አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የኔልሰን #ሮህሊላ #ማንዴላ #አጭር #የህይወት #ታሪክ

ሮሊላሂላ ማንዴላ የተወለዱት ፣ ትራንስኪ በተባለው የደቡብ አፍሪካ ከተማ ጁላይ 18 ቀን 1918 ዓም ነው። ኔልሰን የሚለውን ስማቸውን ያገኙት ከጊዜ በኋላ ከአንድ አስተማሪያቸው እንደሆነ የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል። በተወለዱበት አካባቢ ባለው ቲምቡ ጎሳም በአካባቢው ሰው “ማዲባ” በሚል ስም ይጠራሉ።
አባታቸው ፣ ማንደላ የ 9 ዓመት ልጅ ሳሉ ነው የሞቱት። ማንዴላ 23 ዓመት ሲሞላቸው በጎሳው ደንብ መሰረት የሚመጣላቸውን ሚስት ላለማግባት ሲሉ ያደጉበትን ከተማ ትተው ወደ ጆሃንስበርግ ሄዱ።
በ 25 ዓመታቸው ዩኒቨርሲቲ በመግባት ማንዴላ በፎርት ሃሬ ዩኒቨርሲቲ እና በዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ ተምረው በ1942 በህግ ተመርቀዋል። በተመረቁ በሁለተኛው ዓመት የመጀመሪያ ሚስታቸው የሆኑትን ኤቪሊን ማሴ በማግባት አራት ልጆችን አፈሩ። በ1958 እስከተለያዩበት ቀን ድረስ አብረው ቆይተዋል። ከዚያ ፊታቸውን ወደ ትግሉ በማዞር የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ በተባለው ፓርቲ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆን ጀመሩ። በ1952 ማንዴላ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳት በመሆን የአፓርታይድ ሥርዓትን በጽኑ መታገል ጀመሩ። በ1956 ማንዴላ በአገር ክህደት ወንጀል በጊዜው በነበረው የነጮች መንግስት ተከሰሱ- ክሱ አምስት ዓመት ያህል በክርክር ከቆየ በኋላ ማንዴላ በክርክሩ አሸነፉ።
በማርች ወር 1960 ዓም፣ ሻርፕቪል በተሰኘችው ከተማ ፣ ጸረ አፓርታይድ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ ከነበሩት ጥቁር ሰልፈኞች መካከል 69 ያህሉን ፖሊሶች ተኩሰው በመግደላቸው ብጥብጡ ከፍ ያለ ደረጃ ደረስ። የወቅቱ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ እንቅስቃሴ ሲከለክል እንደማንዴላ በበኩላቸው ሰላማዊ ትግል እንደማያዋጣ በማመን ልዩ የጦር ሃይል አደራጁ። ማንዴላም የጦሩ የበላይ አዛዥ በመሆኑ እርዳታ ፍለጋ ወደሌሎች አገራት ጉዞ ማድረግ ጀመሩ።
ከውጭ አገር ሲመለሱ እዚያ ደቡብ አፍሪካ ላይ ተያዙና አምስት ዓመት እስር ተፈረደባቸው። በ1963 እንደገና ማንዴላና ሌሎች የ ኤ ኤን ሲ መሪዎች መንግስትን በሃይል ለመገልበጥ የሚል ክስ ተከፈተባቸውና ፍርድ ቤት ቀረቡ። ከዚያም ማንዴላ ዕድሜ ይፍታህ ተፈረደባቸውና ሮቢን ደሴት ያለ እስር ቤት ተላኩ። ማንዴላ ከሮቢን ደሴት ሌላ በተዘዋወሩባቸው ተጨማሪ እስር ቤቶች በጠቅላላ 27 ዓመት በ እስር ሲቆዩ ፣ በመላው ዓለም የነጻነት ምሳሌ ተደረገው ተወሰዱ - ዝናቸውም እየሰፋ መጣ።
በ1990 ዓ.ም የደቡብ አፍሪካ የነጮች መንግስት በተደረገበት ዓለም አቀፍ ጫና ማንዴላን ከ እስር ፈታቸው። ኤ ኤን ሲ የተባለው ድርጅታቸውም እንዲንቀሳቀስ ተፈቀደለት - ማንዴላም ተመልሰው ሊቀመንበር ሆኑ።
ማንዴላና የዚያን ጊዜው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኤፍ ደብሊው ደ ክላርክ በጋራ የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማት ተሸለሙ። ይህም የሆነው ጥቁሩ ማንዴላና ነጩ ደ ክላርክ የአፓርታይድ ሥር ዓትን ለማጥፋት ቁርጠኛ ስምምነት በማድረጋቸው ነበር።
በ1994 ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን ነጻ ምርጫ አደረገችና ማንዴላ የአገሪቷ የመጀመሪያ ጥቁር ፕሬዚዳንት ሆኑ። በ1998 ማንዴላ ለሶስተኛ ጊዜ ትዳር በመያዝ ከግራሻ ሚሼል ጋር ተጣመሩ። በ1997 ከ ኤ ኤን ሲ ሊቀመንበርነት ለቀቁ። በ1999 ደግሞ ፕሬዚዳንትነት በቃኝ አሉ። በ2004 ዓ.ም ማንዴላ ከፖሊቲካው ራሳቸውን አራቁና ጡረታ መውጣታቸውን አስታወቁ። እንዲያውም ያን ጊዜ “ለማውቃችሁ ሁሉ እኔ እደውልላችኋለሁ እንጂ እናንተ እንዳትደውልሉኝ” ማለታቸው ይነገርላቸዋል። ጡረታ በወጡ በዓመቱ ትልቁ ወንድ ልጃቸው ማካቶ ማንዴላ መሞቱ ልባቸውን በሃዘን ሰበረው። በተለይ አሟሟቱ በ ኤች አይ ቪ ስለነበር፣ ማንዴላ ያንን ምክንያት አድርገው ደቡብ አፍሪካውያን ከ ኤድስ ቫይረስ እንዲጠበቁና እንደማንኛውም በሽታ ቶሎ እንዲታከሙ ጥሩ አቀረቡ። ከዚያ ወዲህ ግን በበጎ አድራጎት ሥራ ሲሳተፉ ቆይተዋል። በ2010 ደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫን እንድታዘጋጅ ትልቅ ጥረት ያደረጉትን ማንዴላ ነበሩ። በመዝጊያው በዓል ላይም በመገኘት ለውድድሩ ድምቀት ሰጥተዋል። ዕድሜያቸው እየገፋም በመሄዱ 91 ዓመት ከሞላቸው ጊዜ በኋላ፣ በተለይም ከጃንዋሪ 2011 ጀምሮ ግን ባደረባቸው የስንባ ምች እየተስቃዩ በተደጋጋሚ ሆስፒታል ሲገቡና ሲወጡ ቆይተዋል።
ኔልሰን ማንዴል በግል ህይወታቸው ሳቂታና ተጫዋች መሆናቸው ይነገርላቸዋል። ፈግግታቸው ከማንም ልብ ሰርስሮ የሚገባ ነው። በሚገርም ሁኔታ 27 ዓመት በ እስር በመቆየታቸው ምንም የሚሰማቸው ምሬት እንደሌለ ሁልጊዜ ይናገሩ ነበር። ደቡብ አፍሪካም ለክብራቸው በገንዘቧ ላይ ፎቷቸውን ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ማተም ጀምራለች። ኔልሰን ሮህሊላ ማንዴላ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ፣ ኅዳር 26 ቀን 2006 (ዲሴምበር 5 ቀን 2013) በወዳጅ ዘመድና ቤተሰብ ተከበው አረፉ። ማንዴላ ዛሬ በህይወት የሉም፣ በሁሉም ሰው ህሊና ውስጥ ግን ታላቅ ስብዕናቸው ለዘላለም ይኖራል።

