YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በነገው ዕለት በይፋ ስራ ይጀምራል::

#የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት #ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ኤምባሲውን መርቀው #የሚከፍቱት ይሆናል።

በአየርላንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር የሆኑት አቶ #ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል።

#ኤርትራ በኢትዮጵያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መክፈቷ ይታወሳል።

ባለፈው ሃምሌ ወር የተከፈተው የኤርትራ #ኤምባሲ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

©fbc
@YeneTube @mycase27
#የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እየወሰዱት ያለው እርምጃ የኢትዮጵያን ፓለቲካ ምህዳር እያሰፋ መሆኑንና ለዚህም አድናቆት እንደሚገባቸው በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሀላፊ ቲቦር ናገይ አስታወቁ።

ዲፕሎማቱ የ42 ዓመቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ወደ ሀላፊነት ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስኬቶችን እንዳስመዘገቡ ገልፀዋል።
©fbc
@yenetube @mycase27