የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.33K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የፌደራል_መንግስት_የ35_ሚሊዮን_ህዝብን_ጥያቄ_በአፋጣኝ_ምላሽ_እንዲሰጥ_ተጠየቀ

#የኢትዮዽያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን በቢሾፍቱ ኩሪፍቱ ማዕከል ለማልማት ያሰበችዉን እቅድ ለካዉንስሉ አመራሮች፣ስራ አስፈፃሚ ቦርድ እንዲሁም ለአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና ለቤተ ዕምነት አመራሮች በዝርዝር ያቀረበች ሲሆን

መሪዎቹ ሐምሌ 12 ቀን 2016ዓ/ም በኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ዋና ፅ/ቤት ባደረጉት ስብሰባ የቃለ ህይወት ቤ/ክ የቢሾፍቱ ኩሪፍቱ ማዕከልን ታሪካዊ ዳራ፣ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እና ስፍራዉን ዘመኑ በሚጠይቀዉ ደረጃ ለማልማት የያዘችዉን እቅድ ተመልክተዋል።


በመሆኑም የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በቃለህይወት ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ እያደረገ የሚገኘዉን ህገወጥ ድርጊት በአፋጣኝ እንዲያቆም እንዲሁም የፌደራል መንግስት የ35 ሚሊዮን ህዝብን ጥያቄ በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ለዚህ ጥያቄ ምላሽ እስከሚገኝ ድረስ ማንኛዉንም ሰላማዊ ትግል እንደሚያደርጉ መሪዎቹ በመግለጫቸው አስታዉቀዋል።
በመጨረሻም
የወንጌላዊያን አማኙ በዚህ ጉዳይ በፆም እና በፀሎት በእግዚአብሔር ፊት እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍161