አትሮኖስ
279K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል- #አስራ_አንድ #የመጨረሻ_ክፍል

:
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

...ሁሉ ነገር በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ተቀያየረ …..በቤተሰቡ ውሳኔ ትርሲትን
በቋሚነት እናቴን ደግሞ በተመላላሽነት አስከትዬ በአባቴ ወደተዘጋጀልኝ መኖሪያ
ቤት ገብቼያለው…አያችሁ ሰውዬው ማለት ትቼ አባቴ እያልኩኝ ነው…ያ ማለት እኔም እየተቀየርኩ ሳይሆን አይቀርም…? በቀላል ሂሳብ የእኔንም ልብ
እየተቆጣጠረው ነው…የእናቴንማ ቆየ …መቀጣጠር፤ መገባበዝ፤ እንደ አዲስ
ፍቅረኛሞች መጎነታተል ጀምረዋል…እና በቅርብ የድሮ ፍቅራቸው ያገረሻባቸዋል
ብዬ በደንብ አሰባለው….
አባቴ ያዘጋጀልኝ ቤት ሆኜ አባቴ ባዘጋጀልኝ የህክምና መሳሪያዎች በመታገዝ
ሙከራው በከፍተኛ ጥረት እየተከናወነ ነው ..የመጣው ሽማግሌ የፈረንጅ
ዶክተር በሳምንት ሁለት ቀን ወደ ሆስፒታል ወስዶኝ ከሌሎች ዶክተሮች ጋር
በመሆን በተለያዩ ዘመን አመጣሽ የህክምና ማሽኖች በመታገዝ እንድመረመር
ያደርገኛል…ያው ይመራመሩብኛል ማለት ይቀላል..ወጣቷም ቴራፒስት በልዩ
እንክብካቤ እና ጥንቃቄ ስራዋን እየሰራች ቢሆንም ከትርሲት ግን ይሁንታን
ሳላላገኘች የእሷን ማመናጨቅና ግልምጫ አማሯታል…ቢሆንም ተስፋ
አልቆረጠችም….ይሄም ፍሬ እንደሚያፈራ ፍንጭ እያሳየ ነው..የእግሮቼ ጣቶች
ተራ በተራ መንቀሳቀስ ጀምረዋል…
ዛሬ እማዬም ሆነ ትርሲት አብረውኝ ናቸው …ጊዜው መሽቷል …..ተከታታይ ፊልም
ስናይ ስለቆየን ሳናስበው ነው አምስት ሰዓት የሆነው..እናም ሁላችንም ተዳክመናል…
‹‹በሉ ተነሱ እንተኛ ››አለች እናቴ ..ትርሲት በፊቱኑም እናቴ እንደዛ እስክትል
እየጠበቀች ያለ ይመስል ቶሎ ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ጋደም ብዬበት
ከነበረው ሶፋ ወደ ዊልቸሬ አዘዋወረቺኝና እየገፋች ወደ መኝታችን አመራን …
እናቴም ከተቀመጠችበት ተነስታ ከኃላ ስትከተለን ይሰማኛል…ከዛ ሌለኛው
መኝታ ክፍል ውስጥ ገባች፡፡ እኔና ትርሲትም መኝታ ቤታችን እንደገባን
አወላልቀንና ተቃቅፈን ለመተኛት የአስር ደቂቃ ጊዜም አላባከንም…እኔ የምጠቀምበት መኝታ ክፍል በጣም ሰፊና ሁለት አልጋ ማዶና ማዶ ሁለቱን ትይዩ ግድጋዳዎች ተጠግቶ የተዘረጋበት ነው፡፡
ሀኪሞቹ ቀኑን ሙሉ ከወዲህ ወዲያ ሲያንገላቱኝ ድክም ብሎኝ ስለነበር
ወዲያው ነው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰደኝ…ብቻ ከምን ያህል ሰዓት ቡኃላ
