አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አፈር_እንቆቅልህ

አፈር፦
በምድሬ ሥር፦ማፍሪያ
በጥፍሬ ሥር፦ማፈርያ
በውኀ የማባርረው
በደሜ የማስከብረው
በልቤ ስይዘው፦የሚያሸልመኝ
በልብሴ ስይዘው፣የሚያስቀይመኝ።
#ጥጡ_እና_ፈታይዋ

ባበባነት ወቅቱ
ጥጥ ነኝ ብሎ ቀርቧት
ፈታይ ኾና ቀርባው
ከስሩ ፈንቅላው
ከንቡጡ ፈልፍላው
ከማ'ረጉ አውርዳ
መሬት አስተኝታው
በፈገግታ በትር
በሣቅ ማደወርያ
ቀኑን ሙሉ ወቅታው
በድምጧ መንደፊያ
ባይኗ መዳመጫ
ከፍሬው ለይታው
ለካ እሱም ተረትቶ
ሰውነቱን ትቶ
(አምኖ ጥጥነቱን)
መዳፏ ስር ገብቶ
ድድር ገላው ሳስቶ
ጥብቅ ጉልበቱ ላልቶ
ኾኖላት ባዘቶ
በስሜት እንዝርቷ
ታብቶላት ዐሥራው
በራቁት ጭኗ ላይ
አሽከርክራ አሹራው
ሲወፍር አቅጥናው
ሲረግብ አክርራው
ሲያሰኛት ልቃቂት
ሲሻት ቀለም አ'ርጋው
ለካ እሱም ተረቶ
ሰውነቱን ትቶ
ጥጥነቱን አምኖ
እንዳደረገችው እንዳሰኛት ኾኖ
መለወጡን እንኳ ሳያስብ ላ'ንድ አፍታ
ከጥጥነት ልቆ ኾኗት ቀጭን ኩታ
ቀን ቀን ለውበቷ
ማታ ለሙቀቷ
ሲኾን ሰነባብቶ
ዕድፍ እና ትቢያ ከገላዋ አንስቶ
ጸዐዳው አካሉ እያደር ጨቅይቶ
እሷ ሳትለወጥ
እሱ ነትቦ አርጅቶ
ተሽቀንጥሮ ቀረ ኾነና ቡትቶ
በሌላ ጸዐዳ ኩታ ተተክቶ።

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
#አቀበት


#ክፍል_ሦስት (የመጨረሻ ክፍል)


#በገበየሁ_አየለ

..የሚሰማ ነገር የለም፡፡ ዓይኖቻቸውን እሽጉ በር ላይ እንደተከሉ እራስጌያቸው ያለውን መጥረቢያ በዳበሳ አነሱና ጠበቅ አድርገው ያዙት:: እንደገና ጥቂት
ካዳመጡ በኋላ፣ "መተኛቴን ነው የሚያዳምጠው" አሉና ጉሮሯቸውን በመሞረድ ያለማንቀላፋታቸውን
የሚያመለክት ድምጽ አሰሙ።ቀጥለው ደግሞ በያዙት መጥረቢያ ዛቢያ ወለላቸውን መታ መታ አደረጉት።

"አልተኙም እንዴ አካሌ!" አለ ተካ ከሳቅ ጋር በተቀላቀለ አነጋገር፡፡ የመጠጡ ኃይል ምላሱን ትንሽ ያዝ ያድርገው እንጂ. ወፍራም ድምፁ ስልቱን
አልሳተም::

"አይዞት አይፍሩ እኔ ጠብቅዎታለሁ" ብሎ እንደገና ሳቀ::

"ከግንድ ያጣብቅህ" ለማለት አሰቡና ተውት፡፡

"አገር ቤት ነው የከረምኩት" አለ በረጅሙ
ተንፍሶ። የነገሩ አቅጣጫ ድንገት
በመለወጠ ቢገርማቸውም፡ መልስ አልሰጡትም::

"እማዬ እንደምንዎት ደህና ከረሙ ወይ በዓይነ ስጋ ለመገናኘት ያብቃን ብላዎታለች::"

"ደህና ናቸው? " አሉ እካሌ ድምጻቸውን ከፍ እድርገው።

"ደህና ነኝ” ትላለች የገጠር በተለያ የሷ አካባቢ ሰው ደህና አይደለሁም ማለቱን አያውቅበትም። ቃሬዛ ላይ እስኪጫን ድረስ ደህና ነኝ ነው የሚል፡፡ የትውልድ
ቀዬዬ ሰዎች ደህንነትን የሚለኩት ቆመው ከመሄዳቸው አንፃር ነው።

"እህህም" አሉ አካሌ "በ-ጄ ቀጥል » በማለት አኳኋን፡፡የተካ ጉዳይ ከማስረሻ ጉዳይ ወደሌላ በመቀየሩና አነጋገሩም የወዳጅነት በመምሰሉ ፍርሃታቸው ረገብ አለ።

"ታናሽ እህቴ በምጥ ሞተች፡ ሰባተኛ ልጅዋን ስትገላገል፡፡ እኔ እዛው ሆኜ ነው የሞተችው:: አጎቴን ወባ ገላገለው:: እማዬ የአጎቴን ሞት ስታረዳኝ `አረፈ
አለችኝ፡፡ አረፈ ለአካባቢው አገላለጥ ትክክለኛ ቋንቋ ነው:: በችጋርና በበሽታ እየተገረፈ ለሚኖር ሕዝብ፡ ሞት እረፍት ነው: ግልግል:: አይደለም እንዴ አካሌ?"
አለ ድምጹን ከቀድሞው ጎላ አድርጎ።

“እህህም" ብለው ዝም አሉ:: የተካ ንግግር ቀስ በቀስ ወደ አንጀታቸው የሚገባ ቀዝቃዛ ስሜት አሳደረባቸው።

« ሰውን አረገፈው' ትላለች እማዬ ፡ ሞት
በአካባቢው ያለውን ብርታት ስትገልጥ፡፡ እገሌንና እገሌን ተስቦ ወሰዳቸው እገሌ በደም ተቅማጥ አረፈ፣ እገሌን ወራጅ ውሃ ወሰደው፣ ያን የመሰለ ጉብል ፣ 'እናቱ በሀዘን አብዳ መቃብር ቤት ነው እምታድር .. ከብቱ ሣር አጥቶ አለት እየጋጠ በየሜዳው ተፈነቸረ' "ትላለች።

"አቤት አቤት፣ ይሄ ከላይ የመጣ መዓት ነው" አሉ አካሌ ማቃሰት በሚመስል ድምጽ፡፡

"እማዬም እንዲሁ ነው የምትል:: የአገሩ ሰው በየቤተክርስቲያኑና መስጊዱ እየተሰበሰበ "እግዚኦ ከዚህ
መዓት ሰውረን" እያለ አምላኩን በመማጠን ላይ ነው::"ብሎ ካዛጋ በኋላ እንደመሳል አለና፣

"የእማዬ አገር ሰዎች አሟሟትን ያውቁበታል፡አንቀላፉ እንዴ አካሌ?» አለ።

"ኧረ ሰማሀለሁ አሉ ሀዘን በተጫነው ድምጽ፡”

በቁሙ ነው ሞትን የሚጀምረውም የሚጨርሰውም።

"እንዴት? "

'ከችጋር ጋር ስለሚኖር ረሀብ ገደለኝ አይልም፡፡ጠኔ ሲያንገላታው መገጣጠሚያ አንጓዎቹ ሲላሉ፡ በሌላ
በሽታ አመካኝቶ ጣጣቴ እየተተኮሰ፡ ሳንባው ከጀርባው ተጣብቆ መተንፈስ ሲያቅተው ፡ በዋግምት እየተነጠቀ. እንዲያ እንዲያ እያለ ይሞተዋል።

ይሰሙኛል?»

