የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.3K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቻይልድ_ኢቫንጀሊዝም_ፌሎሽፕ ለሁለተኛ ግዜ #የህጻናት_ፌስቲቫል በኮርያ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ አካሄደ::
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/e_CVyeLb3rU
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል እና #ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሽፕ አብረዉ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል እና ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሽፕ ልጆችን በወንጌል በመድረስ እና ደቀመዝሙር በማድረግ በቀጣይ አብረዉ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ባለ ዘጠኝ አንቀፅ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2016ዓ/ም ተፈራርመዋል።
ካዉንስሉ በኢትዮዽያ ዉስጥ የሚገኙ ቤተ-እምነቶች፣ህብረቶች እና ሚኒስትሪዎች አገልግሎታቸዉን በነፃነት እንዲፈፅሙ እያስተባበረ እና ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ መንፈሳዊ ተቋም ሲሆን ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሽፕ ልጆች ጌታ ኢየሱስን እንደግል አዳኝ አድርገዉ በመቀበል የጌታ ደቀመዝሙር በመሆን በአንድ ቤተክርስቲያን ዉስጥ ተተክለዉ እንዲፀኑ በማድረግ እየሰራ የሚገኝ መንፈሳዊ ተቋም ነዉ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/LxjvR-0KDAY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1716🔥6
#ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሺፕ ከተለያየ አብያተክርስቲያናት ለተወጣጡ የልጆች የሰንበት አስተማሪዎች እና አስተባባሪዎች ስልጠና ሰጠ።

ከነሐሴ 28-30 ቀን 2016ዓ/ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት 5ኪሎ በሚገኘዉ መካነ ኢየሱስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስልጠናዉ የተሰጠ ሲሆን አላማዉም ልጆችን ደቀመዝሙር ማድረግ እና ወንጌል ወራሽ ትዉልድን ማፍራት እንደሆነ ተገልፃል።

የካዉንስሉ የሚሽን እና የቲዮሎጂ ዲፓርትመንት መምሪያ ሃላፊ ፓ/ር ሽመልስ ደጀኔ በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ ተገኝተዉ ቃል አካፍለዉ መልዕክት አስተላልፈዋል ልጆችን በወንጌል መድረስ እንደሚገባ እና በእግዚያብሔር ቃል አንፆ ማሳደግ እንደሚገባ ልጆች ላይ መስራት ትዉልድን መለወጥ እንደሆነ ስለዚህ ቤ/ክ በዚህ ላይ ዋጋ ሰጥታ ልትሰራ እንደሚገባ በመግለፅ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሺፕ አስተባባሪ ወንጌላዊት አልማዝ እንደገለፀችዉ ልጆችን ማገልገል ነገን ማገልገል ስለሆነ ስልጠናዉን የወሰዱት መምህራን ወደ ቤተክርስቲያናቸዉ ሲመለሱ ተልኳቸዉን በአግባቡ ከፈፀሙ ትልቅ ለዉጥ እንደሚመጣ ገልፃለች።

ከተለያየ አብያተክርስቲያናት መተዉ በስልጠናዉ የተሳተፋት የሰንበት አስተማሪዎች እና አስተባባሪዎች ስልጠናዉ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀዉ የነገ ትዉልድን ደቀ መዝሙር አድርጎ ለማፍራት እና የበለጠ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸዉን ገልፀዋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍111