አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ኢንጀልራስ ፈገግታ እያሳየ እጁን ይይዘዋል፡፡ ሆኖም ፈገግታውን
ሳይገታ ኢንጆልራስ በስምንት ጥይት ተመትቶ ጥይቱ ከግድግዳው ጋር
ያጣበቀው ይመስል ቆሞ ቀረ:: አንገቱን ግን ደፍቶአል:: በትከሻው ግድግዳውን ተደግፎ ነው የቆመው:: ግራናትዬ ግን ጥምልምል ብሎ ከመሬት ወደቀ።
ከዚያም ወታደሮቹ ቤቱን መፈተሽ ጀመሩ፡፡ ጣራ ላይ አንድ ወታደርና
አንድ ተቃዋሚ አንገት ለአንገት ተያይዘው ሲተናነቁ ሁለቱም ተያይዘው በመውደቃቸው ሕይወታቸው አለፈ:: አንዱ የሴት ቀሚስ ለብሶ በሕይወት
ስለተገኘ ሆዱን በሳንጃ ተርትረው ገደሉት:: ከዚያ በኋላ ምሽጉ ሙሉ
በሙሉ በመንግሥት ወታደሮች ቁጥጥር ስር ሆነ፡፡

ማሪየስ እውነትም ከተመታ በኋላ እንዳለው እስረኛ ሆኖ ቀረ፡፡
ያሠረው ግን ዣን ቫልዣ ነበር፡፡ ከተመታ በኋላ ነፍሱን ስቶ ሲወድቅ ከኋላ መጥቶ የያዘው የዣን ቫልዣ እጅ ነበር::ዣን ቫልዣ ማሪየስን ፍለጋ የመጣው ውጊያው እየተፋፋመ ሲሄድ
አልነበረም፡፡ እውነታው ከዚያው ማሪየስ አጠገብ ሆኖ በውጊያው ሳይሳተፍ ማሪየስን በዓይነ ቁራኛ ሲጠብቅ ነው የቆየው:: ልክ ማርየስ ሲመታ ነብር ፍየልን ከመቅጽበት ከመቼው ደርሶ አፈፍ እንደሚያደርገው ሁሉ ዣን
ቫልዣም ማሪየስ ወድቆ መሬት ሳይከስከስ ዘልሎ በፍጥነት ያዘው:: ከዚያም ተሸክሞት ሄደ::

ልክ ጦርነቱ ተፋፍሞ ወታደሮቹና እነኢንጆልራስ በር ለመዝጋትና
ለመክፈት ሲታገሉ ዣን ቫልዣ ማንም ልብ ሳይለው ማሪየስን ተሸክሞ ይወጣል፡፡ ማሪየስ በዚህን ጊዜ ሕሊናውን ስቶ ስለነበር ነፍሱን አያውቅም::
ዣን ቫልዣ ማሪየስን እንደተሸከመ ከዚያው አካባቢ ወደ አንድ ሰወር ወዳለ ሥፍራ ስለደረሰ ማሪየስን ከመሬት አስቀመጠው: አካባቢውን ቃኘ:: ማምለጫ ቀዳዳ የለውም፡: በጓሮ በኩል የሚያስወጣውን የስርቆሽ በር
እንዳለ ግን ያውቃል፡፡ በዚያች ሾልኮ እንዳይሄድ በዚያች ሰዓት ወታደሮች ምሽጉን ጥሰው ገብተው ከቤቱ ጣራ ላይ ስለወጡ ያዩታል:: እጅግ በጣም አስጨናቂ ቅጽበት ነበር፡፡

በጓሮ በኩል ብቅ ብሉ ቢታይ ሞት እንደሚጠብቀው ያውቃል::
እንዳይመለስ ከበስተኋላው ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው:: ታዲያ የት
ይሂድ? ወፍ አይደል አይበር! መሬቱ ተከፍቶ «ና ከዚህ ተደበቅ» ይለው ይመስል መሬቱን ዝም ብሎ ተመለከተው:: የሰው ዓይን በማየት ብዛት ቀዳዳ የማውጣት ችሎታ ቢኖረው ሁለት ቦታ በሰነጠቀው::

ከቆመበት ጥቂት እርምጃዎች ራቅ ብሉ ከግምብ አጥር ስር ብረት ነገር አለ፡፡ ክብ ነገር ነው:: ዓይኑ እዚያ ላይ ተሰባስቦ ቀረ:: ሰፋ ያለ ነገር ሲሆን የመሬቱን ወለል ነው የያዘው:: ጥቂት ወደፊት ተራምዶ ብረቱን አየው:: የቆሻሻ መውረጃ ትልቅ ቱቦ ክዳን ነበር፡፡ አሳብ ብልጭ አለለት::
ያንን የብረት ክዳን ከፍቶና እንደ ሬሣ የሚከብደውን ማሪየስን ተሸክሞ ከዚያ ውስጥ መግባት::

ያንን የብረት ክዳን ማንሳት ቀላል ባይሆንም ቀደም ብለን እንደገለጽነው ዣን ቫልዣ ጉልበተኛ በመሆኑ አነሳው:: ማሪየስን ተሸክሞ ከዚያ የቆሻሻ
መውረጃ ቱቦ ውስጥ ከገባ ሰኋላ ማሪየስን እንደ ግድግዳ ካለ ነገር ላይ አጋደመው:: እርሱ ተመልሶ ሄዶ በመንጠላጠል ያንን ክብ የብረት መዝጊያ ከውስጥ ሆኖ ከቦታው መለሰው:: ያም ብዙ ልፋት ነበረበት፧ ዝርዝር
ውስጥ አንገባም:: እዚህ ላይ የቱቦውን ሁኔታ መግለጽ ያስፈልጋል፡፡ እኛ የቆሻሻ
መውረጃ ሲባል የሚታየን አንድ ከሲሚንቶ የተሠራ ሰፊ ክብ ነገር ነው:: የፓሪስ ከተማ የቆሻሻ መውረጃ ቱቦ ግን ከዚህ የተለየ ነው:: የፓሪስ ከተማ የቆሻሻ መውረጃ ቱቦ የመሬት ውስጥ ግምብ ነው:: መሬቱ በጥልቀት
ከተቆፈረ በኋላ በድንጋይ ንጣፍ ይለጠፍና ከግራ ተቀኝ ይገነባል፡፡ ከዚያም ሁለቱን ግምብ በማገናኘት ተደፍኖ ከላዩ ላይ መንገድ ይሠራበታል፡፡ ከላዩ
ላይ አጥር ወይም ቤት የተሠራበትም አይጠፋም::
ዣን ቫልዣ የገባው ከዚህ ውስጥ ነው:: ከዚያ ውስጥ ለመግባት
ደግሞ ዘልለው የሚወርዱበት ሳይሆን ከግምቡ ጋር ተጣብቆ የተሠራ የብረት መሰላል ስላለ በዚያ ነው የሚወረደው:: ይህም ማለት ሰው ከዚያ ከገባ የሚሄደው በደረቱ ተንፏቆ ሳይሆን ቆሞ ነው:: ነገር ግን የሚራመደው
በውሃ ከላቆጠ ዓይነ ምድርና ሽንት ላይ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ጥልቀቱ.
ከወገብ በላይ ሊደርስ ይችላል፡፡ እንኳን ሊሄዱበት ሲገልጹትም ይሸታል::

የሚሄደው ውሃ ድምፅ አይሰማም፡፡ ድርግም ያለ ጨለማ ነው:: ዣን ቫልዣ ከወታደሮች ለማምለጥ በግምብ ተንጠላጥሎና ኮዜትን ተሸክሞ
ከገዳም ውስጥ የገባበትን ጊዜ አስታወሰ፡፡ ልዩነቱ አሁን የተሸከመው ኮዜትን ሳይሆን የኮዜትን ፍቅረኛ ነው:: ያን ጊዜ ከመሬት በላይ ሲሆን
አሁን ከመሬት በታች ነው:: ውጊያው ከተካሄደበት ቡና ቤት የነበረው ትርምስ በጭላንጭል እንጂ በውል አይሰማውም::....

💫ይቀጥላል💫
👍202
#እንዴት?

የአለሜን ስፋት
የህልሜን ፍቺ ወሰን
የብርሀኔን ልክ
አንቺን በልቤ የዤ፤
ከጎጆዬ
ከሰማዬ . . .ጣራ፣
የብቸኝነት
ግት
በበረዶ እንገሩ ያቀዘቅዘኛል?
ለእምነቱ የቀረበ
ለእውነቱ የቆረበ
ሞጋች
ወትዋች . . . ልቤ
ስለ ፍቅርሽ ሲሆን፣ እሽሩሩ ይለኛል?

የትኛው ነው እውነት?
የትኛው ነው እምነት?
ከባዶው ሶፋ ላይ ያንቀላፋች ድመት!
የቀረበው ስኒ፣ ቡና ያልተቀዳበት!
የካፌው በረንዳ፣ አንቺ የሌለሽበት!
የማለዳው ጸሀይ፣ አንቺ ያልደመቅሽበት!
. . . . . . . ............የማየው የሚያየኝ?
ወይስ . . .
ትዝታሽ
ጠረንሽ
የሽንቁሬ ውታፍ፣ አሳጥሮ ያሰረኝ?
.........................አትዋጋ ሚለኝ?

ዳሩ በዚህ ቅዠት፣
ዳሩ በዚህ መንፈስ፣
ጨርቁን በጣለ አለም፤
ቋሚ ስፍር የለም
ገፍፈው የሚጥሉት፣
ስልባቦት ነው እምነት፤
ብጣሪ ነው እውነት፡፡

🔘በድሉ ዋቅጅራ)🔘
👍121
#ገረገራ


#ክፍል_ሰባት


#በታደለ_አያሌው


...“በይ እሺ፡፡ በይ ደርሰሽ ነይ”

የምርመራ ማዘዣዎችን ተቀብያት ስወጣ፣ ለአልትራሳውንድ ምርመራዉ ጨመር ያለ ዉሃ መጠጣቱ እንደሚጠቅመኝ ስለማዉቅ፣ ወደ ሆስፒታል
ስመጣ ጀምሬዉ ያጋመስሁትን ኹለት ሊትር ዉሃ እየተጎነጨሁለት
ወደ ቤተ ሙከራዉ ተመለስሁ። እንደ ፈራሁት ስዓቱ ሰዉ የማይበዛበት ሰዓት ሆኖ ይመስለኛል፣ የሚያማርር ወረፋ አልገጠመኝም። በመሆኑም፣
ደሜን ጨምሮ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ናሙናዎችን ሰጥቼ በግማሽ ሰዓት ዉስጥ ዉጤት ደረስልኝ። ዉጤቴን ይዤ እንደገና ወደ ቀድሞዋ የልቤ ሰዉ፣ የአሁኗ ደግሞ ሐኪሜ ቢሮ ወጥሮ የያዘኝን ሽንቴን እንደ
ቆነጠጥሁ ተመለስሁ። ገለጥ አድርጌ እንኳን ወረቀቱን የማየት ሐሳብ ብልጭ አላለልኝም።

ሆስፒታላችሁ ብርሃናዊ አይደል እንዴ አንቺ፣ ፍጥነቱ!”

“ዉጤቱ ደረሰልን?”

“ይኼዉ” አልኋት፣ ጠረጴዛዋ ላይ እንደ ከባድ እቃ በኹለት እጄ
እያስቀመጥሁላት።

“ደፈንሽዉ ኣ?” አለችኝ፣ ትኩረቷን አድርጋበት ከነበረዉ ኮምፒዉተሯ
ወደ ዉጤት ወረቀቴ እያመጣችዉ።

“እረ እኔ ምኑንም አላየሁት”

ለመጨረሻ ጊዜ ሆዴን ሰረቅ አድርጋ አየችዉና ወረቀቱን ገለጠችዉ፡፡ድንገት ፊቷ እብጥ አለብኝ። ዉጤቱ ላይ ደስ የማይል ነገር እንዳገኘች ጠረጠርሁ። ቢሆንም ግን ራሷ እስከምትነግረኝ ድረስ ብጠብቅ ይሻላል ብዬ ያላየኋት መሰልሁ። እሷም ያልደነገጠች ለመምሰል የሆነ ያልሆነዉን ቀበጣጠረች፡፡ እንደገና በሚያደናግር ትኩረት አስተዋለችዉና ወደ አልትራሳዉንድ ክፍሉ እንድከተላት ነገረችኝ፡፡ ስንገባ ያገኘነዉን ራዲዮሎጂስት እንኳን በቅጡ ሰላም አላለችዉም። ቶሎ ብዬ ሆዴን ገልጬ አልጋዉ ላይ እንድንጋለል አዘዘችኝ፡፡ ለወትሮዉ በልዩነት የተማረዉ ባለሙያ ያለበትን አልትራሳዉንድ ይቅርና ተራ ነገርም ቢሆን
ሐኪም ያለሙያዉ ገብቶ አይፈተፍትም፡፡ እሷ ግን እጅግ ከመቻኮሏ የተነሳ እሱን ጨምራ በጥድፊያ ከፍ ዝቅ አደረገችዉ። የእዉር ድንብሯ ወጥቷል። ሌላዉ ቀርቶ ገና በመመርመሪያዉ (ultrasound probe)
እንኳን ሳይዳብሰኝ ነበር ዓይኖቿን ወደ ምስል መከሰቻዉ የተከለቻቸዉ።

ችኮላዋን በበጎ የተረዳት የክፍሉ ባለሙያ፣ ሳይቀየማት የሚደረገዉን ሁሉ አድርጎ የፅንሱን ጥላማ ገጽ ፊት ለፊታችን ባለዉ ዝርግ መከሰቻ አመጣልን። ይኼ ሁሉ ሲሆን የእሷን አድራጎት ብቻ ነበር የምከታተለዉ።
እስኪበቃት ድረስ እያጎላች እና እያሳነሰች ስትመለከተዉ ቆየች። እኔንም እንዳየዉ ጋበዘችኝ፡፡

አየሁት።

ችግር አለ። ከባድ ችግር!
“አይ፤ ያን ያህል እንኳን አንገት የሚያስደፋ አይደለም” አለችኝ፣
ከአልጋዉ ላይ እንድነሳ እየደገፈችኝ። ድንገት ሰዉነቴ እየከዳኝ፣ የበለጠ ድጋፍ እየፈለግሁ መጣሁ። ደግነቷ፣ እጇን አልከለከለችኝም።
“በእርግጥ የማልደብቅሽ ነገር ቢኖር፤ እኔም ልክ የላብራቶሪ ዉጤትሽን ሳየዉ ደንግጫለሁ። በዚያም ላይ ከእኔ ባልተናነስ ስለ ሁኔታዉ ልታወቂ እንደምትችይ ስለማዉቅ በማይመስልሽ ቃል አንቺን አልሸነግልሽም።እንኳንስ የሕክምና ሥነ ምግባር ለማገባት ላንቺ ለጓደኛዬ ይቅርና፣
ለታካሚዎቼ ሁሉ የሆነዉን በግልጽነት የማስረዳት ኃላፊነት አለብኝ። የምልሽ ይገባሻል መቼስ”

ጓደኛዬም ሐኪሜም በሆነችዋ ሸዊት ፊት፣ ግብኔ ብቻ ያልቀረ ለመምሰል ተጣጣርሁ። ጠንካራ ለመምሰል እየሞከርሁ የዉጤት ወረቀቱን እንድትመልስልኝ እና የሆነዉን ሁሉ በራሴ ዓይን እንዳየዉ እጄን ዘረጋሁላት። ሐኪሜ ለምን እንደዚያ እንደሆነች ገባኝ፡፡ ምክንያቱም የፎሊክ አሲድ መጠኑ ከሚጠበቀዉ መጠን እጅግ የወረደ ኖሯል።
እንደዚህ ሲሆን ደግሞ በፅንሱ ላይ የነርቭ ክፍተት የማስከተል ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን እንኳንስ ሥራዬ ብላ ያጠናችዉ እሷ ትቅርና፣ እኔ ዉብርስትም አዉቀዋለሁ። የፎሊክ አሲድ እጥረት ከተከሰተ፣ የነርቭ
ዘንግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በወቅቱ እንዳይዘጋ ያደርገዋል። በመሆኑም፣ የፎሊክ አሲድ እጥረት እንዳያጋጥም፣ እርግዝና ከመፈጠሩ አስቀድሞ ወይ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከተመረጡ ምግቦች፣ ወይ ደግሞ ሰዉ ሰራሽ እንክብሎችን መዉሰድ ያስፈልጋል። ያለበለዚያ ይኼዉ በእኔ የምርመራ ዉጤት ላይ እንደ ታየዉ፣ ልክ ያልሆነ ነገር በፅንሱ ላይ ይፈጠራል።

ምን ዋጋ አለኝ? አርፍጃለኋ!

“በእርግጥ ሌሎችም መነሻዎች ስላሉት፣ የፎሊክ አሲድ እጥረቱ ነዉ ይኼን ያመጣዉ ብሎ አፍን ሞልቶ መደምደም አይቻልም። ሆኖም እኔን ደጋግመዉ ከገጠሙኝ ዐሥር የፎሊክ አሲድ እጥረት ያየሁባቸዉ ነፍሰ
ጡሮች፣ ቢያንስ የስድስቱ ወደ ነርቭ ክፍተት ያደርሳል። የነርቭ ክፍተት ስልሽ የተለመዱትን፣ በተለይም ስፓይናቢፊዳ(አከርካሪው ላይ ያለው ነርቭ ወደ ውጭ መውጣት) ማለቴ ነዉ። ይኼ ደግሞ ያልሰለጠነ ሀገር በሽታ እየሆነ መጥቷል። ምክንያቱም የበለጸጉት ሀገራት ምግባቸዉን በጠቅላላ በፎሊክ እንዲበለጽግ ስላደረጉት፣ ብዙም አያጋጥማቸዉም። የእኛን ሀገር ግን አታንሺዉ”

“በናትሽ መፍትሔ አለዉ በዪኝ”

“ደግሞ በኛ ዘመን መፍትሔ የሌለዉ ነገር ምናለና ዉቤ”

“እኮ ምን?”

“በተአምር ታምኛለሽ?”

የጭንቅ ዝልዝል የተንጠለጠለበትን ፊቴን መለስሁላት።

“ተአምር?”

“አሁን አንዴ ፅንሱ ቅርጽ ይዟል። ተአምር ካልተፈጠረ በቀር፣ ሕጻኗ... በነገራችን ላይ ጾታዋን አልነገርሁሽም አይደል ቅድም? ሴት ናት። እና፤ከላብራቶሪም ሆነ ከአልትራሳዉንድ ባገኘነዉ ዉጤት መሠረት፣ በወሊድ ጊዜ ሊገጥሙን የሚችሉ የነርቭ ዘንግ ክፍተቶች ይኖራሉ፡፡ በተለይ
ስፓ ይናባይፊዳ የሚባለዉ ለብቻዉ ወይም ደግሞ ሀይድሮሴፋለስ(ጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር) ጭምር
ሊሆኑ ይችላሉ። ግን እንዳልሁሽ ነዉ፤ ተወልዳ በዓይናችን እስከምናያት ድረስ መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን አንችልም”

“እንዲያዉ አይበልብኝና ይኼ ነገር እዉነት የሚሆን ከሆነ ምንድነዉ
የሚሆነዉ ግን?”

“እንደምታዉቂዉ፤ ለሐቅ የቀረበ ግምት እንጂ ፍጹም የሚባል ያለቀ
የደቀቀ ሐቅ የለም በሳይንስ፡፡ አንቺም ሐሳቤን የምትጋሪዉ ይመስለኛል።ሆኖም አብዛኛዎቹ የዚህ ክፍተት ተጠቂዎች የታወቁ ጉዳቶች ይገጥሟቸዋል። ለምሳሌ ሽንትና ሰገራ ያለመቆጣጠር፣ የእግርና የእጅ ሽባነት፣ የዓይን መንሸዋረር ወይ መጥፋት እና ሌሎችም ጭምር።እንዲያዉም አልፎ አልፎ የከፋዉ ሲመጣ፣ እነዚህ ያልሁሽ ሁሉም አንድ
ላይ የሚከሰቱበት አጋጣሚ ሁሉ አለ። ታዲያ እንዳልሁሽ፣ በኛ ዘመን
መፍትሔ የሌለዉ ችግር የለም። ቢፈጠርም እንኳን ሕክምና አለዉ”

“አለዉ?” አልሁኝ፣ ለእፎይታ ራሴን እያመቻቸሁ። አንደኛዬን ግልብ
ሆኜ የለ አሁንማ? አሁን መሳቅ አሁን ማልቀስ፣ አሁን ማመን አሁን
መካድ። ስስ ሆኛለሁ።

“አዎ። ቀዶ ጥገናም እኮ አለዉ። አንቺን መምከር ሳይገባኝም፣ ከዚህ በላይ መጨነቅ ግን አይኖርብሽም። ጭንቀት ራሱ ሌላ ጣጣ ስላለዉ፣ እዉነታዉን የምነግርሽ እንድትጨነቂበት ሳይሆን ለግልጽነት ብዬ ነዉ።
በዚያ ላይ አንቺ ጠንካራ ሰዉ መሆንሽን ለእኔ ለጓደኛሽ እንዲነግሩኝ አልጠብቅም። አዉቅሻለኋ!”

ቀዝቃዛ ትንፋሽ ተነፈስሁ። ገና ዛሬ፣ አሁን ገና የእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠራጠርሁት። ወይ ስለ ንስሐ ምንም አላዉቅም፣ ወይ ደግሞ እግዚአብሔር ቂመኛ ነዉ
ስል አሰብሁ። እኔ የተማርሁት ሰዉ ፍጹም ተጸጽቶ ንስሐ ከገባ
ኃጢአቱ ሁሉ ፍጹም ይሰረይለታል የሚለዉን ነበር። ከእግዚአብሔር
ጋር የሚያደረገዉም እርቅ ፍጹም ይሆንለታል ሲባል አዉቃለሁ። ታዲያ እኔ ፍጹም የሆነ ጸጸት ተጸጽቼ ንስሐ አልገባሁም? ቀኖናዬንስ በሚገባ ወይስ እግዚአብሔር ፍጹም አምላክ መሆኑን አላመንሁም?
👍391
አንድ ተረት ትዝ አለኝ። ተረት አልሁት እንጂ ነገሩስ እዉነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ በደጉ ጊዜ ነዉ አሉ፡፡ በደጉ ነዉ በድሮዉ የሚባለዉ? እሺ በድሮዉ ጊዜ ነዉ አሉ፤ ትኩስ የማር እንጀራ ለመሸጥ አንድ ሽማግሌ
ወደ ገበያ ከቤት ሲወጡ፣ መዉጫቸዉ ላይ ጦጣን ተዝለፍልፋ ወድቃ አገኟት። ሽማግሌዉ ደግሞ ለአራዊቱም ለትላትሉም ሳይቀር አዛኝ
ኖረዋልና፣ ጦጣን ከወደቀችበት በሐዘኔታ አነሷት፡፡ ከዚያ ምክንያቷን ሲጠይቋት፣ ወደ ገበያ ለመድረስ ከሩቅ መነሳቷን እና እዚህ ስትደርስ እንደ ደከማት የማስመሰል እያቃሰተች ነገረቻቸዉ። እንዳለችዉ ግን
ደክሟት ሳይሆን፣ ሽማግሌዉ ባለ ማር መሆናቸዉን እያወቀች ለብልጠቷ ኖሯል የመዉጫቸዉን ሰዓት ጠብቃ መዝለፍለፏ። ቀጥላ አንድ የማታለያ ሐሳብ አመጣች። እሷ ማሩን ልትሸከም፣ እሳቸዉ ደግሞ እሷን ሊሸከሟት። ገና ሽማግሌዉ እሺም እምቢም ሳይሏት፣ ማሩን ነጥቃቸዉ
በራሷ ተሸከመችና ትከሻቸዉ ላይ ጉብ አለች፡፡ ሽማግሌዉም እንደ ፈለግሽ ብለዉ ጦጣዋን ከትከሻቸዉ ሳያስወርዱ መንገዳቸዉን ቀጠሉ። ይኸኔ
በራሷ ላይ ወደ ተሸከመችዉ ማር እጁን ሰደድ አድርጋ ያንን የማር
እንጀራ እየቆረሰች ማምሽክ ጀመረች። እዚህ ላይ ነዉ ጉዷ የፈላዉ እንግዲህ። ለካንስ በዚያ ትኩስ የማር እንጀራ ዓይኖች ላይ አልፎ አልፎ ንቦች አድፍጠዉበት ኖሯል። ጦጣ ሆዬ ብልጥ ሆና ሞታ፣ እንደ ለመደችዉ እጇን ደግማ ወደ ማር እንጀራዉ ስትሰድ ንብ ሆዬ እጇን ንድፍ! ይኼ ብቻዉን ነፍሷን ሊያንሰፈስፈዉ፣ ሌሎች ንቦችም ህዉ ብለዉ
ወጥተዉ ኹለቱንም ዓይኖቿን ድርግም!

ይኸኔ ጥፋቷ ተገለጠላት፡፡ ተጸጸተች፡፡ በእርግጥ ዘግይታለች። ቢሆንም ግን ጸጸቷ ከልብ ነዉ፡፡ እንደ ተጸጸተች ይቅር ይበሉኝ ብላ ሽማግሌዉ እግር ሥር ወደቀች፡፡ ይኼን ስታደርግ፣ ቢያንስ ቢያንስ ሽማግሌዉ ብርሃኗን እንደሚመልሱላት ማመኗን ያሳያል። የቅጥፈቴን ሀገሬ ሩቅ
ነዉ ብዬ ዋሸሁ እንጂ፣ እኔስ ደን በሚያስንቀዉ የጓሮዎ ጥቅጥቅ የወይራ ዛፎች ላይ ነዉ የምኖረዉ:: ወደ ዛፎችዎ በየለቱ እየመጡ ስለሚ ጎበኙን ያዉቁኝ ይሆን ብዬ ሰግቼ ነበር እንዲያዉም። አላወቁኝም እዉነት? ደንቆኛል። እባክዎ ስላታለልሁዎ ይማሩኝ” ብላ ተማጸነቻቸዉ::
ሽማግሌዉም አላሳፈሯትም! ይቅር ብለዉ ሸኟት። ዓይኗ ግን እንደ ጠፋ ቀረ አሉ።

ይኼን ተረት እንደ ሰማሁ በሽማግሌዉ ነበር ያዘንሁባቸዉ። ጦጣዋ ተወልዳ ያደገችዉ በጓሯቸዉ መሆኑን እያወቁ፤ ምናለበት እስኪ ገና
የመጀመሪያዋን ዉሽት ስትዋሽ ቢያስቆሟት ኖሮ? ሲጀመር ተናዳፊ ንቦች በማሩ ላይ ሲቀሩ ለምን ዝም አሉ? እሱም ይቅር፤ ምናለበት በማር እንጀራዉ ላይ ንቦች እንዳሉበት ቢነግሯት? እሺ እሱም ይቅር፤ ምናለበት
ይቅርታ ከጠየቀች እና ከእሳቸዉ ጋር ፍጹም የሆነ እርቅ ከታረቁ በኋላ ዓይኗን ቢያክሙላት? ዓይን አልባ ሆና ስትቀር አታሳዝናቸዉም? ቂመኛ
ቢሆኑ ነዉ ስል አሰብሁ። ሆነ ብለዉ መበቀላቸዉ ነዉ። ተበቅለዋታል።

ምንም እንኳን እግዚአብሔር በዚህ ሽማግሌ ይቅርና፣ በሰማይ በምድር ባለ በምንም የማይመሰል አምላክ መሆኑን ባምንም፣ እኔና ጦጣዋ ግን
አንድና ያዉ ነን። አይደለንም ወይ?

ሎቱ ስብሐት! ምኑን ከምን ነዉ የሚያሳስበኝ? ምን ዓይነት ፍርጃ ነዉ የፈረድሁት? ቆይ ከመቼ ወዲህ ነዉ ግን ለእንዲህ ያለ ክፉ መንፈስ ገረድ ሆኜ ያረፍሁት?...

ይቀጥላል
👍291😁1
አትሮኖስ pinned «#ገረገራ ፡ ፡ #ክፍል_ሰባት ፡ ፡ #በታደለ_አያሌው ...“በይ እሺ፡፡ በይ ደርሰሽ ነይ” የምርመራ ማዘዣዎችን ተቀብያት ስወጣ፣ ለአልትራሳውንድ ምርመራዉ ጨመር ያለ ዉሃ መጠጣቱ እንደሚጠቅመኝ ስለማዉቅ፣ ወደ ሆስፒታል ስመጣ ጀምሬዉ ያጋመስሁትን ኹለት ሊትር ዉሃ እየተጎነጨሁለት ወደ ቤተ ሙከራዉ ተመለስሁ። እንደ ፈራሁት ስዓቱ ሰዉ የማይበዛበት ሰዓት ሆኖ ይመስለኛል፣ የሚያማርር ወረፋ አልገጠመኝም።…»
#ምንዱባን


#ክፍል_ሃምሳ

#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

ከብርሃን ወደ ጨለማ

ዣን ቫልዣ ከፓሪስ ከተማ ባህር ውስጥ ነው የገባው:: ከባህር ውስጥ የገባ ዋናተኛ ሊጠፋ እንደሚችል ሁሉ እርሱም ሊጠፋ ይችላል፡፡ ከብርሃን ወደ ጨለማ ነው የተጓዘው:: በእጁ ፋኖስ ወይም ሌላ መብራት የለም፡፡
ሆኖም ከሞት አፋፍ ደርሶ የነበረው ዣን ቫልዣ ማንም ሊደርስበት ከማይችል
ሥፍራ ነው የሄደው:: ከመሃል ከተማ ወጥቶ ሰው ከማይደርስበት ገጠር ነው የገባው ለማለት ይቻላል፡፡ ከጫጫታና ከሁካታ ወደ ፀጥታ ነው የተሸጋገረው:: ከሞት ወደ ደኅንነት ነው የተዛወረው:: እንዲህ ያለው ነው መልካም አጋጣሚ የሚባለው:: ተፈጥሮ ሆን ብላ ዣን ቫልዣን ለማዳን ያዘጋጀችው ይመስላል፡፡
ማሪየስ ነቅነቅ እንኳን አላለም፡፡ ይሙት ወይም በሕይወት ይኑር
አይታወቅም፡፡ መሬት ሊወድቅ ሲል ዣን ቫልዣ ካነሳው ጀምሮ ሕሊናውን እንደሳተ ነው::

ዣን ቫልዣ ያለበትን ሥፍራ ለማወቅ መጀመሪያ ቀኝ እጁን፤ በኋላም ግራ እጁን ወደ ጐን ዘረጋ፡፡ በሁለቱም በኩል ግድግዳ ነካ፡፡ የቆመበትን ቦታ ጎን ስፋት በዚህ አረጋገጠ፡፡ ቀስ እያለ ወደፊት ተራመደ፡፡ መሬቱ ይርጠብ
እንጂ የተነጠፈ ድንጋይ በመሆኑ ቀዳዳ ነገር እንደሌለው ተረዳ፡፡ ስለዚህ የየቆሻሻ መውረጃው አሠራር እንዴት እንደሆነ ስለሚያውቅ ምን ውስጥ
እንደገባ ያውቃል፡፡

አሁን ካለበት አካባቢ እጅግ በጣም አነስተኛ የሆነ ብርሃን በዚያች በብረት ክዳን በኩል ይገባ ስለነበር እንደ ውጋገን ያለ ነገር ይታያል፡፡ስለቦታው ለማወቅ ፈልጎ ጥቂት ወደፊት በተራመደ ጊዜ ግን ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ ሆነበት:: ማሪየስን እንደገና ተሸክሞ ሃምሳ እርምጃ ያህል ከተራመደ
በኋላ ቆም አለ፡፡ ከቆሻሻ መውረጃ መንታ መንገድ ላይ ደረሰ፡፡ እንዲያውም ከግድግዳ ጋር ሊጋጭ ሲል ለትንሽ ነው የዳነው:: የቀኙን ወይስ የግራውን
መንገድ ይከተል? በዚያ በጨለማ ምን አይቶ ይወስን? የቀኙን መረጠ፡፡

የማሪየስ ሁለት እጆችና ጭንቅላት ወደኋላ ተንጠልጥለዋል፡፡ ዣን ቫልዣ የልጁን ሁለት እግሮች ከፊት አድርጎ ትከሻው ላይ ነው የተሸከመው::የልጁን እግሮች በግራ እጁ ጥርቅም አድርጎ ይዞ በቀኙ እጁ ከፊት ለፊቱ
ያለውን እየዳበሰ ይሄዳል:: የተቻለውን ያህል እየፈጠነ በቶሉ ነው የሚራመደው:: የማሪየስና የዣን ቫልዣ አንገት በማሪየስ የረጋ ደም ተጣብቀዋል::

ጥቂት እንደተጓዙ የደረሱበት ሥፍራ ጥቂት ሰፋ ያለ ነበር፡፡ ባለፈው ቀን የዘነበው ዝናብ ውሃ ተሟጥጦ ስላላለቀ ዣን ቫልዣ የሚራመድበት ውሃ መጠን ከፍ አለ፡፡ በቶሎ ለመራመድ ስላስቸገረው በጣም ዝግ አለ፡፡
አንዳንዴ በአንድ እጁ ግድግዳውን ተደግፎ ካልሆነ እግሩን ማነቃነቅ አይችልም::በጭንቀት ተውጦ አልቆመም:: እምነቱን ፈጣሪ ላይ ጥሎ በቀንድ አውጣ ጉዞ መንገዱን ቀጠለ፡፡ ግን የፈሳሽ መጠን ከፍ ብሎ ከጉልበቱ አለፈ::
ጥቂት ሲቆይ ከዚያም ከፍ አለ፡፡ ለመመለስና ቀደም ሲል የተወውን የግራ መንገድ ለመያዝ አስቦ «አይሆንም» ብሎ በመወሰን አሁንም ወደፊት ቀጠለ፡፡ ብዙ በተጓዘ ቁጥር ድካም እየጠናበት ሄደ::

ዣን ቫልገዥ ከረሃብ፣ ከሸክምና ከመንገዱ ይበልጥ የጎዳው ውሃ
ጥሙ ነበር፡፡ ውሃ ላይ እየተራመደ ውሃውን ሊጠጣው ስለማይችል ባህር ላይ እየተጓዘ በውሃ ጥም እንደሚቃጠል ሰው እርሱም በውሃ ጥም ተቃጠለ፤ ነደደ፡፡ ምንም እንኳ እድሜው እየገፋ ቢሄድም ጉልበቱ አልተቀነሰም::
አሁን ግን ሸክሙና የውሃ ጥሙ ያንን ብርቱ ጉልበት አሳጣው:: ጉልበቱ እየቀነሰ ሲሄድ የተሸከመው ሰው ክብደት የጨመረ መሰለው:: እንደ
ጥምብ ስለከበደው «ማሪየስ ሞቶ ሊሆን ይችላል» ሲል አሰበ፡፡ ሰዓቱ ወደ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ይሆናል።

አሁን የደረሰበት አካባቢ የፈሳሹ ጥልቀት ከመጨመሩም በላይ የጉኑም ርቀት ሰፍቶአል:: ከመሃል ሆኖ የግራና ቀኝ ግድግዳ ሊነካ አልቻለም::መንታ መንገድ ላይ ስለደረሰ አሁን ወደ ግራ ታጠፈ:: ውሃ ያልደረሰበት ሾል ያለ ግድግዳ በማየቱ ማሪየስን ከዚያ አሳረፈው፡፡ በአካባቢው ቀዳዳ
ነገር ስለነበረና በዚያ በኩል ብርሃን በመግባቱ ማሪየስን ያሳረፈበት ግምብ በጉልህ እንኳን ባይሆን በጭላንጭል ታየው:: እንዲያውም በደም የተጨማለቀውን የማሪየስን ፊት ለማየት ቻለ፡፡ ማሪየስ ዓይኑን ጨፍኖአል።ፀጉሩ ያልታጠበ የቀለም ብሩሽ ይመስል በረጋ ደም ተቆጣጥሮ ግምባሩን ሸፍኖታል፡፡

ከአፉ ዳርና ዳር የሳሳ የረጋ ደም ይታያል:: እጁ ተዝለፍልፎ
ከግምቡ ላይ ተንጠልጥሎአል፡፡ በተመታበት አካባቢ በረጋ ደም ሸሚዙና ኮቱ ከሰውነቱ ጋር ተጣብቆአል፡፡ ዣን ቫልዣ የማሪየስን ልብስ ከፋፍቶ
በእጁ የማሪየስን ልብ ትርታ አዳመጠ፡፡ ልቡ ይመታል፡፡ ሕይወቱ አለች ማለት ነው:: ዣን ቫልዣ የራሱን ሸሚዝ ቀድዶ የማሪየስን ቁስል ከጠራረገ
በኋላ በተቻለው ሁሉ ጠበቅ አድርጎ አሰረለት::

ኪሱን ሲደባብስ ሁለት ነገሮችን አገኘ፡፡ እነርሱም የማሪየስ የማስታወሻ ደብተርና ካለፈው ቀን ጀምሮ ኪሱ ውስጥ የተረሳው ቁራሽ ዳቦ ነበሩ፡፡ደረቁን ዳቦ ዣን ቫልዣ በላው:: የማስታወሻ ደብተሩን በጭላንጭል ብርሃን
ወደሚገኝበት አቅጣጫ ወስዶ ተመለከተው:: ከመጀመሪያው ገጽ ላይ የሚከተለው ማስታወሻ ተጽፎ ነበር::

«ስሜ ማሪየስ ፓንትመርሲ ይባላል:: ሬሣዬን ለአያቴ ለመሴይ
ጊልኖርማንድ ውሰዱና ስጡልኝ:: የአያቴ እድራሻ ካልቬር ከሚባል ጎዳና የቤት ቁጥር ስድስት ነው::
ዣን ቫልዣ ለተወሰነ ጊዜ ፈዝዞ ቀረ:: የማስታወሻ ደብተሩን ከማሪየስ ኪስ ውስጥ መልሶ አስቀመጠው:: ዳቦውን ስለቀመሰ ነፍሱ ትንሽ መለስ አለች ማሪየስን አንስቶ እንደገና ተሸከመው:: የማሪየስን ጭንቅላት ቀስ
ብሎ ከቀኝ ትከሻው ላይ አሳረፈው:: ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከአንድ ከተወሰነ ሥፍራ ሲደርስ ከባድ ጨለማ ሆነበት:: አልፎ አልፎ ይታዩ የነበሩት ለአየር
መግቢያ እየተባለ የሚሠሩት ቀዳዳዎች ጨርሰው ስለጠፉ እግር ቢወጉ እንኳን የማይታይ ጨለማ ሰፈነ፡፡

ዣን ቫልዣ አሁን የደረሰበት መሬት በደለል የተሞላ መሆኑን
ተገነዘበ፡፡ ከላይ ግን በውሃ ተሞልቷል፡፡ ደለሉ እግሩን ያዘው:: ማሪየስ እየደከመ ሄደ፡፡ እርሱም ቢሆን ጉልበቱ አልቆ በጣም እየደከመ ነው:: ባለው ኃይል በመጠቀም ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከሥር የዘቀጠው ጭቃ መጠን
እየጨመረ ሄደ፡፡ እስከ ጉልበቱ ሊደርስ ምንም ያህል አልቀረውም፡፡እየጨመረ የሄደው ጭቃው ብቻ ሳይሆን ወሃውም ስለነበር እስከወገቡ ደረሰ፡፡ ሆኖም ዣን ቫልዣ አሁንም ተስፋ ሳይቆረጥ ያንን ከሞት አፋፍ
የደረሰውን ሰው ተሸክሞ ተጓዘ፡፡
የውሃው መጠን ከብብቱ ሥር ደረሰ፡፡ የመንቀሳቀሱ ጉዳይ በጣም ችግር ሆነ፡፡ ግን ማሪየስን በሁለት እጁ አጥብቆ ይዞ አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ ባለው ኃይል በመጠቀም ጥቂት ከተራመደ በኋላ ከነበረበት ቆም
ብሎ ትንፋሹን ዋጥ አደረገ፡ እንደገና ጉዞውን ቀጠለ፡፡ የውሃው መጠን ከትከሻው ደረሰ፡፡ ማሪየስ እንዳይታፈን ከእግሩ ወደ ውሃው ጎተት በማድረግ
ከአንገቱ ቀና አደረገው:: ራሱም ቢሆን አንጋጣ ነው የሚራመደው::
ድንገት እግሩ ከአንድ ነገር ጋር ተጋጨ፡፡ ያልተጋጨው እግሩን
👍81👏1
ወደፊት በማምጣት ሲነካው እንደ ደረጃ ያለ ነገር መሆኑን ተረዳ፡፡ ቀስ ብሎ አንድ እግሩን ከደረጃው ላይ አሳረፈው:: ሌላውን እግሩን አንስቶ ከሌላ ደረጃ ላይ አሳረፈ:: እንዲህ እንዲህ እያለ ከተዋጠበት ውሃ ውስጥ ወጣ፡፡
ደረጃው ወደ ጎን የሚሄድ ስለነበር ጥቂት እንደተራመደ የብርሃን ጭላንጭል ካለበት ደረሰ፡፡ ደረጃው አልቆ ጥቂት ውሃ ካለበት ከፍሳሽ መውረጃ መንገድ
ደረሰ፡፡ አሁን አንድ ድንጋይ መሳይ ነገር አደናቅፎት እንደ መውደቅ ብሎ በጉልበቱ ተንበረከከ፡፡ ላለመውደቅ ባደረገው ጥረት ባንድ እጁ መሬቱን ያዘ፡፡ ከዚያ እንዳለ ፈጣሪውን በመማፀን ጸሎት አደረሰ፡፡

ከጸሎቱ በኋላ ተነስቶ ቆመ:: ብርድ ብርድ ብሎት ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡ አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ ወደፊት ተራመደ:: ሆኖም በጣም እየደከመው
ስለሄደ ሦስት ወይም አራት እርምጃዎችን ከተራመደ በኋላ ትንፋሹን ለመዋጥና ሰውነቱን ለመሰብሰብ ቆም ለማለት ተገደደ:: አንዳንዴም ሸክሙን
ከግድግዳው ጋር በማጣጋት ያርፍ ጀመር፡፡ ሲያመቸውም ማሪየስን አንዴ በግራ ትከሻው ከዚያም ወደ ቀኝ ትከሻው አዞረ:: ተስፋው እየመነመነ ቢሄድም የዝግታ ጉዞውን ግን አላቋረጠም:: አንገቱን ቀና ሳያደርግ ብዙ
ተጓዘ፡፡ አቀርቅሮ ይጓዝ ስለነበር ከግምብ ጋር ተጋጨ:: ከአንገቱ ቀና አለ::

ቀና ሲል በሩቁ የብርሃን ጭላንጭል ተመለከተ፡፡ መውጫ ቀዳዳ መሆኑን ዣን ቫልዣ አወቀ፡፡

ተስፋው ደነደነ፤ ሽክሙም ቀለለለት:: ድካሙም የተወገደለት
መሰለው:: በተስፋ የተሞላች ሕይወት ብርቱ ናትና ማዝገሙን ትቶ ፈጠን ያለ እርምጃ ወሰደ፡፡
ከመውጫው ሲደርስ ቆም አለ፡፡ መውጫ ቀዳዳው በክብ ነገር ተደፍኖአል፡፡ በቀላሉ የሚከፈት አይደለም:: ጠንካራው የብረት
ክዳን በመቀርቀርያና በቁልፍ በመያዙ ከውጭ ሰው ካልከፈተለት ዣን ቫልዣ ሊወጣ አይችልም:: ጊዜው ለዓይን ያዝ የሚያደርግ ሰዓት ቢሆንም
ከውስጡ ሆኖ አላፊና አግዳሚ ለመለየት ይቻላል፡፡ በቀዳዳ ሲመለከት ቦታውን የሚያውቀው ለመሆኑ አልተጠራጠረም:: ጭር ያለ ሰፈር ነው::

ደረቅ ካለው የግድግዳ ጠርዝ ላይ ማሪየስን አሳረፈው፡፡ ክዳኑን በሁለት እጁ ይዞ ለመክፈት ሞከረ፡፡ ክዳኑ አልተነቃነቀም፡፡ ሊከፈት እንደማይችል አረጋገጠ።

ከእስር ቤት ሊያመልጥ ቢችልም ከዚህ ለማምለጥ አለመቻሉን በተረዳ ጊዜ ተስፋ ቆረጠ፡፡ ያ ሁሉ ልፋት እስከዚህ በመሆኑ ቀኑ ጨለመበት:: . የማሪየስና የእርሱ ሕይወት መጨረሻ እንደሆነ ተረዳ::

ከተነጠፈ ደረቅ ድንጋይ ላይ ተዘረረ፡፡ ማሪየስ ከአጠገቡ ነበር የተኛው:: ቀና ብሎ አንገቱን ከጉልበቱ መካከል በማስገባት ቁጭ አለ፡፡ ከዚያ ቁጭ ብሎ ስለማን ነበር የሚያስበው? ስለማሪየስ ወይም ስለራሱ? አልነበረም::

ስለኮዜት ነበር የሚያስበው::


ዣን ቫልዣ የመውጫ ቀዳዳ ባጣበት በዚያች ቀውጢ ሰዓት፣ ከዚያ ሁሉም ነገር ጭር ካለበትና ማንም ሆነ ምንም ነገር በማይጠበቅበት ሥፍራ
ተስፋ ቆርጦ በተቅበጠበጠበት ወቅት ሳይታሰብ በድንገት አንድ ሰው ከኋላው መጥቶ ትከሻውን ይነካል። በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ «ትርፍ የእኩል» ይለዋል::

ከዚያ ጨለማ ውስጥ የሰው ድምፅ! ሰው ተስፋ በሚቆርጥበት ጊዜ የሚያየውን ሕልም የሚስተካከል ነገር የለም:: ዣን ቫልዣ የሚያልም መሰለው:: የኮቴ ድምፅ አልሰማም «ሊሆን ይችላል» ብሎ በማሰብ ከአንገቱ
ቀና አለ፡፡

አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞአል::
ሸሚዝ ለብሷል፤ ጫማ ግን አላጠለቀም:: ጫማዎቹን በግራ እጁ አንጠልጥሎ ከትከሻው ላይ አድርጎአቸዋል:: ኮቴው ሳይሰማ ዣን ቫልዣ ከነበረበት ለመድረስ ሲል ጫማውን ለማውለቁ አያጠራጥርም፡፡

ዣን ቫልዣ አላመነታም፡፡ ሰውዬውን በአንድ ጊዜ ነው የለየው፡፡ ይህ ሰው ቴናድዬ ነበር፡፡ ግን ቴናድዬ ዣን ቫልዣን እንዳልለየው አውቆአል።

ለአጭር ጊዜ ሁለቱ ሰዎች ተፋጠጡ፡፡ ላያቸው ሁለቱም በየፊናቸው አንዱ የሌላውን ጉልበት በዓይነ ገመድ የሚለካ ይመስላል፡፡ ቴናድዬ ቀድሞ
ተናገረ።

«እንዴት አድርገህ ነው ከዚህ ጉድጓድ የምትወጣው?»
ዣን ቫልዣ መልስ አልሰጠም:: ቴናድዬ ቀጠለ፡፡

«መቀርቀሪያውን ለማላቀቅ አይቻልም:: ሆኖም ከዚህ መውጣት አለብህ፡፡»

«እውነትህን ነው» ሲል ዣን ቫልዣ ተናገረ::

«እንግዲያውማ ትርፍ የእኩል ነዋ!»

