አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


ወዴት ነው የሚሄዱት?

ያን እለት ከቀኑ ወደ አሥር ሰዓት ገደማ ዣን ቫልዣ ብቸኝነት
ተሰምቶት ብቻውን ተቀምጧል፡፡ ኮዜትን ካየ ስለእርስዋ ብዙ አይጨነቅም፡፡በአንድ ወቅት ገጥሞት የነበረው መጥፎ አጋጣሚ እየተረሳው ሄዷል፡፡
ነገር ግን ከአንድ ወይም ከሁለት ሣምንት በፊት የገጠመው ነገር በጣም እያሳሰበው ሄዶአል:: አንድ ቀን አንድ አውራ ጉዳና ላይ ሲንሸራሸር ቴናድዬን ያየዋል:: የዚህ ክፉ ሰው ከዚያ በነፃ መለቀቅ እጅግ አደገኛ
መሆኑን ተገነዘበ፡፡ ይህም በጣም አስጨነቀው:: ከዚህም በላይ የፓሪስ ከተማ ሰላም ራቀው:: የፖለቲካ ብጥብጥ እያየለ መጣ፡፡ በዚህም የተነሳ ጸጥታ አስከባሪዎችና ፖሊሶች ክትትላቸውን አጠናከሩ፡፡ ዣን ቫልዣ በክትትል መጠናከር ሰበብ የሚያዝ ስለመሰለው በጣም ፈራ:: ዣን ቫልዣ ከሚፈለጉት
ሰዎች አንዱ እንደሆነ ልቡ ያውቃል:: ስለዚህ በአስቸኳይ ከፓሪስ መውጣት ነበረበት:: ከፓሪስ ከተማ ብቻ ሳይሆን ከፈረንሳይ መውጣት እንደሚሻል
አመነ:: ከፈረንሣይ አገር ከሄደ ወደ እንግሊዝ አገር መሄዱን ይመርጣል፡፡ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከፈረንሣይ እንደሚወጡ ለኮዜት የነገራት በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ የቴናድዬ፣ የፖሊስ ክትትል፣ የጉዞውና ፓስፖርት የማውጣቱ
ጉዳይ በጣም አስጨነቀው::

እነዚህ ነገሮች አስጨንቀውት ሳለ ያን እለት በቀን ግቢው ውስጥ
ሲንሸራሸር ከቤቱ ግድግዳ ላይ «ደ ፣ ላ፣ ቤራሪ ጉዳና የቤት ቁጥር 16» የሚል ጽሑፍ በምስማር ተጽፎ ያያል::

ጽሑፉ በቅርቡ ለመጻፉ ያስታውቃል:: ምናልባትም ጽሑፉ ከተጻፈ ቢበዛ አንድ ቀን ውሎ ይደር እንጂ ከዚያ እንደማይበልጥ ይገምታል:: ጽሑፉ ማን ይላል? የሰው አድራሻ ነው? አንድ ሰው ለማመልከት የተጻፈ ይሆን? ለዣን ቫልዣ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ነው? ምንም ይሁን ምን አንድ
ሰው ግቢውን ደፍሮአል፡፡

ይህን እያሰላሰለ ሰው በአካባቢው ለመኖሩ በጥላው አወቀ፡፡ ሰውዬው ድንገት ይቆማል። ዞር ብዬ ልይ በማለት ሲያስብ የተጠቀለለ ወረቀት
ከእግሩ ሥር ይወድቃል የወረቀታ አወዳደቅ ከላይ ወደታች እንጂ ከሩቅ በጎን የወረወሩት አይመስል
ወረቀቱን አንስቶ ዘረጋው «አስወግድ»የሚል ቃል በትልልቅ ጽሑፍ በእርሳስ ተጽፎ አነበበ::

ዣን ቫልዣ ዞር ዞር አለ፡፡ በዚያ አካባቢ ሰው አልነበረም፡፡ ግን
ግራጫ መልክ ያለው ሸሚዝና የወይን ጠጅ ቀለም ያለው ሰሪ የታጠቀ ልጅ አይሉት ትልቅ ሰው በአጥሩ ዘልሎ ወደ ዋናው ጎዳና ሲወጣ በሩቁ ተመለከተ።

ዣን ቫልዣ ቶሎ ብሎ ወደ ቤቱ ገባ። ከከባድ ጭንቀት ላይ ወደቀ።

ማሪየስ ከመሴይ ጊልኖርማንድ ቤት ከወጣ ቆይቷል:: በታላቅ ተስፋ የገባው ሰውዬ ከቤቱ ሲወጣ ከመጠን በላይ ተስፋ ቆርጦ ነው:: መከራና ስቃይ ያስጨነቀው ሰው እንደሚያደርገው ሁሉ እርሱም
በአሳብ ተውጦ እያቀረቀረ ነው የሚጓዘው:: ጭንቅላቱ ባዶውን ስለቀረ የሚያስበው ነገር አልነበረውም:: ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ከጓደኛው ከኩርፌይራክ ቤት ደረሰ፡፡ ከነልብሱ ራሱን ከአልጋው ላይ ወረወረ፡፡
እስኪነጋ እንቅልፍ አልወሰደውም:: ፀሐይ እንደወጣ እንቅልፍ ወስዶት ኖሮ ክፉኛ አቃዠው::

ቅዠቱ ከእንቅልፉ ቀሰቀሰው:: ዓይኑን ገልጦ ሲያይ ከቤቱ ውስጥ
የነበሩት አራቱም ጓደኞቹ ለመሄድ ተዘጋጅተዋል፡፡

«ከጄኔራል ላማርክ ቀብር ትገኛለህ?» ሲል ጓደኛው ኩርፌይራክ ጠየቀው::

በቻይና ቋንቋ የሚያናግረው መሰለው:: ማሪየስ ጓደኞቹ ከቤት ከወጡ ጥቂት ቆይቶ ነው የወጣው፡፡ ዣቬር ከሰጠው ሽጉጥ አንዱን ኪሱ ውስጥ
አደረገ፡፡ ሽጉጡ ጥይት እንደጕረሰ ነው፡፡ ምን አስቦ ሽጉጡን እንደያዘ
ለማወቅ ያስቸግራል፡፡ የት እንደሚሄድ ሳያውቅ ቀኑን ሙሉ ከወዲያ ወዲህ ሲንቀዋለል
ዋለ፡፡ አንዳንዴ ዝናብ ቢያካፋም እርሱ አልተሰማውም:: ጦሙን እንዳያድር ለእራቱ የሚሆን ዳቦ ገዝቶ ኪሱ ውስጥ አደረገው፡፡ ግን ኪሱ ውስጥ እንዳለ ረስቶት ሳይበላው አደረ፡፡ ጊዜው ቶሎ አልመሽ ስላለው በጣም ተቁነጠነጠ፡፡ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ከኮዜት ጋር ቀጠሮ ስለነበረው ያቺን ሰዓት በጉጉት ይጠብቃል፡፡ ከተማው ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲዞር በአሳብ ጭልጥ ይላል፡፡
ከአሳቡ ሲነቃ የተኩስ ድምፅ ስማ፡፡ «ውጊያ ቀጥለዋል ማለት ነው?» ሲል ራሱን ጠየቀ መሽቶ ሦስት ሰዓት ሲቃረብ ወደ ቀጠሮው ቦታ ሄደ፡፡ ኮዜትን ሳያይ
ሁለት ቀን ስላለፈ በጣም ናፍቆአታል:: ሰዓቱ በመድረሱ በጣም ደስ አለው፡፡ የምንጓጓለት ነገር ልብን ያስጨንቃል እንጂ ቶሎ ስለማይደርስ ደቂቃው እንደ ዓመት ይረዝማል፡፡

ማሪየስ በለመደው ቀዳዳ ከግቢው ውስጥ ገባ፡፡ ኮዜት በሌላ ጊዜ ከምትጠብቀው ሥፍራ የለችም፡፡ ምናልባት ከቤቱ አካባቢ ትጠብቀኝ ይሆናል ብሎ ወደዚያ አመራ:: ከዚያም አልነበረችም:: አንገቱን ቀና አድርጎ ሲያይ
የኮዜት መኝታ ቤት መስኮት ተዘግቷል፡፡ አካባቢው በጣም ጭር ብሏል፡፡ በፍቅር ያበደው፣ የነደደው፣ የተቃጠለውና የሰከረው ወጣት ከፍቅረኛው
መኝታ ቤት መስኮት ላይ አፈጠጠ፡፡ ከአሁን አሁን ተከፍቶ «ኮዜትዬ ብቅ ትላለች» ሲል አወጣ፤ አወረደ፡፡ ግን መስኮቱ እንደተዘጋ ቀረ፡፡ በጨለማ
ለማየት እስከቻለ ድረስ በዓይኑ አካባቢውን ቃኘ:: ማንም የለም:: ድንገት አባትዋ ብቅ ያለ እንደሆነ ‹‹ምን ትፈልጋለህ?» ብሎ ያፈጥብኛል በማለት ሳይፈራ ቤቱን ዞረው:: በመጨረሻ አላስችል ብሎት «ኮዜት» እያለ ደጋግሞ
ተጣራ:: መልስ አላገኘም:: አሁንም ደገመና ተጣራ:: መልስ የለም:: ቤቱ ውስጥ ሰው እንደሌለ አወቀ፡፡

ቤቱን ተስፋ በቆረጠ ዓይን አየው፡፡ ከመቃብር ቤት ይበልጥ ጭር
ብሎአል፡፡ ብዙ የደስታ ምሽቶችን ወዳሳለፈበት የድንጋይ መቀመጫ ሄደ:: ልቡ እየከበደው ከመቀመጫው ላይ ቁጭ አለ፡፡ ለኮዜት ያለውን ፍቅር
እያሰላሰለ ኮዜት ከሄደች ከመሞት በስተቀር ሌላ የተሻለ ምርጫ እንደሌለው አመነ፡፡

ከአጥር ውጭ ድንገት ድምፅ ሰማ
«መሴይ ማሪየስ!»
ከተቀመጠበት ብድግ አለ፡፡
‹‹ማነህ?» ሲል ተጣራ
«መሴይ ማሪየስ፣ አንተ ነህ?››
«አዎን፡፡»
«መሴይ ማሪየስ» አለ ድምፁ፣ «ጓደኞችህ ባሪኬድ ከተባለ ሥፍራ ይጠብቁሃል፡፡»

ድምፁ እንግዳ የሆነ ድምፅ አልነበረም፡፡ የኢፓኒንን ድምፅ ይመስላል፡፡ ቶሎ ብሎ ወደ አጥሩ ሄደና በቀዳዳ አየ:: አንድ ወጣት ሮጦ ሲሄድ ተመለከተ፡፡ ጨለማ ስለነበር ሊለየው አልቻለም::
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የመሴይ ማብዩፍ ኑሮ እያቆለቆለ ሄደ እንጂ አልተሻሻለም:: ባለፈው
ዓመት የሠራተኛቸውን ደመወዝ መክፈል አቅቶአቸው ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ደግሞ የቤት ኪራይ መክፈል አቃታቸው፡፡ ቀስ በቀስ የቤቱን እቃ ሽጠው ጨረሱ፡፡ የጻፉትንም መጽሐፍ ገዢ ስላጣ እንደ አሮጌ መጽሐፍ ተቆጥሮ
በቅናሽ ሸጡት፡፡ ቀደም ሲል አልፎ አልፎ ሥጋ ይበሉ ነበር፡፡ ዛሬ ግን
ጠፍቶ የሚበሉት ደረቅ ዳቦና የተቀቀለ ድንች ሆነ፡፡ በመጨረሻ
የሚሽጡት ንብረት ሁሉ አልቆ የቀረው በደህና ዘመን የሰበሰብዋቸውና በጣም የሚወዷቸው መጻሕፍት ብቻ ነበሩ፡፡ መሴይ ማብዩፍ የሚያነዱት እንጨት ስላልነበራቸው ገና ጀምበር ስትጠልቅ ይተኛሉ፡፡ ከጊዜ በኋላማ በጣም እየደኸዩ ስለሄዱ ጎረቤት ሀሉ ይሸሻቸው ጀመር:: ሰዎች እንደሚሸሹዋቸው ስለገባቸው እርሳቸውም ይሸሿቸዋል:: በልጅ ስቃይ
👍18👎1
እናት እንደምትከፋ ሁሉ ጎረምሳ ሲሰቃይም ኮረዳ ይከፋታል፡፡ ሽማግሌ ቢከፋው ግን ማንም ደንታ የለውም:: ሆኖም የሽምግልና ዘመን ስቃይና
መከፋት ከሁሉም ይበልጥ የከበደ ነው:: ይህም ሆኖ መሴይ ማብዩፍ
ሐሞተ ቆራጥ በመሆናቸው ብዙ አልተከፉም:: በተለይ አንድ ብርቅ የሆነ የትም የማይገኝ መጽሐፍ በእጃቸወ በመገኘቱና በዚያ እድሜያቸው ዓይናቸው መጽሐፍ ለማንበብ በመቻሉ ደስ ብሎአቸው ይኖራሉ፡፡ ከቤታቸው ውስጥ የቀረው ደህና እቃ የመጽሐፍ መደርደሪያቸው ብቻ ነበር፡፡ በጣም ስለሚወዱት ሊሸጡት አልፈለጉም::

አንድ ቀን ሠራተኛቸው መጥተው «ዛሬስ እራት የምገዛበት ምንም
ነገር የለኝ!» ስትል አረዳቻቸው:: እርስዋ እራት የምትለው ደረቅ ዳቦና አራት ወይም አምስት የተቀቀለ ድንች ነው::

«በዱቤ መግዛት አትይችም?» አሉ መሴይ ማብዩፍ፡፡
«ምነው፣ ማንም በዱቤ እንደማይሽጥልኝ ያውቁ የለም!»
ወደ መጽሐፍ መደርደሪያቸው ሄደው የተቀሩትን መጻሕፍት አንድ
በአንድ ተመለከቱ፡፡ ልጅ ኖሯቸው ከአንዱ ልጅ ሌላውን የሚያማርጡ መሰላቸው፡፡ በመጨረሻ አንዱን መጽሐፍ ሳብ አድርገው አወጡ:: መጽሐፉን
አንጠልጥለው ከቤት እየሮጠ ወጡ፡፡ ከሁለት ሰዓት በኋላ ባዶ እጃቸውን ተመለሱ፡፡ ከኪሳቸው ውስጥ ሰላሳ ሉስ አውጥተው ከጠረጴዛው ላይ አኖሩ::

«በዚህ ምናምን ገዝተሽ ነይ» ሲሉ ተናገሩ:: ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ፊታቸው ጥቀርሻ እንደመሰለ መቅረቱን ሠራተኛዋ ተገነዘበች:: ምርጥ ተብለው ከተቀመጡት መጻሕፍት መካከል በየቀኑ
አንዳንድ እያወጡ መሸጣቸውን ቀጠሉዐያ ሁሉ መፅሀፍ እየሟሸሸ ሄደ አንዳንድ ቀን «እኔ አሁን እድሜዬ ሰማንያ ነው» ይላሉ መጽሐፉ ሳያልቅ መሞት ፍላጎት ያላቸው ይመስል፡፡ በየቀኑ ሀዘናቸው እየጨመረ ሄደ፡፡
ሆኖም አንድ ቀን ደስ አላቸው፡፡ አንድ መጽሐፍ ይዘው ሄደው በሰላሳ አምስት ሱስ ከሸጠ በኋላ ሌላ እጅግ አድርገው ይፈልጉት የነበረ መጽሐፍ በአርባ ሱስ ገዝተው ተመለሱ፡፡ ያን እለት እራት ሳይበሉ ተኙ፡፡

በየዕለቱ ከመተኛታቸው በፊት ከዚያ ብርቅዬ መጽሐፍ ሁለት ገጽ
ያነባሉ፡፡ ከማንበብ በስተቀር ሌላ ደስታ አልነበራቸውም:: በዚህ ዓይነት ጥቂት ሳምንታት አለፉ፡፡ በድንገት ሠራተኛቸው ታመመች:: ዳቦ መግዣ ቢጠፋ ሳይበሉ መተኛት ይቻላል፡፡ ቤት ውስጥ ሰው ታሞ ሲያጣጥር
መድኃኒት መግዣ ሲጠፋ ግን ምን ይኮናል? የሁለተኛው በጣም ያሳዝናል፡፡ ሐኪሙ ውድ የሆነ መድኃኒት አዘዙ:: ሠራተኛዋ ሕመምዋ እየጠናባት
ሄደ፡፡ አስታማሚ አስፈለገ፡፡ መሴይ ማብዩፍ ወደ መጽሐፍ መደርደሪያው ቢሄዱ የቀረው አንድ መጽሐፍ ነው:: ይህም የትም የማይገኝ ያ ብርቅዬ
መጽሐፍ ነው:: እንደነፍሳቸው ይወዱታል

ጥቂት አሰቡ:: እየተከዘ መጽሐፉን አንጠልጥለው ወደ መጻሕፍት
ተራ ሄዱ:: ቀኑ ሰኔ 4 ቀን 1832 ዓ.ም ነበር፡፡ ሲመለሱ አንድ መቶ ፍራንክ ይዘው መጡ:: ገንዘቡን ከአሮጊትዋ ሠራተኛ ፊት ቆልለው ቃል ሳይናገሩ ተመልሰው ወጡ፡፡
በሚቀጥለው ቀን በጠዋት ተነስተው ወደ ጓሮ ሄደው ከድንጋይ ላይ ቁጭ አሉ፡፡ ወጪና ወራጅ ያያቸዋል፡፡ ከተቀመጡበት ሳይነሱ እንዳቀረቀሩ
ለብዙ ሰዓት ቁጭ አሉ፡፡ በየመካከሉ እንደ ሕፃን ልጅ እንባ እያዛነቡ ያለቅሳሉ:: ማልቀሳቸው ግን አልታወቃቸውም:: ከሰዓት በኋላ ፓሪስ ከተማ ውስጥ ከባድ ግርግርና ረብሻ መፈጠሩ ተሰማ:: ከግርግሩ በኋላ ተኩስ ቀጠለ፡፡

መሴይ ማብዩፍ ቀና ብለው አዩ፡፡ አንድ አትክልተኛ በመንገድ
ሲያልፍ ስላዩት «ምንድነው ነገሩ?» ሲሉ ጠየቁት::
አትክልተኛው አካፋውን ትከሻው ላይ እንዳኖረ በጣም ዝቅ ባለ
ድምፅ መልስ ሰጣቸው::

«ኧረ አገር ተረብሾአል:: :
«የምን ረብሻ ነው?»
«እየተዋጉ ነው::
«ለምንድነው የሚዋጉት?»
«አይ ጌታዬ!» አለ አትክልተኛው::
«የት ነው የሚዋጉት?» ሲሉ መሴይ ማብዩፍ ጠየቁ::
«አርሴናል ከሚባል ሥፍራ አጠገብ፡፡»
መሴይ ማብዩፍ ወደ ቤታቸው ገቡ፡፡ ከቤት እንደገቡ ይዘው የሚሄዱት መጽሐፍ ከመደርደሪያው ፈለጉ፡፡ መጽሐፍ አልነበረም፡፡ «ለካስ እውነትም መፅሀፎቼ አልቀዋል» ሲሉ በመገረም ተናገሩ፡፡

ሰኔ 5 ቀን 1832 ዓ.ም

እንቅስቃሴው እነማንን ይጨምራል? ማንንም እና ሁሉንም፡፡ የኮረንቲ
እሳት ከተቀጣጠለ መጀመሪያ ትንሽ ሆኖ ይጀምርና በመጨረሻ ሁሉንም ያዳርሳል፡፡ አካሄዱ እንደ ነፋስ ሲሆን ይህም ነፋስ የሚናገር አንደበትን፤ሕልም የሚያይ ጭንቅላትን፤ በስቃይ ላይ የምትገኝ ነፍስን፤ በፍቅር
ከተማ የተቃጠሉ ፍቅረኞችን፤ ስቃይ በዝቶባቸው የሚያጓሩትንና እኔን አይነካኝም እያሉ ራሳቸውን የሚደልሉት ሳይቀሩ ሁሉንም ጠራርጎ ይወስዳል፡፡

«ወዴት ነው የሚወስዳቸው?»

