አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዶክተር_አሸብር


#አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም


ቦምብ እንዲኖረኝ እፈልግ ነበር!! እንደ እጅ ስልኬ በፈለግኩበት ሰዓት ቁልፎቹን የምጫነው…
የራሴ፣ የግሌ ቦምብ፡፡ ቦምብ ሲባል ግን ይሄ ሰባት ሰው አቁስሎ፣ ሁለት ሰው ገደለ መስተዋት ሰባበረ ግድግዳ ደረመስ የሚባለው ዓይነት ቦንብ ሳይሆን በጅምላ ፊቱን ያጠቆረብንን፣ በጅምላ
የበደለንን፣ በጅምላ የገፋንን ሕዝብ በጅምላ ድራሹን የሚያጠፉ ኒውክሌር ቦምብ።

ቡምምምምምምምምምም ሰፈራችንን የዶግ አመድ አዲሳባን ከነስሟ ድራሿን የሚያጠፋ..

ወይ አዲስ አበበ አወይ ሸገር ሆይ

ከተማ እንደጤዛ እልም ይላል ወይ

እየተባለ እስኪዘፈን ወላ ሙሾ እስኪወርድ ድረስ በቃ አዲስ አበባን ባዶ የሚያደርግ .እንጦጦን
ሳይቀር ከስሩ ነቅሎ ህንድ ውቅያኖስ የሚጥል አዲሳባ የምትባል ከተማ እዚህ ነበረች፡፡ ምክንያቱ ባልታወቀ ፍንዳታ ጠፋች” እንዲሉ ባለታሪኮች፤ ምከንያት ነጋሪ ባለታሪክ አይተርፍማ፡፡

ኒውክሌር ቦምብ እንዲኖረኝ እፈልግ ነበር፡፡ ሰዎች 'የግል ቤትና መኪና ቢኖረን ብለው
እንደሚመኙት ቦምብ ቢኖረኝ እያልኩ እመኝ ነበር፡፡ እዚሀ መሐል አዲስ አበባ ሲፈነዳ ንዝረቱ የሩሲያን የበረዶ ግግር የሚሰነጣጥቅ ካናዳ ሊታጨድ የደረሰውን የስንዴ አዝመራ
የሚያረግፍ ኒውክሌር ቦምብ፡፡
ይሄ የተመኘሁት ቦምብ ቢኖረኝ ለመጥፎ ነገር አልጠቀምበትም፡፡ እንደ ቤት ዕቃ እንደ ፍሪጅ
ቁምሳጥን በቀጥታ ወስጄ አቶ ቀሰመ ወርቅ ቤት ውስጥ መሐሉ ላይ አስቀምጠውና እንዲፈነዳ
ቁልፉን እጫነዋለሁ፡፡ ቡምምምምምምምምም ከእኛ ሰፈር ጀምሮ አፈር ነሽ ድንጋይ፣ ዛፍ ነሽ ተራራ ነሽ እየጠራረገ...ወደታች ወደ ሜክሲኮ ሕንፃውን ሁሉ አመድ እያደረገ መንገዱን ሁሉ
እየገለባበጠ ይወርድና ወደ ጦር ኃይሎች (አቶ ቀለመወርቅ እዛ ወንድም አላቸው ..ከዛ ወደ
አየር ጤና፣ ዓለም ባንክ (አዲስ ቤት እያስገነቡ ነው ተበሏል ዓለም ባንክ አካሳቢ)

በዚህ በኩል ደግሞ ከመስቀል አደባባይ አድርጎ ካዛንችስ ነሽ ሀያ ሁለት፣ መገናኛ፣ መሪ ሲኤምሲ እየጠራረገ በኮተቤ በኩል ሲቪል ሰርቪስ (እዛ የአቶ ቀለመወርቅ ትልቁ ልጃቸው ይማራል ይሄ ደነዝ ተምሮ ላይገባው የመንግሥት እህል ይፈጃል ! ፍንዳታው ወደ ቦሌ፣ ኢምፔርያል ገርጅም መሄድ አለበት በቃ !! ማነው የሚከለክለኝ የፈለግኩትን ማሰብ መብቴ ነው ማንም ሰው በሀሳሱ ቀአንድ ጀምበር ዓለምን ማጥፋት ይችላል እንኳን ይህቺን ቢጢቃ
ካላቅሟ የምትንጠራራ በውራጅ የምትንደላቀቅ አዲስ አበባን ቀርቶ፡፡

አዲስ አበባ አቅፋ ደብቃ ጠጅ እያጠጣች ጮማ አያስቆረጠች አንቱ ብላ ባኖረችው፣ ቀለመወርቅ
በሚባል ሰው በላ ጭራቅ ሽማግሌ ምክንያት አሸብር የሚባል ቂሙን የማይረሳ ጠላት አፍርታለች፡፡

እኔ ነኝ አሸብር፡፡ አዲስ አበባ አዲስነቷን ሳትወድ ተነጥቃ
'አዲስ ፍራሽ' ትሆናታለች የታባቷ !!

መብቴ ነው በሀሳቤ ሕንፃዎቿን የፍርስራሽ ክምር ማድረግ ታሪክ ማድረግ፡፡ “እዚህ ላይ እኮ
ቀልበት መንገድ ነበር” እያለ ድሮ የሚያውቃት እስኪያዝንላት(ለወሬ ነጋሪ የሚተርፍ ካለ) አመድ ማድረግ ይህቺን አመዳም፣ የሰው ፊት እያየች የምታዳላን ወረተኛ ከተማ ንፋስ ያየው ዱቄት ማድረግ፡፡ ደግሞ ከሷም ብሶ አዱ ገነት…ኡኡቴ!!

እንዲህ እያልኩ ሳስብ ነፍሴ ትረካለች ውስጤ ይረጋጋል፡፡ አዲስ አበባን የተበቀልኳት
ይመስለኛል….ደስ ይለኛለ:: በቁጣ የጋላ ሰውነቴ ይቀዘቅዛል። አዕምሮዬም ተረጋግቶ ወደ
ማሰቡ ይመለሳል፤ አበቦች አበባ ሊመስሉኝ ይጀምራሉ፡፡ አይኔም በጎ በጎውን ማየት ይጀምራል፣
ውርውር የሚለውን ሰው እና መኪና ቆንጆዎቹን ሴቶች፣ ባጠቃላይ ሕዝቡን ማየት እጀምራለሁ…ግን ሁሉንም እጠላቸዋለሁ፣ አልወዳቸውም፡፡

ጥላቻ የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡ የጥፋት ምኞት አባታችን ሆይ የዕለት ድጋሜ !! ምነው “በደፈናው ጥላቻ የሚል የእርጎ ዝንብ ሲንጋጋም አዲስ አበባን ከነሕዝቧ አልወዳትም፡፡ ደግሞ “አዲስ አዱዬ…እዱ ገነት” እያሉ ይመፃደቁላታል፡፡ ኡኡቴ አዱ ሲኦል !! የአፍሪካ ዋና ጀሀነም፣ የሰይጣን ንብረት መሰብሰቢያቸውን !!

አልወዳትም አዲሰ አበባን፡፡ አልወደውም ሕዝቡን፡፡ እንዲህ ነበር የማስበው ሁልጊዜም፡፡ ጧት
የአዲስ አበባ ቅዳሴ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ሲናኝ መስጊዶቿ በአዛን የማለዳ አየሯን ሲሞሉት፣
እናንተ ከፉ ሕዝቦች ደግሞ ነጋላችሁ፡ ለክፉት ተነሱ' የሚሉ ይመስለኝ ነበር፡፡ ማታ ሕዝቡ
በየበረንዳው ተኮልኩሎ ድራፍቱን ሲገለብጥ፣ ቢራውን ሲያጋባ ውስጡ የተከለውን ክፋት
እንዳይደርቅበት ውኃ የሚያጠጣ ይመስለኝ ነበር፡፡ ሕዝቡ ራሱ ስለራሱ ደግነት፣ ስለራሱ ቸርነት፣
ስለራሱ እንግዳ ተቀባይነትና አማኝነት ለራሱ ሲያወራ ይገርመኛል፡፡ ለእኔ የአዲስ አበባ ህዝብ ብዙ አይደለም፤ አንድ አምሳል አንድ አካል ያለው ቀለመወርቅ' የሚባል አንድ ሰው ነው !!


አሸብር ነው ስሜ ዶክተር አሽብር በአምላክ 'በአምላክ' አባቴ አይደለም፣ አያቴም አይደለም
ማን እንደሆነ አላውቅም...እናቴም አታውቅም፡፡ ልክ ለእኔ አሸብር የሚል ሰም እንደወጣልኝ

“አባት' ለሚለውም ቃል በአምላክ የሚል ስም ወጣለት፡፡ የእኔን ስም ያወጣችው ብዙ ላሞች ያሏት ክፋትን እንደ ላም የምታረባ እና ባወራች ቁጥር ከንፈሯን በአውራ ጣቷና በአመልካች ጣቷ በቄንጥ የምትጠርግ ክፉ ባልቴት ነበረች፡፡የአባቴን ስም ያወጣችልኝ ግን እናቴ ናት፡፡ እናቴ አፀደ ! አቲዬ ነው የምላት (በዚህች ምድር ላይ ስሟ ላይ ዩ፥ ጨምሬ እቆላምጬ የምጠራት ብቸኛ ሰው እኔ ልጇ አሸብር ብቻ ነበርኩ፡፡)ደ

አንደኛ ከፍል እስከመዘገብ የአባት ስም አልነበረኝም፡፡ ልክ ትምህርት ቤት አቲዬ ወስዳኝ ስመዝነብ
ጉጉት የመሰለው መዝጋቢ እናቴን እያጣደፈ ጠየቃት፡፡ ድሪቶ ቀሚሷ በዓይኑ ቀፎት እያመናጨቀ
የእኔን ስም ጠየቃት፡፡ የንቀት አስተያየቱን፣ እናቴን ዝቅ የሚያደርግ የፊቱን ገፅታ አይቼዋለሁ በዚያው ድሪቶ ቀሚስ ስር በፍርሃት ተከልዬ.አይቼዋለሁ ቅንድብና ቅንድቡ እስኪነካኩ ሲጠጋጉ እናቴ ላይ ሲኮሳተር፡፡ ለራሷ ኑሮ የገላመጣት እናቴን ሲገላምጣት አይቼዋለሁ፡፡

አቲዩ አስመዝግባኝ ከፊቱ ዞር ስትል ፊቱን ጨፍግጎ መጥፎ ጠረን እንደሚያባርር ሰው ግራ እጁ አየሩን እያራገበ ሲያባርር አይቼዋለሁ፡፡ በእርግጥ አቲዩ እማማ የብርጓል ቤት እንኩሮ እያነኮረች ነበር፡፡ “ምዝገባው ዛሬ ነው የሚያልቀው“ ሲሏት ነው ብድግ ብላ ሳትለቃለቅ የመጣችው፡፡ ቢሆንስ ልክ ቆሻሻ እንደሸተተው ሰው ፊት እንዲያየው አድርጎ እጁን ያራግባል ? የእማማ የብርጓል ቁጥር አንድ የጠላ ደንበኛ እንዳልሆነ ሁሉ፣ አሻሮ ሸተተኝ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል ? ነብር አየው !! እንኳን ይህቺን አይቼ እንዲሁም ጥላቻ ጥላቻ ይለኛል፡፡ ያንን የውሻ ልጅ አስተማሪ እንደ ጠመድኩት
ጡረታ ወጣ !! ደግሞኮ አያፍርም መንገድ ላይ ሲያገኘኝ “የእኔ ተማሪ ነው!" እያለ በኩራት ያወራል።

“ስም ” አላት አቲዬን።

“የእኔን ነው ” አለች እየፈራች። ፈሪ ነበረች እናቴ፡፡ ፈሪው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደያቅሙ ደሀ ማስፈራራትን ተክኖበታል፡፡ በትእቢት ማከላፈቱ፣ በክፋት፣ በስድብና ዘለፋው እናቴን ፈሪ
በርጋጊ እድርጓታል፡፡
👍36👏1
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ሁለት


....አሸብር ብላ ስም ያወጣችልኝ ከቤታችን በላይ ብዙ ላም የምታረባ ቅሌታም ባልቴት ናት፡፡ ሰው ከእኔ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ከአቲዬም ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ እኔ ልወለድ አቲዬ ምጥ የተያዘች ቀን የዚህች አቃጣሪ ባልቴት የአሜሪካ ላም ያልታወቀ ነገር በልታ ሆዷ
ተቆንዝሮና አረፋ ደፍቃ እየጓጎረች ነበር አሉ።

የመንደሩ ሰው ከእኔ እናት ምጥ ይልቅ የዚህች የመንደራችን ሀብታም ላም ነፍስ አስጨንቆት
አዋላጇ አልማዝ ሳትቀር ወደዛው ሂደው ነበርና አቲዩ ብቻዋን እኔን ተገላገለች፡፡ ወለደችኝ!!
የቀን ሥራ ያጠነከራት ብርቱ ሴት ባትሆን ኖሮ ሟች ነበረች፡፡ ብቻዋን ወለደችኝ !!"

አንድ የእንስሳት ሀኪም ተጠርቶ የአቃጣሪዋን ዘርፈ ላም ሆድ እስክሪብቶ በሚመስል ነገር
ወግቶ ሲያስተነፍስላትና ላሟ መጓጎሯን ስታቆም መንደርተኛው እልልታውን አቀለጠው!
እልልልልልልልልልል… አቲዬ እልልታውን ከሩቅ ሰምታለች፡፡ በዚህ መሀል አዋላጇ፡ “በሞትኩት ያቺ ሚስኪን ምን ደርሳ ይሆን?” ብላ ወደ ቤታችን ተጣደፈች። አቲዬን የተፈለቀ ወርቅ የመሰለ ወንድ ልጅ አቅፋ አገኘቻት፡፡ ያ የተፈለቀቀ ወርቅ እኔ ነበርኩ ያውም ገና በእሳት ሊፈተን የተዘጋጀ ወርቅ፡፡

ዘርፌ የሚሏት ሀብታም ባለላም የላሟን ደኅንነት ሊጠይቃት ቤቷ ሲጎርፍ የዋለውን ቅቤ አንጓች
ሁሉ ስታስተናግድ ውላ ወደ ማታ አስር እንጀራና ክክ ወጥ ይዛ ቤታችን መጣችና መንደርተኛው
በእኔ ላም በተሸበረበት ቀን ተወልዷልና አሸብር ብዬዋለሁ” አለች፡፡ አሸብር ሆኜ ቀረሁ!! ነገ አድጌ ብረብሽ! ስምን መልዓክ ያወጣዋል የሚል ሒሳብ 'መልዓክ ነኝ ልትል፡፡ እች…ስድብ የማይገልፃት…!ለ 'አንቱታ' የደረሰች ሴትዮ ናት፣ 'አንች የምላት ባትስማኝም ስንቃት ደስ ስለሚለኝ ነው፡፡
እንግዲህ አሸብር የተባልኩት አንዲት ተራ አጋሰስ..የአሜሪካ ላም ባጋበሰችው ፈስታል ታምማ
መንደርተኛውን ባሸበረችበት ቀን በመወለዴ ነው በቃ ! ደግሞ ምኔም የማያሸብር እንደወም
ቅጠል ሲንኮሻኮሽ እቲዬ አሮጌ ቀሚስ ስር የምደበቅ ፈሪ ነበርኩ ስሜን ያወጣው መልዓክ
አይደለም ዘርፌ የምትባል ቀንዳም ሰይጣን ናት!!

እኔኮ ሚያበሳጨኝ.…የዛን ጊዜ ዘመኑ ስላልሰለጠነ ነው ብዪ ውስጤ ከተመረዘበት ጥላቻ
እንዳይሽር፣ ዛሬም ድረስ ጎረቤቶቻችን ስለዛ ጊዜ ሲያወሩ ፊታቸው የተቀመጠችውን አቲዬን….ብቻዋን መውለዷን ከቁምነገር ሳይቆጥሩት ማለፋቸው ሳይበቃ፣ ከሞተች የቆየችውን የአሜሪካ ላም ደግነት፣ ባልዲ ሙሉ መታለብ ፌስታል በልታ ስታቃስት አንጀታቸው መንሰፍሰፉን
እየተቀባበሉ ማውራታቸው ነው፡፡ ደግሞ የሚንሰፈሰፍ አንጀት እንዳለው ሰው፡፡ጎማ አንጀት ሁሉ!!

አቤት ስጠላቸው! ልቤ ተሸንቁሮ የቋጠረው ፍቅር ፈሶ ያለቀበት ይመስል የተረፈኝ አፅናፍ
የለሽ ጥላቻ ብቻ ነው፡፡ ማንንም አልወድም ሁሉንም እጠላለሁ ! ዘርፌ መልዓክ ብትሆን ጥሩ ነበር
ስሜን እንድሆን፤ ይሄን ከመሬት ተነስቶ የሚሸበርና የሚያሸብር አውራና ምንዝር ጎረቤት ሁሉ እንዳሸብረው !! ወይ ነዶ ለሞላ ቦንብ ምናለ አንዲት ኒውክሌር ቦምብ ብትኖረኝ !! ለክፉ ነገር አልጠቀምባትም፣ ቀለመወርቅ ግቢ እወስድና …

አቲዩ ከገጠር ወደ አዲስ አበባ ስትገባ ገና 14 ዓመት እንኳን አሳምሮ አልሞላትም ነበር፡፡ ገጠር
የሚኖሩ ቤተሰቦቿ ምናምኒት የሌላቸው ያጡ የነጡ ድሆች ስለነበሩ በልጅነቷ ነው ልፋት
ዕጣ ፋንታዋ የሆነው ገጠር ስልችት አላት፡፡ ባል አልነበረም የስደቷ መነሻ፡፡ ያላቻ ጋብቻ
ምንትስ ብላ አልነሳረም ወደ ከተማ መኮብለሏ፡፡ የከተማ ሰው ከድህነት የሚያላቅቅ ዓመድሽን
የሚያራግፍ ደግ ነው ብለዋት እንጂ ባል ሽሽት አልነበረም፡፡

ከተሜው ያላቻ ጋብቻ እያለ የሚወተተው ሲያስመስል እኮ ነው፡፡ ለሀብት፥ በዘር፣ በእምነት
አቻ በማሳደድ ሱስ ስለተለከፈ፣ የመከፋፈልና የማግለል ንቅዘቱ ነው የሚያስለፈልፈው፡፡ ተራራ
ተሻግሮ የሚጮኸው ከተሜ ስንት የነቀዘ ባህል፣ የገማ ዓመል ጉያ ውስጥ ሸጕጧል። አሱን ብሎ የመብት ተከራካሪ፣ እሱን ብሎ ታዳጊ፡፡ ምን በወጣሽ ካለ እድሜሽ ማግባት እያለ
የገጠሯን ሴት በአዞ እንባ ሙሾ የሚያስወርድ ከተሜ በየጓዳው ከከፉ ባል ይከፋል፡፡

የልጅነት እግሮቿ ወደ አዲስ አበባ መሯት። ዘርፌ የምትባል ባለ ብዙ ላም ሴት የደሀ መንደር ከእኔ ወዲያ ሀብታም ላሳር' የምትል ክብረ ቢስ ባልቴት ላይ ሰዎች አምጥተው ጣሏት፡፡ ሴትዮዋ
ብዙ የአሜሪካ ላሞች ስለነበሯት አቲዬን በሰራተኝነት ቀጠረቻት፡፡
ገጠር ትታው የመጣችው አዛባ መዛቅና ላም ማላብ እዚህም መሀል አዲሳባ ጠበቃት፡፡ ሰው
እየመሰለው ይሮጣል እንጂ እጣ ፋንታውን በመሽሽ አያመልጠውም፡፡ እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል ብሂል ጋር ስንተላለፍ እጣ ፉንታችንም አብሮን እያለፈ ከፊታችን ይጠብቁናል፡፡ እንዲያ ነው አቲዩን የገጠማት፣ ከእርሻ ላም ወደ አሜሪካ ላም!! አዲሳባ ራሷ የአሜሪካ ላም ናት፡፡ ብዙ
ላበላት ብዙ የምትታለብ፡፡ አላቢም ታላቢም ግፍ የሞላባት፣ ውጪዋ አብረቅራቂ ቀለም የተቀባ ሰፊ በረት !!

