ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
+#አባ_አብርሃም_ክቡር ገዳማዊ +
ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆን በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ከተነሱ
ከዋክብት አንዱ ነው:: #ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው "ሚስት አግባ" አሉት:: እሺ እንዳይላቸው ከልጅነቱ
ጀምሮ የተመኘው ምናኔ ሊቀርበት ሆነ:: እንቢ እንዳይላቸው
ደግሞ ወላጆቹ ያዝናሉና የልቡን በልቡ ይዞ "እሺ" አላቸው::
ሠርግ ተደግሶ: #ተክሊል ተደርሶ: ከአንዲት ክርስቲያን ጋር
አጋቡት:: በጋብቻው ማግስት ግን ከነ ድንግልናው ጠፍቶ
በርሃ ገባ:: በዚያም አንዲት በዓት አዘጋጅቶ ፈቃደ ሥጋውን
እየቀጣ: ፈቃደ ነፍሱን እያለመለመ ለ10 ዓመታት ተቀመጠ::
+በነዚያ ሁሉ ዘመናት የሞቀ አልለበሰም: የላመ የጣመ ነገር
አልበላም:: የፀሐይ ብርሃን እንኩዋ አልተመለከተም:: በዚያ
ወራትም ወሬ ነጋሪ ወደ በዓቱ መጥቶ "ወላጆችህ ዐረፉ::
በቤት ውስጥ ከ6 ዓመት እህትህ ከማርያ በቀር ማንም
የለምና የወላጆችህን ሃብት ውረስ" አለው::
አባ አብርሃም የሚያደርገውን ያውቃልና ከበርሃ ወጥቶ ወደ
ሃገር ቤት ሔደ:: ትንሽ እህቱን (6 ዓመቷ ነበር) ለቤተ ዘመድ
አደራ ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን አንድ ሳያስቀር ለነዳያን
በትኖ:ወደ በዓቱ ተመለሰ:: በዚያም እንዳስለመደ በጾምና
ጸሎት ተወስኖ ለ10 ዓመታት ቆየ::
ተጋድሎ በጀመረ በ20 ዓመቱ #እግዚአብሔር ለሌላ
አገልግሎት ጠራው:: የግብጽ ሊቀ ዻዻስ #አባ_አብርሃምን
አስመጥቶ ቅስናን ሾመውና "ሒደህ ወንጌልን ስበክ" አለው::
ችግሩ እርሱ የተላከባት ሃገር አንድም ክርስቲያን የሌለባት
ከመሆኗ በባሰ እጅግ ጨካኝ ናቸው::
ማንም ደፍሮ በዚያ ሃገር ውስጥ ነገረ እግዚአብሔርን
የሚናገር ሰው አልነበረም:: አባ #አብርሃም ወደ ሃገር ገብቶ
ወንጌልን ቢሰብክላቸው እንደ ልማዳቸው መሬት ላይ ጥለው
ደበደቡት: አጥንቶቹንም ሰባበሩት:: ሞቷል ብለው ከከተማ
ውጪም ጣሉት::
እርሱ ግን በፈጣሪው ኃይል ጸንቶ ተነሳ:: ማስተማሩ ብቻውን
መፍትሔ እንደማይሆን ተረድቷልና ስለ እነሱ ተግቶ ይጸልይ
ጀመር:: አሕዛብ ጠዋት ቢመጡ በከተማዋ መሐል ላይ
ሲጸልይ አገኙት:: ስለ ተናደዱ ድጋሚ አካሉን በዱላ ሰባብረው
እየጐተቱ ከከተማ አስወጡት:: በዚያም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት::
ነገር ግን ጠዋት ሲመለሱ እዛችው ቦታ ላይ ሲጸልይ
አገኙት:: ይሕ የሚደረገው ለእነርሱ ድኅነት መሆኑን
አልተረዱምና እነርሱ በየቀኑ እየደበደቡና እያሰቃዩት እርሱ ስለ
እነሱ እየጸለየ 10 ዓመታት አለፉ:: ቅዱሳን ተስፋ
አይቆርጡምና በመጨረሻው ተሳካለት::
የቅዱሱ የዘመናት ጸሎት ፍሬ አፍርቶ እግዚአብሔር
በአሕዛብ ልቡና ያደሩ አጋንንትን አራቀለት:: አንድ ቀን ጠዋት
የሃገሩ ሕዝብ ሁሉ (ወንዱ: ሴቱ: ትልቁ: ትንሹ) ወደ ጻድቁ
መጸለያ መጡ:: ለእርሱስ የጠብ መስሎት ነበር:: እነርሱ ግን
በአንድነት በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱ:: ይቅር እንዲላቸውም
