YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ትግራይ የትግራይ ክልል ፖሊስ 75 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ 425 ተቀጣጣይ ፈንጂዎችንን ወደ መቀለ ከተማ ለማስገባት ሲሞከር መያዙን አስታወቀ። ተቀጣጣይ ነገሩ የተያዘው በራያ አዘቦ ወረዳ መሆኒ ከተማ አቅራቢያ መሆኑ ተገልጿል።

©Live Update
@YeneTube @Fikerassefa
በኦሮሚያ ክልል፣ ኢሉአባቦራ ዞን የሚኖሩ የ|#ትግራይ ብሔር ተወላጆች ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ለቢቢሲ ትግርኛ ተናግረዋል።

@YeneTube #Fikerassefa
በ|#ትግራይ_ክልል ደቡባዊ ዞን ኮረም ከተማ በትናንትናው ምሽት አንድ ግለሰብ በአካባቢው የፀጥታ ሀላፊ መገደሉን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት በከተማው ግጭት ተፈጥሮ ነበር።

ለሟች ፍትሕ የጠየቁ የከተማዋ ነዋሪዎች መንገዶችን በድንጋይና በተቀጣጣይ ጎማወች ሲዘጉ ተስተውሏል።

@YeneTube @Fikerassefa
አማራና ኦሮሚያ የሚባሉ ክልሎችን የፈጠረው ኢህአዴግ ነው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

ከማንነት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማፍረስ የሚደረግ ሙከራ ነው ሲሉም የህወሃት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ከድምጸ ወያኔ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ እንደገለጹት የወልቃይትና ራያ የማንነት ጥያቄዎች የቀድሞውን የጠቅላይ ግዛት መዋቅር ለመመለስ የሚደርግ እንቅስቃሴ ነው ።
በሌላ በኩል የማንነት ጥያቄን በተመለከተ በአፈጉባዔዋ የተሰጠውን መግለጫ አዛብቶ አቅርቧል በማለት ፌዴሬሽን ምክር ቤት የአማራ መገናኛ ብዙሃንን ወቅሷል።

የአማራ መገናኛ ብዙሃን የመግለጫውን ያልተቆራረጠ ቪዲዮ ሙሉውን ለህዝብ እንደሚለቅ አስታውቋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ አማራ ክልል ይካለሉ እያሉ አካባቢዎችን እየጠቀሱ የሚጠይቁትን ጂኦግራፊ ምን እንደሆነ ያማያውቁ ናቸው ሲሉ ነው ለድምጸ ወያኔ በሰጡት ቃለመጠይቅ።

ባህርዳርና ጎንደር ላይ ሆነው ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ፣ ራያ አዘቦ የእኛ ነው ብለው የሚጮሁና ሰልፍ የሚወጡ ሰዎች የቀድሞውን ጠቅላይ ግዛት ለመመለስ የሚፈልጉ ናቸው ያሉት አቶ ጌታቸው አማራ ክልልን የፈጠረው ኢህአዴግ፣ አማራ የሚባል ክልል አልነበረም ሲሉ ገልጸዋል።

ወልቃይት፣ ራያም ሆነ ሌላ አካባቢ ወደ አማራ ክልል ይመለስ የሚለው ጥያቄ ህገመንግስቱን የሚያፍርስ እንደሆነም አቶ ጌታቸው በቃለመጠይቁ ላይ አንስተዋል።

‘’የህዝብ ፍላጎትን ግምት ውስጥ ያላስገባ ግዛታችን የሚል ጥያቄ በታሪክም በህግም አያስኬድም።

በኢትዮጵያ ታሪክ አማራ የሚባል ክልል አልነበረም፣ ኦሮሞ የሚባል አልነበረም፣ ትግራይ የሚባል ክልል አልነበረም።
ምናልባት ትግራይ ለረዥም ግዜ የነበረው ግዛት በተወሰነ መልኩ ተቀራራቢ ነው ማለት ይቻላል።

የትግራይ ክፍለ ሃገር በታሪክም ትግራይ የሚባል የሚታወቅ ክፍል አለ። በታሪክ አማራ የሚባል ክልል ግን አልነበረም፣ አማራ ጠቅላይ ግዛት የሚባልም አልነበረም። በታሪክ አማራ የሚባል አካባቢ አልነበረም።
ኦሮሞ የሚባል ክልል በፊት አልነበረም፣ ኦሮሚያ የሚባል ክልል የኢህአዲግ ህገ መንግስት የፈጠረው ነው። ብለዋል የህወሀቱ አቶ ጌታቸው ረዳ።

