ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
+#አቡነ_ኪሮስ_ጻድቅ +
የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው: ክቡር ነው::
በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን
ይበጃል::
ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው
"ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ::
"ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት
መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል:: በዚህ
ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል::
ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል:: አካላቸውንም
እንደነበረ መልሶላቸዋል::
አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው
መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ:: ሱባዔ
ገብተው: ፍጹም አልቅሰው: ከጌታም አማልደው: የዛን
ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል:: በሌላ ጊዜ
ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና
መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ::
ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው:
ሙታኑን አስነስተው: ንስሃ ሰጥተው: ገዳሙን የጻድቃን:
ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል:: ጻድቁ
#እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት
አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር:: እመ አምላክም
ተገልጣ ትባርካቸው ነበር::
ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57
ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ:: ጌታችን
#ኢየሱስ_ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና)
በየቀኑ ይጐበኛቸው: ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር::
በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን:
ጻድቃን ሰማዕታትን: ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን
አስከትሎ ወረደ::
#ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው: በበገናው
እየደረደረላቸው: ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው
ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ጌታችንም ታቅፎ: ስሞ
ይዟቸው አረገ:: ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት:: የአቡነ
ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ: ጽሕማቸውም የተንዠረገገ
ነበር:: እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል
አይመስለኝም::
በረከታቸው ይደርብን!
እንኳዋን ለሐዋርያው "ቅዱስ ናትናኤል" ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
+ቅዱስ ናትናኤል +
በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት
መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ
ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ
ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን
ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000
ሕጻናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል::
እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር::
ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም #ስምዖን ሲሆን
ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ደግሞ #ናትናኤል ብሎታል::
በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና
አካባቢ ስላደገ) አንዳንዴም #ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር::
ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: በገሊላ ቃና
ሰርግ የደገሰው #ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ
ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ
ምክንያትም ይሔው ነው::ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን #ከገማልያል ተምሮ : ከበለስ ቁጭ
ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ?" እያለም ይተክዝ
ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ
#በፊልዾስ አማካኝነት ጠርቶታል::
ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በሁዋላ ግን የጌታችንን
ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት
ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል
አመስግኖታል::
ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምስጢረ
መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ:
ብዙ አሕዛብን ከጨለማ (ጣኦት አምልኮ) ወደ ብርሃን (አሚነ
ክርስቶስ) መልሷል::
እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል::
የጌታችን ወንድም የተባለ #ቅዱስ_ያዕቆብ በአይሁድ
ከተገደለ በሁዋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም 2ኛ
ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ
ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት
አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ
ሰማዕት የሆነው በ150 ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ
ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል::
እንኩዋን ለሰማዕቱ ቅዱስ #አብሮኮሮንዮስ እና ለመነኮሳት አለቃ #ቅዱስ_መቃርስ ዓመታዊ በዓል በሰላም
አደረሳችሁ
+ ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ሰማዕት +
ቅዱሱ ተወልዶ ያደገው በአንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ
ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: አባቱ ደግ ክርስቲያን የነበረ ሲሆን
ስሙ #ክርስቶፎሮስ ይባላል:: "ለባሴ ክርስቶስ" እንደ ማለት
ነው:: እናቱ ግን #ቴዎዳስያ የምትባል አረማዊት ነበረች::
