የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.33K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮዽያ_ወንጌላዊያን_አብያተክርስቲያን_ህብረት_መሪዎች_በካዉንስሉ_ዋና_ፅህፈት_ቤት_ተገኝተዉ_የጉብኝት_እና_የአንድነት_ጊዜ_አካሄዱ
ሐምሌ 20 ቀን 2015ዓ/ም የኢትዮዽያ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያን ህብረት ፕሬዝዳንት ፓ/ር ፃዲቁ አብዶ እንዲሁም ፓ/ር ይልማ ዋቄ እና ፓ/ር አሸብር ከተማ በካዉንስሉ ዋና ፅ/ቤ በመገኘት የጉብኝት እና የአንድነት ጊዜ አካሂደዋል።
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ የእንኳን ደህና መጣቹ ንግግር ካደረጉ በኀላ ከካዉንስሉ ፅ/ቤ ሰራተኞች ጋር የትዉዉቅ ጊዜ ተከናዉኗል።
ፓ/ር ይልማ ዋቄ እና ፓ/ር አሸብር ከተማ በቀጣይ ከካዉንስሉ ጋር በሃላፊነት እንደሚሰሩ ተገልፆ የእንኳን ደህና መጣቹ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/5qQ3ixHS68c
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
የሩስያ ምክር ቤት ጾታ መቀየርን በሕግ ማገድ
የካውስሉ የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎ
2
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከወንጌላዊ_ቢሊ_ግርሃም_አሶሴሽን_መሪዎች_ጋር በካዉንስሉ ዋና ፅ/ቤ #ተወያዩ
ሐምሌ 28 ቀን 2015ዓ/ም የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ከወንጌላዊ ቢሊ ግርሃም አሶሴሽን መሪዎች ጋር በኢትዮዽያ ዉስጥ ስለሚሰሯቸዉ መንፈሳዊ ስራዎች ከካዉንስሉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ ጋር እንዲሁም ከካዉንስሉ መንፈሳዊ ዘርፍ ሃላፊ ፓ/ር ስንሻት ተካ ጋር በቀጣይነት አብረዉ በሚሰሯቸዉ ስራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በዉይይታቸዉም ወንጌልን በምን አይነት ሁኔታ ለምድሪቱ እንደሚያደርሱና በአገልጋዮች እና ቤተሰቦቻቸዉ ዙሪያ ያተኮረ ትምህርት እና ስልጠና በመስጠት ዙሪያ እቅድ በመያዝ ተወያይተዋል።
ወንጌላዊ ቢሊ ግርሃም ላለፋት 70 ዓመታት ወንጌልን ያስተማሩ ለሚሊዮኖች ህይወት መለወጥ ምክኒያት የሆኑ አባት ናቸዉ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/vAIu_qV_4RY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
2
#የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል እና #ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሽፕ አብረዉ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል እና ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሽፕ ልጆችን በወንጌል በመድረስ እና ደቀመዝሙር በማድረግ በቀጣይ አብረዉ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ባለ ዘጠኝ አንቀፅ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2016ዓ/ም ተፈራርመዋል።
ካዉንስሉ በኢትዮዽያ ዉስጥ የሚገኙ ቤተ-እምነቶች፣ህብረቶች እና ሚኒስትሪዎች አገልግሎታቸዉን በነፃነት እንዲፈፅሙ እያስተባበረ እና ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ መንፈሳዊ ተቋም ሲሆን ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሽፕ ልጆች ጌታ ኢየሱስን እንደግል አዳኝ አድርገዉ በመቀበል የጌታ ደቀመዝሙር በመሆን በአንድ ቤተክርስቲያን ዉስጥ ተተክለዉ እንዲፀኑ በማድረግ እየሰራ የሚገኝ መንፈሳዊ ተቋም ነዉ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/LxjvR-0KDAY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1716🔥6
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከፍተኛ_አመራሮች_በባህሬን_የካዉንስሉን_ቅርንጫፍ_ፅ/ቤት_አቋቋሙ።

የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ምክትል ፕሬዝዳንት ሐዋሪያዉ ዩሐንስ ግርማ እና የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ግንቦት 28 ቀን 2016ዓ/ም ወደ ባህሬን ያቀኑ ሲሆን በባህሬን በነበራቸዉ ቆይታ የካዉንስሉን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በማቋቋም የካዉንስሉን ስራ እንዲያስፈፅሙ በአባላት ምርጫ ተደርጎ ቦርድ ተቋቁሟል።

የካዉንስሉ አመራሮች ከተመረጡ መሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በባህሬን የኢትዮዽያ ቆንፅላ ፅ/ቤት ከአንባሳደር ሽፈራዉ ገነቴ ጋር ዉይይት ተደርጎ ወደፊት በጋራ ተቀራርቦ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

አመራሮቹ በባህሬን በነበራቸዉ ቆይታ የስልጠና እና የአምልኮ ጊዜ በዚያ ከሚገኙ ምዕመናን ጋር ያከናወኑ ሲሆን ህዝቡም ደስተኛ በመሆን እግዚያብሔርን አመስግነዋል።
የካዉንስሉ ከፍተኛ አመራር ልዑክ ቡድን በባህሬን የነበረዉን ቆይታ አጠናቀዉ ሰኔ 1 ቀን 2016ዓ/ም ወደ ኢትዮዽያ ተመልሰዋል። #ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/LxjvR-0KDAY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍8
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከኢትዮዽያ_ሃገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን_ጋር_ተወያዩ
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል መሪዎች ከኢትዮዽያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን መሪዎች ጋር ሰኔ 10 ቀን 2016ዓ/ም በካዉንስሉ ዋና ፅ/ቤት ተወያይተዋል።

በዉይይታቸዉም የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም የሰራቸዉን ስራ እና አሁን እየሰራ ስለሚገኘዉ ስራ አብራርተዋል።

ካዉንስሉ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ለሃገር መፍትሄ ይዞ ይመጣል ብሎ ስለሚያስብ እንዲሁም በቅርበት መስራት እንደሚፈልግ ታዉቆ በቂ ዉክልና እንዲሰጠዉና በየደረጃዉ ባሉ የምክክር ሂደቶች ዉስጥ ተካፋይ እንዲሆን ጥያቄ አቅርቧል።

በዚሁ መሰረት ሁለቱም አካላት ሰፊ ዉይይት አድርገዉ በቀጣይ አብሮ ለመስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/LxjvR-0KDAY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍124
#የኢትዮዽያ_ወንጌላዊት_ቤተክርስቲያን_መካነ_ኢየሱስ_ሴሚናሪ_በስነመለኮት_ትምህርት_PHD_ፕሮግራም_በይፋ_አስጀመረ

የኢትዮዽያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ ሰኔ 13 ቀን 2016ዓ/ም በስነመለኮት ትምህርት PHD ፕሮግራም ማስጀመሩን ይፋ አድርጓል።በፕሮግራሙ ላይ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እና የቤተክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ዘርፍ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት ቄስ ዶ/ር ዩናስ ይገዙ PHD ፕሮግራሙን በፀሎት እና ንግግር በማድረግ በይፋ ያስጀመሩት ሲሆን ይህ ፕሮግራም ለሌሎች አብያተክርስቲያናት እና ከኢትዮዽያ ዉጪ ለሚገኙ ሃገራት ሚሽነሪዎችን በእዉቀት ለማስታጠቅ ለረጅም አመት የታሰበ መሆኑን ገልፀወል።

የቤተክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ፀሃፊ እና የሴሚናሪዉ ቦርድ አባል ቄስ ተሾመ አመኑ እንደገለፁት ፕሮግራሙ የተከፈተዉ ሰዎች እንዲማሩ በመሆኑ አገልጋዮች ወደዚህ በመምጣት የማህበረሰቡን ጥያቄዎች የሚመልሱ ጥናቶች እንዲያደርጉ እንጋብዛለን ብለዋል።