የአጋጣሚ ጉዳይ ነው፡፡ አንዱን ለሥልጣን፣ አንዱን ለፍርድ፤ አንዱን ለሀብትና ሌላውን ለቅያሜ ይዳርገዋል፡፡

ነቀፌታ ያናደዳቸው፣ የወደፊት ተስፋ ያንሰፈሰፋቸው፣ የጦርነት
ፍራቻ ያስጨነቃቸው ፤ የወጣትነት ደም ያደፋፈራቸው፤ ትክክለኛ ፍርድ የገፋፋቸው፤ የማወቅና አዲስ ነገር የማየት ጉጉት ያደረባቸው፤ ለውጥ
የማየት ምኞት የተጠናወታቸውና ያልጠበቁትን የማየት ጉጉት ያሳበዳቸው ሁሉ በአንድነት ለውጥን እጅ ዘርግተው ይቀበሉታል፡፡ አንዳንዶቹም የተሰወረ ጥላቻቸውን ታቅፈውና የማይጨበጥ ተስፋቸውን አንግበው «መውደቁ የማይቀር ስለሆነ ያጣነውን ሁሉ መልሰን እናገኘዋለን» በማለት ባዶ ቀፎ
ሕልማቸውን አንግተው ይፈልጉታል፡፡ አፈር በልቶ አፈር ላይ ያደገው ደግሞ ያለፈለት እየመሰለው በማይጨበጥ ተስፋ ሰክሮ እያበደ ያሳብዳል
ሰነፉም ሳይሠራ የሚበላበት ቀን የደረሰ መስሎት ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል )
በአእምሮ ያልበሰለውም ጥቂት አሳብ ይዞ ሲክነፈነፍ አዋቂውም «እስቲ ይሄ ነገር ምን ይመስላል» እያለ መፈላሰፉን ይቀጥላል፡፡ ይሄ ነው የለውጥ፤ የአብዬት ከፊል ገፅታ።

እድል ጠባቂዎች፣ ሥራ አጦች፣ አውደልዳዮች፣ ዱር አዳሪዎች፣
ነግረኞች፣ የተቆረጠ ሥራ ሠርተው ሳይሆን እድል እየጠበቁ የእለት እንጀራቸውን የሚያገኙ ሰዎች፣ ምጽዋተኞች፣ የታረዙ፣ በባዶ እግር የሚኳትኑ ሁሉ የአንድ ዓይነት እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ናቸው፡፡

ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እንደማዕበል ያለ ሲሆን በመጀመሪያ ዝም ብሎ
ይነፍሳል ፤ በኋላ ግን ቅርጽ እያወጣ ይሄዳል። እንቅስቃሴው ቅርጽ እያወጣና እያደገ በሄደ ቁጥር እንደ መብረቅ ይማታል፣ ይበጣጥሳል፣ ያወድማል፣
ያቀጣጥላል፣ ያበላሻል፤ ያለማል፣ ይጠራርጋል፡፡

ተጠርጎ ለሚሄድ ወዮለት፤ መመለሻ የለውምና፡፡ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ አንዱን ከሌላው ጋር ያላትመዋል፡፡ አንዱ ሲያይል ሌላው ይደክማል፡፡
ወዮለት ለደከመው::
ምንም እንኳን ለሦስት ወራት እንቅስቃሴው ጋብ ቢልም በ1832 ዓ.ም በበልግ ወራት የፓሪስ ከተማ ለበለጠ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ስሜት
እንደሚኮረኩራት ኮረዳ ተዘጋጅቶና ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ነበር፡፡ ትልቅ ከተማ ከጎረሰ ጠመንጃ ጋር አንድ ነው፡፡ የጎረሰ ጠብመንጃ ስሙ እንደሚያመለክተው ቃታውን ከነኩት ጠቡን ይነዳዋል። ጥይቱ ከወጣ አይመለስም፡፡ ከነአካቴው ሌላው ይተኰሳል፡፡ እሳት ይቀጣጠላል። በሰኔ ወር 1832 ዓ.ም. የጄኔራል ላማርክ ሞት ነበር እንደመጀመሪያ ጥይት
ሌላውን የቀሰቀሰው፡፡
👍13👏2
ጄኔራል ላማርክ በአገሩ ዝናው የገነነና ጀግንነቱን በጦር ሜዳ ያስመሰከረ ጀኔራል ሲሆን ሰው ፊት ቆሞ ሊናገር አንደበተ ርቱዕ አሳማኝ ሰው ነበር። ሲናገር ቃሉ እንደ ጎራዴ ይሰነጥቃል፡፡ ንጉሡን በቀና መንፈስ ከልብ
በማገልገሉ ሰፊው ሕዝብ ይወደዋል፡፡ ነገርን አመዛዝነውና ቀኝና ግራውን አይተው የወደፊት ሕይወት የሚመራበትን አሳብ የሚያቀርቡ ሰዎችን ስለሚደግፍ ተራማጆችም ያደንቁታል፣ ያከብሩታል፡፡ ስለዚህ ነው በጄኔራሉ መሞት ብዙ ሰው ያዘነው፡፡

የጄኔራሉ ቀብር የተፈጸመው በሙሉ ወታደራዊ ክብር ነበር፡፡ ግብዓተ መሬቱ እንደተፈጸመ አንድ ግለሰብ በእንጨት ላይ የተሰቀለ ቀይ ጨርቅ ወደ ሰማይ በማውለብለብና የነበረውን መንግሥት በመንቀፍ ይናገራል።
ሕዝቡ ይንጫጫል:: መሣሪያ የያዙ ብዙ ሰዎች ብቅ ብቅ አሉ። ከቀብሩ ቦታ ወደ መሐል ከተማ ጉዞው ይቀጥላል፡፡ ከተማው ጤነኛ ስላልነበረ በየቦታው ጸጥታ አስከባሪዎች ተሰልፈዋል:: የረብሻው ማየል ሲሰማ ሕዝቡ
በሚጓዝበት ኣቅጣጫ ከሚገኝ ድልድይ አካባቢ የጦር ኃይል ተሰብስቦ ይጠብቃል፡፡ የአመጹ መሪዎች ሕገዘቡን አስከትለው ይደርሳሉ፡፡ ከዚያማ ምኑ ቅጡ አገር ተተራመሰ

በመጀመሪያ ሦስት ጥይት ተተኮሰ፡፡ ከዚያ ሴቶች እግሬ አውጪኝ አሉ፧ ሕፃናት ተንጫጩ ፣ ጥይት አጓራ፣ ጉራዴ ተብለጨለጨ፣ የተመታ ሲያጓራ የመታ ፎከረ:: ጦርነት መጀመሩ በመላ ፓሪስ ተሰማ፡፡ ቤት
ሲቃጠል ነፋስ ካለው እሳቱ በቶሉ እንደሚዛመት ሁሉ ረብሻ ሲገነፍል፣አብዮት ሲፈነዳ ከእሳቱ ይበልጥ ከመቅጽበት ይስፋፋል፣ አገር ያዳርሳል፣ ማቆሚያና ማባሪያ የለውም:: ረብሻው ቀጠለ፣ የሕዝበ ቁጣ ገነፈለ፣
የፈረንሳይ አብዮት ሰኔ 5 ቀን 1832 ዓ.ም. ተቀጣጠለ፡:
ገንፍሎ በመነሳት ከሚፈጠር ሕዝባዊ ትርምስ ይበልጥ እፁብ ድንቅ የሚያሰኝ ነገር የለም፡፡ በአንድ ጊዜ በያለበት ሕዝቡ ሆ! እያለ ከዳር እስከ ዳር ተንቀሳቀሰ፡፡ ይህ እንቅስቃሴ የተጠበቀ ነበር? አዎን፡፡ ዝግጅት ነበረው? በፍጹም:: የት ነው የተጀመረው? በየሥርቻው:: ከየት ወረደ? ከሰማይ:: ብቻ ዝም ብሎ ከየትም ተፈነቀለ ማለቱ ይሻላል::

መጀመሪያ ከሥፍራው የደረሰ ሰው ሕዝቡን እንደ ቦይ ውሃ
ወደፈለገው አቅጣጫ ይመራዋል፡፡ ሁሉም ያጨበጭባል ሱቆች ይዘጋሉ፣ አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል ፣ ሕዝቡ ከወዲያ ወዲህ ይሯሯጣል፣ ገረዶች
ከየቤቱ መስኮት እየተንጠላጠለ ይሳሳቃሉ፣ ወጣቶች የነገሩን ምንነት ሳያጤኑ ጥልቅ ይላሉ፡፡ «ተነስ ተንቀሳቀስ» እያሉ ጩኸት ያስተጋባሉ፡ ሩብ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፓሪስ ከተማ ላይ የሆነውን ላውጋችሁ።....


💫ይቀጥላል💫
👍10
#ገረገራ


#ክፍል_አንድ


#በታደለ_አያሌው

“እኔ እምልሽ” አለች እናቴ፣ ሆድ ሆዴን እያየች።

“እመት እመዋ?” አልኋት፣ ዳር ዳርታዋ ያልገባኝ ይመስል።

“እምታዋዩኝ ጉዳይ የለሽም ወይ?”

"እ"

በቃ፣ አዉቃብኛለች። ለነገሩማ እንዲህ ሆዴን ገፍጥጬ እንዴት
አይታወቅብኝ? እመዋ አይደለች እንዴ ሴትዮዋ? ለመዋሸትም ለማመንም እያመነታሁ የምንተፍረቴን ሰረቅ አድርጌ ሳያት፣ አሁንም ዓይኗን ከሆዴ
ላይ አልነቀለችውም። በአዛኝቷ! ከቅድሙ ይልቅ አሁን ደግሞ እንዴት ነው ዓይኗ የደፈራረሰው? ጥርሶቿን ልትፈለቅቅ ብትሞክርም፣ እምቢ
እንዳላት ግን ታውቆኛል። እንዲሁ መግቢያ ስታሳጣኝ፣ ዝም ብዬ ወደ ኋላ ሸሽቼ ገረገራውን ተደገፍሁና፣ ኹለተኛ እንኳን የሌለውን የቤተ ክርስቲያኑን ጉልላት ደጋግሜ መቁጠር ጀመርሁ። እንደ ሁኔታዬማ
የተደገፍሁትን ሁሉ ገፍቼ አለመጣሌ አስደንቆኛል።

“ግድየለም ተዬው እሺ፤ ባሰኘሽ ጊዜ ራስሽ ትነግሪኝ አልነበር
እንዲያዉስ? ተዪው በቃ”

“አይ” አልሁ፣ እጄን በዓይኗ እና በሆዴ መካከል ማድረጉን እንደ ተሻለ አማራጭ እየሞከርሁት፡፡ “ጊዜ እየጠበቅሁ ነዉ እንጂ፣ መደበቁን ፈልጌው አልነበረም እኮ እመ። ልደብቀውስ ብል ከእንግዲህ እየገፋ እንጂ እየጠፋ አይኼድልኝ ነገር! መቼስ ጉዴ ፈልቶ የለም አንዴ?”

“እንግዲያው እማትነግሪኝ፤ ንገሪኛ”

“እረ እመዋ ስሞትልሽ”

አንጀቷን ሳልበላው አልቀረሁም። ዓይኖቿን ወደ ዓይኖቼ አምጥታ
በርኅራኄ ስታየኝ ቆየች። እንዲያዉም ለምን እንደሆነ ባይገባኝም፣ ሳቅ ሳቅ እያላት መጣ። ቆይታማ ጭራሽ ስቃ ልታስቀኝ ጭምር ምንም
አልቀራት። እንዲህ ስትሆን ደግሞ እንዲያዉም ከነጭራሹ ያዘነችብኝም አልመስልሽ እያለችኝ መጣች።

“ተንግዲህ አያት መሆኔም አይደል?”

ዝም አልኋት። አያት መሆን የምትጀምረዉ በእኔ ይመስል፣ እንደ ብርቅ ማየቷ አልተዋጠልኝም። እንኳንስ ታላላቆቼ፣ ታናናሾቼ ጭምር አያት
አድርገዋት የለም'ንዴ? ያልሰማሁ መስዬ፣ ዝም አልኋት።

“ሆድሽን አይቼ አንቀጽዋን ልገምት?”

አሁንም ዝም።

“ሴት ናት፤ አይደለችም?”
"ጭጭ"
“ስም ላውጣላት?”
እርጭ፡፡
“ቱናት" ብያታለሁ። ደስ ይል የለ? በቃ ሴት ብትሆንልኝስ፣ ቱናት ነው
እምላት እኔ”

ዓይናማ ድንጋይ እንደ መሰልሁ ቀረሁ፣ በፊቷ። የምለው ቸግሮኝ
እየተንተባተብሁ ሳለ፣ ቄስ ገበዙ ወዳለንበት ቀርበው ሰላምታ አቀረቡልንና ከጉድ አተረፉኝ፡፡ ደራሽ መልአክ መስለዉ ነዉ የታዩኝ። ጎንበስ ቀና እያሉ
በረዥሙ ጤንነታቸውን ከተጠያየቁ በኋላ፣ እመዋን አበመኔቱ እንደሚፈልጓት ነግረዋት ተመለሱ። ወዲያውኑ ፈቃድ እየጠየቀችኝ በሚመስል ሁኔታ፣ ለዐመል ያህል ወደኔ አይታ መልከኛዋን የሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረትን እና ባለ ሞገሱን የበዓታ ለማርያም ገዳም ሕንጻ
ወደሚከፍለው ሰፊ አደባባይ ገባች። እሷ ገና ትንሽ ፈቀቅ ከማለቷ፣ አጭር መልእክት ሲመጣልኝ የእጅ ስልኬ የሚያሰማውን ጺዉጺዉታ
አሰማኝ።

ወጣ አድርጌ ስመለከተዉ፣ ከባልቻ መሆኑን አወቅሁ።

ባልቻ፣ በአሁኑ ጊዜ የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ሲሆን፣ የላከልኝ መልእክት
(አሁኑኑ እዚያዉ ይላል። በአስቸኳይ ስፈለግ የሚመጣልኝ እንዲህ ያለ መልእክት ነው። የምፈለገው ድንገተኛ ለሆነ አጭር ስብሰባ ወይም ለአንዳች ተልእኮ ወይም ለሌላ ለምንም ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ምንም
ቢሆን ምን ግን፣ እንዲህ ያለ መልእክት በደረሰኝ በዐሥር ደቂቃዎች ውስጥ መድረስ ይኖርብኛል። በተለይም የተፈለግሁት እንደ አሁኑ በባልቻ
ከሆነ፣ እኔን የሚፈልግ እጅግ አስቸኳይ ጉዳይ ተፈጥሯል ማለት ነው።ስለዚህ፣ እመዋ አበመኔቱን አነጋግራ እስከምትመለስ ድረስ ለመጠበቅ ቀርቶ፣ በስመ አብ እንኳን የምልበት ጊዜ አይኖረኝም፡፡ ይልቁንስ
አሁኑኑ መሮጥ አለብኝ። ያለበለዚያማ የእመዋ ሰላምታ ብቻውን ጉዞ ፍትሐት ያስጨርሳል። በዚያ ላይ አበመኔቱ የፈለጓት እንዲሁ ለማነጋገር ብቻም ላይሆን እኮ ይችላል። አይበለውና እኔ እዚሁ ከአሁን አሁን መጣች
እያልሁ እሷን ስጠባበቅ፣ ምንጣፎችን እንድታጥብ ወይ ደግሞ የተግባር ቤት ሥራ ቢያዝዟትስ ምን ይዉጠኛል?

ኧረረረ! መሰናበት አለብኝ፡፡ አሁኑኑ።

“እመዋ” አልኋት፣ እንደ መሮጥ ብዬ ከኋላዋ ስደርስባት።
“ምነዉ ምሆንሽ?”
“በቃ ከሰሞኑ ብቅ እላለሁ”
“ምን ልትሆኝ ነው አሁን? ቆዬኝ ይልቅስ ደርሼ መጣሁ”
“አይ፤ ሥራ ቦታ ቶሎ ነይ ተባልሁኝና
“ኤድያ! ያንቺ ሥራ ደሞ። ወይ እንዲህ ነዉ አይሉት፣ ወይ ለእናት
የሚተርፍ ጊዜ አይሰጥ”
“ሰሞኑን እኮ እመጣለሁ”
“ጭራሽ?” አለች ቆጣ ብላ፣ ከቤት እንደ ወጣሁ ማደር ማብዛቴን ጭምር እንደ ከነከናት በሚያስታዉስ ሁኔታ።

“ያዉ የሥራ ነገር አይደል፣ ምን ላድርግ ብለሽኝ ነዉ?”

“እኮኮኮሽ! ብትሄጅስ እዉነት እሱን ሳትነግሪኝ ልትሄጅ ነወይ?”

“የቱን እመ?”

ሆዴ ላይ ዓይኗን ጣለች። ገባኝ፡

“ምን ላድርግ ብለሽኝ ነዉ እመ፤ ያዉ እንጀራ አይደል?”

“ይሁን እሺ። ባይሆን ቶሎ እቤት አትመጭም? ከሥራሽ መልስ?”
አለችኝ፣ በስስት እና በቅያሜ ትንሽ ካስተዋለችኝ በኋላ፡፡

“እሺ” አልኋት፣ ሳላቅማማ። እኔ እንዲያዉም አብሪያት ሆኜ
እየዳበሰችኝም ጭምር፤ ታሳሳኛለች። ለቅጽበት እንኳን የሚለየን ባይኖር ደስታዉን አልችለዉም።

“እሺ እመጣለሁ” አልኋት።

“ትመጫለሽ? በይ ደሞ እንደ ሠለስትናዉ እመጣለሁ ብለሽ ቅሪ አሉሽ።በይ ደህና ዋይ። መኪናሽን ይዘሽ የለ? ቀስ እያልሽ ንጂ ደሞ። ጥድፍ ጥድፍ ትይና ወዮልሽ!”
በዓይኔ ትንሽ ሸኝቻት ሰዓቴን ስመለከት፣ ሦስቱ ደቂቃ እዚሁ ወድሟል።
ቢሆንም የቀረኝ ሰባት ደቂቃ፣ በቂዬ እንደሆነ እያሰብሁ ወደ ግቢዉ መዉጫ በር ዘወር ስል እንደገና ጠራችኝ

"እመት እመዋ?”

“ይቺን ነገር...” ብላ፣ ወደ ጉንፏ እየዳበሰች ወደኔ መለስ ስትል፣ ወደ እሷ ተሽቀዳድሜ ሮጬ ተቀበልኋት። ነገርዮዋ በእራፊ ጨርቅ ስለተጠቀለለች ምን እንደሆነች ላውቃት አልቻልሁም፡፡ የእምነት አፈር ልትሆን እንደምትችል ግን ገምቻለሁ።

“ምን ላድርጋት እመዋ?”

“እቤት አድርሰሽልኝ እለፊማ”

እንደገና በስስት ተሰነባበትንና፣ ወደ ሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት መለስ ብዬ ተሳለምሁ። ጨርሼ እየወጣሁ፣ ልክ በወንዶች መግቢያ በኩል ስደርስ፣ አንድ ሰዉ በትከሻዬ ትክክል ድንገት በኃይል አስነጠሰብኝ። ሰአሊ
ለነ! ከየት ነዉ እንዴ? ድምፁን ተከትዬ ቀና ብል፣ መትረየስ በበሩ
ትክክል ካነጣጠረ አንድ ወታደር ዓይን ጋር በዓይኔ ገጠምሁ። ክዉ ብዬ ነዉ የቀረሁ። ምንም እንኳን ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ ከቤተ መንግሥቱ ግቢ ጋር አጥር ብቻ የሚከፍላቸዉ ቢሆንም፣ ጥበቃዉን ግን በዚህ ደረጃ
አልጠበቅሁትም። ቆይ ምንድነዉ የሚጠብቀዉ? ማን ላይ ነዉ እንዲህ ያነጣጠረዉ? ካልጠፋ ቦታ እስከ ታቦቱ መቀመጫ የመቅደስ ክፍል ድረስ
በሚያሳይ ቅርበት ላይ እንዲህ ያለ ማማ? በዚያም ላይ ያጠመደ ወታደር?ስንት ጊዜ እዚህ ስመላለስ፣ ያለ ዛሬ አስተዉየዉ አላዉቅም። የግንብ
አጥሩን ተከትዬ ዙሪያዉን ስመለከት፣ ተመሳሳይ ወታደሮች በተመሳሳይ አኳኋን ዓይናቸዉን የሰጎን ዓይን አስመስለዉ ቆመዉባቸዋል። በሁሉም
የቤተ መንግሥቱ ወሠንተኛ አብያተ ክርስቲያናት እንደዚሁ ነዉ። ልክ እንደ ኪዳነ ምሕረት ሁሉ ወደ ታዕካ ነገሥትም ወረድ ብዬ አየሁ፣ ወደ ግቢ ገብርኤልም አለፍ ብዬ አስተዋልሁ። በሪፐብሊኩ ጠባቂዎች
ተከቧል።
👍582🥰2👏2😁1😱1
በዚህ ተገርሜ አላበቃሁም። መኪናዬን ፈንጠር አድርጌ ወዳቆምሁበት ቦታ ራመድ ራመድ ስል፣ የማላውቃቸው ኹለት ሴቶች ማለፊያዬ ላይ ቆመው ሲያሙኝ ደረስሁባቸው። ይኸኔ ሲያዩኝ በሐፍረት መድረሻ ያጣሉ
ብዬ ስጠብቅ፣ የባሰ ይግረምሽ ብለዉ ጭራሽ ስሜን እየጠሩ
መሟገታቸውን ተያያዙት። እንዲያውም መስማቴን ሳይፈልጉት ባይቀሩ
ነዉ መሰለኝ፤ በቀረብኳቸው ቁጥር የባሰ አሟሟቁት። ብቻቸውን ቢሆኑም ክርክራቸውን ግን የሕዝብ ለሕዝብ አስመስለውታል። እኔም
እንደሚያልፍ ሰው እግሬን በእግሬ እየጎተትሁ፣ ጆሮዬን ጣል
አደረግሁባቸው።
“እረ እህቱ ናት እሷ!”
“አይደለችም”
“እህቱ ናት”
“በጭራሽ! ያንቺ እርግጠኛነት ከምን እንደ መጣ አይገባኝም። ምናልባት እንዳልሽው እሷ ለእሱ እህቱ ብትሆን እንኳን፤ እሱ ለእሷ ወንድሟ እንዳይደለ ግን በነፍሴ ልወራረድሽ!”

“እርፍ! አሁን ገና ጨዋታ አመጣሽ። ምን ማለት ነው ደግሞ ይኼ? እህቱ ለሆነችለት ሰው፣ ወንድሟ የማይሆንበት ነገር መጣ እንዴ ደሞ? እንዲህ ያለውን ዝምድና ካንቺ በቀር የሚያውቀው አይኖርም መቼስ!”

እኔ ለራሴ ሆዴ እንዳይገፋ ገፍቶብኝ ሰማይ ምድሩ ተደበላልቆብኛል፤ ምንድን ነው ደግሞ እነዚህ የሚያወሩት? በሴቶቹ ሙግት መካከል ቅድም
እመዋ ሴት ከሆነች ቱናት ብያታለሁ ያለችው ስም ትውስ አለኝ። መታወስ ብቻም ሳይሆን ትርጉም አገኘሁለት። እህቱ ናት ለማለት አይደል እንዴ ቱናት ማለቷ? እሷም የእነዚህን ወይም የእነዚህ ዓይነቶቹን ሴቶች ቅልመዳ ቀምሳዋለች ማለት ነዉ። ይኼ ወሬ ተደጋገመብኝሳ! አልፌያቸው ብዙ ርቄ ሁሉ ሴቶቹ ይሰሙኛል። እንደ
መከተልም ይቃጣቸዋል።

“ነፍሴን አስይዤ ልወራረድሽ ከፈለግሽ፤ ወንድሟ አይደለም”

“ምነው አንቺ ደግሞ ነፍሴ የአንድ ብር ናት አልሽ ይህን ያህል? ይልቅ
ለሚረባ ለማይረባው ነፍስ
መምዘዝሽን ትተሽ
አትመልሽልኝም? ምንድን ነው ይህን ያህል እርግጠኛ ያደረገሽ እያልሁሽ አይደል?”
የሚደንቁ ናቸው። የደነቁኝ ግን ስሜን እየጠሩ ስለኔ በመሟገታቸው ብቻ
ሳይሆን፣ እኔ እንድሰማላቸው የሚሆኑትን ባየሁ ጊዜ ነው:: እንጂ፣ እኔ እነሱን ሳላዉቃቸዉ እነሱ እኔን ማወቃቸዉ ይኼን ያህል የሚገርም ሆኖ አይደለም። ምክንያቱም፣ ዕድሜ ለተወዳጅ ድምፄ፣ በብዙዎች ዘንድ
እታወቃለሁ። ይብላኝ ማንነታቸው እስኪገመትባቸው ድረስ ግልብ
ለሆኑት ለእነሱ ለራሳቸው እንጂ፣ እኔስ እነማን እንደሆኑ እየተገለጠልኝ መጥቷል።

ማነኝና ልጅት!

