ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.82K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
▶️ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን #ደቀመዛሙርቶቹ ተሰብስበው #ስለጸሎት እንዲያስተምራቸው በጠየቁት ጊዜ እንግዲህ እናንተ እንዲህ #ጸልዩ፦ <<በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ፥ #ስምህ #ይቀደስ#መንግሥትህ #ትምጣ፤ ፈቃድህ #በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ #በምድር ትሁን፤ የዕለት #እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን #ይቅር እንደምንል በደላችንን #ይቅር በለን፤ ከክፉም #አድነን እንጂ ወደ #ፈተና አታግባን፤ #መንግሥት ያንተ ናትና #ኃይልም #ክብርም #ለዘለዓለሙ፤ አሜን።>> በሉ በማለት አስተምሯል። [ማቴ 6፤ 9-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]።

▶️ ከዚህ ጌታ #ኢየሱስ ከሰጠው #የጸሎት #መመሪያ ላይ በመቀጠል #አድራሻው ወደ #ማርያም የሆነ፦ <<እመቤታችን ቅድስት #ድንግል #ማርያም ሆይ በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ....>> ምናምን የሚለው #ጸሎት ቢኖሮ ኖሮ ወይም መኖር ቢኖርበት ኖሮ ደቀመዛሙርቱ #ጸሎት #አስተምረን ባሉት ጊዜ ባገኘው ምርጥ #አጋጣሚ ወደ #ማርያም #መጸለይ #ትክክል ወይም #ተገቢ መሆኑን ባሳየ ነበር። #ዝንጋኤ የሌለበት በማስተዋልም #ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጌታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ <<መንግስት ያንተ ነውና ኃይልና ክብርም ለዘላለሙ አሜን>> ብሎ #የመዝጊያ #ቃል አስቀምጦ ባልደመደመውም ነበር።

▶️ መምህራችንና #ሊቃችን አንድ እርሱም #ክርስቶስ የሆነው #ጌታ [ማቴ 23፤ 8-11] ያላስተማረውን #ትምህርት ከእርሱ ይልቅ #ሊቅ ለመሆን #በመሞከርና #በመጨመር ሌላ ድርሰት ማምጣት #ከንቱ #ድካምና #ፍሬ #ቢስ ከመሆኑም በላይ የሚያመጣው #ፋይዳ (ጥቅም) አይኖርምና <<እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን #በቃሉ አንዳች #አትጨምር።>> [ምሳ 30፥6]።

▶️ በመሰረቱ <<አባታችን ሆይ>> በሚለው #የማህበር #ጸሎት ላይ <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን ብቻ ሳይሆን <<ሊቃውንቶች>> የጨማመሩት #ሠላም #ለኪን#ውዳሴ #ማርያምን#አንቀጸ #ብርሃንን#ይወድስዋ #መላዕክትን#መልክዓ #ማርያምን....ወ.ዘ.ተ ደራርበውበታል።

▶️ የካቶሊክ #ቤተክርስቲያንና ሌሎች #እህትማማች ተብለው የሚጠሩት #አብያተ #ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ካለው የ<<እመቤታችን.... ሆይ>> ጸሎት #የቃላትና #የይዘት #ልዩነት አለው። የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትለው፦ <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል ነሽ የአሸናፊ የልዑል እግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ይገባሻል እንዲሁም ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታውን ለምኝልን ኃጢታትችንን ያስተሰርይልን ዘንድ አሜን[1]።>> የሚል ሲሆን #የካቶሊክና#የእህትማማች #አብያተ ክርስቲያናት (የግሪክ፣ የህንድ፣ የአርመን የግብጽ. . .ኦርቶዶክስ) ደግሞ <<ድንግል ወላዲት ሆይ! ማርያም ሆይ፣ ጸጋ የሞላሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው፤ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የነፍሳችንን አዳኝ ተሸክመሻልና ደስ ይበልሽ[2]>> #ብቻ ነው የሚለው። ይህ ግን #መጽሀፍ ቅዱስ የማይቀበለውና #መጽሀፍ ቅዱሳዊ #ማስረጃ የሌለው ከንቱ #ፈጠራ ነው።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_____________
[1] 📚፤ ጌታቸው አየነው (መምህር)፤ "የዘውትር ጸሎት በአማርኛ"፥ ገጽ 5 ፥አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።

[2] 📚፤ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጽ/ጠ/ጽ/ቤት ሐዋርያዊ ስራ መምሪያ ፤ "ሕያው እግዚአብሔር" ፤አማርኛ ትርጉም ገጽ 316፤ በገላውዲዎስ ተቋም በአባ ጳውሎስ ጻድዋ ካርዲናል ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እንዲታተም የተፈቀደ፤ ማስተር ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።
<<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን የተቀነባበረ <የጸሎት> ክፍል #በኢየሱስ ክርስቶስ #አስተምህሮ #ወቅት ብቻ ሳይሆን ከእሱ ቡሀላም ለብዙ #ዘመናት አልነበረም። ምናልባትም ሌሎች እንደሚሉት #ማርያም ገና #ክርስቶስን ሳትወልድ የነበረ #የገብርኤል #ሰላምታ ነው ተብሎ እንዳይወሰድ እንኳን #መልአኩ መጥቶ ያደረገው #ውይይት እንጂ #ጸሎት አይደለም። #ክርስቶስም #ለደቀመዛሙርቱ #ጸሎት ባስተማረበት #ወቅት #የገብርኤልንም #ሰላምታ ጨምሩበት በማለት ባስተላለፈ ነበር፤ ያንን ደግሞ አላደረገውም [ማቴ 6፤ 1-13፣ ሉቃ 11፤ 1-4]። << #በሰማያት የምትኖር #አባታችን ሆይ....>> የሚለው #የጸሎት #አስተምህሮቱን #ድንግል ማርያምን በትክክል በሚያውቋት #በደቀመዛሙርቱ ፊት ምናልባትም #በአስተምሮው #ወቅት ብዙ ጊዜ በምትገኝዋም #በድንግል #ማርያምም በራሷ ፊትም ተናግሯል።

▶️ ስለሆነም የተቀነባበረው <<የማርያም የጸሎት>> ምዕራፍ #በክርስቶስ #ወቅት ያልነበረ ከዚያም ቡኋላ #ሐዋሪያቱ #በአገልግሎታቸውና #በጸሎታቸውም ወቅት የማያውቁትና #የጥንት #ቤተ ክርስቲያን #አባቶችም በልዩ ልዩ ምክንያት #ጉባኤ ሲያደርጉ ለምሳሌ፦ #በኒቂያ ጉባኤ #በ325 ዓ.ም 318 የሃይማኖት አባቶች በእነ #እስክንድሮስ አፈጉባዔነት በንጉስ #ቆስጠንጢኖስ ዘመን ተሰብስበው #አርዮስን <<ወልድ #ፍጡር ነው>> ያለበትን #የክህደት ትምህርት #ሲያወግዙና #የሃይማኖት መግለጫ ሲያወጡ #ኢየሱስን ከመውለዷ ውጭ #ስለማርያም ፈጽሞ #መሠረታዊ #ትምህርት እንኳ በወቅቱ እንዳልነበረ መረዳት ይችላል። እንዲሁም #በቁስጥንጥንያ #በ375 ዓ.ም 150 #የሃይማኖት #አባቶች #በጢሞቴዎስ ዘአልቦጥሪት በንጉሥ ዘየዓቢ #ቴዎደስዩስ ወቅት #መቅደንዩስ << #መንፈስ ቅዱስ #ሕጹጽ ወይም #ሀይል ብቻ>> ብሎ በተነሳ ጊዜ ተሰብስበው #አውግዘው ትምህርቱንና እርሱን ሲለዩ #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #የአስተምህሮ #መግለጫ ሲያወጡ ያኔም ቢሆን #ኢየሱስን #ከመውለዷ ውጪ #ስለማርያም ያስተላለፉት ምንም #አዲስ #ትምህርት የለም። #በኤፌሶን ሀገርም #በ435 ዓ.ም 200 #የሃይማኖት #አባቶች #በቄርሎስ አፈጉባዔነት በቴዎደስዩስ ዘይንእስ ንጉሥነት ጊዜ ንስጥሮስ << #ክርስቶስ #ሁለት #አካል #ሁለት #ባህሪይ ነው>> ብሎ ሲነሳ #እርሱንም #ትምህርቱንም #አውግዘው #የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ #አስተምህሮ በመግለጫ መልክ ሲያስቀምጡ ድንግል #ማርያም #ክርስቶስን እንደወለደች ብቻ እንጂ << #እመቤታችን>> ብለውም ሆነ << #ለምኝልን>> የሚል አስተምህሮ አያውቁም። #ጤናማ #አስተምህሮ አይደለምና።

▶️ ዛሬ ሁሉም #አብያተክርስቲያናት የሚቀበሉት #ሙሉ #የሃይማኖት #መግለጫቸው

<<ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን የተፈጠረ ሳይሆን የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምን ምንም የሆነ የለም በሰማይም ያለ በምድርም ያለ ስለእኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር ፈጽሞ ሰው ሆኖ በጴንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ ሞተ ተቀበረም በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና ሙታንንም ይፈርድ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም ጌታ ማህየዊ በሚሆን ከአብ በሰረጸ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነብያት የተነገረ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋሪያት በሰበሰባት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሰረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሳት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።>> የሚል ነው።

ይህንንም መግለጫ #በ1530 ዓ.ም #ሉተራውያን << #የአውግስበርግ #መግለጫ>> በሚል አጸደቁ። እንዲሁም #በ1546 ዓ.ም #ካቶሊክ በድጋሜ << #የትሬንት #መግለጫ>> በማለት አጸደቀችው። #በ1571 ዓ.ም ደግሞ #የአንግሊካን #ቸርች መግለጫውን ተቀብላ አጸደቀችው። #በ1646 ዓ.ም #ፕሪስቢቴሪያን << #የዌስት #ሚኒስቴር #መግለጫ>> በሚል አጸደቀችው[1]።

▶️ ኦርቶዶክስ #ቤተክርስቲያን መግለጫውን በድጋሜ << #ጸሎተ #ሃይማኖት>> በማለት #በ1426-1460 ዓ.ም በኢትዮጵያ የነገሰው #አጼ #ዘርዓ ያዕቆብ ሙሉውን ተቀበሉና ሌላ #በመጨመር << #ለማርያምና #ለእፀ መስቀሉ (ለመስቀሉ እንጨት) #ስግደት ይገባቸዋል>> በማለት እንዲሁም <<እመቤታችን ...ሆይ>> የሚለውን <<ከአባታችን ሆይ>> #ቀጥሎ እንዲባል ብሎ #አዋጅ አወጣ። ከዚህም የተነሳ በርካታ #ካህናት << #አባቶቻችን ካስቀመጡት #ከሃይማኖት #መግለጫው ውጪ ተጨማሪውን #አንቀበልም>> በማለታቸው #በሰይፍ እንደቆራረጣቸውና እንዳሳደዳቸው #ገድለ #እስጢፋኖስ#ገድለ #አበው ወአኀው፣ #ገድለ #አባ አበከረዙል፣ #ገድለ #አባ ዕዝራ፣ #ገድለ #ደቂቀ እስጢፋኖስን ማንበብ #በቂ ነው።

▶️ ነገር ግን #በዘር #ቅብብሎሽ አማካኝነት የነበረው #የንግስና #ሥርአት ለዚህ <<አዳራሻውን ወደ ሳተው ጸሎት>> ሰፊ እድል አግኝቶ #ሰይፍ ያስፈራቸውና በክርስትናው #ትምህርት ብዙም #መሰረታዊ #እውቀት ያልነበራቸው #ህዝብና #ካህናት #የጸሎት #ምዕራፋቸው አድርገው ለቀጣዩ #ትውልድ በማስተላለፋቸው ይሀው አሁን የምናየውን #ከእግዚአብሄር #ቃል ውጪ የሆነ #ትውልድ ፈጥረውልናል። ዛሬ ዛሬ #በየጸሎቱ #መዛግብት ውስጥ እየተጨመረ ተጽፎ #ምዕመናን ሁሉ #በቀን ቢያንስ #አንድ ጊዜ እንዲደግመው በመደረጉ እንግዳው <<ጸሎት>> #የተለመደ ሆኖ ቀረ። እንዲያውም በዚህ #ዘመን አስቀድመን እንዳልነው <<እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ...>> የሚለውን #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል #ጥቅሶችን ያለቦታቸው እንደ #ስጋ #ዘንጥለውና #በጣጥሰው #መጽሀፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል የሚታገሉ ተነስተዋል። እኛ ግን <<የእግዚአብሔርን ቃል #ቀላቅለው #እንደሚሸቃቅጡት እንደ #ብዙዎቹ አይደለንምና፤ #በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ #ተላክን #በእግዚአብሔር ፊት #በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።>> [2ቆሮ 2፥17]

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን፤ አውግስበርግ ሃይማኖታዊ መግለጫ፤ በአማርኛ የተተረጎመ፤ አ.አ፥ 1993 ዓ.ም።