አቶ ጌታቸው የህዝብ ፍላጎትን ከግምት ያላስገባ ሲሉ #ወልቃይትና ራያዎች በየትኛው ህዝበ ውሳኔ ወደ #ትግራይ ክልል እንደተጠቃለሉ የሚገልጽ ማብራሪያ ግን አላቀረቡም።

በትግርኛ ቋንቋ ለድምጸ ወያኔ ቃለመጠይቅ የሰጡት አቶ ጌታቸው ረዳ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወሎ ክፍለሀገር እንደተፈተኑ የገለጹ ሲሆን እሳቸው ፈተናውን የወሰዱበት አከባቢ አሁን #በትግራይ ክልል ውስጥ መጠቃለሉን አለመረዳታቸው #አስገራሚ እንደሆነባቸው ነው ቃለመጥይቁን የተከታተሉ ወገኖች የሚገልጹት።

አቶ ጌታቸው በማንነት ዙሪያ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ህገመንግስቱን የሚያፈርስ በመሆኑ እንደህወሀትና ኢህ አዴግ ልናወግዘው ይገባልም ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደሬሽን ምክር ቤት የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ በአፈጉባዔዋ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ያቀረበው ዘገባ የተዛባ ነው ሲል ቅሬታውን ማቅረቡ ታወቀ።

ፌደሬሽን ምክር ቤት በደብዳቤው እንደገለጸው አፈጉባዔ ወይዘሮ #ኬሪያ መሃመድ የማንነት ጥያቄን በተመለከተ አጠቃላይ በሆነ መልኩ የሰጡትን ማብራሪያ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ባልደረባ በሚመቸው መልኩ አዛብቶ አቅርቧል ሲል ከሷል።

የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ወዲያውኑ ምላሽ የሰጠ ሲሆን በቀረበው ዘገባ የህግም ሆነ የጋዜጠኝነት ስነምግባር ጥሰት #የሌለው ነው ብሏል።

©የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን
@YeneTube @Fikerassefa
#ትግራይ

በትግራይ ክልል በአይነቱ ልዩ የሆነ ነዳጅ መኖሩ በጥናት መረጋገጡን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።

ዶክተር ደብረፂዮን ይህንን ያሉት በዛሬው ዕለት በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚገኘው ኬይ ፒ አር የተሰኘውን የህንድ ኩባንያ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ነው።

ኩባንያው በ2 ነጥብ 5 ሚሊየን መነሻ ካፒታል በኢንዱስትሪ ፓርኩ በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርት የተሰማራ ነው።

እስካሁንም በሁለት ዙር ብቻ ከ200 ሺህ በላይ አልባሳትን ወደ ውጪ የላከ ሲሆን፥ ከ700 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶችም የስራ እድል መፍጠሩ ተገልጿል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ የተገኙት ዶክተር ደብረጺዮን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፥ ኩባንያው ሀገሪቱ ለያዘችው የኢንዱስትሪ ሽግግር የጎላ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ጠቁመዋል።

ዶክተር ደብረጺዮን አያይዘውም፥ በትግራይ ክልል እምባ አላጀ፣ ነበለት እና  ዓዲ-ግራት ባሉት ተራራማ አካባቢዎች በአይነቱ ልዩ የሆነ ነዳጅ መኖሩ በጥናት ተረጋግጧል ብለዋል።

ይህም በአካባቢው የሚገኙ ድንጋይና አለቶችን ሰባብሮ በማቅለጥ የሚገኝ መሆኑን ነው የተናገሩት።

የተፈጥሮ ሃብቱን ጥቅም ላይ ለማዋልም ግዙፍ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ መሆኑን ነው የጠቁሙት።

ስለሆነም በቀጣይ አቅም ያላቸው አለም አቀፋዊ ኩባንያዎችና ባለሃብቶችን በዘርፉ በማሰማራት የተፈጥሮ ሃብቱ ጥቅም ላይ  እንዲውል ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል ።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ዶክተር ደብረጺዮንን ጨምሮ የዓለም አቀፍ የንግድ ዳይሬክተር  እና ሌሎች ተጋባዥ አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

ምንጭ:- FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሲኖዶሱ ምልኣተጉባኤ እንኳ ሳያሟላ በሲኖዶስ ስም ለውሳኔ መቻኮል አግባብነት የለውም ብሏል የኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ፡፡

ከኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ ጋር በስፋት በቀጣይነት መወያየት ኣለብን፤ በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ አንሰጥም ያሉ የሲኖዶስ አባላት ስብሰባውን #ለቀው_እንደወጡ ምንጮች ኣረጋግጧል፡፡

የሲኖዶሱን ስብሰባ ትተው ከወጡት መካከል #የሰሜን_ሸዋ_ደብረብርሃንሀገረስብከት ልቀጳጳስ አቡና #ቄሌሜንጦስ#የአርሲ ሀገረስብከት ልቀጳጳስና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ #አቡነ_ያሬድ፤ የደቡባዊ #ትግራይ መህጮህ ሀገረስብከት ልቀጳጳስ አቡነ ዲዎስቆሮስ፤ የኢሉ አባቦር ሀገረስብከት ልቀጳጳስ አቡነ ሚካኤል ይገኙበታል ተብሏል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ብዙ የሲኖዶስ አባላት ስብሰባው ላይ እንዳልተገኙ ነው ምንጮች የገለፁት፡፡የቦረና ዞን ሀገረስብከት ልቀጳጳስ አቡነ ዜና ማርቆስ፤ የደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን ሀገረስብከት አቡነ ሳዊሮስና ብዙ የሲኖዶሱ አባላት ከሀገር ውስጥም ከውጭ ሀገርም አልተሳተፉም ተብሏል፡፡

Via OMN
@YeneTube @FikerAssefa
#ትግራይ_ክልል

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ቆራሪት በተባለች ከተማ ነዋሪዎች ተቃውሞ ሰልፍ በማካሄዳቸው ሰዎች እያተሰሩ ነው ተባለ። በዚህ ሁለት ቀን ከ150 በላይ ሰዎች መታሰራቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የከተማው አስተዳደር በበኩሉ ታስረዋል ተብሎ የተገለፀው ቁጥር የተጋነነ ነው፤ የህዝብ ሰላም ለማወክ የሚሰሩ ሰዎች በመለየት ህጋዊ የእርምት እርምጃ እየወሰድን ነው በማለት አሳውቋል።

Via:- VOA
@Yenetube @Fikerassefa
#ትግራይ

ትግራይ ክልል ውስጥ በ5 መጠለያ ጣቢያዎች ከ900 በላይ ሰዎች ከምግብ እጦት እና ከመድሃኒት እጥረት ጋር በተያየዝ ሞተዋል ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል።

የተቋሙ የመቐለ ቅርንጫፍ ፤ ረሃብ የሰው ህይወት መንጠቅ ከጀመረ ወራቶች መቆጠሩንም ገልጿል።
* በሽረ
* አክሱም
* በአብይአዲ
* በመቐለ
* ዓዲግራት ባሉ መጠለያ ጣቢያዎች የሰው ህይወት በረሃብ እና በመድሃኒት እጥረት እያለፈ መሆኑን የሚገልጸው ተቋሙ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ምንም እርዳታ ያላገኘ ተፈናቃይ መኖሩንም አሳውቋል።

የዕንባ ጠባቂ ተቋም የመቐለ ቅርንጫፍ ፤ ከህዳር በፊት ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነበር ግን መንግሥት እርምጃ ባለመውሰዱ የከፋ ችግር ደርሷል ብሏል።

በሽረ የተፈናቃዮች ጣቢያ ፤ 309 አረጋዊያን እና 118 ህፃናት የሚገኙበት 849 ሰዎች ሞተዋል ይህ ሁሉ ሰው በአንድ IDP የሞተው በረሃብ እና በመድሃኒት እጦት ነው ሲል አሳውቋል።

በአክሱም 93 ሰዎች፣ በአብይአዲ 35 ሰዎች፣ በአይደር 4 ሰዎች፣ በሞሞና 2 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንም ተቋሙ አደረኩት ባለው ክትትል ማረጋገጡን ገልጿል።

በአጠቃላይ ክትትል በተደረገባቸው መጠለያዎች 980 ሰዎች ላይ ሞት ማጋጠሙን አክሏል።

ከመጠለያ ጣቢያ ውጭም ያሉ በርካታ ዜጎችም በድርቅ ምክንያት እየተሰቃዩና በተከሰተው የምግብ እጥረት ህይወት እየጠፋ ነው ብሏል።

ፅ/ቤቱ በረሃብ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርት አቋርጠው እንዲሰደዱ ፣ ከ600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ለመራው ጫፍ ላይ ደርሰዋል ሲል ይፋ አድርጓል።