ውድ የቻናላችን ተከታታዬች በተብራራ መልኩ በኔል ሰን ማንዴላ የህይወት ታርክ ዙርያ የተፃፈውን
LONG WALK TO FREEDOM በ PDF
ቀርቦላችኋል መልካም ንባብ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
2👍1
#ሮዛ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ(🔞)


#የሚልኪና_ሹገር_ማሚዎቹ_አጭር
#የህይወት_ታሪክ

ከሚልኪ ጋር ሽርክ ነን፡፡ ብዙውን ጊዜ አስራ አንድ ሰዓት ላይ ላፓራዚያን ካፌ እየተገናኘን የሆድ የሆዳችንን
እናወራለን፡፡ ብዙ ሰዎች ታናሽ ወንድሜ እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ጓደኞቼ በበኩላቸው “ወንድምሽ ሲያምር እስኪ አጣብሺን” ይሉኛል፡፡ ሁልጊዜ ስለሚሽቀረቀር ዲያስፖራ ይመስላቸዋል፡፡ እኔን ዲያስፖራ ያድርገኝ! ሚልኪ የጎንደር ልጅ ሲሆን በጣም ሩቅ ሀገር ሄዶ የሚያውቀው ሱዳን ነው፡፡ ለዚያው በአውሮፕላን
ሳይሆን በመተማ፡፡ እውነቱን ለመናገር ከሚልኪ ጋር ምንም አይነት የስጋ ዝምድና የለንም፡፡ ሁለታችንም
ረዥም፣ ቀያዮች ስለሆንን መሰለኝ ሰዎች ወንድምና እህት የምንመስላቸው፡፡

ሚልኪን ማዳም ኤልዛቤጥ ጋር ሲመጣ ነው የማውቀው፡፡ ስናወራ፣ ስናወራ፣ ስናወራ በጣም ተመቻቸን፤ እኔ ብዙ ማዳመጥ ስለምወድ እሱ ደግሞ ሞባይሉን መነካካትና የሹገር ማሚዎቹን ገድል ማውራት ስለሚወድ ሳናስበው አሪፍ ጓደኛሞች ሆንን፡፡ በዚህ አጭር አድሜው ያየውን ረዥም ህይወት አውርቶ አውርቶ ሲደከመው ««ቆይ አንቺ ግን ጋዜጠኛ ነሽ ወይስ መጋኛ ዝም ብለሽ የምታስለፍሊኝ?» ይለኛል፡፡

እስቃለሁ፡፡

ሞባይሉን መነካካት ይጀምራል፡፡ ሚልኪ እያወራ ካልሆነ እጁ አያርፍም፡፡ ወይ ሞባይሉን ይነካካል፣ ወይም ፍሪዝ ጸጉሩን ይጠቀልለል፡፡

ሞባይን መነካካት ሲጀምር እንጣላለን…

«.አታፍርም እንዴ እኔን አስቀምጠህ ጌም ስትጫወት! ደፋር!» እለዋለሁ፡፡

«.ታዲያ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ እንደ ሱዳን ሬዲዬ የማወራው…ሃዬ! አንቺም አውሪልኛ…ሼማም!» ይለኛል፤

«እሺ ምን ላውራልህ…!»

"Anything! ለምሳሌ ትናንትና ማታ ስለበዳሽው ሰውዬ…!»

«...ሂ እዛ! ደፋር! አንተ የንስሃ አባቴ ነህ ወይስ የጽንስ ሀኪሜ የበዳሁትን ሁሉ የምዘከዝካልህ…?» ያኮርፋል!

