#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
“ደብረ ወርቅ ማርያም የሥዕል ንጉሥ አለ።”
የአስራ ስምንት ዓመቱ ብርሃን ሰገድ ኢያሱ በትምህርት የበሰለ፣
በአስተሳሰቡ የበለፀገ፣ በመልኩና በአቋሙ ያማረ ሆነላት ምንትዋብ።ፈረስ ላይ ተቀምጦ፣ ነጭ ሻሹን ሹሩባው ላይ አስሮ፣ በወርቅ ያጌጠ ካባውን ደርቦ፣ የወርቅ በትረ መንግሥቱን ጨብጦ፣ ቀይ ድባብ ተይዞለት፣ ባልደራስ አጅቦት ከግቢ ሲወጣ፣ ሕዝቡ፣ “አቤት አበቃቀሉ!
አቤት የፊቱ አወራረድ!” እያለ አደነቀው: ወደደው፤ አከበረው፤
ሰገደለት፤ “ቋረኛው ኢያሱ” የሚል ቅጽል ስምም አወጣለት።
አደን አፍቃሪው ኢያሱ እንደ በፊቱ ሰስና ድኩላን ሳይሆን፣ ዝሆን፣
አውራሪስና ጎሽ እየገደለ መምጣት ጀምረ። ምንትዋብና እናቷ ግን ለአደን በወጣ ቁጥር ወገባቸውን በገመድ እየታጠቁ፣ መሬት እየተኙ፣ እየጸሙና እንቅልፍ እያጡ ይሰነብታሉ።
ኢያሱ በድፍረቱና በጀግንነቱ ተወዳዳሪ አጣ። ስለሃገር ጉዳይም መከታተል፣ ውሳኔ መስጠትና እርምጃ መውሰድ ያዘ። ከእናቱ መዳፍ ሥር ወጥቶ የራሱ ሰው ሆነ። አክሱም ጽዮን ሄደ። የእናቱን የትውልድ
ቦታ ለማየትም ቋራ ደርሶ መጣ። አንድ ጊዜ የግዛት ማስፋፋት ፍላጎቱ አድጎ ሰቆጣ ሄዶ ተሸንፎ ቢመጣ፣ በቁጭት ወኔውን ሞልቶ ሱዳን ጠረፍ ሄደ፡፡
የገጠመውን ጦር አሸንፎ በሰላም ተመለሰ።
በሰላም ይመለስ እንጂ ከእናቱ ጋር አተካራና ቅያሜ ውስጥ ገባ።
በግራዝማች ኢያሱና በእናቱ መሃል ያለው የፍቅር ግንኙነት ይከነክነው
ገባ። ምንትዋብም ወለተእስራኤል ያለቻትን ሦስተኛ ልጇን ከወለደች
ቆይታለች።
ኢያሱ እናቱ ላይ ቅሬታና ምሬት አደረበት። ምንም እንኳ እናቱን
ቢያከብርና ቢፈራ፣ ከግራዝማች ኢያሱ ጋር ያላትን ግንኙነት ችላ
የማይለው ጉዳይ ሆነበት።
ፀሐይ መግቢያ ላይ ነው። እናትና ልጅ ቤተመንግሥት እንግዳ
መቀበያው ክፍል ተቀምጠዋል። ኢያሱ ነገር ሲገባው ታውቃለች
ምንትዋብ። ገና፣ “ኸያሱ ጋር..” ሲልና ሲጠጣበት የነበረውን የወርቅ ዋንጫ ሲያስቀምጥ፣ የንግግራቸው አቅጣጫ ወዴት እንደሆነ ገባት።
“ኸያሱ ጋር ባለሽ ግንኙነት ሰው ሁሉ ያማሻል። ቀደም ብየ ብሰማም ዕድሜየም ገና ስለነበር ፈርቸ እስተዛሬ በዝምታ ቆየሁ” አላት።
“ኢያሱ አባትህኮ ሲሞቱ ዕድሜዬ ገና ነበር። ብቸኛም ነበርሁ።
ልችም መውለድ ፈልግ ነበር። ደሞስ እንዲህ ያለው በኔ ተዠመረ?” አለችና፣ ለራሷ ዛዲያ እንዴት ልሁን ሰው መሆኔ ቀረ? እቴጌ ያሉኝ እንደሁ ሰው ማይደለሁ እንዴ? ሰው መሆን ዛዲያ ትርጉሙ ምኑ ላይ ነው? ስትል መናገር ሲጀምር ቀና አለች።
“የመዠመርና ያለመዠመር ጉዳይ ማዶል” አለ፣ እናቱ ላይ አድርጎ
በማያውቀው መንገድ ፊቱን አኮማትሮ።
ከእሷ ስሜት በላይ ክብር የሚባል ነገር አለ።
መልስ አልሰጠችውም። ስሜቱ እንደተጎዳ አውቃለች። እባክህ
አምላኬ ኸልዤ ጋር እንዳልጣላ ትግስት ስጠኝ አለች።
“ኢያሱ አንደኛ ያክስቴ ልዥ ነው” ሲል ቀጠለ። “ያባቴ እት...
የወለተስራኤል ልዥ እኮ ነው። ያባቴ ክብርስ ቢሆን፣ ስለምን ይነካል? ላንቺም ቢሆን ነውር ነው። ስለምንስ ስማችን በዝኸ ይነሳል? መልካም ስምሽንስ ስለምን ታጎድፊያለሽ? ግራማች ብትይውም ሰዉ አሁንም
ምልምል ኢያሱ ነው ሚለው። ኸዝኸ ወዲያ ውርደት ምን አለ?”
ንግግሩ ጎመዘዛት። ከንፈሯን በጥርሷ ነከስ ኣድርጋ በግራ ሌባ ጣቷ መታ መታ አደረገችው። ቁጣ ሰውነቷ ውስጥ ሲቀሰቀስ ተሰማት።
“ተው እንጂ ኢያሱ! እኔን እናትህን እንዲህ አትናገር። ምወድህ
እናትህ እንጂ ሌላ ነኝ?”
“ሰዉ ያማሻል እኮ!” ግንባሩ ኩምትር ብሏል።
“አምተው በቅቷቸዋል። ኢያሱ ... ኸግራማች ጋር ተዋልደናል እኮ!
እህቶችህ የማን ይመስሉሃል? እኔ ያባትህን ስም ለማጉደፍ ሳይሆን፣
ብቸኝነት ስላጠቃኝ ነው። ተረዳኝ እንጂ!”
“ኸዝኽ ወዲያ ውርደት ምን አለ?” የሚሉት ቃላቶቹ ረበሿት። ትክ ብላ አየችው። ፊቱ ላይ ቅያሜ አየች። ዛዲያ ዕድሜዬን እንዲሁ
ላሳልፍ ኑሯል እንዴ? አለች።
ለእሱ የክብር ጉዳይ እንደሆነ አላጣችውም። እንኳንስ የባሏን
የእህት ልጅ ባሏ የሞተባት ንግሥት ጨርሶ ሌላ ማግባት እንደሌለባት ታውቃለች።
ግን ደግሞ ውጣ ውረድ ከበዛበት የቤተመንግሥት ሕይወት ዘወር ብላ የምትዝናናበትና ሐሳቧን የምትከፍልበት ነገር ባለመኖሩ፣
አንድ ቀን ከልጇ ጋር የሚያቃቅራትና አልፎም ሊያጣላት የሚችል ነገር እንደሆነ ብታውቅም አድርጋዋለች።
ከልጇ ጋር ይህን ያህል ጠንከር ያለ ንግግር ተለዋውጠው ስለማያውቁ ቅር ብትሰኝም፣ የምትወደውንና የምትሳሳለትን ገራሙን ልጇን መቀየም
አልሆነላትም። ቅሬታና ቅይሜ በሆዷ አምቃ መሄድ አልፈለገችም።
የአባቱ ብቻ ሳይሆን የእሱ፣ ብሎም የእሷ ክብር እንደተነካበት ስላወቀች ትችቱን ተቀብላ ዋጥ ማድረግን ፈለገች።
በራሷ አምሳል ቀርጻ ያወጣችው ቢመስላትም፣ እየተመካከረች፣
ሲሻትም እየተጫነችው ያሳደገችው ልጇ ብሩህ አእምሮ ያለውና በራሱ አስተሳሰብ የሚመራ መሆኑን በመገንዘብ ልቧ ላይ ሊሰርፅ የቃጣውን
ቅሬታ ለመግታት ታገለች።
ለብቻው ለመግዛት ዕድሜው ቢፈቅድለትም፣ ለእሷ ካለው ፍቅር፣አክብሮትና ፍራቻ ጭምር የእሷን የበላይነት ተቀብሎ መኖር እንደቻለ ተገነዘበች። እሱም ቢሆን ከሥልጣኗ ለማውረድ የሚያስችለው በቂ
ምክንያት የለውም።
እንዲያውም የእሱ መንግሥት በእሷ ብርታት፣ ጥበብና ዘዴ የተሞላው አመራር መደላደሉን፣ አንዳንድ መኳንንት ቋረኞች ላይ ያላቸውን ጥላቻ አርግባ ተስማምታና አስማምታ መቆየቷን፣ ከአንዴም ሁለት
ጊዜ የተቃጣባቸውን ዓመጽ ድል መቀዳጀታቸውን፣ ሌሎችን ደግሞ
በሰላማዊ ድርድር እየፈታች ሰላም እንዲሰፍን ማድረጓን ይገነዘብ
እንደሆነ ራሷን ጠየቀች። ይህን ልታስታውሰው ግን አልፈለገችም፤
ዝም ብላ ተቀመጠች። ተነስቶ ሲወጣ በተለመደው የእናትና የልጅ ፍቅር አልተሰነባበቱም።
ከሄደ በኋላ፣ የተነጋገሩትን ሁሉ በጭንቅላቷ ከለሰችው። መቸም
እኔስ ብሆን በነገሩ ሳልጨነቅ ቀርቸ ነው? አልሆንልኝ ብሎ ነው እንጂ።ብቸኝነት አጥቅቶኝ ነው ኸኢያሱ ጋር እዚህ ሁሉ ውስጥ የገባሁት።እሱም ቢሆን እነአስቴርን የመሳሰሉ ልዦች ሰጥቶኛል። ኸንግዲህ
ምን አረጋለሁ። የአብራኬ ክፋይ እንዲህ ሲለኝ መስማት ለእኔ ደግ
ማዶል። መቸስ የክብር ጉዳይ ሆኖበት ነው። በዝኸ አልቀየመውም። እነሱ እንዳይጣሉብኝ እንጂ። ለግራማች ኢያሱ ነግረዋለሁ እያለች አሰላሰለች።
ግራዝማች ኢያሱ፡ “ብርሃን ሰገድ ኢያሱ ተለውጦብኛል” ማለት
ሲያዘወትር፣ እንዳይጣሉባት ሰጋች፤ በሐሳብ ባከነች። እየቆየም በሁለቱ መሃል ነገሮች እየከረሩ፣ ግንኙነታቸው ወደ ፀብ መቀየሩ እንቅልፍ አሳጣት። አስታራቂ ሽማግሌዎች ላከች።
ይህ ሳያንሳት በመጋቤ ሥነ-ጊዮርጊስ አማካኝነት ሁለተኛው የጥላዬ ሥዕል መጣላት። የሥዕሉ ውበትና የያዘው ጥልቅ ሐሳብ
ቢያስደስታትም፣ ሁለቱም ሥዕሎች ከአንድ ሥሙር ከሚባል ሰው መምጣታቸውን በሥራው አረጋገጠች፤ ለወራት ተረበሸች።
እነዚህን ሥዕሎች የሚልከው ሰው ምን አስቦ እንደሆነ ለማወቅ
ቸገራት። እኼ ሰው ስለምን ማንነታቸው ስንኳ በማይታወቅ ሰዎች ይልካል? ይኸ ከበጎ አሳብ የመጣ ነው ወይንስ እኔን ሰላም ለመንሳት ሚደረግ እኔ ለራሴ ኸልዤ ጋር ችግር ውስጥ በገባሁበት ግዝየ ስለምን
እንደዝኸ ያለ ነገር ይገጥመኛል? አንቺ ምወድሽ ቁስቋም የዝኸን ሰው ማንነት አንቺው ግለጭልኝ እያለች ማርያምን ተለማመነች። ለሌላ ሰው የማታዋየው ምሥጢር ሆኖባት ሥዕሉን በመጣበት ጨርቅ መልሳ ጠቅልላ ከበፊተኛው ሥዕል ጋር ደብቃ አስቀመጠችው።

👍14
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
አደገኛው
የበጋው ወራት አልፎ ክረምት ገባ:: ግን አባባ ሸበቶም ሆነ ልጅቷ ድሮ ይመላለሱበት ከነበረው የሽርሽር ቦታ ብቅ አላሉም:: ማሪየስን ያስጨነቀውና ያጓጓው ያቸን ወለላ ፤ ያንን በውበት ያጌጠን ፊት ለማየት
ነበር፡፡ በቃኝ፤ ሰለቸኝ፧ ደከመኝ፤ ሳይል ጠዋት ማታ ፈለጋት:: ወጣ፧
ወረደ፤ ተንከራተተ፤ ግን አላገኛትም:: በዚህም የተነሳ ወትሮ ቆራጥ፧ ደፋር፧ ብልህ፣ አርቆ አስተዋይና የወደፊት ሕይወቱን በኩራትና በተስፉ ይመራ የነበረው ወጣት ከቤት እንደተባረረ ውሻ ዓላማቢስና ተንከራታች ሆነ፡፡ በአሳብ ባህር ሰጠመ:: የእርሱ ነገር በቃ ፤ አከተመ:: ሥራ አስጠላው፡ ቆሞ መሄድ ሰለቸው ፤ ብቸኝነት ሰውነቱን ወረረው:: ከፊቱ፡ ድቅን ብለው ይታዩ የነበሩት ብሩኅ ተስፋ፣ የኑሮ ግብና እውቀት እንደ ጭስ ተነኑበት፡ ዓለም የጨለመችና የተደፋችበት መሰለው:: አሁን የሚኖረው ቀደም ሲል ይኖርበት ከነበረው ቤት ውስጥ ነው::በዚያ አካባቢ ለነበረ ለማንም ደንታ አልነበረውም:: አንድ ጊዜ ተቸግረው የቤት ኪራይ የከፈለላቸው ጎረቤቱ፡ አሁንም አሉ:: ሌሎች ጎረቤቶቹ ግን
ቤት ለቅቀው ወደ ሌላ ሰፈር ሄደዋል፡፡ አንዳንዶቹም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል:: አንዳንዶቹም የቤት ኪራይ ለመክፈል ባለመቻላቸወ
ተባርረዋል::
እንድ ቀን በጠዋት ተነስቶ ቁርሱን በልቶ እንደጨረስ የነበረበት
ክፍል በር በዝግታ ይንኳኳል፡፡ የሚሰረቅ ንብረት ስላልነበረው ብዙውን ጊዜ የቤቱን በር አይቆልፍም፡፡ በሩን የሚቆልፈው ከበድ ያለ ሥራ ሲይዝ ብቻ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወደ ውጭ ሲሄድ እንኳን በሩን ክፍት ትቶ ነበር
የሚሄደው::
በሩ እንደገና በዝግታ ተንኳኳ፡፡
«ይግቡ» አለ ማሪየስ፡፡
በሩ ተከፈተ::
«ይቅርታ ያድርጉልኝ፤ ጌታዬ!»
