Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
ከዕሴ ሥር በትር ወጣች
ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች (ኢሳ 7፡14)›› ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ‹‹ የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች (መዝ 44፡9)›› ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት (ራዕ 12፡1)›› ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡
የድንግል ማርያም ልደት በነቢያት አንደበት
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡ መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡ መዝ 86፡1-7
እግዚአብሔር የዝማሬና የትንቢት ጸጋን ያበዛለት ክቡር ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥርወ ልደት አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት ተገልጾለት ‹‹መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን /መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው/›› በማለት ትንቢት ተናግሯል፡፡ ‹‹የተቀደሱ ተራሮች›› ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ነገር ሲያመለክት ነው፡፡ ይህንን ትንቢትና እውነተኛውን የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ ቤተክርስቲያን ‹‹የእመቤታችን ማርያም ትውልዷ ባባቷ በኩል ከንጉሡ ከዳዊት ወገን ነው፤ በናቷም በኩል ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው፤ የአባቷ ስም ኢያቄም ነው፤ የእናቷም ስም ሐና ነው፡፡›› ብላ ታስተምራለች፡፡
ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል፡፡ ኢሳ 11፡1
ቁጥሩ ከዐበይት ነቢያት ወገን የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስም ጥበብንና እውቀትን በሚገልጽ ስለሚመጣውም ነገር ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም ጽጌ (አበባ) የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት ‹‹ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ /ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል/›› በማለት ታላቅ ትንቢትን ተናግሮ ነበር፡፡ ይህች በትርም ከእሴይ ዘር የተገኘችው በዚህች ዕለት ነውና ልደቷን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከእሴይ ሥር የተገኘሽ መዓዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ›› በማለት በውዳሴ አመስግኗታል፡፡ ‹‹በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ (መዝ 131፡13)›› የተባለልን የአባቶቻችን ልጆች እኛም እንዲሁ እያልን እናመሰግናታለን፡፡
ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፡፡ መኃ 4፡8
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ በሊባኖስ ስለመሆኑ አስቀድሞ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት /ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች/›› በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ የዚህ ትንቢት ምስጢርም የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ትንቢቱም ሲፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት 1 ቀን በ15 ዓ.ዓ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡
ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን የተናገረው ቃልም መፈጸሙን ሲገልጽ ‹‹….የአናብስት ልጅ አልኩሽ፡፡ ሰሎሞን እንዲህ ሲል እንደተናገረ፡- ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡›› በማለት አመስጥሮታል፡፡ እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡የድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌ
ከትንቢቱ በተጨማሪም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌም አስቀድሞ የተገለጸ ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል ከእርሷ ሰባት ትውልድ አስቀድሞ ለነበሩት ደጋግ ሰዎች እንዲሁም ለእናትና ለአባቷ የተገለጹት ምሳሌዎች በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ሰፍረው ይገኛሉ፡፡
ሰባተኛዪቱ እንቦሳ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየሁ (ቴክታ)
በቅድስና የሚኖሩ ነገር ግን መካን የነበሩት ቴክታና ጴጥርቃ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ፤ ስድስተኛዪቱ ጨረቃን ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው መፈክረ ሕልም (ሕልም ፈች ሊቅ) አለና ሂደው ነገሩት፡፡ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፤ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም፤ እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል አላቸው፡፡ እነርሱም ጊዜ ይተርጉመው ብለውት ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ልጅ ወለዱ፡፡ ስሟንም ‹‹ረከብኩ ስእለትዬ፤ ረከብኩ ተምኔትዬ›› /የተሳልኩትን አገኘሁ፤ የተመኘሁትን አገኘሁ/ ሲሉ ‹‹ሄኤሜን››አሏት፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ ከኢያቄምና ከሐናም በጨረቃ የተመሰለች ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡
ፀዓዳ ርግብ ሰባቱ ሰማያትን ሰንጥቃ መጥታ በማሕፀኔ ስታድር አየሁ (ቅድስት ሐና)
ኢያቄምና ሐና መካን ስለነበሩ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ጸልየው፤ ሲሰጣቸውም መልሰው ለእርሱ እንደሚሰጡ ስዕለትን ተስለው ነበር፡፡ ጸሎታቸው ሲደርስ ለሐና በሕልም ተገልጾላት ለባለቤቷ ለኢያቄም ‹‹ብእሴሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ /ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብቶ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ፡፡›› ብላዋለች፡፡ የዚህ ራእይ ምስጢርም ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን፤ ፀዓዳ (ነጭ) መሆኗ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ

ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ›› ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መሆኗን ሲያጠይቅ ነው::
ከሰባተኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ (ቅዱስ ኢያቄም)
በተመሳሳይ ኢያቄምም በሕልሙ ያየውን ለባለቤቱ ለሐና ‹‹እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ /ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ብሎ በሕልሙ የተገለጸለትን ነግሯታል፡፡ የዚህም ራዕይ ምስጢር ዖፍ የተባለው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፡፡ ኢያቄም ‹‹ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ የሚያጠይቅ ሲሆን ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ባህርይው፣ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው:፡
የድንግል ማርያም ልደት በሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት
የሐዲስ ኪዳን ሊቃውንትም ትንቢተ ነቢያትንና ወንጌልን በማጣጣም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት አመስጥረው አስተምረዋል፤ አመስግነዋል፤ ተቃኝተዋልም፡፡ የእርሷን ልደት እጅግ ብዙ ሊቃውንት በስፋትና በጥልቀት ያመሰጠሩት ሲሆን ለምሳሌ ያህል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች (ቅዱስ ያሬድ)
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት ‹‹ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያምስ (ማርያም ግን) ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡›› በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሥርወ ልደቷ ‹‹እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ…ሐረገ ወይን/ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿም በሰማይ ያሉ…የወይን ሐረግ›› በማለት የተወለደችው በምድር ከነበሩት ኢያቄምና ሐና መሆኑን የወለደችው ግን ሰማያዊውን ንጉሥ እንደሆነ በማመስጠር ዘምሯል፡፡ በዚህም ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች መሰላል መሆኗል ገልጾ አስተምሯል፡፡
ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ (አባ ሕርያቆስ)
የብህንሳው ሊቀ ጳጳስ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ‹‹ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ/ ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ›› በማለት የድንግል ማርያም ጽንሰትና ልደት እንዴት እንደነበር በድርሰቱ አስፍሮታል፡፡ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት የሁላችን እናት ድንግል ማርያም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሳ ከዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኋላ ግንቦት 1 ቀን ተወልዳለች፡፡ እርስዋም ስትፀነስ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከጥንተ አብሶ (original Sin) ጠብቋታል፤ አበሳው አልነካትም፡፡ ይህንንም ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በኃጢአት በተከበበ፣ መርገም በሞላበት ዓለም ውስጥ ከኃጢአት ከበደል ርቃ (ተለይታ) እንደ ጌዲዮን ጸምር በንጽህና የጠገኘች ንጽህት ዘር መሆኗን ሲያስረዳ ‹‹የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር (ኢሳ 1፡19)፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲሁም ጠቢቡ ሰሎሞን ንጽህናዋን በትንቢት መነጽር አይቶ “ወዳጄ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፣ ምንም ነውር የለብሽም፡፡ ሙሽሪት ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፡፡” (መሓልይ 4፡7-16) በማለት በንጽህና በቅድስና ያጌጠች፣ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያልነካት፣ የድህነታችን ምክንያት፣ የንጽህናችን መሰረት የሰው ባህርይ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲዋሀድ ምክንያት የሆነች ንጽሕት የሰርግ ቤት ድንግል ማርያም በሊባኖስ የመወለዷን ነገር አስቀድሞ ነግሮናል፡፡ይህች ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀባት ዕለት ናት (ቅዱስ እንድርያስ)
የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ የከበረ ስለሆነው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ታላቅነት ‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል፤ የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ ዕለት (ጌታ) መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” በማለት ገልጾታል፡፡ በእውነት የእርሷ ልደት የልዑል ማደሪያው መቅደስ የተሰራበት ዕለት ነውና ሁላችን እናከብረዋለን፡፡ በዚህም ዕለት ‹‹ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም/ እነሆ ዛሬ በእመቤታችን ልደት ደስታ ሆነ›› እያልን እንዘምራለን። ይህችን የልዑል ማደሪያ እናቷ ሐናና አባቷ ኢያቄምም በእጅጉ ተደስተው በተወለደች በስምንተኛ ቀኗ ስሟን ‹‹ማርያም›› ብለው ሰይመዋታል፡፡
የእመቤታችን የልደት በዓል አከባበር
አባታችን አዳም በኃጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ንስሃ በገባ ጊዜ አምላካችን ጌታ እግዚአብሔር የድህነት ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ቃል ኪዳኑም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚል ነበር፡፡ ስለሆነም አዳም 5500 ዘመን የሕይወት ምክንያት የሆነች የልጅ ልጁ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአብራኩ ከተከፈሉ ቅዱሳን ልጆቹ የምትወለድበትን ቀን ተስፋ እያደረገ ኖረ፡፡ የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የመወለዷን ዜና ተስፋ በማድረግ “ሴት” ይላት የነበረውን ሚስቱን ሔዋንን በእመቤታችን ምሳሌነት “ሔዋን”፣ የሕያዋን ሁሉ እናት ብሎ ሰየማት፡፡ (ዘፍ. 3፡20) ዳግማዊ አዳም የተባለ ክርስቶስም የአዳምን ተስፋ በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ እውነተኛዋን ሔዋን (ዳግሚት፣ አማናዊት ሔዋንን) ድንግል ማርያምን በዮሐንስ ወንጌላዊ በኩል ለሕያዋን ምዕመናን ሁሉ እናት አድርጎ ሰጠ፡፡ (ዮሐ. 19፡26) ይህን የከበረ ምስጢር የማይረዳ “ክርስቲያን” እንዴት ያሳዝናል!? እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን የቀዳማዊ አባታችንን የአዳምን፣ እንዲሁም በዳግም ተፈጥሮ ያከበረንን ዳግማዊ አዳም የተባለ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ተቀብለን “የሕያዋን ሁሉ እናት” ድንግል ማርያምን ልደቷን በፍፁም ደስታ እናከብራለን፣ ከተወደደ ልጇ ምሕረትን ትለምንልን ዘንድም ወደ እርሷ እናንጋጥጣለን፡፡
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለን ምዕመናን ከጌታችን ልደት ቀጥሎ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የልደት በዓል የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን ነው፡፡ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል (ሉቃ 1፡14)›› ከተባለ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን?! የነቢያቱ ትንቢት የተፈፀመበት፣ የታየው ራዕይም በገሀድ የተከናወነበት፣ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ (ለሕያዋን ሁሉ) ታላቅ የደስታ ቀን ነው፡፡ ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም በንጽህናዋ በቅድስናዋ ተደንቀው “እህትነ ነያ/እህታችን እነኋት” ብለው ያመሰግኗታል፡፡ በዘመናችን ያሉ የሰዎች ልደት በድምቀት የሚከበር ከሆነ ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበ

ት ቀን ምንኛ ሊከበር ይገባው ይሆን?! ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ከዚህ ታላቅ በዓል በረከት ረድኤትን እንድናገኝበት ነው፡፡ የሕይወት ክርስቶስ እናት ዛሬ ተወልዳለችና፡፡
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት ‹‹ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ›› እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡ እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን፤ በምሕረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡
ምንጭ :- አስተምህሮ ዘተዋህዶ መካነ ድዕር
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit

#እንግዲህ ከዓለም ጫጫታ ርቀን በእናቶች ሳምንት ብፅዕት እናታችንን እንዳናስብ ብዙሁን ዘበዘቡን አደከሙንም! #ስለዚህ ይህን እል ዘንድ ግድ ሆነብኝ ።
አደባባዮ እራሱኮ የመስቀል ቅርጽ እንጂ የጨረቃና የኮከብ ቅርጾ የለውም ቢያንስ እርሱን እንኳን ለምን አይሰሙትም ?
