የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.3K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከሪል_ላይፍ_ሚኒስትሪ_ጋር በመተባበር ከተለያየ አብያተክርስቲያናት ህብረት ለተወጣጡ አገልጋዮች #ደቀመዝሙር_አድራጊ_ቤተክርስቲያን_ሚናዋ_ምንድነዉ? በሚል ርዕስ #ስልጠና_ተሰጠ። ስልጠናዉ ግንቦት 16 እና 17 ቀን 2015ዓ/ም የሚከናወን ሲሆን ዛሬ በተጀመረዉ የስልጠና ጊዜ የካዉንስሉ መንፈሳዊ ዘርፍ ክፍል ሃላፊ ፓስተር ስንሻት ተካ ፕሮግራሙን በፀሎት አስጀምረዋል። የካዉንስሉ ፅህፈት ቤት ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን “ደቀመዝሙር ለማድረግ መጀመሪያ ደቀመዝሙር መሆን ያስፈልጋል ሌሎቹን ደቀመዝሙር ለማድረግ ደግሞ መትጋት ያስፈልጋል” ብለዋል። ከሪል ላይፍ ሚኒስትሪ የመጡ አገልጋዮች ጥናታዊ ፅሁፎችን በማቅረብ ስልጠናዉን የሰጡ ሲሆን ስልጠናዉ ግንቦት 17 ቀን 2015ዓ/ም የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፦https://youtu.be/tv9Rkx0HuiU
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከዋን_ኢን_ክራይስት_ኢንተርናሽናል_ሚኒስትሪ_ጋር_በመተባበር ከተለያየ አብያተክርስቲያናት ህብረት ለተወጣጡ አገልጋዮች #የአመራር_ዘይቤዎች በሚል ርዕስ በጉዲና ቱምሳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ #ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናዉ ግንቦት 29 እና 30 ቀን 2015ዓ/ም የሚከናወን ሲሆን ዛሬ በተጀመረዉ የስልጠና ጊዜ የካዉንስሉ መንፈሳዊ ዘርፍ ክፍል ሃላፊ ፓስተር ስንሻት ተካ ፕሮግራሙን በፀሎት አስጀምረዋል። ስልጠናዉን የተሰጠዉ ከሪል ላይፍ ሚኒስትሪ ከአሜሪካን ሃገር በመጡ ጥንዶች ሬቨረንድ እስቴሲ ኒኮል አና ሬቨረንድ ኢቫን ሲመንስ ሲሆኑ የዋን ኢን ክራይስት ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ የሚኒስትሪው ዳይሬክተሮች ናቸዉ።በስልጠናዉ አምባገነናዊ አመራር፣ጣልቃ የማይገባ አመራር፣የማህበራዊ እኩልነት አመራር፣ዉጣ ዉረድ የሚያበዛ አመራር እና የአሰልጣኝ አመራር በሚሉ ሃሳቦች ስልጠናዉ ተሰቷል። ኢቫንጀሊካል ቲቪ ያነጋገራቸዉ የስልጠናዉ ተካፋይ አገልጋዮች በስልጠናዉ ተጠቃሚ መሆናቸዉን ገልፀዋል።ስልጠናዉ ግንቦት 30 ቀን 2015ዓ/ም የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፦ https://youtu.be/tmelkKyRnYs
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍3
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል መሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ 500 ሚልዮን ችግኝ ለመትከል በታቀደዉ መሰረት #በአረንጓዴ_አሻራ_መርሃ_ግብር_ላይ_ተሳተፋ
ሃምሌ 10 ቀን 2015ዓ/ም የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር “በጉለሌ እጽዋት ማዕከል” ተካሒዷል።በተዘጋጀዉ መርሃ ግብር ላይ የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ጨምሮ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች የመንግስት ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች የካዉንስሉ የክላስተር አመራሮች መምህራን እና ተማሪዎች በጉለሌ የህፅዋት ማእከል በመገኘት ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ ቃል አረንጓዴ አሻራቸዉን አኑረዋል።
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/5qQ3ixHS68c
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከወንጌላዊ_ቢሊ_ግርሃም_አሶሴሽን_መሪዎች_ጋር በካዉንስሉ ዋና ፅ/ቤ #ተወያዩ
ሐምሌ 28 ቀን 2015ዓ/ም የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ከወንጌላዊ ቢሊ ግርሃም አሶሴሽን መሪዎች ጋር በኢትዮዽያ ዉስጥ ስለሚሰሯቸዉ መንፈሳዊ ስራዎች ከካዉንስሉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ ጋር እንዲሁም ከካዉንስሉ መንፈሳዊ ዘርፍ ሃላፊ ፓ/ር ስንሻት ተካ ጋር በቀጣይነት አብረዉ በሚሰሯቸዉ ስራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በዉይይታቸዉም ወንጌልን በምን አይነት ሁኔታ ለምድሪቱ እንደሚያደርሱና በአገልጋዮች እና ቤተሰቦቻቸዉ ዙሪያ ያተኮረ ትምህርት እና ስልጠና በመስጠት ዙሪያ እቅድ በመያዝ ተወያይተዋል።
ወንጌላዊ ቢሊ ግርሃም ላለፋት 70 ዓመታት ወንጌልን ያስተማሩ ለሚሊዮኖች ህይወት መለወጥ ምክኒያት የሆኑ አባት ናቸዉ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/vAIu_qV_4RY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
2
#የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል እና #ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሽፕ አብረዉ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል እና ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሽፕ ልጆችን በወንጌል በመድረስ እና ደቀመዝሙር በማድረግ በቀጣይ አብረዉ መስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ባለ ዘጠኝ አንቀፅ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2016ዓ/ም ተፈራርመዋል።
ካዉንስሉ በኢትዮዽያ ዉስጥ የሚገኙ ቤተ-እምነቶች፣ህብረቶች እና ሚኒስትሪዎች አገልግሎታቸዉን በነፃነት እንዲፈፅሙ እያስተባበረ እና ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ መንፈሳዊ ተቋም ሲሆን ቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሽፕ ልጆች ጌታ ኢየሱስን እንደግል አዳኝ አድርገዉ በመቀበል የጌታ ደቀመዝሙር በመሆን በአንድ ቤተክርስቲያን ዉስጥ ተተክለዉ እንዲፀኑ በማድረግ እየሰራ የሚገኝ መንፈሳዊ ተቋም ነዉ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/LxjvR-0KDAY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1716🔥6
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከፍተኛ_አመራሮች_በባህሬን_የካዉንስሉን_ቅርንጫፍ_ፅ/ቤት_አቋቋሙ።

የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ምክትል ፕሬዝዳንት ሐዋሪያዉ ዩሐንስ ግርማ እና የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ግንቦት 28 ቀን 2016ዓ/ም ወደ ባህሬን ያቀኑ ሲሆን በባህሬን በነበራቸዉ ቆይታ የካዉንስሉን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በማቋቋም የካዉንስሉን ስራ እንዲያስፈፅሙ በአባላት ምርጫ ተደርጎ ቦርድ ተቋቁሟል።

የካዉንስሉ አመራሮች ከተመረጡ መሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በባህሬን የኢትዮዽያ ቆንፅላ ፅ/ቤት ከአንባሳደር ሽፈራዉ ገነቴ ጋር ዉይይት ተደርጎ ወደፊት በጋራ ተቀራርቦ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

አመራሮቹ በባህሬን በነበራቸዉ ቆይታ የስልጠና እና የአምልኮ ጊዜ በዚያ ከሚገኙ ምዕመናን ጋር ያከናወኑ ሲሆን ህዝቡም ደስተኛ በመሆን እግዚያብሔርን አመስግነዋል።
የካዉንስሉ ከፍተኛ አመራር ልዑክ ቡድን በባህሬን የነበረዉን ቆይታ አጠናቀዉ ሰኔ 1 ቀን 2016ዓ/ም ወደ ኢትዮዽያ ተመልሰዋል። #ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/LxjvR-0KDAY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍8
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከኢትዮዽያ_ሃገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን_ጋር_ተወያዩ
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል መሪዎች ከኢትዮዽያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን መሪዎች ጋር ሰኔ 10 ቀን 2016ዓ/ም በካዉንስሉ ዋና ፅ/ቤት ተወያይተዋል።

በዉይይታቸዉም የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም የሰራቸዉን ስራ እና አሁን እየሰራ ስለሚገኘዉ ስራ አብራርተዋል።

