#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
...“ለምንድነው ግንኙነቱን የፈለጋችሁት? ከሄደ ሄደ፤ ግልግል!” ናትናኤል ጠየቀ፡፡
“የቱን ግንኙነት?”
“ከሱውጋ ያላችሁን ነዋ ከላይቤርያው አታሼ?”
"እህ...ተገረመ አብርሃም፡፡ “ይጠቅሙናላ፡፡ ሰውየውን መዳፋችን
ውስጥ ማቆየታችን፡፡ አየህ...የአንድን የስለላ ድርጅት ወኪል በስውርም ሆነ
በማስገደድ ተቆጣጠርው ማለት ከኋላው ያለውን የስለላ ድርጅት በተወሰነ ደረጃ ተቆጣጠርክ» ማለት ነው፡፡ ጆሴፍ ካልቨርትን፤ በነገራችን ላይ ስሙ ካልቨርት ነው! እና ካልቨርትን ተቆጣጠርን ማለት ስለሞንሮቪያ ሊሰጠን የሚችለውን ሁሉ ከማግኘታችን በተጨማሪ የእንግሊዝን ኤም.አይስድስት ምናልባትም የእሥራኤልን ሞሳድ እንቅስቃሴ ጫፍ ያዝን ማለት ነው::”
“ገባኝ...ገባኝ::” ናትናኤል ራሱን በመስማማት እየነቀነቀ ሰዓቱን
ተመለከተ ስድስት ሰዓት ከአሥር፡፡ “አብርሃም ለምን ወጥተን ምሳችንን
እየበላን አንጫወትም? ”
“ጥሩ፡፡” አለ አብርሃም ከመቀመጫው እየተነሣ፡፡
ከቤት ወጥተን በናትናኤል መኪና ከግቢ ሲወጡ የመኪናውን መስኮት ዝቅ አደረገና..
“የሚፈልገኝ ሰው ኸደወለ ገላውን እየታጠበ ነው በይ ወጥቷል አትበይ፡፡” አላት የግቢውን መዝጊያ ከፍታ የያዘችውን ሠራተኛ፡፡
“እሺ” አለች የግቢውን በር በሁለት እጆቿ እንደያዘች::
ናትናኤልና አብርሃም ከግቢ እንደወጡ የአብረሃም ሠራተኛ የግቢውን በር ዘግታ በጥድፊያ ወደ ዋናው ቤት ተመለሰች:: ወደ መኝታ ክፍሏ ገብታ አነስተኛ ሻንጣ መሰል የሬዲዬ መልዕክት ማስተላለፊያ
መሣሪያዋን ከፈተቻት…ቲቲቲ.… ሃሎ... ሃሎ...ቲቲ-ቲ ቲቲ.ቲ. ቲቲ.ቲ ሃሎ… ሃሎ ቆንጆዎቹ…ቡድን 'ረ' ዜሮ ሶስት ስድስት ሰዓት ከአስራ ሶስት ናትናኤል ከሚባል ሰው ጋር ወጥቷል፡፡ ከአምስት ከሃያ ጀምረው ሲያወሩ ነው የቆዩት፡፡ ቅጅውን ሰሰዓቱ . እልካለሁ… ጨርሻለሁ::" የሬዲዬ
ማስተላለፊዋን ዘግታ ከቦታው መልሳ ወደ ሳሉነ ክፍል ተጣደፈች ጥግ ወዳለው አረንጓዴ ሶፋ ሄደችና በርከክ ብላ ከወንበሩ ስር አነስተኛ የድምፅ መቅጃ አወጥታ ወደ መኝታ ቤቷ ተመለሰች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ናትናኤልና አብርሃም ከልደታ ተነስተው ሜክሲኮ አደባባይ እስኪደርስ አልተነጋገሩም፡፡ ፖሊስ ሆስፒታልን አለፍ እንዳሉ አብርሃም የኋላ መመልከቻ መስተዋቱን ወደ ራሱ እያስተካከለ
“ብጠቀምበት ይክፋሃል? ” አለ፡፡
“ለምን? ምን ያሠራልሃል? " አለ ናትናኤል ጓደኛውን ላንዳፍታ ተመልክቶ::
"የመረጃው መሥሪያ ቤት አባል ከሆንኩ ጀምሮ የምሄድበትን ብቻ ሳይሆን የመጣሁበትንም መንገድ መመልከት ተምሬአለሁ" አላ አብርሃም እየሳቀ “እንደ አሣ፡፡”
“እንዴት? ምኑን ታየዋለህ የመጣህበትን መንገድ?' ናትናኤል የጓደኛው ነገረ ሥራ ሁሉ አለወትሮው ግራ የሚያጋባ ሆነበት::
አብርሃም አልተመለሰም፡፡ ብቻ ፈገግ እለ ፈገግ፡፡ አይኖቹ ግን ገና ከቤት ሲወጡ ራቅ ብሎ ከመንገድ ዳር ቆሞ በነበረው በኋላም በሩቅ እርቀት በሚከተላቸው ነጭ ሲትሮይን መኪና ላይ ነበሩ፡፡
ሜክሲኮ አደባባይን ዞረው ወደ ብሔራዊ ትያትር ሲያቀኑ አብርሃም አሁንም በኋላ መመልኮቻው መስታወት ተመለከተ፡፡ ነጩ ሲትሮይን በተመሣሣይ ርቀት ተከትሏቸዋል፡፡ ናትናኤል መኪናውን ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ለማቆም በረድ ሲያያደርግ
“ቀጥል ቀጥል ናትናኤል ትንሽ ዞር ዞር እንበል፡፡ · መቀመጠ ሰልችቶኛል፡፡" አለ አብርሃም አይኖቹን ከኋላ ከሚከታተላቸው ነጭ ሲትሮይን ላይ ሳይነቅል::
“በል : ቀጥልልኝ እንጅ::” አለ ናትናኤል ጓደኛውን ዞር ብሎ እየተመለከተ፡፡
“እ...?…እ…” አብርሃም ልቡ ሌላ ቦታ የሄደ መሰለ፡፡ “አዎ ምን ብዬ ነበር ያቆምኩት? እ…
“ሰውየው ወደ አገሩ ተጠራ ብለህ ነበር፡፡” አለ ናትናኤል ቀልጠፍ ብሎ፡፡
“
አ.አዎ… እና ሰውየው ወደ አገሩ ሲጠራ እንዳልኩህ ፈርተን ነበር፡፡ ግን ብዙም ሳይቆይ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ መደበኛ ሥራውን ቀጠለ፡፡ እኛም እንደወትሮው ክትትላችንን
ተያያዝነው፡፡ ሆኖም አንድ አዲስ ነገር ተፈጠረ፡፡ ሰውየው እንደበፊቱ መረጃዎችን በውስኪ ጠርሙሶች ውስጥ እየደበቀ ማስተላለፉን ትቶ በተደጋጋሚ በሚከራያቸው የሆቴል ክፍሎች ውስጥ ከእንግሊዝ የስለላ ሰዎች ጋር በቀጥታ መገናኘቱን ተያያዘ፡፡”
“ከሰዎቹ ጋር በቀጥታ መገናኘቱ ለእርሱ አደገኛ አይሆንም? ናትናኤል በመገረም ጠየቀ
“ለእኛም እንቆቅልሽ የሆነብን ይህ ነበር፡፡ ለወትሮው ጠንቃቃ የነበረ ሰው መንቀዥቀዥ አበዛ፡፡ አልፎ ተርፎ በስልክ ቀጠሮ እስከመለዋወጥ ደረሰ። አንድ ዓይነት ጭንቀት ውስጥ እንደ ወደቀ ሁኔታው ለመረዳት ከባድ አልነበረም፡፡ አለቅጥ መጠጣቱም ሌላ አዲስ ፀባዩ ነበር፡፡ መሸ አልመሽ ብሎ ቤቱ ይገባ የነበረ ሰው ካዛንቺስ አንድ ሆቴል : ካላት ወዳጁ ቤት ሲጠጣ አምሽቶ እዛው ያድር ጀመር፡፡ ሁኔታው ግራ አጋብቶን ያብልጥ ተደራጅተን ሁኔታውን ለመከታተል ስንዘጋጅ ድንገት ተሰወረ፡፡ አብርሃም ከደረት ኪሱ ሲጋራ አውጥቶ አፉ ውስጥ ሻጠና ለናትናኤል እየጋበዘው የመኪናውን
የሲጋራ ማያያዣ ተጫነው።
“በቃ፡፡” አለ ናትናኤል አብርሃም ከዘረጋለት የሲጋራ ፓኮ ውስጥ አንድ ሲጋራ መዞ አፉ ውስጥ እየተካ፡፡
"በቃ" አብርሃም ፍም በመሰለው የሲጋራ መለኮሻ ሲጋራውን እየለኮሰ በኋላ መመልከቻው መስታወት ውስጥ ተመለከተ፡፡ ነጩ ሲትሮን አሁንም እየተከተላቸው ነው፡፡
“እና ተሰወረ ብላችሁ ተዋችሁት ማለት ነው ናትናኤል አብርሃም ባቀበለው እሳት ሲጋራውን እያቀጣጠለ ተገርሞ ጠየቀ፡፡”
“የነገሩን ክብደት ይበልጥ እየተረዳን የመጣነው እጅግ ዘግይቶ ነበር፡፡” እለ አብርሃም በረጅሙ ተንፍሶ::
“እንዴት?”ናትናኤል ትዕግሥት አጣ፡፡
“ቆይ…እየነገርኩህኮ ነው፡፡ ሰውየው እንደተሰወረ በመጀመሪያ ሞቷል ማለቴ 'ተገድሏል' የሚለው መላምት ነበር ጠንክሮ የታየን። ስለዚህ በተለይ ማን ሊገድለው ይችላል በሚለው ጥያቄ ላይ ያተኮርን፡፡ የሱንም ጉዳይ ቀደም ሲሉ ተገድለው ከተገኙት ከጊኒና ከሞሮኮ ወታደራዊ አታሼዎች ጋር ደመርነው፡፡”
“አልሞተም አይደል?” ናትናኤል ፊቱን መልሶ ጠየቀ፡፡
“አልሞተም፡፡” አብርሃም ሲጋራውን ማግ አድርጎ ጭሱን በረጅሙ ለቀቀው፡፡
“እንዴት? ምን ማረጋገጫ አገኛችሁ?”
“እዛው ኣካባቢ ያለ ወኪላችን አየው፡፡”
"የት?"
" “ካዛንችስ ከወዳጁ ቤት የሴት ልብስ ለብሶ ድሪያ ተከናንቦ በስርቆሽ
በር ሲወጣ አየወ፡፡”
“ከዛስ?” ናትናኤል መኪናውን በቸርችል ሽቅብ እያሽከረክረ ጠየቀው፡፡
“ወኪላችን ሪፖርቱን እንዳቀረበ ሰዎች አሰማርተን ሃያ አራት ሰዓት አካባቢውን መከታተል ያዝን፡፡ ፡ እሱን ብቻ ሳይሆን ወዳጁንና መጠጥ ቤቱ ውስጥ የሚሰሩትን ፡ ሁሉ አንድም ሳይቀር የማያቋርጥ ክትትል እናደርግባቸው ጀመር፡፡”
"እሺ"
“ያለማቋረጥ ለሣምንት ያህል ስንከታተል ቆየን፡፡ ግን ምንም ፍንጭ ማግኘት አልቻልንም፡፡ ሆኖም ሰውየው አለመሞቱን ሁላችንም ተማምነንበት ስለነበር ክትትላችንን ለማጠናክር ወሰንን፡፡ ያን ጊዜ ድንገት ክትትሉን እንድናቋርጥና ስውየው ስለመሞቱ የሚገልጽ ሪፖርት እንድናቀርብ ከበላይ ታዘዝን፡፡”
“ሰውየው ሳይሞት?”
“ያ ነው'ኮ የሚገርም፡፡ ሁኔታውን ማስረዳት ብንሞክርም ትዕዛዙ በድጋሚ ከማስጠንቀቂያ ጋር ተላለፈልን:: ለጊዜው ጭቅጭቅ መፍጠር ስላልፈለግን የተጠየቅነውን ሪፖርት አስተላለፍን፡፡”
“ሞተ ብሳችሁ?!”
“የፈለጉት እሱን ነዋ!.ሞተ ብለን አስተሳለፍን፡፡ ግን የሚያሳዝን
ሌላ ስህተት ፈጸምን፡፡”
“ምን?”
“ሞቷል የሚለውን ሪፖርት

👍3
ካስተላሰፍን በኋላ በግላችን ሁለት ሰዎች ክትትሉን እንዲቀጥሉ አሰማራን፡፡” እለ ኣብርሃም በኋላ መመልከቻውን መስተዋት እየተመለከተ። ሲትሮይን ተከትላቸዋለች፡፡ ፈገግ አለ፡፡
“እና ስህተቱ ምኑ ላይ ነው?” ናትናኤል ጠየቀው፡፡
“ሁለቱን የክትትል ሰዎች ባሰማራን በሶስተኛው ቀን አንደኛው ሰዋችን በስለት ታርዶ እዛው ካዛንችስ ቱቦ ውስጥ ተጥሉ ተገኘ፡፡
ናትናኤል በድንጋጤ ፊቱን አጨማዶ ጓደኛውን ተመለከተው፡፡
“ሰዋችንን አርዶ የጣለው ስው ወይም ቡድን ማን እንደሆነ ግልጽ ባይሆንልንም ግድያው ከክትትል ጋር የተያያዘ እንደነበረ ስለተረዳን ያሰማራነውን ሁለተኛ ሰው ክትትሉን በፍጥነት እንዲያቋርጥ አደረግን፡፡”
“እሺ።” ናትናኤል ፊቱን እንዳጨማደደ ጓደኛው ፊት ላይ አፍጥጦ ቀረ፡፡
“እያየህ ንዳ እንዳንጋጭ:: በቃ ይኸው ነው::” አለ አብርሃም ሌላ ሲጋራ ባለቀች ሲጋራው እያያያዘ፡፡
“እና በቃ ተዋችሁት.… ተዋችሁት? የገዛ ሠራተኛችሁ ተጎድሉ!”
“አንተ ብትሆን ምን ውሣኔ ትስጥ ነበር?”
“ሰው ጨምሮ መከታተል ነዋ!'ናትናኤል በስጨት አለ፡፡
“በማን ትዕዛዝ? በገዛ ራስህ?” አብርሃም የብስጭት ሳቅ ሳቀ፡፡
“ሁኔታውን በሚገባ የተረዳነው አይመስለኝም እንጅ ናትናኤል በእሳት
እየተጫወትን ነው፡፡ የተሻለው ምርጫ ምን እንደሆነ ልንገርህ?”
“ምንድነው?”
“መተው ነው:: አንተንም የምመክርህ ነገር ቢኖር ይህን ነገር ማነፍነፍህን ትተህ በሰላም ስራህን እንድትሠራ ነው፡፡ የተለመደው ግትርነትና ቅልጥፍና እዚህ ላይ የሚጠቅሙህ አይመስለኝም፡፡”
አብርሃም እየሰራሁ ያለሁትኮ ሥራዬን ነው፡፡ አንተ ነገሩን እርግፍ አድርገህ ልትተው የወሰንከው'ኮ አለቆችህ ስላስፈራሩህ ነው፡፡ የኔ አለቃ ግን
የሚገፋፋኝ ፍሬ ያለው ነገር ይዤ እንድመለስ ነው:: ገባህ?”
“እንግዲያው አለቃህም እንዳንተ ኣይናቸው ተሸብቧል።”
“ማነው አይናችንን የሽበበውዎ” ናትናኤል የጓደኛውን አነጋገር
አልወደደውም።
አብርሃም አልመለሰለትም አይኖቹን በኋላ መመልከቻው መስተዋት ላይ ተክሎ ፈገግ አለ፡፡ ነጯ ሲትሮይን….
“ናትናኤል እውነቱን ልንገርህ?…በጣም ነው የራበኝ እጋብዝሃለሁ ያልከኝ ምሳ እንደ ሰማዩ ነው የራቀኝ፡፡”
💫ይቀጥላል💫

