ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
እንኩዋን ለሰማዕታት ቅዱስ #እንጣዎስ እና ቅዱስ
#ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#ቅዱስ_እንጣዎስ_አሞራዊ ይሕ ቅዱስ በቀደመ ሕይወቱ ክርስቲያኖችን የሚጠላ
አስቸጋሪ አረማዊ ነበር:: ሃገሩ #ሶርያ ( #ደማስቆ ) ሲሆን
ግብሩ ጣዖት ማምለክና መስረቅ ነበር:: በቅድስት ቤተ
ክርስቲያንና በምዕመናን ላይም ግፍን ፈጽሟል:: በሥጋዊ
ጉልበቱ ኃይለኛ ስለ ነበር የተፈራ ነው::
ሁልጊዜ በጠዋት ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ይሔዳል::
የሚሔደው ግን ንዋያተ ቅድሳትን ለመዝረፍ: አንድም
ካህናትን ለመደብደብ ነበር:: የሚገርመው ግን የወቅቱ
ምዕመናንና ካህናት ይህን ሁሉ እያደረገባቸው አይጠሉትም::
ይልቁኑ ይጸልዩለት ነበር እንጂ:: ምክንያቱም ክርስትና ማለት
ጠላትን መውደድ ነውና:: (ማቴ. 7)
የእግዚአብሔር ትዕግስትና የምዕመናን ጸሎት ተደምሮው
አንድ ቀን ፍሬ አፈራ:: እንጣዎስ እንደ ለመደው ለክፉ ሥራ
ወደ # ቅዱስ_ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያን ይሔዳል:: ከዚያም
እንደ ደረሰ ወደ ውስጥ ገብቶ: የሚማታውን ተማቶ:
የሚዘርፈውንም ዘርፎ: የተረፉትን ንዋያተ ቅድሳት በእሳት
አቃጠላቸው::
#እግዚአብሔር ከዚህም በላይ ታጋሽ ነውና አላጠፋውም::
"ዘኢይፈቅድ ለኃጥእ ሞቶ" እንዲል የኃጢአተኛውን መመለስ
እንጂ መሞቱን አይፈልግም:: ለዚያም ነው ዛሬ ይሔ ሁሉ
ግፍ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተሠራ እግዚአብሔር
እንደማያይ ዝም የሚለው:: ለሁሉም ቀን አለውና በፈረደ ቀን
ግን በፊቱ የሚቆም አይኖርም::
እንጣዎስ ግን የሠራውን ሠርቶ እወጣለሁ ሲል
አልተሳካለትም:: ከበሩ አካባቢ ሲደርስ: ከወደ ሰማይ
አካባቢ ድምጽ ሰምቶ ቀና ሲል መላእክት እንደሱ ዓይነት
ኃጢአተኞችን አሰልፈው በጦርና በቀስት ሲወጉአቸው
ተመለከተ::
ድንገት ግን ከመላእክቱ አንዱ ዘወር ብሎ አንድ ቀስት ወደ
እንጣዎስ ወረወረ (ተኮሰ):: ቀስቷ አካሉ ውስጥ ገብታለችና
እንጣዎስ መሬት ላይ ወድቆ ለሞት ደረሰ:: ላበቱ በግንባሩ
ላይ በጭንቅ እየፈሰሰ ጮኸ::
"ጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ማረኝ? ራራልኝ? ይቅር
በለኝ? በድፍረት ባለ ማወቅም በድየሃለሁ:: ይቅር በለኝና
ላምልክህ: ስምህንም ልሸከም" ሲል በጭንቀት ውስጥ ሆኖ
አሰምቶ ጸለየ:: በዚያ የነበሩ ምዕመናን ማን: በምን እንደ
ወጋው ባያውቁም ባዩት ነገር ግን እጅግ ደስ አላቸው::
እነርሱም የፈጉትና የጸለዩለት ነገር ይሔው ነበርና::
ወዲያው ግን እንጣዎስ ከሞት ጫፍ ተመልሶ ተነሳ::
መጀመሪያ በቦታው የነበሩ ካህናትና ምዕመናንን "ይቅር
በሉኝ?" አለ:: ቀጥሎም ወደ ዻዻስ ዘንድ ሔዶ "አጥምቀኝ"
ሲል ጠየቀ:: እርሱ በሚጠመቅበት ቀን ብዙ አሕዛብና
ክርስቲያኖች ተሰብስበው ነበር::
እርሱ በከተማዋ ዝነኛ ነበር:: ሥርዓቱ ሁሉ ተደርሶ ቅዱሱ
ወደ ውሃ ገንዳው ሲገባ ሁሉ እያዩ የብርሃን ምሰሶ ከሰማይ
ወረደ:: ይህንን በገሃድ የተመለከቱ ከ10,000 በላይ አሕዛብ
ወዲያውኑ በክርስቶስ አምነው አብረውት ተጠምቀዋል::
