አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
በጠፍ ጨረቃ ከኮዜት አጥር ግቢ ውስጥ ኮዚትን ሲጠብቅ በስሙ
የጠራው ድምፅ የሕይወቱን ፍጻሜ ይዞለት የመጣ መሰለው:: «አሁንስ የእድሜዬ መጨረሻ በሆነ» ሲል ተመኘ:: ያ በጨለማ በስሙ የጠራው ድምፅ የመቃብር ቤት የሚያንኳኳና ከቤቱም ውስጥ ገብቶ የበሩን ቁልፍ እንደሰጠው ነው የቆጠረው:: በጭንቀት ጊዜ የሚታይ ከጭንቀት ሊያስወጣ
የሚችል መንገድ ፈተና ውስጥ ይጨምራል:: ማሪየስ በቀዳዳ ወደ ውጭ ተመለከተ፡፡ «እንሂድ» ነው ያለው በጨለማ ያናገረው ሰው:-

ልቡ በሀዘንና በጭንቀት ሲዳፈን ሕሊናው በአንድ ነገር ብቻ
ተሞልቷል፡፡ ለስቃይ እንደተፈጠረ ተገነዘበ፡፡ ለአለፉት ሁለት ወራት
ከኮዜት ጋር የፍቅርን አክርማ ሲቀጭ ነበር የሰነበተው:: አሁን ግን በድንገት ጠፋችበት፡፡ የወጣትነት ዘመን የተወሳሰበ ፍቅር ጥናትና ብርታት የደረሰበት ብቻ ያውቀዋል እንጂ በቃላት ኃይል ገልጾ በትክክል ለማስረዳት
አይቻልም:: ስለዚህ እንዲያው ዝም ነው:: ተስፋ መቁረጥ መላ አካላቱን ወረረው:: አንድ ነገር ከፊቱ ድቅን አለ፤ ከዚያ ጭንቀት፣ ከዚያ መከራ በቶሎ መገላገል፡፡

ከግቢው ወጥቶ ቶሎ ቶሎ መራመድ ጀመረ:: ዣቬር የሰጠውን ሽጉጥ በኪሱ ይዞአል፡፡ በስሙ የጠራው ሰው ከዓይኑ ተሰወረ:: በዋና ጎዳና
አድርጎ ሲጓዝ ከንጉሡ ቤተመንግሥት ደረሰ፡፡ ያንንም አልፎ ሄደ።የቤተመንግሥቱ የግቢም ሆነ የውጭ መብራቶች እንደ ወትሮው በብዛት አልበሩም:: በየመንገዱ ዳር የነበሩ ሱቆች ተዘግተዋል፡፡ ከመንገድ ዳር ቆሞ
የሚያወራ ወይም የሚጫወት ሰው የለም:: መንገድ ሁሉ ጭር ከማለቱ የተነሣ የተወረረ ከተማ መስሏል፡፡ ሆኖም የሰልፈኛ ኮቴና ጫጫታ ከሩቁ ይሰማል፡፡ ማሪየስ ተጠምዝዞ ከአንዱ ጎዳና ወደሌላው በተላለፈ ጊዜ በይበልጥ ጭር ካለ ሰፈር ደረሰ፡፡

ጉዞውን ቀጥሎ ጨለም ካለ ሥፍራ ደረሰ:: ፍርሃት ፍርሃት አለው፡፡ አንድ ሰው እየሮጠ በአጠገቡ አለፈ፡፡ «ወንድ ነዉ ወይስ ሴት?» ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡ ለማወቅ አልቻለም:: ከገበያ ቦታ ደረሰ፡፡ የገበያውም አካባቢ
ጭር ብሉአል፡፡ የሚበራ መብራት በሩቅ ባየ ጊዜ ወደዚያ አመራ:: ቀጥሎ ከሚፈልገው ቦታ መድረሱን ተገነዘበ፡፡ ከምሽጉ ገባ፡፡ ከድንጋይ ላይ እጁን አጣምሮ ተቀመጠ፡፡ ያ እድለቢስ አባቱ ትዝ አለው:: አባቱ ኮሎኔል )
ፓንትመርሲ ጎበዝ ወታደር እንደነበር ታወሰው፡፡

እርሱም እንደ አባቱ ጉብዝናውን የሚያስመሰክርበት ጊዜ መድረሱን አወቀ፡፡ ልክ እንደ አባቱ በጥይት መካከል በመሽሎክሎክ ደፋርነቱንና ደረቱን ለጥይት ሰጥቶ ደሙን በማፍሰስ አገር ወዳድነቱን የሚያሳውቅበት ሰዓት አሁን እንደሆነ ተረዳ፡፡ ስለዚህ ጠላቱን እየተከታተለ ማጥቃት እንዳለበት
አመነ፡፡ ጦርነቱ እንዲካሄድ የታቀደው ከተማ ውስጥ ሲሆን ፍልሚያው ከሕዝብ ጠላቶች ጋር ነው፡፡ በዚህ ጦርነት ሕይወቱ እንደምታልፍ በተገነዘበ
ጊዜ መላ ሰውነቱ ተረበሸ፡፡ ሰው እንዳያየው ከጥላ ስር ተደብቆ አለቀሰ፡፡

ታሪኩ አሳዛኝ ነው:: ግን ምን ሊያደርግ ይችላል? ከኮዜት ተለይቶ ከመኖር፤ መሞት ይሻላል:: እርስዋ አገር ጥላ ስለሄደች የእርሱ በሕይወት
መኖር ትርጉም የለውም፡፡ ያን ሁሉ መንገድ ተጉዞ አሁን ካለበት ከደረሰ በኋላ ወደኋላ ማለት ትርፉ ትዝብት ነው:: በቆራጥነት መጥቶ በፍርሃት መሸሽ! ምሽጉን ፍለጋ መጥቶ ካየው በኋላ ማፈግፈግ! አይደረግም፡፡

የአሳቡ ተገዥ በመሆኑና አሁንም ልቆይ ወይስ ከዚህ ልጥፋ የሚል
ሐሳብ ስለተፈራረቀበት ወደ መሬት አቀርቅሮ ለብዙ ጊዜ ቆየ:: በድንገት ወደላይ ቀና አለ፡፡ አንድ ብሩህ የሆነ ነገር ታየው:: ከሞት አፋፍ ስንደርስ የሚታየን ዓይነት እውነታ! ልንሞት ስንል እኮ እውነት ቁልጭ ብላ ትታየናለች::

ከዚህ ፈተና ውስጥ መግባቱ እኮ የሚያስከፋ ሳይሆን የሚያስደስት
ነው:: አባቱ ለምንድነው እንደዚያ የተሰቃየው? ከባለሥልጣኖች ላይ እጅ ማንሳት እንደ ክቡር ተግባር የተቆጠረበት ጊዜ የለም እንዴ? አገሩ ከባድ ሀዘን ላይ ነው ያለችው:: ሕዝብ ደግሞ ተቃውሞውን ይደግፋል:: ፈረንሳይ
እየደማች ነው:: ነፃነት ግን ፈገግታዋን እያስታቀፈችን ነው:: የነፃነት ፈገግታ በእያንዳንዳችን ላይ ከሰፈነ ፈረንሣይ ቁስልዋን ትረሳለች::

ስፍር ቁጥር የሌለው አድልዎ፣ ግላዊ ጥቅም፣ አሉባልታ፣ ውሽት፣
መቀጫ ፣ በሥልጣን መባለግ፣ አመፅ ፣ ፍርደ ገምድልነትና የጨለማ ጉዞ ፈረንሳይ ላይ ሰፍኖአል፡፡ ይሄ ታዲያ እንዲህ የሚታለፍ ነው? ከሥረ መሠረቱ መመንገል አለበት::

ይህኛው አመለካከት ማሪየስን በደስታ ያሰከረው:: በንጉሡ ላይ እጁን እንዲያነሳ አደፋፈረው:: ምሽጉን ተዘዋውሮ ለማየት ከተቀመጠበት ብድግ
አለ:: በያለፈበት የሕዝባዊ እንቅስቃሴ አባላት ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው ይወያያሉ::

ሰዓቱ እያለፈ ሄደ፤ አሁንም ግን ምንም ነገር የለም:: በአካባቢዎ
ከሚገኘው ቤተክርስቲያን የአራት ሰዓት ደወል ተደወለ፡፡ ኢንጆልራስና ኮምብፌሬ የካርባይን ጠብመንጃዎቻቸውን ይዘው ቁጭ አሉ፡፡ እንደተኳረፈ
ሰው አይነጋገሩም:: ምናልባት ወደ እነርሱ የሚመጣ ኃይል ካለ ጆሮአቸውን አቅንተው ለማዳመጥ ይሆናል፡፡

ጋሪ በጥድፊያ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቁ ተመለከቱ፡፡ ትንሹ ልጅ
ከጋሪ ነጂው አጠገብ ተቀምጧል:: ጋሪው እየተቃረበ ሄደ:: ጋብሮች ትንፋሽ
አጥሮት ከጋሪው ላይ ዘሎ ዱብ አለ፡፡

«ጠብመንጃዬን! በጣም ተቃርበዋል» ሲል ጮኸ፡፡

ሁሉም ኮረንቲ እንደያዘው ሰው ተሸማቀቁ፡፡ ከምሽጉ የነበረ ሁሉ
ጠብመንጃውን አነሳ:: የኳኳታ ድምፅ ከያለበት ተሰማ::
«የእኔን ካርባይን ትፈልጋለህ?» ሲል ኢንጆልራስ ልጁን ጠየቀው::
«የአንተን ሳይሆን ሌላ አነስ ያለ ወብመንጃ ሰጡኝ» ሲል ጋቭሮች
መለስ፡፡

የዣቬር ጠብመንጃ ሰጡት::

ከጥቂት ጊዜ በኋላ የሰው ኮቴ ይሰማ ጀመር፡፡ ብዛት ያለው እግረኛ እንደሚመጣ በኮቴው ታወቀ:: እየተቃረቡ መጡ፡፡ በመጨረሻ ጨለማውን
ከሁለት የሚሰነጥቅ ድምፅ ተሰማ፡፡

«ማነህ?»

ወዲያው ብዛት ያለው የጠብመንጃ ቃታ ሲንቋቋ ተሰማ፡፡

«የፈረንሳይ አብዮት» ሲል ኢንጆልራስ አስተጋባ፡፡

«ተኩስ!» ተባለ፡፡
ከዚያ በኋላማ ምን ቅጡ የጥይት እሩምታ እንደ ሐምሌ ዝናብ
ወረደ፡፡ ከጣራ ለይ ተሰቅላ የነበረችው ባንዲራ ከመሬት ወደቀች፡፡

«ጓዶች» ሲል ኩርፌይራክ ጮክ ብላ ተናገረ፡፡ «ረጋ በሉ፡
ጥይታችሁን ቶሎ ቶሎ አትጨርሱ፡፡»

«ዋናው ነገር ደግሞ» አለ ኢንጆልራስ፤ «ባንዲራችንን እንደገና መስቀል
አለብን፡፡»

ከወደቀችበት አነሳው::

ማነው ጀግና ይህችን ባንዲራ ከነበረችበት መልሶ የሚተክል?»
ማንም አልመለሰለትም፡፡ ጠብመንጃ ተደቅኖበት ማነው ከምሽግ ጫፍ፡ ላይ የሚወጣ! ሪሱም ቢሆን ፈርቶአል::

«ፈቃደኛ የለም ማለት ነው!»

ምንም እንኳን መሴይ ማብዩፍ ከምሽጉ መሀል ቢሆኑም ማንም ሰው ልብ አላላቸውም:: ሆኖም ምሽጉ ሲሠራ አብረው ሠርተዋል፡፡ ሥራው ካለቀ በኋላ ከመጠጥ ቤቱ ምድር ቤት ነበር የተቀመጡት:: ቀደም ሲል
ኩርፌይራክና ሌሎችም የእርሳቸው ከዚያ መገኘት አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ነግረዋቸው ነበር፡፡ ሆኖም እርሳቸው አልሰሙም:: የመጀመሪያው ውጊያ ሲከፈት እርሳቸው ከምድር ቤት ስላልወጡ የሆነውን አላዩም:: ሰው ሁሉ ለመዋጋት ቦታ ቦታውን ሲይዝ እርሳቸው ከነበሩበት ቀሩ። ከምድር ቤት ቀርተው የነበሩት እርሳቸው፣ ዣቬርና የዣቬር ጠባቂ ብቻ ነበሩ፡፡ እንዲያውም መሴይ ማብዩፍ ከአሳባቸው የነቁት ውጊያው ተጧጡፎ
👍11
ተኩሱ ሲጋጋል ነው:: ልክ ኢንጆልራስ «ፈቃደኛ የለም ማለት ነው!» ብሎ በመጮህ ሲናገር ድምፁን ስለሰሙ ከተቀመጡበት ብድግ አሉ። ከምድር ቤቱ ወጥተው ስው ሁሉ ከነበረበት ብቅ ሲሉ ሁሉም ዓይኑን ጣለባቸው።

«አበባ እየሸጡ የሚኖሩ ሽማግሌ አይደሉም?» ሲል ሰው ተጠያየቀ::

«እኝህማ የሕዝብ ተወካይ ናቸው» ሲል አንዱ አጉረመረመ:: እርሳቸው ግን ምናልባትም ሰው ያላቸውን አልሰሙም፡፡ በቀጥታ ወደ ኢንጆልራስ ሄዱ:: የያዘውን ባንዲራ ከእጁ ሲነጥቁ
ምሽግ ውስጥ የነበረ ሁሉ ተደናገጠ፡፡ ኢንጀልራስ ራሱ በድንጋጤ ክው አለ:: የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ በመሆናቸው ጭንቅላታቸው ይንገዳገዳል፡፡
ሆኖም ማንም ደፍሮ ጣልቃ ሊገባ ወይም «ይተዉ» ብሎ ለመናገር
ኣልቻለም:: ከምሽጉ ጫፍ ለመውጣት በደረጃው ወደ ላይ መራመድ ጀመሩ፡፡ ከዚያ መሽጎ የተቀመጠ ሁሉ አንድ ደረጃ በተራመዱ ቁጥር በልቡ
አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት እያለ ይቆጥር ጀመር፡፡ በጣም ያስፈራል፡፡ በድንገት
አንድ ሰው «ባርኔጣዎን ያውልቁ» ሲል ጮኸ፡፡ «ያወልቁ፣ ያውልቁ» ሲል ሁሉም ተናገረ::

ባርኔጣቸውን ሲያወልቁ ጥጥ የመሰለው ሽበታቸውና አሳዛኙ የሽማግሌ ፊታቸው በጉልህ ታየ:: ዓይናቸው ሰርጉዶአል ፧ ቆዳቸው ተጨማዷል:: ባንዲራውን ይዘው ኩራት እየተሰማቸው ከምሽጉ ጫፍ ደረሱ::

ቀና ሲሉ በሩቁ አዩ:: ምንም ዓይነት ድምፅ ግን አልተሰማቸውም:: በዚህ
ከጫፍ እንደደረሱ ከአሥራ ሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑ ጠበመንጃዎች ፀጥታ መካከል ባንዲራውን በማውለብለብ ጮክ ብለው ተናገሩ::

«ረጅም እድሜ ለፈረንሣይ አብዮት! ረጅም እድሜ ለሪፑብሊኩ! ወንድማማችነት! እኩልነትና ሞት!»

ቀደም ሲል «ማነህ?» ሲል ጮክ ብሎ የተናገረው ድምፅ አሁንም
ጮክ ብሎ «አጥቃ» ሲል ጮኋል፡፡

የጥይት እሩመታ ተለቀቀ፡፡ መሳይ ማብዩፍ እየተንገዳገዱ ከመሬት
ተዘረሩ፡፡ በደከመ ድምፅ «እድሜ ለሪፑብሊኩ» ሲሉ ተናገሩ::
በርቀት የሚሰማው ኃይለኛ ድምፅ አሁንም «ተኩስ» ሲል አዘዘ::

የሽማግሌው ደም እንደዚያ ሲፈስ ያዩ የንቅናቄው አባሎች ፈዝዘው
ቀሩ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኮ በጣም ሲበዛ ራሳችንን መጠበቅ እንዳለብን ረስተን የምንፈዝበት ጊዜ አለ፡፡ የአሁኑም ከዚያ የተለየ አልነበረም:: እየተንፏቀቁ
ሄደው ሬሳውን አነሱ፡፡

«ምን ዓይነት አረመኔዎች ናቸው» ሲል ኢንጆልራስ ተናገረ፡፡

ኩርፌይራክ ወደ ኢንጆልራስ ጆሮ ጠጋ ብሎ ስለመሴይ ማብዩፍ
ማንነት ነገረው:: ከዚያም ኢንጆልራስ የሚከተለውን ተናገረ፡፡
«ወገኖቼ እኝህ ሽማግሌ በአርአያነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እኛ አመነታን፣ እርሳቸው መጡ:: እኛ ወደኋላ ሸርተት አልን፤ እርሳቸው ወደፊት ተራመዱ:: እዩት እስቲ፤ እርጅና የሚያንቀጠቅጣቸው ሽማግሌ
በፍርሃት ለሚንቀጠቀጡ ወጣቶች ምሳሌ ሆነው ትምህርት ሲሰጡ፡፡ እኒህ ሰው እድሜ የጠገቡና የክብር ሞት የሞቱ ሰው ናቸው:: ስለዚህ የእኚህን ጀግና ሬሣ ላለማስነካት የእርሳቸውን ድፍረት ፤ የእርሳቸውን ጉብዝና ታጥቀን በቆራጥነት እንዋጋ! ይህች ምሽጋችን የማትበገርና የማትደፈር ምሽግ እናድርጋት:: »

ሁሉም በያለበት «እንዋጋለን፧ መሪያችንን አናስደፍርም» ሲል ጮኹ፡

ኢንጆልራስ ጎንበስ ብሎ የራሣውን ጭንቅላት ቀና ካደረገ በኋላ ግምባሩን ሳመው፡፡ ...

💫ይቀጥላል💫
👍13
#ገረገራ


#ክፍል_አራት


#በታደለ_አያሌው


“እንዴት ነህ ጃ?” አልሁት፣ ከተንጋለልሁበት መነሳት የእረጥብ አራስ ያህል እያቃተኝ፡፡ ያቆላመጥሁት ራሱ አልመሰለኝም ማን ብዬ ነዉ ግን የጠራሁት? እንደ እህት ጃ ነዉ ወይስ እንደ ቀበሌ ጃሪም ብዬ? እንጃልኝ
ብቻ።

“ጭራሽ አልጋዬ ላይ?”