#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
...ሉው ጉድማን መኪናውን ወደ ፓስፊክ ፖሊሴድስ እየነዳ ነው። ከብዙ ጊዜያት በፊት እሱ እና ጆንሰን በግድያ ወንጀል ምርመራቸው ላይ የሚገኙትን ተመርማሪዎች በተመለከተ ክፍፍል አድርገው ነበር። ክፍፍላቸውም እንደዚህ ነው። ጉድማን የሚያናግራቸው ሰዎች
ሀብታሞቹን፣ ከፍ ያሉትን እና የተማሩትን ሲሆን በአንፃሩ ጆንሰን የሚያናግራቸው ደግሞ እያሾፈ ያልታጡ ሰዎች የሚላቸውን ነው። ስለሆነም በጆንሰን ምድብ ውስጥ የሚካተቱት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነጮች እና ለረዥም ጊዜ በፀረ አደንዛዥ ዕፅ ምድብ በመሥራቱ ምክንያት የሚያውቃቸው ላቲናዊያን ናቸው፡፡ ያም ቢሆን የድሮ ኤል.ኤ.ፒ.ዲ ፖሊስ ስለነበረ በጥቁሮች ላይ ያለው የበላይነት (ብልጠት) እምብዛም ነው። እሱም አይወዳቸውም፤ እነርሱም በጭራሽ አይወዱትም፡፡
ይሄ ደግሞ የብዙ ጊዜ ችግራቸው ነው ዛሬ ላይ ግን ችግር ሊሆንባቸው
አይችልም፡፡ የዛሬው ሥራው የነጭ ሀብታም ማህበረሰብ መኖሪያ ሰፈር በሆነው ፓስፊክ ፓሊሴድስ ውስጥ ነው እና ያን ያህል ችግር ይገጥመኛል ብሎ ሉው አያስብም። ይህ ሰፋፊ የመኪና መንገድ እና የብዙ ሚሊዬን ዶላር መኖርያ
ቤቶች መገኛ ቦታ የሉው ጉድማን ክልል ስለሆነ ችግር ይገጥመኛል ብሎ
በጭራሽ አያስብም፡፡
“ወደ ቀኝ ታጠፍ” የሚለው ድምፅ ከጎግል ካርታ አፕሊኬሽኑ ስለወጣ
ጉድ ማን የመኪናውን መሪ ወደ ቀኝ አዙሮ በቀኝ በኩል ባለው መንገድ መኪናውን ማሽከርከር ጀመረ። በመንገዱ ዳር እና ዳር የሚገኙት ትላልቅ እና ዘመናዊ ቤቶች አሥር፣ አስራ አምስት ወይንም ሃያ የመኝታ ክፍሎች ያላቸው እና የግቢ በር ላይም የደምብ ልብስ የለበሱ የላቲን ተወላጆች የቤት
ሠራተኞቻቸው ወጣ ገባ ሲሉ ይታያሉ። መኪናውን በቤቶቹ መሀል
በማሽከርከር ላይ እያለም አንደኛው የሚያውቀው አመላላሽ መኪና የተጫነ
ነገር ይዞ ሲሄድ ተመለከተ። ወደ ሌላኛው ቤት ፊቱን ሲያዞር ደግሞ መኪና
ሙሉ በሂልየም የተሞሉ እና በላያቸው ላይ ራየን ዛሬ ዘጠኝ ዓመቱ ነው'
የሚል ፅሁፍ የተፃፈባቸው ትላልቅ ፊኛዎችን በምናቡ ተመለከተና ፈገግ
አለ፡፡
ራየን ታድለሀል' ብሎም ጉድማን ወደ ልጅነቱ የዘጠኝ ዓመቱን ሲያከብር ወደ፥ ነበረው ትውስታ ውስጥ ሰጠመ።ጉድማን ዘጠኝ ዓመቱን ሲያከብር ማርኮ ከተባለው ጓደኛው ጋር በበረዶ በተሸፈነው ተራራ ላይ ነበር። ደስ የሚል ቀን ነበር፡፡ አባቱ ከመክሰሩ በፊት በህይወቱ በጣም ደስ
የሚል ቀን ያሳለፈው ያኔ ነበር። ሉው ጉድማን 10 ዓመት ሲሆነው በጣም
ደስ የሚል ቀን ያሳለፈው ያኔ ነበር። ሉው ጉድማን 10 ዓመት ሲሆነው አባቱ ሞቶ ነበር፡፡ የሞቱ ምክንያት ደግሞ አባቱ የጀመረው ቢዝነስ መክሰር እና መላው ቤተሰቡንም ድህነት ውስጥ በመክተቱ ነበር። ሉው በልጅነቱ ያሳለፈው የድህነት ጊዜን አሁን ላይ ማሰብ ትቷል። ከዚያ ይልቅ ግን በልጅነቱ ያሳለፋቸውን የደስታ ጊዜዎችን እና ጥሩ ጊዜዎቹን ማሰብን
ተለማምዶታል፡፡ ገና ልጅ እያለም ገንዘብ ብዙ ደስታዎችን እንደማይገዛ
ሁሉ፣ ገንዘብ ማጣትም ጭንቀት በሰዎች ላይ እንደሚያመጣ ለማወቅ በቅቷል፡፡ የሉው አባት ሀብት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጠንቅቆ አያውቅም ነበር። ለዚያም ነበር የሆነች ሥራ ጀምሮ ስለተሳካለት በጣም ሀብታም የሆነ የመሰለው። በተለይ ደግሞ የራሱን ቤት መግዛቱ ቤቱ ውስጥም ሰፊ የመኪና ማቆምያ እና ሰፊ ጓሮ ስላለው ራሱን ስኬታማ አድርጎ ነበር የሚቆጥረው። አንድ ጊዜ ግን እነዚያን ነገሮች ሙሉ በሙሉ ሲያጣ ግን ህይወቱ ከመመሰቃቀሉም በላይ ህይወቱን ያሳጣውን በሽታ
ጥሎበት አለፈ።
ሎው ጉድማን ግን ሀብትን በተመለከተ የተለየ አመለካከት ነበረው፡፡
ሀብት ምን እንደሆነም ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ሆኖ ነበር ያደገው:: ሀብትን
ለመሰብሰብ ብለው ምን ያህል አስቸጋሪ፣ ለማመን የሚከብዱ ነገሮችን
እንደሚያደርጉም ተመልክቷል።
.
“
ለመሄድ የፈለክበት ቦታ ከፊት ለፊትህ ይገኛል” አለው የጎግል ካርታው
ድምፅ በመቀጠልም “ቦታው ላይ ደርሰሀል።” አለው ጉድማን የደረሰበትን
ቦታ ቀና ብሎ ሲመለከት በ19772 መንገድ ላይ በጥንታዊው የግንባታ
አሠራር የተገነባውን የግሮልሽ ቤተሰብን ትልቅ መኖሪያ ቪላን አገኘው፡፡
ወደ ግሮልሽ የቤተሰብ መኖሪያ መኪናውን እየነዳ በመምጣት ላይ እያለ
ስለ ግሮልሽ ቤተሰብ የሀብት ምንጭ ከጎግል ላይ አንብቦ ነበር፡፡ በ1980 ዎቹ
በቆሻሻ አወጋገድ ኢንዱስትሪ ላይ የተሰማራውና የናታን ቤተሰብ አባል
የሆነው ግሮልሽ በሙያው ከበቂ በላይ የሚባል ሃብት ለመሰብሰብ በቅቶ
ነበር። ግሮልሽ ሁለት ሴት ልጆች የወለደችለትን የመጀመሪያ ሚስቱን
ፈትቶም በሃምሳዎቹ ዕድሜ ላይ የምትገኘውንና በጊዜው የቁንጅና ውድድር አሸናፊ የነበረችውን ንግስት ፍራንሰስ ዴንተንን አገባ። ከፍራንሰስም
ብራንዶን የሚባል ወንድ ልጅ ወለዱ። ካነበበው ነገር እንደተረዳውም
ብራንዶን ከሦስት ቀን በፊት ሊዛ ፍላንገን በተገደለችበት ዕለት 19ኛ ዓመቱን
የሚያከብርበት ቀን ነበር፡፡
የሬሳ መርማሪ ሀኪም ጄኒ ፎይሌ በሰጠቻቸው የዲ.ኤን.ኤ ውጤት
መሰረት ብራንዶን ግሮልሽ ይሄን ትልቁን የልደቱን ቀን ያሳለፈው ሊዛ ፍላንገንን በጩቤው በመቆራረጥ ልቧ ላይ ጩቤውን ሰክቶ በመግደል እና ሬሳዋን ልክ እንደ ቆሻሻ በቆሻሻ መጣያ ላስቲክ ውስጥ ጠቅልሎ መንገድ ዳር በመጣል ነበር። ያ ካልሆነ ደግሞ የሆነ ሰው ሊዛ ፍላገንን ከገደላት በኋላ የብራንዶንን የቆዳ ፍቅፋቂ በሊዛ ፍላንገን ጥፍር ውስጥ አስቀምጧል ማለት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ሊሆን የማይችል ነገር ቢሆንም ነገሩን በዚህ መልኩ ማሰብ አይከፋም፡፡
ጉድማን የግሮልሽ ቤት የጊቢ በር ላይ ያለውን መጥሪያ በእጁ እየተጫነ ወደ ላይ ተመለከተ። በግራ እና በቀኝ በኩል ከቆመው የእምነበረድ ምሰሶ ላይ ሁለት የአንበሳ ሀውልቶች ቁልቁል ወደ ታች ያዩታል፡፡
“ማን ልበል?” የሚል የሴት ድምፅ በሩ ላይ ካለው ስፒከር ወጣ፡፡
“እንዴት አረፈድሽ” ብሎ ሉው ጉድማን ጉሮሮውን አጠራ እና በመቀጠልም
መርማሪ ፖሊስ ሉው “ጉድማን እባላለሁ ከሎስ አንጀለስ ፖሊስ ብራንዶን ግሮልሽን ለማናገር ነበር የመጣሁት።” አለ፡፡
“አንድ ጊዜ ይቅርታ” ብላ የሜክሲኮ ዘዬ ባለው ድምፅ መለሰችለት ምናልባት የቤተሰቡ ሠራተኛ ሳትሆን አትቀርም ብሎ አሰበ፡ በሩ ላይ የሆነ መንቀጫቀጭ ከተሰማ በኋላ ለረዥም ጊዜ ዝምታ ነገሰ። በድጋሚ መጥሪያውን ሊደውል ሲል ግን የውጨው በር ተከፈተ፤ በሩም ግቢው ወለል ብሎ ይታይ ጀመረ፡፡
መኪናውን ሰማያዊ ወለልን ባለበሰው የመኪና መንገድ እያሽከረከረ የሚያምር በእምነበረድ የተሰራ ፏፏቴን አልፎም መኪናውን አቆመ ከመኪናውም ወርዶ የቪላው መግቢያን ይበልጥ አስውበውት አገኘው::
ከበሩ አጠገብ የሚገኘው የነሀስ መብራት ማንጠልጠያ እና ቋሚ ደግሞ የቪላውን መግቢያ ይበልጥ አሳምሮታል። ብቻ ቪላው ከመኖሪያ ቤት ይልቅ ደልቀቅ ያለ ባለ ትንሽ ኮከብ ሆቴል ነው የሚመስለው።
“እባክዎን ይግቡ” ሜክሲካዊቷ የቤት ሠራተኛ በመብራት ያሸበረቀ ትንሽ
የእንግዳ መቀበያ ውስጥ ይዛው ገባች። ክፍሉ ውስጥ የሚገኙት የቤት ዕቃዎች በሴቶች የተመረጡት እንደሆኑ ያስታውቃሉ። ነጭ የሶፋ ወንበሮች፣ ደብዘዝ ያለ ፒንኪ መጋረጃ፣ የአበባ ስዕል የታተመባቸው የሶፋ ትራሶች እና በካሽሚር የተጠለፉ የሶፋ ወንበር ልባሶች ነበሩ። የቡና ጠረጴዛው ላይም ትላልቅ የአበባ እቅፎች ተቀምጠው አየ። የአበቦቹ ሽታም ክፍሉን አውዶታል፡፡
“ወ/ሮ ግሮልሽ አሁን ትመጣለች። ሻይ ላምጣሎት?” አለችው ሠራተኛዋ
“አመሰግናለሁ አልፈልግም” ብሎ ጉድማን

ፈገግ አለ። ሻይ እንድታመጣለት
ያልፈለገበት ምክንያት ደግሞ የቤተሰቡን ወንድ ልጅ የሆነውን ብራንዶን ግሮልሽን ለጥያቄ ወደ ጣቢያ ሊወስደው ስለሆነ ሻያቸውን መጠጣቱ ፍትሀዊ ስላልመሰለው ነበር። ሰራተኛው ክፍሉን ለቅቃ ከመውጣቷ በፊትም
“ብራንዶን ቤት ውስጥ አለ እንዴ?” ብሎ ጠየቃት፡፡
ሠራተኛዋም እያልጎመገመች “ወ/ሮ ግሮልሽ እየመጣች ነው” ብላ ሌላ
ጥያቄ ከመጠየቋ በፊት ክፍሉን ጥላ ወጣች። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም
እሱ የሚገኝበት ክፍል በር ተከፈተ፡፡ አንዲት ወይዘሮ ወደ ክፍሉ ውስጥ
ገባች፡፡ “ኢንስፔክተር ይቅርታ ስላስጠበቅኩህ፡፡ ፍራን ግሮልሽ ነኝ”
አጠገቡ ያለችውን ሴት እንደጠበቀው አላገኛትም። ወፍራም እና ቅርፅ
አልባ የመድሀኒት ሱሰኛ መሆኗን የሚያሳብቅባት ያባበጡ እና የጠቆረ
የአይን ዙሪያ ይታይባታል። ፍራንስሰ “ግሮልሽ ያኔ የቁንጅና ውድድር
ያሸነፈችበት ከጎግል ላይ ያገኘው ፎቶዋ እና አሁን የሚያየው ፎቶዋ በፍፁም
አይመሳሰሉም። የለበሰችው ልብስ ላይዋ ላይ ከመንጀላጀሉም በላይ ፀጉሯንም
በርካሽ የፀጉር ማስያዢያ ነው ያስያዘችው። ይህቺን ሴት በዚህ ሁኔታዋ
ግለፃት ቢባል የተሸነፈች ሴት' ብሎ ነበር የሚገልፃት፡፡ ሰውነቷ እና ፊቷ ብቻ ሳይሆን ድምጿ ሁሉ ፍፁም ሽንፈት የማይታይበት ነው።
“ስለ ብራንዶን ለማውራት ነው እዚህ ድረስ የመጣኸው?” አለችው እና
አይኗን በድካም ጨፈነች፡፡
“አዎን ወ/ሮ ፍራን ግሮልሽ፡፡ ብራንዶን ቤት ውስጥ አሁን አለ?” ብሎ
ጉድማን ጠየቃት፡፡
“አይይይ” ብላ መለሰችለት አይኗን እንደጨፈነች፡፡
“መቼ እንደሚመለስ ሊነግሩን ይችላሉ?” ብሎ ሲጠይቃት አይኗን በልጥጣ አፍጥጣ ብታየውም ምንም መልስ አልሰጠችውም።
"እመቤቴ…” ብሎ ጉድማን ጥያቄውን ከመጨረሱ በፊት ፍራንሰስ ግሮልሽ አፏን በልቅጣ ቀጭን እና አሰቃቂ የእንሰሳ የመሰለ ድምፅን አወጣች። ድምጿም እየጨመረ፣ እየጨመረ እና እየጨመረ መጥቶ እያጓራች ማልቀሷን ቀጠለች። ይሄኔም ከቤቱ ኋላ የሆነ በር በሀይል ተጠረቀመ፡፡
ተከትሎም ከባድ የእግር ኮቴን ድምፅ ጉድ ማን ሰማ። ከሰከንዶች በኋላም
እነርሱ የሚገኙበት በር በሀይል ተበርግዶ ተከፈተና ጠቆር ያለ ሙሉ ልብስ
የለበስ ትልቅ ሰው ወደ ክፍሉ ገባ፡፡
ፍራኒ ምንድነው የሆንሽው? አፍሽን ዝጊ! እንደ አምቡላንስ እኮ ነው እየጮህሽ ያለሽው። ታውቆሻል? እኔ ተረጋግቼ መስራት አልቻልኩም::” ብሎ
ከጮኸባት በኋላ ወደ ጉድማን ዞሮም “ምን ሆና ነው የምታለቅሰው? አንተስ
ማን ነህ?” ብሎ ጠየቀው፡፡
ጉድማንም የፖሊስ ባጅን አውጥቶ ሲያሳየው ሽማግሌው ባጁን በአይኑ
መርምሮ ምንም አይነት መገረም ፊቱ ላይ ሳያሳይ “የግድያ ወንጀል መርማሪ” ብሎ በቁጣ ድምፅ ጮሆ ተናገረና “ማን ነው የተገደለው? ፍራኒ ዝም በይ ብዬሻለው እኮ!” በሀይለኛ ድምፅ ሚስቱን ሲቆጣት “እርሶ ናታን ግሮልሽ ኖት መሰለኝ ባልሳሳት?” ብሎ ነገሩን ይበልጥ ለመቆጣጠር እና ይህንን ሀይለኛ ሽማግሌ እንዴት ሊያሳምነው እንደሚችል ውስጡን አዘጋጀ፡፡
“ልክ ነህ እኔ ናታን ግሮልሽ ነኝ! ግን አንተን ማን ልበል? አንተ ማን
ነህ የእኔ ጥያቄ?” ጉድማንም በድጋሚ የፖሊስ ባጁን ለሽማግሌው አሳየው፡፡
“እና? አንተ እዚህ እኔ ቤት የመጣኸው ለምንድን ነው?” ብሎ ግሮልሽ
ጠየቀ እና በማስከተልም “እኔ ሥራ የሚበዛብኝ ሰው ነኝ ታውቃለህ” አለው፡፡
ግሮልሽም አይኑን እያጉረጠረጠ “ለዚያ ነበር ማለት ነው ሚስቴ እንደ
አውሬ እያጓራች ያለቀሰችው? ስለ ብራንዶን ጠይቀሀት ነበር?”
“አቶ ግሮልሽ ልጅዎ የት እንደሚገኝ ሊነግሩኝ ይችላሉ?” ብሎ
በሽማግሌው የማመናጨቅ ንግግር እየተናደደ መምጣቱን በሚያሳይ ድምፅ
“አንዲት ወጣት ሴት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላለች። ልጅዎንም ከግድያው
ጋር በተያያዘ ምክንያት ለጥያቄ እንፈልገዋለን” አለው፡፡
“መልካም እንግዲህ በቀላሉ ልመልስልህ” አለ እና በትዕቢት ድምፅ
በማስከተልም “ብራንዶን ሞቷል” አለው፡፡ ጉድማንም ከሽማግሌው በሰማው
ነገር ግራ ተጋብቶ “ምን አሉኝ ይቅርታ?” አለችው። ምክንያቱም ስለ ብራንዶን የሞት ሁኔታ የሚገልፅ ወይንም መጥፋቱን የሚያሳይ ማስረጃ
ሊያገኝ ስላልቻለ።
“አደንዛዥ ዕፅ በብዛት በመውሰዱ ምክንያት ነው የሞተው” አለው እና
በማስከተልም “አንድ መሞቱን የተመለከተች ሴት ናት ከዚህ ወር በፊት
ለእናቱ በደብዳቤ ያሳወቀቻት፡፡ የሆነች ጓደኛው ነኝ ምናምን የምትል ሴት
ማለቴ ነው። ፍራንስ ደግሞ በፍፁም የእሱን ሞት ልታምን አልቻለችም፡፡
ስለሆነም ልክ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ እንደሚገኘው የጠፋው ልጅ ወደ ቤቱ
የሆነ ጊዜ ላይ ይመጣል ብላ ታስባለች።
“እንዴ! ከስምንት ወራት በፊት ልጅህ አደንዛዥ ዕፅ በብዛት ወስዶ ሞቷል ተብሎ አልነበረም እንዴ?” ጉድማን በግርምት ተሞልቶ ጥያቄውን
አቀረበ፡፡
“ለምን ብዬ ነው የማመለክተው?” ብሎ ናታን ባሮልሽ ትከሻውን ሰበቀ። በመቀጠልም “ማንን ነው የምጠይቀው? ይሙት አይሙት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ አየህ የኔ ልጅ በጣም የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኛ ነው እሺ? በቃ የማይረባ ውሸታም፣ ጥቅም የሌለው እና ህይወቱን ለዕፅ አሳልፎ የሰጠ ሰው ነው። ይሄ ደግሞ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ነገር ነው። የእሱን ሞት የሚያረዳኝ ደብዳቤ ከመምጣቱ በፊትም ነበር ልጄን እንደሞተ ያህል የቆጠርኩት፡፡”
“ዋው! ብሎ ጉድማን አሰበ እና በመቀጠልም “እንደዚህ አይነት ክፉ
አባት ያለው ማንኛውም ልጅ ቢሆን ቤቱን ጥሎ ከመጥፋት ወደ ኋላ አይልም ወ/ሮ ግሮልሽ የልጇን ሞት ያረዳት ደብዳቤ አሁንም በእጁ ይገኛል?”
“የለም አቃጥዬዋለሁ” ብሎ ሲናገር የሽማግሌው ግራጫማ አይን እያበራ
ነበር፡፡ “በመጀመሪያ ደረጃ ያቺ ሸርሙጣ ቫለንቲና ባደን የተባለች ሴት ለሚስቴ ፍራንሰስ ደብዳቤውን ማሳየት አልነበረባትም፡፡ ምክንያቱም እናቱ
ይህ ደብዳቤ ሊደርሳት በጣም እንደምትሰቃይ ማወቅ ነበረባት። አየህ እሷ ማድረግ የነበረባት ነገሩን አዳፍና ዝም ማለት ነበር” አለው፡፡
ነገሩን የሰማው ጉድማንም ተገርሞ “ቫላንቲና ባደን ማለት የዊሊ ባደን
ባለቤትን ነው?”
አዎ ልክ ነህ” አለው እና በመቀጠልም “አየህ ወ/ሮ ባደን የጠፉ ሰዎችን
የሚያፈላልግ የበጎ አገልግሎት ድርጅት አላት። ባለቤቴ ፍራንሰስም የልጃችን
ብራንዶንን መጥፋት ለድርጅቱ አሳውቃ ነበር መሰለኝ፡፡ ለዚያም ነው ወ/ሮ
ባደን የልጃችንን ሞት የሚያረዳውን ደብዳቤን ለባለቤቴ የሰጠቻት። እንግዲህ
ብራንዶንን ከሚገኝበት ቦታ ፈልገህ አግኘው እና ምርመራህን መቀጠል
ትችላለህ”.....
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ

#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....እንግዲህ ብራንዶንን ከሚገኝበት ቦታ ፈልገህ አግኘው እና ምርመራህን መቀጠል ትችላለህ”
“ይቅርታ አቶ ግሮልሽ ነገሩ እንደዚህ ቀላል አይደለም” ብሎ ሲናገር በሽማግሌው ፊት ላይ ባየው የንዴት ስሜት ተነቃቅቶ “ብራንዶንን በቀጥታ ከግድያው ጋር የሚያገናኝ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ውጤትን አግኝተናል፡፡ እርስዎ እንደነገሩኝ ከሆነ ደግሞ የብራንዶንን ሞት እርግጠኛ አይደሉም፡፡ ደብዳቤውንም ስላቃጠሉት ተጨባጭ ማስረጃ የለንም፡፡ እርስዎ ከተናገሩት ቃል በስተቀር ምንም ማስረጃ የለንም” አለ ጉድ ማን ኮስተር ብሎ
ሽማግሌው በተናገረው ነገር ማዘኑን በሚያሳብቅ ድምፀት፡፡
እሺ የተገደለችው ሴት ሥም ማን ነው?” ብሎ ናታን ግሮልሽ በረዥሙ ተነፈሰ፡፡ “ሊዛ ፍላንገን ነው ሥሟ” ጉድ ማን መለሰ፡፡
ይሄን ሥም ሰምቼ አላውቅም” ብሎ ግሮልሽ ትከሻውን ሰበቀ፡፡
የዊሊ ባደን ውሽማ ናት” ብሎ ጉድማን በማስከተልም “ትንሽዬ ዓለም ላይ ነው አይደል እየኖርን ያለነው?” አለው፡፡ ለአፍታ ያህል የናታን ግሮልሽ ፊት ላይ ግርምት ታየበት፡፡ ወድያውኑም ከመገረሙ ተመለሰ እና “ያን ያህል ዓለም ትንሽ አይደለችም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከዚህ በላይ ልረዳህ አልችልም፡፡ ምናልባትም የጠፉ ሰዎችን የሚያፈላልግ የበጎ አድራጎት
ድርጅትን የከፈተችው ቫለንቲና የተሻለ ታግዝህ ይሆናል። ልረዳህ ባለመቻሌ
ደግሞ በጣም አዝናለሁ ኢንስፔክተር። ወደድክም ጠላህም ልጄ ብራንዶን
በህይወት አይገኝም፡፡ አንተ ብታምንም ባታምንም እንግዲህ ስለ ልጄ
የማውቀውን ነገር ነው የነገርኩህ።” “ግን ለመጨረሻ ጊዜ ልጅህን ያየኸው
መቼ ነው? ጓደኞቹንስ ታውቃቸዋለህ? አደንዛዥ ዕፅ የሚያቀርቡለትንስ
ሰዎች? የት የት ቦታዎችስ ነው ደውሎ የነበረው?” ብሎ ጉድማን ተጭኖ
ጠየቀ፡፡
“ማናቸውንም አላውቃቸውም!” ብሎ ናታን ግሮልሽ በአጭሩ መለስ እና
በማስከተልም “ምናልባት እናቱ እነዚህን የዘቀጠ ህይወትን የሚኖሩትን የእሱን ጓደኞች ልታውቅ ትችል ይሆናል” አለው እና ንጭንጭ እያለ “ግን ያው ፍራንሰስን እንደተመለከትካት ጥያቄህን በእርግጠኝነት የምትመልስልህ
ሁኔታ ውስጥ አይደለችም። ይቅርታ የሜዳ ቴኒስ አለማማጄ አሁን እየመጣ
ነው እና ለመጫወቻ የሚሆነኝን ልብስ መቀየር አለብኝ” ብሎት ናታን ግሮልሽ ክፍሉን ለቅቆ ወጣ፡፡ ጉድማንም ለጥቂት ጊዜ ያህል ራሱን ሲያረጋጋ ቆየ እና ቅድም ወዳገኛት የቤት ሠራተኛ አመራ።
“የብራንዶን መኝታ ክፍል ድረስ ውሰጂኝ” አላት፡፡
እሷም ከአቶ ግሮልሽ ፈቃድ ውጪ ማንንም ሰው ወደ ማንኛውም የቤቱ
ክፍል ውስጥ ማስገባት ስለማትችል ጉድማን የጠየቃትን ነገር ልታደርግለት
አመነታች፡፡ ነገር ግን የፖሊስ ባጁን አውጥቶ የብራንዶንን ክፍል
እንድታሳየው ትዕዛዝ አዘል በሆነ ድምፅ በድጋሚ ጠየቃት። ስለሆነም ፎቁ
ላይ ወደ ሚገኘው የብራንዶን መኝታ ክፍል ጉድማንን ይዛው ሄደች። እና
ክፍል ውስጥ ብቻውን ጥላው ሄደች፡፡
ጉድማን የገባበት የብራንዶን መኝታ ክፍል ትልቅ እና በደማቁ ያሸበረቀ
ነው። የክፍሉን ሁኔታ አይቶም ውስጡን የሀዘን ስሜት ተሰማው። የሞቀ
ህይወት፣ ትልቅ የዋህነት እና ተስፋ እንዲሁም ደግሞ የብራንዶንን ቆንጆ
ልጅነት እዚህ ክፍል ውስጥ ነበር። እዚህ ክፍል ውስጥ ያሉት የብራንዶንን
ቆንጆ የልጅነት መገለጫዎቹን ነው እንግዲህ አደንዛዥ ዕፅ የነጠቀው።
ወንበሮቹ በኳስ ቅርፅ ነው የተቀመጡት። ግድግዳው ላይ የላምበርጊኒ መኪና
ፎቶዎች በዋና እና በካራቴ ያገኛቸው ዋንጫዎች በአሜሪካ እግር ኳስ
ትላልቅ ተጫዋች ዙሪያ የተፃፉ መፅሀፎች እንዲሁም ደግሞ ስለ ውሃ ምርምር የሚያወሱ መፅሀፍትም ሞልተውታል። የአልጋ ልብሱ ላይም በጣም ትልቅ የ B ፊደል ታትሞበታል። “ይሄ ሁሉ መልካም ነገር የት ሄደ?” የሚል ድምፅ ጉድማንን ወደ ኋላው እንዲዞር አደረገው። ዞር ብሎም ሲመለከት የብራንዶን እናት በሩ ላይ አይኗ በልቅሶ ብዛት ዙሪያውን አብጦ
አገኛት፡፡
“ብራንዶን ኮምፒውተር ወይንም ስልክ ነበረው?” ብሎ ጉድማን ጠየቀ።
አንገቷን ከፍ እና ዝቅ እያደረገች “
ሁለቱም ነገሮች ነበሩት። ግን ያው
የሱስን ገንዘብ ለማሟላት ከቤት ከመጥፋቱ በፊት ሸጧቸዋል።” ብላ ባዶነት በሚታይበት ሁኔታ የልጇን ክፍል በአይኗ መቃኘት ጀመረች።
“ምናልባት ሌላ ስልክ ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ..” አላት እና በማስከተልም “ወሮ ግሮልሽ ባለቤትሽ ብራንዶን እንደሞተ ነው
የሚያምነው። እሱ እንደሚለው ከሆነ ደግሞ ስለ ሞቱ የሚያረዳ ደብዳቤ..."
ብሎ ሊቀጥል ሲል ወ/ሮ ግሮልሽ ጣልቃ ገብታ “በእሱ እንኳ እርግጠኛ አይደለንም” ብላ ከመዳፉ ላይ ውሀ ያለበት እና ለመጥረግ ይመስል መዳፏን
ከታፋዋ ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ በጭንቀት ጠረገች። በማስከተልም “ደብዳቤው
ላይ ምንም አይነት ማህተም የለበትም፡፡ ስህተት ይመስለኛል” አለችው፡፡
“ግን ደብዳቤ ደርሷችሁ ነበር አይደል?” ብሎ ሲጠይቃት ጭንቅላቷን ወደ ላይ እና ታች በመነቅነቅ አዎንታዋን አሳየች፡፡
“ወ/ሮ ባደን ላንቺ ያስተላለፈችው ደብዳቤ?”
አዎን “አለች” እና በማስከተልም ከቅድሙ በሚያሳዝን ድምፅ
“ኢንስፔክተር ምናልባት ልጄ ሞቶ ሊሆን ይችላል። ያን ያህልም ደደብ አይደለሁም አየህ በፊት ላይ ቢያንስ በሳምንት ሁለቴ ሦስቴ ወይም ለአራት ጊዜ ያህል ይደውልልኝ ነበር። ግን ከባለፈው ክረምት ጀምሮ እሱዐእኔ ጋር መደወሉን አቋረጠ” አለች እና ማልቀስ ጀመረች፡፡
“ግን በቃ ወላጅ እንደመሆኔ መጠን ሬሳውን እስካላየሁ ድረስ በፍፁም
ልጄ ሞቷል ብዬ አላምንም። መቼም ደግሞ በእሱ ጉዳይ ላይ ተስፋ
አልቆርጥም። ይገባሀል የምልህ?”
“አዎ ይገባኛል።” ብሎ ጉድማን መለሰላት እና “ለዚያም ብለን ነው እኮ ብራንዶን ላይ ምን እንደደረሰበት ለማወቅ ብዬ ረዥም ርቀት የመጣሁት።
ለማንኛውም በምርመራችን ላይ ስለ ብራንዶን መርምረን የደረስንባቸው
ነገሮችን ሁሉ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩም ቢሆን ማወቅሽ አይቀርም።”
ሲላት የተስፋ ፊት ፊቷ ላይ ታየባት፡፡
“ከቤት ከወጣ በኋላ አዋቂ ሰዎችን ያገኝ ነበር። ምናልባት መምህሮቹን? የስነ አዕምሮ ባለሙያ? ወይንም ደግሞ ሀኪምን?” ብሎ ሲጠይቃት ወ/ሮ
ግሮልሽ በረዥሙ ተነፈሰች እና “ብራንዶን መምህሮቹን አይወድም ነበር። በእርግጥም ብዙ ቴራፒስቶች ነበሩት። ግን የትኞቹን ያግኝ ወይንም አያግኝ
አላውቅም።”
ይሄኔም አንድ ሀሳብ ብልጭ አለለት እና “ዶ/ር ኒኮላስ ሮበርትስ የምትባል ቴራፒስት ጋር ህክምና ይወስድ ነበር?” ብሎ ጠየቃት።
ፍራንሰስም ግንባርዋን ከስክሳ ስታስብ ቆይታ ራስዋን በመነቅነቅ
“አይመስለኝም፡፡ ይህንን ስም ሰምቼው አላውቅም።” ብላ በማስከተልም
“ግን በምን ጉዳይ ላይ ነው የወንጀሉ ምርመራን የምታካሂደው?” ብላ
ጠየቀችው:: ጉድማንም ይህቺን በልጇ መጥፋት ሳቢያ ልቧ የተሰበረ እናትን
ልጇ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተጠርጣሪ መሆኑን መንገር ጭካኔ መሰለው።
“እስከ እሁን በግልፅ ስለ ነገሩ በትክክል አላወቅንም” ብሎ የቢዝነስዐካርዱን ከሰጣት በኋላም “ግን በቃ ለምርመራችን የሚጠቅም አንድም የተለየ ነገር ስለ ብራንዶን ካስታወስሽ ደውይልኝ።” አላት እና ተሰናብቷት ከቪላቸው ወጣ፡፡
ከግሮልሽ ቤተሰብ ጋር ያደረገው ጉብኝት ትንሽ ስሜቱን በርዞታል።ለማንኛውም ከዛሬ የምርመራ ውሎው በመነሳት እሱ እና ባልደረባው ጆንሰንዐበፍጥነት ሁለቱን ባደኖች ማናገር እንዳለባቸው ውሳኔ ላይ ደርሷል።ከቤታቸው እየነዳ ከወጣ በኋላ ከግሮልሽ መኖሪያ ቤት ይዞት የወጣው
የተመረዘ ስሜቱ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት

👍2❤1
ከጀርባው ላይ ለቀቀበት።
ምስኪን ብራንዶን!
ከእነዚህ የግሮልሽ ቤተሰብ የወጡ ልጆች ናቸው እንግዲህ አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም የሚለምዱት ምንም አይነት የገንዘብ ክምችት እንግዲህ ፍቅርን ሊተካ አይችልም፡፡ ለልደት ተብለው ከጎረቤት ቤት ላይ የተሰቀሉ ፊኛዎች እየተመለከቱ
ቤቱን አልፎ ሲሄድም
ቀየተሰቀሉትን ፊኛዎች እየተመለከተ ቤቱን አልፎ ሲሄድም 'መልካም ዕድል
ራየን፤ ይህ ዕድልህ ደግሞ በእርግጥም ያስፈልግሀል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ትሬቮን! ትግራይ!”
ብላ ልጇን የምትጠራው ማርሻ ሬድሞንድ የባለ አንዱ ህንፃ ቤት ውስጥ በጣም አስተጋባ፡፡ ቤታቸው ዴንከር መንገድ ዳር ላይ ነው የሚገኘው። ማርሻ ወደ እዚህች ቤቷ ከነልጇ እና ከእናቷ ኮሬታ ጋር ከተዛወረች ሁለት ዓመት አልፎታል፡፡ ወደዚህኛው ቤታቸው የመጡትም በፊት ይኖሩበት የነበረው ቤታቸው ዌስትመንት ውስጥ በሚገኘው አንድ የወሮበላ ቡድን በማርሻ መስኮት በኩል በተወረወረ በነዳጅ በተሞሉ ጠርሙሶች በተሰሩ ተቀጣጣይ ቦምብ ሙሉ በሙሉ ቤታቸው ከነደደ በኋላ ነበር። በሚገርም ሁኔታ ግን
ቤታቸው ሊነድድ የቻለው ካለምንም ምክንያት ነበር፡፡
ያኔ ታዲያ መላው ቤተሰብ ማለት ይቻላል በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ ነበር። ትሬቨን ዕፁን ያዘዋውርም፣ ይጠቀምም ነበር በጊዜው። ከዚያን ጊዜ በኋላ ግን በጣም ጥሩ የሚባሉ ነገሮች በህይወታቸው ውስጥ ተከናውኖ አልፏል። ወደ እዚህ ቤት ተዘዋወሩ፡፡ ትሬይም ከአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት ነፃ ሆኗል፡፡ሥራም ጀምሯል። የሬይሞንድ ቤተሰቦች ደግሞ ዶ/ር ደግላስን ሊያገኝ በቅቷል እግዚያብሔር ነፍሱን በገነት ያኑራት። የባለቤቷ ዶ/ር ኒኪ ህይወትንም ይባርክ፡፡ አንድ አንዴ ማርሻ እግዜአብሔር ሥራውን እውነትም
በስውር እንደሚሰራ ታሰባለች።
“ትሬይ!” ብላ ልጇ መኝታ ክፍሉ ውስጥ ከሚያስጮኸው ዘፈን ድምፅ
በላይ ጮክ ብላም “አንድ ጥቁር እንግዳ ሊያይህ ይፈልጋል!” ብላ ተጣራች።
ልጇ ጥሪዋን ስላልሰማም ሀዶን ዶፎ ኮሪደሩ ላይ እንደቆመ የትሬይ እናት ወደ ልጇ ክፍል ሄዳ ልጇን ይዛ ስትመለስም በፈገግታ ታጆቦ ነበር የጠበቃቸው፡፡ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ለመድረስ እና ከዕፅ ተጠቃሚነት ነፃ ለመሆን ትሬይ ሬድሞንድ ምን ያህል እንደተጓዘም አሰበ። ያኔ ከባልደረባውዐዶ/ር ዶውግ ጋር የዕፅ ማገገሚያ የበጎ ፈቃድ ክሊኒካቸው ውስጥ ትሬይን ሲያገኙት እንደዚህ አልነበረም፡፡ ያኔ በጣም ቀጫጫ፣ ሞጌው የወጣ፣ አይኑ በተስፋ መቁረጥ የፈዘዘ እና ሰውነቱ ላይም በጣም ብዙ የመርፌ ቁስል ይታየበት ነበር፡፡ ከሆድ በስተቀር በእዚህ ልጅ ህይወት ላይ ምን ያህል ተለፍቶበት ከአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት ነፃ መሆን እንዳስቻሉት ደግሞ ማንም አያውቅም፡፡
“እንዴ! ሰውዬው!” ብሎ ትሬይ አምስት ጣቶቹን አጋጭቶ ሰላምታ ተለዋወጡ።
“እንዴት ይዞሀል ባክህ?”
“ጥሩ ነኝ” አለ ሀዶን በእርግጥም በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ዛሬ ምን እግር ጣለህ?” ብሎም ጠየቀው፡፡
“እዚህ አካባቢ ስለነበርኩኝ ነው” አለው እና ሲጠቅሰው ጊዜ ተያይዘው ሳቁ።
ዌስትሞንት ሀዶንን ለመሰሉ ሰዎች የጉርብትና ቦታ ሊሆን እንደማይችል ሁለቱም ያውቁታል። ይህ ሀዶን ዶፎ የተባለው ሰው ከዶ/ር አባት እና የካሊፎኒያ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ፕሮፌሰር ከሆነች እናቱ ተወልዶ ያደገው ብሬንትውድ ውስጥ ነው፡፡ ምንም እንኳን ትሬይ እና ሀዶን ዶፎ በቆዳ ቀለማቸው ጥቁር ቢሆኑም አስተዳደጋቸው ለየቅል ነበር። በሮበርት እና ዶፍ አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚነትን ለመፈወስ በበጎ አገልግሎት ክሊኒክ ውስጥ የሚታከሙ ጥቁር አሜሪካውያን ህፃናትን የሚረዳ፣ የተማረ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ስኬታማ ሰው በመሆኑ እንዲሁም ደግሞ ከነጮችም በላይ የሚዝናኑባቸው ነገሮች ስለሚያስደስቱት 'ኦባማ' የሚል ስም አውጥተውለት ነበር። በተለይ ደግሞ ለክላሲካል ሙዚቃዎች እና በ1920ዎች ላይ የተሰሩትን ድምፅ አልባ ፊልሞችን ማየት በጣም ያስደስተዋል። ለምሳሌ
ያህል ሀደን ዶፍ የቻርሊ ቻፕሊንን ሁሉንም ፊሊሞች ዝርዝር ሳይሳሳት ይነግርሀል የቱፓክን ግጥሞች ግን አንዱንም አያውቀውም:: በተቃራኒው ደግሞ ትሬይ የተወለደው ከጠንካራዋ እናቱ ማርሻ ሬይሞንድ እና ጥሏቸው ከጠፋው አባቱ ቢሊ ጀምስ ነው።
ትሬይ ሀዶንን ወደ አንድ ትንሽ ክፍሉ ይዞት እየገባ “እውነት ምን እግር ጣለህ? በሰላም ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡
ሀዶንም የትሬይ ትከሻ ላይ እጁን አሳርፎ “ሁሉም ሰላም ነው ትሬይ።
በቃ ሰላም መሆንህን ለማረጋገጥ ነው እዚህ የመጣሁት። ደግሞም ዶውግ
በህይወት ቢኖር ኖሮ ይህንን ያደርግ አልነበር እንዴ?” ብሎ መለሰለት፡፡
በእርግጥም ደግሞ ዶ/ር ዶውግ የትሬይ ቤተሰብ ተወዳጅ እና በጣም የሚከበር ሰው ነበር እና በሀዶን ሀሳብ ተስማማ፡፡
“ሥራ እንዴት ነው? ኒኪስ እንዴት ናት?” ብሎ ሀዶን ጠየቀው፡፡
“ማለትህ ከግድያው በኋላ ነው?” መለሰ ትሬይ፡፡ ሀዶንም ፊቱን ኮስተር አድርጎ “የምን ግድያ ነው ደግሞ?”
“እንዴ! ስለ ግድያው አልሰማህም? በዜናዎች ላይ ሁሉ ስለ ግድያው
ነው የሚወራው” አለው እና ትሬይ ስለ ሊዛ ፍላንገን ግድያ እና ዶ/ር ኒኪን
ሊመረምሩ ከሎስ አንጀለስ ፖሊስ ዲፓርትመንት ስለመጡት የግድያ
መርማሪ ቡድን ፖሊሶችም ነገረው።

❤1👍1
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
...የተወለደው መሃል መርካቶ ነው። የት እንዳደገ ለመናገር ግን እሱም ይቸገራል፡፡ በተወለደ በዓመቱ አባቱ ሲሞቱ እናቱ የአራት አመት ታላቅ ወንድሙንና እሱን ይዘው ቤትሰቦቻቸው ጋ ደብረማርቆስ ገቡ ማርቆስ ብለው ስም ያወጡለትም እዚያው የነበሩት ሴት አያቱ ነበሩ፡፡ወላጅ
እናቱም ብዙ ሳይቆዩ 'የአምስት ዓመት ልጅ ሳላ ሞቱበት፡፡ አዲስ አበባ የነበሩት የእናቱ ታላቅ ወንድም እሱንና ወንድሙን መልሰው አዲስ አበባ ሊያሳድጓቸው ወሰዷቸው:: እኝሁ አጎቱ በስድስተኛው አመት ለሥራ ተቀይረው ወደ ድሬዳዋ ሲሄዱ እሱና ወንድሙም ተከተሉ፡፡ ያኔ አስራ አንደኛ አመቱን ይዞ ነበር፡፡
አጎቱ ኣምስት ዓመታት ድሬዳዋ ውስጥ አገልግለው በጡረታ ሲገለሉ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ ወንድማማቾቹን ይዘው። የታከተሉትን ሶስት አመታት አዲስ አበባ ውስጥ ቆየና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን
እንዳጠናቀቀ በአስራዘጠኝ አመቱ ሐረር ሄዶ የጦር መኮንንነት ስልጠናውን
ጀመረ፡፡ ያን ጊዜ ታላቅ ወንድሙ በዚያን ጊዜው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሁለተኛ ዓመት የህግ ተማሪ ነበር፡፡
ማርቆስ በትምህርቱ እጅግ ጥሩ ውጤት እንደነበረው የሚያውቁ ሁሉ ትምህርቱን ዩኒቨርስቲ ገብቶ እንዲቀጥል ቢገፋፉትም የእርሱ ምርጫ ሌላ ነበር፡፡ አጎቴ ወታደር ይሁን አስተማሪ ዳኛ ይሁን ኣናጢ ግድ
ኣልነበራቸውም፡፡ ዋናው ነገር ሥራ ይዞ .. ራሱን መቻሉ ነበር የሚያሳስባቸው:: ያ ነበር በሰማይ ቤት የሚያስጠይቃቸው፡፡
ሐረር የጦር ትምሀርት ቤት የወታደራዊና የቀለም ትምህርቱን በከፍተኛ ማዕረግ አገባደደ:: በመጀመሪያ ማስተማር ልቡ ባይፈቅደውምዐተሰጥኦውን የተገነዘቡ መምህራነና የማሰልጠኛው ባለሥልጣን አባብለውትናዐገፋፍተውት የተማረበት ማስልጠኛ ረዳት መምህር ኣድርገው ቍጠሩት፡፡
አመቱ የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ከሰለሞን ሥርወ መንግሥት ሥልጣን ለመረከብ ሽርጉድ የሚልበት ፤ ተማሪዎችና ምሁራን ሠራዊቱን የጎሪጥ እያዩ በፈንታቸው ወገባቸውን ያጠባበቁበትና ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ በመጪው
ሶሻሊስታዊ ገነት በአንድ ምሽት ባለመኪናና ባለቤት ሊሆን ተስፋ ያደረገበት፤አለም ፊቷን ወደ ኢትዮጵያ መልሳ ትንፋሽዋን የያዘችበት ዓመት ነበር
1966 በኢትዮጵያውያን ኣቆጣጠር፡፡
በተከተሉት አራት አመታት ውስጥ በሕይወቱ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ
አንኳሮች ተከታትለው አለፋ፡፡ ሚስት አገባ፡፡ በአመቱ ወንድ ልጅ ወለደ፡፡
በ1978 ሙሉ ኮለኔል ሆነ፡፡ በ1981 ጥር ላይ ጋሼ' እያለ የሚጠራቸው እንደ
አባት ያሳደጉት አጎቱ ሞቱ፡፡ በዛው ዓመት ግንቦት በኢትየጵያ ተደርጎ በነበረው የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ውስጥ እጁ ገባ፤ ሁሉ ነገር አበቃ፡፡
በመንግሥት ግልበጣ ንቅናቄ ውስጥ የገባው በአንድ ወቅት አስተማሪው በነበረው በኋላም በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ አለቃው ሆኖ በሰሠራው ብርጋድዬር ጀነራል አብይ ሰናይ ገፋፊነት ነበር፡፡ የሃሣቡንዐትክክለኛነት ከጅምሩ ቢቀበለውም የግልበጣው ተካፋይ ለመሆን ብዙም አልዳዳውም፡፡ ሆኖም ከሁለት ወር የአለቃው ውትወታ በኋላ ከጊዜው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እራሱን ማግለል እንደማይችል በመረዳት ራሱን ሰጠ፡፡
በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ የመንግሥት ግልበጣው ቀንደኛ ተዋንያን
ከነበሩት መሃል ራሱን አገኘው፡፡
በወቅቱ በአዲስ አበባና በአሥመራ ተራርቀው የነበሩት የመፈንቅለ
መንግሥቱ ጠንሳሾች ተከታታይ ዕቅዶችን እያወጡ በተለያዩ ሳንካዎች
የተወጠነው መፈንቅለ መንግሥት ቢዘገይም በመጨረሻ ግንቦት ላይ
አብዛኛው ኢትጵያዊ ሳያስብና ሳይገምት ክብሪቱ ተጫረ፡፡
የተወለካከፈው መፈንቅለ መንግሥት በኣሥመራ ለቀናት በአዲስ ደግሞ ለሰዓታት ሲንገዳገድ ቢቆይም ኮለኔል ማርቆስ ዕቅዱ ገና ጠዋት በአምስት ሰዓት እብዛኛዎቹ የመንፈንቅለ
መንግሥት ጠንሳሽ ጄነራሎች በመሀል አዲስ አበባ መከላከያ ሚኒስቴር
ቅጥር ግቢ ውስጥ በተሰበሰቡበት በታማኝ የመንግሥት ሃይሎች በታንክ
ሲከበቡና የኣንዳንድ የንቅናቄውን ኣባላት ክህደት እንደተረዳ ነበር፡፡
ጊዜ አላጠፋም፡፡ ከበባው ከመግጠሙ በፊት ከግቢው ሹልክ ብሎ ወጣ፡፡ ከዚያ በኋላ ያደረገው ግን ለእርሱ ለራሱም እንቆቅልሽ ነው፡፡ እጁዐንጹህ እንደሆነ ሁሉ ወደ ቤቱ ተመልሶ ሲቀመጥ በእርግጥ እተርፋለሁ ብሎ እንዳልነበር ግልጽ ነበር፡፡ ባለቤቱንና ልጁን ትቶ ጨክኖ ከኣገር ለሙጥፋት ቢሞክር ምናልባት ይሳካለት ነበር፡፡ ኮሎኔል ግን ያንን አልመረጠም፡፡ ከቤቱ ተመልሶ ይጠብቀኛል ብሎ የፈራውን ስቃይና ውርደት ላለመቀበል በምትኩ
የመጨረሻውን መራራ ጽዋ ለመጨለጥ ወሰነ፡፡
ማዕረጉን ገፈው ስሙን በድምጽ ማጉያ እየጠሩ ወጥቶ እጁን እንዲሰጥ ያለበለዚያ ግን እንደሚደመሰስ ሲዝቱ ከቆዩ ሰኋላ ከምሽቱ ለሁለት ሰዓት ሃያ
ጉዳይ ላይ መጠነኛ የሽፋን ተኩስ ኣስቀድመው የግቢውን የአጥር
በር ገርስሰው ከሰፊ ግቢው ሲፈሱ ዙሪያው በአንድ አፍታ በፈንጅ ነበልባል
ጋየ፡፡ በተኩስ ልውውጥ ሚስቱና ልጁ ተገደሉ፡:፡ ራሱን ለመግደል ሞክሮ
ቆሰለና ተያዘ፡፡
እራሱን ሲያውቅ፡፡ ሆስፒታል አልጋ ላይ ነበር፡፡ ግማሽ ፊቱ በፕላስተር ታሽጓል። ሁኔታውን ሲያገናዝብ መልሶ ራሱን ሳተ፡፡ የዚያ ቁስል ውጤት ፊቱ ላይ ጠባሳ ትቶበት አልፏል፡፡
ከሃኪም ፡ ቤት እንደወጣ ወደእስር ቤት ወሰዱት። - ግድ አልነበረውም። በ1983 ግንቦት ላይ የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ ከእሥር ቤት ተፈቶ ካናዳ ሄደ፡፡
ካናዳ ከወንድሙና ከሜክሲካዊ ሚስቱ ጋር የቆየው ለአራት ወራት ነው፡፡ በአራተኛው ወር በአንድ የህፃናት ሆስፒታል በአፅጅነት ተቀጥሮ
ሁለት ክፍል. አፖርታማ ተካራይቶ ወጣ፡፡ የአፅጅነት ሥራውን ያልወደደለት
ወንድሙ ታክሲ ገዝቶ ሊሰጠው ሲጠይቀውም ማርቆስ ፈቃደኛ አልነበረም::ለእርሱ ሕይወት እራሷ ትርጉም አልነበራትም። ማግኘትና ማደግ ሃብትና ክብር ለእሱ የቂል ጌጦች ነበሩ፡፡ በዛን ወቅት የእርሱ ምኞት ያለፈውን ሁሉ
ባለበት ትቶ የተቀሩትን ዓመታት በአንድ የዓለም ጥግ ድምጽ ሳያሰማ ማሳለፍና ድምፅ ሳያሰማ ማለፍ ነበር፡፡ ሩጫና ትግል ለእሱ የተሰበረ መንፈስ የሚመች አልነበረም፡፡ ያንን ነበር የፈለገው:ጸጥታ፡፡
ካናዳ በገባ በሁለተኛው ዓመት ከአዲስ አበባ ተነስቶ እሱን ፈልጎ እቤቱ ድረስ የመጣው እንግዳ ግን ይዞለት የመጣው ጸጥታ አልነበረም::
ማርቆስ የሁለት ክፍል አፓርትመንቱን የተላላጠ የእንጨት በር ከፍቶ ሲመለከት መተላለፊያው ላይ ቆሞ የሚያየው ሰው በቅዠቱ እንደሆነ አልተጠራጠረም፡፥ እንግዳው “ማርቆስ” ብሎ በተከፈተው በር ገብቶ አቅፎ ሲስመው ሁኔታን እውነት ነው ብሎ ለመቀበል ተቸገረ፡፡
በ 1981 የመፈንቅለ መንግሥት ጠንሳሾች መሃል ከመያዝ፣ከመታሰርና ከሞት ካመለጢች በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች መሃል የገዛ እራሱን አለቃ ብርጋዴል ጀነራል አብይ ሰናይን በዛች ትንሽ ክፍሉ ሲያየው ማመን
አቃተው::
ያለፋትን በርካታ ዓመታት በስደት ያሳለፈወ ኣለቃ ከእርሱ በእጅጉ በተሻለ ሁኔታ ላይ እንዳለ ግልጽ ነበር፡፡ አለቃው ዞር ዞር ብሎ የማርቆስን የተላላጠች፣ የተጋጋጠች ክፍል አየና “ እዚህ ነው የምትኖረው…?” አለ የተሻለ ነገር መናገር ያቃተው ይመስል፤ ድንገት እንባ
ያቀረሩትን አይኖቹን በማርቆስ ላይ ተክሎ፡፡ ለአንድ አፍታ ሳይናገር
በዝምታ የቆመውን ማርቆስን ትክ ብሎ ሲመለከት ቆየና የጠፋ ወንድሙን
እንዳገኘ ሁሉ መልሶ ተጠመጠመበት፡፡
ለሰዓታት ቁጭ ብለው አወጉ፡፡ በመጨረሻ ብርጋድየር ጀነራሉ
እሱን ፍለጋ እስከ አለም ጥግ የተጓዘበትን ምክንያት ሲገልጽለት ማርቆስ ፈገግ ብሎ ተመለከተው፡፡
: “ጀነራል እኔ እኮ ሙት ነኝ፡፡” አለ ማርቆሥ ባጭሩ