ቅዱስ እንጣዎስ ከዚህ በሁዋላ ምስጉን ክርስቲያን ሆነ::
ስለ ቀደመ ሕይወቱ ፈንታ ጾምን: ጸሎትን: ፍቅርን: ምጽዋትን
ገንዘብ አደረገ:: ሕይወቱም ለብዙ ሰዎች መስታውት ሆነ::
#እመቤታችን ድንግል ማርያምንም ይወዳት ነበርና ወደ
ቅዱሳን ማሕበር ( #ኢየሩሳሌም ) ወስዳው በሥጋዊ አንደበት
ተከናውኖ ሊነገር የማይቻል ምሥጢርን ገልጣለታለች::
እነዚህን የቅድስና ጊዜያት በስኬት ያሳለፈው ቅዱስ
እንጣዎስ መጨረሻው ሰማዕትነት ሆነ:: አረማውያን ወገኖቹና ቀድሞ የሚያውቁት ወደ ቀደመ ክፋትና
ክህደት እንዲመለስ ጠየቁት:: "አይሆንም" አላቸው::
በአደባባይ ለፍርድ አቅርበው ደሙ እስኪፈስ ገረፉት::
ጥርሶቹን በሙሉ በድንጋይ አረገፏቸው:: ደሙና ጥርሶቹ
መሬት ላይ ተዘሩ:: ነገር ግን ይሕ ስቃይ ቅዱሱን ከፍቅረ
ክርስቶስ ሊለየው አልቻለም:: አሕዛብም ተስፋ ቆርጠው
በዚህች ቀን ገድለውታል:: ቅዱስ እንጣዎስም ከሁዋለኛው
ዘመን #ሰማዕታት እንደ አንዱ ተቆጥሯል::
#አቡነ_ሰላማ_ካልዕ
እኒህ ታላቅ ደግ ሰው የነበሩት በሃገራችን ኢትዮዽያ ከ1340
እስከ 1380 ዓ/ም ነው:: በትውልድ ግብጻዊ ቢሆኑም
ለኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ውለታን ውለዋል:: በዘመኑ
ዻዻስ ሁነው ቢመጡም እንደ ሌሎቹ ዻዻሳት በቤተ መንግስት
አካባቢ ሥራ ፈትተው መቀመጥን አልፈለጉም::
ወዲያው እንደ መጡ የግዕዝ ልሳንን ልቅም አድርገው
ተማሩ:: ቀጥለው ኢትዮዽያውያን ሊቃውንትን ሰብስበው
ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተረጉሙ ገቡ:: አሥራው መጻሕፍትን
(81ዱን) ጨምሮ ብዙ መሠረታዊ መጻሕፍትን መተርጐም
ችለዋል::
ይህም ሥራ አድካሚ በመሆኑ ከ30 ዓመታት በላይ ጊዜን
ወስዷል:: ከተረጐሟቸው መጻሕፍትም:-
* #ስንክሳር
* #ግብረ_ሕማማት
* #ላሃ_ማርያም
* #ፊልክስዩስ (መጽሐፈ መነኮሳት)
* #መጽሐፈ_ግንዘት
*ድርሳን ዘቅዱስ #ያዕቆብ_ዘሥሩግ . . . ይጠቀሳሉ::
#አቡነ_ሰላማ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸውና በገዳማዊ
ሕይወታቸው ይታወቁ ነበር:: በተጨማሪም በየቦታው እየዞሩ
ይናዝዙ: ያጠምቁም ነበር:: በወቅቱ ልክ እንደ ስማቸው ሰላም
እንዲሰፍን ይተጉ ነበር:: መሣፍንቱን: ነገሥታቱን እያስታረቁ
ለቤተ ክርስቲያን በአንድነት እንዲቆሙ አድርገዋል::
ጻድቁ አቡነ ፊልዾስን ጨምሮ ቅዱሳንን ገንዘውም ቀብረዋል::
በቀደመ ስማቸው #አባ_ፊቅጦር የሚባሉት ካልዕ (2ኛው)
ሰላማ በ1380 ዓ/ም ከ40 ዓመታት ትጋት በሁዋላ ዐርፈዋል::
ሲጠሩም:-
* #መተርጉም (መጻሕፍትን የተረጐሙ)
* #ብርሃነ_አዜብ (የኢትዮዽያ ብርሃን)
* #መጋቤ_ሃይማኖት ተብለው ነው::
✿አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹን እንዳጸናቸው ያጽናን::
ከበረከታቸውም ያድለን::
✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን #አብርሃም : #ይስሐቅ
እና #ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
✞✞✞
እኒህ ቅዱሳን ከሰው ወገን እጅግ ክቡራን ከመሆናቸው የተነሳ መንግስተ ሰማያት በእነርሱ ስም
ተጠርታለች:: ጽድቃቸውና ክብራቸው እንደ ሰማይ
ከዋክብት የበዛ ነውና ጽፈንም: ተናግረንም