የሴሚናሪዉ ፕሬዝዳንት ቄስ ዶ/ር ብሩክ አየለ እንደገለፁት ሴሚናራዉ ከተመሰረተ ከ65 አመታት በኋላ አሁን ከፍተኛ የስነ መለኮት ትምህርት ደረጃ ላይ መድረሱን በመግለፅ የቤተክርስቲያኒቱ ሴሚናሪ በራሱ አቅም በአይነቱ የመጀመሪያ ፕሮግራም በማስጀመሩ ለመካነ ኢየሱስ ቤ/ክ እና ለኢትዮዽያ አብያተክርስቲያናት ትልቅ እምርታ መሆኑን አስታዉቋል።

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/LxjvR-0KDAY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍205
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_የተሰጠ_ጋዜጣዊ_መግለጫ
በመጋቢ ጌቱ ለማ የካውንስሉ ጽ/ቤት ሃላፊ
#በኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፋቱ ማዕከል ላይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እየተወሰደ ያለውን ኢ/ህገ መንግታዊ ጥሰት ለመቃወም የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፋቱ ማዕከል በህጋዊ መንገድ ለቃለ ሐይወት ቤተክርስቲያን የተሰጠ ሰነድ ያለው ይዞታ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከቤተክርስቲያኒቱ ቦታ ላይ 40 ሺህ ካሬ ሜትር የሚሆነውን በኃይል በመቀማት ለሁለት ግለሰቦች በመስጠት ኢ.ህገ መንግስታዊ በደል ፈጽሞብናል።
ይህንን ጉደይ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ቤተክርስቲያን ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርባ ፍርድ ቤቱ ቦታው የቃለ ሕይወት ይዞታ መሆኑን ውሳኔ አስተላልፎ ባለበት ሁኔታ የከተማ አስተዳደሩ የግንባታን ሂደቱን እያስተጓጎለ ስለነበር ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ለፌዴራል መንግስት አቅርበን በከፍተኛ አመራር ደረጀ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየታየ ባለበት ሁኔታ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ የቤተክርስቲያኒቱ ይዞታ ውስት ወታደሮችንና የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችን ይዞ በመግባት ችካል በማስቀመጥ የቤተክርስቲያኒቱን ይዞታ ለግለሰቡ በማስተላለፉ ህግ ወጥ ተግባር ፈጽሞብናል ።
ይህ ሁኔታ ከባድ እና በወንጌላውያን አምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ ሐይማኖታዊ ጥላቻ ባለቸው ግለስቦቸ የተቀነባበረ መንግስት የማይወክል የግለሰቦች ፍላጎት እና በልማት ሰበብ ሕዝብን ከመንግስት ጋር ለማጣላት እና ታሪካው ቅራኔ ለመፍጠር ሆን ተብሎ እየተሰራ ያለ መሆኑን እንረዳለን ።
ዛሬ ሃምሌ 4 የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች ወደ ስፍራው፡ በሄዱበት ወቅት የማዋከብ የማሸማቀቅ እና ወደ እስር መውሰድ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል።
በመሆኑም መለው የወንጌል አማኞች በዚሀ የህልውናችን ጉዳይ ህግ መንግስታዊ መብታችንን እስከሚከበር ድረስ ለሚመለከታቸው ለክልሉ እና ለፌዴራል መንግስት አካላት ጥያቄያችንን ከማቅረብ ባሻገር ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ የምንከፍል መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።
በመሆኑም የሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት፣ከፍተኛ አመራሮችና የፌዴራል መንግስት አካላት ይህ ጉዳይ የህዝብ ሰላም በማይፈልጉ አካላት በልማት ሰበብ እየተሰራ የለውን ህግ መንግስቱን የጣሰ ስራ አንድታስቆሙልን እና አስቸኳይ ምላሸ እንዲሰጡን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍112😢2
#የፌደራል_መንግስት_የ35_ሚሊዮን_ህዝብን_ጥያቄ_በአፋጣኝ_ምላሽ_እንዲሰጥ_ተጠየቀ

#የኢትዮዽያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን በቢሾፍቱ ኩሪፍቱ ማዕከል ለማልማት ያሰበችዉን እቅድ ለካዉንስሉ አመራሮች፣ስራ አስፈፃሚ ቦርድ እንዲሁም ለአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና ለቤተ ዕምነት አመራሮች በዝርዝር ያቀረበች ሲሆን

መሪዎቹ ሐምሌ 12 ቀን 2016ዓ/ም በኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ዋና ፅ/ቤት ባደረጉት ስብሰባ የቃለ ህይወት ቤ/ክ የቢሾፍቱ ኩሪፍቱ ማዕከልን ታሪካዊ ዳራ፣ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እና ስፍራዉን ዘመኑ በሚጠይቀዉ ደረጃ ለማልማት የያዘችዉን እቅድ ተመልክተዋል።


በመሆኑም የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በቃለህይወት ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ እያደረገ የሚገኘዉን ህገወጥ ድርጊት በአፋጣኝ እንዲያቆም እንዲሁም የፌደራል መንግስት የ35 ሚሊዮን ህዝብን ጥያቄ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ለዚህ ጥያቄ ምላሽ እስከሚገኝ ድረስ ማንኛዉንም ሰላማዊ ትግል እንደሚያደርጉ መሪዎቹ በመግለጫቸው አስታዉቀዋል።
በመጨረሻም
የወንጌላዊያን አማኙ በዚህ ጉዳይ በፆም እና በፀሎት በእግዚአብሔር ፊት እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍161
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_በቢሾፍቱ_ኩሪፍቱ_ቃለ_ህይወት_ቤ_ክ_ጉዳይ_ሐምሌ_18_ቀን_2016ዓ_ም_ዳግመኛ_ጋዜጣዊ_መግለጫ_ሰጠ

መግለጫዉን የሰጡት የካዉንስሉ ፅ/ቤት ሃላፊ ፓ/ር ጌትነት ለማ ከመግለጫዉ በማስቀደም በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ባጋጠመዉ የመሬት መንሸራተት በደረሰዉ አደጋ ልባዊ ሃዘን በመግለፅ መፅናናትን ተመኝተዋል። በቀጣይም ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች አስፈላጊዉን እገዛ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

በመቀጠል በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘዉ የኩሪፍቱ ማዕከል ከህግ ዉጪ የቤተክርስቲያኒቱን ንብረት በሃይል መነጠቁን አስመልክቶ የፍትህ ጥያቄ ለሚመለከታቸዉ አካላት መቅረቡን በማስታወስ በዚህ መሰረት ካዉንስሉ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር
በደብዳቤ እና በአካል በመነጋገር ጉዳዩ በዉይይት እንዲፈታ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አስታዉቀዋል።

ሆኖም ለቀረቡት ጥያቄዎች ምንም አይነት ምላሽ አለመሰጠቱን እና ህግን በመጣስ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ አጥር አጥሮ ተቀምጦ ይገኛል። ስለዚህ

1-የካዉንስሉ አባል ቤተ ዕምነቶች እና ህብረቶች በሃይል የተወረረዉ መሬት እና በጊቢ ዉስጥ የታጠረዉ አጥር ፈርሶ እስከምናይ ድረስ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምፃችሁን ማሰማታችሁን እንድትቀጥሉ ጥሪ እናቀርባለን።

2-በተለያየ የመንግስት ተቋማት ላይ የምትሰሩ የህግ ባለሞያዎች እና የፍትህ አካላት ይህ ጉዳይ ፍትህ እስከሚያገኝ ድረስ ድጋፋችሁን እንድታደርጉልን እና ድምፃችሁን እንድታሰሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም የፌደራል መንግስት ላዋቀረዉ ኮሚቴ ጉዳዩን እያጣራ ምላሽ ሳይሰጥ በአቋራጭ ያደረጉት ወረራ ዘመን ተሻጋሪዋን መከራ የማይችላትን ቤተክርስቲያንን እንደተራ መቁጠር ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከትል ከመሆኑም ባሻገር ታሪካዊ ጥላቻን ጥሎ የሚያልፍ በመሆኑ የፌደራል መንግስት የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እየወሰደ ያለዉን ኢ-ህገመንግስታዊ እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያስቆም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን።