ካዉንስሉ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ለሃገር መፍትሄ ይዞ ይመጣል ብሎ ስለሚያስብ እንዲሁም በቅርበት መስራት እንደሚፈልግ ታዉቆ በቂ ዉክልና እንዲሰጠዉና በየደረጃዉ ባሉ የምክክር ሂደቶች ዉስጥ ተካፋይ እንዲሆን ጥያቄ አቅርቧል።

በዚሁ መሰረት ሁለቱም አካላት ሰፊ ዉይይት አድርገዉ በቀጣይ አብሮ ለመስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/LxjvR-0KDAY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍124
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_የተሰጠ_ጋዜጣዊ_መግለጫ
በመጋቢ ጌቱ ለማ የካውንስሉ ጽ/ቤት ሃላፊ
#በኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፋቱ ማዕከል ላይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እየተወሰደ ያለውን ኢ/ህገ መንግታዊ ጥሰት ለመቃወም የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ቤተክርስቲያን የኩሪፋቱ ማዕከል በህጋዊ መንገድ ለቃለ ሐይወት ቤተክርስቲያን የተሰጠ ሰነድ ያለው ይዞታ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከቤተክርስቲያኒቱ ቦታ ላይ 40 ሺህ ካሬ ሜትር የሚሆነውን በኃይል በመቀማት ለሁለት ግለሰቦች በመስጠት ኢ.ህገ መንግስታዊ በደል ፈጽሞብናል።
ይህንን ጉደይ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ቤተክርስቲያን ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርባ ፍርድ ቤቱ ቦታው የቃለ ሕይወት ይዞታ መሆኑን ውሳኔ አስተላልፎ ባለበት ሁኔታ የከተማ አስተዳደሩ የግንባታን ሂደቱን እያስተጓጎለ ስለነበር ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ለፌዴራል መንግስት አቅርበን በከፍተኛ አመራር ደረጀ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየታየ ባለበት ሁኔታ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ የቤተክርስቲያኒቱ ይዞታ ውስት ወታደሮችንና የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችን ይዞ በመግባት ችካል በማስቀመጥ የቤተክርስቲያኒቱን ይዞታ ለግለሰቡ በማስተላለፉ ህግ ወጥ ተግባር ፈጽሞብናል ።
ይህ ሁኔታ ከባድ እና በወንጌላውያን አምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ ሐይማኖታዊ ጥላቻ ባለቸው ግለስቦቸ የተቀነባበረ መንግስት የማይወክል የግለሰቦች ፍላጎት እና በልማት ሰበብ ሕዝብን ከመንግስት ጋር ለማጣላት እና ታሪካው ቅራኔ ለመፍጠር ሆን ተብሎ እየተሰራ ያለ መሆኑን እንረዳለን ።
ዛሬ ሃምሌ 4 የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች ወደ ስፍራው፡ በሄዱበት ወቅት የማዋከብ የማሸማቀቅ እና ወደ እስር መውሰድ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል።
በመሆኑም መለው የወንጌል አማኞች በዚሀ የህልውናችን ጉዳይ ህግ መንግስታዊ መብታችንን እስከሚከበር ድረስ ለሚመለከታቸው ለክልሉ እና ለፌዴራል መንግስት አካላት ጥያቄያችንን ከማቅረብ ባሻገር ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ የምንከፍል መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።
በመሆኑም የሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት፣ከፍተኛ አመራሮችና የፌዴራል መንግስት አካላት ይህ ጉዳይ የህዝብ ሰላም በማይፈልጉ አካላት በልማት ሰበብ እየተሰራ የለውን ህግ መንግስቱን የጣሰ ስራ አንድታስቆሙልን እና አስቸኳይ ምላሸ እንዲሰጡን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍112😢2
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_በቢሾፍቱ_ኩሪፍቱ_ቃለ_ህይወት_ቤ_ክ_ጉዳይ_ሐምሌ_18_ቀን_2016ዓ_ም_ዳግመኛ_ጋዜጣዊ_መግለጫ_ሰጠ

መግለጫዉን የሰጡት የካዉንስሉ ፅ/ቤት ሃላፊ ፓ/ር ጌትነት ለማ ከመግለጫዉ በማስቀደም በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ባጋጠመዉ የመሬት መንሸራተት በደረሰዉ አደጋ ልባዊ ሃዘን በመግለፅ መፅናናትን ተመኝተዋል። በቀጣይም ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች አስፈላጊዉን እገዛ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

