#ቀስ_ብሎ_ይቆማል
፡
፡
#ስምንት (የመጨረሻ)
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
...“ቆይ አብርሸ ምንድን ነው … ማለቴ…ተወው በቃ” ግራ ተጋባች። እናም እንዲህ አለችኝ፣ ችግር የለውም እንዳታስብ፣ ምንም ነገር እንዳታስብ !” ስትናገር ዓይኔን ማየት ፈርታ ነበር።እጆቿ እነዛ ቆንጆ
ጣቶቿ በሆነ ፍርሃት ሲንቀጠቀጡ ይታዩኛል። ብርድ ልብሱን ከጎኔ ገልባ ሸርተት ብላ ገባች።
ወዲያው ተመልሳ ተነሳችና የሌሊት ልብሷን ከትራስጌ በኩል አንስታ ለበሰች፤ ተመልሳ ተኛች። ድንብርብሯ ወጥቶ ነበር። በብርድ ልብነስ በታፈነ ድምፅ ችግር የለውም” እለች እንደገና።..
“ሙና” አልኳት ጀርባዋን ሰጥታኝ ነበር የተኛችው። ልክ ሰይጣን የጠራት ይመስል ድንግጥ ብላ፣
“እ” አለችኝ። ድንጋጤዋ እኔንም አስደነገጠኝ።
“ይቅርታ እስካሁን ስላልነገርኩሽ"
“ችግር የለውም ! ይሄ ማንንም ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው እንተኛ።” አነጋገሯ ምንም ለዛ የሌለው የሽሽት ይመስል ነበር፤ ዝም ላለማለት ያህል። ተኛች፤ እንቅልፍ የወሰዳት መሰለኝ። ልነካት ፈራሁ።የሆነ አተኛኘቷ ራሱ ትንሽ ከሰውነቴ ራቅ የማለት ነገር ነበረበት። ይሰማኛል እባብ የሆነ ነፋስ በመሐላችን በተፈጠረ ሰርጥ መለያየት ሲሳብ …
ተነስቼ ከአልጋዬ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ። ከፊቴ ትንሽ ጠረጴዛ አለች፤ መፃፍ ሲያምረኝ ከምኝታዬ ተነስቼ የምፅፍባት። ለምን ያህል ጊዜ እንደተቀመጥኩ እኔጃ፤ ሙና በእንቅልፉ ስትንቀሳቀስ ብርድ ልብሱ ተንሸራትቶ ግማሽ አካሏ .ተራቆተ። ህልም የሚመስል ቀይ ሰውነት፣ ከውስጡ ብርሃን የሚያመነጭ ሙልት ያለ ሰውነት፤ ውብ ሰውነት። በዚህች ቅፅበት ውስጤ በቅናት አረረ። የማላየው የወንድ እጅ እዚህ ሰውነት ላይ ሲያርፍ አሰብኩ። የሙና ሰውነት የደረቀ መሬት መስሎ ተሰማኝ። ውሃ የናፈቀ፡ የተቃጠለ፣ ማንም መቼም ሲዘንብበት ምጥጥ የሚያደርግ ምድረበዳ።
ዝም ብዬ አያታለሁ። ልቤ ታፍኗል። መረረኝ፣ ሕይውት አስጠላኝ። ሙና ስዕል ብትሆን ብዬ ተመኘሁ። የትም የማትሄድ፣ ለዘላለሙ እዚህ ተቀምጬ የማያት ስዕል፣ የምትታይ ብቻ። የስዕል፣የግጥም፣ የዘፈን የሁሉም ጥበብ መነሻ አለመቻል መሆኑ የገባኝ እዚህች ነጥብ ላይ ነው። ሰው አለመቻሉን ሲገልፅ መግለጫው መንገድ ላይ ይጠበብና ጥበበኛ ይባላል። ሰው በአካል ያልደረሰበትን ጥግ
ነው በጥበብ እጆቹ ተንጠራርቶ ለመንካት የሚፍገመገመው።
ሙና ተንቀሳቀሰች። ብርድ ልብሱ ሙሉ ለሙሉ ወደ እንድ ጎን ተሰበሰበ። በስስ የሌሊት ልብስ፣
ሰውነቷ ፍም መስሎ ቀልቷል። እዛጋ ሆና እዚህ ያለሁ እኔን ወላፈኗ ፈጀኝ። እንቁልልጭ የምታጣትን ልጅ ተመልከት.. እንዴት ውብ እንደሆነች እይ” የሚለኝ ሰይጣን ጭንቅላቴ ውስጥ የተቀመጠ መሰለኝ።
እየኋት …. ትክክከከ ብዬ አየኋት። ሕሊናዬ ትልቅ ሸራ ሆኖ መንፈሴ በማይጠፋ ቀለም ሙናን እየሳለ
ነበር። ልቤ ትልቅ ብራና ሆኖ ሙናን እየፃፋት ነበር። ከወንበሬ ተነስቼ የሙናን የእግር ጣቶች ተራ
በታራ ሳምኳቸው፤ አስሩንም። የተለኮሰ የሲጋራ ጫፍ የሳምኩ ይመስል የእግሮቿ ጣቶች ከንፈሬ ላይ ረመጥ ሙቀታቸውን አተሙት። ደግሞ የእግሯ ልስላሴ ! ወደ ቦታዩ ተመለስኩ። ብርድ ልብሱን አላለበስኳትም፤ ላያት ፈልጌያለሁ።
ወንበሬ ላይ ቁጭ ብዬ ሙናን ስመለከታት የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ግጥም ልክ ጎረቤት እንደተከፈተ ዓይነት ከነድምፁ ጥርት ብሎ እንደ ጅረት ውኃ አዕምሮዬ ውስጥ ይፈስስ ጀመረ። ያውም በዓይኖቼ ሞልቶ በሚፈሰስ እንባዬ ታጅቦ። #ሶልያና የእኔ ኑዛዜ - የግጥም አልፋና ኦሜጋዬ … እያንዳንዱ ግጥም የኑሮ ዝባዝንኬ ድንጋዩን ቢጭንበትም አለ ጊዜ እንደ ከርሰ ምድር ውኃ የሚፈነዳበት። ገጣሚው እዚህ ተቀምጦ ሙናን እየተመለከተ የፃፈው እስኪመስለኝ፣ ሶሊያና የሙና የቤት ስሟ፣ የመኝታ ቤት