ሚልኪ ልጅነቱን እንዳልጨረሰ የማውቀው የምር ሲያኮርፈኝ ነው፡፡
አባብዩው እወራለታለሁ....
የሚልኪ ጣቶች ቀን ቀን ሞባይል ይነካኩ አንጂ ማታ ማታ ብዙ ቁም ነገር. እንደሚሰሩ እየነገረ አስቆኛል
ከዚህ በፊት፡፡ ሹገር ማሚዎቹን የሚያስደስተው በነዚህ አለንጋ ጣቶቹ ነው፡፡ እግሮቻቸው መሐል ገብቶ
ይነካካቸዋል፡፡ የመሐል ጣቱን ያለፍቃዳቸው ይሰነቅርባቸዋል፡፡ እስኪረጥቡ ድረስ፡፡ እንኳን ጣቴ
ምላሴም ስራ አይፈታም ይላል ጉራውን ሲነፋ፡፡ “ምንም ሚስጢር የለውም እኮ፣ ባሎቻቸው የማያገኙትን ነገር ስለምሰጣቸው ይወዱኛል" ይላል ስለተመራጭነቱ ሲያብራራልኝ፡፡

ሚልኪ ዝምተኛ አይደለም፡፡ አውርቶ ሲያበቃ ስልኩን መነካካት ይጀምራል፡፡ እቆጠዋለሁ፡፡ ታዲያ እኔ
ብቻ ነኝ እንዴ እንደ ሱዳን ሬዲዬ የማወራልሽም ይለኛል፡፡ እኔ ማውራት ስጀምር ግን ተቅለብልቦ ከአፌ
ይነጥቀኝና የሱን ታሪከ ማውራት ይጀምራል፡፡ ያለማቋረጥ፡፡ አይከፋኝም፡፡ ደስ ብሎኝ አሰማዋለሁ፡፡ አውርቶ ይደhማል እንጂ አውርቶ አይጠግብም፡፡ ሲደከመው እንደገና ሞባይሉን አውጥቶ መነካካት ይጀምራል…ወይም ፍሪዙን፡፡

"ሼም አይንሽም እንዴ እኔን ብቻ ስታስለፈልፊ_! እንደ ሱዳን ሬዲዬ_» ይላል መልሶ መላልሶ፣

"ቅድም አወራሁልህ አይደል እንዴ! እሺ ምን ላውራልህ ሚልኪ?»

"Anything/ ለምሳሌ ዛሬ ማታ ስለምትበጂው ሰውዬ_ ዛሬ ስራ አልገባም፤
ለምን ከስር ነስር በነስር ሆነሻል እንዴ ለካ እንስቃለን፣
እጣ ክፍሉ የሆኑ እስኪመስል ድረስ በሚልኪ ህይውት ውስጥ ጥቂት የማይባሉ ሹገር ማሚዎች
ተመላልሰዋል ወይም የነሱ ግንባር አለው ልንል እንችላለን፡፡

ቀደም ሲል እንደገለጽኩት ሚልኪ ዲያስፖራ ይምሰል እንጂ የጎንደር ልጅ ነው፡፡ፈጣሪ መልክ ፡ቁመናን ቅልጥፍና፣ አፍላ ወጣትነትን አድሎታል፡፡በዚህች ምድር ላይ ሩብ ከፍለዘመን የኖረባትን እለት(25ተኛ አመት የልደት በአሉን ከሁለት ወራት በፊት ወይዘሮ ሳሮን በሚባሎ ሹገር ማሚው ቪላ ውስጥ እሱ ግን “ሀኒ” እያለ ከሚያቆላምጣት የ53 አምት ዲያስፖራ አሮጊት ጋር አከብሯል፡፡ የልደት በአሉ ምን ይመስል እንደነበር ዘወትር ከሚነካካው አይፎን ሞባይሉ ማህደር ውስጥ ካኖራቸው ከሀምሳ በላይ ፎቶዎችና አንድ ቪዲዮ ለመረዳት ችያለሁ::ሚልኪ የልደት ፎቶዎቹን ሲያሳየኝ ቅንጣት የሀፍረትና የይሉኝታ ስሜትን አላስተዋልኩበትም፡፡ በአፍቃሪነትና በትዳር አጋርነት ቀርቦ እጣ ክፍሉ ከሆነች ሹገር ማሚዎች በረቂቅ
ብልሃት የሰበሰበው ሀብት ይሉኝታ ቢስ ሳያደርገው አልቀረም፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተደጋጋሚ የሚያስተጋባት ሹገር ማሚዎችን የተመለከተች አንድ አቋም አላቸው
ሴት ልጅነፍስዋ የወጣት ከሆነ ለኔ ሌላው ትርፍ ነው። Age is nothing but a number' የምትል
ሚልኪ ይቺን አባባል ከአንዷ ዲያስፖራ ሹገር ማሚ እንደሞጨለፋት እ ገምታለሁ፡፡ እሱ መወሰብ
እንጂ ውስብስብ ነገር መናገር አይችልም፡፡

ሚልኪ ለነገሩ የሚደብቀኝ ሚስጥር የለውም፡፡ተራ አሉባልታ ወይም የምርቃና ወሬ እንደማያወራኝም አሳምሬ አውቀዋለሁ፡፡ አብዛኞቹ ወሬዎቹ በፎቶ እና በቪዲዮ የተደገፉ ናቸው፡፡በህይወቱ የገጠሙት ለየት ያሉ ክስተቶች በሞባይል ማህደሩ ዶክመን ማድረግ ሆቢው ሳይሆን አይቀርም፤ዘናጭ እና ቅንጡ አይፎን አለው፡፡ ያለማቋረጥ ሞባይሉን የመነካካት ልምድ አለው፡፡ ወይ ጌም ይጫወታል፡ ወይም
ከጓደኞቹ ጋር ቻት ያደርጋል፣ ወይም ሙዚቃና ቪዲዮ ሞባይሉ ላይ ይመለከታል፡፡ ከሹገር ማሚዎቹ
ቀጥሎ ለሞባይሉ ፍቅር የሚሰጥ ይመስለኛል፡፡

