አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፀሎት

ባላንጣውን የሚሰማ .....
አምላክ የሌለ መስሎት፣
"ጠላቴን አጥፋልኝ" ነው...
የሞኝ ሰው ፀሎት!!!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ 🔘
#ፀሎት

ያገሬ ውበቷ፣
ያገሬ ቅርስ ሃብቷ፣
ምህረትን በማያውቅ
በእሳት እየጋየ፣
በዘመነ ፍጥነት
ዜናው ምን ሆኖ ነው ወዳንተ የዘገየ?
ከምድሪቷ ውሃ...፣
እሳት የሚበቀል የሚያበርድ ከታጣ፤
እባክህ ፈጣሪ ስለ እምነቷ ብለህ
ከሰማይ ውሃ አምጣ፡፡

🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
#ፀሎት

በዛች ቋንጣ ተስፋ
ሆዴ እንዲሞላልኝ
ወይ ቁመት ጨምረኝ
ወይም አውርድልኝ።

🔘ልዑል ሀይሌ🔘