኋት፣ የእኔዋ ቱናት እጣም የባሰ እያስፈራኝ፡ ላላተርፋት ነዋ? የማይደርስ ወረፋ ስጠብቅ ልጄ ልታመልጠኝ ነዉ?
“ነገሩስ አባቱ አብሮኝ ነበር። ዉለን ስናድር ግን እዚያ ያሉት ልጆ ች ደግሞ
ሐሳብ ሆኑብንና ወደ እነሱ ሰደድሁት። እነዚያንም ዘመድ ላይ በትነናቸዉ
ነበር የመጣነዉ''

👍31
ሌላ ሌላዉን ስንጨዋወት በየመሀሉ እናንተስ? እያለች የጠየቀችንን ሁሉ ነገርናት በኋላ በግቢ ካለዉ መካከለኛ ሱቅ ብስኩት እና ዉሃ ነገር ቀማምሼ ተመለስሁና ከእመዋ ጋር አንቺ ወደ ቤት ሂጂ የለም አንቺ ሂጂ እየተባባልን ስንለማመን ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አለፈ፡ በስንት ልመና አሸንፌያት እሸቴም አብሯት ሲሄዱልኝ፣ የማይነቃነቀዉን ረዥም አዳር
ከቱናት ጎን ቁጢጥ ብዬ ተፋጠጥሁት አይነጋ የለም እንዲችዉ ጥርሴን
ሳፋጭ ነጋልኝ ከዉርጩም በላይ ደግሞ በወረፋዉ ነገር ስብከነከን ነዉ
ያደርሁት። ሲነጋልኝ፣ ከእኔ አጠገብ በእኔ ሁኔታ ሌሊቱ የነጋላቸዉን ሰዎች ሀኪሞቹ ግን ቢያንስ ለምን ቁርጥ አድርገዉ አይናገሩም ስል ጠየቅኋቸዉ፡ ሲያስረዱኝ እዉነትም በሀኪሞቹ መፍረድ ይከብዳል::
ምክንያቱም ሀኪሞቹ ራሳቸዉ፣ ዛሬ የተመዘገበ ሰዉ ከስንት ቀን ወይ ከስንት ወር በኋላ ወረፋ እንደሚደርሰዉ አያዉቁትም፡
“ግን ለምን አታዉቁም?” አልኋቸዉ፣ ኃላፊነቱ አለባቸዉ የተባሉ አንድ
ዶክተር ዘንድ ቀርቤ፡ ስሜን እና ጥያቄዬን እንደገና ከጠየቁኝ በኋላ፣
ከጥድፊያቸዉ ቆም ብለዉ፣ ያዉም በሚገርም ትሕትና አብራሩልኝ፡
“እንዴት መሰለሽ ዉብርስት፤ ታካሚዎች ወደ እኛ ሲመጡ የመጀመሪያ
ሥራችን ምር መራ ነዉ: ወይም ደግሞ ምርመራዉን በሌላ ሆስፒታል
አድርገዉ ከሆነም ዉጤቱን እንወስድና ታማሚዋ ወይም ታማሚዉ አሁን
ያለበት ሁኔታ ይመዘገብለታል: ከዚያ ወረፋዉን እንይዝለት እና ሲደርሰዉ ደዉለን እንደምኔጠራዉ ነግረን እንሸኘዋለን። እንዳልሁሽ
የሁሉም ሰዉ ጉዳት እኩል አይደለም።
ለምሳሌ በአንዳንዱ ስፓይናቢፊዳም ሀይድሮሴፋለስም ይሆናል እክሉ: እንደገና ደግሞ በአንደኛዉ ወይም በኹለቱ ምክንያት የመጡ ሌሎች ጉዳቶችም ያሉበት ሊኖሩ ይችላሉ። እና በአሁኑ ሰዓት ለምሳሌ፣ አድ ሺ ታካሚ ወረፋ እየጠበቀ ነዉ እንበል: በዚህ መሀል አንድ ጨቅላ ልጅዛሬ መጥቶ
ከየነዉ። ይኼ ጨቅላ፣ አሁኑኑ ካልታከመ በቀር እንደማይተርፍ አወቅን
እንበል። በዚህ ጊዜ ወረፋ ሳንል እሱን ከሞት እናተርፋለን። ያ ካልገጠመን ደግሞ በወረፋዉ መሠረት እናክማለን” በዚህ ምክንያት ነዉ ቁርጥ አድርገን ወረፋችሁ የዛሬ ወር ወይ የዛሬ ዓመት ነዉ ለማለት
የምንቸገረዉ
“ታዲያ ቱናትም አዩልኛ። ልጄን። ከትናንት ጀምሮ ትታይልሽና ይወሰንላታል ተብዬ እኮ ይኸዉ እንዲህ ሆና ሲሚንቶ ላይ ነዉ
ያደረችዉ ''
“ዉጤቷን እስኪ ወዲህ በይዉ”
“ወይ ጉድ! ጭራሽ እኮ ገና አልታየችልኝም ነዉ የምልዎ''
“ነዉ እንዴ? እሺ፣ ገባኝ። እንግዲያዉስ ሂጂና የምርመራ ዉጤት ይዘሽ
ተመለሺ። ይቀርበኛል ከምትዪዉ ማንኛዉም የምርመራ ማዕከል አሠተሽ
የኤም አር ይ MRI ዉጤቷን ልታመጪ ትችያለሽ: ዉጤቷን አይተን እንደሚሆን እንደሚሆን እናደርጋለን''
በብላሽ ነዋ ካልረጋ ደም የማትሻለዉን ልጄን በሚቆረጥም ሊሾ ላይ
ያሳደርኋት? ግሉኮስ ነበር እንዴ ችግሬ? በጣም ተቆጨሁ ያልጠበቅሁት
ሆኖ ብናደድም፣ እንዲህ ነዉ ብዬ አልተከራhርሁም
ፊት ወደ ፊት ይል ነበር ካህኑ አባቴ ይኼን ያዥኝ ልቀቂኝ የሚለዉን
ስሜቴን ገሰጽሁትና፣ የተባለዉን ምርመራ ላስደርግላት ቱናትን አፋፍሼ
አነሳኋት ከዚያ ወደ የትኛዉ የምርመራ ማዕከል እንዴት አድርጌ መሄድ
እንዳለብኝ እያዉጠነጠንሁ ሳለ እንደኛዋ እህቴ ድንገት ከኋላዬ ከተፍ
አለችልኝ፡፡
“ጎሽ፣ ሳስብሽ ነዉ የመጣሽልኝ መኪናዬን አመጣሽልኝ?” አልኋት፣ ከሰላምታ ሁሉ አስቀድሜ፡ የማደርገዉ ግራ በገባኝ ሰዓት ስለደረሰችልኝ፣ ከሰማይ እንደ ወረደችልኝ ነዉ የቆጠርኋት፡
“መኪናዬን?” አለች፣ ኮስተር ብላ፡፡
“አዎ። ለቱናት አንድ ምርመራ ታዝዞላታል ስለዚህ እንደህ ሆና በታክሲ ወዲያ ከማንገላታት መኪናዬ ታስፈልገኛለች
አምጥተሽልኛል ወይ?”
“አልገባኝም”
“ይሄንን ነዉ መፍራት” አልሁ ትዕግሥት የሚባል እያለቀብኝ፣ እኔ ለራሴ ወደ ምርመራዉ ቶሎ ለመዉሰድ ቸኩዬ ሳለ እሷ ደግሞ ተደርባ አንጀቴን ብትስብብኝ፡፡
“መኪናዬ አንቺ ጋ አይደለች? ያኔ ሆስፒታል የገባሁ ጊዜ እስከምትወልጂ
ልጠቀምባት ብለሽኝ ቁልፉን አልሰጠሁሽም?”
“የሰጠሸኝ እንደሆነስ፤ ማነዉ ያንቺ መኪና ያደረጋት?”
“ ስከማዉቀዉ ድረስ፤ ያንቺ የሆነ ነገር እኔ ላይ የለሽም እንዲያዉ የኔ የሆነ ነገር ነዉ አንቺ ዘንድ ያለዉ”
“አቤት?” አልኋት፣ ሐሳቤ ላይ ጃሪም ቁጭ እያለበት፡ ለምን እንደሆነ
እንጃ፣ አመላለሷን ልብ አድርጌ ሳዳምጠዉ ትዝ ያለኝ ጃሪም ነዉ። ይቺ
ይቺ የእሱ ተንኮል ናት፡ ደግሞ በእሷም በኩል መጣብኝ?
“ይልቅ ሊብሬዉ የት ነዉ ያደረግሽዉ?” ብላኝ አረፈችዉ፣ ጭራሽ ዓይኗን ሙልጭ አድርጋ በጨዉ ታጥባ “ይቺን ሽጬ ሌላ ሻል ያለ መኪና መግዛት እፈልጋለሁ: ሊብሬዉን ስጭኝ'
“ቆይ የምርሽን ነዉ?”
“አይ እየተጫወትሁ ነዉi”
“ተይ ተይ ይኼ በአንቺ አያምርም: ተይ። ለራሴ ስምጥ ዉስጥ ነኝ፣ ተጨማሪ ጉዳት አልፈልግም በእመዋ ሞት ይዤሻለሁ፣ እየቀለድሁ ነዉ በዪኝ''
“አይ እንግዲህ! ትሰጭኝ እንደሆነ ስጭኝ: ካልሆነ ግን ቁርጡን ልንገርሽ… ዘልዝዬም ቢሆን ጎማዉን ለብቻ፣ በሩን ለብቻ እያደረግሁ እሸጠዋለሁ እንጂ አታገኛትም! ቆይ ምቀኝነት ነዉ? ሊብሬዉን ስጭኝ''
“የጃሪም ሥራ ነዉ እ? ኧረ የማይሆን ቀልድ ነዉ የያዛችሁት ተዉ! ተዪ!
በእመዋ ሞት ብሻለሁ!”
“ምነዉ እመዋ እመዋ አልሽ ዐሥሬ? ከፈለጋችሁ ለምን ተቃቅፋችሁ
ድብን አትሉም?”
“ እሀህታለም?”
“አረ ወዲያ! እህትሽን እናትሽ ትዉለድልሽ: አሁን ሊብሬዉን ቁጭ!''
“እ?”....
✨ይቀጥላል✨

👍36❤3
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
..የዌስት ሊን የቤተክርስቲያን ሰዓቶች ሁለት ሰዓት ሲሞላ ጮኹ ደወሎቹም እሑድ መሆኑን ለማብሠር ከሰዓቶቹ ተቀባብለው አስተጋቡ " ኮርነሊያ ልክ የደውሎቹን ድምፅ ስትሰማ እሑድ እሑድ ትለብሰው የነበረውን ዐይነት ሳይሆን ያዘቦት
ቀሚሷን አጥልቃ ከመኝታዋ ብድግ አለች „ ከወፍራም ዝንጉርጉር ጨርቅ የተሰፋ
እግር ጌጥና ባለጐፍላ ጉንጉን መቀነት ያለው አንድ የሌሊት ሰደዶ ቀሚስ ደርባ እስከ ቁርጭምጭሚቷ የሚደርስ ቀሚስ አጥልቃ እግር እግሩ ጥልፍልፍ የወፍ እግር "ጌጥና
ባለጎፍላ ጉንጉን መቀነት ያለው አንድ የለሊት ሰደዶ ቀሚስ ደርባለች " ይኸኛው በጥንቱ ጊዜ የናቷ የጧት ልብስ ነበር " ኮርነሊያ ዘመናዊውን አለባበስ በጣም ትንቅ ስለነበር ይኸን ልትጥለው አልፈለገችም ዘመናዊ ወይዛዝርት
በስፌቱ ዐይነት ሊሥቁ ይችሉ ይሆናል በጨርቁ ዐይነትና ጥራት ግን ሚስ ካርላይል በተለይ ትጠነቀቅበት ስለነበር ነውር ሊያወጡበት አይችሎም እሑድ እሑድ ጧት የእለቱን አለባበሷን አጠናቅቃ የመውጣት ልማድ ነበረባት ዛሬ ጧት ግን እንደ ልማዷ ለውሎዋ ጨርሳ ያለ መልበሷ ከቤት ውስጥ የሚሠራ ነገር እንደ ነበረባት ያመለክታል የራሷ መሸፈኛ ግን በቃላት ሊገለጽ አይችልም በልብስ የሞድ መጽሐፍም ሆነ ከዚያ ውጭ ተመሳሳይ አይገኝለትም " አንዳንድ ሰዎች የወንዶች ጥምጥም የሌሊት ቆብ ነው ሊሉት ይችላሉ ” ሌሎቹ ደግሞ ቅርጹ በጥንት ጊዜ በትምህርት ደካሞች የነበሩ ተማሪዎች ሲሣቅባቸው እንዲተጉ እየተባለ ከራሳቸው እንዲደፉት ይደረግ ከነበረው አፈ ሰፊና ራሰ ሾጣጣ ቆብና ከቤተ ክርስቲያን ደወል የተወሰደ ሊመስላቸው ይችላል " ያም ሆነ ይህ ቁመቱ ሾጠጥ ብሎ የወጣ ረጂምና ጎኑ ሰፊ ቀለሙ ነጭ የሆነ ግርማ ያለው ትልቅ ቁልል ነበር።
ሚስ ካርላይል መተላለፊያውን ተሻግራ ከራሷ መኝታ
ቤት ፊት ለፊት ወደ ነበረ መዝጊያ ሔደችና በቤቱ ውስጥ የተገኙትን ሰባቱንም ሰዎች በአንድ ጊዜ በቅሰቅስ ድምፅ እየደበደበች « †ነሥ አርኪባልድ ! ተነሥ ! » እያለች ጠራችው።
« ተነሥ ? ተነሥ ? » አለ እንቅልፍ የተጫጫነው አንድ ድምፅ ። «ለምንድነው የምነሣው ? ገና'ኮ ሁለት ሰዓት ነው »
« ገና ከጠዋቱ ዐሥራ ሁለትም ቢሆን መነሣት አለብህ » አለችው የሥልጣን ቃና ባለው አነጋገር " «ቁርስ ቀርቦ እየጠበቀ ነው " ሁላችንም የየራሳችን ጣጣ
አለብን ስለዚህ ቶሎ ተበልቶ እንዲያበቃ እፈልጋለሁ ።»
ሚስ ካርላይል ደረጃዎቹን ወረደችና ምግቡ ተዘጋጅቶ ወደሚጠብቅበት የቁርስ ክፍል ገባች » ምላሷ አንዳንድ ጊዜ ሁሉን ነገር ማየት የሚችለው
ሁልጊዜ ንቁና ስለታም ነበሩ " ክፍሉ በአውራ መንገዱ በኩል ነው። መስኮቶቹ ተከፍተዋል"" እንደ ሚስ ካርላይል ምንም ነቁጥ የማይገኝላቸው የሚያምሩት
ነጭ መጋረጃዎች በለስላሳው የበጋ ነፋስ ላመል ያህል ይወዛወዛሉ የክፍሉን
ዙሪያ አትኰራ ትመለከት ትንሽ ብናኝ ታያት ያየችውን ለጆይስ ልታበሥር ወደ ወጥ ቤት ተንደርድራ ሔደች ጆይስ ለቁርስ የሚዘጋጀው ሥጋ ሲጠበስ እየተቆጣጠረች ከእሳቱ ዳር ቁማ አገኘቻት
ይህን ያህል ሥራን ቸለል ማለት ምን የሚሉት ድፍረት ነው ጆይስ ? የሜግብ ቤቱ አቧራ ተወልውሎ አያውቅም»
« ተወልውሉ አያውቅም ?! ዐይኖችዎን ከምን ላይ ቢያሳርፏቸው ነው እንደዚህ የሚሉኝ ? »
አቧራው ላይ ነዋ ! » አለች ሚስ ካርላይል «በይ አሁን መወልወያ ያዥና ሔደሽ እይው » እኔ ከቁሻሻ ክፍል ውስጥ ግብቼ መቀመጥ አልችልም " ዛፊ ጠዋት
እርምሺን ትንሽ ተጨማሪ ሥራ ሠራሽና ነው እንዶዚህ እርግፍ አድርሽ የተውሺው ? »
« ኧረ እንዶሱም አይደለም ... እሜቴ እኔ ለራሴ በተጨማሪ ያዘዙኝን ሥራ ቶሎ ለመጨረስ ስል በዐሥራ አንድ ሰዓት ተነሣሁ አንድም ጉድለት እንዴይገኝ ተጠንቅቄ በተለይ ምግብ ቤቱን ተጨንቄ ነበር ያጸዳሁት " ግን እርስዎ መስኮቶቹ በጣም ይከፈቱ ስለሚሉ የውጭ አቧራ ሊበንበት ይችላል»
ጆይስ መወልወያ ይዛ ስትወጣ መጥሪያው ተደወለ " ወዲያው አንድ ቁመቱ መካከለኛ የሆነ ወፈር ያለ አሽከር ከማብሰያ ቤት ገባ "
« ምን ፈለግህ ፒተር ? » አለችው ሚስ ካርላይል "
« ለጌቶች የጢም ውሃ ብዬ ነው .. እሜቴ " »
« ጌቶች አሁን የጢም ውሃ" አያገኙም። ሒድና ንግረው ቁርስ ቀርቦ እየጠበቀ ስለሆነ ኋላ ይላጭ
ፒተር መልሶ መልእክቱን አለዝቦ ነገረው » ሚስተር ካርላይልም በቀዝቃዛ ውሃ ተላጭቶ ለባብሶ ወደቁርስ ቤት ሲገባ ኮርኒሊያ ከምግቡ ጠሬጴዛ ተቀምጣ
ስትጠብቀው አገኛት።
« ለምንድነው ዛሬ አለወትሮአችን በሁለት ሰዓት የምንበላው ? »
« ብዙ ሥራ አለብኝ » የቁርስን ጣጣ ቀደም ብዬ ካልገላልኩ ሌላ
ሥራዬን ሳላጠናቅቅ የቤተክርስቲያን ሰዓት ይደርስብኛል " ወጥ ቤቷ ሔዳለች»
« ሔዳለች ? » አለ ሚስተር ካርላይል የሷን ንግግር በመድገም
« አዎን አንተ ማምሻህን ከወጣህ በኋላ ነገር ተነሣ " ይኸን ለመንገር ብዬ ደሞ ተቀምጬ አልጠበቅሁሀም ለዛሬ ራት ዶሮ እንዲዘጋጅ ፈልጌ ነበር "
ዶሮቹ ብልታቸው ተለያይተው ታጥበው እንዲቀመጡ ያዘዝኳት ለትናንት ነበር "
ትናንት ብጠይቃት ተሰናድቶ አልቋል አለችኝ »