የልደት በአሉን ከፊል ትእይንት የቀረጸበትን የ2 ደቂቃ ቪዲዮ ያሳየኝ ትላንት ሌሊት ቢሆንም ግርምቱና
አድናቆቱ ከሰከንድ በፊት ያሳየኝ ያህል አሁንም አለቀቀኝም፡፡ቪዲዮው ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች
ወደባለ አንድ ፎቁ ቅንጡ ቪላ ሳሎን ከውጪ ሲገቡ በማሳየት ይጀምራል፡፡ከጥቂት እንግዶች በስተቀር
ሁሉም እንግዶች ማለት ይቻላል የሚስቱ የቲና ወዳጆች ናቸው፡፡በርካታ የዘመኑ ሞዴል መኪናዎች ከሰፊው ቅጥር ግቢ ውስጥ ይታያሉ፤በእግሩ የመጣ እንግዳ ያለ አይመስልም፡፡ከሰፊው ሳሎን ወስጥ
የማይታይ የምግብና የውስኪ ዘር የለም፡፡በዚህ የልደት ድግስ ቅንጭብ ቪዲዮ ላይ ከልጅነቴ ጀምሮ የማደንቃትን አንጋፋ ተዋናይት በሙዚቃው ምት ከቲና እና ከሚልኪ መሀል ስትውረገረግ ሳይ ድንጋጤዬ ልክ አልነበረውም፡፡እሷን የመሰለ እንቁ አርቲስት እዚህ ምን ትሰራለች?

ቲና በሜክአፕ ብዛት ወጣት መስላ ለመታየት ከባድ ተጋድሎ አድርጋለች፤ግን ምን ዋጋ አለው! ተፈጥሮ በእድሜ ርዝመት የሻከረ ቆዳዋንና ሸካራ ቆዳዎቿ ላይ የተጋደሙ በርካታ ደም ስሮቿን ልትደብቅላት አልቻለችም፡፡ርዝመቷ፣ሸንቃጣነቷና የሰውነት ቅርጽዋ ግን እኔንም አስገርሞኛል፡፡ግርምቱ የለቀቀኝ ሚልኪ በሳምንት ሶስቴ ያለማቋረጥ ለሰአታት ጂም እንደምትሰራ ሲነግረኝ ነበር፡፡የ8 አመት ወጣት
እንኳን አንደሷ አይነት አማላይ የሰውነት ቅርጽ አይኖራትም፡፡ውስጥዋን በከፊል የሚያሳይ ስስ ባለ ፒንክ ቀለም ቀሚስ ለብሳለች፤በየአጋጣሚው ከሚልኪ ጋ ከንፈር ለከንፈር በእንግዶቻቸው መሀል ይሳሳማሉ፡፡

ለይምሰል የተደሰቱ ይምሰሉ እንጂ፣ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የቲናም ሆነ የሚልኪ እንግዶች
ገጽታ ላይ ደስታን አልተመለከትኩም ፤ ወዳጅነትና ይሉኝታ ይዟቸው በፈገግታ ቢደምቁም፣በሙዚቃዎቹ ምት ጥንዶቹን ከበው ቢውረገረጉም በልባቸው እንደዚህ የሚሉ ይመስለኛል፤
"ምን እቺ ፈጣሪዋን በመለማመኛ እድሜዋ የልጅ ልጅዋ ከሚሆን እምቦቀቅላ ጋ ምን ያጃጅላታል፤አማረብኝ ብላ ነውድንቄም?! "

"ሼም አይዘውም እንዴ?በአደባባይ አያቱ ከምትሆን ሴት ጋር ከንፈር ለከንፈር ይመጣመጣል እንዴ?ገንዘቧ
👍42
#የህይወት_ጫፍ....


