አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የህይወት_ጫፍ....


#በያሬድ

#እውነተኛ_ታሪክ

ረዘም ያለውን ድርሰት እስከምንጀምር ድረስ አጠር አጠር ባሉ እንቆያለን እናተም #Share ብታደርጉ ደስ ይለኛል።
--- === ==== ==== ==== ------
..አርብ ምሽት ነው ቁርስ እንደበላው ነው የዋልኩት ትልቁ ችግሬ ከራበኝ እንቅልፍ አይወስደኝም እራብ አልችልም ግን ማንም አለኝ ብዬ የምጠይቀው ሰው ስለሌለኝ ሆዴን አቅፌ መተኛቴ ግድ ነው። ግን ሁለት ትዳር ያላቸው አንዱ እራቅ ያለ ሁለተኛው አብሬው የምኖር ወንድሞችና አንድ ክ/ሀገር አግብታ የምትኖር እህት አለችኝ ያለገባሁት እኔ ብቻ ነኝ ትዳር ከመያዛቸው በፊት እንተሳሰባለን ካገቡ በኋላ ግን ሁሉም ወደ እራሳቸው ኑሮ ተጉዘው ተረሳስተናል በይበልጥ እኔን.. ።
በዚህ የኑሮ ውድነት ከሶስት ወራቶች በላይ ስራ ፈቶ ተቀምጦ በልቶ ማደር ማሰብ ስህተት ነው ብቻ ለሊቱን ሆዴን ታቅፌ እንቅልፍ ሳላይ አደርኩ ...በንጋታው ወጪ የሌላትን የጠዋት ፀሀይ ልመገባት ወጥቼ አስፓልት ዳር ባለች ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ የሚወጡትን የሚወርዱትን መኪናዎችን በአይኔ በአዕምሮዬ ሆዴን እያሰብኩ ማማተር ጀመርኩ።
አንድ ያሪስ መኪና ከፊቴ ቆማ ደጋግማ ክላክስ አረገች እኔን ባለ መኪና የሚያውቀኝ የለም ድንገት ቅጥረኛ ሹፌር የሚያውቁኝ ይኖራሉ ስለሆነም ለእኔ ነው ብዬ ስላላሰብኩ ሌሎች እንደኔው ፀሀይን የሚመገቧት አሉና ለእነሱ ነው ብዬ ዝም አልኩ።
ግን ሁሉም በጠቋሚ ጣታቸው ደረታቸውን ነካክተው እነሱን መሆኑን ከጠየቁ በኋላ እኔ ጋር ደርሰና ተጠራው ሄድኩኝ በመስኮት በኩል ዝቅ ብዬ አየሁት ቀይ ድንቡሽቡሽ ብሎ ቀይ ጥርት ያለ ፊት ከአይኑ ላይ ጥቁር መነፅር የሰካ ወፍራም ወጣት ነበር ግን የማውቀው አልመሰለኝም ልጁ ወደ መኪናው እንድገባ ጋበዘኝ ለምን እንድገባ እንደፈለገ ጠየኩት እሱም በግርምት ፈገግ ብሎ በረዶ የመሰሉ ጥርሶቹን አሳየኝና ።
" ምን ሆነህ ነው ፍቃዱ እረሳሀኝ እንዴ ?" አለኝ ጭራሽ ግራ ተጋብቼ በዝምታ አየሁት ስሜን ማወቁ አስገረመኝ ።
ዘድሮ እኮ መተማመን ቀርቷል መኪና ይዞ ስም ጠርቶ ግባ ላለን ሰው ሁሉ ዘሎ መግባት ከባድና አስቸጋሪ ነው። መናገር መቼም መናገር የያለብኝ አይመስለኝም ለምን ይሄን መራራ እና ክፍ ጊዜ ታውቁታላቹሁ ብዬ ስለማስብ ።
ልጁ ንግግሩን ቀጠለ"...ምን ነክቶህ ነው ግራ የተጋባሀው ግባና የሆነ ቦታ ሄደን ቁርስ እንብላ እኔ እኮ ከአንተ ጋር እበላለው ብዬ ሳልበላ ነው ከቤቴ የወጣሁት " አለኝ።
አዕምሮዬ በጭንቀት ሊፈነዳ ደረሰ ለዚህ ሰፈር አዲስ ነኝ በመንገድ ምክንያት ቤታችን በመፍረሱ ቅያሪ የተሰጠን ቤት ነው።በጣት የሚቆጠሩ አመታት ናቸው የኖርነው በአጠቃላይ አዲስ ነን ብዙም አልተግባባንም ።
እቺን ሶስት ወር ምናም ስራ አጥቼ ተራብኩ ተቸገርኩ እንጂ ከእዚ በፊት ጥሩ ስራና ገንዘብ ነበረኝ ችግሬ ደክሜ የማመጣውን ገንዘብ አጠቃቀሙን አለማወቄ ነው ሱስ ኖሮብኝ እያጠፋው ሳይሆን ቸገረኝ እራበኝ ላለኝ ሁሉ 'ና ለቤተሰቤ ዝም ብዬ መበተኔ ነው ። በስራ ላይ ሆኜ የማገኘውን ገንዘብ ብቆጥብ ብቋጥር ወራት አይደለም ለአመት ባልሰራ እንኳን አልራብም ጠግቤ ያሳድረኝ ነበር ። ገንዘብ መያዝ እንዳለብኝና መጨከን አግባብ እንደሆነ የምረዳው እንደዚህ ገንዘብ አጥቼ ሲርበኝና ሰው ካጠገቤ ሳጣ ነው የህይወት ጫፍ ላይ እንደቆምኩ የሚገባኝ እናም ስራ ጀምሬ ገንዘቡን ሳገኝ ያ የችግር የርሀብ የውሳኔ ጊዜን እረሳለው መበተኔን እቀጥላለው።

