አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#የወርቅ_በርጩማውን_ፍስጋ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በእንዳለጌታ_ከበደ ፡ ፡ (በ1996 የተፃፈ ነው ውድ አንባብያን አንዳንዴ አሁን ላይ ቋጥኝ የሚሆኑብን ነገሮች ቀለል ተደርገው ሲገለፁ ግር እንዳይላችሁ መልካም ንባብ።) ----------=======----------======== የቋንቋ መምህርት ነኝ ... አንዳንድ ሰው፣ ጥዋት ከእንቅልፉ እንደነቃ 'ምላሱ ላይ የገባ'ን ዘፈን ቀኑን ሙሉ ሲያንጎራጉረው…»
#ልዕለ _ፍቅር

ካልጠየቀ ጉልበት
ፍቅር እንደ ሩጫ
ያካል እድሜ መግፋት
ልብን ካላጫጫ
ሹገር ዳድ ፣ ሹገር ማም
መባሉ ለምን ነው?,
የፊደላት ድርድር
ዕድሜ እኮ ቁጥር ነው።

🔘ፋሲል ሃይሌ🔘
#ሰምና_ወርቅ

የሚበላ አጥቶ በስደት ቢዝልም
የወገብ ቅማል ግን ከአናት አይውልም
ሰውም እንደቅማል ከወገብ ተጣብቆ
መኖር ከለመደ ተራ ነጠር ሰርቆ
ህይወቱን በሞላ ወርቅ ቢሸክፍም
መዳብ ከሆነ ግን ለማግኘት የሚያልም
አንድ ቀን አይቀርም ጥሎ መፈርጠጡ
የወርቅ ክምችትን ሲያገኘው ከውስጡ።

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#ለልደቴ

እጣ ፈንታ
ባልመረጥሁት ዘመን፣ ባልመረጥኩት ቦታ
ጎዳና ላይ አውጥቶኝ
እንቅፋት በየርምጃው፣ ተለክቶ ተሰጥቶኝ
ሲሻኝ እየሸሸሁ፣ ሲሻኝ እየተዋጋሁ
እንቅፋቴን በባዶ እግሬ፣ እንደ እንቧይ እየለጋሁ
ሕመምን እየሸወድኩ፣ ሞትን እያዘናጋሁ።

መኖር ሳልጠላ
ግና ለመኖር ብየ፤ የግብር እንጀራን ሳልበላ
አሜን የሚል ቃል ሳይወጣኝ
በጌቶች ፊት በፍርሃት፣ ጎንበስ ጎንበስ ሳያቃጣኝ
ነፃነቴን ከጥልቁ ሥር፣ እንደ ብርቅ አሳ አስግሬ

ያሻኝን ተናግሬ
ተጨብጭቦልኝ
አንዳንዴም ተወግሬ
ያለ አጀብ ያለጋሻ ጃግሬ
ባሻኝ እየገሰገስኩ
እንደ ወፍ በነፃነት፣ አገር ምድሩን እያዳረስኩ

በመረጥሁት ዛፍ ስር ተኝቼ
በጅሎች ካብ ስር ሸንቼ
እያወጋሁ፣ እየገጠምኩ፣ እያለመጥሁ፣ እያላገጥሁ
እንባዎቼን በቃል ምትሐት፣ ወደ ሣቅ እየለወጥሁ።
እየጣልኩ እየወደቅሁ እየማቀኩ እየደላኝ
እንሆ አርባ ዓመት ሞላኝ።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#የወርቅ_በርጩማውን_ፍስጋ


#ክፍል_ሁለት


#በእንዳለጌታ_ከበደ

« . . . የአስቴርን ስቃይ ልቀንስ ብዬኮ ነው።
አስቴር እስክትመጣ ድረስ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባታል?አይታወቅም፡፡ ለሁለት ዓመት ብዬ አስምዬ ሸኘኋት!
ምላ ተገዝታ ሆነልኝም አልሆነልኝም ባልከኝ ጊዜ እመለሳለሁ አለችኝ።የት አለች ታዲያ?» አለኝ በመነጫነጭ፡፡

«እኛ አስቸግረናት እኮ ነው! ... ወላጆቼ ናቸው የመምጫ ጊዜዋን ያራዘሙት። እሷ ስትሄድ የችግር ቀዳዳዎቻቸው በእጥፍ በዙ» አልኩት።

«አንቺ የማታውቂው ብዙ ነገር አለ፡፡ አስቴር ጫንቃዋ መሸከም ከሚችለው በላይ ጭነት እያረፈባት እንደሆነ እያወቅሁ ዝም ማለት እንዴት ያስችለኛል?!ፍቅር ማለት ምንድነው?!»
አስቴር ከሄደች ጊዜ አንስቶ የትኛውም መ/ቤት አልተቀጠረም።ወደ የትኛውም ቦታ አስራ ሁለተኛ ክፍል መጨረሰን የሚጠቁም መረጃውን ይዞ ወዲያ
ወዲህ አላለም:: ዕወቀቱም፣ ፍላጎቱም ድፍረቱም የለውም ...

ታዲያ ለምን ዞር ዞር ብሎ እንጀራውን የሚጋግርበት ምጣድ ገዝቶ አይመለስም? የእሱ እጆች የተፈጠሩት
ሌሎች ድል ሲያደርጉ፣ ሌሎች የአሸናፊዎች አሸናፊ ሲሆነ፣ ሌሎች የሜዳሊያ ባለቤት ሲሆኑ እንዲያጨበጭቡ ብቻ ነው እንዴ?

ምን ይሰራል?

«እና ልሰናበትሽ ነው› አለኝ ሩጫውን እንደጨረሰ ሰው መታከት እየታየበት።

ይሂድ! እስኪ ይሂድና ‹‹የወርቅ በርጩማውን» ይፈልግ።
---==--
ዛሬ ምን እንደነካኝ አላውቅም። ቀንድና ጭራው የማይታይ መያዣ መጨበጫ የሌለው ሀሳብ ሲፈታተነኝ አምሽቷል፡፡

የዘሪቱ ነገር........

አገር ቤት ሄዳ በመጣች ቁጥር በቀርከሃ የተሰራ ጌጥ ታመጣልኛለች። ቢላዋ ማስቀመጫ ቄንጠኛ እቃ!የመመገቢያ እቃዎች! የሳጠራ ማስቀመጫዎች!
የወለል ምንጣፎች! የማታመጣልኝ የዕደ
ጥበብ ውጤት አልነበረም። «እናንተ አገር ይሸጣል?»ስላት «አባቴ ነው የሚሰሪው! ውሰጂላት ብሎኝ ነው»ትለኛለች።

በወር ሰባ ብር ነው የምፍላት።
ወር በሞላ ቁጥር «እትዬ ደሞዝ» አትለኝም፡፡ ዓመት ሲሞላ እኔ ዘንድ የተጠራቀመላትን ብር ትቀበለኝና አንዳንድ ነገር ገዛዝታ ለቤቶችዋ ትወስድላቸዋለች።

«የተረፈሽን ገንዘብ ምን አደረግሽበት?! ... ብዬ
እጠይቃታለሁ።

«የወላጆቹን ቤት አሳደስኩበታ ...>>

«አራት መቶ በማይሞላ ገንዘብ?! »

አዎ! በትናንሽ ጎጆ ቤቶች እኮ ነው የምንኖረው!»