በመቀጠል በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘዉ የኩሪፍቱ ማዕከል ከህግ ዉጪ የቤተክርስቲያኒቱን ንብረት በሃይል መነጠቁን አስመልክቶ የፍትህ ጥያቄ ለሚመለከታቸዉ አካላት መቅረቡን በማስታወስ በዚህ መሰረት ካዉንስሉ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር
በደብዳቤ እና በአካል በመነጋገር ጉዳዩ በዉይይት እንዲፈታ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አስታዉቀዋል።

ሆኖም ለቀረቡት ጥያቄዎች ምንም አይነት ምላሽ አለመሰጠቱን እና ህግን በመጣስ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ አጥር አጥሮ ተቀምጦ ይገኛል። ስለዚህ

1-የካዉንስሉ አባል ቤተ ዕምነቶች እና ህብረቶች በሃይል የተወረረዉ መሬት እና በጊቢ ዉስጥ የታጠረዉ አጥር ፈርሶ እስከምናይ ድረስ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምፃችሁን ማሰማታችሁን እንድትቀጥሉ ጥሪ እናቀርባለን።

2-በተለያየ የመንግስት ተቋማት ላይ የምትሰሩ የህግ ባለሞያዎች እና የፍትህ አካላት ይህ ጉዳይ ፍትህ እስከሚያገኝ ድረስ ድጋፋችሁን እንድታደርጉልን እና ድምፃችሁን እንድታሰሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም የፌደራል መንግስት ላዋቀረዉ ኮሚቴ ጉዳዩን እያጣራ ምላሽ ሳይሰጥ በአቋራጭ ያደረጉት ወረራ ዘመን ተሻጋሪዋን መከራ የማይችላትን ቤተክርስቲያንን እንደተራ መቁጠር ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከትል ከመሆኑም ባሻገር ታሪካዊ ጥላቻን ጥሎ የሚያልፍ በመሆኑ የፌደራል መንግስት የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እየወሰደ ያለዉን ኢ-ህገመንግስታዊ እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያስቆም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን።

#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_በቢሾፍቱ_ኩሪፍቱ_ቃለ_ህይወት_ቤ_ክ_ጉዳይ_ሐምሌ_18_ቀን_2016ዓ_ም_ዳግመኛ_ጋዜጣዊ_መግለጫ_ሰጠ


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
🔥9👍63
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_አመራሮች_የጅማ_ከተማ_የካዉንስል_መሪዎችን_ጎበኙ

ከነሐሴ 17-19 ቀን 2016ዓ/ም በተካሄደዉ ጉብኝት የካዉንስሉ መሪዎች በጅማ እና በዞኑ ለሚገኙ 55 ለሚሆኑ የካዉንስሉ የቦርድ አባላት እና አገልጋዮች ስለ ካዉንስሉ ማንነት እና አደረጃጀት ዙሪያ መግለጫ ሰተዋል።
ከመግለጫዉ ባሻገር በልዩነት አንድነት እና የሚሲዮናዊነት አገልግሎት በሚል ርዕሶች ለመሪዎቹ የስልጠና ተሰጥቷል ።

ነሐሴ 19 ቀን 2016ዓ/ም በጅማ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ከየ አጥቢያዉ ለተወጣጡ ከ200 በላይ ለሚሆኑ አገልጋዮች እና ምዕመናን ተከታታይ የማነቃቂያ መልዕክት በመስጠት አገልጋዮችን አበረታተዋል ።

የካዉንስሉ አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓ/ር አሸብር ከተማ ጉብኝቱ የታሰበለትን አላማ እንደመታ ገልፀዉ በጅማ እና አካባቢዉ ያለዉ የወንጌል አማኝ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑን እና ባሉት ችግሮች ዙሪያ ከመሪዎች ጋር በመመካከር ወደፊት ሰፊ ስራዎችን ለመስራት መወያየታቸዉን አስታዉቋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍8🔥42
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_2017_አዲስ_ዓመትን_ከአባል _ቤተ_እምነት_ጋር_በበመማፀኛ_ከተማ_(ዩጎ)_ቤተክርስቲያን_በአንድነት_አከበሩ።