ጨረቃና ከዋክብት እንኳ በስቅለቱ ወቅት ካንተ በላይ ሆነን ልንታይ አይገባንም ሲሉ ከሰማይ ወደ ምድር የረገፋ አይደለምን? አንዳንዴ ከመገለጫዎቻችን ካልተማርን ሳይገባን ነው ማለት ነው ምልክታችን አርገናቸው እንደ ቁራ የምንጮኸው።
#እንደው ድከሙ ሲላቸው እንጂ አብዛኛው የሀገራችን አደባባዮች ባለ መስቀል ናቸው። መስቀል የአደባባይ አደባባይም የመስቀል ነው! አደባባዮ ብዙ ዓይነት መፈክር እና ጥቅስ የተጠቀሰበት አደባባይ ቢሆንም ቅሉ ለእንዲህ ዐይነቶቹ ግን ይህ ይላቸዋል። "ዓለም በእኔ ዘንድ የተሰቀለ ነው እኔም በዓለም ዘንድ የተሰቀልኩኝ(የተመሳቀልኩ ፣መስቀለኛ የሆንኩ) ነኝ!
#ጥያቄያችሁ እንስገድበት ሳይሆን እንስገድለት ከሆነ እናፍጥርበት ሳይሆን መስቀሉን እናፍቅርበት ከሆነ ትድኑ ዘንድ በቀንም አምስት ጊዜ ከመታጠብ ታርፉ ዘንድ አምናችሁ አንዴ ተጠመቁ ያኔ እንተዋችዋለን።

#እንኳን_ለአባታችን_የፍልሰተ_አጽሙ_በዓል_በሰላም_አደረሰን 🙏
#ከደብረ_አስቦ (አሰቦት) ወደ #ደብረ_ሊባኖስ
#ኢትዮጵያዊው_ኤልሳዕ
በአጽሙ ሙት ያስነሳ
፪ኛ ነገሥት ፲ ፫÷፳ -፳ ፩
ገ/ተ ሃይማኖት ም/፶ ፫
አጥንት በመጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌነት ሲጠቀስ ሦስት ነገሮችን ያመለክታል።
፩ የሰው ኃይልን ያመላክታል መዝ ፶ ፫፥፭ ኢሳ፴ ፰፥፲ ፫
፪ የቅርብ ዝምድና መግለጫ ሆኖ ቀርቧል ዘፍ ፳ ፱÷፲ ፬ ሳሙ ፱÷፪
፫ የሞተ ሰውን ክብር ያስረዳል ዘፍ ፶÷፳ ፭ ዕብ ፲ ፩÷፳ ፪
# ይበልጡኑ_የቅዱሳን_ሰዎች ሞት /አጥንት (አጽም)/ እጅግ የከበረ ነው ። መዝ ፻ ፲ ፭ (፻
፲ ፮) ÷፲ ፭ ለአብነትም ተቀብሮ የነበረው የኤልሳዕ አጥንት /አጽም/ ሌላ የሞተ ሰው ከሞት እንዳስነሳ መመልከት በቂ ነው። ከሞዓብም አደጋ ጣዮች በየዓመቱ ወደ አገሩ ይገቡ ነበር።ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ። ፪ኛ ነገሥት ፲ ፫÷፳ - ፳ ፩
በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊው ኤልሳዕ ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖትም የሥጋ ድካም ከትጋቱ እንዳያስታጉለው በስምንት ሰለታም ጦር እራሱን ከቦ ከደብረ አስቦ ዋሻ ከቆመ ሳይቀመጥ
ከዘረጋ ሳያጥፍ ፳ ፪ ዓመት ሲጋደል ሳለ ከመቆም ብዛት አንዲቷ የእግሩ አገዳ ተሰበረችና ከሰውነቱ ተለይታ ወደቀች።
# ደቀ_መዛሙርቱም እንደ ማንም መስሏቸው ስባረ እግሩን ከመቃብር ሥፍራ ወረወሯት የኤልሳዕን አጽም ሲነካው ከሞት ድኖ እንደተነሳው ሰው የአባታችን የእግራቸው አጥንት
የነካው በመቃብሩ ሥፍራ ተቀብሮ የነበረ አንድ ሰው አፈፍ ብሎ ድኖ በእግሩ ቆመ ። ገ/ተ ሃይማኖት ፶ ፫
የአባታችንንም ስባረ አጽም (ስባረ እግር) እያመሰገነ ሰላምታ ሰጠ " ይህን ያዮ ደቀ
መዛሙርቶቻቸውም የጻድቁ ስባረ አጽም ገባሬ ተአምራት መሆኗን አውቀው ከመንበሩ እግር በታች አክብረው በሰበን ጠቅልለው ቀብረዋታል:: " #የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር
አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም። " መዝ ፴ ፫{፴ ፬}÷፲ ፱-፳
ይህ የቅዱሳን አጥንት (አጽም) #እግዚአብሔር የማይለየውና ሌት ተቀን የሚጠብቀው ነውና ቅዱሳን ጻድቃን ካረፉበት ሄዶ መሳለም በረከትን ያሰጣል ከሥጋም ከነፍስም ህመም አድኖ በጤና ያቆማልና የአጽማቸውን በዓል ማክበር እጅግ የሚገባ ነው ::
ቅዱስ ጳውሎስ በልብሱ ጨርቅ " (ሐዋ፲ ፱÷፲ ፩-፲ ፪) ቅዱስ ጴጥሮስ በሰውነቱ ጥላ ድውያንን ሁሉ ይፈውሳቸው ነበር ። ( ሐዋ ፭÷፲ ፭ ) ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው፣ የሥጋቸው ቅድስና ለለበሱት ልብስና ለአካላቸው ጥላ ተርፎ ድንቅ ተአምራትን የሚሰራ ከሆነ እግዚአብሔር የሚጠብቀው አጽማቸውማ እንዴት አብልጦ ድንቆችን አይሰራ?!:: #አጥንት_ለሰዉ ልጅ ተክለ ሰውነት ወሳኝ ድርሻ አለው። ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች
መካከል የተወሰኑት ብንዳስስ፤ ለሰዉነታችን ቅርፅ ለመስጠት፣ የሰዉነት የውስጥ አካላት (Organs) ከአደጋ ለመከላከል #ለምሳሌ ደረት የሚያርፍበት ክፍለ አጥንት ለሳንባና
ለልብ ከለላ(covering) ይሰጣል፤ የራስ ቅል አጥንት አንጎል ምንም አይነት ጉዳት
እንዳይገጥመው ጠንካራ ልባስ ሆኖ ይከላከላል ፣ ሥጋና ጡነቻዎቻችንን አጣብቆ ለመያዝና የካልስየም ንጥረ ነገርን ለማጠራቀም ይረዳል፡፡
ክቡር የሆነ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም ለቀናች ሃይማኖቱ አጥንት ነው። አጥንት የሌለው አካል ጤፍ እንደሌለው ማዳበሪያ መቆም አይቻለሁም:: ሀገሪቱና ቤተክርስቲያኒቱ ዶግማ ቀኖናና ትውፊቷን ይዛ ቅርጻን ሳትለቅ ቀጥ ብላ እንድትቆም አድርጓታልና።
#ምዕመኗ ልዮ ልዮ በሆነ በእግዳ ትምህርት ከበረትቷ እንዳይኮበልሉ ኖላዊ ትጉሁ ሆኖ በጾም በጸሎቱ የሀገር ዋልታ በመሆንም አካል ለምትባል ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደ አጥንት ጋሻ፣ መከታ፣ ጥላ ፣ከለላ ሆነላት። የሃይማኖት ማነስ የምግባር ጉድለት እንዳያጋጥማትም በቃሉ ትምህር በእጁ ተአምራት በበረከቱ ሞላት፤ በረድኤቱ ጋረዳት እንደ አጥንት የሃይማኖት መፍሰሻ ነቅ የወንጌል መፍለቂያ ምንጭም አደረጋት።
ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ጥር ፳ ፬\፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም # ለስባረ አጽሙ ከጻፍኩት በከፊል የተወሰደ::

#የዛከረው ዛኪር
አርዕስቷን በማልነግራችው የዶክተር ተብየው የዛኪር መጻሕፍ ላይ ከታሪክ እንደምንረዳው እስልምና የተመሠረተው በሰይፍ ኃይል ነው ለሚለው ሀሳብ የሰጠው መልስ የሚከተለው ነበር።
#ዛኪር:- እስልምና በኃይል አልተስፋፋም "እስላም" ማለት በራሱ "ሰላም" ማለት ነው ! ሰላምን ለማስከበረ ደግሞ ኃይል ያስፈልጋል።
#እንግዲህ አንባቢ ሆይ አስተውል " #እስላም " የሚለውን መጠሪያ ያለ ማስረጃ በቃል መቀራረብ ብቻ #ሰላም ማለት ነው ብሎ ተርጉሞታል። አያይዞም ሰላምን ለማስከበር ደግሞ ኃይል ያስፈልጋል። ሲል ከተነሳበት ሀሳብ ጋር በፍጽም ሰላም የማይሆን ንግግርን አክሎበታል ።
እንዴት ሊሆን ይችላል? በመዝገበ ቃላት ላይ ማነው እስላምን ሰላም ብሎ የተረጎመው? ቃሉ ከየት መጣ የሰውየው የውስጥ ፍላጎት ሳይሆን የቃሉ ትክክለኛ ጥሬ ዘር ምንን ያመለክታል ። እስልምና የሚለውስ ስም መስማት የተጀመረው ከመቼ ጀምሮ ነው ?
ከመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በገጀራና በሰይፍ በጀአዳዊ ጦርነቶችም ጭምር የተስፋፈው እስልምና የብዙ የንጹሐን ዜጎች ደመ መፈሰስ ምክንያት ሲሆን እንጂ ለዓለም ሰላም ሲሆን አላየነም አላነበብንም።
#ጸረ_ሰላም ኃይሎች ( #terrorism / ሽብርቸኝነት) የሚል ነገር እንኳን መስማት የጀመርነው ከእስልምና መስፉፉት ጋር ተያይዞ የመጣ የዓለም የሰላም ጠንቅ እንደሆነ ነው የምናውቀው ። ይህ ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ምሥጢር ነው ከቅርብ ትውስታችን እንኳን በሊቢያ ጠረፍ በሃይማኖታቸው ብቻ ለይተው ክርስቲያን ወንድሞቻችንን ያለ እርሕራሄ እንደ በግ ተገዝግዘው የተጣሉት በዚሁ እስልምናዊ ቡድን ነው።
ይህን የመሰለውን የዓለማችን ታይ ፎይድ፣ይህን የመሰለውን የዓለም የሰላም ቀውስን " ሰላም " ብሎ መተርጎም ዝም ብሎ በባዶ ሜዳ #መዳከር ነው።
ለቀድሞዋ አፈ ጉባኤ ለወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የሥራ ዕድል ማነው የሥልጣን ዕድል ለመፍጠር ተብሎ አላስፈላጊ መሥሪያ ቤት ያውም በምኒስቴር ደረጃ መቋቋሙ አግባብ አይደለም።
ሰላምኮ ውጤት እንጂ መንስኤ አይደለም መድረሻ እንጂ መገስገሻ አይደለም ። #የመተማመን ምኒስቴር ፣ #የተስፋ ምኒስቴር ፣ #የመፈቃቀር ምኒስቴር ማቋቋም ሳንችል ሰላም ምኒስቴር መመስረት ከንቱ መዳከር ነው ! ። ሰላም የእምነት የተስፋ እና የፍቅር ውጤት ነውና ። እምነት ተስፋና ፍቅር በሌሉበት እነሆ ሰላም ወዴት ይገኛል?