ስሟ እስኪመስለኝ … ገጣሚው የእኔን ሙሾ በደረቀ ሌሊት አወረደው ….
ሶ ሊ ያ ና
እኔን ከወንበር ላይ፤
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ፣
ወረቀት ላይ ወስዶኝ ….
እርሷን ካልጋችን ላይ፣
እንቅልፍ አሽኮርምሟት፣
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት፣
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ፣
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ፣
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ፣
ከደጋው ሐሳቤ በረሃ ስሰደድ፣
እንባን በፊደላት፣
ፊደልን በቃላት፣
ቃላትን በሐሳብ፣
ወረቀት ላይ ልወልድ፣
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ፣
"የኔ ነሽ” የምላት ያንተ ነኝ የምትል፣
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ መሃል
“ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋዬ ላይ፣
አንተን መናፈቅ በስሜት ስሰቃይ"
ቀና ብዬ ሳያት እውነት አለው ቃሏ፣
ፍም መስሏል አካሏ፣
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል፣
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል፣
እኔን በመጓጓት ደሟ ተቆጥቶ፣
ፍቅሯ ተሰውቶ፣
ስሜቷ ተጎድቶ፣
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ሕፃን፣
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉሯ ሲበታተን፣
ካልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን፣
ፍ ቅ ሬ ሶሊያና አወራችኝ መሰል በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ…
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰት ዓለም፣
የሰዎች ጥላ እንጂ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ፣
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ፧
ሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ፣
እኔ ውበቱ ነኝ ለፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም፣
ይህ ሁሉ ቢሆንም... ወዲህ እንዳትመጣ፣
በሌሊት ትጋትህ ሐዘን ሳይቀጣ፣
በኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ፣
ከየሰዉ ዓለም የሚመሳለሉ፣
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ፣
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፉ፣
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰዎችን እንባ
አትፃፍ ግዴለም፡
የፍጥረትን ሐዘን ስለህ አትዘልቅም፣
እውነት እለው ብለህ ሐዘንን አታልም፣
((ያለቀሱም ሰዎች ሐቀኞች እይደሉም}
ይልቅ የኔን ስሜት፤
ያንተንም እንባዎች ሁለቱን አሳየኝ፣
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ ! እኔን ብቻ ፃፈኝ !
“ያልተደሰተች ሴት” በሚል መጽሐፍህ
ዘ ላ ለ ም አሻግረኝ፣
ዘ ላ ለ ም ውሰደኝ፣
ዘ ላ ለ ም አኑረኝ !!”
“የኔ ነሽ” የምላት፣ “ያንተ ነኝ የምትል፣
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ መሃል።
ቁጭ ያልኩበት ወንበር ላይ እንቅልፍ ወሰደኝ…
ሊነጋጋ ሲል….