አንዳንድ የአሜሪካ ላሞች ከሰው ልጆች የበለጠ ክብር ይሰጣቸዋል፡፡ የአሜሪካ ላም ስለሆኑ ወይም፣ ላም ብቻ ስለሆኑ አይደለም ወትት ስለሚታለቡ፡፡ ስጋቸው ስለሚበላና ሌላ የምትታለብ ላም የሚታረድ በሬ ስለሚወልዱ፡፡ ይሄ የዓለማችን የደነዘ የምጣኔ ሀብት ቀመር ነው
የበለጠ የሚታለበውን የበለጠ ተንከባከበው !! ይልኻል በአደባባይ በከራቫት በታነቀ ተወካዩ፡፡ በተወካዩ መሪነት የስግብግብነትና የከፋት ኪራላይሶ የሚደግም አህዛብ ከተሜ ይባላል፡፡

አገር ይሁን ሰው ምንም ከሌለው ምናምቴ ነው፡፡ ይገፋል ይረገጣል፡፡ ለጠብታ ነዳጅ አንድ
አገር ሰው ቢፈጅ ዓለም ጭጭ የሚለው ለፅድቅ የሚሆንን መንገድ በግፍ ለመቀየስ ነው ካለወጉ !!ሰብዓዊነት ገደል ይግባ! ብለው ሰው መሆንህን ሊክዱ የሚዳዳቸው ሁሉ፣ በዕድልም ይሁን በችሎታህ አምልጠህ ሰው ስትሆንባቸው ገደል ያስገቧትን ሰብዓዊነት ጎትተው የሚያወጡባትን
ገመድ እንድትሰጣቸው ፊትህ ቁመው ጅራታቸውን ይቆላሉ፡፡ ደግነቱ ጭራቅ ለጭራቅ እስኪበላላ አይጨካከንም የጭራቅ ሕግ አለ፣ የጭራቅ መሀላ በየወንዙ የሚማማሉት ዓይነት፡፡ እንደ አተዬ አይነት ሚስኪን ልፋት የፈጠራት እንደ አህያ ያሻቸውን የሚጭኑባት ፍጥረት የሚማማሉበት ወንዝ ዳር ከተገኘች፣ አደፈረሽብን ከማለት አይመለሱም

እንደሰው ባልቆጠሯት እናቴ ጉልበት ሰው የሆኑ ብዙዎች ሰው ብቻ እንዳልሆኑ፣ ይልቅ በጣም
ሰው እንደሆኑ ሲሰማቸው (ከጣት ጣት ይበላለጣል የሚል ተረት ሁሉ አላቸው፡፡) የአትዬ ወጣት ሰውነት ላይ አይናቸውን ያቁለጨልጩ ጀመረ፡፡ ቀለመወርቅ የሚባል ካፖርትና ክብ ኮፍያ የማይለየው ባለ ትልቅ ቤትና ባለ መኪና ሰው ነበር። እሱስ አሁንም አለ፣ እኔ ውስጥ ከሞተ ቆየ እንጂ ! በውስጤ ሚሊየን ጊዜ ገድየው፣ ሚሊየን ጊዜ ተነስቷል የክፉ ሰው ነፍስ ጣር ይበዛበታል፡፡

ሁሉም ሰው ጋሽ ቀለሙ ነው የሚለው እና ይሄ ካፖርታም ቤታም እና መኪናም አጋሰስ
👍273
#ዶክተር_አሸብር


#ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም


...አቲዩ ለስድስት ወር ከሰውነት ተራ እስከትወጣ ለባለኪዮስኳ ስትሰራ ከከረመች በኋላ ክረምት ገባ፡፡ ባላኪዮስካ አቲዬን በንስር ዓይን ስትከታተላት ነበር፡፡ ከእያንዳንዱ ቀን ጋር
እየተሽቀጓደመች ነበር፡፡ አንድ ማለዳ የአቲዬን ድሪቶ ልብሶች በፌስታል ቋጥራ ከድፍን ሃምሳ
ብር ጋር ሰጠቻትና፣ “በይ እግዜር ይከትልሽ!” ብላ ከቤቷ አስወጥታ ወረረቻት፡፡ የአቲዬ ሆድ ገፍቶ ነበር፡፡ የቀለመወርቅ ፅንስ ከውስጥ፣ የመንደሩ ሰው ከውጭ እየገፋ ሰው በሞላው አገር
እናቴን ምድረ በዳ ላይ አቆሟት፡፡

አቲዪ ስትፈጭ እና ስታነፍስ የዋለችው የምስር ክክ ብናኝ ፊቷና ፀጉሯ ላይ ተነስንሶ ነበር፡፡ ከስድስት ወር በፊት የነበረችው ልጅ እግር ቆንጆ ልጃገረድ ናት ቢባል ቀለሙ ራሱ አያምንም፡፡ መንገድ ዳር ቆመች፡፡ የክረምት ዝናብ ያካፋል፡፡ አንድ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ሱቅ በር ላይ ፍዝዝ ብላ ቆመች::ምንም እያየች ምንም ሰው፣ ምንም መኪና ምንም ቤት፡፡ ህይወት ዝም የምትልበት፣ አዕምሮ ዝም
የሚልበት፣ የሰው ልጅ ለሆነች ቅፅበት በቁሙ የሚሞትበት ቅፅበት አለ አይደል፡፡ አቲዬ በቁሟ ሞተች፡፡

አላዛርን ከሞት ያስነሳ ራሱም ከሞት የተነሳ ክርስቶስ አቲዬ! ብሎ ልክ እኔ እንደምጠራት
ጠራት፡፡ ዞር አለች ወደ ኋላዋ፡፡ ክርስቶስ ሳይሆን እንዲት ምቾት መድረሻ ያሳጣት ቆንጆ
ወጣት ነበረች … “ወደ ውስጥ ግቢ! ዝናብ መታሽ እኮ” አለቻት አቲዬን፡፡ ገና ሲያጉረመርም
እግሬ አውጭኝ ብሎ ሰው የሚሸሸው ዝናብ እንኳን፣ እንዳሻው ሰው ሳይ ይጨፍር ዘንድ ሰው በቁሙ የሚጠፋበት ቀን አለ፡፡ አቲዬ ጠፍታ ነበር፡፡

ወጣቷ ከፍ ያለ ወንበር ላይ ተቀምጣ እንፋሎቱ ወደ ላይ የሚመዘዝ ትኩስ ሻይ እየጠጣች ነበር፡፡

እቲዬ ወደ ውስተ ገባችና ኩርምት ብላ አንዱ ጥግ ቆመች፡፡ እንደ ቆመች ዝናቡ አባራ፡፡ ሰዉ
በያቅጣጫው ሩጫውን ጀመረ፡፡ አቲዪ ግን አልተንቀሳቀሰችም፡፡ የእርሷ ዝናብ አላባራም፣
መጠጊያ ላጣ ሰው የሕይወት ዶፍ አባርቶ አያውቅም፡፡ ሰው የፍቅር ዣንጥላ፣ የዝምድና ዣንጥላ፤
የጓደኝነት ዣንጥላ፣ የትዳር ዣንጥላ፣ የእውቀት ዣንጥላ፣ የስራ ዣንተላ፣ የተስፋ ዣንጥላ፣
የእምነት ዣንጥላ ይዞ ስለሚኖር እንጂ ከሕይወት ሰማይ ላይ ነፍስን የሚያበሰብስ መንፈስን
እንደ ወረቀት የሚያላሽቅ የብቸኝነት እና የተስፋ መቁረጥ ዝናብ አባርቶ አያውቅም፡፡

የአቲዬ ዝናብ አላባራም፡፡ ይሄን ሁኑ የነፍስ ዣንጥላ ጨካኝ ንፋስ ከእጇ ነጥቋታል፡፡ ንፋሱ
ቀሚሷን በግድ ገልቦ ውስጧ ቅዝቃዜ አስቀምጧል፡፡ ንፋሱ የሕይወት አቧራ አንስቶ ፊቷና
ፀጉሯን አልብሷል።ንፋሱ የተስፋ ጎጆዋን አፈራርሶ እዚህ አቁሟታል፡፡ አቲዬ የእኔ እናት
መሄጃ የላትም።

ቁልፎች ታንኳኩ፡፡ ቆንጆዋ ልጅ ጃኬቷን ደረበች፡፡ ውጭ የተደረደሩ እቃዎችን አስገባች፤ እናም ቁልፏን በሚያማምሩ ጣቶቿ እንዳንጠለጠሰች አቲዩን ግራ በመጋባት አየቻት፣ “
ውጪ!' ማለት ብልግና ነው፡፡ ቀድሞ ወጥቶ፣ ውጪ ጋር መቆም ግን ያው ውጪ ማለት ነው፡፡

አትዬ ዝናብ እስከያባራ ከተጠለለችበት ሱቅ በቀስታ እርምጃ ወጣችና በረንዳው ላይ ቆመች፤ባለሱቋ ቆንጆ ሴት ሱቋን ቆላለፈች፡፡ የአቲዩ ነገር ሳያሳዝናት አልቀረም፣ እ..ምን ሆነሽ ነው
እናትዬ?አለቻት፡፡ እቲዬ ዝም፡፡ ዓይኗ እንባ አቅርሮ ዝም…ወደ ሞቀ ቤቷ አልያም ወደ ቀጠራት ፍቅረኛዋ ልትሄድ ያኮበኮበች ወጣት የአቲዬን የአርባ ቀን ዕጣ ከየት ጀምሮ ቢነገራት ይገባታል? አቲዪ ዝም አለች፡፡ አልለመደባትም እንዲህ ሆንኩ ብሎ ማውራት፣ አልለመደባትም ምሬት መዘብዘብ ልማዷ አይደለም።

ወጣቷ ጥቂት ብሮች ከቦርሳዋ አውጥታ ለአቲዬ ዘረጋችላትና “አይዞሽ! ይሄን ያዥ በቃ” አለቻት።
አተዬ ግን አማትባ ከተዘረጋው የወጣቷ እጅ በድንጋጤ አፈገፈገች፡፡ ልክ ጩቢ እንደተሳነዘረበት ሰው ነበር የበረገገችው፡፡ ለማኝ ልሆን?” ብላ በውስጧ አሰበች፡፡ እንባዋን እያዘራች ሽቅብ እግሯን ተከትላ ትጓዝ ጀመር፡፡

የትም የማያደርሱ የሚመስሉ እርምጃዎች አንዳንዴ አዕምሮ አስቦ ከሚደርስበት የተሻለ መፍትሄ ላይ ይደርሳሉ። ሰዎች የፈጣሪ መንገድ ይሏቸዋል፡፡ አቲዬ ዝም ብላ ብዙ ርቀት ተጓዘች። መታጠፊያ ስታገኝ እየታጠፈች፣ መንገድ ስታገኝ እየተሻገረች ዝም ብላ ወደፊት፡፡ ከዕጣ ፋንታዋ ትሸሽ ይመስል መንገዱ ባያልቅ ብላ ተመኘች፡፡ በቃ እስካዓለም ጥግ ዝም ብሎ ቀሪ እድሜዋን መጓዝ ::

ቀጥ ብላ ተመለከተች። ፀጥ ያለ ቤተከርስቲያን ከነታላቅ ጉልላቱ ፊት ፊቷ መንገዱን ተሻግሮ
ይታያል፡፡ የልብስ ፌስታሏን አንጠልጥላ አሮጌ ሃምሳ ብሯን በእጇ እንደጨበጠች፣ ዓለምን
መዳፉ የጨበጠ እግዚአብሔር ጋር የተፋጠጠች መሰላት፡፡
በዚህ ሁሉ በደል የዚህ ሁሉ ግፍና ስቃይ ጠንሳሽ እግዚኣብሔርን ፊትለፊት ያገኘችው መሰላት፡፡
እግዚአብሔር አይቷት ሳያፈገፍግ፣ የበደላት ሁሉ አሳፍሮት ሳይሸሽ በፊት ልትደርስበት መንገዱን
አቋርጣ ወደ ቤተክርስቲያኑ ገሰገሰች፡፡

እግዜር ፈርቷት እግሬ አውጭኝ የሚል መሰላት አቲዬ፡፡ መኪናዎች አምባረቁ፣ ሹፌሮች መኪናቸው መስኮት ብቅ ብለው ፀያፍ ስድብ ወረወሩባት። አንበሳ ጋር ልትፋለም ታላቁን ፈጣሪ 'በላ ልበልሃ' ልትለው በድፍረት የምትገሰግስ ጀግና በውሻዎች ጩኸት የምትበረግግ መስሏቸው።
አቲዬ ቤተክርስቲያኑ በር ላይ ደረሰች፡፡ እግዜር ያኔ ለያት፡፡ ከሰማየ ሰማያት ዙፋኑ ላይ
እንደተቀመጠ ድምፅ ከወደ ምድር ሰማ፡፡ ቅዱስ ቅዱስ” እያሉ በታላቅ ድምፅ የሚሰግዱና
የሚያሸበሽቡ እልፍ አእላፍ መላክትን “ዝም በሉ አንድ ለየት ያለ ድምፅ ከምድር ሰምቻለሁ” አለ፡፡
“ጌታ ሆይ ሞልቃቆች በስሱ እያማተቡ መኪናቸው ውስጥ ሆነው ሽው የሚሉት አይነት ድምፅ ይሆናል" አሉት መላዕክቱ፡፡

“አይደለም” አለ እግዚአብሔር፡፡

"የኮተታሞች የኮተት ጥያቄ ይሆናል" አሉት በምድራዊ ትርኪምርኪ የስጋ ጥያቄ የተማረሩት መላዕክት፡፡

"አይደለም አልኩ እኮ” አለ እግዚአብሔር በታላቅ ድምፅ፡፡

“ጌታ ሆይ! ምናልባት የሀብታሞች ከስኳር፣ ከደም ግፊት ከፈወስከኝ መጋረጃ ዣንጥላ የሚሉት
አይነት የተለመደው ስእለት ይሆን” ጠየቁ መላዕክቱ፡፡

ዝም አለ እግዚአብሐር !! ዝምታው አንዳች አስፈሪ ነገር አለው፡፡ በዝምታው ውስጥ ፅንፍ
የለሽ ሀዘንና ፍቅር ነበር።

ከልጅ ስጠኝ ንዝንዝ፣ ከስራ ስጠኝ ንትርክም የተለየ ድምፅ ነበር፡፡ ድምፄ ካማረልኝ ብላ
የምትዘምር ሴትም አልነበረችም፡፡ ከታላቅ ግርማ ሞገስ በእሳት ሰረገላ ደርሰህ ጠላቴን አፈር
ድሜ የምታስበላ የነገስታት ንጉስ፡፡ ከፀሐይ አስራ ዘጠኝ እጅ የምታበራ እያለች በተጠና
መንፈሳዊ ፉከራ መንፈሳዊ ዘራፍ የምታደነቁር ሴትም አልነበረችም፡፡ ከታሰበረ ልቧ በወጣ ማቃተት ዙፋኑን የነቃነቀችው እዚህ ግቢ የማትባል ሴት ናት፡፡ አንዲት ሴት በሩ ላይ ስትቆም፣
“ማነው የልብሴን ጫፍ በዕምነት የነካው” ብሏል እግዚአብሔር!

አቲዩ የእኔ ጀግና ማንንም ደጅ አልጠናቸም፡፡ በልብሷ መቆሸሽ ይናቋት እንጂ የእኔ እናት
ከአዲስ አበባ የሕዝብ ጎርፍ ቁራሽ አልለመነችም፡፡ ለማን ስሞታ እንደምትናገር አውቃለች፡፡
አጥሩን በድንጋይ ቢያጥር፣ ባማረ መኪና ቢንፈላሰሰ፣ ሴቱ በወርቅ ሽቆጠቆጥ..የአዲስ አበባ
ሰውና አቲዬ ልብ ለልብ ተነቃቅተዋል፡፡

አይታዋለች ሕዝቡን የህሊናውን ዓይን ጨፍና ጎዳና የፈሰሱትን የራሱን ጉዶች እንቁልልጭ እያለ
በየስጋ ቤቱ በረንዳ ላይ ጥሬ ስጋውን ሲያጋብስ፣ ቢራና ውስኪውን ሲገለብጥ አይታዋለች፡፡
👍271👏1
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አራት


እትዬ ያረፈችባቸው መነኩሲት “የኔ ልጅ አይዞሽ የበላነውን እየበላሽ ልብሽ እስከፈቀደው ጊዜ መቆየት
ችያለሽ የእግዜር ቤት ነው ቤትሽ ነው” አሉና ድርብ የሰሌን ምንጣፍ ብዙ ቦታ ላይ ብዙ ዓይነት ክርና መጣፈያ ከተጠቀመ ብርድ ልብስ ሰጧትና አንዷ ጥግ ላይ ራሳቸው አነጣጠፉላት፡፡

አለም ላይ ጭካኔ ሲፈነጭ ማን አለብኝነት በሀሴት ዋንጫ ልቅለቃውን ሲያስነካው፡ ሰብዓዊነት መቃብር ቤት ውስጥ በፍፁም ፀጥታ ከአትዬ ጋር ተገናኘ፡፡ አትዬ ከደጓ መነኩሴት ጋር በመቃብር ቤት ውስጥ ተቀመጠች፡፡ ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል ቢባልም ቅሉ ኑሮው አልሞቃትም፡፡አጥንቷ ድረስ ዘልቆ የሚያንዘፈዝፍ የፍርሀት ብርድ ሰላም ነሳት፡፡ መሄጃ የለኝም ከሚል ስጋት ለጊዜውም ቢሆን አርፋለች፡፡ ግን መቃብር ቤቱ ውሰጥ የነበራት ቆይታ የስቃይና ዮፍርሀት ነበር፡፡ሰው የተቀበረበት ቤት ውስጥ መተኛቷ ፍርሃት ለቀቀባት፡፡ ከተኛችበት ሰሌን ስር በስብሶ አፅሙ የቀረ ሬሳ ታኝቷል፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሰማችው (አሁንም ድረስ እንደምታምነው ደግሞ ሙታን አካላቸው ቢጋደምም መንፈሳቸው አርፎ አይቀመጥም፡፡ መነኩሲቷ ወጣ ካሉ ተከትላ ደጅ ትቆማለች፡፡ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርጋት አንድ ስጋው ሁሉ ረግፎ ጭራሮ የመሰሉ ጣቶቹ ብቻ የቀሩ አጥንታም እጅ የተኛችበትን መሬት ፈነቃቅሎ አንገቷን ሲያንቃት ይታያትና ኡኡታዋን ታቅልጠዋለች…ቅዠት! መነኩሲቷ አቲዬን ማረጋጋት ለአቲዬ መፀለይ ብቻ ሆነ ስራቸው::

በፍርሀት ሁለት ቀንና ሌሊት እንቅልፍ ስላልወሰዳት በሦስተኛው ቀን ምሽት እንቅልፍ እሰካራትና ሰሌኗ ላይ ኩርምት ብላ ተኛች ዓለም ገፍቶ ገፍቶ የመገነዣ ሰሌኗ ላይ የጣላት ሚስኪን ሴት፧ መነኩሲቷ በሀዘን ግንባሯን እንደ ትንሽ ልጅ እያሻሹና አተነፋፈሷ የተስተካከለ መሆኑን እያዳመጡ እንደ መልካም ወላጅ ቀስ ብለው ድራቡን አልብሰዋት ወደ ፀሎታቸው ተመለሱ::

ብዙ ሳይቆይ ትንሸዋ የመቃብር ቤት በአስደንጋጭ ጩኸት ተሞላች፡፡ እቲዬ ልጄን..ልጄን
እያለች አንደ እብድ ከመኝታዋ በርግጋ በመነሳት ራሷን ይዛ መጮህ ጀመረች፡፡ አቅመ ደካማዋ መነኩሲት አቲዬን ሊያስቆሟት አልቻሉም፡፡ የሷ ባልሆነ ጉልበት ገፈታትራቸው በሚገርም ፍጥነት ሰሌኑን ጠቅልላ የቤቱን ወለል በጥፍሯ ትቧጥጥ ጀመረች፣ "ልጄ.....ልጄን ወሰዱብኝ” እያላች በመረጋጥ ብዛት የደደረውን አፈር ትመነጭር ጀመረ፡፡

እንባዋ በጉንጮቿ ሳይ ለጉድ እየፈሰሰ፣ በላብ ተነክራ እየቃተተች ከትንንሾቹ መቃብር ቤቶች
ጩኸቷን ሰምተው የወጡ መነኮሳት ወደ እማሆይ ቤት መጥተው ተረባርበው እስኪያስቆሟት ድረስ አቲዬ በአስሩም ጥፍሯ መሬቱን እየቧጠጠችና እየቆፈረች ኡኡታዋን ማቅለጥ አላቆመችም
ነበር፡፡

ክፉ ቅዠት የዘወትር ቅዠቷ የሆነው ጭራሮ እጅ ዛሬም ከፈነቀለው መቃብር ውስጥ እጁን
ብቻ ሳይሆን ከትከሻው በላይ ነበር ተመዝዞ የወጣው አፈር እንደለበሰ…!! ከዛም በአስፈሪ
ዓይኖቹ እቲዩ ላይ አፈጠጠባት፤ አየችው ቀለመወርቅ ነበር፡፡ ያውም አፈር ከነሰነሰ ባርኔጣና
ካፖርታው !! "ልጄን አምጪ” ብሎ አጥንታም እጁን ወደ ሆዷ ላከና በቅፅበት አንድ ቀይ የሚያምር ሕፃን ይዞ ተመለሰ፡፡ ሆዷ ባዶ ሲሆን ታያት፤ ቀለላት፡፡ ልጇን በደስታ ትመለከተውና ወደ ውስጥ ወደ መሬት ይዞት ሰረገ፡፡ ልክ ጫጩት ነጥቆ ወደ ጉድጓዱ እንደሚገባ ሸለምጥማጥ'
መሬቱን ከፍቶ ሲገባ፣ መጋረጃ ገልጦ የገባ ነበር የሚመስለው፡፡

በቀጣዩ ቀን አባ እስጢፋኖስ ሁኔታው ሲነገራቸው ድሮም ለአቲዬ ቋሚ መኖሪያ ሲያፈላልጉ ነበርና ፍለጋውን አፋጥነው ከሁለት ቀን በኋላ በፊት ትኖርበት ወደ ነበረው መንደር ወስደው አንዲት ከዋናው የቀበሌ አጥር ጋር ተያይዛ የተሰራች የቆርቆሮ ቤት ውስጥ አስገቧት፡፡ የመንደሩ እድር እቃ ማስቀመጫ ነበረች፡፡ የእቃ ማስቀመጫዋ ቤት ጣራና ግድግዳዋ በድንብ ስላልገጠመ፣ ሌሊት ብርዱ ቀን ፀሐዩ በክፍተቱ ውስጥ እያለፈ ይገባ ነበር፡፡ አባ እስጢፋኖስ ከንሰሀ ልጆቻቸው ለምነውም ተለማምጠውም ያገኟቸውን አሮጌ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስና የውሀ መያዣ ጎማ ለእቲዬ እያሳዩ እንደምታውቂው ቤሳ ቤስቲን የሌላኝ የእግዚሃር አገልጋይ ነኝ፡፡ ከዚህ የተሻለ ባይሆን ጎንሽን ማሳረፊያ ካገኘሽ ሌላው ሌላው በፈጣሪ ፈቃድ ቀስ እያለ ይሟላል እኔም እየመጣሁ አይሻለሁ።" ብለዋት ሄዱ።

የእድሩ ድንኳን፡ እንጨቶች፣ ወንበሮችና ስጋጃ ምንጣፎች በአንድ በኩል ተሰድረው ገባ ብሎ ወደ ውስጥ ካለችው ትርፍ ቦታ ላይ ደግሞ የአቲዬ ፍራሽ ተዘርግታለች፡፡ ብዙ ጊዜ ሞት ወይም መርዶ ሰለሚኖር የእድሩ እቃ አይኖርም፡፡ ስለዚህ ሰፋ ትላለች ቤቷ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ
እድርተኛው እቃውን ሲመልስ በግዴለሽነት ወንበሩን፣ እንጨቱን ከባባዶቹን ምንጣፎች አቲዩ
መኝታ ላይ ጥለውት ይሄዱ ስለነበር ያንን ሁሉ ጓዝ ጎትቶ ቦታ ማስያዙ ለአንዲቷ ነፍሰ ጡር ሴት ፈተና ነበር።

አትዬ ግን ታደርገዋለች፣ እንዲህ አታድርጉ” አትል ነገር ሆሆ ወደዛ ውጪ ቢሏትስ፡፡

አባ እስጢፋኖስ ብዙ ቤት ሊያስቀጥሯት ደክመው ነበር፡፡ ይሁንና ቀጣሪዎቹ ነፍሰ ጡር
መሆኗን ሲሰሙ ሁሉም አቲዬን ቤታቸው ማስገባት አልፈለጉም፡፡ አባ ቢጨንቃቸው የአቲዬ ነገር
ሰላም ቢነሳቸው አቲዩን ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረገቻት ዘርፈ ቤት ሳይቀር ሄዱና፣ እችን ደሀ ይቅር በያት ባክሽ ብለው ታማፀኑ፡፡

አይይይይ አባ ምነው እያወቁት… እንደ ልጆቼ አንከብካቤ በያዘኩ አይደለም እንዴ ጥጋብ ፈንቅሏት ለመንደሩ ሁሉ ስሜን አጥፍታው የሄደች” አለች አቃጣሪዋ፡፡ አባን በአፍ መሸንገል
እግዜርን መሸንገል ይመስል የአቲዬን በደለኝነት ስትዘረዝር ደስ እያላት ነበር፡፡

ልጅ አይደለችም እንደ ወለተማሪያም ደግሞስ አንች ቤት ከመቼ ወዲህ ነው ይቅርታ የነጠፈው ተይ እንጂ” አሉ አባ፡፡

በዛብኛ አባ በዛብኝ ...ምን በደልኩ እናት በሆንኳት…የበላሁትን ባበላሁ የለበስኩትን ባለበስኩ ሰው ሁኝ፣ ሰልጥኝ!' ባልኩ ይሄ ይገባኝ ነበር እንባ እየተናነቃት አባ ፊት በደሏን ዘረዘረች እች አስመሳይ!!

ይሄው የትም ስትንዘላዘል ዲቃላዋን ይዛ አረፈችው” አለች ዘርፌ፡፡ ከእኔ የተጣላ እጣ ፋንታው
ውድቀት ነው" ልትል እየዳዳት…፡፡

አባ እንደሆኑ የአቲዬን ነፍስ መታደግ ይቅደም ብለው እንጂ የቀለመወርቅንና የዘርፌን ሴራ ውስጣቸው ያውቀዋል፡፡ አንዳንዴ የእግዜር አገልጋይ ከመሆን ሽፍታ በሆንኩ፡ ነፍስ ገዳይ በሆንኩ የሚያስብሉ እንደ ዘርፌ ዓይነት ገርፈው የሚጮኹ ጅራፎች ሲያጋጥሙ የንስሀ አባቶች
ልብ ምን ያህል ይሰበር ይሆን? ቢቻል ጥምጣምና መስቀልን ላንዴ አስቀምጦ ምንሽር መታጠቅና እንዲህ አይነቶቹን እድሜ ጠገብ እባቦች ግንባር ግንባራቸውን ማለት ነበር፡፡

ዘርፈ hዚህ ሀሉ ፉከራና ማስመሰል በኋላ እቲዬን ቤቷ እንደማትመልሳትና ከፈለገች ተመላልሳ ላሞቹን የመንከባከብ ልብስ የማጠብ ስራ እንድትሰራ በወር 10 ብር ልትከፍላት ለአባ ቃል ገባች፡፡

“ያው ለነፍሴ ብዬ እንጂ የደረሰች እርጉዝ ምኗ እለቻቸው ሰእባ፡፡

“ግዴለም ወለተማሪያም መቼስ ሰው እንዳረገዘ አይኖር ሁሉ ነገር ሲወለድ ጊዜ አለው፡፡ ደግሜ ይሁን ክፉ ተረግዞ አይቀርም፣ ነገን ነው ማየት” አሉ አባ፡፡ የቄስ ምንሽሩ ቅኔ ነው ተኮሱባት
አባ!

የቅኔ ጥይት ከተኳሹ እስከ ኢላማው ለመድረስ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ለዛ ነው ዘርፈ አባ እግር ስር ድፍት ያላለችው ይድፋትና!! አባ እውነት ነበራቸው፣ እንደ ተረገዘ የሚኖር በደል የለም ይወለዳል አንድ ቀን፡፡
👍23🥰1
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አምስት


...እኔ የተወለድኩ ቀን ጠዋት አቲዬ አቃጣሪዋ ዘርፌ ቤት ወተት ስታልብ ነበር፡፡ ረፋዱ ላይ
የአንዲት ጎረቤት በርበሬ ስትቀነጥስ ዋለች፡፡ ውጋት ሲጀምራትና ምጡ ሲጫናት ከበርበሬ ቅንጠሳው በኋላ ልብስ ወደምታጥብበት ቤት ለመሄድ እየተዘጋጀች ነበር፡፡ ህመሙ ሲጀምራት ግን መንገዷን ቀይራ ወደ መንደር አዋላጅ አልማዝ ቤት ሄዳ እየፈራች፣ “እትዬ አልማዝ
እያመመኝ ነው፡: ምጥ ነው መሰለኝ…" አለቻት፡፡

“ውይ በሞትኩት መጣሁ ሂጂና ቤትሽ አረፍ በይ…" አለቻት፡፡

አቲዬ እንደታዘዘችው አደረገች፡፡ እዛች እሮጌ ፍራሽ ላይ ተኝታ ምጥ እየናጣት በር በሩን ማየት
ጀመረች፡፡ አልማዝ ግን ወደ አቲዬ አልሄደችላትም፡፡ ምክንያቱም እቲቲዬ ምጥ የተያዘች ቀን፣
ዘርፌ የምትባለዋ አቃጣሪ ባልቴት የአሜሪካ ላሟ ያልታወቀ ነገር በልታ ሆዷ ተቆዝሮና አረፋ
ደፍቃ እየጓጎረች ስለነበር፣ መንደርተኛው ሁሉ ወደዚያው ሄዶ ነበር፡፡ አዋላጇ ኣልማዝም
ቅድሚያ ለወርፌ ላም ሰጥታ ነበር፡፡

አንድ ግብርና የሚሰራ የእንስሳት ህክምና ባለሙያ ተጠርቶ እስከሪብቶ በሚመስል ነገር የላሟን ሆድ ወግቶ ካስተነፈሳት በኋላ ላሟ ነፍሷ መለስ በማለቱ የመንደሩ ሰው ደስታውን በእልልታ
ገለፀ፡፡

በዚህ መሐል እዋላጇ አልማዝ፣ “በሞትኩት ያች ሚስኪን ምን ደርሳ ይሆን?” ብላ ወደ ቤታችን
ተጣድፋ ብትደርስ አቲዩ እኔን አቅፋ አገኘቻት፡፡ የወርቅ ፍልቃቂ የመሰልኩ እኔ፣ በእሳት የተፈትንኩና የጥላቻ እሳት የምትፋ እኔ፣ አላፊ አግዳሚውን የምራገም እኔ በእናቴ እቅፍ ላይ ታሪክ ይወቀኝም አይወቀኝም፣ እናት የተባለች ታላቅ ሀገር ከስግብግብ፣ ከአስመሳይ፣ ከራስ
ወዳድ፣ ከአሽቃባጭ፣ ደሀ ከማይወድ፣ እምነት ከሌለው፣ ሆድ አምላኩ ከሆነ አመንዝራ እና
ጨካኝ ጎረቤት ቅኝ ግዛት የወጣሁ ጀግና እኔ ተወለድኩ !! አገሬ እናቴ አፀደ ናት ! ባንዲራዬም
የእናቴ ቀለም አልባ አሮጌ ቀሚስ !! ድምጿ መዝሙሬ ነው፣ ትዕዛዟ ሕገ መንግስቴ !! እናቴ
አፀደ ወይንም ሞት!! አቲዬ ትቅደም !! አቲዬ ለዘላለም ትኑር!

መዝመሬ፣

ተንቀሽ የኖርሽው ድሮ ከዚህ ቀደም፧
እናቴ አፀደ የደፈረሽ ይውደም !!

በሰሜን ስግብግብ የደሀ ደም መጣጭ ጎረቤቶች፣ በደቡብ ራስ ወዳድ በድሀ እምባ የሚዋኙ
እጋሰሶች፣ በምስራቅ የእናቴን ፀሐይ እንዳትወጣ የሚጋርዱ አስመሳይና ሆዳሞች፤ በምዕራብ
ሚስኪን ሴት ደፋሪዎች እና ትውልድ የሚነዱ ካፖርታሞች…፡፡ ከታች በባዶ እግሯ የምትረግጠው
ምድር፣ ከላይ እግዚአብሔር (የባህር በሯን የሚያዋስናት ሀገር አፀደ ትባላለች - የእኔ አገር እሷ
ናት !!

አፀደ ከሰማይ ዱብ እንዳለ ጉድ ዘመድ የላትም፡፡ እናት፣ አባት፣ አክስት፣ አጎት የላትም፡፡
አልተማረችም ገንዘብም የላትም፡፡ ግን ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ለሆነ ባለፅጋ አግዚያብሔር እንብና ድፍን የኢትዮጲያ ሃምሳ ብር ያበደረች ልበ ሙሉ ሴት ናት፡፡ እግዚያብሔርም የማንም
ብድር በእጁ ይቆይ ዘንድ አይወድምና ብድሩን ይከፍል ዘንድ እኔን መንገድ አደረገ፡፡ በድፍን ሀያ አምስት ዓመታትም አነፀኝ ደለደለኝ።

እግዚኣብሔር ፈጠነም ዘገየም ወደ እያንዳንዱ ሰው ሕይወት ውስጥ ይመጣል፡፡ ሲመጣ የእግዜርን እርምጃ የእግሩንም ዳና የሚቋቋም መንገድ የሚሰራው መከራ በሚባል ኮንክሪት ነው :: ዙሪያህን የከበበህን ችግርና እልህ አስጨራሽ የሕይወት ፈተና ስታልፍ፣ የእግዜር የመጀመሪያ
እርምጃ ትጀምራለች፡፡ ያኔ ታዲያ ርሀብን ብቻ ሳይሆን ጥጋብንም የምትችል አድርጎ እንዳነፀህ ይገበሀል።

አሰራሩ እንደዛ ነው፤ ሳይሆንም እኔ እንደዛ ነው እላለሁ፡፡ አንተን ከድህነት ማውጣት ብቻ ሳይሆን መጭውን የጥጋብ ዘመንም የሚሸከም ትከሻ እንዲኖርህ አድርጎ ይሰራሀል ካለመንክ
እንደ የዕምነትህ መጽሀፍህን ግለጥ፣ አዱኒያን እንደ ምናምንቴ ንቀው ፈጣሪን ያመኑ፣ የተከተሉ
ሁሉ ሰፈርህ ሕንፃ አቁሞ እንደሚሸልለው እብሪተኛ ሃብታም ባንዴ ሰማይ ጥግ አልደረሱም፡፡

ፈጣሪ ሲሰራህ ቀስ ብሎ ነው፣ ግን መቼም እንዳትፈርስ አድርጎ፡፡ ያኔ ደስ ይልሃል ወደህ ነው ጎንበስ ብለህ ታመሰግናለህ በግድህ አንተ ላለማመስገን ብትጥር እንኳን ስጋህ ያማረ ፍራሸ ላይ ለሽ ሲል፣ በርሀብ የተንሰፈሰፈ አንጀትሀ ውስጥ የጣመ ምግብ ሲጎዘጎዝ፣ በላዩ ላይ ጥሩ ቡና ስትጨምርበት፣ ከምንም በላይ ደግሞ ራስህን ስትገዛና ልብህ በሰላም ሲሞላ፣ እግሲያብሔር ይመስገን ይልሀል አፍህ ከአንተ ትዕዛዝ ውጭ!!

አቲዬ እኔን ከወለደች በኋላ ትንሽ ተስፋ ልቧ ውስጥ አደረ፡፡ አባቱ በልጁ አይጨክንም መቼም
ብላ፡፡ ግን አባት በልጁ ጨከነ፡፡ ቀለመ ወርቅ አባት የመሆን ሞራሉም ብቃቱም የሌለው
ሴሰኛ ሽማግሌ መሆኑን የአቲዬ ልብ ያወቀው ብዙ ቆይቶ ነበር፡፡ ወንዶች ለአገር ዳር ድንበር
እየፎከሩና እየሸለሉ የመዝመታቸውን ያህል አባትነትን ለመቀበል፣ ትዳርንም አሜን! ብሎ
ለመኖር፣ ከነፍሳቸው ጋር የሚገጥሙት ጦርነት ቀላል አይደለም፡፡ ለመውለድ ወንድ መሆን በቂ ነው፡አባት መሆን ግን ታላቅ ጀግንነትን ይጠይቃል፡፡ ቀለመወርቅ ደግሞ ጀግና አልነበረም፡፡ስለዚህ እኔን ልጁን ዶሮ ሳይጮህ ሦስቴ ካደኝ፡፡

አቲዬ የእኔ ብርቱ ግን በሰባት ቀኗ ከአራስ ቤቷ ተነስታ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ስራዋን
ጀመረች፡፡ “ኧረ ወገብሽ ይጥና” ያላት አልነበረም፡፡ የበሰበሰ ድሪቷቸውን ከምረው ጠበቋት
እንጂ ! 'የምትገርሚ ጠንካራ ልጅ እያሉ ፡፡ እርሳ ቐን ሙሉ አርባ ቀን ሙሉ ተዘፍዝፈው ሊጣቸውን ሲያሻምዱ ኑረው ሲወጡ እንኳን አራስነት ምን ያህል ከባድ መሆኑን እንደማያውቁ ሁሉ፥ አቲዩን በሥራ
ሲያጣድፏት ምንም አልከበዳቸው፡፡

ልጅ ይዛ ሥራ መሥራት ከባድ ነበር ለአቲዬ:: በየቤቱ በረንዳ ላይ እያስተኛች ሳለቅስባት እያጠባችኝ(ምናባቴ እንደሚያስለቅሰኝ እንጃ !)፡፡ አቲዬ እናቴ ብርቱ ሰው ከህይወት ጋር ትግሏን ቀጠለች.…አንድ.. ሁለት..ሦስት...አራት ወር ለአቃጣሪዋ ዘርፌ አቲዬ እየፈራች እንዲህ አለቻት፡

“አትዬ እኔ እንግዲህ እስካሁን ለልጁ አንድ ነገር ያደርጋሉ ብዩ ጠበቅኳቸው እሳቸው ግን
“ማናቸው ልጄ አለች ዘርፈ አካሄዱ አላምር ብሏት ፊቷን አጨፍግጋ፡፡

“ጋሽ ቀለመወርቅ" አለች አቲዬ፡፡

"እህ…ደም እሱ ምን ቤት ነው ባንች ልጅ”

"እትዬ ፈርቼ አልነገርኮትም እንጂ፣ እኔ ሌላም ወንድ ነክቶኝ አያውቅ ተሳቸው ነው :"

“ወዲያ ዝም በይ…ምን ትላለች
እቺ..የተከበረ ሰው አናት ዘሎ ፊጥ ማለት ምን ይሉት ብልግና
ነው?! ሁላተኛ እንዲህ ያለ ነውር ስትተነፍሽ ብሰማ ውርድ ከራሴ፡፡ ሂጂ አሁን ወዲያ ያው
ደሞዝሽ!"