የሚያቃስትና የደከመ ድምፅ ነበር፡፡ በመጠጥ ኃይል ተዳክሞ በቅጡ መናገር የተሳነው የሽማግሌ ድምፅ ይመስላል፡፡ ማሪየስ ዞር ብሎ ሲያይ
አንዲት ወጣት ልጅ ከበሩ ቆማለች::
ወጣትዋ ገና ልጅ ናት:: የለበሰችው ልብስ የተቀዳደደ ቡትቶ ስለነበር ስውነትዋ በብርድ ይንቀጠቀጣል፡፡ ሰውነትዋ ከመገርጣቱም በላይ አመድ
የለበሰች ይመስል ነጫጭባ ሆኖአል፡፡ ትንሽም አካልዋ የተሽፈነው ከወገብዋ
በታች ነው እንጂ ራቁትዋን ናት ማለት ይቻላል፡፡ በቀበቶ ፈንታ ቀሚስዋን የታጠቀችው በገመድ ነው:: ፀጉርዋንም ያሰረችው በቃጫ ገመድ ነው፡፡እጆችዋ በጭቃ ላቁጠዋል:: አንዳንድ ጥርሶችዋ የሉም:: ዓይኖችዋ ከመቦዘዝ አልፈው ፈዝዘዋል:: የአሥራ አምስት ዓመትዋ ወጣት የሃምሣ ዓመት አሮጊት መስላለች:: ታስጠላለች፤ ታሳዝናለች:: ማሪየስ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ በመገረም አያት:: በቅዠት ዓለም የምትታይ እንጂ በእውን ያለች አልመሰለውም።
የሚያሳዝነው አፈጣጠርዋ አስቀያሚ አልነበረም:: ተፈጥሮ የውበት ፀጋ አስታቅፎአታል:: በሕፃንነትዋ በጣም የምታምር፤ በጣም የተዋበች ልጅ እንደነበረች ታስታውቃለች:: የችግር ብዛት ውበትዋን ጨርሶ ሊያጠፋውና ሊያበላሸው አልቻለም:: ደመና በሰፈነበት እለት የፀሐይ ጨረር ለመታየት እንደሚታገልና ብልጭ ድርግም እንደሚል ሁሉ ውበትዋ
በማጣት ጨለማ ቢዋጥም መታየቱ አልቀረም::
«ምን ነበር፤ የእኔ እህት?» ሲል ማሪየስ ጠየቃት::
ልጅትዋ እንደሰከረ ሰው እየተንገዳገደች ተናገረች::
«ይህን ማስታወሻ ስጭ ነው የተባልኩት መሴይ ማሪየስ::
ማሪየስ ብላ ነው በስሙ የጠራችው:: እንደምታውቀው ተገነዘበ፡፡
ግን ማን ናት ይህቺ ልጅ? የማሪየስን ስም እንዴት አወቀች?
«ግቢ» ብሎ ሳይጋብዛት ወደ ውስጥ ገባች፡፡ ያልተነጠፈውን አልጋና ከወለሉ ላይ የተበታተነውን ወረቀት አየች፡፡ ጫማ አላደረገችም ባዶ እግርዋን ናት፡፡ ጭንዋ አካባቢ ልብስዋ ስለተቀደደ ገላዋ ይታያል፡፡ ከጉልበትዋ ጀምሮ ልብስዋ በመቦጫጨቁና ፀጉርዋ በመቆሙ በጣም እንደበረዳት በጉልህ ይታያል፡፡
ደብዳቤውን ሰጠችው:: ማሪየስ ደብዳቤውን ከፍቶ አነበበው::
«ውድ ጎረቤትና የተወደድክ ወጣት..
በጣም እንደምታዝንልኝ ሰምቻለሁ፡፡ ባለፈው ጊዜ የስድስት ወር የቤት ኪራይ እንደከፈልክልኝ ደርሼበታለሁ:: የእኔ ልጅ እግዚአብሔር
ይባርክህ፡፡ ላለፉት ሁለት ቀናት እህል የሚባል ነገር በአፋችን እንዳልገባ ትልቅዋ ልጄ ትነግርሃለች:: ባለቤቴም ታምማለች፡፡ ከአሁን ቀደም ልብህ
እንደራራልኝ ሁሉ አሁንም እንደማትጨክንብኝ እተማመናለሁ፡፡ ስለዚህ
የተቻለህን እርዳን:: ልጄም የፈለገኸውን ሁሉ ትታዘዛለች፡፡»
ማሪየስ ተገርሞ የደብዳቤውን መልዕክት ሲያሳያት ልጅትዋ በድፍረት ክፍሉ ውስጥ ከወዲህ ወዲያ ትላላች:: ራቁትዋን መሆንዋን ብታውቅም
ስሜት አልሰጣትም:: ወንበሮችን አስተካክላ የወዳደቁትን ወረቀቶች አንስታ ከጠረጴዛ ላይ አኖረች::
«እህ መስታወትም አለህ!» አለች::
እንደ ማንጐራጉር ብላ ትዘፍን ጀመር:: ሆኖም በውስጥዋ የተዳፈነ ጭንቀትና ፍርሃት እንዳለባት እንጉርጉሮው ሳያሳጣት አልቀረም፡፡ ካላበዱ
በቀር ከሰው ቤት ገብቶ ባለቤት መሆን እንደሚያሳፍር የታወቀ ነው፡፡
ማሪየስ «ዝም ልበላት ወይስ ልናገራት» እያለ አሰላሰለ፡፡ ወደ መጽሐፍ መደርደሪያው ሄደች::
«እንዴ! ብዙ መጽሐፍ ነው ያለህ» አለች፡፡
ፊትዋ በራ ፧ ኩራት ኩራት አላት:: ማንኛውም ሰው አንድ የሚኩራራበት ነገር ካገኘ መንፈሱ ይረካል፤ ሞራሉ ይገነባል፡፡
«ማንበብ እችላለሁ ፤ እውነቴን ነው እችላለሁ» ስትል ተናገረች::
ቶሎ ብላ ተገልጦ የነበረውን መጽሐፍ አንስታ ማንበብ ጀመረች::ወዲያው ማንበቡን በመተው መጽሐፉን አስቀመጠች:: መንጎል አነሳች::
«መጻፍም እኮ እችላለሁ::»
ከቀለም ብልቃጥ አጠቀሰች:: ወደ ማሪየስ በመዞር «ለማየት
ትፈልጋለህ? መጻፍ እንደምችል ላሳይህ?» ስትል ጠየቀችው::
መልስ እንዲሰጣት ሳትጠብቅ ከጠረጴዛው ላይ ከነበረው ባዶ ወረቀት ላይ ጻፈች፡፡ ከዚያም ቀና ብላ ማሪየስን አየችው::
«በጣም ቆንጆ ልጅ እንደሆንክ ታውቃለህ?» ስትል ጠየቀችው::
እርስዋ ለምን ፈገግታ እንዳሳየችው እርሱ ደግሞ ለምን ፊቱ በቶሎ እንደቀላ በመገረም ሁለቱም በየበኩላቸው ያሰላስሉ ጀመር፡፡
ወደ ማሪየስ ተጠግታ እጅዋን ከትከሻው ላይ አሳረፈች:: ምነው
ሁልጊዜም ትዘጋኛለህ፡፡ እኔ እንደሆነ በደምብ አውቅሃለሁ፡፡ ደረጃ ላይ ዘወትር እንገናኛለን፡፡ እኔ አይሃለሁ ፤ አንተ ግን አታየኝም:: ፀጉርህ እንዲህ ተንጨባሮ ሳየው ደስ ይለኛል፡፡»
ስትናገር አንደበትዋን አለስልሳ ነው፡፡ ድምፅዋን ዝቅ አድርጋ በመናገርዋ ወይም በሌላ ምክንያት ይሁን አይታወቅም ከተናገረቻቸው ቃላት አንዳንዶቹ
ማሪየስ ጆሮ ውስጥ አልገቡም:: ማሪየስ ቀስ ብሎ ወደኋላ አፈገፈገ።በዚህ ጊዜ ወደ አንድ ሌላ ሰው እንድታደርስ የተጻፈውን ሌላ ማስታወሻ ገልጣ አሳየችው::
“ይኸው» አለች ፤ «ይህን ማስታወሻ መንገዱን አቋርጦ ከሚገኘው ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚገኙ መነከሴ የምሰጠው ነው:: ምናልባት ከራሩልን ለቁርሳችን የሚሆን ምግብ ይሰጡናል::»
ይህን እንደተናገረች መሳቅ ጀመረች:: (ማሽላ እያረረ ይስቃል» ይባል የለ፡፡ ንግግርዋን ቀጠለች::
ዛሬ ቁርስ ብናገኝ ምን እንደሚባል ታውቃለህ? ከሁለት ቀን በኋላ
ቁርስ ቀመስን ይባላል:: ቁርስ ከተገኘ እንግዲህ ከትናንት ወዲያ ጀምሮ መብላት የነበረብንን ቁርስ፣ ምሳና እራት በላን ማለት ነው:: ከተገኘማ እሱንም በአንዴ መጠቅጠቅ ነው!»
ይህን ስትናገር ልጅትዋ ለምን እንደመጣች ታወሰው::

👍13
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሳቤላ ጤናዋ ተመልሶላት : ከዚያ አሳፋሪ ፈተና አምልጣ ከአስተማኝ ቦታ ደርሳ ከልጆቿ ጋር ተገናኘች ነገር ግን ጊዜን ጊዜ እየወለዶ ሲሔድ በዓለም የነበሩት
"ምትወዳቸው ሁሎ አልቀውባት ብቻዋን የቀረች ይመስል የሚያስፈራ ስሜት እየተገዳደራትና እያባተታት ኀዘንና ጭንቀት እየገባት መተከዝ መፍዘዝ ጀመረች "ያን ክፉ ሰው ከልቧ ለማውጣት በሞከረች ቁጥር እየታደሰ ይመጣባት ጀመር ራሷም ብትሆን ፍራንሲዝ ሌቪዞንን በሐሳቧ እንኳን እንዳይመጣት እንዳልተጨነቀች ሁሉ አሁን ከሱ መለየቷ ቁርጥ ነገር ሲሆን ጊዜ መልሳ ለአንድ ቀን ኧረ
ሊአንድ ሰዓት እንኳን ቢሆን ብታየውና ናፍቆቷን በዐይን ቢወጣላት ትመኝ ጀመር
አንድ ጊዜ ካየችው በኋላ እንደሚረጋላት ተስፋ ስታደርግና ስትመኝ ራሷን በራሷ
ስትቃረን ከሐሳቧ ብንን ብላ ትነቃለች። ይህ ሐሳብ እሷ ሳትፈልገው ነበር ከልቧ የሚገባው
የፍራንሲዝ ሌቪሰን ምስል ቀኑን ሙሁ እንደ ተደቀነባት ውሎ ሌሊቱንም በሕልሟ ሳይለያት ያድራል " ከእንቅልፋ ስትነቃ ነገሩ ሁሉ ባዶ መሆኑን ስታውቀው ትጨነቃለች እነዚህ ሕልሞች እንደማይመጡባት እሱንም በሔሳቧም ሆነ በሕልሟ እንዳታየው ለማድረግ የፈለገውን መሥዋዕት ለመክፈል አታመነታም ነበር ። ግን ማገድ አልቻችም » ስለዚሀ ምስኪኗ ወይዘሮ ሳቤላ ከዕንቅልፏ በነቃች
ቁጥር የሕሊና ወቀሳ ጭንቀትና ትኰሳት ያጣድፋት ነበር ይህ በሽታ ከሥሩ ተነቅሎ እንዲጠፋላት ብትመኝም ከመልቀቁ በፊት ታላቁ ዋሽ ጊዜ አልፏት እንደ ሚሔድ ታውቅ ነበር
አንድ ቀን ጧት ሚስተር ካርላይል ፈረሱን ጫነና ወደ ሌቪሰን ፓርክ ሔደ ከሰር ፒተር ጋር ለመገናኘት ሲጠይቅ ወደ እመቤት ሌቪሰን አስገቡት " ዐይነ ገብ የሆነ ደማቅ ልብስ የለበሰች መልከኛ ወይዘሮ ነበረች » የመጣበትን ጉዳይ ጠየቀችው ።
"የኔ ጕዳይማ እመቤት .... ከሰር ፒተር ጋር ነው ”
ሰር ፒተር አሟቸው እንደ ስነበተ ስላልተሻላቸው' ባለኍዳዮችን ማነጋር አይችሉም " ይረበሻሉ ይጨነቃሉ ” “ እኔ እንኳን የመጣሁት ራሳቸው በሰጡኝ ቀጠሮ ነው በስድስት ሰዓት ነበር
የቀጠሩኝ " ይኸው አሁን መሙላቱ ነው ።"
ወይዘሮ ሌቪሰን ከንፈሯን ነከሰችና ደስ ላይላት ስትፈቅድለት ወዲያው ወደ ሰር ፒተር የሚያስገባው አሽከር ብቅ አለ " ሚስተር ካርላይል ገባ እዚያ ድረስ
የመጣበትን የፍራንሲዝ ሌቪሰንን ዕዳዎችና ጥፋቶች እንዲሁም ከስደቱ ስለሚመለስበት ነገር አንሥተ ተነጋገሩ "
“ ዛሬ ዕዳውን ሁሉ ከፍዬ ነጻ ባወጣው ነገ ደግሞ ተመልሶ ከዚያ ይገባና ዘለዓለም እንደ ከፈልኩ መኖር ነው እንግዲያ ካያቱ ሌላ ወንድም የለኝም » አባቱም የተባረከ ሰው ነበር " እሱ የሚረባ ሰው አንዳይመስልህ .... ሚስተር ካርላይል " ብላሽ ሰው ነው " አለው ሰር ፒተር "
ታሪኩን ሲነግረኝ አሳዘነኝና እርስዎን እንደማጋግርለት ነገርኩት እንጂ እኔ ስለ ደግነቱና ስለ ክፋቱ የማውቀው ነገር የለም
አለ ሚስተር ካርላይል "
“የሱን ሥራ ባታውቀው ይሻላል አሁን እሱ የሚፈልገው ዕዳውን ሁሉ እንድከፍልለትና እንደገና አዲስ ኑር እንዲጀምር ነው እኔ እዚህ እሱ ባሕር ማዶ ሆነን የሚደረግ ነገር ሊኖር አይችልም ቀርቦ መተሳሰብ አለበት . .
"እሱማ ተደብቆም ቢሆን ወደ ኢንግላንድ መምጣት አለበት »
እዚህ ቤት ግን መግባት አይችልም አለ ሰር ፒተር ፈጠን ብሎ ባለቤቴ ለአንድ ቀን እንኳን አታስጠጋውም።
ኢስት ሊን መጥቶ ሊሰነብት ይችላል መቸም ከዚያ ይመጣል ብሎ ማንም አያስበውም እርስዎ ሊረዱት እየፈለጉ ለመገናኘት ባለመቻላችሁ ብቻ እርዳታው ሊቀርበት አይገባም።
ከሚገባው በላይ አዘነክለትሳ ሚስተር ካርላይል ? ጥብቅና ልትቆምለት አtበሃል ልበል ?
“ አላሰብኩም ! እኔ አልቆምለትም"
ከዚያ ትንሽ ተነጋግረው ካፒቴን ሌቪሰን እንዲላክበት ተስማምተው ሚስተር ካርላይል ተስናብቶ እንደ ወጣ ከወይዘሮ ሌቪሰን ጋር ተገናኙ "
ከባለቤቴ ጋር የተነጋገራችሁት ስለዚያ ስለ ወንድማቸው ልጅ ጕዳይ መስሎኛል።
“ ነው” አላት ሚስተር ካርላይል ።
ስለሱ ያለኝ ግምት በጣም መጥፎ ነው !ይሁንና አንተም በኔ ላይ መጥፎ አስተሳሰብ እንዲያድርብህ አልፈልግም ። ፍራንሲዝ ሌቪሰን የባሌ የወንድም የልጅ ልጅና ተስፈኛ ወራሽ ነው " ስለዚህ በሱ ላይ ጥላቻ ስለ አደረብኝ ነገሩን የማያውቁ ሰዎች በኔ ሊገርማቸው ይችላል " የዛሬ ሦስት ዓመት ግድም ሰር ፒተርን ሳላገባ እንዲያሙም ሰር ፒተርን ግና ሳላውቃቸው ፍራንሲዝ ሌቪሰን የኔ ወዳጆች ከሆኑ ስዎች
ጋር ተዋውቆ ኖሮ ከነሱ ቤት አግኝቸው ነበር " በነሱ ላይ የሚያሳፍር በደል ፈፀመባቸው » ከቤታቸው ተቀብለው ባስተናገዱት የግፍ በደል ከፈላቸው ስለሱ መጥፎነት ሌላም ብዙ ነገር ሰምቸ ነበር በተፈጥሮውም ሆነ በዝንባሌው ለከስካሳና ወራዳ እንደሆነ ይቀራል ብዬ ነው የማምነው " "
“ በውነቱ እኔ ስለሱ ምንም ያህል አላውቅም " አሁን ባነሡት ሁኔታ የፈፀመውን ጥፋት ሊጠቅሱልኝ ይችላሉ ? አላት ሚስተር ካርላይል
እልም አድርጎ አጠፋቸው ነቅሏቸው ቀረ ... ሚስተር ካርላይል " ስለ ማጭበርበር፡ ስለ ተንኮል ምንም የማያውቁ የዋህ ገጠሬ ብጤዎች ነበሩ እሱ እንደነገራቸውና እነሱም እንዳመኑት ለአንድ ወር ያሀል የሚያስፈልገውን ዕቃ በወሰደበት የዕዳ ሠነድ ተጠሪ ሆነው እንዲፈርሙለት በግር በራስ ገብቶ ያግባባቸዋል እነዚሀ ሰዎች በነበራቸው ትንሽ ርስት እንዳቅማቸው የሚተዳዶሩ እንጂ ከዕለት ፍላጎት የሚተርፍ ገንዘብ አልነበራቸውም " የዚያ ሠነድ መከፈያ ጊዜው ሲደርስ
ድሮውንም ሲያውቅ ያደረገው ስለ ነበረ ዙሮ አላያቸውም። ስለዚህ ቤታቸውን በዕዳ አስረክበው ተሰደዱ " ሌላም ጥፋቶች ሞልተውታል ከዚህ ቤት እንደማላስባው ሰር ፒተር ሳይነግሩህ አልቀሩም " እኔ የጠላሁት የሳቸው ወራሽ በመሆኑ ቀንቸበት ሳይሆን ባመሎ ነው " እኔ ሰብአዊ ክብሬን ሳልጥል በጤናዬ ቁሜ እየሔድኩ እሱን
ከዚህ ቤት ምንም አላስጠጋውም ሰር ፒተር ሊቀበሉት ሊረዱት ዕዳውንም ከፍለው ከደረሰበት ችግር ሊያወጡት ይችላሉ እኔ ግን ከዚህ ቤት አላስገባውም ”
“ እርስዎ እንደማይቀበሉት ሰር ፒተር ነግረውኛል " ነገር ግን ከገባበት ጣጣ ለመላቀትና ነገሮችን ለማስተካከል ወደ ኢንግላንድ መጥቶ ከሰር ፒተር ጋር መገናኘቱ አስፈላጊ ነው "
“በስውር ካልሆነ በቀር' አሁን ባለው ሁኔታ እንዴት አድርጎ ወደዚህ ሊመጣ ይችላል ? አለችው "
“ እሱ በስውር ካልሆነ ሊመጣ አይችልም ስለዚህ ወደ ኢስት ሊን መጥቶ እንዲያርፍ አድርጌዋለሁ" መቸም እንደሚያውቁት ከሳቤላ ጋር የዝምድና ግንኙነት አላቸው " "
“ መልካሙን አድራጎትህን በክፋት እንዳይከፍልህ ተጠንቀቅ አለችው
ወይዘር ሌቪሰን ይህ የሱ የተለመደ ተግባሩ ነው !!
ሚስተር ካርይል ሣቀ « ምንም የክፋት ፍላጎት ቢኖረው ምን ጉዳት ሊያደርስብኝ ይችላል ? ደንበኞቼን አያባርርብኝ ልጆቼን አይመታብኝ ገንዘቤን እጠብቃለሁ ደሞ እኮ ከኛ ጋር የሚቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው"
የሰር ፒተር ባለቤትም እንደ መሣቅ ብላ ጨበጠችውና፡ “ምናልባት ያንተ ቤት ለለከስካሳው ዐመሉ ላይመቸው ይችላል ግን ተጠንቀቅ ትንሽ አጋጣሚ ካገኘ አንድ ጥፋት ሳይፌጽም እንደማይሔድ ዕወቅ።

#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
....ክንዱን ለመንካት እጄን ዘረጋሁ። “ክሪስ” እምባ እያነቀኝ በሹክሹክታ ጠራሁት
“ወንድ መሆንህ እንዲሰማህ ምን እንደሚያስፈልግህ የማውቅ ይመስለኛል።"
አልኩት።
“ኧረ? ምን ማድረግ ትችያለሽ?”
አሁን ወደ እኔ እየተመለከተ አይደለም:: በዚያ ፋንታ ኮርኒስ ላይ እያፈጠጠ ነው ለእሱ ታመምኩ ምን እንዳስከፋው አውቄያለሁ። ሀብቱን ወረስንም አልወረስንም ህልሙን የተወው እኔን መምሰል እንዲችል ብሎ ነው: እኔን
መምሰል ደግሞ ጎምዛዛ፣ መራራ፣ ሁሉን የሚጠላና የተደበቀ ምክንያታቸውን
የሚጠራጠር መሆን ማለት ነው።
ቀስ እያልኩ ፀጉሩን ነካካሁትና “የሚያስፈልግህ አንድ ነገር ነው ፀጉር
መቆረጥ። ፀጉርህ በጣም ረጅምና የሚያምር ነው፡ ወንድነት እንዲሰማህ አጭር ፀጉር ሊኖርህ ይገባል። አሁን ግን ፀጉርህ የኔን ፀጉር ነው የሚመስለው”
እና ማነው የአንቺ ፀጉር ያምራል ያለው? ምናልባት በአንድ ወቅት ከሬንጁ
በፊት የሚያምር ፀጉር ነበረሽ” አለኝ፡
“የእውነት?” ብዙ ጊዜ አይኖቹ ፀጉሬ ከማማር በላይ እንደሆነ ነግረውኛል።
hፊት ለፊቴ ያለውን ፀጉሬን ሊቆርጥ መቀስ ሲያነሳ እየተመለከተኝ የነበረበትን
መንገድ ነግሮኛል። በጣም ሲያመነታ ላየው ህመም የማይሰማውን ፀጉር
ሳይሆን ጣቶች የሚቆርጥ ነበር የሚመስለው ከዚያ አንድ ቀን ጣሪያው
ስር ያለው ክፍል ውስጥ ፀሀይ ላይ ተቀምጦ የተቆረጠውን ጸጉሬን በእጆቹ ይዞ ሲያሸተው፣ በጉንጮቹ ሲዳስሰውና ወደ ከንፈሮቹ ሲያስጠጋቸው
አይቼዋለሁ ከዚያ ደግሞ ትራሱ ስር ለማስቀመጥ ካርቶን ውስጥ ሲደብቀው
ተመልክቻለሁ፡
ማየቴን እንዳያውቅ ሳቄን መደበቅ ቀላል አልነበረም: “ኦ ክሪስቶፈር… በጣም ውድ ሰማያዊ አይኖች አሉህ፤ ከዚህ ቦታ ነፃ ስንሆንና ወደ አለም
ስንመለስ አንተን ለሚያፈቅሩ ሴቶች ሁሉ በጣም አዝንላቸዋለሁ። በተለይ ደግሞ ከመልከመልካም ባሏ ጋር የፍቅር ግንኙነት የሚፈልጉ
በሽተኞች ያሉት ዶክተር ባል ላላት ሚስትህ አዝናለሁ። እና እኔ ሚስትህ ብሆን ከጋብቻህ ውጪ አንድ የፍቅር ግንኙነት ቢኖርህ እገድልሀለሁ! በጣም ስለማፈቅርህ እቀናለሁ ምናልባት በሰላሳ አምስት አመትህ ከህክምና
እንድትወጣ አደርግሀለሁ” ያልኩትን ሁሉ ችላ ብሎ “አንድ ጊዜም ፀጉርሽ
ያምራል ብዬ ተናግሬ አላውቅም” አለ።
በቀስታ መላጨት የሚያስፈልጋቸው ፀጉሮች ያሉበትን ጉንጩን ዳሰስ
አደረግኩት፡
ከዚያ “ባለህበት ቁጭ በል! ታውቃለህ ለረጅም ጊዜ ፀጉርህን ቆርጬህ
አላውቅም… መቀስ ላምጣ” አልኩት፡ ግን የፀጉራችን ምንም መምሰል
የህይወት ዘይቤያችን ለመለወጥ አስፈላጊ ካልሆነ የክሪስንና የኮሪን ፀጉር
ለመቁረጥ ለምን እቸገራለሁ? ከፊት ያለው ፀጉሬ ብቻ በዚያች ከብረት
የተሰራች የምትመስል ክፉ አሮጊት መሸነፋችንን ለማሳየት ከመቆረጡ
በስተቀር፤ እዚህ ከመጣን እኔና ኬሪ ፀጉራችን ጫፍ ጫፉ እንኳን ተከርክሞ
አያውቅም።
መቀሱን ላመጣ ስሄድ የእኛ ፀጉር በጣም ሲያድግ አንዳቸውም አረንጓዴ
ተክሎቻችን አለማደጋቸው እንግዳ ነገር መሆኑን አሰብኩ።
ክሪስ ወለሉ ላይ ተቀመጠ ከኋላው ተንበረከክኩ ፀጉሩ ከትከሻው በታች
የወረደ ቢሆንም ብዙ እንዲቆረጥ አልፈለገም፡ “ቀስ እያልሽ ቁረጪ" ሲል
አዘዘኝ “በአንዴ ብዙ አታሳጥሪው ድንገት በአንድ ዝናባማ ከሰአት በኋላ
ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ወንድነት ቢሰማኝ አደገኛ ሊሆን ይችላል
ብሎ ቀለደና ፈገግ አለ። ከዚያ ድርድር ያሉ ነጫጭ ጥርሶቹን እያሳየ ሳቀ:
መምሰል የሚገባውን ያህል አሳምረዋለሁ።
ዙሪያውን እየዞርኩ ፀጉሩን ስቆርጥና ስከረክም እንዴት እንደምወደው እያሰብኩ ነበር፡ ያለማቋረጥ ወደኋላ ሄድ እያልኩ ፀጉሩ በትክክል መቆረጡን አረጋግጣለሁ ጭንቅላቱ የተጣመመ እንዲመስል አልፈለግኩም።
ፀጉር አስተካካዮች ሲያደርጉ እንዳየሁት፣ ፀጉሩን በማበጠሪያ ይዤ በጥንቃቄ ቆረጥኩት። ምን መምሰል እንዳለበት እንደምፈልግ አእምሮዬ ውስጥ አሉ
የሆነ የማደንቀውን ሰው
ስጨርስ ትከሻው ላይ የወደቁትን የተቆራረጡ ፀጉሮች አራገፍኩና ወደኋላ
ራቅ ብዬ በማየት ቆንጆ እንዳደረግኩት አረጋገጥኩ።
“ያው!” አልኩ በድል አድራጊነት ከባድ ጥበብ የሚመስለውን ስራ ባልተጠበቀ ጉብዝና በማጠናቀቄ ደስ ብሎኛል። “የተለየህ መልከመልካም ብቻ ሳይሆን በጣም ወንዳወንድ ሆነሀል! ሁልጊዜም ወንዳወንድ ነበርክ። አለማወቅህ
ያሳዝናል” አልኩት።
ብራማ ጀርባ ያለው የስሜ የመጀመሪያ ፊደል የተቀረፀበትን መስተዋት እጁ ላይ አስቀመጥኩለት፡ ይህ መስተዋት እናታችን ለመጨረሻ ልደቴ ከሰጠችኝ
ስጦታዎች አንዱ ነበር። ብሩሽ፣ ማበጠሪያና መስተዋት አያትየው ሶስቱ
ውድና ኩራት የሚያመጡ እቃዎች እንዳሉኝ እንዳታውቅ የሚቀመጡት
ተደብቀው ነው።
ክሪስ በመስተዋቱ ላይ ለረጅም ደቂቃዎች አፈጠጠ ለቅፅበት ደስ ያላለውና ያልወሰነ ሲመስለኝ ልቤ ደነገጠ፡ ከዚያ ቀስ በቀስ ደማቅ ፈገግታ ፊቱን አበራው።
አምላኬ! ልዑል አስመሰልሽኝ! በመጀመሪያ አልወደድኩትም ነበር። አሁን ግን ሳየው የፀጉሬን ሁኔታ ስለቀየርሽው ፊቴን አሳምሮታል። አመሰግናለሁ
ካተሪን ፀጉር መቁረጥ ላይ እንደዚህ አይነት ችሎታ እንዳለሽ አላውቅም ነበር" አለኝ።
አንተ የማታውቃቸው ብዙ ችሎታዎች አሉኝ፡”
"እኔም መጠርጠር ጀምሬያለሁ”
“እና ልዑሉ መልከመልካም፣ ወንዳወንድና ባለወርቃማ ፀጉሩን ወንድሜን በመምሰሉ እድለኛ ነው” ስል ቀለድኩ። የጥበብ ስራዬን አለማድነቅ
አልቻልኩም። ኦ አምላኬ! አንድ ቀን ልብ የሚሰብር ቆንጆ ነው የሚሆነው።
አሁንም መስተዋቱን እንደያዘ ነበር ከዚያ ቀስ ብሎ ወደጎን አስቀመጠውና
ምን ሊያደርግ እንደሆነ ከማወቄ በፊት እንደ ድመት እመር ብሎ ተነሳ ታገለኝ፤ ወደ ወለሉ እያስጎነበሰኝ መቀሱን ያዘ! ከእጄ ላይ መነጨቀኝና ፀጉሬን በእጁ ያዘ አሁን የኔ ቆንጆ እስቲ እኔም እንዳንቺ ማድረግ እችል እንደሆነ እንመልከት:"
በፍርሀት ገፈተርኩት
ስገፈትረው በጀርባው ወደቀ ከዚያ ተነሳ። ማንም የጸጉሬን ጫፉን እንኳን
አይነካም! ምናልባት አሁን በጣም ስስ ሆኖ ይሆናል። ግን ያለኝ ፀጉር ይኸው
ነው! አሁንም ከብዙ ሴቶች ፀጉር በተሻለ የሚያምር ነው እንዳይዘኝ ሮጥኩ።
ከመማሪያው ክፍል ወጥቼ ሻንጣዎቹን እየዘለልኩ በትልልቆቹ ጠረጴዛዎች
ስር እየሾለኩ ሮጥኩ። እሱም እያሯሯጠኝ ነው፡
ምንም ያህል በፍጥነት ብሮጥና በፍጥነት ብሽሎከለክም ላመልጠው
አልቻልኩም፡ በትከሻዬ በኩል ዞር ብዬ ስመለከተው ፊቱን እንኳን መለየት
አልቻልኩም ያ ደግሞ የበለጠ አስፈራኝ፡ ከጀርባዬ የተበተነውን ረጅሙን
8ጉሬን ለመያዝ ጥረት አደረገ። ፀጉሬን ቆርጦ ለመጣል የወሰነ ይመስላል
አሁን ጠልቶኛል ማለት ነው? ፀጉሬን ለማትረፍ አንድ ቀን ሙሉ በትጋት እንዳልለፋ ሁሉ… አሁን ደስ ስላለው ብቻ ሊቆርጠው ነው?
