#ዶክተር_አሸብር
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
፡
፡
#አስር
....ጥቁር አምበሳ፣ ኮከብ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲስ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ የአስረኛ
ክፍል ተማሪዎች ሁሉ፣ “አንደኛ ጎበዝ አንተ ነህ” አሉና የምስክር ወረቀት ሸለሙኝ፡፡ እኔ ግን ጥቁር አምባሳ፣ ኮከበ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲስ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ቆንጆ የሆነችው ዮርዳኖስ የት ተቀምጣ ይሆን እያልኩ በዓይኔ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀል እየፈለግኳት ነበር፡፡
ዮርዳኖስ ማለት ማንም አይደለችም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመሬት ተነስታ ጉንጬን የሳመችኝ ልጅ ናት፡፡ ጉንጬን ሳይሆን በቀኝ በኩል ከከንፈሬ ጥግ ሁለት….አረ አንድ ተኩል ሴንቲ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሳመችኝ (ለሞላ ጉንጭ፡፡)
ዮርዳኖስ ቀይ ልጅ ናት፡፡ ለነገሩ ቀይ ሳትሆን ጠየም ያለች ግን ቀይ ዳማ እንደሚሉት ሳትሆን
አትቀርም፡፡ አቦ የራሷ ጉዳይ ገደል ትግባ ብትፈልግ ኤጭጭጭ!! ይሄው ስንት ጊዜ ሌትም ቀንም
ዮርዳኖስ ቀይ ናት ቀይ ዳማ እያልኩ ስዛብር ማደር ከጀመርኩ፡፡ እንኳን ሴት ልጅ፣ ቆንጆ ወጣት ሴት ልጅ፣ ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ ሰው ሲስመኝ የመጀመሪያዬ ስለነበር ዮርዳኖስ ጉንጬን
ሳይሆን ልቤ ላይ እንደሳመችኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ማስረጃ ብባል፣ ከዛን ጊዜ ጀምሮ አተነፋፈሴ ልክ አይደለም፤ ሳያት የሆነ ነገር ያፍነኛል፡፡ ሳላያት እንደ ነብር አዳኝ ትንፋሼን ውጬ በጉጉት በዓይኔ እፈልጋታለሁ፡፡ ሳላያት ታፍኜ ሳያትም ታፍኜ ልሞት ሆነ፡፡
"አንቺ ዮርዳኖስ የምትባይ፤ ምን ቆርጦሽ ነው ኧረ ከከንፈሬ አንድ ተኩል ሴንቲሜትር ርቀት
ላይ በሚሞቅና በሚለሰልስ እርጥብ ከንፈርሽ የሳምሽኝ?” ብላት ደስታዬ፡፡ ግን ታፍኛለሁ!!
አርብ ቀን ከትምህርት ቤት ወጥቼ ወደ ቤቴ እሄዳለሁ፡፡ ምንም እያሰብኩ አልነበረም፡፡ ዝም
ብዬ እየተራመድኩና በግዴለሽነት ሁሉንም ከፊቴ ያለውን ነገር እየተመለከትኩ እራመዳለሁ፡፡
“አሸብር፣” አለችኝ ከኋላዬ፡፡
ስሜ ሲጠራ የምደነግጠውን ያህል የሰይጣን ስም ቢጠራ እንኳን አልደነግጥም፡፡ ሰዎች ስሜን ሲጠሩኝ ከዝምታዬ ባሕር በምላሳቸው መንጠቆ ጠልፈው ያወጡኝ ይመስለኛል፡፡
ጭራሽ ጠሪዎ ዮርዳኖስ ስትሆን ደግሞ፣ በመንጠቆው ላይ መረብ ተተበተብኩ !! ከእኔ ጋር
ብዙ ሰዎች ወደኋላ አብረው ዞሩ፡፡ ሰዉ ሁሉ ሳይጠራ ሲዞር፣ ጠሪዋን ተመልከቶ ደሰ ካሰችው