ለመኑት::
ቅዱሱ ይሕንን ሲመለከት ሐሴትን አደረገ:: ሁሉንም
#በስመ_ሥላሴ አጥምቆ ክርስቲያን አደረጋቸው:: አብያተ
ክርስቲያናትንም አነጸላቸው:: በሁዋላ ግን በጣም ሲወዱትና
ሲያከብሩት ተመልክቷልና ከውዳሴ ከንቱ ( #ስብሐት_ብጡል
) መለየት ፈለገ:: ፈጣሪንም በቸርነቱ እንዲጠብቃቸው
ለምኖ: በሌሊት ጠፍቶ ወደ ነበረበት በርሃ ገባ::
+እርሱ በበርሃ ሁኖ ስለ ትንሽ እህቱ #ማርያ ያስብ ነበርና
አስጠራት:: "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት:: እርሷም "እንዳንተ
መሆን" ስላለችው አስተምሮ: ፈትኖ አመነኮሳት:: ለጥቂት
ዓመታት በሥርዓት ከኖረች በሁዋላ ግን ችግር ተፈጠረ::
ከአንድ መነኩሴ ጋር በነበራት ያልተገባ ቅርርብ የዝሙት
ፍላጐታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው በኃጢአት ወደቁ::
በዚህ ተስፋ ቆርጠው 2ቱም ቆባቸውን ጥለው ከተማ ገቡ::
ይልቁኑ እርሷ (ማርያ) ሴተኛ አዳሪ ሆነች::
በዚያ ሰሞን ቅዱሱ አብርሃም ራዕይን ያያል:: ትልቅ ዘንዶ
አንዲት ርግብን ሲውጣት: መልሶም ሲተፋት አይቶ እሕቱ
መሆኗን ተረዳ:: ወዲያው ጥሩ ልብስና ፈረስ ተውሶ ተነሳና
ወደ ከተማ ገባ:: የጦር መኮንን መስሎ እህቱ ቤት ገባ::
ሸሽታ እንዳታመልጠው ቤቱን ዘጋና ራሱን ገለጠላት::
ደንግጣ እንደ በድን ብትሆንም እርሱ አረጋጋት:: "እህቴ! ንስሃ
ግቢ: አምላክ ይራራልሻል" አላት:: ልቧ ወደ ምክሩ
አዘንብሏልና የእህቱን ነፍስ ማርኮ ወደ ገዳም ተመለሰ::
በዚያ በዓት ሠርቶላት: ቀኖናም ሰጥቷት ሔደ:: #ማርያም
ስለ ኃጢአቷ ፈንታ የምትገርም የቅድስና ሰው ሆነች:: ያየ ሁሉ
እየተደነቀባት ከዓመታት ተጋድሎ በሁዋላ ዐረፈች:: አባ
አብርሃም በተረፈ ዘመኑ በንጹሕ ገዳማዊ ሕይወት ተጠምዶ
ኑሯል::
በዘመኑ ሁሉ በጥርሱ ስቆ: በከንፈሩም አልባሌ ነገርን
ተናግሮ አያውቅም:: ልቡ በፈጣሪው ፍቅር የታሠረ ነበርና
ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ እንባው ያለማቁዋረጥ ይፈስ
ነበር:: ደግና ቅዱስ ሰው አብርሃም በዚህች ቀን ዐርፎ
ተቀብሯል::
#አባታችን_ቅዱስ_አብርሃም
#የሃይማኖት-የደግነት-የምጽዋት-የፍቅር አባት የሆነው
#አብርሃም ደጉ በዚህች ቀን ይታሠባል:: በቤተ ክርስቲያን
ትውፊት መሠረት የአብርሃም አባቱ ታራ ጣዖትን ይጠርብና
ይሸጥ ነበር:: ሽጦ ገንዘብ የሚያመጣለት ደግሞ ልጁ
አብርሃም ነበር::
በዚያ ወራት አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ፍለጋ ገብቶ
ነበር:: አንድ ቀን ጣዖቱን ሊሸጥ ወደ ገበያ እየሔደ
የተሸከመውን እንጨት ይመራመረው ገባ:: "አሁን ይሔ ምኑ
ነው አምላክ!" እያለም ያደንቅ ገባ:: መንገድ ላይም ደክሞት
ካረፈበት "ለምን አልጠይቀውም" በሚል አናገረው::
"እርቦኛል አብላኝ" አለው:: መልስ የለም:: "እሺ አጠጣኝ"
አለው:: አሁንም ያው ነው:: "ባይሆን እሺ አጫውተኝ" አለው::
ጣዖቱ ተራ እንጨት ነውና መልሱ ዝምታ ነበር:: ከዚያ ተነስቶ
ወደ ገበያው ሲደርስ "ዐይን እያለው የማያይ: ጀሮ እያለው
የማይሰማ አምላክ የሚገዛ" እያለ ይጮህ ጀመር::
ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ "የታራ ልጅ አብዶ" ሲሉ ሌሎቹ
ደግሞ "እሱ ያቀለለውን ማን ይገዛዋል" ብለውት ሔደዋል::
ከገበያ ሲመለስም ጣዖቱን ተመልክቶ አብርሃም እንዲህ አለ::
"አንተ ቀድሞውን በዕለተ ሠሉስ የተፈጠርክ ዕፅ ነህ" ብሎ
ሰባበረው::
ወደ ቤቱ ሲመለስም ሁሉንም ጣዖታት ሠባበራቸው:: ይህ
የተደረገው ከ2,000 ዓመታት በፊት በዚህች ቀን ነው::
የመንግስተ ሰማያት አበጋዝ: የእግዚአብሔር ወዳጅ አባታችን
አብርሃም በመጨረሻው በውሃ: በነፋስ: በእሳትና በፀሐይ
ተመራምሮ ፈጣሪውን አግኝቷል::
✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን #አብርሃም : #ይስሐቅ
እና #ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
✞✞✞
እኒህ ቅዱሳን ከሰው ወገን እጅግ ክቡራን ከመሆናቸው የተነሳ መንግስተ ሰማያት በእነርሱ ስም
ተጠርታለች:: ጽድቃቸውና ክብራቸው እንደ ሰማይ
ከዋክብት የበዛ ነውና ጽፈንም: ተናግረንም
አንፈጽመውም:: እንዲሁ "ዕጹብ! ዕጹብ!" እያልን
ፈጣሪያቸውን ከማመስገን በቀር::
+"#ቅዱስ_አብርሃም_ርዕሰ_አበው "*+
የሃይማኖት: የደግነት: የምጽዋት: የፍቅር አባት
የሆነው አብርሃም በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት
አባቱ ታራ ጣዖትን ይጠርብና ይሸጥ ነበር:: ሽጦ ገንዘብ
የሚያመጣለት ደግሞ ልጁ አብርሃም ነበር::
¤በዚያ ወራት አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ፍለጋ
ገብቶ ነበር:: አንድ ቀን ጣዖቱን ሊሸጥ ወደ ገበያ
እየሔደ የተሸከመውን እንጨት ይመራመረው ገባ::
"አሁን ይሔ ምኑ ነው አምላክ!" እያለም ያደንቅ ገባ::
መንገድ ላይም ደክሞት ካረፈበት "ለምን
አልጠይቀውም" በሚል አናገረው::
¤"እርቦኛል አብላኝ" አለው:: መልስ የለም:: "እሺ
አጠጣኝ" አለው:: አሁንም ያው ነው:: "ባይሆን እሺ
አጫውተኝ" አለው:: ጣዖቱ ተራ እንጨት ነውና መልሱ
ዝምታ ነበር:: ከዚያ ተነስቶ ወደ ገበያው ሲደርስ "ዐይን
እያለው የማያይ: ጀሮ እያለው የማይሰማ አምላክ
የሚገዛ" እያለ ይጮህ ጀመር::
¤ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ "የታራ ልጅ አብዶ" ሲሉ
ሌሎቹ ደግሞ "እሱ ያቀለለውን ማን ይገዛዋል" ብለውት
ሔደዋል:: ሲመለስም ጣዖቱን ተመልክቶ #አብርሃም
እንዲህ አለ:: "አንተ ቀድሞውን በዕለተ ሠሉስ
የተፈጠርክ ዕፅ ነህ" ብሎ ሰባበረው::
¤ወደ ቤቱ ሲመለስም ሁሉንም ጣዖታት ሠባበራቸው::
የመንግስተ ሰማያት አበጋዝ: የእግዚአብሔር ወዳጅ
አባታችን አብርሃም
የሕዝብና የአሕዛብ አባት የሆነው አብርሃም
እግዚአብሔርን አምልኮ: ጣዖታትን ሰብሮ ወደ # ከነዓን
ከወጣ በሁዋላ ብዙ ችግርን አሳልፏል:: በረሃብ
ምክንያት ከአንድም 2 ጊዜ ወደ ግብጽና ፍልስጥኤም
ተሰዷል:: በዚያ ግን ፈጣሪው አክብሮታል::
¤2ቱ ነገሥታት (ፈርኦንና አቤሜሌክ) ሣራን እንነካለን
ቢሉ ተግሣጽ ደርሶባቸዋል:: #ነቢይ ነውና በአብርሃም
ጸሎት ተፈውሰዋል:: ቅዱስ አብርሃም ከደግነቱ የተነሳ
በኬብሮን (በተመሳቀለ መንገድ) ላይ ድንኩዋን ሠርቶ
እንግዳ ይቀበል ነበር:: ምሥክር ሳይይዝም እህል