ተመልሼ ወደ መማሪያው ክፍል ሮጥኩ። ከዚያ ውስጥ ገብቼ በሩን እቆልፍና ወደ ራሱ ተመልሶ ሲረጋጋና ስህተት መሆኑ ሲገባው ተመልሼ እወጣለሁ::
ምናልባት ያሰብኩት ገብቶት ሳይሆን አይቀርም ረጃጅም ቅልጥሞቹ ላይ ፍጥነት ጨመረና ደርሶብኝ ረጅሙን ፀጉሬን ሲይዘውና ወደፊት ስወድቅ ጮህኩ!
እኔ ብቻ ሳልሆን እሱም ወደቀ ቀጥታ ላዬ ላይ! ጎኔ ላይ ድንገተኛ ህመም
ሲሰማኝ እንደገና በፍርሀት ሳይሆን በድንጋጤ ጮህኩ።
እላዬ ላይ ነው። በእጆቼ መሬቱን ተደግፎ ፊቴን አተኩሮ ይመለከታል። ፊቱ
ነጭ ሆኖ የፈራ ይመስላል። “ተጎዳሽ? ወይኔ አምላኬ! ካቲ ደህና ነሽ?” አለኝ።

👍40❤1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ
ዳያና መልስ የመስጠት ያህል ከንፈሩን መጠጠችው፡
ከዚያማ ምን ይወራል! ቀለል እያላት ሲመጣ መላ ሰውነቷ ዘና አለ፡፡
እየሳመችው ወንበሩን ተደገፈች፡፡ እየሳመችው ጡቷ ደረቱን ሲታከክ
ተሰማት፡ እንደገና ገላ ለገላ መተሻሸት መቻሏ ደስታ ፈጥሮላታል፡ በከንፈሩ
ጫፍ ከንፈሯን ሲዳስስ ስሜት ውስጥ ገብታ አፏን ከፍታ ተቀበለችው፡፡ ጫን
ጫን መተንፈስ ጀመረች፡ በእርግጥ የሚያደርጉት ነገር መረን የለቀቀ
መሆኑ ታውቋታል፡ ዓይኗን ስትከፍት መርቪንን አየችው:
በመጀመሪያ እያለፈ ስለነበር አላስተዋላትም ነበር፡ ድንገት ወዳለችበት
ፊቱን ዞር ሲያደርግ ያየው ነገር ከእርምጃው ገታው፡ እሷም ስታየው ፊቷ
በድንጋጤ አመድ ለበሰ፡፡
ዳያና ባሏን በሚገባ ስለምታውቀው ምን ሊሰማው እንደሚችል
አልጠፋትም ምንም እንኳ ከማርክ ጋር በፍቅር መክነፏን ሰዎች ቢነግሩትም እውነትነቱን ለመቀበል ከብዶታል፡፡ ከወንድ ጋር ስትሳሳም በዓይኑ በብረቱ ሲያይ በድንጋጤ ክው አለ፡፡
መርቪን በንዴት ግምባሩን ከሰከሰ፡፡ ዳያና ባሏ በቀጥታ ጠብ ይጀምራል
ብላ ፈርታ ነበር፡፡ ሆኖም ቃል ሳይተነፍስ ዞረና መንገዱን ቀጠለ፡፡
ማርክ ‹‹ምንድነው ነገሩ?›› ሲል ጠየቃት፡፡ ዳያናን ይዞ እየጨመጨመ
ስለነበር መርቪንን አላየውም ነበር፡፡
መንገር ስለፈራች ‹‹ሰው ሊያየን ይችላል ይበቃናል›› አለችው:
ማርክም ከዳያና መላቀቁን ቢጠላም መሳሙን አቆመ::
ዳያና የመርቪን አድራጎት አናደዳት፡፡ መርቪን የዓለምን ግማሽ ርቀት እግር በእግር ተከትሏት መምጣቱ ሳያንስ ከማርክ ጋር በተላፋች ቁጥር ሊያፈጥባት መብት የለውም፡፡ ትዳር ባርነት አይደለም፡፡ ጥላው መሄዷን
መቀበል አለበት፡ ማርክም በንዴት ሲጋራ ለኮሰ፡፡ ዳያና ባሏን ፊት ለፊ ልትገጥመው ፈልጋለች፡ በቃ አልፈልግህም ልትለው ተዘጋጅታለች
ተነሳችና ‹‹መዝናኛው ክፍል ምን እንዳለ ለማየት ልሄድ ነው›› አለች
‹‹አንተ እዚህ ቁጭ ብለህ ሲጋራህን ማግ›› አለችውና ከማርክ መልስ ሳትጠብቅ እብስ አለች፡
መርቪን የት እንደተቀመጠ ባታውቅም ፍለጋዋን ቀጠለች፡፡ አሁን የአይሮፕላኑ መናወጥ የቀነሰ በመሆኑ ምንም ነገር ሳትይዝ መራመድ ችላለች፡፡ በመዝናኛ ክፍሉ ውስጥ ሰዎች ካርታ ለመጫወት ጉድ ጉድ እያሉ ሲሆን ክፍሉ
በሲጋራ ታፍኗል፡፡ ፊታቸው የመጠጥ ጠርሙሶች
ተኮልኩለዋል፡፡ ሌላ ክፍል ዘው ስትል የኦክሰንፎርድን ቤተሰብ አገኘች፡:ሎርድ ኦክሰንፎርድ ሳይንቲስቱን ካርል ሃርትማንን ከፍ ዝቅ አድርገው ሲሳደቡ መርቪን ላቭሴይ ሰምቶ እሱ እንደተነካ ተቆርቁሮ ሎርዱን
ለመደብደብ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ተሳፋሪው አይቶታል፡ መርቪን አንዳንዴ እውነት አለው፡፡ እሷም ይህን አትክድም፡፡
ከዚያም ወደ ኩሽና ሄደች፡፡ እዚያም ድብልብሉ ኒኪ ሰሃን ሲያጥብ አገኘችው::
ፎቁን ወጣችና ፓይለቶቹ ክፍል ሄደች፡፡ ሁሉም በስራ የተጠመዱ ስለሆነ ወዲያው አላይዋትም፡፡ በኋላ አንዱ አያትና ‹‹ሌላ ጊዜ እያዞርን ሁሉንም ቦታ እናሳይሻለን፡፡ ነገር ግን አሁን እውጭ ያለው የአየር ሁኔታ
መጥፎ ስለሆነ ቦታሽ ሄደሽ እንድትቀመጪ ቀበቶሽን እንድታስሪ እንጠይቃለን›› አላት፡፡
ደረጃውን ወርዳ ስትጨርስ ከማርክ ጋር ፊት ለፊት ግጥም አለች፡ሁኔታው ቢያስደነግጣትም ‹‹እዚህ ምን ልታደርግ መጣህ?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹ራስሽ እዚህ ምን ልታደርጊ መጣሽ?›› አላት፡፡ ካነጋገሩ የተናደደ መሆኑ ያስታውቃል
ዞር ዞር እያልኩ እያየሁ ነው፡፡››
መርቪንን ነው የምትፈልጊው?›› አላት፡
‹‹ማርክ ለምንድነው እንደዚህ የምትሆነው?›› አለች ዳያና፡፡
‹‹ምክንያቱም ባልሽን ለማየት ሹክክ ብለሽ በመሄድሽ››
ኒክ ድንገት መጣና ጭቅጭቃቸውን አቋረጣቸው ወደ
መቀመጫችሁ ተመለሱ፡፡ አሁን በረራው ጥሩ ቢመስልም ትንሽ ቆይቶ
አይሮፕላኑ መወዛወዙ አይቀርም›› አላቸው፡፡
ማርክና ዳያና ወደ ቦታቸው ተመለሱ፡፡ ዳያና ያደረገችው የጅል ስራ መሆኑን ተገንዝባለች፡፡ መርቪንን ስትከታተል መርቪን ደግሞ እሷን ተከታትሎ የምትሰራውን አየባት፡፡
ቦታቸው ቁጭ ብለው ጭቅጭቃቸውን ሊቀጥሉ ሲሉ ኦሊስ ፊልድና
ፍራንክ ጎርደን መጡ፡፡ ጎርደን ነጠላ ጫማውን አወለቀና ላይኛው አልጋ ላይ በመሰላል ወጣ፡፡
ከዚያም ፊልድ ከፒጃማው ውስጥ እጀ ሙቅ ሲያወጣ ዳያና አይታ ደነገጠች፡ ፊልድ ፍራንክ ጎርደንን በጆሮው አንድ ነገር ሲለው ፍራንክ ተቃውሞውን ቢገልጽም ፊልድ ፈርጠም ብሎ የታዘዘውን እንዲፈጽም ሲነግረው አንድ እጁን ሰጠ፡፡ ፊልድ የፍራንክን እጅ በእጀ ሙቁ ከአልጋው ብረት ጋር አሰረና መጋረጃውን ፊቱ ላይ ጋረደበት፡
‹‹ፍራንክ እስረኛ መሆኑ እውነት ሆነ›› አለ ማርክ፡፡
‹‹እኔ ግን ነፍሰ ገዳይ ነው የተባለውን ማመን አቅቶኛል›› አለች ዳያና፡፡
‹‹እኔ ደግሞ ሳይሆን አይቀርም ብዬ ነው የምገምተው›› አለ ማርክ፡
‹‹ሃምሳ ዶላር ከፍለን በመርከብ ከምድረ ምስኪን ጋር ብንሄድ ይሻለን ነበር››
‹‹ፊልድ እጀ ሙቁን ቢፈታለት ጥሩ ነበር፡፡ ልጁ ካልጋው ጋር ተጠፍሮ
እንዴት ሊተኛ እንደሚችል አይገባኝም፡፡ መገላበጥ እንኳን አይችልም፡፡››
‹‹አንቺ ሩህሩህ ነሽ›› አለ ማርክ እቅፉ ውስጥ እየጣላት፡ ‹‹ሰውየው
እኮ ሴቶችን አስገድዶ የሚደፍር ሰው ነው፡፡ አንቺ ደግሞ እንዴት ሆኖ
ሊተኛ ነው ብለሽ ታዝኛለሽ፡፡››
ዳያና ራሷን ማርክ ትከሻ ላይ አስደገፈች፡ ማርክ ጸጉሯን ይደባብሳል፡፡
ከጥቂት ጊዜ በፊት አናዳው ኤሌክትሪክ ሊጨብጥ ምንም አልቀረውም ነበር፡፡
አሁን ግን ንዴቱ በርዷል፡
ማርክዬ አለች ዳያና ይሄ አልጋ ለሁለት ሰው ይበቃል?›› ስትል
ጠየቀች፡፡
‹‹ፈራሽ የኔ ማር?››
‹‹አይ አልፈራሁም፡፡››
በመጀመሪያ ያለችው ግር ብሎት ነበር፡፡ በኋላ ሃሳቧ ገባውና ፈገግ አለ፡፡ ‹‹ሁለት ሰው ሊያስተኛ ይችላል፡፡ ነገር ግን ጎን ለጎን አይደለም፡፡አንዳችን አንዳችን ላይ መውጣት ይኖርብናል፡፡ አንቺ እላዬ ላይ መውጣት ትፈልጊያለሽ?››
‹‹አዎ እወጣለሁ›› አለች ዳያና እየሳቀች።
‹‹እስቲ ላስብበት›› አላት ኮስተር ብሎ በቀልድ ‹‹ስንት ነው ኪሎሽ?››
‹‹ብዙም አልከብድህም››
‹‹የቀን ልብሳችንን እንለውጥ›› አላት፡፡
ዳያና ባርኔጣዋን አውልቃ ወምበሩ ላይ አስቀመጠች፡፡ ማርክ
የሁለቱንም ቦርሳ ከወምበሩ ስር አወጣ፡፡
ዳያና ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድ እንደምትፈልግ ስትነግረው ‹‹ቶሎ በይ›› አለና ደረቱ ላይ ለጥፎ ሳማት፡፡ እቅፍቅፍ ሲሉ የብልቱ መቆም
ተሰማትና አህ!› አለች የእሷም ስሜት ተነሳስቶ፡፡ ስትመለስ እሱም ሊሄድ
ተነሳ፡፡ ‹‹ከመታጠቢያ ቤት ስትመለስ እንደቆመ መምጣት አለብህ››
አለችው፡፡
‹‹አይዞሽ አትስጊ፤ እንደገና እንዴት እንደምታቆሚው አሳይሻለሁ›› አላት፡፡
‹‹እስክትመለስ በቅንዝር መሞቴ ነው›› ስትል በጆሮው አንሾካሾከች፡
ማርክ ቦርሳውን አንጠልጥሎ ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ሄደ፡ መርቪን ከተቃራኒ አቅጣጫ እየመጣ ነው፡፡ ሲተላለፉ ልክ አጥር ላጥር እንደሚተያዩ ድመቶች ቢፋጠጡም ቃል አልተለዋወጡም።
ዳያና መርቫን የለበሰውን ቢጃማ አይታ ‹‹ምንድነው እናትህ የለበስከው?›› ስትል ሳቀችበት፡፡
‹‹ሳቂ እስኪበቃሽ›› አለ፡፡ ‹‹ፎየንስ ላይ ላገኝ የቻልኩት ፒጃማ ይሄ ብቻ ነው›› አላት ‹‹የዚህ አገር ሰዎች ከሃር የተሰራ ፒጃማ መኖሩን እንኳን ሰምተው አያውቁም፡፡ ስጠይቃቸው እብድ ነው ሳይሉ አይቀርም››

👍12🥰1
#ኢቫንጋዲ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#በፍቅረማርቆስ_ደስታ
ኮንችትና ሶራ የሰጎን ላባ የተሰካበትን የራስ ጌጥ(ጶሮ) እንደ አቦ ሸማኔ
አይን አሸጋግሮ እየተንተገተገ የሚመለከተውን አይኑን የተተለተለ ሳንቃ ደረቱን እየተመለከቱ ከንፈሩን አሞጥሙጦ የሚያሽለከልከው ትንፋሹ ከፍ ዝቅ በሚሉት ጣቶቹ እያንኳለለ የሚያጣው ስሜተ ሰላቢ ዜማውን ሳይንቀሳሱ ሲያዳምጡ ወይሳ ተጨዋቾቹ ድንገት ዜማውን ቀጥ አደረገና መሳርያውን አንስቶ ሲያቀባብል ሶራና ኮንቺት
ድንግጥ ብለው ሲመለከቱ ድው አድርጎ ሲተኩስ አመዳቸው ቡን ብሎ ነፌሴ አውጪኝ መሬት ላይ ሲንበለበሉ እንደገና ተኮሰ።
ከዚያ ለጥቂጥ ሰአታት ከመሬቷ ጋር ተላትመው ጠበቁና ቀና ብለው ሲመለከቱ ሰውየው ኦሞ ወንዝ ዳር ሄዶ ተረጋግቶ ወንዝ ዳር ሄዶ ቆሟል ኮንቺት እየተሳበች ወደ ሶራ ተጠግታ
"ለምን ተኮሰ? አለች ሶራን።
"አልገባኝም"
"አይቶን ይሆን?"