👍1
።
“ማርቆስ አድምጠኝ” አለ ጀነራሉ ከተቀመጠበት ተነስቶ ከማርቆስ
ጎን እየተቀመጠ፡፡ “እያንዳንዳችን ያምንወዳቸውን አጥተናል፡፡ . እርግጥ
በአሳዛኝ አጋጣሚ ውስጥ እንዳለፍክ ይገባኛል፤ ግን ለሆነው ነገር እራስህን
ተጠያቂ ማድረግ የለብህም..”
የተከተሉት ሶስት ሳምንታት ኮለኔል ማርቆስ ከቀፎው ላለመውጣት
ብርጋድዬር ጀነራሱ ደግሞ ቀፎውን ለማፈራረሥ ሲታገሉ ቆዩ፡፡ በመጨረሻ
ማርቆስ ለሁለተኛ ጊዜ ተሸነፈ::
ነገርኩህ ማርቆስ…ይህች ዓለም መጥፎም ጥሩም የምትሆነው በእኛ
ተግባር ነው፡፡ የተሳሳተ ነገር ካለ ያንን የማስተካከል ኃላፊነት የኛው ነው::
ሌላ ማን ይደርስልናል...?”
“ከእኔ የሚጠበቀው ምንድነው?” አለ ማርቆስ አለቃውን አቋርጦት፡፡
“ወደ አዲስ አበባ ትመለሳለህ፡፡ ለጊዜው በአፍሪካ ሠላም አስከባሪ ግብረኃይል የምሥራቅ አፍሪካ ክንፍ የቡድን ለ ወታደራዊ ደህንነት ኃላፊ ሆኜ ነው የምሠራው፡፡ ረዳቴ እንድትሆን ነው የምፈልገው::”
በሁዕተኛው ወር ኣዲስ ኣበባ ተመለሰ፤ ማርቆስ።
የአፖርታማው የፊት በር ሲንኳኳ የመታጠቢያ ቤቱን መብራት አጠፋና ወደ ሳሎን ገባ፡፡ ከጠረጴዛው ላይ ያስቀመጠውን ሽጉጥ አንስቶ ወደ በሩ ሄዶ ቁልፋን አዘሮ በሩን በቀጭኑ ከፍቶ ተመለከተ፡፡
ፒተር ነበር፡፡ ፒተር ኦዱዋ በአንድ ወቅት በኬንያ መንግሥት ወታደራዊ ደህንነት ውስጥ የነበረና በአሁኑ ወቅት ለኮሌኔል ማርቆስ በረዳትነት የተመደበ ፤ የቁመቱ እርዝመትና የትከሻው ስፋት አስፈሪ ገጽታ
የሰጡት ሰው ነው፡፡
“ሰዓቱ ደርሷል…” እለ ፒተር እጆቹን ከለበሰው ረጅም የስራ የዝናብ ልብስ ኪሶች ውስጥ እንደከተተ፤ ጥያቀ ይሁን ዓረፍተ ነገር ባልለየ አነጋገር፡፡
“ጨርሻለሁ::” አለ ማርቆስ ወደ ሳሎኑ ተመልሶ ጥቁር የቆዳ ጃኬቱን አጠለቀና ሽጉጡን በጀርባው ሽጦ ፒተርን ተከትሎ ከክፍሉ ወጡ፡፡
“የመጀመሪያውን አሳ አግኝተወታል፡፡” አለ ፒተር ከፊት ለፊት የአፓርታማውን ደረጃ እየወረደ::
ማርቆስ መልስ ሳይመልስ ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት
ይላል ሰዓቱ፡፡ በረጅሙ ተነፈሰና ምንም ሳይናገር ፒተርን ተከተለው:: የአፓርትመንቱን የፊት በር ከመውጣታቸው በፊት ብን ብን የሚለውን
ዝናብ ሲመለከት የቆዳ ኮቱን ኮሌታ ወደላይ ቀለበሰና ሲጋራ ፍለጋ የደረት
ከሱ ውስጥ ገባ፡፡
ህሊናው ሊያርፍሰት አልቻለም፡፡ በሱ አመለካከት ግድያውን መፈጸም ፍጹም ወቅታዊ ኣይደለም፡፡
“ይቅርታ አድርጉልኝና… ለጊዜው የውጭ ጉዳዩ ሰው መገደል ቢዘገይ እመርጣለሁ” ነበር ያለው፡፡ በዛኑ ቀን ከሰዓት በአሥር ሰዓት ላይ በተደረገው የምሥራቅ አፍሪካ ደህንነት ቡድን ስብሰባ ሁለት ሪፖርቶች ከቀረቡ በኋላ ኮሎኔል ሃሳቡን ሲሰጥ፡፡ በክፍሉ ውስጥ የተሰበሰቡት ባለሥጣናት በአንድ አፍታ ከራሳቸው ጋር ሙግት ያዙ፡፡ ወዲያው በስተቀኝዐየተቀመጠው የአጥቂ ስለላ ኃላፊ የሆነው የኬንያው ሰው ዣክ ዊልያም የያዘውን እስክሪፕቶ በፊቱ ካለው ፋይል ላይ አስቀመጠና ጥያቄው ኮ” አለ
በተቀመጠበት ወንበር ላይ ወደኋላ እየተደገፈ “ጥያቄውኮ የመረጃው ቤት
ሰው ለውጭ ጉዳዩ ምን ያህሉን ምስጢር ገልጾለታል የሚለው ነው፡፡ እኔ የምፈራው የሚያውቀውን ሁሉ ዘክዝኮላት ከሆነ ማንኛቸውንም ቢሆን ማቆየቱ በኋላ ልናርመው ከማንችለው ስህተት ውስጥ ይከተናል ብዬ ነው::”
“ከቤት ከመውጣታቸው በፊት…” አለ በስተግራ የተቀመጠው ሩዋንዳዊ ሻለቃ ኣንድሬ ኦማሪ፡፡ በንቅናቄው የእዝ ሠንሠለት ከብርጋዴር ጄነራል አብይ ስናይ ቀጥሎ የበድን የፀጥታ ክፍልን የሚመራ ሰው ነው፡፡ “…የተነጋገሩት ቅጅ ነው ለጊዜው በእጃችን የሚገኘው:: ቢሆንም
ከዝርዝር ነጥቦች አገነባቡ ስንሰሳ እያንዳንዱን ነጥብ ዘክዝኮ ሳይነግረው
የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ሆኖም ኮሎኔል ማርቆስ እንዳለው ለጊዜው የመረጃው ሰው ብቻ እንዲወገድ ተደርጎ የውጭ ጉዳዩን ሰው በቋሚ ክትትል…”
“እዚህ ላይ ተቃውሞ አለኝ!” አለ ኬንያዊው ዣክ ዊልያም
“ስላቋረጥኩህ ይቅርታ አድርግልኝ፡፡ ነገር ግን እያንዳንዳችሁ ልትገነዘቡት የሚገባችሁ ነጥብ ስህተት ለመፈጸም ጊዜ እንደሌለን ነው፡፡”
ክርክሩ ለበርካታ ደቂቃዎች : ሲካሄድም የመጨረሻው ውሣኔ የኮሎኔልን ህሊና የረበሽ ነበር።
“. “ጥሩ..” አለ ብርጋዴር ጀነራል አብይ ሰናይ “ዝርዝር ነጥቦችን አንስተን የተከራከርን ይመስለኛል፡፡ ሆኖም ከኮሎኔል : ሰስተቀር የቀረነው
የተስማማንበት ነጥብ የሁለቱም ሰዎች መወገድ ምናልባት ዘግይቶ ሊጸጽተን
ከሚችል ስህተት ሊያድነን እንደሚችል ነው፡፡ የመረጃው ሰው ካዛንቺስ ያለችውን ሴት ለማግኘት መሞከሩ በራሱ ሰውየው ምን ያህል አደገኛ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ነው፡፡ የውጭ ጉዳዩን ሰው በተመለከተ ምንም እንኳን ሰውየው ጠለቅ ያለ እውቀት ባይኖረውም ምናልባት ካገኛቸው ጥቃቅን ነጥቦች ተነስቶ ችግር ሊፈጥር የሚችል ነው፡፡ ስለዚህ…” .
ኮለኔል ስብሰባው ተበትኖ ከክፍሉ ሲወጣ ህሊናው እየተረበሸበት ነበር፡፡

👍2
#ቀጥረሽኝ....ፈላስፋ አደረግሽኝ
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ሊስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!
በላይ በቀለ ወያ
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ሊስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!
በላይ በቀለ ወያ
👍1
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
...ሊመረምሩ ከሎስ አንጀለስ ፖሊስ ዲፓርትመንት ስለመጡት የግድያ
መርማሪ ቡድን ፖሊሶችም ነገረው።
“ሊዛ የዶ/ር ሮበርትስ ታካሚ ነበረች።”
“በሰዎች ተገድላ መንገድ ላይ ተጥላ ያልካትን ልጅ? ማለትም የዊሊ ባደን ውሽማ (ቅምጥ) ማለትህ ነው?” ብሎ ሀደን ተደንቆ ጥያቄውን አቀረበለት።
“አረ ሊዛ ቅምጥ ብቻ አይደለችም” ብሎ በተቆርቋሪነት ድምፀትም
“እሷ በጣም ቆንጆ ሴት ነበረች። መርማሪ ፖሊሶቹ ዶ/ር ሮበርትስን ለምርመራ የፈለጓትም ከመሞቷ በፊት ከገዳዩ አስቀድማ ያገኘቻት እሷ ስለነበረች ይመስለኛል።” አለው፡፡ “እሺ ይሁን” አለ እና ሀዶን በማስከተልም
"የመርማሪዎቹን አካላዊ ሁኔታን ግለፅልኝ እስቲ?” ሲል ጠየቀው፡፡
“ሁለት ናቸው። አንደኛው ደህና ይመስላል። ነገር ግን ከእሱ ጋር የመጣው ባልደረባው አጭር፣ ወፍራም እና የአይሪሽ ተወላጅ ነገር ነው።
በቃ ሰውዬውን አይተህ እሱ በጣም ክፉ እና ዘረኛ ፖሊስ መሆኑን ማወቅ
ትችላለህ”
ሀደን ዶፎም ገባኝ ለማለት ራሱን ከፍ እና ዝቅ አድርጎ ለትንሽ ጊዜ ያህል ከቆየ በኋላ ሚኪ ከሟቿ ጋር የተለየ ቅርበት ነበራት? ስለግድያው የተሰማት ስሜትስ እንዴት ነበር?”
ትሬይም ትከሻውን ሰበቀ እና “እኔ እንጃ ያን ያህል እንኳን በጣም ቅርበት ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ዶ/ር ሮበርትስ ከግድያው በኋላ ምንም አይነት የተለየ ለውጥን አላየሁባትም። ማለቴ በግድያው አዝናለች። ደግሞም አስቃቂ ግድያ ስለ ነበር ሁሉም ሰው አዝኖ ነበር።”
“ልክ ነህ!” አለው ሀዶን፡፡
በዚህ አይነት ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል ሲያወሩ ቆዩ እና ሀዶን ሊስናበታቸው ሲነሳ የትሬይ እናት ማርሻ እህት አብሯቸው እንዲበላ ለመጋበዝ ፈለገችና “ለእራት ብዙ ነገር አለን እባክህን እራት እንድትበላ እንጋብዝህ?” አለችው፡፡ ለመግደርደር ያህል “ወደ ቢሮ በቶሎ መመለስ አለብኝ፡፡ ዛሬ ማታ ምን ያህል ብዙ የወረቀት ሥራዎችን ጨርሼ ማደር
እንዳለብኝ አታውቂም” ብሎ ዋሻት እና ግብዣዋን ሳይቀበል ቀረ። ማርሻም
ብትሆን ብዙ እራት ነው የሰራሁት ማለቷ ውሸት ነበር። ምክንያቱም የትሬይ ገቢ እንኳን ተጨምሮ በችግር እንደሚኖሩ ዶ/ር ሀደን ዶፍ አይጠፋውም፡፡
ሀዶን ዶፍ በኤሌክትሪክ የሚሰራ መኪናውን እያሽከረከረ ከቤታቸው
ሲርቅ ከጓሮ በመመለስ ላይ ያለችው አያቱ ከፊታል “ይህ መልካም ሰው ነው
በእውነት። ትሬይ አንተ እሱን በማወቅህ ምን ያህል ዕድለኛ እንደሆንክ
አታውቅም” አለችው።
ትሬይም በእርጅና ምክንያት ራሰ በርሀ በመሆን ላይ ያለውን መሀል አናቷን ከሳመ በኋላ “አውቃለሁ አያቴ ደግሞም እድለኛ መሆኔን አምናለሁ።” አላት፡፡ በእርግጥ ሀዶን መጥቶ እሱን መጠየቁ ደግነቱን
የሚያሳይ ተግባርም ነው። ያም ሆኖ ግን ትሬይ ልብ ውስጥ ትንሽ ጥርጣሬ
መፈጠሩም አልቀረም። ለምንድን ነው በምሽት ወደ ዌስት ሞንት የመጣው?
ዶ/ር ዶውግ ሮበርትስ ከሞተ አመት አልፎታል። ከባልደረባው ሞት በኋላ
ደግሞ ለአንድም ጊዜ ቢሆን መጥቶ ጠይቋቸው አያውቅም።
“ደግሞስ ለምንድነው ኒኪን ስለጠየቋት ፖሊሶች ማንነት የጠየቀኝ? መገጣጠም ይሆን? የሊዛ ፍላንገን ድንገተኛ ግድያ ያለማወቁ እና ወደ እዚህ የመምጣቱስ ምክንያት ምንድን ነው?” ትሬይ ራቱን የኤል ፓሎ ክንፍ እየጋጠ በውስጡ የሚሰማውን ምክንያት አልባ ፍርሃትን እና ስለ ሃዶን ዶፎ የሚሰማውን ጥርጣሬ ተወ እና ዝም ብሎ ራቱን መመገብ ጀመረ።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ግን ተንቀሳቃሽ
ስልኩ ነዘረው። ስልኩን አወጣ እና የተላከለትን መልዕክት ሲያነብ ሰውነቱ
ሽምቅቅ አለበት።
“ምንድንነው ልጄ?” ብላ እናቱ ማርሻ ትሬይን ጠየቀችው። ትሬይን ዕፅ
ከሚጠቀምባቸው ጊዜያቶች አንስቶ እያንዳንዱን እንቅስቃሴዎቹን ሁሉ
የምትመለከተው በከፍተኛ ጥንቃቄ ተሞልታ ነው::
“ኧረ ምንም ችግር የለም”
“እርግጠኛ ነህ?” ብላ ለጠየቀችው ጥያቄ ራሱን ከፍ ዝቅ በማድረግ
እርግጠኝነቱን እያረጋገጠላት “የሆነ የረሳሁት ሥራ የሚያሳስብ መልዕክት
ነው አታስቢ እናቴ።” አላት፡፡ ራታቸውን በልተው ከጨረሱ በኋላ ትሬይ የበሉበትን ሳህኖች ሳይቻኮል አጥቦ ጨረሰ፡፡ ይህንን ያደረገው ደግሞ እና እንዳትረበሽ ነበር፡፡
ዕቃዎቹን አጥቦ ከጨረስ እና የማብሰያ ክፍሉን ካፀዳ በኋላ ጃኬቱን እንደያዘ አነሳ እና ለበሰው፡፡
“ልወጣ ነበር ብሎም ለእናቱ ማርሻ ነገራት፡፡ እሷም አይኖቿን አጥብባ
በጭንቀት እየተመለከተች “የት ልትሄድ ነው?” አለችው፡፡ “እስቲ የማታውን
አየር ተንፍሼ ልምጣ ብሎ ጉንጫን ሳማት እና ከቤት ሲወጣ “እኮ ሰላማዊ በሆነው የእኛ መንደር?” ብላ አሽሟጠጠችው እና መሄዱን ፈቀደችለት።አሁን ትሬይ አድጎ ራሱን ችሎ አይደል? ስለዚህ እሱን አብዝቶ መቆጣጠር ተገቢ እንዳልሆነ ተሰማት፡
“በል ራስህን ጠብቅ”
እሺ እማዬ” አላት እና መንገድ ላይ ወጣ፡፡በጄንከር ጓዳና የታችኛው ክፍልን ይዞ በእግሩ እየተጓዘ እያለ ቆዳው ላይ የሚሰማው ቀዝቃዛ እና ነፋሻው የማታ አየር ምቾት አልሰጠውም፡፡ ውስጡ ልክ እንደ ጊታር ክር ውጥር ብሎበታል እና ትንሽ ኮሽታ እንኳን ያስደነብረዋል::
መንገዱን ይዞ እየተጓዘ ኮርነር ላይ ሲደርስ እና ከቤታቸው ዕይታ
መሰወሩን እንዳወቀ ከኪሱ ስልኩን አውጥቶ የተላከለትን መልዕክት
አነበበው፡ የቬርሞንት 135ኛ ጎዳና ላይ በአንድ ሰአት ጊዜ ውስ እንድትደርስ” ይላል።
መልዕክቱ ይሄ ብቻ ቢሆንም መልዕክቱን ማን እንደላከለት እና ለምንም እንደተላከለት በደንብ ያውቃል። ማልቀስ ቢፈልግም ቅሉ እምባው ከየት ይምጣለት። ደግሞስ አሁን ላይ ማልቀሱ ምን ሊፈይድለት?
ከቆመበት ቦታ 50 ያርድ ርቀት ላይ ደምበኛ ቁጭ ብለው ከሚጠብቁ
ሴተኛ አዳሪዎች በስተቀር ማንም የለም። ስልኩ በድጋሚ ነዘረው። አሁን ግን የፅሁፍ መልዕክት ሳይሆን ፎቶ ነበር የተላከለት። መልዕክቱን በጣቱ
ነክቶ ሲከፍተው ግን ጉሮሮው ድረስ ሀሞቱ መጣበት እና ተናነቀው። ፎቶው
አንዲት ሴት በጩቤ የተወጋጋ ከወገብ በላይ ያለ አካል ነው። ጡቶቿ ልክ
ለመበለት እንደተዘጋጀ ዶሮ ተሰንጥቆ ተከፍቷል።
“ማን ናት? ሊዛ ናት ወይስ ሌላ ሴት?”
ከፎቶው በታች ይህ ቃል ተፅፏል
“ፍጠን”
ትሬይ እየሮጠ ትንፋሼ ተቆራርጦ ቦታው ላይ ቢደርስም ማንም የሚጠብቀው ሰው የለም ነበር። መኪናዎች የሉም፡፡ ሰዎች የሉም። ምንም ነገር የለም፡፡ ከመንገዱ ዳር ከሚገኝ መቀመጫ ላይ በዕፅ ቡዝዝ፣ ፍዝዝ ብለው የተቀመጡ ሴተኛ አዳሪዎች ብቻ ናቸው የሚገኙት።
የአንዷን ሴተኛ አዳሪ ትከሻም እየወዘወዘ ከፍዘቷ አነቃት እና “የሆነ ሰው እዚህ ጋ ቆሞ አይተሽ ነበር?” አላት።
ልጅቷም ቀና ብላ ስትመለከተው አይኗ ተጎልጉሎ ሊወጣ መድረሱን እና
መጦዟን አውቆ አጠገቧ ያለችውን ትንሽ ነቃ ያለችውን ሴት በጣም ተስፋ
መቁረጥ በሚታይበት ድምፅ እባክሽን! የሆነ ሰው እዚህ ጋር ቆሞ (መጥቶ
ከነበረ ንገሪኝ? በጣም ያስፈልገኛል እውዬውም አላት፡፡ ልጅቷም ባትሪው
አልቆ አሁን እንደተቀየረላት ሮቦት ነቃ ብላ ቀጥ ብላ ከተቀመጠች በኋላ
“ስኳፊ ያገኘሃት ይመስለሀል” ብላ እየገለፈጠች ከኋላ ይገኛሉ” አለችው።
ትሬይ ወደ ኋላው ሲዞርም ልቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም እና ቃጠሎ
ተሰማው። ህመሙን መቋቋም ስላልቻለም ወደ ኋላው ሲወድቅ አናቱ
ኮንክሪቱ ላይ አረፈ።
ከዚያ በኋላ ደግሞ ሁሉ ነገር በጭለማ ተተካ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ሁለት ወዳድ” ብሎ ሎው ጉድማን 10 እና 8 ቁጥርን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ፡፡ ባልደረባው ሚክ ጆንሰንስን የፖከር ጨዋታ

ሱስ ስላለበት ከዚህ
ሽማግሌ ባልደረባው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ብሎ
ጨዋታውን ለመለማመድ ሞክሮ ነበር፡፡ እሱ እንደገመተው በአጭር ጊዜ
ውስጥ ሊለምደው ባይችልም ጥረቱን ግን አላቋረጠም።
ቀጥታ” ብሎ ጆንሰን ሳቀበት እና ከስድስት እስከ አሥር ያሉትን የፖከር
ጠጠሮች እየደረደረ” እንግዲህ ቁርስ ባንተ ነው ማለት ነው” አለው፡፡
ጉድማንም ባልደረባውን እየተመለከተ ፓንኬኩን አነሳና ሽሮፑን እና ክሬሙን ካፈሰሰበት በኋላም መግመጥ ጀመረ።
ሁለቱ የግድያ ወንጀል መርማሪ ፖሊስ ባልደረባዎች ከፖሊስ ጣቢያው የወጡት ምርመራቸው እንዴት እየሄደ እንዳለ እና ምን ምን ነገርም እንደሚጎድለው ለመገማገም ነበር። የሟቿ ሊዛ ፍላንገን የቀድሞ አፍቃሪ ቢሊየነሩ ዊሊ ባደን ሜክሲኮ ካቦ ሳን ሉካስ ውስጥ ከሰራው የመዝናኛ መኖሪያ ቤቱ ገና አልተመለሰም፡፡ ዊሊ ባደን ሊዛ ፍላንገን በተገደለችበት ምሽት ላይ ከታማኟ ባለቤቱ ቫላንቲና ጋር ሜክሲኮ ውስጥ የእረፍት ጊዜያቸውን እያሳለፋ ነበር።
ዜናዎች ስለ ዊሊ ባደን እና ስለ ቅምጡ ሊዛ ፍላንገን ግንኙነት ማውራታቸውን እስካላቋረጡ ድረስም ወደ ሎስ አንጀለስ እንደማይመለሱ ግልፅ ነው፡፡ ጉድማን ስለ ቫለንቲና የበጎ አድራጎት ድርጅት እና የብራንዶን ግሮልሽ እናት ፍራንሰስ ያላቸውን ግንኙነት ለጆንሰን አሳውቆታል። ነገር ግን ወደ ድርጅቱ ደውለው ስለ ብራንዶን መረጃ ሲጠይቁ ድርጅቱ ብራንዶን ስለሚባል ልጅና ሞቱን የሚያረዳ ደብዳቤን ወደ ግሮልሽ ቤተሰብ መላኩን የሚያሳይ አንድም ማስረጃን ሊያገኙ አልቻሉም።
ጆንሰንም ቢሆን የሟቿን ቤተሰብ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ምንም
ውጤት አላመጣለትም፡፡ ወንድምም ሆነ እህት የላትም፡፡ ሁለቱም ወላጆቿ
በህይወት የሉም፡፡ ሬኖ ውስጥ የምትኖረው አክስቷም ሊዛ ፍላንገን ከስድስት ዓመቷ ጀምሮ አግኝታት አታውቅም፡፡ ጉድማንም ቢሆን ብራንዶን ግሮልሽ በህይወት ይኑር ወይም ሞቶ ይሁን የሚለውን ፍንጭ ሊይዝ አልቻለም።የእሱ ዲ.ኤን.ኤ (ዘረ መልም) በምን ምክንያት የሊዛ ፍላንገን ጥፍር ውስጥ ሊገኝ እንደቻለ ግልፅ አልሆነለትም። ልክ እንደ ብራንዶን ቤተሰቦቹ ሁሉ የበፊት ጓደኞቹም ሆኑ የሴት ጓደኞቹ ከእሱ የስልክ ጥሪ የደረሳቸው እየተገናኘ ስለ ብራንዶን ቢጠይቅም አንድም ተጨባጭ የሆነ መረጃ ስላላገኘ ከስምንት ወራት በፊት ነበር፡፡ ከአደንዛዥ ዕፅ ማገገሚያ ማዕከሎች አባቱ ናታን ግሮሽ እንደደመደመው ብራንዶንን በህይወት የማግኘቱ ነገር ትንሽ የሚያነቃቃ መረጃን ያገኙት የሊዛ ፍላንገን ሬሳ የተጣለበት ቦታ ላይ በቅርብ ርቀት ላይ ሊዛ ለብሳው የነበረችው ቁራጭ ጨርቅ መገኘቱ ብቻ።
ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን ብጫቂ ጨርቁ ላይ የአንድም ሰው የዘረ መል ዲ.ኤንኤ
ህዋስ ሊገኝ እንዳልቻለ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤቱ ያሳያል እና ተስፋ
የላቸውም። ምናልባትም ሊዛ ፍላንገን የተገደለችበት ምሽት ላይ ይዘንብ
የነበረው ሀይለኛ ዝናብ ከብጫቂ ጨርቁ ላይ የህዋሱን ቅሪት አጥቦት ሊሆን
ይችላል። ስለሆነም ያላቸው ብቸኛ ፍንጭ የሊዛ ጥፍር ውስጥ የተገኘው የብራንዶን ዘረመል (ዲ.ኤን.ኤ) ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ የሚያኩራራቸው መረጃ አይደለም።
“ሳይኮሎጂስቷን አላምናትም” አለው ጆንሰን ልክ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ
በሹካው ፓን ኬኩን አንስቶ ወደ አፉ እየላከ “ደግመን ልናናግራት ይገባል
መሰለኝ” አለው። ጉድማንም ጆንሰን በዶር ኒኪ ላይ ያለው ጥላቻ ቀን በቀን
እየጨመረበት መሆኑን በማጤኑ እሷን የሚጠላበትን ምክንያት ማወቅ
ፈለገ፡ ጉድማንም “እሺ ደግመን ስናገኛት ምንድነው የምንጠይቃት?” አለው
በቸልታ፡፡ “ከበሽተኞቿ ጋር በምታሳልፍባቸው ክፍለ ጊዜያት ላይ ስለ
በሽተኞቿ ሁኔታ ስለምትፅፋቸው ኖቶች” ብሎ እያልጎመጎመ በማንኪያም ክሬሙን ፓን ኬኩ ላይ እየቀባ “ከሟቿ ጋር በነበራት የህክምና ጊዜዎች ላይ
ስለ ሊዛ የምታሰፍራቸውን ኖቶች ማለቴ ነው።”
“እንዴ ይህንንማ ከፍርድ ቤት የማዘዥያ ወረቀት ሳናወጣ ማድረግ አንችልም፡፡ የሀኪም እና ታካሚ ሚስጥር እኮ ይጠበቃል አይደል?” ብሎ ጉድማን ሲናገር ጆንሰን ቡፍ ብሎ ሳቀ እና “እሷ እኮ ዶክተር አይደለችም።በቃ የህክምና ትምህርት (ልምምድ) ሳይሆን የወሰደችው በቬነስ የባህር ዳርቻዎች ላይ የታሮት ካርድን እንደሚጠብቁት ሰው ነው ስራዋ” አለው፡፡
“ይሄማ ትክክል አይደለም ሚክ” ብሎ ጉድማን መለሰለት እና በማስከተልም “ለምን ይህን ያህል እንደምትጠላት አይገባኝም?” አለው።
“ባታውቀው ይሻልሀል” ብሎ ጆንሰን አጉረመረመ። “ይሄ ምን ማለት ነው ደግሞ?” ጉድማን ጠየቀ፡፡
“አየህ እሷ ቆንጆ ናት” አለው እና ጆንሰን በማስከተልም “አንተ ደግሞ ቆንጆ ሴቶች ይስቡሃል”
“አንተንስ አይሰቡህም?” ብሎ ጠየቀው እና የቀዘቀዘ ቡና የያዘውን ሲኒ ወደ ጎን ገፋው። እዚህ ደኔም ወደሚባል ካፌ ለምን አብዛኛዎቹ የሥራ ባልደረቦቹ መምጣት እንደሚወዱ አይገባውም። “ለማንኛውም” አለና በማስከተልም “የእሷ ቆንጆ መሆን አለመሆን ከምንም አይነት ነገር ጋር አይያያዝም። እሷ ከግድያው ጋር ግንኙነት የላትም። በቃ እሷ ማዘናጊያ ስለሆነች ትኩረታችንን በባደኖች ላይ በማድረግ ስለ ብራንዶን ግሮልሽ መጨረስ ይኖርብናል” አለው።
ጆንሰንም ለጉድማን ምልከታ ምላሽ ሊሰጥ እያለ ስልኩ ጮኸ፡፡
ሄሎ?” ብሎም ስልኩን ማናገር ጀመረ፡፡
ጉድማንም ሹካውን ሳህኑ ላይ አስቀምጦ በዝግታ ጆንሰን ሲያወራ ማስተዋል ጀመረ። ጆንሰን የደወለለትን ሰው ማስተዋል ጀመረ። ጆንሰን የደወለለትን ሰው ወሬ በአፅንኦት ሲያዳምጥም አስተዋለ። ለብዙ ጊዜ ዝም ብሎ ሲያዳምጥ ቆይቶም “እሺ እየመጣን ነው” ብሎ ስልኩን ዘጋው።
“ምንድነው?” ብሎም ጉድማን ጠየቀ፡፡
ከተቀመጠበት ወንበር ላይ እየተነሳም “ሬይ ሬይሞንድን ታስታውሰዋለህ?” አለው እና በመቀጠልም “በዶ/ር ሮበርትስ ቢሮ ውስጥ የሚሰራው ጥቁር ቀጠን ያለ እንግዳ ተቀባዩን ልጅ አስታወስከው?” አለው ጆንሰን።
“እሺ ስለ እሱ ምን?” ብሎ ጠየቀው ጉድማን።
“ሊዛ ፍላንገን ተገድላ ከተጣለችበት ቦታ በግማሽ ማይል ርቀት ላይ ተጥሎ ተገኝቷል። ራቁቱን ነው፤ ብዙ ቦታዎች በጩቤ ተወግቷል፤ ልቡ ላይም ሀይለኛ ውግ ነው ያለው!” አለው።
“ይገርማል! እንግዲህ ገዳዩ ሴሪያል ገዳይ ሊሆን ነው!” አለ ጉድማን፡፡
“አይደለም” ብሎ ወደ ካፌው በር በችኮላ መራመድ ሲጀምር ጉድማን እየተከተለው “ምን ማለትህ ነው?” አለው።
"ትሬይን ሬይሞንድ በህይወት ይጀኛል !" ብሎ ጉድማን መለሰለት።

#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....መንገድ ዳር ከቆመችው ነጭ ሲትሮይን መኪና ሲደርሱ ሁለቱም
ተከታትለው በስተቀኝ ያለውን የኋላ በር ከፍተው ገቡ፡፡
“እሺ?” አለ ማርቆስ ከፊት ተቀምጦ መሪውን የጨበጠውን አልጀርያዊ መኮንን እየተመለከተ፡፡
“የመጀመሪያውንአጠናቅቀዋል፡፡” አለ አልጀርያዊው አፉ ውስጥ የሰካትን የጥርስ መጎርጎርያ ስንጥር ከአፉ ሳያወጣ እያላመጣት::
“ጥሩ” አለ ኮሎኔል በረጅሙ ተንፍሶ ሰአቱን ለሁለተኛ ጊዜ እየተመለከተ “ሁለተኛውን እንደጨረሳችሁ ሪፖርት ታዘጋጃላችሁ..የሁለቱንም በአንድ ላይ፡፡ ቢሮዬ ነኝ፡፡” አለ የሲትሮይኗን በር ከፍቶ
እያወረደ፡፡ ፒተር ተከተለው፡፡
የቆዳ . ጃኬቱን ኮሌታ ወደላይ እንደመለሰ በረጃጅም እርምጃ መንገዱን ተሻገረና, ጥግ ይዛ ወደቆመች መርሰዲስ አመራ፡፡ ፒተር ቀልጠፍ ብሎ ቀመሪው በኩል ያለውን በር ከፍቶ ከገባ በኋላ ባሻገር ያለውን በ ከፈተለትና ኮሎኔል ገብቶ ከፒተር ጎን ተቀመጠ፡፡
“ፒተር አለ ማርቆስ በዝናቡ ካፊያ በስብሶ ከፊት ለፊቱ ያለውን ሰባብሮና አወላግዶ በሚያሳየው የመርሰዲስ የፊት መስተዋት ላይ አቦዝዞ “.ሁኔታዎች አስገድደውህ የምታደርገውንና ያደረከውን ህሊናህ
መላልሶ መላልሶ ሲፀየፈው ምን ታደርጋለህ?” አለ ጉንጩ ላይ ያለውን
ጠባሳ በጣቱ እየዳሰሰ፡፡
“ህሊናየን እፀየፈዋለህ፡፡!” አለ ፒተር ለማሰብ እንኳን ጊዜ ሳይወስድ
“ወደ ቢሮ?" አለ እክታትሉ፡፡
“አዎ ወደ ቢሮ እንሂድ።” አለ ማርትቆስ ኣይኖቹን ጨፍኖ፡፡
“ቆንጅዬ ለምን አብረን አናድርም?”
“ቆንጅዬ ለምን ቤቱ አታደርሰኝም?''
“አትቀልጅ እንጂ እውነቴንኮ ነው፡፡”
“አንተ አትቀልድ…ጠዋቱኑ ነግሬሃለሁ በሰላም መተኛት ነው የምፈልገው፡፡ ጠዋት ሥራ ገቢ ነኝ፡፡“ የያዘችውን ሹካና ቢላ ከሳሆኖቹ ላይ አስቀመጠችና ከጎን የተቀመጠውን ወረቀት አንስታ አፏን መጠራረግ ያዘች፡፡”
“ስለምንሽ?” እጁን ዘርግቶ ቀኝ እጇን ያዝ አደረገና ኣይኖቹን ኣቁለጨለጨላት፡፡
“እራት ጋብዤሽ እቤት አደርስሻለሁ ነው ያልከው፡፡ አሁን አዲስ ፋይል ኣትክፈት፡፡”
“ምን ነካሽ ርብቃ! አልረብሽሽም ኣርፌ እተኛለሁ…ሙች፡፡”
“አርፈህ አትተኛም! ናቲ እንተዋወቃለንኮ፡፡ ኘሁን ይልቅ እንሂድ፡፡” ቦርሣዋን አነሳች፡፡
“ርብቃ በናትሽ አትድረቂ፡፡” በተቀመጠበት እጆቿን ይዟት ቆየ::
“ብቻዬን ማደር አልፈልግም፡፡ በቃ፡፡ አቅፌሽ እንቅልፋችንን መለጠጥ በቃ፡፡” ናትናኤል የገዛ እራሱ መቀየር አሳፈረው፡፡
“ሚስት አግባና አቅፈሃት እንቅልፍህን ለጥጥ፡፡ ይልቅ አትቀልድ ሂሳቡን ክፈልና እንሂድ…መሸኮ፡፡” ሠዓቷን እየተመለከተች ፡ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት፡፡ውሳኔ ላይ መድረስ አለበት፡፡ አጉል መሸፋፈኑን ትቶ ፍቅሩን መግለጽ አለበት፡፡ ግን እንዳፈቀራት ካወቀች ትጫነዋለች…እንጋባ አለበለዚያ ብትልስ? መከራ ጣጣ ይሄ ጋብቻ የሚሉት ነገር የፈጠረው ወፈፌ ማን ይሆን? የተዋደዱ ሁሉ መጋባት አለባቸው ያለው ማነው? ጭቅጭቅ
ኣስተናጋጁን ጠቀሰው፡፡
ናትናኤል ድፍን ሃምሣ ብር ኣውጥቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጠ።አስተናጋጁ ብሩን አንስቶ በትሪ ላይ ኮፍሶ ካመጣው የዋጋ ማቅረቢያ ወረቀት ጎን አስቀመጠውና ተመልሶ ሄደ።
“ርብቃ..እንደዛሬው ችክ ብዬብሽ አውቃለሁ?” ፈገግ ብሎ ተመለከታት፡፡
“በፍፁም!” አለች ርብቃ እየሳቀች፡፡
“በቃ እንግዲያው 'እሺ በይኝ፡፡” ናትናኤል ብቻውን ቤቱ ገብቶ አልጋው ውስጥ ጥቅልል ማለቱን እንደሞት ፈራው፡፡ ለወትሮው ግድ የለሽ ነው:: ዛሬ ግን ብቻውን ወና ቤቱ ውስጥ መግባቱ ቀፈፈው ምክንያቱ ለራሱ ባይገባውም፡፡
አስተናጋጁ ተመልሶ መጣ፡፡ ናትናኤል መልሉን ተቀብሎ ወፈር ያለ ጉርሻ ትቶለት ተነሳ:: አስተናጋጁ ፊቱ በፈገግታ ረስርሶ በግራው ትሪውን እንደያዘ ከወገቡ ጎንበስ : አለና , ቀኙን ጀርባው ላይ ጭኖ
ተሰናበታቸው “ደህና እደሩልኝ፡፡”
“ኣላበዛኸውም?” .
“ምኑን?”
“ጉርሻውን፡፡” አለች ክንዱን ያዝ አድርጋ፡፡
“ቢቀናኝ ብዬ ነው ባክሽ፡፡” አለ ናትናኤል ፈገግ ብሎ፡፡
“ምንድነው የሚቀናህ?” የሆቴሉን የፊት አዳራሽ ኣቋርጠው ወደ ፊተኛው በር ሲጠጉ በረኛው በሩን ከፍቶ፣ ጎንበስ ብሎ ተሰናበታቸው፡፡
“እሺ እንድትይኝ ነዋ፡፡ እኔ ጋ እንድታድሪ፡፡” እየሳቀ ተመለከተት፡፡
"ብሽቅ!” አለች አብራው እየሳቀች፡፡
ርብቃ ኣብራው ልታድር የወሰነችው ገና ከሆቴሉ ሳይወጡ ነበር፡፡ ነገር ግን መኪናው ውስጥ ከገቡም በኋላ
አሃ! የት ነው የምትሄደው? ናቲ ሙት አይሆንም ብዬሃለሁ:: ቤት ታደርሰኝ እንደሆን አድርሰኝ:: አይሆንም:: ነገርኩህ እንግዲህ፡፡” እያላች ተግደረደረችበት፡፡
ዛሬ ይሄኔ ነው መናገር ያለባት፡፡ የፍቅር ጨዋታዋን ብቻ ሳይሆን ታራ
ሙቀቷን፤ ቅርበቷን፡ እሷነቷን በፈለገ ስዓት ነው መናር ያለባት
“ናቲ…አረገዝኩልህ ኮ ኣዲኣ! እንደዛ እይደለም…” ናቲ…
ሃኪም ቤት
ሄጄ ነበር… እና…” እንደዛም ኣይደለም… ፀጥ ብላ ማልቀስ፡፡ እሱ ራሉ
ደንግጦ “ምንሆንሽ?” ይላት የሌያን ጊዜ ማልቀሷን ሳታቋርጥ አንገቱ ስር
ገብታ በእንባዋ' አንገቱን እያረጠበች፤ ደረቱን እያባበሰች ጣቶቿን ከጀርባ
ፀጉሩ ውስጥ ከትታ እያፍተለተለች መነፋረቅ “ናቲዬናቲ አንድ ነገር
ብነግርህ ኣትቆጣም ኣይደል …እ …ናቲ …የኔ ጌታሙች በለኝና ትወደኛለህ
አይደል…” መነፋረቅ “…ናቲ”
መነፋረቅ
“እሺ፤ ግን ቃል ገብተህልኛል… ኣትረብሸኝም አይደል?” አለች
የሌባ ጣቷን ኣፍንጫው ሥር ቅስራ፡፡
“አልረብሽሽም አልኩኝኮ ርብቃ፡፡” በመጨረሻ ማሽነፉ ደስ አለው
ናትናኤል። ከዚህ ቀደም ከሌሎች ሴቶች ጋር ሊሆን ተሰምቶት የማያውቅ
ልዩ ስሜት እንደሸረሪት ድር በዙሪያው ሲተበተብ ተሰማው፡፡ ፈራ።
ቤቱ ይዟት ሄደ፡፡
የአፖርትመንቱን በር ከፍቶ እንደቡ ናትናኤል መብራቱን አብርቶ
ኮቱን ፍቴ ላይ ወርወር አድርጎ ወደ መጠጥ መደርደሪያው ሄደ።
“ናትናኤል ቁጭ አድርገኸኝ ልትጠጣ አይደለም ያመጣኸኝ”
ወደ መኝታ ቤት ከሚያስገባው በር ስትደርስ ፊቷን መልሳ ገረመመችው።
“ትንሽ ማሰብ ስለፈለኩኝ ነው፡፡” አለ ናትናኤል የጠርሙሱንመክደኛ እየከፈተ፡፡
“እንግዲህ ጀመረህ…” አለች ራመድ ራመድ ብላ ከእጁ ውስጥ
ጠርሙሱን ወስዳ መልሳ መደርደሪያው ላይ እያስቀመጠችው። “አቅፈሽ
ለጥ ነው ብለህ ነው ያመጣኸኝ? ማሰብ ከሆነ የምትፈልገው የእኔ እዚህ
መምጣት አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡” ተኮሳተረችበት፡፡
ናትናኤል በረጅሙ ተነፈሰኛ ትከሻዋን እቅፍ አድርጓት ወደ መኝታ
ቤት ሱ። ርብቃ ቀን የራስጌ መብራት ስታበራ መኝታ ቤቱ ደም ለበሰ
ታኮ ጫማዋን አውልቃ ከእልጋው ግርጌ አስቀመጠችና ልብሷን ማወላለቅ ጀመረች፡፡ ናትናኤል ወደ መስኮቱ ሄዶ ወፍራሙን መጋረጃ ከመዝጋቱ በፊት ድቅድቅ ጨለማ በተከናነበው ከተማ ላይ አይኑን አፈጠጠ፡፡ ርብቃ የሌሊት ልብሷን ለብሳ ወደ መታጠቢያ ቤት ስትገባ ይሄኔ ነው መናገር ያለባት፡፡ የፍቅር ጨዋታዋን ብቻ ሳይሆን ተራ ሙቀቷን፤ ቅርበቷን እሷነቷን በፈለገ ሰዓት ነው መናር ያለባት
“ናቲ…አረገዝኩልህ ኮ አ አ! እንደዛ እይደለም…” ናቲ… ሃኪም ቤት
ሄጄ ነበር… እና…” እንደዛም አይደለም… ፀጥ ብላ ማልቀስ፡፡ እሱ ራሉ ደንግጦ “ምንሆንሽ?” ይላት የዚያን ጊዜ ማልቀሷን ሳታቋርጥ አንገቱ ስር ገብታ በእንባዋ' አንገቱን እያረጠበች፤ ደረቱን እያባበሰች ጣቶቿን ከጀርባ ፀጉሩ ውስጥ ከትታ እያፍተለተለች መነፋረቅ “ናቲዬናቲ አንድ ነገር ብነግርህ አትቆጣም አይደል …እ …ናቲ …የኔ ጌታ ሙች በለኝና ትወደኛለህ
አይደል…” መነፋረቅ “…ናቲ”
መነፋረቅ
“እሺ፤ ግን ቃል ገብተህልኛል