ብላ አስር ብር ወረወረችላት፡፡ ስራዋ አስደንግጧት እንጂ ሳምንት ነው ገና ደሞዝ ለእቲ ከከፈለቻት፡፡

ቀለመወርቅ ይህችን ጭምጭምታ ሲሰማ ተንኮሉን ጀመረው:: አቲዬን ከመንደሩ ሊነቅል እንቅልፍ አጣ፡፡ አቲዬ ለአባ እስጢፋኖስ ሽምግልና ላከችበት፡፡

“ቀለመወርቅ መቼስ ዘር አይጣላም፡፡ ነገ የት እንደሚደርስ አንድ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው፡፡
ሌላው ቢቀር የወተት መግዣ እንኳን ስጣት መቼስ እሷ ጋር እንዲህ ሠራህ፣ እንዲህ አደረግክ
ለማለት ባልደፍርም ልጁ ቆርጠው የጣሉት አንትን ነው…”
👍311
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ስድስት


አቲዬ ለመርገጥ የሚያስፈራው የወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ ውስጥ አንዲት ቆንጆ ሠርቪስ ቤት
ተሰጠቻት፡፡ ያውም ከነሙሉ ዕቃው፡፡

“ማነው ስምሽ እናቱ?” አለቻት አቲዩን ወይዘሮ እጥፍወርቅ፡፡

“አፀደ"

"ውይ የኔ ድንቡሽቡሽ! ስንት ወሩ ነው” አለች እኔን እያያች፡፡

“አሁን የፊታችን ገብሬል መንፈቅ ይሞላዋል" እጇን ወደኔ ዘረጋች። ፈገግ ብዬ እጇን ለቀም፡፡ ሕፃናትን
መለይካው ይመራቸዋል የሚባለው እውነት ሳይሆን አይቀርም። ወይም ሴትዬዋ እጅ ላይ የተገጠገጠው የወርቅ ቀለበትና ጌጣጌጥ መጫወቻ መስሎኝ:: ወይዘሮ እጥፍወርቅ አቲዬን እንዲህ አለቻት፤

“ላንችና ለልጅሽ ሆድ አታስቢ.! እዚህ ተርፎ ለሚደፉ እህል የበላነውን ትበያለሽ፡፡ ብትወጅ እኛ ጋር እየሰራሽ፣ ከፈለግሽም የፈለክሽውን እየሰራሽ እዚሁ ኑሪ ቤትሽ ነው::

ኑሪ ኑረ ኑሪ ኑሪ…ኑሪ…በሕይወት ኑሪ፡፡ ሌሊት ኮሽ ባለ ቁጥር ሳትሰጊ ኑሪ፡፡ ልጅሸን
እንደፈለግሽ የምታጥቢበት፣ የሽንት ጨርቅ የምታጥቢበት ውሀ ሳያሳስብሽ ኑሪ፡፡ ልጅሽ የሚበላው
ነገር ሳይቸግረው ኑሬኑሪ.: እግዚርም ሲናገር ልክ እንዲህ ነበር፡ ያውላችሁ ምድር ኑሩበት፤
ውሀው ያው ምግቡ ያው፣ መኖሪያው ያው ይሄው ወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ ዘፍጥረት
ራሱን ሲደግም፡፡
“በመጀመሪያ ምድር ባዶ ነበረ፡፡ ባዶው ላይ አንዲት የጨለመባት ሚስኪን ሴት ልጅ አዝላ ቆማ ነበረ፡፡ እግዜር ብርሃን ይሁን አለ፡፡ ቦግ !” ከእግዜር ብርሃን ጋር ሲወዳደር ቀለመወርቅ አብሪ ትል ማለት ነው፡፡ ዘርፌ ሀይሏን የጨረሰች የእጅ ባትሪ፡፡ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ጨረቃ የእግዜርን ብርሃን የምታንፀባርቅ፡፡ እግዜር ግን ፀሐይ ከአድማስ እስከ አድማስ በብርሃን የሚያጥለቀልቅ እናም የሚምቅ !

አቲዩ በተሰጣት ምርጫ መሠረት እዛው ቤት ልትሰራ ወሰነች፡፡ በዕርግጥም የተሻለ ምርጫ
ነበረ፡፡ የማንንም ፊት ከማየት በእጅጉ የተሻለ፡፡ ለእኔ በተለይ ግቢው መቦረቂያዬ፣ የወይዘሮ
እጥፍወርቅ ፈገግታ ምቾቴ ሆነልኝ፡፡ በዛ ሰፊ ግቢ ውስጥ ወይዘሮ እጥፍወርቅ፣ ወጣት ተማሪ ልጃቸውና እኛ ብቻ ነበርን የምንኖረው፡፡ የወይዘሮ እጥፍወርቅ አምስት ልጆች ኑሯቸው ቀውጭ ሀገር ነበር፡፡

ወይዘሮ እጥፍወረቅ አስገራሚ ሴት ነበረች፡፡ እንኳን አቲዬ የድሮ እመቤቷ ዘርፌ ራሷ
የማታልመውን ከውጭ ሀገር የመጣ አንድ ሻንጣ ልብስ ለአቲዬ ሰጠቻት፡፡ ለእኔም ቆንጆ
ቆንጆ ልብስ ገዛችልኝ ዘነጥን !! እኔና እቲዬ ቂቅ ብለን ዘነጥን ደግሞ ስናምር!!

አቲዩ ከወይዘሮ እጥፍወርቅ የተሰጣትን ልብስ ለበሳ አበባ መስላ ብቅ ስትል ዘርፌ ዓይኗ ደም ለበሰ፣ ቀለመወርቅ ደም ግፊቱ ከፍ አለ፡፡ ክፉ አሳቢዎች ምን ሀብት ቢተርፋቸው የያዙት ነገር አያስደስታቸውም፡፡ ይልቅ የሚያጠሉት ሰው ጥቃቅን ለውጥ ያንገበግባቸዋል፡፡ ዘርፌና ቀለመወርቅ የምቀኛ ግንባር ፈጥረው ተንገበገቡ፡፡ የግንባሩ ጸሐፊ ሰይጣን!! እናም ሰይጣን ከቀለመወርቅ እና ዘርፌ ኋላ እግዜርም ከአቲዬ ፊት ቆመው ጦርነቱ ተጀመረ !! አሁን በኑሮ ማስፈራራት በክብር መንጠባረር የለም፡፡ ማንም ሆዱ ከሞላ ጀግና ነው፡፡ ማንም ቢመታ የሚወድቅበት፣ ሲቆስል የሚታከምበት ካለው ጀግና ነው፡፡ ማንም የሚያከብረው ሰው ከጎኑ ካለ ለሌሎች ንቀት ሞራሉ እንደደረቅ እንጨት አይሰበርም፡፡ ዋናው ስንቅና ትጥቅ ግን ማንም እግዚያብሄር ከኋላው እንዳለ ካመነ ልበ ሙሉ ነው !!

እቲዬ ይሄን ሁሉ ሆና ነው ወደ ጦርነቱ የገባችው !! እናም ጦርነቱ በታሪክ ወርቃማው ጦርነት በመባል ይታወቃል በእኔ በነፍሴ ዘገባ !! ወደፊት ልጆቼ “ለምን ወርቃማው ጦርነት ተባለ ?” ብለው ሲጠይቁኝ መልሴ አንድ እና አንድ ነው፤ “በቀለመወርቅ እና በእጥፍወርቅ መካከል በተደረገ ሰብዓዊ ጦርነት በእሳት የተፈተኑ ወርቆች ወደ ምቾት አገር ስለተሰደዱ” እላቸዋለሁ፡፡

የባርነት አስከፊ ገፅታ ያለው በባርነት መግዛቱ ላይ ሳይሆን በባርነት የተገዙበት መንገድ ላይ
ነው፡፡ በፍላጎት ለሌሎች ባሪያ መሆን ለራስ ህሊና የጌትነት ማዕረግ ሰለሚያጎናፅፍ፣ ለነፃነት
ትግል ሳይሆን ምስጋና ራስህን እንድታዘጋጅ ነው የሚያደርግህ:: እሰይ! እንኳንም ባሪያ ሆንኩ የሚባልለት ባርነት አለኮ፡፡ ሰዎች በፍቅር ለሀገራቸው ባሪያ ይሆናሉ፡፡ ለፈጣሪያቸው ይገዛሉ፡፡ ለሚወዷቸው ያገለግላሉ፡፡ ግን ደስተኞች ናቸው፡፡ ለምን ? መንገዱ ፍቅር ነዋ !

አቲዬ ዙሪያውን በረዥም የግንብ አጥር ወደተከበበው ግቢ ገብታ ብትከትምም ዕጣፋንታዋን ግን አላመለጠችውም፡፡ ዕጣፋንታ እኮ ጥላ ነው:: በዙሪያህ ያለውን ችግርና መከራ ፍንትው
አድርጎ የሚያሳይ ብርሃን ሲጠፋ፣ አብሮ የጠፋ ይመስለሃል እንጂ፣ ቀን የሚሉት ፀሐይ ወጋገኑን
ሲቀድ ከትላንቱ በላይ ደምቆ ካንተ በላይ ገዝፎ ከፊትህ ይመራሀል ከኋላህም ይከተልሀል፡፡

አትዬም ዕጣ ፋንታዋን ስንዝር አላመለጠችውም፡፡ ከባርነት ወደ ፍቅር ባርነት ተቀይሮ በትልቁ
ነፍስ ዘራችበት፡፡ ሰፊውን ግቢ ከጧት እስከ ማታ አፅድታ ትልቁን ቤት ውብት ትደፋበታለች፤
ግቢ ውስጥ ጠበቃት እንጂ፡፡ሰው አጥቶ፣ ውርማ ውጦት የነበረውን የወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ
የወይዘሮ እጥፍወርቅን ሆቴልም ቀጥ አድርጋ የያዘችው አቲዬ ራሷ ነበረች፡፡

የሆቴሉን እንጀራ ሙሉ በሙሉ ትጋግራለች፡፡ የአልቤረጎዎቹን አንሶላዎች ታጥባለች፡፡ እንደዛም
ሆኖ በጣም ደስተኛ ነበረች፡፡ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ደግ ሴት ነበረችና ምንም በደረግላት ይገባታል፤የአቲዬ ባርነት ጣፋጭ ነበር፡፡ መሀተመ ጋንዲ ወደ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ ጎራ ቢሉ ኖሮ፣ "ነመስቴ…እኛም የታገልነው ለዚህች አይነቷ ባርነት ነበር በርቱ!” ብለው የሚሄዱ ይመስለኛል!

በእርግጥ ወይዘሮ እጥፍወርቅ አቲዬን እንጀራ ጋግሪ አላለቻትም፡፡ ራሷ አቲዬ ለሆቴሉ እንጀራ
ግዥ እየተባለ በቅን የሚወጣውን ብር ስትመለከት፣ “ምጣድ ግዙልኝ ሪሴ እጋግራለሁ" አለች እንጂ፡፡ የሆቴሉን አንሶላ፣ “እጠቢ ያላት ማንም አልነበረም፡፡ አጣቢዋ ስትጨማለቅ ስታያት አቲዬ የኔ የልብ ሰው፣ “ምነው እቴ ሰው የሚታኛበት እይደለም እንዴ” አለችና አጇን ሰቅስቃ
ገባችበት፡፡“አቦ የእጥፍወርቅ ቤርጎ እንሶላው ብትል ፎጣው እንዴት ይጸዳል” እስኪባል፡፡ የወይዘሮ እጥፍወርቅ ልብ አቲን በልጅነት መንበር ላይ ወስዶ አስቀመጣት፤ እኔንም የልጅ ልጅነት !!

ግቢው የእኔ ነበር፡፡ እንዳሻኝ የምሆንበት ግዛቴ፡፡ የሳሎኑ ዕቃ የእኔ ነበር፡፡ ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዋጋ የተከሰከሰበት ሶፋ ላይ ሸንቼበታለሁ፣ ወተት ደፍቼበታለሁ፡ አቀርሽቼበታለሁ፡፡ ለዓይን የሚያሳሳውን የቡፌ ዕቃ እንኮታኩቼዋለሁ፡፡ የወደዘሮ አጥፍወርቅን ባለ አልማዝ ፈርጥ የአንገት ሀብል ከእንገቷ ላይ በጣጥሼዋለሁ፡፡ (የዚህ ሀገር ወርቅ አንጥረኛ አይሰራውም ተብሎ ተቀምጦ ቀረ…) የፋናዬን (እህቴ ማለት ናት - የወይዘሮ እጥፍወርቅ ልጅ) ቀይና ውብ ፊት ቦጫጭረዋለሁ፣ ፋኒዬን እንደ ህፃን ልጅ ነበር የማስለቅሳት፡፡
አትዬ ስትነግረኝ ፋናዬ ከትምህርት ቤት ስትመጣ ቦርሳዋን እንዳዘለች እኔ ላይ ትጠመጠምና ድበድብ ነው፡፡ ሱቅ የተሰቀለ አሻንጉሊት ካየች፣ የሕግን ልብስና መጫወቻ ዓይኗ ውስጥ ከገባ፡ ለእኔ ለመግዛት ከእናቷ ጋር ብር ስጭኝ አልሰጥም” ጦርነት ነው::
የእናቴ ንፁህ ልብ እንደስፖንጅ ፍራሽ በሕይወቴ መንገድ ላይ ተነጥፎ የዛች ቅፅበት የነበረ
👍245
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ሰባት


ቁጥር ስፍር የሌለው ሕዝብ ለቅሶ ለመድረስ የወይዘሮ እጥፍወርቅን ግቢ አጥለቀለቀው:: ቀስ
በቀስ አስተዛዛኙ እየተመናመነ መጥቶ በመጨረሻ ግቢው ወደ ነበረው ገዝምታ ተመለሰ፡፡ ከሀዘኑ
በኋላ ነገሮች ህልም በሚመስል ሁኔታ ተቀያየሩ። ሀዘኑ ባበቃ በጥቂት ወራት ውስጥ ፋናዬን
ወንድሞቿ ሲዊዲን ወደሚባል ሀገር ወሰዷት፡፡

ፋኒ የእኔ እህት አቲዬን ስማ በተሰበረ ልብ ግቢውን ለቀቀች፡፡ አቲዬ በምድር ላይ ያሏትን ሁለት
ዘመዶች አጣች፡፡ ዛሬም ይሄን ስታወራኝ ዓይኗ ውስጥ ህመም ይንቀለቀላል። ነፍሷ ይቃትታል፣
ዝም ብላ ትቆይና፤

"አሹዋ” ትለኛለች፡፡

“አቤት አቲዩ!"

"ሱዲን የሚሎት ሀገር ወዴት ነው? ፡፡ ስዊዲን ሀገር ቤትና ሕዝብ ተቆጥሮ የሕንዘቡ ቁጥር
ምንትስ ሚሊዮን ደረሰ ሲባል አቲዬ አታምንም፡፡ የስዊዲን ህዝብ ቁጥር አንድ ብቻ ነው ፋናዬ ብቻ !! አቲዬ የዛችን ደግ ሴት ልጅ ፋናዬን እንደ እየሩሳሌም አንድ ቀን ልታያት ፅኑ መሻት ፊቷ ላይ ይንቀለቀላል፡፡

አንዲት እድሜዋ አርባ የሚሆን ሽቅርቅር፡ ሲበዛ ቆንጆ የሆነች ሴትዬ (የወይዘሮ እጥፍወርቅ እህት ናት ይላሉ) ከሁለት ጨምላቃ ሴት ልጆቿ ጋር፣
ወር ሳይሆን ጠብቂ ተብላ
እግዜር ይወቅ ብቻ ግቢውን ትኖርበት ጀመረ፡፡ ሆቴሉ ተሸጠ፡፡ እች ሴት አስቴር ትባላለች፡፡ ምኗም የማይጨበጥ ተልካሻ ሴት ! ከዕድሜዋ ጋር ጦርነት የገጠመች ማቶ !

አንዳንዴ በተረት የሚታወቀው አስማተኛ መስተዋት መኝታ ቤቷ ውስጥ የተቀመጠ ይመስል
ገብታ በወጣች ቁጥር ልብስ የምትቀይር፣ “የሆነ ቦታ በመልክ የምትበልጥሽ ውብ ሴት አለች
እያላት መስተዋቱ፡ ፊቷ ላይ የትራስ ሰንበር ከሚወጣ ኢትዮጲያ ላይ ከሰሜን እስከ ደቡብ
ጫፍ አዲስ ስምጥ ሸለቆ ሲፈጠር የምትመርጥ የውበት ስስታም " የዕለት እንጀራዋ የሰው
ዓይን የሆነ ከንቱ፣ የእጥፍወርቅን ግቢ በባለቤትነት ታስተዳድር ጀመር፡፡

አቲዬን እንደ ሰራተኛ ስለምታስባት ማመናጨቅ የጀመረቻት ገና የሀዘንተኛው እግር ጨርሶ ሳይወጣ ነበር፡፡ እኔንማ ግልገል ሰይጣን አድርጋ ነው የምታየኝ፡፡ በወይዘሮ እጥፍወርቅ የለመድኩትን መዘባነን ታጥቄ ወደ ሳሎን ዘው ስል በቲሸርቴ አንጠልጥላ መሬት ለመሬት እየጎተተች በረንዳው
ላይ የመወርወር ያህል ትጎትተኝና፣ “ማነሽ አንች ልጅ ነይ ወደዛ ውሰጅ ይሄን ልጅሽን !
እንዴ የምን መጨማለቅ ነው እሱ…ሁለተኛ እዚህ ምንጣፍ ሳይ ሲወጣ እንዳላይ!" ብላ እጇን
ታራግፋለች::

አቲዬ ነፍስና ስጋዋ እየተሟገተ መወልወያ ይዛ ትገባና ያበላሸሁት ነገር ካለ ትፈልጋለች። ብዙ
ጊዜ ግን የዚህች ከንቱ ጩኻት ምከንያት አልነበረውም፡፡ ምክንያቷ ሰው አለመፈለግ ነው።
ሰውን በማራቅ ሰላም ይገኝ ይመስል ! ሁካታ ነፍሷን ሀቅ አጉርሳ ዝም እንደማስባል የቀረባትን ሁሉ ታፍናለች፡፡

በዚያ ከወራት በፊት ምግብ ይልከሰከስበት በነበረ ግቢ ውስጥ ጣረሞት ራህብ ያንዣብብ
ጀመረ፤ በፊት ወተት የምትገዛልኝ እጥፍወርቅ ነበረች፡፡ መሶቧ መሶባችን፣ ድስቷም ድስታችን
ነበረ፡፡ እንዲህ ባጭር ጊዜ ከጓዳችን ቁራሽ ዳቦ፣ ንጣይ እንጀራ ይነጥፋል ብሎ ማን አስቦ !

አንዳንዴ ምቾት ያዘናጋል፡፡ ምቾት ስትኖርበት ዘላለማዊ ይመስላል፡፡ ሜዳ ላይ ጥሎህ እንደ
ጉም ሲተን ነው ፊቱ ላይ ቀዝቃዛ ውሀ እንደቸለሱሰት ሰው የምትበረግገው:: ስንቱ ቤተሰብ
ድንገት ከምቾቱ ችግር ተኮርኩሞ ነቅቷል፡፡ ስንቱ ባለስራ ስራውን ተደግፎ፣ ድጋፉ ሲከዳው
ወድቆ ቀርቷል፡፡ ሰንቷ ባለትዳር፣ የባሏ እጅ ሲነጥፍ አብሮ ቅስሟ ተሰብሯል፡፡ አግኝቶ ማጣት
ብሎ ህዝቡ የሚጠራው ይሄንን አይደል ተገኝቶ መጥፋት ቢሉት ይሻል ነበር !