ይገርመኝና ሌላ ጥያቄ አስከትላለሁ።

«የመጀመሪያ ልጅ ነሽ?!»

«ለእናቴ አዎ! ለአባቴ አይደለሁም። አባቴ
ብዙ ሚስቶች አሉት:: አምና በወር ውስጥ ሁለቱ ሚስቶች ወልደውለት የሚያበላቸው አጥቶ ሲበሳጭ
የወር ደሞዜን ላክሁለትና በጣም ተደሰተ፡፡ ባለብዙ ሚስት መሆን በኛ ጎሳ ነውር የለውም»

«የት ነበር አልሺኝ ያንቺ አገር . . .»

«ሩቅ ነው! ከአዲስ አበባ ወደ ሆሳዕና በሚወስደው መንገድ....>>

ከዘሪቱ ጋር ባወራሁ ቁጥር ትዝ የምትለኝ አስቴር ናት።
ባለፈው በፃፈችልኝ ደብዳቤ ላይ « . . . ሰሞኑን ወደ ግብፅ ሄደን ነበር፡፡ ወደ ቀጣሪዎቼ ሃገር! ለልጆቻቸው
የትውልድ ሀገራቸውን ሲያስጎበኙ እኔም «ሞግዚት»ነኝና ከጎናቸው አልጠፋሁም ነበር፡፡ የአባይን ወንዝ ሲያሳዩአቸው በደስታ ተቅበጠበጥኩ፡፡ የምሆነውን አሳጣኝ፡፡ ምን ሆነሻል ሲሉኝ «አባይ እኮ የኛ ነው አልኳቸው ሳቁ፡፡ ከት ብለው ሳቁ፡፡ ምነው ስላቸው፣ምናሉኝ መሰለሽ? «አባይ ወይ ልትለውጪው ወይ
ሊለውጥሽ ይገባል አንድ ነገር ካልሰራሽበት ያንቺ አይደለም።እኛ ከዚህ ውጪ መኖር አንችልም፤» ብለው
ስቀው ተሳለቁብኝ ..

ሌላ ጊዜ ደግሞ፣ «ዛሬም ልንሄድ ነው ተዘጋጂ»ሲሉኝ «አልሄድም» አልኳቸው:: አልሄድም ያልኳቸው አንደኛ፣ ባለፈው «አባይ የኛ ነው» በማለቴ «እሷ እኮ
ናት እንዲህ ያለችው» ብለው በብዙ ሰው ስላሳቁብኝ ሲሆን ሁለተኛ፣ ላንቺ ደብዳቤ ለመፃፍ ግዜ እንዲኖረኝ
ብዬ ነበር፡፡ «እንግዲያውስ ከኛ ጋር የማትሄጂ ከሆነ
«ብላ የስራ መዓት ቆለለችብኝ፡፡ ከጉብኝትዋ ስትመለስ ይሰራ ካለችው የተወሰነውን ብቻ ነበርና የሰራሁት
ጮኸችብኝ፡፡ ተንጨረጨረች፡፡» ድሮስ የናንተ ነገር! አባይን የሚያህል የአለማችን ታላቅ ወንዝ ከደጃችሁ
ሲያልፍ ተአምር ልትሰሩበት ቀርቶ ረሃባችሁንም አላሸነፋችሁበት፡፡.ቤት ለማፅዳት፣ መጥረጊያ ለማንሳት»
አለመስነፍሽም ይገርመኛል አለችኝ፡፡ እኔ ደግሞ ሃገር ውስጥ ያልነበረኝን ሃገር የመውደድ ስሜት ከየት እንዳመጣሁት እንጃ-ሃገሬ ስትሰደብ ያመኛል፣ እራስ
ምታት፣ ጨጓራው ኧረ ምኑ ቅጡ?» ብላ ዕፋልኛለች፡፡

አስቴር የልጅ አዋቂ ናት፡፡ ያለሷ ድጋፍ
ይኸን ጊዜ እንዴት ባለ የችግር ህይወት ኑሮአችንን እንገፋ እንደነበር ሲታወሰኝ ይዘገንነኛል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን «እቴትዬ ጡር መፍራት ደግ ነው» የሚሉ ቃላት በየደብዳቤዎቿ መነሻና መቋጫ
ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል፡፡

«ትዝ ይልሻል? አንዲት ሰራተኛችን፤

ሰራተኛ ቀጥረው ሲሞላው አንድ አመት
ሌባ ነው ይሉታል ደሞዝ ለማስቀረት!

የሚል ግጥም ያለበት ዘፈን ዘፍና ምን ማለት ፈልገሽ ነው? ብዬ ከወር ደሞዟ አስር ብር ያስቆረጥኩባትኀቀን?! አቤት ያነባችወ እንባ! ያቺ አስር ብር
ፕሮግራምዋን እንዴት አመሳቅሎባት ይሆን?!
አንጋጠው የተፉት ምራቅ ሆኗል የኔ እጣ! ያን ግጥም ዛሬ እንዴት እንደምወደው እቴትዬ! ይህቺን ባለሁለት መስመር ስንኝ ስንት አይነት አንጀት የሚበላ የሀዘን
እንጉርጉሮ አውጥቼላታለሁ መሰለሽ?! . . ባለፈው በማይረባ ሰበብ የስድስት ወር ደሞዜን እንደከለከሉኝ ነግሬሻለሁ አይደል?! .. .» ብላ ፅፋልኛለች!
• •
ወላጆቼ ሰራተኞቻቸውን ያስተዳድሩ ከነበረው እጅግ በተሻለ ሁኔታ ነው የምንከባከባቸው።በፈራረሰ
ማእድቤት - ምድጃ ስር - የተበጣጠሰ ሰሌን አንጥፌ -አይደለም የማሳድራቸው፤ የምጣድ ማሰሻ የመሰለ ብርድ
ልብስ - ያውም እግር ወይ አናት ብቻ የመሸፈን አቅም ያለውን ብርድ ልብስ ሰጥቼ አይደለም የማኖራቸው።
ትርፍራፊ አይደለም የሚበሉት።

ከ'ቡና ቤት ሴቶች' ይልቅ ለ'ቤት ሠራተኞች' የሚሰበር ልብ አለኝ፡፡ በተለይ መልከ ጥፉዎቹ ወንድን እንደተራቡት ወጣትነታቸው ሲያልፍ አቤት |
ማሳዘናቸው :: ፍቅርን እንደተቸገሩት ያርጣሉ፣ እምዬ የሚል የእምቦቃቅላ ድምፅ ይናፍቃቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ
ደግሞ ከችግር እሸሽ ብለው ዘለው በገቡበት ቤት ይደፈራሉ፡፡ ሻሽ እየተወረወረላት-ቅባት እየተገዛላት- ርካሽ
ሸበጥ እየተቸራት፣ ካረገዘች በኋላ እጣ ፈንታዋ በእመቤትዋ ወይም በጌታዋ መባረር ይሆናል:: 'ያለ ልጅሽ ነው የምንፈልግሽ' የሚል ፈታኝ ጥያቄ ይመጣል፡፡
ቀስ በቀስ ለልመና እጅዋን ትሰጣለች:: ልጅዋም በረንዳ አድሮ በጎዳና መተዳደር ይጀምራል። ካልሆነለት፣ የእለት
ጉርሱን ሊሞላ ማጅራት መቺ ሊሆን!