"በይ አልጋዬን ልቀቂልኝ ያለ በሚመስል ዓይኑ ጠቅ አድርጎኝ ሲቆም፣ ብድግ ብዬ ከአልጋዉ ላይ ወርጄለት ወደ ራሴ ክፍል ሄድሁ። ምን እንዳለኝ እንኳን ልብ ያልሁት በኋላ ሻንጣዎቹን ወደ ዉጪ ማመላለስ ሲጀምር ነበር።

የእመዋ ቤት ጎስቆል ያለች ብትሆንም፣ አሠራሯ ሁልጊዜም
ያስገርመኛል። ክብ አይሏት፣ አራት ማዕዘን አይሏት፣ የግንብ አይሏት፣
የጭቃ አይሏት፣ ብቻ ግን ሁሉንም ትመስላለች። በዚያ ላይ የሞቀች
ናት፡፡ እኔም፣ ምንም እንኳን ከቤተሰባችን ጋር አባታችንን እየተከተልሁ በዞርሁበት ክፍለ ሀገር የኖርሁባቸዉ ቤቶች ሁሉ የነበረኝ ትዝታ ባይለቀኝም፣ በቅጡ ነፍስ ያወቅሁባት ቤት ናትና እንደዚችኛዋ የሚሆንልኝ ቤት ግን የለም፡፡ ጠባብ ብትመስልም ለእኛ ግን ጠብባን አታዉቅም። በዚች ቤት ሁላችንም የየራሳችን ክፍል አለን፡፡ በእርግጥ በዚች ቤት ያለንን ክፍል መጀመሪያ የያዝነዉ እንደ ዋዛ፣ በሽሚያ ነበር።
ትዝ ይለኛል፤ መጨረሻ ከነበርንበት ከተማ ቀይረን ወደ'ዚች ቤት ልንገባ ደጁን የረገጥነዉ ኅዳር 29፣ ሐሙስ ቀን ነበር።


“በሉ እንግዲህ” አለችን እመዋ፣ ልክ ወደ'ዚች ቤት በራፍ
ከመድረሳችን፣ ቤቷ ወዳሏት ክፍሎች እየለቀቀችን፡፡ “መቼም እንግዲህ አድገናል ብላችኋል። ለየብቻ ማደሩን ከሆነ የጓጓችሁለት ይኸዉ እንዳሻችሁ ሞክሩት ደግሞ። በሉ፤ ኮተቶቻችሁን በየክፍላችሁ አስገቡ”

“በየክፍላችሁ?” አልሁኝ እኔ፣ እንክት ብዬ፡ ያደግነዉ አንድ ሰፊ
ምንጣፍ መሀል ወለሉ ላይ አንጥፈን፣ ተቃቅፈን እየተኛን ነዉ። እየተኛን አልሁ እንጂ፣ የሌሊቱን እኩሌታ እንኳን የምናሳልፈዉ እንዲሁ እንዳዉካካን ነበር። ለወጉ መብራቱን እናጠፋፋና፣ ልብሳችንንም ለዋዉጠን በዚያ ሀገር በሚያህለዉ ምንጣፍ ላይ በጎን በጎናችን እንሆናለን። ከዚያ ተረቡ፣ አሽሙሩ፣ ቀልዱ፣ ተረቱ፣ እንቆቅልሹ፣ እንካ ስላንቲያዉ፣ መሳሳቁ፣ መላፋቱ ይመጣል። ያልሆነዉ ምን አለ? ዛሬ ተረኛ እኔ የሆንሁ እንደሆነ፤ አንዴ በቃል ተረብ፣ ቀጥለዉ በልፊያ፣
ቀጥለዉ ቁንጥጫ ሁሉም ይረባረቡብኛል። ታዲያ ያሉኝን ቢሉኝስ ወንድሞቼንና እህቶቼን ላኮርፋቸዉ? ኧረ በጭራሽ! እንዲያዉም አሁን አሁን ሳስበዉ፣ ተረባቸዉን እና ልፊያቸዉን ሁሉ ለመከላከል አደርገዉ
የነበረዉ መፍጨርጨር ሁሉ ሳይጠቅመኝ አልቀረም። ቢያንስ ቢያንስ ንግግሬ እና ጡንቻዬን አዳብሮልኛል። በዚያም ላይ እኮ እኔ በተራዬ የቀመስኋትን ሁሉ፣ እነሱም በየተራቸዉ ይቀምሷታል።

“በየክፍላችሁ? አረ ምን ዓይነት፣ የማን ሐሳብ ነዉ ግን ይኼ?” አልኋት እመዋን፣ ሆዴን ባር ባር እያለዉ።

“ቀርፋፎ! ይልቅ ተመርጦ ሳያልቅብሽ ክፍልሽን አትመርጪም?” አለችኝ
ኣንደኛዋ እህቴ፣ የራሷን ክፍል መርጣ ማንም እንዳይነካባት ቆልፋዉ ወደኔ እየተመለሰች።
ብቻዬን እንደ ቀረሁ አስተዋልሁ። ሁሉም ይሻለኛል የሚለዉን ክፍል
ተሻምቷል። እኔ እዚህ በትዝታ ወዲያ ወዲህ ስል፣ እንደ ዱሯችን
እንድንተኛ እንድመካከራቸዉ እንኳን የሚሆን አፍታ ሳይታገሱኝ መስኮት ያላቸዉን እና በመስኮት በኩል አሻግሮ ለማየት የሚያመቹትን ክፍሎች ሁሉ ተሽቀዳድመዉባቸዋል፡፡ በተለይ የጃሪም ደግሞ ልዩ ነዉ፡፡ ከመስኮት በተጨማሪ፣ በዚህ በኩል ወደ ዋናዉ ሳሎን የሚያስገባ እና በዚያ በኩል
ደግሞ ወደ ዉጪ የሚያስወጣ በር ያለዉን፣ ሰፊዉን ክፍል ነዉ ተሻምቶ የያዘዉ።

ምንም አማራጭ ስላጣሁ እነሱ ያያዟቸዉን ክፍሎች እየተዟዟርሁ
ስመለከት ቆይቼ፣ ያሉኝን ኮተቶች ሁሉ እየጎተትሁ ወደ ተተወችልኝ
ምራጫ ክፍል አስገባሁባት። ያም ሆኖ ግን እምብዛም አልከፋኝም ነበር። ምክንያቱም፣ ዞሮ ዞሮ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ናቸዉ። ለስሙ ክፍሉ የየራሳቸዉ ቢባልም፣ መቼም በፈለግሁት ክፍል እንዳላድር የሚከለክለኝ
አይኖርም፡፡ እነሱም ለጊዜዉ መስሏቸዉ ነዉ እንጂ፣ በዚህ ምርጫቸዉ እንደሚጸጸቱ ገምቻለሁ። ለአንድ ወይም ላኹለት አዳር ለየብቻ ከሞከሩት
በኋላ ወደ መሀል ወለል መጥተዉ እንደ ዱሯችን አብረን እንተኛ
ማለታቸዉ አይቀርም፡፡ ይኼን ይኼን ሳስብ ትንሽ ቀለል ብሎኝ የነበረ ቢሆንም፣ ዉሎ አድሮ የሆነዉ ግን እንደ ጠበቅሁት አይደለም።

ይኼዉ በእንደዚያ ያለ ሁኔታ የያዝነዉ ክፍል አሁንም ድረስ ድርሻችን እንደሆነ አለ። የኋላ በኋላም ቢሆን፣ ጨክነን የየራሳችንን ቤት ስላልሠራን፣ በዚሁ ቤት ያለዉ ክፍላችን እንደ ተጠበቀ አለ። በርግጥ ገሚሶቹ ወንድሞቼ ወጣ ገባ እያሉ የኪራይ ቤት ኑሮ የሞካከሩ አሉ።
የሆነዉ ሆኖ፣ አሁን የየራሳችንን ሥራ ከያዝን እና የየራሳችን ኃላፊዎች ሆነናል ካልን በኋላም የምንኖረዉ እዚሁ ግቢ ነዉ። ቀን የየራሳችንን ሥራ ስንከዉን ዉለን አዳራችንም በየራሳችን ክፍል፣ በየራሳችን አልጋ ሆኗል። በእርግጥ እኔ ከሌሎቹ በተለየ መልኩ፣ ክፍት ባገኘሁት አልጋ
ሁሉ ነዉ የምተኛዉ። እንዲያዉም ብዙ ጊዜ ክፍት ሳይሆንም ጭምር፣ ጠጋ በሉልኝ ብዬ አብሬ የምተኛበት ጊዜ አለኝ። እያየኋቸዉም እንኳን
ደርሰዉ ንፍቅ በሚሉኝ ሰዓት ስስቴን የማስታግሰዉ፣ እነሱን እቅፍ አድርጌ ትንፋሻቸዉን ስምግ ያደርሁ እንደሆነ ብቻ ነዉ። እንደ ነፍሴ በምሳሳላቸዉ እህቶቼ እና ወንድሞቼ አልጋ ላይ ብተኛ፣ ነዉሩ ምን ላይ እንደሆነ አሁንም አይገባኝም፡፡ በእርግጥ ማንም ከልክሎኝ አያዉቅም ነበር። እኔ እንዲያዉም ደስ የሚላቸዉ ነበር የሚመስለኝ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ማጉረምረም አመጡ፡፡ አንዳንዶች እንደ ጨዋታ እያስመስሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ የሆነች የጀመሯት ነገር አልሳካ ያለቻቸዉ
እንደሆነ፣ ቀድመዉ የሚያላክኩት ወደኔ ሆኗል። የእነሱ ማለት የእኔም ነዉ እያልሁ ባደረስኝ ክፍል ሁሉ ስንት እና ስንት ልብስ እና ጌጣጌጥ ያኖርሁ ቢሆንም፣ አሁን ግን እሱን ጭምር ብላሽ አስቀርተዉብኛል።

“ምነዉ ሻንጣህን ሸካከፍህ፣ ንብረት እያሸሽህ ነዉ'ንዴ ወንድሜ?” አልሁት፣ በእኔ ቤት ቀልጄ ሞቼ ልቤ ዉልቅ እያለ፡፡ ይኼም አልበቃ ብሎኝ እኮ ጥርሴን ለፈገግታ አግጥጨዋለሁ ሳላስበዉ ነፍሰ ጡር እንደሆንሁ፣ ሕይወቴ ምስቅልቅሉ እንደወጣ፣ የእሱ የወንድምነት ምክር
እንደሚያስፈልገኝ ልነግረዉ በልቤ ወስኛለሁ። በመሆኑም የመጨረሻ
ሻንጣዉን አንጠልጥሎ ወደ በሩ ሲጣደፍ ተከተልሁት። ለካንስ ሌላ
ደልዳላ ሰዉ ደግሞ ከበሩ በእዳሪ ሆኖ እየተቀበለ ወደ መኪናዉ
እያጓጓዘለት ኖሯል። ልብ ባልለዉ እንጂ፣ ከልብሶቹ ሌላም የእኔ ናቸዉ የሚላቸዉን እቃዎች ከሳሎን ሳይቀር ለቃቅሞ በመኪናዉ ቀርቅቦ አስጭኖ ጨርሷል። አልጋዉን ራሱ ከምን ጊዜዉ እንዳወጣዉ አላየሁትም።

“ምን እያደረግህ ነዉ አንተ?” አልሁት፣ ልሳቅ አልሳቅ በሚል ቃና።

“ቻዉ!” አለኝ፣ ጥያቄዬን እንዳልሰማ ሁሉ የመኪናዉን የጋቢና በር ከፍቶ እየገባ፡፡

“አንተ ጃሪም! ቆይ እንጂ ወዴት ... ምን እየሆንህ ነዉ?” አልሁት፣
ተንደርደሬ ከፊት ለፊቱ መንገዱን ዘግቼ እየቆምሁበት።

“አይበቃንም ብለሽ ነዉ?”

“ምኑ ነዉ የሚበቃን?”

“ዉሽቱ ሁላ! ለጥቅማችሁ ስትሉ ጠብ እርግፍ አላችሁ እንጂ፣ እኔ እኮ ከዚህ ቤተሰብ አይደለሁም። እናትሽም እናቴ፣ አንቺም እህቴ፣
ዘመዶችሽም ምኔም አይደላችሁም በቃ”

“ምንድነዉ የምታወራዉ?”
👍342
“አሁንማ አንቺ እና እናትሽ እንዲህ ዓለማችሁን የምትቀጩበት ቤት
የአባቴ ቤት መሆኑን አዉቂያለሁ። ለጊዜዉ ትቼላችሁ ወጥቻለሁ። መቼ ተመልሼ እንደምመጣ አልነግራችሁም። ብቻ ያኔ እዚህ ካገኘኋችሁ ነዉ ጉዱ”

ቀልድ ነዉ ቢለኝና ሰማዩን በሳምሁት፤ እሱም ባልበቃኝ፡፡ ነገር ግን ዓይኑ ላይ ጥላቻዉን አኑሮ ያንቺ እህትነት በቅቶኛል አለኝ በምሬት:: ወንድምነት ደግሞ ያበቃል እንዴ? ልክ በስምምነት እንዳገኘነዉ ተራ ነገር፣ እህትነትም በቃኝ ሊሉት ይቻላል ለካ? ያዉም ከአንድ አብራክ የተካፈለኝ የእናቴ ልጅ?

እዉነትም ፈተናዉን ሲያመጣዉ አያድርስ! አሁን እኔ በየትኛዉ
ምክንያት ነዉ ማበድ ያለብኝ? መቼም ማበዴ ላይቀር ነዉ እንግዲህ፡፡የሕይወቴ ዓይነተኛ ምሰሶዎች ሁሉ፣ ዓይኔ እያየ ተሰባብረዉብኛል።

«ምንድነዉ እናንተ?” አለችን እመዋ፣ የግቢዉን በር ከርፈድ አድርጋ ስትገባ ከጃሪም ጋር እንደ ተዋጊ ፍየሎች ተፋጠጥን ብትደርስብን። አንደኛዋ እህታችን እና ሌላኛዉ ወንድማችንም ተከትለዋት ገቡ። እሷ ከቤተ ክርስቲያን፣ እነሱ ደግሞ ከጋራ ሱቃቸዉ ሲመለሱ በአጋጣሚ
መንገድ ላይ ተገናኝተዉ እንደሚሆን እገምታለሁ።

“አትናገሩም ወይ?” አለች እመዋ፣
እየተራመደች።

“ልጅሽን አንድ በዪልኝ!” አልን እኩል፣ እኔም ጃሪምም።

“ሆሆሽ” ብላ እርጅና ወስዶባት በተረፉላት ጥርሶቿ ሳቀችብን።
“ሁልጊዜ ልጅነት አለንዴ እናንተ? በሉ ይልቅ እንዲያ እንዲያ በሉና
ምሳ ነገር አቀራርቡ። አንዳችሁ ደግሞ ጀበና ጣዱ እስኪ። በሉ
አልኋችሁ እኮ!” አለችንና ባሞጨሞጩ ዓይኖቿ ጨርቁሳን አለፈች።

በዚህ ዕድሜያችን እቃ እቃ እየተጫወትን መስሏታል እመ። እንደ እዉነቱማ ቢሆን፣ ከዚህ በላይ ቀልድ እኮ በየትም አይገኝም። ኧረ ወንድምና እህት ነን ኧረ አይደለንም ብሎ መለማመንን የመሰለ ጨዋታ ምናለ? አብረዋት የገቡት እህት እና ወንድማችን፣ ግብግቡ
ሲጀመር ሰልፋቸዉን ከማናችን ጋር እንደሚያደርጉ እያሰቡበት ነዉ
የሚመስሉት። አንድ ጊዜ እኔ ላይ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጃሪም ላይ አፍጥጠዉ ይጠባበቃሉ።

“ጉዳችሁን ሰማችሁ?” አልኋቸዉ፣ የእመዋን ወደ ቤት መግባት
ጠብቄ፡፡ “ወንድማችሁ አይደለሁም ብሏችኋል እንግዲህ”

“እ?” አሉ ኹለቱም፣ ፍርጥም ብለዉ፡፡

“ደም እና ነፍስ እንጂ፣ ወሬኛ ይመስል ወንድም እና እህት ያደረገን፣
‹ሰዉም ቢሆን ከመሬት ተነስቶ አያወራም፤ እዉነትም እመ እናቴ
አትመስለኝም ነዉ የሚለዉ እንግዲህ”

“ምን ምን ምን?” አለ ከእመዋ ጋር የገባዉ ወንድሜ፣ ሳቁ አጓጉል
ጥርሶቹ ላይ ከስሎበት።

“እርማችሁን አዉጡ ...”

“እስኪ አንቺ ዝም በይ!” ብላ እህቴ አፌን አስያዘችኝ፡፡ መቼም ሐሜቱን ቀድማም ሳትሰማዉ የቀረች አትመስለኝም። እሱ ብቻ ሳይሆን እሷ ራሷም
የቤተሰቡ አካል እንዳልሆነች ሲወራባት ነዉ የባጀችዉ። እንዲያዉም አልፎ አልፎማ፣ ካህኑ አባታችን በቁመተ ሥጋዉ እያለ በየክፍለ ሀገሩ ተዘዋዉሮ የማገልገሉን ነገር እየጠቀሱ፣ ከየቦታዉ ልክ እንደ ርካሽ ሸቀጥ
እንደ ለቃቀመን ሁሉ ይወራል። ጭራሽ እመዋም አባታችንም መካኖች እንደሆኑ፣ እህ ብለዉ የወለዱት ልጅ እንደ ሌላቸዉ የሚቀባጥሩም አሉ። ለእኔ ለራሴ ሳይቀር እህቶቼ የምርም እህቶቼ እንዳይደሉ ሊያሳምኑኝ የደፈሩ አሉ። በእናቴ ሆድ ሳላ ጀምሮ የማዉቀዉን፣ እሹሩሩ ብዬ
ያሳደግሁትን የታናሼን ታናሽ ሳይቀር ወንድሜ እንዳይደለ
ተወራርደዉብናል፡፡

“ገና ለገና ሰዉ አወራ ተብሎ...” ስል፣

“ዉብርስት!” ብላ ጮኸችብኝ። እንደገና ጸጥ አሰኘችኝ፡፡ ትንፋሼን ሳይቀር ነዉ የዋጥሁት፡፡ የምወዳትን ያህል እንደ ታላቅነቷ ደግሞ እሰማታለሁ፡፡እታዘዛታለሁ። አሁንም ወደ ቤት እንድገባ በዓይኗ ስትገፈትረኝ፣ ያለ ምንም ወለም ዘለም ነዉ ሹክክ ብዬ የገባሁት። በበኩሌ ጃሪም ዓይን ዓይኔን እያየ በዚህ በዚህ ምክንያት ነዉ የተጠራጠርሁት ቢለኝማ፣
አስተካክየለት የልቡን ባደርስለት ደስታዉንም አልችለዉ። እንግዲህ ምን ማድረግ እችላለሁ? እሱን ራሷ እህታችን እንደ ፍጥርጥሯ ታድርገዉ! ከፈለገች አባብላ፣ ካልሆነ አስፈራርታ፣ ያም ቢቀር ተደራድራ ወደ ቤት ትመልሰዉ ይሆናል። ወዲያዉም እኮ እኔ ራሴ የራሴ ራስ ምታት ያለብኝ
ሰዉ ሆኛለሁ።

በራሴ ቡዳ የተሰለቀጥሁ ብኩን ሴት አይደለሁ? የራሴዉ ጣጣ ይበቃኛል፡፡

ልክ ስገባ የእጅ ስልኬ እሪ ብሎ እየጠራኝ ደረስሁበት፡፡ ዓይኔን ወርወር አድርጌ ስመለከተዉ፣ አሁንም ለስንተኛ ጊዜዉ እንደሆነ እንጃለት ባልቻ እየደወለ መሆኑን አየሁ። አላደርገዉም እንጂ ባነሳዉ ግን ምን ሊለኝ
ኖሯል? መቼም እንደ ንጹሕ ሰዉ እንዲያ በሩ የመብረቅ ድምፅ
እስከሚወጣዉ ድረስ ከደፉ ጋር አላትሜባቸዉ ከመጣሁ በኋላ፣ ከሊቀ መንበሩ ጋር ሳይቦጭቁኝ የቀሩ አይመስለኝም። ምን ብለዉኝ ይሆን በማርያም? በተለይ ባልቻ እንዴት ይሳቀቅብኝ ይሆን? ስለተጫወትሁበት
ሕይወቴ በሰማ ጊዜ ሰማይ ምድሩ አይዞርበት ይሆን? አንገቱን ነዉ ያስደፋሁት። «በሰዉ መመካት አይገባም፣ ከተመካሁ ግን ማን እንደ ዉብርስት ብሎ አፉን ሞልቶ በኩራት እንዳላወራልኝ ሁሉ፣ ይኼን
ጉዴን ባወቀ ጊዜስ መሸሽጊያ አያጣብኝ ይሆን? እንኳንስ ለእሱ ቀርቶ በሩቁ ለሚያዉቀኝ ሁሉ ማፈሪያ ሆኛለሁ በቃ።

ከዚህ በኋላ ያየኝ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ግቢ እንደ ገባች ዉሻ ቢያሯሩጠኝ፣ የማልፈርድበት መሆኔን እያሰብሁ ሳለ ኩልል የሚል እንባዬን ለማበስ
አንድ መዳፍ ጉንጬ ላይ አረፈብኝ። ማን አጠገቤ እንዳለ ለማወቅ ግን ዓይኔን መግለጥ አይጠበቅብኝም፡፡ እመዋ ናት። ልጇ በተክሊል ከብሬ
የምታይበት ቀን አልደርስልሽ ብሏት ስትጓጓ፣ ተበላሽቼ ያሳቀቅኋት እናቴ ናት በርኅራኄ አጠገቤ የቆመችልኝ፡፡

እመዋ”

“ንገሪኝ ም'ሆነሻል?”

“አዋረድሁሽ አይደል?” አልኋት፣ እግሯ ሥር እየወደቅሁ።
አላቃናችኝም፡፡ ይልቁንም በትክክሌ በዘፈቀደ ተቀምጣ፣ አንገቷ ሥር ሸሸገችኝ፡፡

“አንቺ እኔን? ምናርገሽ?”

“አፈርሁኝ። አሳፈርሁሽ። ሐፍረቴን ደግሞ አወቀሽብኛል፣ አርግዣለሁ። ማሪኝ እመ”

“ቆይ እስኪ...”

“ከዚህ በላይ ምን ልበድልሽ እችላለሁ? ባስቀመጥሽኝ ቦታ አልተገኘሁም እኮ። እንዳሳደግሽኝ፣ እንደ ጠበቅሽኝ መቼ ተገኘሁ? ምንኩስናም
ተክሊሉም ቢቀር፣ እንደ ባህሉ እንደ ወጉ እንኳን እልል ያላስባልሁበት፤ የትዳር አጋሬ ይኼ ነዉ ብዬ ካላስተዋወቅሁሽ፣ ‹የልጄ አባት ይኼ ነዉ ብዬ ከማልናገርለት ሰዉ ነዉ እኮ ያረገዝሁት”

“ከእሸቴ ማለትም አይደል?”

“እ?”

እሸቴ ነዉ ያለችዉ? ቆይ እሷ የማታዉቀዉ፣ እኔ ምን እነግራታለሁ ከዚህ ሌላ? ድርቅ አድርጋ ነዉ ያስቀረችኝ፡፡ ደግሞ ስሙን በመስማቴ እንደገና ሽቅብ ሽቅብ አለኝ፡፡ አቅለሸለሸኝ፡፡ ቅርንት፣ ክርፍት አለኝ፡፡

“እሽቴን ደግሞ የት አወቅሽዉ?” አልኋት፣ እንደ ምንም ትንፋሽ ወስጄ።

“ተጣልተሽዋል ለካ?”

