ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ሙስሊም ያረደውን ወይም ሌላ ኢአማኝ (የማያምኑ) ወገኖች ያረዱትን መብላት እጅግ በጣም ጸያፍ ነው። "...“መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ #ሆዳቸው_አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።” ፊል3፥19."እንደ ተባለባቸው አንዳንድ ሆድ አደር ክርስቲያን ነኝ ባዮች ምን ችግር አለው መሐመድ የሚባል በግ የለም ፖስተር ኢዮ ጩፋም የሚሉት ፍየል የለም ስለዚህ እንበላለን ብለው እንደ አይጥና አሳማ ሁሉን የሚያግበሰብሱ ሆድ አምኩ የሆነ ሰዎች አሉ። ይህ ግን ለመንፈሳዊ እድገት ማነቆ በመሆን ለብዙ ችግር ያጋልጣል ።

ለምሳሌ ጥቂቶቹን እንመልከት ።
1) የቅዱሳት መጻሕፍትን ትዕዛዝ ያስጥሳል

2)አጋንንት ሰውችን መቁራኘት እንዲችሉ ምክንያት ሆኖ በሰይጣን ለመለከፍና የክፉ መንፈስ ማደሪያ ለመሆን ያጋልጣል።

3)ከማያምኑ ሰዎች ከመናፍቃን ጋር በእምነት ጭምር ወይም በክህደታቸው ጭምር ተባባሪዎች እንድንሆን ያደርጋል።

4) ለሌሎች ወንድሞች ማሰናከያ ያደርገናል"አንተ እውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ስትቀመጥ አንድ ሰው ቢያይህ፥ ደካማ ሰው ቢሆን ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት ሕሊናው አይታነጽበትምን? በአንተ እውቀትም ይህ ደካማ ይጠፋል፥ እርሱም ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው።1ቆሮ 8÷10-11

5)ፍቅረ እግዚአብሔር አሳጥቶ የአስመሳይነት የሐሰት ፍቅረ ቢጽን(የጓደኛ ፍቅር) በማስረጽ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ይለያል ለምሳሌ ተፈጻሚተ ሰማዕት አርዮስ ከክህደቶ አይመለስምና አውግዤዋለው ዳግመኛ የተመለሰ መስሎህ ወደ ቤተክርስቲያን አንድነት እንዳትመልሰው ብሎ ለተማሪው ለአኪላስ አስጠንቅቆት አርፎ ነበር አኪላስ ግን ከአርዮስ ጋር አብረው በአንድ ሥፍት ስላደጉ የጓደኛ ፍቅር አገብሮት ከውግዘቱ ፈታው ከቤተክርስቲያንም አንድነት ቀላቀለው በዚህም ስራው የመምህሩን ትዕዛዝ በመተላለፉ አኪላስ ተቀስፎ ሊሞት ችሏል የአርዮስም መፈታት ሐሰት ሆኗል።(አቡነ ጎርጎርያስ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ)

#ነገር ግን ይህ እውቀት በሁሉ ዘንድ አይገኝም፤ አንዳንዶች ግን ጣዖትን እስከ አሁን ድረስ ስለ ለመዱ፦ ለጣዖት የተሠዋ ነው ብለው ይበላሉና ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል። መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም አይተርፈንም። ዳሩ ግን ይህ መብታችሁ ለደካሞች ዕንቅፋት እንዳይሆንባቸው ተጠንቀቁ። አንተ እውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ስትቀመጥ አንድ ሰው ቢያይህ፥ ደካማ ሰው ቢሆን ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት ሕሊናው አይታነጽበትምን በአንተ እውቀትም ይህ ደካማ ይጠፋል፥ እርሱም ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው። እንዲህም ወንድሞችን እየበደላችሁ ደካማም የሆነውን ሕሊናቸውን እያቆሰላችሁ ክርስቶስን ትበድላላችሁ። ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም። 1ቆሮ 8÷7-13

#እንግዲህ ምን እላለሁ? ለጣዖት የተሠዋ ምናምን ነው እላለሁን? ወይስ ጣዖት ምናምን እንዲሆን እላለሁን?አይደለም፤ ነገር ግን አሕዛብ የሚሠዉት ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር ማኅበረተኞች እንድትሆኑ አልወድም። የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም። ወይስ ጌታን እናስቀናውን? እኛስ ከእርሱ ይልቅ እንበረታለንን?

#ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም። #1ቆሮ10÷19-23

#ማሳሰቢያ :- ቅዱሳን ከሕግ በላይ ናቸው እንዲያውም እራሳቸው ሕጎች ናቸው። ቅዱሳን ግን ከዚህ በተለየ መልኩ ከመናፍቃን ቀርበው ባርከው ሊመገቡ ይችላሉ ይህም ለጥቅም ነው።

በአንድ የጾም ወቅት አንድ አባት ወደ አንድ ልጅ ወዳላቸው ሁለት ባልናሚስት ወደ ሆኑ ሰዎች ቤት ይሄዳሉ ሰዎች መናፍቃን ነበሩና በግ አርደው አወራርደው ሲበሉ ደረሱ ሰዎቹም አባ ይግቡ አብረውንብ ይብሉ አሏቸው አባም እሺ ብለው ሳያንገራግሩ ወደ ቤታቸው ገብተው መስቀላቸውን አውጥተው ባርከው አብረው በጉን በልተው ወጡ :: ከቤቱ ሲወጡም ተመሰገን አምላኬ በአንድ በግ ሦስት በግ አገኘው አሉ ይባላል።

መብል መጠጥ ሰውን ያፋቅራል ቅዱስ ይህን ስለሚገባቸውና በመንፈሳዊ እድገት የበቁ በመሆናቸው እንኳን የማያምኑ ሰዎች ያረዱት ሥጋ ቀርቶ መርዝና ገዳይ ነገር እንኳ ቢበሉና ቢጠጡ የሚጎዳቸው አንዳች የለም ስለዚህ እምነታቸው ከፍ ያለ ቅዱሳን ሰዎችና አባቶች ከነእገሌ ጋር በሉ ተብሉ ብናነብና ብንሰማ ልንደናገርና ግራ ሊገባን አይገባም ቅዱሳን ከሕግ በላይ ናቸውና እኛ ግን እንደ ልካችን እንደ ድካማችን አንጻር ለጣዖት ከተሰዋው ባንበላ የተመረጠ ነው::

#ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።” #ሐዋ 15፥28-29

..........ይቆየን.........
#የእግዚአብሔር_ቸርነት_የድንግል_ማርያም_አማላጅነት_የቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት አይለየን! አሜን🙏

@YEAWEDIMERITE
ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ሕዳር 06/12013ዓ.ም

#ዓውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
"ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ"
#ውዳሴ_ማርያም ዘ አርብ

የውዳሴ ማርያም ጸአፊ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ ቢሆንም ቅሉ ደራሲው ግን መንፈስ ቅዱስ ነው። ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ በገለጠለት መሠረት ሊቁ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን "ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ " ሲል አራቆ ጽፏል ።

አዎን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መሰላል ነች ። በመሠላል እታች ያለው ወደላይ ይወጣል እላይ ያለውም ወደታች ይወርድበታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የምድራዊ ሰዎችን ጸሎትና ልመና ወደ ሰማይ አባታቸው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ታደርሳለች ታሳርጋለች የእግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረትን ደግሞ ወደ ሰው ልጆች ታወርዳለት ፣ታመጣለችና አማናዊት መሰላል ነች። ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማህሌተ ጽጌው "አልቦ ጸሎት  ወአልቦ ትንባሌ እንበሌከ ማርያም የዓአርግ ሉዓሌ" ድንግል ማርያም ሆይ ያላንቺ አማላጅነት ወደ ሰማይ የሚያርግ ጸሎትና ልመና የለም"  እንዳለ

ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ስለ ጌታችን ዕርገት ሲናገር እንዲ ይላል "እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። " #ሉቃ 24÷50