#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_በቢሾፍቱ_ኩሪፍቱ_ቃለ_ህይወት_ቤ_ክ_ጉዳይ_ሐምሌ_18_ቀን_2016ዓ_ም_ዳግመኛ_ጋዜጣዊ_መግለጫ_ሰጠ


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🔥9👍63
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_አመራሮች_የጅማ_ከተማ_የካዉንስል_መሪዎችን_ጎበኙ

ከነሐሴ 17-19 ቀን 2016ዓ/ም በተካሄደዉ ጉብኝት የካዉንስሉ መሪዎች በጅማ እና በዞኑ ለሚገኙ 55 ለሚሆኑ የካዉንስሉ የቦርድ አባላት እና አገልጋዮች ስለ ካዉንስሉ ማንነት እና አደረጃጀት ዙሪያ መግለጫ ሰተዋል።
ከመግለጫዉ ባሻገር በልዩነት አንድነት እና የሚሲዮናዊነት አገልግሎት በሚል ርዕሶች ለመሪዎቹ የስልጠና ተሰጥቷል ።

ነሐሴ 19 ቀን 2016ዓ/ም በጅማ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ከየ አጥቢያዉ ለተወጣጡ ከ200 በላይ ለሚሆኑ አገልጋዮች እና ምዕመናን ተከታታይ የማነቃቂያ መልዕክት በመስጠት አገልጋዮችን አበረታተዋል ።

የካዉንስሉ አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓ/ር አሸብር ከተማ ጉብኝቱ የታሰበለትን አላማ እንደመታ ገልፀዉ በጅማ እና አካባቢዉ ያለዉ የወንጌል አማኝ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን እና ባሉት ችግሮች ዙሪያ ከመሪዎች ጋር በመመካከር ወደፊት ሰፊ ስራዎችን ለመስራት መወያየታቸዉን አስታዉቋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍8🔥42
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_2017_አዲስ_ዓመትን_ከአባል _ቤተ_እምነት_ጋር_በበመማፀኛ_ከተማ_(ዩጎ)_ቤተክርስቲያን_በአንድነት_አከበሩ።

በመርሃ ግብ የአምልኮ የፀሎት እና የቃል ጊዜ እንዲሁም አዲሱን ዓመት የመባረክ ጊዜ ተከናዉኗል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_አዘጋጅነት_ወንጌል_ስርጭት_እና_ደቀመዝሙ_ማፍራት_በሚል_ርዕስ_ስልጠና_ተሰጠ

ጥቅምት 11 ቀን 2017ዓ/ም በተሰጠዉ ስልጠና ከወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ህብረት እና ከካዉንስሉ አዲስ አበባ ክላስተር የተወጣጡ መሪዎች ተካፍለዋል።

ስልጠናዉን የሰጡት የኦርጋኒክ አዉትራች ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ዳይሬክተር ፓ/ር ዋልት ቤኔት ከአሜሪካ ሆስተን ቴክሳስ የመጡ ሲሆን የስልጠናዉ አላማ እና የትኩረት አቅጣጫ ክርስቲያኖች በታላቁ ተልኮ በሚፈለገዉ መንገድ እንዲሰማሩ ማድረግ እና የኢየሱስ ተከታይ የሆኑ ደቀመዛሙርትን ማፍራት ላይ ያተኮረ ስልጠና እንደሆነ ገልፀዋል።

የካዉንስሉ የዉጪ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓ/ር አሸብር ከተማ በወንጌል የምንደርሰዉን ሰዉ ደቀመዝሙር የማድረግ ሃላፊነታችንን እንወጣ ደቀመዝሙር የአራት ወይም የስድስት ወራት ትምህርት መስጠት ሳይሆን የእድሜ ልክ ጉዳይ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