«ምን ማለትህ ነው?»

«ሰውዬውን ገድለኸዋል፧ ግን አሁን ምን ይደረጋል! በእኔ በኩል ግን
የተቀረቀረውን ቀዳዳ የምከፍትበት ቁልፍ አለኝ፡፡»

ቴናድዬ ንግግሩን አቁሞ ወደ ማሪየስ ተመለከተ፡፡ ከዚያም ንግግሩን ቀጠለ::

«አላውቅህም፣ ግን ልረዳህ እፈልጋለሁ፡፡ የሟቹ ጓደኛ ልትሆን
ትችላለህ፤ ግን እኔን አያገባኝም፡፡»
ነፍሰ ገዳይ አድርጎ እንደ ወሰደው ዣን ቫልዣ ገባው:: አሁንም
ቴናድዬ መናገሩን ቀጠለ፡፡

«ስማ ጓድ:: ይህን ሰው ስትገድለው ኪሱ ውስጥ ምን እንዳለ ለማየት እንደሆነ አልጠራጠርም:: ያገኘኸውን ለሁለት ከፍለህ ስጠኝና
በሩን እከፍትልሃለሁ::»
ቴናድዬ ይህን እንደተናገረ ከኪሱ ውስጥ ትልቅ ቁልፍ አወጣ፡፡
«በሩ እንዴት እንደሚከፈት ለማየት ትፈልጋለህ?» ሲል ጠየቀው::
ዣን ቫልዣ እንደተዘጋ ቀረ:: የሚያየው ነገር ፈጣሪ አስተካከሉ
ያምጣው ወይም ደግሞ የሰይጣን ሥራ ይሁን ግራ ተጋብቶ ቆሞአል።

«ይህ ርኩስ ፍጠር የመለኮት ኃይል ሊከሰትበት የተፈጠረ ጉድ ነው ወይስ ምንድነው?» ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡

«አሁን ሥራችንን እንጨርስና ያገኘኸውን ጥቅም እንካፈል::

መክፈቻውን አሳየሁህ:: አንተ በተራህ ገንዘቡን አሳየኝ፡፡»

ዣን ቫልዣ ከኪሱ ውስጥ ገባ፡፡ ጥቂት ሣንቲሞች ብቻ ናቸው
ያሉት:: ኪሱን ገለበጠው: በዚያ በቆሻሻ ነገር ርሷአል፡፡ ሁለት ባለአምስት ፍራንክና አምስት ወይም ስድስት ሱስ አገኘ::

ቴናድዬ በጣም አሽሟጠጠው::

«ወዳጄ፣ ይህን ሰው ለዚህ ብለህ እንዳልገደልከው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡»

ቴናድዬ የዣን ቫልዣንና የማሪየስን ኪስ መበርበር ጀመረ፡፡ ዣን
ቫልዣ ብርሃን በብዛት ወደሚገኝበት ሄዶ ፊቱ እንዳይታይ ብርቱ ጥረት አደረገ፡፡ ቴናድዬ በብርበራው ብዙም ገንዘብ አላገኘም:: ግን ለወደፊቱ !
ተንኰል እንዲረዳው ዣን ቫልዣ ራሰን ከብርሃን ለመደበቅ ሸሸት፣ ሸሽት ሲል ቴናድዬ ከማሪየስ ልብስ ቀስ ብሉ ቀራጭ እራፊ ጨርቅ ወስደ፡፡ ጨርቁን ምናልባት ወደፊት ገዳይንና ሟችን ለማመላከት ይረዳኝ ይሆናል
ብሎ የወሰደው ነበር::

«እውነትም ከዚህ ሌላ ገንዘብ አልያዝክም» ብሉ ከተናገረ በኋላ
«እኩል እንካፈል» ያለውን ረስቶ ገንዘቡን ሁለ ከኪሱ ውስጥ አደረገ።

«እንግዲህ ወዳጄ መውጣት አለብህ:: የመውጫውን ሂሣብ እንደሆነ ከፍለሃል:: ትክክለኛ ፍርድ ይመስለኛል» ካለ በኋላ ከት ብሎ ሳቀ፡፡ ዣን ቫልዣ ማሪየስን ለመሸከም ሲታገል ቴናድዬ ረዳውና እንዲከተለው ምልክት ሰጠው፡፡ ቴናድዬ ዓይኑን በማሾለክ ግራና ቀኙን
ተመለከተ፡፡ ከዚያም የተቆለፈውንና ከጉድጓድ መውጫ የሆነውን ክብ ነገር በያዘው ቁልፍ ከፈተ፡፡ መውጫውን ሙሉ በሙሉ ሳይሆን በከፊል ገርበብ
አድርጎለት ቴናድዬ ወደ መደበቂያው ተመለሰ፡፡ ዣን ቫልዣ ከጉድጓዱ ስለወጣ እሱና ማሪየስ እንደገና ንጹህ አየር ተነፈሱ::
👍141😁1
ከወንዝ ዳር ነው የወጡት:: አካባቢው ጭር ብሎአል፡፡ የወፎች ዝማሪ ግን በብዛት ይሰማል፡፡ ከወንዙ ውሃ ጨልፎ የማሪየስን ፊት አራሰው።
አሁንም ዓይኑን አልገለጠም:: በከፊል በተከፈተው አፉ ግን ይተነፍሳል።ዣን ቫልዣ ወደ ወንዝ ተጠግቶ እንደገና ውሃ ለመጭለፍ ጎንበስ ሲል አንድ ነገር ከበደው:: አለ አይደል ፤ ባናይ እንኳን አጠገባችን አንድ ነገር እንዳለ የሚሰማንና የሚከብደን ዓይነት!:: ምን እንዳለ ለማየት ዞር አለ።

አንድ ረጅም ሰውዬ ካፖርት ለብሶና ቆመጥ ይዞ ከኋላው ቆሞአል።የያዘው ዱላ በጣም ያስፈራል::

ዣቬር እንደሆነ ለማወቅ ዣን ቫልዣ ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ቴናድዩን አምልጦ ከዣቬር ላይ መውደቅ! እስካሮኛ አጋጣሚ!

የሚገርመው ዣቬር ዣን ቫልዣን አላወቀውም:: ዣን ቫልዣ ከዚያ
መከራና ስቃይ በኋላ ከመጠን በላይ ተለዋውጧል፡፡

ቆመጠን እንደጨበጠ ማነህ አንተ?» ሲል ዣቬር ጠየቀው፡፡
«እኔ!››
«ማን?»
«ዣን ቫልዣ!»

ዣቬር ዱላውን በጥርሱ ይዞ የዣን ቫልዣን ትከሻ በሁለት እጁ
ጨምድዶ ያዘ፡፡ እውነትም ዣን ቫልዣ ነው ወይስ አይደለም በማለት ፊቱን አገላብጦ አየው:: ራሱ ነው ፣ ምንም ስህተት የለበትም፡፡ የዣቬር ፊት ተለዋወጠ፡፡

ዣን ቫልዣ ቃል ሳይናገር በነብር ጥፍር እንደተያዘ እንሰሳ ዝም ብሎ
ቆመ:: በኋላ ግን ተናገረ::

«አዛዥ ዣቬር» አለ፤ «አሁን ያዝከኝ፡፡ ከዚህም በላይ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የአንተ እስረኛ እንደሆንኩ ገምቼ ነበር፡፡ ከአንተ ለማምለጥ አድራሻዬን
ደብቄህ ነበር፡፡ አሁን ልትወስደኝ ትችላለህ:: ግን አንድ ነገር ፍቀድልኝ፡፡ የፈለግኸውን ፈጽምብኝ:: ብቻ ይህን ሰው ተሸክሜ ከቤቱ ላድርሰው::

የዣቬር ፊት ተኮማተረ:: እምቢ ግን አላለም:: ዣን ቫልዣ ከኪሱ
መሃረብ ካወጣ በኋላ ውሃ ውስጥ ለመንከር ጎንበስ አለ፡፡ ውሃው ካለበት ደርሶ መረሃቡን አራሰ፡፡ በራስ መሃረብ ከማሪዩስ ግምባር ላይ ደርቆ የነበረውን ደም ለማስለቀቅ ሞከረ::

«ይህ ሰው ከዚያ ምሽግ ውስጥ ነበር» አለ በጣም ዝግ በማለት
በራሱ ይነጋገር ይመስል፡፡ «ማሪየስ በመባል የሚታወቀው እርሱ ነው:: ማሬይ ከሚባል ስፍራ ይኖራል፡፡ ከአያቱ ጋር ነው የሚኖረው ፤ ግን የአያቱ ስም ማን እንደሆነ ተዘነጋኝ::

ከዚያም ዣን ቫልገዢ የማሪየስን ኪስ ዳበሰ፡፡ የማስታወሻ ደብተሩን
አውጥቶ ገለጠው:: ማሪየስ በእርሳስ የጻፈበትን ገጽ ፈልጎ ለዣቬር አሳየው::ዣቬር ማሪየስ የጻፈውን ሲመለከት «ጊልኖርማንድ ካልቬር ጉዳና...
ቁጥር 6» የሚለውን አድራሻ አነበበ፡፡

«ባለሠረገላ» ሲል ተጣራ::

ዣቬር የማሪየስን የማስታወሻ ደብተር ከኪሱ ውስጥ ጨመረ::
ወዲያው ብዙም ሳይቆይ ሦስት ሰው ሊያስቀምጥ የሚችል ሠረገላ መጣ:: ማሪየስ፣ ዣን ቫልገናና ዣቬር ተሳፈሩ:: ከኋለኛው መቀመጫ
ማሪየስ እንዲጋደም ተደረገ፡፡ በሩ ተዘግቶ ጉዞ ቀጠሉ።

ባለሠረገላው ፈረሶቹን በመግረፍ ፍጥነታቸውን እንዲጨምሩ አደረገ።ሠረገላቸው ውስጥ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ማሪየስ ሳይነቃነቅ ተዘርሮ ተኝቷል።አንደኛው እጁ ተዝለፍልፎ ወደ መሬት ተንጠልጥሎአል:: ሲያዩት የሬሳ ሣጥን የሚጠብቅ አስከሬን ነበር የሚመስለወ:: ዣን ቫልዣ ከሰው ጥላ ዣቬር ደግሞ ከድንጋይ የተሰሩ ይመስላሉ

ከማሪየስ ቤት ሲደርሱ ውድቅት ነው፡፡ ዣቬር በመጀመሪያ ወረደ፡፡
የብረት ቆመጡን ይዞ ነው የወረደው:: በሩ ገርበብ ብሎ ስለነበር ዣቬር ገፋ አደረገው
የቤት ሠራተኛ ሻማ ይዞ ብቅ አለ::

የሠረገላ ነጂና ዣን ቫልዣ እየተረዳዱ ማሪየስን አወረዱት። ዣቬር በንቀት ዓይን እያየ ሠራተኛውን ጥያቄ ጠየቀው::

«እዚህ ቤት ውስጥ ጊልኖርማንድ የሚባል ሰው አለ?
አሉ! ምንድነው የሚፈልጉት? ምን ልበላቸው?
«ልጃቸውን ይዘን መጥተናል፡፡»
«ልጃቸው?» ሲል ሠራተኛው በመገረም ጠየቀ::
«ልጁ ግን ሞቷል፡:»

ዣን ቫልዣ በጭቃና በሌላም ቆሻሻ ነገር እንደዚያ ለዓይን በሚያስፈራ ዓይነት ቦክቶና ቆሽሾ ወደ ሠራተኛው እያየ አለመሞቱን በጥቅሻ አስረዳው።

ሠራተኛው ግን የዣቬርን አባባልም ሆነ የዣን ቫልዣ ጥቅሻ ሊገባው አልቻለም:: ዣቬር ንግግሩን ቀጠለ፡፡

«ጦርነቱ ከተካሄደበት ሥፍራ እየተዋጋ ነበር፤ ራሣውን ውሰዱ::
ከዚያ ነው ሕይወቱ ያለፈችው:: በል አሁን ሂድና አባቱን ቀስቅሳቸው:: .

ሠራተኛው ከቆመበት አልተንቀሳቀሰም::

«ለምን አትሄድም?» ሲል ዣቬር ጮኸበት፡፡ ወንዱ ሠራተኛ ሴትዋን
ሠራተኛ፣ እርስዋ ደግሞ የማሪየስን አክስት ቀሰቀሱ:: አያቱን ይተኙ በማለት አልቀሰቅስዋቸውም::

ማሪየስን በሸክም ወደ አንደኛ ፎቅ አው'ጥተው አስተኙት:: ሌትዋ
ሠራተኛ ሐኪም ፍለጋ ሄደች፡፡ ሌላዋ ሠራተኛ ማሪየስን ለማልበስ ቁም ሣጥን ከፈተች:: ልክ እርስዋ ቁም ሳጥን ስትከፍት ዣቬር እጆቹን ከዣን ቫልዣ ትከሻ ላይ አሳረፈ:: ለምን እንደያዘው ገባው:: ሁሉም ተያይዘው ወደ ምድር ቤት ወረዱ፡፡ ከሠረገላው ውስጥ ተመልሰው ገቡ ፤ ሠረገላውም ተጓዘ፡፡ ዣን ቫልዣ ከፊት ዣቬር ከኋላ ሁነው መንገድ ቀጠሉ፡፡

«አዛዥ ዣቬር» ኣላ ዣን ቫልዣ ፤ «አሁንም አንድ ነገር ልጠይቅህና
ፍቀድልኝ::»

«ምን?» ሲል ዣቬር ጠየቀው::

«ለአንዲት ደቂቃ ከቤቴ ልሂድ:: ከዚያ በኋላ አንተ የፈለግኸውን
በእኔ ላይ ትፈጽማለህ፡፡»

ዣቬር ለጥቂት ሴኮንዶች ዝም አለ፡፡ አገጩን ካፖርቱ ኮሌታ ላይ
በኦሳርፎአል፡፡ ወደ ውጭ ተመለከተ፡፡

«ሰማህ ጎበዝ፤ ከአርሜ ጎዳና ላይ ወደሚገኘው የቤት ቁጥር 7
እንሂድ፡፡»

ሥፍራው ራቅ ያለ ቢሆንም ከቤቱ እስኪደርሱ ቃል አልተለዋወጡም:: ጉዞው የዝምታ ነበር፡፡ ከቤቱ እንደደረሱ ሠረገላው ከበራፍ ቆመ:: ዣቬርና
ዣን ቫልዣ ወረዱ፡፡ ወደ ቤቱ አመሩ፡፡ ዣን ቫልዣ በሩን በመምታት አንኳኳ፡፡ በሩ ተከፈተ::
«ይኸውልሃ ግባ» አለ ዣቬር፤ «እኔ ከዚህ እጠብቅሃለሁ» በሚል
አመለካከት::
ዣን ቫልዣ ዣቬርን ቀና ብሎ አየው:: ዣቬር ትንሽ ተለወጠበት፡፡
ዣን ቫልዣ በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ፡: ወደ ፎቅ ወጣ፡፡ ግን በጣም
ደክሞት ስለነበር በጣም ዝግ ብሎ ነው የወጣው::
«ለምንድነው በጨለማ እንደዚህ መስኮቶቹ የተበረገዱት?» ሲል
ሠራተኛዋ ላይ ጮኸ፡፡ በመስኮቱ ወደ ውጭ ተመለከተ:: ግራ ቀኙን አየ::
በጣም የሚገርመው ከበሩ አጠገብ ዣቬር ኣልነበረም::

💫ይቀጥላል💫
👍23
#ገረገራ


#ክፍል_ስምንት


#በታደለ_አያሌው

...ክፉ ያሳሰበኝን መንፈስ እከድከ ሰይጣን እያልሁ በልቤ ደጋግሜ ጸልዬ አስታገስሁት። ቀጥዬም ሰላም ለኪን ደገምሁበት እና ከሆስፒታል ወጣሁ። እንደ ወጣሁ የሆነብኝን ሁሉ የምነግረዉ ስፈልግ ከሁሉ ቀድሞ
ሐሳቤ ላይ የገባልኝ ሰዉ ባልቻ ነበር፡ እመዋን አቆይቼ ማለቴ ነዉ።ለእሷስ ያለፈዉ ይበቃታል፡ የሆስፒታሉንም ነግሬ ዳግመኛ ቅስሟን ልሰብረዉ አልፈልግም።

በእርግጥ እህትና ወንድሞቼም ነበሩልኝ። ጓደኞቼ ሁሉ አሉ። እሽቴም ቢሆን እኮ አለ የኖረዉ ቢኖርም፣ በተለይ አሁን ስላንጨዋለለኝ ፈታኝ ጉዳይ ለማማከር ግን፣ ከምድር ማንም እንደ ባልቻ የሚሆንልኝ ሰዉ
አይታየኝም: እሱ ብቻ ነዉ የጭንቄን መጠን ልክ እንደ ነገርሁት፣ እንዲያዉም ከነገርሁት አልፎ የሚገነዘብልኝ። ለማባበል
አይሸነግለኝም። ማባበል ከፈለገም እንደ'ሱ የሚያዉቅበት የለም። ጆሮዉ የተለየ ነዉ። ጭጭ ብሎ ሲያዳምጥ ብቻ ከጭንቅ ይፈዉሳል። እኔ ራሴ
እንኳን ስለ ራሴ የማላዉቀዉን ከእመዋ ቀጥሎ የሚያውቅልኝ ሌላ ሰዉ አላዉቅም: ባልቻ ብቻ:: እንዲያ ቢሆንም ግን፣ እሸቴም መስማት ስላለበት ኹለቱንም ወደማላጣበት ወደ ሲራክ-፯ ማዕከል ሄድሁ።

“አባትዮ” አልሁት፣ ወደ ትልቁ የማኅበሩ ሕንጻ እየተቃረብሁ ሳለ ወደ ባልቻ ስልክ ደዉዬለት።

“አቤት ልጅየዋ”

“ለአንድ አፍታ ፈልጌህ ነበር”

“መቼ”

“አሁን”

“ዉይ፣ አሁን እንኳ አንዲት የጀመርኋት ሥራ አለችብኝ: ባይሆን ይቺን እንደ ጨረስሁ ልደዉልልሽ?”

“በማርያም! አሁኑኑ ነዉ የምፈልግህ፤ ይልቅ ቶሎ ናና ጉዴን ስማልኝ'

“እህ፤ እየነገርሁሽ?”

“ስሞትልህ! ከእሸቴ ጋር እዚሁ አንደኛ ፎቅ ባለዉ ምግብ ቤት
ብትመጡልኝ፣ የምጋብዛችሁ አታዉቁትም: አንተስ ምናለ ለአንዳንዴስ እንኳን ንፋስ ቢያገኝህ? ሁልጊዜ እዚያ ዉስጥ ተቀብረህ” አልሁት፣ ለግብዣዬ ያለዉን ከበሬታ ዘንግቶ ላለመምጣት ሲያቅማማ በዚያም ላይ ሰዓቱ የምሳ ስለሆነ ሦስታችን አብረን የምንበላበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ይሆንልናል። እንዳሰብሁት፣ ብዙም ሳያስጠብቁኝ ከእሸቴ ጋር ፊት እና
ኋላ ሆነዉ መጡልኝ፡

“አንቺ፤ ብለሽ ብለሽ ደግሞ እንዴት እንዴት ነዉ ያናገርሽኝ? እንደ ልጅ ና ከረሜላ ልግዛልህ ማለት እኮ ነዉ የቀረሽ አሁንማ አሁንማ” አለኝ በጨዋታ፣ ወንበር ስቦ ከአጠገቤ እየተቀመጠ፡ መልስ ከለከልሁት

“አንቺ? ምንድነዉ ደግሞ ለንቦጭሽ የታላቁን ንጉሥ አወዳደቅ ወድቋልሳ: ገና ለገና እርምሽን ልትጋብዥን ብትይ፣ ከአሁኑ ማኩረፍሽ ነዉ? አየህልኝ እሽቴ? ገና ከአሁኑ እንዲህ ከሆነች፣ ሂሳቡን ስትከፍልማ
እንደ ጨዉ ሟሙታ ወደ መሬት መስረጓ ነዉ በለኛ”

ወድጄ አይደለም ዝም ያልኋቸዉ ሆስፒታል የጀመሩኝ ክፉ ክፉ የሚባሉ ሐሳቦች ሁሉ አሁንም አሁንም ወደ ልቡናዬ እየመጡ ግብግብ ገጥመዉኛል፡ እንደ ምንም ጥርሴን ለመፈልቀቅ ሞከርሁ። የዉጤቱን ወሬ ከምሳ በኋላ መንገሩን ስለመረጥሁ፣ በግድ ፈገግ ለማለት እየታገልሁ
ነዉ፡ ብቻ የሆነ ያልሆነዉን እየቀላቀልሁ የጨዋታ ወሬ ለማምጣት ተዉሸለሸልሁ

“ምንድነዉ ልጄ?” አለ ባልቻ አዉቆብኝ ያልፈሰሰ እንባዬን እያበሰልኝ “ አሃ፤ ዛሬ ከነጋ አላየሁሽም ለካ? የት ዋልሽ?”