አይመስለኝም ቢያየን ወይንም ድምፅ ሰምቶረ ቢሆን ኖሮ በሁኔታው ማወቅ እንችል ነበር።
"እሱስ ልክ ነህ ቢገርመኝ እኮ ነው ተረጋግቶ መቆሙም ለጠየቅሁት ጥያቄ ፍንጭ ሰጪ አይደለም ስትለው ከኦሞ ወንዝ ማዶ ድምፅ ተሰማ ሰባቶ ጎረምሶች ናቸው። ወደ ወንዙ ሲጠጉ
"ፃሊ!” አላቸው በካሮኛ ሰላም ናችሁ ለማለት:
'ፃሊና..." አሉትና አምስቱ ወንዙ ዳር እንደቆሙ ፤ ሁለቱ ዳር ላይ የቆመች ቀጠን ብላ ረዘም ያለች የእንጨት ታንኳ ላይ
ወጡና በረጅም ዘንግ ውሃውን ቁልቁል ሲገፉት ታንኳዋ እንደ ውሃ
እናት ውሃውን ወደ ጎን እየሰነጠቀች መጣች::
ለካ የተኮሰው እነሱን ለመጥራት ነው:: ጥሪ በተኩስ አይገርምም!” ስትል ሶራ በአድናቆት ራሱን ወዘወዘ።
“እነሱ ግን እነማን ናቸው?"
"አላውቅም ኮንችት ብናነጋግራቸው ይሻላል?" ሲላት ወዲያው ከተደበቁበት ወጥተው ወደ ሰውዬው ሲጓዙ ፊቱን ዞሮ
የቆመው ሰው የሰው ዳና ሲሰማ ከመቅፅበት መሳሪያውን ከትከሻው
አውርዶ፡-
“ከጠን ማሲዲ" ብሎ መሣሪያውን አቀባብሉ ደገነባቸው።
“ኖት አሱስቴ" አለች ኮንችት በስፓኒሽ እጅዋን እያወዛወዘች ተረጋጋ ለማለት:
ባለመሣሪያው ትኩር ብሎ ሲያያቸው ቆየና “ነጋያ! አለ
ከተቀመጠበት ተነስቶ መሳሪያውን ወደ ትከሻው እየመለሰ: ሶራ ለሰላምታ አፀፋውን መለሰ። “...ሐመር አፎ ዴሲቲኒ" አለው ባለመሣሪያው ሐመርኛ ትችላለህ ለማለት።
ሶራ ፈገግ ብሎ “ሊካ ሊካ ቂንሲዲ...” (ትንሽ ትንሽ
እችላለሁ) አለው። ባለመሳሪያው ፈገግ አለ: ያኔ ነብርነቱ ተለውጦ
እንደ ድንቡሽዬ ህፃን ፈገግታው የሚማርክ ሆነ
ባለመሳሪያውና ኮንችት ከሁለቱ የታንኳዋ ቀዛፊዎች ጋር ተሻግረው ሲጠብቁ ሶራ ጀልባዋን ይዞ ሄደና በጀርባቸው አዝለው
ጀልባዋን ከአምስቱ ጎረምሶች ሁለቱ እየተሳሳቁ ተሸክመው ጫካው
ውስጥ ገቡና በመስመር ሆነው በትላልቅ የግራር የኮሶ... ዛፍ ውስጥ ለውስጥ ትንሽ እንደተጓዙ ኮንችትና ሶራ ዛፍ ላይ እንደ ጦጣ የሚንጨዋለሉ ልጆች አዩ: ቆይቶ ደግሞ በቋንቋቸው ቶሎ ቶሎ
የሚናገሩ ልጃቸውን በቆዳ ብብታቸው ስር ያዘሉ እናቶችና ሽምገል
ያሉ ወንዶችን አዩ።
ጨቅላ ህፃናት ዛፍ ላይ በቆዳ ተንጠልጥለው አንዳንዶቹ ተኝተው እየተቁለጨለጩ ሲወዛወዙ እያዩ እንደ ሄዱ ከርቀት ላይ
የወፍ ጎጆ የሚመስል የኤሊ ቅርፅ ያለው ጎጆ ቤት ተመለከቱ።
ኮንችትን ሲያዩ ህፃናት ወላጆቻቸው ጉያ እየገቡ ወደ መንደራቸው እየሮጡ አለቀሱ: ለኩዩጉ ህፃናት አስፈሪው አውሬ ቀላ ያለ ልብስ ለባሽ ሰው ነው። ከፍ ያሉት ግን የመጣው ይምጣ ብለው በቋንቋቸው ሰላም ቢሏትም ፍርሃታቸው ግን ያስታውቃል: ለጊዜው
ሰላምታቸውን ልብ ብላ አልተከታተለችም ነበር ድንገት አንድ ሽማግሌ፡-
“አሹቃ” ሲሏት አያቷ የነገራት ሰላምታ ትዝ አላት:
ኮንችት አያቷ የሚጠቀምባትን መቀመጫ የመሰለች ሁሉም
ሽማግሌዎችና ወንዶች ይዘው አየች:: ሶራን ዘወር አለችና ምን የሚባሉት ማህበረሰቦች ናቸው?" አለችው ማፕ ላይ ያየችውን ስም ለማስታወስ እየሞከረች:: ሶራ መጀመሪያ ያዩትን ባለ ዋሽንት ጠየቀው።
ሙጉጅዎች ናቸው። እነሱ ግን ራሳቸውን ኩዩጉ ነው
የሚሉት አለው ነገራት ሶራ ለኮንችት። ማፕ ላይ መጉጅም ሆነ ኩዩጉ የሚል እንዳላየች እርግጠኛ ነች: ለማረጋገጥ ግን ወዲያው
ማፕዋን ዘርግታ አየች፤ ሁሉም እሷ ላይ አፈጠጡባት። ማፑ ላይ
የሉም። ካርታው ላይ አየች የሉም፤ ይበልጥ ደነቃት።
ኦኗኗራቸውም ልዩ ነው ፤ የጫካና የወንዝ ዳር ሰዎች: ከመንደሩ እንደደረሱ ሰዉ በአድናቆት ቆሞ አያቸው: ህፃናት ራቅ ብለው ሽሽተው ያያሉ:: አንዱ 'መጡላችሁ' ሲል ሌሎች ህፃናት ደግሞ
እየተሯሯጡ በመላቀስ ይጯጯሃሉ…..
ኮንችት ከጀርባዋ ያዘለችውን ጓዟን አውርዳ ተለቅ ተለቅ ያሉ የአያቷን ፎቶ አወጣች: የዘጠኝ ሰዓት ፀሐይ አሁንም ማቃጠሏ
እንብዛም አልቀነሰም:
ፎቶውን የያዘውን እጅዋን ወደ ህዝቡ ዘረጋችው። ፈሯት፤በምልክት እንኩ' አለቻቸው: ትክ ብለው እያዩ ዝም አሏት ከዚያ ባለዋሽንቱ ውሰዱ' አላቸው በሐመርኛ።
ሶራ ደስ አለው የራሳቸውን የሆነውን ቋንቋ ሲናገሩ
አንድም ቃል ሊገባው አልቻለም ነበር ሐመርኛ ከቻሉ ግን እሱም
ሊያናግራቸው ይችላል። ኩዩጉዎች ግን ሐመርኛን ብቻ አይደለም የሚችሉት። ሙርሲኛ ኒያንጋቶምኛም ይችላሉ።ስለዚህ ሶራ
በሐመርኛ፦
“ውሰዱና እዩ ችግር የለም” አላቸው። አሁንም ዝም ብለው ኮንችትን ሲመለከቷት ቆዩና አንዱ
ሽማግሌ ሌላውን በጆሮው አናገረው ከዚያ ብድግ ብሎ መጣና ተቀበላት።
ፎቶውን ዘቅዝቆ ስለያዘው ኮንችት አስተካክላ ሰጠችው ሽማግሌው ቀረብ እራቅ አድርጎ አየውና በቋንቋው የሆነ ነገር
ተናግሮ ወደ ሀዝቡ ሲጠጋ ለማየት ህዝቡ እንደ ንብ ዙሪያውን ከበበውና ሁካታ ሆነ: ማንም ሌላውን አያዳምጥም።
ከዚያ ሁሉም እነ ኮንችትን ጥለው እንደ ድንጉላ እምም.. እያሉ ወደ አንድ አቅጣጫ ተሯሯጡ: ኮንችትና ሶራ እርስ በርስ
ተያዩ ህዝቡ የሄደበትን ምክንያት ግን ከመካካላቸው ሊመልስ የቻለ አልነበረም።
አንድ ጎጆ ቤት ሲደርሱ ሁሉም ቆሙ። ከውስጥ የሆኑ ሽማግሌ አንጀታቸው ካጥንታቸው ጋር የተጣበቀ አጎንብሰው ወጡ ህዝቡ አሁንም ክብብ አደረጓቸው።
ከዚያ እንደገና ሁካታ ሆነና ጎረምሶች እየተሯሯጡ ርቀው ሄዱ። ፎቶዎችም በልጥ ታስረው ሽማግሌው ከወጡበት ጎጆ ፊት
ለፊት ተንጠለጠሉና ሴቶች ሰማይ ሰማይ እያዩ እልልታውን አቀለጡት ወንዶች እየዘለሉ ጭፈራ ጀመሩ።
ኮንችትና ሶራ እንደገና ተያዩ። ምን እየተሰራ እንደሆነ ማወቅ ተሳናቸው: ባለ ዋሽንቱን ጠየቁት፤ መልስ አጡ። ከዚያ
አራት አምስት መሳሪያ የያዙ ሽቅብ ተኮሱ።
ኮንችትና ሶራ ደነገጡ፡ “ምን እየሰሩ ነው ሶራ?" አለች
የሶራን ትክሻ እየወዘወዘች
በፍርሃት: ሶራ ትከሻው ከፍ ዝቅ አድርጎ አላውቅም አላት በምልክት። ሰው ከየጫካው ተሰባሰበ !
ጥሩንባው እየተነፋ እልል መባል ጀመረ።
ጫካ የሄዱት ጎረምሶች በሾርቃ የሆነ ነገር ይዘው
እየተሯሯጡ መጡ የደከማቸው አይመስሉም የግንባራቸው ደም
ስር ግን ውሃ እንደሽረሸረው የዋርካ ስር አበጥ አበጥ ብሎ በየአቅጣጫው ተጋድሟል። እንደ ተመለሱ ከህዝቡ መሃል ገቡ
ከሌላ ጎጆ ደግሞ ማር የያዘ ትልቅ ቅልና ውሃ ሌሎች ጎረምሶች አመጡ። ውሃውና ማሩ ተቀላቀለና በእንጨት ተማሰለ።
ከዚያ ጥሩንባው እየተነፋ እልል እየተባለ እየተጨፈረ... ሁሉም የሉካዬን ስም እየጠሩ ሰማይ እያዩ ቆዩና ከሲታ ሽማግሌውን አስቀድመው ሶራ ኮንችትና ባለወይሳው ወደ ቆሙት እያሸበሸቡ
እየዘለሉ ጡሩንባው እየተነፋ መጡ።

👍18😢2👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹አይዞሽ..አይዞሽ››
‹‹ያስፈራል..››
‹‹እኔ ደግፍሻለሁ… ቀስ ብለሽ ዋኚ..››እጆቹ ከስር ሲደግፈኝ በማወቅና ባለማወቅ መካከል ሆኖ አንዴ ጡቶቼን ሲጨፈልቃት..አንዴ ወደጭኑ አካባቢ ሲንሸራተት..እሷም ደግሞ ልክ እንደፕሮፌሽናል ተዋናይ ፍጽም በማስመሰል … አንዴ የፈራች መስላ አንገቱ ላይ በመጠምጠም ከሰውነቱ ስትጣበቅ..አንዴ ከእጁ ሾልካ ውሀ ውስጥ እራሷን በመድፈቅ ስትንደፋደፍ…..በመጋል እና በመቃተት መካከል ሆና ግማሽ ሰዓት ያህል ካለማመዳት በኃላ
‹‹ለዛሬ ይብቃሽ ልወጣ ነው ››አለት…
ቅፅበታዊ ውሳኔው አበሳጫት
‹‹እንዴ ምነው …?በደንብ ሳልችል…?››ኮስተር ብላ..ኮስተር አባባሎን ለተመለከተ ገንዘብ ከፍላው የሚያስተምራትን ሰው የምታወራ ነው የሚመስለው፡፡
መቼም የመልመድ ተስፋ የላትም የሚል በሚመስል ስሜት ‹‹አረ ባክሽ..!!እኛ በስንት አመትና ልፋት የቻልነውን ዋና አንቺ በአንድ ቀን ..ለዛውም በግማሽ ሰዓት መልመድ ትልጊያለሽ……?.››አላት..