" ......እረ ፍቃዱ ምን እያሰብክ ነው? .....እባክህ ግባና እንሂድ " አለኝ ። ከሄድኩበት ዓለም እና እያየሁ እንዳላይ ከደረገኝ ሀሳብ ተመልሼ አይኔን ገልጬ አየሁትና ደነገጥኩ።

💫ይቀጥላል💫

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
#የህይወት_ጫፍ....


#ክፍል_ሁለት


#በያሬድ

እንደ ፎቶ ካሜራ ብልጭታ አይኑን የጋረደበትን መነፅር አንስቶት ስመለከተው እንደ መብራቱ የሆነ ቦታ የማውቀው ትውስታዬ በራና ወዲያው ጠፋ በድንጋጤ አየሁትና።

"እንዴ አንተ አውቀሀለው .... አዎ አውቅሀለው እናቴ ትሙት ፣ማርያምን አውቅሀለው ..ግን የት? እኔንጃ" አልኩት ንግግሬ ለእኔው ገረመኝ እሱ መቼ አላውቅህም አለኝ እስከ መሀላ ምን አስደረሰኝ እኔም እሱም ተገረምን።በእውነቱ ምግብ ካየ 24 ሰአት የሞላው ሆዴ የርሀቡን ስሜት በመርሳቴ እንደበላ ሰው ደስ አለኝ። አንባቢዎቼ? እርሀብን ቀምሳቹሀት ታውቃላቹሁ መራራ እርሀብ...ይሄኔ ጠግባቹሁ ታውቃላቹ ብትባሉ ስንቶቻችን እጅ አውጥተን በመሰክርን ሰማቹሁኝ ምሳ ወይ እራት ቆይቶባቹሁ አላልኩም... አያቹሁ አታውቁትም ለዚህ ነው እርቦኛል ላለን መረዳት ተስኖን ቦርሳችንና ኪሳችንን በብር አጭቀን እ/ሄር ወይም አላህ ይስጥልን የምንለው ድንገት ፈጣሪ ስላለን ልኮን ይሆናል።

አሁን ወደ መኪናው ግባ እስኪለኝ አልጠበኩም ዘልዬ ገባሁና አጠገቡ ቁጭ አልኩና በትከሻ ችርስ ስናጋጭ እሱ በፈገግታ ያየኛል አውቀዋለው የት? እኔንጃ.......
" ..ብዙ አትጨናነቅ ልንገርህ የዛሬ አንድ አመት ከአምስት ወር ትሰራቐት......." ሲለኝ።ድንጋጤዬ ጨመረ ይሄኔ ነው መሸሽ በአምሮዬ ሳልኩት የያኔው ከሰንደል የሚከሳው ግርማቸው የአሁኑ ማን እንደሆነ የማለውቀው ማመን የተሳነኝ ግርማቸው አስደናቂም አስገራሚም ሆነብኝ።