“አብርሽ” የሙና ድምጽ እንደ ህልም ተሰማኝ። ዓይኖቼን ስገልጥ ፊቴ ቆማ ነበር። ልብሷን ለባብሳ፣አንድ እርምጃ የሚሆን ከእኔ ራቅ ብላ ቆማ ነበር። ሙና ስትቀሰቅሰኝ እንዲህ አልነበረም፡፡ ከተኛሁበት የምትቀሰቅሰኝ በከንፈሯ ነበር። በተኛሁበት ስትስመኝ ነበር የምነቃው። እና እዛጋ ምን አቆማት ፣
ሁሉን እንቅልፍ ባስረሳው በደበዘዘ አዕምሮ አያታለሁ።
“ተነስ ቁርስ ሰርቼልሃለሁ”
በዝምታ እንቁላል ፍርፍር በላን፣ ሻይ ጠጣን፤ (በዝምታ) ዕቃዎቹን አነሳስታ አጣጠበች እና መጥታ
ጎኔ ተቀመጠች። ሁለታችንም በአስፈሪ ዝምታ ውስጥ በዝምታ እንደተቀመጥን ድንገት የሙና እንባ ተዘረገፈ፤ እናም አቀፈችኝ። ከሙና እንዲህ ዓይነት ጉልበት ያለው አስተቃቀፍ አልጠበቅኩም ነበር።

👍25❤1🥰1
#ዶክተር_አሸብር
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
፡
፡
#ስምንት
መማርን ጌታ ይባርከው ! መማር መቃጠል ነው ይላሉ ተምሮ ማቃጠል ለእኔ ዓለሜ ሆነች "
ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት አንደኛ ከፍል እስከመዘገብ የአባት ስም አልነበረኝም፡፡ አሸብር ብቻ
ነበርኩ፡፡ ልክ ትምህርት ቤት አቲዬ ወስዳኝ ስመዘገብ ጉጉት የመሰለው መዝጋቢ የእናቴ ድሪቶ ቀሚስ ለዓይኑ ቀፎት እያመናጨቃት አይቼዋለሁ፡፡ ተመዝግቤ ስንመለስ አቲዬ ከፊቱ ዞር ስትል፣ ፊቱን አጨፍግጎ መጥፎ ጠረን እንደሚያባርር ሰው በግራ እጁ አየሩን እያራገበ ሲያባርር አይቼዋለሁ፡፡
በእርግጥ አቲዩ እማማ የብርጓል ቤት እንኩሮ እያነኮረች ነበር፡፡ ምዝገባው ዛሬ ነው የሚያልቀው
ሲሏት ብድግ ብላ ነው የመጣችው፡፡ ቢሆንስ ልክ ቆሻሻ እንደሸተተው ሰው ሰው እንዲያየው አድርጎ እጁን ያራግባል እንዴ…፡፡ የእማማ የብርጓል ቁጥር አንድ የጠላ ደንበኛ እንዳልሆነ ሁሉ፡፡ ሊያስተምረን ክፍል ውስጥ ሲገባ እንደባቡር ሀዲድ የረዘመ የጠላ ትንፋግ ተከትሎት
እንደማይገባ ሁሉ ነብር አየው ያንን የውሻ ልጅ። አስተማሪውን እንደጠመድኩት ጡረታ
ወጣ !! ደግሞኮ አያፍርም መንገድ ላይ ላገኘው ሁሉ፣ እኔ ነኝ ያስተማርኩት“ እያለ በኩራት
ያወራል፡፡ በርሱ የትምህርት ዓይነት ብቻ ዶክተር የሆንኩ ይመስል!!
“ስም ?” አላት አቲዩን ድሮ፡፡
“የእኔን ነው ?” አለች እየፈራች፡፡
ፈሪ ነበረች እናቴ፡፡ ፈሪው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንደያቅሙ ደሀ ማስፈራራትን ተክኖበታል።
“አንች ነሽ አንደኛ ክፍል የምትመዘገቢው?" አላት፡፡ አጠገባችን ያሉት ሁሉ ሳቁለት፡፡ አቲዬ ተሳቀቀች፡፡ ሰውነቷ ሽምቅቅ ሲል ቀሚሷን አንቄ ተሰምቶኛል መሸማቀቋ፡፡
የልጅሽን ሰም ንገሪኝ ሴትዮ አላት እያከላፈታት፡፡
“የእሱ አሸብር…አሸብር ነው ስሙ አለች ራሴን እያሻሸች፡፡
“የአባት ስም ?”