#በያሬድ

#እውነተኛ_ታሪክ

ረዘም ያለውን ድርሰት እስከምንጀምር ድረስ አጠር አጠር ባሉ እንቆያለን እናተም #Share ብታደርጉ ደስ ይለኛል።
--- === ==== ==== ==== ------
..አርብ ምሽት ነው ቁርስ እንደበላው ነው የዋልኩት ትልቁ ችግሬ ከራበኝ እንቅልፍ አይወስደኝም እራብ አልችልም ግን ማንም አለኝ ብዬ የምጠይቀው ሰው ስለሌለኝ ሆዴን አቅፌ መተኛቴ ግድ ነው። ግን ሁለት ትዳር ያላቸው አንዱ እራቅ ያለ ሁለተኛው አብሬው የምኖር ወንድሞችና አንድ ክ/ሀገር አግብታ የምትኖር እህት አለችኝ ያለገባሁት እኔ ብቻ ነኝ ትዳር ከመያዛቸው በፊት እንተሳሰባለን ካገቡ በኋላ ግን ሁሉም ወደ እራሳቸው ኑሮ ተጉዘው ተረሳስተናል በይበልጥ እኔን.. ።
በዚህ የኑሮ ውድነት ከሶስት ወራቶች በላይ ስራ ፈቶ ተቀምጦ በልቶ ማደር ማሰብ ስህተት ነው ብቻ ለሊቱን ሆዴን ታቅፌ እንቅልፍ ሳላይ አደርኩ ...በንጋታው ወጪ የሌላትን የጠዋት ፀሀይ ልመገባት ወጥቼ አስፓልት ዳር ባለች ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ የሚወጡትን የሚወርዱትን መኪናዎችን በአይኔ በአዕምሮዬ ሆዴን እያሰብኩ ማማተር ጀመርኩ።
አንድ ያሪስ መኪና ከፊቴ ቆማ ደጋግማ ክላክስ አረገች እኔን ባለ መኪና የሚያውቀኝ የለም ድንገት ቅጥረኛ ሹፌር የሚያውቁኝ ይኖራሉ ስለሆነም ለእኔ ነው ብዬ ስላላሰብኩ ሌሎች እንደኔው ፀሀይን የሚመገቧት አሉና ለእነሱ ነው ብዬ ዝም አልኩ።
ግን ሁሉም በጠቋሚ ጣታቸው ደረታቸውን ነካክተው እነሱን መሆኑን ከጠየቁ በኋላ እኔ ጋር ደርሰና ተጠራው ሄድኩኝ በመስኮት በኩል ዝቅ ብዬ አየሁት ቀይ ድንቡሽቡሽ ብሎ ቀይ ጥርት ያለ ፊት ከአይኑ ላይ ጥቁር መነፅር የሰካ ወፍራም ወጣት ነበር ግን የማውቀው አልመሰለኝም ልጁ ወደ መኪናው እንድገባ ጋበዘኝ ለምን እንድገባ እንደፈለገ ጠየኩት እሱም በግርምት ፈገግ ብሎ በረዶ የመሰሉ ጥርሶቹን አሳየኝና ።
" ምን ሆነህ ነው ፍቃዱ እረሳሀኝ እንዴ ?" አለኝ ጭራሽ ግራ ተጋብቼ በዝምታ አየሁት ስሜን ማወቁ አስገረመኝ ።
ዘድሮ እኮ መተማመን ቀርቷል መኪና ይዞ ስም ጠርቶ ግባ ላለን ሰው ሁሉ ዘሎ መግባት ከባድና አስቸጋሪ ነው። መናገር መቼም መናገር የያለብኝ አይመስለኝም ለምን ይሄን መራራ እና ክፍ ጊዜ ታውቁታላቹሁ ብዬ ስለማስብ ።
ልጁ ንግግሩን ቀጠለ"...ምን ነክቶህ ነው ግራ የተጋባሀው ግባና የሆነ ቦታ ሄደን ቁርስ እንብላ እኔ እኮ ከአንተ ጋር እበላለው ብዬ ሳልበላ ነው ከቤቴ የወጣሁት " አለኝ።
አዕምሮዬ በጭንቀት ሊፈነዳ ደረሰ ለዚህ ሰፈር አዲስ ነኝ በመንገድ ምክንያት ቤታችን በመፍረሱ ቅያሪ የተሰጠን ቤት ነው።በጣት የሚቆጠሩ አመታት ናቸው የኖርነው በአጠቃላይ አዲስ ነን ብዙም አልተግባባንም ።
እቺን ሶስት ወር ምናም ስራ አጥቼ ተራብኩ ተቸገርኩ እንጂ ከእዚ በፊት ጥሩ ስራና ገንዘብ ነበረኝ ችግሬ ደክሜ የማመጣውን ገንዘብ አጠቃቀሙን አለማወቄ ነው ሱስ ኖሮብኝ እያጠፋው ሳይሆን ቸገረኝ እራበኝ ላለኝ ሁሉ 'ና ለቤተሰቤ ዝም ብዬ መበተኔ ነው ። በስራ ላይ ሆኜ የማገኘውን ገንዘብ ብቆጥብ ብቋጥር ወራት አይደለም ለአመት ባልሰራ እንኳን አልራብም ጠግቤ ያሳድረኝ ነበር ። ገንዘብ መያዝ እንዳለብኝና መጨከን አግባብ እንደሆነ የምረዳው እንደዚህ ገንዘብ አጥቼ ሲርበኝና ሰው ካጠገቤ ሳጣ ነው የህይወት ጫፍ ላይ እንደቆምኩ የሚገባኝ እናም ስራ ጀምሬ ገንዘቡን ሳገኝ ያ የችግር የርሀብ የውሳኔ ጊዜን እረሳለው መበተኔን እቀጥላለው።

" ......እረ ፍቃዱ ምን እያሰብክ ነው? .....እባክህ ግባና እንሂድ " አለኝ ። ከሄድኩበት ዓለም እና እያየሁ እንዳላይ ከደረገኝ ሀሳብ ተመልሼ አይኔን ገልጬ አየሁትና ደነገጥኩ።

💫ይቀጥላል💫

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
#የህይወት_ጫፍ....


#ክፍል_ሁለት


#በያሬድ

እንደ ፎቶ ካሜራ ብልጭታ አይኑን የጋረደበትን መነፅር አንስቶት ስመለከተው እንደ መብራቱ የሆነ ቦታ የማውቀው ትውስታዬ በራና ወዲያው ጠፋ በድንጋጤ አየሁትና።

"እንዴ አንተ አውቀሀለው .... አዎ አውቅሀለው እናቴ ትሙት ፣ማርያምን አውቅሀለው ..ግን የት? እኔንጃ" አልኩት ንግግሬ ለእኔው ገረመኝ እሱ መቼ አላውቅህም አለኝ እስከ መሀላ ምን አስደረሰኝ እኔም እሱም ተገረምን።በእውነቱ ምግብ ካየ 24 ሰአት የሞላው ሆዴ የርሀቡን ስሜት በመርሳቴ እንደበላ ሰው ደስ አለኝ። አንባቢዎቼ? እርሀብን ቀምሳቹሀት ታውቃላቹሁ መራራ እርሀብ...ይሄኔ ጠግባቹሁ ታውቃላቹ ብትባሉ ስንቶቻችን እጅ አውጥተን በመሰክርን ሰማቹሁኝ ምሳ ወይ እራት ቆይቶባቹሁ አላልኩም... አያቹሁ አታውቁትም ለዚህ ነው እርቦኛል ላለን መረዳት ተስኖን ቦርሳችንና ኪሳችንን በብር አጭቀን እ/ሄር ወይም አላህ ይስጥልን የምንለው ድንገት ፈጣሪ ስላለን ልኮን ይሆናል።