እንደሆነ አላውቅም ኃይለኛ የበር መንኳኳት አረ ከመንኳኳትም አለፍ ያለ
የመንጎጎት አይነት ድምጽ ነበር ከእንቅልፌ ያባነነኝ….አይኔን ስገልጥ ትርሲትም
በድንጋጤ እና በመበርገግ ‹‹ማነው… ?ምንድነው ? ››እያለች በስስ ቢጃማ
የተሸፈነ ሰውነት እያምታታች ከአልጋው ዘላ ስትወርድ የመኝታ ቤታችን በራፍ
ተበርግዶ ሲከፈት ጥቁር ጭንብል የለበሱ ሁለት ወጠምሻ ሰዎች እናቴን
ከግራና..:
ከቀኝ አንጠልጥለው እየገፈታተሩ ይዘዋት ወደ ውስጥ ገቡ..ሶስተኛ
ጓደኛቸው በአንድ እጁ ሽጉጥ በአንድ እጅ ደግሞ የሚያብረቀርቅ ጩቤ ወድሮ
ይከተላቸዋል…
‹‹ እኔን እንደፈለጋችሁ ..ልጆቼን አንዳትነኩብኝ..ልጆቼ ጫፍ
እንዳትደርሱ….››እያለች ትማፀናቸዋለች ‹‹ምንድነው ምትፈልጉት …እናቴን
ልቀቋት …የፈለጋችሁትን ይዛችሁ ውጡ››ትርሲትም እየተርበተበተች መለፍለፍ
ጀመረች…..እኔ በተኛውበት ድንዝዝ እንዳልኩ ነው …የማየው ነገር በህልም
ይሁን በእውን እርግጠኛ መሆን አቃቶኛል..እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ …?
ግቢውን ሚጠብቅ ዘበኛ አለ እሱን እንዴት አለፉት….?
‹‹አትለፍልፊብን››ብሎ አንዴ በጥፊ አላሳት ትርሲትን…ፀጥ አለች….
‹‹በል እሰራት›› አለው… ሽጉጥና ጩቤ የደገነው ባዶውን ያለውን ጎደኛውን
‹‹መጀመሪያ ጎረምሳውን ባስረው አይሻለም…?››ጠየቀ ወደ እኔ እጠቆመ
‹‹ምኑን ታስረዋለህ .. ?ፈርቶ ከአልጋው ላይ መንቀሳቀስ አቅቶት በድን ሆኖ
እያየህ››መለሰለት በእኔ በማፌዝ
‹‹አረ እግዚያብሄርን ፍሩ… ልጄ መንቀሳቀስ የማይችል ዊልቸር ተጠቃሚ
ነው…››እናቴ ነች ተናጋሪዋ፡፡
‹‹አሀ እንደዛ ነው..?ስራ ቀለለልና….››አለ አንድ ሌላው እንደተባለው ከሰፊ
የጃኬት ኪሱ ውስጥ ገመድ አወጣና የትርሲትን እጆች ወደኃላ ጠምዝዞ አንድ
ላይ በማጣመር ጠፈነጋትና ከአልጋው የራስጌ ብረት ጋር አሰራት ‹‹እሷንም
ልሰራት?››ጠየቀ እናቴን እያየ..
‹‹አይ መጀመሪያ እሷኑ አፎን ክደንልኝ… አትለፍልፍብኝ ››ከአልጋው ላይ ለብሰን
የነበረውን አንሶላ መዥርጦ አወጣና በጩቤው የሚበቃውን መጠን ያህል
መጥኖ ሸረከተውና ለጓደኛው አቀበለው..
እሱም የትርሲትን አፍ በጨርቁ ጠቀጠቀና ..እናቴንም በተመሳሳይ ሁኔታ
አሰራት… በል አንተ ጠብቃቸው እኛ የሚጠቅም ዕቃ ከቤት ውስጥ እንምረጥን
በመኪናችን እንጫን …ስንጨርስ መጥተን እንነግርሀለን››ብለውት ሁለቱ
ተያይዘው ወጡ…የቀረው ጩቤውንም ሽጉጡንም በእጆቹ እያሽከረከረ የመኝታ
ቤቱን በራፍ ከውስጥ ቀረቀረና ፊት ለፊት ያለው ደረቅ ወንበር ላይ ተቀመጠና
ሶስታችንንም በማፈራረቅ መመልከት ጀመር..የተቀመጠበት መቀመጫ እኔ
