አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
586 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ተራራ_ነፋስ_ማዕበል

ማዕበል ምን አይቶ ? . . .
መፏከር ጀመረ ከቆመ ተራራ
እኩያ የመኾን የስሌት ቅመራ።
የውሃን ባሕርይ መርጋትን ዘንግቶ
ሽቅብ የመቆምን እብሪትን አንግቶ
ምን ሊረባው ቆመ?
ምን መኾን ተመኘ?

(. . . ውሃ ፍስነት ላይ . . . )
ነፋስ ሆዱ ገባ ፣ ነፋስ ውስጡ ኖረ
ተራራን ለማከል ፣ ሽቅብ ተወጠረ።
.......ካ'ለት ተጋጠመ . . .
.......ካ'ለት ተላተመ . .
.......ካ'ለት ተፋለመ . . .

( . . . ነፋስ ምን አስገባው? . . .)
ካልጠፋ ሰገባ ውሃን የመረጠ፤
የረጋን ውሃ ልብ ፣ገብቶ በጠበጠ።

( . . . ነፋስ በምን ገዱ . . . )
ውቅያኖስ የሚያቆም ከጋራ 'ሚያማስል ፤
በየት ተሽሎክሉኮ
ዐቅም አኮብኩቦ
የተኛን ሙት ባሕር ተራራ ሚያስመስል።

እኔም እንደዚኽ ነኝ . .
ሠርክ የምገዳደር ከሊቅ ፣ ከእግዜሩ፤
ለማከል ፣ ለመኾን እንደ ምስለ ፍቅሩ።

( እኮ እንዴት . . .? )
ልቤ ምን ገብቶት ነው? ከፍጥረት ለይቶ
አንችኑ ያስመኘኝ ሆዴ ጽድቅን ሽቶ።
በየትኛው ዕቅሙ ... ? ?
ፍጡር ከፈጣሪው ደርሶ ይፏከራል?
ያንን! ፍጹም ፍቅር ለመስጠት ይጥራል?
ሽቅብ ተቆልሎ ?!

🔘ተስፉሁን ከበደ🔘