እኔ እንደዚህ እንዲሆነብኝ አልሻም።

ግና ምን ዋጋ አለው?!

ዘሪቱ ልትሄድብኝ ሳይሆን አይቀርም። ከጥዋት ጀምሮ ሲቀፈኝ የዋለው ያላንዳች ምክንያት አይደለም።እናቷ የመጡት ሊወስዷት ከሆነ፣ እኔ ከምከፍላት የተሻለ
የሚከፍላት ሰው ቢገኝ ነው።

አስር ብር ልጨምርላት ይሆን?

(አንባቢዎቼ በ1996 ነው የተፃፈው የዚ ሰዓት አስር ብር ዋጋውን ለናንተው ልተወው)

ዘሪቱ እናቷን ካገኘች ጊዜ ጀምሮ «እማ! ለምንድነው የመጣሽው?» ብላ መልሳ መላልሳ ስትጠይቃቸው እናትየው ግን ስለጤንነቷና ስለ ሥራዋ ነበር
የሚያነሱባት፡፡ ዘሪቱ መወትወቷን ስትቀጥል «ማታ ስንተኛ እነግርሻለሁ» ሲሏት ሰምቻለሁ፡፡ ምንም በሹክሹክታ ቢሆን!

ዘሪቱ ተስማምታኝ ነበር፡፡ ባለቤቴ ያረፈ ጊዜ እንዴት ትንከባከበኝ እንደነበር መርሳት አልችልም፡፡ አፅናንታኛ
ለች፤
👍6
አኩርታኝ ነበር:: ምን ዋጋ አለው ልትሄድብኝ ነው መሰለኝ፡፡

እስኪመሽ ጨነቀኝ:: ልጆቼን አጣጥቤ - አጫውቼ አስጠንቼ አስተኛኋቸው።
እነዘሪቱ ሳሎን ነበር መኝታቸውን ያነጠፉት።

ሁላችንም የተኛን ሲመስላቸው እናቷ «ልጄ የቸገረ ነገር ገጥሞኛል።ዘንድሮም እንደ ድሮ ወንድምሽ ስራ-ጠል ሆኗል። አይሰራም:: አያርስም:: «የዌራ እንደትን»
ብቻ ነው የሚያመልካት:: ትንሽ ዘርቶ ካጨደ ወስዶ ለሷ ነው:: ምንም ሀብት ንብረት ሳይኖረው «ባርኪልኝ!»
ብሉ ይለምናታል:: ያ! የወርቅ በርጩማ! ልቡን ወስዶታል አባትሽም ችላ ይለኛል:: እኔ በወለድኩ እንዲህ መረሳት አለብኝ ወይ?!»

«እማም! ድምዕሽን ቀንሺ ... እቴትዬን ከእንቅልፍ ትቀሰቅሻታለሽ!»

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
አትሮኖስ pinned «#የወርቅ_በርጩማውን_ፍስጋ ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #በእንዳለጌታ_ከበደ « . . . የአስቴርን ስቃይ ልቀንስ ብዬኮ ነው። አስቴር እስክትመጣ ድረስ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባታል?አይታወቅም፡፡ ለሁለት ዓመት ብዬ አስምዬ ሸኘኋት! ምላ ተገዝታ ሆነልኝም አልሆነልኝም ባልከኝ ጊዜ እመለሳለሁ አለችኝ።የት አለች ታዲያ?» አለኝ በመነጫነጭ፡፡ «እኛ አስቸግረናት እኮ ነው! ... ወላጆቼ ናቸው የመምጫ ጊዜዋን…»
#ፀሎት

ባላንጣውን የሚሰማ .....
አምላክ የሌለ መስሎት፣
"ጠላቴን አጥፋልኝ" ነው...
የሞኝ ሰው ፀሎት!!!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ 🔘
#እንቅፋትና_ህልም

ከእንቅፋቶች በስትያ ጉዞ እንድትቀጥሉ
ከግር ከፍ አርጋቹ ህልማቹን ስቀሉ
ወድቆም ፣ ተንገዳግዶም
ዳግም መራመድ ነው በቀንም ፣ በማታ
ድንጋይ እግር እንጂ ራእይን አይመታ።
#የወርቅ_በርጩማውን_ፍለጋ


#ክፍል_ሦስት(የመጨረሻ ክፍል)


#በእንዳለጌታ_ከበደ


...እናቷ ቀጠሉ፡፡ « . . . እንዴት እየኖርኩ እንደሆነ ብታይልኝ! የሰፈር ሰው ያሾፍብኛል ብጤዎቻችን ሊያሳብዱኝ ደርሰዋል . . .»

«አሁን ደግሞ ምን ሆናችሁ? ማለቂያ የለው የናንተ ጣጣ!»

ገንዘብ አይደለም የጎደለብን ልጄ! ከአፍሽ
ነጥቀሽ አይደል የምታጎርሽን? ዕድሜሽን ያርዝመው እንጂ ስራ ከጀመርሽ በኋላ ሰፈርተኛ የሚቀናብን ሆነናል
ተንቀባርረን ከሰው ጋር እንቀላቀላለን በፊት የአፈር ገንፎ ይመስላሉ እያሉ ይሳለቁብን የነበሩ ሁሉ አሁን
አፋቸውን ይዘዋል፡ ዕድሜ ላንቺ!»