ዉብርስት እባላለሁ። ዉብርስት በልስቲ።ዐጽሙን ያለምልምልኝ እና ወላጅ አባቴ ቡሩክ የሆነ ካህን ነበር። ቀዳሽ፡፡ ቄስ በልስቲ አሁንገና ይባላል። እሱ ያልተሳለመው ገዳም እና ያልቀደሰበት ክፍለ ሀገር በኢትዮጵያ መኖሩ ያጠራጥረኛል። እናታችንም እሱ በሄደበት
ሁሉ ተንከራታለች። እኛ ልጆቻቸዉ ደግሞ የእናታችንን ቀሚስ እየያዝን፤ እሱ በዞረበት ሁሉ እየተከተልን ያላየነው የለም። በደቡብ ጫፍ ኬንያ
ድንበር ሳይቀር፣ ሞያሌ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ለኹለት
ዓመታት ሲቀድስ እኛም እዚያ ነበርን። እንደዚሁ ባለ ዕድል አብዛኛውን የሰሜኑንም፣ የምሥራቁንም ሆነ የምዕራቡን ክፍል እንደ ልብ ዞሬበታለሁ። እንዲያውም አንዲት የትምህርት ካርዶቼን ያሳየኋት ጓደኛዬ፤ «ኢትዮጵያ ብዙ ከተማ እንዳለት ያወቅሁት ዉብርስት
ካስቆጠረችኝ በኋላ ነው። እሷ ከተማ እና ትምህርት ቤት የቀያየረችውን ያህል፤ ምድር ፀሐይን አልተሸከረከረቻትም ብላ እያሾፈች የጓደኞቿ መሳለቂያ አድርጋኛለች። የሆነው ሆኖ እንደኔ የጓደኛ ሀብታም አይኖርም። የወንድምና የእህትስ ቢሆን! እንደኔ በሰዉ የተከበበ ይኖር
ይሆን? በሄድሁበት ቦታ ሁሉ እንደ ነፍሴ የሚያሳሱኝ ጓደኞች ያፈራሁ
ሲሆን፣ ስሙ በተጠራ ቁጥር የማልደነግጥለት የኢትዮጵያ ወንዝ አንድ እንኳን ለምልክት አይገኝም። ምክንያቱም በብዙ ወንዞች እግሬን ታጠቢያለኋ! በዚህም የተነሳ፣ የየት ከተማ ልጅ ነሽ ስባል የምቸገርበትን
ያህል፣ በቀላሉ የማልመልሰው ጥያቄ ገጥሞኝ አያውቅም።
እናቴም አብራ ነበር የተንከራተተችዉ። በኋላ አባቴ ከመሞቱ በፊት፣ የመጨረሻ አገልግሎቱ በነበረበት ከታላቁ ቤተ መንግሥት ጋር አጥር
በምትጋራዉ ሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን፣ ተመላላሽ አገልጋይ ሆና ቀጠለች። በእርግጥ አንድ አንድ ሰሞን፣ በዚሁ ግቢ ዉስጥ ባለችዉ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ዉስጥም ስታገለግል
አግኝቻት አዉቃለሁ። በእነዚህም ብቻ ሳትወሰን፣ በሌላ ሰሞን ደግሞ አጠገብ ባለዉ የግቢ ገብርኤል ገዳም ዉስጥ ለሥራ ላይ እና ታች ስትል ትታያለች። ማዕረጓ እና የአገልግሎት ድርሻዋ ግን እስከ አሁንም ድረስ
አይገባኝም፡፡ አንድ አንድ ጊዜ እንደ ዐቃቢት፣ ሌላ ጊዜ እንደ አንጣፊ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ማንኛዉም ምእመን ትሆናላች። ለነገሩ፣ ለምን እንደሆነ እኔም ቁም ነገር ብዬ ጠይቂያት አላዉቅም። መቼም ከሁሉም ጋር ተግባብቶ የመኖር ጥበቡን፣ ማንም የእሷን ያህል የታደለዉ የለም::
ትንሹም ትልቁም ያዉቃታል። እሷም የማታዉቀዉ አገልጋይ ከሦስቱም ግቢዎች ተፈልጎ አንድ እንኳን ለምልክት መገኘቱን እኔ እንጃ፡፡

እኔ ዉብርስትስ?

የኋላ ኋላ ያወቀኝ ሰዉ
ሁሉ በተለየ የሚያዉቀኝ፣ ከእጄ በማይጠፋው ክራሬ እና እንጉርጉሮዬ ሊሆን ይችላል። በእርግጥ ለክራር ባለኝ ፍቅር
እና ችሎታ የተነሳ፣ ያልደረስሁበት ቦታ የለም። የክራሩ ሁሉ ንግሥት
የምላት፣ ስመ ጥሩዋ አስናቀች ወርቁ እንኳን ሳትቀር ይኼንን ነገሬን አይታልኛለች፡፡ ማየትም ብቻ ሳይሆን እንደ ልጇ የምትሳሳለትን የራሷን ክራር ሽልማኛለች። ያዉም ወዛሙን፣ ዕድሜ ጠገቡን ክራሯን! አልጋ ላይ በዋለችበት ጊዜ ደግሞ እንዲሁ ከስንት አንድ ሲሞላልኝ እየሄድሁ ክራር የተጫወትሁላትን ከቁም ነገር ቆጥራልኝ፣ ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረገችዉ ቃለ ምልልሷ ጭምር ስሜን
ጠርታልኛለች። እኔም ይኼዉ የዚህን ቃላ ምልልስ ቅጂ፣ በዞርሁበት ሁሉ በሞባይሌ ይዤዉ እየዞርሁ ሳልሰማዉ አድሬ አልዉልም። መታደል
አይደል!

በእርግጥ መልኬንም አይቶ ቆንጆ ነሽ የማይል ሰው አጋጥሞኝ
አያውቅም። ምንም የማያልቅበት አምላክ ዉብ አድርጎ ፈጥሮኛል። ዓይን ሁሉ የሚከተለኝ ቆንጆ አድርጎ ከመፍጠሩ ሌላ፣ ማር ማር የሚል ድምፅ የሠራልኝ ታዲያ፣ እሱን የማመሰግንበት ሌላ ምክንያት ሲጨምርልኝ
አይደለም? እንግዲያዉስ እግዚአብሔርን አመስግኜዉ አልጠግብም። ወደ የትም ቢሆን ጉዞዬ፣ ያለ መንገዳቸዉም ቢሆን ሰዎች እንዲከተሉኝ
የሚያስገድድ ዉበት አድሎኛል። አያልቅበት እግዜር!
አንዱ እንዲያዉም ምን ነበር ያለኝ? አንቺ አክሱም ማርያም ከደጀ ሰላሙ ቁጭ ብለሽ ያንጎራጎርሽ ጊዜ፣ እኔ ከባሮ ወንዝ ዳር ፀሐይ እየሞቅሁ ሰምቼሻለሁ” ብሎኝ እርፍ! እሱም ብቻ ሳይሆን የጸጉርሽ፣ጥርስሽ፣ ጉንጭሽ፣ ድምፅሽ፣ ምናምንሽ እየተባልሁ መደነቁን ትንፋሽ የመሳቡን ያህል ለምጄዋለሁ። ጉራ እንዳይመስልብኝ፣ ደግሞስ ስንቱን
እናገረዋለሁ ብዬ እንጂማ የአቆላማጩ ብዛት፣ የወዳጄ እና የዟሪዬ ብዛት ዓለም ሁሉ የእኔ ግዛት እስከምትመስለኝ ድረስ ስፍር ቁጥር የለውም።
ክራሬን ይዤ ወጣ ያልሁ እንደሆነማ፣ ሴት ወንድ ሳይባባል አሰፍስፎ የሚከተለኝ ሰው ብዛቱ፤ አይሆንም እንጂ እንደ ኮከብ ቢሰፈር ሦስት ሰማይ እንኳን መብቃቱን እንጃለት። እንዲህ እንደ ንግሥት በአጀብ ወጥቼ ከመልከኛዋ የአመሻሽ ፀሐይ ፊት ለፊት እቀመጥና፣ እንዲህ ብዬ
እጀምራለሁ።

ጀንበር በግዜርሽ አብረን እንደር፣
ፀሐይ እንደ ሳቅሽ አብረን እንኑር
ቀን እያጠረኝ ሌት ከምቸገር።
👍334🔥1
ከዚያ በኋላማ ምኑ ይነገራል? ውዳሴ እንደ ዶፍ ይዘንብልኛል። ታዲያ ያሉትን ቢሉ፣ እኔ ማንንም ውሸታም ብዬ አላውቅም። ማንንም አልቃወምም፡፡ ባሪያዎችሽ ነን ሲሉኝ እንኳን፤ ሆነ ብዬ መሬት መሬቱን ከማየት በቀር፣ ናችሁም አይደላችሁም ብዬ አላውቅም። አልችልበትም።
የማልችለው ግን ሙቀቱ ስለሚመቸኝ ሳይሆን፣ ሥራዬ እንዲህ ያለ ሲሳይ እንድፈጥር እና ያለኝን ዕድል ሁሉ አሟጥጬ እንድጠቀምበት የግድ ስለሚለኝ ብቻ ነው። ምክንያቱም እኔ የታላቁ ማኅበር መረጃ ማዕከል የሆነው፣ የሲራክ ፯ አባል ስለሆንሁ። በታላቁ ማኅበራችንም ሆነ
በማዕከላችን በሲራክ ፯ ሕግ ደግሞ ዕድልን እንደ ማባከን ያለ ወንጀል የለም።

ኹለቱ ሴቶች ሆነ ብለው እንዲህ ከመንገዴ ቆመው በኩራት
የሚከራከሩት፣ በዚህኛው ጎኔ አውቀውኝ መሆኑን ጠርጥሪያለሁ። ስለ
እኔም ሆነ ስለ ሲራክ፤ የጠረጠሩት ነገር ቢኖር ይሆናል እንጂ፣ ካልጠፋ ቦታ እናቴ በተመላላሽነት ከምታገለግልበት ገዳም አጠገብ መጥተው ነገር
መፈለጉን ምን ይሉታል? ያውም የእኔን መውጫ ጠብቀው፣ ያውም ያለ ሐፍረት በስሜት፣ በዚያ ላይ ስለኔ እህትነት የሚሟገቱት እነሱ
ለወንድሜ ምኑ ቢሆኑ ነው? በእርግጥ ይኼ ስሙን የሚጠሩት ወንድሜ ራሱ የድሮ ፍቅሩ ቀዝቅዞብኛል። በጣም፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ
መረር እያደረገ፣ ምን እህት አለኝ እኔ?› ሲል ደጋግሜ ከራሱ አፍ
ሰምቼዋለሁ። ጭራሽ አሁን አሁንማ እንዲያዉም፣ እንኳንስ ቀልጀለት የፈለገ ብኮረኩረዉ እንኳን አይስቅልኝም። እንደ ልጅነታችን መላፋት ትተናል። እንደ ወንድም (እታለሜ ብሎም አያቆላምጠኝም። የእሱ
ሳያንስ፣ ሌሎች እህት እና ወንድሞቼንም እንዲጠሉኝ ነገር ማመሰቃቀል አምጥቷል።

የሆነው ቢሆን፣ እነዚህ ልጆች ምናችን ግድ ቢላቸው ነው እንዲህ አረፋ እስኪደፍቁ ስለ እኛ የሚያወሩት?...

ይቀጥላል
👍24👎1
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_ሦስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ


....ከየቤቱ መስኮት እየተንጠላጠለ ይሳሳቃሉ፣ ወጣቶች የነገሩን ምንነት ሳያጤኑ ጥልቅ ይላሉ፡፡ «ተነስ ተንቀሳቀስ» እያሉ ጩኸት ያስተጋባሉ፡ ሩብ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፓሪስ ከተማ ላይ የሆነውን ላውጋችሁ።
በየአውራ ጎዳናው፣ በየገበያ ቦታ፣ በየመንደሩ ትንፋሽ ያጠራቸው ሰዎች፣ሠራተኞችና ተማሪዎች፣ «ተነስ፣ ተንቀሳቀስ፣ ክንድህን አንሳ» እያለ በአንድ ቋንቋ ይጮሃሉ፡፡ የመንገድ መብራት፣ መስተዋት፣ የመጓጓዣ ጋሪዎችንና
ሠረገላዎችን ይበረብራሉ፣ ድንጋይ ይወረውራሉ፣ ቤት ውስጥ እየገቡ የቤት እቃ ያንኮታከታሉ፣ ሰሌዳ ይዘው በየመንገዱ ይዞራሉ፡፡ ማን
አስተባበራቸው? ማን አነሳሳቸው? ማን ያውቃል!

የአድመኞቹ ወላፈን እንደ ጭድ እሳት ተቀጣጠለ፡፡ በሦስት ሰዓት
ጊዜ ውስጥ አንዳንድ ቁልፍ የሆኑትን ስፍራዎች ከቁጥጥራቸው ሥር አደረጉ፡፡ ከሰዓት በኋላ ወደ አሥራ አንድ ሰዓት ገደማ የፓሪስ ከተማን |
ሦስት አራተኛ የሚሆነውን ክፍል ያዘ:: ይህም ከድንጋይ ውርወራ ወደ ጦር መሣሪያ መጨበጥ አሸጋገራቸው:: አድመኞቹ የመሣሪያ መጋዘን ስለማረኩ የጦር መሣሪያ ከዚያ ዘረፉ:: በአሥራ ሁለት ሰዓት ቅልጥ ያለ ዝርፊያ
ተጀመረ።

በአንድ ፊት አድመኞቹ በሌላ አቅጣጫ የመንግሥት ወታደሮች
ሥፍራ ሥፍራቸውን ያዙ፡፡ ተኩሰ ተጧጧፈ፡፡ ለወሬ ሞትኩ ያለ፣
ወደፊት በሚሆነው እጠቀማለሁ ብሎ ያለመ፤ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ
ጭምር ሁኔታውን ለማየት እየተሽሎከሎከ ወደ ጦር ሜዳው አመሩ፡፡እንደ እነቪክተር ህዩጎ ያለ አልጠግብ ባይ ከእሳተ ገሞራ ውስጥ ገብቶ መውጫ በማጣት ተቅበዘበዘ፡፡ ከጦርነቱ፡ መካከል በመግባታቸው ጥግ ይዘው
አውጣን» ከማለት በስተቀር ሌላ ምርጫ አልነበራቸውም፡፡ ቅልጥ ያለ ጥይት እሩምታ ግማሽ ሰዓት ወሰደ:: የጦሩ ክፍል በያለበት መሯሯጥ፣መንቀሳቀስ ሆነ፡፡ ከጦር ሜዳው በብዛት የጦር ኃይል ጎረፈ:: ውጊያው ፓሪስ ከተማ ውስጥ ነበር፡፡

የጦር ኃይሉ እንዳላ መንቀሳቀሱን የተመለከተ ሕዝብ ወደኋላ መሸሽ
ጀመረ፡፡ በየአቅጣጫው ተንሰራፍቶ የነበረው ሰልፈኛ እንደመበተን አለ::ትርምስምሱ ወጣ:: አንዳንዱማ ፈሪ በሩጫ እግሬ አውጪኝ አለ፡፡

ዝናብ በሀይል ይጥላል:: ከዚህ ትርምስ ውስጥ አንድ ልጅ ውራጅ
እቃ ከሚሽጥበት ሱቅ አካባቢ ብቅ አለ፡፡ አንዲት አሮጊት ሽጉጥ ይዘው መቀመጣቸውን ስለተመለከተ ልጁ ወደ ሴትዮዋ ሮጠ
«እማማ፣ አንድ ጊዜ ሽጉጥዎን ያውሱኛል?» ሲል ጠየቃቸው:::

ሽጉጡን ለማግኘት ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ወዲያው መሣሪያውን ከእጁ አስገብቶ ወደ መጣበት ተመልሶ ሮጠ፡፡

ልጁ ከአሁን ቀደም ያነሳነው ሚስተር ቴናድዩ ከእስር ቤት እንዲያመልጥ የረዳውና ጋቭሮች የሚባለው ነበር፡፡ መንገድ ከጀመረ በኋላ ነበር ሽጉጡ
ጥይት እንደሌለው የተገነዘበው:: ቢሆንም መንገዱን ቀጠለ፡፡

እነ ኩርፌይራክና ኤንጆልሪስ ከቁጥጥራቸው ስር ካደረጉት ሰፈር ደረሰ:: ከሌላ አቅጣጫ ሌሎች በድኖች የሚመሩት የአድመኞች ቡድን መጥቶ ሲደባለቅ ተመለከተ፡፡ ጋቭሮችም አብሮ ከሰልፈኞቹ ጋር ተደባለቀ::

««ወዴት ነው የምንሄደው?» ሲል ጠየቀ::

‹‹ተከተለን» ሲል ኩርፌይራክ መለሰለት::

የረብሻው ቀንደኛ መሪዎች ከአፍ እስከ ገደፍ ታጥቀዋል:: ከኋላ
የተከተላቸው ጀሌ አንዳንዱ የጦር መሣሪያ ሲይዝ አንዳንዱ ዱላ ብቻ ነው የያዘውን ፡፡ ከሠራዊቱ መካከል አንድ በእድሜ የገፉ ሽማግሌዎም ነበሩ::
ሽማግሌው ምንም ዓይነት የጦር መሣሪያ አልያዘም:: ግን በጣም እየተቻኮለ ነበር የሚሄዱት፡፡ ፊታቸውን ሲያዩት ከአሳብ ባህር የሰመጠ ይመስላል፡፡

ጋቭሮች ከሩቁ አያቸው::
«ያ ማነው?» ሲል ኩርፌይራክን ጠየቀው::
«አንድ ሽማግሌ ነዋ!» ሲል መለሰለት::
ከአሁን ቀደም ያየናቸው መሴይ ማብዩፍ ነበሩ::
ሽማግሌው ፊት ለፊት ከሚሄደው መስመር ሊደርሱ ምንም ያህል
አልቀራቸውም::

«ምን ዓይነት ቆራጥ ሽማግሌ ናቸው!» ሲሉ ተማሪዎቹ አጉረመረሙ። ማን እንደሆኑ ለማወቅ ተማሪዎቹ ጊዜ አልወሰደባቸውም ገዳም ውስጥ
ይኖሩ እንደነበር የሚያውቋቸው ሰዎች በሹክሹክታ ስማቸውን አስተጋቡ ሠራዊቱ አንዱን ጎዳና ጨርሶ ወደ ሌላው ተሸጋገረ፡፡ ጋቭሮችም መጓዙን ቀጠለ።

ብዙ በተጓዘ ቁጥር የሠራዊቱ ቁጥር እየጨመረ ሄደ፡፡ አንድ ግዙፍ ሰውነት ያለው ረጅም ሰው መጥቶ ተደባለቀ፡፡ ሽበት ጣል ጣል አድርጎበታል ፡መሪዎቹ ይህ ሰው ማን እንደሆነ አላወቁትም፡፡ ግን ወደ እነርሱ ለመጠጋት
በጣም ይፈልጋል፡፡ ጋቭሮች በሚያዜመው መዝሙር ተመስጦ ስለነበረ ሰውዬውን ልብ አላለውም፡፡ ልጁ መዝሙር ሲሰለቸው ያፏጫል፤ አንዳንዴ
ያንን ጥይት የሌለውን ሽጉጡን ያሻሻል፡፡

ሰልፈኛው መንገዱን ቀጥሎ እንደአጋጣሚ ሆኖ በኩርፌይራክ መኖሪያ ቤት ደጃፍ ያልፋል፡፡

«ጥሩ አጋጣሚ ነው» ይላል ኩርፌይራክ፡፡ «ቆቤ ጠፍቷል፤ ጠዋት ደግሞ ቦርሳዬን ረስቼ ነው የመጣሁት፡፡»

ከሰልፈኛው ተገንጥሎ ደረጃዎቹን በእጥፍ እየዘለለ ወደ ቤቱ ገባ
አንድ አሮጌ ቆብና የኪስ ቦርሳውን አነሳ፡፡ ከቆሻሻ ልብስ ውስጥ
የነበረ ሌላ አነስተኛ የእጅ ቦርሳም ወሰደ:: ደረጃውን በችኮላ ሲወርድ በጨለማ ውስጥ አንድ ሰው «ሊያነጋግርህ የሚፈልግ ሰው አለ» ሲል ነገረው፡፡

በዚህ ጊዜ አንድ የተቦጫጨቀ የሴት ቀሚስ ከላይ ያጠለቀ ወንድ
ከወደ ውስጥ ብቅ ብሎ አነጋገረው:: ድምፁ የሴት እንጂ የወንድ አይመስልም:: በጣም ቀጭን ነው::

«ማሪየስን አይተውታል?»
«የለም፤ ከቤት አልመጣም::»
«ማታ ይመጣ ይሆን?»
«እኔ እንጃ፡፡ እኔ ግን ዛሬ ወደቤት አልመለስም::»
አለባበሱና ድምፁ ሴት ያስመስለው ወጣት ኩርፌይራክን አፍጥጦ አየው
ለምን አይመለሱም?» ሲል በድፍረት ጠየቀው::
«ምክንያቱም...»
«እንግዲያው አንተ ወዴት ነው የምትሄደው?» በማለት ጣልቃ ገባ፡፡
«ምን ያደርግልሃል?»
«ቦርሳህን ልያዝልህ?»
«ወደ ጦርነቱ ቦታ ነው የምሄደው?»
«አብሬህ ብሄድ ትፈቅድልኛለህ?»
«ከፈለግህ፣ እኔ ምን ቸገረኝ» ሲል ኩርፌይራክ መለሰለት:: «መንገዱ
ነጻ፣ ጎዳናው የጋራ!»