በመርሃ ግብ የአምልኮ የፀሎት እና የቃል ጊዜ እንዲሁም አዲሱን ዓመት የመባረክ ጊዜ ተከናዉኗል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_አዘጋጅነት_ወንጌል_ስርጭት_እና_ደቀመዝሙ_ማፍራት_በሚል_ርዕስ_ስልጠና_ተሰጠ

ጥቅምት 11 ቀን 2017ዓ/ም በተሰጠዉ ስልጠና ከወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ህብረት እና ከካዉንስሉ አዲስ አበባ ክላስተር የተወጣጡ መሪዎች ተካፍለዋል።

ስልጠናዉን የሰጡት የኦርጋኒክ አዉትራች ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ዳይሬክተር ፓ/ር ዋልት ቤኔት ከአሜሪካ ሆስተን ቴክሳስ የመጡ ሲሆን የስልጠናዉ አላማ እና የትኩረት አቅጣጫ ክርስቲያኖች በታላቁ ተልኮ በሚፈለገዉ መንገድ እንዲሰማሩ ማድረግ እና የኢየሱስ ተከታይ የሆኑ ደቀመዛሙርትን ማፍራት ላይ ያተኮረ ስልጠና እንደሆነ ገልፀዋል።

የካዉንስሉ የዉጪ ግንኙነት ዳይሬክተር ፓ/ር አሸብር ከተማ በወንጌል የምንደርሰዉን ሰዉ ደቀመዝሙር የማድረግ ሃላፊነታችንን እንወጣ ደቀመዝሙር የአራት ወይም የስድስት ወራት ትምህርት መስጠት ሳይሆን የእድሜ ልክ ጉዳይ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

የካዉንስሉ በምክትል ጠቅላይ ፀሃፊ ማዕረግ የመንፈሳዊ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ሃላፊ ፓ/ር ይልማ ዋቄ እንደገለፁት እንደቀድሞ በፀሎት እና ወንጌልን በመስበክ በመትጋት በአለም ላይ ከታወቁ የወንጌል ስራን ከሚሰሩ ሚኒስትሪዎች ጋር በመተባበር የወንጌል አማኝ አባሎችን በማሰልጠን እና በማስታጠቅ ላይ እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
4👍1
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከየካቲት_10_13_2017 ዓ.ም ለሁለት መቶ የሰንበት አስተማሪዎች በልጆች አገልግሎት ጉዳይ ላይ ሰጠ።
ከቢሊግራሃም እቫንጀልስቲክ አሶሴሽን እህት ድርጅት ከሆነው ሰማሪታን ፐርስ የተባለው ተቋም አንድ ዘርፍ የለው ሲሆን በዚህም ልጆችን መሰራት አድረጎ የሚሰራ ተቋም ነው።
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ከኦሲሲ ኦፕሬሽን ክሪስማስ ቻይልድ፣ ከዚህ ድርጅት ጋር በጣም በቅርበት እየሰራ ሲሆን በቅርቡ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በተለይም በጦርነት የተጎዱትን ልጆች በጥቂቱም ቢሆን ያላቸውን መጎዳት ሊቀርፍላቸው ይችላል ብለው በማመን ሁለት ኮንቴይነር የስጦታ እቃዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብቶአል፡፡
ይህንን ስጦታ አስመልክቶ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለሆኑቱ የካቲት 7 ለ52 የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የቁርስ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ በዛ ላይ ስለፕሮግራም መግለጫ ተሰቶዋል፡፡
ከየካቲት 10_ 13 በአጠቃላይ ለሁለት መቶ የሰንበት አስተማሪዎች በልጆች አገልግሎት ጉዳይ ላይ ከዚህ ተቋም ከዩጋንዳ ፣ከኬንያ እና ከብሩንዲ የመጡ አሰልጠኞች ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
እነዚህ ስልጠናዎች በጉዲና ቱምሳ፣ በሀያት የጉባዔ እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያንና ፣በኮልፌ መካነ ኢየሱስ ተሰቶዋል፡፡ አጠቃላይ በዚህ ስልጠና ሁለት መቶ ያህል የሰንበት አስተማሪዎች ከመቶ ዘጠና አከባቢ የመጡ የሰንበት አስተማሪዎች ስልጠናውን መካፈል ችለዋል፡፡
4👍3🙏1