#አሁን_እስቲ የሰላም ምኒስቴር #የሥራ_ድርሻና_ፋይዳው ምንድ ነው?
___________________________________1 #የሰላም ጊዜ መምጫን በአህያ በተቀመጡ ነቢያት ከወዲሁ ማስተንበይ?
2 #ሰላም ሲመጣ ሰላም ሆነላችሁ ብሎ የሚያበሥር መብሠሬ ሰላም መሆን?
3 #በሰላም ስም የተመሰረተ ፌደራላዊ የእስላማዊ መዋቅር ማደርጀት? ዓላማና ተልዕኮው አልገባንም? !
ወደ ፊት ሚኒስትሯ ሰላም ማለት ኢስላም ማለት ነው ኢስላምም ማለት ሰላም ማለት ነው ሰላምን ለማስከበር ደግሞ ኃይል ያስፈልጋል ስለዚህ ምኒስትር መሥሪያ ቤቱ የራሱ የሆነ የጦር ኃይል ሊቋቋምለት ይገባዋል የሚል መግለጫ መስጠታቸው የማይቀር ነው። እኛ እንደሆንን እንቅልፉ ተመችቶናል!
__ #ንቁ_በሃይማኖት_ቁሙ _
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ግንቦት ፲ ፪ / ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም

#ዜና ዕረፍት !
____~_____
አዲስ አበባ በሚገኝው በደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን እስከ ሥጋዊ ሕይውታቸው ፍጻሜ ድረስ በጠበል ቤት ሕሙማንን በማጥመቅ ፈውሰ ጸጋ የነበራቸው እና በቅንነት ከ35 ዓመት በላይ ሲያገለግሉ የነበሩት አባታችን መምሬ ብሩ ታከለ ሰኞ ግንቦት 16 ቀን በድንገት ታመው ሆስፒታል ከሄዱ በኃላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማክሰኞ ለሊት ለረቡዕ አጥቢያ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።
እግዚአብሔር አምላክ የአባታችንን ነፍስ በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት እቅፍ ያኑርልን ከዚህ ቀጥለን አባታችን መምሬ ብሩ ታከለ በአንድ ወቅት እንዴትና ለምን ወደ ደብራችን ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን እንደመጡ የሰጡትን ምስክርነት እናስነብባችኋለን
#መምሬ_ብሩ_ታከለ ( #ገ/ሥላሴ )
ጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቡ አውራጃ አዲስ ዘመን ወረዳ መኖሪያ ቦታ ጎድንዲት ኪዳነምሕረት፥ ሥራ ቅስና ጎድንዲት ኪዳነምሕረት ማገልገል (አገልጋይ)። በ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. በወርኃ መስከረም ወር በገባ በ፳ ቀን ታመምሁ። የሕመሙ ዓይነት እንደ ልክፍት አድርጎ ይጥለኝ ነበር።
ሲጥለኝ አይታወቀኝም ነገር ግን ሊጥለኝ ሲል በገሀድ ቁመቱ እንደ ምሰሶ የረዘመ ጥቁር ሰው ይታየኛል። ያ ሰው ይመጣና ከትከሻዬ ላይ ይሰቀላል (ይቀመጣል)። በዚህ ጊዜ ኑህያዬን (አእምሮዬን ) አላውቀውም። ሲጥለኝ በየቀኑ ሆኖ በሦስት ሰዓት፣ በመዓልትና በስድስት ሰዓት፣ በዘጠኝ ሰዓት ቀድሼ በመጣሁበት ሰዓት ይጥለኝ ነበር። ሌሊት በሰው ተመስሎ ከበላዬ ተጭኖ ስለሚያድር፥ ራሴን አላውቅም ነበር። ይህም ብቻ አይደለም፥ ከአመመኝ ጊዜ ጀምሮ፥ ዳዊት መድገም የለም፣ ውዳሴ ማርያም ትቻለሁ፣ መቀደስ ማስቀደስ፣ ቃለ እግዚአብሔር መሳተፍ አልችልም ነበር። የደዌው መነሻ፥ በቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ እኔ በጸሐፊነት መምሬ በላይ ገላዬ በግምጃ ቤት አገልግሎት እንሠራ ነበር። ቤተ ክርስቲያቱ የሣር ስለ ነበረች፥ በቆርቆሮ አሠርተን፣ ቅጽር አስቀጽረን፣ መንበር አሠርተን ከወጪ ቀሪ ገንዘብ ነበር። ያን ቀሪ መቶ ሃምሳ ስድስ ብር መምሬ በላይ ገላዬ ስለ በላው፤ ካህናቱና ምእመናን ገባኤ አድርገው፥ ጸሐፊም ተቆጣጣሪም ስለ ነበርሁ፥ የሒሳብ መዝገቡን አቅርብ ተብዬ አቀረብሁ። መቶ ሃምሳ ስድስ ብር ጉድለት ተገኘ። አገሬው . . . . (ጉባኤው) ክፈል ቢለው እንቢ ስላለ፥ በዳኛ ተከሶ ከፈለ። በኋላም አገሬው እርሱን ሽረናል፤ በግምጃ ቤትነት መምሬ ብሩ ይሠራልናል ብለው