"አዎን እሰማሀለሁ"

"ሽዋዬ እንደሞተች እናቴ ዘንድ ሄድኩ፣ ሞትን እዚያ ሆኜ ልጠብቀው ብዬ:: ለካ ሞት ወደነገሰበት ሥፍራ ኖሯል የሄድኩት:: ፊት ለፊት የተገናኘሁት
እስኪመስለኝ ድረስ በሥራው አየሁት፡፡ በችጋርና በደዌ ፈረስ እየጋለበ ሕዝቡንና ከብቱን ፈጅቶታል፣ አገሩን ወና አድርጎታል፡፡"

"ሞትን ተሸክሜ እንደሄድኩባት ያልጠረጠረችው እናቴ ምን አለች መሰለዎት" ብሎ እንደማሰብ አለና፣
ለወራት ከተኛችበት መደብ ላይ ቀና ብላ፣ የፈዘዙ ዓይኖቿን እያንከራተተች፣ ማመን አቅቷት እንደ እንሰት በደረቁ እጆቿ እራሴንና ፊቴን እየደባበሰች፣ ቀባሪ
ያላሳጣኸኝ ፈጣሪ ተመስገን፡፡ በመሞቻዬ ዋዜማ የልጄን ዓይን አሳየኸኝ' አለች፡፡ ድምጽ አጣች እንጂ እልል ለማለትም ሞክራለች፡፡ በደረቁ ከንፈሮቿ ፊቴን፣ እራሴን የአንገቴ ሥር ሁሉ ሳመችኝ ከመኪና ተራ የገዛሁትን ደረቅ ዳቦ በውኃ እየነከርኩ ሳጎርሳት በስስት ቶሎ ቶሎ
በላችና፣ 'ተመስገን አምላኬ፣ እንደኔ ማንን አድለሃል በቃ አሁን ጠግቤአለሁ የሞት ስንቄን አግኝቻለሁ፣ቀባሪዪም መጥቷል፤
ቶሎ ውሰደኝ አለች::"

"እኔን እኔን እንዴት ተጎድተው ኖሯል? " አሉ አካሌ ከልብ በሆነ ሀዘኔታ፡፡

"ፀሎቷ አልተመለሰላትም፤ እስከዛሬ አለች::"ብሎ ትንሽ ዝም አለና ለጉድ የጎለተኝ' ትላለች እማዬ ስለራሷ በምትናገርበት ጊዜ፡፡ «የመከራ ምስክር አድርጎኛል ጎተራዬ ሙሉ፣ በረቴ በከብት ትንፋሽ የሞቀ፣ ቤቴ የርሃብተኞች መሸሻ እንዳልነበረ ሁሉ የችጋርና የሞት ምሳሌ ሆኛለሁ" ትላለች፡፡ «እየሰሙኝ ነው አካሌ?»

«አዎን፣ ሰማሃለሁ::»

"እንዲህ ሆኖ አገኘሁት፣ የእማዬንና የአካባቢዋን ሁኔታ:: እኔማ በድብቅ የምሞትበትን ሥፍራ መርጨ
ነበር ወደዚያ መሄዴ፡፡ ሀገሩ ግን የሚሸሹት እንጂ የሚሸሽበት አልሆነም፡፡ እኔ ውስጥ ካለው ሞት ይልቅ፣እዚያ ያለው ገዝፎ ታየኝ፡፡ የሞት መላእክት ትዕዛዝ ለመፈጸም በየተራራው አናት ላይ በተጠንቀቅ ቆመው ቁልቁል የሚመለከቱ እስኪመስል ድረስ ነው፣ አካባቢው
የሚያስጨንቀው:: ለዚህ ነው ሸሽቼ እንደሄድኩ የመጣሁት:: ሕይወት ካለ ተስፋም መኖሩ ተሰማኝ፡፡አንድ ቀንም ዕድሜ ነው አልኩ፡፡ ነገ የተሻለ ነገር ይዞ
አይመጣም ያለው ማነው? ብዬ አሰብኩ፡፡ የሞትን ሹክሹክታ ከማዳመጥ ይልቅ፣ ተስፋን ማዛጋት ጥሩ ሆኖ ታየኝ፡፡ ተስፋ ሲሞት ነው እውነተኛው ሞት::
አይደለም እንዴ አካሌ?››

"ነው እንጂ! እኔ እምልህ ተካ'

"እመት"

“እውን መንፈቁን በሙሉ እናትህ ዘንድ ነበርክ?"

"አዎን"

እንዴት ብትጨክን ነው ብቅ ብለህ እንኳን ሳታየን መክረምህ?

"ጨክኜ አይደለም አካሌ፣ እንደሞትኩ ቆጥራችሁ እንድትረሱኝ ፈልጌ ነበር፡፡ በተለይ ሚጣዬ እናቷን እንዳጣች ሁሉ እኔንም እንደሌለሁ ብትቆጥረኝ ይሻላል
ብዬ አሰብኩ፡፡ እናቷን ስታጣ ተሳቀቀች፣ እኔ ስለያት ደግሞ ለምን ትደንግጥ? በተለይ ይበልጥ ከተላመደችኝና
የአባትነቴ ትርጉሙ ከገባት በኋላ ስታጣኝ፣ ሀዘኗ መሪር ይሆናል በማለት ነበር

"ቀድሞ ሟቹን እግዜአብሄር ነው የሚያውቀው:: ደግሞም ቅድም እንዳልከው ደግ ደጉን ማሰብ ይሻላል"
አሉ አካሌ፡፡

"ደግ ደጉን በማሰቤ ነው መንገዴን የቀየርኩ"

"ይሻላል ደጉን ማሰብ፣ ደጉን ማድረግ. .

"ደጉን መኖር" አለ ተካ ፈጠን ብሎ ጥቂት ዝም አለና ደግሞ፣
"ታዲያ እርስዎ ስለኔ ለምን ደግ አያስቡም? " አለ

ዝም አሉት አካሌ፡፡

"አካሌ"

"ወይ"

"ስለኔ ደግ አያስቡም? "

"ስለራሱ ደግ ለማያሰብ ሰው እንደምን ደግ ይታሰብለታል?

እንዲህ ሲወያዩ እኩለ ሌሊት አለፈ:: አካሌ ሀሳባቸውን ወደ ክፍላቸው ሰብሰብ አድርገው ሲመለከቱ፣
ጨብጠውት የነበረ መጥረቢያ ከእጃቸው ተንሸራትቶ መሬት ወድቋል፡፡ ወደ ማስረሻ ተመለከቱ፣ ከእንቅልፉ ከነቃች የቆየች ትመስላለች፡፡ ዓይኖቿን በሰፊው ከፍታ
ታያቸዋለች:: አልጋው ላይ ወጡና ዘና ብለው በመተኛት አቀፏት::

"ስለ ራሴም ሆነ፣ ለእርስዎና ለማስረሻ መልካም ማሰቤን በተግባር አሳይዎታለሁ አካሌ" አለ ተካ ሲያሰላስል ቆይቶ:፡ ኣካሌ ዝም ብለው የማስረሻን ፊት አንሶላውን እስከደረቷ ዝቅ አደረገችው::

"አይግፉኝ አካሌ" አለ ተካ ድምጸን ለዘብ አድርጎ

ውይይታቸውን ማስረሻ እንድትሰማው ስላልፈለጉ ዝም አሉት

አይግፉኝ፣ ዕድል
👍3
አቆራኝታናለች ፣ ሞት ሽዋዬን በመንጠቅ የጎዳው ሁለታችንንም ነው:: ሚጣዬን ጥዬቦት ሸክማችንን እየተረዳዳን የመከራን አቀበት አብረን ብንወጣው አይሻልም።

አካሌ የተካን ንግግር በሰሙትና ባሰላሰሉት ቁጥር፣ውስጣቸው የነበረው የጥላቻና የቅሬታ ካብ ቀስ በቀስ
ይናድ ጀመር፡፡ እሳቸውም እንዲህ በግድግዳ ተለያይተው ሳይሆን ፊት ለፊት እየተያዩ ሀዘንና ስብራታቸውን ሊያወያዩት ከጀሉ፡፡ ሀዘንና ብሶት ለወዳጅ ፣ በተለይም ለቅርብ ሰው ሲያዋዩት ይቀንሳል ይባል የለ?

የተካንና የአካሌን ውይይት ታዳምጥ የነበረችው ማስረሻ ቀና ብላ በመቀመጥ ወደ አካሌ አፈጠጠች::አስተያየቷን ስለፈሩ እሳቸውም ቁጭ አሉና እቅፍ
አደረጓት።

"አካሌ" ተጣራ ተካ፡፡

ዝም አሉት፡፡ እንደገና ተጣራ፡፡

"እንቅልፌ መጥቷል ልተኛ :: የቀረውን ነገ
እንጨዋወታለን” አሉ ማስረሻን እያዩ፡፡

"አዎን ብንጨዋወትና ብንመካከር ይሻላል።የእህል ርሀቤንስ እንደምንም አስታግሰዋለሁ፣ የሚጣዪን ርሀብ እንዴት ልቻለው? የመኖር ፍላጐት ካሳደሩብኝ
ነገሮች አንዱ የርሷ ርሀብ ነው::"

"እራበኝ አለ? " አለች ማስረሻ በኮልታፋ
አንደበቷ፣ አንዴ ወይዘሮ አካሌን አንዴ ደግሞ እሽጉን በር እየተመለከተች አነጋገሯ የጥድፊያ ነበር፡፡

"አይደለም፣ ሌላ ነገር ነው፣ ተኚ ተኚ መሽቷል" አሉ አካሌ በጀርባዋ ሊያጋድሟት እየሞከሩ፣በእምቢታ እጃቸውን እየገፋች ወደ እሽጉ በር አፈጠ
ጠች።

"ተኚ መብራቱን ላጠፋው ነው"

"እምቢየው" ብላ ታለቅስ ጀመር፡፡ ባባበሏት ቁጥር የልቅሶ ድምጽዋ እየጎላ ሄደ፡፡ ጭር ባለው ውድቅት እንዲያ መሆኗ አስጨነቃቸው:: አፏን በመዳፋቸው ከድነው ዝም ሊያሰኝዋት ሞከሩ አልሆነላቸውም፡፡እንዲ.ያ በመሆን ላይ እንዳሉ ተካ ድምጹን ከፍ አደረገና፣

"ሚጣዬ ምነው? " አለ፡፡ ማስረሻ ይህን ስትሰማ ለቅሶዋን አቋረጠችና ወደ እሽጉ በር አፈጠጠች::




ል አቆራኝታናለች ፣ ሞት ሽዋዬን በመንጠቅ የጎዳው ሁለታችንንም ነው:: ሚጣዬን ጥዬቦት ሸክማችንን እየተረዳዳን የመከራን አቀበት አብረን ብንወጣው አይሻልም።

አካሌ የተካን ንግግር በሰሙትና ባሰላሰሉት ቁጥር፣ውስጣቸው የነበረው የጥላቻና የቅሬታ ካብ ቀስ በቀስ
ይናድ ጀመር፡፡ እሳቸውም እንዲህ በግድግዳ ተለያይተው ሳይሆን ፊት ለፊት እየተያዩ ሀዘንና ስብራታቸውን ሊያወያዩት ከጀሉ፡፡ ሀዘንና ብሶት ለወዳጅ ፣ በተለይም ለቅርብ ሰው ሲያዋዩት ይቀንሳል ይባል የለ?

የተካንና የአካሌን ውይይት ታዳምጥ የነበረችው ማስረሻ ቀና ብላ በመቀመጥ ወደ አካሌ አፈጠጠች::

"እንጀራ ልስጥሽ? ዳቦ ወተት ላምጣ?» አሉ አካሌ እየተርበተበቱ፡፡ የጠየቋትን ሁለ እንደማትፈልግ ትከሻዋን ሽቅብ ቁልቁል በመነቅነቅ ገለጠችላቸው::
አኳኋኗን ስለፈሩት ወደኋላቸው ደገፍ ብለው በዝምታ ይመለከቷት ጀመር፡፡ ዓይኖቿን አፍጣና አንገቷን አስግጋ
ከተካ ክፍል የሚመጣ ድምጽ ስትጠብቅ ቆየችና ከቀድሞው በከፋ ሁኔታ አለቀሰች::

"ተካ?" አሉ አካሌ ከአልጋው ላይ እየወረዱ።ማስረሻም እያለቀሰች ተከተለቻቸው::

"እመት"

"ምን ይሻላል"

ዝም አላቸው::

"የፊትለፊቱን በር እከፍትልሀለሁ ዙረህ ና" አሉ ጭንቅ እያላቸው:: ማስረሻ ይህን ስትሰማ ዝም አለች፡፡

ትንሽ ጠበቁና "ተካ" አሉ አካሌ

እመት"

"ምነው ዞረህ በፊት ለፊቱ በር ና አልኩህ እኮ!"
"
የመሀለን በር ይክፈቱት"

"እንዴት አድርጌ?" አለ በሩ የታሸገባቸውን ሁለት ቀጫጭን ማገሮች እየተመለከቱ::

"እኔ ልክፈተው? " አለ ፈጠን ብሎ
ዝም አሉ።

ወዲያው በሩ ከወደ ተካ ክፍል ስለተገፋ ከሁለቱ የማሽጊያ ማገሮች የላይኛው የተመታበት ምስማር ተነቀለ፣ ቀጥሎ ደግሞ የታችኛው ማገር ምስማር
ተነቀለና በሩ በትንሹ ከፈት አለ፡፡ ተካ ክፍሉ ውስጥ ቆሟል፡፡ ከአካሌ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጡ:: ፈገግ አለና ነጫጭ ጥርሶቹን አሳያቸው:: ትንሽ ከሳና ጎስቆል
ከማለቱ በቀር ብዙ አካላዊ ለውጥ አይታይበትም፡፡ሉጫ ፀጉሩ እንደመጎፈር ብሏል፡፡ የጠይም ፊቱ አጋማሽ
በጺም ተሸፍኗል:: በረጅም ቁመናው ጎንበስ ባለ ጊዜ ነው፣ ማስረሻ እግሩ ሥር መቆሟን አካሌ ልብ ያሉት፡፡
ብድግ አደረገና አቀፋት:: ፊቷን አንገቱ ሥር ሽጉጥ አደረገችው:: የተካ ትልልቅ ዓይኖች እንባ ያዘንቡ ጀመር::

አካሌም ከእንባ እየተናነቁ ወደፊት ራመድ አሉና ወደተካ ክፍል የሚያስገባውን በር በሰፊው ከፈቱት፡፡
ማስረሻን ጥብቅ አድርጎ እንዳቀፋት ታቦት የተሸከመ ይመስል በቀስታ እየተራመደ ወደ አካሌ ክፍል ገባ፡:

ሁለቱም በእንባ ደፍ ውስጥ እየተያዩ ለብዙ ሰኮንዶች ተፋጠጡ፡፡ አንዳቸው እሌላው ውስጥ ያለን የመከራ ታሪክ የሚያነብቡ ይመስሉ ነበር::
"እማዬ" አለች ማስረሻ በመሃለ:: እንባቸውን ጠራረጉና ቀና ብለው አዩዋት:: በአንድ እጅዋ የተካን
አንገት አቅፋ ሌላውን ወደሳቸው ዘርግታለች::ተጠጓት እሳቸውንም አቀፈቻቸው:: ኣካሌ ደሞ አንዱን
እጃቸውን ተካ ትከሻ ላይ አሳረፉና ጉንጨን ሳሙት::እርሱም አጸፋውን መለሰላቸውና።