አንፈጽመውም:: እንዲሁ "ዕጹብ! ዕጹብ!" እያልን
ፈጣሪያቸውን ከማመስገን በቀር::
+"#ቅዱስ_አብርሃም_ርዕሰ_አበው "*+
የሃይማኖት: የደግነት: የምጽዋት: የፍቅር አባት
የሆነው አብርሃም በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት
አባቱ ታራ ጣዖትን ይጠርብና ይሸጥ ነበር:: ሽጦ ገንዘብ
የሚያመጣለት ደግሞ ልጁ አብርሃም ነበር::
¤በዚያ ወራት አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ፍለጋ
ገብቶ ነበር:: አንድ ቀን ጣዖቱን ሊሸጥ ወደ ገበያ
እየሔደ የተሸከመውን እንጨት ይመራመረው ገባ::
"አሁን ይሔ ምኑ ነው አምላክ!" እያለም ያደንቅ ገባ::
መንገድ ላይም ደክሞት ካረፈበት "ለምን
አልጠይቀውም" በሚል አናገረው::
¤"እርቦኛል አብላኝ" አለው:: መልስ የለም:: "እሺ
አጠጣኝ" አለው:: አሁንም ያው ነው:: "ባይሆን እሺ
አጫውተኝ" አለው:: ጣዖቱ ተራ እንጨት ነውና መልሱ
ዝምታ ነበር:: ከዚያ ተነስቶ ወደ ገበያው ሲደርስ "ዐይን
እያለው የማያይ: ጀሮ እያለው የማይሰማ አምላክ
የሚገዛ" እያለ ይጮህ ጀመር::
¤ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ "የታራ ልጅ አብዶ" ሲሉ
ሌሎቹ ደግሞ "እሱ ያቀለለውን ማን ይገዛዋል" ብለውት
ሔደዋል:: ሲመለስም ጣዖቱን ተመልክቶ #አብርሃም
እንዲህ አለ:: "አንተ ቀድሞውን በዕለተ ሠሉስ
የተፈጠርክ ዕፅ ነህ" ብሎ ሰባበረው::
¤ወደ ቤቱ ሲመለስም ሁሉንም ጣዖታት ሠባበራቸው::
የመንግስተ ሰማያት አበጋዝ: የእግዚአብሔር ወዳጅ
አባታችን አብርሃም፡
የሕዝብና የአሕዛብ አባት የሆነው አብርሃም
እግዚአብሔርን አምልኮ: ጣዖታትን ሰብሮ ወደ # ከነዓን
ከወጣ በሁዋላ ብዙ ችግርን አሳልፏል:: በረሃብ
ምክንያት ከአንድም 2 ጊዜ ወደ ግብጽና ፍልስጥኤም
ተሰዷል:: በዚያ ግን ፈጣሪው አክብሮታል::
¤2ቱ ነገሥታት (ፈርኦንና አቤሜሌክ) ሣራን እንነካለን
ቢሉ ተግሣጽ ደርሶባቸዋል:: #ነቢይ ነውና በአብርሃም
ጸሎት ተፈውሰዋል:: ቅዱስ አብርሃም ከደግነቱ የተነሳ
በኬብሮን (በተመሳቀለ መንገድ) ላይ ድንኩዋን ሠርቶ
እንግዳ ይቀበል ነበር:: ምሥክር ሳይይዝም እህል
አይቀምስም ነበር::
¤ሰይጣን ከፍቶ እንግዳ ቢያስቀርበት ያለ ምግብ ለ3 ቀናት
ቆይቷል:: በፍጻሜውም #ሥላሴ በእንግድነት
መጥተውለት በክብር ላይ ክብር: በጸጋ ላይ ጸጋ:
በጣዕም ላይ ጣዕም ተጨምሮለታል:: እርሱ የሥላሴን
እግር ያጥብ ዘንድ: በጀርባውም ይሸከማቸው ዘንድ
አድሎታልና:: ሥላሴም በቤቱ ተስተናግደው: ልደተ
ይስሐቅን አክብሥረውታል:: ጻድቁ ሰውም በፈጣሪው ፊት
ስለ ሰዶምና ገሞራ ለምኗል::
¤አብርሃም በአምልኮው ፍጹም ነውና የሚወደውን ልጁን
ይስሐቅን ለመስዋዕት አቅርቧል:: በዚህም የነቢያት:
የሐዋርያት: የነገሥታት: የካህናት አባት:
#ሥርወ_ሃይማኖት (የሃይማኖት ሥር) ተብሏል::
ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ አያቱም ተብሏል::
¤አንድ ቀን #እግዚአብሔር መላእክቱን "ብየ አርክ
አብርሃም በዲበ ምድር - በምድር ላይ ወዳጄ አብርሃም
አለ" አላቸው:: ያን ጊዜ 99ኙ ነገደ መላእክት
ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ:-