አስተናጋጁ እየተሸቆጠቆጠ መጥቶ የምንፈልገዉን ሊታዘዘን አጎበደደ፡ እሰይ! ገላገለኝ። በባዶ ሆዳቸዉ ሐቲታቸዉን ከምበላዉ፣
ምሳችንን በሰላም ብንበላ ለእነሱም ይሻላቸዋል። የቤቱን
የአገልግል ምግብ ከተጨማሪ ሱፍ ፍትፍት ጋር እንዲያመጣልን አዘዝን ሱፍ ፍትፍት የባልቻ የምንጊዜም ምርጫ መሆኑን
ከእሱ ጋር ለአንዴም
ቢሆን ማዕድ የተጋሩ ሁሉ ያዉቁለታል። የሚበላም የሚጣጠም ሲጠየቅ
ቀድሞ የሚመጣለት ነገር ሱፍ ነዉ። በሀገር ዉስጥ ምግብ ቤቶች ብቻም ሳይሆን፣ አንዴ ሩስያ አብረን የሄድን ጊዜ ሁሉ ቀዝቀዝ ያለ ሱፍ ፍትፍት ይኖራችኋል? ብሎ ሩስያዊቷን አስተናጋጅ ሲጠይቃት
ሰምቼዉ፣ የሳቅሁትን ሳቅ ሞቼም መርሳቴን እንጃልኝ! እስከ አሁን ትዝ ባለኝ ቁጥር ስቄ አይወጣልኝም: ሱፍ አዝዞ የለም ከተባለ፣ ለሆቴሉ የሚኖረዉ ግምት ሁሉ ወርዶ እንዴት እንደሚያደርገዉ አያድርስ ነዉ።
ይኼ ደግሞ ሆቴል ነዉ? ሱፍ ፍትፍት እንኳን የሌለበት ቤት! ብሎ
ሲያጣጥል ብዙ ጊዜ ሰምቼዋለሁ። ለእኔ ግን የሚበላ ይሁን እንጂ ምንም ቢሆን ያን ያህል አላማርጥም: በተለይ አሁን በኃይል ሞርሙሮኛል። ለወትሮዉ እንዲህ ድባቴ ዉስጥ ስሆን እንኳንስ ሊርበኝ ይቅርና የምግብ
ሽታ ሁሉ አይደርስብኝም ነበር አሁን ግን ምራቄ ኩችር ብሎ፣
ትንፋሼም ሳይቀር ሽታዉ እንደ ተለወጠ ለእኔም ታዉቆኛል።

“ችግር አለ እንዴ ዉቤ?” አለ እሸቴ፣ ከበላን በኋላ ከሁላችን በኋላ እጁን ታጥቦ ከመመለሱ፡
“ፊትሽ በፍጹም ልክ አይደለም” አለ፣ ባልቻም ተደርቦ፡
“ሆስፒታል ሄጄ ነበር''
“እ?” አሉ ኹለቱም፣ እኩል። የሆነዉን እና በሐኪሟ የተባልሁትን ሁሉ አንድም ሳላስቀር ነገርኋቸዉ። በየመሀሉ በድንጋጤ ከአሁን አሁን
ራሳቸዉን ይስታሉ ብዬ ስጠባበቅ፣ እነሱ ከመጤፍ ሳይቆጥሩት ቀሩብኝ ጭራሽ ባልቻማ ሊስቅብኝ ምንም አልቀረዉ፡ እሸቴም ቢሆን የምጠብቅበትን ያህል ጸጸት ቀርቶ ሐዘኔታ እንኳን አላሳየኝም፡

“ለዚህ ነዉ እንዴ ፊትሽን እንዲህ የክረምት ሰማይ ያስመሰልሽዉ?
“ከዚህ በላይ ምን አለና አባታለም?”
“ኧረ ዝም በይ! ደም አርግቶ የፈጠረንን አምላክ ለምናመልክ ለኛ፤ ይኼንን ጉዳይ ብለሽ … ምን እና ምኑ ተገናኝቶ፣ ሰዉ ሆነን እንደ
ተፈጠርን ጠፍቶሽ ነዉ? ልጄ ሙች! ካንቺ ይኼን አልጠብቅም”

ድንገት የእጅ ስልኩ ጮኸ፡ ወዲያዉ ፈገግታዉንም ተግሳጹንም አቋርጦ ስልኩን አነሳና፣ ለቅጽበት ያህል ከወዲያ በኩል አዳመጠ። ወዲያዉም
የምግቡን ሂሳብ ለመክፈል ኪሱን መፈታተሽ ሲጀምር አስቸኳይ ሁኔታ እንደ ተፈጠረ ገባኝ። ቀድሜዉ ሦስት ድፍን ድፍን መቶ ብሮች ጠረጴዛዉ ላይ አስቀመጥሁ።

“ምን ተፈጠረ?” አለ እሸቴ፣ እሱም እንደኔ ጥድፊያዉን በጥሞና እየተከታተለዉ ቆይቶ።
“ዕረፍት ያስፈልግሽ ነበር እዴ ዉቤ? አንድ መጥፎ ወሬ ደርሶኛል”

“ምነዉ ምን ተፈጠረ? ከየት ነዉ?”
“መስጊድ ላይ እሳት ተነስቷል ነዉ የሚሉኝ”
“የ..ት?” አለ እሸቴ፣ ልለዉ የነበረዉን ከአፌ ነጥቆኝ።
“ተከተሉኝ” ብሎ ከምግብ ቤቱ የመሮጥ ያህል ተራምዶ ወጣ፡ በእሱ ፍጥነት እግር በእግር ተከትለነዉ አሳንሠሩ ዉስጥ ገባንና ቁልፉን ተጭነን ወደ ላይኛዉ ፎቅ ጋለብን፡ በጠመዝማዛዉ መንገድ ገብተን
የለመድናቸዉን የደኅንነት ኬላዎች ሁሉ አልፈን በዚሁ ሕንጻ ወደ
ተሠወረዉ የሲራክ ፯ ማዕከል ስንደርስ፣ ሁሉም በየጥፍራቸዉ ቆመዉ አገኘናቸዉ እንኳንስ የጭንቅ ወሬ ተሰምቶበት፣ እንዲያዉም የዕረፍት
አልባዎች ቤት ነዉ ማዕከሉ
“እስኪ የታለ?” አለ ባልቻ፣ ከወገብ በላይ በግድግዳዉ ዙሪያ ወደ ተንጣለለዉ ዝርግ መከሰቻ ዓይኑን እያነጣጠረ፡
ደዉሎ የጠራዉ ልጅ የባልቻ ጥያቄ ስለገባዉ፣ የሚነካዉን ነካክቶ በርከት ያሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በሰፊዉ መከሰቻ ከዳር እስከ ዳር ደረደረልን እስከ ሚናራዉ ድረስ በኃይለኛ እሳት ሲንቀለቀል የሚያሳዩ
የመስጊድ ምስሎች ናቸዉ። ወላፈኑ እዚህ ያለንበት ድረስ በሚለበልብ እሳት ሲነድ ይታያል። ብዙ ሰዎችም እሳቱን ለማጥፋት ዙሪያዉን ሲዋደቁ ይታያሉ እንደ እሳቱ አያያዝ ግን መስጊዱን ማትረፍ የሚቻል አይመስለኝም:: ባይሆን ዙሪያዉን ባልተዛመተ እና በአካባቢዉ ተጨማሪ ዉድመት ባልደረሰ ስል በልቤ ጸለይሁ
👍352👎1
"ጭራሽ እዚሁ አዲስ አበባ አይደል እንዴ?” አልሁኝ፣ ከምስሎቹ ባንዱ የማዉቀዉን ሰፈር አይቼ: ማንም አልመለሰልኝም ያደመጠኝ ሁሉ ያለ አይመስለኝም: ሁሉም ዓይናቸዉ እዚህ ልባቸዉ ግን እዚያዉ ነዉ፡ እኔ በጣም ብዙ ሙለስሊም ወዳጆች አሉኝ፡ እነሱ እንደ እምነታቸዉ የሚያመልኩበት መስጊድ ቀርቶ የግለሰብ አነስተኛ ሱቅ ሲቃጠል ያሳዝነኛል የባልቻ እና የሌሎች ሐዘን ግን እንደ ማንኛዉም ሐዘን ብቻ
አልመስልሽ አለኝ፡ በተለይም እንደ ሲራክ ፯ አባል ሆኜ ሳስበዉ፣
ያልታየኝ ነገር እንዳለ ጠረጠርሁ

“በል አገናኘ” አለ ባልቻ፣ የተዘበራረቀ ትንፋሽ በጭንቅ እየተነፈሰ ክፍሉ እንዴት ጸጥ ብሎ ኖሯል! ሁሉም ወደ ዉስጥ ከመተንፈስ በቀር ጭጭ ብሎ ኖሯል ምስሎቹን የተመለከታቸዉ። ባልቻን ተከትለዉ ሁሉም ትንፋሽ ወሰድ መለስ አደረጉ፡

"በል አገናኘኝ"

"ማንን?"

"ቢራራ"

“ታዲያ እሱን' አገናኘኛ! ቶሎ በል” አለ ባልቻ፣ ማዳመጫዉን ወደ ጆሮዉ እያደረገ፡ በቅጽበት ቢራራን መስመር ላይ አገኘዉ መሰል፣ ጥም ጥሙን ትእዛዝ ያስተላልፍለት ጀመረ፡ “እየሰማኸኝ ነዉ ቢራራ? እሳት ማጥፋቱ
ላይ እየተሳተፉ ያሉት፣ በአቅራቢያ አልፎ ሂያጆች፣ ሥራዬ ብለዉ እሳት
ለመሞቅ የመጡት ምን እያሉ እንደሆነ አዳምጠህ እንድትነግረኝ
እፈልጋለሁ: ምንም ጊዜ የሚባል ግን የለንም:: ፍጥነት! በየመሀሉ
ጠቃሚ የሚመስሉ መረጃዎች ካጋጠሙህ ወዲያዉኑ ላክልኝ። ደግሞስ ትንሽ ፈቀቅ ብሎስ አይደል የቅዱስ ዑራኤል ካቴዴራል ያለዉ? ተጨማሪ
ሰዉም አሁኑኑ ይመጣልሃል” አለ፣ ግንባሩን ወደ እኔ እየጨረቆሰ እ;
በእጁም ምልክት እየሰጠኝ፡
ማድረግ ያለብኝን እየሄድሁም ቢሆን በስልክ ሊነግረኝ እንዳሰበ በማወቅ፣ ቀልጠፍ ብዬ ወጣሁ። መኪናዬን አስነስቼ እሳት ወደ በላዉ መስጊድ አሽከረከርሁ: የቅድሙ የባልቻ ድንጋጤ ከእኔ በላይ ለመስጊዱዐበመቆርቆር ብቻ ሳይሆን ቀጥሎ የሚመጣዉ ጥፋት አሳስቦት መሆኑ
ተገለጠልኝ።

ስለዚህ ባልቻ እዉነት አለዉ። ከዚህ በኋላ እንዲያዉም መስጊዶችንም ሆነ አብያተ ክርስቲያናቱን እኩል የመጠበቅ ሥራ መጀመር ይኖርብናል።
ለራሳችን ደኅንነት ስንል የቀረን አማራጭ ይኼ ብቻ ይመስለኛል።
ይኼንን ሳብስለስል፣ ቅድም በሆስፒታል የሆነዉ ሁሉ ለጊዜዉ ዐዚሙ ቀለልኝ። እንደጠበቅሁት፣ ልክ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ካቴዴራል ስቃረብ ባልቻ ስልክ ደወለልኝ።

“ምን የተለየ ነገር ይታይሻል?”
“ጭር ብሏልኧረ: ሀሉም ሰዉ የመስጊዱ ን እሳት ለማጥፋት ሄዶ
ይመስለኛል፣ በቅጽሩ የቀረ ሰዉ አላገኘሁም”
“እንደ ፈራሁት! እና ማንም የለም?”
“ማንም የለም: ጥበቃዎችም ጭምር የሉም”
“በይ ዓይንሽን ግለጭ: ደወሉ ይታይሽ የለም?” ዞር ዞር ስል በትልቅ ማማ ላይ የተንጠለጠለዉን ግዙፍ ደወል
ተመለከትሁ። ደወል በቤተ ክርስቲያን ተቆጥረዉ የማያልቁ ሁነኛ ጥቅሞች ነዉ ያሉት፡ እንዲያዉም የራሱ ባለሞያ አለዉ
ቄሰ ገበዝ እንደሚባለዉ ሁሉ ደዋይ የሚባል ማዕረግ አለ
ደወል አንድም በቅዳሴ፣ በማኅሌት፣ በፍትሐት፣ በንግሥ እና በሌሎች መርሐ ግብራትም
ጭምር ለተለያዩ ዓላማዎች ይደወላል በሌላ በኩልም ነፍስ በእጁ ያጠፋ፣ቤት ንብረት ያቃጠለ ወይም በብዙ የበደለ ሰው አማልዱኝ ለማለት ወደ
ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ደወሉን ሊመታዉ ይቻላል እንዲሁም በቅጽረ ቤተ ርስቲያኑ ዉስጥ ዝርፊያ ወይ ደግሞ እሳት የተነሳበት እንደሆነ ጠባቂዉ
ደወሉን ደዉሎ፣ ምእመናኑ እንዲደርሱለት ሊጠራበት ይችላል
የባልቻ ሐሳብ ገብቶኛል። የተለየ ክፉ ነገር ከመጣ፣ ጊዜ ሳልፈጅ ደወሉን እንድጠቀምበት ማስታዎሱ ነዉ፡ እሺ ብዬ ገና ስልኩን ከመዝጋቴ፣
ሦስት ጎረምሶች ዲጂኖና ጀሪካን በግራ በቀኝ ተሸክመዉ እያናፉ መጡ።

የማየዉን ማመን አልቻልሁም እንደገና ዓይኔን ጨፍኜ ገለጥሁት። አዎ፤ ኹለቱን ባለነዳጆች እየመራ ያመጣቸዉ የራሴዉ ጉድ ነዉ ጃሪም!
እህትነትሽ በቅቶኛል ያለኝ የራሴዉ ወንድም ጃሪም ቤተ ክርስቲያን
ሊያቃጥል መጣ? ሰአሊ ለነ!
ጀምረዉ የሚሆነዉን ሁሉ ለመከታተል በአንድ ግዙፍ ዋርካ ወዲያዉኑ ራሴን ከለልሁ ገርበብ ብሎ የተዘጋዉን የገረገራዉን በር ከርፈድ አድርገዉ እንደ ገቡ፣ በግቢዉ ማንም አለመኖሩን አረጋገጡ፡ ከዚያም ከጉልላቱ
ጀምረዉ በዓይናቸዉ ሁሉን አዳረሱት እጅግ እንደ ጎመዡ ምንም ጥያቄ የለኝም ከየት
እንደሚለኩሱት እርስ በእርስ ትንሽ
ከተጨቃጨቁ በኋላ ዲጂኖና ጀሪካኖቹን ተካፈሉ፡ ጃሪም ወደ ዋናዉ እቃ ግምጃ ቤት፣ ቀጣዩ ወደ ካህናት መግቢያ በር፣ ሌላኛዉ ደግሞ ወደ ቤተልሔሙ ተሯሯጡ፡ ያን ያህል የተዘጋጁበት የተጻፈ ዕቅድ ባይኖራቸዉም፣ ቢያንስ ቢያንስ ለካቴድራሉ ግን እንግዳ እንዳልሆኑ ከሁኔታቸዉ ተረድቻለሁ። ለነገሩማ መሪያቸዉ ማን ሆነና! የራሴዉ ወንድም ጃሪም አይደል? ገና የስድስት ዓመት ልጅ እያለ በዲቁና የቀደሰዉ ጃሪም፣ እንኳንስ የካቴዴራሉን ዙሪያ ይቅርና የመቅደሱን ዉስጣ ዉስጥ
ሁሉ ነዉ አሳምሮ የሚያዉቀዉ።
ተልእኮ ላየ በምሆን ሰዓት አዘዉትሬ በምደረንቀዉ መነጽሬ ላይ በተገጠመልኝ ረቂቅ የምስል ማንሻ እያነሳሁ የሦስቱንም ምስል ወደ ሲራክ-፯ ከላክሁ በኋላ ተሽሎክሉኬ ወደ ደወሉ ተጠጋሁ። ልክ እነሱ በሮችን ለመገነጣጠል በዲጂኗቸዉ መደዝደዝሲጀምሩ፣ እኔም ያለ ማቋረጥ ደወሉን ደወልሁት፡ ድብልቅልቁ እስኪወጣ ድረስ ደዘደዝሁት።

የካህናቱን በር ሊፈለቅቅ የሚታገለዉ ልጅ በዛፎች መካhል አጮልቆ አየኝ፡ ወዲያዉ ዲጂኖዉን እንደ ጦር ሰብቆ እየነቀነቀብኝ ፍሕም ልሶ
መጣብኝ፡ ባሻገር ወደ ግምጃ ቤቱ ገደማ ጭስ ይታየኛል በወዲህም
ከወደ ቤተልሔሙ ዉስጥ ቀላል የእሳት ነበልባል መዉጣት ጀምሯል:: ባለ ዲጂኖዉ ወደ'ኔ እየቀረበ ነዉ። እኔም አንዳች የደገስሁለት ነገር ያለ
ይመስል፣ ደወሉን ያለ ፋታ መቀጥቀጤን ሳላቋርጥ ጠበቅሁት። ምንም መሮጫ ማምለጫ መንገድ ግን አይታየኝም: ልጁ የማርያም መንገድ እንኳን ብለምነዉ የሚሰጠኝ አይደለም። ከኋላዬ በኩል ባለ ፍርግርግ
ብረቱ ገረገራ ነዉ ያለዉ። ከፊት ለፊቴ ደግሞ ሆድ እቃዬን ለመዘርገፍ የጎመጀ ሰዉ ከነዲጂኖዉ ደርሶብኛል።
ሆኖም የመነጽሬ ካሜራ ምስል ማንሻ፣ ልጁን አሁንም ከመቅረጽ
አልቦዘነም፡.....

ይቀጥላል
👍2313🥰1
#ምንዱባን


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

...ሐኪሙ እስኪመጣ ማሪየስ ከተኛበት አልተንቀሳቀሰም:: አክስቱ ግን ከመኝታዋ ተነስታ ከአጠገቡ ቁጭ ብላለች:: «ወይኔ ጉዴ ፧ አምላኬ ከዚህ አውጣኝ» ብሎ ከማልቀስና ከወዲያ ወዲህ ከመንቆራጠጥ ሌላ ያደረገችው
ነገር አልነበረም::

ሐኪሙ ማሪየስን መረመረው:: እስትንፋሱ አለች፡፡ በጀርባው አስተኝቶ ቁስል እንደሌለበት ተረዳ፡፡ ልብሱንተ ሲያወልቁለት አክስትየው ወደ ውጭ ወጣች:: መቁጠሪያዋን ይዛ ትጸልይ ጀመር፡፡

ከጎድኑ ላይ ቁስል አለ፡፡ ግን በጣም ወደ ውስጥ የገባ ቁስል አይደለም::እጁም ላይ በጐራዴ ተመትቶአል፡፡ ከጭንቅላቱም ላይ እንዲሁ በመወጋቱ የደማ ቁስል አለ፡፡ ከግምባሩ ላይ አጥንቱ ተሰብሮ እንደሆነ ሐኪሙ በዝግታ
ነካካው:: ለመለየት አቃተው:: ሆኖም ሐኪሙን ከዚህ ሁሉ ይበልጥ ያሳሰበው የማሪየስ ነፍስ አለማወቅ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ ወንዶች ነፍሳቸውን ከሳቱ በዚያው ይቀራሉ እንጂ አይነቁም:: አሁን ታዲያ ማሪየስ ይነቃል ወይስ አይነቃም ሲል ተጨነቀ:: ብዙ ደም ስለፈሰሰው ሰውነቱ ዝሉአል::

ሴቶቹ የማሪየስን ቁስል ካጣጠቡ በኋላ ሐኪሙ እያዠ የሚወጣውን
ደም አቆመው፡፡ ጭንቅላቱን በቃገቃዛ ውሃና ሳሙና አጠቡት፡፡ ሐኪሙ የማሪየስን ግምባር እያሻሸ ሲጠራርግ በር ተከፈተ፡፡ በጣም ደነገጠና የገረጣ
ፊት ብቅ አለ፡፡

አያቱ ነበሩ፡፡ ሰውነታቸው እየተንቀጠቀጠ አንገታቸውን ብቻ ወደ ውስጥ በማስገባት ተመለከቱ፡፡ የሌሊት ልብስ ነው የለበሱት:: መቃብር
እንጂ ደህና ነገር የሚያዩ አይመስሉም፡፡ ማሪየስ አልጋ ላይ ተዘርሮና አዓይኑን ጨፍኖ ነው ያዩት:: እስከ መታወቂያው ራቁቱን ነው የተኛው::በጥፊ እንደ ተመታ ሰው ክው እንዳሉ ወደ አልጋው ተጠጉ:: ልባቸው በኃይል ይመታል፡፡

«ማሪየስ!» ሲሉ በዝግታ ተጣሩ፡፡

«አባባ» አለች አንደኛዋ ሠራተኛ «አሁን ነው ሰዎች ይዘውት
የመጡት:: ከጦርነቱ ቦታ ነበር ብለዋል፡፡›

«ሞቷል!» ሲሉ ሽማግሌው መጮህ ጀመሩ:: «ዶክተር» አሉ፤ «አንተ ነህ ሁሉንም የምታውቀው:: አንድ ነገር ብቻ ንገረኝ:: ሞቷል ፤ አይደል?»