አሁን ወደ መኪናው ግባ እስኪለኝ አልጠበኩም ዘልዬ ገባሁና አጠገቡ ቁጭ አልኩና በትከሻ ችርስ ስናጋጭ እሱ በፈገግታ ያየኛል አውቀዋለው የት? እኔንጃ.......
" ..ብዙ አትጨናነቅ ልንገርህ የዛሬ አንድ አመት ከአምስት ወር ትሰራቐት......." ሲለኝ።ድንጋጤዬ ጨመረ ይሄኔ ነው መሸሽ በአምሮዬ ሳልኩት የያኔው ከሰንደል የሚከሳው ግርማቸው የአሁኑ ማን እንደሆነ የማለውቀው ማመን የተሳነኝ ግርማቸው አስደናቂም አስገራሚም ሆነብኝ።

ምግብ ቤት ደርሰን ምግብ እስከሚቀርብ አይኔ ከእሱ ላይ አልተነቀለም ምግቡ ቀርቦ አበላሌን አልነግራቹሁም ብነግራቹሁ እዛ እንዳለው ተመጋቢ ትታዘቡኛላቹሁ ስለዚህ ይቅር በህሊናቹሁ ሳሉትና ታዘቡኝ።
ግርማቸውን የማውቀው በአንድ ሳይት ላይ ተመድቤ ስሰራ በነበረበት ወቅት ነግሬያቹሁ አይደል አንድ ሰው መጥቶ ቸገረኝ እራበኝ ላለኝ ሁሉ እንደ ዋነተኛ እጄ ኪሴ ውስጥ ጠልቆ ይገባል ያኔ ነው ግርማቸው ከስቶ ጠቁሮ ገርጥቶ በእራብ የተነሳ ሆድና ጀርባው ተጣብቆ መውጪያው በር ላይ ቁሽሽ ያለ ልብስና ያለቀ ጫማ አርጎ ከአንዲት ድንጋይ ላይ ተቀምጦ ይጠብቀኝ እና ምግብ ግዛልኝ ይለኛል .....
አሁን እኔ ተርቤ እሱ እየገዛልኝ ነው አለምም ህይወትም እቺ ነች አትገረሙ ምግቡን ሆዴ ሊፈነዳ እስከሚደርስ አብረን በላንና ጨርሰን በግድ ሲንግል ድራፍት ጋብዞኝ እየጠጣን ያኔ ስጠይቀው የነበረው ጥያቄ አሁንም በፊቴ ላይ ተመለከተና ዛሬ ሊነግረኝ ወሰነ። የተበላው ቅባት ጉሮሮውን ዘግቶት ይዞት ነበረና ጠራርጎ መናገር ጀመረ።
" .....ትክክለኛ ወንድሜ ነህ.... ያኔ መጀመሪያ ስታወቀኝ ጥያቄ ነበረህ ሳይመለስህ ተለያየን አሁን መልስ ነግሬህ መልስ ሳልሰጥህ እንለያያለን......
...አንተ እኔን የምታቀኝ ከመስራቤትህ በር በርሀብ ጉልበቴ ዝሎ የሰው አፍ ስጋዬን በልቶት ጨርሶት ጭላጭሏ የተስፋ ብርሀኔ ጠፍታ የህይወት ጉዞዬ የማብቂያ ጫፍ.... ላይ ሆኜ በመኖርና በመሞት ምርጫ ውስጥ ገብቼ ለመወሰን በማመነታበት ጊዜ ነው። ፍቄ ብቸኛ መሆን ቁስሉንና ህመሙን ለአንተ ማስረዳት በጣም ይከብዳል ታውቀዋለው የማያልቅ መከራና ችግርህ ለሰዎች ሰልችቶ ሁሉም ሲርቁህ ... " አለና ዝም አለኝ እውነቱን ነው ሁሌም ችግሮች ቀለል ካላሉ ጭራሽ እየባሱብህ ሲሄዱ አይደለም ባደ ደምህ የእኔ ነው የምትለው ሁሉ ሰው ሰልችቶህ ይሸሻል ማንም ልብህን ወይም የዋህነትህን አይቶ ሳይሆን ኪስህ ውስጥ ያለውን ገንዘብ አይቶ ይቀርበሀል ይርቅሀል።
ግርማቸው ከአይኖቹ እንባ ዱብ ዱብ እያሉ ለደቂቃዎች
በዝምታ ከቆየ በኋላ ከአይኖቹ በአራት አቅጣጫ የሚወርዱት እንባዎች በእጁ መዳፍ ገደብ አበጀላቸው እና ቀና ብሎ አይቶኝ ንግግሩን ቀጠለ።