*"አብርሃም አርከ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ወዳጅ)"
*"አብርሃም ብእሴ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ሰው)"
*"አብርሃም ገብረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር አገልጋይ)"
*"አብርሃም ምዕመነ እግዚአብሔር
(አብርሃም የእግዚአብሔር ታማኝ)
"አብርሃም ፍቁረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ተወዳጁ ነው) እያሉ አሰምተው
ተናግረዋል::
¤አባታችን አብርሃም በክብር: በቅድስናና በሞገስ
ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ተጠቅሷል::
ፈጣሪ በስሙ ለቅዱሳን ተለምኗል:: ስለ ክብሩም
በሲዖል ውስጥ እንኩዋ ማረፊያን ሠርቶለታል::
አጋንንትም ሊቀርቡት አልተቻላቸውም:: ያረፈውም
ከክርስቶስ ልደት 1,900 ዓመታት በፊት ነው::
እድሜውም 175 ዓመት ነበር::
*ፍቅሩን የተረዱ ሊቃውንት ድንግል ማርያምን "ሐይመቱ
(ድንኩዋኑ): ተናግዶቱ (እንግድነቱ) ለአብርሃም" ሲሉ
አመስግነዋታል:: ሊቁም:-
"አብርሃም ፍጹም በሒሩት ወበአምልኮ:
እግዚአብሔር አዕበየከ ወባረከከ ባርኮ:
እስከ ሰመየከ ዲበ ምድር አርኮ::" ብሎ በምሥጢር
ገልጾታል::
Forwarded from ግጻዌ
#የካቲት_18
፫ተኛ መዝሙር ዘምኵራብ ቦአ ኢየሱስ ምኵራበ ይሁዳ፡፡
#ዘቅዳሴ
#ቆላስ_2:16-ፍጻሜ፡ዑቁ እንከ አልቦ ዘይግእዘክሙ"እንግዲህ በመብልም ቢሆን በመጠጥም ቢሆን በልዩ ልዩ በዓላትም ቢሆን በመባቻም ቢሆን በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡...............................................................................ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለውም፡፡"
#ያዕቆብ_2:14-ፍጻሜ፡ምንተ ይበቁዕ አኃዊነ"ወንድሞቻችን ሆይ እምነት አለኝ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል?...........................................................................ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ አንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_10:1-9፡ወሀሎ ፩ ብእሲ በሀገረ ቂሣርያ"በቂሳርያም ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ.........................................................................................ነገሩንም ሁሉ ነግሮ ወደ ኢዮጴ ከተማ ላካቸው፡፡"
#ምስባክ
እስመ ቅንአተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡
#ትርጉም
የቤትህ ቅናት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና
ነፍሴን በጾም አስመረርኋት፡፡
#መዝ_68:9-10
#ወንጌል
#ዮሐንስ_2:12-ፍጻሜ፡ወእምድኅረ ዝንቱ ወረዱ ቅፍርናሆም"ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ....................
