#ሲታነፅ_ሲወቀር
እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰሎሞን
“ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል”
ሳይጥሉ መታገል፣ ሳይከብሩ መባተል
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር።
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል፣ ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ
እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሐይዋ በቻት፣ ግልገል ፀሐይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ፣ ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ፣ ሸማ ሆኖ ቆየኝ
ከንቱ የነበረው፣ አንቱ ሆኖ ታየኝ።
ለካስ
ጠቢብ ቢያስተምረው፣ መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ ቢታነፅ፣ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም፣ ካልወደደ በቀር።
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰሎሞን
“ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል”
ሳይጥሉ መታገል፣ ሳይከብሩ መባተል
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር።
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል፣ ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ
እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሐይዋ በቻት፣ ግልገል ፀሐይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ፣ ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ፣ ሸማ ሆኖ ቆየኝ
ከንቱ የነበረው፣ አንቱ ሆኖ ታየኝ።
ለካስ
ጠቢብ ቢያስተምረው፣ መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ ቢታነፅ፣ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም፣ ካልወደደ በቀር።
🔘በውቀቱ ስዩም🔘