በሌለሁበት መረጡኝ። ጸሐፊነቱና ተቆጣጣሪነቱን ለቄስ አጠና ከበደ ሰጡት። በግድ ተረከብ ብለው የግጃ ቤትትነት ሥራውን ተረከብሁ።
#ከዚያ ይዤ . . . ስሠራ፥ መምሬ በላይ በዚሁ ምክያት ቂም ይዞ፥ ከቤተ ክርስቲያን ስወጣ መዝጊያ እየዘጋሁ ሳለ፤ በጨለማ ተከልሎ በዱላ ማዥራቴን መታኝ። ከቅድስቱ የመቆሚያ ሰሌን ላይ ወደቅሁ። ከዚያ በኋላ የሆንሁትን አላውቅምና አብረውኝ የቀደሱት ደጀ ሰላም ገብተው የነበሩት ቀረብንሳ ብለው ዲያቆን ጠጋ ፈረድን እንዲፈልገኝ ላኩ። ቢያየኝ ከዚያ ወድቄ ራሴን ስቼ አገኘኝ። እሪ ብሎ ያሉት ሁሉ ተሰብሰው መጡ።
ተጯጩኸው አገሬው ሰምቶ ቄስ በላይን ያዙት። ቢጠየቅ አዎን መትቼዋለሁ ብሎ ለገበሬ ማኅበሩ ሊቀ መንበር ገለጠ። እኔን በቃሬዛ ተሸክመው፥ ሕይወቴን (ራሴን) ሳላውቅ፤ የመታኝንም ቄስ በላይን ይዘው፥አዲስ ዘመን ከሊቡ አውራጃ አስተዳደር አቀረቡን። ተጠይቆ ያንኑ ለገበሬ ማኅበር
ሊቀመንበር የሰጠውን ቃል ሰጠ። እርሱ ወደ እሥር ቤት ተላላፈ። እኔም ወደ ሐኪም ቤት ተወሰድሁ። ወር ያህል በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ስረዳ ቆይቼ አልሻል ስላለኝ፤ በጎንደር ክፍለ ሀገር ካለው ቼቼላ ሆስፒታል ገባሁ።
#ሁለት ሳምንት ሆስፒታል ተኛሁ። የጭን መርፌ፣ የትከሻ መርፌና የሚዋጥ ኪኒን ተደረገልኝ (ተሰጠኝ)። አልፎ አልፎ ነብሴን (ራሴን) ባውቅም የሚጥለኝ ደዌ ሲመጣብኝ ግን ሊሻለኝ አልቻለም። ከዚህ በኋላ ጠበል ይሻልሀል ብለው ሊቦ ጎዮርጊስ ተወሰድሁ። እዚያ ተስፋ ሳላገኝ ቀረሁ። ጎንድ ተክለሃይማኖት ጠበል ሄድሁ፥ እዚያም ተስፋ አላገኘሁም። ዙሬ ተመልሼ ደብረ ታቦር አውራጃ ሕክምና ይሻላል ብለው ከደብረ ታቦር ሆስፒታል ወሰዱኝ።
ምርመራ ተደርጎልኝ አዲስ አበባ አማኑኤል ሆስፒታል ተወስዶ ካልዳነ ከዚህ ልንረዳው አንችልም ተብየ ተሰናበትሁ። ከዚያ ተመልሼ ቤቴ ገባሁ። በገባሁ በአምስት ቀኔ ቤተ ዘመዶቼ ተስፋ ቆርጠው አይድንም ብለው ተዉኝ። ከዚያ በኋላ ከዘመድም ከባዕድም ብዬ ለማምኜ፥ ሞቴን ሞት ያድርገው ብዬ መቶ ሠላሳ ብር ይዤ አዲስ ዘመን መኪና ተሳፍሬ ባሕር ዳር ደስኩ። ከመኪና ወርጄ ለምሳ ስንዘጋጅ ሕመሙ ተነሥቶብኝ ጣለኝ። ዘመድ ተመስሎ አንድ ሰው ደገፈኝ። ትንሽ ነብሴን ሳውቀው፥ ያው ደግፎ የያዘኝ ሰው የት ልትሔድ ነው? ብሎ ጠየቀኝ። አዲስ አበባ አማኑኤል ሆስፒታል ነው የምሄደው አልሁት። እኔም አብሬህ እሄዳለሁ፥ ዘመዶች ከሆስፒታሉ አሉኝ፤ አስታምሜ እመልስሃለሁ አለኝ። እውነት መስሎኝ ዘመድ አርድጌው ደግፍና ከመኪናው ስቀለኝ (አሳፍረኝ) አልሁት። ገድፎ አሳፍሮኝ ቡሬ በዓሥር ሰዓት ደረስን። አውታንቲው መኝታ ፈልጉና አልቤርጎ እደሩ ብሎን ወረድን። ከወረድን በኋላ ያሰው ዘመድ አለኝ የማሳድርህ ቦታ አለ ብሎ ወደ በረሐ ይዞኝ ሄደ።
#ከዚያ በረሐ እንደ ደረስን፥ ከዚህ ነው የምተኛው አለኝ። የዚያን ጊዜ ሊዘርፈኝ እንዳሰበ ዐወቅሁና ስደነግጥ አእምሮዬን ስቼ ወደቅሁ። በነጻ እንድታከም ከገበሬ ማኅበር ያወጣሁትን
ደብዳቤና አንድ መቶ ብር በአንድ ላይ አሥሬ የያዝሁትን ወሰደብኝ። ሕመሙ ጋብ ብሎ አእምሮዬ እንደ ተመለሰ ሳውቀው፥ ሰውየውም ጠፋ ኪሴም ባዶ ሆነ። ከዚያው በጨለማ ውስጥ ሳለቅስ አደርሁ። ምነው ብትገድለኝ ከምሰቃይ ብዬ ወደ ፈጣሪዬ አለቀስሁ። የጎጃም ጅብ አጠገቤ እየመጣ ይጮኻል፥ ግን ሳይበላኝ አደርሁ። ሲነጋ ወደ ቡሬ ከተማ ገባሁ። የተሳፈርሁበት መኪና የት እንዳለ ብጠይቅ ሄዷል ተባልሁ። ከዚያ ወዲያ ሳለቅስ አንድ ብርም ሁለት ብርም ብሎ ሕዝቡ በአዘኔታ ሰጠኝ። ዓሥራ ሦስት ብር አገኘሁ። ያንኑ ዕለት መኪና ተሳፍሬ አዲስ አበባ ከቀኑ ዓሥር ሰዓት ሲሆን ገባሁ።