ስሙን አሸብር ሊያስብል ያሰበ ይመስል እኔ ለተጠራሁት መዓት ሰው ዞረ፡፡
ዮርዳኖስን ዞሬ አየኋት፡፡ ጉርድ ቀሚሷ በደንብ አላራምዳት ስላለ በእጇ ሰብሰብ አድርጋ ወደ
እኔ ትጣደፋለች፡፡ እግሯ ቀይ ነው፡፡ ባቷ ፍርጥም ያለ ከእድሜዋ በላይ ትልቅ የሚያስመስላት
ነው፡፡ ባቷ ብቻውን አስራሁለተኛ ክፍል ይመስለኛል። ጡቶቿ ደግም እዛና እዚህ ይላጋሉ:: ስትጣደፍ፣ በሁለት እጆቿ ክንዶች ገፋ አድርጋ ታረጋጋቸዋለች፡፡ ፀጉርዋ አጭር ነው፡፡ ግንባሯ ትንሽ ወጣ ያለ፡ ቀረበችኝ ፈገግ አለች፡፡ ዓይኖቿ እንዴት ያምራሉ፡፡
ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍ አሁን ስትጠራኝ መኪና እየነዳሁ ቢሆን ኖሮ ከዓይኖቿ ለማምለጥ ስል
ፊት ለፊት የሚያላዝነው ቦት መኪና ጋር እላተም ነበር፡፡ የያዘው ነዳጅ ይዘረገፍና ከዮርዳኖስ
ፈገግታ እሳት ለኩሶ ጭሱ ፀሐይን ጥቁር ጉልቻ እስከትመስል የሚያጥን፡፡ ሰማይ የሚነካ እሳት
ይነሳ ነበር፡፡ በቁሜ ቅዥት ስጀምር ታወቀኝ፡፡
“እንዴት ነው የምትርጠው ወተት ጥደሄል ቤትህ ?” ቀለደች።
አልሳቅኩላትም፡፡ ስላልሳቅኵላት ግን ራሷ ከመሳቅ አልታቀበችም፡፡ እየሳቀች ወሬዋን ቀጠለች፡፡
"ቤትህ በዚህ በኩል ነው እንዴ ?”
“እዎ"
“እኔ ግን አይቼሀ አላውቅም"
ዝም አልኩ፡፡ ካላየችኝ ምን ይሁን፣ ወሬዋን ቀጠለች፡፡
አዎ
አዎ
አዎ
“አዎ ብቻ ነው እንዴ የምታውቀው ?
“አይ” እላታለሁ፡፡ አነጋገሬ ሴት የመፍራት ሳይሆን ሰው የመሰልቸት ነበር፡፡ እንዳንዴ የሰዎች ንግግር ይረዝምብኛል፡፡
"ሰላም ሲሉኝ ይረዝምብኛል፡፡ ሰላም፤ እጃቸውን አንስተው፣ ግንባራቸውን ነቅንቀው፣ ፈገግ
ብለው፡፡ አንዳንዴም እጃቸውን ለሰላምታ ዘርግተው፣ ይሄን ሁሉ አድርገው፣ “ሰላም” ብቻ "
ዝም አለች፡፡ አብረን ሄድን ሄድንና የሆነ መገንጠያ ላይ ስንደርስ ክንዴን ይዛ አቆመችኝና ተንጠራርታ ሳመችኝ፡፡ ምንም አላማ የሌለው፣ ምክንያት የሌለው ወይም “ደፋር ነኝ አየህ" የሚል ምናልባትም፣ “ዘመናዊ ነኝ መንገድ ላይ የወንድ ጉንጭ መሳም አልፈራም” አሳሳሟ
የሆነ ድምፅ አለው፣ የሚያፏጭ ዓይነት ድምፅ፡፡ የመምጠጥ አይነት ድምፅ፡፡ የበዛ ግለኝነቴን
ምጥጥ አድርጋ የሐሳብ ሀይቄን አደረቀችው፡፡ የሰው አለማያ ሆንኩ !! ባደረቀችው የብቸኝነት
ኩሬ ራሷን ሞላችው፡፡እዚህ ዮርዳኖስ የምትባል ውሃ የሞላችው ባህር ውስጥ ልቤ አምልጦኝ ገባ፡፡ ይሄው አስባታላሁ፣ የተረገመች ዮርዳኖስ ! እየጠበቀችኝ ይሁን እየተገጣጠምን ብቻ ከዛን ጊዜ በኋላ በየቀኑ እንገኛኝ ጀመረ፡፡ ሲቆይ ግን ጉዳዩ የነፍስ ቀጠሮ ሆነ፡፡ ጠበቅኩሽ ላለማለት በቀስታ እየተራመድኩ እጓዛለሁ፣ ከየትኛውም ርቀት ላይ አውቃታለሁ፡፡
ፊት ለፊት ሳላያት መንፈሷ እዛ አካባቢ ካረበበ ትካሻዬ ሹክ ይለኛል፡፡ ትከብደኛለች፣ “ሃይ አሹ” የሚል ድምጽ እጠብቃለሁ፡፡ ሀይ አሹ ትለኛለች ውስጣችን ያውቃል እንደምንጠባበቅ፡፡ ከዛም ታወራኛለች።
"ዛሬ ይበርዳል!”