የካዉንስሉ በምክትል ጠቅላይ ፀሃፊ ማዕረግ የመንፈሳዊ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ሃላፊ ፓ/ር ይልማ ዋቄ እንደገለፁት እንደቀድሞ በፀሎት እና ወንጌልን በመስበክ በመትጋት በአለም ላይ ከታወቁ የወንጌል ስራን ከሚሰሩ ሚኒስትሪዎች ጋር በመተባበር የወንጌል አማኝ አባሎችን በማሰልጠን እና በማስታጠቅ ላይ እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
4👍1
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_በአዲሰ_አበባ_ከተማ_የሚገኙ_የካውንስሉን_አባል_ቤተ_አምነቶቸን_በራ_እንዲሰሩ_አደራጀ

ፕሮግራሙ ጥቅምት16-2017/ዓ.ም በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ዋና ጽ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዘዳንት ፓስተር ፃድቁ አብዶ የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈሉ ሲሆን እግዚአብሔር ትሁት ነውና በትህትና እና በአንድ ልብ ተያይዘን እናገልግል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ጽ/ቤ ሃላፊ ፖስተር ጌቱ ለማ ስለ ካዉንስሉ አደረጃጀት ገለፃ በማድረግ እንዲሁም ለህብረት ሲባል ብዙ መሰዋዕትነት መክፈል ይገባል በተለይም በአዲስ አበባ ያላችሁ መዋቅሮች ምሳሌ ልንሆን ይገባል ብለዋል። 
በአዲሰ አበባ ከተማ የካዉንስሉን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በማቋቋም የካዉንስሉን ስራ እንዲያስፈፅሙ የኮሚቴ ምርጫ ተደርጎ ቦርድ ተቋቁሟል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍10🙏1
#የኢትዮዽያ ቲር ፈንድ ቢሮ ቤተክርስቲያን እና የማህበረሰብ ለዉጥ ላይ አተኩሮ የሚሰራ ቦርድ አቋቋመ። በኢትዮዽያ የቦርዱ ሰብሳቢ የካዉንስሉ ተወካይ የሆኑት ፓስተር አሸብር ከተማ ሆነዉ ተመርጠዋል።

ከህዳር 3 እስከ ህዳር 6 ቀን 2017ዓ/ም በኬኒያ በተካሄደዉ ስብሰባ የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓ/ር አሸብር ከተማ ጨምሮ አራት ተወካዮች በስብሰባዉ ተካፍለዋል።

በስብሰባዉ ከሯንዳ፣ቡርንዲ፣ከዲሞክራቲክ ሪፐፕሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ከደቡብ ሱዳን እና ኢትዮዽያን ጨምሮ ከስድስት ሀገራት የተወጣጡ ወደ 30 የሚሆኑ ተወካዮች ተገኝተዋል።

ስብሰባዉ የትኩረት አቅጣጫዉን ያደረገዉ ቤተክርስቲያን ማህበረሰቡን መለወጥ እንደምትችል እና በሰላም፣ተስፋ በማደስ እነዚህን እና በመሳሰሉ ጉዳዮች የለዉጥ ሐዋሪያ ሆና ማገልገል እንደምትችል በዋነኝነት ተወያይተዋል። ከዉይይቱ ባሻገር የስልጠና ጊዜ እና በሌሎች ሀገራት የተሰሩ ስራዎች የግምገማ ጊዜ ተከናዉኗል።

በመጨረሻም በኢስት አፍሪካና በሴንትራል አፍሪካ ሪጅን ምርጫ ተካሂዶ የካዉንስሉ አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓስተር አሸብር ከተማ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዉ ተመርጠዉ ስብሰባዉ ተጠናቋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🙏6👍4
#የኢትዮዽያ_ሙሉ_ወንጌል_አማኞች_ቤተክርስቲያ_ኢየሱስ_ሰዉን_ሁሉ_ይወዳል_በሚል_መሪ_ቃል_በአዲስ_አበባ_ስታዲየሚ_የሚካሄደዉን_ኮንፍራስ_በማስመልከት_ህዳር_20_ቀን_2017_ዓ/ም_ጋዜጣዊ_መግለጫ_ሰጠች።