“ማን? ነገረሽ?”

“እሸቴ። በእርግጥ ስለጠባችሁ እንኳን ምንም ያለኝ የለም። የራሴዉ ግምት ነዉ። ብቻ ይኼዉ ኹለት ሦስት ወር ያልፈዋል፤ ተመላልሶ እኔን ያልጠየቀበት ዕለት አልነበረም። ግሩም ልጅ ገጥሞሻል። ቡሩክ ልጅ!”

“አይ ቡሩክ ልጅ'ቴ! ወይ አለማወቅሽ!” አልኋት፣ በማሽሟጠጥ።የሴተኛ አዳሪ ጭን ሱሰኛ መሆኑን ብነግራት ቅስሟ እንዳይሰበር ፈራሁላት። እንዳልተወዉ ደግሞ ለእሱ ያላት ግምት አናደደኝ፡፡ ስለዚህ
ካልሁት አይቀር፣ ገመናዉን አፍረጥርጬ ልናገርለት ይገባል።

“ለመሆኑ ምን አጣላችሁ?”

“እንደምትገምቺዉ አይደለም ልጁ። እንዲሁ በቆዳዉ ስታይዉ ቡሩክ መስሎሽ ይሆናል እንጂ ራሱ ተልከስክሶ እኔንም ጽሞና አልባ ያደረገኝ እሱ ነዉ”

«ማን? እሽቴ?”

“እመዋ አፈር ስሆንልሽ”
👍23😁2🥰1
እ?”

"ስሞትልሽ ስሙን አትጥሪብኝ!”

“እንደዚያ ያለ ልጅ እንኳን አይመስልም። ይሁንና አሁን ግን የት ነዉ ያለዉ? ብቅ ካለ እኮ ዉሎ አደረ”

“የት አዉቄለት”

“ምንድነዉ የት አዉቄለት ብሎ ነገር? ይሁንና የቅድሟን ነገር የት
አደረግሻት? እስኪ አምጫት”

“የቷን ነገር?”

“እህእ? ቅድም እዚያ ከበዓታ ስንለያይ እቤት አኑሪልኝ ብዬም
አልሰጠሁሽ?”

“እ...” ብዬ ጎስጉሼ አኑሬበት ከነበረዉ የራሷ አልጋ ትራስጌ ሥር
አዉጥቼ ሰነዘርኩላት፡፡ አልተቀበለችኝም፡፡

“ያንቺ ነዉ” አለችኝ፣ እኛ እያለን ራሷ ወደ ጀመረችዉ የምሳ ጉድ ጉዷ እየተመለሰች፡፡ “ታዲያ አደራሽን ምንድነዉ ቅብጥርሴ እንዳትጠኝ። እኔ ምኑንም አላዉቅልሽም። ስጭ ነበር የተባልሁት፣ ይኼዉ ሰጥቼሻለሁ።
አበቃሁ” በእራፊ ጨርቅ የተጠቀለለች ትንሽ ነገር መሆኗን ቀድሞዉንም ስትሰጠኝ
ኣስተዉያለሁ፡፡ ምን እንደሆነች ለማየት ገለጥ ባደርጋትም፣ ጥቅልሉ ስለበዛ ፍሬ እቃዋን ቶሎ ልደርስበት አልቻልሁም፡፡ ስቀበላት እምነት መስላኝ ነበር። አይደለችም ማለት ነዉ? በዚያ ላይ ስንት ዙር እንደ
ተጠቀለለች! ተርትሬ ተርትሬ ስጨርስ ያገኘሁት ግን ጥፍር እንኳን የማታህል ሚሞሪ ካርድ ብቻ ነበረች፡፡ መጠቅለያ ጨርቁን ባራግፈዉም፣ ከእሷ ሌላ ምንም የለም። እመዋ ደግሞ እንዳልጠይቃት ቀድማ መንገዱን
ሁሉ ዘጋግታብኛለች፡፡ ምን ቸገረኝ ብዬ ወደ ሞባይሌ ቀፎ ከተትኋት።

ይቀጥላል
👍24
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....ኢንጆልራስ ጎንበስ ብሎ የራሣውን ጭንቅላት ቀና ካደረገ በኋላ ግምባሩን ሳመው፡፡
መሞቱን በመርሳት በጥንቃቄ ያልያዘው እንደሆነ የሚያምመው ይመስል ቀስ ብሎ በክርኑ ደግፎ ቀና አደረገው፡፡ የሟቹን
ኮት ካወለቀ በኋላ የሚደሙትን ቀዳዳዎች ለተመልካች አሳየ።

«ይሄ ነው ባንዲራችን!»

ነጭ አንሶላ አምጥተው የመሴይ ማብዩፍን አስከሬን ሸፈኑት:: ስድስት ሰዎች ጠብመንጃዎቻቸውን ከስር አጋድመው ሬሣውን ከዚያ ላይ ካሳረፉ በኋላ ወደ ምድር ቤት በዝግታ ወስደው ከትልቅ ጠረጴዛ ላይ አጋደሙት፡፡ ሰዎቹ በሚፈጽሙት ተግባር ቅዱስነት በመዋጥ አደገኛ ሁናቴ ውስጥ
መሆናቸውን ጨርሰው ረሱ::

አስከሬኑ ከዣቬር ከታሰረበት ግንድ አጠገብ ሲያልፍ ኢንጆልራስ
ሰላዩን አናገረው::

«የምትቀጥለው አንተ ነህ::»

በዚህ ጊዜ ብቻውን የጥበቃውን ተግባር ያከናውን የነበረው ጋብሮች ሰዎች ከምሽጉ ውስጥ ሲገቡ ውልብ አለው:: በድንገት ጩኸት ተሰማ::

‹‹ተጠንቀቁ!»

የአድማው መሪዎች በሙሉ ዘልለው ወደ ውጭ ወጡ:: የሚያባክኑት ጊዜ አልነበራቸውም:: ወታደሮች ሳንጃቸውን ወድረው ከምሽጉ ሲገቡ ተመለከቱ፡፡

ያቺ ሰዓት ወሳኝ ነበረች:: ምሽጉ በንጉሡ ወታደሮች ተወረረ::
በመጀመሪያ ዘልሎ የገባው ወታደር ከውስጥ የነበረ አንድ ሰው ግምባሩን ብሎ ጣለው:: ገዳዩ ወዲያው በጠላት ወገን ወታደር ተገደለ:: አሁንም ሌላ
ወታደር ከርፌይራክን ከመሬት ስለዘረረው እንደወደቀ «እርዱኝ» እያለ ጮኸ፡፡ በዚያው ወቅት እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ ወታደር ጋቭሮች ከነበረበት ክፍል ገባ፡፡ ጋቭሮች ጠብመንጃዋን ከዣቬር ወደ ወታደሩ አዙራ ለመተኮስ
ቶሎ ብላ ቃታውን ሳብ አደረገች:: ግን ምን ይሆናል ዣቬር ጠብመንጃውን ሲሰጥ ለካስ ጥይት አላጎረሰው ኖር ፀጥ አለ፡፡ ወታደሩ ከት ብሎ ሳቀ፡፡
ሳንጃውን ወድሮ ወደ ልጁ ሄደ::

ወታደሩ ልጁ ዘንድ ከመድረሱ በፊት ከኋላው ስለተመታ በአፍጢሙ ተደፋ:: ወዲያው ከርፌይራክን የመታው ወታደር ሲወድቅ ታየ፡፡ ሁለቱን
ሰዎች የገደላቸወ ማሪየስ ነበር፡፡
ማሪየስ የመጀመሪያውን ውጊያ በሩቁ ሆኖ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ
ነበር ያየው:: በሁለተኛው ግን የጋብሮችን ሕይወት በመጀመሪያ ሲያድን ጓደኛውን ቀጥሎ ነው ነፃ ያወጣው፡፡ ኩርፌይራክ ከመሬት ወደቀ እንጂ አልተመታም ነበር፡፡

ወታደሮቹ ከምሽጉ ሁለት ሦስተኛ የሚሆነውን ክፍል ከቁጥጥራቸው
ሥር አውለዋል፡፡ በጣም ወደ ውስጥ ዘልቀው ለመግባት ግን አልደፈሩም:: ምናልባት አንድ ዓይነት ወጥመድ ቢኖር ብለው ተጠራጥረዋል። በዚያ !
አካባቢ ይበራ የነበረው መብራት እስከ ውስጥ ዘልቆ አያሳይም::

አንድ ወታደር ማሪየስን ለመጣል ሲያነጣጥር ድንገት ከመሀል አንድ ሰው በመግባቱ የእርሱን እጣ ሰውዬው ወሰደ:: ወዲያው በድንገት አንድ በጣም የሚጮህ ድምፅ ተሰማ::

«እጃችሁን ስጡ ፤ አለበለዚያ ምሽጉን እንዳለ እናቃጥለዋለን፡፡»

አድምኞቹ ሁሉ ድምፁ ወደ ተሰማበት አቅጣጫ ፊታቸውን አዞሩ፡፡ ማሪየስ ከየት መጣ ሳይባል ይህን ያለውን የሃምሣ አለቃ ስለጣለው ምሽጉ ከመጥፋት ዳነ፡፡

አድመኞቹ በሙሉ ማሪየስን ከበቡት:: ኩርፌይራክ ከወደቀበት ተነስቶ ከአንገቱ ላይ ተጠመጠመ
«እንዴት ያለ አጋጣሚ ነው» አለ ኮምብፌሬ::

«ጥሩ ጊዜ ደረስክ» አለ ቦስዩ ቀጠለና::

«አንተ ባትደርስ ይህን ጊዜ በሕይወት የለሁም» አለ ከርፌይራክ።

«እኔ ደግሞ ይህን ጊዜ በአፍጢሜ ተደፍቼ ነበር» አለ ጋቭሮች ቀጥሎ፡፡

ወዲያው አንድ ድርጊት በመፈጸሙ ደስታቸው በሀዘን ተለወጠ። ከመካከላቸው በጣም የሚወዱትና የሚያደንቁት አንዱ ጓደኛቸው ተሰወረ። ከቁስለኛ መካከል ፈለጉት:: ከዚያ አልነበረም:: ከሞቱት መካከል አዩት ከዚያም አልነበረም፡፡ ተማርኳል ማለት ነበር፡፡

«ወንድማችንን ወሰዱት፤ እኛ የእነርሱን መኮንን እንደያዝን ሁሉ
እነርሱም ጓደኛችንን ያዙት ማለት ነው:: በሰላዩ ላይ ስለምንወስደው
እርምጃ ወስነናል?» ሲል ኮምብፌሬ ኢንጆልራስን ጠየቀው፡፡

«አዎን» አለ ኢንጆልራስ የኮምብፌሬን ትከሻ እየነካካ፡፡ «ሆኖም የሰላዩ ደም የጓደኛችንን የዣን ጥሩቬርንን ደም አያህልም፡፡»

«እንግዲያውማ» አለ ኮምብፌራ «መሐረቤን ከጠመንጃዬ ጫፍ
አስሬ ልውጣና ሰላዩን በጓደኛችን እንዲለወጡን ልጠይቅ::»

«ስማ» ብሎ ኢንጆልራስ ሲናገር ከውጭ አንድ ድምፅ ተሰማ፡፡
የወንድ ድምፅ ነበር::

«ፈረንሣይ ለዘላለም ትኑር!»

የጓደኛቸው ድምዕ እንደሆነ አወቀ፡፡ ጥይት ተተኩሰ፡፡ ከዚያም ሁሉም ነገር እርጭ አለ::

«ጓደኛችንን ገደሉት!» አለ ኮምብፌሬ:: ኢንጆልራስ ወደ ዣቬር ዞር ብሎ «ጓደኞችህ አሁን አንተን ነው የገደሉት» አለው::

አድመኞቹ ሁሉ አሁን ከቤት ወስጥ ገብቷል:: ማሪየስም
ተከትሉኣቸው ሊገባ ሲል «መሴይ ማሪየስ» ተብሎ ስሙ ሲጠራ ሰምቶ በመደንገጥ ዞር አለ፡፡ ከሁለት ሰዓት በፊት ኮዜትን እየጠበቀ ሳለ ከአጥር ውጭ ሆኖ የጠራው ድምፅ እንደሆነ አውቋል፡፡ ማን እንደሆነ ለማወቅ
ፊቱን ቢያዞርም መለየት አልቻለም:: «እዚህ ነኝ» አለ ያው ድምፅ በጣም የደከመ በመምሰል፡፡

መሬት ለመሬት እየተንፏቀቀ የሚመጣ ሰው በሩቁ ተመለከተ፡፡
መብራት ካለበት ሲደርስ የሴት ሸሚዝ የለበሰ ሰው መሆኑን አየ:: ከስር የተቀዳደደ ሱሪ ታጥቋል፡፡ ጫማ አላጠለቀም፡፡ ይህ ፍጡር ማሪየስ ከነበረበት ሲደርስ የገረጣ ፊቱን ቀና አደረገ፡፡

«አታውቀኝም?»
«የለም»
«ኢፓኒን፡፡»
ማሪየስ ቶሎ ብሎ ወደ መሬት አጎነበሰ፡፡ እውነትም ያቺ እድለቢስ
ኢፖኒን ነበረች፡፡ እንደ ወንድ ነው የለበሰችው::
«እንዴት መጣሽ?» ከዚህ ደግሞ ምን ትሠሪያለሽ?
‹‹መሞቴ ነው» ስትል መለሰችለት::
ማሪየስ ደንግጦ «ተመትተሻል እንዴ?» ሲል ጠየቃት::
ከመሬት ብድግ ሊያደርጋት ቀኝ እጁን ከወገብዋ ስር አስገባ፡፡ ብድግ ሲያደርጋት እጅዋ ተዝለፈለፈ:: የማቃሰት ድምፅ አሰማች፡፡
«አሳመምኩሽ?»
«ትንሽ»
«ምነው እጅሽ ዛለ?» ብሎ" ሲያየው በጥይት ተመትቷል፡፡
«ቆስሎአል፧ አይደለም?»
«አዎን፡፡»
«ማን መታሽ?»
«ከጥቂት ጊዜ በፊት ጠብመንጃ ተደቅኖብህ ልትመታ ስትል አንድ
ሰው ከመሀል መግባቱ ትዝ ይልሃል?»
«አዎን፣ አስታውሳለሁ::»
የእኔ እጅ ነው ጣልቃ የገባው::
የማሪየስ ልብ ከሁለት የተሰነጠቀ መሰለው:: ነገሩ አልገባውም::
ምነው እንደዚያ አደረግሽ! ምስኪን! ብቻ ቁስሉ ለክፉ አይሰጥሽም።
ለማንኛውም ከውስጥ አስገብቼ ላስተኛሽ፡፡»
እጄ ብቻ እኮ አይደለም የተመታው:: ጥይቱ በእጄ አልፎ ከብብቴ ጥቂት ዝቅ ብሉ ወደ ወገቤ በመግባቱ ቀስፎ ይዞኛል» አለች በኃይል ለመተንፈስ እየታገለች::

«ስለዚህ ወደ ውስጥ መግባቱ ዋጋ የለውም:: አሁን ብቻ ከአጠገቤ ቁጭ ብለህ አጫውተኝ፡፡ ጨዋታህ ከሐኪም እርዳታ ይበልጥብኛል፡፡»

ትእዛዝዋን ተቀብሎ እግሩን በመዘርጋት ከአጠገብዋ ቁጭ አለ።

ጭንቅላትዋን ከጉልበቱ ላይ አሳረፈች:: ቀና ብላ ሳታየው «እፎይ ተመስገን እንዴት ይመቻል? ምን ዓይነት ደግ ሰው ነህ! በቃ! ሕመሙ ተቀነሰልኝ
ስትል ቀባጠረች፣::

ከዚያም ለጥቂት ጊዜ ፀጥ አለች:: ቀስ ብላ ፊትዋን ወደ ማሪየስ
አዙራ ቀና ብላ አየችው::

«አስቀያሚ ናት ነው ያልከው፤ አይደል? » ንግግርዋን በማቆም ጥቂት ዝም ካለች በኋላ እንደገና ቀጠለች::
👍19
«መቼስ አሁን አልቆልሃል:: ከዚህች ምሽግ ማንም በሕይወት
አይወጣም:: እኔ ነኝ፧ ከዚህ እሳት ውስጥ የጨመርኩህ:: እርግጠኛ
ነኝ አንተም ትመታለህ:: ሆኖም ሰውዬው ጠብመንጃውን እነጣጠር ሊገድልህ ሲል እጄን አፈሙዙ ላይ በማድረግ አዳንሁህ:: ይህንንም ያደረግሁት
ከአንተ በፊት ለመሞት ፈልጌ ነው፡፡ ከተመታሁ በኋላ በደረቴ እየተንፏቀቅሁ ከዚህ ስመጣ ማንም አላየኝም፡፡ ማንም ደግሞ ከወደቅሁበት አላነሳኝም::
አንተን ነበር የምጠብቀው:: ነገር ግን ከወደቅሁበት እንደማትመጣ አወቅሁ፡፡በመካከሉ እኔ በጣም ተሰቃየሁ፡፡ አሁን ግን ተሽሎኛል:: ከቤትህ መጥቼ ሰውነቴን አንተ ቤት ባለው መስታወት ያየሁበት ቀን ትዝ ይልሃል? ደግሞስ መንገድ መገናኘታችን ትዝ ይልሃል? አንተ እንኳን አንድ መቶ ሱስ
ስትሰጠኝ «ገንዘብህን አልፈልግም ብዬ እንኳን መለስኩልህ! ለመሆኑ ገንዘቡን
መሬት ስጥለው መልሰህ አነሳኸው? ሀብታም ስላልነበርክ መቼስ አትተወውም፡፡ ታዲያ መሴይ ማሪየስ ፤ ሁሉንም አስታወስክ? አቦ እንዴት
ደስ አለኝ! ሁላችንም ልንሞት ነው::
ዓይንዋ ተቅበዘበዘ፡፡ አሳብዋ ተንቀዋለለ:: እጅዋን ሊጠቀልልበት ከደረትዋ አካባቢ ሸሚዝዋን ቀደደ:: ደረትዋን ሲገልጥ ጥይት የገባበት ቦታ
በግልጽ ታየ:: ደም ይወጣው ነበር፡፡ ማሪየስ ያቺን እድለቢስ ልጅ ዝም ብሎ አፍጥጦ አያት::

«ወይኔ» ስትል በድንገት ጮኸች፡፡ «ሕመሙ እንደገና መጣ፡፡ ምነው
አፈነኝሳ!» ከለበሰችው ልብስ አንዱን ክፍል አፍዋ ውስጥ በመጉሰር ንክስ አደረገችው:: እግሮችዋ ተንቀጠቀ፡፡

«እባክህን አትሂድ» አለችው:: «አሁንማ ረጅም ጊዜ አይሆንም:: :

ብድግ ብላ ቁጭ አለች:: ድምፅዋ ግን እየሰለለ ሄዶ ውጪ ነፍስ ግቢ
ነፍስ ሆነ:: እንግዳ በሆነ ድምፅ በማቃሰት ትናገር ጀመር፡፡

«ስማ፤ ለአሞኝህ አልፈልግም:: ኪሴ ውስጥ የአንተ ደብዳቤ አለ::
ትናንትና እንድሰጥህ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ግን እኔ ዘንድ አቆየሁት:: ላገኝህ አልፈልግሁም ነበር:: ምናልባት ቶሉ ቶሎ ስንገናኝ ደስ አይልህ እንደሆነ ብዬ ነው:: ሆኖም ተገናኘን አይደል? ደብዳቤህን ውሰድ::»

በሚደማው እጅዋ ማሪየስን እጅ አፈፍ አደረገችው፡ የቁስሉ ሕመም
አልተሰማትም:: እጁን ይዛ ከኪስዋ ውስጥ ጨመረችው:: ኪስዋ ውስጥ የነበረውን ወረቀት በመንካቱ፡ ደብዳቤ እንዳለ ማሪየስ አመነ::

«ውሰደው » አለችው::

ማሪየስ ደብዳቤሁን አወጣ:: የደስታ ምልክት የፊትዋ አሳየችው::

«ለስቃዩ ስትል አሁን ቃል ግባልኝ::»

«ምን ብዬ?»ሲል ማሪየስ ጠየቃት::

«ቃል ግባልኝ፡፡»

«ቃሌን ሰጥቻለሁ፡፡››

«ከሞትኩ በኋላ ግምባሬን እንድትስምልኝ ቃል ግባልኝ፣ ስትስመኝ ደግሞ ይሰማኛል፡፡»

ማሪየስ ጉልበት ላይ ተደፋች፡፡ ዓይንዋን ጨፈነች፡፡ ያቺ ምስኪን
የሞተች መሰለው፡፡ ኢፓኒን ሳትነቃነቅ ዝም ብላ ቆየች፡፡ ማሪየስ «አሁንስ የዘላለም እንቅልፍ ወስዷታል ብሎ ሲያስብ ነቅነቅ አለች፡፡ ዓይንዋን ለመግለጥ ሞከረች፡ የሞት ጥላ አጥልሎባታል፡፡ ከዚያ በዝግታ ከወትሮው በተለየ ድምፅ አናገረችው፡፡»

«ማሪየስ ከአንተ ፍቅር እንደያዘኝ አምናለሁ፤ አንተ ግን ይህን ታውቅ
ኖሮአል?»