ኩርፌይራክ ይህን እንደተናገረ ከጓደኞቹ ለመድረስ በሩጫ ወጣ፡፡
እንደደረሰም የእጅ ቦርሳውን እንዲይዝለት ለአንዱ ጓደኛው ሰጠው:: ከሩብ ሰዓት ጉዞ በኋላ መለስ ቢል ወጣቱ እንደተከተለው ተገነዘበ፡፡
ለአመዕ የተነሳሳ ሰልፈኛ ብዙውን ጊዜ የሚመራው በነፋስ ስለሆነ
አንዳንዴ ወደፈለገበት ሳይሆን ወደ አልፈለገበት አቅጣጫ ነው የሚጓዘው::ይህም በመሆኑ ይህ ሰልፈኛ ሴንትሜሪ ከተባለ ሥፍራ ለመሄድ ፈልጎ ሳይታወቀው ይህን ቦታ አልፎ ከሴንት ዴኒስ ይደርሳል፡፡

ከሰላሳ ዓመታት በፊት አንድ መንገደኛ ሴንት ዴኒስ ከተባለ ሥፍራ ቢያልፍ መንገዱ እየጠበበ ሄዶ በመጨረሻ እንደ አቁማዳ ጫፍ መደፈኑን ይገነዘብ ነበር፡፡ አካባቢውን አጥርቶ የማያውቅ ከሆነማ በግራና በቀኝ በኩል
የጨለማ መንገድ መኖሩን ስለማይረዳ መድረሻ ያጣል:: ውስጥ አዋቂ ግን በእነዚህ ጠባብ የጨለማ መንገዶች ተሹለክልኮ ሊያልፍ ይችላል፡፡ በስተቀኝ
በኩል ያለውን የቀኝ መንገድ ይዞ ሲጓዝ ከአንድ መሸታና ምግብ ቤት
👍14😁21
ይደርሳል፡፡ ቤቱ ቢያንስ የሦስት መቶ ዓመት እድሜ አያጣም፡፡
ቤቱ ባለ ሦስት ፎቅ ቤት ሲሆን የእንግዳ መቀበያውና የቤልያርዶ
መጫወቻ ክፍሎች ከምድር ቤት ናቸው:: ወደፎቅ የመውጫ ደረጃው ጠመዝማዛ ነው:: ደረጃው ከእንጨት የተሠራ በመሆኑ በላዩ ላይ ሲራመዱ
በኃይል ይንጫጫል:: ፎቅ ላይ ያለው ሰፊ ክፍል የወይን ጠጅ መጠጫ ክፍል ነው፡፡ አንድ ሰው ከክፍሉ ቢገባ ጠረጴዛ ላይ በብዛት የወይን ጠጅ
ጠርሙሶች ተደርድረው፣ ግድግዳውና ጣራው በጭስ ታፍኖ፤ ሻማዎች በየመቅረዙ ሲነዱ ይመለከታል፡፡ ከምድር ቤቱ፡ ስር ሌላ የጨለማ ቤት አለ፡፡ ከሁለተኛ ፎቅ በላይ ያሉት ክፍሎች የባለቤቶቹ መኖሪያ ናቸው::

ከመጠጥ ቤቱ ውስጥ ተቀምጠው የወይን ወጅ ይጠጡ የነበሩ ሦስት ሰዎች ተሳክረዋል:: ከሰዓት በኋላ ወደ ስምንት ሰዓት
ጥምብርብራቸው ወጥቷል:: በክርናቸው የተደገፉት ጠረጴዛ በባዶ ጠርሙስ ተሞልቷል፡፡ ከሶስቱ አንደኛው ጠጪ በጣም ደስ ብሎት መንፈሱ በኃይል
ተነቃቅቶአል፡፡ ከረባቱን አላልቶና ግራ ክርኑን ከጠረጴዛው ላይ አንስቶ ቀጥ ብሎ ለመቀመጥ ይሞክራል፡፡ በቀኝ እጁ ብርጭቆውን ወደ ላይ አንስቶ
በአካባቢው ትገኝ የነበረችውን ቂጣም አሳላፊን እያየ «የቤተ መንግሥቱ በሮች ይከፈቱ፤ ሁሉም ሰው ከዚያ ገብቶ ይንፈላሰስ፣ ሁሉም ማዳም ኸሽሉፕን የማቀፍ መብት ይኑረው ፤ ለማንኛውም እንጠጣ» ሲል ይናገራል::
ማዳም ኸሽሉፕ የመጠጥ ቤቱ ባለቤት ናቸው::

ፊቱን ዞር ቢያደርግ ማዳም ዝሽሉፕ ከዚያ ቁጭ ብለዋል፡፡ ንግግሩን ቀጠለ ።

«አንቺ በአገልግሎት ብዛት ወደ ክቡር እቃነት የተለወጥሽ ሴት
እስቲ ወደ እኔ ጠጋ በይና ዓይን ዓይንሽን ልይ! »

አጠገቡ የተቀመጠ ጓደኛው እየተኮላተፈ ይናገራል::

በእ..ትሽ ሌላ አቲ ቂድለት..የምና....ገር….አውቅም:: ገንዘብ ሳጨ...ስ አቀቅም

ሦስተኛው ጠጪ ቢሰክርም እስከዚህም ሕሊናውን ስላልሳተ ከመናገር ተቆጠበ:: የተቀመጠው ከተከፈተ መስኮት አጠገብ በመሆን በመስኮት የሚገባው ውሽንፍር ጀርባውን አርሶታል:: ሁለቱን ጓደኞቹን እያፈጠጠ ያያል

በድንገት ከሥሩ ታላቅ እሩምታና ጫጫታ እንዲሁም የብዙ ሰው
ኮቴ ይሰማል፡፡ «ተነሱ፣ እጃችሁን አንሱ» የሚል ጩኸትም ያዳምጣል። ፡አንገቱን በመስኮቱ በኩል ወጣ አድርጎ ሲያይ ከሴንት ዴኒስ ጎዳና ላይ ኡንጀልራስ የካርባይን ጠመንጃ፣ ጋቭሮች ሽጉጥ፣ ኩርፈይሪክ ጉራዴ
ፕሩቬይር፣ ኮምቦፌሬና ባሆራል ቀስት ይዞ፤ ስፍር ቁጥር የሌለው
ሕዝብ ደግሞ ግማሹ መሣሪያ ሌላው ድንጋይና ዱላ ይዞ ሲከተላቸው ይመለከታል፡፡

ይኸው መስኮት አጠገብ የተቀመጠው ጠጪ
ኩርፌይራክ ሰማህ» እያለ ይጣራል፡፡

ከርፌይሪክ ጥሪውን ስለሰማ ከሰልፈኛው ገንጠል ብሎ ጥሪው ወደ ቤቱ አቅጣጫ ጥቂት በመራመድ ምን ይፈልጋሉ?» ሲል ያጠይቀዋል፡፡

«ወዴት ነው የምትሄዱት? »

«ምሽግ ለመሥራት» ሲል ኩርፈይራክ መለሰለት::
ታዲያ እዚህ መመሸግ ነዋ! እዚህ የተሻለ ቦታ የት አለ? እዚሁ
ዳርጉት አይሻልም!»
እውነትክን ነው» ሲል ኩርፌያራክ መለሰ::
ኩርፌይራክ ምልክት ስለሰጣቸው ሰልፈኛው ወደ ቤቱ ፊቱን አዞረ::

💫ይቀጥላል💫
👍171
#ገረገራ


#ክፍል_ሁለት


#በታደለ_አያሌው

..ማን ቢሆኑ ነዉ? ምን አገባቸዉ?
ዞር ብዬ በቁጣ ላጠናግራቸዉ አሰብሁና፣ መልሼ ተዉሁት፡፡
ካለኝ ልምድ ግን ማንነታቸዉን መገመት እችላላሁ፤ የጠላት ወገን ጆሮ ጠቢዎች ናቸው። ቢሆንም ግን ዓላማቸው አልገለጥልሽ ብሎኛል። ይኼን ጉዳይ እንዲሁ እያውጠነጠንሁ፣ እመዋ የላከችኝንም ከቤቷ አድረሼላት
ታላቁን ቤተ መንግሥት አለፍሁት። ከዚያም በታላቁ የማኅበራችን ሕንጻ ምድር ቤት በሚገኘው መኪና ማቆሚያ ደርሼ መኪናዬን አቆምሁና፣ ሰዓቴን ስመለከት መንገዱ ስድስት ደቂቃዎች ብቻ ፈጅቶብኛል። ሰባት
ኪሎ ሜትር፣ ያውም እናቴ የላከችኝን ጭምር ወደ ቤት አድርሼ፣ ያዉም በአዲስ አበባ መንገድ በስድስት ደቂቃ ብቻ? (እንኳንም እመዋ አላየችኝ
ብዬ አማትቤ፣ የቀረችኝን አንድ ደቂቃ አብቃቅቼ ወደ ዋናዉ የሲራክ፤ ማዕከል ለመግባት ተጣደፍሁ፡፡

ወደ ዐሥራ ስምንተኛው ፎቅ የሚያደርሰኝ አሳንሰር ውስጥ ጥልቅ አልሁ። አሁን ወደ ላይኛው የመጨረሻ ወለል እያቀናሁ ቢሆንም፣ የሲራክ ፯ ዋና ማዕከል የሚገኘው ግን በተቃራኒዉ ከምድር ቤቱ የመኪና
ማቆሚያም በታች ተሠውሮ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ፣ በቤተ ክርስቲያን ፊት በይፋ የሚታውቁለት የማኅበሩ ብዙ አገልግሎቶች የሚከናወኑት በዚሁ ሕንጻ ሲሆን፣ በምድር ቤት ካለው ሰፊ የመኪና ማቆሚያ እስከ ላይኛው የመጨረሻ ወለል ድረስ የሚገኙ ቢሮዎች ሁሉ፣
ለእነዚሁ አገልግሎቶች በግላጭ የተደለደሉ ናቸው። ለምሳሌ ‹ጥናትና ምርምር የሚባለው አንድ ማዕከል ብቻውን ኹለት ሙሉ ወለሎች ይዟል። ሌሎቹም እንደዚሁ። እያንዳንዷ ቢሮ ደግሞ የራሷ ስም እና ቁጥር ተሰጥቷታል፡፡

የሲራክ፮ን ህልውና ይቅርና፣ ከነጭራሹ ከሕንጻው ምድር በታች ሌሎች ወለሎች እንዳሉ የሚያውቁት እጅግ ጥቂት የራሱ የሲራክ ማዕከል አባላት እና ዋና ዋናዎቹ የማኅበሩ አመራሮች ብቻ ናቸዉ፡፡ ቀድሞ ነገር ለሕንጻዉ ንድፍ ያወጡለትም ሆነ ያሳነጹት በራሳቸዉ በአመራሮቹ
በጥብቅ ምስጢር የተመረጡ ባለሙያዎች ስለሆነ፣ ከእነሱ በቀር የሚያዉቀዉ የለም። እኔም የዚህን ጠመዝማዛ የምድር ቤት መግቢያ ዘልቀው እንዲገቡበትም ሆነ እንዲወጡበት ፈቃድ ካላቸው ጥቂቶች መካከል አንዷ በመሆኔ፣ ከምንም የሚበልጥ ዕድለኛነት መሆኑን አምናለሁ። በመሆኑም የዚህ ማዕከል ኃላፊ የሆነዉ ባልቻ፣ በአስቸኳይ እንድደርስ ወደ ጠራኝ ኮቴ አልባው የሲራክ፤ ማዕከል ለመግባት ወደ
ላይኛው ወለል ደርሼ ከአሳንሠሩ ወርጃለሁ። ከአሳንሠሩ ፊት ለፊት ትንሽ ከተራመድሁ በኋላ ወደ ግራ እጥፍ አልሁ። አሁንም ትንሽ እንደ ሄድሁ ከላይ “ ፲፰፻፴ ከታች ደግሞ “ምክረ ካህን” የሚል ቃል እንደ ነገሩ የተጻፈበት ክፍል ከፍቼ ገባሁ። ቢሮዋ መጻሕፍት በመደርደሪያዎች የታጨቁባት ክፍል ስትሆን፣ ሰዉስጥ በኩል ከበሯ አጠገብ ሁልጊዜም
ካባ የደረቡ አንድ ሽማግሌ ለይስሙላ ይቀመጡባታል። ምናልባትም ግራ የገባዉ ወይም ጥርጣሬ ያደረበት ባይተዋር ሰዉ ወደ ክፍሉ ሲያንኳኳ፣
በማያስጠረጥር ትሕትናቸዉ ከርፈድ ያደርጉና እንደሚሆን እንደሚሆን ሸንግለዉ የሚመልሱት እኒህ በሩ አጠገብ የሚቀመጡት ካህን መሳይ ባለ
ካባ ስዉዬ ናቸዉ፡፡

እጀታዉን በመያዜ ብቻ እኔ መሆኔን በአሻራዬ አውቆ የተከፈተልኝ የዚች ክፍል በር ልክ ወደ ውስጥ እንደ ዘለቅሁ በራሱ ተቆለፈ። በመቀጠል
ወደ ምዕራቡ ግድግዳ ተራመድሁና በመጻሕፍት መካከል እጄን ሰድጄ ግድግዳውን እንደ አዛኝ እናት ስደባብሰው፣ በነጭ ቀለም የደመቀዉ ልሙጥ ግድግዳ ስንጥቅ እየፈጠረ፣ እየሰረገ ሄደልኝ፡፡ ጨርሶ ጥልም ካለ በኋላ ወደ ጎን ተንሸራቶ ጠባብ በራፍ ወጣለት።

አቤት ለመጀመሪያ ጊዜ እዚህ የደረስሁ ጊዜ የተደነቅሁት፤
ወደ ዉስጠኛዉ ክፍል እንደ ዘለቅሁ፣ ይኸኛዉም በር እንደገና ወደ መጽሐፍ መደርደሪያነት ከተመለሰ በኋላ፣ ልክ እንደ መጀመሪያው ሁሉ በራሱ ተቆለፈ። ወደ ነበረበት ተመልሶ ከግድግዳዉ ጋር ለመመሳሰል
ቅጽበትም አልፈጀበት፡፡ ከዚያም ጠበብ ባለችዋ ኮሪደር ትንሽ እንደ
ተራመድሁ፣ በጨረር የታጠረ በር ላይ ደረስሁ። ዝግንትሉ የወጣ ቀይ ክር የሚመስል ኤሌክትሮናዊ ጨረር ከላይ እስከ ታች ተመሳቅሎበታል። ጨረሩ ካልጠፋ በቀር፣ በጭራሽ ማለፍ አይሞከርም። በፍጹም፡፡ ያለበዚያ
ጨረሩን ሊጥሰዉ የሞከረዉን ሁሉ አንጨርጭሮ ሕቅ የማድረግ ጭካኔ አለበት። ከፊት ለፊት ያለዉ ካሜራ ሲያየኝ ስለነበር፣ ለቅጽበት ያህል እንኳን ሳያስጠብቀኝ ጨረሩ ድርግም ብሎ ከሰመልኝ፡፡ ካሜራ መኖሩን ያወቅሁት የኋላ ኋላ ስለመኖሩ ከተነገረኝ በኋላ ነዉ እንጂ፣ በትክክል የት እንዳለ እንኳን ያኔ፣ አሁንም ድረስ አይታየኝም። ብቻ ይኼ እሱ
የሚያየኝ፣ እኔ ግን የማላየዉ ካሜራ አዉቆኝ ጨረሩን አከሰመልኝ፡፡ ከዚያም ወደ ቀኝ ታጥፌ ትንሽ እንደ ተራመድሁ፣ ባለ ኹለት ተከፋች በር አጠገብ ደረስሁ። እሱም ገና ስጠጋው ወለል ብሎ ተከፈተልኝ።
ይህንንም አልፌ አልደረስሁም ገና። ገና ወደ ታች የሚወስደኝ ሥሩ የዉስጥ ለዉስጥ አሳንሰር ይጠብቀኛል። ልክ ወደ አሳንሠሩ እንደ ገባሁ ወደ ታች ይዞኝ ተፈተለከ።

ከመኪናዬ ወርጄ፣ ከዚያ ደግሞ ያንን ሁሉ ተጠንቅቄ፣ እዚህ በምድር ቤት ከሚገኘው የሲራክ ፯ ማዕከል ለመድረስ ኹለት ደቂቃዎች ብቻ ፈጀብኝ።

ልክ እኔ እንደሆንሁት ሁሉ፣ ዕድል ብሎለት ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕከሉን የሚጎበኝ ሰው መደንገጡ አይቀርም። ምክንያቱም መግቢያው
የመንግሥተ ሰማያት፣ ውስጡ ደግሞ ከገጠር ዳስ የማይሻል አዳራሽ ይመስልበታል። የሚከናወንበትን ተአምር እስከሚያውቅ ድረስ የታላቁ
ማኅበር መረጃ ማዕከል፣ ሲራክ፤ ይቺ ናት በቃ?› ብሎ ቢያናንቅ
አልፈርድበትም፡፡ ከፊት ለፊት ከጠፍር አልጋ በማይለዩ መጠነኛ ወንበሮች ላይ ተቀምጠዉ በየኮምፒዉተሮቻቸዉ ላይ ያፈጠጡ ጥቂት ሰዎች
ይታያሉ። ግድግዳዉ ዙሪያዉን ከወገቡ በላይ ዝርግ መከሰቻ ኖሮት ከተለያዩ ሥፍራዎች በሥዉር በተጠመዱ ካሜራዎች የሚቀርጹትን ተንቀሳቃሽ ምስል ሁሉ በመቃን በመቃን ከፋፍሎ ከስቶታል። ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢዉን፣ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ውስጠ ገጹን፣ ብሔራዊ ቤተ መዘክር ውስጡን፣ የአክሱም ጽዮንን ቅጽረ ግቢ፣ የሌሎች ታላላቅ ገዳማትን እቃ ቤቶች፣ የማኅበሩ ጥቂት ቅርንጫፎች ዙሪያ ገባቸዉን
ያለብዥታ ያስመለክታሉ። በነዚህ ሁሉ ማን እንደሚወጣና ማን
እንደሚገባ ያለማቆራረጥ ኩልል አድርገው ያሳያሉ፡፡ ምንም እንኳን ሌላ መጠባበቂያ የመረጃ ማዕከል በሌላ ቦታ እንደሚኖረዉ ብገምትም፣አብዛኛው ከወኪሎች የተሰበሰበው መረጃ ሁሉ የሚተነተነው እና ትርጉም
የሚሰጠው ግን በዚችኛዋ ክፍል ነው፡፡ በውስጧ የተለያዩ ሚናዎች
የተሰጣቸው ሃያ ሦስት የማዕከሉ አባላት በለም አእምሯቸው ቁጭ ብድግ ይሉበታል። ወጣቶች ቢበዙበትም ጥቂት ጎልማሳዎች እና በዕድሜ ጠና ያሉ ሴቶችም አሉበት፡፡

ዕረፍት በቤቱ እምበዛም አትታወቅም፡፡

ሁልጊዜም ወደዚህ ክፍል ስገባ የሚሰማኝ ስሜት አሁንም ተሰማኝ። ወኔዬ ሞቀ። ኩራት ኩራት፣ ደስ ደስ አለኝ፡፡ ልቡናዬ እንደ መሙላት፣ ነፍሴ እንደ መርካት፣ ዓይኔ እንደ መብራት አለልኝ፡፡ በሐቅ ቤት እንዳለሁ
ተሰማኝ፡፡ ከቅኑዓን ጋር እንደ ሆንሁ ታወቀኝ፡፡ ከበጎዎች ወገን መሆኔ መጣብኝ። ሁሉም በየሥራው ተጠምዶ ልብ ያለኝ ባይኖርም፣ ጎንበስ ቀና
ብዬ ለሁሉም የፍቅር ሰላምታ እያቀረብሁ የማዕከላችን የሲራክ፤ ዋና ኃላፊ የሆነዉ ባልቻ ወደሚገኝበት ቀጣይ ክፍል ተራመድሁ።

“ልጅየዋ?” ሲል ተቀበለኝ፣
👍331
በማይጠገብ ፈገግታው፡፡ ባልቻ፡፡
“አባትዮው” አልሁት፣ እየተፍለቀለቅሁ፡፡ ጥምጥም ብዬ አቀፍሁት። ከትናንት ጀምረን ስላልተያየን ንፍቅ ብሎኝ ነበር። እኔና ባልቻ እንዲህ ነን። ለአንድ ቀን ቀርቶ ለሰዓታት ካልተያየን የምንሆነው አያድርስ ያስብላል፡፡ እወደዋለሁ፡፡ እሱም ይወደኛል፡፡ መካሪ ሁሉ «ኧረ እናንተ
ሰዎች ይኼ ነገራችሁ ልክ ይኑረው ሲለን፣ እኛ ግን ጭራሽ ብሶብናል።
እሱ እንዲያውም፣ ምን አገባችሁ ብሎ ያሳፍርልኛል። እንዲህ ስንሆን
እያየን፡ እኔና ባልቻ የተገናኘነው በዚሁ በማኅበራችን አገልግሎት ነው ብንለው ማንም አያምነንም። እንኳንስ ሌላው እኔ ራሴ አላምንም።የእዉነትም አባትና ልጅ የሆንን፣ ከመፈጠራችን በፊት ጭምር የምንተዋወቅ ያህል ነዉ አኳኋናችን።ሁለመናዉ ደስ ይለኛል። መቼም እግዜር አያልቅበትምና፣ ለሰዉ
የሚያስፈልጉ ጸጋዎችን ሁሉ፣ እየዛቀ ነዉ የሰጠዉ። እሱ ሲናገር
እንኳንስ ጆሮዉ፣ ልቡ ሁሉ የማያዳምጥ የለም፡፡ የጻፈም እንደሆነ ሁሉን ማነጋገሩ፣ የተከራከረም እንደሆነ ማሸነፉ ይሆንለታል፡፡ ያዉ ዐመል
ሆኖብኝ፣ የሆነዉንም ያልሆነዉንም ጥያቄ በጠየቅሁት ጊዜ፣ አብዛኛዉን መልሱን የሚጨርስልኝ የተናገርሁትን ልቅም አድርጎ በማዳመጥ ብቻ
ነዉ። በማዳመጡ ብቻ ከስንት ከፍና ዝቅ እንደ ፈወሰኝ፣ እኔ ነኝ
የማዉቅለት። ጆሮዉ ልዩ ነዉ። ትዕግሥቱ ልዩ ነዉ፡፡ በቀላሉ ከሰው ጋር ለመቀላቀል ባይቸግረውም፣ ይሁነኝ ብሎ ዳተኛ ነው። ብዙውን ጊዜ
ብቸኝነት ይመርጣል። አርምሞ ያዘወትራል። ብቸኛ ይሁንም እንጂ
ለሰው ደስታ ሲል የማይሆነው የለም፡፡ የሰዉ ፍጹም የለም ሲሉ፣ ‹ኧረ አለ ብዬ መከራከር የጀመርሁት፤ ባልቻን ምሳሌ በማድረግ ነዉ።

“እኔ ምለው...” አለኝ፣ ያበዛሁበትን ዓይን ለመመከት በሚመስል
ድምፅ፡፡

“አቤት አባቴ”

“ኤሊ እየጋለብሽ ነዉ አይደል የመጣሽው?”

“ዘገየሁ እንዴ?”

“ብቻ? ትቀጫለሽ!”

“ምሕረት ብለምንህስ?”

“ደህና! ልመናሽን በክራር ካደረግሽው ባይሆን፣ የዛሬን አልፍሽ እንደሆነ... መቼስ ጨክኜ አልጨክንብሽ”

“ጉዳዩ አስቸኳይ ነው አላልከኝም ወይ?”

“አስቸኳይስ አስቸኳይ ነው አረ”

“እና ታዲያ! እኔና አንተ እንዲህ ስንለማመን” አልሁት፣ በቅንድቤ
እየጠቀስሁት፡፡ ክራር ግረፊልኝ ማለቱን ለማረሳሳት ሳይሆን፣ በእርግጥም ለአስቸኳይ ተልእኮ ተፈልጌ ከሆነ ጊዜ እንዳያልፍ በማሰብ፡፡

“እሱስ ልክ ነሽ”

“ለመሆኑ በደህና ነዉ የተፈለግሁት?”

“እ። ሊቀ መንበሩ አንድ ስብሰባ ጠርተውናል”

የቱ ሊቀ መንበር?”

“አንቺ ደግሞ ... ሌላ ሊቀ መንበር አለሽ እንዴ ከማኅበራችን ሌላ?»
አለኝ፣ ወደ ሲራክ፤ ማዕከላዊ የመግለጫ ክፍል እንድከተለዉ እያመራ።

“ያለ ደረጃዬ፣ በሊቀ መንበር ደረጃ ለስብሰባ መጋበዜ አይገርምም?
አንተም እኮ አንተ ሆነህ ነዉ እንጂ፣ በተዋረድ ቢሆንማ እንኳንስ እንዲህ አፍ ለአፍ ልገጥምህ ይቅርና ሰላምታህን በሩቁ ማግኘትስ ብርቅ እና
ድንቅ አይደል! ያንተ ሳያንስ ጭራሽ ከታላቁ ማኅበር ሊቀ መንበር ጋር ስብሰባ?”