ጆሮዬን ቀስሬ ማዳመጤን ቀጥያለሁ:: የእናትና የልጅ የሹክሹክታ ድምፅ፡፡

ከየጣሪያው ስር ስንት አይነት አቤቱታ አለ? ስንት አይነት የተከፋ ልብ? ስንት አይነት አፅናኝ ያጣ ልቅሶ? ልብን የሚያጨልም መልሶ መላልሶ፡፡

«አጥሩን ኣሳጠርኩት:: ቤቱን አሳደስኩት:: አሁን ደግሞ ታናሽሽ ሊያገባ ነው አግዢው አላችሁኝ።ስንቱን ቀዳዳ ልሽፍን? እኔስ እማ? እኔስ! ... ለእኔስ?! »

በእንባ ሳትታጠብ አልቀረችም፡፡ ድምፅዋ ነገረኝ፡፡

«ከወንድምሽ ጋር ተጣልተናል ... ተኮራርፈናል! ባንቺ ጉዳይም ተቀያይመናል»

__«በእኔ ጉዳይ? ለምን?!»

«እህትህን ለምን ታስቸግራታለህ? . . .
ለኛ በመጨነቅ ዕድሜዋን ልትገፋ ነወይ!
· . . ስለው
"እኔ ትዳር ልመሰርት ስል ነው ወይ እንደዚህ አይነት እንድታመነታና እንዳትረዳኝ የሚያደርጋት ሃሳብ
የምታመነጨው?' ብሎ ተቆጥቶ አኮረፈ .

ዘሪቱ «እሺ አሁን እኔ ምን እንዳደርግ ነው
የምትፈልጊው?» አለች።

«የሰርግህን መሉ ወጪ እሸፍንልሃለሁ ብለሽ ደብዳቤ ጻፈለት፡፡ ቁጥርና ፊደል ታውቂበት የለ? »

«እንዴ? የወንድሜን የሰርግ ወጪ ለመሸፈንኮ ቢያንስ ሁለት ሶስት ዓመት መስራት አለብኝ ያውም የደሞዝ ጭማሪ ካገኘሁ! .. .ከየት አመጣለሁ እማ? .
በእርግጥ ታሳዝኚኛለሽ ግን ... »

አሳዘነችኝ፡፡ ይህቺ ከተወለደች ሃያ አምስት ዓመት ያስቆጠረች የማትመስል ሴት ስንት መከራ ተሸክማለች?
ቆይ ደሞዟን ...

«ለሱ አታስቢ!» አሉ እናቷ

«ለምኑ?»

«ለወንድምሽ ሰርግ ወጪ»

«ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው የማላስበው? እናንተ ሃሳባችሁን ሁሉ እኔ ጫንቃ ላይ ጥላችሁ አይደል በሰላም
ዕንቅልፋችሁን የምትለጥጡት?! መስራት
የሚገባችሁን ያህል ለመስራት ሰንፋችሁ በኔ ገንዘብ የከርሞ እቅድ ትነድፋላችሁ! ...››

« ይኸውልሽ ዘሪቱ፣ ጅማ ያሉት የቀርከሃ ሶፋ የሚሠሩ ወንድሞቼ ተደራጂበት፣ ነግጂበት ብለው የላኩልኝ ሁለት መቶ ብር አለ፡፡ ለወንድምሽ ' ለአንዳንድ
ጉዳይ ማሟያ' ብለሽ ትልኪለታለሽ፡፡ ከማግባትህ በፊት ስራ መያዝ አለብህ' ብለሽ - ገንዘቡን 'ተሳፈርበት ወደኔ
ናበት' ትይዋለሽ፡፡ ከኪስሽ እንዳወጣሽው እንጂ እኔ እንደሰጠሁሽ ወፍ እንዳይሰማ!»

አንዳንዴ የምታመነጨው ሃሳብኮ
«አይ እማዬ . . .

«ምን ላድርግ? ብቻሽን ስትለፊ እያየሁ እጄን አጣጥፌ አልቀመጥ! ... የምሰጥሽን ብር ከላክሽለት
ከተማ ገብቶ መስራት ብዙ ገንዘብ የማያስገኝ ይመስለዋል»

የተስማሙ መሰለኝ።

እኔም እፎይ ብዬ ዘሪቱ እንደማትሄድብኝ እርግጠኛ ሆኜ በባለቤቴ ሞት ምክንያት ያገኘሁትን ብር ምን መስራት እንዳለብኝ እያውጠነጠንኩ፣ የለውጥ ቀን ቅርብ
እንደሆነ አስተውዬ . . . ወደ መኝታ ቤቴ ልሄድ ስል ስልኩ ጮኸ።

ደነገጥኩ፡፡

በዚህ ሰዓት የሚደወልልኝ ከአስቴር ነው::
አስቴር ምን ሆና ይሆን? ስፈራ ስቸር ስልኩን አነሳሁት። ልክ ነኝ።

ረጅም የሆነ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ፡
«እቴትዬ!» አለችኝ:: አቤት ድምዕዋ ውስጥ ያለው ፍቅር! በናፍቆት የተሞላ ዜማ! እንደዚህች ያለችዋን እህቴን በባዕድ አገር እንድትጎሳቆል መፍቀዱ ምን ሆኜ ነው?

«ወዬ!»

‹ደወለልኝ!! »

«ጓደኛሽ?››

«አዎ! ከደቡብ አፍሪካ! ... አሳዘነኝ:: ተላቀስን፡፡

እንዳያሳስበኝ ብለ አጽናናኝ:: የተባባልነወን እፅፍልሻለሁ ... እሺ እቴትዬ!»
«አይዟችሁ ይነጋል . . .»

«እንዴት ነው እቴት ቤተሰብ አቤቱታ ማሰማት አልጀመረም? . . ባለፈው የሰራሁበትን ብር ሁሉ ለጓደኛዬ ላክሁለት፡፡ ከወላጆቹ የወረሰውን ቤት አሳድሶ በኮንትራት ለሆቴል አከራይቶት እኮ ነው፤ በደቡብ አፍሪካ አድርጎ አሜሪካ ለመግባት ስንቁን የቋጠረው! .
ስንደራጅ ቤቱን እኛ እንስራበታለን!»
:
«ይሁን እስኪ እንግዲህ . . .»

«እቴትዬ! . . . ሁልጊዜ እጠይቅሻለሁ ብዬ እየረሳሁ!»

«ምን?››

«ሰራተኛሽ ዘሪቱ አጫውታሽ ያዝናናሽኝ ያ
የወርቅ በርጩማ ነገር የት ደረሰ? ለወንድሜ ተበረከተለት?»

ተሳሳቅን::

«ለምን ጠየቅሽኝ?»

«ወደሃገር ቤት ስገባ የራሴን የወርቅ በርጩማ ለመስራት ላቤን ማፍሰስ እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ በከንቱ
ምኞት የሚገኝ ሳይሆን ጠንክሮ የመስራት ውጤት ነው ያ የወርቅ በርጩማ!»

ያለችበት ሃገር ስራን አለመናቅን አስተምሯታል፡፡ ሰው ትልቅ የሚባለው ጊዜውን በተግባር መተርጎም የቻለ እንደሆነ መሆኑን ዕውቀትና ልምድ ቀስማለች።ይሄ ነው ብላ ልታሳየኝ የማትችለው ዲግሪ እንደተበረከተላትም ተረዳሁ:: ከመሪር ሕይወት የተገኘ
ዲግሪ!

«አሪፍ ሃሳብ ነው!» አልኳት!

ትንሽ ቆይታ «እቴትዬ! መርሮኛል! ትንሽ
ሰራርቼ እመጣለሁ ላብድ ጥቂት ነው የቀረኝ ..በየጊዜው የጓደኞቼ ቁጥር ሲቀንስ፣በሙቅ ውሃ ሲነፍሩ፣
ከፎቅ ሲወረወሩ አሟሟታቸው ሲከፋ እያየሁ እንዴት እንዴት ሆኜ ነው እዚህ በሰው አገር የምኖረው »
አለችኝ።

« ለምን አትመጪም? ነይ እዚህ! ዛሬ ነገ አትበይ! እኛም በስጋት አለቅንኮ! የግድ ቤተሰቦችሽ እንዲያልፍላቸው ያንቺ ህይወት ማለፍ አለበት?»

«አይ እቴትዬ! ...ዛሬ ነገ ሳትይ ነይ' አልሺኝ?
ምን ይዤ? መጥቼስ ምን ሰርቼ ልበላ?!»
«አንድ የመጣልኝን ሃሳብ ልንገርሽ?» አልኳት ለጥቂት ደቂቃ ሳሰላስል ቆይቼ።

«ምንድነው?»

«ላበድርሽ ነው! መለስተኛ ንግድ ሊያስጀምርሽ የሚችል ብር! .. ጓደኛሽ በውርስ ያገኘውን ቤት ወደ
ንግድ ተቋም የመለወጥ ዕቅድ አላችሁ አይደል? እረዳችኋለሁ!»

«ከየት አምጥተሽ?» እንደተገረመች ያስታውቃል::

«ለማንም እንዳትነግሪ! . . . ቤተሰብም ቢሆን እንዳያውቀው! ባለቤቴ ይሰራበት የነበረው ድርጅት ኢንሹራንስ ከፍሎኛል፡፡ ስለዚህ እሰጥሽና - ገንዘቡን
ትሰሪበትና - ዕቁብ ገብተሽ ትከፍይኛለሽ .. .»

«አይ እቴትዬ!» ከድምፅዋ ሃሳቤን እንደወደደችው ያስታውቃል፡፡

ስልኩን ከዘጋሁት በኋላ ነው፣ መፍትሄውን
የኮረጅኩት ከዘሪቱና ከእናቷ እንደሆነ የታወሰኝ!

በተገማሸረ መስክ ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውሃ
. . እፎይ ብላ የተረጋጋች የምትመስለዋ
ህይወታችን መንቀሳቀስ የምትጀምርበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን ተሰማኝ፡፡
የዛሬዋን ማታ ወደድኳት፡፡

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
አትሮኖስ pinned «#የወርቅ_በርጩማውን_ፍለጋ ፡ ፡ #ክፍል_ሦስት(የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ #በእንዳለጌታ_ከበደ ...እናቷ ቀጠሉ፡፡ « . . . እንዴት እየኖርኩ እንደሆነ ብታይልኝ! የሰፈር ሰው ያሾፍብኛል ብጤዎቻችን ሊያሳብዱኝ ደርሰዋል . . .» «አሁን ደግሞ ምን ሆናችሁ? ማለቂያ የለው የናንተ ጣጣ!» ገንዘብ አይደለም የጎደለብን ልጄ! ከአፍሽ ነጥቀሽ አይደል የምታጎርሽን? ዕድሜሽን ያርዝመው እንጂ ስራ ከጀመርሽ…»
#ፍኖተ_አርነት

ተበዳይ መናፍስት
ታፍነው የኖሩ
ወደ አርነት ዐውድ በድንገት ሲጠሩ
ያለጠባቂ ዘብ ተከፍቶ ሳል በሩ
የገቡ አይመስላቸው ቅጽሩን ካልሰበሩ።

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
አሜን በይ ሃገሬ
እርግማን ነውና
አንቺን አለመውደድ
የሚያቆረቁዝሽ
ነፍስ ከስጋው ይንደድ

🔘ኢዛና መስፍን🔘
#አቀበት


#ክፍል_አንድ


#በገበየሁ_አየለ

አካሌ ቀድሞ ከነበሩበት ፈረንሳይ ለጋስዮን፣ አሁን ወዳሉበት ቶሎሣ ሰፈር ከተዛወሩ አንድ ዓመት ቢሆናቸውም፣ ከአካባቢውም ሆነ ከቅርብ ጎረቤቶቻቸው
ጋር መላመዱ አልሆነላቸውም፡፡ ዓይናፋርና ሽቁጥቁጥ ናቸው፣ ቶሎ ሰው የማይቀርቡ፡፡ የቀድሞ መኖሪያቸውን
የቀየሩት፣ ቀዳሚና ተከታይ ያልነበራት ልጃቸው ሸዋዬ ስትሞትባቸው ነው። ባላቸው በአፍላ ዕድሜ በድንገተኛ
ህመም ስለሞቱባቸው እናትም አባትም ሆነው ነበር ሸዋዬን ያሳደጓት በኋላም የዳሯት፡፡

ሸዋዬና መምህሩ ባሏ ተካ ትዳራቸውን ለማደላደል ሌተ ቀን ይጥሩ ጀመር፡፡ በተጋቡ በዓመቱ ሴት ልጅ ወለዱ። በሸዋዬ መውለድ እጅግ የተደሰቱት፣ ከባልና ሚስቱ ይልቅ አካሌ ናቸው:: ሕጻኗን ከእቅፋቸው አላወጣት አሉ: በኋላም ውሎና አዳራቸው በአብዛኛው
እዚያው ሆነ፡፡ የዚህ ምክንያቱ፡፡ በፊት በፊት የህጻኗ ፍቅር ቢሆንም፣ በኋላ ግን የሸዋዩ ሕመም ነበር።ከዛሬ ነገ ይሻላታል ቢባል፣ ከሆስፒታል ሆስፒታል ቢያንከራትቷት፣ የሚፈውሳት መድኃኒት ታጣ፡፡ የኋላ ኋላ ሀኪሞቹ በሽታዋ የማይድን መሆኑን ገልጠው"ሸዋዬ ሕጻኗን ጡት እንዳታጠባት" በማለት አስጠነቀቁ።

በዚህ ሁኔታ የሸዋዬ በሽታ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ ሄደና በዓመት ከመንፈቋ ሞተች፡፡ እሷ ባሞተች በሳልስቱ ባሏ ተካ የሚሄድበትን ሳይናገር ተሰወረ::በሽዋዬ ሞት ቅስማቸው የተሰበረው አካሌ ክፉኛ
ደነገጠ:: በከባዱ ሀዘናቸው ላይ እናትና አባት የሌላትን ሕጻን የማሳደጉ ኃላፊነት ተጨመረ፡፡ዙሪያው ገደል ሆነባቸው:: "ይሁን፣ ተመስገን፣ ሸዋዬ ምትኳን ትታልኝ
ነው የሞተችው:: ህጻኗ በዕድሏ ታድጋለች" እንዳይሉ፣
"ሸዋዬን የገደላት ክፉ ደዌ ወደ ልጅዋም ይተላለፋል" ማለትን ስለሰሙ ተስፋቸው ይበልጥ ጨለመ።