ፈገግታ ለማሳየት ሞከረች፤ ግን አልቻለችም፣ ነጐደች፤ ለዘላለም
ሄደች፡፡

ማሪየስ ቃሉን አከበረ፡፡

የቀዘቀዘውን ግምባርዋን ምጥጥ አድርጎ ሳመው፡፡ ነገር ግን ኮዜትን መክዳቱ አልነበረም፡፡ ያንን የተከፋ ነፍስ ለመሰናበት የፈጸመው ተግባር ነበር፡፡

ደብዳቤው ትዝ አለው:: ለማንበብ ቸኮለ፡፡ ወዲያው ልጅትዋ እንደ
ሞተች ደብዳቤውን ገልጦ ለማየት ጓጓ:: ይኸው ነው የሰው ልጅ ጠባይ።ለእርሱ የሚሆን ምን ነገር እንዳለ ለማወቅ ይቸኩላል፡፡ ከመሬት ላይ በዝግታ አስተኝቶኣት ከዚያ ተነስቶ ሄደ::

የሻማ መብራት ወደ ነበረበት ምድር ቤት ወረደ:: በሚገባ የታሸገ አነስተኛ ደብዳቤ ሲሆን እሽጉ የሴቶች ጥንቃቄ የታከለበት ይመስላል።

በፖስታው ላይ የተጻፈው አድራሻ የራሱና የጓደኛው የከርፌይራክ ነበር። ቶሎ ብሎ ፖስታውን ቀድዶ ማንበብ ጀመረ::

«የእኔ ፍቅር፣ የሚገርምህ ነው፤ አባዬ አሁኑኑ እንድንሄድ ይፈልጋል። ዛሬ ማታ ሆም አርሜ ከተባለ ሥፍራ እንሄዳለን:: በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከእንግሊዝ አገር እንገባለን፡፡ ኮዜት፣ ሰኔ 4፡፡»

ደብዳቤውን ከሳመው በኋላ አጣጥፎ ፖስታው ውስጥ ጨመረው። የፍቅርዋን ጽናት በማረጋገጡ ደስ አለው:: ሁልጊዜም ቢሆን የሌላው ወገን
ፍቅር ብርታትና ጽናት ማወቅ ያስደስተናል፤ ለመወደዳችን ማረጋገጫ ነውና::

«መሄድዋ ነው ፤ አባትዋ ይዟት ሊሄድ ነው:: አያቴ ደግሞ እንድንጋባ አልፈቀዱም፡፡ ምንም የተለወጠ ነገር የለም» ሲል እርስ በራሱ ተነጋገረ፡፡ እንደ ማሪየስ ያለና በቅዠት ዓለም ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ የዚህ ዓይነት
ሁናቴ ሲገጥማቸው በሀዘን ተጨማልቀውና ተስፋ ቆርጠው የማይሆን መንገድ በመምረጥ ከማይሆን መደምደሚያ ላይ ይደርሳሉ፡፡ ሕይወት መሯአቸው በቶሎ መሞትን ይመርጣሉ፡፡ ይህም በመሆኑ ማሪየስ ሁለት
ነገሮችን ብቻ መፈጸም እንዳለበት ይወስናል፡፡ ይኸውም ስለመሞቱ ለኮዜት መግለጽና የመጨረሻውን የስንበት ቃል በመልእክተኛ መላክና የዚያችን የምስኪን የኢፓኒን ወንድም ማለት የሚስተር ቴናድዩ ወንድ ልጅ ከዚያ
አስከፊ አደጋ ማውጣት ነበር፡፡
የማስታወሻ ደብተሩን ከኪሱ አወጣ፡፡ አንድዋን ቅጠል ቀድዶ
የሚከተለውን ጻፈ::

«ጋብቻችን አልሆነም:: አያቴን ስጠይቃቸው እንድንጋባ አልፈቀዱም:: እኔ እንደሆነ ምንም ዓይነት ሀብት የለኝም:: አንቺም ብትሆኚ ከእኔ አትሻይም::
ወደ ቤት መጥቼ ነበር፧፧ ግን አላገኘሁሽም:: ምን ብዬ ቃል እንደገባሁልሽ
የምታውቂው ነው:: ቃሌን አከብራለሁ፤ እሞታለሁ፣ እወድሻለሁ፡፡ ይህን
ደብዳቤ ስታነቢ ነፍሴ ከአጠገብሽ ትሆናለች፤ እናም በፈገግታ ታይሻለች፡፡»
ደብዳቤውን የሚያሽግበት ፖስታ አልነበረውም፡፡ ስለዚህ ወረቀቱን
አጣጥፎ አድራሻዋን ጻፈበት:: ማስታወሻ ደብተሩን ወደ ኪሱ መለሰ፡፡ ከዚያም ጋብሮችን ጠራው:: ልጁ እየሮጠ ወደ ማሪየስ ሄደ:: «ውለታ
እንድትውልልኝ ብጠይቅህ እሺ ትለኛለህ?» ሲል ማሪየስ ልጁን ጠየቀው::
«እንዴታ» ሲል ልጁ በፈገግታ መለሰለት፡፡ «እግዚኣብሔር
በሚያውቀው ኣንተ ባትደርስልኝ ኖሮ አሁን እኮ የሞትኩ ሰው ነበርኩ፡፡»
«ይህን ደብዳቤ ታየዋለህ?»
«አዎን፡፡»
«እንካ ያዘው:: በቶሎ ከዚህ ምሽግ ውጣና ሂድ::» ጋቭሮች በመገረምና
በመረበሽ ፀጉሩን አከከ፡፡
«ነገ ጠዋት ደብዳቤውን በአድራሻው ለኮዜት ስጥልኝ::»
እስከ ነገ ምሽጋችንን ይይዙታል፡፡ ታዲያ ሲይዙት እኔ ከዚሁ ለመሆን
እፈልጋለሁ አለ ልጁ በኩራት መንፈስ፡፡
«እስኪነጋ ድረስ ሁለተኛ ምሽጋችንን አያጠቁም:: ስለዚህ ምናልባትም እስከ ነገ እኩለ ቀን ድረስ ምሽጋችን ከእጃችን አትወጣም::»

«እሺ እንግዲያውስ» ሲል ልጁ መለሰ፡፡

ልጁ በሩጫ ከዚያ ወጥቶ ሄደ:: ከዚያ ሲሄድ አንድ አሳብ ነበረው::
ግን ለማሪየስ የነገረው እንደሆነ የሚቃወመው ስለመሰለው አሳበን ሳይገልጽ ነው የሄደው:: አሳቡም ይህ ነበር፡፡

«እኩለ ሌሊት እንኳን አልሆነም:: ኮዜት ያለችበት ሰፈር ደግሞ
እስከዚህም ሩቅ አይደለም:: ደብዳቤውን አሁኑኑ እወስድላታለሁ፡፡ ከዚያም
በቶሉ እመለሳለሁ::......

💫ይቀጥላል💫
👍212
Forwarded from Eyos bot
💎 የናንተን ቴሌግራም profile 👤 ማን በብዛት እንዳየው ማወቅ ይፈልጋሉ!
profile ፎቶአቹን የሚያየውን ሰው ስም ዝርዝር ለማግኘት እነዲሁም ስንት ጊዜ እንዳየውና የቱን "save" እንዳረገው ለማወቅ ከፈለጉ 👇"START"የሚለውን ይንኩት!
👍4👎2🤔1
Forwarded from 🌹 ፍቅሬን-በ-ግጥም 🌹
🔞. መርየም ብለው ይጠሩኛል...

ወጣት እና መልከ መልካም ልጅ ነበርኩ። በዩኒቨርሲቲ ትምህርት ላይ ሳለሁ ከአንድ የሌላ አገር ወጣት ጋር ተዋወቅኩኝ። እሱም የአገሬ ልጅ ካለመሆኑም ባሻገር በሁኔታዎችም አሰገዳጅነት በብዛት እየተገናኘን አንድ ላይ በመሆን አብረን እናሳልፍ ነበር ።

ከመጀመሪያ የግንኙነት ጊዜያችን ጀምሮ በሃሳብ ደረጃ በደንብ ተግባባን ቀናቶች እያለፉ በመጡ ቁጥር ግንኙነታችን ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቶ መለያየት ከባድ ሆነብን። ይህንን የሰሙ የሀገሬ ልጆች በኔ ላይ ሴራን ይሸርቡ ጀመር። አንድ ቀን ከዶርም በመውጣት ላይ ሳለሁ በጣም የሚዘገንን ነገር ሰሩብኝ። ያን እለት የሆንኩት አስታውሼ መናገር ይከብደኛል። እጅግ ሚሰቀጥጥ ድርጊት ነበር። ከዶርም ስወጣ …see more read
👍7👏2😁21
#ገረገራ


#ክፍል_አምስት


#በታደለ_አያሌው

.....“ያንቺ ነዉ” አለችኝ፣ እኛ እያለን ራሷ ወደ ጀመረችዉ የምሳ ጉድ ጉዷ እየተመለሰች፡፡ “ታዲያ አደራሽን ምንድነዉ ቅብጥርሴ እንዳትጠኝ። እኔ ምኑንም አላዉቅልሽም። ስጭ ነበር የተባልሁት፣ ይኼዉ ሰጥቼሻለሁ።
አበቃሁ” በእራፊ ጨርቅ የተጠቀለለች ትንሽ ነገር መሆኗን ቀድሞዉንም ስትሰጠኝ
ኣስተዉያለሁ፡፡ ምን እንደሆነች ለማየት ገለጥ ባደርጋትም፣ ጥቅልሉ ስለበዛ ፍሬ እቃዋን ቶሎ ልደርስበት አልቻልሁም፡፡ ስቀበላት እምነት መስላኝ ነበር። አይደለችም ማለት ነዉ? በዚያ ላይ ስንት ዙር እንደ
ተጠቀለለች! ተርትሬ ተርትሬ ስጨርስ ያገኘሁት ግን ጥፍር እንኳን የማታህል ሚሞሪ ካርድ ብቻ ነበረች፡፡ መጠቅለያ ጨርቁን ባራግፈዉም፣ ከእሷ ሌላ ምንም የለም። እመዋ ደግሞ እንዳልጠይቃት ቀድማ መንገዱን
ሁሉ ዘጋግታብኛለች፡፡ ምን ቸገረኝ ብዬ ወደ ሞባይሌ ቀፎ ከተትኋት።
ከዚያም በድምፅ ማጫወቻዉ ከፈትሁት፡፡ ከትንሽ የነፋስ እና የወፎች ጺዉጺዉታ በኋላ፤ ማሲንቆ የሚያስንቅ አንቺሆዬ ዓይነት ፉጨት መጣ፡፡

የት ነበር የማዉቀዉ ይኼን ድንቅ ትንፋሽ?

መቼ አጣኋቸዉ! ወይዘሮ ብርሃኔ ናቸዉ፡፡ እሳቸዉ ናቸዉ ትንፋሻቸዉን እንደ ፈለጉ የሚያሽሞነሙኑት። እንኳን በሴት በወንድ እንኳን የማላዉቀዉን፣ ማንኛዉንም ዜማ በፉጨታቸዉ ብቻ ሲያወጡት አያድርስ ነዉ። በዘለሰኛ ጨዋታቸዉ የሁሉን ነፍስ የሚገዙት፣ በሸክላ ሥራ ጥበባቸዉ ሁሉን የሚያስደንቁት፣ ፉጨት እና ሽለላዉን
የሚያዉቁበት፣ ወይዘሮ ብርሃኔ ናቸዉ። አትጠገቤዋ፣ ደርባባዋ ሰዉ! በእርግጥ መጀመሪያ ያወቅኋቸዉ በእሸቴ በኩል ነበር። የእሱ እናት ናቸዉ፡፡ እንደ ጣና ሐይቅ የተረጋጉት፣ እንደ ዥማ ወንዝ የልብ የሚያደርሱት ሴት ናቸዉ በፉጨት የመጡብኝ። ጥሎብኝ አንጎራጓሪ ሰዉ
አይሆንልኝም፡፡ እጅግ አድርጌ እወዳለሁ። በተለይ ዘለሰኛ! ዘለሰኛ ለመስማት ስል ምንም ነገር ቢሆን እተዋለሁ። አሁን አሁን እንዲህ እሸቴ የሚባል ስም በአፍንጫዬ ይውጣ ልል፣ ያኔ ልቤን ወለል አድርጌ
እንድከፍትለት ካደረገበት ብዙ ምክንያቶቹ አንዷ እናቱ ነበሩ።

ልዩ ናቸዋ!

ፉጨቱን ተከትሎ በድምፃቸዉ ደግሞ መጡብኝ። ያ ከእሕልም
ከመጠጥም የሚጣፍጠዉ ዘለሰኛቸዉ!

ኧኧኧኧኧኧ...
ሸክላ ሠሪ አርገህ ሾመኸኛል
የሸክላ ጥበብ ይገባኛል፡፡
ኧኸ

ሸክላ ማለት የእጄ ሥራ
እኔ ደግሞ የእጅህ ሥራ፤
የእጄ ተሰብሮ ብመኝም ሞት
የእጅህን ማትረፍ ግን አወቅህበት!

ኧ ኸ ኧ ኸ ኧ.....

ምንም እንኳን ቀረጻዉ ጥራት ያልሞላለት ሆኖ ሞገዱ እንደሚዋዥቅበት ሬዲዮ ወስድ መለስ ሲያደርገዉም፣ እየደጋገምሁ አጣጣምሁት። ከምኔዉ እንደሆነ እንጃልኝ ብቻ አሁን መረጋጋት ይታይብኛል። አሁን ከፋኝ ብዬ ስነፈርቅ አልነበር እንዴ? ፊቴን ዳበስሁት፤ እንባ የሚባል ጠብታዉ ሳይቀር የለም። ወደ መስታዎት ሮጬ ዓይኔን አየሁት። እንኳንስ ደም
ሊመስል! ልክ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ወደ ነባሩ ቀልቤ ተመልሻለሁ። ያውም ወደ ደስተኛዋ ዉብርስት። ጃሪም የለ፣ እሸቴ የለ፣ እርግዝና የለ
ሁሉም ደህና። ፍጹም ሰላም፡፡

“እመዋ?” አልኋት፣ እንጀራ ይዛ ወደ ሳሎን ብቅ ከማለቷ፡፡

ለወጉ ያህል ብቻ ቀና ብላልኝ፣ ወደ ማዕድ ቤት አልፋኝ ሄደች። ምን ላርግሽ፣ ይልቅ ማቀራረቡን አትረጅኝም? ማለቷ መሰለኝ። ከምኔዉ እንዲህ እንደ ተረጋጋሁ እሷንም ሳይደንቃት አልቀረም።

“ማነዉ የሰጠሽ ግን?” አልኋት፣

እግር በእግር እየተከታተልኳት።
“ማን ይመስልሻል?” አለችኝ፣ ፍርጥም ብላ።

“ብቻ እሽቴ ነዉ እንዳትዪኝ በማርያም”

“እሸቴ የሆነ እንደሆንስ? ስጦታ ሁሉ ያዉ ስጦታ አይደለም ወይ?”
“እህእ?”
ስጦታ ሁሉማ ያዉ አይደለም፡፡ ከእሸቴ ነዉ ማለት ነዉ? እንደ ፈራሁት መልሶ ከፋኝ፡፡ እንደገና ስምጥ ወደ ሆነዉ ድባቴ ዉስጥ ተወርዉሬ ወደቅሁ። መቼም ከእሱ ሌላ የእናቱን ድምፅ ቀርጾ በእናቴ በኩል የሚልክልኝ አይኖርም፡፡ ለዚያዉም ድምፁ ሌሊት ወፍ ጭጭ ሲል በድብቅ የተቀረጸ ነዉ የሚመስለዉ። ስለዚህ አብሮ የሚያድር ሰዉ ነዉ ማለት ነዉ የቀረጻቸዉ፡፡ ያም ሰዉ ከእሸቴ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ እሱ
ነዉ የላከልኝ። እጅ መንሻ መሆኑ ነዉ? የተጣላነዉ በእናቱ ይመስል፣ በዚህ ሊያባብለኝ መሞከሩ የበለጠ እልህ ዉስጥ ጨመረኝ፡፡

እናቱ ሌላ፣ እሱ ሌላ።

ራሴን ግን ታዘብሁት፡፡ ቶሎ የሚከፋኝ፣ ቶሎ የምደሰት ግልብ ሆኜ አርፌዋለሁ ማለት ነዉ በቃ? አሁን ለቅሶ፣ አሁን ሳቅ፣ እንደገና ለቅሶ?
ሰአሊ ለነ ቅድስት!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሐዘንም ሐፍረትም ቀላቅሎ ከመታኝ ይኸዉ ቀናት አለፉ፡፡ ያዉም እንደ ሙጀሌያም እየተሙጀለጀሉብኝ። በእነዚህ ቀናት ሁሉ በእመዋ ቤት ተደብቼ ራሴን አዳመጥሁት። እንደ ወትሮዬ ወደ አደባባይ ሳልወጣ፣
እንደ ድሮዉ በወዳጅ ሳልከበብ፣ እንደ ሁልጊዜዉ ወደ ሲራክ-፯ ማዕከል ሳልመላለስ ዐሥራ አንድ ረዣዥም ቀናት እያለፉኝ ሄደዋል። እንዲሁ አልፎ አልፎ ብቻ ሲልብኝ፣ ክራሬን አንስቼ ለብቻዬ እያንጎራጎርሁ በእናቴ ቤት ሰነበትሁ፡፡

በዚህ ምክንያት እመዋም ሁኔታዬን እያየች ስትብሰለሰል፣ እያሳዘነችኝ መጣች፡፡ ምናልባት ዘወር ብልላት ይቀላት እንደሆነ ብዬ፣ ሲራክ-፯ ለአንዳንድ ተልእኮዎች በማሰብ በምስጢር ቀድሞም ወደ ተከራየልኝ
ምስጢራዊዋ ቤት ደግሞ ሄድሁ። ይቺ ቤት፣ በተልእኮዬ ሂደት መሀል
እንድቀራረባቸዉ የሚያስገድዱ ሰዎች ቢኖሩ ቤቴ ብዬ የማሳያቸዉ ቤት ናት። እንደ ሁኔታዉ፣ እነዚህ ዒላማ የተደረጉ ሰዎች ረዥም ጊዜ እና የተለየ መቀራረብ የግድ የሚፈልጉ ስለሚሆን፣ የቤት ቡና የምጋብዛቸዉ በእመዋ ቤት ባለኝ ክፍል ሳይሆን፣ በዚሁ ምስጢራዊ የኪራይ ቤት ነዉ።

ወደ'ዚህ ቤት እንደመጣሁ፣ እመዋ አዘዉትራ እሸቴ ምን በደለሽ?»
ስትለኝ የሰነበተችዉ ጥያቂ ድንገት ሽዉ አለችብኝ፡፡ ገና ዛሬ፣ አሁን ገና። እንደገና አስብሁበት:: እዉነትስ ግን እሱ ምን በድሎኛል? ምንም። ምንም ወንጀል አጣሁበት። ቆይ እኔ ራሴ አይደለሁ እንዴ፣ ዓለም በቃኝ ብሎ
ከመነነበት የእናቱ ከተማ ሄጄ የተዋወቅሁት? እኔ ባልሄድበት እንኳንስ መበደል፣ ጭራሽ የት ያዉቀኝ ኖሯል? ደረስሁበት እንጂ አልደረሰብኝም እኮ፡፡ ይልቅስ ራሴ ነኝ በገዛ ሕይወቴ የተጫወትሁት። እኔን ማንም አልበደለኝም። ከተበደልሁም የተበደልሁት በራሴ ነዉ። እኔዉ ነኝ ራሴንም እግዚአብሔርንም የበደልሁት። ስለዚህ ራሴን ለካህን ማሳየት
አለብኝ።

ንስሐ ያስፈልገኛል።

ወዲያዉኑ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና፣ ነጠላዬን እንደ ነገሩ አንገቴ ላይ ጥዬ ወደ መኪናዬ ሮጥሁ። ምስጢራዊዋ ቤቴ በአዲስ አበባ ልዩ ሰፈሩ ልደታ በሚባለዉ የምትገኝ ኮንዶሚኒየም ስለሆነች፣ ተዘግቶ እስከሚከፈት
የሚያጉላላኝ የአጥር በር የለብኝም፡፡ ይቺን መከራ ቻይ መኪናዬን ዛሬም ያለቅጥ ረግጬ አበረርኋት። የትራፊክ መብራት የሚባል ለቅጽበት አላስቆመኝም። ንስሐ አባቴ የሚያገለግሉት እዚሁ ልደታ ጎን ባለዉ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቢሆንም፣ በዚህ አመሻሽ ግን እሳቸዉ የት
እንዳሉ አላዉቅም። በቤታቸዉ ሊሆኑ እንደሚችሉ በመገመት ነበር ቀጥታ ወደ መኖሪያ ቤታቸዉ የሄድሁ። እዚያ ስደርስ ግን አጣኋቸዉ።

አቤት ጥድፊያ! ስልክ ቁጥራቸዉ አለኝ አይደል እንዴ?
ደወልሁላቸዉ።
“እዚያዉ ልደታ እኮ ጉባዔ ላይ ነበርሁ። ምናለ ከመድከምሽ ፊት ደዉለሽ ብትጠይቂኝ ኖሮ ልጄ?” አሉኝ፣ በሐዘኔታ፡፡

“ግድየለም፡፡ እዚያዉ ልምጣ ታዲያ?”