................................................የሰውንም ግብሩን ሊነግሩት አይሻም እርሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዚእነ፡፡(ነአኵተከ)
@gitsawe
Forwarded from ግጻዌ
#የካቲት_25
፬ተኛ መዝሙር ዘመፃጉዕ አምላኩሰ ለአዳም
#ዘቅዳሴ
#ገላትያ_5:1-ፍጻሜ፡ቁሙ እንከ ወኢትሑሩ ዳግመ"እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትኑሩ፡፡...........
.................................................ኩሩዎች አንሁን እርስ በርሳችን አንተማማ እርስ በርሳችንም አንቀናና፡፡"
#ያዕቆብ_5:14-ፍጻሜ፡ወእመቦ ዘይደዊ አምኔክሙ"ከእናንተ የታመመ ሰው ቢኖር በቤተ ክርስቲያን ያሉ ቀሳውስትን ይጥራና ይጸልዩለት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጸለየበትንም ዘይት ይቀቡት፡፡...
................................................ኀጢአተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ራሱን ከሞት እንደ አዳነ ብዙ ኀጢአቱንም እንደ አስተሰረየ ይወቅ፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_3:1-12፡ወዐርጉ ምኵራበ ጴጥሮስ"ጴጥሮስና ዮሐንስም በዘጠኝ ሰዓት ለጸሎት በአንድነት ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፡፡.....................................................................................ጴጥሮስና ዮሐንስም ይዘውት ወደ መቅደስ ሲገቡ ሕዝቡ ሁሉ ደንግጠው ወደ ሰሎሞን መመላለሻ ወደ እነርሱ ሮጡ፡፡"
#ምስባክ
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሀለኒ
#ትርጉም
እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል
እኔስ አቤቱ ማረኝ
#መዝ_40:3-4
#ወንጌል
#ዮሐንስ_5:1-25፡ወእምድኅረዝ ኮነ በበዓሎሙ ለአይሁድ"ከዚህም በኋላ በአይሁድ በዓል እንዲህ ሆነ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡......................................................................................እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛል ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይሄድም፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዚእነ፡፡(ነአኵተከ)
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
Forwarded from ግጻዌ
#ሚያዚያ_17
ያዕቆብ ሐዋርያ ወሰማዕት
#ዘቅዳሴ
#1ኛ_ቆሮ_12:1-12፡ወበእንተሂ ዘመንፈስ ቅዱስ"ወንድሞቻችን ሆይ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታም ታውቁ ዘንድ እንጂ አለቃዎች ልትሆኑ አልወድድም፡፡................
................................................በዚህም ሁሉ ያው እንዱ መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ይረዳል ለሁሉም እንደ ወደደ ያድላቸዋል፡፡"
#ያዕቆብ_1:1-17፡ያዕቆብ ገብረ እግዚአብሔር"የእግዚአብሔር አብና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ከሚሆን ከያዕቆብ ለተበተኑ ዐሥራ ሁለቱ ነገድ ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡.....................................................................................የተወደዳችሁ ወንድሞቻችን ሆይ አትሳቱ፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_14:19-ፍጻሜ፡
ወመጽኡ አይሁድ እምአንጾኪያ"አይሁድም ከአንጾኪያና ከኢቆንያ መጡ.........
................................................ከደቀ መዛሙርትም ጋር አያሌ ቀን ተቀመጡ፡፡"
#ምስባክ
እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኵሎ አሚረ
ወኮነ አመ አባግዕ ዘይጠብሑ
ንቃህ እግዚኦ ለምንት ትነውም፡፡
#ትርጉም
ስላንተ ሁልጊዜ ተገድለናል
እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል
አቤቱ ንቃ ለምንስ ትተኛለህ?