ዕርገቱም እንደ ኤልያስ በሠረገላ እንደ ሄኖክም በመሰወር እንደ ሕዝራም ሱቱኤል በመላእክት እገዛ የሆነ አይደለም ። ደመና ከዐይናቸው ሰውራ እስክትቀበለው ድረስ ከፍ ከፍ አለ እንጂ አልጠፋባቸውም ሰማይን አተኩረው እስኪመለከቱ ድረስ የሰማይ መላእክትም እንኪገስጾቸው ድረስ በተመስጦ ሆነው ሲያርግ አዮት እንጂ አረቀቀባቸውም በሰው አምሮ በሚረዳና በሚገባ መልኩ በርዕቀት ከነርሱ ተለይቶ ከፍ ከፍ አለ ዐረገ ። " እናንት የገሊላ ሰዎች እንዲህ አተኩራችሁ ወደ ሰማይ የምትመለከቱት ስለምንድነው እንዲሁ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ደግሞ ይመጣልና " #ሐዋ 1÷11

መሰላል ሁለት ትይይዮ የሆኑ ቋሚ ዘንጎች ያሉት ሲሆን በመካከላቸውም በየተወሰነ ርቀቱ በተደረደሩ አግዳሚ ዘንጎች ሁለቱ ትይዮ ዘንጎች የተጋጠሙ ናቸው ::

ሁለቱ ትይዮ የሆኑ ረጃችም ዘንጎች በሁለት ወገን ድንግል መሆኗን (ድንግል በክሌ) ያመሰጥራሉ። አንድም ብሉይና ሐዲስን ሲወክሉ በመካከላቸው ያሉ ርብራብ ዘንጎች ደግሞ የብሉይና የሐዲስ መገናኛው ድልድይ እመቤታችን መሆኟን ያስረዳሉ በቡሉይ መጨረሻ በሐዲስ መጀመሪያ ተገኝታለችን አንድም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ፈራጅ የሆነ ንጉሥ ሰው ሲሆን አምላክ አምላክ ሲሆን ደግሞ ሰው የሆነውን መካከለኛ ትወልደዋለችና። አንድም የጠቡ ግድግዳ የፈረሰባት ሰማይና ምድር ሰውና መላእክት ነፍስና ሥጋ የታረቁባት የተቀራረቡባት የዕርቅ ሰነድ እመቤታችን ነችና መሰላል የእመቤታችን ምሳሌ ነው።
በመጻሕፍ ቅዱስ ላይም ይህ ነገር የጎላ የተረዳ ነው::..." ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ፤ #እነሆም_መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም_የእግዚአብሔር_መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥# እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ #ዘፍ 28÷10-13

ታድያ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ አንቺ ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ሲል ግን እንደ መሰላል ተረግጧት ወጣ ማለት አይደለም የወጣው ወደ ሰማይ ነው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቁመትም እንደ ሰው ሁሉ ሦስት ክንድ ከስንዝር ብቻ ነው ።

በምሥጢር ሊናገር የፈለገው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ባይነሳ ኖሮ ለመለኮት ወደ ሰማይ ዐረገ የሚልል ነገር ባልተነገረለት ነበር የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ ስላደረገ ውጣ ፣ከፍ ፣ከፍ አለ ዐረገ የሚሉት ነገሮች ተነገረለት ። ቅዱስ ኤፍሬም ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ብቻ ይበል እንጂ ቅሉ እመቤታችንስ ለቃል ከሰማይ ወደ ምድር ለመውረድም መሰላል ሆናዋለች። ድንግል ማርያም ባትኖር ኖሮ ከማን ሰው ይሆን ነበር? መንክር ኦ ዝ ምሥጢር!

እንዲያውም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዕርገቱንና ሰው የመሆኑን ምሥጢር ሲያወዳጁ እንዲ ይላሉ"የቃል ርደት በማኅጸን የሥጋ ዕርገት በአርባ ቀን"

ምን ማለታቸው ነው ቢሉ ለቃል ርደትም ለሥጋ ዕርገትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ መሰላል ሆና ለች ያለ እመቤታችን የቃል ርደት (መውረድ) ሆነ የሥጋ ዕርገት አይታሰብምና ነው።