“ምን ገዶኝ? ነይ በይ እዚሁ”
👍352
ከምኔዉ እንደ ደረስሁ። ከቅጽሩ ገብቼ፣ ለአርምሞ ወደሚያዘወትሩበት
ሥፍራቸዉ ስሄድ፣ የግላቸዉን የሠርክ ጸሎት ጀምረዉ አገኘኋቸዉ።ፈንጠር ብሎ በሚገኝ ለስላሳ ድንጋይ ላይ ተቀምጩ ጠበቅኋቸዉ።

“መጥተሽ ነወይ ፍቅርተማርያም? እንደምን አምሽተሻል?” አሉኝ፣
ከረዥሙ ጸሎታቸዉ መልስ።

ተመስገን!

ምኑንም ሳላስቀር ዝክዝክ አድርጌ ተናዘዝሁላቸዉ። መቼም ንስሐ ከገባሁ በኋላ እንደማገኘዉ ያለ ዕረፍት በሌላ በምንም አላገኝም፡፡ አረፍሁ። በዚያዉም ላይ፣ በክርስትና እምነት አንዴ ተጸጽቶ ንስሐ የተቀበሉበትን ኃጢአት እያወሱ ማዘን፣ ክህደት እንደሆነ አባቴ ራሳቸዉ ደጋግመዉ
ነግረዉኛል። መሐሪ ነዋ አምላካችን! የሆነዉ ሁሉ ሆኖ አልፏል በቃ። አለቀ፡፡ የተቀበልሁትን ቀኖና መፈጸም እና ስለ ይቅር ባይነቱ ማመስገን
እንጂ፣ ከእንግዲህ ማለቃቀስ አይገባኝም፡፡ አጠፋሁ ይቅርታ ለመንሁ
ይቅርታ አገኘሁ። አበቃ::

ቅልል ብሎኛል።

“ምስጢር ልንገርሽ?” አሉኝ፣ መስቀል ተሳልሜ የንስሐ አባቴን
ይፍቱኝ ብዬ ልሰናበታቸዉ ወደ ጉልበታቸዉ አፌን ሳሞጠሙጥ። ቆም ብዬ ጠበቅኋቸዉ። አፍ አፋቸዉን እያየሁ ለመስማት ብጠባበቅም፣ እሳቸዉ ግን ለማጓጓት ይመስላል፤ ምስጢር ያሉትን ለመናገር ሆነ ብለዉ
አዘገዩብኝ፡፡ እዉነትም ጓጓሁላቸዉ። ለነገሩ ምስጢር መስማት የማያጓጓዉ ማን አለ? ሰዉ በምንም ዓይነት ስሜት ዉስጥ ቢሆን እንኳን፣ ምስጢር
ከተባለ ጆሮዉ መቆሙ የማይቀር ነዉ። ያዉም ከካህን ልብ አምልጦ
የሚገኝ ምስጢር! በጣም ጓጓሁ።

“ቀድሞሻል”

“ማን?”

እሸቴ”

ኧረ በስመ አብ! የዚህን ልጅ ስም የማልሰማበት ቦታ የለም በቃ? በእርግጥ እሳቸዉን እንኳን እሸቴን እንዴት አወቁት ማለት አልችልም። እኔ ራሴ ነኝ የንስሐ አባት ይኑርህ ብዬ እሳቸዉ ዘንድ አምጥቼ እሸቴን ያስተዋወቅኋቸዉ፡፡ እኔ ለስንትና ስንት ቀናት እንደዚያ ቀኑ
ሲጨልምብኝ፣ አጅሬ እሽቴ ቀድሞኝ ንስሐ በመግባቱ አደነቅሁት። የትና የት ጥሎኝ ሄዷል፡፡ በልጦኛል፡፡ የንስሐ አባቴ ግን ጉዴን ያዉቁ ኖሯል ማለት ነዉ? ታዲያ ምነዋ ቀድመዉ ቢነግሩኝ? ቢያንስ ደዉለዉ ልጄ
ጠፋሽብኝ ሊሉኝ አይገባም ነበር? አይዞሽ ብለዉ ማጽናናት
አልነበረባቸዉም?
“አታኩርፊ” አሉኝ፣ የዉስጤን ሁሉ እንደሚያዉቁበት አዉቀዉብኝ::
“ራስሽ እንደምትመጪ ስለማምን ነበር እንዲህ ነዉ እንዲህ ነዉ ሳልል የጠበቅሁሽ። ጸጸት ከዉስጥ ሲሆን አይዶል ዋጋ የሚኖረዉ?”

አሳመኑኝ፡፡ እንኳንስ እንደኔ ላለ ትዕቢተኛ ይቅርና ማንም ቢሆን ጥፋቱን ማመን ያለበት ራሱ ጥፋተኛዉ ነዉ። ጥፋት የሆነዉንና ያልሆነዉን ለይቶ የማስተማር የካህኑ ድርሻ ሲሆን፣ ይኼን ይኼን በድያለሁ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቁኝ ብሎ ካህን ፊት መዉደቅ ግን የኔ ፋንታ ነዉ። ያለበለዚያማ ምኑን ኑዛዜ ሆነዉ? መቼስ እንደ መርማሪ ፖሊስ
አይመረምሩኝ።

እሳቸዉ ልክ ነበሩ። አበጁ!
ክብረ ንጽሕናዬን እንደ ዘበት ማጣቴን ካወቅሁባት ዕለት ጀምሮ እሽቴ በደረሰበት ላለመድረስ ያልሞከርሁት መሸሸጊያ ጭንብል የለም፡፡ እሱም እኔ ያለሁበት ቦታ እንዳይደርስ ያልሠራሁበት ተንኮል የለም። በተለይም ዕለት በዕለት ሊያገናኘን ይችል ከነበረዉ የሲራክ-፯ ማዕከል ያስወጣሁበት
ሴራ ትዝ ብሎኝ ፈገግ አልሁ።
በደንቡ እንደሚታወቀዉ፣ አንድ ሰዉ የማኅበሩ አባል ለመሆን ኹለት መሠረታዊ ቅድመ ግዴታዎች ተቀምጠዉለታል። በቅድሚያ ከጀርባዉ ምንም የቅሰጣ እከክ የሌለበት ክርስቲያን መሆን፣ ሲቀጥል ደግሞ
የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ተገንዝቦ መቀበል ይጠበቅበታል። ከዚያ በኋላ በሕዝብ ዘንድ በግላጭ ከሚታወቁት እና እጅግ ከበሬታ ካላቸዉ የማኅበሩ የአገልግሎት ማዕከላት በአንደኛዉ ገብቶ ማገልገል ይጀምራል።
ይኼ ለማኅበራችን ማኅበርተኞች ሁሉ የሚሠራ ሲሆን፣ ደንቡም
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀጥተኛ ይሁንታ አለዉ። ሕዝብም ሆነ
መንግስት ይኼንን ጠንቅቀዉ ያውቁለታል። ከማኅበሩ ማዕከላት አንዱ፣ የመረጃና ደኅንነት ጉዳይ የሚመለከተዉ ሲራክ፯ ግን እንኳንስ በሰፊዉ ሕዝብ ይቅርና በራሱ በማኅበሩ ማኅበርተኞችም አይታወቅም። በጣም ከጥቂቶች በቀር፣ ሲራክ ፯ን የሚያዉቀዉ ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነዉ።
ስለሆነም የሲራክ ፯ አባል ለመሆን እንደ ሌሎቹ ማዕከላት በምርጫ የሚገኝ አይደለም። ይልቁንም ራሱ ማዕከሉ ነዉ አባሎቹን በሥዉር ከማኅበሩ አባላት መካከል መርጦ የሚመመለምለዉ። ምልመላዉም እጅግ ዘለግ ያለ ሂደት አለዉ። አንድ ዕጩ አባል ወደ ማዕከሉ መመልመል ሲጀመር፣ ቅድሚያ ከአፍ መፍቻ ቋንቋዉ ተጨማሪ፣ ቢያንስ ኹለት የሀገር ዉስጥ ቋንቋዎች እንዲማር ይደረጋል። በኹለተኛነት ደግሞ መደበኛ ሙያዉ ምንም ሆነ ምን ለስድስት ወራት ያህል ወደሚመደበበት
ገጠር ሄዶ በሙያዉ እንዲያገለግል ግዳጅ አለበት። በዚያም ለኗሪዎቹ የሚያበረክተዉ በጎ ሥራ ታይቶ፣ ነጥብ ይሰጠዋል። ያመጣዉ ነጥብ
ከተወደደለት ብቻ ወደ ከተማ ተመልሶ ተጨማሪ የመስክ ልምምድ ይጀምራል፡፡ በእርግጥ የተመለመለዉ ለመረጃ ሰብሳቢነት ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ቢሆንም ባይሆንም ግን ቀጥታ ወደ ታጨበት ንኡስ
ክፍል ዘሎ መግባት የለም።

በሁሉም ምዕራፎች ደግሞ የጎንዮሽ ሥልጠናዎች እና ግዴታዎች አሉ።

ሂደቱ እንደዚህ ቢሆንም፣ እሸቴ የተመለመለዉ ግን በመደበኛዉ የሲራክ ፯ የምልመላ መንገድ አልነበረም። እሱ እንዲያዉም ከነጭራሹም የማኅበሩ አባል አልነበረም:: አባል አለመሆን ብቻም ሳይሆን፣ ማኅበሩን
ከነስሙ ይጠላዉ ነበር። ማንም ያልታደለዉን ዕዉቀቱን ለመጠቀም ሲባል ብቻ፣ በቀጥታ ነዉ የሲራክ ፯ አባል እንዲሆን የተደረገዉ፡፡ እኔም እሱን የመረጃ ማዕከሉ አባል በማድረግ ሂደቱ ላይ እንዲያ ከፍ ዝቅ እንዳላልሁ
ሁሉ፣ ማየት ባስጠላኝ ጊዜ ደግሞ ከሲራክ ፯ ላማስባረር ያልፈነቀልሁት ድንጋይ አልነበረም። በመጨረሻም ተሳካልኝ፡፡ ባልቻ የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ሆኖ የተሾመ ዕለት በቡና ሰዓት ስንጨዋወት፣ የምመኘዉን ዜና አበሠረኝ፡፡

(እሸቴ ወደ ባንቱ ሊሄድ መሆኑን አዉቀሻል ወይ? አለኝ፡፡
‹ እረ በጭራሽ! የት ነዉ ደግሞ ባንቱ?)


(አሃ. ለእሱ እኮ ተነግሮታል። እንዴት አልነገረሽም?)

(የት አባቱ!) አልሁኝ በለሆሳስ፣ ዞር ብዬ ለልቤ ደስታ እያጠጣሁት።
ለይስሙላ እንደማያዉቅ ሆንሁበት እንጂ፣ ለምን ጉዳይ እና ለምን ያህል ጊዜ ባንቱ እንደሚሄድ ሳይቀር ጠንቅቄ አዉቃለሁ፡፡ እንደገና እንደ ዕጩ
አባል ተቆጥሮ የስድስት ወሩን የገጠር የግዳጅ አገልግሎት ለመወጣት፣ በደቡብ ምዕራብ በኩል በምትገኘዉ ባንቱ መመደቡን ሳዉቅ ማንም
አልቀደመኝም፡፡ ባንቱ ከአዲስ አበባ በምን ያህል ርቀት ላይ እንደምትገኝ ሳይቀር ራሴ ከተማዋ ድረስ ሄጄ ለክቼዋለሁ። ምክንያቱም ራሴ ነኛ ወደ'ዚያ እንዲልከዉ ከባልቻ በፊት የነበረዉን የሲራክ፤ ኃላፊ
የወተወትሁት። እንደ ተባለዉም ጓዙን ጠቅልሎ ሄደልኝ፡፡ ነገር ግን
ሳምንት ያህል እንኳን ሳይቆይ፣ ግዳጁን እያቋረጠ ወደ አዲስ አበባ መለስ ቀለስ አበዛ፡፡ የኋላ ኋላ እንዲያዉም ከነጭራሹ አልሄድም ብሎ መቅረቱን
ሰምቼለታለሁ። እንዲችዉ ሲቅበጠበጥ ከራርሞ አሁን ግን አይቼዉ አላዉቅም።

በእርግጥ ግዳጁን ለማቋረጥም ምክንያቱ እኔ እንደ ሆንሁ አላጣሁትም።

“እህእ” ብለዉ ጎሮሯቸዉን ሲጠራርጉ ባነንሁ። ለካንስ የንስሐ አባቴ ከፊቴ ቆመዉ ኖሯል በትዝታ እንዲህ ጭልጥ ያልሁት? ወይ እኔ!

“ሐሳብ ገባሽሳ”

“እሸቴ ሲሉኝ ጊዜ...”

“ልትነግሪኝ የምትፈልጊዉ ነገር አለ ልበል፣ ስለ እሸቴ?”

“ሰሞኑን ድምፁ ለኔም ጠፍቶብኛል። የት እንዳለ ያዉቃሉ? ነግሮዎት ከሆነ”
👍271
“አንቺም አታዉቂም ማለት ነዉ? ይኼዉ ስንት ቀኑ ስልኩንም ስሞክረዉ እምቢ ብሎኛል። ምናልባት የምታዉቂዉ ካለ ብዬ እኔም ልጠይቅሽ አልጠይቅሽ እያልሁ ነበር። አታዉቂማ?”

“ኧረ በጭራሽ። በደህናዉ ይሆን ብለዉ ነዉ?”

“ምኑን አዉቄ ልጄ፤ ምን በላብኝ ልጄን?”

“እረ እንጃልኝ”

“ይሁንና ለመጨረሻ ጊዜ መቼ ነዉ አንቺ ያገኘሽዉ?”

“የዚያዉ ዕለት። ነገሩ የተበላሸበት ጊዜ የተያየን ነን”

“በስመ አብ! ከስንት ከአምስት ወር በፊት?”

“ያዉ እሱማ፣ ያዉ አልፎ አልፎማ እየተደበቀ ያየኝ ነበር። እኔም አልፎ አልፎ እንደሱ”

“እንጂ ይቅር ለማለት አሳስቦሽ አያውቅም?”

“አልፎ አልፎ”

“አልፎ አልፎ?

አልፎ አልፎ ብሎ ጉድ! እንዲያማ ክርስቶስ አምላክ አይደለም የሚሉ ክርስቲያኖችስ የሉም ብለሽ ነወይ? አልፎ አልፎማ ልጅ
የማይወዱ እናቶች፣ የማታሞቅ ፀሐይ፣ የማይመሽ ቀናት፣ የማይቀድሱ ካህናት፣ የማይዘንብ ደመና፣ የማይሞቱ ሰዎች ይታጣሉ ብለሽ ነዉ? አረ አሉ፡፡ ከስንት አንድማ የሚዳሰስስ ሰማይ፣ የሚቀመስስ መርዝ፣ የሚለበስስ
ጨለማ፣ የሚደረስበትስ እንጦርጦስ፣ የሚገመጥስ ድንጋይ፣ የሚሽተትስ
ዉሃ አለ አይደል?”

አፌን ከፍቼ ቀረሁ። ለመሆኑ ገብቶኛል ግን? ምንድነዉ ያሉኝ? ወጣ ወረደ ስለ እሽቴ ነዉ አይደል ያወሩት?

አንዴ የእሸቴ ሐሳብ ስለሞላብኝ፣ ንስሐ አባቴ ያሉት ምንም ሆነ ምን
የገባኝ እሽቴን መፈለግ እንዳለብኝ ብቻ ነዉ። ልቤን ተወግቻለሁ። ምን አግኝቶት ይሆን? በቅጽበት ስንቱን አሰብሁት! እሸቴ ማለት ፈላጊዉ ብዙ የሆነ ባለ ልዩ አእምሮ ልጅ ነዉ። ሌላዉ ይቅርና ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት (NISS) የሚባለዉ የኢትዮጵያ የመንግሥት
የደኅንነት ተቋም በጥብቅ እንደሚፈልገዉ አዉቃለሁ። ቢቻል ቢቻል ወደር በሌለዉ አእምሮዉ ለመጠቀም፣ ያ ካልሆነ ደግሞ ማኅበሩ እንዳይጠቀምበት ሊገድለዉ ያሳድደዉ ነበር። ሁልጊዜም ቢሆን በድብቅ
ጥበቃ የሚያደርጉለት የእኛዎቹ የሲራክ አባላት እያሰናከሉባቸዉ እንጂ የመንግሥት የደኅንነት ወኪሎች ብዙ ጊዜ አንቀዉ ሊወስዱት ሞክረዋል።

አሁን እንዲህ የጠፋዉ ምናልባት በእነሱ እጅ ወድቆ ቢሆንስ?

ወደ መኪናዬ ሽምጥ እየሮጥሁ ሳለ ነበር፣ የንስሐ አባቴን እንኳን
እንዳልተሰናበትኋቸዉ ያወቅሁት፡፡ እንደ ልማዴ በጥድፊያ ወደ ሲራክ፯ አሽከረከርኩ....

ይቀጥላል
👍316👏3
አትሮኖስ pinned «#ገረገራ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በታደለ_አያሌው .....“ያንቺ ነዉ” አለችኝ፣ እኛ እያለን ራሷ ወደ ጀመረችዉ የምሳ ጉድ ጉዷ እየተመለሰች፡፡ “ታዲያ አደራሽን ምንድነዉ ቅብጥርሴ እንዳትጠኝ። እኔ ምኑንም አላዉቅልሽም። ስጭ ነበር የተባልሁት፣ ይኼዉ ሰጥቼሻለሁ። አበቃሁ” በእራፊ ጨርቅ የተጠቀለለች ትንሽ ነገር መሆኗን ቀድሞዉንም ስትሰጠኝ ኣስተዉያለሁ፡፡ ምን እንደሆነች ለማየት ገለጥ ባደርጋትም፣…»
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


የልጅትዋ አድራሻ

ኮዜት ቀኑን ሙሉ እህል በአፍዋ ሳይገባ ከክፍልዋ ውስጥ ተዘግታ
ዋለች፡፡ መሄጃቸው ስለተቃረበ ያንን የነበሩበትን ትልቅ ቤት ለቅቀው ሆቴል ቤት ነበር የገቡት:: ያን እለት የዣን ቫልዥ የመብላት ፍላጎት ከመቼውም ይበልጥ ስለተከፈተ እራቱን በጊዜ እንክት አድርጎ ይበላል።
ኮዜት ከማዕዱ አልቀረበችም፡፡ እራቱን እየበላ ሳለ ሠራተኛው ከአንዴም ሁለቴ፣ ከሁለቴ ሦስቴ ብቅ ጥልቅ እያለች «ኧረ እኔ አላማረኝም፤ አገሩ ተረብሿል፧ ውጊያው ተጧጡፏል አሉ» በማለት ስታናግረው መንፈሱ
ጥቂት ይሽበራል፡፡ ሆኖም እስከዚህም ስሜት አልሰጠውም:: ኮዜትን ይዞ ወደ እንግሊዝ አገር ከሄደ ከዚያ ደስ ብሎት ሊኖር እንደሚችል ያሰላስላል።
ከነበረበት ብድግ ብሎ ነበር ወደ መስኮት፧ ከመስኮት ወደ በር በአሳብ ተውጦ ሲንቆራጠጥ አንድ ነገር አየ፡፡

ተሰቅሎ ከነበረው መስታወት አጠገብ አንድ ጽሑፍ ሳይተጣጠፍ
ከመሬት ወድቆ ስለነበር በመስታወቱ አንጸባራቂነት ከውስጥ በኩል አየው፡፡
ጽሑፉም እንዲህ ይላል፡፡

የእኔ ፍቅር! የሚገርምህ ነው፤ አባዬ አሁኑኑ እንድንሄድ ይፈልጋል፡
ዛሬ ማታ ሆም አርሜ ከተባለ ሥፍራ እንሄዳለን:: በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከእንግሊዝ አገር እንገባለን፡፡ ኮዜት ሰኔ 4»

ዣን ቫልዣ ፈዝዞ ቀረ::
ኮዜት ሀዘን በዝቶባት ስለነበር ለማሪየስ የላከችውን ደብዳቤ ረቂቅ ጽሑፉን ከጻፈችበት ሥፍራ ረስታዋለች::

ዣን ቫልዣ ወደ መስታወቱ ጠጋ ብሎ ጽሑፉን እንደገና አነበበው::
ማመን አቃተው፡፡ ከኮዜት የተለየ መሰለው:: «ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?» ሲል ጭንቀት ያዘው:: ጎንበስ ብሎ ጽሑፉን አነሳው:: በጣም ተረበሸ፡፡ ዓለም ጨለመችበት:: መቼስ በሕይወት ሊደርስ ከሚችል ማንኛውም
አሲቃቂ ነገር ሁሉ የወደዱትን ከማጣት ይበልጥ የሚያንገበግብ፣ የሚያሳርር
ነገር የለም:: ዣን ቫልዣ ያንን ጽሑፍ በማንበቡ ያቺን የሚወዳትንና ብቸኝነቱን የሚረሳባትን ኮዜት ያጣ መሰለው:: ከአሁን በፊት እንደጠቀስነው ዣን ቫልዣ ኮዜትን እንደ ልጅ ብቻ ኣልነበረም የሚያያት:: ኮዜት ለእርሱ
እንደ ልጅም፣ እንደ እህትም፣ እንደ እናትም ነበረች:: ሕይወትን ጠልቶ ሳለ ሕይወትን መልሶ እንዲያፈቅር ያደረገችው ኮዚት ናት:: ዣን ቫልዣ
ፍቅረኛ ወይም ሚስት አልነበረውም:: ስለዚህ የፍቅሩ ጽናት የሰፈረው ኮዜት ላይ ነበር ለማለት ይቻላል:: በአባትነቱ እርስዋም ከልብ ትወደዋለች::
ያ ፍቅር አክትሞ በሌላ የተተካ ስለመሰለው ነበር እንደዚያ እጢው ዱብ እስኪል የደነገጠው:: ሌላ ማስረጃ የሚያሻው ነገር አይደለም፡፡ ወረቀቱ ከፊቱ ላይ ነው ያለው:: «ፍቅረኛ አላት ማለት ነው ፤ መሄድዋ ነው እንግዲህ» ሲል አጉረመረመ:: የብቸኝነት ስሜት ወረረው:: «እኔን እንደጎበያ
ድንጋይ ጎልታ ልትሄድ! » ለእኔ የሚለው የራስ ወዳድነት ስሜት
ተጠናወተው:: ልቡ የተቃውሞ ኃይል አረገዘ:: ዣን ቫልዣ ይህን እያሰላሰለ ሳለ ሠሪተኛዋ እርሱ ከነበረበት ክፍል ገባች::

«ውጊያ ይካሄዳል ያለሽው የት ሰፈር ነበር? ቦታውን አውቀሽዋል?»

ሠራተኛዋ ተገርማ «እርስዎ ከፈለጉ ምን ገድዶኝ እነግሮታለሁ» ስትል መለሰች::

«ውጊ.ያው ተጧጡፎአል ብለሽ አሁን አልነገርሽኝም እንዴ!» በማለት ቀጠለ::

«አዎን ጌታዬ!›› አለች ሠራተኛዋ ፤ ከዚያ ከማርያም ቤተ ክርስቲያን
ባሻገር ነው:: ››

ዣን ቫልዣ ከነበረበት ውጭ ወጥቶ ደንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡
ጊዜው ጨልሞአል::

ውርጭ ላይ ለምን ያህል ሰዓት ተቀመጠ? እግሩን በመዘርጋትና
በማጣጠፍ ራሱን አዝናና ወይስ ኩርምት ብሎ ነው የቀረው? እንዳጎነበሰ ቀረ ወይስ ቀና አለ? አንድ ነገር ተደግፎ ነው ወይስ እንዲሁ ጉች ብሎ ነው
የተቀመጠው? ራሱ እንኳን ቢሆን ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጥ አይችልም።

በአንድ ወቅት የኮቴ ድምፅ ስለሰማ ብቻ ቀና አለ፡፡ አንድ ልጅ ወደ እርሱ ሲመጣ ተመለከተ፡፡ ጋቭሮች መልእክቱን ለማድረስ ከቤቱ ደረሰ። ወደ ላይ እያየ የቤት ቁጥር ሲፈልግ ዣን ቫልዣ አየው:: ሆኖም ከቁጥር አላስገባውም::

«አንተ ልጅ» አለ ዣን ቫልዣ ፧

«ምን ሆነሃል?»

«የሆንኩትማ እርቦኛል» ሲል ጋቭሮች በድፍረት መለሰለት:: ምናምን ይሰጡኛል?» አለ ቀጠለና፡፡

ዣን ቫልዣ ከኪሱ አንድ መቶ ሱስ አወጣና ሰጠው::

ግን ጋቭሮች አደብ የሌለው ተቅበጥባጭ ልጅ እንደመሆኑ መጠን ገንዘቡን እንደ መቀበል ድንጋይ አነሳ፡፡ የሚሰራ የመንገድ መብራት አየ::

«አሁንም የውጭ መብራት ታበራላችሁ እንዴ?» ሲል ጋቭሮች
ጠየቀ፡፡ «በአሁኑ ጊዜ እኮ መብራት ማብራት ጥሩ አይደለም» ካለ በኋላ
ድንጋዩን ወርውሮ መብራቱን ሰበረው፡፡ አካባቢው በድንገት ጨለመ::

ዣን ቫልዣ ወደ ልጁ ተጠጋ::

«ወይ ምስኪን፣ እንዲህ የሚያስደርገው ምናልባት ረሃቡ ይሆናል። ሲል እርስ በራሱ ተነጋገረ፡፡ መቶውን ሱስ አስጨበጠው::

ጋብሮች የምንተ እፍረቱን ገንዘቡን ተቀበለ፡፡

«ሌላ መብራት እንዳልሰብር ነው» አለ እንዳቀረቀረ፡፡

«እንደ ፈለግህ ስበር፧ እኔ ምን አገባኝ» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰለት።

«ጥሩ ሰው ነዎት!» አለ ጋቭሮች::
አምስቱን ፍራንክ ማለት አንድ መቶ ሱስ ከኪሱ ውስጥ ጨመረ።
ሰውዬውን ስለወደደው በድፍረት ጥያቄ ጠየቀው::

«የዚሁ ሰፈር ሰው ነዎት?»

«ምን ፈለግህ?»

«የቤት ቁጥር 7 የትኛው እንደሆነ ያሳዩኛል?»

«ከዚያ ምን አለህ?»

እዚህ ላይ ልጁ አመነታ:: ሰውዩውን ያስቀየመው መስለው:: ፀጉሩን በጥፍሩ ያክ ጀመር፡፡

«ብቻ» በማለት የያዘውን ደብዳቤ አሳየው::

ዣን ቫልዣ በድንገት አንድ ሀሳብ ስለመጣለት «ስጠብቀው የነበረውን ደብዳቤ አመጣህልኝ» አለው::

«ለእርስዎ?» ሲል ጋቭሮች ጠየቀ፡፡ «እርስዎ ሴት አይደሉ!»

«ደብዳቤው ለወ/ት ኮዜት ነው፤ አይደለም?»

«ኮዜት?» ሲል ጋቭሮች አጉረመረመ:: «አዎን ደብዳቤው የእርሳቸው ነው ፤ ስማቸው ግን ያስቃል፡፡»

«ይሁን ግድ የለም» አለ ዣን ቫልዣ ፤ «ደብዳቤውን እኔ እሰጣታለሁና
ለእኔ ስጠኝ፡፡»

«እንግዲያውስ ውጊያው ከሚካሄድበት ቦታ እንደመጣ እንዲነግሯት እፈልጋለሁ::»

«ጥሩ» አለ ዣን ቫልዣ::

ጋቭሮች ደብዳቤውን ከሰጠው በኋላ ለዣን ቫልዣ ወታደራዊ ሰላምታ ሰጠው::

«ደብዳቤውን በጥንቃቄ ይያዙት ፤ ከአስተዳደር ነው የመጣው::
እርስዎም ይቸኩላሉ እንዴ? ለመሆኑ ደብዳቤውን የተቀበለው ማነው እላለሁ? ስምዎን ይንገሩኛ ደብዳቤውን ለላኩት እመቤት እንድነግር» ሲል
ኩራት እየተሰማው ተናገረ፡፡
‹‹ጥያቄውን የሚያቀርቡት ቅድስት ፍንዱቄ ናቸው?» ሲል ዣን
ቫልዣ ጠየቀው::

«ቸኩያለሁ፤ ደብዳቤውን ያመጣሁት ከውጊያ ሥፍራ ነው፤ አሁንም ወደዚያው መመለሴ ነው» ብሎ መንገዱን በመቀጠል ሰፈር እንደጠፋበት ወፍ በርሮ ሄደ::

ዣን ቫልዣ ማሪየስ የጻፈውን ደብዳቤ ይዞ ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ከክፍሉ ውስጥ ገብቶ በሩን ከዘጋ በኋላ ጥምብ እንዳገኘ አሞራ በመቸኵል ደብዳቤውን
ገለጠው:: የታየሁ እንደሆነ ብሎ በመፍራት ቀና አለና ዙሪያውን ተመለከተ፡፡
ማንም የለም:: ኮዜትና ሠራተኛዋ ተኝተዋል ሲል ግምት ወሰደ::

የሚያደርገው ነገር የሌብነት ስለሆነ ሻማ ለመለኮስ ክብሪት ሲጭር እጁ ተንቀጥቅጦበት ነበር፡፡ አሁን ግን ትንሽ መንፈሱ ስለተረጋጋ ሻማውን አቀጣጠለ፡፡ ከጠረጴዛ ላይ ክርኑን አስደግፎ ደብዳቤውን ማንበብ ጀመረ::
ማሪየስ ለኮዜት ከጻፈው ደብዳቤ ውስጥ የሚከተሉትን ቃላት ብቻ
አጤነ፡፡

«እሞታለሁ፤ ይህን ደብዳቤ ስታነቢ ነፍሴ ከአጠገብሽ ይሆናል፡፡»
👍21👏21
ይህን ሲያነብ ፊደሎቹ የሚዘልለ መሰለው:: ልክ እንደ ሰከረ ሰው
እየተንገዳገደ ነበር ጽሑፉን አንብቦ የጨረሰው:: ያ በመንፈስ የጠላው ሰው ከሞት አፋፍ ቆሞ በማየቱ ውስጥ ውስጡን ደስ አለው:: አለቀ እንግዲህ፣ ያ የፈራው ነገር ተወገደለት፡፡ ከአሰበው ጊዜ አጥሮ ለፍጻሜ ደረሰለት::የወደፊት ሕይወቴን አበላሸብኝ ያለው ሰው ሕይወት መጨረሻ ተቃርቦአል::
ስለዚህ «ውስጥ ውስጡን ደስታ እንክት ያድርገኝ እንጂ» ሆነ፡፡ ለዚህ ሰው መሞት ደግሞ ዣን ቫልዣ ያደረገው አስተዋጽኦ የለም፡፡ ኮዜትን ሊጋራበት
የነበረው ሰው በፈጣሪ ኃይል ተወገደለት::

ደብዳቤውን ለኮዜት ካልሰጣት ማሪየስ የት እንደደረሰ ካዜት
አታውቅም:: ከጦርነት መካከል የገባ ሰው ሊያመልጥ አይችልም፡፡ ማሪየስም ቢሆን ይህን አውቆአል፡፡ እስከዚያች ሰዓት ካልሞተ በቅርቡ እንደሚሞት
ጥርጥር የለውም:: ጥሩ አጋጣሚ! ውብ የሆነ ደስታ!
ልቦናው ይህን ሲያሰላስል ዣን ቫልዣ ሳይታወቀው ከልቡ ውስጥ
ሀዘን ተሰማው:: ከአንድ ሰዓት በኋላ ሙሉ የሚሊቴሪ ልብስ ለብሶ ከቤቱ ወጣ፡፡ በአካባቢው የነበረ አንድ ወዝ አደር የሚፈልገውን ልብስና መሣሪያ
በቀላሉ አሟላለት:: ጠብመንጃ ሳይቀር ይዞ ዣን ቫልዣ ወደ ውጊያው ሥፍራ አመራ::

💫ይቀጥላል💫
👍16👏2
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

የቤት ውስጥ ጦርነት

ሌሊቱን ሌላ ውጊያ ስላልተካሄደ አድመኞቹ የፈራረሰውን ምሽጋቸውን ለማደስና ለማስፋት ጊዜ አገኙ፡፡ ከቁመቱ ትንሽ ጨመሩለት፡፡ ብረት መከላከያም አበጁ፡፡ ወጥ ቤቱን አጸዳድተው የቁስለኛ ማከሚያ ክፍል
አደረጉት:: የሞቱትን ሰዎች አስከሬን አንስተው ጥግ አስያዙ፡፡ በስርቆሹ በር በኩል ያለውን መግቢያና መውጫ በሚገባ ተጠቀመበት፡፡ ቡና ቤቱ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሦስት ሴቶች ጨለማን ተገን በማድረግ በጓሮ በር በኩል ወጥተው በመሄዳቸው አድመኞቹ እፎይታን አገኙ::

ጎህ ሲቀድ ኢንጆልራስ ሁናቴውን ለመቃኘት በስርቆሹ በር በኩል
ወደ ውጭ ወጣ፡፡ አድመኞቹ «እናሸንፋለን» የሚል እምነት ነበራቸው:: ሆኖም ኢንጆልራስ ከተመለሰ በኋላ ሁኔታው በአንድ ጊዜ ተለወጠ፡፡ ኢንጆልራስ በከተማው የነበረው ጦር በሙሉ እነርሱን ሊያጠቃ መውጣቱን
ሕዝቡ ግን ባለፈው ቀን ገንፍሎ ወጣ እንጂ በእለቱ ሁሉም ከቤቱ መከተቱን ሊነግራቸው መሞቻቸው መቃረቡን ጠረጠሩ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ «ወንድሞቼ ሕዝቡ ሪፑብሊኩን ሲከዳ እኛ ሕዝቡን አንከዳም፡፡ እኛ አሁን
ማድረግ ያለብን ምሽጋችንን አጠናክረን በአለን ኃይል መዋጋት ነው» ብሎ ተናገረ፡፡

እነዚህ ቃሎች የአድመኞቹን ሞራል ገነቡት፡፡ ይህ ቃል የማን እንደነበር
እስከዛሬ አልታወቀም:: ብቻ ቀቢጸ ተስፋ በሚገኝበት ጊዜ ዘወትር አንዱ ብቅ ብሎ ሁኔታውን እንደሚለውጥ ሁሉ ይህም ከዚህ የተለየ አልነበረም::

ያ «የሕዝብ ወገን ነኝ» የሚለው ሁሉ ተቃውሞውን ካሰማ በኋላ
«እድሜ ለሞት፧ ለዚያች ቅጽበት ሁላችንም እንቆይ!» ሲሉ ሁሉም በአንድነት ጮኹ::

«ለምን ሁላችንም?» ሲል ኢንጂልራስ ጠየቀ፡፡

«ሁላችንም! ሁላችንም!» የሚል ድምፅ አስተጋባ፡፡

«ምሽጉ ጥሩ ነው:: ለመመከት ሰላሳ ሰዎች ይበቃሉ:: ለምን አርባ
ሰዎችን እንሰዋለን» በማለት ኢንጆልራስ ተናገረ::

«ምክንያቱማ ከዚህ ለመሄድ የሚፈልግ ሰው ባለመኖሩ ነዋ!» አሉ ሁሉም በአንድነት::

ኢንጆልራስና ኮምብፌሬ ወደ ምድር ቤት ወርደው አራት የወታደር ልብስ ይዘው መጡ፡፡

«ከመካከላችን ቤተሰብ ማለት የሚጦሯቸው እናት! እህት፣ ሚስት፣ ልጆች ያልዋቸው አይጠፉም፡፡ የዚህ ዓይነት ኃላፊነት ያለባቸው ከዚህ
ይሂዱ» ሲሉ ኢንጆልራስ አሳሰበ፡፡

«እውነት ነው! አሁን እርስዎ ቤተሰብ አለዎት! እርስዎ ቢሄዱ»
በማለት አንዱ ወጣት ከአጠገቡ የነበሩ ጠና ያሉትን ሰው መከራቸው፡፡

«ይልቅስ አንተ ሁለት እህቶችህ በአንተ ላይ አይደለም ያሉት?»

ሁሉም በየፊናው «አንተ ሂድ፣ አንቱ ሂዱ» ሲባባል ጫጫታ ሆነ፡፡
«ወንድሞቼ! የምንዋጋው ለሪፑብሊኩ ነው ! አሁን ጭቅጭቀን ተዉና መሄድ ያለባቸው ይሂዱ» አለ ኢንጆልራስ፡፡

አምስት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አምስት ሰዎች በኣንድ ድምፅ ተመርጠው እንዲሄዱ ተወሰነ፡፡

«አምስት ናቸው» ሲል ማሪየስ ተናገረ፡፡

የነበረው ዩኒፎርም ግን አራት ነው:: በዚህ ጊዜ ከሰማይ የወረደ
ይመስል አንድ ሌላ ዩኒፎርም ተጣለ፡፡ የአምስተኛው ሰው ሕይወት ዳነ ማለት ነው::
ማሪየስ ልብሱን ማን እንደጣለው ለማየት ቀና ብሎ ሲያይ መሴይ
ፎሽለማንን አየው:: ዣን ቫልዣ ከምሽጉ መግባቱ ነበር፡፡
በጓሮ በኩል ማንም ሳያይ በሚያስገባው መንገድ ነው የገባው:: ያንን መንገድ ቀደም ብሎ ይወቀው ወይም በአጋጣሚ ይድረስበት አይታወቅም፡፡
ከቤቱ ሲወጣ የወታደር ልብስ ለብሶ ስለወጣ ለማለፍ ብዙም አልተቸገረም::

«ይህ ሰው ማነው?» ሲል አንዱ ጠየቀ::

«እሱማ» አለ ኮምብፌሬ የሌሎችን ሕይወት የሚያድን ሰው ነው::

«እኔም አውቀዋለሁ» ሲል ማሪየስ ሀዘን እየተሰማው ተናገረ::

ከዚህ ይበልጥ ሌላ ማረጋገጫ አልተፈለገም:: ኢንጆልራስ ወደ ዣን ቫልዣ ዞረ::

«እንኳን ደህና መጡ፡፡ እንደምንሞት ያውቃሉ?»

ዣን ቫልዣ መልስ ሳይሰጥ ዩኒፎርም የጣለለትን ሰውዬ ያለብስ ጀመር

ምንም እንኳን ጊዜው ረፈድ ቢልም አንድም መስኮት አልተከፈተም።
በሩቁ ግን ሰዎች ከወዲያ ወዲህ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ፡፡ ወሳኙ ሰዓት
እንደቀረበ ያስታውቃል፡፡

ኢንጆልራስ ከመጠጥ ቤቱ በራፍ ድንጋይ ቆልሉአል፡፡ እያንዳንዱ
ሰው ለውጊያ እንዲዘጋጅ አስጠነቀቀ፡፡ ብዙም አልጠበቁም፡፡ ከባድ ጦር
ወደነበሩት ሲመጣ ተመለከቱ፡፡ የተኩስ ድምፅ ተሰማ::

«ተኩስ» ሲል ኢንጆልራስ አዘዘ፡፡

ከዚያ በኋላ ምኑ ቅጡ፤ አገር ተቃጠለ፡፡ ሰማዩ ሁሉ በጭስ ተሸፈኑ።ፊት ለፊት የነበረውን ጣልኩ ሲባል ሌላው ከኋላ ብቅ ይላል::

«ቶሎ ቶሎ እያላችሁ ጠብመንጃችሁን አጉርሱ» ሲል ኢንጆልራስ ጮኸ፡

አድመኞቹ ከባድ መሣሪያ መተኰስ ጀመሩ፡፡ ብዙ ስው ተረፈረፈ።ሁሉም በያለበት «ብራቮ፣ ብራቮ» ሲል ጮኸ፡፡ ሁሉም ተተራመሰ፡፡ ጋቭሮች
እየሮጠ ወደፊት መጣ፡፡ ልጁን ሲያዩ ሁሉም ተበራታ::

«ጓዶች በርቱ» ሲል ጋቭሮች ተናገረ:: «በርቱና ተዋጉ፤ ከየአቅጣጫው ብዙ ጦር እየመጣ ነው።»

«ይኸው ነው፤ እስቲ ሞራል ስጥልኝ!» አለ ኢንጆልራስ፡፡ ጦሩ
ሲመጣባቸው «ጭንቅላታችሁን ዝቅ አድርጉ፤ ደግሞም ወደ ግድግዳው ጠጋ በሉ» በማለት ኢንጆልራስ ምክር ለገሠ፡፡ ከባድ መሣሪያ የያዘ ወጣት
መሣሪያውን እየገፋ ሲመጣ ያዩታል:: ኮምብፌሬ ወጣቱን ሲያየው በጣም አዘነ፡፡

«እንዴት ያሳዝናል፧ ምን ዓይነት የጭካኔ ሥራ ነው የሚፈጽሙት።
ምናልባት ንጉሦች ሲጠፉ ጦርነትም ይጠፋ ይሆናል፡፡ ኢንጆልራስ፣ ወጣቱ ላይ ነው እንዴ የምታነጣጥረው ምን ማለትህ ነው? ይህ ወጣት እኮ ገና ለጋ ነው፡፡ ቢበዛ 25 ዓመት ቢሆነው ነው:: ምናልባት የሚጦራቸው አባት ፤ እናት፣ ወንድምና እህት ይኖሩት ይሆናል፡፡ ከዚህም በላይ መልከ ቀና እንደመሆኑ የሚወዳትና የምትወደው ፍቅረኛ ትኖረው ይሆናል።
ደግሞም የእኔ ወይም የአንተ ወንድም ሊሆን ይችላል፡፡»