#መዝ_43:22-23
#ወንጌል
#ሉቃስ_17:7-11፡መኑ እምኔክሙ ዘቦ ገብረ ሐረሳዊ"አራሽ ወይም ከብት ጠባቂ አገልጋይ ያለው ከእናንተ ማን ነው?ከእርሻው በተመለሰ ጊዜ ጌታው ና ፈጥነህ ወደዚህ ውጣና ከእኔ ጋር በማዕድ ተቀመጥ ይለዋልን?....................
................................................'እኛ ሥራ ፈቶች አገልጋዮች ነን ለመሥራትም የሚገባንን ሠራን' በሉ፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘሐዋርያት፡፡(ዘበደኃሪ)
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
Forwarded from ግጻዌ
#ሚያዚያ_20
በብኑዳ ሰማዕት ዘእምሀገረ ዴንዴራ ወተዝካሩ ለአባ አሞኒ፡፡
#ዘቅዳሴ
#2ኛ_ቆሮ_3:7-12፡ወሶበ ለእንታክቲ መልእክተ ሞት"ስለዚያ ስለ አለፈው የፊቱ ብርሃን የእስራኤል ልጆች የሙሴን ፊት መመልከት እንኪሳናቸው ድረስ በዚያች በድንጋይ ላይ በፊደል ለተቀረጸች ለሞት መልእክት ክብር ከተደረገላት ለመንፈስ ቅዱስ መልእክትማ ምንኛ እጅግ ክብር ሊደረግ ይገባ ይሆን?..................
.................................................ያ የሚያልፈው ክብር ካገኘ ያ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት እጅግ ክብር ያገኝ ይሆን?"
#ያዕቆብ_3:13-ፍጻሜ፡ወመኑ ጠቢብ እምኔክሙ"ከእናንተ ብልህና አስተዋይ ማን ነው?........
.................................................የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_5:38-ፍጻሜ፡
ወይእዜኒ እብለክሙ"አሁንም እላችኋለሁ ከእነዚህ ሰዎች ራቁ ተዉአቸውም ይህ ምክራቸው ይህም ሥራቸው ከሰው የተገኘ ከሆነ ያልፋል ይጠፋልም፡፡.........
................................................ሁልጊዜም በቤተ መቅደስና በቤት ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አልተዉም፡፡"
#ምስባክ
ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ
በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ
ይባእ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሓን፡፡
#ትርጉም
የፈሰሰውን የባሮችህን ደም በቀል
በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ
የባሮችህም ጭንቀት ወደፊትህ ይግባ፡፡ #መዝ_78:10-11
#ወንጌል
#ማቴዎስ_25:14-31፡እስመ ከመ ብእሲ ዘይነግድ"መንገድ እንደሚሄድ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡.........................................................................................ክፉውን አገልጋይ ግን ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ አውጡት፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘ፫፻(ግሩም፡፡)
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
Forwarded from ግጻዌ
#ሰኔ_2
አስተርእዮተ ሥጋሆሙ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ወለኤልሳዕ ነቢይ ወበዓለ ሰዊት አው ዝአዊት ወቄርሎስ ወአኬልጥስ ወቀውስጦስ፡፡
#ዘቅዳሴ
#1ኛ_ቆሮ_14:29-ፍጻሜ፡
ወነቢያትኒ ይትናገሩ በበ፪ቱ ወበበ፫ቱ"ነቢያትም ቃላቸው ለቤተ ክርስቲያን ይታወቅ ዘንድ ሁለት ሁለት ወይም ሦስት ሦስት ሆነው ይናገሩ፡፡...................................................................................ነገር ግን ሁሉን በአገባብና በሥርዐት አድርጉ፡፡"
#ያዕቆብ_5:12-17፡ወእምኵሉሰ ዘይቀድም"ወንድሞቻችን ሆይ ከሁሉ አስቀድሞ በሰማይም ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም ፈጽሞ አትማሉ.....
