የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.3K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_አመራሮች_የጅማ_ከተማ_የካዉንስል_መሪዎችን_ጎበኙ

ከነሐሴ 17-19 ቀን 2016ዓ/ም በተካሄደዉ ጉብኝት የካዉንስሉ መሪዎች በጅማ እና በዞኑ ለሚገኙ 55 ለሚሆኑ የካዉንስሉ የቦርድ አባላት እና አገልጋዮች ስለ ካዉንስሉ ማንነት እና አደረጃጀት ዙሪያ መግለጫ ሰተዋል።
ከመግለጫዉ ባሻገር በልዩነት አንድነት እና የሚሲዮናዊነት አገልግሎት በሚል ርዕሶች ለመሪዎቹ የስልጠና ተሰጥቷል ።

ነሐሴ 19 ቀን 2016ዓ/ም በጅማ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ከየ አጥቢያዉ ለተወጣጡ ከ200 በላይ ለሚሆኑ አገልጋዮች እና ምዕመናን ተከታታይ የማነቃቂያ መልዕክት በመስጠት አገልጋዮችን አበረታተዋል ።

የካዉንስሉ አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓ/ር አሸብር ከተማ ጉብኝቱ የታሰበለትን አላማ እንደመታ ገልፀዉ በጅማ እና አካባቢዉ ያለዉ የወንጌል አማኝ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን እና ባሉት ችግሮች ዙሪያ ከመሪዎች ጋር በመመካከር ወደፊት ሰፊ ስራዎችን ለመስራት መወያየታቸዉን አስታዉቋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍8🔥42