እንደ ተደነቅሁ ተከትየው ስሄድ፣ የሲራክ ፯ ምክትል ኃላፊም ቀድሞን ገብቶ ኖሮ በቦታው ተሰይሞበታል። በእጅ ተጨባብጠን ሰላምታ በአጭሩ
ከተለዋወጥን በኋላ፣ ባልቻ ጉሮሮውን እየጠራረገ የግድግዳውን ዝርግ
መከሰቻ (flat screen) ነካክቶ አበራልን፡፡

“ደህና፤ ምን መሰላችሁ? ለየራሳችሁ እንደ ነገርኋችሁ፣ አራት ሰዓት ላይ ሊቀ መንበራችን አንድ ጉዳይ ላይ አብረን እንድንመክር ጠርተውናል”
አለ ባልቻ፣ የእጅ ሰዓቱን እየተመለከተ። “እሳቸው ዘንድ ከመሄዳችን በፊት አንድ ዐሥራ አምስት ደቂቃዎች ይኖሩናል። ስለ ጉዳዩ እውቂያ እንዲኖራችሁ እና አስቀድመን መወያየት ስላለብን ነው ቀድሜ እዚህ የፈለግኋችሁ” ብሎ ጀመረ፡፡

“ባልቻ እና ዉብርስት!” አሉን ሊቀ መንበሩ፣ በማስታወሻ ደብተራቸው
የሚሞነጫጭሩት ነገር ላይ እንዳፈጠጡ።

ከማኅበራችን ዋና ሊቀ መንበር ጋር የነበረንን ጠንከር ያለ ስብሰባ ጨርሰን ልንወጣ ብድግ ብድግ ማለት ጀምረናል። በስብሰባው ላይ፣ ሲራክ ፯ ከወር በፊት ባቀረበው ዝርዝር ትንተና መሠረት፣ ቤተ ክርስቲያን ልዕልናዋን እንድታጣ ሥራዬ ብለዉ የተያያዙትን አካላት ዋነኞቹ በስም ተለይተዉ ከተጠቀሱልን በኋላ፣ ስለኛ ሚና እንዲሁም ሲራክ፯ን የሚራዱ ተጨማሪ
ሁነኛ አባላትን እና ወኪሎችን ለመመልመል በሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎች ዙሪያ ተወያየን።

በሃያ ደቂቃ ዉስጥ ጨረስን።

“ቆዩ እስኪ” አሉን ሊቀ መንበሩ፣ ወደ እኔ እና ባልቻ ብቻ ጠመም
አድርገዉ ተመልክተዉ።
አብሮን የገባው የሲራክ ፯ ምክትል ኃላፊ፣ የማኅበሩ ምክትል ሊቀ መንበር እና ዋና ጸሐፊዉ ሹልክ ሹልክ እያሉ ሲወጡ እኔ፣ ባልቻ እና ሊቀ መንበሩ ብቻ ቀረን፡፡ ሊቀ መንበሩ የሚጽፉትን ነገር ፈልገውት አይመስለኝም። ሲመስለኝ ግን እኛን ቀና ብሎ ለማየት ቅፍፍ ብሏቸዋል።
ይኸኔ የባልቻ ልብ እንዴት እየመታ እንደሆነ ባላዉቅም፣ የኔስ ምነም
አይወራ።
“እሺ፤ አባትና ልጅ” አሉ ሊቀመንበሩ፣ ለደቂቃ ያህል በጭንቅ ካቆዩን በኋላ። ንግግራቸው ቁልጭ ያለ ሽሙጥ ነዉ። “በላ ጀብዶችሁን
ንገሩኝ” ሲሉ አፈጠጡብን፣ በዚያው የድምፅ ቃናቸው። ባልቻን ላየው ቀና ስል ለካስ እሱም ቀድሞ እያየኝ ኖሯል። ለዐመል ያህል ተፋጠጥን።

“ንገሩኛ!”

“ምኑን?” አለ ባልቻ፣ ቀድሞኝ።

“ጀብዱችሁን ነዋ!”

“ይቅርታ፣ ምኑን ማለትዎ እንደሆነ አልተገለጠልኝም”

“ባልቻ!” አሉ ሊቀ መንበሩ፣ በኃይል ቱግ ብለው፡፡ በዚህ አያያዛቸው በንዴት እሳት እንደ ነካዉ ቅቤ ፊታችን ላይ እንዳይቀልጡብን ሰጋሁላቸዉ። ከእኔ እኩል በመሰለኝ ግርታ ውስጥ ያለው ባልቻ፣ በላብ
ተጠምቋል። በበኩሌ ያጎደልነው ነገር ምንም ሊከሰትልኝ አልቻለም፡፡በቅድሙ ዋና ስብሰባ ላይ የነበረው የሊቀ መንበራችን ጸዳላማው ፊታቸው ከመቼው እንደ ተለወጠ እንኳን እንጃ፣ ብቻ ዝናቸዉን በሩቁም ቢሆን
አዉቀዋለሁና እንዲህ ያለ ቁጣ ሰምቼባቸው አላውቅም፡፡ ኧረ ከነጭራሹ ማንም እንዲህ የመከራ ፊቱን አሳይቶኝ አያውቅም። እስከ መጨረሻው
ብው ብለዋል። ከወንበራቸው ተነሱና ዝጉን በር ደግመው ለመዝጋት ታገሉ። በሩ አልሆን ሲላቸው ደግሞ፣ በቤተ ክህነት በኩል ያለውን መስኮታቸውን ከፍተው ለአፍታ ያህል ዉጪ ዉጪውን ተመለከቱ።
ቢሯቸው የላይኛው ወለል ላይ መሆኑ ጠቅሟቸዋል። መቼም የአዲስ አበባን ምሥራቃዊ ክፍል እንደዚህ ቢሮ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሁነኛ ቦታ የለም። ሌላ አንድ ረዥም ደቂቃ እንደዚሁ ከቆየን በኋላ፣ ዓይናቸውን
በመዳፋቸው ሞዥቀው ተቀመጡ።

“እኔ ራሴ እዚሁ አሁን የተቀመጣችሁበት ወንበር ላይ አስቀምጬ አልነበረም ወይ የጠየቅኋችሁ? ለኔ ለራሴ አልነበረም እንዲህ ያለ ነገር
አይፈጠርም ብላችሁ የተገዘታችሁልኝ?" ብለዉ ቀጠሉ፣ የእልህ ሳግ በጉሮሯቸዉ ጢም እንዳለ፡፡ እንዴት ልጁን በሌላ እጠረጠራለሁ ብለህ
ተመጻድቀህብኝ አልነበር? ምነው ባልቻ? ምነው ዉብርስት? እናንተ እኮ እንደ ተለኮሰ ሻማ ናችሁ። በዚህ ማኅበር የምናገለግል ማናችንም ማኅበርተኞች ብንሆን እንደዚያ ነን። ብዙዎች ናቸዉ በምሳሌነት ከሩቁ የሚያዩን። በተለይ አንተ፣ ባልቻ። በድርሰቶችህ አንተን የማያዉቅ ሰዉ ማን አለ? አንቺስ ዉብርስት፣ በተለይ ከወጣቱ አንቺን የማይወድ እኮ አይገኝም። ከኹለታችሁም ኋላ ብዙ ሰዉ መኖሩን ዘንግታችሁታል
ልበል? ወደምትሄዱበት ሁሉ ለመሄድ የሚከተላችሁ ብዙ ሰዉ አለ። ሌላዉ ቢቀር ለዚያ አታስቡም? በዚያ ላይ እናንተ ከተርታዉ ማኅበርተኛ በተለየ የሲራክ ፲ ድርብ ኃላፊነት አለባችሁ። ምነው ያንን ሁሉ
አውርተን?”
👍251
“ስለ እኔና ስለ ዉብርስት ነው እንዴ ጉዳዩ ጭራሽ?” አለ ባልቻ፣ በአንድ ዓይኑ ወደኔ እየሰረቀ፡፡ እሱም ስለ ምን እንደሚብከነከኑ እስከ አሁን አልገባዉም ኖሯል።

“እናንተ ናችሁ እንጂ ሌላማ ማን እንዲህ ጉድ ይሠራኛል?”

“እባክዎ በግልጽ ይንገሩን፣ ምን አጉድለን ነው?”

“ምናለበት እንደ ወጉ እንኳን ብታደርጉት? በዚያ ዓይን ከተፈላለጋችሁ በሥርዓቱ እንዳትጋቡ የሚከለክላችሁ አልነበረ! ለምን የኃጢአቱን
መንገድ መረጣችሁት ባልቻ?”

“ምንም ሊገባኝ አልቻለም ዛሬ” አለ ባልቻ፣ ወደኔ መዞር እየሰለቸው። እኔ ግን እየገባኝ መጥቷል። የኔው ጉድ ነው። ደርሶ ሆዴን ገዘገዘኝ። አመመኝ፡፡

“አይደል” አሉ፣ የቅድሟን ለበጣ መልሰዉ እያመጧት። “መቀባባቱ
እንኳ ባንተ ይቅርና በሌላውም አያምር። ይልቅ እሱን ተወዉ፣
እንዳይለምድብህ። ለመሆኑ ምን ያህል ጊዜ ሆነው?”

“ባዛኝቷ! የምኑ?” አለ ባልቻ፣ በንዴት እየተስተካከላቸው፡፡

“ሃያ ሳምንት!” አልሁኝ፣ ከአፋቸው ነጥቄ፡፡ ሳይታወቀኝ ደረቅ ቁጣ
አንቆኛል፡፡ በእኔም ብሶ ደግሞ እንደ አሮጌ ቆርቆሮ ነው የጮህኩት። “ሃያ ሳምንት ከአራት ቀን!” አልኋቸው፣ የባሰ እየተንኳኳሁ። የባልቻ ያላ
ኃጢአቱ መጠርጠር ሁሉ ግድ አልሰጠኝም። ወንበሩን ወደ ኋላ
አሽቀነጠርሁና፣ እየተቆናጠርሁ ወደ በሩ ሄድሁኝ፡፡ በሩን በኃይል በርግጄ ከከፈትሁ በኋላ፣ ግው አድርጌ ዘግቼባቸው ወጣሁ። ምን እየሆንሁ እንደሆነ እንኳን እነሱ ለኔም አልታወቀኝም፡፡....

ይቀጥላል
👍18
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_አራት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

...እውነትም ቦታው እስትራቴጂካዊ ነበር በአንድ በኩል ወደቤቱ ሚያስገባው መንገድ ሰፊ ነው:: በጓሮ በኩል ቀደም ሲል እንደተገለጸው ቀጭን የጨለማ መንገድ አለው:: ማንኛውም አጥቂ ጦር በሴንት ዴኒስ
ጎዳና በኩል ባለው ሰፊ ጎዳና እንጂ በጓሮ በኩል ደፍሮ ሊገባ አይችልም::ስለዚህ የፊት ለፊቱን አጥብቀው ከያዙ የኋላውን በቀላሉ መመከት ይቻላል።
ድንገት ማፈግፈግም ቢመጣ በጓሮ በኩል የማምለጥ እድል አለ::

ያ ሁሉ ሕዝብ ሆ እያለ መለስ ሲል መንገዱ ሁሉ ጨነቀው::
ባለሱቅ ቶሎ ብሎ ሱቁን ዘጋ:: ከግራና ከቀኝ የነበሩ ሴቶች ሁሉ የውጭ በር ካላቸው የውጭ በራቸውን፣ አለዚያም የየቤታቸውን በርና መስኮት ቀረቀሩ፡፡ ለወሬ ሞትኩ ባይ መስኮቱን ከፍቶ በትንሹ ያያል፡፡ አላስችል
ያለውና «ምን ይቀርብኛል ብሎ ተስፋ የቆረጠው ከሰልፈኛው ጋር
ይደባለቃል፡፡

አንዲት በጣም የተደናገጠች አርጊት ምን አደረገች? ቶሎ ብላ አሮጌ ፍራሽ ከውጭ በኩል በገመድ በማንጠልጠል መስኮትዋን ሸፈነችው:: ሌላ
ፍራሽ ደግሞ ከውስጥ በኩል በማቆም ጋረደችው፡፡ ከዚያም ከመስኮቱ በር ወለል ላይ ለጥ ብላ ተኛች:: ጥይት ሲተኮስ እንዳይመታት ነበር፡፡

በዚያ አካባቢ በርና መስኮቱ የተከፈተ ቤት ሲኖር ያ መሸታ ቤትና ምግብ ቤት ብቻ ነበር:: ይሄ ደግሞ ያለ ምክንያት አልነበረም:: ትርምሱ፣ ጩኸቱ፣ ስድቡና
መዝሙሩ ድብልቅል ያለ ስለነበር የምጽዓት ቀን የመጣ
ስላስመሰለው ነው::

“ወያኔ ፣ ወይኔ፣ አምላኬ የዛሬን! ከዛሬው ብቻ ሰውረኝ» አሉ ማዳም ኻሽሉፕ ፡
ወዲያው በሃያ ደቂቃ ውስጥ ከሴትዮዋ መጠጥና ምግብ ቤት ምሽግ ተሠራ፡፡ በርሜሎች ተለቃቅመው በአሸዋና ጠጠር ተሞሉ፡፡ ጋብሮች በርሜል በማንከባለል ረዳ፡፡ በርሜል ሊሸፍነው ያልቻለውን ቦታ በአፈርና
በድንጋይ ቁልል ታጠረ፡፡ ኤንጂልራስ በጓሮው በኩል ወዳለው ጨለማ መንገድ የሚወስደውን በር ወለል አድርጎ ከፈተው:: ከዚያም ከቤቱ በር
ወደሚገኘው እቃ ማስቀመጫ ክፍል ወረደ:: ከምድር ቤቱ ውስጥ ወደሚገኘው ጥቂት በርሜሎችን አገኘ፡፡ እነርሱንም ለምሽግ ሥራ ተጠቀሙባቸው::መቼም እጅ ከተባበረ የማይሠራው ሥራ የለምና «ብዙ ቀናት ፈጅቷል
ተብሎ ሊገመት የሚችል ምሽግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀቀ፡፡ በዚያች አጭር ሰዓት ያ ቤት ከቡናና ምግብ ቤትነት ወደ ጦር ካምፕ ተሸጋገረ::

አንድ ጋሪ ሴቶችን ጭኖ በዚያ በኩል ለማለፍ ይመጣል፡፡ ከሰልፈኞቹ መሪ አንደኛው ሮጦ ሄዶ ባለጋሪውንና ሴቶችን ካስወረደ በኋላ ሴቶቹን
ከይቅርታ ጋር አሰናበታቸው:: የፈረሱን ልጓም ይዞ በመጐተት ጋሪውን ወደ ምሽጉ ወሰደው::

«ጋሪ ደግሞ በዚህ ሰዓት፣ በዚህ መንገድ ምን ያደርጋል?» ሲል
ጠየቀ፡፡ «ከአሁን ቀደም በዚህ መንገድ ጋሪ አልፎ አያውቅም» ብሎ ከተናገረ በኋላ ፈረሱን ከጋሪው አላቅቆ አባረረው:: ፈረሱ ከሄደ በኋላ ጋሪውን በጎን
በማጋደም ያንን መንገድ ለመዝጋት ተጠቀመበት::

ማዳም ኸሽሉፕ ተናደዱ፣ የሚያደርጉትን ስላጡ ከአንደኛው ፎቅ ቁጭ ብለው ቀሩ፡፡ ዓይናቸው ከወዲያ ወዲህ ይቅበዘበዛል፡፡ፀ ሳይታወቃቸው እንባቸው በጉንጫቸው እንደ ጎርፍ ይወርዳል፡፡ ድምፅ አሰምተው ለማልቀስ ተሰብረዋል
አልደፈሩም::

«ምፅዓት ነው ይሄ» ሲሉ አጉረመረሙ::

ከሰካራሙ አንደኛው መጥቶ ጉንጫቸውን ከሳመ በኋላ «መቼም
እንደ ሴት ጉንጭ የሚለሰልስ ነገር የለም» ይላል፡፡

ቫውደር የተባለች ሠራተኛ እነርሱ ከነበሩበት ክፍል ገባች:: ከሰካራሞች ሌላው በሳቅ እየተፍነከነከ የሴትዮዋን ጨርቅ በመጎተት ወደ መስኮት
ወሰዳቸው:: ወደ ጆሮአቸው ተጠግቶ አናገራቸው::
«ቫውደር እኮ በጣም ፉንጋ ናት:: መቼስ ለፉንጋዎች ምሳሌ ሆና |
ልትቀርብ የምትችል ናት:: »

ወዲያው ኤንጆልራስ ጮክ እያለ ተናገረ፡፡

«እናንተ ሰካራሞች የምሽጉን ስም አታጉድፉ:: ቶሎ እንዲበርድላቸው

ከዚህ ሂዱና ከምትተኙበት ተኙ፡፡ ይህ ሥፍራ በአገር ፍቅር ለነደዱ እንጂ ለሰካራሞቹ አይደለም

ከሰካራሞቹ ማለትም ብዙም ያልጠነበዘው በዚህ ስድብ
ከተሞላበት ንግግር ስሜቱ በጣም ስለተነካ ውሃ በጣሳ አንስቶ ፊቱ ላይ ቸለበሰ፡፡ የውሃው ቅዝቃዜ እውነትም ስካሩን ትንሽ አበረደለት:: ወደ መስኮቱ ሄዶ ኢንጆልራስን ጥያቄ ጠየቀው::

«ከዚሁ ልተኛ?»

የለም፣ ከምትተኛበት ሂድና ተኛ እንጂ ከዚህ መተኛት አይቻልም::»
«እባካችሁ ነፍሴ እስክትወጣ ከዚሁ ልተኛ» ሲል ሰካራሙ በለዘበ አነጋገር ተናገረ፡፡

ኢንጆልራስ በንቀት ዓይን አየው:: ሰካራሙም የሚባለውን ሳይሰማ
ጥቂት ከተንተባተበ በኋላ አጠገቡ ከነበረው ጠረጴዛ ላይ ጭንቅላቱን አስደግፎ ብዙም ሳይቆይ እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡ቸ

ዝናቡ ቆሞአል፡፡ ተጨማሪ ሰልፈኛ የተለያየ መሳርሪያ እየያዘ መጣ፡፡
በሩቁ የምትታይ አንዲት የመንገድ መብራት ብቻ ነበረች:: እስዋም ብዙ አልቆየችም፤ ሰልፈኞቹ ሰበርዋት:: የተቀሩት መብራቶች ቀደም ሲል
ተሰብረዋል፡፡

ኢንጆልራስ፣ ካምብፌራና ከርፌይራክ ለሰልፈኛው አመራር መስጠት ጀመሩ፡፡ መንገዱ በሁለቱም አቅጣጫ በምሽግ ተዘጋ:: የጦር መሣሪያ የያዙ
ሁሉ ቦታ ቦታቸውን ያዙ:: አንዳንዶቹ ቆብ መሳይ ነገር አጥልቀዋል::አንዳንዱ በአጭር ታጥቆ ጎራዴ ሲይዝ ሌላው ጠብመንጃ አንግቷል።
መሣሪያ ይዞ ፈረስ ላይ የተቀመጠም አለ፡፡ አንዳንዱ የመጨረሻው ሰው እስከቀረ ድረስ እንዋጋለን» እያለ ይፎክራል፡፡ ሌላው ጥይት ሲያልቅ
በድንጋይ እንማታለን» ይላል:: አንዱ ያቅራራል፣ ሌላው ይሸልላል::አንዳንዱም እነርሱ ሲጠቁ የከተማው ሰው እንደሚደርስላቻው እርስ በእርስ
ይወያያል፡፡ ሁሉም በየፊናው ይነጋገራል፤ ይቻኮላል፤ ሥራ ለመሥራትና ቦታ ለመያዝ ይጣደፋል፡፡ ሰካራሞቹና የቡና ቤቱ ባለቤት የሚያደርጉትን
አጥተው ከአንድ ክፍል ውስጥ ተፋጥጠው ቁጭ ብለዋል::
ከቁመቱ፡ ዘለግ ያለውና የሰልፈኛው መሪ የሆነው ሰው ከሰልፈኛው መካከል ገብቶ ምሽግ ይሠራል:: ጋብሮችም ከምሽጉ ጫፍ ላይ ከወዲያ ወዲህ ይሯሯጣል:: ማሪየስን የጠየቀውና ኩርፊያሪክን ጠብቀኝ
ያለው የሴት መልክ ያለው ግለሰብ ግን ከዚያ አልነበረም፡፡ ጋብሮትች
ከደስታው ብዛት ከወዲህ ወዲያ የሚለው እየዘፈነ ስለነበር አብዛኛው ሰልፈኛ ለይቶታል:: እንዲያውም ከነአካቴው ሰው ሁሉ የእርሱን ንቃትና ሞራል እያየ በጣም ተደፋፈረ፣ ሰነፉንና ዳተኛውን አነቃቃ:: ለፈሪውም
ልብ ዋጀለት። ለተደነባበረውም መንገድ ከፈተለት።

ጋብሮች ከአሮጊትዋ በነጠቀው ሽጉጥ ስላልረካ «ጠብመንጃ
እፈልጋለሁ፣ ምነው ብትሰጡኝ» እያለ ይጠይቃል::

«ጠብመንጃ ለአንተ ነው ወይስ ለማነው?» ሲል ካምብፌሪ ጠየቀው
«ምነው?» ሲል ጋብሮች ጥያቄን በጥያቄ ይመልሳል፡፡ «ምን ይጉድለኛል? ድሮ እኮ እንዴት ያለ ጠብመንጃ ነበረኝ» ሲል ይሸልላል::
ኢንጆልራስ ይስቃል፡፡
«አዋቂዎቹ ሲዳረሳቸው ለልጆች ይሰጣል::»
ጋብሮች በቁጣ ዞር ብሎ ይመልሳል፡፡
«አንተን ከእኔ በፊት ከገደሉህ እኔ እኮ ነኝ አንተን የምተካው:: ላከወ
«ጉረኛ» ሲል በቀልድ መልክ ኢንጆልሪስ መለሰለት::

«ጉረኛ አልከኝ?» ሲል ጋቭሮች ቃሉን ደገመ:: ይህን እንደጠየቀ
አንድ ሰው ከሰልፉ ወጥቶ ያያል:: ሮጦ ሄዶ «ከሰልፈኛው ተለይተው
አይሄዱ፤ ለዚህች ምስኪን አገር የሚውሉት ውለታ ቢኖር አሁን ነው፤ ስለዚህ አይሂዱ» ሲል ይማጠናቸዋል፡፡ ሰውየው ግን ፈጠን ብለው በመራመድ
ይሄዳሉ፡፡
👍12
የአንዳንዶቹ ምሽግ እስከ ሁለት ሜትር ከፍታ ነበረው፡፡ ስለዚህ
ተዋጊዎቹ ከፈለጉ ከምሽጉ ኋላ ሊደበቁ ወይም እየተዋጉ ራሳቸው
ሊመክቱበት ይችላሉ:: ከተሠሩት ረዣዥም ምሽጎች መካከል በአንድ አንድ ሰው ብቻ ሊያሳልፍ የሚችል ክፍት ቦታ አልፎ አልፎ ይታያል ከምሽጎቹ አናት ላይ ቀይ ጨርቅ ተሰቅሎአል:: ከመጠጥ ቤቱ ጀርባ ያለው ምሽግ ጨርሶ አይታይም።

ከመጠጥ ቤቱ አንድ ጠረጴዛ ከወጣ በኋላ ኢንጆልራስ ከጠረጴዛው ላይ ወጣ:: አንድ ትልቅ ሳጥን ከእግሩ ስር አስቀመጡለት:: ሳጥኑ ተከፈቱ
በጥይት የተሞላ ነበር፡፡ ጥይቱን ከምሽግ ዘሪያ ለተቀመጠ ተዋጊ አከፋፈለ፡፡ እያንዳንዱ ሰወ ሰላሣ ጥይት ደረሰ::: ተዋጊች
ጠብመንጃዎቻቸውን አጎረሱ፡፡ መንገዱ ሁሉ ረጭ አለ፡፡ ከዚያ አካባቢው አንድ ድምፅ አይሰማም::

ሁሉም ሰው «ቀጥሎ ምን ይሆን?» እያለ ይጠባበቃል፡፡ ቀኑ እየጨለመ ሄደ:: ምሽጉ ውስጥ ከተቀመጡት ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ መብራት አበሩ፡፡ ጊዜው እየገፋ ሄደ፡፡ አሁንም ምንም ነገር የለም፣ የመንግሥት
ወታደሮች ከፍተኛ ዝግጅት ላይ እንደሆነ የአድማው መሪዎች ጠረጠሩ፡፡ እነዚያ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሺህ የሚቆጠር የመንግሥት ሠራዊትን ነበር
የሚጠብቁት::

ኤንጆልራስ ጋብሮችን ፍለጋ ሄደ፡፡ ጋቭሮች ከምድር ቤት ውስጥ
ተቀምጦ ሥራ እየረዳ ነበር:: ያ ከወደኋላ መጥቶ ከሠራዊቱ ጋር
የተደባለቀው ረጅሙ ሰውዬም ከዚያው ነበር፡፡ ጋቭሮች ግን ልብ አላለውም፤ ምክንያቱም ይህ ሰው ጠብመንጃውን ይዞ የተቀመጠው ጨለም ካለ ሥፍራ ላይ ነበር፡፡ ሰውዬው በአሳብ ተውጦ የሚሆነውን ሁሉ ተግራ ተቀኝ እያለ ያጤናል::

ኢንጂልራስ ወደ ጋቭሮች ጠጋ ብሉ «ትንሽ ልጅ ስለሆንክ አንተን
ማንም ልብ አይልህምና ቶሎ ብለህ ወደ ዋናው ጎዳና ብቅ በል፡፡ ከዚያ የሚሆነውን በሚገባ ካጤንክ በኋላ ምን እንዳለ ተመልሰህ ንገረኝ ብሎ ላከው::

ጋብርች ኢንጆልራስን ቀና ብሉ አየው::

«ትንንሽ ሰዎችም ይጠቅማሉና» ካለ በኋላ «ይህማ ለክፉ አይሰጥም፣ ደህና ነው:: ሄጄ ወሬ ቃርሜ እመጣለሁ:: ግን ይገርማል፤ ትንንሽ ልጆች
ሲታመኑ ትልልቆቹ ለምን አይታመኑም?» ብሎ ይጠይቃል፡፡
ጋቭሮች ለመውጣት አንገቱን ቀና ሲያደርግ ያንን ግዙፍ ሰው
አየው፡፡ «ያንን ሰው ታዩታላችሁ?» ብሎ ጣቱን እየቀሰረ ያሳያል፡፡
«ያ ጠመንጃ ይዞ የተቀመጠው» ሲሉ ጠየቁት::
ለጥያቄው መልስ ሳይሰጥ «ሰላይ ነው» ይላቸዋል፡፡
«እርግጠኛ ነህ?» ሲሉ ጠየቁት::
«ሁለት ሳምንት አይሞላውም ጆሮዬን ቆንጥጦ ከጎተተኝ::
ኢንጂልራስ ድምፁን ዝቅ አድርጎ ለነበረው ሰው አንድ የሆነ ነገር
ነገረው:: ሰውዬው ከዚያ ወጥቶ ሄደ:: ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ሌሎች ሦስት ሰዎችን ይዞ ተመለሰ፡፡ አራቱ ዕዎች በማያስነቃ ሁኔታ ቀስ ብለው ሰውዬው ተቀምጦበት ከነበረው ሥፍራ በተለያየ አቅጣጫ ሄደው ከብበውት ቆሙ፡፡

በዚህ ጊዜ ኢንጂልራስ በቀጥታ ሄዶ ሰውዬውን አነጋገረው::

«ማነህ አንተ» ሲል በድፍረት ጠየቀው::

በዚህ ባልተጠበቀ ድንገተኛ ጥያቄ ሰውዬው በመጀመሪያ እንደመደንገጥ አለ፡፡ አንገቱን ሳይሰብር የኢጆልራስን ዓይን እያየ በቆራጥነትና በሚያስጠላ
ፈገግታ ፊቱን አስውቦ በድፍረት መልስ ሰጠው::

«ሥራችሁና ዓላማችሁ ምን እንደሆነ ተረድቼዋለሁ፡፡»
«ሰላይ ነህ አይደል?»
«አዎን፣ የመንግሥት ባለሥልጣን ነኝ»
«ማነው ስምህ?»
«ዣቬር እባላለሁ፡፡»
ኢንጂልራስ ለአራቱ ሰዎች ምልክት ሰጣቸው፡፡ ከመቅጽበት ሰዎች ዣቬር ላይ ተረባረቡ፡፡ ወዲያው ዣቬር ፊቱን አዙሮ ማየት እንኳን ጊዜ ሳያገኝ አንቀው ይዘው እጅ እግሩን ጠፍረው አሰሩት፡፡ እጁን የፍጥኝ ካሰሩ በኋላ መላ ሰውነቱን ፈተሹ፡፡ ከቋሚ የብረት ግንድ ጋር አሠሩት::
ጋቭሮች የተደረገውን ሁሉ ቆሞ ተመለከተ፡፡ ይህ ሰው ቀደም ብሎ
ለመምሰል የበደለው ስለነበረ በድርጊቱ አንጀቱ ራሰ፡፡ ወደ ዣቬር ጠጋ ብሎ « ድመት በአይጥ ተያዘ» አለው::

«ዣቬር ይህ ሁሉ ሲሆን ድምፅ አላሰማም፡፡ ከቋሚ ብረት ጋር
በመታሠሩ መነቃነቅ አይችልም፡፡ እነኩርፌይራክና ኮምብፌሬ ተመለከቱት።
«ሰላይ ነው» ሲል ኢንጆልራስ ኋላ ለመጡት ጓደኞቹ አስረዳቸው::
ወደ ዣቬር ዞር ብሉ «ምሽጋችን ከተያዘ ትገደላለህ» አለው::
«ለምን አሁኑኑ አትጨርሱኝም» ሲል ቁጣ በተሞላበት እንደበት
ዣቬር ጠየቃቸው::
«ጥይት እንዳይባክን» ሲሉ መለሱለት::
«ለምን በቢላዋ አንገቴን አትቆርጡትም፡፡»
«አንተ ሰላይ» አለ መልኩመልካሙ ኢንጆልራስ፡፡ «እኛ ዳኞች ነን እንጂ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች አይደለንም፡፡»
ከዚያም ጋቭሮችን ጠራው፡፡
«አንቺ፣ ሂጅና የተላክሽበትን ፈጽሚ፡፡ የነገርኩርህን ፈጽመህ በቶሎ ተመለስ፡፡»
«መሄዱ ነው» ብሎ ጮክ ብሎ ተናገረ፡፡....

💫ይቀጥላል💫
👍14😁1
#ገረገራ


#ክፍል_ሶስት


#በታደለ_አያሌው


...“ሃያ ሳምንት!” አልሁኝ፣ ከአፋቸው ነጥቄ፡፡ ሳይታወቀኝ ደረቅ ቁጣ አንቆኛል፡፡ በእኔም ብሶ ደግሞ እንደ አሮጌ ቆርቆሮ ነው የጮህኩት። “ሃያ ሳምንት ከአራት ቀን!” አልኋቸው፣ የባሰ እየተንኳኳሁ። የባልቻ ያላ
ኃጢአቱ መጠርጠር ሁሉ ግድ አልሰጠኝም። ወንበሩን ወደ ኋላ
አሽቀነጠርሁና፣ እየተቆናጠርሁ ወደ በሩ ሄድሁኝ፡፡ በሩን በኃይል በርግጄ ከከፈትሁ በኋላ፣ ግው አድርጌ ዘግቼባቸው ወጣሁ። ምን እየሆንሁ እንደሆነ እንኳን እነሱ ለኔም አልታወቀኝም፡፡

መኪናዬ ዉስጥ ገብቼ እንዴት አድርጌ በየት በኩል እንደ ነዳሁት
አላስታውሰውም፡፡ እንዲሁ ብዥ እንዳለብኝ ወደ ራሴ ቤት የሚወስድ በመሰለኝ መንገድ የእውር ድንብሬን እያሽከረከርሁ ነበር፡፡ ገና ትንሽ እንደ ነዳሁ፣ ሁሉም ነገር ሰለቸኝ፡፡ ጠነባኝ፡፡
ይበልጥ ድቅድቅ ብሎ ጨለመብኝ፡፡ እንደ ምንም ዳር ይዤ አረፍ አልሁና ወደ ልቡናዬ
ለመመለስ ረዥም ጸሎት አደረስሁ፡፡ ሻል እንዳለኝ፣ የተሻለ ቦታ ተከሰተልኝ፡፡ የእናቴ ቤት!
የመኪናዬን መሪ በግራ በኩል ጠመዘዝሁት እና ወደ እመዋ ቤት
የሚወስደዉን መንገድ ተያያዝሁት። እግዚአብሔር ከክፉ አደጋ ጠብቆኝ በደህና ደረስሁ እንጂ፣ አኳኋኔ እንኳን አያድርስ ነበር። ወደ እመዋ ቤት ደርሼ ስገባ ግን ማንንም አላገኘሁም፡፡ ባዶዉ ቤት ሊዉጠኝ አፉን አ ብሎ
ከፍቶ ጠበቀኝ፡፡ ይኼ ሰፊ ቤት አሁንም አሁንም እንባዉን እስከማዉቅለት ድረስ አዛጋብኝ፡፡ እንደ ገና ደግሞ ሊያስገባኝ የቀፈፈውም መሰለኝ፡፡ እንደ
ምንም ወደ ዉስጥ ብዘልቅም፣ በዚህ ቀትር እንደ እኩለ ሌሊት ነው የጨላለመብኝ፡፡ እግሬን እየጎተትሁ ግራ ቀኝ ከተቅበዘበዝሁ በኋላ፤
ለሳሎኑ ወደሚቀርበዉ ክፍል ገብቼ አልጋዉ ላይ ወደቅሁበት።

ጥቅልል ብዬ መተኛት ነበር የሚሻለኝ፡፡ እንቅልፍ ግን ከየት አባቱ ይምጣልኝ? ነገሩ ሁሉ ተደበላልቆብኛል፡፡ እህል የሚባል ለመጨረሻ ጊዜ የቀመስሁት ትናንትና ማታ ነው:: ግን አሁንም አልራበኝም። ለነገሩ፣ እንደ ሥራዬ ቢሆንማ፣ እንኳንስ እመዋ ቤት ይቅርና እመዋ የረገጠችው
አፈር ላይ እንኳን የመተኛት ሞራሉ የለኝም፡፡ በዚያም ላይ ይኼ አልጋ
ጠዋት ከእመዋ ጋር በታዕካ ነገሥት ገዳም ቆይቼ ስወጣ መንገዴ ላይ ቆመዉ እህቱ አይደለችም ብለዉ የተወራረዱበት፣ የወንድሜ የጃሪም አልጋ ነዉ።

ሁሉንም ነገር ማፈር ጀምሬያለሁ።

የአባቴ ነፍስ እንዴት ትጠየፈኝ ይሆን? የየዋኋ እናቴ አምላክስ እንዴት ይጠላኝ ይሆን? እያልሁ ተበጠበጥሁ። ይኼ አልበቃ ብሎኝ፣ ከአንድ መቶ አርባ አራት ቀናት በፊት የተፈጠረው ነገር ሁሉ በዓይነ ኅሊናዬ እየተመላለሰ ዕረፍት የሚባል ነገር ከለከለኝ፡፡ ላለማስታወስ ከራሴ ጋር
ብዙ ብቦቃቀስም፣ አለማስታወስ ግን አልቻልሁም፡፡ ዕለቷ ከነቅጽበቷ ሳትቀር መጥታ የሚከብድ ጥላዋን ጥላብኝ ዓይነ ልቡናዬ ላይ ቁጭ አለችብኝ፡፡

ትዝ አለኝ።

ዕለቷ እሁድ ነበረች። በዚያች ዕለት፣ አመሻሽ ላይ እንደ ልማዴ ክራሬን ይዤ ወደ አንድ ምዕራባዊ የአዲስ አበባ ዳገታማ ሥፍራ ላይ ወጥቻለሁ። ልክ እንደ ሁልጊዜው፣ ከሚወዱኝ የቀረ ሰው አልነበረም። ጠይም ወይ ቀይ፣ ያገባ ወይ ያላገባ፣ ወንድ ወይ ሴት፣ የወለደ ወይ ያልወለደ፣ አማኝ
ወይ ከሃዲ ሳይቀር ግልብጥ ብሎ ከቦኛል። አንዳንዱ መልኬ ጠርቶት፣ አንዳንዱ ድምፄ ናፍቆት፣ አንዳንዱ ደግሞ ሌላ ሰው ተከትሎ መጥቷል። አለባበሴም ፀሐያማ ነበር።

አስታዉሳለሁ።

ዉቧ ጀንበር ሄድሁ ሄድሁ ብላለች፡፡

ሲጀመር ለፀሐይ ምንም አይወጣላት። ለኔ ደግሞ ምንም ሲሆን፣ ከዚህ ሰዓት ሌላ ዉበቷ ደምቆ አይታየኝም። በአድማሱ ላይ እግሮቿን ከፋፍታ፣ ደልቀቅ ብላ የምትታየኝ ሲመሻሽ ብቻ ነው፡፡ ነፃነቷስ! ራሷን ወደ ታች
በምድር ላይ፣ እግሯን ደግሞ ወደ ላይ በሰማዩ ትሰቅለዋለች። መዘቅዘቋን ተከትሎ፣ ስስ ፀሐያማ ቀሚሷ ገለብ ቢልም፣ ሐፍረተ እንትኗን ግን አናይባትም፡፡ የእኔን ጉጉት እያየች ነዉ መሰለኝ፣ ፈገግ ትልብኛለች።ፈገግታዋ ደግሞ በማንም ቆዳ ላይ አይደርስም፡፡ ይኼ ራሷ ለራሷ የሰጠችው የፍስሐ ጊዜዋ ይመስለኛል። ባትሞት ትታመም፣ ሥጋ
የሚባል ግን አይኖራት ይሆን?
በዚሁ ዕለትም ከጀንበሯ ፈገግታ ፊት ለፊት ሆኜ የግራ እጆቼን ጣቶች በክራሬ አዉታሮች ላይ ዘርግቻለሁ። ከዚያም ምዕራብ ምዕራቡን እያየሁ፣
ለስለስ አድርጌ መግረፍ ጀመርሁ።

ደገኛዉ መጽሐፍ
ባሪያዎችህም ጭምር፣
ኢትዮጵያን ይሏታል
ጌታ ያንተ ሀገር።
እንግዲያዉ ጌታዬ፤
አልሟገትህም
ሀገሬን ወደ ጫፍ ሲገፉት ብትል ዝም፣
ባገርህ ነኝና ካንተ አይብስብኝም።

ድምፄን ጨመር አድርጌ እንደ ገና አንጎራጎርሁ።

ጌታ በናትህ መልሰው፣
እረ ጌታ በማርያም መልሰው
የጀግናዬ ን ልብ እንደ ሰው።

ይኼንን ብዬ፣ ያለ ልማዴ እንደ አጋጣሚ ቀና ብል፣ ከመካከላቸው አንድ ወጣት ሹልክ ብሎ ሲሄድ አየሁት። የከበበኝን ሰዉ ሁሉ ከምንም ሳልቆጥር በረቃቅሼዉ ብድግ ብዬ ተከተልሁት። ይኼን ልጅ ነው ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ
ነፍስ የተያየሁት፡፡ ይኼን ልጅ
እስከማውቀው ድረስ ዕለት በዕለት የምቆጨው መነኩሴ ባለመሆኔ ነበር።በተለይም ልጅ እያለሁ ካህኑን አባቴን ተከትዬ ለመሳለም ወደ ገዳም በምሄድ ጊዜ፣ ለደስታዬ ወደር አልነበረውም፡፡ ከዛሬ ነገ ገዳም ገብቼ በአመክሮ እጀምራለሁ እያልሁ ቀን እቆጥራለሁ። አባቴ እና እናቴ እንኳን ከእኔ የሕይወት መስመር በቀር የሚያከራክራቸው ጉዳይ መኖሩን አላዉቅም። አባቴ ሁልጊዜም ቢሆን ዉብርስቴ መንኩሳ እስከ እመምኔትነት ደርሳ ሳታሳየኝ አልሙት» የሚል ነበር ጸሎቱ ሁሉ። እናቴ ደግሞ በተቃራኒዉ ልጄ ማለፊያ ትዳር ገብታ ዓይኗን በዓይኗ ሳታሳየኝ
አትግደለኝ ባይ ናት። እንዲያዉ ድከሙ ቢላቸዉ ነዉ እንጂ፣ እመዋ ሆኖላት አባቴን እንዴትም ብላ ብታሳምነዉ እንኳን፣ የእኔ ዝንባሌ ግን የአባቴ ምርጫ ነበር። እማሆይነት። ቢሆንልኝ ብዬ የምመኘዉን የምንኩስና ስም ሁሉ ለራሴ አዉጥቼ አዉቃለሁ። አብዝቼ የተለማመድሁት ሕይወትም ምንኩስናን ነዉ። እጅግ በጣም የምቀናባቸው ሰዎች፣ በአርምሞ ዉስጥ ያሉ መነኮሳት ብቻ ናቸዉ።
በሕልሜም በዉኔም የሚታየኝ ብቸኛ ቦታ በጽዶች እና በዝግባዎች የተከበበ ጸጥ ያለ ገዳም ነበር።

ይኼን ልጅ ካወቅሁት በኋላ፣ ሕልሜን በሌላ ሕልም አስለወጠኝ። እሸቴ
ይባላል።

እሸቴ!

ቆዳው ሞኛሞኝ፣ አእምሮው ግን እሳታማ የሆነለት ልጅ ነው። ወይ
ጭንቅላት! አወይ መታደል! ባልወደው ነበር የሚደንቀኝ። አነጋገሩ የጅል፣ ንግግሩ ግን የንጉሥ የሆነለት ልጅ ነዉ። እንኳን እሱ እናቱም ጭምር ለልብ የሚደርሱ የሙቀት ወንዛወንዝ ናቸው።

ጭልጥ አልሁለታ!

በዚሁ በሲራክ-፯ ጀማሪ አባል ሳለሁ፣ የመጀመሪያ ተልእኮ የተሰጠኝ የእሸቴ ጉዳይ ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም ስሙን እና ዝናውን በሩቁ ከመስማት በቀር ትውውቁ አልነበረንም። ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁትም ያኔ የእሱን ጉዳይ ተልእኮዬ አድርጌ የተቀበልሁ ጊዜ ነው። በዚያን ጊዜ እሱ የአዲስ አበባ ኑሮ በአፍንጫዬ ይውጣ ብሎ፤ የት ይደርስበታል
የሚባልበትን የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን እርግፍ አድርጎ ጥሎት አልዩ አምባ ወደምትባል ጥንታዊት ትንሽ ከተማ ከሸክላ ሠሪ እናቱ ጋር መኖር ጀምሯል፡፡ ሲራክ-፯ ደግሞ የእሸቴን የአእምሮ ያውቀዋልና፤ ይኼን የመሰለ ልጅ ባክኖ ከሚቀር ልጠቀምበት ብሎ ወሰነ።
የእኔ ተልእኮም እሱን ለሲራክ፯ አባልነት መመልመል እና ማብቃት
ነበር።
👍272😁1
ተልእኮዬን ገባሁበት። ግን፣ እንዳሰብሁት ቀላል አልሆነልኝም::
ለዚሁ ስል ብቻ በአልዩ አምባ ጤና ጣቢያ ጠቅላላ ሐኪም ሆኜ
ተቀጠርሁ። ለመቀራረብም ቢሆን እንኳን መጀመሪያ የግድ ከእሱ
መምጣት ስለ ነበረበት፣ እኔ በሽፋንነት የተዘጋጀልኝን የሕክምና ሥራ አንገቴን ደፍቼ መሥራት ጀመርሁ። ተልእኮዬ እንዲሰምርልኝ ከፈለግሁ፣
እሱን እንደምፈልገው ይቅርና ከነመፈጠሩ እንኳን የማውቀው መምሰል የለብኝም፡፡ በዚህም ምክንያት ከፊቴ መንገድ ዘግቶ ቢቆም እንኳን እንደማይታየው ነፋስ መቁጠር ጀመርሁ። ታዲያ፣ ከመንደሩ ከፍ ብሎ አንዲት ዓይኑግቡ ሥፍራ አለች። እሸቴ ሁልጊዜም ቢሆን ጀንበር ዘቅዘቅ
ስትል የእግር ሽርሽር ካደረገ በኋላ፣ በዚያች ጉብታ ላይ የማረፍ ልማድ እንዳለዉ ቀድሞዉንም ተልእኮዉን የሰጠኝ ሰዉ ገለጻ አድርጎልኛል። ስለሆነም ዕለት በዕለት ክራሬን ይዤ ከጉብታዋ ላይ የማልታጣ ሰዉ ሆንሁ። በእርግጥ ከጀንበሯ ጋርም ፊት ለፊት የምታገናኝ ቦታ ስለሆነች፣
ቦታዋ ለእኔም ድንቅ ናት። ሁልጊዜ እሄዳለሁ፣ ሁልጊዜ ያየኛል፣ ሁልጊዜ ያዳምጠኛል፣ ሁልጊዜም ማደናነቅ ጀምሯል።

በመሆኑም ዓይኑ ዉስጥ ለመግባት የፈራሁትን ያህል አልተቸገርሁም፡፡እንዲያውም ከሌሎቹ ወጣት ወንዶች ጋር
እየተደባበቀ እሱም
ሲያንዣብብኝ ቀናት አለፉ፡፡ ለሳምንታት እንዲሁ ቀጠልን። የኋላ ኋላ ማታ ማታ ጉብታዋ ላይ የሚያየኝ አልበቃ ብሎት አንዳንድ ቀን የታመመ ሰው እየደገፈ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ራሱ ታማሚ እየመሰለ ወደ ምሠራበት
ጤና ጣቢያ መምጣት ጀመረ።

እንዲችዉ አመላለስሁት፡፡

“እእእእ እንዴት እንደሆነ እእእ እንጃ..” አለኝ አንድ ቀን፣ እንደ ልማዱ ራሴን ብሎ መጥቶ፡፡ ቀና አልሁለት፡፡ “መመመ መተዋወቅ አይቻልም?” አለኝ፣ ቀና ብዬ ማየቴን እንደ ምን እንደ ቆጠረው ሳይገባኝ። ‹አሁን ነው ጊዜው አልሁት ለልቤ። የክሊኒኩን በር መለስ አደረግሁት። ለነገሩ
የዘጋሁት እኔ ያለሁበትን ክፍል ነዉ። ግን ክሊኒኳ ያላት ክፍል አንድ ብቻ ስለሆነች፣ እሷም እኔ ያለሁባት ክፍል ስለሆነች፣ የኔን ክፍል ዘጋሁት ማለት ክሊኒኩን እንዳለ ጠረቀምሁት ማለት ነዉ። ይኼንን ሳደርግ ከየትና የት ድረስ እታከማለሁ ብሎ በፍዳ የመጣዉን ምስኪን ሕመምተኛ ሁሉ ማጉላላቴ አይቀርም፡፡ ባይሆን መልሼ ቶሎ መክፈት
ስላለብኝ፣ ያለ ተጨማሪ መግደርደር ለትዉዉቅ ፈቃደኛ የሆነ መልኬን አወጣሁለት።

“እእእ-እሸቴ እባላለሁ”

ቀጥል የማለት ያህል፣ ግንባሬን ፈታሁለት።

“ጓጓደ-ደደደደ-ኛ የየየ-የሚባል ሰ-ሰው የለኝም። ቀልጁ የሚስቅልኝ ሰው የለም፡፡ የ-የሚያዝንልኝም የለ። ለለለ-ለምን እንደሆነ ልልልል-
ልንገርሽ?”