................................................እርስ በርሳችሁ ኀጢአታችሁን ተናዘዙ እንድትድኑም ለወንድሞቻችሁ ጸልዩ የጻድቅ ሰው ጸሎቱ ብዙ ትረዳለች ግዳጅም ትፈጽማለች፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_13:24-32፡ወሰበከ ሎሙ ዮሐንስ ጥምቀተ"እርሱ ከመምጣቱ አስቀድሞ ዮሐንስ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሓ ጥምቀትን ሰበከላቸው፡፡.............
................................................ከተነሣም በኋላ ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም አብረውት ለወጡት ብዙ ቀን ተገለጠላቸው፡፡እነርሱም በሕዝብ ዘንድ ምስክሮች ሆኑት፡፡"
#ምስባክ
ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም
ሶበ ይሄልዉ አኀው ኅቡረ
ከመ ዕፍረት ዘይውኅዝ እምርእሱ እስከ ጽሕሙ፡፡
#ትርጉም
ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ
እነሆ መልካም ነው እነሆም ያማረ ነው
ከራስ እስከ ጽሕም እንደሚፈስ፡፡
#መዝ_132:1-2
#ወንጌል
#ማቴዎስ_11:1-16፡ወኮነ እምዘ ሠለጠ"ጌታችን ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዙን ከፈጸመ በኋላ ሊሰብክና ሊያስተምር ወደ ከተሞቻቸው ሄደ፡፡..........................................................................................ዦሮ ያለው መስማትን ይስማ፡፡"
#ቅዳሴ፡ዘእግዝእትነ፡፡(ጎሥዓ)
👇👇👇👇👇👇
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👉 @gitsawe👈
👆👆👆👆👆👆
💚💛 አቡነ ሰላማ ካልዕ 💛❤️
እኒህ ታላቅ ደግ ሰው የነበሩት በሃገራችን ኢትዮዽያ ከ1340 እስከ 1380 ዓ/ም ነው:: በትውልድ ግብጻዊ ቢሆኑም ለኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ውለታን ውለዋል::
በዘመኑ ዻዻስ ሁነው ቢመጡም እንደ ሌሎቹ ዻዻሳት በቤተ
መንግስት አካባቢ ሥራ ፈትተው መቀመጥን አልፈለጉም::
ወዲያው እንደ መጡ የግዕዝ ልሳንን ልቅም አድርገው
ተማሩ:: ቀጥለው ኢትዮዽያውያን ሊቃውንትን ሰብስበው
ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተረጉሙ ገቡ:: አሥራው መጻሕፍትን
(81ዱን) ጨምሮ ብዙ መሠረታዊ መጻሕፍትን መተርጐም
ችለዋል::
ይህም ሥራ አድካሚ በመሆኑ ከ30 ዓመታት በላይ ጊዜን ወስዷል:: ከተረጐሟቸው መጻሕፍትም:-
* #ስንክሳር
* #ግብረ_ሕማማት
* #ላሃ_ማርያም
* #ፊልክስዩስ (መጽሐፈ መነኮሳት)
* #መጽሐፈ_ግንዘት
*ድርሳን ዘቅዱስ #ያዕቆብ_ዘሥሩግ . . . ይጠቀሳሉ::
#አቡነ_ሰላማ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸውና
በገዳማዊ ሕይወታቸው ይታወቁ ነበር:: በተጨማሪም
በየቦታው እየዞሩ ይናዝዙ: ያጠምቁም ነበር:: በወቅቱ ልክ
እንደ ስማቸው ሰላም እንዲሰፍን ይተጉ ነበር:: መሣፍንቱን:
ነገሥታቱን እያስታረቁ ለቤተ ክርስቲያን በአንድነት እንዲቆሙ
አድርገዋል::
ጻድቁ አቡነ ፊልዾስን ጨምሮ ቅዱሳንን ገንዘውም
ቀብረዋል:: በቀደመ ስማቸው #አባ_ፊቅጦር የሚባሉት
ካልዕ (2ኛው) ሰላማ በ1380 ዓ/ም ከ40 ዓመታት ትጋት
በሁዋላ ዐርፈዋል:: ሲጠሩም:-
* #መተርጉም (መጻሕፍትን የተረጐሙ)
* #ብርሃነ_አዜብ (የኢትዮዽያ ብርሃን)
* #መጋቤ_ሃይማኖት ተብለው ነው::
🌼አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹን እንዳጸናቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::🌼