የሚያወሩት በጣም ጥልቅ ያልሆነ የገንዳው ጠርዝ አካባቢ ቆመው ነው..ውሀው እሷን ጡቷ አካባቢ እሱን ደግሞ እንብርቱን አካባቢ ድረስ ሸፍኖቸዋል…ከፊል እርቃናቸውን እየታያዩ ፊት ለፊት ተፋጠው ነው የምያወሩት..እሷ ለወሲብ እየጎመዣች..እሱ በትምክት እየጎረረባት
‹‹አረ በናትህ ዋናን እኮ የተለየ ጥበብ አደረከው..›› አለችው..እወነቷን ነበር ያለችውት፡፡
እሷ የደሎ መና ልጅ ነኝ..ዋና እየተስገመገመ በሚጋልበው የያዶት ወንዝ በ3 አመቷ በቀልድ ነው የለመደችው…በዕቃ ዕቃ ጫወታ…ያዶት መዋኘት ለለመደ ሰው ደግሞ እዚህ የረጋ ወሃ ላይ መዋኘት ቀልድ ነው፡፡
‹‹እንግዲህ ጥበብ ካልሆነ ያው ሜዳው…አሳይና››ብሎ አበሳጫት…የጀመረችውን የማጥመጃ ዘዴ በደቂቃ ውስጥ እረስታ ያልሸነፍ ባይነት እና የበላይነት መንፈሷ ከውስጧ ተንቀልቅሎ ገነፈለባት…በቆመችበት ቦታ ድንገት ሰመጠችና ውስጥ ለውስጥ መሹለክለክ ጀመረች … ካለችበት ጫፍ ወደሌላ ጫፍ ተወነጨፈችና በሰካንድ በዛኛው ጫፍ ስትወጣ እሱም እሷን ፍለጋ ሰምጦ ኖሮ በድንጋጤ ከመሀከል አካባቢ ከውሀ ውስጥ ሲወጣ ተመለከተችው..አይኑን ከወዲህ ወዲያ አማተረና እሱ ካለበት በብዙ እርቀት ተስፈንጥራ ከውሀ ውስጥ በሰላም እና በፈገግታ ታጅባ ብቅ ጥልቅ እያለች ሲያያት በመገረም እና በንዴት አፈጠጠባት… በቄንጥና ቲያትራዊ በሆነ ትዕይንት ከላይ እየተንሳፈፈች ፤ እየዋኛችና እየተገለባበጠች ስሩ ደረሰች፡፡
‹‹እያሾፍሽብኝ ነበር..…?እኔ ደግሞ የሰመጥሽ መስሎኝ መደንገጤ››
‹‹ብሰምጥስ ምን ያስደነግጥሀል…?››
‹‹እንዴ ሰው አይደለሽ …? ለምን አልደነግጥ…?››
‹‹ስለተጨነክልኝ አመሰግናለሁ››
‹‹አረ ምስጋናሽን ቀቅለሽ ብይው..በአንቺ ቤት አራዳ ሆነሽ በዘዴ መጥበስሽ ነው?››
‹‹ምን ለማለት ፈልገህ ነው…?››ንግግራቸውን በቅርባቸው የነበሩ ሁለት ሰዎች የሚዋኙ መስለው ግን ጆሮቸውን ወደ እነሱ ቀስረው እያዳመጡ ነው..ደንታም አልሰጣት፡፡
‹‹ሰምተሻል ባክሽ….እኔ ለእንደአንቺ አየነት ጩሉሌ ከምሸነፍ አራሴን ባጠፋ ይሻለኛል…..
"እኔ ደግሞ በጥቂት ቀን አንተን መጥበስ ካልቻልኩ እራሴን አጠፋለሁ"
"አፍጥጦ አያትና ምንም ሳይናገር ጥሏት ሄደ
እሷም ከገንዳው ወጥታ ወደመኪናዋ ተንደረደረች...
ከፍታ ገባችና በውሀ የራሰውን የዋና ልብሷን አውልቃ ሌላ ልብሷን በመልበስ ከመኪናው ወጣች..ኮፈኑን ተደግፋ ንስሯ ፊት ለፊት ቆማ ማሰብ ጀመረች …. በአካባቢው የሚያልፍ ሰዎች ከንስር ጋር ባልተለመደ ሁኔታ ፊት ለፊት ተፋጣ ሲያዩት በመገረም እየተገላመጡ ሲያልፍ አስተውላለች፡፡
‹‹የሆነውን አይተሀል አይደል…?በቃ ፈልገዋለሁ››የምታወራው ለንስሯ ነው
(ይቅርብሽ የሚል ቃል ወደ አዕምሮዋ ላከላት)
‹‹ አታበሳጨኝ..በቃ ፈለኩት ማለት ፈለኩት ነው …አሁን የሆነ ነገር አድርግልኝ …ሆቴሉ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ቢራ እየተጎነጨው እጠብቅሀለሁ…››
ተነስቶ በረረ……..
እሷም እንዳለችው ወደሆቴሉ በረንዳ በመሄድ ወንበር ይዛ ተቀመጠችና ቢራ አዘዘች….እንግዲህ ያሰበችው እስኪሳካ ሌላነገር ማሰብም አልቻለችም…ቀልቧን ሁሉ ጥቁሩ ልጅ ላይ እንደተጣበቀ ነው…….ጭኗ መካከል ይበላት የነበረው አሁንም እየበላት ነው…. ከመብላቱም አልፎ እያቁነጠነጣት ነው… አሁን እንደዚህ የሚያደርጋት የወሲብ ጥማት ነው…እንጂማ በቅጽበታዊ የፍቅር ፍላፃ ተመታ አይመስልም… ‹‹እንደዛ አይነት ደካማነትማ አይነካካኝም…መጀመሪያውኑስ ፍቅር ምንድነው …...?የፍቅር መነሻውም መድረሻውም አይስማማኝም፡፡ማለቴ በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል ያለው የፍቅር ስሜት መነሻው የተለያየ ቢሆንም መዳረሻው ለምን ተቀራራቢ ወይም ተመሳሳይ ሆነ….ሁል ጊዜ ለምን ፍቅር በወሲብ ልጥ ይታሰራል፡፡ልጡስ ለምን በጋብቻ ሰንሰለት እንዲቀየር ይጠበቃል?ለምን ፍቅር….ወሲብ..መለያት ወይም ፍቅር….ወሲብ ..ጋብቻ ..ልጅ መውለድ….፡፡ሌላስ አማራጭ ለምን አይኖርም…ለምሳሌ ፍቅር …ጓደኝነት….በቃ፡፡እንደዛ ቢሆን ምንም ገደብ አያጨናግፈውም…አንድ ወንድ መቶ ሴት ቢያፈቅር ሚኮንነው ሰው የለም…ምክንያቱም ፍቅር ከዛ ጓደኝነት ነው…ባል ይኑራቸው አይኑራቸው….ወደፊት ያግብ አያግቡ አያስጨንቀውም…፡፡ፍቅር ብቻ…ከልብ ማፍቀር ግን ደግሞ እንዳሻቸው ሲበሩና ሲከንፉ እያዩ መደሰት…ሲያገቡ መጨፈር..ሲወልዱ መሳም….ሲያለቅሱ ጉያ ውስጥ ሸጉጦ ማባበል፡፡ግን ይህ ህልም ብቻ ነው …አጉል ምኞት ፡፡ተፈጥሮም ማህበረሰብም አይፈቅድም፡፡ወንድ አንድን ሴት አፍቅሮ እጆቾን ሲነካ በሰውነቱ እሳተ ጎመራ ይንቀለቀላል…ከንፈሯን መገሽለጥ ጭኖቾን መፈልቀቅ ቀዳሚ ምኞቱ ይሆናል…በቃ ማህበረሰብም ተፋቀሩ ሲል ተኙ መከተል እንዳለበት ያምናል..ፍቅር እና አልጋ…ነገሩ ጥሩ ነው ጤነኝነትም ነው…ፍቅርም ወሲብም ለሰው ልጅ የተሰጡ ደስታቸውን የሚያመርቱባቸው ተፈጥሮአዊ የስሜት እርካታ ፍብሪካዎቻቸው ናቸው፡፡ግን ቢሆንስ ሁሉም ፍቅር ወደወሲብ ሁሉም ወሲብ ደግሞ ወደ ጋብቻ መቀየር አለበት ወይ… ?….አይ ምን እየቀባጠርኩ ነው …አትፍረዱብኝ ምን አልባት ይሄንን አይነት ከሰው ልጅ አስተሳሰብ ውጭ የሆነ ነገር ከአባቴ ዝርያ በደም የወረስኩት ይሆናል፡፡››በማለት ስትብሰለሰል ቆየች
ከ15 ደቂቃ በኋላ ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ንስሯ ተመልሷ መጣና በቅርብ ርቀት ጨለማውን እየሰነጠቃ በአየር ላይ ሲንሳፈፍ ተመለከተችው…ሀሳቧን ሰበሰበችና ከእሱ አእምሮው ጋር አገናኘችት… ያየችውን ወይም አሁን እያየች ያለውን ነገር ለማየት ….
✨ይቀጥላል✨

👍130❤16😁5😱4👎3🔥1🤔1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ዶ/ር ሶፊያ ከታዲዬስ ጋር ላላት የቁርስ ግብዣ ቀጠሮ ለመዘጋጀት በለሊት ነው የተነሳችው፡፡ ስለእሱ እና ስለልጆቹ ስታሰላስል ስላደረች በቂ እንቅልፍ አልተኛችም፡፡ቀለል እንዲላት ሻወር ወሰደች ፡፡ ልብሷን በመለባበስ ላይ እያለች ሞባይሏ ጠራ.የማታውቀው ቁጥር ነው፡፡አነሳችው፡፡፡
<<ሄሎ>>
‹‹ሄሎ ሰላም አደርሽ?››
‹‹እግዜያብሄር ይመስገን ...ይቅርታ ግን ማን ልበል አላወቅኩህም፡፡››
‹‹አላዓዛር እባላለሁ፡፡››
‹‹አላዓዛር..አላዓዛር››
‹‹የሰላም ስዕል አስተማሪ፤የታዲዬስ…፡፡››
‹‹አወቅኩህ፤አንተ ቁምነገረኛ ነህ፡፡››
‹‹በጣም እንጂ ፤ ይሄው ሰማይና ምድሩ ከመላቀቁ ደወልኩልሽ››
‹‹በጣም አመሰግናለሁ፤ እንደውም በጣም ስፈልግህ ነበር፡፡ >>
ውስጡን ሞቀው‹‹... እኔ እንደፈለግኳት እሷም ስትፈልገኝ ነበር ማለት ነው ? >> ሲል ተኩራራ፡፡
‹‹ለምንድን ነበር የፈለግሺኝ፤በሰላም ነው?››
‹‹አይ ሰላም ነው፤ስለታዲዬስ አንዳንድ ነገሮችን ልጠይቅህ ነበር?››
‹‹ለምሳሌ ምን?››
‹‹ማኛውንም ነገር ፤ለምሳሌ ያንን የመሰለ ቪላ ቤት ከየት አመጣው?››
‹‹ውርስ ነው፡፡እናቱ ይርጋጨፌ አካባቢ ትልቅ የቡና መሬት ነበራቸው፡፡ ባለሀብት ነበሩ ፡፡ ሲሞቱ ቤቱንም ፤ የቡና ማሳውንም መጠኑን የማላውቀው ጥሬ ብርም እንዳወረሱት አውቃለሁ፡፡እሱ ደግሞ በነሰላም ላይ ኢንቨስት እያደረገው ነው፡፡››
‹‹ቆይ አንድ ያልገባኝ ነገር ታዲያ ይሄ ሁሉ ንብረት ካለው ለምን የሊስትሮ መስራት አስፈለገው?››
‹‹ቆይ ስለታዲዬስ ምንም አታውቂም ማለት ነው?>>
‹‹አዎ እውቂያችን አጭር ነው፡፡በጣም ሚስጥራዊ ሰው ሆኖብኛል፡፡››
አላዓዛር የዶክተሯ አካሄድ አላማረውም‹‹ዘመድሽ አይደለም አይደል?››
‹‹አዎ አይደለውም፡፡በአጋጣሚ ነው የተዋወቅኩት፡፡ከዛ በኃላ ግን ፈፅሞ ልረሳው አልተቻለኝም፡፡››
‹‹ማለት ፍቅር ቢጤ ማለትሽ ነው?››
‹‹እንደዛ ማለት እንኳን ይከብደኛል፤አይ አይደለም…..እኔ በባለፈ ህይወቴ ብዙ ያልተጠናቀቀ የፍቅር ጣጣ ያለብኝ ሰው ነኝ፤ግን ተረዳኝ አላዓዛር በታዲዬስ በጣም ተስቤበታለሁ ...እና ጥያቄዬን መልስልኝ፡፡ የገንዘብ ችግር ከሌለበት ለምን ሊስትሮ ይሰራል?››
‹‹ዶ/ር ..ታዲዬስ ማይሰራው የስራ አይነት የለም፡፡ሲያሰኘው የሆቴል አስተናጋጅ ይሆናል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ የትልቅ መስሪያ ቤት ስራ አስኪያጅ ይሆናል፡፡ስራን የሚሰራው ለገንዘብ ሳይሆን በውስጡ ላለው ፍልስፍና ሲል ነው፡››
‹‹ቆይ ስለትምህርት ደረጃው ልትነግረኝ ትችላለህ?››
‹‹ሁለት ዲግሪ 3 ዲፕሎማ እና ቁጥራቸውን የማላውቀው ሰርተፍኬት በተለያየ ሞያዎች አለው፡፡››
‹‹ስለታዲዬስ እኮ ነው የምጠይቅህ? >>
‹‹እኔም ስለእሱ ነው እያወራሁሽ ያለሁት፡፡››
‹‹ቆይ ግን..››ቀጣዩን ጥያቄ ካማጠናቀቋ በፊት የአላዓዛር ስልክ ተቋረጠ፤ሳንቲም ጨርሶ ነው ብላ በማሰብ መልሳ ደወለችለት፤ ጥሪ አይቀበልም ይላል፡፡
‹‹ብሽቅ አለች››ጥያቄቿን ከማጠናቀቋ በፊት የስልኩ መቋረጥ አበሳጭቷታል፡፡ልብሷን ለብሳ ካጠናቀቀች በኋላ በቀጠሮዋ መሰረት 2 ሰዓት ሲሆን ግቢ ውስጥ ያለውን መኪናዋን በማስነሳት ታዲዬስ ሊስትሮ ወደሚሰራበት ቦታ አሸከረከረች፡፡አገኘችው፡፡ስላምታ ተለዋወጡ፡፡
‹‹በቀጠሮችን መሰረት መጥቻለሁ›› አለችው ፡፡
‹‹መሄድ እንችላለን ››ብሎ ቀድሟት ወደ መኪናው አመራ፡፡
‹‹ዕቃህንስ… ?ማን ይጠብቅልሀል?››
‹‹ችግር የለውም፡፡››
‹‹ማለት መፅሀፎቹን አይሰርቁህም?››
‹‹መፅሀፍ የሚሰርቅ ሰው ሰረቀ አይባልም፡፡››
‹‹እንዴት ?››አለችው መኪናው ውስጥ ገብታ ሞተሩን እያስነሳች፡፡
‹‹ከዚህ የሚወስደው ወይ ለማንበብ ነው አልያም ለሚያነብ ሰው ለመሸጥ ነው፡፡ በሁለቱም መንገድ አውቆም ይሁን ሳያውቅ እውቀትን እያስፋፋ ነው፤ስለዚህ ሊመሰገን ይገበዋል፡፡››
‹‹ትገርማለህ..እሺ ቁርሱ የት ይሁን ?>>
‹‹ጋባዥ አንቺ አይደለሽ የፈለግሺው ቦታ፡፡›› ተስማምታ አሽከረከረች፤ ወደ ሀይሌ ሪዞርት ወሰደችው ፡፡ህንጻውን አልፈው ከጓሮ ሀይቁ ዳር ከሚገኝ አንድ መቀመጫ ላይ ፊታቸውን ወደሀይቁ አዙረው ጐን ለጐን ተቀመጡ፡፡
ወዲያው አስተናጋጁ መጣና የሞቀ ሰላምታ ካቀረበላቸው በኃላ የታዘዘውን ቁርስ መዝግቦ ሲመለስ የሆቴሉ ስራ‐አስኪያጅ በቦታው ተተካና ለታዲዬስ የወዳጅነት የሞቀ ሰላምታ አቅርቦለት ከእሷ ጋርም ተዋውቆ ተመለሰ፡፡
‹‹ታዲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?››
‹‹አልፈልግም፡፡>>
‹‹እውነቴን እኮ ነው፡፡››
‹‹እውነትሽን እንደሆነ አውቃለሁ..ይህ ቁርስ እስኪመጣ 15 ደቂቃ ይፈጃል..ይህቺን ጊዜ በዝምታ ፀሀይ እየሞቅኩ ማሳለፍ ነው የምፈልገው››አላት ዓይኖቹን ወደ ሀይቁ እየላከ፡፡እሷም በኩርፊያ እና በንዴት መካከል ሆና ዝምታውን ተቀላቀለች፡፡የጥዋቷ ፀሀይ ከወደ ምስራቁ የምትረጨው ጨረር ሀይቁ ላይ ሲያርፍ በአከባቢው ሊነገር የማይችል የቀለማት ህብረ ቀለም እና ልዩ የሆነ ስሜትን በሰውነት ውስጥ ይረጫል፤የጥዋቱ ቀዝቃዛ
አየርም እንደዛው ለውስጥ ሰላምን ያጓናፅፋል፡፡በንዴት ጀምራው የነበረውን ዝምታ ቀስ በቀስ በደሰታ ታጣጥመው ጀመር፡፡ልክ ታዲዬስ እንደገመተው ከ15 ደቂቃ በኃላ ቁርሱ ቀረበ እና መመገብ ጀመሩ፡፡
አንድ ጉርሻ ጠቅልላ ወደ አፏ እየላከች‹‹እሺ አሁን ጥያቄዬን መጠየቅ የምችል ይመስለኛል፡፡››አለችው፡፡
‹‹የምታደርጊውን ነገር ሁሉ በጽሞና ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ስትበይ ዝም ብለሽ ብይ፤ሁሉ ነገር በማስተዋል ሲያጣጠጥሙት ነው እርካታ የሚያጐናጽፈው፡፡›.