👍12
« እኔ ደግሞ እነዚያን የውስጥ ብልቶች ስትጠብስ እንደ ልማዷ አሳርራቸው እንዳይሆን ብዬ እንድታሳየኝ ብጠይቃት ከየት ታምጣው - ለካ ዶሮዎቹ እንደ
መጡ ሳትነካ አስቀምጣቸዋለች » መዋሸቷ አነሰና ከኔ ጋር እኩል መመላለስ አማራት በዚህ ጠባይዋና በውሸቷ ሳስጠነቅቃት ጊዜ ትናንት ማታ ወጥታ ሔዶች "
አሁን ሁሉንም ብቻዬን መሥራት አለብኝ »
« ታዲያስ ጆይስ አትሠራውም እንዴ ? »
« ጆይስ ? ስለ ምግብ ምን ታውቅና ነው? እሷ ያበሰለችውስ ከፊቴ አይቀርብም ባርባራ ሔርም ዛሬ ከኛ ጋር ትውላለች » እስቲ ! እስቲ ! ደወሎቹን ትሰማቸዋለህ?
ሚስተር ካርይል አንገቱን ቀና አድርጎ ሲያዳምጥ የቤተ ክርስቲያኑ ደወሎች በሠርግ ወይም በማንኛውም ታላቅ ደስታ ጊዜ የሚያሰሙትን ድምፅ ያስተጋባሉ «
"ለምን ይሆን አለ?"
«አርኪባልድ ... እኔ አንተን ሳክል ሳስበው የነበረውን ያህል እንኳን ማስብ አትችልም" በሎርድ ማውንት እስቨርን መሞት ደስታቸውን መግለጻቸው ነው
እንጂ ሌለ ለምን ብለው ይደውሉ መስሎሃል
ኢስት ሊን” ባለቤት ለውጦ የሚስተር ካርይል ንብረት ሆኗል ቤቱ ከነቤት ዕቃው እንዳለ ገዛው ስም ማዛወሩ በምስጢር ስለ መከናወኑ የጠረጠረ አልነበረም
ሎርድ ማውንት እስቨርንም አንድም ሰው የምስጢሩን ዳና እንዳያገኝ ለማጠናከር ይሁን ወይም ያን የሚወደውን ቦታ ለመሰናበት አይታወቅም ለሁለት ሳምንት ያህል ሰንብቶበት ለመመለስ ስለ ፈለገና ሚስተር ካርላይልም የእርሱን ጥያቄ በደስታ ስለተቀበለው ከልጁና ከአሽከሮቹ ጋር መጥቶ አድሮ ነበር
ዊልያም ቬን የዘለቄታ መኖሪያውን ኢስት ሊን ለማድረግ እንደ መጣ በመገመት ዌስት ሊን ውስጥ ታላቅ ደስታ ሆነ ውበት ወዳድ ዐይኖቹን ለማስደሰት የተደረገው ዝግጅት እጅግ አስደነቀው " ወይዛዝርትና ቆነጃጅት በምርጥ ልብሶችና ጌጣጌጦች አሸብርቀው ወጡ " ደማቁን አቀባበል ለመመልከት ወደ ቤተክርስቲያን ደምቀውና አሸብርቀው ከመጡት ቆነጃጅት አንዷ ባርባራ ነበረች "
ሚስ ካርላይልጆይስን አምና ልትሰጣት ያልፈለገችውን የራት መስናዶ ሥራዋን አጠናቃ ልብሷን በደንብ አድርጋ ለብሳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሔድ ከአርኪባልድ ጋር ሲወጡ አንድ ነገር ሲያንጸባርቅ ታያቸው " መጀመሪያ አንድ ወይን ጠጅ የሴት ጃንጥላ ብቅ አለ " ቀጠለና ወይን ጠጅ የራስ መሸፈኛ ከረቂቅ የወርቅ
ጉንጉን የተሠራ ቀሚስና ነጭ የእጅ ሹራቦች ታዩዋቸው።
« ይች ግብዝ የሞተች!» አለች ሚስ ካርላይል ገና ማንነቷን ሳታውቅ " የተባላችውን ያልሰማችውን ባርባራ መንገዱን ተሻግራ ወደነሱ መጣች።
« አበጀሽ ባርባራ ዛሬስ አባትሽም ሳይገርመው አይቀርም - ከፀሐይ ጮራ የበለጠ ደምቀሻል » አለቻት
« ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ከሚታዩት ብዙ ቆነጃጅት ያጌጡትን ያንዷን ግማሽ ያህል እንኳን አላጌጥኩም » አለች ባርባራ ለሚስ ካርላይል የአድናቆት ሰላምታ ምላሽ ስትሰጥ ዐይኗንና በማፈር ፍም የመሰለውን ፊቷን ቀና አድርጋ "
« ዛሬ ዌስት ሊን በአለባበስ ሳቤላ ቬንን ለማስናቅ የተነሣ መስሏል " አንቺም ትናንት ጠዋት ከባርኔጣ ሰፊው ቤት መምጣት ነበረብሽ ... ሚስ ካርላይል "
« የክት ልብስና ጌጥ መውጫው ዛሬ ነው ? » አለ ሚስተር ካርላይል
« እንዴታ » አለች ባርባራ «የማውንት እስቨርን ኧርል እኮ ዛሬ ከልጃቸው ጋር ወዶ ቤተክርስቲያን ይመጣሉ »
« የገነት ወፍ ላባ ባርኔጣዋ ላይ ሰክታ ባትመጣስ ? » አለች ሚስ ካርላይል
« የከበረና ያማረ ልብስ ለብሳ ለማለት ፈልገሽ ከሆነ በደንብ ለብሳ እንደምትመጣ አትጠራጠሪ» አለቻት ባርባራ "
« ወደ ቤተክርስቲያን ከነጭራሹ ባይመጡስ ? » አለ ሚስተር ካርላይል እየሣቀ " « በራስ ጌጥና በላባ ያሸበረቁት ወይዛዝርት ሁሉ ምን ያህል ቁጭት ይሰማቸው ! »
« ኧረ እንዲያውስ ምኖቻችን ናቸው ? እኛስ ምኖቻቸው ነን ? ከነሱ ጋር ምንም ላናገኝ እንችላለን እኛ የዌስት ሊን ተራ ስዎች ነን " ወደ ኢስት ሊኖች ጠጋ ማለቱ
ኧርሎም ሆነ ልጁ አጉል መንጠራራት አድርገው ሊገምቱብን ይችላሎ » አለች
ኮርነሊያ ።
« አባባም ያለው ልክ ይኸንኑ ነው» አለች ባርባራ " « ትናንት ይኸን ቆቤን ሲያየው ጊዜ ፡ እነሱን ጥየቃ ለመሔድ ስለ ፈለግሁ እንደ ገዛሁት ነገርኩት " ከቁጥር
የማይıፈገቡ የዌስት ሊን ተራ ሰዎች ራሳቸውን ከፍ ከፍ በማድረግ ሎርድ ማውንት
እስቨርንን የሚያህል ታላቅ መኮንን ለመጠየቅ ማሰብ አጐል ድፍረት ይመስላል አለኝ በተለይ ላባውን ሲያይማ በጣም ተገረመ»
« በጣም ረጂም ነውኮ » አላት ሚስተር ካርላይል።
አባቷ ከራሷ የሰካችውን ላባ በሥርዓተ ጸሎት ጊዜ እንዳይሰብርባት በመሥጋት ከሱ ተነጥላ ካርላይሎች ጋር ተቀመጠች " ገና ሲቀመጡ ግንባሩ የተቋጠረ ጸጉሩ የሸበተና አንከስ ያለ የሚራመድ አንድ መኮንንና አንዲት ልጅ እግር
ሴት ብቅ አሉ " ባርባራ በጉጉት ስትመለከት እነዚያ ሕዝብ በናፍቆት የሚጠብቃቸው እንግዶች አልመስል ሲሉዋት ፊቷን አዞረች በተለይ ወጣቷ እመቤት ተራ ቀሚስ አጥልቃ የሣር ባርኔጣ ደፍታ ስታያት እነሱ ሊሆኑ እንዶማይችሎ ገመተች "
ነግር ግን የቤተ ክርስቲያኑ አስ†ባባሪ በትረ ሥልጣኑን ግራና ቀኝ እያወዛወዘ ለብዙ ዓመት ማንም ሳይቀመጥበት ባዶውን ወደኖረው የኢስት ሊን መንበር መራቸው "
« እነዚህ ደግሞ እነማን ይሆኑ ? » አለቻት ባርባራ ለሚስ ካርይል "
« እርሱና ልጁ እመቤት ሳቤላ » አለቻት "
«እንዴ!ሐር እንኳን ሳትለብስ?ላባ ሳትሰካ? ምንም ነር የሌላት ? ከዚህ ቤተክርስቲያን ካለው ከማንኛውም ተራ ሰው ያነሰ ነው የለበሰችው » አለች ባርባራ
« እዚህ ካሉት ጥሩ ልብሶች ለምሳሌ ካንቺ ያነሰ ነው ኧርሎ ግን በጣም ተለዋውጧል " ዐይኖቿንና ደስ ዶስ የሚለው ፈግታዋን ሲያስተውሎት ያቺን «ምስኪን እናቷን ነው የምትመስለው » አለች ሚስ ካርላይል ።
« ደስ የምትል ልጅ ናት » አለች ባርባራ በሐሳቧ «አለባበሷም የጨዋ ወይዘሮ አለባበስ ነው
ምነው ይህን የሚዘናፈለውን ወይን ጠጅ ላባ ባላደረግሁት "
እኛ መቸም ቁራዎች መስለን ሳንታይ አንቀርም።
የሎርድ ዊልያም ቬን ግልጥ ሠረገላ በጸሎት ማብቂያ ጊዜ ከበሩ ይጠብቅ ነበር " አባትና ልጅ ሠረገላቸው ወደሚጠብቅበት ተመለሱ I መጀመሪያ ልጅቱ
ተሳፊረች ቀጠለና አባትዮው ሊሳፈር በሽተኛው እግሩን ደረጃው ሳይ ሲያሳርፍ ሚስተር ካርላይልን አየው " ምልስ አለና እጁን ዘረጋለት " ምንም እንኳን ሚስተር ካርላይል አንድ የገጠር ጠበቃ ቢሆንም ኢስት ሊንን ለመግዛት የቻለ ሰውዐበአቻነት ደረጃ አይቶ መቀበል የተገባ ነው "
ሚስተር ካርላይል አባትዮውን ከጨበጠ በኋላ ወደ ሠረገላው ጠጋ ብሎ ለሳቤላ ባኔጣውን አነሣላት » እሷም እጅ ነሥታ ጨበጠችው "
« ብዙ የማጫውትህ ነገር አለኝ " አብረኸኝ ወዶ ቤት ብትሔድ ደስ ይለኝ ነበር ብርቱ ጉዳይ ከሌለህ ከእንግዲህ ያለውን የዛሬ ቀን ሰዓት የኢስት ሊን እንግዳ ሆነህ ብታሳልፈውስ ? » አለው "
ሎርድ ማውንት እስቨርን ሲናገር ልዩ ፈገግታ አሳየው ሚስተር ካርላይልም አጸፋውን መለሰለትና ዞር ብሎ ለእኅቱ «ኮርኒሊያ ዛሬ ለምሳ አልመጣም ከሎርድ
ማውንት እስቨርን ጋር መሔዴ ነው» አላት "
ሚስተር ካርላይል ከሠረግላው ገባ " ሎርድ ዊልያም ተከተለው " ሰረገላው ተጓዘ " ፀሐይዋ ፍንትው ብላ ደምቃለች » ለባርባራ ሔር ግን የቀኑ ብርሃን ጨልሞባት ነበር።
«ሃርሎን በምን ምክንያት ነው ይኸን ያሀል ሊያውቀው የቻለው
ሳቤላንስ እንዴት ተዋወቃት ? » አለች ባርባራ በመገረም እየመላለሰች "

👍17
« አርኪባልድ ስለ ብዙ ሰዎች አንድ ነገር ያውቃል « ባለፈው ጸደይ ወደ ከተማ ሄዶ ሳለ ከርሱ ጋር ብዙ ተገናኝተዋል ሳቤላንም አንድ ሁለት ጊዜ አይቷት ነበር
«ገጿ እንዴት ያምራል ልጄ» አለች ኮረሊያ ባርባራ መልስ አልሰጠቻትም » ከሚስ ካርላይል ጋር አብራ ተመለሰችና ያ መዓዛው ከሩቅ የሚጣራ የዶሮ ጥብስ ቀረበላት ባርባራ ግን በአካል እንጂ በመንፈስ ወደ ኢስት ሊን
ሄዳ ነበር።
ሚስተር ካርላይል ከቤት ገብቶ ከምግብ ገበታ ተቀመጠ ። ከገበታ ላይ የቀረቡትን የብር
እቃዎች እንደ መስታወት የሚፈልቁ ብርጭቆዎች ማብረጃዎች ልዩ ልዩ የሚያማምሩና ብርቅ የሆኑ የሸክላ ቁሳቁሶችን ተመለከ በጤንነቱ ምክንያት ባለቤቱ ሊቀምሳቸው የማይችል የተለያዩ የወይን ጠጅና የምግብ 0ይነቶች
እንዶዚሁም በከበረ ልብስ ተሸላልመው ከቤት የሚንጋጉትን አንድ መንጋ አሽከሮች
ተመልክቶ የድግሱን ባለቤትና ረጋ ያለችዋን እመቤት ሲያይ በሁኔታው በጣም ተገረመና አዬ ! የነዚህ ትልልቅ ሰዎች ኑሮ ኑሮ አይበለው : ለውዳሴ ከንቱ ሲሉ
ዐቅም የማይፈቅደውን ወጭ እያወጡ የይምሰል የመግደርደር ኑሮ ነው የሚኖሩት ብሎ አሰበ " ኧርሎ በዕዳ ተወጥሮ የሚሆነው ጨንቆት ተቸግሮ እያለ ስሙን
በታላቅ ሰውነትና በቸርነት ለማስጠራት ሲል የቤቱን ወጭ ለመቀነስ እንኳን አልሞከረም » በዚህ ዐይነት ችግሩን እንዴት ተቋቁሞ መኖር እንደ ቻለ የሚገርም ነበር።
ለወደፊትም እስከ መቼ ሊገፋው እንደሚችልም አስቸጋሪ ጉዳይ ነው በርግጥም ካርላይል የተመለከተው መሰናዶ በጣም የሚያስዶንቅ ቢሆንም የቤቱ ጌታ ከነበረበት ችግር ጋር ሲገናዘብ አስፈላጊም ተገቢም አልነበረም።
ምሳ እንደ ተበላ ሳቤላ አባቷንና ካርላይልን ለብቻቸው ትታቸው ብቻዋን ..ተቀመጠች ። ሐሳቧ ከአንዱ አበባ ወደ ሌላው ከሌላው ደግሞ ወደ ሌላው እንዶ
ቢራቢሮ ከአንዱ ትዝታ ወደ ሌላው ትዝታ ከአንዱ ምኞት ወደሌላው ምኞት እያረፈ ይበራል " እየበረረ ያርፋል " ስለ እናቷ ስታስብ ያባቷ በሺታ ከፊቷ ይደቀንባታል " ያን ትታ ለንደን ውስጥ ያየቻቸው ነገሮች በሐሳቧ ይመጡባታል " በተለይ ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ አብራው ብትሰነብት ኖሮ የመንፈሷን ሰላም አጥታ አደገኛ
ሁኔታ ላይ ሊጥላት ይችል የነበረው የፍራንሊዝ ሌቪሰን ትዝታ ሲመጣባት የልቧ ምት ይጨምራል ። ነገሩ ሁሉ ወደ ሕልም ይመለስባታል ልቧ ስውር ይላል።
የዚህ መርዙ በቀላሉ የማይነቀል ትዝታ መፈጠር ዋናዋ ጠንቅ የነበረችው እንዲቀራረቡና ብቻቸውን እንዲሆኑ አመቺ ሁኔታ የፈጠረችው ያቺ ለሰው በጐ
አመለካከት የጐደላት ንፉግ ጨካኝና ክፉዋ ሚሲዝ ቬን ነበረች
ሳቤላ በረጂሙ ተንፍሳ ብድግ አለችና ውስብስብ ብለውባት የነበሩትን ሐሳቦች ሁሉ ለነፋስ በተነቻቸው አባቷና እንግዳው ወደሻይ መጠጫ ክፍል ለመምጣት የቸኮሉ አልመሰሉም " እሷም ወደ ፒያኖዋ ሒዳ መጫወት ጀመረች
ዊልያም በርግጥም አልቸኮለም ። እሱ የወይን ጠጁን ትቶ ለመነሣት ምንጊዜም ቸኩሎ አያውቅም
ለነበረበት የጤንነተት
የመርዝ ያህል ይጐዳው እንደ ነበር ቢያውቅም መተው አልቻለም" ሁለቱም ጥብቅ
ጭሙውት እንዶያዙ ሚስተር ካርላይል የጀመረውን ዐረፍ† ነገር ሳይጨርስ ከመኻል አቋርጦ ጆሮውን ቀና አደረገ።
ደስ የሚል የሙዚቃ ምት ሲንቆረቆር ሰማ ልክ ከጆሮው አጠግብ ያለ መስለው!
ከየት እንደሚመጣ ግን አላወቀውም ሙዚቃውን ዝግ ግልጽ ያለ የሰው ድምፅ
ሲያጅበው ሰማና ሚስተር ካርላይል ትንፋሹን ያዝ አደረገ በተመስጦ ያዳምጠው ጀመር "
ሎርድ ዊልያም ቬንና ሚስተር ካርላይል በጭውውታቸው ስለዚህ ዓለም ድካምና ጣጣ" ስለገንዘብ ማግኘትና ማጥፋት ስለ መውሰድና መመለስ አንሥተው ሲነጋገሩ ' የዚህ ጋር ተቃራኒ የሆነው መዝሙር ለጆሮ እየመጣና እየለሰለሰ ሕሊናን
እየወቀሰ ከመኻል ድንቅር አለባቸው።
« ሳቤላ ናት ኮ » አለ አባቷ
« ዝማሬዋ ልዩ የሆነ መስሕብ አለው ይህም ጣዕምና ለዛ ያለው መስሕብ ሊኖረው የቻለው የድምጿ ቃና ዝግ ያለ በመሆኑና በመለስለሱ ነው። ጨዋታዋ ሁልጊዜ እንደዚሁ ነው እኔ እምልህ የሚያቧርቅ ሙዚቃ
አልወድልህም " ለመሆኑ አንተ ሙዚቃ ትወዳለህ? »
« ባለሙያዎቹ ጥሩ ነው ብለው የሚጠሩትን ሙዚቃ የምቀበልበት ጆሮ ' የማጣጥምበት ስሜት እንደሌለኝ አድርገውይነቅፉኛል " ይኸን ግን እወደዋለሁ »
አለ ሚስተር ካርላይል እንደ መሣቅ ብሎ "
« የምትጫወትበት መሣሪያ ከግድግዳው ተጠግቷል የክፍሎቹ መለያያ ደግሞ
ስስ ነው » አለ የሳቤላ አባት አሁን ሳቤላ እኛንም ሆነ ራሷን ማዝናናቷ አይታወቃትም»
«ርግጥም አልታወቃትም እሷ እየቀያየረች መዝሙሮቿን ስትጫወት ሚስተር ካርላይልም ምሽቱ ወዶ ሌሊት እንዴት እንደሚሮጥ ልብ ሳይለ ደስ ደስ የሚለውን ሙዚቃ እያዳመጠ ተቀመጠ ".....
💫ይቀጥላል💫