#አውቶቢስ ተራ ከመኪና እንደወረድሁ ኑህዬን . . . (አእምሮዬን) አላወቅሁም። አንድ አዛውንት ሽማግሌ ደግፈውኝ ቆይተው ቆይተው፥ አእምሮዬ ሲመልስልኝ ከየት ነው የመጣኸው? ብለው ጠየቁኝ። ከጎንደር ነው አልኋቸው። ዘመድ አለህ ብለው ቢጠይቁኝ፥ ዘመድ እንኳ የለኝም። ነገር ግን ከሀገሬ ሳለሁ የማውቃቸው አንድ ቄስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አሉና የአማኤልን ቤተ ክርስቲያ ያሳዩኝ አልኋቸው። ሰውየውም ወስደው አሳዩኝ። የማውቀውንም ቄስ አገኘሁት። መምሬ ጸዳሉ ይልማ ይባላል። ቄሱም የመጣሁበትን ምክያት ጠየቀኝ። ስለታመምሁ ለሕክምና ነው የመጣሁት ማደሪያ ፈልግልኝ አልሁት። የንስሐ ልጁ ስዕለ ማርያም የምትባል ዘንድ ወስዶ፥ እባክዎን ይህንን ሰው ያሳድሩልኝ፤ ነገ*አማኑኤል ሆስፒታል እወስደዋለሁ አለ። በዚህ ሁኔታ ሴትየዋ ቤት ሰጥተውኝ ከዚያ አደርሁ።
#ሌሊት_ተኝቼ በሕልሜ፥ ሀገር ቤት የማውቀው መኰንን የሚባል ቀይ ሰው፤ የቤተ ክርስቲያን መቋሚያ ይዞ፥ አንተ ተክለሃይማኖት ተጠመቅ እንጂ፥ ይህ ሐኪም ምንም እይሠራልህም ብሎ ይለኛል።

የተክለሃይማኖትን ቤተ ክርስቲያን መቼ ዐውቀዋለሁ? ብዬ ስለው፤ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አሉልህ ብሎ ይለኛል። ወደ ምሥራቅ ስሄድ፥ የደብረ አሚን ተክለሃይማኖትን ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ቤተ ክርስቲያን ዐየሁ። ከቤተ ክርስቲያኑ ደረጃ ላይ ሦስት መነኰሳት አገኛለሁ። ሁለቱ ይይዙኝና አንደኛው እንደ ቱቦ ባለ ነገር ሲያጠምቀኝ ዐየሁ።
አረ ለቀቅሁኝ ለቀቅሁኝ እያልሁ የምጮኽ ይመስለኛል። በሕልሜ ስጮኽ ድምፄ ተሰምቷቸው ሴትዮይቱ ዳጃፉን ቆፍቁፈው (ቆርቁረው)፥ ምን ሁነህ ትለፈልፋለህ? አሉኝ። ለፈለፍሁ? አልዃቸው። አዎ አሉኝ። ኧረ ሕልም ታይቶኝ ነው አልኋቸው።
ወዲያውም ተክለሃይማኖት ከዚህ ሀገር አለ ወይ? አልዃቸው። አዎን አሉኝ። ወዴት ናቸው? ብዬ ብላቸው፥ ወደ ጸሐይ መውጫ ናቸው ያሉት ቅርብ ናቸው ብለው አሉኝ። ጠበል
አላቸው ወይ ብዬ ብላቸው አዎን አለ፤ ማንም የክፍለ ሀገር ሕዝብ እየመጣ የሚድንባቸው ናቸው። በጋዜጣም ተጽፏል አሉኝ። እንግዲያስ ማለዳ እንዲያሳዩኝ አልዃቸው።
ማልዳ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘውኝ ሲመጡ፥ ከቅጽረ ጊቢው ልገባ ስል፤ ከቤተ ክርስቲያኑ (ፊቴ) . . . ፊት ለፊት ላይ ቀስተ ደመና ተተክሎ ዐየሁ። መሄድ አቅቶኝ ተጎንብሼ ከትከሻዬ ላይ ትልቅ ሸክም የተሸከምኩ የመሰለኝ ሰው፤ ቀስተ ደመናውን እንዳየሁ፥ ሸክሙ ወርዶ ከጀርባዬ ሲወድቅ ተሰማኝ። ምን ዕቃ ጣልሁ? ብዬ ወደ ኋላዬ ዘወር ብል፥ ባዶ ሆነ። ከዚያ በኋላ ትከሻዬን ስለ ለቀቀኝ ቀና አልሁ። ቤተ ክርስቲያ ሄጄ ተሳልሜ በመስቀል አማተብሁ።
በስመ አብ ብዬ ለመጸለይ በቃሁ። የዕለት ውዳሴ ማርያም መጽሐፈ ጎልጎታ ደገምሁ። ከዚህ በኋላ ወደ ጠበሉ ገባሁ። ባዩህና አሰፋ ከየት እንደ መጣሁ ጠየቁኝ። ከጎንደር አልኋቸው። አስታማሚ የለኝም ብዬ ብነግራቸው፥ በነጻ ትጠመቃለህ ማደሪያ ፈልግ ተባልሁ። እሺ ብዬ ተጠመቅሁ። ምንም ሳያስጮኸኝ አንደበቴም ሕሊናዬም ተመለሰልኝ።
ከሴትዮይቱ ቤት እያደርሁ ሰባት ቀን በተከታታይ ተጠመቅሁ። ሴትዮይቱም
እንዳልከብዳቸው ራሴን ስለቻልሁ ማደሪያ ቤት ስጡኝ ብዬ እነባዩህን (እንባዬን)
ለመንኋቸው። ለሰባት ቀን ብቻ ከአዳሹ ግባ አሉኝና ገባሁ።
ሰባት ቀን ተጠመቅሁ። እነሱም ውጣም አላሉኝ። ጠበሉን ስለወደድሁት እንደ ሱባኤ አድርጌ ጸሎት እያደረግሁ ተጠመቅሁ። ጤናዬን ካገኘሁ አገሬ አልሄድም ብዬ እስከ አሁን አለሁ። ከሚያዝያ ፳፱ ቀን ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. ጀምሮ፥ እስከ ዛሬ የካቲን ፫ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. ድረስ እዚሁ ጠበል ቤት እየተጠመቅሁ፤ በቤተ ክርስቲያንም እያገለገልሁ አለሁ። ልብሴም ጉርሴም አባቴ ተክሃይማኖት ሁነውኝ እስከ አሁን አለሁ።
ምንጭ :- ምክሖን ለደናግል Mkhon Ledenagil

__ # አባቴ ወዴት ኖት? _
የምን ጫጫታ ነው የምን ጭነት ነገር?