አትረብሸኝም አይደል?” አለች የሌባ ጣቷን ኣፍንጫው ሥር ቀስራ፡፡
“አልረብሽሽም አልኩኝኮ ርብቃ፡፡” በመጨረሻ ማሽነፉ ደስ አለው ናትናኤል። ከዚህ ቀደም ከሌሎች ሴቶች ጋር ሲሆን ተሰምቶት የማያውቅ ልዩ ስሜት እንደሸረሪት ድር በዙሪያው ሲተበተብ ተሰማው፡፡ ፈራ።
ቤቱ ይዟት ሄደ፡፡
የአፖርትመንቱን በር ከፍቶ እንደቡ ናትናኤል መብራቱን አብርቶ ኮቱን ፍቴ ላይ ወርወር አድርጎ ወደ መጠጥ መደርደሪያው ሄደ።
“ናትናኤል ቁጭ አድርገኸኝ ልትጠጣ አይደለም ያመጣኸኝ” ወደ መኝታ ቤት ከሚያስገባው በር ስትደርስ ፊቷን መልሳ
ገረመመችው።
“ትንሽ ማሰብ ስለፈለኩኝ ነው፡፡” አለ ናትናኤል የጠርሙሱን መክደኛ እየከፈተ፡፡
“እንግዲህ ጀመረህ…” አለች ራመድ ራመድ ብላ ከእጁ ውስጥ ጠርሙሱን ወስዳ መልሳ መደርደሪያው ላይ እያስቀመጠችው። “አቅፈሽ ለጥ ነው ብለህ ነው ያመጣኸኝ?ማሰብ ከሆነ የምትፈልገው የእኔ እዚህ መምጣት አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡” ተኮሳተረችበት፡፡
ናትናኤል በረጅሙ ተነፈሰና ትከሻዋን እቅፍ አድርጓት ወደ መኝታ ቤት ገቡ። ርብቃ ቀዩን የራስጌ መብራት ስታበራ መኝታ ቤቱ ደም መሰለ፡ታኮ ጫማዋን አውልቃ ከእልጋው ግርጌ አስቀመጠችና ልብሷን ማወላለቅ ጀመረች፡፡ ናትናኤል ወደ መስኮቱ ሄዶ ወፍራሙን መጋረጃ ከመዝጋቱ በፊት ድቅድቅ ጨለማ በተከናነበው ከተማ ላይ አይኑን አፈጠጠ፡፡ ርብቃ የሌሊት ልብሷን ለብሳ ወደ መታጠቢያ ቤት ስትገባ
“ምንድን ነው የምታየው በጨለማ? ይልቅ ልብስህን ቀይር፡፡” አለችው፡፡
መታጠቢያ ቤት ገብታ ተጣጥባ ስትመለስም ናትናኤል እዛው መስኮቱ
አጠገብ እንደቆመ ነበር።
“ምን ሆነሃል” ጠጋ ብላ ፀጉሩን እያሻሸች ፊቱን ወደራሷ መልሳ ጠየቀችው፡፡
“እኔ እንጃ፡፡”
“ምንድነው?”
“ምኑ?”
“የምታስበው፡፡”
ናትናኤል አመነታ፡፡ ውሳኔውን ራሱ መውሰድ አለበት። ለርብቃ የሚያማክራት፤ ነገር አይደለም፡፡ የግል ህይወቱ ቢሆን አዎ ግን ይሄ ከሥራው ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው፡፡ ያንን ደግሞ ራሱ ሊወስነው የሚገባ ነገር ነው፡፡
ቀን ምሳ ላይ ከአብርሃም ጋር አጥብቀው ተከራክረውበታል። ለጊዜው ባይሸነፍለትም የአብርሃም፣ አመለካከትም መሠረት ያለው መሆኑን
ሊክድ አልቻለም::
“እየው ናትናኤል. እኔ ይህን ስራ ያንን አትስራ እያልኩኝ አልመራህም ግን ደግሞ እንደ እሳት እራት መጥፊያህን ስታሳድድ ዝም ማለት አልችልም፡፡” ነበር ያለው አብርሃም፡፡ l
"ምንድነው መጥፊያዬን የማሳድደው? እኔ'ኮ መደበኛ ሥራዬን ነው ?
እያሰራሁ ያለሁት።በማንም ጉዳይ አልገባሁም፡፡”
“ናትናኤል የኛን ሰው አርደው ድልድይ ሥር የጣሉት ሰዎች ለምን ያንን ዓይነት ኣስቃቂ እርምጃ የወሰዱ ይመስልሃል? ባጭሩ የጆሴፍ ካልሽርትን አድራሻ ሲያነፈንፍ ስላገኙት ብቻ ነው፡፡ አሁን አንተ እያደረግህ ያለኸው እሱ ሲያደርግ የተገኘውን ነገር ነው፡፡ ናትናኤል አንድ ምክር ብቻ ነው የምሰጥህ…ተጠንቀቅ!”
“ለምን ታስፈራራኛለህ?” በስጨት አለ ናትናኤል።
“አላስፈራራሁህም!” ለመጀመሪያ ጊዜ የተናደደ መሰለ አብርሃም የማስፈራራበትም ምክንያት የለኝም:: የሚያስፈራራስ አላወቅኸውም እንጂ
አንተ ራስህ ፈቅደህ የገባህበት አለም ነው፡፡”
“ሥራዬን ነው እየሰራሁኮ ያለሁት አብርሃም፡፡'
“የኛም ሰው ሥራውን ሲሰራ ነው እንደ ዶሮ ታርዶ የተጣለው፧ በድኑ ድልድይ ስር የተሸጎጠው፤ ደሙ ከወንዝ የተደባለቀው
ትሰማኛለህ?!” አብርሃም ፊቱን ወደ ናትናኤል አዙሮ አፈጠጠበት፡፡ “ያው
የድሮው ጋኔን አሁንም እየጋለበህ መሰለኝ” ነበር አብርሃም ያለው
የናትናኤልን የወትሮ ግትርነት አስታውሶ።
“እ…? ንገረኝ እንጂ ምን ሆነሃል?” ርብቃ ፀጉሩን እያሻሸች ጠየቀችው፡፡
“ዝም ብዬ ነው ርብቃ፡፡” ኣለ ናትናኤል ጀርባዋን እያሻሻት፡፡
እጁን ይዛ ወደ አልጋው ወሰደችው። አልጋው ላይ ቁጭ ብለው ልብሱን አወለቀችለት። አንድ በኣንድ ኮቱን፣ ሸሚዙን፣ : ሱሪውን፡ጫማውንና ካልሲውን ስታወልቅለት በዝምታ አይን አይኗን ሲመለከታት ቆየ፡፡ እንደ ህፃን ልጅ ፒጃማውን ካለበሰችው በኋላ ተነስቶ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ።
በተቻላት መጠን ሃሣቡን መሰብሰብ አለባት። አለበለዚያ ልትነግረው
የፈለገችውን መናገር አትችልም፡፡ ምንድነው ግን የሚያስበው… .. አንድ
ያስጨነቀው ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነች፡፡ ማርገዟን ተጠራጥሮ ይሆን እንዴ?
ወይኔ ገብሬልዬ! ሆዷ ባይገፋም ወገቧ አካባቢዐጡቶቿም…፡፡ ሃሳብ ገባት
ርብቃ:: ያበጠው ይፈንዳ ዛሬ ታወጣዋለች፡፡ ሳይቀድማት መቅደም አለባት፡፡ዛሬ ነገ ስትል ዘጠኝ ወር ደርሶ ወልዳ ሳታርፈው አትቀርም፡፡ አሁኑኑ
ተናግራ ካልወጣላት ከጥቂት ጊዜ በኋላ በደንብ ነው የምታስታውቀው፡፡
የመጣው ይምጣ ዛሬ
ናትናኤል የመታጠቢያ ቤቱን መብራት አጥፍቶ በሩን ሲከፍት ስትለማ ርብቃ ቶሎ ብላ በጀርባዋ ተንጋላ በተቻላት ዘና ብላ ጠበቀችው፡፡በሩን ዘግቶ ወደ መኝታ ቤት ዘለቀ፡፡ ወደ አልጋው ሄዶ ብርድ ልብሱን
ገልጦ እልጋው ውስጥ ሲገባ ርብቃ አልተነቃነቀችም፡፡ አልጋው ውስጥ ከገባ
በኋላ ዞር ብሎ ራስጌ ያስቀመጠውን ጀምሮ ያቋረጠውን መጽሐፍ አነሳ፡፡
“ናትናኤል…አሁን ማንበቢያ ዕዓት አይደለም::” አለች ድንገት ቀና
ብላ መጽሓፋን ከእጁ ላይ እየወሰደችበት፡፡
ናትናኤል አልተከራከራትም:: እንድ ዓይነት ጭንቅት እንደወረረው ግን ፊቱ ላይ በግልጽ ይነበብ ነበር፡፡ ሸርተት ብሎ አልጋ ውስጥ ገባ። ርብቃ ጠጋ ብላው ተኛች። ትኩስ ገላዋ መጥቶ ልጥፍ ሲልበት እጁን ሰድዶ በስሱ የሌሊት ልብስ ውስጥ ያለውን መግቢያ መውጫውን የሚያውቀውን ገላ ያሻሽ ጀመር፡፡ በየት እንደሆነ ባይገባውም እጆቹ የሌሊት ልብሷን አልፈው የሚፋጅ ገላዋ ላይ መቅለጥ ጀመሩ። ትኩስ ትንፋሽዋ አንገቱን ሲለበልበው የሚወደው ፀጉራ ደረቱ ላይ ብትን አለ፡፡
ያ ሁሉ ፋከራ ለዚሀ ነው? አሁን ነው ማልቀስ ያለባት! እጆቹ እየዳበሷት እያሉ፤ ደረቱ ላይ ተኝታ እያለች ምን ይመጣል? አውቀሽዐነው ያረግሽው ብሎ ቢያመርስ? ያምርራ! ታዲያ ምን ማድረግ ትችላለች…
ከአሁን በኃላ አንዱ ሆኗል! መናገርና የሚመጣውን መቀበል፡፡ ገብሬልዬ!
“ናትናኤል...” ከደረቱ ላይ ቀና አለች ርብቃ፡ዐናትናኤል…” በተቻላት ድምጿን አለስልሳ ስሙን ጠራችው፡፡.....