ከተኛውበት አልጋ የሁለት ሜትር ያህል እርቀት አለው….ሰውዬው ሲታይ
ወጠምሻ እና አስፈሪ ነገር ነው..ምንም እንኳን በለበሰው ጭንብል ምክንያት ፊቱ
ባይታየኝም የሆነ ጥቁርና አሳፈሪ እንደሆነ እንዲሁ መገመት ችያለው
..ቀስ በቀስ እይታውን ከማፈራረቅ ወደ ማተኮር አሸጋገረው..አዎ ዓይኖቹን
ትርሲት ላይ እንደሰካ ፈዞ ቀረ …አዎ የሚያየው ደግሞ የተጋለጠ ገላ
..ስትንፈራገጥ ቢጃማዋ ወደ ላይ ስለተሰበሰበ የተራቆተ ጭኖን ነው…ድሮም
ለአመል ያህል ስውነቷን ይሸፍንላት የነበረውን ቢጃማ አሁን ጭረሽ ወደ ላይ
ተሰብስቦ ከውስጥ የለበሰች ሰማያዊ ፓንት እስኪታይ ድረስ ለእይታ
ተጋልጣለች…ትዝ ይለኛል አሁን የለበሰችውን ፓንትም ሆነ ቢጃማ የገዛችላት
እናቴ ነች.. ፡፡
ሶደሬ ሄደን በነበረበት ቀን …አሁን በዚህ ሰአት ይሄንን ማሰብ ምን ይሉታል …?
ሰውዬው በተቀመጠበት በመቁነጥነጥ ምራቅ እየዋጠ ነው..ምኑም
አላመረኝም..፡፡ቀስ ብሎ ተነሳና ቆመ‹‹አንቺ እንዴት አባሽ ታምሪያለሽ?››አለ የዛን
ጊዜ የሶስታችንም አይን በድንጋጤ ፈጠጠ..መላ ነገራችን በስጋት ታፈነ…
‹‹ይሄን ገላማ ጎደኛቼ እኪመጡ ዘና ልበልበት››
‹‹የፈራውት ደረሰ ..››አልኩ በልቤ አሁን እንዴት ነው ሚሆነው…?በምንስ ተዐምር
ነው ከዚህ ጉድ የምንወጣው…?እንዲህ ማፈቅራትን ሴት እንዴት ፊቴ
ይደፍራታል…?ከዛስ ብኃላ ሕይወታችን እንዴት ይቀጥላል…?ለመጀመሪያ ጊዜ
ያለውበትን ሁኔታ አምኜ መቀበል አቃተኝ….፡፡ ውስጤ በቁጣና በንዴት ከውስጥ
ይቀጣጠል ጀመረ … ሰውዬው በሀሳቡ እንደገፋበት ነው…የያዘውን ጩቤ ወንበር
ላይ እንዳስቀመጠ ሽጉጡን ብቻ በአንድ እጁ ቀስሮ ወደ ትርሲት ሄደና እጆቾን
ፈታቻው…እጆን አንጠለጠለና ወደ ሌለኛው አልጋ እየጎተተ ይዞት ሄደ …እጆቼን
እና አንገቴን እያወራጨው የሆነ ነገር ለማድረግ እየሞከርኩ ቢሆንም እሱ ግን
ነገሬም አላለኝ..እናቴም እጆቾም አፎም ስለተለጎመ አቅመ ቢስ ሆናለች….
ትርሲትን አልጋው ላይ ዘራራትና አንደኛው እጆን የአንዱ አልጋ ጫፍ ብረት ጋር
ሌለኛውን እጆን ከሌለኛው ብረት ጫፍ ሰትሮ አሰራት… ከዛ ደግፎ ሙሉ በሙሉ
ወደ አልጋው አወጣትና ዘረራት…እሷ በታሰረችበት በፍርሀት ጉንጮቾ ቀልተው
ፊ.ቷ በእናባ እየታጠበ… በአይኖቾ ስትለማመጠውና ስትለምንው ሳይ ውስጤ
ተገለባበጠ..ምንው አምላክ ለ5 ደቂቃ በተአምሩ ጤነኛ ቢያደርገኝ…?በዚህ
ሰዓት የመፅሀፍ ቅዱሱ ሳምሶን ነው ትዝ ያለኝ… በፍቅረኛው ደሊላ ተታሎ
ኃይሉን አጥቶ በጠላቶቹ እጅ ወድቆ በነበረበት በዛ ክፉ ደቂቃ የተሰማው ስሜት
ነው አሁን እኔንም እየተተሰማኝ ያለው.
👍7
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_አንድ