ምንም እንኩዋ አባቱ ክርስቲያን ቢሆን እናቱ ኃይለኛ የቤተ
መንግስት ሰው ስለነበረች በልጅነቱ አብሮኮሮንዮስ ክርስትናን
ሊማር አልቻለም::
የልጁን አረማዊ መሆን ያልወደደ አባት አማራጩ አንድ ብቻ
ነበር:: እሱም ወደ ጌታ መለመን ነበር:: በእንዲሕ ያለ ግብር
ዘመናት ጐርፈው አብሮኮሮንዮስ ክርስቶስን ሳያውቅ 20
ዓመት ሆነው:: እናቱ ወስዳ: አሰልጥና ለጣዖት አምላኪ
ንጉሥ ሰጠችው:: ንጉሡም የጦር አለቃ አድርጐ ሾመውና
አንድ ትዕዛዝ ሰጠው:: "ክርስቲያኖችን ሁሉ ባገኘህበት ቦታ ጨፍጭፍ:: ቤታቸውንም አቃጥል::" #አብሮኮሮንዮስ የታዘዘውን ሊፈጽም ሠራዊት አስከትሎ ሲወጣ ግን የአባቱ የ20 ዘመናት ለቅሶና ጸሎት ፍሬ አፈራ::
ገና መንገድ ላይ ሳለ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና
መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ድምጹን ከሰማይ ላከለት::
"ወደ እውነተኛ መንገድ ተመለስ:: ካልሆነ ግን ሾተሉን
ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል" አለው:: አብሮኮሮንዮስም እየተንቀጠቀጠ "አቤቱ አንተ ማነህ?" አለው:: ጌታም "ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ" ሲል መለሰለት::
ዳግመኛም "ምልክት ስጠኝ" ቢለው የብርሃን #መስቀል
በሰማይ ላይ ገለጠለት:: ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ጊዜ
አላጠፋም:: ሠራዊቱን ይዞ ወደ ንጉሡ ከተማ ተመልሶ ንጉሡን በድፍረት አለው:- "እኔ ክርስቲያን ነኝ:: ክርስቶስንም አመልካለሁ::"
ካነጋገሩ የተነሳ አባቱን ደስ ሲለው ንጉሡና እናቱ ግን ደነገጡ::
ንጉሡ ሊያስፈራራው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: ከዚያማ
ያሰቃየው ገባ:: አንድ ቀን አካሉ እስኪቆራረጥ ገረፉት:: በእሳትም
አቃጠሉት:: ሞተ ብለው አስበው ነበር:: ወደ እርሱ ሲመለሱ
ግን ጌታችን አድኖታልና የሰንበር ምልክት እንኩዋ በአካሉ ላይ
አልተገኘም:: እናቱ #ቴዎዳስያ ከዚህ በላይ ምልክትን
አልፈለገችም:: በደቂቃዎች ልዩነት እርሷም ወደ #ክርስትና
ተመለሰች:: ልጇንም ቀድማ ሐምሌ 6 ቀን ሰማዕት ሆነች::
+ቅዱስ አብሮኮርዮስን ግን ለበርካታ ጊዜያት አሰቃይተው
ከክርስቶስ ፍቅር ሊለዩት ባለመቻላቸው በዚህች ቀን
ገድለውታል:: አባት: እናትና ልጅ (ክርስቶፎሮስ: ቴዎዳስያና
አብሮኮሮንዮስ) ለሰማያዊ ርስት በቅተዋል:: አባት ይሏቹሃል
እንዲህ ነው!
#ቅዱስ_ሚክያስ
ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ.ል. ክርስቶስ በ800 ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ
ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው::
አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ 14 ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ
ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::
ሚክያስ ትውልዱ ከነገደ ሲሆን አባቱ ሞራት (ሞሬት)
ይባላል:: #ሚክያስ ማለት " #መኑ_ከመ_አምላክ - እንደ
እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!" ማለት ነው:: አንድም "መልአከ
እግዚአብሔር" ማለት ነው:: የአባቶቻችን ሁሉ ስማቸው
እግዚአብሔርን የሚሰብክ ነው::
ቅዱሱ ነቢይ ገና ልጅ እያለ #መላእክት ያነጋግሩት ነበር::
በዚህ ምክንያት ከሰው አይቀርብም:: ትክ ብለው ሲያዩት በፊቱ ላይ ብርሃን ቦግ ቦግ እያለ ይታይ ነበር:: በወጣትነት ዘመኑ
#እግዚአብሔር ለትንቢት ሲጠራው በእሺታ ታዘዘ:: በ3ቱ
ነገሥታት (በኢዮአታም: አካዝና ሕዝቅያስ) ዘመንም ትንቢቶችን
ተናግሯል:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን: ነገሥታቱን አስተምሮ
ገስጿል::
አንድ ቀን በቤተ ልሔም ሲያልፍ #የዳዊት_ከተማ ፈት ሁና:
ዳዋ በቅሎባት ቢመለከት አዘነ:: ወዲያውም ትንቢት
ተናገረላት::
"ወአንቲኒ #ቤተ_ልሔም ምድረ # ኤፍራታ : ኢትቴሐቲ
እምነገሥተ #ይሁዳ: እስመ እምኔኪ ይወጽዕ ንጉሥ:
ዘይርዕዮሙ ለሕዝብየ እሥራኤል::"
"አንቺም የኤፍራታ ምድር ቤተ ልሔም: የይሁዳ ነገሥታት
ከነገሡባቸው ከተሞች ከቶ አታንሺም:: ወገኖቼን እሥራኤልን
የሚጠብቃቸው ንጉሥ (መስፍን) ካንቺ ዘንድ ይወጣልና" አለ::
ይኸውም አልቀረ ለጊዜው ከሚጠት በሁዋላ ደጉ #ዘሩባቤል
ነግሦባታል:: በፍጻሜው ግን የባሕርይ ንጉሠ ነግሥት #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከንጽሕት #ድንግል_ማርያም ተወልዶባታል::
ቅዱስ ሚክያስ ወገኖቹን ሲያስተምርና ሲመራ ኑሮ: 7
ምዕራፎች ያሉትን ሐረገ ትንቢት ተናግሮ: በመልካም ሽምግልና:
በንጉሡ #ሕዝቅያስ ዘመን ዐርፏል:: ወገኖቹ ቀብረውታል::
ጌታም በክብረ ነቢያት ከልሎታል::
✿ቸር አምላከ ነቢያት የነቢያቱን መከራ አስቦ ከመከራ:
በእንባቸውም ከእንባ ይሰውረን:: ከተረፈ በረከታቸውም
አያጉድለን::
✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን #አብርሃም : #ይስሐቅ
እና #ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
✞✞✞
እኒህ ቅዱሳን ከሰው ወገን እጅግ ክቡራን ከመሆናቸው የተነሳ መንግስተ ሰማያት በእነርሱ ስም
ተጠርታለች:: ጽድቃቸውና ክብራቸው እንደ ሰማይ
ከዋክብት የበዛ ነውና ጽፈንም: ተናግረንም
አንፈጽመውም:: እንዲሁ "ዕጹብ! ዕጹብ!" እያልን
ፈጣሪያቸውን ከማመስገን በቀር::
+"#ቅዱስ_አብርሃም_ርዕሰ_አበው "*+
የሃይማኖት: የደግነት: የምጽዋት: የፍቅር አባት
የሆነው አብርሃም በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት
አባቱ ታራ ጣዖትን ይጠርብና ይሸጥ ነበር:: ሽጦ ገንዘብ
የሚያመጣለት ደግሞ ልጁ አብርሃም ነበር::
¤በዚያ ወራት አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ፍለጋ
ገብቶ ነበር:: አንድ ቀን ጣዖቱን ሊሸጥ ወደ ገበያ
እየሔደ የተሸከመውን እንጨት ይመራመረው ገባ::
"አሁን ይሔ ምኑ ነው አምላክ!" እያለም ያደንቅ ገባ::
መንገድ ላይም ደክሞት ካረፈበት "ለምን
አልጠይቀውም" በሚል አናገረው::
¤"እርቦኛል አብላኝ" አለው:: መልስ የለም:: "እሺ
አጠጣኝ" አለው:: አሁንም ያው ነው:: "ባይሆን እሺ
አጫውተኝ" አለው:: ጣዖቱ ተራ እንጨት ነውና መልሱ
ዝምታ ነበር:: ከዚያ ተነስቶ ወደ ገበያው ሲደርስ "ዐይን
እያለው የማያይ: ጀሮ እያለው የማይሰማ አምላክ
የሚገዛ" እያለ ይጮህ ጀመር::
¤ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ "የታራ ልጅ አብዶ" ሲሉ
ሌሎቹ ደግሞ "እሱ ያቀለለውን ማን ይገዛዋል" ብለውት
ሔደዋል:: ሲመለስም ጣዖቱን ተመልክቶ #አብርሃም
እንዲህ አለ:: "አንተ ቀድሞውን በዕለተ ሠሉስ
የተፈጠርክ ዕፅ ነህ" ብሎ ሰባበረው::
¤ወደ ቤቱ ሲመለስም ሁሉንም ጣዖታት ሠባበራቸው::
የመንግስተ ሰማያት አበጋዝ: የእግዚአብሔር ወዳጅ
አባታችን አብርሃም፡
የሕዝብና የአሕዛብ አባት የሆነው አብርሃም
እግዚአብሔርን አምልኮ: ጣዖታትን ሰብሮ ወደ # ከነዓን
ከወጣ በሁዋላ ብዙ ችግርን አሳልፏል:: በረሃብ
ምክንያት ከአንድም 2 ጊዜ ወደ ግብጽና ፍልስጥኤም
ተሰዷል:: በዚያ ግን ፈጣሪው አክብሮታል::
¤2ቱ ነገሥታት (ፈርኦንና አቤሜሌክ) ሣራን እንነካለን
ቢሉ ተግሣጽ ደርሶባቸዋል:: #ነቢይ ነውና በአብርሃም
ጸሎት ተፈውሰዋል:: ቅዱስ አብርሃም ከደግነቱ የተነሳ