አስቴር አቲየን ታዝዛታለች፣ ታመናጭቃታለች፣ ትልካታለች፣ ግን ብርም ሆነ ምግብ አትሰጣትም፤ የሚገርመው ደግሞ ቤቱ ውስጥ እንጀራ አይጋገርም ወጥም አይሰራም፡፡ እናትና ቦዘኔ ልጆቿ የታሸገ ነገር ይገዙና መኪናውም ውስጥ መንገድም ላይ ይበላሉ ማሸጊያውን ወዳገኙበት ይወረውሩታል፡፡ እነዛን ደማቅ ጽሑፍ ያላቸው የቸኮሌት ላስቲኮች በርሃብ እየተንሰፈሰፍኩ
ቀድጄ የላስኩባቸው ጊዚያት ብዙ ነበሩ ዛሬ ቸኮሌት እንደ መርዝ እጠላለሁ !! እነዛ ባዶ
የፍራፍሬ ጭማቂ ዕቃዎች ስይት ነበሩ ለኔ፡፡ ዘመናዊነት ያደነዘዛቸው እናትና ልጆች ምቾት
ውስጥ የመነኑ የስንፍናና የክፋት ቆብ የጫኑ ርኩሶች ነበሩ፡፡ እንኳን ግቢያቸው ውስጥ ለተጠጉ
ሚስኪኖች፣ እርስ በርሳቸውም የተለያዩ የሰው ከብቶች፡፡

መኝታ ቤታቸውን በየፊናቸው ዘግተው፣ ማንም አራት እግሩን ቢበላ አልሰማንም አላየንም
ብሎ የሚጮህ ጋግርታም የግለኝነት ባሕር ውስጥ የተጠመቁ፡፡ የምዕራባዊያኑን ቆሻሻ ግለኝነት የስልጣኔ አልፋ፣ የዕውቀት ኦሜጋ ያደረጉ ፉዙዎች፡፡ በእንግሊዝኛ እየተለፋደዱ፣ በአማርኛ
የአዕምሮ መቃወስ ውስጥ የተዘፈቁ የቤት ዕቃዎች፡፡ የሞራልም ይሁን የሀይማኖት፣ አልያም ከነፍስ ስልጣኔ የሚመነጭ ጠንካራ ስብዕና የሌለው ኢትዮጲያዊ፣ ውጭ ሀገር ደርሶ ሲመለስ ምን አይነት አስቃቂ ማቶንት ውስጥ እንደሚነከር የታዘብኩት በእነዚህ ከንቱዎት ነበር፡፡እናታቸው ሀያ ዓመት፣ ልጆቹ እየሄዱ እየመጡ ከአስር ዓመት በላይ አሜሪካ ኖረዋል፡፡ አስቴር
ታዲያ ለዓመታት ከኖረችበት አሜሪካ ምን ይዛ መጣች? ሰምቻታለሁ ለመጣ ለሄደው፣

“አበሻ ስራ አይወድም፣ ነጮቹ እኮ ለሰዓት ያላቸው ክብር ለስራ ያላቸው… "

“አበሻ የተመጣጠነ ምግብ አያውቅም ማድፋፋት፣ ጥሬ ከብስል ማጋበስ…"

“አበሻ መች ንፅህና ይወዳል ነጮቹ እኮ."

"ኤዲያ የሀበሻ ወንድ መች ሴት ያከብራል ነጮቹኮ”

“የአበሻ ልጅ አስተዳደግ.…

የአበሻ ሕክምና ደግሞ ራሱ በሽታ ነው፡፡ ነጮቹ እኮ”

አበሻ ገንዘብ ከመሬት የሚታፈስ ነው የሚመስለው፡፡ ዓይኑን በጨው አጥቦ፣ ዶላር ላኩ ነው
ነጮቹ እኮ አስራ ስምንት ዓመት ከሞላቸው… "

ነጭ የባርነት ቀንበር ጫንቃዋ ላይ ተሸክማ የምትደሰኩር ቱልቱላ፡ ከየትም የፈለፈለቻቸው ልጆቿ
በአስተዳደግ ይሁን የግል ባህሪ ምን ዓይነት እናት አንደሆነች ጮኸው እያወጁ፣ “ዓይናችሁን
ጨፍኑ ላሞኛችሁ” ትለናለች፡፡

የነጮቹ ፅንፍ የለሽ ውክቢያ ዕድሜዋን ሙሉ ያጨቀባት የታላቅነት አባዜ አበሻን በበጎ እንዳታይ እንደ ጋሪ ፈረስ ቀይዷት፣ ለእግዜር ሰላምታ የቀረባት ሁሉ የፈጋችበትን ዶላር የሚነጥቃት
እየመሰላት ስጋዋ ያልቃል፡፡ ልጆቿም በየአጥሩ ጥግ ከሚያናንቁት የአበሻ ወንድ ጋር ሲሳሳሙ እና በየመሸታ ቤቱ ሲዳሩ ከማምሸት ውጭ የፈየዱት ተዓምር የለም፡፡ በነፃይቱ ሀገር ኖረው ለመጡ የስልጣኔ ጥጎች፣ የከንፈር ዋጋው የዶላሩን ያህል ውድ አይደለም፡፡ እነዛ ወንበር ስበው በክብር ሴትን ልጅ የሚያስቀምጡ ነጫጭ ወንዶች የሴትነትን ክብር እየሰበኩ ሰብዓዊነታቸውን ከእግራቸው ስር እንደጨፈላለቁት ለመረዳት የጋረዳቸው ነጭ ደመና አይፈቅድላቸውም

ለእነዚህ የስልጣኔ ርዝራዦች የሰው ልጅ ስለክብሩ መኖር፣ ስለማተቡ ዓለማዊነትን በልክ ይሁን ማለቱ ተራ መኮፈስ ነው:: ቦርሳቸውን ከመከፈት፣ ለማንም አላፊ አግዳሚ እግራቸውን መከፈት ይቀላቸዋል፡፡ ምክንያቱም “ዶላር የተከበሩት የነጮች ውድ ቅርስ” ሲሆን ሰውነታቸው ግን
የርካሾቹ፣ የሰነፎቹ፣ ያልተማሩት፣ ሥራ የማይወዱት፣ ብር ከመሬት የሚታፈስ የሚመስላቸው
አበሾች ርካሽ ንብረት ነው፡፡

በዚህ ፍልስፍና አገሩን አጥምቀውት አገሬው ፈረንጅ ባል ፍለጋ ሲራኮት ሲታይ ምን ይገርማል !

አቲዬ አንድ ቀን እየፈራች ሴትየዋን አናገረቻት፤ “እትዬ ወጥቼ አንዳንድ ስራ ልሰራ ነበረ ምናልባት ከፈለጉኝ ብዩ ነው…"
👍312
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ስምንት

መማርን ጌታ ይባርከው ! መማር መቃጠል ነው ይላሉ ተምሮ ማቃጠል ለእኔ ዓለሜ ሆነች "
ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት አንደኛ ከፍል እስከመዘገብ የአባት ስም አልነበረኝም፡፡ አሸብር ብቻ
ነበርኩ፡፡ ልክ ትምህርት ቤት አቲዬ ወስዳኝ ስመዘገብ ጉጉት የመሰለው መዝጋቢ የእናቴ ድሪቶ ቀሚስ ለዓይኑ ቀፎት እያመናጨቃት አይቼዋለሁ፡፡ ተመዝግቤ ስንመለስ አቲዬ ከፊቱ ዞር ስትል፣ ፊቱን አጨፍግጎ መጥፎ ጠረን እንደሚያባርር ሰው በግራ እጁ አየሩን እያራገበ ሲያባርር አይቼዋለሁ፡፡

በእርግጥ አቲዩ እማማ የብርጓል ቤት እንኩሮ እያነኮረች ነበር፡፡ ምዝገባው ዛሬ ነው የሚያልቀው
ሲሏት ብድግ ብላ ነው የመጣችው፡፡ ቢሆንስ ልክ ቆሻሻ እንደሸተተው ሰው ሰው እንዲያየው አድርጎ እጁን ያራግባል እንዴ…፡፡ የእማማ የብርጓል ቁጥር አንድ የጠላ ደንበኛ እንዳልሆነ ሁሉ፡፡ ሊያስተምረን ክፍል ውስጥ ሲገባ እንደባቡር ሀዲድ የረዘመ የጠላ ትንፋግ ተከትሎት
እንደማይገባ ሁሉ ነብር አየው ያንን የውሻ ልጅ። አስተማሪውን እንደጠመድኩት ጡረታ
ወጣ !! ደግሞኮ አያፍርም መንገድ ላይ ላገኘው ሁሉ፣ እኔ ነኝ ያስተማርኩት“ እያለ በኩራት
ያወራል፡፡ በርሱ የትምህርት ዓይነት ብቻ ዶክተር የሆንኩ ይመስል!!

“ስም ?” አላት አቲዩን ድሮ፡፡

“የእኔን ነው ?” አለች እየፈራች፡፡

ፈሪ ነበረች እናቴ፡፡ ፈሪው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደያቅሙ ደሀ ማስፈራራትን ተክኖበታል።

“አንች ነሽ አንደኛ ክፍል የምትመዘገቢው?" አላት፡፡ አጠገባችን ያሉት ሁሉ ሳቁለት፡፡ አቲዬ ተሳቀቀች፡፡ ሰውነቷ ሽምቅቅ ሲል ቀሚሷን አንቄ ተሰምቶኛል መሸማቀቋ፡፡

የልጅሽን ሰም ንገሪኝ ሴትዮ አላት እያከላፈታት፡፡

“የእሱ አሸብር…አሸብር ነው ስሙ አለች ራሴን እያሻሸች፡፡

“የአባት ስም ?”

“እባ…ት” ብላ ዝም አለች፡፡

“የአባቱ ስም ማነው…

'ቀ' መጨረስ አልቻለችም፡፡ ቀለመወርቅ ልትል ፈልጋ እንደነበር የገባኝ ካደግኩ በኋላ ነው፡፡

የዛሬዋ ደግሞ የጉድ ናት፡፡ የልጇም አባት የሚጠፋት
እንደገና እንዲስቁለት ሰዎቹን አየ
ያልደመቀ ሳቅ ተሳቀለት፡፡

"በይ ወደዛ ሁኝ! ስታስታውሽ ትመለሻለሽ፤ ተረኛ ቀጥል!” አለ እስኪርቢቶውን እያወናጨፊ፡፡

(አልረሳትም ግማሽ ድረስ ቀለሟ ያለቀ ሰሚያዊ ቢክ እስክርቢቶ።

እናቴ ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው፣ “በአምላክ..በአምላክ ነው የአባቱ ስም፡፡” አለች፡፡

መዝጋቢው ራሱን ግራና ቀኝ በብስጭት እያወዛወዘ መዘገበኝ፡፡

የአባት ሰም በአምላክ (በአምላክ አባቴ አይደለም፡፡ እቲዬ ለአምላክ ሰጠችኝ፡፡) የሃምሳ ብሩ ሲገርመው፣ ለእግዜር ሰው አበደረችው አቲዬ፡፡ የእኔ እናት በሕይወት ባንክ ውስጥ ብድር
ለሚመልስ ብድር በመስጠት የተካነች ባለሙያ ነበረች ነገን የምታይ !! እግዜር የተበደረው
ትውልድ፣ ወለዱ የተባረከ ዘር ማንዘር ነው፡፡ “እስከ ሺ ትውልድ ዘርህን እባርካለሁ፡፡ ብሏል
ራሱ እግዜር

ትምህርት ቤት ገባሁ…!!

የክፍላችን ልጆች የኑሮ ደረጃ በዳግማዊትና በእኔ መካከል የተወሰነ ነበር፡፡ ዳግማዊት የሚታዘል ባለዚፕ ቦርሳ ያላት ቆንጆ አንደኛ የሀብታም ልጅ ስትሆን፣ እኔ ከሹራብ የተሰራች ኮሮጆ የነበረኝ አንደኛ የደህ ልጅ፡፡ ይሁን እንጂ በንፅህና አልታማም፡፡ ልብሶቼ ሁልጊዜም ንፁዎች ነበሩ
ንፁህና አሮጌ፡፡ ሰኞ ሰኞ ሰልፍ ሜዳ ላይ የእጅ ጥፍሮቻችን ሲታዩ ንፁሀ ጥፍርቼን በኩራት
ነበር የምዘረጋው:: የዳግማዊትን ያህል በፈገግታ “ጎበዝ“ ባልባልም፣ ከቆሻሻና ከስንፍና የተጣላች ቆራጥ ደሀ እናት አለችኝና ስንፍናና ቆሻሻ አጠገቤ ዝር አይሉም ! (ሰው ወዶ አይደለም ለካ ዘራፍ የሚለው፡፡)

አንድ ቀን ግን በሕይወቱ ስሳቀቅበት የኖርኩበት ነገር ተፈጠረ፡፡

እንግዲህ አስቴር ከዋናው ቤት እሮጌ ፍራሽ (የሆቴሉ አልቤርጎ ውስጥ የነበሩ፡፡) እና ሌሎችም
ከፍል ውስጥ ቤት፡፡ እናም ቤታችን ውስጥ በታጨቀው ዕቃ ምከንያት ቤቱን አንደ ልብ ማፅዳት ባለመቻሉ ቁንጫ እንደጉድ ይፈነጭ ጀመረ፡፡

ጋሽ መሀሪ ኣካባቢ ሳይንስ መምህራችን ነበር፡፡ ሲያስተምር ስወደው:: የርሱን ትምህረት አስር
ካስር ነው ሁልጊዜም የምደፍነው፡፡ እኔ ስለምወደው፣ የሚወደኝ ይመስለኝ ነበር ፡፡ አንድ ቀን ግን ዘላለማዊ ጠላቴ ያደረገውን የማይረባ ነገር አደረገ።

ስለ ጓር አትክልት ጥቅም እያስተማረ ነበር፡፡ ድንገት ዳግማዊት፣ “ ዋይ” ብላ ጮኸች::
ቦርሳዋ ላይ ሁለት እሳት የመሳሰሉ ቁንጫዎች ዘለውባት ነበር፡፡ የክፍሉ ልጅ ሁሉ በድንጋጤ
ወደ ዳግማዊት ዞረ፡፡ መምህሩ ሁኔታውን ሊያጣራ ከምኔው አጠገባችን እንደደረሰ እንጃላት::

“ምንጩን ነው?”

“ቁ..ን..ጫ አለች ለቅሶ በሚመስል ሞልቃቃ ድምፅ፡፡

እኔ ከዳግማዊት ጎን ነበር የምቀመጠው፡፡ ባልገባኝ ምክንያት ተቆጣ፡፡

"እስቲ ቦርሳህ” አለኝ፡፡ በቃ እንዲህ ነው ያለኝ፡፡ ከወንበሩ ስር ከተሰራው የደብትር ማስቀመጫ፣
የሹራብ ኮሮጆዬን አወጣሁ፡፡ በዚህች ቅፅበት የተከሰተው ነገር አስደንጋጭ ነገር ነበር፡፡ በርካታ
ቁንች ከእኔ ኮሮጆ ላይ ተፈናጠሩ፡፡

መምህር ምሀሪ ፊቱን አጨፍግጎ ኮሮጆዬን አነሳና ወደፊት ወደ ጥቁር ሰሌዳው ወረወረው::
ደብተሮቼ በአየር ላይ ወረቀታቸውን እያርገበገቡ ተበታተኑ፡፡ (እስከዛሬም ደብተሮቼ በአየር ላይ እየተንሳፈፉ ይታዩኛል አላረፉም፡፡)

“ውጣ ጆሮህን ያዝ ብሎ በኩርኩም አፈለሰኝ፡፡ ወጥቼ ጆሮዬን ያዝኩ፡፡ ከኩርኩሙ በላይ
ሀፍረቱ ጠዝጥዛኝ ነበር፡፡

የታፈነ የጓደኞቼ ሳቅ፡፡ በትምህርት አልችለኝ ሲሉ እችን እንደውድቀት፣ እችን ከእነሱ እንዳነስኩባት አጋጣሚ ሊጠቀሙባት፡፡ የእፉኝት ልጆች…ስንቱን ትምህርት ስደፍን ለጭብጨባ በመከራ የሚነሳ እጃቸው፧ ዛሬ ሳቃቸውን ሊያፍን ወደ አፋቸው ተወነጨፈ።

ቡፍ.….ቡፍ...ሂሂሂ..

መምህሩ መሀሪ (ስሙን ቄስ ይጥራውና!) ስለጓሮ አትክልት የፃፈውን አጥፍቶ ጥቁር ሰሌዳው ላይ፣

“ተስቦ" ብሎ በትልቁ ፃፈና ከስሩ በድርቡ አሰመረበት፡፡ ያውም አረንጓዴ ቀለም ባለውና እንደ
ብርቅ በምናየው ጠመኔ !!

ከዛም ስለተስቦ ሙሉ ክፍለጊዜውን ሲለፈልፍ ዋለ፡፡

“አያችሁ ልክ እናንተ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ዘመድ ለመጠየቅ በታክሲ፣ በአውቶብስ
ተሳፍራችሁ እንደምትሄዱት፣ ቁንጫዎችም በአይጦች ተሳፍረው ንፅህናው ወዳልተጠበቃ ቤት ይሄዳሉ፡፡ አሁን እሱ ደብተር መያዣ ላይ እንዳያችሁት እኔን እየጠቆመ)፣ ንፅህናው ባልተጠበቀ የልብስ ሻንጣ፣ የደብተር መያዣ፣ በሌላም ቁሳቁሶች አማካይነት እየተንጠላጠሉና እየተደበቁ
ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ፣ እንደ ዳግማዊት ዓይነት ንፁህ ልጆች በተስቦ ይያዛሉ..” በማለት
አስተማረ፡፡ ምን ያስተምራል አስተማሪ የሚባለው ነገር የጠላት ስም እንዲመስለኝ እደረገ እንጂ !
ለረዥም ጊዜ 'ተስቦ' እያሉ ጓደኞቼ ያበሽቁኝ ነበር፡፡ ከአርባው ስንፈተን ግን ስለተሳቦ ተጠይቀን
የደፈንኩት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ ሰው ስድሱን አይረሰማ !! በተለይ እኔ ስድቤን አልረሳም !! መገፋቴን አረሳም።

ስድስና መግፋት እንደ አረግራጊ ሳንቃ ሽቅ

ብ ተኩሰው በቀል የሚባል ጨረቃ ላይ የሚያሳርፉኝ
👍36🥰32😁1😢1
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ዘጠኝ

የአስቴር ትልቋ ልጅ ዛፒ ትባላለች፡፡ ትርጉሙ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ምናልባትም 'ሰይጣናዊ መዝገበ ቃላት የሚባል ነገር ካለ፣ ትክከለኛ ትርጕሙ እዛ ላይ ሳገኝ አይቀርም፡፡ እስከዛው
ግን በግምት “ዋጋ ቢስ' ብዬ ተርጉሜዋለሁ።

ዘር ከልጓም ይስባል እንዲሉ ቁርጥ እናቷን (ለነገሩ አባቷን የት አውቄው?)እኔ ከስምንተኛ ክፍል
ወደ ዘጠነኛ ክፍል ሳልፍ እሷ የሀያ አምሰት ወይም የሀያ ስድስት ዓመት ወጣት ነበረች፥ ተስፋ
የቆረጠች ወጣት፡፡ እናቷ አስቴርና ትንሽ እህቷ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ውጭ አገር ሲመለሱ
እሷ እዚሁ እኛ የነበርንበት ግቢ ውስጥ ከንድ ደስ የሚል የተረጋጋ ወጣት ጋር መኖር ጀመረች፣

ምናልባት እዚሁ የቀረችው ልጁን ስለወደደችው ይሆናል፡፡

መጀመሪያ መኪናውን ውጭ ጋር ያቆምና ተያይዘው ይሄዱ ነበር፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ዋጋ ቢሷ ትጠራኝና አሸብር ኛ እችን መኪና ወልውል!” ትላለች፡፡

ዛፒዩ አሁን እኮ ነው ያሳጠብኳት!” ይላታል፡፡ እርሱ የዋጋ ቢሷ መልዕክት ተንቀጥቅጦ
የሚታዘዛት ሚስኪን መኖሩን ማሳየት መሆኑን መቼ አውቆ፡፡

ቆይታ እቤት እየገባ መቆየት ጀመረ፡፡

“አሽብር ና ለስላሳ ግዛ! ና ቢራ ግዛ” ብታምኑም ባታምኑም ኮንዶም ሁሉ ታስገዛኝ ነበር፡፡
መላላኬ ሳይሆን በዛ እድሜ ፋርማሲ ሂዶ ኮንዶም መግዛት ያሳቅቀኝ ነበር፡፡ ፋርማሲስቶቹ
በትዝብት ያዩኛል፣ “የተቀደደ ሱሪውን ሳይቀይር…” በሚል ግርምት…ሱሪው የተቀደደ ሰው
እንትን አያደርግም የተባለ ይመስል፡፡