“እባ…ት” ብላ ዝም አለች፡፡
“የአባቱ ስም ማነው…
'ቀ' መጨረስ አልቻለችም፡፡ ቀለመወርቅ ልትል ፈልጋ እንደነበር የገባኝ ካደግኩ በኋላ ነው፡፡
የዛሬዋ ደግሞ የጉድ ናት፡፡ የልጇም አባት የሚጠፋት
እንደገና እንዲስቁለት ሰዎቹን አየ
ያልደመቀ ሳቅ ተሳቀለት፡፡
"በይ ወደዛ ሁኝ! ስታስታውሽ ትመለሻለሽ፤ ተረኛ ቀጥል!” አለ እስኪርቢቶውን እያወናጨፊ፡፡
(አልረሳትም ግማሽ ድረስ ቀለሟ ያለቀ ሰሚያዊ ቢክ እስክርቢቶ።
እናቴ ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው፣ “በአምላክ..በአምላክ ነው የአባቱ ስም፡፡” አለች፡፡
መዝጋቢው ራሱን ግራና ቀኝ በብስጭት እያወዛወዘ መዘገበኝ፡፡
የአባት ሰም በአምላክ (በአምላክ አባቴ አይደለም፡፡ እቲዬ ለአምላክ ሰጠችኝ፡፡) የሃምሳ ብሩ ሲገርመው፣ ለእግዜር ሰው አበደረችው አቲዬ፡፡ የእኔ እናት በሕይወት ባንክ ውስጥ ብድር
ለሚመልስ ብድር በመስጠት የተካነች ባለሙያ ነበረች ነገን የምታይ !! እግዜር የተበደረው
ትውልድ፣ ወለዱ የተባረከ ዘር ማንዘር ነው፡፡ “እስከ ሺ ትውልድ ዘርህን እባርካለሁ፡፡ ብሏል
ራሱ እግዜር
ትምህርት ቤት ገባሁ…!!
የክፍላችን ልጆች የኑሮ ደረጃ በዳግማዊትና በእኔ መካከል የተወሰነ ነበር፡፡ ዳግማዊት የሚታዘል ባለዚፕ ቦርሳ ያላት ቆንጆ አንደኛ የሀብታም ልጅ ስትሆን፣ እኔ ከሹራብ የተሰራች ኮሮጆ የነበረኝ አንደኛ የደህ ልጅ፡፡ ይሁን እንጂ በንፅህና አልታማም፡፡ ልብሶቼ ሁልጊዜም ንፁዎች ነበሩ
ንፁህና አሮጌ፡፡ ሰኞ ሰኞ ሰልፍ ሜዳ ላይ የእጅ ጥፍሮቻችን ሲታዩ ንፁሀ ጥፍርቼን በኩራት
ነበር የምዘረጋው:: የዳግማዊትን ያህል በፈገግታ “ጎበዝ“ ባልባልም፣ ከቆሻሻና ከስንፍና የተጣላች ቆራጥ ደሀ እናት አለችኝና ስንፍናና ቆሻሻ አጠገቤ ዝር አይሉም ! (ሰው ወዶ አይደለም ለካ ዘራፍ የሚለው፡፡)
አንድ ቀን ግን በሕይወቱ ስሳቀቅበት የኖርኩበት ነገር ተፈጠረ፡፡
እንግዲህ አስቴር ከዋናው ቤት እሮጌ ፍራሽ (የሆቴሉ አልቤርጎ ውስጥ የነበሩ፡፡) እና ሌሎችም
ከፍል ውስጥ ቤት፡፡ እናም ቤታችን ውስጥ በታጨቀው ዕቃ ምከንያት ቤቱን አንደ ልብ ማፅዳት ባለመቻሉ ቁንጫ እንደጉድ ይፈነጭ ጀመረ፡፡
ጋሽ መሀሪ ኣካባቢ ሳይንስ መምህራችን ነበር፡፡ ሲያስተምር ስወደው:: የርሱን ትምህረት አስር
ካስር ነው ሁልጊዜም የምደፍነው፡፡ እኔ ስለምወደው፣ የሚወደኝ ይመስለኝ ነበር ፡፡ አንድ ቀን ግን ዘላለማዊ ጠላቴ ያደረገውን የማይረባ ነገር አደረገ።
ስለ ጓር አትክልት ጥቅም እያስተማረ ነበር፡፡ ድንገት ዳግማዊት፣ “ ዋይ” ብላ ጮኸች::
ቦርሳዋ ላይ ሁለት እሳት የመሳሰሉ ቁንጫዎች ዘለውባት ነበር፡፡ የክፍሉ ልጅ ሁሉ በድንጋጤ
ወደ ዳግማዊት ዞረ፡፡ መምህሩ ሁኔታውን ሊያጣራ ከምኔው አጠገባችን እንደደረሰ እንጃላት::
“ምንጩን ነው?”
