YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በነገው ዕለት በይፋ ስራ ይጀምራል::

#የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት #ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ኤምባሲውን መርቀው #የሚከፍቱት ይሆናል።

በአየርላንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር የሆኑት አቶ #ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል።

#ኤርትራ በኢትዮጵያ የሚገኘው ኤምባሲዋን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መክፈቷ ይታወሳል።

ባለፈው ሃምሌ ወር የተከፈተው የኤርትራ #ኤምባሲ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

©fbc
@YeneTube @mycase27