#ሀገር_ስጡኝ
እኔ ልክ እንደ አስኳል ነኝ፣
ከቅርፊቴ ውጭ ብቻዬን ፍጹም ህልውና የሌለኝ፡፡
ውበት ድምቀቴን.......መኖሬን፣
እስትንፋስ ልቤን........ብሌኔን
የኔን መጠሪያ ማንነት
ሃገሬን ያጠበባችሁ፣
በሰፈር በመንደር - - በጎጥ
በወንዝ በድልድይ ድንበር፣
እንደ እይታችሁ ጥበት
ግዙፏን ያሳነሳችሁ
የኔ ሃገሬ ባህር ነች
ሰፊ ነች ምጡቅና ጥልቅ፣
እንደ እናንተ ማነስ አልቻልኩም
የዘር ሰበዝ ስሰነጥቅ፣
በናንተ አለም አልኖርም
እውነትን ክጄ ታሪክ ስፍቅ፡፡
ይልቅ እንጥፍጣፊ የሃገር ፍቅር ከቀራችሁ፣
በጥቁር አፈሯ እንድቀበር
ኢትዮጵያን ስጡኝ እባካችሁ፡፡
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ🔘
እኔ ልክ እንደ አስኳል ነኝ፣
ከቅርፊቴ ውጭ ብቻዬን ፍጹም ህልውና የሌለኝ፡፡
ውበት ድምቀቴን.......መኖሬን፣
እስትንፋስ ልቤን........ብሌኔን
የኔን መጠሪያ ማንነት
ሃገሬን ያጠበባችሁ፣
በሰፈር በመንደር - - በጎጥ
በወንዝ በድልድይ ድንበር፣
እንደ እይታችሁ ጥበት
ግዙፏን ያሳነሳችሁ
የኔ ሃገሬ ባህር ነች
ሰፊ ነች ምጡቅና ጥልቅ፣
እንደ እናንተ ማነስ አልቻልኩም
የዘር ሰበዝ ስሰነጥቅ፣
በናንተ አለም አልኖርም
እውነትን ክጄ ታሪክ ስፍቅ፡፡
ይልቅ እንጥፍጣፊ የሃገር ፍቅር ከቀራችሁ፣
በጥቁር አፈሯ እንድቀበር
ኢትዮጵያን ስጡኝ እባካችሁ፡፡
🔘በሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ🔘
#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
...በምዕራብ ሆሊውድ መሀል ላይ የሚገኘው የሴዳርስ ሲናይ ሆስፒታል
ብዙውን ጊዜ ታዋቂ ሰዎች የሚታከሙበት ቦታ ነው። ለምሳሌ ያህል
ፍራንክ ሲናትራ እና ሪቨር ፎኒክስ ሲታከሙ ቆይተው የሞቱት እዚያ ነው።
የማይክል ጃክሰን ህፃናት ልጆችም የተወለዱት እዚያ ነው። ብሪትኒ
ስፒርስም ከአደንዛዥ ዕፅ ነፃ የመሆን ህክምናዋን የተከታተለችው በስነ
አዕምሮ ዲፓርትመንት በዚሁ ሆስፒታል ውስጥ ነበር።
ያም ሆኖ ግን ሴዳርስ በከተማው መሀል ላይ የሚገኝ ሆስፒታል እንደመሆኑ መጠን ሎስ አንጀለስ ውስጥ በሚደርሱ የመኪና አደጋዎች ፣ ከመጠን በላይ የአደንዛዥ ዕፅ ወስደው የተጎዱ ሰዎች፣ በጥይት የተመቱ ሰዎችን እና ተገድደው የተደፈሩ ሰዎች በአምቡላንሶች ወደ እዚህ ሆስፒታል ይመጣሉ። የከተማው ምርጥ ምርጥ የቀዶ ጥገና ሀኪሞች እና ስፔሻሊስት ዶክተሮችም እዚህ ሆስፒታል ውስጥ ነው የሚሰሩት። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነው በእርጋታ የሚናገረው ኢራናዊው ዶ/ር ሮበርት ራህማትያን ትሬይን ቀዶ ጥገና ሠርቶ ሲጨርስ ነበር ጉድማን እና ጆንሰን ከሆስፒታሉ
የደረሱት።
“መቼ ነው የምናናግረው?” ብሎ ጉድማን ሀኪሙን ጠየቀና በማስከተልም
“እሱ ስለ አደጋው የሚነግረንን ነገር ማወቃችን በጣም ይጠቅመናል።”
ዶ/ር ራህማትያን ለስድስት ሰዓት ያህል ትሬይን ቀዶ ጥገና ሲሰራ ስለዋለ በጣም ደክሞታል። አሁን ደግሞ እነዚህን ፖሊሶች የሚያወራበት እና የሚያሳምንበት ስሜት ውስጥ አይደለም።
የምናገረው የገባህ አልመስለኝም መርማሪ ፖሊስ ጉድማን” አለው
ትግዕስቱን እንዳጣ በሚያሳብቅበት መልኩ። “ሚ/ር ሬድሞንድ እጅግ በጣም
ለሞት በሚያደርስ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚገኘው። በዚያ ላይ ደግሞ አሁን
ለቀዶ ጥገናው የተሰጠው ማደንዘዣ ውስጥ ስለሚገኝ ብታወራውም ምንም
ሊሰማህ አይችልም፡፡ ምንም እንኳን የቀዶ ጥገናው በመልካም ሁኔታ
የተካሄደ ቢሆንም የግራ ልቡ ላይ የደረሰው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ
ስለሆነ የሚተርፍ አይመስለኝም::” አለው፡፡
ይህንን የሰማው ጉድማንም አይኑን በግርምት በለጠጠ፡፡ የቀዶ ጥገና
ሀኪሙም “ልቡ ላይ በስለት ተወግቷል።” ብሎ በማስከተልም “ቀዶ ጥገናውን በደንብ ያደረግንለት ቢሆንም የልቡ ውግ ግን ለሞት የሚያደርስው ይመስለኛል።”
“ምንም አይነት ምክንያት ብትሰጠንም ልናናግረው ግድ ይለናል።” አለ
እና ጆንሰን በትዕቢት ድምፅ፡፡በማስከተልም እንደምንም ብለህ
ልትቀሰቅስልን ትችላለህ?”
“አይሆንም” ብሎ በላብ የወረዛውን የመርማሪ ፖሊሱን ሽሮፕ ቀለም
ያለውን ሸሚዙን በጥላቻ አይን እየተመለከተ “አልችልም አልቀሰቅሰውም” አለው።
“እሺ ከቀዶ ጥገናው በፊት አደጋውን ስላደረሱበት ሰዎች ተናግሮ ነበር?”
አለ ጉድማን ባልደረባው ጆንሰን ነገሮችን ከማበላሸቱ በፊት ስለ ትሬይ ቅድመ ቀዶ ጥገና ሁኔታ ለማወቅ በማስብ፡፡ “እዚህ ሲደርስ ራሱን ያውቅ ነበር? ይቅርታ ስለተጫንኩህ ዶ/ር ራህመታይ። ለምን መሰለህ ትሬይ ሬይሞንድ ላይ ግድያውን ለመፈፀም ያሰበው ግለሰብ ከጥቂት ቀናት በፊት አንዲት ወጣትን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለው ሰው ጋር ግንኙነት አለው ብለን ስለምናስብ ነው። ነገሩ የግድ አስፈላጊ ነው” ብሎ በልምምጥ ስሜት
ጥያቄውን አቀረበ።
“ገባኝ” አለ እና ዶክተር በማስከተልም “ከቀዶ ጥገናው በፊት ምን እንዳወራ እኔ አላውቅም። ምናልባት እዚህ ሆስፒታል ድረስ ያመጡት ፓራሜዲስ ሰዎች ሊያውቁ ይችላሉ እና የእነርሱን ሥም ልሰጣቸሁ እችላለሁ።” ብሎ ዞር ሲል ጆንሰን ትሬይ የተኛበትን ክፍል የበር እጀታ ይዞ በሩን ለመክፈት ሲታገል በመመልከቱ በቁጣ አይኑ እየነደደበት “ ሂድ ከዚህ!
ምን እየሰራህ ነው? አንተ እዚያ ክፍል መግባት አትችልም!” ብሎ ጮኸበት።
“ኦ! እችላለሁ እዚህ ክፍል መግባት ይኖርብኛል” ብሎ ብልግና
በሚታይበት ድምፅ መለሰለት እና በመቀጠልም “ያ ልጅ ይሞታል ብለሀል
አይደል? ስለዚህ ከመሞቱ በፊት አንድ አንድ ጥያቄዎችን ልጠይቀው ግድ
ይለኛል።”
“ነገርኩህ እኮ አሁን በማደንዘዣ ምክንያት ሰመመን ውስጥ ስለሆነ የምታወራውን አንድም ነገር አይሰማም።”
“ስለዚህ አላስቸግረውም ማለት ነው። አይደል?” ብሎ ጆንሰን መለሰለት
እና “ዶክ አንተ ሥራህን ስርተህ ጨርስሀል። አሁን ደግሞ እኛ ሥራችንን
መስራት ይጠበቅብናል።” ዶ/ር ራህመት ያንም ኧረ የሆነ ነገር አድርግ እና
አስቁመው? በሚል አይን ጉድማንን በአይኑ ተለማመጠው፡፡
“በጣም ይቅርታ” ብሎ ጉድማን ቢንተባተብም ባልደረባውን ጆንሰን በሩን
ከፍቶ ትሬይ ወደ ተኛበት ሪከቨሪ' ክፍል ከመግባት አላገደውም፡፡
“አዝናለሁ! ይሄ እኮ ንቀት እና ማን አለብኝነት ነው!” ብሎ በንዴት
እየተወራጨ የሆስፒታሉን የጥበቃ ሰዎችን ይዞ ለመምጣት ጥሎት ሄደ፡፡
ይሄኔም ጉድማን ጆንሰንን ተከትሎ ወደ ሪከቨሪው ክፍል ገባ። እና “ሁል ጊዜ
እንደዚህ ደረቅ መሆን አለብህ?! ሀኪሙ እየተባበረን አልነበረም እንዴ?” አለው፡፡ “እየተባበረን አልነበረም!” አለው እና ጆንሰን አልጋው ላይ የተለያዩ
ቱቦዎች እና የህክምና ዕቃዎች የተሰኩለትን ትሬይ ሬይሞንድን መመልከት ጀመረ። ደረቱ ላይ በትልቅ ነገር ታሽጓል። ክንዶቹ እና አንገቱም በስለት ተተልትሏል። ፊቱ ደግሞ ልክ እንደ ሊዛ ፍላንገን በጣም ስለተተለተለ
ማንነቱ አይለይም ነበር።
“ልጁ ሊሞት ትንሽ ጊዜ ነው የቀረው ሉው” ብሎ ጆንሰን መለሰ እና
“ይሄው የልጁን ነገር እንደምታየው ስለሆነ እሱን ማውራት ያለብን አሁን ብቻ ነው።” አለው፡፡ “እሱን አውቃለሁ” ብሎ ተናገረ እና “ግን…” ብሎ ሊቀጥል ሲል በጆንስን ወፋፍራም መዳፎች የሚወጣው የጭብጨባ ድምፅ አቋረጠው። ጆንሰን ሰመመን ውስጥ ከሚገኘው የትሬይ ፊት በትንሽ ርቀት ላይ ሆኖ
“ተነስ! ተነስ! ማን እንደዚህ እንዳረገህ ንገረን። ትሬይ!” ብሎ ጮኸ፡፡
“ሚክ ምን እየሰራህ ነው ተው እንጂ...”
“ተነስ! ንቃ አንተ እበት! በል አሁኑኑ አይንህን ግለጥ!”
“በእየሱስ ክርስቶስ ስም!” ብሎ የሚክን ትከሻ ይዞ ወደ ኋላ እየጎተተው
“እንዴ ተው እንጂ! ምን ነካህ?” አለው።
ጆንሰንም ወደ ጉድማን ዞሮ ንዴቱን ለመግለፅ በቦክስ ፊቱን ሊመታው
እየተዘጋጀ እያለ ትሬይ አይኖቹን ከፈተ እና ተስፋ በቆረጠ ድምፅ በሀይል
መጮህ ጀመረ፡፡
“ኧረ አላውቅም!” ትሬይ እጆቹን እንደ እብድ እያወራጨ ቃል አወጣ፡፡
“ኧረ እባክህ! በእግዚአብሔር! እኔ እኮ አላውቅም!” እያለ ጭንቅላቱን ግራ
እና ቀኝ በሀይል መወዝወዝ ጀመረ። ይሄኔም ከሆዱ ወደ ጉሮሮው የሚመጣ
የእንስሳ ማጓራት የመሰለ ድምፅ መጣ። ይሄኔም አንደኛው ትሬይ ላይ የተነሳው ማሽን መጮህ ጀመረ። የማሽኑን ድምፅ እና የትሬይን ጩኸት የሰሙት የህክምና ሰዎችም ትሬይ ወደተኛበት ክፍል በር ከፍተው ሲገቡ ትሬይን በድን ሆኖ ነበር ያገኙት።
ከህክምና ሰዎቹ ውስጥ አንደኛው “ማን ነው እዚህ ክፍል ያስገባችሁ? ይሄ እኮ የህክምና ባለሙያ ሰዎች ብቻ የሚገቡበት ክፍል ነው። አሁን ውጡ!” ብሎ ጮኸባቸው፡፡ ጆንሰንም ለአፍታ ያህል አመነታ እና ክፍሉን ለቅቆ የሚወጣውን ባልደረባውን ጉድማንን ተከትሎት ከክፍሉ ወጣ፡፡
ኮሪደሩ ላይ ሲደርሱም ጉድማን ወደ ጆንሰን ፊቱን አዙሮ “ዐእያደረግክ
ያለውን ነገር ታውቀዋለህ? ይህ ድርጊታችን እኮ በህግ የሚያስቀጣን ነገር
ነው። እንዴ የልጁ ቤተሰቦች ለጣቢያችን ቅሬታቸውን ቢያቀርቡስ?” ብሎ ጠየቀው።
ጆንሰንም በጉድማን ጥያቄ ከት ብሎ ከሳቀ በኋላ “ቅሬታቸውን ቢያቀርቡስ ምን የሚመጣ ይመስልሀል?” አለው ፍፁም ዘረኝነቱን በሚያሳይ

👍4
ድምፀት። ከጆንሰን ድምፅ ጉድማን የተረዳው ነገር ቢኖር እንደ ማርሻ ሬይሞንድ ያሉ ደሀ ጥቁሮችና የዌስት ሞንድ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን
ለፖሊስ ቢያቀርቡ ማንም የሚሰማቸው እንደማይኖር ነበር።
ይህንን የጆንሰንን ስሜት የተረዳው ጉድማንም ከዚህ ሰው ጋር ያጣመረው ዕድሉን በጣም ጠላው።
“የት ነው የምትሄደው?” ብሎ ጆንሰንን ከኋላው እየተከተለ ጠየቀው፡፡
“ነገሩ ወደ መራን ቦታ ነዋ። ያው እንዳየኸው ልጁ የሚተርፍ አይደለም። አሁን ግን ቢያንስ አንድ ነገር እርግጠኛ መሆን የቻልን መሰለኝ”
“ብለህ ነው? ምን?”
“አዎን ይሄ ትሬይን ሞቷል ብሎ ጥሎት የሄደው ሰው በዚህ ሳምንት ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ሊዛ ፍላንገንን ገድሎ ጥሏታል።”
“እሺ” አለው ባልደረባው ሁለቱን ነገሮች በማገናኘቱ ለምን ሊደሰትዐእንደቻለ ስላልገባው፡፡ “አንተው ራስህ እስቲ መልስልኝ፡ እነዚህ ሁለት
ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች በጋራ የሚያውቁት አንድ ሰው ማን ነው?” ብሎ
ጠየቀው።
ጉድማንም የጆንሰን ጥያቄ ወዴት እንደሚያመራ ስላወቀ ነገሩን
ባይወደውም ጆንሰን ያነሳውን ሀሳብ መጣል አልቻለም።
ሁለቱም እንደሚያውቁት ደግሞ ሊዛ ፍላንገን እና ትሬይ ሬይሞንድ በጋራ የሚያውቋት ሴት ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ናት፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሌሊቱ ሊነጋጋ አቅራብያ ዶ/ር ኒኪ ሮበርትስ ከእንቅልፏ ብንን ብላ
ተስፈንጥራ ተነሳች እና ከአልጋው ላይ ቁጭ ብላ ቁና ቁና መተንፈስ ጀመረች፡፡ በላቧ የተዘፈቀው ቲሸርቷ ከሰውነቷ ላይ ተጣብቋል። ልክ በረዶ ከተጨመረበት
ውሀ ውስጥ እንደወጣ ሰውም ጥርሶቿ ጭምር እየተንቀጫቀጨ መላ ሰውነቷ ይንዘፈዘፋል። ቀና ብላ የጠረጴዛ ሰዓቷን
ስትመለከት ከለሊቱ 10:52 መሆኑን አየች፡፡ ተመልሳም አልጋዋ ላይ
በጀርባዋ ዘፍ አለች እና ለመተኛት ሞከረች።
ይሄ ከእንቅልፏ አባኖ ያስነሳት አስፈሪ ህልሟ ልክ ከዚህ በፊት እንደምታያቸው አይነት ነው። በቃ ባሏ ዶውግ ለሞት የሚያደርስ አደጋ ውስጥ ሆኖ እሷን እንድታድነው ለምኗት እሷም ደግሞ ልመናውን ሳትሰማው ስትቀር እና ልትረዳውም ባለመፈለጓ ጭምር ሲሞት ነበር::በዚህም ድርጊቷ በህልሟ የፀፀት ስሜት ይሰማታል። አንድ አንዴ ውሃ
ውስጥ እየሰመጠ እያለ እሷም የምታግዘው ሁኔታ ውስጥ ሆና ሟቹ ባሏ
ዶውግ ደግሞ መኪና ውስጥ ሆኖ የመኪናውን ፍሬን እየደፈጠጠ ፍሬን
ሊይዝ ሲል አይሳካለትም። እሷ ግን በእጇ የመኪናውን ፍሬን ሊይዝ እና
ሊያስቆመው የሚችል ሪሞት ኮንትሮል ብትይዝም ሪሞቱን ለመጫን ስላልፈለገች ብቻ መኪናው ተገልብጦ እሱ ሲሞት ታያለች፡፡
የዛሬው ህልሟ ደግሞ እሱ እና እሷ ከገደል ጫፍ ላይ እየተራመዱ እያለ ዶውግ ያዳልጠዋል። እንደ ምንም ብሎ ከገደሉ ጫፍ ላይ ያለ ድንጋይን በእጁ አጥብቆ ይዞም እሷን ወደ ላይ እጁን ይዛ እድትጎትተው ይለምናታል፡፡ እሷ ግን ሆነ ብላ ድንጋዩን የያዘበትን የእጁን ጣቶች ፈልቅቃ እያስለቀቀች ወደ ታች ከገደሉ ስር ወርዶ እንዲፈጠፈጥ ታደርገዋለች። በዚህ
ድርጊቷ የተሰማት ግን ሀዘን ሳይሆን ከእሱ የመለየት ፍላጎት እና ከፍተኛ
የሆነ የሀይለኝነት ስሜት ነበር።
የዚያኑ ቀን ላይ ህልሟን ካየች ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ኒኪ ጓደኛዋን ግሬቸን አድልረን ለቁርስ አገኘቻት።
“ዛሬም ያንን ህልም አየሁ እኮ” አለቻት ጓደኛዋ እና እሷ ግሎሪየስ ግሪን
ካፌ ውስጥ ቁጭ እንዳሉ።
“ስለ ዶውግ ነው ህልምሽ?” ግሬቸን ጠየቀች፡፡
.…
ኒኪም አዎን ለማለት ያህል ራሷን ከፍ እና ዝቅ አድርጋ በማስከተልም
“ግን የዛሬው ህልም ከሌሎቹ ህልሞች ሁሉ የከፋ ነበር።”
ኒኪ ለጓደኛዋ ግሬቸን ሌሊት ላይ ስላየችው ህልም እየነገረቻት እያለ
አንድ ወጣት ቆንጆ የካፌው አስተናጋጅ ሊታዘዛቸው አጠገባቸው ቆመ። ኒኪ
የተለመደውን እንቁላል ጥብስ ከተጠበሰ ትሪፕል ሾት ላቴ ጋር ስታዝ ግሬቸን ደግሞ በስሱ የተጠበስ ቀይ ስር እና የተጠበሰ በቆልት አዘዘችው።ግሬቸን እና ኒኪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ ጓደኛሞች ናቸው።
የልብም ጓደኛሞች ናቸው። አዋቂ ከሆኑ በኋላ ግሬቸን ከሚመጣው እና
ከሚሄደው የሰውነት ውፍረቷ ጋር ትግል ውስጥ ናት። ኒኪ እንደምታውቀው ከሆነ የግሬቸን ውፍረት ባይቀንስም ግሬቸን ግን ሁል ጊዜ ውፍረትን የሚቀንሱ ምግቦችን በየጊዜው እየቀያየረች ስትበላ ነው::
ፊትሽ ላይ ድካም ይታያል!” ብላ ግሬቸን ለኒኪ ከነገረቻት በኋላዐበማስከተልም “ይሄውልሽ የእንቅልፍ ችግር ካለብሽ ማታ ማታ የምትበያቸውን ነገሮች በማስተካከል ያለምንም ረብሻ በደንብ መተኛት ትችያለሽ። እሺ ማታ ራትሽን የበላሽው ምንድነው?” ብላ ጠየቀቻት፡፡
"በርገር” ብላ ኒኪ መለሰችላት።
“አየሽ!” ብላ ሀሳቧ ትክክል በመሆኑ ደስ እያላት ወንበሩ ላይ ጀርባዋን በደንብ ለጥፋም “ቀይ ስጋ እሱማ አስፈሪ ቅዠት ነው ይዞብሽ የሚመጣው።”
“ኧረ ከምርሽ ነው?”
አዎ እሱን የሚበልጠው ደግሞ ቺዝ በርገር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቺዝ
በርገር አይደለም የበላሽው?” ብላ ዜማ ባለው ድምፅ ኒኪን ጠየቀቻት።ኒኪም ከት ብላ ከሳቀች በኋላ እውነትም ቺዝ በርገር ራቷን እንደበላች ነገረቻት። በማስከተልም ህልሟ ግን የተከሰተው በበላችው
ምግብ እንዳልሆነም ጭምር አስረዳቻት። የኒኪ መልስ ያልጣማት ጓደኛዋ ግሬቸንም ኮስተር ብላ
“እና ምንድን ነው ምክንያቱ ትያለሽ?” ብላም ጠየቀቻት፡፡
“እኔንጃ፡፡ ምናልባት የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማኝ ይሆን?” ግሬቸንም የኒኪ መልስ ስላልገባት “ይሄ ውሃ የማያነሳ ሀሳብ ነው። ለምንድነው የጥፋተኝነት ስሜት የሚሰማሽ? ዶውግ የሞተው እኮ በመኪና አደጋ ነው።”
“አውቃለሁ”
“አንቺ ደግሞ ለዶውግ የምትገርሚ ምርጥ ሚስቱ ነበርሽ ኒኪ ልክ ነው የምገርም እና ምርጥ ግን ልጅ የማልሰጠው ሚስቱ ነበርኩኝ”
ብላ ኒኪ ሀሳቧን ተናገረች።.....

