ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.84K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ሰው #በእግዚአብሄር #መልክና #አምሳል ስለተፈጠረ #ከእግዚአብሄር ጋር ለመገናኘት ሲፈልግ #መገናኛ መንገዱ #ጸሎት ነው። #ጸሎት #ከእግዚአብሄር ጋር ያለን የመገናኛ #ምልክትና የግንኙነታችን #ማጽኛ ነው። #ጸሎት #ህብረትን#ምስጋናን#ስግደትን#ንስሀን#ልመናን#ምልጃን ሁሉ ያጠቃልላል። ይህንንም #ሰዎች በራሳቸው #ቋንቋ#ቦታና #ጊዜ ሊያከናውኑት ይችላሉ። ዋናው ነገር #የልብ #መሰበር ነው [ዩሀ 4፤ 20-24]።

▶️ የሁሉም ሰዎች #ጸሎት አድራሻው ሁሉን #ለእርሱ #በራሱ #ለራሱ ወደ ፈጠረው ወደ #እግዚአብሔር #ብቻ እንደሆነና ወደ እሱ #ብቻ ሊሆን እንደሚገባው #መጽሀፍ ቅዱስ ይመሰክራል [ኢዮ 38፥41 ፣ ሉቃ 12፥24]። ለዛ ነው ዳዊት <<ሥጋ ለባሽ ሁሉ ጸሎትን ወደ ምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል>> በማለት የተናገረው። [መዝ 65፥2 ]። ሌላ #ጸሎትን #መስማት የሚችል አካል የለም ማለት ነው[1]።

▶️ ጸሎት #ለክርስቲያኖች ሁሉ የተሰጠ #መለኮታዊ #ትእዛዝ ነው [1ተሰ 5፥17 ፣ ማር 14፥38]። አንዳንድ ጊዜ #እግዚአብሔር የሁሉም #አባት እንደመሆኑ መጠን ምንም እንኳን #መብታቸው ባይሆንም #መጋቤ #ዓለማት የሆነው ጌታ #በቸርነቱ #ለማያምኑና #ላልጸለዩም ሰዎችና ፍጥረታት ሁሉ #ይመግባቸዋል [ሐዋ 10፤ 1-6፣ ማቴ 6፥8]። ይሁን እንጂ አንድ #ሰው #ለመጸለይ ሲያስብ ግን መጀመሪያ #እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም #ዋጋ #እንደሚሰጥ በእርግጠኝነት #ማመን ያስፈልገዋል [ዕብ 11፥6]። ከዚህ #አንጻር በቀጥታ ወደ #እግዚአብሔር ያልሆኑ ነገር ግን ወደ #ማርያም የሆኑ #ጸሎቶችን #ክርስቲያን ሊቀበላቸው የማያስፈልጉበት #ዋና #ዋና #ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
____________
[1] ወደፊት <ጸሎት> በሚል ርእስ በሰፊው የምናየው ይሆናል።
<<ሁሉም ወደ #አምላኩ ወደ #እግዚአብሔር አንጋጦ #ሲለምን በአየን ጊዜ #መንፈሳዊ #ቅንዓትን ቀንቶ #ገሰጻቸው። በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች #አምላክን ወደ ወለደች ወደ ክብርት #እመቤታችን #ማርያም ለምን #እርዳታ አትሹም እርሱዋ #ከቅዱሳን ሁሉ #ድንቅ ድንቅ #ተአምራትን የምታደርግ፣ #ፈጥና #የምታደርስ #ልመናን የምትሰማ ናትና አላቸው። በዚያችም ጊዜ #ተአምራትን ወደ ምታደርግ #በድንጋሌ #ስጋ #በድንጋሌ #ነፍስ ወደ ጸናች ወደ ክብርት እመቤታችን #ማርያም ለመኑ .... የሃገሩም ሰዎች #እመቤታችንን አመሰገኑ[1]።>>