ሐኪሙ በጣም ተጨንቆ ስለነበር መልስም አልሰጣቸውም::

ሽማግሌው እያጨበጨቡ ይስቁ ጀመር፡፡ ተደጋግሞ እንደተባለው
«ማሽላ እያረረ ይስቃል» ይሉ የለ!
«ሞቷል! ሞቷል! ከዚያ ከምሽጋቸው ወስጥ ነው የተገደለው! ሳንታረቅ! በጥላቻ ዓይን እየተመለከተኝ ነዋ ሕይወቱ ያለፈችው! ይኼ ርኩስ! ሞቶ ሬሣው ይምጣልኝ! ይኼ ነዋ የእኔ እጣ ፋንታ! ሞቷል! ሞቷል!»
ሐኪመ ማሪየስን ትቶ ወደ መሴይ ጊልኖርማንድ ሄደ:: ሰውዬውም
ዞር ብለው በአበጠ ዓይናቸው ተመለከቱት::

«ይቅርታህን ዝም እላለሁ፡፡ ምንም እንኳን ብዘ ሰው ከአጠገቤ
ሲለይ ባይም የአሁኑ በዚህ እድሜዬ አላስችል ስላለኝ ነው:: ብቻ በማያገባቸው ነገር ይገቡ፤ ይለፈልፉና ውጤታቸው ይሄ በመሆኑ አሳዘነኝ፡፡ ይጽፋሉ፤
ይናገራሉ፤ ወደፊት፤ ወደኋላ፤ አዲስ ሕይወት፧ ነፃነት፣ መብት፧ ሌላም ሌላም እያሉ ይጮሁና ሬሣ ይዘውልን ይመጣሉ፡፡ ብቻ ምን ይሆናል ይቅር! ልቻለው፤ አይ ልጄ ማሪየስ! ገደለህ፤ ከእኔ በፊት ሞትክ፣ ያሳደግሁት ልጄ እኮ ነው! ገና አንድ ፍሬ ሆኖ ሳለ እኮ ነው እኔ ያረጀሁት:: ታዲያ እኔ
ቆሜ እርሱ ይሙት:: እርሱ የፈጨውን አፈር እኮ አብረን አብኩተናል፡፡ እርሱ በሕፃንነቱ እኔ በስተርጅናዬ! ብቻ ምን ይሆናል ተዉት፡፡ ጠዋት ጠዋት ከመኝታ ክፍሌ እየሮጠ ሲመጣ፣ ስቆጣው፣ እርሱ ሲስቅ፣ የማታ
ማታውማ ከላዬ ላይ ካልወጣሁ ሲል «ኧረ እኔ አልችልም» እያልኩ
ስቆጣው ፧ የጨዋታ መሆኑ እየገባው አይቆጣ! ኧረ ስንቱን ላንሳው! የሕይወቴ ብርሃን ነበር፡፡ እንደዚህ ልጅ የሚወደድ ፧ አንጀት የሚበላ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም::»

ጠጋ ብለው አዩት:: አሁንም ነቅነቅ አይልም:: «እነዚህ አረመኔዎች»
ሲሉ ጮሁ:: የማሪየስ የዓይን ሽፋን ተነቃነቀ፡፡ በፈዘዘ ዓይን አያቸው፡፡
«ማሪየስ» ሲሉ ሽማግሌው ተናገሩ፡: «ማሪየስ፤ የእኔ ጌታ! ልጄ! ሕይወትህ አለ? አየኸኝ እኮ! ተመስገን፣ ተመስገን አምላኬ!»
ነፍሳቸውን ስተው ከመሬት ተዘረሩ::
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ዣቬር መስመር ሲለቅ

ዣቬር እያዘገመ ከገዣን ቫልገዣ ቤት ወጥቶ ሄደ:: የሚራመደው
እያቀረቀረ ነው:: በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ እጁን ወደኋላ አድርጎ ተራመደ:: ፀጥ ካለው አውራ ጎዳና ውስጥ ደረሰ፡፡ ዝም ብሉ ብቻ ወደፊት ነው የሚሄደው:: ወደ ሳይን ወንዝ የሚወስደውን መንገድ ይዞ ነው የሚጓዘው::
ትልቅ ድልድይ ካለበት ስለደረሰ የድልድዩን አግዳሚ ብረት ተደግፎ
ቆመ:: በጣቶቹ ሪዙን እያፍተለተለ አገጩን በእጆቹ ደግፎ ነው የቆመው::በሀሳብ ነጉዷል።

ሰውነቱ ውስጥ አዲስ ነገር፣ አንድ ዓይነት ለውጥ፣ እረፍት የሚነሳ
ስቃይ እየተፈራረቀ ነው:: ራሱን ማለት የግል ሕይወቱን ይመረምር
ጀመር፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ ዣቬር እየተሰቃየ ነው:: ዣቬር ልክ አልነበረም::ጥቂት ሰዓት አለፈ:: አንጎሉ ተረበሽ፣ ሁለም ነገር ተመስቃቀለበት::ስለሥራው የነበረው ደንዳና እምነት ላላ፡፡ ህሊናው ውስጥ የነበረው
የማይደፈር ሥልጣን ዋዠቀ፡፡ ይህን ሁኔታ ከራሱ ሊሸሽገው አልቻለም:: ይች ካልጠበቀው ቦታና ባላሰበው ጊዜ ዣን ቫልዣን ከወንዞ ዳር አገኘው:: ዣን
ቫልዣን ሲያገኘው ጥምቡን መልሶ እንዳገኘ ተኩላ ወይም የጠፋበትን ጌታ እንዳገኘ ውሻ ዓይነት ስሜት ነበረው::

ሁለት ዋና መንገዶችን አየ:: ከሁለቱ ዋና መንገዶች የትኛው ነው ! እውነተኛ? ልቡ ፈራ:: እድሜ ልኩን ያየው የነበረውና ትክከለኛ ነው ብሎ የሚያምንበት አንድ መንገድ ብቻ ነበር፡፡ አሁን ግን ሁለት ሆኑበት፡፡ ጨርሶ ግራ ተጋባ፡፡ ለማንኛውም ከህሊናው ውስጥ ምን ይተራመስ እንደነበር
አረጋግጦ ለመጻፍ ትንሽ ያስቸግራል::

አንድ ነገር ግን በጣም አስገርሞታል፡፡ ይኸውም የእርሱ ሕይወት በዣን ቫልዣ ምክንያት መትረፉንና የዣን ቫልዣ ሕይወት ደግሞ ከእርሱ ምህረት ማግኘቱ ነበር፡፡ የት ነው ያለው? አሁን ምን ይሥራ? ዣን ቫልዣን ይርዳው? ትክክል ሥራ አይሆንም:: ዣን ቫልዣ ነፃ ይውጣ? ስህተት ይሆናል፡፡ ታዲያ ከከፍተኛ ማዕረግ ላይ ያለ ሰው ከአንድ እስረኛ
ይነስ? በሌላ አንፃር ደግሞ ወንጀለኛ ከሕግ በላይ ሆኖ ሕግን ሲረግጥ? በሁለቱም መንገድ ቢሆን ለእርሱ ለዣቬር ውርደት ነው::

በሕይወት ዘመናችን የምንደርስባቸወ እንደዚህ ያለ ምርጫ የሚያሳጡና መፍትሔ ከሌለው ነገር ጫፍ የሚያደርስ አጋጣሚዎች አሉ:: እነዚህ አጋጣሚዎች መያዣ ወይም መጨበጫ የሚያሳጡ ናቸው::
ዣቬር ከእንደዚያ ያለ ፈተና ውስጥ ነበር የገባው::

የጭንቀቱ መነሻ ከአሳብ ውስጥ እንዲገባ መገደዱ ነው:: እነዚያ
ተቃራኒ አሳቦች ናቸው እንዲጨነቅና እንዲያስብ ያደረጉት: አሳብና ጭንቀት
ለእርሱ እንግዳ ነገሮች ናቸው:: አዲስ በመሆናቸውም አሰቃዩት፡፡ እርሱ የለመደው አንድን አሳብ «ወደፊት» ማራመድ ብቻ ነበር:: አሳብ ጭንቅላታችን ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ለአንድ ድርጊት የሚገፋፋን የአመፅ ስሜት በውስጣችን አለ፡፡ ይህ ዓይነት ስሜት ስላደረበት ዣቬር ተናደደ፡፡

ታዲያ ከምን ውሳኔ ላይ ይድረስ? ያለው ምርጫ አንድ ሲሆን
ይኸውም ወደ ዣን ቫልዣ ቤት ተመልሶ ሄዶ ዣን ቫልዣን ማሰር ነው፡፡ ከአንድ የፖሊስ አዛዥ የሚጠበቀውም ይኸው ነው፡፡ ግን እንዴት አድርጎ! አይችልም፡፡ ይህን እንዳይፈጽም መንገዱን የዘጋበት ነገር አለ፡፡
👍16
እንድ ነገር? ምንድነው እሱ? ለሕግ ሰው ከችሎት፣ ከፍርድ፣
ከፖሊስና ከሥልጣን በላይ ሌላ ምን ነገር አለ? የዣቬር አሳብ ተገለበጠ፡፡

አንድ አስፈሪ ነገር ነፍሱን እንደምትቦረቡር ዣቬር ተሰማው::
ወንጀለኛን ማድነቅ! ለወህኒ ቤት እስረኛ ክብር ማጎናጸፍ! ይህ ሊሆን ይችላል? ሰውነቱ ተርበደበደ፡፡ ሆኖም ከሕሊናው ሊያወጣው አልቻለም፡፡
ዋጋ የሌለው ነገር ሆኖ አገኘው:: ራሱን መቆጣጠር ተሳነው::

የመጨረሻውን ስቃይ ያደረሰበት ይህ አሳብ እንደሆነ ለማወቅ ፈልጎ
ከእውነታው ለመድረስ በተሳነው ጊዜ ነበር «ዋጋ የሌለኝ ፍጡር ነኝ» እስከ ማለት የደረሰው:: እስከዚያች ሰዓት ድረስ የሕይወቱ ዋና መመሪያ ሕግ ነበር፡፡ አሁን ግን ሌላ ነገር ጣልቃ ገብቷል:: ከዚያች ቅጽበት በኋላ ግን
ጨርሶ በሕግ ብቻ መመራት እንደማይበቃ ተገነዘበ፡፡ ይህም ግንዛቤ የአዲስ ኣሳብ
ባሪያ አደረገው:: ነፍሱ አዲስ ዓለም፣ ጨርሶ እንግዳ የሆነ ዓለም ማየት ጀመረች:: የግለሰብ ውለታ ከሕግ በላይ ሆኖ ተመላለሰበት:: ታዲያ አመፅ
በሀዘኔታ ይለወጣል? ሕግ ትድማ? ሕግ ትጣስ፤ ታልቅስ?

የሞራል ግዴታ አካሉን ሲሰረስረው ጉልህ ሆኖ ታየው:: ይህም
የጥንት እምነቱን ሲያኮላሽበት ተመለከተ፡፡ ለነስር አሞራ ማፍጠጥ ጉጉት እጅዋን ስትሰጥ::

ዣቬር ሰአሳብ ተዋጠ፡፡

«ይህን ወንጀለኛ፣ ይህን ተስፋ የቆረጠ ሰው እስከ መጨረሻው
አሳደድኩት:: በመጨረሻ ግን ከመዳፉ ስር አገኘኝ:: ሊበቀለኝ ሲችል ማረኝ::ለመበቀል ብቻ ሳይሆን ለራሱ ደህንነትና ለወደፊት ሕይወቱም ጭምር ሲል
ማድረግ ነበረበት:: ለእኔ ሕይወት መሳሳቱ፤ እኔን ከሞት ማትረፉ ምንድነው የሠራው? ማድረግ የነበረበትን ነው? የለም፧ እርሱ የሠራው ሥራ ከዚህ የላቀ ነው:: እኔስ በተራዬ የእርሱን ሕይወት በማትረፌ ምንድ ነው
የሠራሁት? ማድረግ ያለብኝን? የለም፤ ይህም ከዚህ በላይ ነው::

አሁንም ግራ ተጋባ፡፡ በእድሜ የበሰለ ሰው ነው:: እድሜውን በሙሉ ሥራው ሃይማኖቱ፡ ነበር:: ከሥራውና ከተቀበለው ኃላፊነት የበለጠ ምንም ነገር አልነበረም:: ስራው ከእግዚአብሔር በላይ ነበር፡፡ አሁን የደረሰበት

አዲስ አምላክ እጅግ በጣም አስፈራው::

በአንድ ወቅት የሰውን ልብ ሰንጥቆ የሚገባው፣ ፀሐይ ጨረርዋን
የመጨረሻው ውብ ነገር... አምላክ! እንድትወረውር ትእዛዝ የሚሰጠው ፤ እውነት ማለት ምን እንደሆነ እንድታውቅ ለነፍስ ትምህርት የሚሰጠው: ፤ ከውስጣችን የሚኖር የመጨረሻው ውብ ነገር... አምላክ!

ዣቬር ይህን አወቀ? ገባው? ከዚህ እውነት ለመድረስ ቻለ?
አይመስለኝም:: ሆኖም አሁን በገጠመው መላ ቅብ በጠፋና ሊገባ በማይችል ግፊት የተነሣ ጭንቅላቱ ሊፈነዳ መድረሱን ግን አውቆአል::

ጭንቀቱ ሊሸከሙት የሚቻል ነው? አይደለም:: «ከዚህ ለመውጣት ያለው መንገድ ሁለት ነው:: አንድ በቆራጥነት ወደ ዣን ቫልዣ ሄዶ እርምጃ በመውሰድ ወንጀለኛውን ከእስር ቤት ማስገባት ሲሆን ሌላው»
ብሉ አሳቡን ሳይጨርስ መንገዱን ቀጠለ፡፡ አሁን ግን አጎንብሶ ሳይሆን ቀጥ ብሎ ነው የሚሄደው:: ከአንድ ከተወሰነ ስፍራ ሲደርስ ከከተማው ዘብ
ቤት ስለደረሰ መታወቂያውን አሳይቶ ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ከክፍሉ ውስጥ ጠረጴዛ ነበር፡፡ ከጠረጴዛ ላይ ደግሞ ብዕርና ወረቀት ተቀምጧል::

ዣቬር ወረቀቱንና ብዕሩን አንስቶ የሚቀጥለውን ጻፈ::

ለወደፊት ሥራችን ሊረዱ የሚችሉ አንዳንድ የተገነዘብኳቸው ነጥቦች

1. ነጥቦቹን ጠቅላይ አዛዡ እንዲመለከቱልኝ እለምናለሁ::
2. እስረኞች ከምርመራ ተመልሰው ሲፈተሹ ጫማዎቻቸውን እንዲያውቁልና ፍተሻው እስካለቀ ድረስ በባዶ እግራቸው ከወለል ላይ
እንዲቆሙ::

3. በጥበቃ ጊዜ እርስ በርስ መጠባበቅ ጥሩ ነው፤ በተለይ በዓል በሚሆንበት ጊዜ ሁለት መኮንኖች ለዓይን ሳይሰዋወሩ መጠባበቅ አለባቸው::
ምክንያቱም አንዱ መኮንን ደከም" ሲል ሌላው ይጠብቀዋል፤ ሊተካውም ይችላል፡፡

4. እስር ቤቱ ውስጥ ለምን መቀመጫ ወንበር እንደሚከለከል
አይገባኝም:: እስረኞች እየከፈሉ እንኳን ቢሆን መቀመጫ ቢኖራቸው መልካም ነው::

5. አንዳንድ እስር ቤት ውስጥ የወንጀለኛችን ስም ስለጠሩ ብቻ ገንዘብ የሚከፈላቸው ሰዎች አሉ:: ይህ ሌብነት ስለሆነ እስረኞች ለአንድ ጉዳይ ስለተጠሩ ብቻ ገንዘብ መከፈል የለባቸውም::

6. እስረኞች ለክር ይከፍላለ፣ ይህም አግባብ አይደለም፡፡

ገዣቬር ይህንና ሌላም አሳብ በወረቀቱ ላይ ካሰፈረ በኋላ ፈረመበት፡፡ ማስታወሻውን የጻፈው በእርጋታ ነበር፡፡ በመጨረሻም ማዕረጉንና የእለቱን ቀን አከለበት፡፡ ጽሑፉን ሲጨርስ ከሌሊቱ ወደ ሰባት ሰዓት ገደማ ይሆናል፡፡

ዣቬር ማስታወሻውን በደብዳቤ መልክ አጣጠፈው፡፡ ከዚያም ፖስታ ውስጥ ጨምሮ አሽገው፡፡ ከኢንቬሎፑ ጀርባ «ለአስተዳደር ማስታወሻ» የሚል ነገር ጻፈበት:: ከዚያም ወጥቶ ሄደ፡፡ፀ

አሥራ አምስት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ትቶት ወደ ሄደ ድልድይ
ተመለሰ፡፡ ወደታች ጎንበስ ብሎ ተመለከተ፡፡ እንደገና አሳብ ውስጥ ሰጠመ:: ልክ፡ ቀደም ሲል ረግጦአት ከነበረው ሥፍራ ነው የቆመው:: ቀደም ሲል
ያየው ሰው ቢመለስ «ከቦታው አልተነቃነቀም ነው» የሚለው::
በጣም ጨልሞአል:: ደመና ስለዞረ ከዋክብት አይታዩም:: በአካባቢው ደግሞ የመንገድ መብራት አልነበረም:: የሚያልፍ ሰው ስላልነበረ ደግሞ በጣም ጭር ብሉአል:: ከባድ ዝናብ ዘንቦ ስለነበር ወንዙ በኃይል ሞልቶአል::
ዣቬር የቆመው ከድልድዩ መሃል ቤት ነው:: ወደታች ሲመለከት በቀጥታ ያየው የወንዙን ማዕበል ነበር፡፡ ሆኖም የታየው ጥቁር ነገር ብቻ ነው:: በኃይል ተነፈሰ፡፡

ዣቬር ለጥቂት ደቂቃዎች ሳይነቃነቅ ተገትሮ ቀረ:: ውሃው የተለየ ድምፅ አሰማ፡፡ እርሱም በድንገት ቆቡን አውልቆ ከድንጋዩ ጠርዝ ላይ አስቀመጠው:: ጥቂት ካመነታ በኋላ በዚያ በጨለማ ከውሃው ውስጥ ዘልሉ ገባ፡፡ ውሃው ቦጭረቅ አለ፡፡ ዣቬር ሰመጠ፤ ሁለተኛም ድምፁ
አልተሰማም::.....

💫ይቀጥላል💫
👍203
#ገረገራ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በታደለ_አያሌው


...ባለ ዲጂኖዉ ትንፋሹ ሳይቀር የሚሰማበት ቅርበት ላይ ከአጠገቤ ደርሷል። ምኔን ቢወጋኝ አንድ ምት እንደሚበቃኝ እያማረጠ ይመስለኛል ትንሽ ፋታ ስጠኝ። ዓይኔን ጨፍኜ ብቻ ስንቱን እንዳሰብሁት በዚች ቅጽበት! ሞት እንዲህ አብሮኝ ኖሯል ለካ። “ቁልቁል ወደ ምድር
ለመዉረድ የፈጀነዉን ያህል፣ የሩብ ሩቡን እንኳን ሽቅብ ወደ ሰማይ ለመዉጣት አንፈጀዉም” ትላለች እመዋ። እዉነቷን አይደል? እንዲያዉ ማርያም ብላዉ የምጡ ጭንቅ ቀለል ያለ ቢሆን እንኳን፣ ለመወለድ ቢያንስ ቢያንስ ለዘጠኝ ወራት በማሕጸን ዉስጥ መክረም የግድ ነዉ።ለመሞት ግን ይኸዉ አንዲት ቅጽበት እና ዲጂኖ ያለዉ ገዳይ በቂ የሚሆኑበት ጊዜ አለ።

ግንባሬን ይለኛል ጸጥ እላለሁ። አበቃልኝ።

እንደ ዛሬ ሞትን ቀርቤ፣ ትንፋሽ ለትንፋሽ ተሻትቼዉ አላዉቅም: በዓይነ ኅሊናዬ የመጡልኝን ሁሉ በልቤ ተሰናብቼ ራሴን ለሞት አደላደልሁ።እመዋ፣ ባልቻ እና እሸቴ ነበሩ ቀድመዉ ትዝ ያሉኝ፡ በእርግጥ በየመሀሉ
የመጡልኝን ሌሎች ማኅበርተኞቼን እና ጓደኞቼን ሁሉ አዳርሻለሁ።በመጨረሻም፣ በሆዴ ወደ ተሸከምሁት ፅንስ እጆቼን ሰድጄ ደባበስሁት፡ እህ? ለካንስ ሐኪሟ ፅንሱ የሴት ነዉ ብላኛለች፡ ሴት ከሆነች ደግሞ እመዋ ስም አዉጥታላታለች: ማን ብላ? ቱናት። ቱናትን በዳሰሳ ተሰናበትኋት፡ ፀእንዲያዉ ነዉ የተሰናበትኂት እንጂ፣ መቼስ እኔ ሞቼ
ቱናት አትተርፍ፡ አብረን ወደ ሞት ተጓዦች ነን

“ዉብርስት?” የሚል ቃል ድንገት አጠገቤ ሰማሁ ገዳዬ አይደል? እንደ ምንም የአንድ ዓይኔን ሽፋሽፍት ፈልቅቄ ስገልጥ፣ ገዳዬ ቆሞበት በነበረ ሥፍራ ቢራራ ቆሞበታል እንደገና ጨፈንሁና ብገልጥም፣ ከቢራራ በቀር ማንም በፊቴ የለም፡፡

“የት ገባ?”

“ማ ?”

“ባለ ዲጂኖዉ?”

ፍርስ ብሎ የንቀት ሳቁን ለቀቀብኝ፡ “ለካ ስ እንዲህ ፈሪ ነሽና” እያለ
እንደ መሽኮርመም እያደረገዉም ጭምር አሁንም አሁንም አሽካካብኝ::እዉነትም ገና ድንጋጤዬ አለቀቀኝም: ድንገት እርም እርም የሚል የብዙ
ሰዉ ሆታ ሰማሁና፣ ዞር ስል ሰዎች ወደ ቤተልሔሙ እና ወደ ግምጃ
ቤቱ ይሯሯጣሉ፡ አንዳንዱ አፈር፣ አንዳንዱ ዉሃ፣ አንዳንዱ ደግሞ
ቅጠል እየያዘ ይራወጣል ያ ይባስ ያ ይቅደም ያን ተወዉ. እዚህ
ጋ አምጣዉ የሚል የተለያየ ሰዉ ድምፅ ተሰማኝ፡

እሳቱ! አሁን ገና ወደ ልቡናዬ ተመለስሁ፡

“እሳቱ! ወይኔ ወይኔ! ቤተልሔሙን ፈጀዉ” ስል ጮኹኩ፣ በሚርገበገብ ድምፅ ብሞትስ ቆይ!? ደግሞ እኮ ለሰማዕትነት ዝግጁ ነኝ እያልሁ ስመጻደቅ ነበር እንደ ደህና ሰዉ በቤተ ክርስቲያን ከመጡብኝ እንኳንስ
ሌላ፣ ሞትንም አልፈራ ባይ ነበርሁ ሐሰት ይኼዋ ልኬን አወቅሁት መስዋእትነቱም ይቅርና፣ ከራሴ ቀድሜ የማተርፈዉ ምንም ነገር
አለመኖሩን ነዉ ያየሁት ቢሆንም ግን ቀደም ብዬ የደወልሁት ደወል
የጠራቸዉ ምዕመናን እንደ ደራሽ ጎርፈዉ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እሳቱን በአጭር አስቀረተዉታል። ቢራራም አጠገቤ ቆሞ በእኔ የሚስቀዉ፣ የእሳቱን መጥፋት ካረጋገጠ በኋላ እንደሆነ ገባኝ፡
ሰአሊ ለነ!