እኔ እየቀጣጠልሁ እሰማዋለሁ እንጂ፣ አንድ ቃል ለማዉጣት ብቻ ዘመን ይፈጅበታል። ስለሱ ያን ያህል መረጃ ስሰበስብ፣ ስለ ተብታባነቱ ግን ማንም የነገረኝ የለም። ቢሆንም ግን ተብታባነቱ ሳይቀር የደስ ደስ አለዉ።
ያምርበታል። ቢያንስ እኔ ወድጄለታለሁ። ለመሸነፍ ይኼን ያህል በጫፍ ላይ ኖሪያለሁ እንዴ? ቀድሜ የሰማሁለት ዝናዉ ሳያዳክመኝ አልቀረም።የእሺታ ፊቴን አይቶ ቀጠለለኝ፣ እኔም እንደ ምንም እየቀጣጠልሁ
አዳመጥሁት።

“አአአ-አየሽ ብቸኝነት መቃብር ነው። ለብቻ መቅረት ሞት አይደለም? እኔ ዓይኔ ቢታወር እመርጣለሁ። ብቸኝነት ግን ከምንም የባሰ ገሀነም ነው። የፈለገ ቢሆን ከሰው እንዳለመላመድ መጥፎ ቅጣት ያለ አይመስለኝም። ጭንቁን አይጣልብሽ! ከሰው መሀል ሆኖ በሰው እንዳለመፈለግ ያለ ጭቆና የለም። ያማል! ያንገበግባል!”
ሊያለቅስ ደረሰ፡፡ አንጀቴን በላዉ፡፡

“እእእ እንዴት እንደሆነ እንጃ፤ አንድ ቀን ወደ ሴት ተራ መሄድ
አማረኝ። ብዙም አላሰብሁበትም ልበል? እኔ እንጃ። ብብብ ብቻ
መገኛቸዉን ከብዙ የአማርኛ መጻሕፍት ስላወቅሁ ፒያሳን መርጨ ወደዚያ ወጣሁ። ገበያ ታውቂያለሽ? ለዓይን ከያዘ ፒያሳን ብታያት ቁጭ ገበያ ናት። ያዉም ድብልቅልቅ ያለች የሴት ገበያ! ወንደኞችን ከሴተኞች
ታሽማምታለች። ከከከ ከላይ
እስከ ታች ሴተኞች ተጠጋግተዉ
ይሰለፋሉ። የጊዮርጊስ ገረገራውን ተደግፈው፣ የምኒልክ አደባባይን
ከበው፣ በሲኒማ ቤቶች ደጃፍ ተንቋጠው፣ የየሰቀላቸውን ጉበን
አንቀው፣ የሰሜን ማዘጋጃ መንገዱን ዘግተው ይቆማሉ። ወንደኛው ደግሞ እጁን በኪሱ ደብቆ እየገላመጠ በፊታቸው ያልፍልሻል። እኔም እንዲሁ ሁኔታውን እየታዘብሁ ወዲያ ወዲህ ስል፣ አንዷ አትጠራኝም
መሰለሽ? ‹እ ነፍሴ› አለችኛ! አፍሬ ስደነባበር መሬቱን ሳይቀር በእርግጫ ሳትሁት። አየር ላይ የምንሳፈፍ መሰለኝ። የሆነዉ ሆኖ ያልሰማሁ ለመምሰል ሞከርሁ። ዝዝ ዝም ብላ ተከተለችኝ”

ይኼን ሲል ሐፍረት ተሰማዉ። የባሰ አቀረቀረ፡፡ እኔ ደግሞ ገመናውን ከራሱ አፍ የመስማት ጉጉቴ የትና የት ደርሷል። እንዳያቋርጥብኝ ስለ ፈራሁ እንደ መወትወት ሁሉ ቃጣኝ፡፡

“እና? ተመለሺ አልካት?”

“እእእ እኔ?... እረ እኔስ ተመለሺም ተከተዪኝም አላልኋትም ነበር። እሷ ናት እንጂ፤ ጭጭጭጭጭ ጭራሽ ቀደመችኝ እና ወደ ሆነ መስቃላ ቤት ጎተተችኝ እንጂ። እዚህ ላይ ነዉ ታሪኬ የተለወጠዉ። ሌላ ዓለም ዉስጥ
ሌላ ነገር አየሁ። እንዲህ እንደ ዋዛ የገባሁበትን ሌላ ዓለም፣ በበነጋታዉም ደግሜ ማየት አሰኘኝ። እያደር እየለመድሁት መጣሁ። ጭራሽ ሱስ
ሆኖብኝ አረፈዉ። ከዚያ በኋላማ ምኑ ቅጡ! አጥር ተደግፋ የቆመች ሴት ሁሉ ገላ ሻጭ እየመሰለችኝ፣ ስንት ብር ነሽ? እላታለሁ ጠጋ ብዬ። ለብቻዋ ፈንጠር ብላ የቆመች ሴት ሁሉ አላልፍም። ወይ ውርደት!
ስስስስ ስንት ሰው አስደንግጫለሁ መሰለሽ”

እውነትም ገራሚ ልጅ አይደለም? ገና ስሙን ነግሮኝ እየተዋወቀኝ
ለመስለው ለእኔ ያለ ሐፍረት እንዲህ ከመሀሉ ጀምሮ መናዘዙ
አይገርምም? ቅሌቴ የሚለዉን ነገር የመናገሪያ አመጣዉ? እንዴት ሆነለት? በጣም ደነቀኝ፡፡ እኔ እሱን ብሆንስ?.....

ይቀጥላል
👍342👎1👏1
#ማወቅ_እና_ማመን

ከቀጠርኩሽ ቦታ ቀርተሻል አውቃለሁ
ያወቅሁትን እውነት
ማመን ቢቸግረኝ
ትመጣለች እያልሁ እጠብቅሻለሁ
“አትመጣም" እያለ
ለሚነግረኝ ሁሉ መቅረትሽን አውቆ
የቀረበት እንጂ
የመጣለትማ አያውቅም ጠብቆ
ብዬ እመልሳለሁ
በቃትመለሽ ቀርተሻል አውቃለሁ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍238👏2😁1
#ገረገራ


#ክፍል_ሶስት


#በታደለ_አያሌው


..እውነትም ገራሚ ልጅ አይደለም? ገና ስሙን ነግሮኝ እየተዋወቀኝ ለመስለው ለእኔ ያለ ሐፍረት እንዲህ ከመሀሉ ጀምሮ መናዘዙ አይገርምም? ቅሌቴ የሚለዉን ነገር የመናገሪያ አመጣዉ? እንዴት ሆነለት? በጣም ደነቀኝ፡፡ እኔ እሱን ብሆንስ?አይደለም ለሌላ ሰው ልነግረው ይቅርና፣ ራሴንም እንደማልክደው እርግጠኛ አይደለሁም። እሸቴ የተለየ ሰዉ መሆኑን አመንሁ። ገራገር ነው። በዚያም ላይ በግልጽነቱ ላይ ወሰን አጣሁበት። ይኼን ሰው
ከማድነቅ በቀር አማራጭ የለኝም።

“ስለ ለምንድን ነው ግን የነገርሁሽ?” አለ፣ እንደ ማፈርም እንደ መሳቅም ብሎ።

“እንጃ” አልሁት፣ ባይነግረኝ እንደማለቅስ እያወቅሁት። በእኔ ቤት ለእሱ ግድ የሌለኝ መምሰሌ ነዉ። ዉሸት! ለምን ሆነና ስንትና ስንት ኪሎ ሜትሮች አቆራርጬ፣ እዚህ አልዩ አምባ የመጣሁት? ለእሱ ብዬ እኮ ነዉ። የገዛ ታሪኩን ከራሱ አፍ ለመስማት፡፡ ደካማ ጎኑን ለማወቅና የሲራክ ፯ አባል ለማድረግ ነዉ እዚህ ድረስ መምጫ ምክንያቴ፡፡ ቢሆንም
ግን እንደማዉቀዉ ሊያዉቅብኝ አይገባም፡፡ ስለዚህ የባሰ ፊት ነሳሁት።

“ቅቅቅቅቅቅ ቅሌታም ነኝ አይደል?”

“ነህ እንዴ?”

“ይኼን ያወቁ የግቢ ልጆች ምን ብለው ቅጽል ስም እንዳወጡልኝ
ታዉቂያለሽ?”

“ግቢ...?” አልሁት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኮምፒዉተር ሳይንስ
ተማሪ እንደነበር ጠንቅቄ የማላውቅ ይመስል። እንኳንስ ይቺን፣ ስለሚያዘወትረዉ የካልሲ ቀለም ሳይቀር ተነግሮኛል። ግቢ ነበርህ እንዴ?” አልሁት አሁንም፣ ስለሱ ምንም እንደማላዉቅ መስየ።

“አዎ”

“እሺ፣ ምን አሉህ?”

“ዎዎዎዎ ዎከር”

“ዎከር?”

«ሂያጅ ማለታቸዉ እንደሆነ። ያያያያ ያው የቀላዋጭ መጠሪያው
እንደዚያ አይደል? እኔ ከዚያ በፊት ለማንም ሐሜት ደንታ የለኝም ባይ
ነበርሁ። ይኸኔ ግን ተሰማኝ። አመመኝ። በጣም አፈርሁ። ራሴን መናቅ ሁሉ ጀመርሁ። ተማሪ አስጠላኝ። አስተማሪ አስጠላኝ። ዩኒቨርስቲ አስጠላኝ። መማር ጠላሁ። በበበ በቃ ሁሉ ነገር ጉሮሮዬ ላይ መጣ።
የጀመርሁትን በጅምር ትቸው ወጣሁ። ከዚያ ሁሉም ነገር በአፍንጫዬ ይውጣ ብዬ ወደ እናቴ መጣሁ እልሻለሁ” አለና፣ ኧሁሁ ብሎ በረዥሙ ሲተነፍስ፣ ወዠቦ ያለፈ ነበር የመሰለኝ። ቅዝዝ ብዬ አየሁት፡፡ አዘንሁለት። ሰነባብቼ እንዲያዉም ሲራክ፤ ከሰጠኝ ተልእኮዬ ጎን ለጎን
ለእሱ ማዘኑንም ለራሴ እየደረብሁበት መጣሁ፡፡ ይባስ ብዬ ራሴን ሳታልለው ደግሞ «እሸቴ እኮ የእኔ እርዳታ ያስፈልገዋል ማለት ጀመርሁ። አዝኜ ሞትኋ! እኔ ማነኝና ለእሽቴ አዝናለሁ? ዉሽት።
የምንኩስና ምኞቴን የሚያስረሳ ቦታ በልቤ ዉስጥ ጠርጌ ማስረከቤን ላለማመን የፈጠርኋት መሸንገያዬ ናት። መከጀሌን ከውርደት ብቆጥረው
እንጂ አሸንፎኛል። በቃ ገዳም የሚለዉ የልጅነት ምኞቴ ቀረና ትዳር ያሰኘኝ ጀመር። መነኩሴነት ቀረ እና ሚስትነት በዓይን በዓይኔ ዞረ። በእርግጥ እሱ ብቻ ሳይሆን እኔም አሸንፌዋለሁ። ማኅበሩን ጨምሮ ጠላሁት ያለውን ነገር ሁሉ አስወድጀዋለሁ። ልክ እንደ ተላክሁት ሄጄ አምጥቼዋለሁ። ማምጣት ብቻ ሳይሆን የሲራክ-፯ አባል ማድረግ ችያለሁ። ያዉም ተራ ሳይሆን፣ እንደ ዓይን የሚቆጠር መኩሪያ አባል።

ተልእኮዬን በፍጽምና ተወጥቼዋለሁ።

ከዚያ በኋላ አፍ አዉጥተን ፍቅረኛሞች ነን ባንባባልም፣ ያዉ ሆነናል። በበኩሌ ልቤን ሰጥቼዋለሁ፡፡ ስለ እሱ ሞኝነት እና ጉብዝና መስማቱ ሱስ ሆኖብኛል፡፡ እሱም ቢሆን አይቶኝ እና እንጉርጉሮዬን ሰምቶ አይጠግብም፡፡ነገር ግን ገና ማንም ያወቀብን አይመስለኝም፡፡ ምናልባት፣ ባልቻ እና
የእሽቴ እናት ጥርጣሬው ይኖራቸው ይሆናል እንዳይታወቅብን የተለየ ጥንቃቄ አድርገን ሳይሆን እኔ ክራሬን ይዤ
ወደ አደባባይ ስወጣ ብዙ ወጣት ግልብጥ ብሎ እንደሚያጅበኝ የታወቀ በመሆኑ ይመስለኛል
በሲራክ ፯ ማዕከልም ቢሆን ከብዙዎች ጋር ጥሩ ቀረቤታ ስላለን፣ የእሽቱን የተለየ አያስመስለውም። ወይ
እኔን በእንዲህ ያለ ነገር
የሚጠረጥረኝ አይኖር ይሆናል፡፡ በተለይ ቤተሰቦቼ ሴትና ወንድ እንኳ ለይቼ ማወቅ የሚሆንልኝ አይመስላቸዉም፡፡ እንዲያውም አንደኛዋ እህቴን ልነግራት ስሞክር፤ አንቺ እንኳን እንደ እሸቴ ላለ ዘሟች ይቅርና ለጳጳስ ልጅም አትደነግጭት ብላኛለች፡፡ ጳጳስ ልጅ እንደማይወልድ ጠፍቷት ሳይሆን ምን ያህል እኔን በእንዲህ ዓይነት መንገድ
እንደማትገምተኝ ስታሳምነኝ ነው።

አላወቀችኝማ፣ ለእሽቴ ስል የማይተወዉን ሕልሜን እንደ ተዉሁት።

“እኔ ምልህ እሸቴ” አልሁት፣ በዚያች ጎደሎ ምሽት በእኔ ቤት እራት በልተን ከመጨረሳችን። ቀደም ብሎ፣ አመሻሹ ላይ ከጀንበሯ ፊት ክራር ይዤ ሳለሁ፣ እኔን ከብቦ እንጉርጉሮዬን በስስት የሚያዳምጠኝን ሰዉ
ሁሉ ከምንም ሳልቆጥር ረግጬ፤ እሱን ተከትዬዉ ቀጥታ ወደኔ ቤት
ነበር እራት እንብላ ብዬ የወሰድሁት።

“ትናንት” አልሁት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወይን ለመቅመስ እጄን ወደ
ብርጭቆዉ እየሰደድሁ። አልኮል የሚባል ነገር በአፌ ዞሮ ስለማያውቅ፣ ምን ምን እንደሚል መቅመሱ ሳያጓጓኝ አልቀረም።

“ትትትትት-ትናንት ምን?”

አንድ ነገር ብጠይቅህ ሳትደብቅ ትነግረኛለህ እ?”

“ካካካ ካንቺ መደበቁ ሆኖልኝ እኔ?”

“አዉቃለሁ፣ አትደብቀኝም”

“ስስስ-ስለኔ ላንቺ ምንድነዉ ያልነገርሁሽ ዉቤዋ?”

“ትናንትና በዚህ ሰዓት የት ነበርህ?” አልሁት ዓይን ዓይኑን እያየሁ፣ ቁርጥ አድርጌ፡፡

“ትትትት ትናንትና?” አለ፣ ደም እንደሚጎነጭ ዝግንን ብሎት የወይኑን ብርጭቆ ወደ አፉ እያስጠጋ።

“የት ነበርህ?”

እንደ ትኩስ ቡና በፍራቻ ፉት ያለዉን ወይን በአፉ እንደ ያዘዉ ለረዥም ጊዜ ጣሪያ ጣሪያዉን አየ። እኔም ልቤ ለምላሹ እንደ ተንጠለጠለች፣ በዝምታ ጠበቅሁት። የጠረጠርሁት ነገር አለ። መቼም ዐመል በዋዛ
አይለቅምና፣ ምናልባት ወደ ሴተኛ አዳሪዎች መሄዱን የተወዉ
አልመስልሽ ስላለኝ ነዉ አጠያየቄ፡፡ ቢሆንም፣ ከእሱ ጋር ያለዉን እዉነት መስማት አለብኝ፡፡ እኔን እንደማይዋሸኝ ደግሞ አዉቃለሁ። እንኳንስ እንዲህ እየተቁለጨለጭሁ ጠይቄው ይቅርና፣ ድሮዉንም ግልጽነቱን
ማንም እንደ እሱ አልታደለዉ። የት ነበርሁ ይለኝ ይሆን?

“እእእ አልሆነልኝማ” ብሎኝ አረፈዉ፣ እንባ በዓይኑ ጢም እያለበት፡፡
እንደ ፈራሁት!

“ምን ማለት ነዉ አልሆነልኝም ማለት?”

“በቃ ሄጄ ነበር። እሱን አይደል የምትጠይቂኝ? ትናንትና በዚህ ሠዐት ፒያሳ ዶሮ ማነቂያ ነበርሁ”

“እኮ ምን ልትሆን!?”

“አአአ አልቻልሁም። ምን ጎትቶ እንደሚወስደኝም አላውቀው። ምኑ ሽዉ እንደሚያደርገኝ ሁሉ እንጃለቴን። ግን ትናንትም ሴተኛ አዳሪዎች ጋ ሄጄ ነበር። አቅቶኛል እኔ”

እየየ ብለን ተላቀስን። እንባዬ እየወረደም ንዴት ተናንቆኛል። እየቆየማ ጥርሴ ሁሉ ተፋጨብኝ። ይኸኔ በንክሻ ብዘለዝለዉ ሁሉ የልቤ አይደርስም። ለንዴቴ ማብረጃ አጣሁለት።

“ደግሞ አታፍርም? ጀብዱ እንደ ፈጸመ ሰዉ ጉድህን ስትናገር ሐፍረት የሚባል የለህም!?”

“ብዋሽሽ የባሰ አታዝኝብኝም ነበር?”

“ዋሽተህ መሞከር ነበራ! ሁልጊዜ አንድ ዓይነት መልስ አያሳፍርህም? ሁልጊዜ ‹አቃተኝ ስትለኝ አታፍርም!? ጨክነዉ ከተዉት እንኳን ዝሙት
ሌላዉስ ይቀር የለም እንዴ!?
ሁልጊዜ አንጀቴን የምትበላው
ይመስልሃል? ቆይ ጅል ነዉ እንዴ የምመስልህ!?”

ሌላ መልስ አጣ። ደግሞ ምናባቱንስ ይመልስልኛል?

“ልንገርህ አይደል? አንተ መቼም አያልፍልህም! መቼም አትለወጥም!”

“አሳፈርሁሽ አይደል?”

“ነገርሁህ። ተንፏቀህ ተልከስክሰህ ትቀራታለህ እንጂ፣ መቼም
አትለወጥም!”
👍432
“እእእ .እእ..እባክሽ አግዥኝ። አንቺ አግዘሽኝ ያልሆነልኝ ነገር የለም።
በማርያም እርጅኝ”

“ባክህ ወደዛ! የራስህ ጉዳይ!!” ብየ አበሻቀጥሁት፣ የበለጠ ብልጭ ብሎብኝ። ልቤ የሚረጨዉ ደም ያለ ቅጥ እንደ ፈላ ይታወቀኛል።
ዉስጤን ለመጠጠኝ። ለወትሮዉ እንኳንስ እንደዚህ የሰማዩንና የባሕሩን ኗሪዎች ጨምሮ እስከማስደንገጥ ይቅርና፣ ማንንም ኃይለ ቃል ተናግሬ
አላዉቅም። ልክ እንደ ወይኑ መጠጥ ሁሉ፣ እንዲህ ስቆጣም
የመጀመሪያዬ ይመስለኛል። እንደ ነባር ጠጭ ብርጭቆዬን ብድግ አድርጌ ወይኑን ባንድ ትንፋሽ ጨለጥሁት። ፊልም ላይ እንዳየሁት መጠጡ
ጉሮሮዬን ፍቆኝ ዓይኔን ያስጨፍነኛል ብዬ ስጠብቅ፣ እንዲያዉም ጥፍጥናዉ ነዉ አፌ ላይ የቀረብኝ። ጠጪኝ ጠጪኝ፣ ድገሚኝ ድገሚኝ አለኝ፡፡ ድጋሚ ጢም አድርጌ በብርጭቆዉ ቀዳሁበትና አሁንም ልምድ
እንዳለዉ ጠጪ ግርግጭ እያደረግሁ በጉሮሮዬ አንቆረቆርሁት። ወይኑ
ወደ ጉሮሮዬ በወረደ ቁጥር ስካር ወደ ጭንቅላቴ፣ የተንቀለቀለ ቂም
ደግሞ ወደ ልቤ ሰተት ብሎ ሲገሰግስ ይታወቀኛል። ያባብለኛል ብዬ የጠበቅሁት እሸቴ፣ ገና ለገና የራስህ ጉዳይ ስላልሁት ሐሞቱ ፈሷል።እንዲያዉም አልቅስ አልቅስ ብሎታል፣ እንኳንስ እኔ ፊት ነስቼዉ። እኔ ደግሞ ምን ስል ነዉ ይህን ሰዉ ሕልሜ ያደረገሁት ስል ራሴን አጠቃሁት፡፡ ንዴት ቀላቅሎ፣ ቁጭት መታኝ፡፡ ወይኑን ከነጠርሙሱ አንስቶ መጨለጥ አሰኘኝ፡፡ የጠርሙሱን አንገት አፈፍ አድርጌ አነሳሁትና
አንዶቀዶቅሁት።

“እንዲህ ነኝና ልጅቷ!” ስል ተገለገልሁ፣ ግማሽ በግማሽ የስካር ሐይቅ ዉስጥ ገብቼ፡፡ እሸቴ በብርጭቆዉ ጠብ ያደረገዉ እና በጉንጩ የያዘዉ
ሲቀር፣ አንድ ሙሉ ጠርሙስ ብቻዬን ፈጀሁ ማለት ነው። “ወይን
እንዲህ ጣፈጭ ኖሯል ለካ!” ስል እንደ ጥንባዣም ተለፋደድሁ።

“ሰሰሰ ሰከርሽ እንዴ ?”