አይቀምስም ነበር::
¤ሰይጣን ከፍቶ እንግዳ ቢያስቀርበት ያለ ምግብ ለ3 ቀናት
ቆይቷል:: በፍጻሜውም #ሥላሴ በእንግድነት
መጥተውለት በክብር ላይ ክብር: በጸጋ ላይ ጸጋ:
በጣዕም ላይ ጣዕም ተጨምሮለታል:: እርሱ የሥላሴን
እግር ያጥብ ዘንድ: በጀርባውም ይሸከማቸው ዘንድ
አድሎታልና:: ሥላሴም በቤቱ ተስተናግደው: ልደተ
ይስሐቅን አክብሥረውታል:: ጻድቁ ሰውም በፈጣሪው ፊት
ስለ ሰዶምና ገሞራ ለምኗል::
¤አብርሃም በአምልኮው ፍጹም ነውና የሚወደውን ልጁን
ይስሐቅን ለመስዋዕት አቅርቧል:: በዚህም የነቢያት:
የሐዋርያት: የነገሥታት: የካህናት አባት:
#ሥርወ_ሃይማኖት (የሃይማኖት ሥር) ተብሏል::
ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ አያቱም ተብሏል::
¤አንድ ቀን #እግዚአብሔር መላእክቱን "ብየ አርክ
አብርሃም በዲበ ምድር - በምድር ላይ ወዳጄ አብርሃም
አለ" አላቸው:: ያን ጊዜ 99ኙ ነገደ መላእክት
ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ:-
*"አብርሃም አርከ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ወዳጅ)"
*"አብርሃም ብእሴ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ሰው)"
*"አብርሃም ገብረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር አገልጋይ)"
*"አብርሃም ምዕመነ እግዚአብሔር
(አብርሃም የእግዚአብሔር ታማኝ)
"አብርሃም ፍቁረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ተወዳጁ ነው) እያሉ አሰምተው
ተናግረዋል::
¤አባታችን አብርሃም በክብር: በቅድስናና በሞገስ
ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ተጠቅሷል::
ፈጣሪ በስሙ ለቅዱሳን ተለምኗል:: ስለ ክብሩም
በሲዖል ውስጥ እንኩዋ ማረፊያን ሠርቶለታል::
አጋንንትም ሊቀርቡት አልተቻላቸውም:: ያረፈውም
ከክርስቶስ ልደት 1,900 ዓመታት በፊት ነው::
እድሜውም 175 ዓመት ነበር::
*ፍቅሩን የተረዱ ሊቃውንት ድንግል ማርያምን "ሐይመቱ
(ድንኩዋኑ): ተናግዶቱ (እንግድነቱ) ለአብርሃም" ሲሉ
አመስግነዋታል:: ሊቁም:-
"አብርሃም ፍጹም በሒሩት ወበአምልኮ:
እግዚአብሔር አዕበየከ ወባረከከ ባርኮ:
እስከ ሰመየከ ዲበ ምድር አርኮ::" ብሎ በምሥጢር
ገልጾታል::
💚💛 ቅድስት ሣራ ብጽዕት💛❤️
አበው እናታችን ሣራን " #ቡርክተ_ማሕጸን " ይሏታል::
(የቅዱሱ ዘር የይስሐቅ እናት ናትና) በዚያውም ላይ የደጉ
ሰው የአብርሃም ሚስት ናት:: ልክ በዓለም ታሪክ "ከጠንካራና
ስኬታማ ወንዶች ጀርባ ጠንካራ ሴቶች አሉ" እንደሚባለው
ከአብርሃም አባታችን ስኬታማ የቅድስና ሕይወት ጀርባ
ብጽዕት ሣራ አለች::
ለአብርሃም አባታችን መጽሐፍ የተናገረው ክብር ሁሉ
ለቅድስት ሣራ ይገባታል:: አንድም ገንዘቧ ነው:: ቅድስቷ እናት
ደጉ አብርሃምን ያገባችው ገና በከላውዴዎን (በ2ቱ ወንዞች
መካከል) ሳለ ነው:: ገና ከልጅነቷ ጀምራ አብርሃምን "ጌታየ"
እያለች ታገለግለው እንደ ነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል::
(1ዼጥ. 3:5)
