የ|#ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ ኮሚዩኒቲ በዶሃ የእርቅ ፕሮግራም ተካሂዷል።
በኳታር ዶሃ የሚኖሩ የ|#ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ ኮሚዩኒቲ አባላት በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን እርቅና ሰላም ምክንያት በማድረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታውን የሚያጠናክሩበት የጋራ ስብሰባ አካሄዱ፡፡
በኳታር የኢፌዲሪ አምባሳደር መታሰቢያ ታደሰ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ ሲሆን፤ በወጭ ሀገር የሚኖሩ ዳያስፖራዎች በሁለቱ ሀገራት የተጀመረውን የእርቅ ሂደት የበለጠ ለማጠናከር የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው ብለዋል።
እርቁ ለአፍሪካ ቀንድ ክልል ያለው ፋይዳ በአርአያነት የሚጠቀስ ነው ሲሉ አምባሳደር መታሰቢያ አክለው ተናግረዋል፡፡
በኳታር የኤርትራ አምባሳደር አሊ ኢብራሂም አህመድ በበኩላቸው የተፈጠረው ሰላም እና እርቅ ሁለቱ ህዝቦች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፍ ላይ መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው እንዲሁም ለቀጠናው በሙሉ ትልቅ እድል የሚፈጥር እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ.ም.
@YeneTube @Fikerassefa

#ኤርትራ ወደብ ልትገነባ ነው⬇
ኤርትራ ተጨማሪ ወደብ ልትገነባ መሆኑን ተገለጸ።
ኤርትራ በኢትዮጵያ እያደገ ያለውን ኢንቨስትመንት ማስተናገድ እንዲያስችላት ተጨማሪ ወደብ ልትገነባ መሆኑን ብሉምበርግ አስነብቧል።
በኤርትራ በኢነርጂና ማዕድን ሚኒስቴር የማዕድን ዳይሬክተር አለም ክብረኣብ ኤርትራ በቀይ ባህር ላይ የምትገነባው ወደብ በተለይ በኢትዮጵያ የሚመረተውን የፖታሽ ማዕድን ወደ ፣ ጁቡቲ እና ሶማሌላንድ ማጓጓዝ እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
ሶማሊያወደቡ በሚለማበት አከባቢ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን የፖታሽ ማዕድን ክምችት መኖሩን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። የወደቡ ግንባታ በአምስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ወደቡ የሁለቱን አገራት የፖታሽ ማዕድን ለማጓጓዝ አዋጭ ፕሮጀክት መሆኑም ተገልጿል።
ኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላም ስምምነት ከፈረሙ በኋላ በቀጠናው በጋራ የመልማት አዝማሚያ እያደገ መሆኑን የብሉምበርግ ዘገባ አመልክቷል።
©ETV
@Yenetube @Fikerassefa

#በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በነገው ዕለት በይፋ ስራ ይጀምራል::
#የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት #ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ኤምባሲውን መርቀው #የሚከፍቱት ይሆናል።
በአየርላንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር የሆኑት አቶ #ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል።
#ኤርትራ በኢትዮጵያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መክፈቷ ይታወሳል።
ባለፈው ሃምሌ ወር የተከፈተው የኤርትራ #ኤምባሲ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
©fbc
@YeneTube @mycase27

#Ertirea #ኤርትራ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የካሳ ጥያቄ አቀረበች👇🏼👇🏼
ኤርትራ ለዓመታት በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት ላጋጠማት ችግር የተባበሩት
መንግሥት ድርጅት ካሳ እንዲከፍላት ጠየቀች።
የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ዑስማን ሳልሕ በ73ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መደበኛ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ሃገራቸው በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዳጋጠማትና ለዚህም ካሳ እንደሚገባት ገልፀዋል።
በ2009 ላይ የተጣለው የመሳርያ ግዢ ማዕቀብ ላለፉት 9 ዓመታት በመፅናቱ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ችግር እንዳስከተለም አስረድተዋል።
"የኤርትራ ህዝብ ማዕቀቡ እንዲነሳለት ብቻ ሳይሆን ለደረሰበት ውድቀትና ለከሰራቸው ዕድሎች ነው ካሳ እየጠየቀ ያለው" ያሉት ሚንስትሩ ካሳውም በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ለተጀመረው የሰላም ጉዞ የሁለትዮሽ ጥቅሞች እንደሚውል ተናግረዋል።
ሚንስትሩ "ሕጋዊ ያልሆነ" በማለት የገለፁት በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዳይነሳ የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሃገራት እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከኢትዮጵያ ጋር የነበረው አለመግባባት ዓለም-ዓቀፍ ተቀባይነት ባለው የሰላም ውል መሰረት በተፈታበት በአሁኑ ጊዜ ማዕቀቡ እንዲቀጥል የተፈለገበት ምክንያት ግልፅ አለመሆኑን በመጥቀስ ማዕቀቡ ተነስቶ የኤርትራ ህዝብ ካሳ እንዲከፈለው በማለት ጠይቀዋል።
@BBC

ኢትዮጵያ በከፍተኛ የ#ውጭ ምንዛሬ ወደ ሐገር ቤት የምታስገባውን ነዳጅ የበዙ የ#ኤርትራ መኪኖች ድንበር እያቋረጡ እየቀዱ ይወጣሉ ተብሏል፡፡
©SHEGER FM 102.1 RADIO
@YeneTube @Fikerassefa
©SHEGER FM 102.1 RADIO
@YeneTube @Fikerassefa
#ኤርትራ
የኮሮና ተሕዋሲ በኤርትራ እስር ቤቶች ሊያደርስ የሚችለውን ቀውስ ለመከላከል የአገሪቱ ባለሥልጣናት ሰብዓዊነት ተሰምቷቸው እስረኞችን እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።
ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ትናንት 23ኛ የልደት በዓሏን በእስር ያከበረችው ሲሐም አሊ አሕመድን ጨምሮ ንፅህናቸው ባልተጠበቀ እስር ቤቶች የታሰሩ በርካታ ኤርትራውያን በኮሮና የመያዝ ሥጋት አለባቸው ብሏል።
የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር እንዳለው በአገሪቱ እስካሁን 22 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል።
በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴፕሮሴ ሙቼና «እንደ ሲሐም አሊ መብቶቻቸውን ተግባራዊ በማድረጋቸው የታሰሩ ዜጎችን የኤርትራ ባለሥልጣናት እንዲፈቱ የሚወተውቱ እጅግ የተጨነቁ ቤተሰቦች እና የለውጥ አራማጆችን ተቀላቅለናል» ብለዋል።
«የተጨናነቁ እና ንፅህናቸው ያልተጠበቀ የኤርትራ እስር ቤቶች ሲሐም እና ሌሎች እስረኞች በኮሮና የመያዝ ዕድላቸውን ከፍተኛ ያደርጉታል፤ ጤና እና ሕይወታቸው አደጋ ላይ ይወድቃል» ያሉት ዴፕሮሴ ሙቼና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የታሰሩ፤ ዕድሜያቸው የገፋ እና የጤና ዕክል ያለባቸውን በመልቀቅ በእስር ቤቶች ያሉ ታሳሪዎችን ቁጥር እንዲቀንሱ ጠይቀዋል።
የኮሮና ምርመራ እና ሕክምናን ጨምሮ እስረኞች እንደ ሌላው ዜጋ ሁሉ ተመሳሳይ የጤና አገልግሎት ማግኘታቸውን የኤርትራ ባለሥልጣናት እንዲያረጋግጡ አምነስቲ ጥሪ አቅርቧል።
የኮሮና ወረርሽኝ በመላው ዓለም ሲበረታ ኢትዮጵያ፣ አሜሪካ እና ሕንድን ጨምሮ በርካታ አገራት በሺሕዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ለቀዋል።
Via:- DW