❤9👍6
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሦስት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...በእኩል ሰሞን ኹለት ተቃራኒ የሚመስሉ ጥቅሶች ሰማሁ አንደኛዉ:-
“ተስፋ የሚባል ተሟጦ ተሟጦ፣ ጭልጥ ብሎ አልቋል:
እንጥፍጣፊዉ እንኳን በማንም እጅ ላይ የለም፡ አሁን ማንም
ላይ መንጠልጠል አንችልም:: የራሳችንን ተስፋ ግን ራሳችን
እንዳንፈጥር የሚከለክለን የለም!” ሲለኝ
ሌላኛዉ ደግሞ፡-
“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን
ያድሳሉ፧ እንደ ንሥር በክንፍ ይወጣሉ፡ ይሮጣሉ፣አይታክቱም: ይኼዳሉ፣ አይደክሙም” ይላል
ኹለቱም ስለ ተስፋ ናቸዉ፡፡ ለኹለቱም ምንጭ ተጠቅሶልኛል ኹለቱንም የነገሩኝ ሰዎች ለእኔ ከማሰብ እንደ ነገሩኝ አዉቃለሁ የመጀመሪያዉን በቅጡ የማዉቃቸዉ ዘመናዊ የሥነ ልቡና ባለሙያ፣ ኹለተኛዉን ደግሞ
በቅጡ የሚያዉቁኝ የንስሐ አባቴ ናቸዉ የነገሩኝ፡ የመጀመሪያዉ
እምነቱንም ሥራዉንም ያንቺ ጉዳይ ነዉ ሲሉኝ፤ ኹለተኛዉ ደግሞ ማመኑ ያንቺ፣ ሥራዉ ግን የእግዚአብሔር ነዉ ብለዉኛል፡
ሕይወት ደግሞ የምርጫ ወንበር ናት አሉ᎓ ታዲያ እኔ የቱን ልምረጥ?
የቱን ነዉ መምረጥ ያለብኝ?
እህቶቼ እና ወንድሞቼ እንደ ዋዛ ጀምረዉ፣ አንድ በአንድ ሸርተት እያሉ ጥለዉኝ ጥለዉኝ፣ አሁን አፉን ሞልቶ እህቴ ነሽ የሚለኝ ጠፍቷል።
እንዲያዉ ምናልባት ቆርጠዉ ያልቆረጡ ቢኖሩም እንኳን፣ ጨክነዉ እህታችን አይደለሽም አይሉኝ እንደሆነ እንጂ፣ እንደ ወትሮዉ ግን በእርግጠኝነት ‹እህታችን ነሽ አይሉኝም: እኔን ከመጥላታቸዉ የተነሳ
እህ ብላ የወለደቻቸዉን እመዋን ሳይቀር የዉብርስት እናት› እስከ ማለት ደርሰዋል የጃሪምስ እንዲያዉም አይወራም:
ይኼ ሁሉ ለሆነብኝ ለእኔ፣ ልጄ ባትኖርልኝ ኖሮ፣ ይኸኔ ሟች ነበርሁ። አፈር ገብቼ ነበር።
በስንት ዉጣ ዉረድ ቢሆንም፣ ልጄ ቱናት የመጀመሪያ ሕክምናዋን አግኝታልኛለች:: ጭንቅላቷ ላይ የሚመነጨዉ የዉሃ ክምችት እና ጥቅም
ላይ የሚዉለዉ ዉሃ
እንዲመጣጠን የሚያደርግ ቀዶ ሕክምና ተደርጎላታል በእርግጥ ሕክምናዉ እንኳንስ የእኔን የእናቷን አንጀት፣ ደመኛዬ ነሽ የሚለኝን ጃሪምን ሳይቀር አንሰፍስፋዋለች አሉ ያቺን ከደም የቀዘቀዘች እርጥብ ገላዋን ተቀዳ፣ ጀርባዋ ላይ ለነበረዉ የአጥንት ክፍተት
ጉዳቷ ሕክምና ተደርጎላታል፡ ይኼም አይብቃሽ ብሏት፣ ከላይ
ከጭንቅላቷ እና ዝቅ ብሎ ደግሞ ሆዷ ላይ ቀዳደዉ ነበር ማስተንፈሻ ቱቦዉን (shunt) የቀበሩላት።
አቤት መቻሏ!
እንደ'ኔ ፍራቻ ሳይሆን እንደ እሷ ብርቱነት፣ በትንሽ በትልቁ ሞተችብኝ እያልሁ ሥርበተበት ቱናት ናትና ልጅቷ፣ ሁሉንም ቻለችዉ፡ ችላ አሳለፈችዉ፡ እንደ ቱናት ቻይ አለ ወይ በምድር? እኔ አላዉቅም።
“አልሄድሽም እንዴ እመዋ?” አልሁ፣ ከልጄ ጋር ብቻ ዘግቼ
የተቀመጥሁበትን ክፍል በር ድንገት ያንኳኳችብኝ እመዋ መስላኝ ሌላ ሰዉ መሆኑን ያወቅሁት ድምፁን ስሰማ ነዉ፡፡
“ሰላም አደርሽ ዉብርስት?''
“እግዚአብሔር ይመስገን ማነዉ?” አልሁ፣ በሩን ለመክፈት
እያቅማማሁ አቅማምቼ አቅማምቼ ስከፍተዉ፣ አንድ ወጣት ከደጅ ቆሞ አገኘሁት ቁመናዉ ልጅ እግር ቢሆንም፣ አንተ ብሎ ማቅለሉ
አልመጣልኝም የእመዋን ቤት በረሃ፣ ልጄ ቱናትን ደግሞ ገዳም አድርጌ እሷ ዉስጥ ከመነንሁ ወዲህ፣ የመነኮሳቱ ባህል እና ሥርዓት እያደረብኝ መጥቷል፡ ማልዬለታለሁ አነጋገሬን፣ አመጋገቤን፣ ጸሎቴን፣ አጠቃላይ
ሥነ ሥርዓቴን እና ለዓለም ያለኝን ርቀት እንደ መነኮሳት ለማድረግ
ልምምድ ላይ ነኝ የማነባቸዉ መጻሕፍት ሁሉ የምንኩስናን ሕይወት የሚያወሱ እንዲሆኑ እመርጣለሁ፡ ከዚህ ሌላ፣ ማንኛዉም ወደ ዓለም የሚስብ ነገር ላይ ድርሽ ማለቱን ትቼዋለሁ፡ ፈታኙን የቱናትን የሕክምና
ጣጣ ጨርሼ እመዋ ቤት ባለኝ ክፍል ዉስጥ ጠቅልዬ ከገባሁ
ወዲህ የከተማዉን ግርግር አይቼዉ አላዉቅም፡ እንኳንስ በአካል በወሬም እንኳን፣ ስለ ከንቱዉ ዓለም የመስማት ፍላጎቴ ሞቷል፡ አላስችል ብሎኝ
ካስቀረኋት አንድ ክራሬ በቀር የቀድሞ ልብሶቼን፣ የቀድሞ ጌጣጌቶቼን የቀድሞ ሥራዬን ሁሉ እንዳለ እርግፍ አድርጌዋለሁ
“ምን ልርዳዎ የኔ ወንድም?” አልሁት፣ በደህና ትሕትና᎓
“ጋሽ ባልቻ ሊያናግሩሽ ይፈልጋሉ” አለኝ፣ ሞባይሉን ሊያቀብለኝ እጁን
ወደ'ኔ እየዘረጋ
“ባልቻ?”
“አዎ፤ መስመር ላይ ናቸዉ: እንኪ አናግሪያቸዉ” አለ፣ እንደገና የበለጠ ቀረብ ብሎኝ፡፡
“ሄ..ሎ” አልሁ፣ እያቅማማሁ ሞባይሉን ተቀብዬ ወደ ጆሮዬ አድርጌዉ፡
“ማንም አልቀደመኝም አይደል?” አለኝ ባልቻ፣ አብሮኝ ያደረ ይመስል ጨርሶ ሰላም እንኳን ሳይለኝ፡
“ምኑን?”
“እህ! ረስቼዋለሁ እንዳትዪኝ ብቻ”
“ምኑን?”
“አንቺ! ቀኑን ረስተሽዋል?”
“እህእ፣ የቱን ቀን?”
“የዛሬ ዓመት እኮ ነዉ ቱናት የተወለደችዉ። ልደቷ መሆኑ ረስተሽዉ ነዉ?”
ወይ መርሳት! እንኳንስ የተወለደችበትን ይቅርና፣ መቼ ሕክምና እንደ ገባች፣ መቼ እንደ ወጣች፣ ለመጀመሪያ ጊዜ መቼ ፈገግ እንዳለችልኝ፣ የትኛዉን ልብሷን መቼ እንዳስገዛሁላት ጭምር ከነዕለቱ እና ከነሰዓቱ
ልረሳዉ አልችልም: ያም ቢሆን ግን የልደት ቀኗ ላይ ትንሽ ተወዛግቤ ነበር፡ ያለ ቀኗ ከሆዴ የተወለደችበትን ዕለት ነዉ ልደቷ ብዬ የማከብርላት ወይስ ከዚያ በኋላ ለኹለት ወራት ያህል ቆይታ ከማቆያ ክፍል ወጥታ እቅፌ ዉስጥ የገባችበትን ዕለት የሚለዉ ግራ አጋብቶኝ
ነበር ባልቻ የሚለዉን ከወሰድሁ ግን፣ እዉነትም የቱናት ልደት ዛሬ
ዛሬ ከሆዴ ከወጣች አንድ ሙሉ ዓመት የደፈነችበት ዕለት ነዉ።
“ረስተሽዋል አይደል?”
“ኧረ በጭራሽ!”
“እኮ ይዘሻት ነያ”
“የት?”
“አጠገብሽ ያለዉ ልጅ መኪና ይዟል: እሸቴ ነበር ሊመጣልሽ የነበረዉ: ግን አንድ ድንገተኛ ተልእኮ ተሰጠዉ እና መምጣት አልቻለም አንቺ እስከምትደርሺ ግን እሱም ሥራዉን ይጨርሳል። ስለዚህ ቱናት ቆንጆ አድርገሽ አልብሻትና ይዘሻት ቶሎ ነይ”
“እህእ፤ መቀለድህ ነዉ እንዴ? ከመቼ ወዲህ ነዉ እንኳንስ ገዳሜ
ቱናትን ይዤ ይቅርና ለራሴስ ብሆን ከዚህ ወጥቼ የማዉቀዉ?”
“ይልቅ እንዳትቆዩ” ብሎ፣ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ጠረቀመዉ፡ እንደ
ወትሮዉ ቢሆን እንኳንስ እያወራሁለት ሊዘጋብኝ ይቅርና፣ ቻዉ ተባብለን እንኳን ለመዝጋት እጁ እሺ አይለዉም: የአሁኑ ግን በእሱ የማላዉቀዉ እንግዳ ዐመል ሆነብኝ፡ ተዋክቦ ነዉ እንዳልል፣ ምንም የቸኮለ አይመስልም: መቼም ጊዜ ባይኖረዉ ኖሮ የቱናትን ልደት ካላከበርን
አይለኝም።
ከተቀየመም ይቀየመኝ እንጂ ቱናትን የትም ወስጄ አላንገላታትም ብዬ
ወሰንሁና ሞባይሉን ለሰጠኝ ልጅ ልመልስለት ዞር ስል አጣሁት ባልቻን
አናግሬ ስጨርስ እንደምከተለዉ እርግጠኛ በመሆን ከግቢ ዉጪ ወደ
መኪናዉ ተመልሷል፡ እየጠበቀኝ ስዘገይበት ጊዜ፣ ያቺን የሲራክ ፯ ኮድ
የሆነችዋን የመኪና ጥሩንባ አሰማኝ፡ ቢያንስ ሞባይሉን መመለስ
ስላለብኝ፣ ልጄ ለቅጽበት ብታጣኝ የማጣት መስሎኝ እንደ ፈራሁላት
ወደ መኪናዉ ሮጥሁ።
“ይቅርታ ወንድሜ፣ ባልቻ ዝም ብሎ ነዉ እዚህ ድረስ ያደከመዎ” አልሁት፣ በመነኩሴ የትሕትና ልምምዴ፡
ቱናት ገዳምሽ ናት ብለዉኝ የለ የንስሐ አባቴ? ታዲያ ገዳምን ወዳለበት
ሄደዉ ይሳለሙታል እንጂ፣ ራሱ ገዳም ተነቅሎ ካልመጣልኝ ይባላል እንዴ? በጭራሽ! ያዉም የገዳምን ክብር ከሚያዉቀዉ ከባልቻ ይኼ
ይጠበቃል? አዝናለሁ፣ ያለ ተፈጥሮዋ ወደ ጩኸት አዉጥቼ ገዳም አላስረብሻትም: አልሄድም፡ በእሷ የሚያድረዉን አምላክ ማመስገን የፈለገ ቢኖር እየመጣ ይሳለማት እንጂ፣ ገዳሜን ለመንቀል በጭራሽ አላደርገዉም
አልሞክረውም

👍29
ገዳሜ ቱናት፣ ምንም እንኳን ሕክምናዋን ብታገኝልኝም፣ እግሮቿ ግን አሁንም ቢሆን አይላወሱም፡፡ ሕክምናዉ የጠቀማት ዋና ነገር፣ ጭንቅላቷ ላይ ከጥቅም የሚተርፈዉ ፈሳሽ እንዳይጨምር እና የጀርባ አጥንቷ ላይ ያለዉ ክፍተት እንዲዘጋ ብቻ ነዉ እንጂ፣ ዛሬም ራሷን ችላ ከጎን ወደ ጎን እንኳን አትገላበጥም፡ እንዲያዉ ዓይን ለዓይን እንዳያት አልጋዋን
ከወደ ትራስጌዉ ቀና አድርጌ ስለጥጠዉ ከፍ ብላ ትታየኛለች እንጂ በቂጧ መቀመጥ የሚሞከር አይደለም፡ አብዛኛዉን ጊዜ በግሉኮስ፣ ከስንት አንድ
ደግሞ ከጡቴ ትቀምስለታለች እንጂ፣
ዛሬም ምግብ አልጀመረችልኝም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአንጎሏ እና ይኼ ጉዳይ የሚመለከተዉ የአንጀት ክፍል ተግባቦት የላቸዉም በዚህ የተነሳ ራሷን
ችላ ዓይነ ምድሯን መጣል አትችልም: ካካ ማለት አይሆንላትም ያዉም እኮ ራስን መቻል ሲባል፣ ያለ ድጋፍ ፖፖ ላይ ቁጭ ማለት አይደለም እሱማ ለእሷ ቅንጦት ነዉ፡፡ ልክ ለማንኛዉም ሰዉ እንደሚሆነዉ
አድርጎ፣ ካካ በራሱ ጊዜ አይመጣላትም እንዲያዉም ካካዋ መምጣት
አለመምጣቱን ሁሉ አታዉቀዉም: እኔ ነኝ ትንሿን ጣቴን በፊንጢጣዋ በኩል እያስገባሁ ካካ የማስደርጋት ዓይነ ምድር ደግሞ በባሕሪዉ ሲመጣ ይመጣል እንጂ ሰዓት የመቅጠር ልማድ የለዉም: ስለሆነም መጥቶባት ይሆናል ብዬ በገመትሁበት ጊዜ ሁሉ እሞክራታለሁ።
አንዳንድ ይኼንን ጭንቋን ሳይ፣
ጊዜ እንደ መረታት እላለሁ፡
እንዲያዉም አንዳንድ ጊዜስ የሸዊት ጓደኛ፣ እኔ አንቺን ብሆን፣ ወደ
ማሞቂያ ክፍል አላስገባትም ነበር› ያላት ምክር የእናት ልቤን ሳይቀር ቅርጥፍ ያደርግብኛል: ያም ቢቀር ፈጣሪ በራሱ መንገድ በወሰዳት የሚል ምኞትም ሞክሮኝ ያዉቃል፡ የማላዉቀዉ ስሜት ይፈታተነኛል።
በዚያ ላይ የመድኃኒቷ ብዛት!
ይኼን ሁሉ ጉድ የቻለችዉ የአንድ ዓመት ጨቅላ መሆኗ እንኳን ለእኔ፣
ለራሱ ለእግዚአብሔር ጭምር ሳይደንቀዉ አይቀርም፡ ሁሉንም መቻሏ
ሳያንስ ደግሞ፣ አልፎ አልፎ ፈገግ ትልልኛለች፡ ያን ጊዜ ነዉ እኔን
እናቷን ማየት! ልቤ ቅልጥ ትላለች፡ ዓይኗን ጥላብኝ እንደሆነ ፈገግ ያለችልኝ፣ ሰማዩን ዘልዬ ካልሳምሁት ብዬ ያዙኝ ልቀቁኝ እንደምል ታዉቅልኝ ይሆን? የትንፋሿ ጠረን እንደ ቤተ መቅደስ እጣን ነዉ
የሚያማልለኝ፡፡ በጭንቋ ሰዓት ክፉ እና ደግ የሚያሳስበኝን መንፈስም
የምዋጋዉ በዚህ ትንፋሿ ነዉ፡ ይኼን እያሰብሁ ስጾም እና ስጸልይ፣
ተጫጭኖኝ የነበረ ፈተና ሁሉ ይቀልልኛል፡
የምትደንቅ ናት!
ይኼን ሁሉ እያወቀ ነዉ እንግዲህ፣ ባልቻ ቱናትን አምጫት የሚለኝ፡ ገዳሜን ከገደምሁበት የእናቴ ቤት ማንቀሳቀስ ይቻለኝ ይመስል ታይቶም ተሰምቶም የማያዉቀዉን!
“ዝም ብሎ ነዉ ያስቸገረዎ:: ግድየለም ይመለሱ፣ ለባልቻ እኔ ራሴ እደዉልለታለሁ” አልሁት ሹፌሩን፣ እንደ ታዘዘዉ እኔን ይዞ ካልሆነ ወደ የትም ንቅንቅ የማይል መሆኑን አንገቱን እየወዘወዘ ስላሳየኝ፡
“ኧረ ዉብርስት…” አለኝ፣ አጣብቂኝ ዉስጥ የከተትሁት ስለ መሰለዉ፡
“ግድየለም እሺ” አልሁት፣ እዚሁ በፊቱ ለባልቻ ልደዉልለት ሞባይሉን
መልሼ እየተቀበልሁት የትም እንደማልሄድ ደዉዬ ላሳምነዉ እና ለዚህ ሹፌርም ትእዛዙን እንዲያነሳለት ላስደርግለት ይገባል፡ ያለበለዚያ ከባልቻ የትእዛዝ ክቡርነት አንጻር፣ ለዚህ ሰዉ እኔ ምንም ነኝ፡፡ ባልቻ ተወዉ ካላለዉ በቀር፣ የፊጥኝ አስሮም ቢሆን ሊወስደኝ ሁሉ ይችላል
ለባልቻ መልሼ ስደዉልለት ግን ስልኩን ሊያነሳልኝ አልቻለም፡፡ ወይም
አልፈለገም: ነይ ብያለሁ ነይ ነዉ ነገሩ?
ወይ ፈተና! ምን ማድረግ እንደምችል እያወጠነጠንሁ ወደ ቱናት ተመለስሁ። ከዚያ በሩ ላይ ቆሜ፣ መዉጣትን እና አለመዉጣትን እንደገና አሰብሁባቸዉ
ልክ አባ እንጦንስ እንደ ተፈተነዉ ተፈተንሁ ማለት ነዉ? አባ እንጦን ማለት እንግዲህ ርእሰ መነኮሳት ተብሎ የተጠራ፣ ምንኩስናን ሀ ብሎ የጀመረዉ አባት መሆኑን አዉቃለሁ፡ ሀብት እና ድሎቱን እርግፍ አድረጎ በበዓት ዉስጥ ብቻ መንኖ ኖሮ ኖሮ፣ አንድ ቀን ከበዓቱ ዉጣ
ዉጣ የሚል መንፈስ ይገፋፋዋል፡ ልክ አሁን እኔ እንደ ቆምሁት፣ አንድ
እግሩን ከዉስጥ ሌላኛዉን ደግሞ hዉጪ አድርጎ ወደ ዉስጥም ወደ ዉጪም ለመሄድ ግራ ገባዉ፡ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ምሳሌ ገልጾ ወደ
በዓቱ የሚመልሰዉን መልአክ ላከለት
ለእኔስ? መልአክ ቀርቶ ራሱ እግዚአብሔር ወርዶ ቢያናግረኝ እንኳን
የማስተዉልበት ልቡና ያለኝ ይመስል፣ ደጅ ደጁን አየሁ አይዞሽ የሚለኝን መልአክ በዙሪያዬ ፈለግሁት በእርግጥ በዓይኔ በብረቱ ባላየዉም፣ ለዓይነ ልቡናዬ ግን ተገልጦልኛል። እንደ አባ እንጦንስ ወደ በዓቴ የሚመልሰኝን ሳይሆን፣ ለባልቻ ስል ልሸነፍ እንደሚገባኝ የሚናገር መልአክ ነዉ ወደ'ኔ እንደ መጣ ያመንሁት
አላጣሁትም: አገኘሁት።
እስከ አሁን ድረስ ባልቻ ነይ ወዳለኝ ሄጄ አትርፌ እንጂ ተጎድቼ አላውቅም፡ ሌላዉ ቀርቶ፣ ቱናትን በተመለከተ በተለይም በየሆስፒታሉ ስወጣ ስወርድ እሱ ከአጠገቤ ያልነበረበት ጊዜ የለም: ሲጀመርስ የተዋወቅሁት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ጉዳይ አይደለም? ከሌለዉ
ጊዜ እያፈስ የሰጠኝ መከራዎቼን የተጋራኝ፣ በጉዞዬ ሁሉ ያገዘኝ እሱ
ነዉ፡ በዕድሜም በሙያም በስምም የስንት ጊዜ ታላቄ ሆኖ ሳለ፣ ዝቅ ብሎ እኔን ወዳጅ አድርጎኛል ያዉም የኔ ልጅ እያለኝ በፍቅር ቃል።ታዲያ እሱ ለእኔ ሲል ያን ሁሉ ከሆነ፣ እርሙን አንድ ዉለታ ቢጠይቀኝ እምቢ ልበለዉ? ያዉም እንደ ዉለታ ከቆጠርሁት! እሱን አስቀይሜስ
ሞልቶም አይሞላልኝ።
“መጣሁ መጣሁ” አልሁት ጮህ ብዬ፣ ወደ ባልቻ ወሳጄ የመኪናዉን
ጥሩንባ ለስንተኛ ጊዜ እንደሆነ ሲነፋ ሰምቼዉ፡
በለበስሁት ልብስ ላይ መደረቢያ ጣል አደርጌበት፣ በልኳ የተሠራችዋን
ተሽከርካሪ አልጋ እየገፋሁላት ቱናትን መኪናዉ ዉስጥ አስገባኋት፡ ከዚያ
ጎኗ ተቀምጬ ተመቻት አልተመቻት እያልሁ እሷን እሷን ሳይ ሹፌሩ
በየት በኩል ወደ የት እንደ ወሰደኝ እንኳን ቀና ብዬ አላየሁትም፡መኪናዉን ትንሽ ፈጠን እያለ ገጭ እጓ ሲያደርግብኝ ቀስ እንዳል ከመንገር ዉጪ፣ ሌላ ቃል አልተለዋወጥንም: በዚህ ሁኔታ ለግማሽ
ሰዓት ያህል እንደ ተጓዝን መኪናዉን አብርዶ ቆመ: በእኔ ግምት ሲራክ፯ የተሠወረበት የማኅበራችን ዋና ሕንጻ መኪና ማቆሚያ ዉስጥ ደርሰናል
ብዬ ነበር፡ የቱናትን አልጋ ሸርተት አድርጌ ለመዉረድ በሩን ከፍቼ
ስመለከት ግን፣ የቆምንበት ቦታ በጭራሽ እንደጠበቅሁት አይደለም
“ይቅርታ” አልሁት ሹፌሩን፣ እንደ መደንገጥ ብዬ፡ ዙሪያ ገባዉን ሁሉ
ተዟዙሬ ብመለከት አንድም የማዉቀዉ ምልክት ላገኝበት አልቻልሁም ብቻ አንድ የመንደር አማካይ በሚመስል አካባቢ ላይ፣ መንገድ ዳር ቆመናል፡
“ይቅርታ፤ ወዴት ነዉ ያመጡኝ ወንድማለም”
“ደርሰናል”
“ደርሰናል? የት ነዉ የደረስነዉ?” አልሁት ፊቴን ኩስኩስ አድርጌበት፣
የሰሞኑንም ትእግስቴንና ትሕትናዬን በኃይል እየሸረሸርሁት፡
“እዚህ ነዉ እንዳደርስሽ ጋሼ ባልቻ ያዘዙኝ” አለ ከእኔ በላይ ተኮሳትሮ፣
ከመኪናዉ ወርዶ በእኔ በኩል ያለዉን በር እየከፈተልኝ፡፡
ጉድ ፈላ አልሁኝ ለራሴ: ምንም ሊገባኝ አልቻለም:: ቢሆንም ግን እንድወርድ እየተቁለጨለጨብኝ ስለሆነ፣ እምቢ ብዬ መቀመጥ አልችልም: ቀድሜ እኔ ወረድሁና፣ ቱናትን ከነአልጋዋ ታቀፌ መሬት ላይ አሳረፍኋት፡ ደግነቱ አለፍ ብሎ ትንሽ ግራር ስላየሁ ጠንራዋ የረፋድ ፀሐይ አታሰጋትም፡፡ ጥላዋ ላይ ቱናትን አሣርፌ፣ እያደረገ ስላለዉ ጉድ ሁሉ እንዲያስረዳኝ ላፋጥጠዉ ዞር ስል፣ መኪናዉን የኋሊት አሽከርክሮ እብስ ብሏል፡ በቃ ተጫዉቶብኛል አልሁ። በዚች ቅጽበት ስንቱን እንደ ጠረጠርሁት! ጃሪም ከእነ ልጄ ሊያጠቃኝ