ክቡር ዳዊትም ይህን የሊቁን ሀሳብ የቅዱስ ኤፍሬምን ሀሳብ ሲደግፍ እንዲ ይላል። “ #በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ #ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።” #መዝ (68) 68፥33 በምሥራቅ በኩል ማለቱ አቅጣጫን ብቻ የሚጠቁም ሳይሆን ከምሥራቅ ፀሐይ እንደሚወጣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምም ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወጣልና እመቤታችን #ምሥራቀ_ምሥራቃት_ሞጻ_ፀሐይ ትባላለችና ፀሐይ ክርስቶስ የወጣባት ምሥራቃዊ መሠላል እርሷ ነች ። መለኮት በሁሉ የመላ ፣ በሁሉ ያለ ነው የሌለበት ቦታ የለም በዚህ አለ በዚያ የለም አይባልለትም # መዝ 138 (139)÷7-10 ነገር ግን የምሥራቅ የእመቤታችንን ሥጋና ነፍስ በመዋሕዱ ግን ከምድር ወደ ሰማይ ሄደ ከፍ ከፍ አለ ዐረገ ተባለለት ። መለኮት ዐረገ እንዲባል ምክንያትቱ ምሥራቁ ሆነችው ።

የነዚህ የዳዊትና የኤፍሬም የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ምን ይረቅ?
__ #ለምን_ዐረገ ? ___
#ትንቢቱን_ለመፈጸም :-"አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ። #መዝ46(47)÷5-6 ነቢዮ ዳዊት ይህን የተናገረው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ ነው።
#ሥፍራን_ለማዘጋጀት :- መግሥተ ሠማያት ቀድማ ያልተዘጋጀች አሁን ሄዶ የሚያዘጋጃት ሆና ሳይሆን ለእናንተ ለአባቴ ብሩካኖች የተገባች ሆና በመጨረሻው ቀን ተገልጣ እንድትሰጣችሁ የማደርግ እኔ ነኝ አሁን ሄጄ በአባቴ ዕሪና (ትክክል ) በአብ ቀኝ በክብሩ ዙፋን ልቀመጥ ይገባኛል ሲል ነው “በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤” #ዮሐንስ 14፥2
#መንፈስ_ቅዱስን_ለመላክ :- “እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።” #ዮሐንስ 16፥7

አ.አ ኢትዮጵያ
ሰኔ ፫ቀን / ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም
ተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዘመናቱን በአራቱ ወንጌላውያን ከፍላ ዓመቱን ደግሞ በአራቱ ወቅቶች ሰድራ ወቅቱን ተንተርሳ ለልጆቿ ለአምሯቸው በተመቸ ልባቸውን በማረከ መልኩ ቃለ ወንጌልን ትመግባቸዋለች።

ዛሬ ግን በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ብዙ ግዜ ስለማይስተዋሉ ተጨማሪ ሁለት ዘመኑችን እንመለከታለን ዘመነ ሳውል እና ዘመነ ጳውሎስን።

#የዘመነ_ሳውል መገለጫዎች

*ጭፍን ጥላቻ
*መደብደብ
*ማስደብደብ
*መግደል
*ማስገደል መንግሥት ሥልጣንን በመጠቀም የግድያ ደብዳቤ በክርስቲያኖች ላይ ማጻፍ
*ሰው ስለ እምነቱ እና ስለ አመለካከቱ ማሳደድ ማፈናቀል ንብረቱን ማውደም

“ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር፤ ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር።”
#ሐዋ 8፥3

ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው ገና እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናት ሄደ፥ በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ። ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው። #ሐዋ 9÷15
#የዘመነ_ጳውሎስ መገለጫዎች

*መደብደብ
*መሰደድ
*መታሰር
*መታረድ

" እንደ እብድ ሰው እላለሁ፤ እኔ እበልጣለሁ፤ በድካም አብዝቼ፥ በመገረፍ አብዝቼ፥ በመታሰር አትርፌ፥ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ። አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ። ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረ፤ ሌሊትና ቀን በባሕር ውስጥ ኖርሁ።
#2ኛ_ቆሮ 11÷23-25

እንባቢ ሆይ ዘመንህ የማነው? የሳውል ወይስ የጳውሎስ ዘመን?