ያኔ ነው የአሁኗ ቡና አጣጭ ጎደኛቸው ወይዘሮ ብርቄ ህፃኗን እናስመርምራት
እንደሚባለው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል እኮ ያሏቸው:: እንዳሉት አደረጉ፣
ህጻኗ ከደዌው ነጻ ነች ተባለ፡፡ ይህ ለአካሌ ታላቅ የምስራች ነበር፡፡ "ተመስገን አምላኬ የዓይን ማረፊያ አልነሳኸኝም፣ የሀዘኔን ማስረሻ ሰጥተኸኛል" አሉ፡፡
ህጻኗንም ማስረሻ ብለው ጠሯት፡፡

የአካሌ ጓደኛ ወይዘሮ ብርቄ ትንሽ ዘግየት ብለው ደግሞ ሌላ ምክር አመጡ፡፡ "ሸዋዬ እሞተችበት ሆስፒታል እንሂድና የሞቷን ምክንያት የሚገልጥ ወረቀት ስጡን እንበላቸው:: የሞተችበት በሽታ እርዳታ የሚያስገኝ ሆኗል።ወረቀቱ ከተገኘ ህጻኗን ይዘው ወደ እርዳታ ለጋሾቹ በመቅረብ 'ወላጆቿን አጥታለች::ደካማ አሮጊት ነኝ፣ እልሰው እቀምሰው የሌለኝ ይበሉ፡፡በደንብ ይረዱዎታል :: ማንም አይደለም እንዴ የሚረዳው? ዛሬ በአዲሱ በሽታ ዘመድ የሚሞትበት ድሀ እርዳታ ይገኛል! ነባሮቹ በሽታዎቻችን እንዲህ ከእርዳታ ጋር ቢመጡ ኖሮ ደግ ነበር፣ 'የቸገረው ዱቄት ከንፋስ ይዛመዳል ማለትኮ ውነትነት አለው' አሉ
ዓይኖቻቸውን እያሻሹ::

አካሌ በብርቄ ምክርና አይዞሽ ባይነት እየተበረታቱ በየቢሮው ብዙ ከተንከራተቱ በኋላ ተሳካላቸውና በኤድስ
ህመም ወላጆቿን ያጣች ህጻን አሳዳጊ በመባል ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች እርዳታ ያገኙ ጀመር፡፡የማስረሻን አባት፣ የተካን መሰወር አስመልከተው ሰዎች ብዙ መላምት አወሩ፣ "ሚስቱን የገደላት በሽታ
እሱንም የያዘው መሆኑን ስላወቀ እራሱን ገድሏል፣ገዳም ገብቶ ነው፣ እማይታወቅበት ስፍራ ሄዶ ኑሮውን
እዚያው መስርቷል. .አሉ፡፡

እንዲህ ያለ ብዙ ነገር ከተወራበትና ከተረሳ ከ 6 ወር በኋላ ተካ አንድ ቀን ብቅ አለ።

የቅርብ ጎረቤቶቹ በመገረምም፣ በሀዘኔታም፣ "እንኳን ደህና መጣህ" እያሉ ሲቀባበሉት፣ አካሌ ግን "ዓይኑን
አላየውም" አሉ ክፉኛ ተቀይመውት፡፡ ከዚያም ይልቅ ከተረሳና እንደሞተ ከተቆጠረ በኋላ መምጣቱ ለመልካም
አለመሆኑ ተሰማቸው:: "ያሰበው ደባ ቢኖር ነው" ብለው
ክፉኛ ሰጉ፡፡ በመሆኑም አማላጆች ቢለምኗቸው፣ ቢማጠኗቸው "ከኔ ጋር አይኖራትም!" አሉ።

በአማላጅነት አልሆንልህ ያለው ተካ፣ አካሌን የቀበሌ ሹሞች ዘንድ ከሰሳቸው:: ሹሞቹ የሁለቱንም ክርክር ካዳመጡ በኋላ፣ "ጠፍቶ ቢከርምም፣ የቤቱ
ተከራይ እሱ ነው፣ አብሮኝ አይኖርም፣ አጠገቤ አይድረስ ካሉ የቤቱ መሀል በር ታሽጎ ሁለት ላይ ይከፈልና
በተለያየ በርና አቅጣጫ እየተገለገላችሁ ለየብቻ መኖር አለባችሁ" በማለት ወሰኑ፡፡
በዚሁ መሠረት በግድግዳ የተለያዩ ደባሎች ሆነው አንድ ሳምንት ያህል እንደቆዩ፣ ተካ እንደገና አካሌን
ከሰሰና ሹሞቹ ዘንድ አቀረባቸው::
አንድ ቀን አመሻሹ ላይ አካሌ እንደ ሁልጊዜያቸው ቡና አፈሉና ብርቄን ጠሯቸው።ሥጋትና ፍርሃታቸውን ሊያወያዩዋቸው አስበዋል፡፡

"ይሄን ሰውዬ ፈራሁት" አሉ አካሌ የቀዱትን አቦል ቡና ለብርቄ እየሰጧቸው፡፡
የቀይ ዳማ ፊታቸው እንደለበሱት የሀዘን ልብስ ጠቁሯል።

"ተካን ማለትዎ ነው?" አሉ ብርቄ ትንንሽ
ዓይኖቻቸውን አፍጠው።

«አዎን» በረጅሙ ተነፈሱ አካሌ፡፡
ከእንግዲህ የሚያገናኛችሁ በር ታሽጓል» አሉ ሽበታቸውን በእንዝርታቸው ጫፍ እያከኩ።

"ያ ከምን ያግደዋል ብርቄ ? ይህችን ልጅ
ለመውሰድ ሲል እሽጉን በር ሰብሮ በመግባት ቢገድለኝስ? ምኑ ይታመናል? የት ከርሞ እንደመጣ፣ ወዴትስ እንደሚሄድ ማን ያውቃል?"

"ዛሬ ከተካ ጋር አካባቢው ሹሞች ዘንድ
የቀረባችሁት ለምን ነበር?" አሉ ብርቄ

"ከሶኝ ነዋ ልጄን ትስጠኝ ብሎ::"

"ማስረሻን?"