"..... የማውቅህ ከመስራቤትህ ደጃፍ እያገኘሁ ምግብ ስትገዛልኝ አይደለም ልንገርህ አንተ እረስተሀው ይሆናል... ቀኑ አመትባል ነበር እኔም የምኖረው ወንድሜ ለጊዜው ማረፊያ ብሎ በሰጠኝ ደሳሳ ቤት መሳይ ቤት ውስጥ ነበር እሱ ትዳር አለው እናም ያ የሞቀ በአል ለእኔ ጨለማ ነበር ሰው ሲበላ ሲጠጣ እኔ ግን ከፍቶኝ እርቦኝ አልጋ ላይ ተኝቼ ነበር ። እኛ ኢትዮጵያዊያን ነገ መልሶ ብድሩን ለሚከፍል እንጂ አይከፍልም ብለን ለምንስበው ከማድረግ እንቆጠባለን ብናደርግም የጤፍ ጥሬ የምታህል..... ብቻ ወንድሜ ጋር ጎሮቤት ተሰብስቦ ሲበላ ሲጠጣ እኔ እንቅልፍ ላይ ነበር.. የተከፈተው የበአል ዘፈን አነቃኝ አይኔ እንባ ሞላ አእምሮዬ ብቸኝነቴን ለእኔ የሚያስብ የሚጨነቅ ሰው እንደሌለ እየነገረኝ በቃህ መኖር ይብቃህ እቺ ቀን የህይወትህ የመጨረሻዋ ጫፍ አርጋት በገመድ ሲጥ በል ብትል ዛሬ ማንም አያገኝህም ዛሬ ተደስተው ህይወት አልባ አካልህን ነገ ታገኘዋለህ ሙት በዚህ አለም ማን አለህ እያለ በአእምሮዬ ደጋግሞ አቃጨለብኝ ግድግዳ ላይ ለልብስ ማስጫ ብዬ ገዝቼ ያስቀመጥኩትን ሲባጎ አየው ክፍቱንም የጣራ አግዳሚ እንጨቱን አስተዋልኩና ከተኛሁበት ብድግ አልኩ..." ሲለኝ ደነገጥኩና ከጠቀመጥኩበት ተነሳሁና ወሬውን አስቋርጬ ምን ሊያረግ እንደሆነ ጠየኩት ።እሱም በዝምታ አየኝ.....

💫ነገ እንጨርሰዋለን💫

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
#የህይወት_ጫፍ....


#ከያሬድ


#ክፍል_ሶስት (የመጨረሻው ክፍል)

ልቤ በሞት ጫፍ ላይ እንደተጠለጠለች ነፍስ ትር ትር እያለች እንደቆምኩ ቁልቁል እያየሁት ጠየኩት እሱም ቀና ብሎ እያየኝ በሀዘን ምክንያት እየፈሰሱ ያሉትን እንባውንና በአፍጫው የመጣውንን ፈሳሽ በእጁ ጠረገና....