‹‹ይሄማ ሰይጣን አለበት››ስትል በውስጧ ደመደመችና እንዳዘዛት በዝምታ መብላት ጀመረች፡፡
በልተው ካጠናቀቁ <<አሁን የፈለግሽውን ጠይቂኝ ..15 ደቂቃ መጫወት እንችላለን፡፡››
‹‹ግራ ገባት፡፡ በአእምሮዋ ታጭቀው የነበሩት ጥያቄዎች ሁሉ ተበታትነው የት እንደገቡባት አታውቅም..…ዝም ብላ አፏ ላይ የመጣለትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡››
‹‹ትናንት እራት የበላንበት ቤትም ሆነ እዚህ ያሉ ሰራተኛች ከስራ‐አስኪያጆቹ ጭምር በጣም ይቀርቡሀል፤ይወዱሀል፡፡››
አዎ እዚህ በአስተናጋጅነት ..የማታው ቤት ደግሞ በስራ‐አስኪያጅነት ሰርቼ ስለነበር ነው ፤ሌላ ሚስጥር የለውም፡፡››
‹‹በሞያው ሰልጥነሀል?››
‹‹አዎ በሆቴል ማነጅመንት ዲፕሎማ አለኝ፡፡››
‹‹ሌሎች ሁለት ዲግሪዎችም እንዳሉህ ሰምቼያለሁ፡፡›.
‹‹በምን ፊልድ››
‹‹ሲቪል ኢንጂነሪንግ እና ሶሾሎጂ›.
‹‹የምትገርም ነህ፤ታዲያ በተማርክበት ሞያ ደህና የተባለ ስራ መስራት ስትችል...››
አላስጨረሳትም‹‹ደህና የሚባል ስራ የለም፤ሁሉም ስራዎች በጣም አስፈላጊዎች ናቸው፡፡እስቲ ለሊት ተነስተው አስፓልቱን
የሚያጸዱ የፅዳት ሰራተኛች ባይኖሩ የከተማችን መንገዶች እንዴት አስጠሊታ
ይሆኑ እንደነበር አስበሽ ታውቂያለሽ?
በየበረንዳው የጀበና ቡና አፍልተው በርካሽ የሚሸጡ ወጣት ሴቶች ባይኖሩ ስንቱ ቡና ሱሰኛ ቀኑ ተበላሽቶበት እንደሚውል አልመሸ
ታውቂያለሽ.?ቁራሊዬ ባይኖር ሰፈራችን ባልባሌ ኮተቶች ምንያህል ተጨናንቆ እንደነበር ገምተሻል?ድንጋይ ፈላጩ
፤ግንበኛው እና አናፂው ባይኖር ኢንጂነሩ
ይሄንን ህንፃ ማነፅ እንደማይችል አታውቂም.?

👍87👏5❤3😱3👎2
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ቤት እንደገባች ስልኳን ከፈተችና አሰላ ስንዱ ጋር ደወለች "እንዴት ነሽ ሳባ...? ሀኪሙ ጋር ሄድሽ?" ማውራት ስለማትፈልገው ርዕስ ብታወራላትም እንደምንም እራሷን ተቆጣጥራ መለሰችላት
"አዎ ሄጄ ነበር..መድሀኒት ቀይሮ አዞልኛል.. ግን አሁን የደወልኩት አንድ ጓደኛዬ ሱባኤ ልትገባ ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም ልትሄድ ነበር. ለተወሰነ ጊዜ በፆምና በፀሎት ብናሳልፍ ጥሩ ነው አለቺኝ"
"እና ምን አሰብሽ?"
"እኔ እንጃ ..ውስጤ ግን ሂጂ ሂጂ እያለኝ ነው፡፡"
"ብትሄጂ ጥሩ ነው ብቻ እንዳይከብድሽ ነው የምፈራው"
"ግድ የለሽም ስንድ.. እንደምንም ልሞክረው"
‹‹ታዲያ መች አሰባችሁ?"
‹‹ነገ ጠዋት"
"ስንቅ ምናምን ሳለዘጋጅልሽ?"
"ስንዱ ደግሞ ሁሉ ነገር ሱፐር ማርኬት አለ...›› "ዳቦ ቆሎ፤ኩኪስ፤በሶም እንዳትረሺ.."
"በቃ ስንዱ አታስቢ….ምን አልባት ስልክ ካልተፈቀደ ላልደውልልሽ እችላለሁ"
"እሺ የአባትሽ አምላክ ከአንቺ ጋር ይሁን...እኔም ፀልይልሻለሁ"
"ቻው ስንድ ..ለራጂ ንገሪው" ስልኩን ዘጋችው፡፡ ወዲያው ሙሉ በሙሉ አጥፍታ ኮመዲኖ መሳቢያ ውስጥ ከተተች። ተወዳጅ የእንጀራ እናቷን ስለዋሸቻት ፀፅቷታል.. ግን ምንም ማድረግ አትችልም።ላልተወሰነ ቀናተሰ ከሰው ጋር በአካል መገናኘትም ሆነ በስልክ ማውራት አትፈልግም፡፡ ለዚህም ዘዴ መዘየድ ነበረባት
..መጥሪያውን አንጣረረች፡፡ታች ምድር ቤት ኪችን ያለችው..ሰራተኛዋ አለም እየሮጠች መጣች
"ምነው ሳባ ፈለግሺኝ?" "አዎ ቁጭ በይ"
በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አውርታት ስለማታውቅ ደነገጠች...ሽምቅቅ ብላ በራፋ አጠገብ ያለው ወንበር ላይ ተቀመጠችና የምትነግራትን ነገር ለመስማት ዝግጅ ሆና መጠበቅ ጀመረች።
"አሁን የምነግርሽን..ለልጁም ንገሪው፤ ከዛሬ ጀምሮ ማንም መጥቶ በራፍ አንኳኩቶ ቢጠይቃችሁ የለሁም ..ፀበል ሄጃለሁ.. እዚህ መኖሬን ማንም በስህተት እንኳን እንዲያውቅ አልፈልግም።ማንም እንዲረብሸኝ አልፈልግም። ጫጫታ ኳኳታ እንዳልሰማ። ስራሽን እስከአሁን እንደምትሰሪው መስራትሽን ቀጥይ፤ ግን መቶ ፐርሰንት ራስሽን ችለሽ በመሠለሽ መንገድ ነው የምትሰሪው.. በየቀኑ ደግሞ አንድ አንድ ጠርሙስ ውስኪ እዚህ ጠረጴዛ ላይ ታስቀምጪልኛለሽ... ለጊዜው መጋዘን አለ፡፡ እሱ ሲያልቅ ያው ከተለመደው ቦታ ታስመጪያለሽ...የምትፈልጊውን ነገር ከደንበኛችን ሱፐር ማርኬት ሄደሽ እያስመዘገብሽ ትወስጂያለሽ... ከእነሡ ጋር ስለተነጋገርኩ ሂሳቡን እኔ ነኝ የምዘጋው። እዛ የማይገኝ እቃ የምትፈልጊ ከሆነ እዛ ቁም ሳጥኑ የታችኛው ኪስ ውስጥ ብር አለልሽ፡፡እኔን መጠየቅ አያስፈልግሽም ..ቀጥታ የምትፈልጊውን ያህል ትወስጂያለሽ..ደሞዛችሁ ያው እንደተለመደው ከባንክ ጋር አጀስት ስላደረኩ ቀናችሁ ሲደርስ በደብተራችሁ ይገባል። ልጁ ቁርስ ምሳ ራቱን እንዳታጎይበት፡፡የሚፈልገው ነገር ካለም እንዳትከለክይው። ጨርሻለሁ በቃ ወደ ስራሽ ተመለሽ።"
"ሳባ ሰላም ነሽ ግን ?አስፈራሺኝ እኮ"
"ጨረስኩ አልኩሽ እኮ" ወደአልጋው ወጣችና ብርድልብሱን ጥቅልል ብላ ተኛች። አለምም ግራ መጋባቷን በልቧ እንደያዘች ሹክክ ብላ ወጥታ ወደ ስራዋ ተመለሠች። ከዛ በማግስቱ ጠዋት ስትመጣ የተለየች ሳባ ነበረች የጠበቀቻት፤
//////
ሳባ ክፍሏ ውስጥ ከተከተተች 35 ቀን ሞላት
ከሆስፒታል የዶክተሯ ምርመራ ክፍል ውስጥ ድንገት ከተገናኘችው ኤፍሬም የተባለ ሰው ጋር አጓጉል ነገር አድርጋ ከተመለሰችበት ቀን አንስቶ ከበፊቱ በባሰ መልኩ መኝታ ቤቷ ውስጥ ራሷን ደበቀች፡፡ ሰራተኛዋ በቀን ሁለት ጊዜ ምግብ ወደ ክፍሏ አስገብታ ከአልጋው ጎን ባለው ኮመዲኖ ላይ ታስቀምጥላትና ሹክክ ብላ ተመልሳ ትወጣለች፡፡እሷም ከቀረበላት ምግብ 20 ፐርሰንቱን ብቻ ስትጠቀም ከመጠጡ ግን እንጥፍጣፊ ጠብታ አታስተርፍም፡፡
ይህ ድባቴ እስከመቼ እንደሚዘልቅ ማብቂያው የት ጋር እንደሆነ ማንም አያውቅም፡ እሷም እያስጨነቃት አይደለም፡፡ከአስር አመት በፊት ከአዲስአባ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግ ተመርቃ ስራ ፍለጋ በየቢሮው የምትንከራተት፤ የታክሲ የሚቸግራት፤ ካፌ ግብቶ ማኪያቶ ለመጠጣት ድፍረት ያልነበራት፤ ሚስኪን ንፅህና ፤ባለብሩህ ተስፋ ወጣት ነበረች፡ዛሬ ከአስር አመት በኃላ የተንጣለለ ባለ10 ክፍል ቢላ ቤት ያላት፤ ምርጥ የተባለ ሴቶች ሁሉ አይናቸውን የሚያንከራትቱበት መኪና ምታሽከረክር ፤የባንክ ደብተሯ ላይ አስራ ምናምን ሚሊዬን ብር ያላት የ33 ዓመት አማላይ ግን ደግሞ አባቷን ጨምሮ የአራት ሰዎችን ህይወት ያመከነች ከዚህም በኃላ በአጠቃላይ የህይወት አላማው ትርጉሙም ውሉም የጠፋባት ስብርብረ ያለች ሴት ነች፡፡
በተኛችበት አልጋ ላይ ሳትነሳ እጇን ሰደደችና ኮሚዶኖ ላይ የተቀመጠ ውስኪ ጠርሙስን እንደምንም ጎትታ አነሳች፡፡ገርገጭ ገርገጭ እያደረገች ጠጣችና ክዳኑን በመከራ አሽከርክራ በመዝጋት እዛው ቅርቧ ትራሱ ስር አስቀመጠችና ወደድባቴዋ ተመለሰች፡፡
አለም እንደመጣች ወደሳባ ክፍል በመሄድ ሰላም ማደሯን ከተለመለከተች በኃላ ወደኪችን ሄዳ በተቻላት መጣን አጣፍጣ ቁርስ ሰራችና እንደጨረሰች ከዳድና በማስቀመጥ ተመልሳ ወደሳባ ክፍል ሄደች ፤ስትገባ ሳባ ተዘርራ በተኛችበት አይኖቾን ኮርኒሱ ላይ ሰክታ በሀሳብ ጠፍታ ነው ያገኘቻት ፤ቀጥታ ወደ ቁም ሳጥኑ ሄደችና ከፈተች.. ልብስ መምረጥ ጀመረች…ፎጣ፤ፓንት…ቢጃማ ከያሉበት መረጠችና አወጣች…..ወደሻወር ቤት ይዛ ገባች.የሻወሩን ሙቅ ውሀ ለኮሰችው…ገንዳውን በውሀ ሞላችው..