“ቁ..ን..ጫ አለች ለቅሶ በሚመስል ሞልቃቃ ድምፅ፡፡
እኔ ከዳግማዊት ጎን ነበር የምቀመጠው፡፡ ባልገባኝ ምክንያት ተቆጣ፡፡
"እስቲ ቦርሳህ” አለኝ፡፡ በቃ እንዲህ ነው ያለኝ፡፡ ከወንበሩ ስር ከተሰራው የደብትር ማስቀመጫ፣
የሹራብ ኮሮጆዬን አወጣሁ፡፡ በዚህች ቅፅበት የተከሰተው ነገር አስደንጋጭ ነገር ነበር፡፡ በርካታ
ቁንች ከእኔ ኮሮጆ ላይ ተፈናጠሩ፡፡
መምህር ምሀሪ ፊቱን አጨፍግጎ ኮሮጆዬን አነሳና ወደፊት ወደ ጥቁር ሰሌዳው ወረወረው::
ደብተሮቼ በአየር ላይ ወረቀታቸውን እያርገበገቡ ተበታተኑ፡፡ (እስከዛሬም ደብተሮቼ በአየር ላይ እየተንሳፈፉ ይታዩኛል አላረፉም፡፡)
“ውጣ ጆሮህን ያዝ ብሎ በኩርኩም አፈለሰኝ፡፡ ወጥቼ ጆሮዬን ያዝኩ፡፡ ከኩርኩሙ በላይ
ሀፍረቱ ጠዝጥዛኝ ነበር፡፡
የታፈነ የጓደኞቼ ሳቅ፡፡ በትምህርት አልችለኝ ሲሉ እችን እንደውድቀት፣ እችን ከእነሱ እንዳነስኩባት አጋጣሚ ሊጠቀሙባት፡፡ የእፉኝት ልጆች…ስንቱን ትምህርት ስደፍን ለጭብጨባ በመከራ የሚነሳ እጃቸው፧ ዛሬ ሳቃቸውን ሊያፍን ወደ አፋቸው ተወነጨፈ።
ቡፍ.….ቡፍ...ሂሂሂ..
መምህሩ መሀሪ (ስሙን ቄስ ይጥራውና!) ስለጓሮ አትክልት የፃፈውን አጥፍቶ ጥቁር ሰሌዳው ላይ፣
“ተስቦ" ብሎ በትልቁ ፃፈና ከስሩ በድርቡ አሰመረበት፡፡ ያውም አረንጓዴ ቀለም ባለውና እንደ
ብርቅ በምናየው ጠመኔ !!
ከዛም ስለተስቦ ሙሉ ክፍለጊዜውን ሲለፈልፍ ዋለ፡፡
“አያችሁ ልክ እናንተ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ዘመድ ለመጠየቅ በታክሲ፣ በአውቶብስ
ተሳፍራችሁ እንደምትሄዱት፣ ቁንጫዎችም በአይጦች ተሳፍረው ንፅህናው ወዳልተጠበቃ ቤት ይሄዳሉ፡፡ አሁን እሱ ደብተር መያዣ ላይ እንዳያችሁት እኔን እየጠቆመ)፣ ንፅህናው ባልተጠበቀ የልብስ ሻንጣ፣ የደብተር መያዣ፣ በሌላም ቁሳቁሶች አማካይነት እየተንጠላጠሉና እየተደበቁ
ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ፣ እንደ ዳግማዊት ዓይነት ንፁህ ልጆች በተስቦ ይያዛሉ..” በማለት
አስተማረ፡፡ ምን ያስተምራል አስተማሪ የሚባለው ነገር የጠላት ስም እንዲመስለኝ እደረገ እንጂ !
ለረዥም ጊዜ 'ተስቦ' እያሉ ጓደኞቼ ያበሽቁኝ ነበር፡፡ ከአርባው ስንፈተን ግን ስለተሳቦ ተጠይቀን
የደፈንኩት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ ሰው ስድሱን አይረሰማ !! በተለይ እኔ ስድቤን አልረሳም !! መገፋቴን አረሳም።
ስድስና መግፋት እንደ አረግራጊ ሳንቃ ሽቅ
ብ ተኩሰው በቀል የሚባል ጨረቃ ላይ የሚያሳርፉኝ

👍36🥰3❤2😁1😢1