👍24❤2😁1😱1
ነዉ፣
የመንግሥት ደኅንነቶች ናቸዉ፣ የእህቴ አድራጎት ነዉ› እያልሁ ያልጠረጠርሁት እና የቀረኝ የለም: ያለ አንዳች ነገርማ አስችሎት ባልቻ ጥድፍ ብሎ ጆሮዬ ላይ ስልክ አይዘጋብኝም:: ቀድሞነገር፣ በስልክ ያናገርሁት ራሱ ባልቻን ባይሆንስ?
ያላስተዋልኋት ነገርማ አለች፡
“እንደምን አረፈድሽ የኔ እህት?” አለችኝ አንዲት ደርባባ ሴት፣ እንጀ አጋጣሚ በመንገዱ እያለፈች ሳለ እንደ ዋዛ መለስ ብላ እጅ ነስታኝ።
“እግ..እግዚአብሔር ይመስገ” አልሁኝ፣ እንደ መደናገር ብዬ፡ መልኳ እንግዳ አልሆነብኝም:
“ምነዉ በደህናሽ ነዉ፤ ልጅ ይዘሽ በመንገድ ዳር?”
“ደህና ነኝ” አለሁኝ፣ የሴትዮዋን መልክ አስታዋሽ ልቤ ላይ ብቅ ብሎ
ጥልቅ እያለብኝ፡፡ የት እንደማዉቃት ልጠይቅ አልጠይቅ ብዬ ከራሴ ጋር
ትንሽ ተከራከርሁ፡
“ቱናትስ እንዴት ናት?”
ይኸዋ! እሷ ጭራሽ ከእኔም አልፋ ከማንም ሸሽጌ የማኖራትን ገዳሜን
ሳይቀር ታዉቃለች፡ ኧረ ይቺ ሰዉ ማናት?
“አጠፋሽኝ መሰል”
“አይ ማጥፋት ሳይሆ” አልሁ፣ እሷ በዚህ መጠን አዉቃኝ እኔ አላወቅሁሽም ማለቱ ቢያሳፍረኝ፡.....

❤13👍12
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
... ሎርድ ማውንት አስቨርን ኢስትሊን ለመሰንበት ያሰበው የሁለት ሳምንት ጊዜ ከማለፉ በፊት የእግሩ በሽታ ክፉኛ ስለ ተቀስቀሰበት ወቶ ሊሔድ አልቻለም ሚስቸር ካርይልን ግን
ሁኔታውን በማየት አስከ ፈለገበት ጊዜ ድረስ ሳይሰቀቅ ቢቆይ እንደማይከፋው ገለጸለት ኧርሎም ቶሎ ሽሎት በእግፋ እንደሚቆም ተስፋ በማድረግ ሚስተር ካርላይልን አመሰግነው።
ቢሆንም እንዳሰበው አልተሻለውም " በሽታው ሙሉ በሙሉ ባያስተኛውም ከቤት መውጣት ሳይችል እስከ ጥቅምት ቆየና ትንሽ ምልስ አለለት »
በአጥቢያው የታወቁ ሰዎችም በሽኛውን ተመላልስው ከመጠየቃቸውም ሌላ ሳቤላንም ከቤታቸው እየጠሩ በማነጋገርና በማስተናድ መልካም ጉርብትናቸውን አሳዩዋት " ከሁሉ የበለጠ የርሱ ዋና ጠያቂ ግን ሚስተር ካርላይል ነበር "
ከኧርሎና ከሳቤላ ጋር በጣም ተቀራረቡ " ኧርሎ ከመጠን በላይ ስላላመደወና ስለ ወደደው አንዳንድ ቀን ብቅ ሳይል የቀረ እንዴሆነ በጣም ቅር ይለው ነበር
« እኔ ከኅብረተሰብ የቶለየሁ ብቸኛ ነኝ » አላት ለልጁ " « ሚስትር ካርላይል ይህን ችግሬን ዐውቆ እዚህ ድረስ እየተመለሰ የብቸኝነት በሺታዬን ሲያቀልልኝ ደግነቱና ለሰው አሳቢነቱ በጣም ይሰማኛል።
« በጣም ደግ ሰው ነው እኔማ በጣም ነው የምወደው..አባባ » አለችው
« እኔ ልጄ . . . የሱን ያህል የምወደው ሰው የለኝም » ሚስተር ካርላይል እንደ
ልማዱ በሽተኛውን ለማነጋገር መጥቶ ሳለ አባቷ ሳቤላን እንድትዘምርላቸው
ጠየቃት።
«ካልክ እሺ ... አባባ " ግን የፒያኖው ቅኝት በጣም ስለ ተበላሸ ምቱ ከድምፄ ጋር አይስማማም ደስ አይልም ዌስትሊን ውስጥ እዚህ ድረስ መጥቶ ፒያኖ የሚያይልኝ ሰው አይገኝም ... ሚስተር ካርላይል ?
« ኧረ አለ ሚስተር ኬን ሊያስተካክለው ይችላል » ነገ ልላከው ? »
« የማያስቸግርህ ከሆነ በጣም ደስ ይለኛል " ዕቃው እንኳ ስለ አረጀ ለጊዜው እንጂ ቅኝቱ እምብዛም አይረዳውም " ኢስት ሊን ውስጥ ብዙ የምንሰነብት ከሆነ በአዲስ እንዲተካው አባባን እጠይቀዋለሁ»
ምስኪኗ ሳቤላ ' ፒያኖው የሚስተር ካርላይል እንጂ የሷ አለመሆኑን አላወቀችም » ኧርሎ እንደ መሳል አለና ከሚስተር ካርላይል ጋር በፊት ፈገግታና በዐይን ጥቅሻ ተነጋገሩ ።
ሚስተር ኬን የቤተ ክርስቲያን ኦርጋኖን ተጫዋችና ተማሪ ነበር በበነጋው ወደ ኢስት ሊን ሲመጣ ሳቤላ እንዳጋጣሚ ፒያኖ ስትጫወት አገኛት " በትሕትና
በፈገግታ ተቀበለችው ለማንም ቢሆን ትሑትና ማራኪ ጠባይ ነበራት አታስፈራም " አትከብድም " ሙዚቀኛዋ በፈገግታዋ በመበራታት ድፍረት ተሰማውና
የራሱን የኑሮ ስንክሳር ይተርክላት ጀመር " ምንም ያልነበረው ድሃ መሆኑን ብዙ እየተጨነቀ ነገራት " ከችግሩ ጥናት የተነሣም ትንሽ ገንዘብ ቢያገኝ ብሎ በተከታይ ሳምንት አንድ የሙዚቃ ትርዒት ለማሳየት ተዘጋጅቶ ነበር " ስለዚህ ሳቤላና አባቷ ቢገኙለት ' የነሱን አርዓያ በመከተል ብዙ ሕዝብ እንደሚገባለትና ደኅና ገንዘብም ማግኘት እንደሚችል ገልጾ ለመናት " የሙዚቃው ትርዒት የተሳካ እንደሆነ ኑሮውን በደኅና ለመቀጠል እንደሚችል ካልተሳካ ግን ካለበት ቤት እንኳን ከነቤተሰቡ እንደሚባረር የቤት ዕቃውም ለተቀመጠበት የሁለት ዓመት ውዝፍ ኪራይ በሐራጅ እንደሚሸጥ እያስተዛዘነ አወጋት ሚስተር ኬን የሰባት ልጆች አባት ነበር" ሳቤላ የሰውየውን ታሪክ ስትሰማና ሁኔታውን ስትረዳ አንጀቷ ተንሰፈሰፈና
አባቷን ለመነችው "
« አባባ . . . አንድ ትልቅ ነገር እንድታደርግልኝ ብለምንህ እሺ ትለኛለህ ? »
« ምናለ ልጄ ... ብዙ ጊዜ ጠይቀሽኝ አታውቂም ምንድነው እሱ ? »
« ዌስት ሊን ውስጥ በቅርቡ ከሚታይ አንድ የሙዚቃ ትርዒት እንድትወሰደኝ እፈልግ ነበር " »
ኧርሎ በመገረም ሳቤላን ዐይኑን አፍጥጦ ተመለከታት
«ዌስት ሊን ላይ የሚታይ የሙዚቃ ትርዒት? » አለና ሳቀ « ባላገር ጅማት ሲከረክር ለመስማት ? ላቤላ ልጄ ምን ነካሽ ? »
ሳቤላ የሰማችውን የዚያን ሰው ታሪክና የራሷንም እያከለች አብራርታ ተረከችለት "
« ሰባት ልጆች . . . አባባ ! የሙዚቃው ትርዒት ካልተዋጣለት ያለበትን ቤት ለቆ እነዚያን ልጆች ሁሉ እንደያዘ ከአውራ መንገድ መፍሰሱ ነው ለሱ የሞትና
የሕይወት ጉዳይ ነው #ምናምኒት የሌለው ድሃ ነው»
« እኔም ድሃ ነኝ » አላት አባቷ "
«ሲናገር ብትሰማው አባባ ... ፊቱ ዐሥር ጊዜ ሲለዋወጥ ፡ የችግሩን ጥናት ስለገለጸ ኃፍረት እያስጨነቅው ትንፋሹን ያዝ ለቀቅ ሲያዶርግ ንግግሩ ቁርጥ
ቁርጥ ሲል አንጀት ይበላል እርግጠኛ ነኝ ሰውየው ቀን የጣለው የሀብታም ወገን
ነው »
« አዬ ጉድ የመንዶር ሙዚቃ ! በይ ደግ ነው የአንድ ፓውንድ ቲኬቶች ገዝተሽ ለትልልቆቹ አሽከሮች መስጠት ትችያለሽ »
« እንደሱ አይዶለም እኮ አባባ ( አንተና እኔ እንደምንገኝለት ቃል ከገባንለት በዌስት ሊን አካባቢ ያሉ ታላላቅ ሰዎች ስለሚመጡ አዳራሹ ሊሞላ ይችላል " አሽከሮቻችንን ልከን እኛ እንደምንቀር ከሰሙ ግን ለመገኘት ያሰቡት ሁሉ ይቀራሉ ።እስኪ አንተም አስበው . . . አባባ " አሁን ይኸን ቤትህን ከነዕቃው እንዳለ ቢወስዱብህ ምን ይሰማሃል ? ሰው አዳራሹ እስኪሞላ ከገባለት ግን ከዚህ ጉድ ሊድን ይችላል " አባባ ...እንደ ምንም ብለህ ለአንድ ሰዓት ቢሆንም ተገኝለት እኔ የታምቡር ጓጓታና የክራር ክርከራ ብቻ ቢሆንም ያስደስተኛል
« መንቻካ ለማኝ ነሽ ! በይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ተገኝተን እናይለታለን ንገሪው»
ወደ ሚስተር ኬን እየሮጠች ሔደችና« ሚስተር ኬን... አባቴ ጥያቄህን ተቀብሎታል እሱ አራት ቲኬቶች ይገዛል " አባባና እኔ እንገኛለን » አለችው።
የሚስተር ኬን ዐይኖች የደስታ እንባ አቀረሩ ። ሳቤላም የሰውየውን ደስታ ስታይ የእሷም ዐይኖች እንባ ማቅረር አማራቸው።
« ብዙ ሰው እንዲባልህ የሚረዳህ ከሆነ ለምታገኘው ሁሉ ንገር « እኔም ለሰው ሁሉ እንደምንግባ እየነገርኩ እነሱም እንዲገኙ እጠይቅልሀለው አለችው።
ማታ ሚስተር ካርላይል ሎርድ ዊልያም ቬንን ለመጠየቅ መጣ ኧርሎ ለጊዜው ከክፍሉ አልነበረም ሳቤላ ስለ ሚስተር ኬን ትርዒት አነሣችለት "
« ሚስተር ኬን ከባድ ድፍረት ነው ያደረገው» አለ ሚስተር ካርላይል"
« ይልቅ የበለጠ ገንዘብ እንዳያወጣና በችግሩ ላይ ችግር እንዳይጨምር እፈራለታለሁ
« ለምንድነው ይኸ ሥጋት የተሰማህ ? »
« እሱ ዌስት ሊን ውስጥ ሙዚቃ ለማሳየት ቢሞክር ሰው አያደንቅለትም ሕዝቡ የሱን ችግር ደጋግሞ የሰማውና የሚያውቀው ስለሆነ አንድም ሰው ዞሮ አያየውም አንድ ያልታወቀ እንግዳ ተጫዋች ከውጭ ቢመጣ ግን የዌስት ሊን ሕዝብ ይጐርፍለት ነበር»
«ግን ድህነቱ እሱ እንደሚናገረው እውነት ነው ? » አለችው ሳቤላ "
«በጣም በርግጥ እንጀራ ሊኖረው ይችላል ግን የተሟላ ምግብ አያገኝም በኦርጋኖ ተጨዋችነቱ ባመት ሠላላ ፖውንድ ያገኛል ! ዐልፎ ዐልፎ በማስተማር
ይደጎማል ሚስቱና ልጆቹ የሚኖሩት በዚህ ገቢ ነው " ቤተሰቡ ሥጋ የሚባል ነገር ቀምሰው የሚያውቁ አይመስለኝም»
« ሰውዬውን ሳየው ሚስተር ካርላይል የትልቅ ሰው ልጅ ይመስላል»
« እውነትሽን ነው " የትልቅ ሰው ልጅ ነበር " አባቱ ካህን ነበሩ " እሱ ሙዚቃ በመውደዱ ነው ኑሮው የተበላሸው ደኅና ክፍያ ከሚገኝበት ሥፍራ እንዳይረጋ
አደረገው " ሌላው የውድቀቱ ምክንያት ደግሞ ገና በልጅነቱ በማግባቱ ነው . .

👍13❤2
« አይ አልችልም ። በኔ ሐሳብ ምን ጊዜም ቢሆን ምስኪኑ ዲክ የራሱ እንጂ የማንም ጠላት አይደለም ። ጭላንጭል ስለምትለኝ ነገር ግን አልችልም " በዲክ ላይ ለመመስከር ወደ መርማሪዎችም መጠራት አልነበረብኝም ሎክስሌይ ከዚያ ቦታ መኖሬን ባለመናገሩ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር ። ኋላ ነገሩ እንዴት እንደወጣ አላውቅም ። ቢሆን ምስክርነቴ ለፍርድ ስለአልረዳ ምንም አይደለም ግን ካርላይል . .
ሪቻርድ አነጋግሮኝ እንደነበር እንዴት ዐወቅህ ? እኔ እንደሆንኩ ስለዚህ ጉዳይ ለአንድም ሰው ቃል አልተነፈስኩም »
« እንዴት እንዶ ሰማሁት መናገሩ አይጠቅምም ዐውቃለሁ ።ማወቁ ብቻ ይበቃል " እኔ ግን ይህ ቶርን የሚባለውን ሰው ከጀሊሆን ቤት ሲወጣ አይተኸዋል የሚል እምነት ነበረኝ»
ኦትዌይ ቤተል ራሱን ነቀነቀና «እኔ አንተን ብሆን ካርላይል በውነቱ
የፈለገው ቶርን ከዚህ አካባቢ ነበር ለሚለው ወሬ ከፍተኛ ግምት አልሰጠውም ያንለት ማታ ዲክ ሔር ከመደንገጡ የተነሣ እንደ ዕብደት አድርጐት ስለ ነበር ነፍሱን አያውቅም " ስለዚህ ብዙ በእውነት ያልነበሩ ቅርጾችና ምስሎች ታይተውት ይሆናል»...

👍8❤2
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አራት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
“እንደምን አረፈድሽ የኔ እህት?” አለችኝ አንዲት ደርባባ ሴት፣ እንጀ አጋጣሚ በመንገዱ እያለፈች ሳለ እንደ ዋዛ መለስ ብላ እጅ ነስታኝ።
“እግ..እግዚአብሔር ይመስገ” አልሁኝ፣ እንደ መደናገር ብዬ፡ መልኳ እንግዳ አልሆነብኝም:
“ምነዉ በደህናሽ ነዉ፤ ልጅ ይዘሽ በመንገድ ዳር?”
“ደህና ነኝ” አለሁኝ፣ የሴትዮዋን መልክ አስታዋሽ ልቤ ላይ ብቅ ብሎ
ጥልቅ እያለብኝ፡፡ የት እንደማዉቃት ልጠይቅ አልጠይቅ ብዬ ከራሴ ጋር
ትንሽ ተከራከርሁ፡
“ቱናትስ እንዴት ናት?”
ይኸዋ! እሷ ጭራሽ ከእኔም አልፋ ከማንም ሸሽጌ የማኖራትን ገዳሜን
ሳይቀር ታዉቃለች፡ ኧረ ይቺ ሰዉ ማናት?
“አጠፋሽኝ መሰል”
“አይ ማጥፋት ሳይሆ” አልሁ፣ እሷ በዚህ መጠን አዉቃኝ እኔ አላወቅሁሽም ማለቱ ቢያሳፍረኝ፡
“ምነዉ እንኳን” አለችኝ፣ ጭንቀቴ ገብቷት ልትገላግለኝ፡ “ምነዉ
እንኳን ዘዉዲቱ ሆስፒታል ተዋዉቀን ?”
"አዎ!” አልሁ፣ ነፍሴን እያሳረፍኋት። “እዚያ ነዉ አይደል
የምንተዋወቀዉ ?»
መጣችልኝ፡ የቱናትን ሕክምና ለመጀመር ወደ ዘዉዲቱ ሆስፒታል የገባን ዕለት ማታዉን የተዋወቅናት ሴት ናት ከዳር ሀገር መጥታ፣ እዚያ ዘግናኝ ወለል ላይ ወረፋ ጥበቃ ወር ሙሉ ሕመምተኛ ልጇን ይዛ
መቀመጧን ነግራን እንደ ነበር ሁሉ አስታወስሁ፡ አስታወስኋት
የቀድሞዉ ባሌ መተት አስመትቶብኝ፣ ልጄ እንዲህ ሆኖብኝ ቀረ› ብላ ለእመዋ የነገረቻት ሴትዮ ናት።
እዴት ሆነልዎ ... ማነዉ ... እንዴት ሆነለሽ ልጅሽ?” አልኋት አንቱ
ማለት እና አንቺ በማለት መካከል እየዋለልሁ: አሁን አሁን
ምቸገርባቸዉ ነገሮች አንደኛዉ ይኼ ነዉ፡ በምለማመደዉ የምንኩስና ሕይወት ማንኛዉንም ሰዉ አንቱ ብዬ ማክበር እፈልጋለሁ ግን ደግሞ ቀደም ብዬ አንተ ወይ አንቺ እያልሁ የማዉቃቸዉ ሰዎች ግራ
እንዳይጋቡብኝም እሰጋለሁ።
“መቼም ወረፋዉ ደርሶሽ ይሆናል። ዳነልሽ፤ እንዴት ሆነ ልጅሽ?”
“ወረፋዉስ ደርሶኝ ነበር” አለች፣ በቅጽበት አንገቷን እየሰበረች ክፉ ነገር እንዳትነግረኝ እግዚአብሔርን በልቤ ለመንሁት፡ ልጇ እንደዳነላት ብቻ ነዉ መስማት የምፈልገዉ፡
“አልሆነም” አለችኝ፡፡
“እ?”
“አልዳነልኝም ወረፋዉ ደርሶት እንደ ነገ ተቀጥሮልኝ፣ እንደ ዛሬ
ማታዉን እቅፌ ላይ አረፈብኝ” አለችኝ፣ እንባዋን በሺህ መንታ
እያወረደች፡ የእኔም እንባ መቆሚያ አጣ፡ የልጁ ሁኔታ አሁንም ዓይኔ ላይ አለ፡ ምንም እንኳን ልጇን ገጥሞት የነበረዉ ከቱናት ቀለል ባለ ሁኔታ፣ ያልተመጣጠነ የጭንቅላት የዉሃ መጠን (hydrocephalus) ብቻ
ቢሆንም፣ ሁኔታዉ ግን አንጀት ይበላ ነበር፡፡ እሷም ይድንልኛል ብላ ያን ሁሉ መከራ አይታ በመቀርቷ አንጀቴን በላችዉ፡
“አልቅሼ ያልሞትሁትም አንዲት
ማጽናናት የሚያዉቁበት እናት
አባብለዉኝ ነዉ። አሁን እኮ እንዲያዉም እሳቸዉ ጸበል ጸዲቅ
ካልቀመስሽ ብለዉኝ ነዉ የልጄን ሬሳ ይዤ የወጣሁበትን ከተማ
ከመንፈቅ በኋላ ዳግመኛ የተመለስሁበት ያ ጊዜ እሳቸዉ ባይራዱኝ ኖሮ እኮ የልጄን ሬሳ እንኳን ጭኜ ወደ ሀገሬ መዉሰድ ባልቻልሁ ነበር።ዉለታቸዉ አለብኝ። በምን እከፍላቸዉ ይሆን ብለሽ?”
“እግዚአብሔር ዉለታ አዋቂ ነዉ። ግድየለም፣ እሱ በነፍስ ይክስልሻል”አልኋት፣ የተባሉት ሴትዮ ደግነት እያስቀናኝ፡
“ልመልስስ ብል በምን አቅሜ እቴ! እንዲያዉ የማትቸኩይ ከሆነ
እንዲያዉ ባስቸግርሽ፤ አብረን ሄደን ብናመሰግናቸዉ”
“አይ” አልሁ፣ እሺም እምቢ ማለትም እየከበደኝ፡
“እዚያች ዘንድ፣ ያዉና እኮ ቤታቸዉ: ያ በሰፊ ቆርቆሮ የታጠረዉው ግቢ ነዉ ቤታቸዉ መሆኑን ሰዎች የጠቆሙኝ። ነይ እንሂድ እስኪ እባክሽ”።
የእኔ አስፈላጊነት ባይገባኝም፣ እምቢ ማለት ግን አልቻልሁም፡ እሺ ብዬ ባለ ተሽከርካሪዉን የቱናትን አልጋ እያሽከረከርሁ ተከተልኋት። እሷም ጮራዋ የቱናት ዓይኖች ላይ መፈንጠቋን አይታ አላስቻላትም የራሷን ነጠላ ቀልጠፍ ብላ አውልቃ፣ ራስጌዋ ላይ አጠላችላት።
በነበርንበት የመንገዱ ጠርዝ ትንሽ ተራምደን መንገዱን አቋረጥነዉ።
ከዚያ በማቋረጫዉ ፊት ለፊት ባለዉ ቅያስ ትንሽ እንደ ሄድን በቆርቆሮዉ አጥር የታጠረዉን ግቢ በር አገኘነዉ: ቅድም ቆመንበት ከነበረዉ መንገድ
ዳር ሆኖ የታየዉ አጥር እዚህ ድረስ መስፋቱን አይቼ፣ ‹ምን ዓይነት ሴትዮ ቢሆኑ ነዉ? መቼም ሀብታም መሆን አለባቸዉ ልላት ወደ እሷ ስዞር ፊቷን በሳቅ ሞልታ ጠበቀችኝ፡
“ዝግጁ?” አለችኝ፣ በደስታ እየተፍለቀለቀች
“እኮ ሴትዮዋን ለማመስገን?” አልኋት፣ ድንገት ስለ ተሞላችዉ
የደስታዋ ምንጭ ምክንያት እየፈለግሁለት።
“እ" እንደዚያ ነዉ አዎ ግን ምንም ቢገጥምሽ እንዳትደነግጪ። ዝግጁ ነሽ አይደል ለዚያ?”
“ይቅርታ…”
“ይቅርታ አድርጊልኝ ዉብርስት: ትንሽ ዋሽቼሻለሁ: ዉለታ የዋሉልኝ
ሴትዮ የአንቺ እናት፣ እመዋ ናቸዉ። ይኼ በር ሲከፈትም የምናገኘዉ እመዋን እና የእሳቸዉ ዓይነት ዉለታ ዋዮችን ነዉ በእርግጥ ሌላ ያልጠበቅሽዉ ሰዉም ልታይ ትችያለሽ። ምንም ቢሆን ግን እንዳትደነግጪ” አለችኝ፣ እንደ ማቀፍ ጭምር እያደረገችኝ።
ተለዋዋጭ ሁኔታዋን ሳይ ትክክል አልመሰለችኝም፡ እንደዚያም ሆኖ ግን የሚጎዳ ነገር ዉስጥ እንደማትከተኝ በነፍሴ አምኛታለሁ ለምን እንደሆነ እንጃ ከቅድሙ ሹፌር ይልቅ እሷን በሙሉ ልቤ ነበረ ያመንኋት የልጄን ተሽከርካሪ አልጋ የሚገፉ እጆቼን ጠበቅ አድርጌ ይዤ፣ የሚሆነዉን ሁሉ
ለማየት ዓይኔን በሩ ላይ ተከልሁ። እኔን ያቀፈችበትም ሆነ በሩን
ለመክፈት የሚገፋዉ እጇ ይንቀጠቀጣል፡ ቀስ አድርጋ ከርፈድ አደረገችልኝ፡ አንድ የጠመጠሙ ቄስ ቀድመዉ ዓይኔ ዉስጥ ገቡ።
አሁንም ቀስ አድርጋ መግፋቷን ጨመር ስታደርግልኝ፣ ወዲያ ወዲህ የሚሉ የሰንበት ተማሪዎችን መለዮ የለበሱ ወጣቶች አየሁ ክፍተቱን
ሰፋ ባደረገችዉ ቁጥር፣ ዓይኔ ዉስጥ የሚገባዉም ሰዉ እየጨመረ እየጨመረ መጥቶ ጨርሳ ሙሉ በሙሉ ወለል አድርጋ ስትከፍተዉ፤አንድ ትልቅ ጉባዔ የሚሞላ ብዙ ሰዉ በግቢዉ ተጥለቅልቋል፡ በተለይም በአንደኛዉ ማዕዘን በኩል በድንኳን ዉስጥ ሰብሰብ ብሎ ወደ እኛ የሚመለከተዉን ሕዝብ ተመለከትሁት ነገሩ፣ ትክክለኛ ጉባዔ ነዉ።
“እንዴት እንዴት ነዉ ነገሩ?” አልኋት ወደ ሰዎቹ እንድንሄድ
የመጎተት ያህል ስትመራኝ። “ጭራሽ እመዋም አለችበት? ባልቻም፣ እሸቴም? ኧረ ምንድነዉ ጉዱ?” አልሁኝ፣ በቀረብን ቁጥር እንደ አዲስ እያላበኝ፡ ዓይኔን ከጫፍ እስከ ጫፍ አንከራተትሁት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ጨምሮ፣ ሦስት ጳጳሳት ከጉባያተኛዉ የፊተኛዉ ረድፍ ላይ
ይታዩኛል፡ የጤና ሚኒስትሯን ጨምሮ አንዳንድ የማዉቃቸዉ
የመንግሥት ባለስልጣናትም መኖራቸዉን አስተዋልሁ: በርከት ያሉ ካህናት፣ የማኅበራችን ዋና ሊቀመንበር፣ ባልቻ፣ እሽቴ፣ እመዋ
ሌሎች የማኅበራችንም ሆነ የሲራክ ፯ አባላት ሁሉ አሉበት።
“እንኳን በደህና መጣችሁ” ሲሉ ተቀበሉን፣ ሁሉም: ያልቆመ
የማያጨበጭብ አለ ይሆን?
“ክቡራንና ክቡራት እንግዶቻችን፣ የጉባዔያችን መነሻ ምክንያቶቻችንም ተሟልተዉ ተገኝተዉልናል እንደ ቆማችሁ ማርያም ትቁምላችሁ እባካችሁ በየመቀመጫችሁ አረፍ አረፍ በሉልን” አለ የመርሐ ግብር

👍46❤3
መሪዉ፣ በጥሩ ሥነ ትሕትና፡ እሱንም አዉቀዋለሁ፣ የማኅበራችንን አንደኛዉ አስተናባሪ፣ ወደ እኛ መጥቶ ቱናትን ከነአልጋዋ አቀፈልኝ እና
እንድንከተለዉ ከፊታችን ቀደመ: መደዳዉን ወደ ተቀመጡት ሦስቱ
ጳጳሳት ወሰደኝ እና መስቀል እንድሳለም ምልክት ሰጠኝ ተሳልሜ ሳበቃ በርከክ እያልሁ የሦስቱንም ጫማ ስሜ አስተናባሪዉ ባሳየኝ ቦታ
ተቀመጥሁ። ትንፋሽ ወስጄ ሳበቃ፣ በማን መካከል እንደ ተቀመጥሁ ለማወቅ ተዟዙሬ ስመለከት ያኔ ዘዉዲቱ ሆስፒታል ሳለሁ ልጆቻቸዉን ለማሳከም እምሽክ ገልታ ሲሉ ያየኋቸዉን እናቶች ከአጠገቤ አገኘሁ::
የአንገት ሰላምታ ካቀረብሁላቸዉ በኋላ ወደ መድረኩ መለስ ስል የማኅበሩ ሊቀ መንበር ለመክፈቻ ንግግር ተጋብዘዉ ወጥተዉ ኖሮ፣ ጉሮሯቸዉን ሲጠራርጉ ደረስሁባቸዉ፡
“ከመንግሥትም ከቤተ ክህነትም ጥሪያችን አክብራችሁ የተገኛችሁል እንግዶቻችን፣ እንኳን ወደዚህ መልካም ሥፍራ በደህና መጣችሁልን። እንግዲህ እንደሚታወቀዉ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናች፣ ከጥንት ጀምሮ
ሰዎች ለማያልፈዉ የእግዚአብሔር መንግሥት ከማብቃት ጎን ለጎ ማኅበራዊ ጉዳቶችን ለማቅለል ከመራዳት ቦዝና አታዉቅም: በጤናዉ፣
በትምህርቱ፣ በወጉ፣ በልማዱ
ሁሉ ቢባል ቤተ ክርስቲያናችን
የማትመሰገንበት በጎ ተግባር የለም። ማኅበራችም የእናት ቤት
ክርስቲያኑን ጥሪ በመከተል በበጎ ሥራዎች ሁሉ ሲሳተፍ ኖሯል።
በመሆኑም፣ መጥሪያችንም ላይ እንደ ገለጽነዉ፣ ዛሬ እናንተን ወደዚህ ሥፍራ የጠራናችሁ ለሌላ በጎ የምሥራች ነዉ። ምንድነዉ ያላችሁኝም እንደሆነ፤ አሁን መጨረሻ ላይ የገባችዋ የልጅ እናት፣ ዶክተር ዉብርስት
ትባላለች: ማኅበርተኛች ናት።
ዉብርስት የመጀመሪያ ልጇን
በምትወልድበት ጊዜ፣ ተደራራቢ የጤና ጉዳተኛ ሆነችባት: በመሆኑም፤የዛሬ ዘጠኝ ወር ገደማ የውብርስት እናት ወደ ማኅበራችን ተመላልሰዉ
የልጄን ልጅ አሳክሙልኝ ብለዉ ደጅ ጠንተዉን ነበር። ዉብርስት
ማኅበርተኛች ስለሆነች ብቻ ሳይሆን፣ የልጇ የቱናት ጉዳት አሳሳቢ ስለነበር፣ በጊዜዉ መጠነኛ ድጋፍ አድር ገንላታል። እንግዲህ በዚህ መነሻነት፣ ኋላ ኋላ የጉዳቱን መጠን ማኅበራችን በቅጡ ሲያስጠናዉ፣ በሀገራችን እጅግ በስፋት ያለ፣ ነገር ግን በሕክምና እና በመረጃ እጥረት
የተነሳ ብዙ ሰዉ ልጁን በሞት እያጣ ሐዘንተኛ ሆኖ መቅረቱን አወቅን ከሞት የተረፉትም ቢሆኑ ለተደራራቢ የአካል ጉዳቶች ተጋልጠዉ በሰቆቃና በፈተና ይኖራሉ።
ስለሆነም ክቡራንና ክቡራት፣ ዛሬ የተገናኘነዉ ከንድፏ እስከ ግጓባታዉ ሙሉ ወጪው በማኅበራችን የሚሸፈነዉን እና በአሕጉራችን ትልቅ የሚሆነዉን የሕጻናት ሆስፒታል ግዓባታ መሠረት ለመጣል ነዉ: ይኼ
ትኩረቱን ሀይድሮሴፋለስ እና ስፓይናቢፊዳ ላይ ስለሚያደርግ ከእኛ አልፎ ለጎረቤት ሀገራትም ይተርፋል ብለን እናስባለን።
ቢያንስ ቢያስ ግን የዉብርስትን እና አጠገቧ የተቀመጡትን ዓይነት ጨምሮ ብዙ ሺ ጉዳተኞች እንባ ያብሳል: ይኼ ሆስፒታል፣ ለሀገራ ችን ትልቅ ሀብት፣ ለቤተ ክርስቲያናች ተጨማሪ መመስገኛ፣ ለማኅበራችንም በጎ ስም መሆኑን እናምናለን: እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን!”
ከጎኔ የተቀመጡት የእኔ ብጤዎች፣ “እልልልልል!” ብለዉ አቀለጡት ሊቀ መንበሩ ንግግራቸዉን ጨርሰዉ ሲወርዱ፣ ጭብጨባ እና እልልታዉ
ዳግመኛ እንደ ጉድ ቀለጠ፡ ምሥጋና በላይ በላይ ተዥጎደጎደላቸዉ “እልልልል!… እግዚሀር ይስጥልን ... እግዚአብሔር ማኅበሩን ያስፋልን!”
“አሜን!” አልሁኝ፣ ጮህ ብዬ: አሜን! ምንም እንኳን ድንጋጤ እና
ደስታ ሲፈራረቁብኝ ብኖርም፤ እንደ ዛሬም መደንገጤንና መደሰቴን ግን እንጃልኝ፡፡ ከደስታዬ ብዛት የተነሳ ወደ ሊቀ መንበሩ ሂጂ ሂጂ የሚል መንፈስ አቁነጥንጦኝ ነበር፡ የማንን ጉልበት ልሳም?
በጣም ደስ አለኝ በጣም!
ከሊቀ መንበሩ በኋላ፣ የጤና ሚኒስትሯም ወጥተዉ ደስታቸዉን ገለጹ በእርግጥ ምን እንደ ተናገሩ ከልቤ አልሰማኋቸዉም:: በደስታ እየዋኘሁ ስለነበር የመርሐ ግብር መሪዉ እሳቸዉን ሸኝቶ ስሜን ደጋግሞ እየጠራ እንደ ነበር እንኳን አልሰማሁትም: አጠገቤ ያሉት ሰዎች ናቸዉ ጎሻሽመዉ ያባነኑኝ፡
“ዶክተር ዉብርስት?” አለኝ እንደገና፣ በድምፅ ማጉያዉ፡
“አቤት”
“እስኪ እባክሽን ወደ መድረኩ ብቅ በይና በልጅሽ እንደሆነዉ ዓይነት የሆነባቸዉንም በመወከል የተሰማሽ ስሜት ግለጪልን” አለኝ፣ እየተቅለሰለሰ::
እንዴ? እኔ ማነኝና ማንን እወክላለሁ? ጸጥ ብዬ ቆየሁበት፡ ነገር ግን እሱም ሐሳቡን፣ ከጎኔ ያሉትም ዉትዉታቸዉን ሊተዉልኝ አልቻሉም በደመ ነፍስ እሺ ብዬ ስቆም ጳጳሳቱ ታዩኝ፡፡ በእነሱ ፊት ምን ልናገር እንደምችል ሳስብ የባሰ ብርክ ያዘኝ፡ ፈራሁ ቢሆንም ግን አንድ ጊዜ ተነስቻለሁና እንዲሁ እየተወለካከፍሁ ወደ
የጉባያተኛዉ ዓይን ሁሉ ሰፍሮብኛል፡ እንዲሁ ዝም ብዬ ጉሮሮዬን ጠረግሁት፡ ምን ልል ነዉ ግን?
“ህህ” ብዬ ደገምሁበት፣ ይኼን መከረኛ ጉሮሮ
“ ግዚአብሔርይመስገ” ብሎ ጀመረልኝ፣ እንዳልተረጋጋሁ የተረዳኝ የመርሐ ግብሩ መሪ በዜማ፡ ዜማዉን ተቀበልሁትና መዝሙሩን አብረን ወጣነዉ፡ ከምኔዉ እንደ ቀለለኝ! ደህና እየዘመርሁ ሳለ ከየት እንዳመጣዉ ሳላየዉ፣ ከቤት ጥየዉ የመጣሁትን ክራሬን በግራ እጄ አስጨበጠኝ፡፡ ምን እንዳደርግበት እንደ
ተፈለገ ግን ምኑንም አላወቅሁም ምን ይፈለግብኝ ምን በቅጡ
ሳላዉቀዉ፣ ክራሬን በሰላምታ ቅኝት ቃኘሁት። በቅኝቴ መሀል በቅዳሴ ትናቴዎስ ላይ ደጋግሜ ሰምቻቸዉ ልቤ ላይ ከቀሩት መካከል ከአባቱ ወገብ ታወጣዉና በእናቱ ማሕጸን የምትልከዉ፣ በረቂቅ ሰፋድል የምትጠቀልለዉ በአርባ ቀኑ ለሀብትም ሆነ ለድህነት፣ ለጽድቅም ሆነ
ለኩነኔ ትሾመዋለህ የሚሉት ቃላት በሐሳቤ ተመላለሱብኝ እና፣
የእግዚአብሔርን ረቺነት በልቤ እያሰብሁ፣ እንዲህ ብዬ አንጎራጎርሁ።
ነሳኸን እያልን አማንህ ጌታ ሆይ
ብታፈርስ ብትሠራ ትሳሳታለህ ወይ?
ለዚች ለአንድ ልጄ
ለትንፋሿም እንኳ የከፈልሁህ ሳይኖር
እንኳን ያልሰጠኸኝ ያለኝም የኔ አይደል።
ኧረ ጌታዬ አላማህም
አንተስ ለኔ አትሳሳትም።
ሁለመናዉ እዚሁ ላይ ክራሬን ከጨበጥሁት በኋላ የመጣልኝን ይኼንን መዝሙር በደስታ ስሜት አንጎራጉሬ ሳበቃ፣ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ወደ አእምሮዬ መጣችልኝ፡ ሁልጊዜም በጎ ነገርን ብቻ የምታደርገዋን እሷን ላወድሳት በዚያዉ በሰላምታ ቅኝት ክራሬን እየገረፍሁ ሳለ፣ ከፊት ለፊቴ
ካለዉ ታዳሚ መካከል ጃሪም ብድግ ሲል አየሁት በስጨት ብሎ እመር አለና ጉባያተኛዉን ረግጦ ሲወጣ ሳየዉ፣ ልቤ ፍስስ አለችብኝ፡፡ እሱ እዚህ ይኖራል ብዬ በጭራሽ ስላልጠበቅሁ ይሁን፣ አወጣጡ ደስ ስለማይል፣ ብቻ በጣም ተረበሽሁ፡ በዚህ የተነሳ፣ እንቅፋት እንደ መታዉ
ሰዉ ስወለካከፍ በዚያ ሁሉ ሰዉ ፊት እንዴት እንዴት እንደሆንሁ እንኳን አልታወቀኝም።....

👍48❤8🔥1
#ሰው_ሁን_በይኝ
በቀደም ለት ጉንጬ መሐል
በከንፈሯ ብትዳብሰኝ፣
ሙት አካሌ ፊት እንዳለኝ አስታወሰኝ፣
ደሞ ድንገት ቀልድ ነግራኝ
ስቄ ስቄ እንዳባራሁ ፤
"ጥርስህ ሲያምር" ስላለችኝ
ዘላለሜን ማልቀስ ፈራሁ ፤
ተካተትኩኝ ከተፈጥሮ
እፍ ...አልሸብኝ ድብቅ ውበት፤
እስቲ ባክሽ አሁን ደሞ
'ሰው ሁን ብለሽ ሹሚኝና
ሰው መሆኔን ልመንበት ፤
ሰው ተብዬ ልጠራበት።
🔘አስታወሰኝ ረጋሳ🔘
በቀደም ለት ጉንጬ መሐል
በከንፈሯ ብትዳብሰኝ፣
ሙት አካሌ ፊት እንዳለኝ አስታወሰኝ፣
ደሞ ድንገት ቀልድ ነግራኝ
ስቄ ስቄ እንዳባራሁ ፤
"ጥርስህ ሲያምር" ስላለችኝ
ዘላለሜን ማልቀስ ፈራሁ ፤
ተካተትኩኝ ከተፈጥሮ
እፍ ...አልሸብኝ ድብቅ ውበት፤
እስቲ ባክሽ አሁን ደሞ
'ሰው ሁን ብለሽ ሹሚኝና
ሰው መሆኔን ልመንበት ፤
ሰው ተብዬ ልጠራበት።
🔘አስታወሰኝ ረጋሳ🔘
👍44🥰5🔥4❤3👏1
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...የጃሪም አወጣጥ በኃይል እየቆረቆረኝ ቢሆንም፣ ደስታዬ ግን ጢም እንዳለ ነዉ።
የመሠረት ድንጋዩ በጳጳሳቱ እና ሌሎች ታላላቅ ስዎች ተቀምጦ ከአበቃና የጉባዔዉ አጋፋሪ ‹ሂዱ በሰላም› ካለን ከብዙ ደቂቃዎች በኋላም ቢሆን፣ ችዬ መነሳት አልቻልሁም ነበር፡ ልጄ ቱናት የተኛችበትን አልጋ ወደ
ተቀመጠዉ የመሠረት ድንጋይ አስጠግቼ፣ በደስታ እንባዬን ሳወርድ ብዙ ቆየሁ፡ ሁኔታዬን ሁሉ እመዋ በሩቁ ስትመለከት ኖሯል መሰለኝ፣ ከእንግዳዉ ጋር መዉጣቷን ትታ ወደ'ኔ መጣች፡
“ደስ እለሽ ዉብዬዋ?” አለችኝ፣ ወደ እቅፏ እየሳበችኝ፡፡
“በጣም!” አልኋት፣ እንባዬን በቀሚሷ እያበስሁ
“እሰይ! እንኳ ንም ደስ አለሽ ልጄ”
“እንደ ዛሬዉም ደስ ብሎኝ አያዉቅ”
“እኔም” አለችኝ፣ ወደ አንገቷ ሥር ጠበቅ አድርጋ እየሳበችኝ ቀና ብዬ
ሳያት፣ እዉነትም ተጫጭኗት የነበረዉን እርጅና ሳይቀር ድል ነስታዉ ታየችኝ: ግንባሯ ላይ በተደረደሩ መስመሮች ሁሉ ደስታ ሲፈስ አየሁ በጣም ደስ ብሏታል። ይኼ ደስታዋ የኔንም ደስታ የትና የት አደረሰዉ።
“የቱናት እናት” አለ ባልቻ፣ እንግዳዉ ቀለል እስከሚልለት ድረስ ሲሸኝ ቆይቶ ወደ እኛ እየመጣ፡ የእሱም ፊት ከእኛ በሚስተካከል ደስታ ተጥለቅልቋል ቱናትን ከነአልጋዋ አቅፎ አነሳትና የመሠረት ድንጋዩ አናት ላይ ጉብ አደረጋት: “ይኼን ወደ መሰለ ሥፍራ ስጠራት እንዲያ
እንዳልተግደረደረች፣ ደስታ እንዴት እንደሚያደርጋት አየሽልኝ አይደል
ይቺን እናትሽ?” አላት፣ ቱናትን በስስት እየተመለከታት
የመሠረት ድንጋዩ ላይ ከነአልጋዋ ያደረግናትን ቱናትን ለረዥም ጊዜ
ከብበን ከቆየንና፣ ለዚሁ ደስታችንም ወሰን ልናበጅለት ከሞከርን በኋላ እኔና ባልቻ ቱናት የተኛችበትን አልጋ ከግራ እና ከቀኝ ይዘን ወደ ባልቻ
መኪና ተሳፈርን
“በሉ እንግዲህ” አለችን እመዋ፣ ከሀገር ርቀን የምንጓዝ ይመስል አቅፋ እየተሰናበተችን፡
“አብረሽን አትሄጅም ወይ እመዋ? ዉቤ እኮ ወደ ሲራክ እየተመለሰች
ያለችዉ ከዓመት በኋላ ነዉ። መቼም በዚህ አንድ ዓመት ዉስጥ
በማዕከላችን የተለዋወጠዉ ነገር ሁሉ እያየች እንደ ጀማሪ ጎብኚ
ይኼ ደግሞ ምንድነዉ እያለች በጥያቄ ማስቸገሯ አይቀርም: ብቻዬን እችላታለሁ ብለሽ ነዉ?” አለ ዓይኖቹን በእኔ፣ በእመዋ እና በቱናት ላይ እያንከባለለ፡፡
“ወደ ሲራክ ነዉ እንዴ የምንሄደዉ?”
“አዎ ምነዉ?” አሉኝ እኩል፣ ድንግጥ ብለዉ፡ ደግሞ ልትለመንብን ነዉ› ብለዉ ነዉ መሰለኝ፣ በቅጽበት አመዳቸዉ ቡንን አለ
“እሺ”
“እኮ! እንዳንቺም በሕጋችን የቀለደበት ሰዉ የለም: እንዲያዉ የቱናት እናት መሆንሽ አተረፈሽ እጂ፣ አንቺስ ደህና አድር ገዉ ቢቀጡሽ ሁሉ የምታጸድቂ ወንጀለኛ ነሽ” አለኝ፣ እንደ መሳቅም በእፎይታ እንደ
መተንፈስም ብሎ፡
“ታዲያ እኔ እምቢ ብዬ ነወይ? ልብ ካላችሁ መቅጣት ነበራ” አልሁት፣ የቱናትን ልብስ እያስተካከልሁ
“ይቀርልሽ መስሎሻል!”
“ቆይ ምን አጥፍቼ ነዉ ግን?”
ያልሰማኝ መስሎ ፊቱን አዞረብኝና፣ እመዋን እንደገና ተሰናበታት፡ እኔም እንደ'ሱ የመኪናዉን መስታዎት ዝቅ አድርጌ ልሰናበታት ስል፣ ሆነ ብሎ
መኪናዉን አንቀሳቀሰብኝ፡፡
“ አየሽልኝ አይደል ምቀኝነቱን እመዋ?” አልኋት፣ ልክ እንደ በባቡር ተጓዥ እጄን እያዉለበለብሁላት፡
እሷን ተለይተን መንገድ ከጀመርን በኋላ፣ ቅድም ያልሰማ መስሎ
ያለፈብኝን ጥያቄዬን እንደገና አነሳሁበት
“እ፣ በል ገረኛ”
“ምኑን?”
“ብቀጣበት የምትጸድቁበትን ጥፋቴን ነዋ”
ፍርጥም ብሎ ጥርሶቹን ገለጠልኝ፡
“እዉነት ጥፋትሽ ጠፍቶሽ ነዉ አንቺ? ሌላዉ ቢቀር፣ አንዲት የሲራክ አባል ብትወልድም እንኳን ፈቃዷ ምን ያህል እንደሆነ አጥተሽዉ ነዉ?”
“ወይ ጉድ… እኔስ አሁንም ወደ ሲራክ እየሄድሁ መሆኑ ደንቆኛል”
ቱናትን ከወለድሁ፣ በተለይም ኋላ በሕክምናዎቿ ጊዜ ያለፈችበትን አበሳ ካየሁ በኋላ፣ ወደ ሲራክ ፯ እመለሳለሁ አላልሁም ነበር፡ እንኳንስ እስከዚህ ድረስ፣ ገዳሜን ከገደምሁበት የእመዋ ቤት አንድም ርምጃ ንቅንቅ የምል አይመስለኝም ነበር፡ ዛሬ ግን ባልቻ ገና ‹እንሂድ› ሲለኝ፣
‹እሺ› ብዬ ከመከተል በቀር ምንም ያሳሰብኝ ነገር የለም፡
በዚህ ሁኔታ ከዋናዉ የማኅበራችን ሕንጻ ደርሰን፣ ጥብቁን እና ረዥሙን የሲራክ ፯ መንገድም አልፈን ከመጨረሻዉ በራፍ አጠገብ ስንደርስ ድንገት ቆመ፡፡ ጭራሽ እንደ መቅለስለስ ብሎ አየኝ፡፡ ይኼ አስተያየቱ
ነበር ቀድሞዉንም እኔን እና እሱን በሌላ ያስጠረጥረን የነበረዉ፡፡ ግራ ገብቶኝ አየሁት፡ በሩ ደግሞ ሲጠም፣ እኛ መሆናችንን አዉቆ በራሱ ጊዜ እንደ ቀድሞዉ ይከፈትልናል ብዬ ብጠባበቀዉም፣ ክርችም እንዳለ ቀረ፡
ምነዉ” አልሁት፣ ዓይን ቢያበዛብኝ፡ “ኧረ አባትዮ፣ እንዴት እንዴት እየሆንህ እንደሆነ ታዉቆሃል ግ?”
“እንዴት እንዴት ሆንሁ?”
“ለራስህ አይታወቀህም?''
መቅለስለሱን ተከትሎ፣ በዚያዉ ሐሳብ ገባዉና፣ ቁዝም ብሎ ቆየብኝ፡
“ምንድነዉ ጉዱ፣ የማትነግረኝ?”
“እንዳትቆጪኝ ፈራሁ እንጂ”
“እንዳትቆጪኝ?”ፈራሁ
“ለእሷ የምትሆኚዉን ሳይ፣ ትንሽ ፈራሁ”
“ማናት ደሞ እሷ?”
ልጅሽ፣ ቱናት” አለኝ፣ የቱናትን አልጋ የያዘ እጄን እያስለቀቀብኝ፡ እሱዐበአንደኛዉ ጎን፣ እኔ ደግሞ በሌላኛዉ ጎን ሆነን ነበር በየእጃችን የያዝናት አሁን ግን የመፈልቀቅ ያህል እጄን አስለቅቆ ለብቻዉ ወደ እቅፉ ወሰዳት አድራጎቱ ሊገባኝ ባይችልም፣ ባልቻ ነዉና ሰዉየዉ ልጄን አትንካብኝ ብዬ ልከላከለዉ አልቻልሁም፡ ትንፋሼን ዉጬ
መጨረሻዉን ጠበቅሁት፡፡ በእርግጥ፣ ደግሞ ሌላ የምሥራች
የተዘጋጀልኝም መስሎኝ ራሴን ለደስታ እያመቻቸሁ ነበር የለመደች ጦጣ አሉ!
“በቃ ዉቤ፤ በቃ ቱናትን ወስጄብሻለሁ” አለ፣ ስለ ራሱ ንግግር ራሱ ሐፍረት እየተሰማዉ፡፡
"እ" አልሁት፣ በግንባሬ፡ ብቻ ያንን የመሰለ ደስታ እንዳይከስምብኝ፡
ዓይኔን በልጥጬ በግርታ አየሁት፡
“አዎ”
“ኧረ አባትዮዉ ተዉ አታስቀኝ” ብዬ፣ እንደ ምንም ጥርሴን ለመግለጥ ሞከርሁ: ሳቄን የሚጋራኝ መስሎኝ ሳቅ ብርቃቸዉ የሆኑት ጥርሶቹ እስኪገለጡ ብጠብቅም፣ እሱ ግን ክርችም እንዳለ ነዉ አሁንም:
“እየቀለድህብኝማ አይደለም: ነዉ እንዴ?”
“በፍጹም! ከእሽቴ ጋርም ተመካክረበታል: ለማኅበራች
ሊቀመንበርም አወያይቼዋለሁ:: ያዉ እመዋንም ቢሆን ጫፍ ጫፏ
አጫዉቻታለሁ: ሁላችንም ጋ ያለዉ ሐሳብ ተመሳሳይ ነዉ''
“ቆይ ቆይ”
“ተዪ ዉቤ: በቃሽ: እዲያዉም ግልጹን ንገረኝ ካልሽኝ፣ ቱናት በዚህ መልኩ የምትጠቅሚያት አይመስለኝም” አለ፣ ቆምጨጭ ብሎ፡ ጭጭ ብዬ ከማዳመጥ በቀር የምሆነዉን እንጃልኝ፡፡
“ስለዚህ ቱናት እየወሰድሁብሽ ነዉ። ከእንግዲህ ቱናትን ለብቻሽ ቤት ዘግተሽባት የብቻሽ ማድረግሽ ይቀርና፣ የሁላችንም ልጅ አድር ገንእናሳድጋታለን። አንቺም ቱናት የምታገኛት እንደ ማናችም አልፎ አልፎ እና ከሥራ ዉጪ ይሆናል ማለት ነዉ። በማኅበራችን የሕጻናት መዋያ ዉስጥ እናስገባት እና እንደ ማንኛዉም ልጅ ጨዋታ እና ግበረ ሕጻናት እየፈጸመች ታድጋለች”
“እንደ ማንኛዉም ልጅ?”

👍27
“ይገባኛል። ይገባኛል፣ከማንኛዉም ልጅ ደግሞ እሷ ተጨ ማሪ
እ ክብካቤ ትፈልጋለች: ለዚያም ቢሆን እኮ ታዲያ ትክክለኛ ቦታዋ
የማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት ነዉ: ከሰዉ ጋር ነዉ ማደግ ያለባት እንጂ በጠባብ ክፍል ከሰዉ ተሽሽጋ አይደለም: በዚያ ላይ ማኅበራችን ዘንግቶት
የነበረዉን የእሷን ዓይነት ልጆች የማገዝ ኃላፊነቱ እንዲወጣ ዓይኑን የገለጠችለትን ቱናትን ለዉለታዋ የሚሆ ነገር እዲያደርግላት ዕድል
መስጠት ያለብሽ ይመስለኛል”።
እመር ብዬ ልጄን ከእጁ መንጠቅ ፈለግሁ
“ግድ የለሽም፤ አሁ ነግሬሽ አሁኑኑ አልወስድብሽም: ግን ልብ
አድርገሽ አስቢበት። አንቺንም እኮ አጣንሽ ዉቤ? ለዚህ ማዕከል፣ ለዚህ ማኅበር ይልቁንም ለቤተ ክርስቲያናችን ምን ያህል አስፈላጊ ሰዉ እንደ ሆንሽ ላንቺ ላይታወቅሽ ይችላል: ግን አንቺም ልጅሽም እስካሁ በቆያችሁበት መንገድ ከሰዉ የምትነጠሉ ከሆነ፣ የሚጎድለዉ እንዲህ ነዉ ተብሎ የሚነገርም አይሆም: ግድ የለሽም አስቢበት''
ምንም መግባባት የቻልን አልመሰለኝም፡ እኔ በአርምሞ ተሞልቼ፣ ልጄንም ገዳሜ አድርጌ ገዳማዊ ሕይወት እየኖርሁ ነኝ ስል፣ እሱ ግን ሰዉ ጠልቼ ከሰዉ የተደበቅሁ ሳይመስለዉ አልቀረም፡
“በይ እባክሽ፤ ወደ ቀልብሽ ተመለሺና በቅጡ አስቢበት: እርግጠ ነኝ ለመቼም ፣ እስከ ማታ እሺ የሚል መልስ ከልብሽ አገኛለሁ” አለኝና፣ ወደ
ፊት ቀደም አለ፡፡ የበሩ እስካሁን አለመከፈት ገርሞኝ ነበር፡ ለካንስ እኔ ስለ ቀደምሁ እና በየሳምንቱ መታደስ የነበረበት የይለፍ ፈቃዴ ከቋቶች ሁሉ ስለ ተሰረዘ ኖሯል ክርችም እንዳለ የቆየዉ፡ ልክ ባልቻ እኔን አልፎ፣ ከፊት ከመሆኑ ወለል ብሎ ተከፈተልን
እዉነትም ቅድም ባልቻ እንዳለዉ፣ የማዕከሉ የዉስጠኛዉ ክፍል
ልዉጥዉጥ ብሏል፡ በዚህ የነበረዉ ወደዚያ፣ በወዲያ የነበረዉ ደግሞ በሌላ በኩል ቦታ ተቀያይሯል፡ እዚህ ዉስጥ የሚሠሩትን አብዛኛዉን
የማዕከሉን አባላት የሚይዘዉን ሰፊዉን ክፍል አልፎ ይገኝ የነበረዉ የዋና ዳይሬክተሩ ቢሮ ሳይቀር ወደ በሩ አጠገብ መጥቷል
“ማን ናፈቀሽ?” አለኝ ባልቻ፣ ቱናትን ይዞ ወደ ቢሮዉ እየወሰደኝ
“ማንም”
“ዉሽታም! ማንም ማንም?”
“ማን ይናፍቀኛል ብለህ ነዉ ከቱናት በቀር? እሷ ብቻ ናት እቅፌ ላይ ሆና ጭምር አብራኝ እንዳለች የማላምናት። ሌላ ማንም”
“እነሱ ግን ‹ናፈቀችን ናፈቀችን እያሉ ትንፋሽ አሳጥረዉኛል”
“እነማናቸዉ እነሱ?”
“ኧረ ስንቱ! አንቺንና እኔን አብረዉ የሚያዉቁን ሁሉ። በተለይ እዚህ
የሚሠሩት የሲራክ አባላትማ አይወራም: አንቺ ግን ያ ሁሉ ለሰዉ የነበረሽ ስስት ቀርቶ፣ አሁን የናፈቀኝ የለም, ብትዪኝ ደንቆኛል። ለነገሩ አላምንሽም: እንዴት ግን?”
እዉነት አለዉ እኮ የናፈቀኝ የለም እዉነት? የባልቻን አግራሞት ተከትዬ እንደገና ባስበዉ፣ እኔንም ገረመኝ፡ ሌላዉ ቢቀር ወንድሞቼና እህቶቼ አልናፈቁኝም ወይ? እመዋ ቤት ባለኝ ክፍል ተወስኜ ከቱናት ጋር ብቻ ከተቀመጥሁ በኋላ፣ ሲወጡ ሲገቡ ዳናቸዉን በሩቁ እሰማቸዋለሁ እንጂ
ዓይን ለዓይን ከተያየን ስንት ጊዜያችን! እመዋንስ እሺ በቀን አንድ ጊዜም ቢሆን፣ መቁነን ስለምታቀርብልኝ እና አልፎ አልፎ ደግሞ ለቱናት የሚሆኑትን ነገሮች በገፍ አስገዝታ ስለምታቀብለኝ ሳንተያይ አድረን አናዉቅም፡ እነ ጃሪም ግን ከናፋቂ ልቤ እንዴት ሊወጡ ቻሉ? በእንቅልፍ
ልቤ እንኳን ባጣቸዉ የምሞት ሲመስለኝ ኖሬ፣ አሁን ግን እንዴት የእናቴ ልጆች አይናፍቁኝም?
እንዴት?....
✨ይቀጥላል ✨