...ዮርዲ” ነው ያልኩት ? ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ከአቲዬ ቀጥሎ በዚች ምድር ያቆላመጥኩት ስም እነሆ..

ጠዋት ዩኒፎርሚን ለብሼ ደብተሮቼን አዘጋጀሁና እየቀፈፈኝ ወደ ትልቁ ቤት ሄጀ አንኳኳሁ፡፡

“ማነው?” አለችኝ ዛፒ፡፡ ደነገጠኩ፡

እኔ ነኝ አልኩ እየፈራሁ፡፡

«ግባ ክፍት ነው»፡፡ ገፋ ሳደርገው የሚያብረቀርቀው የጣውላ ሰር ድምፅ ሳያሰማ ተከፈተ ክፍቱን ነው ያደረው ማለት ነው::
ዝርከርክ ያለው ሳሎን ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ ዛፒ ሶፋው ላይ
የአልጋ ልብስ ጣል አድርጋ ተኝታለች፡፡ ፊቷ የተቀመጠው ጠረጴዛ ላይ የሻይ ብርጭቆ፣ የውሃ ጠርሙስ፡ ሩቡ ብቻ የተበላ ሰላጣ፣ ምንም ያልተነካ ዳቦ ዝርክርክ ብሏል፡፡ ብዙ ምግብ
ማቅረብና ምንም አለመብላት ልማዷ ነው ይገርመኛል፡፡

“ምንድነው በጠዋቱ“ አለች እየተነጫነጨች፡፡ ድምጿ የወንድ ይመስላል ጎርንኗል፡፡

"እ..ትምህርት ቤት ከሁሉም ትምህርት ቤቶች እንደኛ ወጣሁና ልንገርሽ ብዬ ነው"
ድምጼ ተንቀጠቀጠብኝ፡፡

ቀጥ ብላ ግራ በገባው ፊት እየችኝ፡፡ የሌሊት ልብሷን ትከሻዋና ትከሻዎ አካባቢ ይዛ አስተካከለች!
አቤት ደረቷ ቅላቱ ይንቦገቦጋል፡፡ ከኋላው ቢጫ መብራት የበራበት መስተዋት ይመስላል፡፡

"እኔ ምናገባኝ ታዲያ?!" የምትል መስሎኝ ነበር፡፡ ድንገት የሆነ ነገር ትዝ እንዳለው ሰው ፈገግ ብላ፤

"እና ሳመኛ! እንደዚህ ነው እንዴ የምስራች የሚነገረው? መርዶ አስመሰልከው እኮ!” አለችኝና
ሁለት እጆቿን እንደ ክንፍ ዘረጋቻቸው፤ ያውም በፈገግታ፡፡ ሁለት ጡቶቿ አፈጠጡብኝ፡፡

ግራ ገብቶኝ እንደቆምኩ፣ ና እንጂ ሳመኝ!” ብላ ጮኸትብኝ፡፡

በደመነፍስ እየተደነቃቀፍኩ ሄጄሄጄ ሄጄ ሄጄሄጀ.ሄጀ እጆቿ ሲጠመጠሙብኝ ሁሉ እርምጃዬን
ያቆምኩ አልመሰለኝም፡፡ ጥብቅ አድርጋ እቅፉኝ፣ “ጎበዝ የኔ ወንድም እኮራብሀለሁ!” አለችኝ፤
በለው ! ከሽ አለ የሻዩ ብርጭቆ ከጠረጴዛው ላይ ወድቆ፡፡ “ይሰበር ተወው!” አለቸኝና ጉንጬን
ስማ ለቀቀችኝ፡፡ ይሄ ቤት ለካ የወይዘሮ እጥፍወርቅ ቤት ነው !!