«እሱማ ነው» ሲል ኢንጆልራስ መለሰለት፡፡

«እንግዲያውማ እርሱን መምታትና መግደል የለብንም።»

«እባክህን ዝም በለኝ፣ ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን፡፡

ደም ከመሰለው የኢንጆልራስ ጉንጭ እምባ እንደ ጐርፍ ይወርድ
ጀመር፡፡ ወዲያው የጠመንጃውን ቃታ ሳብ አደረገና ለቀቀው:: ያ ለግላጋ ወጣት ከመሬት ተዘረረ፡፡ አየር ይበላ ይመስል አፉን ከፍቶ ከአንገቱ ቀና አለ፡፡ ይጎትተው ከነበረ ከባድ መሣሪያ ላይ ተደፍቶ ፀጥ እንዳለ ቀረ፡፡ዐከጀርባው ደም ሲፍለቀለቅ ታየ:: የወጣቱ ነፍስ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ከሥጋው ተለየች::

ውጊያው ቀጠለ፡፡ ስለውጊያው ከዚህ ይበልጥ ዝርዝር ውስጥ ለመግባት ቢፈለግ ሌላ መጽሐፍ ይወጣዋል፡፡ ሆኖም በዚያች ቀውጢ ቀን የነበረው ሁኔታ ስለጦርነቱ ትንሽ መጨመር ያስገድዳል፡፡ የንጉሡ ጦር በሚገባ ተዘጋጅቶ የመጣ ስለነበር የአድመኞቹን ጥይት ለማስጨረስ ፈልጎ ኃይሉን በመበታተን ከተለያየ አቅጣጫ ተኩስ ይከፍታል፡፡ በአንድ ወገን በከባድ መሣሪያ በመጠቀም ምሽጉን አፈራረሰው:: ያንን ለመቋቋም አድመኞቹ
ባላቸው ኃይል በመታኮስ ተከላከሉ፡፡ ይህም በመሆኑ ጊዜያዊ ድልን ተቀዳጁ፡፡
ሁሉም ደስ አላቸው:: ግን የሚያሳዝነው የነበራቸው ጥይት ተገባድዶ ያገኙታል::
👍16
«በጣም ጥሩ ነው ፤ ድል መታናቸው አይደል» ሲል ጓደኛው
ኢንጆልራስን ያሞቀዋል፡፡ ኢንጆልራስ ጭንቅላቱን በመነቅነቅ «አልመሰለኝም፤
ይህ ድል ከሩብ ሰዓት ወዲያ አይዘልቅም፤ ጥይት እያለቀብን ነው» ይለዋል፡፡ ጋቭሮች ይህን ጭውውታቸውን ይሰማል፡፡ ጥቂት ቆይቶ ኩርፌይራክ ቀና ብሎ ሲያይ መንገድ ላይ እየተንፏቀቀ የሚሄድ ነገር ያያል፡፡ ጋቭሮች
ከሞቱት የንጉሡ ወታደሮች አጠገብ የተዘሩትን ጥይቶች በያዘው ከረጢት ይለቅማል፡፡ ቦታው ምሽጉ ከነበረበት ሥፍራ ብዙ ሩቅ አልነበረም::
ልጁ ጥይት ሲለቅም እንዴት አልታየም:: በመጀመሪያ ደረጃ በጉም የተሸፈነ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ ሌላው ምሥጢር ደግሞ ቀደም ሲል ከባድ ተኩስ ተካሂዶ ስለነበርና በዚያን ዘመን የነበሩ መሣሪያዎች ሲተኮሱ ብዙ
ጭስ ይወጣቸው ስለነበር አካባቢው በጭስ ተሸፍኗል:: ውጊያው በመሀል ጋብ ያለው መሪዎቹ ጭሱ በንኖ እስኪጠፋ እየጠበቁ ሊሆን ይችላል፡፡ ልጁ
ደግሞ ጥይቱን የሚለቅመው በደረቱ እየተንፏቀቀ ሲሆን የከረጢቱን ጫፍ በጥርሱ ይዞ ነበር የሚጐትተው:: በዚህ ዓይነት ጥቂት ጥይቶችን ሰብስቦ
አመላለሰ፡፡

ግን አሳዛኝ ልጁ ብዙም አልቆየ፤ ተደፋ፡፡ እርሱ ከወደቁት ሰዎች
ጥይት ሲለቅም እዚያው ከሞቱት ጋር ተደባልቆ ቀረ፡፡ የልጅ ነገር ወዲያው ብድግ ብሎ እኔስ ወድቄአለሁ፣ ግን የእነ ቮልቴር፣ የእነ ሩሶ አገር አትወድቅም» እያለ ሲጮህ ደግሞ ተመታ:: ከአፈሩ ላይ ተደፋ :: ሁለተኛም አልተነቃነቀም:: ነፍሱ ከሥጋው ተለየች::

ልጁ ሲወድቅ ማሪየስ ከምሽጉ ሮጦ ወጣ፡፡ ኮምብሬ ተከተለው፡፡
ግን አልደረሰበትም:: ጋቭሮች ሞቷል:: ኮምብፌሬ ከረጢቱን፣
ማሪየስ ይዘው ተመለሱ።

ማርየስ የልጁን ሬሣ ታቅፎ ሲመጣ እርሱም ፊት እንደ ልጁ በደም ተጨማልቆ ነበር፡፡ ለካስ ጋቭሮችን ለማንሳት ጎንበስ ሲል ግምባሩ ላይ በጨረፍታ ተመትቶ ነበር፡፡ ግን አልታወቀውም:: ኩርፌይራክ እራፊ ጨርቅ ቀድዶ ቁስሉን አሰረለት::

የጋቭሮችን አስከሬን ከማብዩፍ አስከሬን አጠገብ ጠረጴዛ ላይ አስተኙት፡፡ ሁለቱንም ሬሣ በጨርቅ መሳይ ነገር ሸፈንዋቸው:: ዣን ቫልዣ ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ አልተነቃነቀም:: ኮምብፌሬ ጥይት ሲሰጠው ራሱን ነቀነቀ።

«ምን ማለቱ ነው፧ አሁን ከዚህ ገብቶ አልዋጋም ለማለት ነው» ሲል ኮምብፌሬ አጉረመረመ::

ኮምብፌሬ ወገቡ ላይ ጨርቅ አስሮ ቁስለኞችን ያክማል፡፡ ሁለት
ጓደኞቹ ደግሞ ጋቭሮች ከሞቱት ሰዎች አጠገብ የለቃቀማቸውን ጥይት ያጎርሳሉ፡፡ ኩርፌይራክ ጠመንጃውና ሽጉጦቹ መጉረሳቸውንና ጐራዴው
በትክክል ቦታ መቀመጡን አረጋገጠ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁሉም በየፊናው ማድረግ ያለበትን ሲሰራ ዣን ቫልዣ ጥግ ይዞ ይመለከታቸዋል፡፡ ከዚያ ከነበሩ አንዳንድ ሰዎች የቡና ቤቱን ጠረጴዛ ኪሶች ሳብ ሲያደርጉ የደረቁና አንዳንዶቹም የሻገቱ ዳቦዎችን ያገኛሉ፡፡ ያንን ሲቆረጣጥሙ ማሪየስ የአባቱ መንፈስ ምን እንደሚለው ያሰላስላል፡፡

ኢንጆልራስ ወደ ዣቬር ዞር ብሎ «አንተን አልረሳሁህም፧ ከዚህች
ክፍል በሕይወት የሚወጣው የመጨረሻው ሰው ግምባርህን ብሎ ነው የሚወጣው» አለው ሽጉጡን ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠ፡፡

ዣን ቫልዣ ወደ ኢንጆልራስ ጠጋ አለ፡፡
«አንተ ነህ አዛዡ!»
«አዎን ነኝ:: »
«በሪፑብሊኩ ስም አንድ ነገር ልለምንህ::»
«ምንድነው የምትፈልገው?»
«የዚህን ሰው ጭንቅላት እኔ ላፍርሰው?»
ዣቬር ቀና ብሎ ሲመለከት ዣን ቫልዣን አየው:: የኢንጆልራስን
ዓይን እያየ «ይገባዋል» አለው::

ኢንጆልራስ «ግድ የለኝም» ካለ በኋላ ወደ ዣን ቫልዣ ዞር ብሎ
ስላዩን ከዚህ ዞር አድርግና በለው» ሲል ትእዛዙን ሰጠው::

ዣን ቫልዣ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ሽጉጥ አነሳ:: በዚያች
ቅጽበት የመለከት ድምፅ ተሰማ፡፡

«ጥግ ያዙ» ሲል ማሪየስ ፎቅ ላይ ሆኖ ጮኸ፡፡

ዣቬር ብዙም ድምፅ ሳያሰማ ሳቀ፡፡ ከዚያ የነበሩትን እያየ «የእናንተም እድል ከእኔ ብዙም አይሻል» ሲል ተናገረ::

«ሁላችሁም ውጡ!» ሲል ኢንጆልራስ አዘዘ፡፡ሁለቱ ተፋላሚዎች ብቻቸውን ቀሩ፡፡ ሰላዩ ከግንድ ጋር የታሠረበትን
ገመድ ዣን ቫልዣ አላቀቀ፡፡ ዣቬር የፍጥኝ እንደታሰረ እየጎተተ ከክፍሉ ይዞት ወጣ፡፡ እግሩም ታስሮ ስለነበር ሰላዩ በአጭሩ ነው የሚራመደው፡ ዣን ቫልዣ ሽጉጡን ከኪሱ አወጣ፡፡ አድመኞቹ ከባድ ውጊያ ላይ ስለነበሩ ዣን ቫልዣና ሰላዩ ከክፍል ወጥተው ወደ ጓሮ ሲሄዱ ልብ አላልዋቸውም:: ማሪየስ ግን አይቶአቸዋል፡፡
በስርቆሽ በር በኩል ወጥተው ከመንገድ ደረሱ፡፡ የሞቱት ሰዎች አስከሬን ከመውጫው ላይ ተቆልሎ ስለነበር በችግር ነው ያለፉት:: የሰው ሬሣ እንደ
ድንጋይ ተቆልሎ ማየቱም በጣም አሰቃቂ ነበር፡፡....

💫ይቀጥላል💫
👍11
#ገረገራ


#ክፍል_ስድስት


#በታደለ_አያሌው

...ወደ መኪናዬ ሽምጥ እየሮጥሁ ሳለ ነበር፣ የንስሐ አባቴን እንኳን
እንዳልተሰናበትኋቸዉ ያወቅሁት፡፡ እንደ ልማዴ በጥድፊያ ወደ ሲራክ፯ አሽከረከርኩ። መቼም ከባልቻ የተደበቀ ነገር የለም፡፡ እሱን አግኝቼ እስከማማክረዉ ድረስ ትንፋሼን እንኳን ወደ ዉስጥ መሳብ አልሆነልኝም፡፡ ቸኩያለሁ። አይደርሱት የለም ደረስሁና ቢሮዉን በርግጄ ስገባ፣ ባልቻ በወንበሩ ላይ ለጠጥ ብሎ እንቅልፍ አሸልቦት አገኘሁት።
በተለይም የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ከሆነ በኋላ የግል መኖሪያ ቤቱን አይቶት የሚያዉቅ አይመስለኝም። ዉሎዉም አዳሩም እዚሁ ሆኗል። እዚሁ ምግብ ያስመጣል፣ እዚሁ ወንበሩ ላይ ትንሽ ዕረፍት ያደርጋል። ከስንት አንድ ወደ ዉጪ ቢወጣ እንኳን ምክንያቱ ለዚሁ ለሲራክ ጉዳይ ብቻ
ነዉ፡፡

“ባልቻ!” ብዬ ስጮህበት፣ ብርግግ ብሎ ብድግ አለልኝ።
“ዉብርስት?” አለ ተጨናብሶ፣ እጁን ለሰላምታ እየዘረጋልኝ፡፡
“እሰይ! ‹ዉብርስት?” አልሁት፣ ልጃለሜ የሚለዉ ቁልምጫዉ
መቅረቱ ከንክኖኝ፡፡ እኔ ደግሞ ከእሱ ብቻ ሳይሆን ከማንም ቁልምጫ የለመድሁ ሰዉ ነኝ። ቁልምጫዉን ሳይቀር እንደገና በሚያቆላምጥ ቤተሰብ መሀል ነዉ ያደግሁት። ያዉም ዉብዬዋ፣ ‹ዉቤዋ፣ የኔ ዉብ፣ ዓለሜዋ፣ ‹ልጃለሜ› እየተባልሁ። ባልቻ እንዲሁ እንደ ወረደ በስሜ ጠርቶኝ ካለማወቁ የተነሳ፣ ስሜን ሁሉ የሚያዉቀዉ አይመስለኝም
ነበር። ትዝ ሲለኝ እኔ ራሴ ባልቻ ብዬ ነዉ የጠራሁት ለካ። «አባታለም» የሚለዉ ቁልምጫዬስ? የት ተዉሁት?

“ይኸዉ መጣሽ። በስንት ጊዜሽ? ስደዉል ሳታነሺ፣ ሳስጠራሽ ሳትመጪ፣ ስፈልግሽ ሳትገኘ፤ ዛሬ ምን አመጣሽ በይ?”

“እሸቴ ጠፍቷል”

“ጠፋ? ማን እፍ ብሎት ይሆን በናትሽ? ቀድሞስ በርቶ ኖሯል እንዴi” ሲል አላገጠብኝ፡፡

“ማላገጥህ ነዉ?”

“ራስሽ ከመሀል ጀመርሽዋ! እኔና አንቺ እኮ ገና እንደገና መተዋወቅ
አለብን። ቆይ የት አዉቅሻለሁ? አንቺ ታዉቂኛለሽ?”

“በማርያም አባታለም? ፈርቻለሁ። እሽቴ በመንግሥት ደኅንነቶች እጅ
ወድቆ እንዳይሆን ልቤ ሰግቷል”

“እና ምናገባኝ እኔን?”

“ኧረ ባዛኝቱ? እንዴት ነዉ የማያገባህ፤ እሽቴ እኮ ነዉ!”

"የሆነስ እንደሆነ!”

“አዉቃለሁ አሳዝኜሃለሁ። ለዚያም እንዴ ት ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ አላዉቅም። ቢሆንም ግን በዚህ መሀል እሸቴ በጨካኞች እጅ ወድቆ
ከሆነ አያሳዝንህም?”

“ያሳዝነኛል”

“እኮ አንድ ነገር አድርጋ”

“ምን ላድርግ?”

“የማታስፈልገዉ?”

“እሺ። አስፈልጌ ሳገኘዉስ?”

“ያንተን አላዉቅም። እኔ ግን ተንበርክኬ ይቅርታ እለምነዋለሁ”

“ለምን?”

“ስለሚገባዉ”

“እሺ። መጀመሪያ ግን እንስማማ”

“ንገረኝ በምን?”

“ተንበርክከሽ የምትጠብቀዉ ከሆነና፣ ተሳክቶልኝ ካገኘሁት ደግሞ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ቃል ከገባሽልኝ.…”

“ይኼዉ!” ብዬ ጉልበቴ ግዉ እስከሚል ድረስ ወድቄ ተንበረከክሁ፡፡
“ብቻ አንተ እሺ በለኝ። እገባለሁ። እሄዳለሁ፤ አሁኑኑ ፈልግልኝ!”

“ዉዉዉ-ዉቤ?” የሚል ድምፅ ከኋላዬ ሰማሁ። ማን በተብታባ ድምፁ እንደ ጠራኝ ለማጣራት ዞሬ ማየት ያስፈልገኝ ኖሯል? ኧረ በጭራሽ በጠረኑ ብቻ አዉቀዋለሁ፡፡ እሸቴ ነዉ፡፡ ወይ ባልቻ! ምን ዓይነት ልብ
ነዉ የታደለዉ ግን? መቼም ጨክኖ ማኩረፉን አያውቅበት! ሆነ ብሎ ኖሯል ለካ እሸቴን ከሁላችንም እይታ እንዲጠፋ ያደረገዉ፡፡ እኔ እንደሆነ
እንዳልሞተ ሰዉ የማራክስዉ ነገር የለኝም፡፡ ጊዜ እንኳን ዉድ
የሚሆንብኝ ካለፈ በኋላ ዞሬ ሳየዉ ብቻ ነዉ። እቃም ቢሆን ከእጅ አምልጦ ካልተሰበረ ወይ ደግሞ ካልተሰረቀ በቀር ዉድነቱ አይታወቀኝም።እሸቴንም ባላጣዉ ኖሮ አልፈልገዉም ነበር። ለዚህ ይመስለኛል ባልቻም
እሸቴን ከዓይኔ እንዲጠፋ ያደረገብኝ። የእሽቴን ዉድነት እንዳምን፣ ከዓይኔ ሠወረብኝ፡፡ እንኳንም ሠወረብኝ፣ እንኳንም ናፈቅሁት፣ እንኳንም
አገኘሁት። ተሳክቶለታል።

ባልቻን በስስትም በኩራትም እያየሁት ሳለ፣ እሸቴ ከፊት ለፊቴ መጥቶ እንደኔዉ በጉልበቱ ወደቀ። ጥዉልግ ብሏል። ከንፈሩ ሳይቀር ኩችር ብሎ ደርቆ ታየኝ፡፡

“እሽቴ?”

“ጨጨጨ ጨከንሽብኝ እኮ
ዉቤ”

“ኹለተኛ አላደርገዉም”

“አአአ አአ አለሽልኝ ግን?”

“አለሁልህ። አለህልኝ?”

የባልቻን መኖር ሁሉ ረስተን፣ አንገት ለአንገት ተቆላልፈን ቆየን፡፡
እንደዚሁ እንዳለን፣ ልክ እሸቴን እንዳገኘልኝ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ የገባሁት ቃል ትዝ አለኝ። እስከሚነጋ ቸኮልሁ።

ከአምስት ወር በላይ በሆዴ ፅንስ ይዤ፣ ያዉም እኔ ራሴ የሕክምና
ባለሙያ ሆኜ ፤ እስከ አሁን ግን የሕክምና ክትትል አለመጀመሬ ለግድ የለሽነቱ ወደር የማይገኝልኝ ሴት መሆኔን መስክሮብኛል፡፡ ይኼንን ማንም ሳይነግረኝ አዉቄዋለሁ። ሲሆን ሲሆን እርግዝና ከመፈጠሩ ከዓመት ወይ
ከወራት ቀደም ሲል ጀምሬ ዝግጅት ማድረግ ነበረብኝ፡፡ እንደኔ እንኳን እርግዝናዉ በድንገት ለተፈጠረበትም ቢሆን፣ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ
ሙሉ ምርመራ እና ክትትል ማድረግ የግድ ነዉ። እኔ ግን ቢያንስ ቅሪት መሆኔን ያወቅሁት ቶሎ ቢሆንም፣ ይኼዉ 22ኛ ሳምንቴን ጭልጥ አድርጌ ነዉ ገና ነገርዮዉን እንኳን በበጎነቱ የተቀበልሁት።

ዛሬ ነዉ ወደ ሆስፒታል ለመምጣት የወሰንሁት። ዛሬ ገና።

ዛሬ ግን ቆርጬ መጥቻለሁ።

በእናቶች እና ሕጻናት ሕክምና ዝነኛ ወደ ሆነዉ ሐሚያሉ ሆስፒታል ገብቼ ካርድ አወጣሁና ወደ ተጠቆምሁት የዶክተር ክፍል አመራሁ። ብዙም ሳልቆይ ወረፋዬ ደረሰኝና፣ መለስ ያለዉን በር ገፍቼ ወደ ዉስጥ ገባሁ። ሆስፒታሉን በበጎ ስሙ መረጥሁት እንጂ፣ የተለየ የሐኪም ምርጫ አላደረግሁም ነበር። ሆኖም ከዉስጥ የጠበቀችኝን ሐኪም ካየሁ በኋላ፤ ሕይወት የአጋጣሚዎች ጋን መሆኗን አመንሁ።

ሐኪሟ ስንቱን አብራኝ ያሳለፈች፣ የቀድሞ ጓደኛዬ ሆና እርፍ!