አካሌ በአዎንታ እራሳቸውን ነቀነቁና በማቃሰት ተነፈሱ፡፡

"ማስረሻ ልውሰዳት ማለቱ እንዴት ሊያሳድጋት ነው? ምን ሊያበላት? ለራሱ ይቀምሰው ይልሰው የለው:: አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል' አሉ፡፡"

"ምን አውቄለት፡፡" አሉ አካሌ ማስረሻ ወደተኛችበት ቦታ አልጋ አንጋጠው እየተመለከቱ፡፡

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍4
#አንሺና_ወዳቂ

ተዘርሮ አየሁት
ቀርቤ አነሳሁት
እሱ ግን ተከፋ
ቅስሙ ተሰበረ
አብሬው ባልወድቅ
ሳይፅናና ቀረ።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#መልክአ_ሕይወት

ቧልትን ከፈገግታ
ሣቅን ከፌዝ ጋር
ባ'ንድ ላይ ቀይጠን
አቅልመን በጥብጠን
በሐዘን በሃር ላይ፣ብናቆረቁርም
ባሕሩ ሰፊ ነው፣መልኩን አይቀይርም

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
#ሲታነፅ_ሲወቀር

እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰሎሞን
“ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል”
ሳይጥሉ መታገል፣ ሳይከብሩ መባተል
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር።

ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል፣ ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ
እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሐይዋ በቻት፣ ግልገል ፀሐይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ፣ ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ፣ ሸማ ሆኖ ቆየኝ
ከንቱ የነበረው፣ አንቱ ሆኖ ታየኝ።

ለካስ
ጠቢብ ቢያስተምረው፣ መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ ቢታነፅ፣ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም፣ ካልወደደ በቀር።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#አቀበት


#ክፍል_ሁለት


#በገበየሁ_አየለ

"ምን አሉት ታዲያ ሹሞቹ?"

"ትሰጭዋለሽ ወይ ብለው ጠየቁኝ፡፡
አላደርገውም ብዬ ክፉኛ ስከራከራቸው ጊዜ ፍርድ ቤት ሂድና ክሰሳት፣ ይህን የመሰለውን ጉዳይ መበየን የኛ ስልጣን አይደለም" አለት።

"እሰይ፡ ይሂድና ይክሰስዎት፣ ያኔ ደግሞ አንድዬ ያውቅሉሃል::"

"ኧረ እሱ እስከዚያውም የሚታገስ አይመስል ክፉኛ ነው የፎከረብኝ::"

ብርቄ ፡ "ልጅቱን አላሳይ ስላሉት ነው ልውሰዳት ማለቱ።ምናለበት ብቅ እያለ እንዲያያት ቢፈቅዱለት?"ለማለት አሰቡና ተውት።አካሌ በግልጽ አይናገሩት
እንጂ ተካ ከማስረሻ ጋር እንዳይቀራረብ አጥብቀው የሚከላከሉት ከሷ ይለየኛል ብለው ብቻ ሳይሆን እሱ ከወሰዳት በሷ ምክንያት የማገኘው እርዳታ ይቀርብኛል
በሚል ሥጋት ጭምር መሆኑን ተረድተዋል፡፡

ሁለቱም የየራሳቸውን አሳብ ሲያሰላስሉ ሳለ ብርቄ ጉሮሯቸውን ሞረዱና "የሰፈሩ ሰዎች ናቸው ተካን ክፉ የሚመክሩት፡፡ መከራ ሰውን ዓመለኛ ያደርገዋል እንጂ
ተካ ደግ ሰው ነበር" አሉ።

"መክረውት ይሆናል ብዬ እኔም እጠራጠራለሁ::ቢያደርጉትም አያፈረድባቸውም፡ አብሯቸው የኖረ እሱ፡
እኔን የት ያውቁኛል፡፡" አለ አካሌ ማስረሻን ከአልጋ ላይ አንስተው እያቀፏት::

መከራም ያልፋል::" አሉ የማስረሻን ፀጉር እያሻሹ::
"ሰው ቢመክርና ቢመቀኝ ምን ሊያመጣ የማታ እንጀራ ያልነፈገዎ ፈጣሪ ያውቅሉሀል::" አሉ ብርቄ

ትንሽ አሰብ አደረጉና ደግሞ እኔም አለሁ
በደከሙ ዓይኖቼ እየተጨናበስኩና እየፈተልኩ ልቃቂት ሽጨ አዳሪዋ፣ ፈጣሪ ቢያድለኝና ሁለቱ ልጆቼ በሕይወት
ቢኖሩልኝ ኑሮ ያሳርፉኝ ነበር::"

“ሁለት ብቻ ነበር የወለዱት? "

"አዎን ሁለት ብቻ ነበሩ፡: ደረሱልኝ ሊያሳርፉኝ ነው እያልኩ ዓይን ዓይናቸውን በጉጉት ስመለከት ሳለሁ ድንገት ብድግ ብለው ለናት አገራችን ካልሞትን አሉ፡፡
ተው ልጆቼ እኔን ለማን ጥላችሁ ነው የምትሞቱ፡ከመኖራችሁ እንጂ ከሞታችሁ ምን እጠቀማለሁ የምትገዳደሉትኮ ያንድ እናት ልጆች ናችሁ::' ብላቸው
አልሰማሽ አሉ:: ፀባቸውን ከቤት ጀመሩት:: ከመገዳደል ሌላ የፀብ ማብረጃ መንገድ አልታይ አላቸው:: አንደኛው የመንግሥት ሆነ ሌላው ከመንግሥት ጋር ከሚጣላው
ወገን ነበረ፡፡ እየተዛዛቱና እየተጣደፉ ወደሞታቸው ሮጡ:: እንዳሉትም ተገዳደሉና እኔን የወላድ መካን
አደረጉኝ:: ማን የት እንደወደቀ እንኳን የሚነግረኝ አላገኘሁም::" ብለው እንባቸውን በነጠላቸው ጫፍ እየጠራረጉ "ፎቶግራፋቸውን አቅፌ ቀረሁ” አሉ፡፡ አካሌም እንባ ያጤዙ አይኖቻቸውን ጠራረጉና፣" አይዘኑ፣ እስከዛሬ ያኖረዎ እግዚአብሄር ያውቅልዎታል፡ ሀዘንም ይረሳል፡መከራም ያልፋል::" አሉ የማስረሻን ፀጉር እያሻሹ::

በዚህ ሁኔታ ሲወያዩ ካመሹ በኋላ ብርቄ ወደ ቤታቸው ለመሄድ በላስቲክ ከረጢት የያዙትን ጥጥ እንዝርት ያስተካክሉ ጀመር፡፡

"እንግዲህ ያድምጡኝ ተካ ዛሬ ክፉኛ ነው
የዛተብኝ:: ከተተናኮለኝ መጮሄ አይቀርም::" አሉ ኣካሌ ጓደኛቸውን ለመሸኘት ብድግ እያሉ፡፡ "አይዝዎት፣
እንኳን ከዛቻ ከተወረወረም የሚያድን አምላክ ይጠብቅዎታል" አሉ ብርቄ ዓይኖቻቸውን ወደጣራው
አቅንተው።