"ትላንት የነበረን ደስታ ዛሬ እስፍራው አለመኖሩ፡ ሊያገፋፋን አይገባም አካሌ:: የተሻለን ነገር ተስፋ እናድርግ፡ ሀሳብና ምኞታችንን እናጣምር:: እንዲያ
ስናደርግ ነው እፊታችን ያለውን የመከራ አቀበት የመውጫ አቅም የምናገኘው" አለ ከሽኩሽኩታ ትንሽ ጎላ በሚል ድምጽ፡፡ ይሄኔ ማስረሻ የሁለቱንም ትካሻ
መታ መታ አደረገች:: ሁለቱም ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ብሩህ የህጻን ፈገግታዋን በሳቃቸው አጀቡት::

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1👍1
አትሮኖስ pinned «#አቀበት ፡ ፡ #ክፍል_ሦስት (የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ #በገበየሁ_አየለ ..የሚሰማ ነገር የለም፡፡ ዓይኖቻቸውን እሽጉ በር ላይ እንደተከሉ እራስጌያቸው ያለውን መጥረቢያ በዳበሳ አነሱና ጠበቅ አድርገው ያዙት:: እንደገና ጥቂት ካዳመጡ በኋላ፣ "መተኛቴን ነው የሚያዳምጠው" አሉና ጉሮሯቸውን በመሞረድ ያለማንቀላፋታቸውን የሚያመለክት ድምጽ አሰሙ።ቀጥለው ደግሞ በያዙት መጥረቢያ ዛቢያ ወለላቸውን መታ መታ…»
#መንገዱን_ጨርቅ_ያድርግልሽ

"የወደደ አበደ ፣ ሲባል የሰማሁት
ባንቺ ነው ዘንድሮ ፣ ደርሶብኝ ያየሁት
የሚለውን ዘፈን
እየሰማሁ ሳለ ፣ ጥዬው ሄድኩኝ ጨርቄን
ይኸው አሳበድሽኝ!
በእርግማን መረኩሽ ፣ እንባሽ ያምጣው ሳቄን

ይኸው አሳበድሸኝ!
አካሄድሽ እንጂ ፣ መች ጎዳኝ መሄድሽ
ልሸኝሽ መርቄ
የወደድሽው ይጥላሽ ፣ ያመንሽው ይካድሽ
ቆመሽ የሰቀልሽው ፣ ቁጭ ብሎ ያውርድሽ
ጨርቃቸውን ጥለው
እብዶች ያለፉበት ፣ ጨርቅ ይሁን መንገድሽ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ኑሮ

የሰው ኑሮ
አንድም የንብ መንጋ፣
ተፈጥሮ በስርአት ያደላደለው፤
አንድም የውሻ ስርያ፣
ፍትወት ያግተለተለው።

🔘በድሉ ዋቅጅራ🔘

ሚያዝያ 2012
#በዚህ_አለም

በዚህ ገጸብዙ ዓለም፣
እንደጠዋ ጸሃይ ገልፋጭ፤
እንደአመሻሽ ጀምበር አሽሟጣጭ፤
የለም።

🔘በዱሉ ዋቅጅራ🔘

መስከረም 2009
#አካሔድ

ፍጥነት የምንለው ነው የማዝገም ጥላ
ወደፊት የሄደ ቀርቷል ወደኋላ።
ብልሆች በመንገድ ማዝገም ነው የሚመርጡት
የደረሱ ናቸው መድረሻ የሚያጡት።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#የሐገር_ሥራ

ጥበበኛ መምህር
ለደቀመዝሙር ፥ ጠቦ አይገለጥም
ፀሐይ መፍጠር ሲችል ፥ ሻማ ሆኖ አይቀልጥም
የሀገር ሥራ እያለ ፥ የቤት ሥራ አይሰጥም።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
"ቆንጆ ነኝ" ባይ ማነሽ?

በውበትሽ ማርከሽ
ንጉስን ከዙፋን ፥ ማውረድ ሳትችዪ
ማነሽ "ቆንጆ" ሲሉሽ ፥ አቤት የምትዪ?

ድሮ ድሮ እኮ
የሴት ልጅ ውበቷ ፥ ዙፋንን ያስረሳል
ያንዲት ሴት ቁንጅና ፥ ካንድ ጦር ይብሳል።

ድሮኮ ድሮኮ
መንግስት ህዝብ ላይ ፥ በስልጣን ሲለግም
ከዙፋን ለማውረድ
አንዲት ቆንጆ እንጂ ፥ ትግል አያስፈልግም።

ድሮኮ ድሮኮ
ፈጣሪ የሾመው ፥ ጥበብን አድሎት
ዙፋኑን እንዳይለቅ
"ቆንጆ አታሳየኝ" ነው ፥ ያንድ ጠቢብ ፀሎት።

ንጉስን ለማውረድ ፥ህዝብ ሲያጣ አቅም
እኛው ከኛው ጦር ጋር ፥"ልቀቅ አንለቅም"
እየተባባልን ፥እርስ በርስ ብናልቅም
ቆንጆ ስንል አቤት ፥ ያለንን አናውቅም።

ንጉስን ከዙፋን
በውበትሽ ማርከሸ ፥ ማውረድ የማትችዬ
አንዳችም ደም ሳይፈስ ፥ ህዝብ የምታስጥዬ
ማነሸሸ "ቆንጆ" ሲሉሽ ፣ "አቤት"የምትዪ

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ቅበላ


#ክፍል_አንድ


#ከአዶኒስ

በደብዛዛ ቀይ ብርሃን በተሞላችው ባለ አንድ ክፍል ቤቷ ውስጥ ወደ በሩ ጠጋ ብላ ተቀምጣ ውጭ ውጭውን ታያለች፡፡ ቅዝዝ ያሉ ዐይኖቿን ጨለማው ላይ የሰካች ቢሆንም ምንም ነገር የምታይ አትመስልም።ቀያይ ጭኖቿ ለሚተላለፈዉ መንገደኛ በቅጡ እንዲታዩላት ባለስንጥቅ ቀሚሷን ሆነ ብላ ገለጥለጥ
አድርጋዋለች።አልፎ አልፎ በውል የማይሰሙ ቃላት እያጉተመተመች ከንፈሯን ትመጥጣለች:: ድንገት
ስትታይ ጠና ያለች ሴት ብትመስልም ልብ ብሉይ ላስተዋላት ከሰላሳ አምስት እስከ አርባ ባሉት የዕድሜ አንጓዎች መሃል እንደምትገኝ መገመት አያዳግትም፡፡
ፀዳል ትባላለች።

ከፀዳል በር በስተግራም በስተቀኝም በርካታ ተመሳሳይ በሮች በመደዳው ይታያሉ:: እያንዳንዱ ቤት ምን ያህል ጠባብ እንደሆነ ከበሮቹ መቀራረብ መገመት ይቻላል፡፡ በየቤቱ የተለያዩ ቀለማት ያላቸው አምፖሎች በርተዋል፡፡ ከአንዳንዱ ቤት የሚወጣው ደመና መሰል የጊርጊራ ጢስ መጀመሪያ የቤቱን የመብራት ቀለም እንደያዘ በራፉ ላይ ቡልቅ ይልና ወዲያው ደግሞ ጭለማው ውስጥ ክስም ይላል።

አለፍ አለፍ ብለው ጥቂት የተዘጉ በሮች ይታያሉ፡፡እነኚህ ታዲያ ከውጪ የተቆለፉ ሳይሆኑ ምሽቱ የቀናቸው ባለቤቶቻቸው ለጊዜው ከውስጥ የቀረቀሯቸው
ናቸው:: ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይከፈቱና የተቀሩትን በሮች ይመስላሉ፡: ባለቤቶቻቸውም ልክ ምንም ያልተፈጠረ ዓይነት ምሽቱ ላይ እንደገና ያፈጡበታል፡፡