“ቆይ ግን ገዳዬ የት ተሰለበ? አሁን እኮ እንዲህ ብሎ ቆሞ ነበር''
አልሁት ቢራራን፣ እጄን ጦር እንደሚወረዉር አዳኝ አድርጌ እያሳየሁት እሺ እሳቱስ ከምኔዉ ጠፋ? ይኼ ሁሉ ሲሆን እንዴት እንደሆነ የማስታዉሰዉ ምንም ነገር የለኝም:: የሚደንቀዉ ደግሞ አሁንም ገና ድንጋጤዉ ጨርሶ አልለቀቀኝም: ቆመች ቆመች እንደሚባልላት ጨቅላ
የሚያደርገዉን የጉልበቴን መንቀጥቀጥ ማንም እንዳያይብኝ ተሳቀቅሁ፡ቢራራ ከፊቴ እስከሚሄድልኝ ድረስ በዝምታ ብጠባበቀዉም አልሄድልሽ
አለኝ፡ ባለሁበት ቁጢጥ አልሁና ወደ ልቡናዬ ለመመለስ፣ መድኃኒቴ የሆነችዋን ጸሎቴን በለሆሳስ አደረስሁ: ከቅድሙ አንጻር ልቤም የሚመታበት ፍጥነቱ በረድ ቢልም፣ ጨርሶ ግን ልክ ሊሆንልኝ አልቻለም

"እና ፈርቼ ነዉ?” አልሁት ቢራራን፣ ፈቀቅ ብሎ ወዳለዉ የእንጨት
መቀመጫ እየጎተትሁት።

“እንክት!” አለኝ፣ በእርግጠኝነት

“በእርግጥ ፈተና ባይኖር ሁሉ ተማሪ፣ ጠያቂ ባይኖር ሁሉ አስተማሪ መባሉን አዉቃለሁ: ግን እንደዚያ ነበርሁ ወይ እኔ? ተሞክሬ ባላዉቅ ነዉ
እዉነት? በጅቦች መካከል፣ በጨለማ አካፋይ ሞትን ተፋጥጬዉ አላዉቅም? ሌላዉ ሌላዉ ቢቀር፣ ሲራክን ከተቀላቀልሁ እንኳ ን
ይኼዉ ኹለተኛ ዓመቴን ጨልጫለሁ: እስከ አሁንም ድረስ ሐሞቴን የሚፈትኑ ስትና ስጓት ተልእኮዎች በየዕለቱ ከማዕከሉ እቀበላለሁ:: እንዲያዉ ምን ብረሳ ብረሳ በታላቁ ቤተ መንግሥት የገጠመኝን እረሳዋለሁ? እዉነት አተስ ያን ጀብዱ ሳትሰማ ቀርተህ ነዉ?” አልሁት፣ ቤተ መንግሥቱን መጥቀሴ ክፋት እንደ ሌላዉ በማስተዋል እኔ አሁን ጀብዱ ስለምለዉ ነገሬ ላይሰማ ቢችልም፣ ማዕከላችን ሲራክ ፯ በቤተ መንግሥት ምስጢር እንዳለዉ ያወቅነዉ ግን አብረን ነበር

“ሳትሰማ ቀርተህ ነዉ እዉነት ቢራራ?” አልሁት፣ ባለማመን። ይኼ ታሪክ ከተፈጸመ በኋላ፣ እንደኔ ላሉ የሲራክ ፯ መረጃ ሰብሳቢዎች በነበረዉ ወቅታዊ ስልጠና ጭምር ለምሳሌነት ተጠቅሶ እንደ ነበር
በማስታወስ፡
“በታላቁ ቤተ መ ግሥት?”
“ታዲያስ!”
“እንደምታዉቀዉ፣መአከላችን ሲራክ ዋና ዋና በሚባል
የመንግሥት…ብዬ ጀመርሁለት። እዉነትም አልሰማም ኖሯል
እየተቁነጠነጠ አዳመጠኝ።
እንደምታዉቀዉ፣ ማዕከላች ሲራክ ዋና ዋና በሚባሉ የመንግሥት እና ዓለም አቀፍ ዋና በሚባሉ የመንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ዉስጥም እጅግ ቁልፍ ሥራ ያላቸዉን ዳሳሾች (Sensors) እና ካሜራዎች በሥዉር አስቀምጧል: አንዳንዶቹ ድምፅ፣ አንዳንዶቹ ምስል፣ አንዳዶቹ ደግሞ እንቅስቃሴ በድብቅ እየዳሰሱ እና እየቀዱ ወደ ማዕከላችን የመረጃ ቋት
በቀጥታ የሚልኩ ናቸዉ:: ስለሆነም እነዚህ መሣሪያዎች በተሸሸጉበት አካባቢ ሁሉ የተፈሳችም ሆነ የተተነፈሰች ነገር ሲራክን አምልጣ ?
አታዉቅም: ምንም እንኳን መተዳደሪያ ሥነ ሥርዓቱ ስለማይፈቅድልኝ በየትኛዉ ቦታ ስንት ዳሳሽ መሣሪያ እንደ ተተከለ የማዉቅበት ደረጃ ላይ ባልሆንም፣ ከዐሥር ሺ ያላነሱ ዘመናዊ ዳሳሾች በተለያዩ ቦታዎች
እንደሚኖሩ እገምታለሁ: ለግምቴ ደግሞ በቂ ምክንያት አለኝ” አልሁት፣ የማዳመጥ ጉጉቱን ቀና ብዬ እያስተዋልሁበት ቋምጧል።

“ሰኞ ይሁን ማክሰኞ ቀኑን ዘነጋሁት እንጂ…”

ሰኞ ይሁን ማክሰኞ ቀኑን ዘነጋሁት እንጂ፣ የዛሬ ሰባት ወር ገደማ
ለአንድ ተልእኮ እንድዘጋጅ በራሱ በቀድሞዉ የሲራክ ፯ ኃላፊ ታዘዝሁ። “ ስለ ምንነቱ በዝርዝር ከመንገሩ በፊት፣ ስለ አደገኛነቱ አጥብቆ ሊያስረዳኝ ከሞከረ፡ እኔም ተልእኮዉ ምን ይሁን የት ይሁን ገና ሳላዉቀዉ፤ ምንም
ሥጋት እንዳይገባዉ በልበ ሙሉነት ገለጽሁለት።

“የለም የለም፣ የገባሽ አልመሰለኝም” አለኝ እንደገና፣ ጉዳዩን ማቃለሌ ገርሞት ባላስተዋልኋቸዉ ነገሮችም ሳይታዘበኝ የቀረ አይመስለኝም።
እንዲሁ ላይ ላዩን ፍርጥም አለብኝ፡ እዉነትም ከእሱ ጋር ቃል እየተመላለስሁ መሆኑን ራሱ ያስተዋልሁት ዘግይቼ ነበር
“ለወትሮዉ ማንኛዉንም ተልእኮ የምቀበለዉም ሆነ ተልዕኮዬን በተመለከተ የምነጋገረዉ ከቅርብ ኃላፊዬ ጋር ብቻ ነዉ። ሲጀመር የቀድሞዉን ዋና “ ኃላፊ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅርበት ያየሁት ራሱ፣ በዚሁ ዕለት ባልቻ
👍385🥰1
ሲያስተዋዉቀን ነበር። ረፋድ ላይ እንደ ድንገት ባልቻ ስልክ ደወለልኝና ክራሬን ይዤ ወደ ትልቁ የማኅበራችን ሕንጻ የጣሪያዉ ወለል (terrace) ላይ እንዳገኘዉ ነገረኝ፡ አነጋገሩ በእርግጥ የትእዛዝ ይመስል ነበር እኔም
ሻይ ልዉጣ አልዉጣ እያልሁ እያመነታሁ ስለነበር፣ ከቆየሁበት
የዘወትር ንባብ ላይ ተነሳሁ፡ ክራር መያዙ ስላላሰኘኝ፣ በዚህ ምክንያት ግን እንዳይቆጣኝ ብዬ በመፍራት፣ ኹለት ለስላሳ መጠጦች ይዤ ወደ ባልቻ ሄድሁኝ ማባበያ መሆኑ ነዉ: እንደ ደረስሁ አንደኛዉን ለስላሳ
መጠጥ ለራሴ አስቀርቼ፣ ሌላኛዉን ስሰነዝርለት ያላየ መስሎ ወሬ ጀመረኝ።

በወሬያችን መሀል እንደ ዋዛ በሚመስል ሁኔታ ለሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ስለሌ እንደ ነገረዉና፣ ሊያስተዋወቀኝም እንዳሰበ ሲነግረኝ በደስታ ዘለልሁ። ምክንያቱም እጅግ ድንቅ የሆነ ዝና ካለዉ ሰዉ ጋር ልተዋወቅ
ነዋ! የምኮራበትን ሲራክ ፯ን በብቃት ከሚመራዉ ሰዉ ጋር ገጽ ለገጽ ልተዋወቅ? ደስ አለኝ፡ አፍታም ሳይቆይ አንድ ጎልማሳ ጥላዉን ጥሎብኝ ከፊቴ ቆመ የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ መሆኑን አላጣሁትም እንደ ቀድሞ
ግምቴ ቢሆን፣ ሰዉዬዉን በሙሉ ዓይን ለማየት ቀርቶ በአጠገቡ ማለፍ ሁሉ የሚቻለኝ አይመስለኝም ነበር እሱ ግን ወዲያዉ የሚለመድ ቀለል
ያለ ገጽታ ያለዉ ሰዉ ነዉ፡ ሰላምታዉ ብቻ ያጠግባል በዚህ ሁኔታ ነበር ለአንድ ተልእኮ እንደ ፈለገኝ የነገረኝና፣ እኔም ዝግጁነቴን በልበ ሙሉነት የገለጽሁለት፡

“የለም የለም፣ የገባሽ አልመሰለኝም” አለኝ ትኩር ብሎ እንደገና ተመለከተኝ በኋላ። ለባልቻ ብዬ ያመጣሁትን ለስላሳ ከግራ እጄ ላይ ወስዶ፣ ትኩረቱን ሳያነሳልኝ ደጋግሞ ተጎነጨለት አሁንም ዓይኑን ዓይኔ ላይ እንዳኖረብኝ፣ “የት እንደሆነ ግን ነግረሃታል ወይ ባልቻ?” ሲል
ጠየቀዉ እንዳልነገረኝ መለሰለት

የት ነዉ ግ?” አልኋቸዉ፣ ቀለል አድርጌ። ለልቤ ደግሞ የትስ ቢሆን ምን ለዉጥ አለዉ? ብዬ እየተንደላቀቅሁበት

“ቤተ መ ግሥት"

"እ"

“አዎ"

በቤተ መንግሥት ከሠወርናቸዉ ካሜራዎቻችን መካከል
አንደኛዉ ከትናንት ማታ ጀምሮ ከርቀት ቁጥጥ (Remote
management) ዉጪ ሆኖብናል: እዚህ ሆነን ለመጠገን ያልሞከርነው የለም: ምናልባትም የኃይል ምንጩ ተቋርጧል፣ አለዚያም ደግሞ
የመንግሥት ደኅንነት ሰዎች ደርሰዉብናል ማለት ነዉ: አያድርገዉና ደኅንነቶች ደርሰዉብን ከሆነ፣ እጅግ አደገኛ ሁኔታ ዉስጥ መግባታችን
እወቂዉ: ለዚህ ነዉ አንቺን የፈለግሁሽ” አለኝ፣ ቤተ መንግሥቱ ወደ ተሸፋፈነባቸዉ ሀገር በቀል ዛፎች አሻግሮ እየተመለከተ።

“ሙያዬ ሌላ፤ ምን ላደርግ እችላለሁ እኔ?”

“ሙያ ሳይሆ ልብ ነዉ ካንቺ የሚፈለገዉ አሁን”

“ልብ?”

“ልብ ብቻ:: ማለቴ፣ ንቁ አእምሮ የሚመራዉ ሙሉ ልብ”

“እንደዚያስ ቢሆን ታዲያ… እኔ ከናጓተ ባላዉቅም፣ ለዚህ ተልእኮ እኮ ከእኔ ይልቅ…” ብዬ ካሜራዎቹን መጀመሪያ በቤተ መንግሥት በድብቅ ተክሏቸዋል ብዬ የማስበዉን ሰዉ ስም ልጠራ ስል፣ ዋና ኃላፊዉ ፊቱን
መለሰብኝ። እሱም ባልቻም አላዳመጡኝም። እዉነትስ ከእነሱ
እንደማላዉቅ ካመንሁ፣ ከመስማማት በቀር መሟገቴን ምን አመጣዉ? እሺ ማለት ነዉ ያለብኝ እሺታዬን በልበ ሙሉነት መለስሁ።

“ደህና” አለ፣ ዋና ኃላፊዉ። “ጥሩ: ያዉ በዚህ በኩል እሽቴ አለልሽ::
ከእኔና ከባልቻም ጋር እንደ አስፈላጊነቱ በመሀሉ የስልክ ግንኙነት ይኖረናል: ታዲያ እንደ ተለመደዉ፣ የማዕከላችን ሥነ ሥርዓት ይጠበቅ!” በዓይኔ ዉስጥ እንደገና እምነት በዓይኑ ቀድቶ፣ ከለስላሳዉም አንድ ጉንጭ ስቦለት ተሰናብቶን ሄደ ድብልቅልቅ ባለ ስሜት ዉስጥ ገብቼ፣ ከራሴ ጋር አንድ አፍታ ከቆየሁ በኋላ የተልእኮ ዕቅድ አዉጠነጠንሁ ኹለት ሦስት የሚሆኑ መንገዶች በሐሳቤ ቢመላለሱም
ከእነሱ መካከል የተሻለ የመሰለኝን ለባልቻ አማከርሁት።

ሁልጊዜም በማይታጎለዉ የማዕከላችን የዛሬዉ የጠዋት አጭር መግለጫ
(briefing) ላይ፣ በሀገር ዉስጥ ስለሚጠበቁ የዕለቱ ዐበይት ሁነቶች በተጠቃቀሱ ጊዜ፣ በታላቁ ቤተ መንግሥት ስለሚኖረዉ የእራት ግብዣም ተነስቶልን ነበር ግብዣዉን ያሰናዱት ራሳቸዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆኑ፣ በዋናነት የሃይማኖት አባቶች እንደሚገኙበት ታዉቋል።
በመሆኑም ሦስቱ የቋሚ ሲኖዶስ አባል ሊቃነ ጳጳሳት እና ሌሎች ኹለት የጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በስም ተጠቅሰዉ ግብዣዉን እንደሚታደሙ ቤተ ክህነት ወደ ቤተ መንግሥት የተመለሰዉን የማረጋገጫ ደብዳቤ ቅጂ ተመልክተነዋል። እንደኔ ግምት ግብዣዉ የሃይማኖት ሰዎች
የተጠሩበት እስከሆነ ድረስ፣ ከሰፊዋ ቤተ ክርስቲያን በደብዳቤዉ ላይ የተጠቀሱት ጳጳሳት ብቻ የሚሄዱ አይመስለኝም፡ ምናልባት ግን እነዚህ የተለየ ሥፍራ የሚሰጣቸዉ (VIP) እንግዶች ሊሆኑ ይችላሉ

hሌሎች ሃይማኖቶችም ተመሳሳይ ቁጥር እንደሚገኝ ከመገመት ዉጪ እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ ግን አናውቅም ከቤተ መንግሥትም የራሳቸዉ የጠቅላይ ሚንስትሩ ባልደረቦች መኖራቸዉ አይቀርም በዚያ ላይ አብልተዉ እና አጠጥተዉ ብቻ ደህና ሁኑ የሚሏቸዉ አይመስለኝም: ቤቱም ተራ አይደል፣ እንግዶችም ተርታዎች አይደሉማ!
እንዲያዉ ዘፈን ባይኖር፣ መርሐ ግብሩን የሚያዋዙ ነገሮች ይጠፋሉ? የሆነዉ ሆኖ ጨመር ያለ እንግዳ መገኘቱ ላይቀር ነዉ ለዚህም እንዲበቃ ዋናዉ አዳራሽ መመረጡ አይቀርም: ዋናዉ አዳራሽ ማለት ደግሞ አሁን
ግንኙነቱ ተቋርጧል የተባለዉ ካሜራ አቅራቢያ ነዉ።

ይኼንን ለባልቻ አማhርሁት፡ በእራት ግብዣዉ ላይ ስለመታደም እና ተልእኮዬን ያለኮሽታ ስለመከወን ስነግረዉ፣ እሱም እንደ'ኔ እያሰበበት እንደነበር በግርምት ነገረኝ፡ እሺ፣ ባልቻስ ዕቅዴን ወደደልኝ፡፡ ግን ማንን ሆኜ ነዉ የምታደመዉ? ጳጳስ ሆኜ ነዉ? ሼህ ወይስ ፓስተር? ለእራትም ግብዣዉ የሃይማኖት አባት እንጂ የሃይማኖት እናት አልተጠራች!
“ለእሱ አታስቢ” አለኝ ባልቻ፣ ይኼን ሐሳብ ሳነሳበት፡ “እሱ እዳዉ ገብስ ነዉ

“ንገረኝ እንዴት?”

“እሱን ለኔ ተዪልኝ: አዳራሹ ላይ እንደምትደርሽ ጥርጥር የለኝም:
ይልቅ፤ ከአዳራሹ ሾልከሽ ወደ ተቋረጠዉ ካሜራ እንዴት እደምትደርሺ እና ማንም ሳያይሽ እንዴት ልትመለሺ እንደምትችይ ብቻ አስቢበት አለኝ፣ ቁልቁል ወደ ቤተ መንግሥት የሚያደርሰኝን አዉራ ጎዳና እያየ:
ወዲያዉም እንድከተለዉ የዓይን ምልክት ሰጥቶኝ ቀደመ ተከተልሁ, ወደ ሲራክ፯ ወርደን የቤተ መንግሥቱን በተለይም የተቋረጠዉ የሚገኝበትን አካባቢ በካርታ ነደፈልኝ በዋናዉ አዳራሽ እና ደብዛው በጠፋብን ካሜራ መካከል ያለዉን ርቀት፣ ከአዳራሹ ጀምሮ ስለሚኖሩ የቤተ መንግሥት ጠባቂዎች ብዛት፣ ሊገጥሙኝ ስለሚችሉት አደጋዎች
ሁኔታዎች ጭምር አሰብንበት እየቆየሁ ሳስተዉል፣ ባልቻ ስለ ቤተመንግሥቱ ዉስጣዊ ገጽታ ያለዉ ዕዉቀት እየገረመኝ መጣ፡ በግቢዉ ስንት አምፖል እንዳለ ሳይቀር ነዉ ልቅም አድርጎ የሚያዉቀዉ። ታዲያ ይኼን
ሁሉ የሚያዉቀዉ እሱ እያለ ለምን እኔ ተመረጥሁ? ምንም አልገባሽ
ብሎኛል።

እንዲህ እንዲህ ስንል፣ ሰዓቱ ነጎደ

እንግዶች ወደ ቤተ መንግሥቱ ቅጽር ግቢ እየገቡ መሆኑን በአካባቢዉ ያሉ የኛ ወኪሎች ነግረዉናል። ፓትርያርኩን ጨምሮ ከቤተ ክህነት የሚሄዱትን ተጋባዦች የሚወስዱ ሾፌሮችም የመኪናዎቻቸዉን ሞተር
አሙቀዉ አዘጋጅተዋል በዚህ በኩል፣ ሁሉም ተጋባዥ ጳጳሳት አንዳንድ ረዳቶቻቸዉን ብቻ አስከትለዉ በየራሳቸዉ ሾፌርና መኪና እንደሚሄዱ ቀድሜ ባዉቅም፣ ከመካከላቸዉ አንዱን በሆነ ብልሃት አስቀርተን እኔ
ልተካ የምችልበት መንገድ ግን ክርችም ብሎብናል። ስለዚህ ወደ ቅጽረ ቤተ መንግሥቱም ሆነ ወደ አዳራሹ የመዝለቄ ነገር ራሱ ፈታኝ ሆኖ ታየኝ፡
👍342
ሰዓቱ ደግሞ ደርሷል።

“በይ ክራርሽን ያዥ” አለኝ ባልቻ የመሄጃ ሰዓቴ መድረሱን እያሳየኝ
እዉነትም ለግብዣዉ ዐሥራ አምስት ደቂቃዎች ብቻ ነዉ የሚቀሩት።

ከምሽቱ 12፡45 ሆኗል።

“ከዚያስ?” አልሁት ክራሬን ብድግ አድርጌ።

“ድንግል እንድትራዳሽ ተማጽነሻት ዉልቅ ነዋ: በይ፤ መልካም ዕድል!”
አለኝ፣ ወደ መዉጫ በሩ እያመላከተኝ፡ በቃ? ወደ ግቢ የመግቢያዉን ብልሃት ለኔ ተዪዉ ብሎኝ አልነበር እንዴ? እዳዉ ገብስ ነዉ ብሎኝ? አሁን ባለቀ ሰዓትማ እንዲህ የራስሽ ጉዳይ አይለኝም ብዬ ዞር ስል፣
ብቻዬን ቀርቻለሁ። “ኧረ አባትዮዉ” ብል፣ ባልቻን ከየት ላግኘዉ? ኧረ ባዛኝቷ!

ዉሃ ሆንሁ፣ የመጨረሻዉን ድንጋጤ ደነገጥሁ።....

