ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
+ሥሉስ_ቅዱስ +
በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ
(አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ
ፈጣሪ #እግዚአብሔር ነው:: #አብ: #ወልድ :#መንፈስ_ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት:
በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ
ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም
መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::
+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "#ቅድስት_ሥላሴ "
እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም::
የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም
መጥተው ያድራሉ::
+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል
በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን
#ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን
በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ
አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር
ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::
+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ
ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን
አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ
አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት::
በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት::
#ቅድስት_ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ
አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት
አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት
ነው " #ይስሐቅ " የተባለው::
+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል
እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ
ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ
ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::
✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን #አብርሃም : #ይስሐቅ
እና #ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
✞✞✞
እኒህ ቅዱሳን ከሰው ወገን እጅግ ክቡራን ከመሆናቸው የተነሳ መንግስተ ሰማያት በእነርሱ ስም
ተጠርታለች:: ጽድቃቸውና ክብራቸው እንደ ሰማይ
ከዋክብት የበዛ ነውና ጽፈንም: ተናግረንም
አንፈጽመውም:: እንዲሁ "ዕጹብ! ዕጹብ!" እያልን
ፈጣሪያቸውን ከማመስገን በቀር::
+"#ቅዱስ_አብርሃም_ርዕሰ_አበው "*+
የሃይማኖት: የደግነት: የምጽዋት: የፍቅር አባት
የሆነው አብርሃም በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት
አባቱ ታራ ጣዖትን ይጠርብና ይሸጥ ነበር:: ሽጦ ገንዘብ
የሚያመጣለት ደግሞ ልጁ አብርሃም ነበር::
¤በዚያ ወራት አብርሃም እውነተኛውን አምላክ ፍለጋ
ገብቶ ነበር:: አንድ ቀን ጣዖቱን ሊሸጥ ወደ ገበያ
እየሔደ የተሸከመውን እንጨት ይመራመረው ገባ::
"አሁን ይሔ ምኑ ነው አምላክ!" እያለም ያደንቅ ገባ::
መንገድ ላይም ደክሞት ካረፈበት "ለምን
አልጠይቀውም" በሚል አናገረው::
¤"እርቦኛል አብላኝ" አለው:: መልስ የለም:: "እሺ
አጠጣኝ" አለው:: አሁንም ያው ነው:: "ባይሆን እሺ
አጫውተኝ" አለው:: ጣዖቱ ተራ እንጨት ነውና መልሱ
ዝምታ ነበር:: ከዚያ ተነስቶ ወደ ገበያው ሲደርስ "ዐይን
እያለው የማያይ: ጀሮ እያለው የማይሰማ አምላክ
የሚገዛ" እያለ ይጮህ ጀመር::
¤ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ "የታራ ልጅ አብዶ" ሲሉ
ሌሎቹ ደግሞ "እሱ ያቀለለውን ማን ይገዛዋል" ብለውት
ሔደዋል:: ሲመለስም ጣዖቱን ተመልክቶ #አብርሃም
እንዲህ አለ:: "አንተ ቀድሞውን በዕለተ ሠሉስ
የተፈጠርክ ዕፅ ነህ" ብሎ ሰባበረው::
¤ወደ ቤቱ ሲመለስም ሁሉንም ጣዖታት ሠባበራቸው::
የመንግስተ ሰማያት አበጋዝ: የእግዚአብሔር ወዳጅ
አባታችን አብርሃም፡
የሕዝብና የአሕዛብ አባት የሆነው አብርሃም
እግዚአብሔርን አምልኮ: ጣዖታትን ሰብሮ ወደ # ከነዓን
ከወጣ በሁዋላ ብዙ ችግርን አሳልፏል:: በረሃብ
ምክንያት ከአንድም 2 ጊዜ ወደ ግብጽና ፍልስጥኤም
ተሰዷል:: በዚያ ግን ፈጣሪው አክብሮታል::
¤2ቱ ነገሥታት (ፈርኦንና አቤሜሌክ) ሣራን እንነካለን
ቢሉ ተግሣጽ ደርሶባቸዋል:: #ነቢይ ነውና በአብርሃም
ጸሎት ተፈውሰዋል:: ቅዱስ አብርሃም ከደግነቱ የተነሳ
በኬብሮን (በተመሳቀለ መንገድ) ላይ ድንኩዋን ሠርቶ
እንግዳ ይቀበል ነበር:: ምሥክር ሳይይዝም እህል
አይቀምስም ነበር::
¤ሰይጣን ከፍቶ እንግዳ ቢያስቀርበት ያለ ምግብ ለ3 ቀናት
ቆይቷል:: በፍጻሜውም #ሥላሴ በእንግድነት
መጥተውለት በክብር ላይ ክብር: በጸጋ ላይ ጸጋ:
በጣዕም ላይ ጣዕም ተጨምሮለታል:: እርሱ የሥላሴን
እግር ያጥብ ዘንድ: በጀርባውም ይሸከማቸው ዘንድ
አድሎታልና:: ሥላሴም በቤቱ ተስተናግደው: ልደተ
ይስሐቅን አክብሥረውታል:: ጻድቁ ሰውም በፈጣሪው ፊት
ስለ ሰዶምና ገሞራ ለምኗል::
¤አብርሃም በአምልኮው ፍጹም ነውና የሚወደውን ልጁን
ይስሐቅን ለመስዋዕት አቅርቧል:: በዚህም የነቢያት:
የሐዋርያት: የነገሥታት: የካህናት አባት:
#ሥርወ_ሃይማኖት (የሃይማኖት ሥር) ተብሏል::
ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ አያቱም ተብሏል::
¤አንድ ቀን #እግዚአብሔር መላእክቱን "ብየ አርክ
አብርሃም በዲበ ምድር - በምድር ላይ ወዳጄ አብርሃም
አለ" አላቸው:: ያን ጊዜ 99ኙ ነገደ መላእክት
ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ:-
*"አብርሃም አርከ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ወዳጅ)"
*"አብርሃም ብእሴ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ሰው)"
*"አብርሃም ገብረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር አገልጋይ)"
*"አብርሃም ምዕመነ እግዚአብሔር
(አብርሃም የእግዚአብሔር ታማኝ)
"አብርሃም ፍቁረ እግዚአብሔር (አብርሃም
የእግዚአብሔር ተወዳጁ ነው) እያሉ አሰምተው
ተናግረዋል::
¤አባታችን አብርሃም በክብር: በቅድስናና በሞገስ
ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ተጠቅሷል::
ፈጣሪ በስሙ ለቅዱሳን ተለምኗል:: ስለ ክብሩም
በሲዖል ውስጥ እንኩዋ ማረፊያን ሠርቶለታል::
አጋንንትም ሊቀርቡት አልተቻላቸውም:: ያረፈውም
ከክርስቶስ ልደት 1,900 ዓመታት በፊት ነው::
እድሜውም 175 ዓመት ነበር::
*ፍቅሩን የተረዱ ሊቃውንት ድንግል ማርያምን "ሐይመቱ
(ድንኩዋኑ): ተናግዶቱ (እንግድነቱ) ለአብርሃም" ሲሉ
አመስግነዋታል:: ሊቁም:-
"አብርሃም ፍጹም በሒሩት ወበአምልኮ:
እግዚአብሔር አዕበየከ ወባረከከ ባርኮ:
እስከ ሰመየከ ዲበ ምድር አርኮ::" ብሎ በምሥጢር
ገልጾታል::
#ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ
ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ #ማርያም_እግዝእት
በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ
መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
ከግራ ቁመት:
ከገሃነመ እሳት:
ከሰይጣን ባርነት:
ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ እንዳለ
ሊቁ::
ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ
ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው
ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ
አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም
ራሷ አርአያ #ትዕምርተ_መስቀል ናት::
እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት
(ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
#ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
#ቅዱስ_ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ.
48:14):
ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው #የሙሴ_በትር (ዘጸ.
14:15):
# የናሱ_ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8)
ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ
መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
# ቅዱስ_ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ
ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ
መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)
በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ
መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን
አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት::
ስለዚህም "#መስቀል_ብርሃን_ለኩሉ_ዓለም :
#መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን " ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
#ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ
ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን
ይነግረናል:: #ብርሃነ_ዓለም #ቅዱስ_ዻውሎስም ስለ
መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን
ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)
አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል::
የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ:
የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ:
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ
በወዴት አለና::
ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር
አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን:
እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት:
ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ
ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን
ተሻግረዋል::
በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም
አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን
እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ
ምስክርን አንፈልግም::
💚💛 ቅድስት ሣራ ብጽዕት💛❤️
አበው እናታችን ሣራን " #ቡርክተ_ማሕጸን " ይሏታል::
(የቅዱሱ ዘር የይስሐቅ እናት ናትና) በዚያውም ላይ የደጉ
ሰው የአብርሃም ሚስት ናት:: ልክ በዓለም ታሪክ "ከጠንካራና
ስኬታማ ወንዶች ጀርባ ጠንካራ ሴቶች አሉ" እንደሚባለው
ከአብርሃም አባታችን ስኬታማ የቅድስና ሕይወት ጀርባ
ብጽዕት ሣራ አለች::
ለአብርሃም አባታችን መጽሐፍ የተናገረው ክብር ሁሉ
ለቅድስት ሣራ ይገባታል:: አንድም ገንዘቧ ነው:: ቅድስቷ እናት
ደጉ አብርሃምን ያገባችው ገና በከላውዴዎን (በ2ቱ ወንዞች
መካከል) ሳለ ነው:: ገና ከልጅነቷ ጀምራ አብርሃምን "ጌታየ"
እያለች ታገለግለው እንደ ነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል::
(1ዼጥ. 3:5)
በዚህም ከብራበታለች: ገናበታለች እንጂ አልተጐዳችበትም::
አብርሃም ወደ ካራን ሲወጣ "ለምን?" አላላችም:: እንዲሁ
ለፈቃደ እግዚአብሔር ታዘዘች እንጂ:: በካራን ታራን ቀብረው:
በፈጣሪ ትዕዛዝ ወደ #ከነዓን ሲፈልሱም ቅድስት ሣራ
አልተቃወመችም::
ለፈጣሪዋ ትዕዛዝና ለባሏ ስትል ርስቷን: ሃገሯን: ዘመዶቿን
ሁሉ ትታ ሔዳለች:: ይሔውም በጐ ምናኔ ነው:: እናታችን ሳራ
በከነዓን የተመቸ ነገር አልገጠማትም:: ከአንዴም ሁለቴ
በረሃብና በድርቅ ምክንያት ወደ ግብጽ እና #ጌራራ ተሰደዋል::
በዚያም ፈርዖን "እነካለሁ" ቢል እግዚአብሔር ተቆጥቶ:
ፈርኦንንና ግብጽን በደዌ መታ:: በዚህም ክብረ ሣራን
ተመለከትን:: ከስደት መልስም በኬብሮን (በተመሳቀለ
መንገድ ላይ) ድንኩዋን ሠርተው የወጣ የወረደውን ሲያበሉ:
እንግዳ ሲቀበሉ ኑረዋል::
(ልብ በሉልኝ ይህን ትጋትና ደግነት ያሳየችውን ቅድስት ሣራን
ልናከብራት ይገባል)
እድሜ ዘመኗን ያሳለፈችው እንግዳ በመቀበል:
እግዚአብሔርን በማምለክ ነው:: ምንም እንኩዋ ማሕጸኗ
ለጊዜው ቢዘጋ ተስፋ አልቆረጠችም:: ለአብርሃምም ከአጋር እንዲወልድ ፈቃድ ሰጥታለች:: ዕድሜዋ 89 ዓመት በሆነ ጊዜ ሰይጣን እንግዳ እንዳይመጣ ለ3 ቀናት ቢያስቀርባቸው እንደ ባሏ እርሷም 3 ቀናትን ያለ ምግብ አሣልፋለች:: በ3ኛው ቀን ሥላሴን በቤቷ
አስተናግዳለች:: ስለ ክብሯም ከ3 መሥፈሪያ ዱቄት ለውሳ
ያዘጋጀችውን እንጐቻ ሥላሴ በልተውላታል:: (ምንም ሥላሴ
ምግብን ባይመገቡም)
የሥላሴ በዚያች ድንኩዋን ውስጥ መስተናገድ ታላቅ
ምሥጢር አለው:: ከግብዣው በሁዋላም እግዚአብሔር አለ:-
"አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ . . . እንዲሁ ከርሞ
እመለሳለሁ: ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች" አለው::
ያን ጊዜ ሣራ በውሳጤ ሐይመት (በድኩዋኑ ውስጥ) ሆና
ሰምታ ሣቀች:: ለምን ሳቀች ቢሉ:- እጅግ ደስ ቢላት! አንድም
ቢገርማት:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ:- ልጇ " #ይስሐቅ "
የተባለው "ለእናቱ ሣቅን: ደስታን ያመጣ" ለማለት ነውና::
ሥላሴም:- "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ: እንዘ ትብል
ዓዲየኑ እስከ ይእዜ: ወእግዚእየኑ ልሕቀ: ቦኑ ነገር ዘይሰዓኖ
ለእግዚአብሔር - ሣራን ምን አሳቃት? ለእግዚአብሔርስ
የሚሳነው ነገር አለን" ብለዋል::
ቅድስት ሣራ በ90 ዓመቷ ይስሐቅን ወልዳ በቀሪ ዘመኖቿ
በደስታ ኑራለች:: በዚህች ቀንም በመልካም ሽምግልና ዐርፋ:
አባታችን #አብርሃም ከታላቅ ሐዘን ጋር ቀብሯታል:: ሐዋርያው
#ቅዱስ_ዻውሎስ ብጽዕት ሣራን በበጐ ምሳሌ መስሏታል::
(ዕብ. 11:11)