" እስቲ ቁጭ በል.... ያኔ እራሴን ባጠፋ ያኔም ዛሬም ባልተገናኘን ነበር ... በል ተቀመጥ...." አለኝ። ተመልሼ ወንበሬ ላይ ቁጭ እያልኩ።
" ያኔ ሞክረህም ቢሆን አግባብ አይደለም " አልኩት እሱም ፈገግ ብሎ አየኝና አለመሞከሩን ጭንቅላቱን ከግራ ወደ ቀኝ በመወዝወዝ ጭምር ነገረኝ በዛው ንግግሩን ቀጠለ።
".... ታውቃለህ በጭንቅላቴ ውስጥ እንደዚህ አይነት ነገር መፈጠሩ ብቻዬን ስለሆኩኝ እንደሆነ አሰብኩ ከመኝታዬ ተነስቼ ከሰው ጋር ለመደባለቅ ወደ ውጭ ወጣሁ ግን ማን አለኝና ማን ጋር ልሂድ በበአል ተርቤያለው ህፃናት እንኳን ብር ኪሳቸው በማያጡበት እኔ ባዶ ኪስ አስር ሳንቲም የሌለኝ የፀዳ ልብስ ሳለብስ መሄጃ ሳይኖረኝ ክርር ባለ የምሳ ሰአት ፀሀይ አስባልት ዳር ቆሜ ደስተኛ ቤተሰቦችን ህፃናትን እያየሁ በሀዘን ልቤ እየተወጋ አይኖቼ እንባ ቋጥረው ሳለ አንተንና ጭንቅላቱን ቢፈልጡት እንኳን ገንዘብ አይደለም ደም እንኳን የማይወጣው ከልጅነት ጭቃ አብኩተን ያደግነውን አማረን ተያይዛቹሁ ስትሄዱ አየኋቹሁ አንተን አላውቅህም እሱን ጠራሁትና ጠጋ ብያቹሁ ሰላም ካልካቹሁ በኋላ እራሴን ዝቅ ማድረጌ እያሸማቀቀኝ እርሀብ ክብርህን ያወርደሀል እናም "እርቦኛል ሳንቲም" ...አላስጨረሰኝም እንደሌለው ነግሮኝ ተያይዛቹሁ መንገድ ጀመራቹሁ እኔ ሽምቅቅ አልኩኝ በመጠየቄ አንተን እንደ እኔ ህይወት በጠቆረው አስፓልት ላይ አይኔን ተከልኩኝና ቀና ስል አንተ ከፊቴ ቆመህ ድፍን ሀምሳ ብር ይዘህ እጅህን ዘርግተሀል የገረመኝ የተናገርከው ቃል ነው ይቅርታ ለታክሲ ከያዝኩት ውጪ ሌላ ምንም ገንዘብ እንደሌለህ ነግረህኝ ሄድክ በጣም ገረመኝ የሰው ልጅ ለሰው የሆነ ነገር ሲያረግ መልስ ይፈልጋል ልጠይቅህ አንተ ግን ምን ፈልገህ አደረክልኝ?" ....አለኝ።
እውነት ግን ምን ፈልጌ አረኩት አላውቅም እናም መለስ ብዬ ጊዜውን ለማስታወስ አሰብኩ አንድ ጊዜ ብልጭ ሌላ ጊዜ ጥፍት በሚል ሁኔታ አስታውሳለው ግን ማንነቱ ትዝ አይለኝም አማረ ማለት ባለ ትዳር ነው ልጅ ግን ያኔ አልወለደም አብረን ነው የምንሰራው ደመወዙ ከእኔ የተሻለ ነው እንደተባለው ገንዘብ ማውጣት አይወድም ያኔ ስራ ቦታችን እዛው እነሱ ሰፈር ስነበር ለበአል ጠርቶኝ ሄጄ ነው ይህ የሆነው ግን ማንነቱን አላስታውስም ........
" እኔንጃ ለምን እንደሰጠሁሁ በቃ ወይ አሳዝነህኝ ....." አልኩት እሱም ተገርሞ ፈገግ አለና።
" ... ሰው ስለሆኩ ችግሬ ተሰምቶህ ነው ... ከዛ ቀን በኋላ መስራቤትህ በር ላይ ሲርበኝ መጥቼ እለምንህ ነበር ባይኖርህ እንኳን አመጣለው ብለህ ትገዛልኛለህ አንዴ የምጠላውን ጥያቄ ጠየከኝ ተናደድኩኝ ... ስራ ለምን አትሰራም እንዴ? አልከኝ ሰው እየራበው አልሰራም ይላል እንዴ? አይለም ለሆዱ ሲል ወይ ይሰርቃል ወይ ይሰራል አሊያም ይደበድባል ብሎም ሊገል ይችላል ቁጭ ብሎ እርሀቡን አይራብም ለምን አትሰራም ከማለት ስራ ሰጥቶ ያን ሰው ምን እንደሚወስን ማየት .... በወቅቱ ስራ ሰጠህኝ እንቢ ሳልልህ መስራት ጀመርኩ አንተንም አብላኝ ከማለት አቆምኩ ሰርቼ ስበላም ውስጤ የነበረው እርካታ ልነግርህ አልችልም ከ15 ቀን በኋላ ሌላ ቦታ ተመድበህ ስትሄድ እንድበረታ ነገርከኝ ነበር .... ያኔ ከጀርባህ እያየሁሁ ፈጣሪን አንድ ነገር ለመንኩት ሰው አርገኝና ብድርህን እንድከፍል...." አለኝና ጥቂት ደቂቃ ፍዝዝ ብሎ ዝም አለኝና ቀጠለ......
" ..... የሚገርምህ በችግሮቼ ወቅት አንድ ቀን ከእንቅልፌ ደስተኛ ሆኜ ተነስቼ አላውቅም እናም..... ያኔ አንተ ከሄድክ በኋላ ሁለት ወር ሳልሰራ አሰናበቱኝ እጅግ አለቀስኩ እንደገና እርሀቤን ሳስብ የረሳሁትን ሞት መመኘት ጀመርኩ....
ሁሌም ከፍቶኝ እነሳ እንዳልነበር ከቀናት በኋላ እየራበኝ ነገር ግን ደስተኛ ሆኜ ተነሳው ገረመኝ እርሀቤን ሳይሆን ደስታዬን ማሰብ ጀመርኩ ፈጣሪን ሳማርር እና እንደረሳኝ አምኜ ተመስገን ማለት ትቼ እንዳልነበር ተመስገን አልኩኝ በባዶ ሆዴ ግን ደስተኛ ሆኜ ከደሳሳዋ ቤቴ ወጣሁ ለካ ፈጣሪ ይዘገያል እንጂ ለጥያቄዎች መልስ አለው የራስን ይመስለናል እንጂ አይረሳንም እናም ያኔ ትልቅ ነገር አዘጋጅቶልኝ ነበር እኛ ሰዎች ችኩል ስለሆንን ነው ስለ አንተም ብዙ ነገር ሰምቻለው ተስፋ አትቁረጥ ያቺ ቀን ትመጣለች ...." አለኝና የእጅ ሰአቱን ተመለከተና".... አሁን ወደ ውጭ በረራ አለብኝ ቸኩያለው ስመጣ እደውልሀለው እሺ ማናችንም በየዕምነታችን ተስፈችንን በፈጣሪ ላይ እናርግ እንገናኛለን....." አለኝና ትከሻዬን ነካ ነካ አርጎኝ ተሰናበተኝ እኔም ፈጣሪን ያማረርኩበትን ወቅቶች እያሰብኩ በሀሳብ ተመስጬ ሳለው ከአጠገቤ ተነስቶ ሄዷል ።
ከሀሳቤ ነቅቼ ዙሪያዬን ተመለከትኩኝና ሳለስበው ከተቀመጥኩበት በደስታ ውስጥ ሆኜ ከሆቴሉ ወጣሁ ፈገግና በርታ እንደወጣችው ቀን የእኔም ህሊናና መንፈስ ፍክት ብሎ ውስጤ በደስታ ተሞልቶ መንገድ ጀመርኩ።

አለቀ

ነገ በሌላ ታሪክ እንገናኝ እስቲ እናንተም #Share እያደረጋችሁ።

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ።
👍2
#የህይወት_ታሪክ

አሁን እኔ ብሞት ፥ ከኔ ምን ይቀራል?
ስኖር “ክፉ” ያለኝ
“ደግ ሰው ነበረ " ; እያለ ያወራል
“እሱ ሰው አይደለም” ፥ ሰይጣን ነው መሠሪ"
ሲለኝ የከረመ
“መልካም ሰው ነበረ ፥ መልአክ መሥሎ ኗሪ”
ብሎ ቀብሬ ላይ ፥ እንባውን ይዘራል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የተናቀ ፥ ሲሞት ይከበራል ።
•••
የሚጠላኝ ሁላ
ተወዳጅነቴን ፥ ቀብሬ ላይ ያወሳል
መቼም በዚህ ሀገር
ሲኖር የሚነቀፍ ፥ ሲሞት ይወደሳል
ሲኖር የተረሳ ሲሞት ይታወሳል ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