" አሁንም በርካታ ትምህርት ቤቶች በተፈናቃዮች ተሞልተዋል   እዛ ያሉ ተማሪዎችም ድንኳን ሰርተው ለመማር ተገደዋል " ብሏል።

ምንም እኳን የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ረሃብ አልተከሰትም ቢልም የህዝብ ዕንባ ጠባቂ የመቐለ ቅርንጫፍ ረሃብ መከሰቱን አረጋጫለሁ ብሏል። በፌዴራልም ይሁን በክልል እየተሰጠ ያለው ትኩረትና ድጋፍም የሞተ በመሆኑ በቀጣይ አደጋው የከፋ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል። ህዝቡ ቀጣይ ክረምት አምርቶ እራሱን እስኪመግብ እርዳታ ማግኘት አለበትም ብሏል።

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ባለሃብቶች፣ድጋፍ አድራጊ ተቋማት፣ አቅም ያላቸው ክልሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ በድርቅ ምክንያት ረሃብ አንዣቧል ፌዴራል መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የህግና የሞራል ግዴታቸውን ይወጡ ማለቱ ይታወሳል።

የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ደግሞ በትግራይ ረሃብ ስለመከሰቱ አለመከሰቱ በመዘኛ መስፈርቶች መዝኖ መናገር የሚችለው የፌዴራል መንግሥት ተቋም ነው "ረሃብ የሚባለው ሀሰት ነው" ማለቱ አይዘነጋም።

ከቀናት በፊት ደግሞ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፤ 'ድርቁ ወደ ረሃብ እየተቀየረ ነው' የሚለው ሃሳብ የተሳሳተ ድምዳሜ መሆኑን በማስረዳት ሠብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም በመቻልና የልማት ስራዎችን በማስፋፋት፣ ትርፍ አምራች ለመሆን ይሰራል ብሏል።

በተጨማሪ ከሳምንታት በፊት ኮሚሽኑ በሰጠው ቃል በረሃብ ምክንያት የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ማረጋገጫ እንደሌለው አሳውቆ ነበር።

የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የሀገሪቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት የሚፈቅድ እንዳልሆነም ነው የገለፀው።

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ከድርቅ ጋር ተያይዞ በክልልና በፌዴራል መንግሥት መካከል አለመግባባት እንዳለ ጠቁመው፤ በድርቅ ምክንያት ስለደረሰ ጉዳት ቁጥጥር እንዳካሄዱና በቅርብ እውነቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

Via Sheger Radio
@Yenetube @Fikeryassefa
😭21👍191
#ህወሓት በ50 አመታት ታሪኬ አጋጥሞኝ የማያውቅ ፈተና ውስጥ ነኝ አለ፣ በቀጣይ ሳምንታት የፓርቲ ጉባኤየን ለማካሄድ ወስኛለሁ ብሏል

በሰሞኑ የፓርቲው ስብሰባ ወቅት ስብሰባ ረግጠው የወጡ ከፍተኛ አመራሮች ጭምር አሉ ተብሏል

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት #ትግራይ (ህወሓት) ለ11 ቀናት ሳካሂደው የነበረው የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ስብሰባ እና ግምገማ አጠናቅቂያለሁ ሲል ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ሳካሂደው የሰነበትኩት በፓርቲው አመራራ ላይ ያተኮረ የ11 ቀናት ስብሰባ እና ግምገማ “ፓርቲውን ከመበታተን ሊታደግ የሚችል ጉባኤ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታዎችን የፈጠረ ነው” ብሏል።

በያዝነው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ባሉት ቀጣይ ጥቂት ሳምንታት የፓርቲ ጉባኤ ይካሄዳል ሲል የገለጸው የህወሓት መግለጫ “ብሔራዊ ህልውናችንን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተልኳችን ነው” ሲል አስታውቋል።

አሁን “በፓርቲው የማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ያጋጠመው ችግር ድርጅቱ ከተመሰረተ ጀምሮ ባሉት 50 አመታት አጋጥሞኝ አያውቅም” ያለው ህወሓት ዋነኛ የለየኋቸው ችግሮቼ “ቡድንተኝነት፣ ፀረ ዲሞክራሲያዊነት፣ ጎጠኝነት እና ሙስና ወደ ላቀ ደረጃ አድጎ ፓርቲውን አላፈናፍን ከማለት ባለፈ የመፈራረስ አደጋ ደቅነውብኝ ነበር” ብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁30👍26🔥1
#ኤርትራ ሠራዊት በ #ትግራይ ክልል ጉሎምካዳ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጽመው አፈና ተባብሶ ቀጥሏል ተባለ

የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ክልል ጉሎምካዳ ወረዳ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ አፈና መፈጸሙን አባብሶ ቀጥሏል ሲሉ የተጎጂ ቤተሰቦች አስታወቁ።

"የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ባለመመለሱ ለአፈናና ለከፋ የጸጥታ ስጋት ተጋለጠናል” ሲሉ በወረዳዋ የሚገኙ የተለያዩ ቀበሌ ነዋሪዎች መናገራቸውን ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

“የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ ባለመደረጉ፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ባለመመለሱ፣ በርካታ የክልሉ አከባቢዎች በወራሪዎች እጅ የሚገኝ መሆኑ ለአፈናና ለጸጥታ ስጋት ተጋልጠናል” ሲሉ በጉሎ መቅዳ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ጣቢያ ነዋሪዎች ተናግረዋል ብሏል ዘገባው።

ተጎጂዎቹ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እና የትግራይን ግዛታዊ አንድነት እንዲመልስ መጠየቃቸውንም ተገልጿል።

“የኤርትራ ሠራዊት ተቆጣጥሯቸው ከሚገኙ የጉሎመካዳ ወረዳ ጣቢያዎች ውስጥ ነዋሪዎችን በየጊዜው እያፈና እየወሰደ ይገኛል” ሲሉ የጉሎ መቅዳ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነብዩ ስዩም መግለጻቸውንም ዘገባው አካቷል።

Via Addis Standard
@Yenetube @Fikerassefa
👍173
ህወሓትን በመቃወም የትጥቅ ትግል ውስጥ የገቡት ብርጋዴር ጄነራል ገብረእግዚአብሄር በየነ፤ በ #አፋር እና በ #ትግራይ ክልሎች ውስጥ “አራት ክፍለ ጦር” ያለው የራሳቸውን ሠራዊት ማደራጀታቸውን ተናገሩ።

#ከትግራይ ኃይሎች በመለየት የራሳቸውን ሠራዊት እየገነቡ መሆናቸውን የጠቀሱት ብርጋዴር ጄነራል ገብረእግዚአብሄር፤ "አዲስ ነገር ለመፍጠር" ወደ በረሃ መውደረዳቸውን እና "ከፓርቲ ነጻ የሆነ ኃይል ለመፍጠር፣... ፓርቲ የማያዝዘው ሠራዊት ለመፍጠር" እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገልፀዋል።

ጄነራሉ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ከትግራይ ሠራዊት አመራሮች ጋር የተለያዩት ከጥር 15/20017 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑን አስረድተዋል።

የትግራይ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጥር 15 ተሰብስበው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውን ጊዜያዊ አስተዳደር ሲያወግዙ፣ ተቃውመው ስብሰባውን ረግጠው ከወጡ አመራሮች መካከል አንዱ ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ ናቸው።

ይህንንም ተከትሎ የሠራዊቱ አመራሮች ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነን እና ሌሎች የሠራዊቱን ውሳኔ የተቃወሙትን ማገዳቸው ይታወሳል።

ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር "ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ ማህተም የሚነጥቅ፣ ከፓርቲ ጋር ተጣብቆ የሚሾም እና የሚሽር ኃይል ለወጣቱ ትውልድ ትተን መሄድ አንፈልግም። ወገንተኛ ያልሆነ ፍትሃዊ ኃይል ለመፍጠር እንጂ፣ የሆነ ፓርቲ አሽከርነት የለንም፤ አናደርገውም" ብለዋል።

ለተቃውሟቸው ጠመንጃ ማንሳትን መምረጣቸው በጦርነት ውስጥ የቆየውን የትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግጭት አዙሪት አይከተውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ጄነራሉ "እኔ ኢንተርናሽናል ጄነራል ነኝ። ይህንን ሆኜ የህወሓት ሚሊሻ መሆን አልፈልግም። ህወሓት ፓርቲያችን ነው የሚሉ የእርሱን ሚሊሻ እንደሆኑ ነው የሚቆጥረው። ሚሊሻነትን ደግሞ አልቀበልም" ብለዋል።

@Yenetube
43😁15👀1