#በዓለማችን በኮሮና ከተጠቁ ሰዎች ውስጥ ከ723 ሺህ በላይ ዜጎች ድነዋል፡፡
በአለም ዙርያ ይሄንን ዜና እስካጠናቀርንበት ሰአት ድረስ 2 ሚሊዮን 646 ሺህ 428 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 723 ሺህ 713 ያህሉ ሲያገግሙ 184 ሺህ 353 ያህሉ ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡
በህመሙ ከተጠቁት ውስጥ 1 ሚሊዮን 600 ሺህ 140 ያህሉ በደህና ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ 58 ሺህ 222 ሰዎች ህመሙ ፀንቶባቸው በፅኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ ናቸው፡፡
- በኮሮና ተጠቂ ብዛት #አሜሪካ አንደኛ ስትሆን ከሁለተኛ እስከ ሰባተኛ ያሉት የአውሮፓ ሀገራት ናቸው፡፡
- #አሜሪካ በኮሮና ከተጠቁባት 849 ሺህ 92 ሰዎች መካከል 84 ሺህ 50 ያህሉ ሲድኑ 47 ሺህ 681 ደግሞ ሞቶባታል፡፡
- #ስፔን_ጣልያንና_ኢራን በቅደም ተከተል ብዙ ዜጎቻቸውን በሞት ያጡ አገራት ናቸው።
የወረርሽኙ መነሻ የሆነችው ቻይና 82 ሺህ 798 ተጠቂ አስመዝግባ 77 ሺህ 207 ሰዎች ሲድኑ ከ4 ሺህ በላይ ያህሉ ደግሞ ሞተዋል፡፡
- ወደ ደበቡ አሜሪካ ስናቀና በኮሮና ተጠቂ ብዛት #ብራዚል ትቀድማለች፤ 46 ሺህ 182 ተጠቅተው 25 ሺህ 318 አገግመው 2 ሺህ 924 ሞተውባታል፡፡
- የመካከለኛው ምስራቅ ሀያል ሀገር እስራኤል 14 ሺህ 592 ተጠቂ አስመዝግባ 5 ሺህ 334 አገግመው 2 ሰው ብቻ ሞተውባታል።
- #ሳውዲ_አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ከ20 ሺህ በላይ ዜጎች በቫይረሱ ሲጠቁ ከ150 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
- #በአውስትራሊያ 6 ሺህ 660 ሰው በኮሮና ተይዞ 75 ሰዎች ሞተዋል፡፡
- #ከአፍሪቃ በተጠቂዎች ብዛት ቀዳሚ የሆነችው አገር ደግሞ #ግብፅ ነች፤3 ሺህ 659 ተጠቂ አስመዝግባ 935 ያህሉ ሲያገግሙ 276 ያህል ሰዎች ሞተውባታል፡፡
- #ደቡብ_አፍሪካም ከግብፅ ጋር ተቀራራቢ ያህል ሰው ነው በኮሮና የተጠቃባት፤ 3 ሺህ 635 ሰው ተጠቅቷል፡፡ 1 ሺህ 55 ሰው ሲያገግም 65 ሰው ደግሞ ሞቷል፡፡
- ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት #ጅቡቲ ብዙ ሰው በኮሮና የተያዘባት ሀገር ነች፡፡ 974 ሰው ተይዞ 183 አገግሞ 2 ደግሞ ሞቷል፡፡
- #ኬንያ 303 ተጠቂ አስመዝግባ 83 አገግመውላታል 14 ሰዎች ደግሞ ሞተውባታል፡፡ #ሶማሊያ 286 ሰዎች ተጠቅተው 4 አገግመው 8 ደግሞ ሞተዋል፡፡
- #ኤርትራ 39 ሰው ተጠቅቶ 6ቱ ሲያገግሙ እስካሁን የሞተ ሰው የለም፡፡
- ሀገራችን #ኢትዮጵያ 116 የኮሮና ተጠቂ ስታስመዘግብ 21 ሰዎች አገግመው 3 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡
Via:- Ethio FM // ጆንሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ ድረገጽ
@Yenetube @Fikerassef

የ #ኤርትራ ሠራዊት በ #ትግራይ ክልል ጉሎምካዳ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጽመው አፈና ተባብሶ ቀጥሏል ተባለ
የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጉሎምካዳ ወረዳ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ አፈና መፈጸሙን አባብሶ ቀጥሏል ሲሉ የተጎጂ ቤተሰቦች አስታወቁ።
"የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ባለመመለሱ ለአፈናና ለከፋ የጸጥታ ስጋት ተጋለጠናል” ሲሉ በወረዳዋ የሚገኙ የተለያዩ ቀበሌ ነዋሪዎች መናገራቸውን ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
“የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ ባለመደረጉ፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ባለመመለሱ፣ በርካታ የክልሉ አከባቢዎች በወራሪዎች እጅ የሚገኝ መሆኑ ለአፈናና ለጸጥታ ስጋት ተጋልጠናል” ሲሉ በጉሎ መቅዳ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ጣቢያ ነዋሪዎች ተናግረዋል ብሏል ዘገባው።
ተጎጂዎቹ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እና የትግራይን ግዛታዊ አንድነት እንዲመልስ መጠየቃቸውንም ተገልጿል።
“የኤርትራ ሠራዊት ተቆጣጥሯቸው ከሚገኙ የጉሎመካዳ ወረዳ ጣቢያዎች ውስጥ ነዋሪዎችን በየጊዜው እያፈና እየወሰደ ይገኛል” ሲሉ የጉሎ መቅዳ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነብዩ ስዩም መግለጻቸውንም ዘገባው አካቷል።
Via Addis Standard

👍17❤3