👍20❤5👏2🔥1
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...የሚስተር ኬን የሙዚቃ ትርዒት ሀሙስ ታይቶ ሲያበቃ ሎርድ ማውንት ስቨርን ቅዳሜውን ከኢስት ሊን ጓዙን ጠቅልሎ ለመነሳት አቀደ የጉዞው ዝግጅትም አስቀድሞ ተጀመረ ነግር ግን ቀኑ ከይረሰ በኋላ ያ ሁሉ የመነሳት ዝግጅት ለሁለተኛ ጊዜ እንዳይሰናከል አጠራጣሪ መስሎ ታየ ገና ሲነጋ ቤቱ ተሸበረ ከዌስትሊን ቀዶ ጠጋኝ ሐኪም ሚስተር ዌይን ራይት ተጠርቶሰ ከኧፕርሎ መኝታ ቤት
ገባ " ኧሮሎ አሁንም በሽታው እንደገና ክፉኛ ተቀሰቀሰበትና በጣም ተበሳጨ።
« በዚህ ዐይነት ገና ሳምንት ሁለት ሳምንት ወይም አንድ ወር እዚህ እቆይ ይሆናል » አላት ለሳቤላ ።
« በጣም አዝናለሁ... አባባ ኤስት ሊንን በጣም ስልችኸዋል " »
« መሰልቸት ይደለም ። ከኢስትሊን እንድወጣ የምፈልግበት ሌሎች ምክንያቶች አሉኝ አሁን ኮ አንቺም ወደ ሙዚቃ ትርዒት መሔድ ላትችይ ነው »
ሳቤላ ፊቷ ቀላ ። ምነው አባባ ? ላትችይ ነው አልከኝ?»
«አዎን ማን ይዞሽ ይሔዳል ? እኔ እንደ ሆንኩ ከመኝታዬ እንኳን መነሣት አልቻልኩም »
« መገኘት አለብኝ . . . አባባ " አለዚያማ እንግኛለን ብለን አስወርተን ብንቀር ዱሮውንም እንደማናደርገው አወቀን ያስወራነው ይመስልብናል " ደግሞ እንደምታውቀው ከዱሲ ቤተሰብ ጋር እዚያ ለመናኘት †ቃጥረናል " ባይሆን ሠረገላው እዚያው ያድርሰኝና እኔ ከነሱ ጋር እገባለሁ" »
« በይ እሺ ላንቺ ደስ እንዲለሽ እኔ እንኳን የምትቀሪበትን ስበብ ካገኘሽ እንዳጋጣ ቀርተሽ የምትጠቀሚበት መስሎኝ ነበር » አላት "
« በጭራሽ ! እኔ ሚስተር ኬንን ከነሙዚቃው የማልንቀው መሆኔን ዌስት ሊን እንዲያይ እፈልጋለሁ » አለች ሳቤላ እየሣቀች ።
ቀን ላይ የዊልያም ቬን በሽታ በጣም ከሚያሳስብ ደረጃ ላይ ደረሰ " ስቃዩ በጣም የሚያሰቅቅና የሚያስጨንቅ ነበር ከክፍሉ እንዳትገባ የተደረገችው ሳቤላ
ስለ በሽታው መባባስ ምንም አላወቀችም " ያን ያህል ሲያቃስት እንኳን ምንም ድምፅ ከጆሮዋ አልደረሰም » ስለዚህ ያለምንም ሐሳብና ጥርጣሬ እየሣቀችና
እየተጫወተች ደንገጡሯ ማርቨል እየረዳቻት መልበስ ጀመረች ማርቨል እመቤቷ የመረጠችውን ልብስና ጌጥ ሳትወደው እየከፋት አልብሳት አበቃች » ሳቤላ ልዩ ሁና
አጊጣና ለብሳ ወደ አባቷ ክፍል ገባች እንግዲህ ልሒድ አባባ ? » አለችው።
እሱም አዘብዝበው ያበጡትን ያይኑን ቆቦችና ደም የለበሰው ፊቱን ገለጥ አድርጎ” ሲያይ በትክክል ምን እንደምትመስል ባያረጋግጥም የምታምር ንግሥት የምታበራ መንፈስ መስላ ታየችው "ነጭ ዳንቴል ሥራ ቀሚስ ለብሳ አልማዟን በጸጉሯ ባንገቷና በክንዷ አድርጋለች " ቀሚሱ በጣም ምርጥ ከሆነ ጨርቅ የተስፋ ነበር " አልማዞቹ ከመልካሙ አንገቷና ከሚያሳሱት ክንዶቿ ላይ ሲብለጨለጩ ጫፉ
ቅልብስ ቅልብስ ብሎ የተበጠረ ከትከሻዋና ከደረቷ ወርዶ ከተኛው ጸጉሯ ጋር ልዩ ሁነው አምሮባት ነበር።
ኧርሉ ሲያያት በጣም ገረመውና ትክ ብሎ ካስተዋላት በኋላ «እንዴት ለአንድ የሙዚቃ ትርዒት እንደዚህ ሆነሽ ትለብሻለሽ ? አብደሽ ነው በጤናሽ ? » አላት
« ማርልም እንዳንተ አለችኝ » አለችው አሁንም በደስታ እየተፍነከነከች "
«እንዲያውም ልብሱንም አላቀርብም ብላኝ በግድ ነው ያስጣኋት እኔ ግን አባባ የሚስተር ኬንን ዝግጅት በደንብ ለብሰው ሊያዩት የሚገባ ትልቅ ትሮዒት
መሆኑን እነዚህ ዌስት ሊኖች እንዲያውቁት አስቤና ሆነ ብዬ ነው ያደረግሁት " »
« በአዳራሹ ያለው ሕዝብ በሙሉ እንደ ጉድ ይመለከትሻል »
« ግድ የለኝም " የፈለገ አፉን ከፍቶ ሲያየኝ ያምሽ ውጤቱን ይዠልህ እመጣለሁ " »
« ቀጣፊ በሰበቡ ለመታየት ፈልገሽ ነው እንጂ እንደዚህ የለበስሺው ግን ሳቤላ ...ኡ ኡኡ ! ኡህ ! ኡህ ! »
ሳቤላ እንደ ቆመች ድንግጥ አለች አባቷ ሲያቃስት ሰሚውን ያስጨንቅ ነበር
«ክፉ ልክፍት ! ልጄ . . . በይ ሒጂ ስናገር ይብስብኛል " »
« አባባ ልቅርና አጠገብህ ልሁንልህ ? » አለችው ኮስተር ብላ " ከማንኛውም ሐሳብና ሥራ በሽታ ይቀድማል " እንድቀር ከፈለግኸኝ ወይም የማደርግልህ ነገር
ቢኖር ልቅር " »
« እንዲያውም መሔድሺን እፈልገዋለሁ " ልታደርጊልኝ የምትችይው አንድም ምድራዊ ነገር ስለሌለ ሒጂ ይልቅስ ሚስተር ካርላይልን ያገኘሽው እንደሆነ ነገ ላነጋግረው እንደምፈልገው ንገሪው »
ማርቨል አንድ ካባ በትከሻዋ ላይ ጣል አዶረገችላትና ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ ወደነበረው ሠረገላ ሔዳ ገባች።
የሙዚቃው ትርዒት ከገበያው ላይ ከነበረውና የከተማ አዳራሽ እየተባለ ከሚጠራው ከፍርድ ችሎት አዳራሽ ውስጥ ነበር " ድምፅ ለማስተጋባት የተመቸ
አዳራሽ ነበር ከዌስት ሊን የበለጡ በጣም የታወቁ ከተሞች እንኳን ይህን የሚያህል የሚመኩበት አዳራሽ አልነበራቸውም " ሚስተር ኬን ችሎታው በፈቀደለት መጠን ትርዒቱን ለማሳመር ሞከረ አንዲት በአራተኛ ደረጃ ልትመደብ
የምትችል ተጫወተች ከለንደን ቀጥሮ አምጥቶ ሌሎች አጃቢዎችም ከአካባቢው
አሟላ።
ባርባራ ሔርም የፈለገው ነገር ይምጣ እንጂ ትርዒቱን ሳታየው እንዶማትቀር አሳውቃ ነበር እናቷ ሚስዝ ሔር ግን ፍላጐቱም ጤንነቱም አልነበራትም" ስለዚህ
ሚስተር ሔርና ባርባራ ከሚስ እና ከሚስተር ካርላይል ጋር አብረው ለመሔድ ተነጋግረው ነበር ስለዚህ ቀደም ብለው በቡና ሰዓትላይ ለመድረስ ወደ ሚስ ካርላይል ቤት ሔዱ ከተገናኙ በኋላ በሠረገላ የመሔድ ነገር ሲነሣ ቦታው ቅርብ የምሽቱ
አየር ጥሩ ስለነበር ሚስ ካርላይል « እግሮቻችን ምን ሆኑና ነው ? » ብላ ተቃወመች " ባርባራም ከሚስተር ካርላይል ጋር እየተጫወተች በእግር መሔዱን አልጠላችውም " እነሆ ዳኛው ሔርና ሚስ ካርላይል ፊት ፊት እየተጫወቱ ሲሐዱ ባርባራና ሚስተር ካርላይል ቀረት ብለው እያወጉ ከኋላ ይከተሉ ነበር "
« እንዴት ነው አሁንስ ጠፋህሳ ? » አለችው ባርባራ "
«ሎርድ ዊልም ቬን ብቸኝነት እተሰማቸው ሲቸግሩ አየሁዋቸውና በየቀኑ ኢስት ሊን እተሻገርኩ አብሪአቸው ስለማመሽ ነው " ከእንግዲህ ግን ቅዳሜ ስለሚሔዱ በቂ ጊዜ ይኖረኛል።
« ትናንት ከደብሩ አለቃ ቤት ትመጣለህ ተብለህ ስትጠበቅ ነበር አኛም ማምሻውን ስንፈልግህ አመሸን»
« አለቃው ሚስተር ሊትልና ባለቤታቸው እንኳን የጠበቁኝ አልመሰለኝም ኢስት ሊን የራት ቀጠሮ እንደ ነበረኝ ነግሬአቸው ነበር »
« ኧረ ካልክስ አንዳንዶቹ ይህን ያህል ከዚያ ቤት የሚያመላልስህ ጉዳይ ምን እንደሆነ ይርማቸዋል " አጠቃሌለህ ኢስት ሊን ሳትግባ አትቀርም እየተባልክ ነው " እንዲያውም ሳቤላ ቬን እመቤት ሳቤላ ባትሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ምልልስ እሷን ፍለጋ ነው ተብለህ ትታማ ነበር " »
ስለኔ ይህን ያህል በማሰባቸው አመሰግናለሁ የሚሰማኝ ደስታና የምቆጥርላቸው ውለታ እመቤት ሳቤላ ቬን ከሚሰማትና ከምትቈጥርላቸው የላቀ ሊሆን ይችላል " እኔን የገረመኝ ግን ባርባራ....አንቺም ይህን የማይረባ ወሬ ከቁም ነገር ቆጥረሽ ስትደግሚው ነው " »
« ሰው እኮ ነው እንዲህ የሚለው እኔ አላልኩ » አለችውና ነገሯን በመቀጠል! «ወይዘሮ ሳቤላ ድምፀ መልካም ናት የሚሏት እውነት ነው ? መቸም ያንጐራረች እንደሆነ የድምጿ ቃና ከሰማይ የወረደ እንጂ ከሰው አንደበት የወጣ አይመስልም አሉ።
« በይ ይህን አባባልሽን እኔ እንደ ሰማሁሽ ኮርሊያ እንዳትሰማሽ " ፊቷ የመልአክ ፊት ይመስላል » ስል ስምታኝ የቁጣ መዓት እንዳወረደችብኝ እንዳታወርድብሽ» አላት እየሣቀ።

👍22❤1
ባርባራ ፡ ፊቷን ወደሱ ምልስ አድርጋ አየችውኛ «ግን እውነት መልአክ ትመሰላለች ? አንተስ እንደዚህ ብለህ ተናግረሃል ? » አለችው
« የተናገርኩ ይመስለኛል ብቻ ኮርኒሊያ ካፌ ስለ ነጠቀችኝ እርግጠኛ አይደለሁም " ኧረ ስሚ እስኪ ... ስለ ሪቻርድ እስከዛሬ ምንም ወሬ የለም ? »
«የለም ሁልጊዜም አንተና እማማ ናችሁ ይጽፋል የምትሉ " እኔ ግን ምነም እንኳን እሱ እጽፋለሁ ብሎን ቢሔድም ስለሚፈራ ይጽፋል ብዬ ተስፋ አላደርግም""
« በሌላ ስም አድርጎ ቢልክልኝ ምንም አያሠጋም " ለሚስዝ ሔርም ትልቅ እፎይታ ነበር »
«የሪቻርድን ፍራት ታውቀዋለህ ኦትዌይ ቤተል እኮ ተመለሰ" ሲመለስ እንደምትጠይቀው ነግረኸኝ ነበር ... አርኪባልድ»
« ጠየቅሁትና ምንም እንደማያውቅ ነገረኝ » ጥፋቱን ሁሉ በሪቻርድ ላይ ነው
ያላከከው»
«እኔስ ይህ ቶርን የሚባል ምን ዐይነት ሰው እንደሆነ ጨንቆኛል»
« ይገርምሻል ኮ በስዌንሰን በኩል ባጠያይቅም ምንም ፍንጭ አላገኘሁም "
በዚያን ጊዜ በዚሀ ስም የሚጠራ ሰው በዚያ አካባቢ እንዳልነበረ ተረድቻለሁ እንግዲህ ጊዜ የራሱን መብራት ይዞ መጥቶ የቶርንን ማንነትና የትነት እስኪያሳየን ድረስ በተስፋ መጠበቅ እንጂ ሌላ የምናደርገው የለም»
ባርባራና ካርላይል፡ስለዚህ እየተጫወቱ ከከተማው አዳራሽ ደረሱ - ከበሩ ብዙ ሰው ነበር " እንግዶቹ ትርዒቱን ለማየት ሲገቡ ብዙ ሕዝብ ደግሞ ከውጭ
ሆና ገቢዎቹን ይመለከት ነበር " የሎርድ ማውንት እስቨርን ሠረገላ ለሌሎች እንግዶች ሠረገላዎች መንገድ እንዳይዘጋ ጥግ ይዞ ቆመ "
« እመቤት ሳቤላ ቬንም ያቻትና እዚያ ተቀምጣለች » አለች ባርባራ
"ሚስተር ካርላይል ድንግጥ አለ " ምን ትጠብቃለች ? አባቷ የት ይሆኑ ? ጥርጣሬ ተሰማው " ምን እንደሆነ መለየት ባይችልም , አንድ የሆነ ነገር እንደነበረ
ጠረጠረ
« ይቅርታ አድርጊልኝ . . . ባርባራ " አንድ ጊዜ እስካነጋግራት ድረስ ልለይሽ ነው » አላትና መልሱን ሳይጠብቅ ሔዶ ሳቤላን አነጋገራት
«ሚስዝ ዲሲን እየጠበቅሁ ነው ... ሚስተር ካርላይል " ብቻዬን መግባቱ ደስ አላለኝም " የሚስዝ ዲሲ ሠረገላ ሲመጣ እወርድና ከሷ ጋር እገባለሁ » አለችው
« ጌቶችሳ ? »
« አዬ ለካ አልሰማህም ? እንደገና ታመመ "
« አሁንም እንዶገና ? »
«አዎን በጣም ታሟል ሚስተር ዌይንራይት ከሌሊቱ በዐሥራ አንድ ሰዓት ተልኮበት መጥቶ አብሮት እንደዋለ ነው " አባባ አን†ንም ነገ ሊያነጋግርህ እንደሚፈልግ ንግሪው ብሎኛል»
ሚስተር ካርላይል ወደ ባርባራ ተመለሰና ከአዳራሹ ገብተው በደረጃዎቹ ሲወጡ አንድ ሌላ ያማረ ሠረገላ ደረሰ " ባርባራ ዞር ብትል የሚስዝ ዲሲ ሠረገላ
መሆኑን አየች "
አዳራሹ ሞልቶ ነበር " ሚስዝ ዱሲ ከሁለት ሴት ልጆቿና ከሳቤላ ቬን ጋር ሆና ስትገባ ሚስተር ኬን አስቀድሞ ከኦርኬስትራው አጠገብ ይዞላቸው ወዶ ነበረው
ከፍተኛ ቦታ እየመራ ወሰዳቸው " ቀደም ሲል ሎርድ ማውንት እስቨርንን ያስገረመው የሳቤላ ቬን አለባበስና ጌጥ በአዳራሹ ሞልቶ የነበረው ሕዝብንም አስገረመው "
የሚስዝ ዲሲ ልጆች አፍንጫቸውን ነፍተው ሲመለከቷት እናቲቱም ብትሆን በጣም ያዘነች ትመስል ነበር «ተዉ ልጆች አትፍረዱባት ይህች እናት የሌላት ምስኪን ልጅ የሚያስከፋባትን የሚያስቅባትን ነገር ገልጾና ለይቶ የሚነግራት
የሚመክራት ሁነኛ ሰው የላትም ። አሁን እንዶምታይዋት አሻንጉሊት መስላ ለብሳ እንድትመጣ ያደረገቻት ማርቨል ናት » አለቻቸው "
ሚስ ካርላይል ሔርና ባርባራም ከኦርኬስትራው ጥግ ቦታ ተይዞላቸው ነበር "ሚስ ካርላይል በዌስት ሊን ከሁሉ ቀድማ የምትታይ እንጂ ከሌሎች በስተጀርባ የምትሸሸግ ሰው አልነበረችም ሚስተር ካርላይል ግን አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው
ከነበሩት ሰዎች ጋር ተደባልቆ በአካባቢው መቆሙን ስለፈለገ ከነሱ ተለየ " በአዳራሹ ውስጥ የእግር መቆሚያ ቦታ እንኳን አልነበረም " ለሚስተር ኬን ይህን ሁሉ ሕዝብ የሰበሰበለት የሱ ሙያ ተወዳጅነትና ችሎታ ሳይሆን የሳቤላ ጥረት እንደሆነ
በማወቁ እንደ መለኮት ቢሰግድላትም በወደደ ነበር ።
እንደ ማንኛውም የገጠር ዝግጅት ሁሉ የሙዚቃው ትርዒት ሪጂም ነበር " ከወታው ሩብ ያህል እንደ ተገባደዶ የሽቶ ዱቄት የተነሰነሰበት ጭንቅላት ከበራፉ አጠገብ ከነበሩት ሰዎች በስተኋላ በደረጃዎቹ ሲወርድ የሎርድ ማውንት አስቨርን አሽከር መሆኑ ሙሉ በሉ ከዘለቀ በኋላ ታወቀ " ሰውየው በዚያ ጭንቅላቱ
ግራና ቀኝ እየተገመጠ ወደ ሰዎቹ ተጠግቶ ተመልካቾችን በማስቸገሩ ይቅርታ የመጠየቅ ያህል ዝቅ ብሎ እጅ ነሣ "
ሰውየው የደነገጠና ግራ የተጋባ ይመስል ነበር ።ዐይኖቹን ከመአዘን ማእዘን እያቅበዘበዘ ፈለገና ሚስተር ካርላይልን ድንገት ሲያየው ቅልል አለው
« ይቅርታ ያድርጉልኝ ጌታዬ እመቤቲቱ የት እንዳለች ሊያሳዩኝ ይችላሉ
« ከመድረኩ አጠግብ ነው ያለች "
« ታዲያ እንዴት አድርጌ ከዚያ መድረስ እችላለሁ ? » አለ ሰውየው ከራሱ ጋር የሚነጋገር መስሎ ድምፁን ዝቅ በማድረግ
አዳራሹ እንደዚህ ሞልቶ እያለ
ይህን ሁሉ ሕዝብ ጥሎ ማለፉ ደስ አይለኝም ጌቶች በጣም ደክመውበን ነው አለው ለሚስተር ካርላይል « ሁኔታቸው በጣም የሚያሰጋ ነው »
ሚስተር ካርላይልም ሲሰማ በጣም ደነገጠ "
« ሲያቃስቱ ሲጓጉሩ በጣም ነው የሚስጮንቁት ሚስተር ዌይን ራይትና አንድ ሌላ ሐኪም አብረዋቸው አሉ " በተጨማሪም ሌሎች ሐኪሞች ለማምጣት
ወደ ሊንበራ ባስቸኳይ ተልኳል አሁን ሚስዝ ሚዞን እመቤት ሳቤላን እንድጠራት ስለ ነገረችን ሠረገላ ይዘን መጥተን ነበር " »
« ደኅና እኔ እጠራታለሁ » አለና ሚስተር ካርላይል በዚያ ግጥም ብሎ በሞላው ሕዝብ መኻል ዐልፎ ሔደ " በዚያ ሰዓት አንዲቷ የለንደን ተጫዋች አሳዛኝ
ዘፈን ስትዘፍን ስለነበር ተመልካቹ ሁሉም ሚስተር ካርላይልን በክፉ ዐይን ዐየው የሰውን መከፋት ችላ ብሎ አለፈና ከሳቤላ ፊት ቆመ።

