ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ዜና ዕረፍት !
____~_____
አዲስ አበባ በሚገኝው በደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን እስከ ሥጋዊ ሕይውታቸው ፍጻሜ ድረስ በጠበል ቤት ሕሙማንን በማጥመቅ ፈውሰ ጸጋ የነበራቸው እና በቅንነት ከ35 ዓመት በላይ ሲያገለግሉ የነበሩት አባታችን መምሬ ብሩ ታከለ ሰኞ ግንቦት 16 ቀን በድንገት ታመው ሆስፒታል ከሄዱ በኃላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማክሰኞ ለሊት ለረቡዕ አጥቢያ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።

እግዚአብሔር አምላክ የአባታችንን ነፍስ በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት እቅፍ ያኑርልን ከዚህ ቀጥለን አባታችን መምሬ ብሩ ታከለ በአንድ ወቅት እንዴትና ለምን ወደ ደብራችን ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን እንደመጡ የሰጡትን ምስክርነት እናስነብባችኋለን
#መምሬ_ብሩ_ታከለ ( #ገ/ሥላሴ )

ጎንደር ክፍለ ሀገር ሊቡ አውራጃ አዲስ ዘመን ወረዳ መኖሪያ ቦታ ጎድንዲት ኪዳነምሕረት፥ ሥራ ቅስና ጎድንዲት ኪዳነምሕረት ማገልገል (አገልጋይ)። በ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. በወርኃ መስከረም ወር በገባ በ፳ ቀን ታመምሁ። የሕመሙ ዓይነት እንደ ልክፍት አድርጎ ይጥለኝ ነበር።
ሲጥለኝ አይታወቀኝም ነገር ግን ሊጥለኝ ሲል በገሀድ ቁመቱ እንደ ምሰሶ የረዘመ ጥቁር ሰው ይታየኛል። ያ ሰው ይመጣና ከትከሻዬ ላይ ይሰቀላል (ይቀመጣል)። በዚህ ጊዜ ኑህያዬን (አእምሮዬን ) አላውቀውም። ሲጥለኝ በየቀኑ ሆኖ በሦስት ሰዓት፣ በመዓልትና በስድስት ሰዓት፣ በዘጠኝ ሰዓት ቀድሼ በመጣሁበት ሰዓት ይጥለኝ ነበር። ሌሊት በሰው ተመስሎ ከበላዬ ተጭኖ ስለሚያድር፥ ራሴን አላውቅም ነበር። ይህም ብቻ አይደለም፥ ከአመመኝ ጊዜ ጀምሮ፥ ዳዊት መድገም የለም፣ ውዳሴ ማርያም ትቻለሁ፣ መቀደስ ማስቀደስ፣ ቃለ እግዚአብሔር መሳተፍ አልችልም ነበር። የደዌው መነሻ፥ በቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ እኔ በጸሐፊነት መምሬ በላይ ገላዬ በግምጃ ቤት አገልግሎት እንሠራ ነበር። ቤተ ክርስቲያቱ የሣር ስለ ነበረች፥ በቆርቆሮ አሠርተን፣ ቅጽር አስቀጽረን፣ መንበር አሠርተን ከወጪ ቀሪ ገንዘብ ነበር። ያን ቀሪ መቶ ሃምሳ ስድስ ብር መምሬ በላይ ገላዬ ስለ በላው፤ ካህናቱና ምእመናን ገባኤ አድርገው፥ ጸሐፊም ተቆጣጣሪም ስለ ነበርሁ፥ የሒሳብ መዝገቡን አቅርብ ተብዬ አቀረብሁ። መቶ ሃምሳ ስድስ ብር ጉድለት ተገኘ። አገሬው . . . . (ጉባኤው) ክፈል ቢለው እንቢ ስላለ፥ በዳኛ ተከሶ ከፈለ። በኋላም አገሬው እርሱን ሽረናል፤ በግምጃ ቤትነት መምሬ ብሩ ይሠራልናል ብለው
በሌለሁበት መረጡኝ። ጸሐፊነቱና ተቆጣጣሪነቱን ለቄስ አጠና ከበደ ሰጡት። በግድ ተረከብ ብለው የግጃ ቤትትነት ሥራውን ተረከብሁ።