አካሌ ብርቄን ከሸኙአቸው በኋላ ማስረሻን በነጠላቸው ጥብቅ አድርገው አዘሏትና የምሽት ተግባራቸውን ለማጠናቀቅ ጉድ ጉድ ይሉ ጀመር፡፡ ተካ
ከመጣ ወዲህ ሲንቀሳቀሱም ሆነ ሲቀመጡ ማስረሻ እንዳትለያቸው ወስነዋል፣ አካሏ ከአካላቸው ትንፋሽዋ
ከትንፋሻቸው እንዳይርቅ::በራቸውን ከወትሮው ይልቅ ጠበቅብቅ አድርገው
ዘጉት:: ተካ ያመጣብኛል ብለው የፈሩት ችግር ከደቂቃ ደቀቃ ከሰዓት ወደ ሰዓት ያሳስባቸው ጀመር፡፡
"የሚያደርገውን ያድርግ እንግዲህ ምነው ኣካለወርቅ የሚሆነው ከመሆኑ በፊት በፍርሃት አልሞትም::" አሉ
ለራሳቸው::

እንዲህ እራሳቸውን ለማጎበዝ ይሞክሩ እንጂ ምሽቱ፡እየገፋ በሄደ ቁጥር ብርታታቸው መናዱ ኣልቀረም።

ማስረሻን አልጋቸው ላይ እስተኙዋትና፣ ቆም ብለው ወደ ተካ ክፍል ያስገባ የነበረውን እሽግ በር በጥርጣሬ
ተመለከቱት፣ የተካ ኣቋራጭ ማጥቂያ በዚያ እንደሚሆን እርግጠኛ ናቸው።

አሮጌ መጥረብያቸውን ከስርቻ ፈልገው ያዙና በእድሜ የላላ የእጅ ጡንቻቸውን ፈርጠም አድርገው ለጥቂት ጊዜ ወደ እሽጉ በር ካፈጠጠ በኋላ። እራስጌያቸው አስቀመጡት::

እንዲህ በማድረግ ላይ ሳሉ ነው ድንገት ተካ ክፍል ውስጥ የእርምጃና የእንቅስቃሴ ድምጽ የሰሙት::ወዲያውኑ የልባቸው አመታት ስለፈጠነባቸው
ደረታቸውን በሁለት እጆቻቸው ያዙና "እንዴ!" አሉ በሹክሽኩታ:: ተካ ከወትሮው ቀደም ብሎ መምጣቱ
ይበልጥ አስደነገጣቸው በፀጥታ አዳመጠ:: እያገሣ ያንጎራጉር ጀመር፡፡ ሞቅ ብሎት ሲመጣ የሚያደርገው
ልምድ ነው:: አካሌ ከአስፈሪ አውሬ ጋር የተፋጠጡ ይመስል እቆሙበት ተተክለው ቀሩ፡፡

"ዝግጅቱን በጊዜ ለመጀመር ነው ቀደም ብሎ የመጣው" አሉ በአሳባቸው:: የተካ እንጉርጉሮ ብዙም አልቆየ ሰው የሌለበት እስኪመስል ድረስ ክፍሉን ፀጥታ ዋጠው
አካሌ ለአስር ደቂቃ ያህል በዝምታ ካዳመጡ በኋላ፡ ቀስ ብለው አልጋቸው ጠርዝ ላይ ቁጭ አሉ።

እንደገና ለአምስት ደቂቃ ያህል አዳመጡ ከማስረሻ የእንቅልፍ ልብ አተነፋፈስና ከራሳቸው ልብ ምት ሌላ የሚሰማ ነገር የለም አይኖቻቸውን እሽጉ በር ላይ እንደተከሉ እራስጊያቸው ያለውን መጥረቢያ በዳበሳ አነሱና ጠበቅ አድርገው ያዙት:: እንደገና ጥቂት
ካዳመጡ በኋላ፣ "መተኛቴን ነው የሚያዳምጠው"አሉና ጉሮሯቸውን በመሞረድ ያለማንቀላፋታቸውን
የሚያመለክት ድምጽ አሰሙ:: ቀጥለው ደግሞ በያዙት መጥረቢያ ዛቢያ ወለላቸውን መታ መታ አደረጉት።.....

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
🔥1
#ላንዲት_የገጠር_ሴት

ስትፈጭ የኖረች ሴት
መጁ በመጠኗ ፣ ወፍጮውም በልኳ
ጓያ ትፈጫለች
ጓያ ሽሮ ሲኾን ያበቃል ታሪኳ።

አስባው አታውቅም
ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደ መጣች
ከ'ለታት አንድ ቀን ከ ናቷ ሆድ ወጣች
ከ'ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች
ከ'ለታት ሌላ ቀን ለባሏ ተሰጠች
ተዚያን ቀን ጀምራ
ተዚያን ቀን ጀምሮ
ድንግል ድንጋይ ወቅራ
ትፈጫለች ሽሮ።
አታውቅም፣
ማን እንደሚባሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ
አታውቅም፣
ሹማምንት፣ በ'ሷ ስም፣ምን እንደሚሰሩ
አነሣኹት እንጂ እኔም ለነገሩ
በፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ
ምን ይጠቅማትና፣ጓያዋን ለማድቀቅ።
ከቶ ማንም የለ፣አበባ የሚሰጣት
ከቶ ማንም የለ፣ከተማ የሚያወጣት
ከቶ ማንም የለ፣በዳንኪራ መላ፣ወጠቧን የሚያቅፋት
ልፋቷም፣ዕረፍቷም፣
ወደዚህ መጅ መሳብ
ወደዚያ መጅ መግፋት።
እንደ ዓባይ ፏፏቴ ሺሕ ዓመትቢንጣለል
ቢጎርፍም ዱቄቱ
እንደ ሲኦል ወለል
ጫፍ የለውም ቋቱ ።

ከዘመናት ባ'ንዱ
መስታወት ፊት ቆማ፣በተወለወለው
ፊቷን ለማየት
ከፀጉሯ ላይ ያለው
ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለየት
ያኔ ይገባታል የተሰጣት እጣ
ከማድቀቅ ቀጥሎ መድቀቅ እንደ መጣ።

የመጅ አገፋፏ አምሳለ ሲሲፈስ
ከቋት ስስት እንጂ ሲሳይ አይታፈስ
ትቢያ ሚተነብይ ዱቄት በዙርያዋ
ከባርኔጣ አይሰፋም የኑሮ ጣርያዋ
"ስትፈጭ የኖረች ሴት " ይህ ነው መጠሪያዋ።


#ሲሲፈስ- በግሪክ ተረት ውስጥ የሚገኝ ተኮናኝ ሲኾን ኩነኔው ያለግብ ድንደፈጋይ መግፋት ነው።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
ኀሠሣ_ሥጋ

እልፍ ከሲታዎች ቀጥነው የሞገጉ
"ሥጋችን የት ሄደ?" ብለው ሲፈልጉ
በየሸንተረሩ በየጥጋጥጉ
አሥሠው አሦሠው በምድር በሰማይ
አገኙት ቦርጭ ኾኖ ባ'ንድ ሰው ገላ ለይ።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