ከዛ ማደር ጀመሩ፡፡ በጨለማ በዛ በኮረኮንች መንገድ ቢራ ተሽከሜ እጀን የፌስታሉ እጄታ እየከረከረኝ የተላላኩበት ጊዜ መቼም አይረሳኝም (እስከዛሬ እቃ በፌስታል መያዝ አልወድም፡፡ አቲዩ የግቢው በር ላይ ብርድ እያቆራመታት ቆማ ትጠብቀኛለች፤
ገብቼ ቢራውን ስሰጥ ዛፒ ልክ ከፍሪጅ ያወጣችው ያህል ከእጄ ላይ ትወስድና፣ እንካ ሁለት ፓኬት ሮዝማን ግዛና ና” ትላለች፡፡
በመጨረሻ ጠቅልሎ ገባና አብረው መኖር ጀመሩ፡፡ መኪና ማጠብ ቋሚ ስራዬ ሆነ፡፡ እውነቱን
ለመናገር ጥሩ ባል ነበር፡፡ ዋሲሁን ይባላል። ቤቱ የባለትዳር ቤት እንዲመስል የተቻለውን ሁሉ
ይጥር ነበረ፡፡ ዛፒ ግን የሚቋቋማት ዓይነት 'ሚስት አልነበረችም፡፡ ጉራዋ ፀጉር ያስነጫል፣ በውበቷ ስትመካ ልክ የላትም፡፡ የእናቷ ጫማ ውስጥ ዘላ የገባች ጉረኛ ! አቤት ጉረኛ ሴት እንዴት እንደምትቀፍ፡፡ ከምትናገራቸው አስር ዓረፍተ ነገሮች፣ አስራ አንዱ ስለራሷ ውበት፣ ስለቆዳዋ ጥራት፣ ስልጣቶቿ አለንጋነት፣ ስለልብስና ሽቶዎቿ ብራንድ በቀጥታ አልያም በተዘዋዋሪ ይተርካሉ ፡፡

ዘላ የተዘፈቀችበት ትዳር ከጭፈራ ቤት መዳራት በምን እንደሚለይ ገና ያልገባት አካሏ ብቻ
ህሊናዋን ጥሎ ያደገባት ከንቱ ነበረች፡፡ ዋሲሁን ውጭ መመገብ አይወድም፡፡ የታሸጉ ምግቦችን
ገና ሲመለከታቸው ያንገሸግሸዋል፡፡ እንጀራ በሽሮ ወጥ ነፍሱ ነው:፡ ዛፒ ታዲያ ቤት ውስጥ ለባለቤቷ ምግብ አብስሎ ማቅረብን በሴት ልጅ ላይ የሚፈፀም ታላቅ በደል አድርጋ ነበር የምታየው፡፡አበሻ ወንድ ጓዳለጓዳ ካልተንደፋደፈች ሚስቱ ሚስት አትመስለውም፡፡ ሴት አደባባይ መውጣቷ ያማቸዋል” የምትለው ከእናቷ የወረሰችው ዘይቤ አላት፡፡ በጓዳም በአደባባይም ምንም የማትፈይድ የወሬ ቋት፡፡ ኩኪስ አልያም ጭማቂ ነገር ከፍሪጅ ታወጣና ሶፏዋ ላይ እግሯን አጣጥፋ ቴሌቪዥን እያየች ትበላለች፣ ትጠጣለች፡፡ ስለፋሽን ሳታቋርጥ ትቀባጥራለች፤ በዓለም ላይ ስላሉ የቅንጦት ሆቴሎችና ጌጣጌጦች ዋ.….ው” እያለች ትቋምጣለች፡፡ ቤትም የለችም፡ የምትመኘውም ቦታ የለችም፡፡ የትም የሌሎች የውሀ ላይ ኩበት ነገር!!

ዋሲሁን ያደበትን የቤተሰብ ስነስርዓት፣ የኢትዮጵያዊነ ወግ ምሳ ተዘጋጅቶ፣ ቡና ተፈልቶ፣ ቤቱ
ሞቅ ብሎ እንደሚጠብቀው በማመን እንደ ኣባወራ
ምሳ ሰዓት ላይ ሲመጣ ዛፒ ጠረጴዛው ላይ እግሯን ሰቅላ ዙሪያዋን የጥፍር ቀለም ጠርሙሶች ከበዋት ቤቱ በአልኮል ሽታ ታፍኖ ስትቆነጃጅ
ያገኛታል፡፡ ማታ ሲመጣ ዛፒ ለባብሳ ኣንዲወጡ ስትጠብቀው ይደርሳል፡፡

ሀኒ ዎከ እናድርግ ትለዋለች፣ ባል ጋር መታየት እንጂ የባልን መሻት ማየት አልፈጠረባትም፣
የሆሊዉድ ተረቶች ባዶ ጭንቅላቷን ሞልተውት ነበር፡፡ ከንዱን ይዛ መንገድ ላይ ስትውረገረግ ብጤዎቿ፣ “ዋው ምናይነት ጥምረት ነው? ማች ያደርጋሉ" እያሉ ያወሩላታል፡፡
ሚስኪን ዋሲሁን ሳይወድ በግድ እግሩ እስኪቀጥን ሲዞር አምሽቶ እኩለ ሌሊት ላይ ስልችት
ብሎት ይመለሳሉ፡፡ የተሰቀለችበት ባለ ተረከዝ ጫማ ለመራመድ ስለማይመቻት ክንዱ ላይ
ተዘፍዝፋ ትወናገራለች፡፡

“ሃኒ ዲጄው ሽቶሽ ብራንዱ ምንድን ነው?' ሲለኝ ሰምተኸዋል?”

“አልሰማሁትም ይላል ትክት ብሎት፡፡

"ሃሃሃሃሃሃሃ ጠጥተህ ነበር ብዙ.ሰካራም ሃሃሃሃሃ” ትላለች እየተለፉደደች፡፡ አብሯት አይስቅም፡፡

"በናትህ ቀሚሴ ላይ ዋይን ደፋብኝ ያ ወልካፋ አስተናጋጅ" ትላለች ረዥም የራት ቀሚሷን
እያሳየችው::

“ይታጠባል.ደግሞ አንቺ ስታልፊ እኮ ነው የገጨሽው” ይላታል ስልችት ብሎት፡፡

“እዚህ አገር ምን ላውንደሪ አለ? ሰባት መቶ ዶላር የወጣበት ቀሚስ እንደቀልድ - ምን አይነት
አገር ነው? ብላ ቀሚሷ ባአደባባይ ባለመከበሩ አስራ አምስት ቀን ታወራለች፡፡ ስለ ተራ ቀሚስ
ሳይሆን ስለ ባንዲራ መደፈር የምታወራ ነው የምትመስለው::
ጧት ተነስቶ በተሳሳት መንፈስ ወደ ስራ ሲሄድ ዛፒ አትሰማም አትላማም ተኝታለች፡፡ ምሳ
ሰዓት እንደገና ጓደኞቿ ጋር እንደሄደች ትደውልለትና፣ “ምሳህን ውጭ ብላ ሃኒ" ትለዋለች፣ በዛውም አያችሁ ባሌን ሳዘው!' እያለች በከንቱ ጓደኞቿ፡፡ ምሳ፣ ራት፣ ቁርስ በአበሻ ባህል
ከምግብ የዘለለ ፋይዳ ያለው ጉዳይ መሆኑ ለዛፒ አልታያትም ነበር፡፡

የቤተሰብ እትብት ከእናት ማዕድ ጋር እንደሚያያዝ ማን ይመከራታል? ዋሲሁን ለአንድ ዓመት አብሯት ቆየና ከፉ ደግ ሳይናገር፣ አንቺ ጋር እንግዲህ በቃኝ ብሏት ሄደ...!! መሄድ ብቻ
አይደለም፡ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ድል ባለ ሰርግ ሌላ ሴት አገባ፡፡ ዛፒ መጀመሪያ፣ “ጥርግ
ይበል! ለሞላ ወንድ!" አለች፡፡ ቆይታ፣ “ይሄ ችጋራም ፒዛ እንኳን መብላት ያለማመድኩት እኔ
ነበርኩ፡ ጥጋበኛ የደሀ ልጅ” ማለት ጀመረች፡፡ በመጨረሻ ፎቶውን እያየች ማልቀስ ሆነ ስራዋ፡፡

ዛፒ ሲበዛ ቆንጆ ናት፡፡ ልብሶቿ ጌጣጌጦቿ የብዙ ሴቶች የቁም ቅዠት፡፡ ግን ዋሲሁን ከሄደ በኋላ
ወንድ የሚባል አልቀርብ አላት፡፡ ይፈሯታል፡፡ የተጋነነ ቁንጅናዋና ውድ ጌጣጌጦቿ የማትደፈር
ግዛት ስለሚያስመስሳት የሚመኛት እንጂ ድፍሮ የሚቀርባት ጠፋ፡፡

የአበሻ ወንድ ተመካከሮ ሸሸ

ዛፒ ታዲያ የለየላት ስካራም ሆነች። ማታ ማታ ሰክራ ትመጣና፣
በምን አባታችሁ ዕድላችሁ ነው እኔን የምትስሙት!? እዛ የጉራጌ ጫማ ደንቅረው የቻይና ሱሪ ውስጥ የተቆጠሩ ኋላ ቀር ሠራተኛ ሴቶቻችሁ ጋር ኑሩ! ጎ ቱ ሄል ቆሻሾች! ቦርጫሞች! ቀ'ጂም'
አጠገብ አልፋችሁ የማታውቁ” እያለች በረንዳዋ ላይ ቆማ ድፍን የአበሻን ወንድ ትሳደባለች ።

በጣም ስከር ብላ ጨርቅ ሆና ያመጣት ባሰታከሲ ግቢ ውስጥ ደግፎ አስገብቷት ሲመለስ
ትጠራኛለች፣

“አሸብር ና ጫማዩን አውልቅ!”
👍26👏1
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስር

....ጥቁር አምበሳ፣ ኮከብ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲስ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ የአስረኛ
ክፍል ተማሪዎች ሁሉ፣ “አንደኛ ጎበዝ አንተ ነህ” አሉና የምስክር ወረቀት ሸለሙኝ፡፡ እኔ ግን ጥቁር አምባሳ፣ ኮከበ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲስ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ቆንጆ የሆነችው ዮርዳኖስ የት ተቀምጣ ይሆን እያልኩ በዓይኔ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀል እየፈለግኳት ነበር፡፡

ዮርዳኖስ ማለት ማንም አይደለችም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሬት ተነስታ ጉንጬን የሳመችኝ ልጅ ናት፡፡ ጉንጬን ሳይሆን በቀኝ በኩል ከከንፈሬ ጥግ ሁለት….አረ አንድ ተኩል ሴንቲ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሳመችኝ (ለሞላ ጉንጭ፡፡)

ዮርዳኖስ ቀይ ልጅ ናት፡፡ ለነገሩ ቀይ ሳትሆን ጠየም ያለች ግን ቀይ ዳማ እንደሚሉት ሳትሆን
አትቀርም፡፡ አቦ የራሷ ጉዳይ ገደል ትግባ ብትፈልግ ኤጭጭጭ!! ይሄው ስንት ጊዜ ሌትም ቀንም
ዮርዳኖስ ቀይ ናት ቀይ ዳማ እያልኩ ስዛብር ማደር ከጀመርኩ፡፡ እንኳን ሴት ልጅ፣ ቆንጆ ወጣት ሴት ልጅ፣ ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ ሰው ሲስመኝ የመጀመሪያዬ ስለነበር ዮርዳኖስ ጉንጬን
ሳይሆን ልቤ ላይ እንደሳመችኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ማስረጃ ብባል፣ ከዛን ጊዜ ጀምሮ አተነፋፈሴ ልክ አይደለም፤ ሳያት የሆነ ነገር ያፍነኛል፡፡ ሳላያት እንደ ነብር አዳኝ ትንፋሼን ውጬ በጉጉት በዓይኔ እፈልጋታለሁ፡፡ ሳላያት ታፍኜ ሳያትም ታፍኜ ልሞት ሆነ፡፡

"አንቺ ዮርዳኖስ የምትባይ፤ ምን ቆርጦሽ ነው ኧረ ከከንፈሬ አንድ ተኩል ሴንቲሜትር ርቀት
ላይ በሚሞቅና በሚለሰልስ እርጥብ ከንፈርሽ የሳምሽኝ?” ብላት ደስታዬ፡፡ ግን ታፍኛለሁ!!

አርብ ቀን ከትምህርት ቤት ወጥቼ ወደ ቤቴ እሄዳለሁ፡፡ ምንም እያሰብኩ አልነበረም፡፡ ዝም
ብዬ እየተራመድኩና በግዴለሽነት ሁሉንም ከፊቴ ያለውን ነገር እየተመለከትኩ እራመዳለሁ፡፡

“አሸብር፣” አለችኝ ከኋላዬ፡፡

ስሜ ሲጠራ የምደነግጠውን ያህል የሰይጣን ስም ቢጠራ እንኳን አልደነግጥም፡፡ ሰዎች ስሜን ሲጠሩኝ ከዝምታዬ ባሕር በምላሳቸው መንጠቆ ጠልፈው ያወጡኝ ይመስለኛል፡፡

ጭራሽ ጠሪዎ ዮርዳኖስ ስትሆን ደግሞ፣ በመንጠቆው ላይ መረብ ተተበተብኩ !! ከእኔ ጋር
ብዙ ሰዎች ወደኋላ አብረው ዞሩ፡፡ ሰዉ ሁሉ ሳይጠራ ሲዞር፣ ጠሪዋን ተመልከቶ ደሰ ካሰችው
ስሙን አሸብር ሊያስብል ያሰበ ይመስል እኔ ለተጠራሁት መዓት ሰው ዞረ፡፡

ዮርዳኖስን ዞሬ አየኋት፡፡ ጉርድ ቀሚሷ በደንብ አላራምዳት ስላለ በእጇ ሰብሰብ አድርጋ ወደ
እኔ ትጣደፋለች፡፡ እግሯ ቀይ ነው፡፡ ባቷ ፍርጥም ያለ ከእድሜዋ በላይ ትልቅ የሚያስመስላት
ነው፡፡ ባቷ ብቻውን አስራሁለተኛ ክፍል ይመስለኛል። ጡቶቿ ደግም እዛና እዚህ ይላጋሉ:: ስትጣደፍ፣ በሁለት እጆቿ ክንዶች ገፋ አድርጋ ታረጋጋቸዋለች፡፡ ፀጉርዋ አጭር ነው፡፡ ግንባሯ ትንሽ ወጣ ያለ፡ ቀረበችኝ ፈገግ አለች፡፡ ዓይኖቿ እንዴት ያምራሉ፡፡

ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍ አሁን ስትጠራኝ መኪና እየነዳሁ ቢሆን ኖሮ ከዓይኖቿ ለማምለጥ ስል
ፊት ለፊት የሚያላዝነው ቦት መኪና ጋር እላተም ነበር፡፡ የያዘው ነዳጅ ይዘረገፍና ከዮርዳኖስ
ፈገግታ እሳት ለኩሶ ጭሱ ፀሐይን ጥቁር ጉልቻ እስከትመስል የሚያጥን፡፡ ሰማይ የሚነካ እሳት
ይነሳ ነበር፡፡ በቁሜ ቅዥት ስጀምር ታወቀኝ፡፡

“እንዴት ነው የምትርጠው ወተት ጥደሄል ቤትህ ?” ቀለደች።

አልሳቅኩላትም፡፡ ስላልሳቅኵላት ግን ራሷ ከመሳቅ አልታቀበችም፡፡ እየሳቀች ወሬዋን ቀጠለች፡፡

"ቤትህ በዚህ በኩል ነው እንዴ ?”

“እዎ"

“እኔ ግን አይቼሀ አላውቅም"

ዝም አልኩ፡፡ ካላየችኝ ምን ይሁን፣ ወሬዋን ቀጠለች፡፡
አዎ

አዎ

አዎ

“አዎ ብቻ ነው እንዴ የምታውቀው ?
“አይ” እላታለሁ፡፡ አነጋገሬ ሴት የመፍራት ሳይሆን ሰው የመሰልቸት ነበር፡፡ እንዳንዴ የሰዎች ንግግር ይረዝምብኛል፡፡
"ሰላም ሲሉኝ ይረዝምብኛል፡፡ ሰላም፤ እጃቸውን አንስተው፣ ግንባራቸውን ነቅንቀው፣ ፈገግ
ብለው፡፡ አንዳንዴም እጃቸውን ለሰላምታ ዘርግተው፣ ይሄን ሁሉ አድርገው፣ “ሰላም” ብቻ "

ዝም አለች፡፡ አብረን ሄድን ሄድንና የሆነ መገንጠያ ላይ ስንደርስ ክንዴን ይዛ አቆመችኝና ተንጠራርታ ሳመችኝ፡፡ ምንም አላማ የሌለው፣ ምክንያት የሌለው ወይም “ደፋር ነኝ አየህ" የሚል ምናልባትም፣ “ዘመናዊ ነኝ መንገድ ላይ የወንድ ጉንጭ መሳም አልፈራም” አሳሳሟ
የሆነ ድምፅ አለው፣ የሚያፏጭ ዓይነት ድምፅ፡፡ የመምጠጥ አይነት ድምፅ፡፡ የበዛ ግለኝነቴን
ምጥጥ አድርጋ የሐሳብ ሀይቄን አደረቀችው፡፡ የሰው አለማያ ሆንኩ !! ባደረቀችው የብቸኝነት
ኩሬ ራሷን ሞላችው፡፡እዚህ ዮርዳኖስ የምትባል ውሃ የሞላችው ባህር ውስጥ ልቤ አምልጦኝ ገባ፡፡ ይሄው አስባታላሁ፣ የተረገመች ዮርዳኖስ ! እየጠበቀችኝ ይሁን እየተገጣጠምን ብቻ ከዛን ጊዜ በኋላ በየቀኑ እንገኛኝ ጀመረ፡፡ ሲቆይ ግን ጉዳዩ የነፍስ ቀጠሮ ሆነ፡፡ ጠበቅኩሽ ላለማለት በቀስታ እየተራመድኩ እጓዛለሁ፣ ከየትኛውም ርቀት ላይ አውቃታለሁ፡፡

ፊት ለፊት ሳላያት መንፈሷ እዛ አካባቢ ካረበበ ትካሻዬ ሹክ ይለኛል፡፡ ትከብደኛለች፣ “ሃይ አሹ” የሚል ድምጽ እጠብቃለሁ፡፡ ሀይ አሹ ትለኛለች ውስጣችን ያውቃል እንደምንጠባበቅ፡፡ ከዛም ታወራኛለች።

"ዛሬ ይበርዳል!”

"አዎ"

"ሆም ወርክ ሰራህ ?”

"አዎ"
.
.
.
“አዎ ብቻ ነው የምታውቀው፡፡”

"አይይ"። አሁን ግን ምን ማውራት እንዳለብኝ እያሰብኩ ነው ችግሩ፣ አስቤ ሳልጨርስ እንደርሳለን፡፡

ስንመለስም እንገናኛለን፡፡ ስንመለስ መለያያችን ላይ ትስመኛለች፣ “ቻው” ከሚል ስርቅርቅ ያለ መለያየቱ ያስከፋው ድምፅ ጋር ከንፈሯ ጆሮዬ ላይ ያፏጫል፡፡

አንዴ መሀል ጉንጩ ላይ፣ አንዴ ዝቅ አንዴ ከፍ እያለች ትስመኛለች፡፡ በየቀኑ ትስመኛለች፡፡ ዝም ብዬ አሳማለሁ፡፡ ከንፈሯ ክብ ነው፤ በሃሳቤ ስትስመኝ ከብ ቅርፅ ጉንጩ ላይ የታተመ ይመስለኛል፥
የሳምንቱ ክቦች ተቆላልፈው፤ ቅዳሜ የኦሎምቲካ አርማ ጉንጩ ላይ ታትሞ በጉልህ ይታየኛል፡፡
እንዱ ከብ እንደ ደቡብ ኦሞ ሴቶች፣ ከንፈሬን ተልትሎ ከንፈሬ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት በህልሜ!