#ከዚያ ይዤ . . . ስሠራ፥ መምሬ በላይ በዚሁ ምክያት ቂም ይዞ፥ ከቤተ ክርስቲያን ስወጣ መዝጊያ እየዘጋሁ ሳለ፤ በጨለማ ተከልሎ በዱላ ማዥራቴን መታኝ። ከቅድስቱ የመቆሚያ ሰሌን ላይ ወደቅሁ። ከዚያ በኋላ የሆንሁትን አላውቅምና አብረውኝ የቀደሱት ደጀ ሰላም ገብተው የነበሩት ቀረብንሳ ብለው ዲያቆን ጠጋ ፈረድን እንዲፈልገኝ ላኩ። ቢያየኝ ከዚያ ወድቄ ራሴን ስቼ አገኘኝ። እሪ ብሎ ያሉት ሁሉ ተሰብሰው መጡ።
ተጯጩኸው አገሬው ሰምቶ ቄስ በላይን ያዙት። ቢጠየቅ አዎን መትቼዋለሁ ብሎ ለገበሬ ማኅበሩ ሊቀ መንበር ገለጠ። እኔን በቃሬዛ ተሸክመው፥ ሕይወቴን (ራሴን) ሳላውቅ፤ የመታኝንም ቄስ በላይን ይዘው፥አዲስ ዘመን ከሊቡ አውራጃ አስተዳደር አቀረቡን። ተጠይቆ ያንኑ ለገበሬ ማኅበር
ሊቀመንበር የሰጠውን ቃል ሰጠ። እርሱ ወደ እሥር ቤት ተላላፈ። እኔም ወደ ሐኪም ቤት ተወሰድሁ። ወር ያህል በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ስረዳ ቆይቼ አልሻል ስላለኝ፤ በጎንደር ክፍለ ሀገር ካለው ቼቼላ ሆስፒታል ገባሁ።

#ሁለት ሳምንት ሆስፒታል ተኛሁ። የጭን መርፌ፣ የትከሻ መርፌና የሚዋጥ ኪኒን ተደረገልኝ (ተሰጠኝ)። አልፎ አልፎ ነብሴን (ራሴን) ባውቅም የሚጥለኝ ደዌ ሲመጣብኝ ግን ሊሻለኝ አልቻለም። ከዚህ በኋላ ጠበል ይሻልሀል ብለው ሊቦ ጎዮርጊስ ተወሰድሁ። እዚያ ተስፋ ሳላገኝ ቀረሁ። ጎንድ ተክለሃይማኖት ጠበል ሄድሁ፥ እዚያም ተስፋ አላገኘሁም። ዙሬ ተመልሼ ደብረ ታቦር አውራጃ ሕክምና ይሻላል ብለው ከደብረ ታቦር ሆስፒታል ወሰዱኝ።
ምርመራ ተደርጎልኝ አዲስ አበባ አማኑኤል ሆስፒታል ተወስዶ ካልዳነ ከዚህ ልንረዳው አንችልም ተብየ ተሰናበትሁ። ከዚያ ተመልሼ ቤቴ ገባሁ። በገባሁ በአምስት ቀኔ ቤተ ዘመዶቼ ተስፋ ቆርጠው አይድንም ብለው ተዉኝ። ከዚያ በኋላ ከዘመድም ከባዕድም ብዬ ለማምኜ፥ ሞቴን ሞት ያድርገው ብዬ መቶ ሠላሳ ብር ይዤ አዲስ ዘመን መኪና ተሳፍሬ ባሕር ዳር ደስኩ። ከመኪና ወርጄ ለምሳ ስንዘጋጅ ሕመሙ ተነሥቶብኝ ጣለኝ። ዘመድ ተመስሎ አንድ ሰው ደገፈኝ። ትንሽ ነብሴን ሳውቀው፥ ያው ደግፎ የያዘኝ ሰው የት ልትሔድ ነው? ብሎ ጠየቀኝ። አዲስ አበባ አማኑኤል ሆስፒታል ነው የምሄደው አልሁት። እኔም አብሬህ እሄዳለሁ፥ ዘመዶች ከሆስፒታሉ አሉኝ፤ አስታምሜ እመልስሃለሁ አለኝ። እውነት መስሎኝ ዘመድ አርድጌው ደግፍና ከመኪናው ስቀለኝ (አሳፍረኝ) አልሁት። ገድፎ አሳፍሮኝ ቡሬ በዓሥር ሰዓት ደረስን። አውታንቲው መኝታ ፈልጉና አልቤርጎ እደሩ ብሎን ወረድን። ከወረድን በኋላ ያሰው ዘመድ አለኝ የማሳድርህ ቦታ አለ ብሎ ወደ በረሐ ይዞኝ ሄደ።