እዚህ ቦታ እያንዳንዱ ምሽት ለእያንዳንዷ ሴት አዲስ ነው። ትናንት እንዲህ ነበረና ዛሬ እንዲህ ይሆናል ብሎ መገመት አይቻልም:: ዛሬ ሶስት አራት ደንበኞች
ያስተናገደች ሴት ነገ አንድም ላይቀናት ይችላል።ገበያ የሸሻቸው ዕለት ሴቶቹ የማይጠረጥሩት ነገር የለም።ቢሆንም ባይሆንም በሚል የተለያዩ ሙከራዎችን
ያደርጋሉ:: አለባበስ ይቀይራሉ - ልዩ ልዩ ነገሮች በውሃ እየበጠበጠ ደጃፋቸውን ይረጫሉ የጊርጊራቸውን ጭሳጭስ እየቀያየሩ ይሞክራሉ የተረጩትን ሽቶ
በገደቢስነት ይጠረጥሩና ሌላ ሽቶ ይረጫሉ - የፀጉር አሰራራቸውን ይቀይራሉ - ብቻ የዕለቱ “ቋጠሮ” ይፈታ
ዘንድ የመሰላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡

ዛሬ ከሁለት ወር በኋላ የሚፈታው አቢይ ፆም የሚያዝበት የቅበላ ምሽት ነው:: እናም ፀዳል ወዲህም ወዲያም ብላ ቢያንስ ግማሽ ኪሎ ሥጋ - ይህም አልሆን ካለ የሁለት የሶስት ብር ቅንጥብጣቢ መግዛት መቻል አለበት።
ባጣ ባጣ አንድ ደንበኛ አላጣም በሚል
ተስፋ ወዲያውም በግራና ቀኝ ያሉ ባላንጣዎቿ “አጣች ብለው ደስ እንዳይላቸው” በማለት - ሽንኩርቷን
ስትከታትፍና ስታቁላላ ነው ያመሸችው::

__የፓርላማው ሰዓት የአራት ሰዓቱን ደወል አሰማ::ፀዳል እንደመገረምም እንደመቁ ነጥነጥም አለች::
በባለላስቲክ ጨርቅ ወደላይ ሰብሰባ አስይዛው የነበረውን ፀጉራን የመመንጨቅ ዓይነት ፈታችና ወደ ታች
እየነሰነሰች ማስተካከል ጀመረች።

በስተቀኝ ካለችው የሥራ ባላንጣዋ ቤት እየመጣ ፀዳልን ሲረብሻት የቆየው ቅቤ የጠገበ የረጋ ወጥ ሽታ ጭራሹን እየገነነ መጣ፡፡ ፀዳል መጥፎ ጠረን እንደሽተታት
ሁሉ በአውራ ጣቷና በሌባ ጣቷ አፍንጫዋን ጨመቅ ጨመቅ አደረገችና ከአንገቷ ብቻ ወደ ውስጥ ዘወር ብላ
ግድግዳው ጥግ ካለችው የኬሮሲን ምድጃዋ ላይ አንድ አገር ሽንኩርት ከትፋ የጣደችበትን አነስተኛ የብረት ድስት
አየችው፡፡ ለአፍታ ያህል ወደ ውስጧ ፈገግ ብላ በራሷ ስትመፀት ቆየችና ድንገት በመርፌ ጠቅ ያደረጓት ይመስል
ነጠቅ ብላ በመነሳት ወደ ምድጃው አመራች:: ድስቱን አውርዳ ኬሮሲኑን አጠፋችና እጆቿን ደረቷ ላይ አጣምራ
ከወዲያ ወዲህ መንቆራጠጥ ጀመረች፡፡

“እንግዲህ ወይ እዛች ሜንጦ ጋ ደርስህ ትመጣ እንደሆን እንጂ አለች ለጣራ ግድግዳው የምታወራ ዓይነት።“አንዳንድ ቀን እኮ አያምጣው ነው::” ስትል አጉተመተመችና እንደገና ቦታዋን ይዛ ተቀመጠች።

በመንገዱ የሚያልፈውና የሚያገድመው ሰው ቁጥር እየሳሳ መጥቷል።ብዙም ሳይቆይ መሉ በመሉ ጥምብዝ ማለታቸው በግልፅ የሚታይባቸው አንድ አዛውንተ መላ ቅጡ በጠፋ አረማመድ እየተውተረተሩ በማለፍ ላይ ሳሉ ከፀዳል በራፍ ሲደርሱ ቆም አሉና
ነፋስ እንዳየለበት ለጋ ተክል እየተወዛወዘ ትክ ብለው ያዩዋት ጀመር፡፡ ፀዳል ስንጥቁን ቀሚሷን ከወትሮው በተለየ ግልጥልጥ አድርጋ ጭኖቿን እያሳየቻቸውና ይበልጥ ይስቧቸው ይሆናል ብላ የገመተቻቸውን
ተጨማሪ “እንቁልልጮች እያፈራረቀችባቸው ወጥመዷን ማጠባበቅ ጀመረች:: እጆቻቸውን ሱሪ
ኪሳቸው ውስጥ እንደከተቱ አዛውቱ- ለአፍታ ያህል ዐይኖቻቸውን በፀዳል የተጋለጠ ጭኖች ላይ ሲያንከባልሉ
ከቆዩ በኋላ ግንባራቸውን ቋጠር ፈታ ከንፈራቸውን ሸፈፍ ሸፈፍ አደረጉና ትከሻቸውን ሰብቀው እየተወላከፉ
መንገዳቸውን ቀጠሉ:: ዐዳል ሁለመናዋን መልሳ በመጠኑ ሽከፍከፍ አደረገችና በመገረም ዓይነት እንደገና ከንፈሯን መጠጠች።

“አንተን አይደለም እንዴ ምለው? - እዛች መናጢ ጋ ደርሰህ ና ማለት አማርኛ አይደለም?” አለች ዐይኖቿን ከመንገዱ ላይ ሳትነቅል ወዲያው ከአልጋዋ ስር በደረቱ እየተሳበ አንድ እድሜው ከአስራ አምስት የማይበልጥ ልጅ ብቅ አሐ።

ምን ልበላት” ሲል ጠየቃት ከጀርባዋ ቆሞ ራሱን እያከከና እንደመንጠራራት እያለ።

ስትላት ካለሽ አስር ብር ካልሆነልሽ ደግሞ አምስትም ቢሆን ላኪልኝ ነገ ጠዋት ለቡና ስመጣ ይዤልሽ እመጣለሁ አደራ አደራ ጦም መያዣ አጥቼ ነውና የዛሬን ብቻ ቅበሪኝ ብላሻለች በላት አለችው፣ ዘወር ብላ እንኳን ሳታየው ዐይኖቿን መንገዱ ላይ እንዳቀዘዘች፡፡ “ደግሞ እንደ ዔሊ ስትጎተት ዓመት
ቆይተህ ና አሉ!
ማሙሽት ሙት አምስት ደቂቃ አሳልፍና እንተያያለን

ማሙሸት ልጇ ነው :: ገና ወጣት ሳለች በትዳር ከተቆራኘችውና ብዙም አብሯት ለመኖር ካልታደለው የሕግ ባለቤቷ ያፈራችው:: ማሙሸት ሁለተኛ ዓመቱን
እንኳን በቅጡ ሳያገባድድና አዲሱ ትዳርም ገና ሞቅ ሞቅ ሳይል ነበር የማመሸት አባት ወደ አፈርነቱ
የተመለሰው:: ሕይወተ ገና በጠዋቱ፡ በረቂቅ ጥፊዋ ያስደነገጠቻት ፀዳል ባለቤቷ ትቶላት ባለፈው አነስተኛ
ጥሪት ጥቂት ጊዜ ስትንገታገት ቆየች:: ቀሪ ሀብቴ የምትለውና መማያዋም መገዘቻዋም የሆነው ማሙሸትም
ትምህርት ጀምሮ አንድ ሁለት ክፍል ቆጠረ:: የአባቱ በሕይወት ያለመኖር ልጇ ላይ ሊፈጥርበት የሚችለውን
ክፍተት ለማጥበብ ፀዳል የአቅሟን ሁሉ ጣረች።በሕይወት እስካለች ድረስም ማሙሸት ቢያንስ መሰረታዊ
የሚባሉት ነገሮች ሲያጥሩት ላለማየት ለራሷ ቃል ገባች፡፡