ይቀጥላል
15👍13
#ምንዱባን


#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

የልጅ ልጅና አያቱ

ማሪየስ ለረጅም ጊዜ ስለታመመ መሞቱ ወይም በሕይወት መኖሩ
ሳይታወቅ ለረጅም ጊዜ ቆየ:: ለብዙ ሳምንታት ትኩሳቱ አልበረደለትም::አንዳንዴም ያቃዠዋል:: የአያቱ የመሴይ ጊልኖርማንድም ሁኔታ ከማሪየስ
የተለየ አልነበረም:: የልጁ ጉዳይ እስኪለይ ድረስ እርሳቸውም ከአልጋው አጠገብ እየተቀመጡ በሞትና በሽረት መካከል ኖሩ::

በየቀኑ አንዳንዴም በቀን ሁለት ጊዜ አንድ ሽበት የወረረው አዛውንት እየመጣ ይጠይቀዋል:: የሰውየው አለባበስ በጣም ሸጋ ሲሆን ከማረየስ ቤት በመጣ ቁጥር አንድ ነገር ይዞ ነው የሚመጣው::

በመጨረሻ ልክ በታመመ በሦስት ወሩ የማሪየስ በሽታ የማያሰጋ
ለመሆኑ በሐኪሙ ተገለጸ ፤ አያቱ ፈነጠዘ፡፡ ወደ ላይና ወደ ታች ሮጠ፡፡በዚሁ የተነሣ አንድ ቀን ለጎረቤታቸው የደስታ መግለጫ በመላካቸው ሰው ሁሉ ተገረመ:: ሌላው ቀርቶ ማሪየስን «ጌታው» እያለ ይጠሩት ጀመር፡፡
ከነአካቴው ሪፑብሊኩ ለዘላለም ይኑር» ብሉ እስከመጮህ ደረሱ፡፡ በአጭሩ ጮቤ መቱ።

በማሪየስ በኩል የነበረው አሳብ አንድ ነበር፡፡ ሲያክሙት፣ ቁስሉን
ሲጠግነት፣ እህል ሲቀርብለት፣ አዲስ ሰው ብቅ ሲልም ሆነ በማንኛውም ሰዓት ትዝ የምትለውና እረፍት የምትነሳው ኮዜት ነበረች፡፡ ለእርሱ ሕይወትና ኮዜት አንድ ናቸው:: ኮዜት ከሌለች ሕይወት የለችም:: ከሁለት
አንደኛቸው ከሌሉ ሁለቱም እንደሌሉ በልቡ ወስኖአል::

ማሪየስ ነፍስ ከዘራ በኋላ አንድም ቀን ቢሆን «አባባ» ብሎ ስላልጠራቸው መሴይ ጊልኖርማንድ ይታዘባሉ፡፡ ነገር ግን ጤናው በጣም ተመልሶአል::
አንድ ቀን ከአልጋው ላይ ቁጭ እንዳለ አያቱ ላይ ያፈጥጣል፡፡ ሁለቱ ተያዩ፡፡ ንግግር የሚጀምር ግን ጠፋ:: በመጨረሻ ማሪየስ ዝምታውን ይሰብራል፡፡

‹‹የምነግርህ ነገር ነበረኝ::>

«ምንድነው እሱ?»

«ትዳር ለመያዝ እፈልጋለሁ::»

«ጠርጥሬአለሁ» አሉ አያቱ:: ከዚያም ከት ብለው ሳቁ::

«እንዴት ጠረጠርክ?»

ቀደም ሲል አውቄዋለሁ ፤ አታመልጥህም ታገባታለህ::
ማሪየስ በደስታ ፈነደቀ፡፡ ፊቱ እንደ ማታ ጀምበር እዩኝ እዩኝ አለ::"
እንደ ጠዋት ፀሐይም በራ:: ልቡ እንደ ከበሮ ራሱን ሲደልቅ በውጭ
አልታየም እንጂ በኃይል ተማታ::

አያቱ ንግግራቸውን ቀጠሉ::

«አዎን፣ ያቺ ለግላጋ ፣ ያቺ ሽንኩርት የመሰለች ቆንጆ ያንተው
ትሆናለች:: እንደ አሮጊት ለብሳ ሁናቴህን ለመጠየቅ በየቀኑ ትመላለሳለች።ቆስለህ ከተመለስክ ጀምሮ በየቀኑ እየመጣች አልቅሳ ነው የምትመለሰው::ማን እንደሆነች አጠያያቄ ደርሼበታለሁ:: አድራሻዋንም አወቅሁት፡፡ ለማንኛውም እኛ ተዘጋጅተናል፤ አንተም ፈልገሃል:: እርስዋም ሳትፈልግ አትቀርም፡፡
ስለዚህ ከዚህ በኋላ የቀረው አንድ ነገር ነው! ትዳር መመሥረት፡፡ ነገሩን ስታነሳብኝ እየፈራህ ነው የተናገርከው፡፡ የምጮህብህና የምቆጣህ መስሎህ ነው! አይፈረድብህም:: የለም! አልቆጣም፡፡ ኮዜት ትሁን ወይም ሌላ ፍቅር ብቻ ይስፈን፡፡ አግብተሃት ደስ ብሎህ ኑር ልጄ፡፡»

ሽማግሌው ይህን እንዳሉ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ። እያለቀሱ የማሪየስን ፀጉር አሻሹ፡፡ በዛለ የሽማግሌ እጃቸው አቀፉት፡፡ የደስታ ብዛት መጨረሻው
ለቅሶ ነውና ሁለቱም ለረጅም ጊዜ ተላቀሱ::

‹‹አባባ» አለ ማሪየስ፡፡
«እንግዲያውማ አልጠላኸኝም ማለት ነዋ!» አሉ አያቱ፡፡
ተቃቅፈው ስለቀሩ መነጋገር አልቻሉም:: ቆይተው፣ ቆይተው ግን ሽማግሌው ተናገሩ፡፡
«በል ና፤ ጋሬጣው ተገልጧል፡፡»
ማሪየስ ከተሸሸገበት ከአያቱ ጉያ ብቅ አለ፡፡
«እንግዲያውስ አባባ ሄጄ ልያት፤ አሁን ተሽሎኛል::»
«ይህንንም ጠርጥሬአለሁ፤ ነገ ሄደህ ታያታለህ፡፡»
«አባባ!»
«ምነው?»
«ለምን ዛሬ አይሆንም?»
የሚከለክለን የለም፧ ይህንንም ጠርጥሬአለሀ:::»

ኮዜትና ማሪየስ እንደገና ተገናኙ፡፡ ሲገናኙ ምን እንደተጠያየቁ
ለመግለጸ አንሞክርም:: አንዳንድ ጊዜ አንባቢ ተመራምሮ ማወቅ ያለበትን በመዘርዘር ከሰው ሥራ ወስጥ አንገባም:: እናንተው አስቡት::

በእለቱ ኮዜት ማሪየስን ለመጠየቅ ስትመጣ የቤት ሰው በሙሉ
አንድም ሳይቀር ከማሪየስ ክፍል ይጠብቃታል:: ልክ እርስዋ ከክፍሉ ውስጥ ልትገባ ስትል ሽማግሌ ሊያስነጥሳቸው ይላል፡፡ በመሃረባቸው አፋቸውን
እፍን አደረጉ::
«አይ ቁንጅና!» ይላሉ እርስ በራሳቸው ሲነጋገሩ::

ውስጣዊ ደስታ ፊትን እንደ ብርሃን እንዲበራ ያደርጋል ቢባል የኮዜት
ፊት ማስረጃ ይሆናል:: ኮዜት በደስታ ብዛት ቆነጀች:: ተቅበጠበጠች፣ ሰከረች፣ ዘልላ ሄዳ ከማሪየስ አንገት ላይ ብትጠመጠም ደስ ይላታል፡፡ ግን
ሰው እያለ ፍቅርዋን አደባባይ ማውጣቱ አሳፈራት፡፡ አንዳንድ ጊዜ በፍቅረኞች ላይ እንጨክናለን፡፡ እነርሱ ብቻቸውን መሆን ሲፈልጉ እኛ የሙጥኝ
በማለት አብረን እንቀመጣለን፡፡ እኛ እንፈልጋቸዋለን፤ እነርሱ ግን
አይፈልጉንም

ከኮዜት ጋር አብሮ የመጣ ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው አባባ ሸበቶ ነው::
ይህ ሰው መሴይ ማንደላይን ነው:: ይህ ሰው መሴይ ፎሽለማ ነው፡፡ ይህ ሰው ዣን ቫልዣ ነው:: ዣን ቫልዣ ፊቱን በፈገግታ አስውቦና እሱነቱን በሽበት አስከብሮ ኮዜትን በመከተል ነበር ከቤቱ የገባው:: ሽክ ብሎ ለብሷል፡፡ጥቁር ሱፍ ለብሶ ነጭ ከረቫት አስሮአል::

ሰኔ 6 ቀን እንደዚያ ተጎሳቁሎና ቆሽሾ ማሪየስን ተሸክሞ የመጣው
ሰው ለመሆኑ ሠራተኛው አልጠረጠረም:: ጌታ የጌታ ልጅ መስሎታል ዣን ቫልዣ የተቀመጠው ከበር አጠገብ ሲሆን ከብብቱ ስር እንደ
መጽሐፍ ያለ የተጠቀለለ ነገር ይዟል፡፡ ይህን ያየች የማሪየስ አክስት ወደ አባትዋ ተጠግታ አንድ ነገር ትናገራለች::

«ይህ ሰው ዘወትር መጽሐፍ ይሸከማል?»

መጽሐፍ የሚባል ነገር ጠላትዋ ነው::

«ምን ያድርገው ብለሽ፤ ምሑር እኮ ነው፤ ጥፋት የለበትም» ሲሉ
የማሪየስ አያት መለሰላት::

«መሴይ ፍችለሹ» አሉ መሴይ ጊልኖርማንድ::

ስሙን አሳስተው የጠሩት ሽማግሌው ሆን ብለው አልነበረም:: እንደ እርሳቸው የለመዱት የመኳንንት ስሞችን እንጂ እንደ «ፎሽለማ» ያለ ደረሰ
ያልታወቀ ዘር ስም አስተካክሎ መጥራት አይሆንላቸውም::
«መሴይ ፍችለሽ፣ ልጅህን ለልጄ እንድትሰጠኝ እለምናለሁ::»

መሴይ ፎሽለማ ጎንበስ ብሎ እጅ ከነሳ በኋላ «ተስማምቻለሁ» አለ፡፡

«ተጫወቱ» ብለው ሽማግሌዎቹ ከክፍሉ ውስጥ ጥለዋቸው ወጡ፡፡ኮዜትና ማሪየስ አንገት ለአንገት ለመተቃቀፍ ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡
ንግግር አላስፈለጋቸውም:: መተያየትና መታሻሸቱ በቂ ነበር፡፡

መሴይ ጊልኖርማንድ ልጅትዋን በማድነቅ አወሱ፡፡ ስለውበትዋና
ስለቁንጅናዋ ብዙ ተናገሩ:: ፍቅራቸው የፀና እንዲሆንና እርስ በርስ እንዲከባበሩ መከሩ:: ፍቅር ሰዎች ቂል የሚሆኑበትና የእግዚአብሔር ጥበብ የሚገለጽበት ነገር እንደሆነ አስረዱ፡፡

«ብቻ» አሉ ቀጥለው ሊናገሩ፧ «ብቻ እኔ በሕይወት እስካለሁ ድረስ በቂ መተዳዳሪያ ይኖራችኋል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን እንጃ! ትቸገራላችሁ፡፡
አሁን በኋላ ፈጣሪ የሀያ ዓመት እድሜ ቢለግሰኝ እንኳን ያለው ንብረት ይበቃል::

«አይጨነቁ፤ ኮዜት ስድስት መቶ ሺህ ፍራንክ አላት::
የዣን ቫልዣ ድምፅ ነበር፡፡
«እኔ!» ስትል ኮዜት ጮኸች::
«ስድስት መቶ ሺህ ፍራንክ?» ሲሉ መሴይ ጊልኖርማንድ ጠየቁ፡፡
«አዎን፤ ስድስት መቶ ሺህ.… ብቻ ምናልባት አሥራ አራት ወይም
አሥራ አምስት ሺህ ፍራንክ ቢቀነስ ነው» ሲል ዣን ቫልዣ ተናገረ፡፡
👍192
የማሪየስ አክስት መጽሐፍ ነው ያለችው የተጠቀለለውን ነገር ዣን
ቫልዣ ወደ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው:: የታሠረበትን ገመድና የተጠቀለለበትን ወረቀት ፈታው:: ባለከፍተኛ የገንዘብ ኖታ ብቻ ነበር፡፡ ገንዘቡ ተቆጠረ:: 500 ባለ አንድ ሺህ፤ 168 ባለ አምስት መቶ ፤ በድምሩ 584ዐዐዐ ፍራንክ ሆነ፡፡
«ጥሩ መጽሐፍ ነው» አለች የማሪየስ አክስት:: በዚህ ጊዜ ማሪየስና ኮዜት ዓይን ለዓይን ተያዩ:: ብዙም በገንዘቡ አልተሳቡም::

ለጋብቻው በዓል የሚያስፈልገው ዝግጅት ሁሉ ተደረገ፡፡ ቀኑን
ለመወሰን ሐኪሙ ሲጠየቅ ከአንድ ወር በኋላ በጥር ወር መጨረሻ ለማድረግ እንደሚቻል
አበሰረ:: በደስታ ጊዜ ሰዓቱ ሳይታወቅ ስለሚያልፍ ቀኑ ቶሎ
ደረሰ፡: ኮዜትና ማሪየስ በድንገት ከመቃብር ወደ ገነት ገቡ:: አንዳንዴ የማሪየስ አባት ኮዜት ላይ አፍጥጠው ለረጅም ጊዜ ይቆያሎ:: ኮዚትም በውበትዋ ተማርከው እንደሆነ በመገመት በዚህ አትከፋም::

«ነገሩ ሁሉ እንዴት እንደተለወጠ ይገባሻል?» ሲል ማሪየስ ኮዜትን
ጠየቃት::

«እኔ አይገባኝም፧ ብቻ ሀያሉ አምላክ ፊቱን ወደ እኛ እንዳዞረ
አውቃለሁ» ስትል መለሰችለት::

ዣን ቫልዣ ሁሉንም አስተካከለው:: ነገሩ ሁሉ ትክክል እንዲሆን
አደረገ፡፡ ከባድ ነገር ቀላል እንዲሆን አመቻቸው:: ኮዜት ደስ እንዲላት ብቻ የሚችለውን ሁሉ ፈጸመ:: የኮዜኔትም ደስታ እጥፍ በእጥፍ እየሆነ ሄደ፡፡
ማሪየስን አገኘች:: የደጉ ሰው ፍቅር ቀስ በቀስ በወጣቱ ፍቅር እየተተካ ሄደ፡፡ ይህ ደግሞ አያስገርምም፤ የሕይወት እውነታ ይኸው ነውና!

ነገር ግን ዣን ቫልዣን «አባባ» ከማለት አልተቆጠበችም::
ከጋብቻው በኋላ ማሪየስና ኮዜት ከማሪየስ አያት ጋር እንዲኖሩ
ተደረገ፡፡ ዣን ቫልዣ ደግሞ ከቤታቸው አልጠፋም::

ታሪክ ውስጥ የተከታተልናት ሚስስ ቴናድዬ ከእስር ቤት ውስጥ
ሞተች፡፡ ከእነዚያ አሰቃቂ ቤተሰቦች በሕይወት የቀሩ ሚስተር ቴናድዬና አንደኛዋ ልጅ አዜልማ ነበሩ፡፡ ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ የት እንደገቡና መጨረሻቸው ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ተሸፋፍኖ ቀረ:: ተሸፋፍኖ የቀረ ታሪክ ይህ ብቻ አልነበረም::

ማሪየስ ከጦርነቱ መካከል ከተመታ በኋላ ማን ከዚያ አንስቶ ከአያቱ ቤት እንዳመጣው እንዲሁ ሳይታወቅ ቀረ፡፡ ምሥጢሩን ለማወቅ ብዙ ሙከራ ተደርጎ ነበር፡፡ ሆኖም ጥረቱና ልፋቱ መና ሆነ፡፡

አንድ ቀን ጨዋታ ደርቶ ሲጫወቱ ማሪየስ በቁጣ ስለዚያ ሰው
ያነሳል፡፡

«አዎ! ያ ሰውዬ፤ ማንም ይሁን ማን፣ ለእኔ ብሎ እንደዚያ የተሰቃየ
ሰው እንደ ጉም ተንኖ ቀረ፡፡ የኮዜት ስድስት መቶ ሺህ ፍራንክ የእኔ በሆነና» ብሎ ሲናገር ዣን ቫልዣ ጣልቃ ይገባል፡፡

«ገንዘቡ የአንተ ነው፡፡»

እንግዲያውማ ያ ሰው ማን እንደሆነ ለሚነግረኝ እከፍለው ነበር። አለ ማሪየስ ለዣን ቫልዣ ሲመልስለት::

ዣን ቫልዣ ዝም አለ፡፡

የሠርጉ እለት ዣን ቫልዣ ከበር አጠገብ ተቀምጦ መተከዙን ኮዜት
ተመለከታለች፡፡ ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ወደ እርሱ ሄደች፡፡
«እባዬ ደስ ብሉሃል?» ብላ ጠየቀችው::
“አዎን አለ ዣን ቫልዣ ፧ “ለምን ደስ አይለኝም ፤ ደስ ብሎኛል
እንጂ::"
እንግዲያውማ ሳቅ ሳቅ በላ ስትለው ከት ከት ብሎ ሳቀ፡፡

በእራት ሰዓት ግን ዣን ቫልዣ ከሠርጉ ቤት አልነበረም፡፡ ትንሽ
ስላመመው በጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ የእርሱ ከዚያ አለመገኘት ኮዜትን ቅር አሰኛት:: ሆኖም የእርሱን ቦታ ማሪየስ በመውሰዱ ሀዘንዋ እየተቃለለ ሄደ፡፡ በመጨረሻ ዣን ቫልዣን እስከ መርሳት ደረሰች::...

💫ይቀጥላል💫
👍212
#ምንዱባን


#ክፍል_ሃምሳ_ሶስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

....በእራት ሰዓት ግን ዣን ቫልዣ ከሠርጉ ቤት አልነበረም፡፡ ትንሽ
ስላመመው በጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ የእርሱ ከዚያ አለመገኘት ኮዜትን ቅር አሰኛት:: ሆኖም የእርሱን ቦታ ማሪየስ በመውሰዱ ሀዘንዋ እየተቃለለ ሄደ፡፡ በመጨረሻ ዣን ቫልዣን እስከ መርሳት ደረሰች::...

ዣን ቫልዣ ከቤቱ ሲደርስ ቤቱ ውስጥ ማንም አልነበረም፡፡ ወደ
ኮዜት ክፍል ሲሄድ አልጋዋ አለመነጠፉን ተገነዘበ፡፡ አንሶላዎቹና የትራስ ልብሶች ተነስተዋል፡፡ አንዳንድ የኮዜት የግል እቃዎችም ከዚያ ተወስደዋል፡፡ከዚያ የቀሩት ከባድ የቤት እቃና አራቱ ግድግዳዎች ብቻ ናቸው፡፡ ዣን ቫልዣ ክፍት የነበረውን ሣጥን ዘጋግቶ ከክፍሉ ወጣ፡፡ ክፍሎቹን ሁሉ እየተዘዋወረ ጎበኘ፡፡ ከራሱ መኝታ ቤት ደረሰ፡፡ ወደ አልጋው ሲሄድ ዓይኑ
ከአንድ ነገር ላይ አረፈ፡፡ ዘወትር ከዓይኑ የማይለየው አነስተኛ ሣጥን ከዚያ ተቀምጧል፡፡ ከአጠገቡ ስለማይለየውና በጣም ስለሚንከባከበው ኮዜት
ትቀናበት ነበር፡፡ ከኪሱ ቁልፍ አውጥቶ ትንሹን ሻንጣ ከፈተው::
ከውስጡ የነበሩትን ልብሶች አወጣ፡፡ በመጀመሪያ ጥቁር ቀሚስ፤ ቀጥሎ ጥቁር እስካርፍ፤ ከዚያም ዛሬም ቢሆን ኮዜት ልታደርገው የምትችል ትልቅ የልጅ ጫማ፤ በመጨረሻ ባለኪስ ሽርጥና የተቀደደ የእግር ሹራቦችን
አወጣ፡፡ ኮዜት ከአሥር ዓመት በፊት ሞንትፌርሜን ለቅቃ ስትወጣ የተቀመጠና እናትዋ ከሞተች በኋላ ኮዜትን ፍለጋ ሲሄድ ዣን ቫልዣ የወሰደላት ጥቁር ልብሶች ናቸው:: ልብሶቹን ከአልጋው ላይ ዘርግቶ
እንዳስቀመጣቸው የኮዜት እናት ትዝ አለችው:: በዚያን ጊዜ ኮዜትም ምን ትመስል እንደነበረና እንዴት ከእዚያ አስከፊ ቤት አስወጥቶ ለእናትዋ ሀዘን
ያመጣላትን ጥቁር ልብስ ለብሳ ምን ትመስል እንደነበረ አስታወሰ፡፡ በእናትዋ ሞት ምክንያት ከል ለብሳ እናትዋ በመንፈስ ስታያት ሳትደሰት አልቀረችም ሲል አሰበ፡፡

ኮዜት ከዣን ቫልዣ ጋር ጥቅጥቅ ባለው ጨለማ ያቋረጠችውንም
ጫካ አስታወሰ፡፡ ኮዜት ደስ ብሎአት ያንን የገዛላትን ትልቅ አሻንጉሊት ተሸክማና የሀዘን ልብስ ለብሳ ከማታውቀው ሰው ጋር በደስታ ስትጓዝ ምን ትመስል እንደነበር ትዝ አለው:: ሆዱን ባር ባር አለው፡፡ ከአልጋው ላይ
ከዘረጋው የኮዜት ልብስ ላይ ተደፍቶ ማልቀስ ጀመረ::
ያን እለት ማታ የሕይወቱን የመጨረሻ ትግል፣ የመጨረሻ ፈተና እንደሆነ ዣን ቫልዣ ተገነዘበ፡፡ እንደ ልማዱ ዣን ቫልዣ ከሌላ ፈተና ውስጥ ገባ፡፡

እንዴት አድርጎ ነው የማሪየስንና የኮዜትን ፍቅር ሳያበላሽ አብሮ
የሚኖረው? ለግል ጥቅሙ ሲል ደንቃራ ይሁን ወይስ ብቻውን ውስጥ ውስጡን ይሰቃይ? ይህ ሁልጊዜም ቤተሰቦችን ያስጨነቀና የብዙ ፍቅረኞችን ሕይወት ያበላሸ ጥያቄ ነው::

በሥጋ ፈቃድ ተመርቶ እርምጃ መውሰድ ውጤቱ ግጭት ነው::
ታዲያ እስከመቼ ነው የነፍስ ተገኝዎች ሆነን የምንቀረው? ዣን ቫልዣ ለሥጋው አድሮ ኮዜትን አልለቅም ይበል ወይስ ለነፍሱ አድሮ ሙሉ በሙሉ ለማሪየስ አሳልፎ ይስጣት?