"አዎ"
"ሆም ወርክ ሰራህ ?”
"አዎ"
.
.
.
“አዎ ብቻ ነው የምታውቀው፡፡”
"አይይ"። አሁን ግን ምን ማውራት እንዳለብኝ እያሰብኩ ነው ችግሩ፣ አስቤ ሳልጨርስ እንደርሳለን፡፡
ስንመለስም እንገናኛለን፡፡ ስንመለስ መለያያችን ላይ ትስመኛለች፣ “ቻው” ከሚል ስርቅርቅ ያለ መለያየቱ ያስከፋው ድምፅ ጋር ከንፈሯ ጆሮዬ ላይ ያፏጫል፡፡
አንዴ መሀል ጉንጩ ላይ፣ አንዴ ዝቅ አንዴ ከፍ እያለች ትስመኛለች፡፡ በየቀኑ ትስመኛለች፡፡ ዝም ብዬ አሳማለሁ፡፡ ከንፈሯ ክብ ነው፤ በሃሳቤ ስትስመኝ ከብ ቅርፅ ጉንጩ ላይ የታተመ ይመስለኛል፥
የሳምንቱ ክቦች ተቆላልፈው፤ ቅዳሜ የኦሎምቲካ አርማ ጉንጩ ላይ ታትሞ በጉልህ ይታየኛል፡፡
እንዱ ከብ እንደ ደቡብ ኦሞ ሴቶች፣ ከንፈሬን ተልትሎ ከንፈሬ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት በህልሜ!
አንድ ቀን ግጥም ጻፍኩ፡፡ በህይወት ዘመኔ የጻፍኩት ብቸኛ ግጥም ነበር፡፡ ወደፊትም ግጥም
አልጽፍም " ግጥም ያስጠላኛል፡፡ ሰው ዝም ማለት እያለለት፣ ለማውራት ቃል መጠምዘዝ
መድከም ምን ያደርግለታል? ቢፅፍ ላይጠቀም፣ ባይፅፍ ላይጎዳ ባይ ነኝ፡፡ ደግሞ አዲስ
ግጥም ሰምቼ አላውቅም፡፡ ግጥሞች ሁሉ አንድ ናቸው፤ ደራሲያቸው ይለያይ እንጂ ባይ ነኝ::
እኔን የገረመኝ (ርእሱ)
እኔን የገረመኝ፣
እኔ የጠላሁትን፣
እኔነት ሳትጠላ፤
ልጅቱ ስትስመኝ !!
በቃ !! ይሄው ነው ግጥሙ።
ግጥም ማለት ቤት የሚመታ፣ ቀለሙ፣ ስንኙ የሚሉ ሰዎችን ተዋቸውና ግጥም ማለት እስክርቢቶ ሳትጨብጥ ወረቀት ፊትህ ሳይነጠፍ አንደ አፍ ወለምታ ከከንፈርህም፣ ከነፍስሀም፣ ከአዕምሮህም
የሚያመልጥ እውነት ነው፡፡ ለምሳሌ በዚች ዓለም ላይ ከሰማኋቸው ግጥሞች አሳዛኙ የአቲዬ ግጥም ነው፡፡ ርእሱ፣ “እሺ፤ ግጥሙም፣ “እሺ” አበቃ፡፡
ማንም ለጀመረው የትዕዛዝ ስንኝ፣ አቲዩ 'እሺ' የሚል ግጣም እየሰራችለት፣ የማንም ቤት
እንዲቆም አድርጋለች። የእኔ እናት ገጣሚ ናት፡፡
“ቤት ጥረጊ!”
“እሺ!"
“ልብስ እጠቢ”
“እሺ”
“ሂጂና ሳሙና ግዢ!
"እሺ"
“እንጀራ ጋግሪ”
"እሺ
“ደመወዝሽን ሌላ ቀን ውሰጂ!”
"እሺ"
ግጥም ይሄ ነው !! ከትዕዛዘ እኩል ይሁንታው ዜማ ሲፈጥር፡፡ እናም ያሉትን ሲሆኑ፡፡

👍39