YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#Ertirea #ኤርትራ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የካሳ ጥያቄ አቀረበች👇🏼👇🏼

ኤርትራ ለዓመታት በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት ላጋጠማት ችግር የተባበሩት
መንግሥት ድርጅት ካሳ እንዲከፍላት ጠየቀች።

የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ዑስማን ሳልሕ በ73ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መደበኛ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ሃገራቸው በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንዳጋጠማትና ለዚህም ካሳ እንደሚገባት ገልፀዋል።

በ2009 ላይ የተጣለው የመሳርያ ግዢ ማዕቀብ ላለፉት 9 ዓመታት በመፅናቱ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ችግር እንዳስከተለም አስረድተዋል።

"የኤርትራ ህዝብ ማዕቀቡ እንዲነሳለት ብቻ ሳይሆን ለደረሰበት ውድቀትና ለከሰራቸው ዕድሎች ነው ካሳ እየጠየቀ ያለው" ያሉት ሚንስትሩ ካሳውም በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ለተጀመረው የሰላም ጉዞ የሁለትዮሽ ጥቅሞች እንደሚውል ተናግረዋል።

ሚንስትሩ "ሕጋዊ ያልሆነ" በማለት የገለፁት በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዳይነሳ የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሃገራት እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከኢትዮጵያ ጋር የነበረው አለመግባባት ዓለም-ዓቀፍ ተቀባይነት ባለው የሰላም ውል መሰረት በተፈታበት በአሁኑ ጊዜ ማዕቀቡ እንዲቀጥል የተፈለገበት ምክንያት ግልፅ አለመሆኑን በመጥቀስ ማዕቀቡ ተነስቶ የኤርትራ ህዝብ ካሳ እንዲከፈለው በማለት ጠይቀዋል።

@BBC
@YeneTube @Fikerassefa