ከዛ ተመልሳ ወደመኝታ ቤት ገባችና ወደሳባ ተጠግታ ጎንበስ አለችና ወዝውዛ ከገባችበት ሀሳብ በግድ መነጭቃ በማውጣት ‹ሳቢ ተነሽ ሰውነትሽን ታጠቢና ልብስ ቀይሪ››አለቻት፡፡
‹‹ምን? ››
‹‹ሰውነትሽን ታጠቢ. ..ውሀውን ለኩሼልሻለሁ….ቀለል ይልሻል››
‹‹ምነው ሰውነቴ ሸተተሸ እንዴ?››
አለም ያላሰበችውን ነገር ስለተናገረቻት ደነገጠች‹‹ኸረ ሳቢ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም››
‹‹በቃ ውጪልኝ››ሰሞኑን ከነበራት ኃይል በመቶ እጥፍ በበለጠ ኃይል አንቧረቀችባት…አለም በጣም ተከፍታ ወደሻወር ቤት ተመልሳ ገባችና የለኮሰቸችውን ውሀ አጠፋፍታ ያወጣችውን ልብስ ወደቁምሳጥኑ መልሳ ሹክክ ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣች፡
ሳባ ልጅቷን እንዲህ ለማበሻቀጥ ምንም ፍላጎት አልነበረትም፡፡እንደዛም ስላደረገች እፍረት ተሰምቷታል..የጮኸችው በእሷ ላይ ይሁን እንጂ እውነታው ግን በራሷ ላይ ነበር ለመጮኸ የፈለገቸው፡፡በገዛ ማንነቷ ነው የተበሳጨችው፡፡
ለመሆኑ እንዲህ ከንቱ ከሆንኩ ቀድሞውንስ ለምን ተፈጠርኩ..?ለምንስ እኖራለሁ? ህይወት ምንድነው? ሞትስ..?በመኖሬ ምን አተርፋለሁ.?.በሞቴስ የማጣው ነገር አለ?ያለፈትን አንድ ወር ሙሉ በእምሮዋ ሚጉላሉ ግን ደግሞ ቁርጥ ያሉ መልሶችን ልታገኝላቸው ያልቸለች ግትልትል በህይወት ትርጉም ላይ ሚያጠነጥኑ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
እንዲሁ በድን ሆና ተዝለፍልፋ እንደተኛች..ቀኑ ነጎደ መሸ..አራት ሰዓት ሆነ

👍67❤8👏2🔥1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
‹‹እሺ በቃ ..እንዳልክ ይሁን ….እኔ እንዳግዝህ የምትፈልገው ነገር ካለ ምንም ሳታቅማማ ንገረኝ››አለው አለማየሁ ከልብ ለአላዛር ከፍተኛ ሀዘኔታ ተሰምቶት፡፡
‹‹እሺ….ለጊዜው እኔ እስክመጣ ቤት እንድትሆን ነው የምፈልገው..ማለቴ አንተና ሁሴን እኔ ቤት እንድትሆኑ እፈልጋለው››
ኩማንደሩ‹‹ያ ግን ምንድነው የሚጠቅምህ?››ሲል በገረሜታ ጠየቀው፡፡
‹‹ሁለት ጓደኞቾ አብረዋት ከሆኑ …ምንም ሳይታወቃትና ሳይደብራት ነው ህክምናዬን ጨርሼ የምመጣው…ብቻዋን ከሆነች ግን ማብሰልሰሏና መበሳጨቷ አይቀርም…ያ እንዳይሆን አግዙኝ››
‹‹ቀላል ነው..አንተ ብቻ ተረጋግተህ ችግርህን ለመቅረፍ ሞክር ››ሲል ቃል ገባለት፡፡
‹‹እሺ ሞክራለው››እርግጠኝነት በማይነበብበት የድምፅ ቅላጼ መለሰለት፡፡
‹‹ካልተሳካም ምንም ተስፋ አትቁረጥ..አየህ ትልቁ ነገር የችግርህ መነሻ ምን እንደሆነ በግልፅ አውቀሀል..ስለዚህ ምንም ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አይኖርም…እዛ ካልተሳካ እዚህ መልሰን አንሞክራለን››
‹‹አመሰግናለሁ….››
//////
አላዛር ወደቱርክ በበረረ በሁለተኛው ቀን ሰሎሜ አለማየሁና ሁሴን እራት በልተው ቢራ እየተጎነጩ እስከምሽቱ ሰባት ሰዓት ሲጫወቱና ሲሳሳቁ ከቆዩ በኋላ ፤አለማየሁ ድንገት ሞባዩሉን አወጣና ስልኩን ካየ በኃላ ‹‹ሰዎች ነገ ሰኞ ነው..እኔ ደግሞ ስራ አለብኝ….እና ጥያችሁ ልገባ ነው››አላቸው፡፡
ሰሎሜም ‹‹አረ..ሁላችንም እንተኛ..ነገም እኮ ሌላ ቀን ነው››ስትል ለቀረበው ሀሳብ ድጋፍ ሰጠችው፡፡
ሁሴንም ‹‹እንደዛ ከሆነማ እንነሳ›› አለና የቀረችውን ቢራ ጨልጦ ቀድሞ ከመቀመጫው ተነሳ…ሁለቱም ተከትለውት ተነሱ፡፡
መራመድ ሲጀምሩ እሷን ከመሀከል አደረጓት….የሁሉም መኝታ ክፍል አንደኛ ፎቅ ላይ ሚገኝ ሲሆን የፎቁን መወጣጫ እንደወጡ በተከታታይ የሁለቱ መኝታ ክፍል ይገኛል…የእሷ መኝታ ክፍል ግን የግራውን ኮሪደር ይዞ መጨረሻ ላይ ነው የሚገኘው..መለያያቸው ላይ ሲደርሱ ‹‹‹እንግዲህ ስለያችሁ በእንባ ነው..ደህና እደሩ››አለቻቸው፡፡
‹‹አይ…እንሸኝሻለን…ክፍልሽማ ሳናደርስሽ አውላላ ሜዳ ላይ ጥለንሽ ወደቤታችን ብንገባ ቀልባችን አርፎ አይተኛም››አላት አሌክስ፡፡
ሁሉም በአንድነት ተሳሳቁ‹‹አይመሽባችሁም?››ስትል ቀልዱን በቀልድ መለሰች፡፡
‹‹ግድ የለም…ከመሸብንም እዛው እናድራለን››መለሰላት ሁሴን፡፡
‹‹እንግዲያው ሸኙኝ ደስ ይለኛል፡፡››ፈቀደችላቸው፡፡
መሀከላቸው እንዳደረጎት የግራውን ኮሪደር ያዙና ወደመኝታ ቤቷ መራመድ ጀመሩ…አስራአንድ ወይም አስራሁለት እርምጃ እንደተራመዱ መኝታ ቤቷ በራፏ ላይ ደረሱ፡፡
በራፉን ገፋችና ከፈተችው፡፡
‹‹አሁን ደህና እደሪ››ሁሴን ነው ተናጋሪው፡፡
‹‹አይ እዚህ ድረስ ለፍታችሁማ የሆነ ነገር ሳትቀምሱ አትሄዱም ..ግቡ››ብላ ቀድማ ገባችና የመኝታ ቤቱን በራ ወለል አድርጋ ከፍታ እንዲከተሏት ትጠብቅ ጀመር፡፡
ሁለቱ ወንዶች እርስ በርስ ተያዩ፡፡
‹‹እንዴ…ግቡ አይዟችሁ …አትፍሩኝ …መቼስ አቅም ኖሮኝ ሁለት ወንድ በአንድ ላይ አልደፍርም፡፡››
ሁለቱም በየልባቸው ሲፈልጉት የነበረ ነገር ስለሆነ ተጣብቀው እየተገፋፉ ገቡ፡፡በራፉን መልሳ ዘጋችና እየመራች ወሰደቻቸው፡፡መኝታ ቤቱ ግዙፍና ሳሎን መሳይ ነው..ከአልጋው በሶስት ሜትር ርቀት ያለ አነስተኛ ጠረጴዛን የከበቡ አራት ዘመናዊ ውብ ደረቅ ወንበሮች አለ፡፡እነሱን ከጠረጴዛው ስር እየጎተተች እንዲቀመጡ አመቻቸችላቸው፡፡ተቀመጡ፡፡
ወደኮመዲኖ ሄደችና ከስር ያለውን መሳቢያ ከፈተች፡፡ውብ ጥቁር እና አብረቅራቂ ካርቶን አወጣችና አምጥታ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠችው፡፡ሶስት ብርጭቆ አመጣችና ከፊት ለፊታቸው ደረደረች፡፡
‹‹ልብስ ልቀይር እስከዛ እራሳችሁን አስተናግዱ፡፡››
‹‹ወደ ክፍሌ ግቡ ስትይ እኮ ሻይ ወይም ቡና ልታቀርቢልን መስሎኝ ነበር፡፡››አላት ኩማንደሩ፡፡
‹‹ያው በለው…..እስኪ ካርቶኑን ክፈትና እየው .ቁርጥ ሻይ ነው የሚመስለው፡፡››.አለችና እየሳቀች ወደቁምሳጥኑ ሄዳ በመክፈት የለሊት ልብስ መራርጣ ይዛ ወደመልበሻ ክፍል ገባች፡፡
ኩማንደሩም‹‹ሰውዬ እንግዲህ ምን እናዳርጋለን እራሳችሁን እናስተናግድ፡፡›› አለና ካርቶኑን ከፍቶ የውስኪ ጠርሙሱን አወጣው፤ ክዳኑን ከፈተ፡፡ሁለቱ ብርጭቆ ውስጥ ቀዳ…አንዱን ለሁሴን አስጠጋለትና የራሱን ብርጭቆ አንስቶ ተጎነጨለትና ጣዕሙን አጣጥሞ መልሶ አስቀመጠው፡፡
‹‹ነገ ስራ ገባለው መሸብኝ ያልክ መስሎንኝ?››ሲል ጠየቀው ሁሴን፡፡
‹‹አዎ..እና ››
‹‹እናማ አሁን ወደክፍልህ ሄደህ ብትተኛ ምን ይመስልሀል?››
‹‹አንተስ?››
‹‹እኔማ ነገም ተኝቼ መዋል እችላለሁ…ከሰሎሜ ጋር አንድ ሁለት ብርጭቆ ተጎንጭቼ ወደ ክፍሌ እሄዳለው፡፡››
‹‹አይ አመሰግናለሁ…እንደውም ስላመመኝ ነገ ስራ አልገባም….››
‹‹ተው እንጂ!! አሞኛል በሚል ተልካሻ ምክንያት ከስራ ገበታ ላይ መቅረት ለዛውም እንደአንተ ሀላፊነት ላይ ላለ ሰው ሲሆን ትልቅ ሙስና ነው እኮ››
‹‹ይሁን ችግር የለውም..በሀገሪቱ ያለሁት ሙሰኛ ባለስልጣን እኔ ብቻ አይደለሁም…በዛ ላይ …የአላዛር አደራ አለብኝ…ጠብቃታለሁ፡፡››
‹‹ከምንድነው የምትጠብቃት?››
‹‹ከማንኛውም ትንኳሳ ሆነ ጥቃት…ምንም አልከኝ ምንም አይጧን ድመቱ እቅፍ ውስጥ ጥዬ አልሄድም፡፡››
‹‹የተረገምክ ነህ››አለው ፡፡
ሁለቱም ተሳሳቁ…..
በዚህ ጊዜ ሰሎሜ ውብ የሆነ ስስ ሀመራዊ ቀለም ያለው ቢጃማ ቀሚስ ለብሳ ከመልበሻ ክፍል ወጥታ ወደእነሱ ስትመጣ ተመለከቱ፡፡ሁለቱም መሳሳቃቸውን አቁመው አፋቸውን በመክፈት አይኖቻቸውን ተከሉባት፡፡የለበሰችው ቢጃማ ስስ ስለሆነ የሰውነቷን ቅርፅ እና ከውስጥ የለበሰችውን ፓንት ሳይቀር በግልፅ ያሳያል፡፡
የተነጋገሩትን ሳትሰማ ፈገግታቸው ተጋብቶባት እሷም እየፈገገች ‹‹ምንድነው እንዲህ የሚያሳስቃችሁ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
ኩማንደሩ‹‹የሻይ ግብዣሽ አስደስቶን ነው…ነይ ቁጭ በይ፡፡›› በማለት ከተቀመጠበት ተነሳና ወንበር ሳበላት፡፡ ተቀመጠች..ባዶውን ብርጭቆ ወደእሷ አስጠጋና ከውስኪው ቀዳላት፡፡
‹‹እኔም ልጠጣ እንዴ?››
‹‹መጠጣት ፈልገሽ አይደል..ሶስት ብርጭቆ ያመጣሽው?››
‹‹አሁን እራሱ እኮ ሰክሬለሁ….ይሄንን ስጨምርበት ደግሞ..››
‹‹አንቺማ ስከሪ….የገዛ ክፍልሽ ነው ያለሽው..ምን አሰጋሽ?››
‹‹እናንተም ሳትሰጉ ጠጡ..እንደምታዩት አልጋው ሰፊ ነው…አንግዳ በአጉል ሰዓት ከቤታችን አናባርርም፡፡››
አለማየሁ ከአንደበቷ ነጥቆ‹‹በአንድ አፍ….››አላት፡፡
‹‹..ችግር የለውም …ዘና ብላች ጠጡ!!››
‹‹ምን እደሚገርመኝ ታዊቂያለሽ?››ሲል ድንገት ጠየቃት፡፡
‹‹ምንድነው የሚገርምህ?››
‹‹በፊት እኮ መጠጥ በጣም ነበር የምትጠይው..ሽታው እራሱ ያምሽ ነበር..አሁን ግን ይሄው ከእኛ እኩል ትቀመቅሚያለሽ?››
‹‹አዎ…እኔም ገርሞኝ በውስጤ ሳማሽ ነበር››ሁሴን የአለማየሁን አስተያየት ደግፎ ተናገረ፡፡
‹‹አይ የወንደላጤ ነገር!››ስትል በሽሙጥ መለሰችላቸው፡፡
‹‹እንዴ ይሄ ደግሞ ከወንደላጤና ከትባለትዳር ጋር ምን አገናኘው?፡››
‹‹አንድ ሰው ከትዳር በፊትና ከትዳር በኃላ በብዙ ነገር የተለያየ ሰው ነው የሚሆነው…ከለውጦቹ ውስጥ አንድ.. ባልትዳር የሆነ ሰው ወይ ጠጪ ወይ ፈላስፋ ወይ ደግሞ ወፈፌ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው፡፡››
‹‹እና አታግቡ እያልሺኝ ነው፡፡››

👍56❤6🥰1