#ከዚያ በረሐ እንደ ደረስን፥ ከዚህ ነው የምተኛው አለኝ። የዚያን ጊዜ ሊዘርፈኝ እንዳሰበ ዐወቅሁና ስደነግጥ አእምሮዬን ስቼ ወደቅሁ። በነጻ እንድታከም ከገበሬ ማኅበር ያወጣሁትን
ደብዳቤና አንድ መቶ ብር በአንድ ላይ አሥሬ የያዝሁትን ወሰደብኝ። ሕመሙ ጋብ ብሎ አእምሮዬ እንደ ተመለሰ ሳውቀው፥ ሰውየውም ጠፋ ኪሴም ባዶ ሆነ። ከዚያው በጨለማ ውስጥ ሳለቅስ አደርሁ። ምነው ብትገድለኝ ከምሰቃይ ብዬ ወደ ፈጣሪዬ አለቀስሁ። የጎጃም ጅብ አጠገቤ እየመጣ ይጮኻል፥ ግን ሳይበላኝ አደርሁ። ሲነጋ ወደ ቡሬ ከተማ ገባሁ። የተሳፈርሁበት መኪና የት እንዳለ ብጠይቅ ሄዷል ተባልሁ። ከዚያ ወዲያ ሳለቅስ አንድ ብርም ሁለት ብርም ብሎ ሕዝቡ በአዘኔታ ሰጠኝ። ዓሥራ ሦስት ብር አገኘሁ። ያንኑ ዕለት መኪና ተሳፍሬ አዲስ አበባ ከቀኑ ዓሥር ሰዓት ሲሆን ገባሁ።
#አውቶቢስ ተራ ከመኪና እንደወረድሁ ኑህዬን . . . (አእምሮዬን) አላወቅሁም። አንድ አዛውንት ሽማግሌ ደግፈውኝ ቆይተው ቆይተው፥ አእምሮዬ ሲመልስልኝ ከየት ነው የመጣኸው? ብለው ጠየቁኝ። ከጎንደር ነው አልኋቸው። ዘመድ አለህ ብለው ቢጠይቁኝ፥ ዘመድ እንኳ የለኝም። ነገር ግን ከሀገሬ ሳለሁ የማውቃቸው አንድ ቄስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አሉና የአማኤልን ቤተ ክርስቲያ ያሳዩኝ አልኋቸው። ሰውየውም ወስደው አሳዩኝ። የማውቀውንም ቄስ አገኘሁት። መምሬ ጸዳሉ ይልማ ይባላል። ቄሱም የመጣሁበትን ምክያት ጠየቀኝ። ስለታመምሁ ለሕክምና ነው የመጣሁት ማደሪያ ፈልግልኝ አልሁት። የንስሐ ልጁ ስዕለ ማርያም የምትባል ዘንድ ወስዶ፥ እባክዎን ይህንን ሰው ያሳድሩልኝ፤ ነገ*አማኑኤል ሆስፒታል እወስደዋለሁ አለ። በዚህ ሁኔታ ሴትየዋ ቤት ሰጥተውኝ ከዚያ አደርሁ።

#ሌሊት_ተኝቼ በሕልሜ፥ ሀገር ቤት የማውቀው መኰንን የሚባል ቀይ ሰው፤ የቤተ ክርስቲያን መቋሚያ ይዞ፥ አንተ ተክለሃይማኖት ተጠመቅ እንጂ፥ ይህ ሐኪም ምንም እይሠራልህም ብሎ ይለኛል።