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ሐምሌ ፮ ቀን /፳ ፻ ፲ ፫ /ዓ.ም
#ይህን ያለው ሻለቃ ኃይለ ገብረ ሥላሴ አይደለም ። እንዲ ያለው የደማስቆው ሯጭ ቅዱስ ጳውሎስ ነው ። “በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ።” #1ኛ ቆሮ 9፥24 ክርስቲያኖች የዚህች ዓለም ዙር እስኪያልቅ ድረስ በትጋት እና በውድድር መንፈስ መሮጥ አለባቸው ። ያሸነፉ ሁሉ እንጂ የሮጡ ሁሉ ጥሩ ዋጋን አይሸለሙም። “ እላችኋለሁና ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።” #ማቴ 5፥20 በእርግጥ የኑሮ ሩጫ ለየ ቅል ነው እግዚአብሔር ወንዱን ከሴቱ ሕጻኑን ከአዋቂው ደምሮ በአንድ መስፈርት አያወዳድርም ለሁሉም እንደስራው መደብ በጽድቅ ይፈርድለታል እንጂ። ጻድቁ ወደፊት ይጽደቅ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ ጠማማውም ወደ ፊት ይጥመም "እነሆ በቶሎ እመጣለሁ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍለው ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ዘንድ አለ እንዳለ ራእይ .ዮሐ22÷12

#ቅዱስ_ጳውሎስ ምርጥ ዕቃዬ ከመባሉ በፊት ሳዉል ይባል ነበር። ሁል ጊዜ ለኦሪት ሕግ የሚቀና ስለነበር ክርስቶስን እንከተላለን የሚሉ ክርስቲያኖች ሲመጡ ከኦሪቷ ሕግ ያፈነገጡ ስለመሰለው እነርሱን ያጠፉ ዘንድ ሌሊትና ቀን ሳይታክት ተሯሩጧል ። #ሐዋ 8፥3

ክርስቲያኖችን ለማሰር ብዙ ጊዜ ሮጧል፤ ክርስቲያኖችን ለማስደብደብ ብዙ ጊዜ ጥሯል፤ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ብዙ ጊዜ ሽምጥ ጋልቧል፤ክርስቲያኖችም በድንጋይ ተወግረው ሲሞቱ የገዳዮችን ልብሶች በደስታ ጠብቆል። ሳውል በዚህ ነገር ሁሉ ሮጧል ግን በምድርም ሆነ በሰማይ ኒሻን የሚሸልመው አልነበረም።

#በመጨረሻ ግን ክርስቲያኖችን ጨርሶ ይፈጅ ዘንድም የፍቃድ ደብዳቤ ሊያጽፍ ወደ ደማስቆ ሽምጥ ጋለበ በአጥፊነት መንፈስም ሮጠ #ሐዋ 9÷15

ወደ ከተማዋ ሲገባ ግን በታላቅ ብርሃን ተመታ ከፈረሱም ወድቆ ከብርሃኑ ጸዳል የተነሳ ዐይኑ ታውሮ ማየት ተሳነው ወዲያውም ሳውል ሳውል ስለምን ታሳድደኛለህ የሚል ቃል ሰማ።

#የማሳድድህ_አንተ ማነህ ? ብሎ ጠየቀ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል አለው ሳውልም ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ አለው ወደ ደማስቆም ግባ ሐናንያ የሚባል የእግዚአብሔር ሰው ታገኛለህ እርሱ ይፈውስሃል አለው ።

ሳዉልም ከምድር ተነሳ ዐይኖቹም እንደታወሩ ነበሩ እየመሩም ወደ ከተማዋ አገቡት ለሐናንያም የጠርሴስ ሰው ሳውል ወደ እርሱ እንደሚመጣ በራዕይ ተነገረው ።

#ሐናንያ_ግን ስለ ሳውል ክፋት ብዙ ይሰማ ነበርና እንዴት እፈውሰው ዘንድ ይገባልን አለው ። ጌታም ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና አለው። #ሐዋ 9÷ 13-15