በዚህም ከብራበታለች: ገናበታለች እንጂ አልተጐዳችበትም::
አብርሃም ወደ ካራን ሲወጣ "ለምን?" አላላችም:: እንዲሁ
ለፈቃደ እግዚአብሔር ታዘዘች እንጂ:: በካራን ታራን ቀብረው:
በፈጣሪ ትዕዛዝ ወደ #ከነዓን ሲፈልሱም ቅድስት ሣራ
አልተቃወመችም::
ለፈጣሪዋ ትዕዛዝና ለባሏ ስትል ርስቷን: ሃገሯን: ዘመዶቿን
ሁሉ ትታ ሔዳለች:: ይሔውም በጐ ምናኔ ነው:: እናታችን ሳራ
በከነዓን የተመቸ ነገር አልገጠማትም:: ከአንዴም ሁለቴ
በረሃብና በድርቅ ምክንያት ወደ ግብጽ እና #ጌራራ ተሰደዋል::
በዚያም ፈርዖን "እነካለሁ" ቢል እግዚአብሔር ተቆጥቶ:
ፈርኦንንና ግብጽን በደዌ መታ:: በዚህም ክብረ ሣራን
ተመለከትን:: ከስደት መልስም በኬብሮን (በተመሳቀለ
መንገድ ላይ) ድንኩዋን ሠርተው የወጣ የወረደውን ሲያበሉ:
እንግዳ ሲቀበሉ ኑረዋል::
(ልብ በሉልኝ ይህን ትጋትና ደግነት ያሳየችውን ቅድስት ሣራን
ልናከብራት ይገባል)
እድሜ ዘመኗን ያሳለፈችው እንግዳ በመቀበል:
እግዚአብሔርን በማምለክ ነው:: ምንም እንኩዋ ማሕጸኗ
ለጊዜው ቢዘጋ ተስፋ አልቆረጠችም:: ለአብርሃምም ከአጋር እንዲወልድ ፈቃድ ሰጥታለች:: ዕድሜዋ 89 ዓመት በሆነ ጊዜ ሰይጣን እንግዳ እንዳይመጣ ለ3 ቀናት ቢያስቀርባቸው እንደ ባሏ እርሷም 3 ቀናትን ያለ ምግብ አሣልፋለች:: በ3ኛው ቀን ሥላሴን በቤቷ
አስተናግዳለች:: ስለ ክብሯም ከ3 መሥፈሪያ ዱቄት ለውሳ
ያዘጋጀችውን እንጐቻ ሥላሴ በልተውላታል:: (ምንም ሥላሴ
ምግብን ባይመገቡም)
የሥላሴ በዚያች ድንኩዋን ውስጥ መስተናገድ ታላቅ
ምሥጢር አለው:: ከግብዣው በሁዋላም እግዚአብሔር አለ:-
"አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ . . . እንዲሁ ከርሞ
እመለሳለሁ: ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች" አለው::
ያን ጊዜ ሣራ በውሳጤ ሐይመት (በድኩዋኑ ውስጥ) ሆና
ሰምታ ሣቀች:: ለምን ሳቀች ቢሉ:- እጅግ ደስ ቢላት! አንድም
ቢገርማት:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ:- ልጇ " #ይስሐቅ "
የተባለው "ለእናቱ ሣቅን: ደስታን ያመጣ" ለማለት ነውና::
ሥላሴም:- "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ: እንዘ ትብል
ዓዲየኑ እስከ ይእዜ: ወእግዚእየኑ ልሕቀ: ቦኑ ነገር ዘይሰዓኖ
ለእግዚአብሔር - ሣራን ምን አሳቃት? ለእግዚአብሔርስ
የሚሳነው ነገር አለን" ብለዋል::
ቅድስት ሣራ በ90 ዓመቷ ይስሐቅን ወልዳ በቀሪ ዘመኖቿ
በደስታ ኑራለች:: በዚህች ቀንም በመልካም ሽምግልና ዐርፋ:
አባታችን #አብርሃም ከታላቅ ሐዘን ጋር ቀብሯታል:: ሐዋርያው
#ቅዱስ_ዻውሎስ ብጽዕት ሣራን በበጐ ምሳሌ መስሏታል::
(ዕብ. 11:11)
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ባህር ዳር🔝

#በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉት የፀጥታ ችግሮች በርካቶች ከቀያቸው #እንዲፈናቀሉ እና የሰው ሕይወት በየቦታው #እንዲቀጠፍ ምክንያት እየሆኑ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ 51 አህጉረ ስብከቶች ስለሰላም የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና አተገባበር ዙሪያ ለሃይማኖት አባቶች እና ለምዕመናን በባሕር ዳር ስልጠና እየሰጠች ነው፡፡

በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ደብረ ፀሐይ ሰላም አድርጊው ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ፍቅረ ማርያም ‹‹አሁን ላይ በሀገሪቱ የተፈጠረው የሰላም እጦት የሰው ልጆች ለእግዚአብሔር ያለመታዘዝ ምንጮች ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ ሳለን የሰላም አስፈላጊነት የሁሉም ነገር ቁልፍ ናት ብሎ አስተምሮናል፤ ይህ ሰላም እንዲኖር የሃይማኖት አባቶች በጸሎት እና አስተምህሮ ከዚህ የበለጠ መሥራት እንደሚጠበቅብን አመላካች ነው›› ብለዋል፡፡

የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ሰፊው ወልደትንሳኤ ካህናት ሕዝቡ ሰላምን ያገኝ ዘንድ እንዲያስተምሩ አደራ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ካህናት ስለሰላም የሠራነው ሥራ ስለምን በዚህ ትውልድ ፍሬ #አላፈራም? ሕዝቡስ ስለምን ሰላምን አጣ? ብለን ሁከት የሚፈጥር እንዳይኖር በትኩረት እንድንሠራ ኃለፊነት አለብን›› ብለዋል፡፡

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ #አብርሃም ደግሞ ሀገሪቱ ዜጎች እየተሰደዱ፣ ሀብት ንብረታቸው እየወደመ እና ሕይወታቸውን እያጡ ያሉበት ወቅት ላይ እንደምትገኝ ነው የተናገሩት፡፡ ሁኔታው ቤተ ክርስቲያን #ስለሰላም ከዚህ በላይ መሥራት እንዳለባት አመላካች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ብጹዕነታቸው ‹‹ሰላምን የማይሻ ሰው ውስጡ የፍርሃት ባሕር አለ፡፡ በፍርሃት የሚቅበዘበዝ ትውልድ ደግሞ የተዋቡ ከተሞችን ዶግ አመድ ያደርጋል›› ነው ያሉት፡፡ ግጭት የሕጻናት እና እናቶችን ዋይታ እንደሚያበዛና ለፀብ የሚያነሳሱ ሰበቦችና መደለያዎች ግን በርካታ መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡ ‹‹የምንመራው ሕዝብ #ሰላም_ከሌለው አይጸድቅም፤ ጽድቅ የማያገኝ የእግዚአብሔር ትውልድ እንዳይኖር ደግሞ የሃይማኖት አባቶች ከዚህም በላይ መሥራት ይኖርብናል›› በማለትም አቡነ አብርሃም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethioia
#ጾመ_ነቢያት_ክፍል_2
#አብርሃም_ቀኔን_ያይ_ዘንድ_ሐሤት_አደረገ

በዚህ በክፍል ሁለት አቅርቦታችን ሊያዩና ሊሰሙ ናፍቀው አረፍተ ዘመን ከገታቸው ነቢያት አርእስተ አበው አብርሃምን በስፋት ቃኝተነዋል። እግዚአብሔር አምላካችን እንዲያስተምረን እንዲመክረን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።

#ዲ/ን_ከሣቴብርሃን_ገ/ኢየሱስ

👇👇👇👇👇

https://youtu.be/72thko8bYc4

ክፍል አንድን ለማግኘት
👇👇👇👇
https://youtu.be/8bOLhVcFDiI

ቀጣዩ ክፍል እንዲደርስዎት ሰብስክራይብ በማድረግ የደውል ምልክቱን ይጫኑ
👇👇👇
https://youtu.be/8bOLhVcFDiI