ከዛፒ ጋር እንደወጣሁ በደስታ ሰከሬ መንገዱን ሁሉ፣ ሰውን ሁሉ አየሁት፡፡ መቼ ነው ይሄ ትልቅ
የመኪና ኪራይ ማስታወቂያ ነዳጅ ማደያው ፊትለፊት የተሰቀለው ? መቼ ነው ይሄንኛው ሕንፃ
ተሰርቶ ያለቀው? ወቸ ጉድ አዲስአበባ እንዴት ተለውጣላች? ከሆነ አገር የመጣሁ መሰለኝ፡፡
ደግም ደስ የሚል ነገር ይሸተኛል፡፡ አፍንጫዬም ዛሬ ገና የተከፈተ ይመስል።

ዮርዳኖስ ጋር ስንገናኝ፣ “ምነው?” አለችኝ፡፡

"እ" አልኳት፡፡

"አይ ቆመህ ሳገኝህ ነዋ” አለችኝ፡፡ ለካስ ዮርዳኖስን ቆሜ አልነበረም የምጠብቃት። ያልጠበቅኳት
መስዬ ነበር መጠበቅ የነበረብኝ፡፡ ሳመችኝ ጉንጬን፡፡ ዛፒና ዮርዳኖስ እኔ በምባል ኳስ
በከንፈራቸው እየተቀባበሉ ቮሊ ቦል የሚጫወቱ መሰለኝ፡፡ "ተስመህ ትወጣለህ፣ ሰመው
ይቀባሉሀል የሚል ትንቢት ከሰማይ የታወጀም መሰለኝ፡፡ ድፍን አዲስ አበባ እንደ ዳቦ፡ እንደ
ዘይት፣ እንደታክሲ እኔን ለመሳም የተሰለፈ መስሎ ተሰማኝ፡፡(ቀስ ትደርሳላችሁ አትጋፉ ሂሂሂሂ)

ዮርዳኖስ ፈገግ ብላ አፍንጫዋን በመቀሰር ጠጋ አለችኝና፣ ደሞ አሪፍ ሽቶ ፣ እፉፉፉፉፉፉ
ያደረጉብ ማነው?" አለችኝ:: አፈርኩ፡፡ ለካ የዛፒ ሽቶ ነው ሲከተለኝ የነበረው፡፡ የዛቲ ሽፋ
የዋዛ አልነበረም፡፡ ከዚች ቀን ጀምሮ እድሜ ልኬን ሲከተለኝ ነው የኖረው፡፡ ሲያሳድደኝ ሳይሆን
ሲከታለኝ፡፡ የሆነ ዙሪያዬን ከብቦ እንደ እናት አቅፎኝ፡፡

ሰው ወደ ውስጥ የሚስበው አየር እክስጅን፥ ወደ ውጭ የማያስወጣው ካርቦንዳይ ኦክሳይድ እያሉ ያስተማሩን ቅኔ ነበር ሳይንሳዊ ቅኔ !! አሁን አሸብር ወደ ውስጥ የሚስበው ፍቅር፣ መፈቀር፣ መከበር፣ መፈለግን ነው፡፡ ወደ ውጭ የሚተነፍሰው እርካታ፡፡ የአየር ብክለት ማለት ሌላ ትርጉም የለውም እኮ የተገፉ፣ የተገለሉ፣ የተናቁ፣ ሕዝቦች ጥላቻን ወደ ውስጣቸው ሰበው መልሰው ጥላቻን ወደ መላው ዓለም መተንፈሳቸው ነው:: መፍትሄው የፍቅር ችግኝ በልባቸው
መትከል ነው:: እነሆ ዮርዳኖስ የተከለችውን ዝግባ ዛፒ የምትባል ዝናብ ስታረሰርሰው ዘርፈፍ
ብሎ በቀለ፡፡ ሕያውነት ከስሩ አረፍ የሚልበት ጥላ ሆነ፡፡

እኔማ ዛፒ ጥቁር ደመና አዝላ እያጉረመረመች ሰማይ ላይ ተንጠልጥላ ሳያት፣ መሽቆጥቆጥና ጥላቻዬን እንደ ዥንጥላ ስዘረጋ ነበር የኖርኩት፡፡ ክፉትም ጉልበት የሚኖረው እንደክፋት ልንቀበለው በተዘጋጀነው መጠን ነው::

“አንተ ሴት ነህ እንዴ?” ብላ ዛፒ ሳቀችብኝ፡፡ አፈርኩ፡፡ አንደኛ መውጣቴን ምክንያት በማድረግ
ዛፒ ልብስ ልትገዛልኝ ወሰደችኝና ምረጥ! ስትላኝ መጀመሪያ እጄ አንድ ቀሚስ ላይ አረፈ፡፡
ለእቲዬ ልኳ የሚሆን ቀሚስ ነበረ፡፡ ለዛ ነበር የሳቃችው::ልብስና ጫማ ገዛችልኝ፡፡ የሱሪዬን ቁጥር ስጠየቅ አላውቅም ነበር፡፡ ሱሪ ገዝቼ አላውቅማ፤ የጫማ
ቁጥርም አላውቅም፡፡ የሀብታም ልጆች ልብስና ጫማቸው ከሱቅ የተገባ ሳይሆን አብሯቸው
የሚወለድ ይመስለኝ ነበረ፡፡
ሃሃሃ… ግን ይሄው ሁሉ ነገር ሱቅ ውስጥ አለ ሸቀጥ ነው፡፡ ያው እዛጋ ቶማስ የሚባለው
ሁልጊዜ በሴት የሚከስሰው የክፍላችን ልጅ ጫማ ይሄው የራሄል ቦርሳ ኧረ ጉድ የቲቸር
ተስፋ የጥቁር ባለ ብዙ ኪስ ጃኬትም ያውና፡፡ ትንሽ ብቆይ እነዛ ውድ ነን የሚሉ ልጆች
እዚህ ተደርድረው ሲሸጡ አገኛቸው ይሆናል፡፡
ሲገርም ሁለት ሱሪ፣ አንድ ጫማ፣ ሁሉት ሸሚዝና አንድ ሹራብ ነፍስ ካወቅኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ልብስ ከሱቅ ገዛሁ፡፡ ለካሁት፡፡ መስተዋቱ ፊት ስቆም ደነገጥኩ፡፡ ልብስ ማለት ተራ ድሪቶ ነው ምናምን የሚሱ ሰዎች እንዴት ጅሎች ናቸው እባካችሁ! ራሴን በመስተዋት ሳየው ታላቅ ፍንዳታ እዕምሮዬ ውስጥ ተፈጠረ፡፡

እወራረዳለሁ ጥቁር አምበሳ፣ ኮከበ ፅባህ፣ ምኒሊክ፣ መነን፣ አዲሰ ከተማ፣ ድልበር፣ ቦሌ ከሚማሩ ተማሪዎች ሁሉ አንደኛ ቆንጆና ወንዳወንድ አቋም ያለኝ ልጅ እኔ ነኝ !! እፎይ! ከቤተክርስቲያን ሃጢያቱን ተናዞ እንደወጣ ሰው ሸክሜ ቀለለኝ አደግኩ ደግሞ !! የክፍሌን ልጆች በየቤታቸው እየሄድኩ እጄን ኪስና ኪሴ እስገብቼ “ሃይ!” ማለት አማረኝ፡፡

ዛፒ የለበስኩት አዲስ ሹራቡ ላይ የነበረውን ወረቀት ከኋላ ክሩን በጥርሷ በጥሳ አላቀቀችልኝና፣
አንተ ልጅ ቆንጆ እኮ ነህ አለችኝ፡፡ በሙቅ ውሃ በተሞላ ገንዳ ውስጥ የመግባት ያህል ቓሏ ይሞቅ ነበር፡፡ ቆንጆ መሆን ማለት የአፍንጫ መሰልከከ፣ የዓይን መንከባለል፤ የጥርስ መደርደርና
ንጣት ማለት አልነበረም፡፡ ለኔ ቆንጆ ማለት በሰው ዓይን መሙላት ማለት ሆነልኝ፡፡

ዝም ብላችሁ የሕይወት መንገዳችሁኝ ዙሩና ተመልከቱ! አለቀ ያላችሁበት ቦታ ላይ የነበረውን የሚመጣውን የሚያያይዝ ድልድይ ይኖራል፡፡ ይሄን ድልድይ የሚያምኑ ፈጣሪ ነው ይሉታል የማያምኑ 'የስነሕይወት መርህ ነው' ይሉታል፡፡ ለእምነቱም ለሳይንሱም ግድ የማይሰጣቸው እድል ይሉታል፡፡ እኔ ግን ይሄ አንዴ በዛ አንዴ በዚህ የሕይወቴን ተራዳ አየደገፈ የሚያቆመው
ከአቲዬ ድፍን ሃምሳ ብር የተበደረው እግዚያብሔር ነው እላለሁ፡፡
👍3316