#ኑ_ይህን_ድንቅ_እዩ !
______________
#የእመቤታችን በደብረ ምጥማቅ ለ"፭ ቀናት ያክል የመገለጥ በዓል
#ከቅዱሳን_ክብር_የማርያም_ክብር_ይበልጣል ፤ የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና። መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማሕፀንዋ ተሸከመችው። ይህች ከኪሩቤል ትበልጣለች፤ ከሱራፌልም ትበልጣለች ከሦስቱ አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና። የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ይህች ናት።
#ለቅዱሳን_ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት። በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሁኗልና።
#ኑ_ይህንድንቅ_እዩ። ስለተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና፤ቃል ተዋሕዷልና ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፤ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት።
የማይታወቅ ተገለጠ፤ የማይታይ ታየ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በርግጥ ሰው ሆነ። ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለትና እናመስግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው። #ቅድስት_ሆይ_ለምኝልን።
____ሶሪያዊው_ቅዱስ_ኤፍሬም_የረቡዕ ውዳሴ ማርያም____