አንድ ቀን ግጥም ጻፍኩ፡፡ በህይወት ዘመኔ የጻፍኩት ብቸኛ ግጥም ነበር፡፡ ወደፊትም ግጥም
አልጽፍም " ግጥም ያስጠላኛል፡፡ ሰው ዝም ማለት እያለለት፣ ለማውራት ቃል መጠምዘዝ
መድከም ምን ያደርግለታል? ቢፅፍ ላይጠቀም፣ ባይፅፍ ላይጎዳ ባይ ነኝ፡፡ ደግሞ አዲስ
ግጥም ሰምቼ አላውቅም፡፡ ግጥሞች ሁሉ አንድ ናቸው፤ ደራሲያቸው ይለያይ እንጂ ባይ ነኝ::

እኔን የገረመኝ (ርእሱ)

እኔን የገረመኝ፣
እኔ የጠላሁትን፣
እኔነት ሳትጠላ፤
ልጅቱ ስትስመኝ !!

በቃ !! ይሄው ነው ግጥሙ።

ግጥም ማለት ቤት የሚመታ፣ ቀለሙ፣ ስንኙ የሚሉ ሰዎችን ተዋቸውና ግጥም ማለት እስክርቢቶ ሳትጨብጥ ወረቀት ፊትህ ሳይነጠፍ አንደ አፍ ወለምታ ከከንፈርህም፣ ከነፍስሀም፣ ከአዕምሮህም
የሚያመልጥ እውነት ነው፡፡ ለምሳሌ በዚች ዓለም ላይ ከሰማኋቸው ግጥሞች አሳዛኙ የአቲዬ ግጥም ነው፡፡ ርእሱ፣ “እሺ፤ ግጥሙም፣ “እሺ” አበቃ፡፡

ማንም ለጀመረው የትዕዛዝ ስንኝ፣ አቲዩ 'እሺ' የሚል ግጣም እየሰራችለት፣ የማንም ቤት
እንዲቆም አድርጋለች። የእኔ እናት ገጣሚ ናት፡፡

“ቤት ጥረጊ!”
“እሺ!"
“ልብስ እጠቢ”
“እሺ”
“ሂጂና ሳሙና ግዢ!
"እሺ"
“እንጀራ ጋግሪ”
"እሺ
“ደመወዝሽን ሌላ ቀን ውሰጂ!”
"እሺ"
ግጥም ይሄ ነው !! ከትዕዛዘ እኩል ይሁንታው ዜማ ሲፈጥር፡፡ እናም ያሉትን ሲሆኑ፡፡
👍39
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_አንድ

...ዮርዲ” ነው ያልኩት ? ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ከአቲዬ ቀጥሎ በዚች ምድር ያቆላመጥኩት ስም እነሆ..

ጠዋት ዩኒፎርሚን ለብሼ ደብተሮቼን አዘጋጀሁና እየቀፈፈኝ ወደ ትልቁ ቤት ሄጀ አንኳኳሁ፡፡

“ማነው?” አለችኝ ዛፒ፡፡ ደነገጠኩ፡

እኔ ነኝ አልኩ እየፈራሁ፡፡

«ግባ ክፍት ነው»፡፡ ገፋ ሳደርገው የሚያብረቀርቀው የጣውላ ሰር ድምፅ ሳያሰማ ተከፈተ ክፍቱን ነው ያደረው ማለት ነው::
ዝርከርክ ያለው ሳሎን ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ ዛፒ ሶፋው ላይ
የአልጋ ልብስ ጣል አድርጋ ተኝታለች፡፡ ፊቷ የተቀመጠው ጠረጴዛ ላይ የሻይ ብርጭቆ፣ የውሃ ጠርሙስ፡ ሩቡ ብቻ የተበላ ሰላጣ፣ ምንም ያልተነካ ዳቦ ዝርክርክ ብሏል፡፡ ብዙ ምግብ
ማቅረብና ምንም አለመብላት ልማዷ ነው ይገርመኛል፡፡

“ምንድነው በጠዋቱ“ አለች እየተነጫነጨች፡፡ ድምጿ የወንድ ይመስላል ጎርንኗል፡፡

"እ..ትምህርት ቤት ከሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደኛ ወጣሁና ልንገርሽ ብዬ ነው"
ድምጼ ተንቀጠቀጠብኝ፡፡

ቀጥ ብላ ግራ በገባው ፊት እየችኝ፡፡ የሌሊት ልብሷን ትከሻዋና ትከሻዎ አካባቢ ይዛ አስተካከለች!
አቤት ደረቷ ቅላቱ ይንቦገቦጋል፡፡ ከኋላው ቢጫ መብራት የበራበት መስተዋት ይመስላል፡፡

"እኔ ምናገባኝ ታዲያ?!" የምትል መስሎኝ ነበር፡፡ ድንገት የሆነ ነገር ትዝ እንዳለው ሰው ፈገግ ብላ፤

"እና ሳመኛ! እንደዚህ ነው እንዴ የምስራች የሚነገረው? መርዶ አስመሰልከው እኮ!” አለችኝና
ሁለት እጆቿን እንደ ክንፍ ዘረጋቻቸው፤ ያውም በፈገግታ፡፡ ሁለት ጡቶቿ አፈጠጡብኝ፡፡

ግራ ገብቶኝ እንደቆምኩ፣ ና እንጂ ሳመኝ!” ብላ ጮኸትብኝ፡፡

በደመነፍስ እየተደነቃቀፍኩ ሄጄሄጄ ሄጄ ሄጄሄጀ.ሄጀ እጆቿ ሲጠመጠሙብኝ ሁሉ እርምጃዬን
ያቆምኩ አልመሰለኝም፡፡ ጥብቅ አድርጋ እቅፉኝ፣ “ጎበዝ የኔ ወንድም እኮራብሀለሁ!” አለችኝ፤
በለው ! ከሽ አለ የሻዩ ብርጭቆ ከጠረጴዛው ላይ ወድቆ፡፡ “ይሰበር ተወው!” አለቸኝና ጉንጬን
ስማ ለቀቀችኝ፡፡ ይሄ ቤት ለካ የወይዘሮ እጥፍወርቅ ቤት ነው !!

ከዛፒ ጋር እንደወጣሁ በደስታ ሰከሬ መንገዱን ሁሉ፣ ሰውን ሁሉ አየሁት፡፡ መቼ ነው ይሄ ትልቅ
የመኪና ኪራይ ማስታወቂያ ነዳጅ ማደያው ፊትለፊት የተሰቀለው ? መቼ ነው ይሄንኛው ሕንፃ
ተሰርቶ ያለቀው? ወቸ ጉድ አዲስአበባ እንዴት ተለውጣላች? ከሆነ አገር የመጣሁ መሰለኝ፡፡
ደግም ደስ የሚል ነገር ይሸተኛል፡፡ አፍንጫዬም ዛሬ ገና የተከፈተ ይመስል።

ዮርዳኖስ ጋር ስንገናኝ፣ “ምነው?” አለችኝ፡፡

"እ" አልኳት፡፡

"አይ ቆመህ ሳገኝህ ነዋ” አለችኝ፡፡ ለካስ ዮርዳኖስን ቆሜ አልነበረም የምጠብቃት። ያልጠበቅኳት
መስዬ ነበር መጠበቅ የነበረብኝ፡፡ ሳመችኝ ጉንጬን፡፡ ዛፒና ዮርዳኖስ እኔ በምባል ኳስ
በከንፈራቸው እየተቀባበሉ ቮሊ ቦል የሚጫወቱ መሰለኝ፡፡ "ተስመህ ትወጣለህ፣ ሰመው
ይቀባሉሀል የሚል ትንቢት ከሰማይ የታወጀም መሰለኝ፡፡ ድፍን አዲስ አበባ እንደ ዳቦ፡ እንደ
ዘይት፣ እንደታክሲ እኔን ለመሳም የተሰለፈ መስሎ ተሰማኝ፡፡(ቀስ ትደርሳላችሁ አትጋፉ ሂሂሂሂ)

ዮርዳኖስ ፈገግ ብላ አፍንጫዋን በመቀሰር ጠጋ አለችኝና፣ ደሞ አሪፍ ሽቶ ፣ እፉፉፉፉፉፉ
ያደረጉብ ማነው?" አለችኝ:: አፈርኩ፡፡ ለካ የዛፒ ሽቶ ነው ሲከተለኝ የነበረው፡፡ የዛቲ ሽፋ
የዋዛ አልነበረም፡፡ ከዚች ቀን ጀምሮ እድሜ ልኬን ሲከተለኝ ነው የኖረው፡፡ ሲያሳድደኝ ሳይሆን
ሲከታለኝ፡፡ የሆነ ዙሪያዬን ከብቦ እንደ እናት አቅፎኝ፡፡

ሰው ወደ ውስጥ የሚስበው አየር እክስጅን፥ ወደ ውጭ የማያስወጣው ካርቦንዳይ ኦክሳይድ እያሉ ያስተማሩን ቅኔ ነበር ሳይንሳዊ ቅኔ !! አሁን አሸብር ወደ ውስጥ የሚስበው ፍቅር፣ መፈቀር፣ መከበር፣ መፈለግን ነው፡፡ ወደ ውጭ የሚተነፍሰው እርካታ፡፡ የአየር ብክለት ማለት ሌላ ትርጉም የለውም እኮ የተገፉ፣ የተገለሉ፣ የተናቁ፣ ሕዝቦች ጥላቻን ወደ ውስጣቸው ሰበው መልሰው ጥላቻን ወደ መላው ዓለም መተንፈሳቸው ነው:: መፍትሄው የፍቅር ችግኝ በልባቸው
መትከል ነው:: እነሆ ዮርዳኖስ የተከለችውን ዝግባ ዛፒ የምትባል ዝናብ ስታረሰርሰው ዘርፈፍ
ብሎ በቀለ፡፡ ሕያውነት ከስሩ አረፍ የሚልበት ጥላ ሆነ፡፡

እኔማ ዛፒ ጥቁር ደመና አዝላ እያጉረመረመች ሰማይ ላይ ተንጠልጥላ ሳያት፣ መሽቆጥቆጥና ጥላቻዬን እንደ ዥንጥላ ስዘረጋ ነበር የኖርኩት፡፡ ክፉትም ጉልበት የሚኖረው እንደክፋት ልንቀበለው በተዘጋጀነው መጠን ነው::

“አንተ ሴት ነህ እንዴ?” ብላ ዛፒ ሳቀችብኝ፡፡ አፈርኩ፡፡ አንደኛ መውጣቴን ምክንያት በማድረግ
ዛፒ ልብስ ልትገዛልኝ ወሰደችኝና ምረጥ! ስትላኝ መጀመሪያ እጄ አንድ ቀሚስ ላይ አረፈ፡፡
ለእቲዬ ልኳ የሚሆን ቀሚስ ነበረ፡፡ ለዛ ነበር የሳቃችው::ልብስና ጫማ ገዛችልኝ፡፡ የሱሪዬን ቁጥር ስጠየቅ አላውቅም ነበር፡፡ ሱሪ ገዝቼ አላውቅማ፤ የጫማ
ቁጥርም አላውቅም፡፡ የሀብታም ልጆች ልብስና ጫማቸው ከሱቅ የተገባ ሳይሆን አብሯቸው
የሚወለድ ይመስለኝ ነበረ፡፡
ሃሃሃ… ግን ይሄው ሁሉ ነገር ሱቅ ውስጥ አለ ሸቀጥ ነው፡፡ ያው እዛጋ ቶማስ የሚባለው
ሁልጊዜ በሴት የሚከስሰው የክፍላችን ልጅ ጫማ ይሄው የራሄል ቦርሳ ኧረ ጉድ የቲቸር
ተስፋ የጥቁር ባለ ብዙ ኪስ ጃኬትም ያውና፡፡ ትንሽ ብቆይ እነዛ ውድ ነን የሚሉ ልጆች
እዚህ ተደርድረው ሲሸጡ አገኛቸው ይሆናል፡፡
ሲገርም ሁለት ሱሪ፣ አንድ ጫማ፣ ሁሉት ሸሚዝና አንድ ሹራብ ነፍስ ካወቅኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ልብስ ከሱቅ ገዛሁ፡፡ ለካሁት፡፡ መስተዋቱ ፊት ስቆም ደነገጥኩ፡፡ ልብስ ማለት ተራ ድሪቶ ነው ምናምን የሚሱ ሰዎች እንዴት ጅሎች ናቸው እባካችሁ! ራሴን በመስተዋት ሳየው ታላቅ ፍንዳታ እዕምሮዬ ውስጥ ተፈጠረ፡፡

እወራረዳለሁ ጥቁር አምበሳ፣ ኮከበ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲሰ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ቆንጆና ወንዳወንድ አቋም ያለኝ ልጅ እኔ ነኝ !! እፎይ! ከቤተክርስቲያን ሃጢያቱን ተናዞ እንደወጣ ሰው ሸክሜ ቀለለኝ አደግኩ ደግሞ !! የክፍሌን ልጆች በየቤታቸው እየሄድኩ እጄን ኪስና ኪሴ እስገብቼ “ሃይ!” ማለት አማረኝ፡፡

ዛፒ የለበስኩት አዲስ ሹራቡ ላይ የነበረውን ወረቀት ከኋላ ክሩን በጥርሷ በጥሳ አላቀቀችልኝና፣
አንተ ልጅ ቆንጆ እኮ ነህ አለችኝ፡፡ በሙቅ ውሃ በተሞላ ገንዳ ውስጥ የመግባት ያህል ቓሏ ይሞቅ ነበር፡፡ ቆንጆ መሆን ማለት የአፍንጫ መሰልከከ፣ የዓይን መንከባለል፤ የጥርስ መደርደርና
ንጣት ማለት አልነበረም፡፡ ለኔ ቆንጆ ማለት በሰው ዓይን መሙላት ማለት ሆነልኝ፡፡

ዝም ብላችሁ የሕይወት መንገዳችሁኝ ዙሩና ተመልከቱ! አለቀ ያላችሁበት ቦታ ላይ የነበረውን የሚመጣውን የሚያያይዝ ድልድይ ይኖራል፡፡ ይሄን ድልድይ የሚያምኑ ፈጣሪ ነው ይሉታል የማያምኑ 'የስነሕይወት መርህ ነው' ይሉታል፡፡ ለእምነቱም ለሳይንሱም ግድ የማይሰጣቸው እድል ይሉታል፡፡ እኔ ግን ይሄ አንዴ በዛ አንዴ በዚህ የሕይወቴን ተራዳ አየደገፈ የሚያቆመው
ከአቲዬ ድፍን ሃምሳ ብር የተበደረው እግዚያብሔር ነው እላለሁ፡፡
👍3316
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_ሁለት


...ጠላትህ የትም የሚገኝ እንደ ትቢያ እያፈስክ የትም የምትበትነው ገላባ ነው። አስተማሪ ብትሆን ከጠመኔህ ስር ጠላትህ አለ። ጥላቻ አእምሮው ውስጥ እየዘራህ ሰይጣን ታፈራለህ፡፡ ሹፌር ብትሆን የጠላትህ ነፍስ በእጅህ ነው፣ ይዘኸው ገደል ልትገባ ትችላለህ፡፡ ግንበኛ ወላ አናፂ ብትሆን
ምትሰራለት ቤት በላዩ ላይ ፈርሶ እንዲቀብረው የማድረግ ስልጣን በእጅህ ነው፡፡ ባለሰልጣን ከሆንክማ፥ እባቡም ከእግርህ፣ ዱላውም ከእጅህ ብትፈልግ ቀይሽብር ወንጀለኛ' ምናምን
ቅብርጥስ ብለህ በየመንገዱ ትደፋዋለህ፡፡ ካሻህ እድሜ ልኩን በድህነት እንዲማቅቅ ታደርገዋለህ፡፡

ደግሞ ለበቀልህ ማን ይተባበረኛል?' ብለህ አትሰጋም፣ ሕዝቡ ራሱ ለመባረክ ስትቆም ነጠላውን አጣፍቶ ከጎንህ ነው፡፡ ለማረድ ስትቆምም ቢላውን ስሎ ከጎንህ ነው፡፡ ከሌላ ዓለም ረዳት
መጥራት ሳያሻህ፤ ወንድሙ ላይ የሚጨከን ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ሕዝብ ጠላትህ ከሆነ
አደግድጎ ለበቀልህ ታዛዥ ነው

ደነዝ ሕዝብ፣ ደነዝ መሪ እንደሚወልድ እስኪገባው ትጫወትበታለህ፡፡ ጭራቅ ሕዝብ፣ ጭራቅ መሪዎች እንደሚፈለፍል እስኪያውቅ ታሸዋለህ፡፡ አዎ ጠላትህ ሕዝብ ከሆነ በቀልህ ቦታ እና ጊዜ ሳይመርጥ የትም ሊፈፀም ይችላል፡፡ ደግሞ ታዝበህ ከሆነ ከልብህ የሕዝብ ጠላት ከሆንክ ሕዝብ ይወድሃል፡፡ ስላንተ ይዘምራል፡፡ ጀግና! እያለ ሲያወሳህ ይኖራል፡፡ ለምን መሰለህ፤
ውስጡ ያለው ጭካኔ ነው በአደባባይ ያሳየኸው !

ወዳጁን እየካደና እየቀረጠፈ ውለታውን ትቢያ የሚያለብስ ሕዝብ የትናቴን ጉልበት እንደምስጥ መጥጦ እንጨቷን አስቀረ ብዪ አላዝንም፡፡ ሰው እሆናለሁ፡፡ በእኔ ሰው መሆን ትላንት ፍሬ የምትሰጥ ለምለም ዛፍ የነበረች ሕዝብ ያደረቃት እናት የምትባል እንጨት ከማገዶነት አፋፍ ተመልሳ እንደ እሴይ በትር ትለመልማለች፡፡

ያኔ በልጅ ልጆቿ ልብ ውስጥ ከቅዱስቅዱሳኑ ለዘላለም በከብር ትቀመጣላች፡፡ ቱ! አሸብር
አይደለሁማ !

አዎ ታጋይ ነኝ !! ታጋይ በሴት አይፈትንም፡፡ ሴቷ ቀይ እግር ቢኖራትም፤ አይኗ ቢያምርም፣
ተንጠራርታ ብትስምም፣ ስሟ ዮርዳኖስ ቢሆንም፣ ማታ ማታ ትዝ ብትልም፣ ከነድሪቶቹ
ብትቀርበኝም የጠላት ልጅ ያው ጠላት ነው !! ዮርዳኖስን ርግፍ አድርጌ ተውኳት !