ወዴት መሄዶት ነው አባ ከዚህ መንደር?
ፍቱት አትሰሩ አያስቸግረኝም
ብሎ የሚስፈታኝ ከንግዲ አላገኝም
እጽናናለሁ እንጂ በርሶ ሥልጣን ፍቺህ
የጸና ነውና በሰማዮም ደጅህ
አባቴ ወዴት ኖት? ጭነቱስ ወዴት ነው?
ለአልጋ ቁራኞች፤ ለድዌ ዳኞች
ባላወቁት ገመድ ለዋሌት እስረኞች
ባልቋጠሩት ገመድ ለተተበተቡ
አልቅሰው ሲያጠምቁ
አጥምቀው ሲያለቅሱ
የዘመድ ቄስ ሆነው እየፈቱ ያነቡ
አባቴ ወዴት ኖት? ጭነቱስ ወዴት ነው?
በጻድቁ ተአምር በርሶ አጥማቂነት
ለስንቱ እስረኛ መፍትሔ ሆኑለት
ወዴት መሄዶት ነው ከመሸ ሽሽት
እዚም አፈር አለ ለጭነት ጭነት
አባቴ ወዴት ኖት? ጭነቱስ ወዴት ነው?
ሕመምተኛው ፋዋሽ ባለ ጠጋው ነዳይ
ያለኝ ጥቂት ነገር ይበቃኛልም ባይ
የማይደለሉ በነ ፍቅረ ነዋይ
አባቴ ወዴት ኖት? ጭነቱስ ወዴት ነው?
ደርሼ ሳልጦሮት አባ ብሩ ብዬ
ደህና ነህ ? እንዴት ነህ?
ተሻለህ ያሉኝን ያችን ቀን ቆጥሬ
ለምን ተሳፈሩ ?
ከሰፈር ከደብሩ?
ምስጋና ሳይሹ
ለነገሩ ተውት ገብቶኛል ዘይግይቶ
በጸሎት ያቆሞት ከሞት ያስጣሉት
የዘገየ ምንዳ ምን ያሊደርግሎት
አንዳንድ ሰው አለ ሲሰጥ የማይጠብቅ
ስለሰጠው ፈንታ
ለዋለው ውለታ
አይሻም ወረታ
አንዳንድ ሰው አለ ውሎ የሚውልብህ
በቅን ሥጦታ ውስጥ በቸርነት ሥራ
መቀበል እንዳለ ፈጽሞ የረሳ
አንዳንድ ሰው አለ ! አንድ ጊዜ ቸሮ
ብዙሁን ጊዜ አውርቶ ብዙሁን ቀምሮ
በእጅሁ የካበውን የጽድቁን ግድግዳ
በአፉ ዜሮ ብዜት ያስከተ ናዳ
አባቴ ወዴት ኖት? ጭነቱስ ወዴት ነው?
ከንግዲህ አልሎትም
በሥራህ ባልገባ ባላዝ በሥልጣንህ
ደስታ ከሞላበት ይግቡ ከእልፍኝህ
ከአባትህ ቡሩካን ደምርልኝ እባክህ
ወንጌልን ኖረዋል
ታምሜ መተዋል
ጎብኝተውኝማል
መሳፈሪያው ዕድሜ መገስገሻው ሞት
ሥራችን መግቢያችን ይህቺ ናት ገነት
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ግንቦት ፲ ፱ ቀን/ ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም photography cradit እናት ማኅበሬምክሖን ለደናግል
Mkhon Ledenagil

#ኑ_ይህን_ድንቅ_እዩ !
______________
#የእመቤታችን በደብረ ምጥማቅ ለ"፭ ቀናት ያክል የመገለጥ በዓል
#ከቅዱሳን_ክብር_የማርያም_ክብር_ይበልጣል ፤ የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና። መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማሕፀንዋ ተሸከመችው። ይህች ከኪሩቤል ትበልጣለች፤ ከሱራፌልም ትበልጣለች ከሦስቱ አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና። የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ይህች ናት።
#ለቅዱሳን_ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት። በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሁኗልና።
#ኑ_ይህንድንቅ_እዩ። ስለተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና፤ቃል ተዋሕዷልና ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፤ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት።
የማይታወቅ ተገለጠ፤ የማይታይ ታየ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በርግጥ ሰው ሆነ። ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለትና እናመስግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው። #ቅድስት_ሆይ_ለምኝልን።
____ሶሪያዊው_ቅዱስ_ኤፍሬም_የረቡዕ ውዳሴ ማርያም____