በመግለጫዉ ከታህሳስ 4 እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2017ዓ/ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ኢየሱስ ሰዉን ሁሉ ይወዳል በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንፍራንሱ እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን ከአዲስ አበባ እና ከሸገር ከተማ የተሰባሰቡ 206 የሚሆኑ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ኮንፍራንሱን በጋራ እንዳዘጋጁት ተገልፃል።

ከኮንፍራንሱ በማስቀደም ለ10 ተከታታይ ወራት የወንጌል ስርጭት ስራ ሲሰራ መቆየቱ እና በቀጣይ 10 ቀናት በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች የወንጌል ስርጭት እንቅስቃሴ እንደሚደረግ አስታዉቀዋል።
እንዲሁም በልዩ ልዩ በጎ ተግባራት ማለትም ነፃ የህክምና አገልግሎት በቂርቆስ ጤና ጣቢያ ታህሳስ 2 እና 3 እንደሚሰጥ እና በቂሊንጦ፣በዳለቲ እና በቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ልዩ ልዩ ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልፃል።

ቤተክርስቲያኒቱ በሀገር ዉስጥ እና ከሀገር ዉጪ በደቡብ አፍሪካ፣በሶማሊያ፣በደቡብ ሱዳን እና በጅቡቲ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስራዎችን ስትሰራ እንደቆየች በመግለጫዉ ተካቷል።

መግለጫዉን የሰጡት የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት ፓስተር ላኮ በዳሶ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ፓስተር ለወየው ስንሻው እና የፕሮግራሙ አስተባባሪ ፓስተር አበራ አብዋሬ ሁሉም የወንጌል አማኝ በኮንፍራንሱ ላይ ሰዎችን በመጋበዝ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
2👍2
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከየካቲት_10_13_2017 ዓ.ም ለሁለት መቶ የሰንበት አስተማሪዎች በልጆች አገልግሎት ጉዳይ ላይ ሰጠ።
ከቢሊግራሃም እቫንጀልስቲክ አሶሴሽን እህት ድርጅት ከሆነው ሰማሪታን ፐርስ የተባለው ተቋም አንድ ዘርፍ የለው ሲሆን በዚህም ልጆችን መሰራት አድረጎ የሚሰራ ተቋም ነው።
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ከኦሲሲ ኦፕሬሽን ክሪስማስ ቻይልድ፣ ከዚህ ድርጅት ጋር በጣም በቅርበት እየሰራ ሲሆን በቅርቡ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በተለይም በጦርነት የተጎዱትን ልጆች በጥቂቱም ቢሆን ያላቸውን መጎዳት ሊቀርፍላቸው ይችላል ብለው በማመን ሁለት ኮንቴይነር የስጦታ እቃዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብቶአል፡፡
ይህንን ስጦታ አስመልክቶ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለሆኑቱ የካቲት 7 ለ52 የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የቁርስ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ በዛ ላይ ስለፕሮግራም መግለጫ ተሰቶዋል፡፡
ከየካቲት 10_ 13 በአጠቃላይ ለሁለት መቶ የሰንበት አስተማሪዎች በልጆች አገልግሎት ጉዳይ ላይ ከዚህ ተቋም ከዩጋንዳ ፣ከኬንያ እና ከብሩንዲ የመጡ አሰልጠኞች ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
እነዚህ ስልጠናዎች በጉዲና ቱምሳ፣ በሀያት የጉባዔ እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያንና ፣በኮልፌ መካነ ኢየሱስ ተሰቶዋል፡፡ አጠቃላይ በዚህ ስልጠና ሁለት መቶ ያህል የሰንበት አስተማሪዎች ከመቶ ዘጠና አከባቢ የመጡ የሰንበት አስተማሪዎች ስልጠናውን መካፈል ችለዋል፡፡
4👍3🙏1