#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
...“ናትናኤል...” ከደረቱ ላይ ቀና አለች ርብቃ፡ ናትናኤል…” በተቻላት ድምጿን አለስልሳ ስሙን ጠራችው፡፡
“ናትናኤልዩ…” ድምጿ በጭንቀት ተንቀጠቀጠ፡፡
“ምነው?” ጣቶቹን ልኮ ፀጉሯን አፍተለተለው ግራ እጇን በጀርባዋ
ቁልቁል ሰድዶ የሚወደውን ገላ ሳብ አቀፍ አደረገው፡፡ ቀኝ እጁን መለስ አድርጎ የሌሊት ቀሚሷን ወደላይ ሰበሰበው፡፡ ቀሚሷ ጭኖቿን አልፎ ወገቧ
ዙሪያ አሰፈሰፈ::
“ናትናኤል አንድ የምነግርህ ነገር ነበር፡፡” ድምጿ እንደቢራቢሮ ክንፍ፡ ተርገበገበ፡፡
“ምንድነው? ንገሪኝ” አላ ናትናኤል ድምጿ አለቅጥ ሲለሰልስበት ፀጉሯን ከፊቷ ላይ ወደኋላ እየመለስ በደሪቱ ቁልቁል እየተመለከታት፡፡
“እስካሁንም ያልነገርኩህ ፈርቼህ ነው፡፡ ናቲዩ እንባዋን ለማምጣት ታገለች:: የጠፈራት ድንጋጤ ምራቋን ከአፏ ውስጥ አደረቀው፡፡
“ለምን…ምንድነው?” እጆቹ ቦታቸውን ያዙ ጭኖቿ ውስጥ
ናትናኤል የኔ ጌታ…” ሳታውቀው አይኖቿ በእንባ ግጥም አሉ። ገና! ና! ምነ ተይዞ ተንሰቅስቃ ካላለቀሰች ካልተነፋረቀች በዚህ ጨለማ ኣይኗ ስር ያቆረዘዘው እንባ የት ታይቶ አሰበች፡፡
“ምንድነው የሆንሽው?” ሁኔታዋ ግራ ሲገባው ድንገት በሁለት እጆቹ ሁለት ጉንጮቿን ይዞ ቀና አደረጋት፡፡
“ናቲዬ…ና…” ድምጿ እንደ ወፍ ትንፋሽ ሳሳ፡፡
“ምንድነው ንገሪኝ ርብቃ፡፡” ጉንጮቿን እንደያዘ ደግሞ ጠየቃት::
“ናቲዬ…”
“ኪርርር - ር!”
ከተዘጋው የመኝታ ቤት በር ወዲያ የስልክ ጥሪ ተሰማቸው፡፡
“ስልክ ነው…አይደል?” ናትናኤል ከተኛበት ቀና አለ።
“ኪርርር ር!”
ናትናኤል ቀልጠፍ ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳና ነጠላ ጫማውን አጥልቆ የመኝታ ቤቱን በር ከፍቶ ወጣ፡፡
“ሃሉ” አለ እንግዳ መቀበያ ክፍል ውስጥ ያለውን ስልክ አንስቶ፡፡
“ሃሎ ናትናኤል?” አለ የታፈነ የሚመስል ጎርነን ያለ ድምጽ፡፡
“ነኝ..ማን ልበል?”
“አብርሃም ነኝ፡፡ እንድንገናኝ እፈልጋለሁ፡፡ አሁን በአስር ደቂቃ ውስጥ እንድትደርስ፡ ሆቴል ዲ-ኣፍሪክ ነው ያለሁት… ትስማኛለህ? የመኪናሀን ትንሹን መብራት ሳታጠፋ በሩ ላይ መኪናህን አቁም::
እጠብቅሃለሁ…”
“ሃሎ.… ሃሎ” ናትናኤል ተጣራ፡፡ ስልኩ ግን ተዘግቶ ነበር፡፡
ለጥቂት ሴኮንዶች የስልኩን መነጋገሪያ እንዳንጠለጠለ አመነታ፡፡
ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ ለሶስት ሰዓት ሩብ ጉዳይ፡፡ አብርሃም ውጪ የማምሸት ፀባይ የለውም፡፡ እስከሚያውቀው ድረስ፡፡ ደግሞስ ቀን ያልተነጋገሩት አሁን የሚነግረው ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? ስልኩንስ ለምን ቸኩሎ ዘጋ? አነጋገሩም ጥድፊያና ችኮላ የተቀላቀለው ነበር፡፡ ምን ሆኖ ይሆን? ናትናኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ክፉ ታሰበው፡፡ አደጋ ደርሶበት ይሆን?
ድምፁም ትክክል አይደለም ጎረነነ፡፡
“ማነው? ምን ሆንክ?” አለች ሲቻኮል ስታየው ርብቃ ከተኛችበት ተነስታ አልጋው መሃል ቁጭ እያለች፡፡
“ደህና ነኝ:: ኣብርሃም ነው፡፡” ቀልጠፍ ብሎ ልብሱን ይለባብስ ጀመር፡፡
“እና የት ልትሄድ ነው በሌሊት?” ከላይዋ ላይ ብርድ ልብሱን ገፋ ተነሳች፡፡
“ሆቴል ዲ አፍሪክ ነው ያለኝ፡፡ ትንሽ ችግር ሳይገጥመው አይቀርም፡፡ እንጃ አነጋገሩ ትክክል አይደለም፡፡” ናትናኤል ፈጠን ብሎ ሱሪውን አጠለቀ:: ሸሚዙን እስኪለብስ መቆየት አልፈለገም፡፡ ድፍን አንገት ዐያለውን ወፍራም ሹራቡን አጠለቀና ፀጉራም ካፖርቱን ከቁም ሳጥን ውስጥ ጎትቶ አወጣው፡፡
“ምን ሆንኩ አለ?” አለች ርብቃ ግራ ተጋብታ፡፡
“ዛሬ ጠዋት አግኝቼው ነበር ለአንድ ጉዳይ፡፡ ለምን እንደፈለገኝ ግን
እልነገረኝም፡፡ ዝም ብሎ 'ና ነው ያለኝ፡፡” ናትናኤል የሚለው ሲጠፋው ትከሻውን ሰበቀና ተወው፡፡ ከራስጌ የመኪናውን ቁልፍ አነሳና አልጋውን ዞሮ
እቅፍ አድርጎ ግንባሯ ላይ : ሳማት፡፡ “ተኚ፡፡ አልቆይም፡፡ እሺ በሩን ከውጭ ቆልፌ በበር እወረውረዋለሁ።” እየተቻኮለ ወጣ፡፡ ዘግቶት የሄደው በር ላይ አፍጥጣ ቀረች፡፡
አሳንሰሩ እስኪመጣ መጠበቅ አልፈለገም፡፡ አስር ደቂቃ ነው ያለው
አብርሃም:: ሁለት ሁለቱን ሁለት ሁለቱን እየዘለለ በፎቁ ቁልቁል ተንደረደረ፡፡
“ምነው ደህና?አሉት የማታው ዘበኛ ወፍራም የሌሊት ካፖርታቸውን እንደደረቡ ከተኮፈሱበት አጥር ላይ እየተነሱ።
“ሠላም ነው።” ፈጠን ብሎ መኪናው ውስጥ ገባ፡፡
መኪናውን አስነስቶ ከግቢው ወጣ፡፡ መንገዱ ጭር ብሏል፡፡ ብንብን
የሚለው ካፊያ የመኪናውን የፊት መስታወት በጥቃቅን ነጠብጣቦች
ሽፈነው። የዝናብ መጥረጊያውን ተጫነና ፍጥነቱን ጨመረ፡፡ ብሔራዊ ቲአትር ኣጠገብ ሲደርስ ዝናቡ ሃይል ጨምሮ የመኪናውን ጣሪያ ያቀልጠው ጀመር፡፡ ያለ እረፍት ውልብ ውልብ የሚለው የዝናብ መጥረጊያ ትንፋሽ
ያጠረው. መሰሎ፡፡ ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ እራት ሊሞላ ጥቂት ደቂቃዎች
ቀርተዋል፡፡ ዘግይቷል። ፍጥነቱን ጨመረ፡፡ ሰንጋ ተራ ያለው የመንገድ
መብራት ቦግ ብሏል፡፡ ቀዩ የትራፊክ መብራት ከመሬቱ ላይ ሲያርፍ በዝናቡ
የተዘፈቀው አስፋልት የእሳት ጎርፍ የፈሰሰበት ይመስል ደም ይመስላል፡፡
ናትናኤል ከጎንና ከጎን የሚመጣ መኪና እንዳለ ተመለከተ፡፡ መስቀልያው
መንገድ ንፁህ ነው አማን ነው፡፡ ቤንዚን መስጫው ላይ ቆመበት፡፡
መኪናው ቀዩን የትራፊክ መብራት አልፉ ተሽቀነጠረች፡፡ ሜክሲኮ አደባባይ
እንደደረስ ወደቀኝ ታጠፈና ጎኑን ሰጥቶ ወደቆመው ሆቴል ተጣደፈ፡፡
መንገድ ዳር ከተገተረው ሆቴል አፋፍ ሲደርስ ጥግ ይዞ ቆመ:: ሞተሩን አጠፋና መብራቱን ቀንሶ ትንሹን መብራት እንዳበራ ተጠባብቀ።.
እልሁ ቢወጣለትም ዝናቡ አሁንም ሳግ ይተናነቀዋል፡፡ የዝናብ መጥረጊያው በዝግታ እላይ እታች ይላል፡፡ የፊት መስተዋቱ በዛ ትንፋሹ በጉም ተሸፍኗል፡፡ እጁን ሰድዶ ወለወለው፡፡ ዙሪያውን ተመለከተ። የሆቴሉዐደንበኞች ያቆሟቸው ጥቂት መኪናዎች ከፎቁ ስር በተርታ ተኮልኩለዋል መንገዱ ጭር ብሏል። ከመንገዱ. ባሻገር ጥጉን ይዛ አንድ ሲትሮይን ቆማለች። አብርሃም የለም
“አሌ ቀጥል፡፡” አለ የአረብ ገጽታ ያለው ከሲትሮይኗ መሪ ኋላ የተቀመጠው ሰው በፊረንሳይኛ፡፡ “አስታውስ፤ ጊዜ አትውሰድ፤ መስሎቱን አንኳኳ፡፡ ዝቅ እንዳደረገ አንድ ፡ ብቻ ክተትለት፡፡ መኪናውን አዙሬ እጠብቅሃለሁ።”
አጠገቡ የተቀመጠው ጥቁር ሰው ጭንቅላቱን በስምምነት ነቀነቀ፡፡
ከደረበው ካፖርት የጎን ኪስ ውስጥ ሽጉጥ አወጣና በግራ እጁ ይዞት
የነበረውን ቱቦ የመሰለ የድምጽ ማፈኛ ገጠመለት፡፡ በአውራ ጣቱ የሽጉጡን
መዶሻ ወደኋላ መልሶ የሲትሮይኗን በር ከፍቶ ወጣ።
ዝናቡ ይሁን ወይ አለቅጥ የረዘመው ቁመቱ ሰውየው ከትከሻው ጎበጥ ያለ ነው፡፡ በቀን የያዘውን ሽጉጥ በካፖርቱ የጎን ኪስ ውስጥ ሽጉጦ መንገዱን ተሻግሮ ኣነስተኛ መብራቷን እንዳበራች ወደቆመችው 131 ፊያት አመራ፡፡
ዝናቡ ይወርዳል፡፡ የዝናብ መጥረጊው ሳይሰለች ከወዲያ ወዲህ ይንቀዠቀዣል፡፡ ናትናኤል የመኪናውን ትንሽ መብራት ሳያጠፋ አይኖቹን በሰፊው ከፍቶ የሆቴሉን በር ይመለከታል፡፡ ዝናቡ ብን ብን ይላል፡፡ አብርሃም የለም፡፡
ድንገት የመኪናው መስኮት ሲንኳኳ ተሰማው:: ናትናኤል ፊቱን መለስ አድርጎ ተመለከተ፡፡ በዝናቡ ነጠብጣብ በተሸፈነው መስኮት ውስጥ የታየው ግን የተሰባበረና የተወለጋገደ ምስል ነበር፤ ቢሆንም የስው ቅርጽ መሆኑ ይለያል፡፡ አብርሃም?' ናትናኤል እጁን ሰድዶ መስኮቱን ዝቅ አደረገ፡፡
የዝናብ ካፖርት ደርቦ ብንብን በሚለው ዝናብ ውስጥ የቆመው ሰው አብርሃም ኣለመሆኑን ወዲያው ተረዳ፡፡ ደነገጠ፡፡ ስህተቱ ትዝ አለው!ያጠፋው ጥፋት ፊቱ ሳይ ድቅን አለበት፡፡
“አቤት…” እለ የሚከተለው

እየታወቀው፡፡
“መንጃ ፈቃድ።” አለው ትራፊክ ፖሊሱ ሠላምታ ከሰጠው በኋላ።የሠንጋ ተራን የትራፊክ መብራት ጥሶ ሲያልፍ ነበር ጥግ ይዞ የነበረ ሞተረኛ ትራፊክ ፖሊስ ሞተር ብስክሌቱን አስነስቶ በዝናብ ውስጥ የተከታተለው፡፡
ናትናኤል ደረቱን ዳበሰ፡፡ ሹራብ ድፍን ሹራብ፡፡ መንጃ ፈቃዱስ?
ኮቱ ኪስ ውስጥ? እቤት፤ የሚከተለው ጭቅጭቅ ሲታስበው ጭንቅላቱን
ይፈልጠው ጀመር፡፡
“ይቅርታ ወንድም ችግር ገጥሞኝ…” የሚለው ጠፋው ናትናኤል፡
“መንጃ ፈቃድ ጌታዬ፡፡” ፈርጠም ኣለ ትራፊክ ፖሊሱ
ናትናኤል መኪናው ውስጥ ተኮፍሶ መደራደሩ እንደማያዛልቀው ሲረዳ ቀልጠፍ ብሎ በሩን ከፈተና ከመኪናው ወረደ፡፡ ትራፊክ ፖሊሱ ወደኋላው አፈግፍጎ በዝምታ ይመለከተው ጀመር፡፡
“ወንድም…. ችግር አጋጥሞኝ ድንገት ከቤት ቸኩዬ ነው የወጣሁት መብራቱንም የጣስኩት ለዚህ ነው፡፡ ይቅርታ አድርግልኝ፡፡” ወደጎን ሸፈፍ ሸፈፍ እያለ የሚዘንበው ዝናብ ፊት ፊቱን አለው፡፡
በመጀመሪያ መንጃ ፈቃድዎን ጌታዬ፡፡”
“እሱን ነውኮ የምልህ፡፡ አየህ ቸኩዬ ስወጣ”
“መንጃ ፈቃድ የሎትም? በጨለማው ውስጥ ትራፊክ ፖሊሱ ፈገግ ያለ መሰለው::
“አለኝ . አላኝ፡፡ እቤት እረስቼው ስለወጣሁ ነው፡፡” ናትናኤል በራሱ ተናደደ፡፡
“እሺ ጌታዬ ወደ ጣቢያ ሄደን ብንነጋገር ይሻላል።”
“ቆይ ቆይ እንደሱ ኣይደለም ረጋ በል እንጅ፡፡”
“ይቅርታ ጌታዬ ጊዜ ባናጠፋ ይሻላል፡፡ ዝናብ ውስጥ ነው ያለነው፡፡”
“መጀመሪያ የምልህን ስማኝ::” አለ ናትናኤል ሳይታወቀው ንዴት
የገዛ ህሊናውን እየሰለበው፡፡
እዚህ ድረስ መጥቶ አብርሃምን ሳያገኝ ሊሄድ አይችልም! በፍጹም አብርሃም አንድ አይነት ችግር ገጥሞት እንደሆነስ?
“እየው… ምን መሰለህ... ጠጋ አለ ናትናኤል ወደትራፊክ ፖሊሱ፡፡
የሚበጀው መለማመጥ ነው! ረጋ ብሎ ማባበል፤ ክንዱን ያዝ አድርጎ
እሽሩሩ ማለት፡፡
“በህግ አምላክ!” አለ የትራፊክ ፖሊሱ ናትናኤል ሲጠጋው ወደኋላው አፈግፍጎ እጁን ወገቡ ላይ ወዳንጠለጠለው መሣሪያ አየሰደደ፡፡ ቀጥል ማለት ቀጥል ነው”
ናትናኤል መኪናው ውስጥ ገብቶ¨ ሞተሩን አስነሳና ወደ መንገድ ገባ፡፡ ሮጥ ብሎ የሞተር ብስክሌቱ ላይ ጉብ ያለው የትራፊክ ፖሊስ ፍጥነት ሰጠት አድርጎ ከጎን ከጎኑ እየሄደ ያናግረው ጀመር። ። .
· “ቀስ እያልክ አሽከርክር አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ፡፡” "
ናትናኤል የመኪናውን መስኮት ዘጋበት::
ከፖሊስ ጣቢያው ደጃፍ እንደደረሱ ናትናኤል ከአጥር ውጭ መኪናውን አቁሞ ሲወርድ ትራፊክ ፖሊሱ ቁልፉን ተረከበው፡፡
“ውስጥ አንግባ፡፡” አለ ትራፊክ ፖሊሱ ሰቅንድቡ ወደ ጣቢያው መግቢያ እያመለከተ፡፡
ናትናኤል ፊት ፊት እየቀደመ ተከታትለው ወደ ጣቢያው አመሩ፡፡
“መብራት ሲጥስ ተከታትዬ አስቆምኩት፡፡ መንጃ ፈቃድም የለውም:”አለ ትራፊክ ፖሊሱ ከጠባቡ ጠረጴዛ ኋላ ለተቀመጠ ተረኛ መኮንን የናትናኤልን የመኪና ቁልፍ እያቀበለው::
“መታወቂያ::” አለ ተረኛ መኮንኑ ፊቱን ወደናትናኤል መልሶ በተቀመጠበት አንጋጦ እየገመገመው:: አልያዝኩም፡፡”
ተረኛ መኮንነና ትራፊክ ፖሊሱ ተያዩ፡፡ ሁኔታው እንዳላማራቸው ግልጽ ነበር፡፡
“መንጃ ፈቃድ የለህም፤ መታወቂያም የለህም፡፡ ይህ ሁሉ አንሶህ ወንጀል ትፈጽማለህ፡፡” ተረኛ መኮንነ ፊቱን ወደ ናትናኤል መልሶ አፈጠጠበት::
“ምን ወንጀል ፈጸምኩ ደግሞ? ” ናትናኤል ተገረመ::
“ጥሰኸው የሄድከው መብራትኮ የዳንስ ቤት አምፑል አይደለም፡፡”
አለ ትራፊክ ፖሊሱ በተራው እየተገረመ፡፡
ናትናኤል በራሱ ጥፋት ብግን አለ፡፡
“ምንም ወረቀት የለህም ማለት ነው?” ተረኛ መኮንኑ ጠየቀው፡፡
“የምን ወረቀት?” ናትናኤል ከዚህ በኋላ የፈለገው ቢመጣ ግድ ያለው አይመስልም፡፡
“አንድ ሰው'ኮ ማንነቱን የሚገልጽ ወረቀት ሊያዝ ይገባዋል::
እንደው እንደ እንሰሳ ኣንመላለስም::” ተረኛ መኮንኑ ቆጣ አለ፡፡
“ተናገርኩኮ… ከቤት ስወጣ ችግር አጋጥሞኝ ተጣድፌ ስለነበር የመታወቂያ ወረቀቶቼን ሁሉ ኮቴ ውስጥ ነወ ትቼ የወጣሁት፤መብራቱንም የጣስኩት ለዚህ ነው፡፡” በስጨት አላ ናትናኤል፡፡
“አሃ ቁጣም! አለ እንዴ!?” አለ ተረኛ መኮንነ ደስ የማይል ፈገግታ
እያሳየ፡፡ ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደ ውስጥ የሚያስገባ ጠባብ በር ከፈተና
“አስር አለቃ!” ብሎ ተጣራ።
ረጅም ደንደሳም ፖሊስ አሥር አለቃ፡፡
ናትናኤል ከውስጠኛው ክፍል ብቅ ያለውን ሰው ሲመለከት ወኔው ክዳው፤ ተስፋ ቆረጠ፡፡ ከዚህ በኋላ ተከራክሮም ሆነ : አግባብቶ ከገባባት ወጥመድ እንደማይውጣ ተገነዘበ፡፡
“እሽ ወንድም፤ ስም፡፡” ቆፍጠንጠን አለ ተረኛ መኮንኑ አውሬዐየሚመስለውን የአሠር አለቃውን ከጎኑ አቁሞ፡፡
“ናትናኤል ግርማ፡፡”
“አድራሻ? ”
ናትናኤል በተቻለው መጠን ንዴቱንና ብስጭቱን ቀጥ አድርጎ ለተጠየቀው ሁሉ መልስ ሰጠ፡፡
“ጥሩ እንግዲህ... መኪናዋ የተስረቀች አለመሆኗ ከተረጋገጠ በኋላ የመታወቂያ ወረቀቶችንና የመንጃ ፈቃድህን አይተን በህጉ መሠረት ላጠፋኸው ጥፋት እንከሰሃለን፡ እስከዚያ ድረስ ግን ማረፊያ ቤት መቆየት ይኖርብሃል።”
ናትናኤል አልተከራከረም። ክርክር ለውጥ አያመጣም፡፡ አስር አለቃውን ተከትሎ በጠባቧ ባር ኣልፎ ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ከፊት ለፊቱ ለማዳ እንስሳ እንዳስከተለ
ገበሬ ዘና ብሎ የሚራመደውን ደንደሳም - ፖሊስ ሲመለከት ዘገነነው እንደ ወንጀለኛ ከፍርግርግ በር ጀርባ ሲዘጋበት ሲጣደፉ
ሲያይ በለው በለው አለው ከተራ ቀማኞች ማጅራት መቺዎች መንጋ ሊደባልቁት? ጨክነው?!
አስር አለቃው ከአንድ በር እንደደረሰ ቆም ብሎ ወገቡ ላይ በሰንሰለት ከተንጠላጠሉ ቁልፎች አንደኛውን በበሩ ቀዳዳ ውስጥ ሰደደና በሩን ከፈተ:: ወዲያው ፊቱን ወደ ናትናኤል መልሶ በቀኝ እጁ በያዘው አጭር ዱላ የገዛ ጭኑን ይተመትም ገባ። ቋንቋው ..ትገባለህ ወይስ
እንፈታተሽ?' መሆኑ ሲገባው ናትናኤል ጊዜ ሳያጠፋ በተከፈተው በር ሹልክ
ብሎ ገባ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨለማው ክፍል ባዶ መሆኑን ከመተላለፊያው
በሚመጣው ብርህን ሲመለከት ነፍሱ መሰስ አለችለት፡፡ ወዲያው አስር አለቃው በሩን ዘግቶ ከውጭ ሲቆልፍበት ድቅድቅ ጨለማ ዋጠው፡፡
ለጥቂት ደቂቃዎች በጨለማው ውስጥ አንደቆመ ቆየ፡፡ አብርሃም በዚያ ሰዓት ምን ፈልጎ ይሆን የደወለው ርብቃ ትዝ አለችው:: ታስባለች፤ እንደወጣ ጥፍት ሲልባት ያለጥርጥር “አንዱጋ ተደፍቶ ቀረ” ነው የምትለው፡፡ በረጅሙ ተነፈሰ ናትናኤል በጨለማው ውስጥ ማጅራቱን
አሻሸ....

ዐየሽ ፣
የፍቅር ንቃቱን?
የ አምላክ ብቃቱን?
ዓለም ጀርባው ቢሰጠው ፣ ሰው ስሙን ባይጠሪ፣
ኤልሻዳይ፣
አዶናይ፣
መታረቂያ ብሎ ፣መላዕክቱን ሠራ፡፡
መላእክቱ ለፍትሕ ፣ ቢያቅቱ ለዳኛ
"ሰዓሊ ለነ” እንዲል
እናቱን ፈጠረ ፣ ለሰው መማፀኛ።
ዐየሽ
ሰው ፍቅርን ጀሞሮት
በፍቅር ሊጨርስ
ቢያወጣም ቢያወርደም ፣ተምኔቱ አይቀናሞ
የተሳሳች ትዳር
በይቅርታ እንጂ ፣ በፍቅር አይፀናም፡፡
ከሰው ስለኮንን
ለነፍስ እና ለልብ ፣የከበደ ነውር ፣ስለምናፈራ
ስንጣላ ጊዜ የሚያለማምነን ፣ መላእክት እንሥራ፡፡
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
የፍቅር ንቃቱን?
የ አምላክ ብቃቱን?
ዓለም ጀርባው ቢሰጠው ፣ ሰው ስሙን ባይጠሪ፣
ኤልሻዳይ፣
አዶናይ፣
መታረቂያ ብሎ ፣መላዕክቱን ሠራ፡፡
መላእክቱ ለፍትሕ ፣ ቢያቅቱ ለዳኛ
"ሰዓሊ ለነ” እንዲል
እናቱን ፈጠረ ፣ ለሰው መማፀኛ።
ዐየሽ
ሰው ፍቅርን ጀሞሮት
በፍቅር ሊጨርስ
ቢያወጣም ቢያወርደም ፣ተምኔቱ አይቀናሞ
የተሳሳች ትዳር
በይቅርታ እንጂ ፣ በፍቅር አይፀናም፡፡
ከሰው ስለኮንን
ለነፍስ እና ለልብ ፣የከበደ ነውር ፣ስለምናፈራ
ስንጣላ ጊዜ የሚያለማምነን ፣ መላእክት እንሥራ፡፡
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