ግን እኮ ቀላል አይደለም:: እርሱስ ምን ይሁን? ከትቢያ አንስቶ ለዚህ
አደረሳት:: የመንፈስ ልጁ ናት:: በዓለም ላይ ያለ እርስዋ ሌላ ሀብት የለውም:: ወንድሙም፣ እህቱም፣ እናቱም፣ አባቱም፣ ጎረቤቱም፣ ምኑም ምኑም ኮዜት ናት:: ኮዜት ትሂድና ሙልጭ ይውጣ? ታዲያ ምን ይሁን?
ታዲያ ለዣን ቫልዣ ሲባል የኮዚት ሕይወት ይበላሽ?

እንዴ፣ ሕይወትዋ የማን ሆነና?

መስዋዕትነት መትነን ነው፣ ለመደሰት መሰቃየት አለ፤ ይህን መፈጸም ማለት ደግሞ ከጋለ ብረት ላይ መቀመጥ ነው:: ግን ካጋለ ብረት ላይ መቀመጥ ከቻለ ዓለምን ከቁጥጥር ስር ማድረግ ይሆናላ!

ዣን ቫልዣ ፍልስፍናውን ትቶ ተስፋ በመቁረጥ ጋደም አለ፡፡ ነገሩን
ሁሉ ለካው፣ መዘነው:: ከዉሳኔ አሳብ ላይ ደረሰ፡፡ እርሱና ጨለማ
ብቻቸውን ቀሩ፡፡

በሠርግ ማግሥት ሁሉም ነገር ጭር ይላል:: ለፍቅረኞች እድል
ለመስጠት ታስቦ ይመስል ሁሉም አርፍዶ ነው ከመኝታው የሚነሳው::ዣን ቫልዣ ግን በጠዋት ተነስቶ ወደ ማሪየስና ኮዜት ቤት ሄደ::

«እርስዎ ነዎት አባባ!» አለ ማሪየስ ዣን ቫልዣ ከነበረበት መጥቶ::
ማሪየስ ብዙም ስላልተኛ በጣም ከብዶታል፡፡

«ምነው በጠዋቱ? ኮዜት ገና አልተነሳችም፡፡ ማታ ቶሎ በመሄድዎ በጣም ቅር አለን፡፡ ስለእርስዎ ብዙ ተጫወትን፡፡ ኮዜት በጣም ትወድዎታለች:
ከዚሁ ጥሩ ክፍል እንደተዘጋጀልዎት ቀደም ብዩ ነግራዎት ነበር፡፡ ከእኛ ጋር መቀመጥ አለብዎት:: ከዚያ ብቻዎን ምን ያደርጋለ? እንዲያውም ከዛሬ ጀምሮ ከዚሁ ነው የሚሆነት:: አባባንም እንደሆነ በመንፈስ ገዝተወታል፡፡ እርሱ የእርስዎ ነገር አይሆንለትም:: በጣም ነው
የሚያከብርዎትና የሚወድዎት፡፡ አብረን የኖርን ተደስተን ነው የምንኖረው።
እርስዎ ደግሞ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው:: አሁን እንሂድ ቁርስ ቀርቦአል» አለ፡፡

«ሰማሀ ማሪየስ» አለ ዣን ቫልዣ ፤ «አንድ የምነግርህ ነገር አለ፡፡ እኔ
እንደሆንኩ አሮጌና ሽማግሌ ወንጀለኛ ነኝ::»

አንዳንድ ጊዜ ጆሮ ለመስማት የማይፈልገውን አይሰማም፡፡ በተለይም ካልተጠበቀ ምንጭ የሚወጣ የማይሆን ወሬ ጆሮ ያልፈዋል፡፡ “ወንጀለኛ ነኝ" የሚለውን ዜና ከ መሴይ ፎሽለማ የሚጠበቅ ስላልሆነ የማሪየስ ጆሮ ሊሰማው አልፈቀደም አንድ ነገር ግን እንደሰማ ስለሚያውቅ ፈዝዞ ቀረ።

ምን ማለትዎ ነው?» ሲል በማጉረምረም ይጠይቃል፡፡
«ይህም ማለት» አለ ዣን ቫልዣ ፣ «ወህኒ ቤት ነበርኩ ማለት ነው፡፡»
ምነው እኔን ለማሞኘት ነው?» ሲል ማሪየስ ቅሬታውን ገለጸ፡፡
«ማሪየስ» አለ ዣን ቫልዣ፣ «ከወህኒ ቤት አሥራ ዘጠኝ ዓመት
ኖሬአለሁ:: በሌብነት ወንጀል ተከስሼ ነው የታሰርኩት:: በመጨረሻ ላደረስኩት ጥፋት የእድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶብኝ ነበር፡፡ ሆኖም አምልጬ
በመውጣቴ አሁንም ወንጀለኛ ነኝ::

ማሪየስ አሁን መከራከሩ ዋጋ እንደሌለው ስላመነ ዝም ብሎ ይሰማ ጀመር፡፡ ነገሩ እየገባው ሄደ፡፡ እንዲያውም ከነአካቴው ራሱም ፈራ፡፡

«ይቀጥሉ፤ ይቀጥሉ፤ ሁሉንም ይንገሩኝ» ሲል ተናገረ፡፡ «እርስዎ
የኮዜት አባት ነዎት!»
ፍርሃቱን ለመግለጽ ሁለት እርምጃ ወደኋላ ተራመደ፡፡
ዣን ቫልዣ በኩራት መንፈስ ጭንቅላቱን ወደ ጣራ አቅንቶ ያለምንም ማፈር ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«ምንም እንኳን የምለው ነገር የሚዋጥና የሚጥም ባይሆንም
እንድታምነኝ ያስፈልጋል::)
እዚህ ላይ ዣን ቫልገዥ ጥቂት ቆም ብሎ ንግግሩን በዝግታና ግርማ ሞገስ በተሞላበት አንደበት ቀጠለ፡፡

«ታምነኛለህ ፧ እኔ የኮዜት አባት ነኝ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ግን
አባትዋ አይደለሁም:: ፌቨሮል ከሚባል ሥፍራ ገበሬ ነበርኩ፡፡ ሥራዬ አትክልት መከርከም ነበር:: ስሜ ፎሽለማ ሳይሆን ዣን ቫልዣ ነው:: ከኮዜት ጋር ዝምድና የለንም:: ኣእምርህን ሰብሰብ አድርግ፡፡»
ለማሪየስ እድል ለመስጠት ንግግሩን ካቋረጠ በኋላ እንደገና ጀመረ፡፡
«ታዲያ ለኮዜት ምንዋ ነኝ?አዛኝ! ከአሥር ዓመት በፊት በሕይወት
መኖርዋን እንኳን አላውቅም ነበር፡፡ በእርግጥ እወዳታለሁ፡፡ የሙት ልጅ ስለሆነች አባትና እናት የላትም:: የዛሬ አሥር ዓመት ገደማ የእኔን እርዳታ በጣም ያስፈልጋት ስለነበር እርስዋን ማፍቀር ጀመርኩ፡፡ ልጆች ደካሞች
👍19
ስለሆኑ የማንንም ፤ እንደ እኔ ያለውን እንኳን፣ እርዳታ ይሻሉ፡፡ ይህን ግዴታዬን ለመወጣት ነበር ያስጠጋኋትና የሕይወቴ ቁራጭ ልትሆን የቻለችው:: ዛሬ ኮዚት የሰጠችኝን ሕይወት: ከእኔ ትታ እየሄደች ነው::መንገዶቻችን ተለያይተዋል:: ከአሁን በኋላ ምንም ላደርጋት አልችልም::
ዛሬ ጠባቂዋ ሌላ ሰው ነው:: ጠባቂዋ በመቀየሩ ደግሞ ተጠቅማለች እንጂ አልተጓዳችም
መጠቀሟ ደግሞ መልካም ነው።

ዣን ቫልዣ የማሪየስን ፊት ተመለከተ፡፡ ነገሩን እየረገጠ አሁንም ንግግሩን ቀጠለ።

«ማሪየስ ይህ ግምታዊ አነጋገር ሳይሆን እውነት ነው:: እኔ ትክክለኛና ቅን ሰው ነኝ:: በአንተ አመለካካት ራሴን ዝቅ በማድረጌ እርሱነቱን ከፍ ያደርጋል ብለህ ትገምት ይሆናል አሁን የምነግርህ
አሁን የምነግርህ ነገር ቀደም ሲል የደረሰብኝ ሲሆን በዚያን ጊዜ እንዳሁኑ የሚያሳዝን ጉዳይ አልነበረም::አዎን ትክክለኛና ቅን ሰው! በራሴው ጥፋት ሊሆን ይችላል፤ ስለእኔ ያለህ
ግምት ዝቅተኛ ይሆን ይሆናል:: አንተ የፈለግኸውን ግምት ልትወስድ ትችላለህ፡፡ እኔ ግን ቀና ሰው ነኝ፡፡ ከወህኒ ቤት አምልጬ ስለጠፋሁ ሕገ ወጥ ብሆንም ሕይወቴን የምመራው በሕሊና ዳኝነት ነው፡፡ ቃሌን አከብራለሁ:: መጥፎ አጋጣሚ የሙጥኝ ከሚል ወጥመድ ሲጨምረን
መጥፎ እድል ደግሞ ታላቅ ኃላፊነትን ከሚጠይቅ ሥራ ውስጥ ይከትተናል።
አየህ ማሪየስ፣ በሕይወቴ ዘመን ብዙ ነገር አይቻለሁ፡፡

ዣን ቫልዣ አሁንም ንግግሩን ለጊዜው ቆም አደረገ፡፡ ቃል መርሮት ምራቁን ለመዋጥ እንደሚታገል ሰው እርሱም ተቸገረ:: ሆነም ቀረም
ንግግሩን ቀጠለ፡፡

በኣንድ ወቅት ለመኖር ስል ዳቦ ሰረቅሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ ለመኖር ስል
ስም አልሠርቅም::

«ለመኖር!» አለ ማሪየስ ጣልቃ ገብቶ ፤ ለመኖር አዲስ ስም
አያስፈልጎትም እኮ!

«ይገባኛል» ሲል ዣን ቫልዣ መለሰ፡፡ አንገቱን ወደ ላይና ወደ ታች ደጋግሞ እየነቀነቀ::

ማሪየስ ወደ ዣን ቫልዣ ጠጋ ብሎ እጁን ዘረጋለት:: ዣን ቫልዣም
የማሪየስን እጅ ጨበጠ፡፡ «ምስኪን ኮዜት!» ሲል አጉረመረመ፡፡ «ይህን
ስትሰማ ምን ትላለች?››
«ኮዜት! አዎን፤ እውነት ነው:: የነገርኩህን ሁሉ ንገራት:: ይህም
ትክክለኛ አሠራር ይሆናል፡፡ ይህን አላሰብኩም ነበር፡፡ የለም! የለም አሳቤን ለውጫለሁ:: ላትነግራት አሁኑኑ ቃል ግባልኝ:: አንተ ካወቅህ ይበቃል።»
«ረጋ ይበሉ አባባ» አለ ማሪየስ ፤ «አትናገር ካሉኝ አልናገርም።
ምሥጢር ሆኖ ይቅር ካሉ ይሆናል::
«ይብቃን መሰለኝ» አለ ዣን ቫልዣ «ግን እኮ አንድ ነገር ቀርቷል፡፡»
ምን?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ::
«አሁን ማን እንደሆንክ ካወቅህ በኋላ የኮዜት አሳዳሪ እንደመሆንህ መጠን ሁለተኛ አያታለሁ ወይስ ባልገናኛት ይሻላል?»
ባይገናኝዋት የሚሻል ይመስለኛል» አለ ማሪየስ፡፡
«ሁለተኛ ዓይንዋን አላይም» ሲል ዣን ቫልዣ በማጉረምረም ተናገረ፡፡
ይህን እንዳለ ወደ በሩ አመራ፡፡ ለመውጣት በሩን እንደከፈተ እንደገና ቆም አለ፡፡ በሩን መልሶ ዘጋው::
«ግን» አለ፤ «ፈቃድህ ከሆነ፤ መጥቼ አያታለሁ:: እርስዋን ለማየት በጣም እፈልጋለሁ፡፡ ለእርስዋ ያለኝ ፍቅር ብርቱ ባይሆን «ከመካከላቸው ልግባና ልበጥብጥ» የሚል ሥጋዊ ፍላጎት አያድርብኝም ነበር፡፡ የዚህ
ዓይነት ብርቱ ፍላጎት ባይኖር ኖሮ ደግሞ አሁን የነገርኩህን ባልነገርኩህ፡፡ባልነግረህ ኖሮ ደግሞ አሁን እንደቀለለኝ አይቀለኝም ነበር፡፡ ስለዚህ ይህን
ሁሉ ያመጣው የኮዜት ፍቅርና እርስዋን የማየት ፍላጎት ስለሆነ አያታለሁ፡፡ነገር ግን እኔ ለእርስዋ ያለኝን ፍቅር ለማርካት ስል «አብሬያቸው በመኖር ከፍቅራችሁ መካከል አልገባም:: እንዲያውም ሁለተኛ ከአጠገባቸው አልደርስም» በሚል ውሳኔ ነው ያን ሁሉ ታሪክ የነገርኩህ፡፡ አሁን ሳስበው ደግሞ አብሮ መኖርና መተያየት ለየቅል መሆናቸውን ስለተገነዘብኩ ልያት ብዬ ጠየቅኩህ:: ለመሆኑ ለማለት የፈለግሁት ምን እንደሆነ በትክክል ገብቶሃል? አየህ! ኮዜት ካጠገቤ ሳትለይ ከዘጠኝ ዓመት በላይ ኖራለች::ስለዚህ አንተን ቅር ካላለህ ኮዜትን በየጊዜው እየመጣሁ አያታለሁ:: እግር
ግን አላበዛም:: ስመጣም ለብዙ ጊዜ አልቆይም:: እልም ብዬ ብጠፋ ደግሞ ደግ አይሆንም::»

«ከፈለጉ ለምን በየቀኑ አይመጡም» አለ ማሪየስ፤ «ኮዜት ደግሞ ደስ ይላታል እንጂ አይከፋትም::»
«እርሱማ እኔንም ደስ ይለኛል፤ እንዳላስቀይማችሁ፤ ደግሞም
በፍቅራችሁ መካከል እንዳልገባ ብዬ ነው እንጂ፡፡ ለማንኛውም ምስጋናዬ የላቀ ነው፤ ደግ ሰው ነህ ማለት ነው» አለ ዣን ቫልዣ፡፡
ማሪየስ ዣን ቫልዣን ለጥ ብሎ እጅ ነሳው:: ደስታና ተስፋ መቁረጥ ተሳክረውባቸው ነው ሁለቱ ሰዎች የተለያዩት::....

ማሪየስ ከመጀመሪያው ጀምሮ ዣን ቫልዣን ይጠራጠረው ነበር፡፡
ቀንቶ ይሁን ወይም በምን ምክንያት እንደሆነ አይታወቅም ብቻ ግን ዣን ቫልዣን ይጠላዋል፡፡ የዣን ቫልዣም ስሜት ከዚህ የተለየ አልነበረም::አሁን ግን ለማሪየስ ግልጽ ሆነለት፡፡ ይህም በመሆኑ ለሰውየው አዘነለት::
ይህ ለካ የሁለት ጊዜ ወንጀለኛ ቢሆንም የተናገረው ነገር እውነትነት እንዳለው ማሪየስ አምኖ ተቀብሎታል፡፡

እንዴት ያለ እምነት? ስድስት መቶ ሺህ ፍራንክ በገዛ ፈቃዱ ከእጁ
አውጥቶ መስጠቱ ቀላል አልነበረም:: ገንዘቡ ከየትም መጣ፣ ምስክር ሳይኖር በሕሊና ዳኝነት ብቻ ያን ሁሉ ገንዘብ ሰጥቶታል፡፡ ለምን? ይህ ሰው
ምንድነው የሚፈልገው? ሰውዬው የፈለገው ወንጀለኛ ቢሆንም በሕሊናው ዳኝነት የሚኖር ንጹህ ሰው እንደሆነ ማሪየስ እንዲያውቅለት ነበር፡፡ በሕሊና
ዳኝነት ሕይወቱን የሚመራ ሰው ደግሞ ታላቅ ነፍስ ያለው ነው::
ማሪየስ የዣን ቫልዣን ማንነት በትክክል ለማወቅ ሌሎች ጥያቄዎችን አነሳ::
ለምንድነው ይህ ሰው ጦርነቱ ቦታ የመጣው? ጠመንጃ አንስቶ
አልተዋጋም፡፡ ዣቬርን ለመበቀል ሲል ይሆናል በማለት ደመደመ፡፡ ዣቬር ታስሮ ዣን ቫልዣ እየጐተተ ወደ ጓሮ መውሰዱንና በኋላ በጥይት መተኮሱ ለበቀል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ምናልባት በሁለቱ መካከል ከባድ ጥላቻ ኖሮ
ይሆናል ሲል አሰበ፡፡ ያም ሆነ ይህ፣ ዣቬር በዣን ቫልዣእጅ ነው
የሞተወ::

ከዚያም ማሪየስ መልስ የሌለው ጥያቄ ይጠይቃል:: ይህም ጥያቄ
እንደ መርፌ ወጋው:: የኮዜትና የዣን ቫልዣ ሕይወት ይህን ያህል ምን አቀራረበው? ምን ዓይነት ተአምር፣ ምን ዓይነት ኃይል ነው ያቺን ምስኪን ከዚህ ሰው እጅ ላይ እንድትወድቅ ያደረገው? ይህቺን ድንግል ልጅ ክብረ
ንጽህናዋን ጠብቃ እንድትኖርና ራሱ ንጹህ ሳይሆን እርስዋን በንጽህና እንዲጠብቃት፧ እንዲንከባከባት ያደረገው የትኛው ሃይማኖቱ፡ ነው? በትምህርት እስክትበስል ድረስ ለምን አስተማራት? የመጨረሻው ፍላጎቱ ምን ሆኖ ነው እስከዚህ ተጨንቆና ተጠብቦ ያሳደጋት?

የዣን ቫልዥ ምሥጢር ማለት ይህ ሲሆን የፈጣሪም ምሥጢር ይህ
ነው:: ምሥጢር መሆኑም ማሪየስ በይበልጥ ግራ ተጋባ እንጂ ለጥያቄዎቹ መልስ አላገኘም::
ዣን ቫልዣ አላፊ ሰው ሲሆን ይህን ራሱም ተናግሮታል:: ሰውዬው
ማንም ይሁን ማን የበኩሉን ተወጥቶ አልፎአል:: ከአሁን በኋላ ስለኮዜት ሃላፊነት ያለበት ማሪየስ ነው፡፡ ኮዜት በአጋጣሚ የኑሮ ጓደኛዋን ፍቅረኛዋን፣ ባልዋን፣ በአሳብ የሳለችውን ወንድ አግኝታለች:: ኮዜት ክንፍ
አውጥታና ራስዋን ለውጣ ከአንዱ ዓለም ወደ ሌላው ስትሄድ ጠባቂዋን ብቻ ሳይሆን ሁለተኛ ፈጣሪዋን ዣን ቫልዣን ጥላ ነው የሄደች::
👍21
ማሪየስ በዚህ ዓይነት ያስብ፣ ያስብና ዞሮ ተመልሶ ከነበረበት
ይመለሳል፡፡ የዣን ቫልዣ ፍራቻ ከፊቱ፡ ድቅን ይልበታል:: ማሪየስ ምንም እንኳን የሕግ ሰው ቢሆንና ብዙ ቢያውቅም በሰዎች በተደነገገው ሕግና
በእግዚአብሔር ሕግ መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ አያውቅም::ስለአጠቃላይ ሕግና ትክክል ሥራም ልዩነት የነበረው እውቀት ግልጽ አልነበረም፡፡ በእርሱ አመለካከት ሰው ሕግ ከጣስ በሕጉ መሠረት መቀጣት
አለበት::

ዣን ቫልዣ ስለራሱ በሚናገርበት ጊዜ ቅን ሰው እንደሆነ ነው
የተናገረው:: ቢሆንም በማሪየስ ዓይን ዣን ቫልዣ ከኅብረተሰሱ መገለል ያለበት ወንጀለኛ ነው:: ለዚህ ነበር ዣን ቫልዣና ኮዜት ከአሁን በኋላ ግንኙነት እንዳይኖራቸው ማሪየስ የፈለገው:: ቢሆንም ይህ ሰው ራሱን እንደ
ንጹህና ትክክለኛ ሰው ወይም ደግሞ እንበል ራሱን እንደ ደካማ ሰው አድርጎ ቆጥሮአል፡፡ ያ ድክመቱ ነው ከስህተት ላይ እንዲወድቅ ያደረገው::ታዲያ ዣን ቫልዣን ከእርሱ ማራቅ እንጂ ወንጀለኛ ነው ብሎ መደምደም
ትክክል ነው?»
የዣን ቫልዣ ከቤቱ መምጣት ማሪየስን ያበሳጨዋል:: የዚህ ሰው
ከቤቴ መምጣት ምን ይጠቅማል? እንዳይመጣ ምን ማድረግ አለብኝ?» እያለ የተለያየ አሳብ መጣበት:: አንዱ አሳብ ሲሄድ ሌላው ይተካል:: አዲስ
አሳብ በመጣ ቁጥር መፍትሔውን ያገኘ እየመሰለው ይጎመጃል:: ይህን ስሜት ከኮዜት መደበቅ ቀላል አልነበረም:: ነገር ግን ፍቅር ማለት ችሎታና በቀላሉ ራስን ማታለል ማለት ስለሆነ በቀላሉ ሊወጣው ቻለ፡፡ አንዳንድ
ጥያቄዎችን በዘዴ በሚያነሳበት ጊዜ ልብዋ እንደ ነጭ ርግብ የነጣ በመሆነ ምንም አልጠረጠረችም:: ሆኖም ስለሕፃንነትና ስለወጣትነት ዘመንዋ እያነሱ ሲጫወቱ ይህ ምሥጢረኛና ወንጀለኛ ክብር የሚገባው ጥሩ ሰው እንደሆነና
ኮዜትንም ማንም ሰው ከሚያደርገው በላይ መንከባከቡንና ከልብ ማፍቀሩን
አልካደም::....

💫ይቀጥላል💫
👍185