ይሁን እንጂ ነገሮች እንደግምቷ አልሄዱም። ዕለት ተዕለት ማጣፊያው እያጠራት መጣ፡፡ ይሄኔ ነበር
እንደመጨረሻ አማራጭ ሴትኛ ለማደር የቆረጠችው።ታዲያ ይህም ቢሆን እንደአጀማመሩ አልቀጠለም።
ከዓመት ዓመት ዝቅ እያለ የሚሄድ የሕይወት ቁልቁለት ሆነ። ፀዳ ፀዳ ባሉ ሆቴሎችና መዝናኛዎች የተጀመረው
የእንጀራ ገመዷ እየሰለሰለ በመምጣት እዚህ አሁን ካለበት ደረጃ ደረሰ። ያም ሆኖ የልጇ የማሙሸት ትምህርት
አንድም ጊዜ ተስተጓጉሉበት አያውቅም። ማሙሸት የሚያስፈልጉትን ነገሮች ያሟላች ከመሰላት ደግሞ ሌላ
የሚያሳስባት ነገር የለም። በተለይ አሁን አሁን ለዐዳል ሕይወት” ማለት ማሙሸት” ማለት ሆኗል።

በዚህ እንጀራ ከተሰማሩ የፀዳል ጎረቤቶች የተወሰነቱ እንደሷው ሁሉ ባለልጆች ናቸው:: ታዲያ በሥራው ፀባይ ምክንያት ልጆቻቸውን እንደሚፈልጉት
አድርገው ማሳደግ አይቻላቸውም:: ደንበኞቻቸውን የሚያስተናግዱት በአብዛኛው ከአመሻሹ እስከ እኩለ
ሌሊት ባለው ጊዜ ውስጥ በመሆኑ ይሄንን ጊዜ ልጆቹ ከየቤታቸው ውጪ ለማሳለፍ ይገደዳሉ። አንዱ ሎተሪ
ሲያዞር ያመሻል - ሌላው
👍1
ሲጋራ ያዞራል ሌላኛው ቅቅል እንቁላል - ሌላኛዋ ቆሎ- ያኛው መፋቂያ - ያቺኛዋ በቆልት - ወ.ዘ.ተ:: የተሰማሩበት ሲመለሱ ደግሞ
እዚያው መንደራቸው ውስጥ ውር ውር ሲሉ፣ ሲላፉ፣ አላፊ አግዳሚውን ሲያስቸግሩ፣ ሰካራም ሲዘርፉና
የመሳሰሉትን ሲያደርጉ የመግቢያ ሰዓታቸዉን ይጠባበቃሉ:: የትምህርት ነገር በአብዛኛው የሚታሰብ አይደለም። አንዳንዶቹ፣ ለወጉ ቢጀምሩት እንኳ እምብዛም ሊገፉበት አይቻላቸውም።

ፀዳል ወደዚህ ቦታ ስትመጣ ማሙሽተ ስምንተኛ ዓመቱን እያጋመስ ነበር፡፡ ታዲያ እንደደረሰች አካባቢውን በሚገባ ካጤነች በኋላ በመጀመሪያ የወሰነችው ልጇ
የተቀሩትን የመንደሩ ልጆች ዕጣ የሚጋራበት ሁኔታ እንዳይፈጠር የአቅሟን ሁሉ ለማድረግ ነበር፡፡ እናም
ማሙሸት ቀን ቀን ትምህርት ቤት ይውላል - ከዚያ መልስ ከሷው ጋር እቤት ውስጥ ያመሻሻል እንግዳ በምታስተናግድባቸው ሰዓታት አልጋዋ ሥር ለጥ ብሎ ይቆያል:: ከመንደሩ ልጆች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዲፈጥር ዕድል አትሰጠውም።

ማሙሽት አልጋ ሥር የሚገባወ እንግዳ
እስኪመጣ ጠብቆ አይደለም:: እንግዳው በየትኛው ሰዓትና ደቂቃ እንደሚመጣ አይታወቅም:: እናም ገና መሸትሸት
ማለት ሲጀምር ማመሽት ከእናቱ አልጋ ሥር ይገባና ለዚሁ ብላ በደረተችለት ጨርቃጨርቅ ላይ ለጥ ይላል፡፡
ፀዳል የቤቷን ሥራ ስትሰራም ሆነ በራፏ ላይ ተቀምጣ ደንበኛ ስትጠብቅ አልጋዋ ሥር ካለው ልጇ ጋር የቆጥ
የባጡን ስታወራ ታመሻለች:: ታዲያ ሚስጥሩን ለማያውቅ ብቻዋን የምትለፈልፍ ወፈፌ ነው የምትመስለው።

ፀዳል ሥራዋን የጀመረች ሰሞን ነባሮቹን ሴቶች ክፉኛ እረፍት የነሳቸው አንድ ጥያቄ ነበር - ከደንበኞቿ
ጋር በምትሆንባቸው ሰዓታት ልጇ የት እንደሚቆይ፡፡የኋላ የኋላ ግን በዚህም በዚያም ብለው አልጋዋ ሥር
የማምሽቱን ሚስጥር ደረሱበት።

እንደው በፈጠረሽ ልጅሽ አይደል እንዴ?
እንዴት ያን ሁሉ ጉድሽን እንዲሰማ ታደርጊዋለሽ?”...

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍1
#አቃፊ_ነሽ

ቆፈን በረታብኝ ፥ ብርዱ በኔ አየለ
ደሜ ቀዘቀዘ
ኩንታል ምናምኔ ፥ ኪንታሮት አከለ።
ይህ አልበቃ ብሎኝ
በአልጋዬ በኩል ፥ ጣሪያዬ ያፈሳል
ነይ አቅፈሽኝ ተኚ
ክንድሽ ከበረዶ ፥ እሳት ይለኩሳል
ያንቺ ገላ ሙቀት
እንኳን የተኛ እንትን
ከተኛ ሕዝብ ላይ ፥ ተቃውሞ ያስነሳል!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍1
#ቅበላ


#ክፍል_ሁለት


#ከአዶኒስ

እንደው በፈጠረሽ ልጅሽ አይደል እንዴ? "እንዴት ያን ሁሉ ጉድሽን እንዲሰማ ታደርጊያለሽ?"