<<እግዚአብሔር #ሲመሰገን #ግሣጼ መጣ #ስለማርያም ግን #ምስጋና ሽልማት ይሆናል #ቀሲስ #እንድርያስም #የማርያምን #ቅዳሴ #ዘወትር ይቀድሳል #ከእርሷም #በቀር ሌላ #ቅዳሴ አያውቅም ነበር ... #ኤጲስቆጶሱ ጠርቶ ሁልጊዜ #ከአንድ #ቅዳሴ በቀር ለምን #ለእግዚአብሄር #አትቀድስም ብሎ ተቆጥቶ #እንዳይቀድስ ቢከለክለው #ማርያም ተገልጣ #የእኔን #ቅዳሴ ሲቀደስ አገልጋዩን #ያወገዝከው ለምንድን ነው? ... #በክፉ #አሟሟት እንድትሞት #በእውነት እነግርሃለው አለችው #ኤጲስቆጶሱም ከዛሬ ጀምሮ #ከእመቤታችን #ቅዳሴ በቀር ሌላ #ቅዳሴ #አትቀድስ አለው[2]።>>

▶️ ከላይ ያየነው ሁሉ #ስለማርያም የሚናገሩት #አዋልድ #መጽሀፍት #ከእግዚአብሄር ይልቅ #ማርያምን የሚያስበልጡና እርሷን #ስለማምለክ የሚያሳዩ የጠቀስናቸው #ጥቂት #አጸያፊ #ክፍሎች ሲሆኑ ከዚህ በታች ደግሞ #ከእግዚአብሄር ጋር ባልተናነሰ መልኩ #ስትመለክና #ስትመሰገን የሚያሳዩ #ጥቂት #ክፍሎችን ደግሞ #በመገረም እንመልከት፦

<< #ለአብ #ምስጋና ይገባል፣ #ለወልድ #ምስጋና ይገባል፣ #ለመንፈስ ቅዱስም #ምስጋና ይገባል፣ #አምላክን #ለወለደች #ለእመቤታችን #ድንግል #ማርያም #ምስጋና ይገባል[3]>>

ይህም ማለት #ከአብ #ከወልድና #ከመንፈስቅዱስ ጋር #እኩል #ምስጋና የምትቀበል #የስላሴ 4ተኛ #አካል ሆነች ማለት ነው። በሌላ መጽሐፍም
<<ወላዲተ አምላክ ማርያም ሆይ፥ ጧት ስነሳ #እግዚአብሔርንና #አንቺን እመቤቴን #በጸሎት #እንዳመሰግን የሚያነቃቃ መንፈስ ኅሊና አሳድሪብኝ፤[4]>> ይላል።

▶️ ከዚህም የከፋ #ማርያም እንደ #አምላክ #እግዚአብሔር ደግሞ ከእርሷ #ዝቅ ብሎ #እንደመማለጃዋ ሆኖም የቀረበበትን #መጽሀፍ ደግሞ እስኪ እንታዘብ ፦

<< #ዘጠኝ ወር #የተሸከምሽው ከሃሊ በሚሆን #ከጡትሽ #ወተቱን ባጠባሽውም #ልጅሽም #በሰው ልጅ ላይ #ቸርነቱና #ይቅርታው በበዛ #በአባቱ... #በእግዚአብሄርም #እማጸንሻለው #እማልድሻለሁ #እለምንሻለሁ[5]>> ይላል።

▶️ ስለዚህ እነዚህን የመሳሰሉ #ኢ-መጽሀፍ ቅዱሳዊና #አጸያፊ የሆኑ #አዋልድ መጽሀፍት ይዞ እግዚአብሔርን #አመልካለሁ ማለት ራስን #ማታለል ነው። እግዚአብሔር ግን <<እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ ይላል ቅዱሱ>> |ኢሳ 40፥25] ደግሞም <<እንደ እኔ ያለ ማን ነው ይነሳና ይጣራ ይናገርም>> ይላል እግዚአብሔር [ኢሳ 44፥7]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
___________
[1] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ "መጽሀፈ ግብረ ህማማት፤ ዘረቡዕ በ1 ሰአት በነግህ የሚነበብ፤ ገጽ 394፤ ቁጥር 1-13፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፥ አ.አ፥ 1996 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ "መጽሀፈ ግብረ ሕማማት" ዘሐሙስ በመዓልት በ11 ሠዐት የሚነበብ፤ ገጽ 587 - 588 ቁጥር 1፤ 10 ፤ 1996 ዓ.ም።

[3] 📚፤ ተስፋ ገብረስላሴ፤ "ውዳሴ ማርያም ምስለ መልክዓ ማርያም በአማርኛ"፤ የዘውትር ጸሎት፤ ገጽ 6 ፥1986 ዓ.ም።

[4] እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት አርኬ 15።

[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም ግእዝና አማርኛ 3ተኛ ዕትም፥ ምዕ 102፥7፤ ገጽ 170፤ ትንሳዔ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።