#እግዚአብሔር እንዲህ ነው እያሳደድከውም ይወድሃል እየገደልከው ያኖርሃል እያሰርከው ይፈታሃል እየሸሸህው በፍቅር ይከተልሃል ሰዎች እንደ ሸክም ሲቆጥሩህ ሁሉን ቻይ ትከሻህ ያለው ይሆናል ብሎ ይመሰክርልሃል ሰው ኃጢያተኛ እያለህ እርሱ ግን ምርጤ ይልሃል። #እግዚአብሔር እንዲህ ነው!
ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ አለ። #ወዲያውም_እንደ_ቅርፊት_ያለ ከዓይኑ ወደቀ፥ ያን ጊዜም ደግሞ አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፥ በክፉት መንገድ ሮጦ ያተረፈው እውርነትን ተረዳ አሁን ግን በጽድቁም መንገድ መሮጥን መረጠ።“
#እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ #ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን ” ያለ ዐይን መመልከት፣ መሄድ እንዲሁም መሮጥ አይቻልም።
በሥጋ ለመሮጥ ዓይነ ሥጋ በመንፈሳዊ ሕይወት ለመሮጥ ዐይነ ልቡና ሊኖረን ይገባል ያለ ዐይን እንኳን መሮጥ በደህንነትና በምቶት መራመድ አይቻልም። ዐይን ለሰውነት ሁሉ ወሳኝ አካል ናት በእርግጥ ዐይን አይሮጥም የሚሮጠው እግር ነው ሆኖም መነሻውን መገስገሻውንና መዳረሻውን ዐይን ካላመለከተችሁ እግር ወስዶ ወስዶ ገደል ይከታል ። “ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ።” #ማቴ 15፥14
ስለሆነም በእግረ ሥጋ ለመሮጥ ዐይነ ሥጋ በእግረ ልቡና ለመሮጥ ዐይነ ልቡና የግድ ያስፈልገናል። #ታገኙ_ዘንድ_ሩጡ " ብሎ ስለ መንፈሳዊ ሩጫ የመከረን ቅዱስ ጳውሎስ ከሥጋው ዐይንና ከልቦናው ዐይን ላይ ጋርዶት የነበረው ቅርፊት ከወደቀለት በኋላ ነው።
#አሁን የሚያሯሩጠው ሳውል ተብሎ አይጠራም ፤ አሁን የሚያሳድደው ሳውል መባሉ ቀርቷል፤አሁን ደብዳቢ መሆኑ አብቅቷል። አሁን ስለ ስሙ ከቦታ ቦታ የሚሯሯጥ ምርጥ ዕቃ ጳውሎስ ሆኗልና አሁን ስለስሙ ከሀገር ወደ ሀገር የሚንከራተት ስደተኛው ሆኗልና ። 2ቆሮ 11÷23-27
ዋጋ ለማግኘት መሮጥ እንዳናይ የጋረደንን ግርዶሽ ከመጣል ይጀምራል ። ከሳውል ዐይን ቅርፊት መሳይ ነገር ወደቀ ሲል ከአስተሳሰቡና ከልቦናውም ዐይን ጭምር ቅርፊቱ እንደወደቀለት ማስተዋል ያስፈልጋል። ክርስቶስን ወዶ እናቱን ማሳደድ ክርስቶስን ወዶ ክርስቲያኖችን መጥላት ይህ የልቡና ግርዶሽ ፣ ይህ የልቡና ሽፋን፣ ይህ የዕሊና ቅርፊትም ነውና። #እግዚአብሔር እንደ ሳውል ነቅሎ ይጣልላቸው አጥርተው ያዮ ዘንድም የተንሸዋረረ ዐይነ ልቦናቸውን ሐናንያ በመሰሉ የቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ ያብራላቸው።

#ሃይማኖት የሌላችሁ ወደ ሃይማኖት ሩጡ
#ሃይማኖት ያላችሁ ወደ ምግባር ገስግሱ
#ምግባር ያላችሁ ወደ ትሩፉት ፍጠኑ ወደ ገነት በር ትደርሳላችሁ ተከፍቶም ታገኙታላችሁ ከየት ናችሁ የሚላችሁም አይኖርም። ያን ጊዜ የደማስቆውን ሯጭ ታኙታላችሁ አብራችሁትም “ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤” ትላላችሁ ። #2ኛ ጢሞ 4፥7

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ሐምሌ ፳፮/፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም