#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_የተሰጠ_ጋዜጣዊ_መግለጫ
በመጋቢ ጌቱ ለማ የካውንስሉ ጽ/ቤት ሃላፊ
#በኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፋቱ ማዕከል ላይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እየተወሰደ ያለውን ኢ/ህገ መንግታዊ ጥሰት ለመቃወም የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፋቱ ማዕከል በህጋዊ መንገድ ለቃለ ሐይወት ቤተክርስቲያን የተሰጠ ሰነድ ያለው ይዞታ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከቤተክርስቲያኒቱ ቦታ ላይ 40 ሺህ ካሬ ሜትር የሚሆነውን በኃይል በመቀማት ለሁለት ግለሰቦች በመስጠት ኢ.ህገ መንግስታዊ በደል ፈጽሞብናል።
ይህንን ጉደይ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ቤተክርስቲያን ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርባ ፍርድ ቤቱ ቦታው የቃለ ሕይወት ይዞታ መሆኑን ውሳኔ አስተላልፎ ባለበት ሁኔታ የከተማ አስተዳደሩ የግንባታን ሂደቱን እያስተጓጎለ ስለነበር ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ለፌዴራል መንግስት አቅርበን በከፍተኛ አመራር ደረጀ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየታየ ባለበት ሁኔታ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ የቤተክርስቲያኒቱ ይዞታ ውስት ወታደሮችንና የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችን ይዞ በመግባት ችካል በማስቀመጥ የቤተክርስቲያኒቱን ይዞታ ለግለሰቡ በማስተላለፉ ህግ ወጥ ተግባር ፈጽሞብናል ።
ይህ ሁኔታ ከባድ እና በወንጌላውያን አምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ ሐይማኖታዊ ጥላቻ ባለቸው ግለስቦቸ የተቀነባበረ መንግስት የማይወክል የግለሰቦች ፍላጎት እና በልማት ሰበብ ሕዝብን ከመንግስት ጋር ለማጣላት እና ታሪካው ቅራኔ ለመፍጠር ሆን ተብሎ እየተሰራ ያለ መሆኑን እንረዳለን ።
ዛሬ ሃምሌ 4 የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች ወደ ስፍራው፡ በሄዱበት ወቅት የማዋከብ የማሸማቀቅ እና ወደ እስር መውሰድ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል።
በመሆኑም መለው የወንጌል አማኞች በዚሀ የህልውናችን ጉዳይ ህግ መንግስታዊ መብታችንን እስከሚከበር ድረስ ለሚመለከታቸው ለክልሉ እና ለፌዴራል መንግስት አካላት ጥያቄያችንን ከማቅረብ ባሻገር ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ የምንከፍል መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።
በመሆኑም የሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት፣ከፍተኛ አመራሮችና የፌዴራል መንግስት አካላት ይህ ጉዳይ የህዝብ ሰላም በማይፈልጉ አካላት በልማት ሰበብ እየተሰራ የለውን ህግ መንግስቱን የጣሰ ስራ አንድታስቆሙልን እና አስቸኳይ ምላሸ እንዲሰጡን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍11❤2😢2