ምግብ ቤት ደርሰን ምግብ እስከሚቀርብ አይኔ ከእሱ ላይ አልተነቀለም ምግቡ ቀርቦ አበላሌን አልነግራቹሁም ብነግራቹሁ እዛ እንዳለው ተመጋቢ ትታዘቡኛላቹሁ ስለዚህ ይቅር በህሊናቹሁ ሳሉትና ታዘቡኝ።
ግርማቸውን የማውቀው በአንድ ሳይት ላይ ተመድቤ ስሰራ በነበረበት ወቅት ነግሬያቹሁ አይደል አንድ ሰው መጥቶ ቸገረኝ እራበኝ ላለኝ ሁሉ እንደ ዋነተኛ እጄ ኪሴ ውስጥ ጠልቆ ይገባል ያኔ ነው ግርማቸው ከስቶ ጠቁሮ ገርጥቶ በእራብ የተነሳ ሆድና ጀርባው ተጣብቆ መውጪያው በር ላይ ቁሽሽ ያለ ልብስና ያለቀ ጫማ አርጎ ከአንዲት ድንጋይ ላይ ተቀምጦ ይጠብቀኝ እና ምግብ ግዛልኝ ይለኛል .....
አሁን እኔ ተርቤ እሱ እየገዛልኝ ነው አለምም ህይወትም እቺ ነች አትገረሙ ምግቡን ሆዴ ሊፈነዳ እስከሚደርስ አብረን በላንና ጨርሰን በግድ ሲንግል ድራፍት ጋብዞኝ እየጠጣን ያኔ ስጠይቀው የነበረው ጥያቄ አሁንም በፊቴ ላይ ተመለከተና ዛሬ ሊነግረኝ ወሰነ። የተበላው ቅባት ጉሮሮውን ዘግቶት ይዞት ነበረና ጠራርጎ መናገር ጀመረ።
" .....ትክክለኛ ወንድሜ ነህ.... ያኔ መጀመሪያ ስታወቀኝ ጥያቄ ነበረህ ሳይመለስህ ተለያየን አሁን መልስ ነግሬህ መልስ ሳልሰጥህ እንለያያለን......
...አንተ እኔን የምታቀኝ ከመስራቤትህ በር በርሀብ ጉልበቴ ዝሎ የሰው አፍ ስጋዬን በልቶት ጨርሶት ጭላጭሏ የተስፋ ብርሀኔ ጠፍታ የህይወት ጉዞዬ የማብቂያ ጫፍ.... ላይ ሆኜ በመኖርና በመሞት ምርጫ ውስጥ ገብቼ ለመወሰን በማመነታበት ጊዜ ነው። ፍቄ ብቸኛ መሆን ቁስሉንና ህመሙን ለአንተ ማስረዳት በጣም ይከብዳል ታውቀዋለው የማያልቅ መከራና ችግርህ ለሰዎች ሰልችቶ ሁሉም ሲርቁህ ... " አለና ዝም አለኝ እውነቱን ነው ሁሌም ችግሮች ቀለል ካላሉ ጭራሽ እየባሱብህ ሲሄዱ አይደለም ባደ ደምህ የእኔ ነው የምትለው ሁሉ ሰው ሰልችቶህ ይሸሻል ማንም ልብህን ወይም የዋህነትህን አይቶ ሳይሆን ኪስህ ውስጥ ያለውን ገንዘብ አይቶ ይቀርበሀል ይርቅሀል።
ግርማቸው ከአይኖቹ እንባ ዱብ ዱብ እያሉ ለደቂቃዎች
በዝምታ ከቆየ በኋላ ከአይኖቹ በአራት አቅጣጫ የሚወርዱት እንባዎች በእጁ መዳፍ ገደብ አበጀላቸው እና ቀና ብሎ አይቶኝ ንግግሩን ቀጠለ።

"..... የማውቅህ ከመስራቤትህ ደጃፍ እያገኘሁ ምግብ ስትገዛልኝ አይደለም ልንገርህ አንተ እረስተሀው ይሆናል... ቀኑ አመትባል ነበር እኔም የምኖረው ወንድሜ ለጊዜው ማረፊያ ብሎ በሰጠኝ ደሳሳ ቤት መሳይ ቤት ውስጥ ነበር እሱ ትዳር አለው እናም ያ የሞቀ በአል ለእኔ ጨለማ ነበር ሰው ሲበላ ሲጠጣ እኔ ግን ከፍቶኝ እርቦኝ አልጋ ላይ ተኝቼ ነበር ። እኛ ኢትዮጵያዊያን ነገ መልሶ ብድሩን ለሚከፍል እንጂ አይከፍልም ብለን ለምንስበው ከማድረግ እንቆጠባለን ብናደርግም የጤፍ ጥሬ የምታህል..... ብቻ ወንድሜ ጋር ጎሮቤት ተሰብስቦ ሲበላ ሲጠጣ እኔ እንቅልፍ ላይ ነበር.. የተከፈተው የበአል ዘፈን አነቃኝ አይኔ እንባ ሞላ አእምሮዬ ብቸኝነቴን ለእኔ የሚያስብ የሚጨነቅ ሰው እንደሌለ እየነገረኝ በቃህ መኖር ይብቃህ እቺ ቀን የህይወትህ የመጨረሻዋ ጫፍ አርጋት በገመድ ሲጥ በል ብትል ዛሬ ማንም አያገኝህም ዛሬ ተደስተው ህይወት አልባ አካልህን ነገ ታገኘዋለህ ሙት በዚህ አለም ማን አለህ እያለ በአእምሮዬ ደጋግሞ አቃጨለብኝ ግድግዳ ላይ ለልብስ ማስጫ ብዬ ገዝቼ ያስቀመጥኩትን ሲባጎ አየው ክፍቱንም የጣራ አግዳሚ እንጨቱን አስተዋልኩና ከተኛሁበት ብድግ አልኩ..." ሲለኝ ደነገጥኩና ከጠቀመጥኩበት ተነሳሁና ወሬውን አስቋርጬ ምን ሊያረግ እንደሆነ ጠየኩት ።እሱም በዝምታ አየኝ.....

💫ነገ እንጨርሰዋለን💫

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2