“ሰከርሁ እንዴ?”

“እረ አፍሽ እየተሳሰረ ነዉ ዉቤ”

“ምናገባህ! እሰይ እንኳን ሰከርሁ!”

“ስካርስ አያምርብሽም”

“ሂድ ሂድሂሂድድድድ...”

ትክትክ ብዬ ሳቅሁበት። ሳቄን ተቀብሎ እሱም አሽካካብኝ። ሳቁ
ለመጀመሪያ ጊዜ አስጠላኝ፡፡ የሆነ የጉርጥ መንጋ መሀል ያለሁ መሰለኝ፡፡
ድምፁ ሰቀጠጠኝ። ጠላሁት።

ሆሆሽ. በይ ልሂድልሽ። አንቺም ብትተኝ ይሻልሻል” ብሎ
ከመቀመጫዉ ሲነሳ፣ በብዥታ ይታየኛል። እንደገና እንባዬ እስኪወርድ ሳቅሁበት።

“ወደ ሴተኞቹ መሄድህ ነው እ?” አልሁት፣ ሳቄ እንደ ሳል እያካለበኝ።
“ጅል! ይልቅ ቅድም እርጅኝ ብለኸኝ አልነበር? ና ተቀመጥ ልርዳህ”

“እአአ አይ ነገ...”

“አሁንስ? አሃ... ሰዓት አሳለፍሁብህ መሰለኝ። ለመሆኑ የት ሰፈር ያለችዋ ናት የዛሬዋ ተረኛ? ሰባተኛ ነዉ እ? ወይስ የጨርቆሷ? መቸስ ጭፈራ ቤት የሚቆሙት ላይ ገና አልደረስህም። አይደል? ወይስ ደርሰሃል? አይዞህ አይዞህ በዚህ አያያዝህ ከዋናዎቹ የገላ ደላላዎች ጋር መተዋወቅህ ስለማይቀር፣ የምትፈልጋትን ዓይነት ሴት እቤትህ ድረስ
ያስመጡልሃል። ሃሃሃ... ይልቅ አንተ ደከመኝ ሰለቸኝ አትበል። ለነገሩ እነዚህ በየጉራንጉሩ ያሉትስ ማን አላቸዉ? ማዳረስ እኮ ይጠበቅብሃል።

መቼስ ጎዳናዉ ሁሉ በአዳሪ ሴቶች አይደል የተጥለቀለቀዉ?... ደግሞም እኮ ከመንገድ መብራቶች ይልቅ፣ መንገድ ዳር የሚቆሙ ሴተኞች
እንደሚበልጡ ነግረኸኛል። እኔ ራሴ ትናንትና ከቤተ መንግሥት በር ላይ የቆሙ ሴተኞች በዓይኔ በብረቱ አይቼ ገርሞኝ ልሞት። በቤተ መንግሥትም ዉስጥ ቤርጎ አለ ማለት ነዉ? ዞሮ ዞሮ አይዞህ በርታ። አላስመሸሁብህም አይደል? ትደርሳለህ ግን?”

በኃይል አሽካካሁበት፡፡

“እረ በእናትሽ፤ በእናትሽ ተይ”

“እሁ!” አልሁ፣ ያለሁበት እየተንጨዋለለብኝ፡፡ ዓለም በዙሪያዬ ስትሽከረከር ይታወቀኛል። ወደ ሌላ ዓለም እንደ ገባሁም ጠርጥሬያለሁ።
ከዚያ በኋላ የሆነዉን የቱንም አላስታዉሰም፡፡ ብቻ ግን በነጋታዉ
አረፋፍጄ ከእንቅልፌ ስባንን፣ ራሴን በራሴዉ አልጋ ዉስጥ ነዉ
ያገኘሁት። ትልቅ የድንጋይ ወፍጮ ራሴ ላይ የተጫነብኝ ያህል ናላዬን
ክብድብድ ብሎኛል። ጭንቅላቴን በኹለት እጄ ጨብጬ እንደ ምንም ለመነቃቃት ሳዛጋ፣ አንድ የሚንሰቀሰቅ ድምፅ ከአጠገቤ ተሰማኝ። ቀና ብዬ ሳየዉ እሸቴ እያለቀሰ ነዉ።

“ምነዉ አንተ?” አልሁት፣ ገስግሶ በጠዋቱ ወደ ቤቴ እንደ መጣ
በመገመት፡፡ ከብርድ ልብሴ በሥር ገላዬን ስዳብሰዉ ምንም የቀረ ነገር የለም። የጡት ማስያዣዬ ሳይቀር፣ ሁሉም ልብስ ወላልቋል። መቼ እንዳወለቅሁት ሁሉ ትዝ አይለኝም። እሸቴን አየሁት፣ አሁንም ያለቅሳል።

“ምን ሆነሀል? ምነዉ እናትህ ደህና አይደሉም?”

እየባሰበት መጣ። ንፍጥ እና ለሃጩ እስኪዝረከረክ ድረስ እህህ አለ። ለማባበል ከነብርድ ልብሴ ወደ እሱ ስንፏቀቅ ይሸሸኛል። በራሱ ጊዜ ዝም ለማለት ሲሞክር ደግሞ ሲቃ ያካልበዋል፡፡

“እናትህን ምን አገኛቸዉ?”
“ምምም-ም-ምንም አልሆነች እእእ-እሷ”

“እና ምንድነዉ?”

“ገደልሁሽ እኮ ዉቤ”

አሁንም ይንሰቀሰቃል፡፡ እኔን ግን እንደ መሳቅም ገፋፋኝ፡፡ ገና ሳቁን
ሳልጀምረዉ ግን አንድ ነገር ዓይኔ ዉስጥ ጥልቅ አለ። በቦታዉ ላይ
ያጣሁትን የዉስጥ ሱሪዬን በእሸቴ እግሮች መካከል ወድቆ አየሁት::
ቅፍፍ አለኝ፡፡ ጭዉ አለብኝ፡፡ እንዳልዉጠውም እንዳልተፋዉም አጉል ሆኖ፣ ምራቄ ጉሮሮዬ ላይ ቀረ። የገዛ ምራቄ በትንታ አንፈራፈረኝ፡፡ ትንፋሽ አጠረኝ፡፡

“ገገገ ገድየሻለሁ” አለ፣ እንደገና እንባዉን እያዘነበዉ።
እሱ ባይሆንም ገዳዩ፣ መሞቱንማ ከዚህ በላይ? ሞቻለሁ እንጂ፡፡ የአባቴ ነፍስ ለምንኩስና እንደ ተመኘችኝ፣ እናቴ ደግሞ ለተክሊል እንደ ጠበቀችኝ ቀረሁ። ለእናቴም ለአባቴም ምኞት ሳልበቃ ቀረሁ። ጓደኞቼም፣ እህቶቼም፣ ወንድሞቼም እንደ ኮሩብኝ ሳልሆን ቀረሁ። የገዛ ዕድሌን
አልከሰከስሁት። በቃ በአንድ አዳር ዕድሜ ምንም ሆንሁኝ። ከዚህ በኋላ ምንድነኝ እኔ? መደዳዉን ለቀናት ብተኛም አልሻልሽ አለኝ ልክ እንደ ጽኑ በሽተኛ፣ ከወደቅሁበት መነሳት አቃተኝ።

መሞቴን አምኜ ተቀበልሁ።

እሸቴ ለቀናት አባብሎ አባብሎ ሲያቅተዉ በስንተኛዉ ቀን እንደሆነ እንጃ፣ የሆነ ምሽት ላይ እናቱን ይዞ መጥቶ ደግሞ ሞከረኝ። ትከሻዬን መታ
መታ አድርገዉ ከሞትሁበት ቀሰቀሱኝ። ለወትሮዉ እናቱን የታቦት ያህል አከብራቸዉ ነበር። አሁን ግን እሳቸዉ መሆናቸዉን ሳይ የባዕ ተቅበዘበዝሁ። እግዚአብሔር ራሱ ዘንበል ብሎ እንደሚያናግረኝ አፍሬ
መሸሸጊያዉ ጨነቀኝ፡፡ ብርድ ልብስ ዉስጥ ከነሙሉ ልብሴ የወደቅሁ ቢሆንም፣ መለመላዬን ያጣሁ ያህል ነዉ የሚሰማኝ፡፡ ክብሬ ተገፏል። ርቃኔ ቀርቷል።

እሳቸዉ እንደ ነገሩ አጽናኑኝ፡፡ተቆጥተዉኝም፣ መክረዉኝም፣
አባብለዉኝም፣ ሄዱ።

ሆኖም ራሴን ወደ ቀድሞዋ ዉብርስት መመለስ አልሆነልኝም፡፡ እሸቴን
ይቅርና ራሴን ይቅር የማልል፣ ራሴን የማልወድ ሴት ሆኜ አረፍሁት።እሸቴማ ከፈለገ ዛሬዉኑ ድፍት ቢል መቃብሩ ላይ እንኳን መድረስ አልፈልግም።

የጉድም ጉድ ሲያመጣብኝ ደግሞ፣ የወር አበባዬን ብጠብቀዉ ብጠብቀዉ
ጠልቆ ቀረ። አጅሬ ለካ በሆዴ ቀርቷል። ተጋለጥሁ። እንግዲህ እንዲሁ በድንገት የልጅ እናት መሆኔ ነዋ! ይኼስ እንዴት ተብሎ ለማን ይነገራል? እንዳይታወቅብኝ የማላደርገዉ ጥረት አልነበረም። ያለወትሮዬ ወፍራም
👍191👎1
ባለ ዘርፍ ሹራብ መደረብ አዘዉትሬያለሁ። ከሰዉ ጋር ስቆም፣ ሆዴን ሰልቤ ወደ ፊት ዘመም እላለሁ። ቢሆንስ ግን ሽል አይደል ነገርዮዉ? እስከ መቼ መደበቅ እችል ኖሯል? እንኳንስ በልብስ በምንም መደበቅ
እንዳልችል አድርጎ እየፈጠጠ መጣብኛ! በእኔ ቤት ማንም አላወቀብኝ ብዬ ከራሴ ጋር ስሹለከሎክ፣ ይኸዉ ቢያንስ እናቴ እና የማኅበሩ ሊቀ መንበር አዉቀዉብኛል። ሌላዉም ሳይነግረኝ እየተጠቋቆመብኝ ነዉ
እንጂ፣ ይኸኔ ጉዴ ገሀድ ወጥቶብኛል በቃ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሚከፈት የበር ድምፅ ሰምቼ ቀና ስል፣ ጠዋት ከእመዋ ጋር ተሰነባብቼ ከበዓታ ገዳም ስወጣ ‹እህቱ አይደለችም ብለዉ ለዉርርድ የደረሱበት ወንድሜ ጃሪም የሸሚዙን እጅጌ ሰብስቦ ከፊቴ ቆሟል።

“ጭራሽ!” አለ፣ የወትሮዉ ፊቱ ልዉጥዉጥ እንዳለ።.....

ይቀጥላል
👍134😁1🤔1
#ምንዱባን


#ክፍል_አርባ_አምስት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

...«ዣቬር ይህ ሁሉ ሲሆን ድምፅ አላሰማም፡፡ ከቋሚ ብረት ጋር
በመታሠሩ መነቃነቅ አይችልም፡፡ እነኩርፌይራክና ኮምብፌሬ ተመለከቱት።
«ሰላይ ነው» ሲል ኢንጆልራስ ኋላ ለመጡት ጓደኞቹ አስረዳቸው::
ወደ ዣቬር ዞር ብሉ «ምሽጋችን ከተያዘ ትገደላለህ» አለው::
«ለምን አሁኑኑ አትጨርሱኝም» ሲል ቁጣ በተሞላበት እንደበት
ዣቬር ጠየቃቸው::
«ጥይት እንዳይባክን» ሲሉ መለሱለት::
«ለምን በቢላዋ አንገቴን አትቆርጡትም፡፡»
«አንተ ሰላይ» አለ መልኩመልካሙ ኢንጆልራስ፡፡ «እኛ ዳኞች ነን እንጂ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች አይደለንም፡፡»
ከዚያም ጋቭሮችን ጠራው፡፡
«አንቺ፣ ሂጅና የተላክሽበትን ፈጽሚ፡፡ የነገርኩርህን ፈጽመህ በቶሎ ተመለስ፡፡»
«መሄዱ ነው» ብሎ ጮክ ብሎ ተናገረ፡፡

ሊወጣ ሲል መለስ ብሎ «በነገራችን ላይ የሰውዬውን ጠብመንጃ ለእኔ አትሰጡኝም?» ሲል ጠየቀ፡፡ «ሙዚቀኛው ለእናንተ፣ ዋሽንቱ ግን
ለእኔ ቢሆን መልካም ነው፡፡)

ሁሉም ሳቅ አሉ ከዣቬር በስተቀር፡

ጋቭሮች ወጥቶ እንደሄደ የሆነውን አሳዛኝ ታሪክ ባይነገር ሕዝባዊ
እንቅስቃሴ በሚካሄድበት ጊዜ ምን ዓይነት ድርጊት እንደሚፈጸም አንባቢ ሊያውቅ አይችልም፡፡ ቢያውቅም እውቀቱ የተሟላ አይሆንም፡፡

ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በበረዶ ሊመሰል ይችላል፡፡ አንድ ዓይነት
እንቅስቃሴ በሚነሳበት ጊዜ ሕዝብ ከየት መጣ ሳይባል እንደ ክረምት በረዶ ይቆለላል፤ ይሰበሰባል፡፡ ሰዎቹ ከየት እንደመጡ አይጠያየቁም። ዝም
ብለው ይሰበሰባሉ፡፡ በዚህ ዓይነት ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል ከየት እንደመጣ የማይታወቅ አንድ ወዝ አደር ነበር፡፡ የለበሰው ጃኬት ከክርኑ ላይ ተቀድዷል፡፡ አጢነው ሲመለከቱት የሰካራም መልክ ነው ያለው፡፡ ይህ
ሰው አብሮአቸው ከቆሙት ሌሎች ሰዎች መካከል የሚያውቀው የለም፡፡ ከዚያ እንደቆመ ሲናገር እንደ ሰካራም ወይም ሳይሰክር አውቆ የሰከረ ለመምሰል እንደሚንተባተብ ሰው ይንተባተባል፡፡ በድንገት ወደ ዋናው አውራ ጎዳና እያየ በሰካራም አንደበት ይናገራል::

«ጓደኞች፣ ታውቃላችሁ? የመጀመሪያውን ተኩስ የምንከፍተው ከዚያች
ማዶ ከምትታይ ቤት ውስጥ ሆነን መሆን አለበት:: የመስኮቱን ጥግ ይዘን ከተኮስን በማንም አንበገርም::»

« ቤቱን እንዲከፍቱ ማንኳኳት ነዋ!»

«ቢንኳኳም አይከፍቱም::»

«እኔ አስከፍተዋለሁ» በማለት ያ ሰው ራሱ ወደ ጠቆመው ቤት
አቅጣጫ አመራ:: ከበሩ ላይ ሆኖ አንኳኳ፡፡ ቤቱ አልተከፈተም። ደግሞ በኃይል አንኳኳ፡፡ ጥቂት ቆይቶ ለሦስተኛ ጊዜ በድፍረት በኃይል አንኳኳ፡፡ አሁንም ዝምታ ሆነ፡፡

«ቤቶች! እዚህ ቤት! ሰው የለም እንዴ?» ሲል በጣም ጮክ ብሎ
ተናገረ:: የሚንኳኳ ድምፅ ወይም የሚንቀሳቀስ ፍጡር አልነበረም:: በያዘው ጠብመንጃ ሰደፍ በሩን በኃይል ቀጠቀጠው:: ከድብደባው ብዛት ቤቱ የተነቃነቀ
መሰለ፡፡ ይህ ሲሆን ከመስኮቶቹ አንደኛው በጥቂቱ ተከፈተ:: ከውስጥ የሻማ ብርሃን ታየ:: ፀጉራቸው የሸበተ ሽማግሌ ሰው አንገታቸውን ብቅ አደረጉ።

በር ደብዳቢው መደብደቡን አቆመ::

“ምን ይፈልጋሉ ጌቶች?»

«በሩን ክፈትልን» ሲል መለሰላቸው::

«ጌታዬ ፣ ይህ ሊሆን አይችልም::

«ክፈት ብያለሁ፤ በሩ ቢከፈት ይሻላል::»

«አልችልም ጌታው::»

ጨለማ ስለነበር መሣሪያውን ሲያነጣጥርባቸው አላዩትም::

«እሺ ወይስ እምቢ?
አትከፍትም?» ሲል እንደገና የቤቱን ጌታ ጠየቃቸው

«እምቢ፣ አልከፍትም» ሲሉ መለሰሉት::

«እምቢ አልክ?»

«አዎን የእኔ ጀግ…»

የሚሰጡትን መልስ ሳይጨርሱ ጠብመንጃው ተተኩሶ ግንባራቸውን ተረተረው:: ጥይቱ ከፊት ገብቶ ከኋላ በኩል ወጣ፡፡ ሰውዬው ጩኸት ሳያሰሙ መስኮቱ ላይ ተደፉ፡፡ ደማቸው ከመሬት ላይ ተንጠባጠበ:: ከመስኮቱ ላይ ሲወድቁ ሻማውን ነክተውት ኖሮ ከወለል ላይ ወድቆ መብራቱ ስለጠፋ ቤቱን ጨለማ ወረረው::

«ወንዱ» ሲል ገዳዩ ፎከረ፡፡ የጠመንጃውን አፈሙዝ ወደ መሬት እየመለሰ፡፡ ይህን ቃል ከአፉ አውጥቶ ሳይጨርስ አንድ ሰው ከኋላው መጥቶ ትከሻውን ጨምድዶ ያዘው::

«እጅ ወደ ላይ!» አለው::

ገዳዩ ፊቱን ቢያዞር ኢንጀልራስ እንደሆነ አወቀ፡፡ ጣቱን ከያዘው
ሽጉጥ ላይ አሳርፎአል:: የጠመንጃው ድምፅ ሰምቶ ነው ሲሮጥ የመጣው። ግስላ መስሎአል፡፡

«እጅ ወደ ላይ!» ሲል በድጋሚ ተናገረ፡፡

የሃያ ዓመቱ ወጣት በድንጋጤ እጁን ወደ ላይ ከዘረጋ በኋላ ከጭቃ ላይ ተንበረከከ፡ በአንድ ጊዜ ፊቱ ቀላ:: ሲደነግጡ የፈረንጅ ገላ መቅላት
የተለመደ ነው፡፡ ከዚያ የተሰበሰበው ሰው ዓይን ሁሉ ከእርሱ ላይ አረፈ፡፡
ሰው ሁሉ ዝም አለ፡፡ ገዳዩም ለመከላከል ወይም ለመናገር አልደፈረም።

ኢንጆልራስ ትከሻውን ለቅቆ ከመሬቱ ላይ በግንባሩ ደፋው፡፡

«አሳብህን ሰብስብ» አለው:: «ጸሉት ማድረስ ከፈለግህ መጸለይ ትችላለህ፡፡ ሌላም የምታስበው ነገር ካለ አስብ፡፡ ያለህ ጊዜ አንድ ደቂቃ ብቻ
ነው፡፡»

ማረኝ ይቅርታ አድርግልኝ፤ ተሳስቼአለሁ» ሲል ተንተባተበ፡፡
ከዚያም እንጀልሪስ እግር ላይ ተደፋ::

ኢንጂልራስ ዓይኑን ከወጣቱ ዓይን ላይ አላነሳም፡፡ ለአንድ ደቂቃ ጊዜ
ጠበቀው:: አንድ ደቂቃ ሲሞላ ከእግሩ ስር ይንደፋደፍ የነበረውን ሰው ፀጉር ይዞ ከጎተተው በኋላ እንደገና ወደ መሬት ወረወረው:: የያዘውን ሽጉጥ ቃታ ሳብ በማድረግ ጆሮው ላይ ለቀቀበት፡፡ ከዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ
ወደመሬት አቀረቀሩ፡፡ ሟቹ ከጭቃው ላይ ተደፋ፡፡ ኢንጆልራስ ለመሞት የሚያጣጥረውን ሰው በእግሩ ከገፈተረ በኋላ የሚክተለውን ተናገረ፡፡

«ይህን ጥምብ ከምሽግ ውጭ ወርውሩና ጣሉት::»

ሶስት ሰዎች የሚያጣጥረውን ወጣት ከመሬት አንስተው ከምሽጉ ውጭ አውራ ጎዳና ላይ ወርውረው ጣሉት::

ኢንጆልራስ በአሳብ ተመስጦ ጥቂት ከቆየ በኋላ ከአሳቡ ይነቃል፡፡ራሱን ሰብሰብ አድርጎ ጸጥታውን በንግግር አደፈረሰ፡፡

«ጓዶች›› አለ ኢንጀልራስ፧ «ይህ ሰው የፈጸመው ተግባር አስጸያፊ
ሲሆን እኔ የወሰድኩበት እርምጃ ደግሞ አስከፊ ነው:: የሰው ሕይወት ስላጠፋ ነው የገደልኩት:: ይህን ቅጣት የፈጸምኩት ተገድጄ እንጂ ወድጄ
አይደለም:: እንቅስቃሴያችን ሥርዓት እንዲኖረው ያስፈልጋል:: የሰውን ሕይወት ማጥፋት ታላቅ ወንጀል ነው:: የአብዮታችን ዓይን እንደሚያየን መርሳት የለብንም:: እኛ የሪፑብሊክ ቄሶች ነን:: ኃላፊነት ስላለብን ፍልሚያችን በማንም መታወክ የለበትም:: በዚህ ምክንያት ነው ይህ ሰው
የፍርድ ውሳኔ የተበየነበትና አስፈላጊወም እርምጃ የተወሰደበት:: ፍርዱን የበየንኩት በዚህ ሰው ብቻ ላይ ሳይሆን በራሴም ላይ የፈረድኩ ስለሆነ
ውጤቱን ወደፊት የምታዩት ይሆናል::

የመጨረሻውን አነጋገር የሰሙ ሁሉ ተሸበሩ፡፡

«በአንተ ላይ የሚደርሰውን ሁሉ እኩል እንካፈላለን» ሲል ኮምብፌራ በጩኸት ተናገረ::

«ይሁና» ሲል ኢንጀልራስ መለሰለት:: «አንድ ነገር አለ ደግሞ:: የዚህን ሰው ብያኔ በማስፈጸም የሚጠበቅብኝን ግዴታ ነው የተወጣሁት::»
የወጣቱ ነፍስ ከወጣች በኋላ ልብሱ ሲመረመር ከኪሱ ውስጥ የፖሊስ አዛዥ ካርድ ተገኘ፡፡ ይህ ሰው ቆይቶ እንደተደረሰበት ከማሪየስ ቤት መጥቶ ማሪየስ የት እንዳለ ኩርፌይራን የጠየቀው ወጣት እንደሆነ ታውቋል፡፡

ማሪየስ ከጥላው ሥር ተደበቀ
👍9