በኬብሮን (በተመሳቀለ መንገድ) ላይ ድንኩዋን ሠርቶ
እንግዳ ይቀበል ነበር:: ምሥክር ሳይይዝም እህል
አይቀምስም ነበር::
¤ሰይጣን ከፍቶ እንግዳ ቢያስቀርበት ያለ ምግብ ለ3 ቀናት
ቆይቷል:: በፍጻሜውም #ሥላሴ በእንግድነት
መጥተውለት በክብር ላይ ክብር: በጸጋ ላይ ጸጋ:
በጣዕም ላይ ጣዕም ተጨምሮለታል:: እርሱ የሥላሴን
እግር ያጥብ ዘንድ: በጀርባውም ይሸከማቸው ዘንድ
አድሎታልና:: ሥላሴም በቤቱ ተስተናግደው: ልደተ
ይስሐቅን አክብሥረውታል:: ጻድቁ ሰውም በፈጣሪው ፊት
ስለ ሰዶምና ገሞራ ለምኗል::
¤አብርሃም በአምልኮው ፍጹም ነውና የሚወደውን ልጁን
ይስሐቅን ለመስዋዕት አቅርቧል:: በዚህም የነቢያት:
የሐዋርያት: የነገሥታት: የካህናት አባት:
#ሥርወ_ሃይማኖት (የሃይማኖት ሥር) ተብሏል::
ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ አያቱም ተብሏል::
¤አንድ ቀን #እግዚአብሔር መላእክቱን "ብየ አርክ
አብርሃም በዲበ ምድር - በምድር ላይ ወዳጄ አብርሃም
አለ" አላቸው:: ያን ጊዜ 99ኙ ነገደ መላእክት
ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ:-
*"አብርሃም አርከ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ወዳጅ)"
*"አብርሃም ብእሴ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ሰው)"
*"አብርሃም ገብረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር አገልጋይ)"
*"አብርሃም ምዕመነ እግዚአብሔር
(አብርሃም የእግዚአብሔር ታማኝ)
"አብርሃም ፍቁረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ተወዳጁ ነው) እያሉ አሰምተው
ተናግረዋል::
¤አባታችን አብርሃም በክብር: በቅድስናና በሞገስ
ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ተጠቅሷል::
ፈጣሪ በስሙ ለቅዱሳን ተለምኗል:: ስለ ክብሩም
በሲዖል ውስጥ እንኩዋ ማረፊያን ሠርቶለታል::
አጋንንትም ሊቀርቡት አልተቻላቸውም:: ያረፈውም
ከክርስቶስ ልደት 1,900 ዓመታት በፊት ነው::
እድሜውም 175 ዓመት ነበር::
*ፍቅሩን የተረዱ ሊቃውንት ድንግል ማርያምን "ሐይመቱ
(ድንኩዋኑ): ተናግዶቱ (እንግድነቱ) ለአብርሃም" ሲሉ
አመስግነዋታል:: ሊቁም:-
"አብርሃም ፍጹም በሒሩት ወበአምልኮ:
እግዚአብሔር አዕበየከ ወባረከከ ባርኮ:
እስከ ሰመየከ ዲበ ምድር አርኮ::" ብሎ በምሥጢር
ገልጾታል::
#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ
ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር
ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: #ቅዱስ_ሉቃስ
ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ
ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "#ዘካርያስ ካህኑና
#ቅድስት_ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ
ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ
መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው
ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ
ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90
የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::
ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ
እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው
የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን
ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን
ላከላቸው::
ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ
ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው
ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት
ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል
#እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች::
ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
የአምላክ እናቱ ስትደርስና "#ሰላም " ስትላቸው መንፈስ
ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ
ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ
በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው
አንደበቱ
ተፈትቶለታል::
ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው
ጊዜ #ሰብአ_ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር
የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም
አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ
የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ
'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን
ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል::
አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ
ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7)
ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች::
ከሰማይ ዘካርያስና # ስምዖን ወርደው ቀበሯት::
ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ #ድንግል_ማርያም ስንት አገር
አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ
ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም
"እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን
"ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት::
ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::
ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል
ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25
(23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና
ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን
ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::
ከዚህ በሁዋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር
ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ"
አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ.
40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን
ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ
እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ
መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::
ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ #መንፈስ_ቅዱስ
እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት:
አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር
የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ:
ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::
ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ:: ለንስሃም በርካቶችን
አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ
ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን
ከነግሱ: ምድርን ከነ ልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ'
ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::
"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን
"ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት
ይሔው እስከ ዛሬም "#መጥምቀ_መለኮት " ሲባል
ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው::
ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::
በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ
በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ
ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው
"እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ
መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ
ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ
ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ.
1:6)
ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ
የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት
ጌታችን ወዳለበት #ደብረ_ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች::
#ቅዱሳን_ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ
ነሷት::
ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለቅዱስ
ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት::
በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች
ቀን ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::
#ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ
ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ #ማርያም_እግዝእት
በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ
መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
ከግራ ቁመት:
ከገሃነመ እሳት:
ከሰይጣን ባርነት:
ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ እንዳለ
ሊቁ::
ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ
ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው
ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ
አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም
ራሷ አርአያ #ትዕምርተ_መስቀል ናት::
እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት
(ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
#ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
#ቅዱስ_ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ.
48:14):
ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው #የሙሴ_በትር (ዘጸ.
14:15):
# የናሱ_ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8)
ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ
መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
# ቅዱስ_ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ
ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ
መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)
በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ
መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን
አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት::
ስለዚህም "#መስቀል_ብርሃን_ለኩሉ_ዓለም :
#መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን " ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
#ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ
ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን
ይነግረናል:: #ብርሃነ_ዓለም #ቅዱስ_ዻውሎስም ስለ
መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን
ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)
አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል::
የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ:
የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ:
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ
በወዴት አለና::
ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር
አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን:
እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት:
ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ
ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን
ተሻግረዋል::
በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም
አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን
እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ
ምስክርን አንፈልግም::
+"+ # ቅዱስ_ይሁዳ ሐዋርያ +"+
=>በዘመነ ሐዋርያት # ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው
# ቅዱስ_ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ #ማርያም ትባል ነበር:: እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ
ቢሆንም ገና በልጅነቱ # ድንግል_ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች::
አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር::
+ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል:: ቅዱስ
ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን # ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል:: (ዮሐ.
14:22)
+ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ
አሕጉራትን ዙሯል:: አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና
ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል:: አንዲት አጭር (ባለ አንድ ምዕራፍ) መልእክትም ጽፏል::
አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው::
¤ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ
ደርቧል::
+"+ ቅዱሳን # ዺላጦስና_አብሮቅላ +"+
=>ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ #መጽሐፍ_ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል
ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን:: የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት
የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል:: የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ
ላይ አያበቃም::
+ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ
ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል:: ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል:: በመጨረሻ ግን
በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ
ተሠይፏል::
=>ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት
ነው:: ጌታችንን ተከትላ: ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ: ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ
ዐርፏለች:: ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ::
💚💛ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ሰማዕት 💛❤️
ቅዱሱ ተወልዶ ያደገው በአንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው
መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: አባቱ ደግ ክርስቲያን የነበረ
ሲሆን ስሙ #ክርስቶፎሮስ ይባላል:: "ለባሴ ክርስቶስ" እንደ
ማለት ነው:: እናቱ ግን #ቴዎዳስያ የምትባል አረማዊት ነበረች:: ምንም እንኩዋ አባቱ ክርስቲያን ቢሆን እናቱ ኃይለኛ የቤተ መንግስት ሰው ስለነበረች በልጅነቱ አብሮኮሮንዮስ
ክርስትናን ሊማር አልቻለም::
የልጁን አረማዊ መሆን ያልወደደ አባት አማራጩ አንድ ብቻ
ነበር:: እሱም ወደ ጌታ መለመን ነበር:: በእንዲሕ ያለ ግብር
ዘመናት ጐርፈው አብሮኮሮንዮስ ክርስቶስን ሳያውቅ 20
ዓመት ሆነው:: እናቱ ወስዳ: አሰልጥና ለጣዖት አምላኪ
ንጉሥ ሰጠችው:: ንጉሡም የጦር አለቃ አድርጐ ሾመውና አንድ ትዕዛዝ ሰጠው:: "ክርስቲያኖችን ሁሉ ባገኘህበት ቦታ ጨፍጭፍ:: ቤታቸውንም አቃጥል::"
#አብሮኮሮንዮስ የታዘዘውን ሊፈጽም ሠራዊት አስከትሎ
ሲወጣ ግን የአባቱ የ20 ዘመናት ለቅሶና ጸሎት ፍሬ አፈራ::
ገና መንገድ ላይ ሳለ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና
መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ድምጹን ከሰማይ ላከለት:: "ወደ እውነተኛ መንገድ ተመለስ:: ካልሆነ ግን ሾተሉን ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል" አለው::
አብሮኮሮንዮስም እየተንቀጠቀጠ "አቤቱ አንተ ማነህ?" አለው:: ጌታም "ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ" ሲል መለሰለት:: ዳግመኛም "ምልክት ስጠኝ" ቢለው የብርሃን #መስቀል በሰማይ ላይ ገለጠለት:: ቅዱስ አብሮኮሮንዮስ ጊዜ አላጠፋም:: ሠራዊቱን ይዞ ወደ ንጉሡ ከተማ ተመልሶ ንጉሡን በድፍረት
አለው:- "እኔ ክርስቲያን ነኝ:: ክርስቶስንም አመልካለሁ::"
ካነጋገሩ የተነሳ አባቱን ደስ ሲለው ንጉሡና እናቱ ግን ደነገጡ:: ንጉሡ ሊያስፈራራው ሞከረ:: ግን
አልተሳካለትም:: ከዚያማ ያሰቃየው ገባ:: አንድ ቀን አካሉ እስኪቆራረጥ ገረፉት:: በእሳትም
አቃጠሉት:: ሞተ ብለው አስበው ነበር:: ወደ እርሱ ሲመለሱ
ግን ጌታችን አድኖታልና የሰንበር ምልክት እንኩዋ በአካሉ ላይ
አልተገኘም:: እናቱ #ቴዎዳስያ ከዚህ በላይ ምልክትን
አልፈለገችም:: በደቂቃዎች ልዩነት እርሷም ወደ #ክርስትና
ተመለሰች:: ልጇንም ቀድማ ሐምሌ 6 ቀን ሰማዕት ሆነች::
ቅዱስ አብሮኮርዮስን ግን ለበርካታ ጊዜያት አሰቃይተው
ከክርስቶስ ፍቅር ሊለዩት ባለመቻላቸው በዚህች ቀን
ገድለውታል:: አባት: እናትና ልጅ (ክርስቶፎሮስ: ቴዎዳስያና
አብሮኮሮንዮስ) ለሰማያዊ ርስት በቅተዋል:: አባት ይሏቹሃል
እንዲህ ነው!
💚💛ነሐሴ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት💛❤️
1.ቅድስት አትናስያ ቡርክት
2.ቅድስት ኢዮዸራቅስያ ድንግል
3.ቅዱስ ዴሚና ሰማዕት
🌈ወርኀዊ በዓላት🌈
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ
7.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም
መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ
ነው:: ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ:: ስለዚህ ግን የዘላለምን
ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች
ምሳሌ እንድሆን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ:: "
(1ጢሞ. 1:15)
💚💛 አቡነ ኪሮስ ጻድቅ 💛❤️
የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው: ክቡር ነው:: በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል::
#አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው:: ተወልደው ባደጉባት ሃገር #ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል:: ወንድማቸው (ታላቁ #ቴዎዶስዮስ) በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው: አሕጉር አቋርጠው ወደ ግብፅ ( #ገዳመ_አስቄጥስ) መጡ::

እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም:: ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ #ገብረ_ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ:: "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ #ቅዱስ_ዳዊት:: አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው:: አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ #አቡነ_በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል::

ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ:: "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል:: በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል:: ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል:: አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል::
አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ:: ሱባዔ ገብተው: ፍጹም አልቅሰው: ከጌታም አማልደው: የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል:: በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ::

ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው: ሙታኑን አስነስተው: ንስሃ ሰጥተው: ገዳሙን የጻድቃን: ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል:: ጻድቁ #እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር:: እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር::

ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ:: ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና) በየቀኑ ይጐበኛቸው: ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ::

#ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው: በበገናው እየደረደረላቸው: ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ጌታችንም ታቅፎ: ስሞ ይዟቸው አረገ:: ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት:: የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ: ጽሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር:: እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም::
From d/n yordanos abebe
@senkesar @senkesar
💚💛ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም💛❤️
ቸር #እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ #ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ #ጽድቅ መድረስ አይቻልም::

ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 7 አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው::

"ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን " #ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: #እመ_ብርሃን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም::
ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው #ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ7ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት::

ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል::

*የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ::

*ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ::

*የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል::

በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን::

#ጽንዕት_በድንግልና: #ሥርጉት_በቅድስና
#እመቤታችን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
*ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን::*
From dn yordanos abebe
@senkesar @senkesar