ስትል ለመጀመሪያ ጊዜ ትጠይቃታለች የፀዳል ድርጊት
በእጅጉ ከዘገነናቸው መሰል ጎረቤቶቿ አንዷ፡፡ የተቀሩትም በየራሳቸው ጊዜ ይህንኑ ይጠይቋታል:: “እንደናንተ ልጆች ዱርዬ . ሌባ - መጨረሻው ከርቸሌ የሚሆን ወንጀለኛ ከሚሆንብኝ ጉዴን ቢሰማብኝ ይሻለኛል::” ትላቸዋለች
ደግሞስ ምኑ ላይ ነው ጉድነቱ?
የእናንተዎቹም እኮ አልጋችሁ ሥር ሆነው አልሰሙም አላዩም ማለት አያውቁም ማለት አይደለም::”

እንጀራችን አይደል እንዴ? ይህ አባባሏ ለፀዳል በቂ ምክንያት ያቀረበች መስሉ ይታያት እንጂ ለጎረቤቶቿ ጨርሶ
አይዋጥላቸውም:: በተለይ እሷ በሌለችበት ጉዳዩን ካነሱት እየተቀባበለ ሲያብጠለጥሏት ነዉ የሚመሸዉ
የሚነጋው:: ደግሞኮ ዱርዬ ከሚሆንብኝ ትላለች . ሞልቃቃ! ሆሆ......ይ! - የገዛ ልጄ ገበናዬን ከሚያይብኝ እንኳን ዱርዬ ለምን ሰው የሚበላ ጭራቅ አይሆንብኝም!”
አልጋ ሥር ተኝቶ የእናቱን ጉድ
ሲሰማ ማምሽት ልጅን ጨዋ የሚያደርግ ከሆነ እንግዲህ እናያለና - የኛ ዘበናይ - ከጎኗ ስታገኘው ልክ ትገባ የለ!” ትላለች ሌላዋ:: ሌላ ርዕስ እስኪገኝ “ዘበናይ”ቱን መላጥ መፈልፈሉ ይቀጥላል፡፡

ፀዳል ከወደመንገዱ የማመሸት ኮቴ እየቀረበ ሲመጣ ተሰማት፡፡ እንኳንስ ብቻውን ሆኖ በሚተላለፍ ግርግር መሃልም የማሙሸትን ኮቴ መለየት ተስኗት
አያውቅም:: ሌላው ቀርቶ የላከችውን ነገር አግኝቶ ሲመጣና አጥቶ ሲመጣ እንኳን በአረማመዱ ታውቃለች::

“የለኝም አለችህ አይደል ይቺ የተረገመች ሜንጦ?” አለችው ገና ከመግባቱና የመልዕክቱን ቃላት በሆዱ እያረቀ ሳለ፡፡

“እምም እንዳለችሽ - " በማለት ጀመረ ፀጉሩን አከክ አከክ እያደረገ፡፡ “የኔ ቆንጆ የኔ ቆንጆ - ምናምኒት የለኝም - እንደውም እኔ ራሴ ትንሽ ካለሽ ብዬ አንቺጋ
ልመጣ ስል ነው የላክሺብኝ - እንግዲህ - ባይሆን ....

“ዝጋ!” እንደብራቅ ጮኻ አቋረጠችው:: “ወሬ ይዘህልኝ ና ብዬ ነው የላኩህ? አልሰጠችኝም ማለት አትችልም በአጭር አማርኛ? ዱሮስ ከዚች መናጢ
እጅ ገንዘብ ይወጣል ብዬ ሊያውም በዛሬው ቀን ! -ተወው እኔው ነኝ ጥፋተኛዋ::”

“ምን አስጨነቀሽ ግን ፀዲ?
አላት በአንድ እጁ ፀጉሯን በሌላኛው እጁ የገዛ ሆዱን እያሻሽ፡፡ “ሥጋ
ቢቀርስ? - ምንድነው ይሄን ያህል? ”::
“ እሱማ ቀርቷል ! - ወደህ ነው የሚቀረው? አለችው ውጪ ውጪውን እያየች፡፡

እኔ ምልህ -አንተ ስትደርስ ምን ምን
እያደረገች ነበር?

.....ምንም::”

“እንዴት “ምንም ? "

“በቃ - ቡና ተፈልቷል - ቄጤማ ምናምን ተጎዝጉዟል ፈንዲሻ ምናምን ... በቃ::”

“ሌላስ ?”

“ሌላ ቴፑ ተከፍቷል ... ሰንደል ይሁን እጣን ነገር ይጨሳል....በቃ::”

“ማሙሽት!” አለችው አሁንም ዐይኖቿን ከመንገዱ ላይ ሳትነቅል፡፡ “አርቲ ቡርቲውን ትተህ የጠየኩህን
መልስልኝ - እሷ ምን እያደረገች ነበር?”

“እሷ? . ምንም::”

“ንገረኝ ! ” አምባረቀችበት።

“እንትን - እንትን እያደረገች - ”

“ምን እያደረገች?”

"እም እንትን"

“ንገረኝ አንተ! ” አፉ አልላቀቅ ወዳለው ልጇ ዞራ አጉረጠረጠችበት።

“እ - እየ - እየከተፈች::”

“ምን እየከተፈች?

“እም....እ - እንትን::”
..
“ዋ ብቻ ዛሬ! ሰይጣኔን ባታመጣው ይሻልሃል! . "አለችው ብድግ ብላ ልታንቀው እየቃጣት:: “ምን
ድነው - እየከ - ተፈች የነ - በረው?”

“' ሥ. .” ጋ ።

መች አጣሁት! - ይቺ ከርሳም!” ፊቷን ወደ
መንገዱ መልሳ አንገቷን በትዝብት ወዘወዘችና ዐይኖቿን ድቅድቁ ላይ ተከለች:: በል አንተ ደግሞ እነዚህ
አትገተርብኝ::” ማለቷ ማሙሸት እንደሰለጠነ ውሻ ሸክክክ ብሎ አልጋዋ ስር ገባ።

“እኔ ምልህ አለች ለአፍታዎች ያህል
ስታሰላስል ከቆየች በኋላ:: ያ ጓደኛህስ? - ትንሽ እንኳን ሊያገኝልህ አይችልም? ከፊት ለፊቷ: ካለው ጭለማ እንጂ ከልጇ ጋር የምታወራ አትመስልም::
“እሱ ቢችልማ እስካሁን አስችሎኝ ዝም እልሽ ነበር? አላት ማሙሸት አልጋው ሥር እየተመቻቸ፡፡ይህ እናትና ልጅ የተግባቡበት ቋንቋ የሁለታቸው ብቻ
ሚስጥር ነው:: ያ ጓደኛህስ? " ስትለው ምን ማለቷ እንደሆነ ማሙሸት ገብቶታል
እሷም እንደሚገባው ታውቃለች:: ግን ፡ ማሙሸት ምንም ዓይነት ጓደኛ እንደሌለው እንኳንስ እናቱ እያንዳንዱ መንደርተኛ ያውቃል።

ከሰባት ዓመታት በፊት ማሙሸት ከእናቱ ጋር ወደዚህ ቦታ እንደመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ በእናቱ አልጋ ሥር ያሳለፈው ምሽት ቀሪ ዕድሜውን ሙሉ ሊረሳው የማይችለውና የስምንት ዓመት ጮርቃ
አዕምሮው ውሉ እንደጠፋ ጉልጉል ልቃቂት ዳግም ወደ ቀድሞ ሁኔታው
ላይመለስ የተዛባበት ነበር::

ያን ምሽት የመጀመሪያው የፀዳል እንግዳ እንደገባ ቀደም ብሎ አልጋው ጋር ቦታውን ይዞ የነበረው ማሙሸት እናቱ በሰጠችው መመሪያ መሰረት ትንፋሹን
ሳይቀር እየተቆጣጠረ ፀጥ ረጭ ብሎ መጠባበቅ እንደጀመረ ነበር ድንገት አንድ ጥያቄ ዉል ያለበት::
በእርግጥ ፀዳል በዚህ በአዲሱ ሥራዋ ለሁለታቸውም የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች የምታሟላበት ገንዘብ ልታገኝ
እንደምትችል አስቀድማ ነግራዋለች:: ይሁን እንጂ አሁንም ግልፅ ያልሆነለት ነገር አለ፡፡ ይህ የመጣው ሰውዬ በእርግጥ ከፀዳል የሚፈልገው ምንድነው? ምንስ ብታደርግለት ነው ገንዘብ ሊሰጣት የሚችለው? ለምንስ
ይሆን ወደሷ የሚመጡት እንግዶች ሁሉ ወንዶች እነደሚሆኑ የነገረችው?

ሕፃን ማሙሸት እነኚህን ጥያቄዎች እየፈተለና እያጠነጠነ ሳለ በሚሰማቸው ድምፅች ፀዳልም እንግዳውም ልብሶቻቸውን እያወላለቁ እንደሆነ ይረዳል።

አእምሮው ውስጥ እየተብላሉ ባሉት ጥያቄዎች ላይ ሌላ ጥያቄ ! ልብስ ማውለቅን ደግሞ ምን አመጣው?
ማሙሸት እስከሚያውቀው ድረስ ልብስ የሚወለቀው ገላ ለመታጠብ ወይ ደግሞ ለመተኛት ነው:: እና ውሃም ሆነ ዕቃ ስታዘጋጅ አላያትም:: ስለዚህ ገላቸውን
ሊታጠቡ ሊሆን አይችልም። አብረው ሊተኙ ነው ማለት ነው? ከሆነስ ሰውዬው
ከፀዳል ጋር ለመተኛት ሲል ብቻ ገንዘብ ይከፍላታል?

ከጥቂት አፍታዎች በኋላ የአልጋው ትዕይንት ይጀመርና ከበላዩ በሚሰማሁ ድምፅ ማሙሸት ጭራሹን ግራ ይጋባል። የትግል ዓይነት ድምፅ ይሰማዋል፡፡ሰውዬው ቁና ቁና ይተነፍሳል:: ፀዳል አልፎ አልፎ የማቃሰት ዓይነት ሕእ” ማለቷ በቀር ድምጿ ሰውየው ፀዳልን ምን እያደረጋት እንደሆነ ለመገመት ማሙሸት
የቱንም ያህል ጨቅላይቱ ናላወን ቢያዞራት ቢያሽከረክራት ይህ ነው የሚባል ስዕል አልመጣልህ ይለዋል፡፡ በደፈናው ግን በአንድ ነገር ላይ እርግጠኛ
ይሆናል ይህ ሰውየው ፀዳልን እያደረጋት ያለው ነገር ምንም ይሁን ምን በጭራሽ ፀዳል የምትፈልገው ነገር አይደለም:: ማሙሸት አንድ ከዚህ በፊት የማያውቀው
ዓይነት የፍርሃት ስሜት ይጫነዋል፡፡

ማሙሸት ከእናቱ ጋር የገባበትንና ገና ከጅምሩ ውንጅብጅብ የሆነበትን ይህን አዲስ ሕይወት ቀስ በቀስ ለመላመድ የወሰደበት ጊዜ ቀላል አልነበረም። ከዚህም በላይ በየምሽቱ፡ ለዚህ ምን እንደሆነ ሊገባው ላልቻለ እንቆቅልሽ ጉዳይ ከእናቱ ዘንድ የሚመጡት የተለያዩ
ወንዶች እናቱ ላይ የሚያደርሱባት የስጋም ሆነ የመንፈስ ጫና ጉዳያቸውን ጨርሰው ሲወጡ ከሚጥሉላት አራትና አምስት ብር ጋር ጨርሶ ተጣጥሞለት
ኢያውቅም።እናም - ለእነዚህ በድምፃቸው እንጂ በአካል ለማያውቃቸው የእናቱ እንግዶች ያለው አመለካከት በጥላቻና በበቀል ስሜት የተለወሰ ሆነ።

ከወራት በፊት አንድ አመሻሽቶ የመጣ የእናቱ እንግዳ ሱሪውን
👍2
እያወለቀ ሳለ የኪስ ቦርሳው ይወድቃል።እንደወትሮው ሁሉ
አልጋ ስር የነበረው ማሙሸት በተንዘረፈፈው የአልጋው ምንጣፍ
ክፍተት መሃል ቦርሳውን ያየዋል:: ለመጣበት ጉዳይ የተቻኮለው ሰው ቦርሳውን እዚያውበወደቀበት ትቶ
እየተጣደፈ አልጋ ላይ ይወጣል:: የተለመደው የአልጋ ላይ ግርግር እንደተጀመረ ማሙሸት ድንገት አንድ ሃሣብ ይመጣበታል።ቢያንስ ዛሬ እናቱ የሚገባትን ክፍያ ማግኘት አለባት በማለት አጋጣሚው የፈጠረለትን ዕድል
ላለማለፍ ይቆርጣል:: ቀስ ብሎ እጁን በመላክ ቦርሳውን ሳብ ካደረገ በኋላ በውስጡ ከነበሩ የባለ አስር ብር ኖቶች
መሃል አንዲን ይመዝና ቦርሳውን መልሶ እንደነበረ ያስቀምጣል።ሰውዬው ከሚሰጣት አምስት ብር ይሄ ሲጨመር ለእናቱ፡ በቂ ክፍያ እንኳን ባይባል የተሻለ
መሆኑን እያሰበ የሰውዬውን መውጣት ይጠባበቃል።

በማግስቱ ማለዳ ላይ ስለሁሉም ነገር በዝርዝር ነግራት አስር ብሩን ሲሰጣት እናቱ፡ ላይ ያየው ስሜት ግን ማሙሸት ፈፅሞ ያልጠበቀው ዓይነት ነበር፡፡ ውቃቢ
እስኪርቀው የቁጣ መዓት ካወረደችበት በኋላ ዳግም
“እንዲህ ዓይነት ነገር” ሲያደርግ የሷና የሱ “መጨረሻ” እንደሚሆን አስጠንቅቃው ነበር ጭራውን ቆልፎ ወደ ትምህርት ቤት የሄደው፡፡

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
1
አትሮኖስ pinned «#ቅበላ ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #ከአዶኒስ እንደው በፈጠረሽ ልጅሽ አይደል እንዴ? "እንዴት ያን ሁሉ ጉድሽን እንዲሰማ ታደርጊያለሽ?" ስትል ለመጀመሪያ ጊዜ ትጠይቃታለች የፀዳል ድርጊት በእጅጉ ከዘገነናቸው መሰል ጎረቤቶቿ አንዷ፡፡ የተቀሩትም በየራሳቸው ጊዜ ይህንኑ ይጠይቋታል:: “እንደናንተ ልጆች ዱርዬ . ሌባ - መጨረሻው ከርቸሌ የሚሆን ወንጀለኛ ከሚሆንብኝ ጉዴን ቢሰማብኝ ይሻለኛል::”…»
#ድቅድቅ_ብርሃን

ሁሉ "ፀሐይ ነኝ ሲል
ጨለማ ዘመኔ ፥ መንጋቱን አመነ
ግን ብርሃን ሲበዘ
ያሳውራልና ፥ ጭራሽ ድቅድቅ ሆነ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#በጎደለ_ሙላ

በለስ ስትዘርፍ
አካሏ ሲራቆት
አዳም ግን ደረበ
አገለደመባት
እኔም የልጅ ልጁ
ያልተሸፈነ አካል
ራቁት አይቼ
ሙሉ አካሌን ከፈንኩ
ጠቦት በግ ሸልቼ።

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
1
#ዜሮን_ፅፌ_አንድ_አለኝ

ሁለት ነው ልቤ!
አንድም ሞኝ ሲሆን ፤ አንድም ነው ወረቀት
አንድ የሚያደርጋቸው ፤ አለ አንድ ተረት
አለ አንዳች እውነት።

የያዙትን ነገር ፤ አይለቁም ሁለቱም
ዜሮን እየፃፉ
"አንድ አለኝ ይላሉ ፤ ሞኙም ወረቀቱም።

እኔ ካንቺ በፊት ፤ የማውቃቸው ሴቶች
ዛሬ ዜሮ ናቸው
ተፅፈው የቀሩ ፥ የሌሉ ስሌቶች።
ሔደዋል ብዙዎቹ ፤ በኔ እየተገፉ
አልፈዋል ብዙዎቹ ፤ እኔን እየገፉ
ዛሬ አንቺ ስትመጪ
በሞኝ ልቤ ላይ ፤ አኖርኩሽ አቅፌ
ለወረቀት ልቤ
"አንድ አለችኝ" አልኩት ፤ ዜሮዎቼን ፅፌ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