👍18❤6
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
“እንዴት? ተለዉጫለሁ ማለት ነዉ በቃ?” እያልሁ፣ ከራሴ ጋር
ስተዛዘብ ቆየሁ።
እንዲያዉ ራሴንም ጭምር ስዋሸዉ የናፈቀኝ የለም አልሁ እንጂ፣ እንዴት ነዉ የማይኖረዉ? የጎዳናዉን ሰዉ ሁሉ የልቤ ሰዉ ማድረግ ይሆንልኝ የነበርሁት እኔ ዉብርስት፣የእናቴን ልጆች ከልቤ ችዬ ላስወጣ? አይሆንም፡ የናፈቀኝ የለም ያለ አፌን ይዤ እንኳንስ በባልቻ ፊት፣ በራሴ ኅሊናም ሚዛን ላይ ለመቆም ተሸማቀቅሁ።
አፈርሁ።
“ወዴት ነዉ ታዲያ?” አለኝ ባልቻ፣ ቱናት ያለችበትን አልጋ እየሳብሁ
ወደ መዉጫዉ ስራመድ አይቶኝ፡
“ወደ በረሃ”
“ወዴት?”
“ገዳሜን ወደ ገደምሁበት ወደ በረሃዬ። ወደ እመዋ ቤት!”
“ቅድም ምን ተባብለ'? ተይ እንጂ በማርያም: ይልቅ ቱናትን ይዘሽ
የማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት እየጎበኛችሁት፣ ቅድም ያልሁሽን
አታስቢበትም?”
“እኔ የፈለገዉን ያህል ባስበዉ፣ የሚሆን የሚሆን መስሎ አልታኝም”
“ግድ የለሽም፣ እስከማታ ጊዜ አለሽ: ደጋግመሽ አስቢበት”
“እስኪ ይሁን። እሺ። መኪናህን አታዉሰኝም ታዲያ? ለማሰቡም ቢሆን እኮ የከረምሁባት በረሃዬ ትሻለኛለች: ወደ እመዋ ቤት መሄድ አለብኝ ትክ ብሎ ሲያየኝ ቆየና አንገቱን በይሁንታ ነቅንቆ፣ ቀድሞኝ ወደ በሩ አመራ፡ ዝም ብዬ ኖሯል እንጂ ቀደም ቀደም ያልሁት፣ ቀድሞ የነበሩኝ
የትለፍ ፈቃዶች ሁሉ መልሰዉ ካልታደሱልኝ በቀር ያለ'ሱ ወደ ሲራክ ፯ መግባትም ሆነ ከማዕከሉ መውጣት
አልችልም:: ስለሆነም
ጠመዝማዛዉን እና ባለ ብዙ በሩን ሲራክ ፯ አሳልፎኝ መኪናዉ
እስከቆመበት ድረስ ቱናትን ከነአልጋዋ አቅፎ አደረሰልኝ፡፡
“በይ እንግዲህ። ማታ፣ ልክ አንድ ሰዓት ሲሆን እደዉልልሻለሁ” አለኝ፣ የጠየቅሁትን የመኪናዉን ቁልፍና ያልጠየቅሁትን አንድ የእጅ ስልክ ጭምር አዉጥቶ እያቀበለኝ፡፡ እሺም፣ እምቢም፣ ቻዉም ሳልለዉ፣ ቱናትን ጭኜ የመኪናዉን ሞተር አስነሳሁ፡ እንደ ድሮዉ በችኮላ ሳይሆን፣ የመኪና መሪ ከነካሁ ቢያንስ መንፈቅ እንዳለፈኝ እና ከአጠገቤ
የጫንኋትም ሰዉ ገዳሜ ቱናት መሆኗን በማሰብ ወደ እመዋ ቤት
የሚወስደኝን ጎዳና በዝግታ አሽከረከርሁበት እንደ ደረስሁ፣ የግቢዉን በር ራሴዉ ለመክፈት ቀልጠፍ ብዬ ወረድሁ።
ስሞክረዉ ግን አልከፈትልሽ አለኝ፡፡ ለወትሮዉ ማናችንም የቤተሰቡ አባላት አድርሶን በመጣን ጊዜ እንዳንቸገር በሚል፣ ግቢያችን ተቆልፎብን
አያዉቅም: እንዲሁ በዉስጥ በኩል ይሸነጎርና፣ መሸንጎሪያዋን
የምንስብባት ደግሞ እኛ ብቻ የምናዉቃት አልባሌ ገመድ አለችልን፡አሁን ግን ይቺ ገመድ በሩን ልትከፍትልኝ አልቻለችም፡፡ እንዲያዉም እጄ ላይ ስለቀለለችብኝ፣ ሳብ ሳደርጋት ጭራሽ ምዝዝ ብላ ወጣች ገመዷ
ተበጥሳለች::
ቆይ፣ ገመዳችንን የበጠሰብን ማነዉ? ምንድነዉ?
“ኤጭ!” አልሁኝ፣ ንድድ ብሎኝ፡ በዚያ ላይ ልጄ ቱናት ምግብ
ከቀመሰች ቆይታለች፡፡ እንዲያዉም ለመንገድ ብዬ ይዤላት የነበረዉ
ምግብ ስለ ቀዘቀዘባት፣ እዚህ ደርሼ ትኩስ ምግብ እስከማጎርሳት ነበር
ችኮላዬ::
“ቆይ፤ ገመዳችንን ማነዉ የበጠሰብን?” አልሁኝ፣ እጄ ላይ ያለዉን የገመድ ቁራጭ ጨብጬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ቢገባኝ፡
“እኔ” አለኝ፣ ከዉስጥ በኩል።
“አሃ፣አላችሁ እንዴ? በሉ ክፈቱልኝ' አልሁኝ በደፈናዉ፣ ማን
እንዳናገረኝ ስላላወቅሁት
“ምን ልትሆኚ?” አለኝ አሁን በድምፁ ለየሁት፡ ጃሪም ነዉ፡
“ክፈትልኝ”
“እንዳታስቢዉ!”
“ኧረ ባክህ አትቀልድብኝ። ለራሴ ልጄን ርቦብኛል። በል ክፈተዉ ይልቅ”
“አይ እግዲህ! በቋንቋሽ መሰለኝ ያናገርሁሽ!''
“ምን መሆንህ ነዉ፣ ክፈትልኝ እኮ ነዉ የምልህ”
“ሴትዮ! ምናለበት ባትፈታተኚኝ? ነገርሁሽ፤ ከዛሬ በኋላ እዚህ ግቢ ላይሽ አልፈልግም”
“እኔ ተናግሪያለሁ ጃሪም! ክፈተዉ ልጄን ርቧታል። አላበዛኸዉም እንዴ ?
ብለህ ብለህ ደግሞ ወደ እናቴ ቤት እንዳልገባ ልትከለክለኝም ያምርሃል ጭራሽ?” እልህ እየመጣ ጉሮሮዬን ተናነቀኝ፡፡
“ዉነት የእናትሽ ቤት እንግዲያዉስ እርምሽን አዉጪ። ሰማይ ዝቅ
ቢል ይቺን ግቢ ደግመሽ አትረግጫትም: በጭራሽ! ለአንቺም ሆነ ለእናትሽ፣ በቂ ጊዜ ሰጥቻችሁ ነበር: የማያልቅ መስሏችሁ ስትቀልዱበት
ያለቀባችሁ እንደሆነ፣ እኔ ጃሪም ምን እዳዬ? ከዚህ በቀር ምን
ላድርጋችሁ? የራሳችሁ ችግር ነዉ፣ ሥራችሁ ያዉጣችሁ: ከደጄ ግን ፈቀቅ! ያቺ ቆዳ እናትሽ መቼም ልብ የላትም፣ ያልኋትን ረስታ ድርሽ እንዳትልብኝ ብቻ!"
ይኼን ሁሉ ስንባባል፣ ጎረቤት እና አላፊ አግዳሚዉ ሁሉ በግላጭ
እየሰማና እያየኝ ነዉ አንዳንዱ ለእኔ አዛኝ መስሎ ጠጋ ይልና፣ ‹እንዲህ በይዉ› ብሎ ይመክረኛል የተረፈዉ ደግሞ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደ'ሱ ልክ ልኳን ንገራት ጃሪምን
ይመክረዋል አንዳንዱ እንዳትከፍትላት፣ ደግ አደረግህ!» ይለዋል እሱን፣ ሌላዉ ደግሞ ምን አለማመነሽ? ፈሪ ነሽ እንዴ? መኪና ይዘሽ የለ? ዝም ብለሽ ደርምሰሽዉ የማትገቢ! ይለኛል እኔን፡ አልደነቀኝም ምክራቸዉን ሰምቼ የእናቴን
አጥር ብደረምሰዉ እና ቢፈርስ፣ እኛ እንጂ እነሱ አይጎዱም፡
መካሪ እና ግርግሩ መብዛቱን ሳይ፣ ለመሸሽ መረጥሁ: ምስስ ብዬ ወደ መኪናዉ ገባሁና፣ ቆይቼ ብመለስ
አልፎለት እንደሚጠብቀኝ
በመተማመን፣ እሱን ትቼ እመዋን ፍለጋ ወደ ኋላ መንዳት ጀመርሁ።
እሺ ጎረቤት እና አልፎ ሂያጅስ የእኛን ነገር ያባብስብን ግድየለም፣ የቀሩት
እህትና ወንድሞቼን ድምፅ አለመስማቴ ግን ደነቀኝ፡፡ መቼም በግቢዉ
ዉስጥ ያለዉ ጃሪም ብቻዉን አይመስለኝም: ያም ብቻ ሳይሆን፣ እኔን
ከብቦ እኔንም ግፊ፣ እሱንም ግፋ ይል ከነበረዉ ሰዉ መሀል አንደኛዋ
እህቴ ጭጭ ብላ፣ ልክ እንደሌላዉ ሰዉ ስትታዘበን አይቻታለሁ የሆነዉ ሆኖ በቅቶኛል፡ እየተንገሸገሽሁ ከመንደራችን ራቅ እንዳልሁ፣ መኪናዉን ዳር አስይዤ
አቆምሁትና፣ አብሮ በሚዞረዉ አልጋዋ ላይ ከኋላዬ ያስተኛኋትን ልጄን
ዳበስኋት፡ ቱናትን፡ ትራፊ ምግብ አላበላትም ብዬ የመብያ ሰዓቷን
በጣም አሳልፌባታለሁ፡ አሁን ግን አማራጭ ስለ ሌለኝ፣ ቅድም
ቀማምሳለት የተረፈዉን ቀዝቃዛ ፍትፍትም ቢሆን ማብላት አለብኝ በተጨማሪም እንደ ልማዴ ዓይኔን ጨፍኜ እየተንሰፈሰፍሁ፣ ትንሿን ጣቴን በፊንጢጣዋ በኩል ሰድጄ ካካ ማስባል አለብኝ፡ ይኼንንም በየሦስት
ሰዓቱ ማድረግ ሲጠበቅብኝ፣ ዛሬ ግን አሳልፌባታለሁ በዚያም ላይ
ከጠዋት ጀምሬ ወዲያ ወዲህ ስላልኋት ነዉ መሰለኝ፣ እነዚያ ቁልቁል
የሰረጉ ዓይኖቿ ይበልጡኑ ቡዝዝ ብለዉ ታዩኝ፡
ቱናትን እንደ ነገሩ አቀማመስኋትና፣ ሌላ ሌላዋንም እንደሚሆን እንደሚሆን አድርጌላት ስጨርስ፣ ወደ ነበረችበት መልሼ አስተኛኋት። ከዚያ፣ እመዋን ፍለጋ ወደ ታዕካ ነገሥት ገዳም ማሽከርhር ጀመርሁ።
ምን እየተደረገ እንደሆነ እመዋን መጠየቅ አለብኝ፡፡ መቼም እሷ መልስ
አታጣልንም አሁኑኑ አግኝቻት እስከዛሬ እየናቅሁ ያለፍሁትን ጥያቄ
ሁሉ መጠየቅ አለብኝ፡ ምን እስኪፈጠር ነዉ ከዚህ በላይ? አይበቃም? ኧረ በቃ በቃኝ...
“እመዋን አይተዋታል አባ?” አልኋቸዉ ቄሰ ገበዙን፣ በሥዕል ቤት ኪዳነምሕረ እና ታዕካ ነገሥት በዓታ መካከል ባለዉ ሰፊ አደባባይ አግኝቻቸዉ፡
“እግዚአብሔር ይመስገን: ደህና ዉለዋል?” አሉኝ፣ መንገዳቸዉን ገታ አድርገዉ አቤት ትሕትና! እኔን እኮ ነዉ አንቱ ያሉኝ፡ መቼም ትሕትና ከገዳም ሌላ መኖሪያም የላት! ያልኋቸዉን ባይሰሙኝም፣ ሰላምታ እንዳቀረብሁላቸዉ ገምተዋል።
“እመዋን አይተዋት ይሆን?” ስል አቻኮልኋቸዉ አሁንም፣ ሰላምታቸዉ ጊዜ የሚወስድብኝ ስለመለሰኝ፡፡

👍22
“አላወቅኋቸዉም፣ ማናቸዉ?” አሉኝ፣ አዉቅሻለሁ አላውቅሽም በሚል ግርታ ትኩር ብለዉ እየተመለከቱኝ፡ “አሃ ፍቅርተ ማርያም፣ አንቺ አይደለሽም ወይ?” አሉኝ፣ የክርስትና ስሜን ጠርተዉ “እኔ ነኝ:
እመዋ አላይዋትም ከቀትር በኋላ?” “ዛሬ ወዲህ ባይመጡ መሰለኝ ጨርሶም አላየኋቸዉ: ምነዉ ደህናም አይደሉ?”
“አይ” ብዬ፣ በቆሙበት ትቻቸዉ ወደ ግቢ ገብርኤል ተፈተለክሁ
እዚያም አጣኋት፡ ትኖርበታለች ብዬ በገመትሁበት ቦታ ሁሉ፣ ወደ
ላይም ወደ ታችም ብዬ ብፈልጋት ላገኛት አልቻልሁም፡ ተስፋ ስቆርጥ፣ ቱናትን ለብቻዋ ትቼበት ወደ ሄድሁበት መኪና ተመለስሁ
የቀረኝ አማራጭ፣ ወደ ባልቻ መደወል ነዉ፡ ቅድም እሱ የሰጠኝ ስልክ እንዳለኝ አስታወስሁና፣ ደወልሁለት
“ኅሽ! አሰብሽበት?” አለኝ፣ ስልኩን ከማንሳቱ፡ ቱናትን ወደ ማኅበራችን
መዋእለ ሕጻናት ለማስገባት እና እኔም ወደ ቀድሞዉ የሲራክ፯
አገልግሎቴ ለመመለስ እንዳስብበት ነግሮኝ ስለነበር፣ መስማማቴን ልገልጽ የደወልሁለት መስሎታል፡ እኔ ግን እመዋ የት እንዳለች እንዲነግረኝ ነበር አደዋወሌ፡ መቼም ያለችበትን እንደሚያዉቅ ጥርጥር
የለኝም::
“አሰብሽበት አይደል?” አለኝ፣ ትንሽ እየተንተባተብሁ ስለ ቆየሁበት።
“አዎ” አልሁት፣ እንኳንስ ጨክኜ ወደ መዋእለ ሕጻናቱ ላስገባት
ይቅርና፣ ትንፋሿን ለቅጽበት የተለየሁት እንደሆነ የምሞት መሆኔን ሊያዉቀዉ እንደሚገባ ልነግረዉ በልቤ ወስኜ፡፡
“ንገሪኝ”
“አዎ፣ አሰብሁበት”
“አላልሁሽም? አሁን እኮ እንዲያዉም፣ እመዋ እና እሸቴ ወደ ማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት ሄደዉ አስፈላጊ ፈቃዶችን እና ለቱናት መሠረታዊ የሆኑ
ነገሮችን አሟልተዉ መጨረሳቸዉን እየነገሩኝ ሳለ ነዉ የደወልሽልኝ''
“እመዋ?”
“በይ አሁኑኑ ቱናትን እዚያዉ ዉሰጃት''
“ቆይ ቆይ… እመዋ አጠገብህ አለች እንዴ አሁን?''
“ ኧረ ስሚኝ እስኪ ቱናትን ወደ መዋእለ ሕጻናቱ አድርሻት መጀመሪያ እስኪ ለማንኛዉም” አለኝ፣ ስልኩን ለመዝጋት የተቻኮለ መሆኑን በሚገልጽ ሁኔታ ቅድም ወደ ቤት ስሄድ የሆነብኝን ሁሉ ሳያዉቅ እንደማይቀር በመገመት ሐሳቡን ለመቀበል አመነታሁ
“ዉሰጃት”
“እሺ”
“ከዚያ ስትመለሺ ደዉዪልኝ''
“እሺ፤ ግን እመዋን እዚያዉ አገኛታለሁ አይደል?”
“ደዉዪልኝ አልኩሽ እኮ: በይ ስትጨርሺ ደዉዪልኝ''
አሁን ገና ነዉ በቅጡ ያሰብሁበት ስልኩን ከዘጋሁት በኋላ፣ ቱናትን
ወደ ማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት ማስገባት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሀ ብዬ አሰብሁበት በእርግጥ መንፈቅ ያልሞላቸዉ ጨቅላዎች ሳይቀር የሚዉሉበት ቤት መሆኑን አዉቃለሁ በዚያ የሚያገለግሉት ሠራተኞች፣ ልባቸዉ ለሕጻናት የተመቸ መሆኑም ይገባኛል፡
ለቱናት ግን የሚሆን ነዉ? እኔስ እሷን መለየቱ ይሆንልኛል ወይ?
ስፍስፍ አልሁላት።
ቢሆንም ሌላ ምርጫ አጣሁ ሁሉም ነገር የሞት የሽረት ጉዳይ እየሆነ መጥቶብኛል። ምርር ላለብኝ ነገር ሁሉ ምርር ማለት አለብኝ የቤተሰባችንን መጨረሻ እስከማየዉ ድረስ፣ ለጊዜዉም ቢሆን ለቱናት ማቆያ ያስፈልጋታል እንደ ምንም፣ ጨክኜ መጨከን አለብኝ፡
ሰዓቴን ተመለከትሁ
ቀትሩ አልፏል።
ጥርሴን ነክሼ የመኪናዉን ሞተር ቀሰቀስሁት እንዲችዉ ሆዴ እንደ
ተንቦጫቦጨብኝ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አልፎ ከምስካየ ኅዙናን
መድኃኔዓለም ገዳም ማዶ ባለዉ ቅያስ ገባ ብሎ ወደሚገኘዉ የማኅበራችን መዋእለ ሕጻናት አሽከረከርሁ። ልጄን በየቅጽበቱ እየዞርሁ እያየኋት፣ እንደ ጀማሪ አሽከርካሪ መኪናዉን ወዲያ ወዲህ እያወላገድሁ ነዳሁት፡
ዞሬ ባየኋት ቁጥር ደግሞ፣ እንዲህ ነዉ የማይሉት ድንጋጤ ጥብስቅ
እያደረገ ይወጋኛል። በኃይል ተሸበርሁ።
ለአንዳፍታም ቢሆን እንኳን ቱናትን መለየት ያሸብራል፡ መቼስ እንዲህ
የሚያደርገኝ ልጅነቷ ወይም መላመዳችን ወይ ደግሞ ገዳሜ ስለሆነች ብቻ አይመስለኝም፡ ታዲያ ምንድነዉ? ብቻ ክብድ ብሎኛል፡...

👍32❤12👏3