ከባድ አልነበረም፡፡ እንዲያውም ዐይኔን ስገልጥ ዮርዳኖስ ለእኔ ሸክም ነበረች፡፡

በብልጣ ብልጥ ሴትነት ነገን አሻግራ ያየች፣ መረቧን ተሽክማ ግራ በገባው አሳ ዙሪያ የምትሸከረከር ብልጥ ሴት፡፡ እሾሁን አራግፋ ልትቀረጥፈው !! ተውኳት፡፡

“ልብሱን ሲቀይር ተወኝ አለች ተባለ፤ እሷ የድሮ ልብሷን የሆነች ይመስል፡፡ ብዙ ፆታዊ
ግንኙነቶች ላይ ኣለመፈለግ ክህደት ተደርጎ ይታያል፡፡

አስራ ሁለተኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ዩኒቨርስቲ ሲገሱ ከትዘጋጁ ጥቂት ተማሪዎች
መካከል አንዱ እኔ ነበርኩ አራት ነጥብ : አራት ነጥብ የሚባል አንድ ጠመንጃ ይዤ ለትጥቅ
ትግል ዩኒቨርስቲ ወደሚባል ጫካ ልዘምት ተዘጋጀሁ፡፡

ዛፒ እንጅ የናጠ የሃብታም ልጅ ሊኖረው ከሚችለው በላይ ልብስና ጫማ፣ ለሎችም ቁሳቁሶችን
ከአገር ዉስጥ ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቿም ጭምር አስመጥታ አምባሻበሻኝ፡፡ ምርር ያለ ቤተሰባዊ ፍቅር ውስጥ ገብተን ነበር፡፡ ዕይኗ ይወደኝ ነበረ ያስታውቃል፡፡ በተለይ አስራ ሁለተኛ ከፍል ተፈትኜ ውጤት ስጠብቅ ከዛፒ ጋር ያሳለፍነው ጊዜ የማይረሳ ነበረ፡፡
ያልዞርንበት መዝናኛ አልነበረም፡፡ የትም ስትሄድ ከ አለሁ፡፡ እኔን “ወንድሜ ብላ ማስተዋወቅ
እንዴት እንደሚያኮራት ዐይቼ ራሴን ለወንድምነት አሳልፌ ሰጥቻለሁ፡፡ የእውነትም ደግሞ
ወንድሟ እመስል ነበረ፡፡ ዛፒ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለአቲዬም ደግነቷ ተንሰራፍቶ ነበር፡፡ ማታ
ማታ ቡና ተፈልቶ በረንዳ ላይ ወይም ሳሎን ደስ የሚል ጊዜ ሦስታችንም እናሳልፋለን፡፡

ዛፒን ከምቾት ጋር ያገለለ ዓለም እኔና አቲዬንም ከጉስቁልና ጋር የተፋ ሕይወት በምን ሂሳብ
እንዳቀሳቀሰን ባይገባኝም ቅልቅሉ ግን ከልብ የሆነ ቤተሰባዊ ትስስርን ፈጥሮ ነበረ፡፡

አንድቀን “አቲዩ!አልኳት፣

“አቤት!”

“ምን ብሆን ደስ ይልሻል?”

“ኧረ እኔ ምን አውቄ፣ እኔ ትምርት የለኝ አላቀው“ ብላ ሳቀች፡፡

“ግዴለሽም ተምሬ እኔ ልጅሽ ምን ብሆንልሽ ደስ ይልሻል?”

“እሷን አማክራት እስቲ“ አለችኝ ዛፒን ማለቷ ነበር፡፡

“አቲ ዛሬ ካልነገርሽኝ አልለቅሽም ራስሽ ንገሪኝ"

ትንሽ አሰበችና፣ “ዶፍተር” አለችኝ በሳቅ፡፡ ሁለታችንም ባሳቅ ፍርስስስስ አልን።

አነጋገሯ በዕርግጥም ያስቅ ነበር፡፡ ህክምና የመማሬ ብቸኛ ምከንያት ይሄው ነው!! ሕዝቤንና
ውገኔን ከበሽታ ለመታደግ ምናምን በዬ አልነበረም!! እናቴ፣ የምወዳት እናቴ፡ የእዕምሮዋ ጥግ
የታላቅነት መጨረሻ የመሰላትን ነገር ለመሆን እንጂ!!

የዩኒቨርስቲ ቆይታዬ የደስታና የቅንጦት ነበረ፡፡ ዛፒ ውብ ሆና ግቢ ስትመጣ ዐይኑን የማይጥልባት ተማሪ አልነበረም፡፡ ብዙ ሰው እናቴ ያደርጋት ነበረ፡፡ ሴቶቹ የዛፒ ጫማና ልብስ ላይ ዐይናቸው ይጎለጎላል፡፡ ከዚህ የቆንጆ ዘር በረከቱን ሊካፈሉ የቋመጡ፣ በስልምልም ዐይን፣ በጨዋ መሳይ ፈገግታ ሲቀርቡኝ ሲዞሩኝ ነበር፡፡ 'ፀዳ ያለ ልጅ ይሉኛል፡፡ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ! አላልኳችሁም፣በድፍን ግምት ወደድን ብለው ከሰልፍ ሊያስወጡ መሞከር ይሄ ነው እኮ፣

የወደዱኝን ያከበሩኝን ሁሉ ቁምነገር ባለመቁጠር በቀሌን አንድ ብዬ ጀመርኩ፡፡ ኮተታሞቹ
የግቢ ልጆት ራሳቸውን ችለው መቆም ይፈራሉ፡፡ ሴቶቹ ወንድ ታዛ ስር ካልተጠለሉ ሰው የሆኑ
አይመስላቸውም፡፡ ወንዶቹ የተፈጥሮን ጾታዊ መፈላለግ
ሳይንስ ሊያደርጉት ጅራት ሲቆሉ፣ ግራ የገባቸው የከተማ ልጆች ጭልጥ ወዳለው ማሕበራዊ እንስሳነት ሲወርዱ፣ በግቢያችን ውስጥ እንደሰው መኖርን ያጣጣምኳት እኔ ከፍ ባለ ክብር እየተማርኩ ሁሉንም ተማሪ ፅንፍ በሌለውጥላቻና ንቀት እመለከት ነበረ፡፡

የናቀውን የሚወድ ሕዝብ ግን ከጎኔ ነበር! አሹዬ፣ እሹጎት፣ ሹ፣ .ሸቢ፣ ሹሹ፣ ከቤተሰቦቻቸው
የወረሱት እባብነት የስም ግንድ ላይ ሲጠመጠም ላለመነደፍ ልቤን ቆዳ አልብሼው ነበረ፡፡
ማቆላመጥ የሚወድ ሰው ጤነኛ አይመስለኝም፡፡ አጭበርባሪ ነጋዴ ነው የሚመስለኝ። በየስሙ ላይ ዬ' መለደፍ የፍቅር ሃዋሪያ መሆን ይመስላቸዋል፡፡

የቤተሰቦቻቸው መርዝ አልሰራ ሲል፣ (የተመረተበት ጊዜ አልፎ እንዳይሆን ሰግተው) ከፊልምም
ከመጽሄትም አዳዲስ መርዝ እየተሸከሙ ብቅ ይላሉ፡፡ በአነጋገር፣ በአለባበስ፣ በአስተያየት፣ በእግር፣ በዳሌ፣ በጣት፣ በፀጉር እናም በመጨረሻ በሃሜት፣ “ይሄ ልጅ ሴት አይመቸውም እንዴ? ማን ያውቃል? ዘመኑ ክፉ ነው እናትዬ፣ እንትን እንዳይሆን::

እነሱ ጋር ያልሆነ፣ እነሱን ያልፈለገ ጭራ አለው፤ ደብቆት ነው እንጂ፡፡ ቀንድ አለው፣ ጥፍር አለው፡፡ በዚህች ምድር ላይ እንደመናቅ የሚያም ነገር የለም፡፡ ንቀቴ አመማቸው !!

ቡምምምምምምምምም እውነት ፈነዳ !! “ይሄ ቀብራራ እዚህ ይኮፈሳል እናቱ እኝጀራ ጋጋሪ፣
ልብስ አጣቢ ነች አሉ”፡፡ ጮማ ወሬ ተገኘ፡፡ ዳሌያቸውን እየናጠጡ ፀጉራቸውን እየነሰነሱ፣ ጅራታቸውን ከሚቆሉላቸው ወንዶቻቸው ጋር አወሩ፡፡ ተሳለቁ፡፡ ሲያሸማቅቁኝ ሞከሩ፡ ራሳቸውን
ችለው መቆም ሲፈሩ፣ የእፉኝት ልጆች በልብስ አጣቢ ልጅ ሳቁ፡፡ የቤታቸውን አጠራቅመው
ለዘመን መለወጫ ቤታቸውን የሚያፀዱ ሁሉ፣ ሰው ሰራሽ ጠጉራቸው ራሳቸው ላይ ጀልቶ በጾም በጸሎት የሚፈታ ሁሉ፣ ተብረቅርቀው ሰው ነን ሊሉ፡፡ ልክ ለልክ ከተዋወቅን ቆየና ይሄም ጥይታቸው ከሸፈ፡፡
👍383👎1🥰1
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_ሦስት

....ዩኒቨርስቲ ውስጥ የነበረኝ ሕይወት የአንድ መልካም ተረት ፍፃሜ ይመስል ነበር፡፡ ልክ
ከዛም በሰላምና በደስታ ይኖሩ ጀመር” ተብሎ እንዳለቀ ተረት፡፡ ብር አልቸገርም ነበር እድሜ
ለዛፒ፡፡ ጊዜ ባገኘሁበት ቀን ሁሉ አቲዬን አያታለሁ፡፡ በየቀኑም እደውላለሁ፡፡ አቲዬን በስልክ
ማውራት ከባድ ነው፡፡ በቃ ጥያቄዎቿ አንድ ዓይነት ናቸው፤ “
እንጀራው ጥሩ ነው ?”፣ “ልብስህ
አልቆሸሽም ?”፣ “ንባብ አታብዛ፣ በጊዜ ተኛ፤ ራስህን ያምህል፣ ማታ ማታ ጋቢ ልበስ፣ አሹ..
ደሞ እጅህን ወጣ ወጣ አታድርግ የሰው ዐይን ጥሩ አይደለም ሁሉንም በጥሞና አዳምጣታለሁ፥
ስለራሷ ስጠይቃት “እኔ ምን አለብኝ ብለህ” ብቻ ነው መልሷ፡፡ አቲዬ የሚያሰቃይ የወገብ ህመም
እንዳለባት እንኳን ያወቅኩት ከተመረቅኩ ከሁለት ዓመት በኋላ ነበር፡፡ እንዳልጨነቅ ደብቃኝ፤
ፍፁም በተረጋጋ ሕይወት ውስጥ ትምህርቴ ላይ ብቻ መሉ ሐሳቤን ሰብስቤ እንዳጠና:: የሰው አፈጣጠሩ እየገረመኝ፣ የበሽታ መከሰቻው ምክንያት ብዛት እና መነገድ እያስደነቀኝ፣ ለዛውም የሰው ልጅ ምህረቱ ባይበዛለት በቀናት እድሜ ከምድር ተጠራርጎ የሚጠፋ ትበያ መሆኑ እያስደመመኝ፣ ሰው የምጠላው እኔ የሰው ጠላት የሆነ በሽታ ጋር ድብብቆሽ ስጫወት ወደ መመረቂያዬ ተቃረብኩ፡፡

ሴት አይቀርብም" ይሉኛል፡፡ ይሄም እንደ ጨዋነት ተቆጥሮልኝ ነበር፡፡ እኔ ባጠቃላይ ሰው
ነው የማልቀርበው፡፡ ለምን ለይተው፣ “ሴት አይቅርብም' እንደሚሉኝ ይገርመኛል፡፡ ሲጀመር
ማንም ጋር የሚያገናኘኝ የትምህርትና መሰል ጉዳዮች ከሴትም ይሁን ከወንድ ርቄ አላውቅም፡፡

ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለዛውም የሕክምና ትምህርት ላይ ብቸኛ መሆን ቀላል ነገር አይደለም፡፡
ቢሆንም ከማይረባ መጠላለፍና በሕይወቴ አንድ እርምጃ እልፍ በማያደርገኝ ጉዳይ ውስጥ ገብቼ
የመዳከር ፍላጎቱ አልነበረኝም፡፡ ለምሳሌ ፆታዊ ፍቅር !! ወንድ እና ሴት ቆመው ወይም አንድ
ጥግ ተቀምጠው ያንን ሁሉ ሰዓት ሲቆዩ ምን ጉድ እንደሚያውሩ ይገርመኛል፡፡ ፍቅር ለምን
አይይዘኝም ብዬ ያሰብኩት አንዲት ልጅ እንዳፈቀረችኝ የነገረችኝ ጊዜ ነው፡፡ ማህሌት ነው
ስሟ መጀመሪያ ስታፈጥብኝ አጋጣሚ መስሎኝ ነበር፣ ሲደጋጋም የሆነ ነገር ፈልጋ ይሆናል ብዬ ችላ አልኩት። ከዛ ከበበችኝ፡፡ አየር ሆነች፡፡ ላይብረሪ ካለሁ አለች፡፡ የሆነ ቦታ ከተቀመጥኩ ከሆነ ቦታው ፊትለፊት፣ ከኋላ ወይም ከጎን አለች። ባለፍኩበት ታጋጥመኛለች፡፡ ከሰላሳ መንታ
እህቶቿ ጋር ወደ ዩኒቨርስቲው አብራ የገባች እስኪመስለኝ በዛችብኝ፡፡ በመጨረሻ ወደድኩህ
አለችኝና እርፍ !!

እንደው አጋጣሚውን አልለፈው ምንስ ኣባቴ ቢክደኝ ባባቴ ወንድ አይደለሁ አልኩና ልሞክር
ወሰንኩ፡ ግን ልጅቱ በቀጣዩ ቀን ሰለቸችኝ !!

በቃ እግዚኣብሔርን ባፈቅር ይሻላል የሴት ፍቅር አያዋጣም' አልኩ፡፡ ሳይቆይ ግን ዓለም እግዜርን የሚያፈቅርበት አካሄድ እኔ ከማፈቅርበት ጋር አልገጥም አለኝ፡፡ አንድ እግዜርን በስንት መንገድ እንደሚያፈቅሩት ስመለከት አፈቃቀሬ የተሳሳተ ይሆን እንዴ ብዬ ፈራሁ፡፡

አንድ ቀን ከግቢ ወጥቼ የተማሪው ኪስ ሞላ ሲል የሚያዘወትራት ሬስቶራንት ሄድኩ፡፡ ምሳዬን
ኣዝዤ ስጠብቅ የዲፓርትመንቴ ልጆች መጡና ፊት ለፊት ተቀመጡ ሦስት ሴታች፡፡ ብዙ
ሴቶች ሲሰበሰቡ ኀብረተሰቡ የጫነባቸውን የፆታ ተፅእኖ ቀንበር የሰበሩት ይመስላቸዋል መሰል
ድፍረት ይጨምራሉ ጮክ ብለው ማውራት መሳቅ ምናምን…፡፡

ያዘዝኩት ምግብ ጭሱን እያግተለተለ መጣ፡፡ አስተናጋጇ ገነትን በስሀን ይዛልኝ የመጣች ነው የመሰለኝ፡፡ ርቦኝ ስለነበረ የምግቡ ሽታ የተለየ ሆንብኝ፡፡ አንገቴን ዝቅ እድርጌ ዐይኖቼን ጨፈንኩ፣ጸሎት ይመስላል፡ ግን አልነበረም:: በጭራሽ ! መቼ እንደጀመርኩት ባላስታውስም፡ በተለይ ርቦኝ የሚበላ ነገር ሳገኝ፡ ደሰ የሚል ምግብ ሲቀርብልኝ ሁልጊዜም እንዲህ አደርጋለሁ፡፡ ጥልቅ የሆነ ስሜት ውስጤን ይሞላውና የሚያስገርም የአፍታ ዝምታ ውስጥ እገባለሁ፡፡ ለሞተው
የረሀብ ዘመኔ አጭር የህሊና ጸሎት !

ቀና ስል ሴቶቹ በግርምት አፋቸውን ከፍተው ያዩኛል፡፡ ፊታቸው ላይ ማክበር፡ መቀራረብ መፈለግ ነበር፡፡ ልክ እንደማላውቃቸው ሰዎች ችላ ብያቸው መብላት ጀመርኩ። በልቼ እንደጨረስኩ ቡና አዘዝኩ፡፡ እንዷ ወደኔ መጣች…ኤጭጭጭጭ !

“ሰላም ላንተ ይሁን፣ አሸብር!”

“ሃይ” አልኳት ባጭሩ፣ ስናገር ሊያገሳኝ ነበር፡፡

“መቀመጥ ይቻላል ?” አለች ለመቀመጥ መንገድ ጀምራ፡፡ ከዛም እንደ እኔ ቡና አዘዘችና ወሬ
ጀመረች፡፡ “ስታመሰግን አየንህ ክርስቲያን እንደሆክ አናውቅም ነበር” አለች ፈገግታዋ ፊቷ ላይ እየተንተገተግ፣
አልመሰስኩሳትም፡፡

“ፈሎሽፕ አለን ብንጋብዝህህህ ደስ ይለኛል፡፡ በቃ አብረን ጌታን ማምለክ ነው አላማው፡፡ ዕሮብና
ቅዳሜ ከሰዓት ነው ፕሮግራሙ” የሆነች ወረቀት ሰጠችኝና አመሰግናኝ ቡናዋን ሳታጋምሰው
ሄደች፡፡ ከጓደኞቿ ጋር ተያይዘው ወጡ፡፡ ተመራርጠው ጓደኛ የሆኑ ይመስል ሦስቱም በቁመትም
በቅጥነትም አንድ ዓይነት ነበሩ፡፡

እንግዲህ ይሄ ምግብ ሲቀርብ ማቀርቀሬ ነው የአብረን እናምልክ!” ግብዣ ያመጣብኝ፣ ወላ ያመጣልኝ፡፡ ዝም ብዬ ሳስብ ከእነዚህ ልጆች ጋር እንዴት ነው በጋራ የምናመልከው?" ብዬ
ገረመኝ፤ እኔ ለየትኛውም እምነት፣ ለየትኛውም አምልኮ ግድ ያለኝ ሰው አይደለሁም፡፡ በሕይወቴ
ሙሉ የፀለይኩበት ቀን ኖሮ አያውቅም፡፡ እግዚአብሔር የእኔ ብቻ ስለሚመስለኝ ሌሎች ጋር
በጋራ ማምለኩም፣ መዘመሩም ምኑም ትዝ ብሎኝ አያውቅም፡፡
እግዚእብሔር እኔ ጋር በመተባበር አዲስ አበባን ድራሽዋን ለማጥፋት እስከመረቅ እየጠበቀኝ
አልያም እንደ ኖህና ቤተሰቡ እኔና አቲዬ ወደ መርከበ እንድንገባ ፈልጎ የጥፋት ውሀውን
ያዘገየው ስሰሚመስለኝ ማንም ጋር ማምለክ ፈልጌ አላውቅም፡፡ ስለዚህ ቀተጋበዝኩበት ቀን
ቀረሁ፡፡ ንዝንዛቸው ግን መቆሚያ መቀመጫ ኣሳጣኝ፡፡ አንድ ቀን፣ “ይቅርታ የምትሉቀት ቦታ
መሄድ ስለማልፈልግ ካሁን በኋላ በዚሁ ብናቆም' አልኳት አንዷን በቁጣ፡፡

አዎ ተቆጥቼ ነበር " እግዚአብሄርን በምቾት የሚያውቁት ሞልቃቆች የቻፕስቲክ መግዣ ሲያጡ፣
“አግዚአብሔር ማነው?” የሚሉ..እግዚአብሄርን እንዲያስተዋውቁኝ አልፈልግም፡፡ አይቻቸዋለሁ በዩኒቨርስቲ ቆይታዬ፣ ዶሮ ሦስት ጊዜ ሳይጮህ ጴጥሮስ ጌታን ሦስት ጊዜ እንደካደው የሚያትት መዝሙር እያንጎራጎሩ እነሱ ራሳቸው የሃብታም መኪና ጡሩንባ ባምባረቀ ቁጥር ከራሳቸው ሰላሳ ጊዜ ሲካካዱ፡፡ አይቻቸዋለሁ
የጌታ የማዳን ድንበር አቃቂና ኮተቤ ድረስ ብቻ ይመስል የአዲስ አበባ ልጆች ብቻ ተጠራርተው፤ “በጌታ ፍቅር” ምሳ ሲገባበዙ፣ ቸርች ሲሄዱ - የፅንፍየለሽ ከታማያዊ ዘረኝነት የሚነበብ ነገር ሲዋዋሱ፡፡አይቻቸዋለው በየእምነቱ ተቧድነው ሲናቆሩ ሲጠዛጠዙ፡፡ እኔ እና እናቴ እግዚእብሄርን ገደል ጫፍ ላይ እንደተንጠለጠለ ገመድ የሙጥኝ ብለን ሕዝብ ከዛ ከዚህ ሲገፋን፣ ድህነት እጃችንን እየቀጠቀጠ የመዳኛ ገመዳችንን ሊያስለቅቀን ሲታገል፣አንለቅም" ብለን የተረፍን ሚስኪኖች ነን፡፡ ሰው አትመልከት እግዜርን እንጂ” ይሉኛል፣
አብረን እናምልክ! ብሎ ጠርቶ 'ሰው አትመልከት፣ ማለት ምንድን ነው?
👍39