“ሸዊት!” አልኋት፣ ለረዥም ደቂቃ እጄን አፌ ላይ ጭኜ ስደነቅ ከቆየሁ በኋላ።

"የፈጣሪ ያለህ! ዉብዬ ?” አለች እሷም፣ አሁንም አሁንም ዓይኖቿን
ጨፍና እየገለጠቻቸዉ። ከመልኬ እኩል በሆዴ ያለዉን አስተዉላለች፡፡ ከነጭራሹ የምንገናኝ፣ ያዉም እንዲህ ሆኜ፣ አልጠበቀችኝም ነበር። ለነገሩማ እኔስ እንዴት ብዬ እጠብቃለሁ? በጎንደር ዩኒቨርስቲ የሕክምና
ዶክትሬት ዲግሪያችንን አብረን በተማርንበት ወቅት የነበረንን ጓደኝነት አይቶ ትንሽ ትልቁ እንደዚያ ከዓይን ያዉጣችሁ እንዳላለን ሁሉ፣ እንደዚህ በአንድ ከተማ መኖራችንን እንኳን እስካለመተዋወቅ ድረስ
መራራቃችን ዋዛ ነዉ፡፡ ምን ሆነን ነዉ ግን? ምንም፡፡ ለነገሩ ዩኒቨርስቲ ካስተዋወቀኝ ወዳጆቼ ማንን አግኝቼ አዉቃለሁ? ከስንት አንድ በአጋጣሚ ካልሆነ በቀር፣ አብዛኞቹ የት እንዳሉ እንኳን አላዉቅም፡፡

“ዋዉ!” አለችኝ፣ እንደ ታቦት እየዞረችኝ፡፡

“እሩ እስኪ ሰላም በዪኝ መጀመሪያ”

“እንኳን ለዚህ አበቃሽ ዉብዬ” ብላ መጥታ አንገቴ ሥር ሰረገች፡፡
እንደገና ሆድ ሆዴን ትኩር ብላ አየችኝና፣ ጭምጭም አድርጋ ሳመችኝ፡፡የምር ደስ ብሏታል። እንባዋ ሳይቀር ጠይም ጉንጮቿን እያራሰ በብርቅዬ አንገቷ በኩል ፈሰሰ።

ሀገር ዉስጥ ነዉ የምትኖሪዉ? ጭራሽ እዚሁ አዲስ አበባ?” አልኋት፣

ደስታዋ እንዲጋባብኝ ልቤን እየደቃሁት።

“አይ፤ ቅርብ ጊዜ ነዉ የመጣሁት። ጀርመን ነበርሁ፣ ትምህርት ላይ”

“ተዪ እንጂ? ጀርመን፤ ምን ስፔሻላይዝ አደረግሽ ታዲያ?”

“ይኸዉ እያየሽኝ? ለእር ግዝና ክትትል አይደል እንዴ እኔ ጋ
የመጣሽዉ?”

“አይ አጅሪት! እንዲያ ነዉ እንጂ የኔ እህት! ደግሞ ጥሩ ምርጫ ነዉ”

“አንቺስ ምን አጠናሽ?”
👍481
“አይ እኔን እንኳን ተዪኝ። እዚያዉ እንዳስቀመጥሽኝ ነኝ። ሰዉ ሁሉ
እንዳንቺ ቁም ነገረኛ መስሎሻል ኣ?”

“ኧረ ሾርኔ! ... ከትዳር እና ከልጅ የሚበልጥ ቁም ነገር አለና ነዉ? ቁም ነገረኛስ አንቺ!” አለችኝ፣ ሆዴን እንደገና እያየች፡፡

ትዳር የሚለዉን ቃል ስሰማ ድንገት ሆዴን ወጋኝ፡፡ እንደገና ወደ ኋላ ተመልሼ ወደዚያ የድባቴ ስሜት እንዳልዘፈቅ ፈራሁ፡፡

“ሰዉዬሽን አዉቀዋለሁ? ከዚያ ከጥብርያዶስ ጋር ተጋባሁ እንዳትዪኝ ብቻ! ግቢ እያለን እኮ የብቻ ለብቻ መንገድ ኣብዝታችሁ ነበር። እሱን ነዉ ያገባሽዉ?”

“ጥብርያዶስ? ጭራሽ እኔና እሱን በሌላ ትጠረጥሪን ኖሯል እንዴ?”

“እንክት!”

“እንደዚያ የሚያደርግ እንደዚያ ያወራል የሚለዉን አስታወስሽኝ። ካነሳሽዉማ፣ ባንቺ አይብስም ነበር?”

“እርፍ! ወዴት ወዴት?”

“ምነዉ አንቺ ዉሸታም! ነግሬሽ አላውቅምና ነዉ?”

“አረ ዉቤ ተዩ። እሺ አሁን የት እንዳለ ታዉቂያለሽ? በእናትሽ ንገሪኝ”

ከፊቷ የቆመ ይመስል ጥምልል ብላ ተሽኮረመመች። ምስኪን! ፍርስ ብዬ ሳቅሁባት፡፡ ቀድሞዉንም ከእሱ ጋር እንቀላለድ ስለነበር ልታዉጣጣኝ
ስሙን አነሳችብኝ እንጂ፣ ከእሷ በላይ ጥብርያዶስን በሌላ የሚመኝ ኖሮ አይመስለኝም። በእርግጥ እንዳለችዉም ከእሷ ባልተናነሰ ከጥብርያዶስም
ጋር ጥሩ ቀረቤታ ነበረን። ነገር ግን በስሕተት እንኳን እሷ በምትለዉ
ዓይን አይቼዉ አላዉቅም፡፡ ሲጀመር ካልመነኮስሁ ብዬ ገጭ እጓ የምልበት ጊዜ አልነበረ? በዚያን ጊዜ ልቤ ላይ እንዲህ ያለ ምኞት ደርሶብኝ መቼ ያዉቅና! እሷ ግን ትወደዉ ነበር፡፡ በዚያም ላይ ባል ያስፈልገኛል ብላ ያመነችበት ዕድሜዋ ላይ የደረሰች ትመስላለች፡፡ ብዙ ዶክተሮች ሥራና ትምህርታቸዉን ብቻ እያዩ ዕድሜያቸዉን ይፈጁና፣ ያመለጣቸዉ የሕይወት ምዕራፍ እንዳለ ሲያስተዉሱ ይዋከባሉ ተብለዉ ይታማሉ። ትምህርቱ በራሱ ረዥም በመሆኑ፣ ሐሜቱ ዉሸት ነዉ ማለት ከይቻልም፡፡ ምናልባት ጓደኛዬም የጎደላት ያለ መስሎ ይሰማት ይሆን?
ልጠይቃት ስል፣ ሆነ ብላ ወሬ ለወጠችብኝ፡፡

እንግዲያዉ ሰዉዬሽ ማነዉ፤ አዉቀዋለሁ?”.....

“አይ”

“እኮ ንገሪኛ ልወቀዉ”

"እሸቴ ይባላል”

“እሽቴ?”

“አዎ””

“መቼም መልካም ሰዉ መሆን አለበት። ደሞ ጥንታዊት፣ ታሪካዊት ...ሃሃሃ ... ጓደኛዬን ለዚህ ቁም ነገር ያበቃትን ሰዉማ መተዋወቅ ይኖርብኛል። እንኳንም አንዴ አጋጣሚዉ መልሶ አገናኘን እንጂ፣ በዐሥር ዓይነት ቅመም ያበደ ሻይም ቢሆን አፍልቼ እቤቴ እጠራችኋለሁ”

“እሺ” አልኋት፣ ጓደኝነታችን እንዲቀጥል እኔም ከልብ እየፈለግሁ።ፈገግ ብላ አየችኝ። ፈገግታዋ እየጎላ፣ ደስታዋ እያየለ መሆኑን አስተዉያለሁ። ድሮዉንም ልበ ቀና ናት። ለስንተኛ ጊዜ እንደሆነ እንጃ፣ ሆዴን እንደገና በስስት አየችዉ። ሳመችዉ። ጨመጨመችዉ።

“በይ እስኪ ንገሪኝ፤ ምን ያህል ጊዜ ሆነዉ?”

“ሃያ ሶስት ሳምንት ይመስለኛል”

“አዉቀሽ!” አለችኝ፣ ለመሳቅ ጥርሶቿን በብርሃን እየለኮሰች።
ይመስለኛል ማለቴ ሳይሆን አይቀርም ለሳቅ ኩሎ የዳራት።

“በናትሽ እንዳትስቂብኝ። ገና ክትትል ልጀመር ነዉ አመጣጤ።
አዉቃለሁ፣ እጅግ አርፍጃለሁ። ምክንያቴን ብቻ ጠይቂኝ። ያን ያልሽኝን ባለቅመም ሻይ የምትጋብዥኝ ከሆነ አጫዉትሻለሁ ጉዴን”

ጨክና እንዳትስቅብኝም፣ እንዳትቆጣኝም ሆነች። በዚሁ ስሜቷ ፍጥጥ ብላብኝ ቆየችና የሚያስፈልጉ ምርመራዎችን ሁሉ ከዜሮ ጀምራ ዘርዝራ ጻፈችልኝ፡፡ ያኮረፈችኝም መሰለኝ፡፡ በአንዴ ከጓደኝነት ወርዳ፣
ከማንኛዉም ታካሚ በታች ፈጠፈጠችኝ፡፡

“በይ ሌላ ሌላዉን ጨርቪና ነይ። ባይሆን ወደ አልትራሳዉንድ ክፍል
አብሬሽ ልገባ እችላለሁ። እስከዚያዉ ሌሎች ታካሚዎች ካሉ እያስተናገድሁ ልጠብቅሽ። ይሻላል ኣ?”

እሺ። ከገዛ ጓደኛ እጅ ሕክምና ማግኘት እንደምን ያለ መታደል እንደሆነ ባየሽልኝ!”

“በይ እሺ፡፡ በይ ደርሰሽ ነይ”....

ይቀጥላል
👍341
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....የሞቱት ሰዎች አስከሬን
ከመውጫው ላይ ተቆልሎ ስለነበር በችግር ነው ያለፉት:: የሰው ሬሣ እንደ ድንጋይ ተቆልሎ ማየቱም በጣም አሰቃቂ ነበር፡፡
ቁና ዣቬር በረጋ መንፈስ «ይህችን ልጅ አውቃት ነበር» ሲል ድምፁን ዝቅ አድርጎ የኢፖኒን የተገላለጠ ጡትና ገላ እያየ ይናገራል፡፡ ከዚያም ወደ
ዣን ቫልዣ ዞር አለ፡፡"

ዣን ቫልዣ ቃል ሳይናገር ዝም ብሎ በማፍጠጥ አየው:: ደግሞ
መናገርም አያስፈልግም ነበር፡፡ አስተያየቱ ብቻ ዣቬር እኔው ነኝ!» ለማለቱ ግልጽ ነበር፡፡

ዣቬር ንግግሩን ቀጠለ፡፡

«አሁን ልትበቀለኝ ትችላለህ::»
ዣን ቫልዣ ሽጉጡን ከኪሱ ከከተተ በኋላ ሰንጢውን አወጣ፡፡ ሰንጢውን ዘረጋው፡፡

«ወይ ጉድ!» አለ ዣቬር፡፡ «ልክ ነህ፣ እሱ ይሻልሃል»

«ፊትህን አዙር» ሲል ዣቬርን አዘዘው:: ዣቬርም ፊቱን ወደ
ግድግዳው አዞረ:: ከዚያም ዣን ቫልዣ ጠላቱ የፍጥኝ የታሠረበትን ገመድ ይቆርጥ ጀመር፡፡ እጁንና እግሩን አላቀቀለት:: እግሮቹ የታሠሩባቸውን ገመድ ቆርጦ እንደጨረሰ እዚያው ከመሬት ሆኖ ዣቬርን ቀና ብሎ አያየ

«መሄድ ትችላለህ» አለው::

ዣቬር ግራ ተጋብቶ አፉን እንደከፈተ ቀረ:: ዣን ቫልዣ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

«እኔ ግን ከዚሁ ማለት ከምሽጉ ውስጥ እቆያለሁ፡፡ ምናልባት በአጋጣሚ በሕይወት ከወጣሁ አድራሻዬን ልስጥህ» ብሎ የቤቱን አድራሻ ሰጠው።ዣቬር በመገረም እያየውና ከንፈሩን በግድ አላቅቆ «ራስህን ጠብቅ» ሲል መከረው::

«ለማንኛውም ሂድ ብያለሁ፤ ቶሎ ብለህ ከዚህ ጥፋ» ሲል ዣን
ቫልዣ በተራው መከረው::

ዣቬር አድራሻውን ለማረጋገጥ «ሆም አርሚ ጐዳና የቤት ቁጥር
ሰባት ነው ያልከኝ?» ሲል ጠየቀው::

«በደምብ ይዘኸዋል» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰለት::

ዣቬር ልብሱን አስተካክሎና በአንድ እጁ ጉንጩን ይዞ መንገዱን ቀጠለ፡፡ ዣን ቫልዣ ከዚያው እንደቆመ በዓይኑ ተከተለው:: ዣቬር ጥቂት
ከተጓዘ በኋላ ወደ ኋላ መለስ ብሎ «አናደድከኝ፣ ለምን አልገደልከኝም ነበር»ሲል ተናገረው:: «ሂድ ብያለሁ፤ ሂድ» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰለት።

ዣቬር በዝግታ እየተራመደ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ኩርባ ላይ ሲደርስ ወደ ግራ ታጠፈ::ዣቬር ከዓይኑ ሲሰወር ዣን ቫልዣ ሁለት ጊዜ ወደ ሰማይ ተኩሰ፡፡ ከዚያም ወደ ምሽጉ ተመልሶ «እርምጃው ተወስዷል» ሲል ሪፖርቱን አቀረበ።

«አጥቃ» የሚለው የከበሮ ምልክት እንደገና በኃይል ተመታ፡፡ ማጥቃቱ እርምጃ ከማዕበል የከፋ ነበር፡፡ እግረኛው ጦር ጠመንጃን ወድሮ በቀጥታ ወደ ምሽጉ ገሠገሠ፡፡ መለከቱና ከበሮው ተንጣጣ፡፡ የእግረኛው እርምጃ መሬቱን አነቃነቀው::

ከምሽጉ ውስጥ በሕይወት የቀሩት አድመኞች ጠመንጃቸውን
አንጣጡት:: ኢንጆልራስ በአንድ ፊት ማሪየስ በሌላ በኩል አጋሮቻቸውን ለማነቃቃት ይጮሃሉ፡፡ ጦሩ እየቀረባቸው መጣ፡፡ ከአጠገባቸው የደረሰው
እየተንገዳገደ ከእግራቸው ስር ይወድቃል:: ኃይለኛ የመከላከያ ምሽግን ተገን አድርጎ በቀዳዳ የሚዋጋን ጦር ቶሎ ለመጣል ያዳግታል። ሆኖም ! የነበረው
ምንም እንኳን የምሽጉ አቀማመጥ ቢረዳቸውም በመጨረሻ ለመቋቋም አልቻሉም።

እህል ከቀመሱና የእንቅልፍ ዓይን ካዩ ሃያ አራት ሰዓታት ኣልፈዋል።
ቁጥራቸው አንድ ስልሣ ይሆናል:: የነበራቸው ጥይት እየተሟጠጠ ነው።ከመካከላቸው ያልቆሰለ ቢኖር በጣም ጥቂት ነው፡፡ የመንግሥት ጦር ከምሽጉ ለመግባት አሥር ጊዜ ያህል ሞክሮአል፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉ ደረት
ለደረት በጠብመንጃና በጎራዴ በመከላከል በሙሉ ልብ ተዋጉ፡፡ በዚህ ውጊያ እነኩርፌይራክ፣ ቦሌይና ሌሎችም ሲሞቱ ኮምብፌሬ በሳንጃ ደረቱ ላይ
ከሦስት ቦታ ተወግቷል፡፡ እሱም ቢሆን ከተወጋ በኋላ ብዙ አልቆየም፧ ሕይወቱ አለፈች፡፡ ማሪየስ እስከመጨረሻው ቢዋጋም ቆስሉ ስለነበር እየደከመ
ሄደ፡፡ ኢንጆልራስ ብቻ ነበር ያልተነካው::

በየአቅጣጫው ጥግ ይዞ ይዋጋ የነበረው ሰው ቀስ በቀስ አንዱ
ከሌላው ቀጥሎ ስለተመታና ስለወደቀ ወደ ምሽጉ የሚያስገባ ቀዳዳ እየሰፋ ሄደ፡፡ የመንግሥት ጦርም ከምሽጉ መሃል ለመግባት ቻለ፡፡ ሰው ሲያልቅ የምሽጉ የውጭ ግምብም በመሣሪያ ኃይል ተናደ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር በሕይወት የቆዩት እጅግ ጥቂት አድመኞች የመጨረሻውን መንፈራገጥ ያሳዩት።በዚህች የመጨረሻ ደቂቃ ነው የሰው ልጅ የመኖር ፍላጎቱ የሚያይልበትና
የእንስሳ ባሕርዩ የሚጎላው:: ያቺን ሰዓት ለማለፍ የማያስበው ዘዴና
የማያልመው መላ አይኖርም፡፡ ወደ ፎቅ የሚሮጠውን የተዘጋ በር ለመክፈት የሚታገለው፤ ተከፍቶ የነበረውን በር ላመቀርቀር የሚሽቀዳደመው ሲታይ
በጣም አሳዛኝ ትርዒት ነበር::
በዚያች ቀውጢ ሰዓት በድንጋጤ መንፈሱ ተረብሾ ወደ ስርቆቱ በር
የሚወስደውን መንገድ በጉልህ ያስታወሰ ኢንጆልራስ ብቻ ነበር፡፡ በአንድ እጁ ጠመንጃውን በሌላው ጎራዴ ይዞ ከፊት ለፊት የሚመጣውን ጦር እየተከላከለ በሕይወት የቀሩትን ሰዎች ወደ ውስጥ እንዳስገባ ወታደሮች
ደርሰው የብረቱን በር ለመግፋት ይታገላሉ:: አድመኞቹ ከውስጥ ወታደሮች ከውጭ ሆነው በሩን ሲገፉ አንድ ወታደር ጣቱ በበሩ በመቀርጠፉ ይጮሃል፡፡
ማሪየስ በመመታቱ በበሩ አላለፈም:: እንዲያውም ከነአካቴው ሕሊናውን ስቶ ይወድቃል፡፡ ልክ ሲወድቅ አንድ ሰው መጥቶ ሲይዘው
ይታወቀው እንጂ ከዚያ በኋላ የሆነውን አያውቅም:: ከዚያ ጥቂት ቀደም ብሎ እንደ ተመታ ኮዜት ትዝ ብላው «ስለቆሰልኩ እማረካለሁ፤ ከዚያም
በጥይት ተደብድቤ እሞታለሁ» ሲል ያስባል፡፡ ልክ ኮዜት አጠገቡ እንዳለች ቆጥሮ ነበር ታሪኩን የሚነግራት::

እነ ኢንጂልራስ ከውስጥ ወታደሮች ከውጭ ሆነው ከአንደኛ ፎቅ ላይ የነበረውን ክፍል በር በጥይት አጋዩት:: በዚያች ሰዓት የነበረው ጩኸት ! የነበረው ዋይታና የስቃይ እንጉርጉር በቃላት ለመግለጽ እጅግ በጣም
ስለሚያዳግት እንዲያው ዝም ይሻላል፡፡

በመጨረሻ በሩ ተበርግዶ ሲከፈት በሕይወት የቆየው ኢንጂልራስ
ብቻ ነበር፡፡ ኢንጆልራስ ጥይት አልቀበት ሰውነቱ በደም ተበክሎና ልብሱ ተቦጫጭቆ ጥግ ይዞ ቆሞአል፡፡ ጠመንጃውን ግን በእጁ እንደያዘ ነው።አንድ ሰው ገና ሲያየው በኃይል እየጮኸ ይናገራል::

«መሪው እሱ ነው፡፡ ያንን መልከ መልካም ወጣት የገደለ እርሱ
ነው:: እዚህቹ ከቆመበት በሉት::»

«ግደሉኝ» አለ ኢንጆልራስ ረጋ ብሎ ደረቱን እየገለበጠ፡፡

አሥራ ሁለት ወታደሮች ኢንጆልራስ ላይ ለመተኰስ ጥግ ይዘው
ጠመንጃቸውን አቀኑ።

የሃምሣ አለቃ «ለመተኩስ ተዘጋጁ» ሲል ትእዛዝ ሰጠ::

የሃምሳ አለቃው ጩኸት ግራናትዬን ከእንቅልፉ ቀሰቀሰው:: ግራናትዬ ከሰካራሞቹ አንዱ ነው:: ከመጠጥ ቤቱ ተኝቶ እንቅልፍ የወሰደው ከአንድ ቀን በፊት ነበር::

እንደሚታወቀው ሰካራም አንዴ እንቅልፍ ከወሰደው እንቅልፉን
ካልጨረሰ በቀር ምንም ዓይነት ድምፅ አይቀሰቅሰውም፡፡ ከእንቅልፉ እንደነቃ በእንቅልፍ ልቡ «ሪፑብሊኩ ለዘላለም ይኑር፤ እኔም የዚያው አባል ነኝ
በማለት ጮክ ብሉ ሲናገር ወታደሮቹ ደንግጠው ወደ ግራናትዬ ፊታቸውን
አዞሩ፡፡

ሰካራሙ ከተኛበት ብድግ ይላል:: ሁለም አፍጥጦ ያየዋል፡፡
የሚያናግረው ግን የለም::
«ሪፑብሊኩ ለዘላለም ይኑር» ይላል በድጋሚ፡፡ በቀጥታ ወደ ኢንጆልራስ ሄዶ ከአጠገቡ ቆመ::

«በአንድ ጥይት ሁለት ሰው» ይላል:: ከዚያም ወደ ኢንጆልራስ ዞር ብሎ ረጋ ባለ መንፈስ «አብሬህ ብሞት ትፈቅድልኛህ?» ሲል ጠየቀው።
👍182