አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የኔልሰን #ሮህሊላ #ማንዴላ #አጭር #የህይወት #ታሪክ

ሮሊላሂላ ማንዴላ የተወለዱት ፣ ትራንስኪ በተባለው የደቡብ አፍሪካ ከተማ ጁላይ 18 ቀን 1918 ዓም ነው። ኔልሰን የሚለውን ስማቸውን ያገኙት ከጊዜ በኋላ ከአንድ አስተማሪያቸው እንደሆነ የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል። በተወለዱበት አካባቢ ባለው ቲምቡ ጎሳም በአካባቢው ሰው “ማዲባ” በሚል ስም ይጠራሉ።
አባታቸው ፣ ማንደላ የ 9 ዓመት ልጅ ሳሉ ነው የሞቱት። ማንዴላ 23 ዓመት ሲሞላቸው በጎሳው ደንብ መሰረት የሚመጣላቸውን ሚስት ላለማግባት ሲሉ ያደጉበትን ከተማ ትተው ወደ ጆሃንስበርግ ሄዱ።
በ 25 ዓመታቸው ዩኒቨርሲቲ በመግባት ማንዴላ በፎርት ሃሬ ዩኒቨርሲቲ እና በዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ ተምረው በ1942 በህግ ተመርቀዋል። በተመረቁ በሁለተኛው ዓመት የመጀመሪያ ሚስታቸው የሆኑትን ኤቪሊን ማሴ በማግባት አራት ልጆችን አፈሩ። በ1958 እስከተለያዩበት ቀን ድረስ አብረው ቆይተዋል። ከዚያ ፊታቸውን ወደ ትግሉ በማዞር የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ በተባለው ፓርቲ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ መሆን ጀመሩ። በ1952 ማንዴላ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳት በመሆን የአፓርታይድ ሥርዓትን በጽኑ መታገል ጀመሩ። በ1956 ማንዴላ በአገር ክህደት ወንጀል በጊዜው በነበረው የነጮች መንግስት ተከሰሱ- ክሱ አምስት ዓመት ያህል በክርክር ከቆየ በኋላ ማንዴላ በክርክሩ አሸነፉ።
በማርች ወር 1960 ዓም፣ ሻርፕቪል በተሰኘችው ከተማ ፣ ጸረ አፓርታይድ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ ከነበሩት ጥቁር ሰልፈኞች መካከል 69 ያህሉን ፖሊሶች ተኩሰው በመግደላቸው ብጥብጡ ከፍ ያለ ደረጃ ደረስ። የወቅቱ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ እንቅስቃሴ ሲከለክል እንደማንዴላ በበኩላቸው ሰላማዊ ትግል እንደማያዋጣ በማመን ልዩ የጦር ሃይል አደራጁ። ማንዴላም የጦሩ የበላይ አዛዥ በመሆኑ እርዳታ ፍለጋ ወደሌሎች አገራት ጉዞ ማድረግ ጀመሩ።
ከውጭ አገር ሲመለሱ እዚያ ደቡብ አፍሪካ ላይ ተያዙና አምስት ዓመት እስር ተፈረደባቸው። በ1963 እንደገና ማንዴላና ሌሎች የ ኤ ኤን ሲ መሪዎች መንግስትን በሃይል ለመገልበጥ የሚል ክስ ተከፈተባቸውና ፍርድ ቤት ቀረቡ። ከዚያም ማንዴላ ዕድሜ ይፍታህ ተፈረደባቸውና ሮቢን ደሴት ያለ እስር ቤት ተላኩ። ማንዴላ ከሮቢን ደሴት ሌላ በተዘዋወሩባቸው ተጨማሪ እስር ቤቶች በጠቅላላ 27 ዓመት በ እስር ሲቆዩ ፣ በመላው ዓለም የነጻነት ምሳሌ ተደረገው ተወሰዱ - ዝናቸውም እየሰፋ መጣ።
በ1990 ዓ.ም የደቡብ አፍሪካ የነጮች መንግስት በተደረገበት ዓለም አቀፍ ጫና ማንዴላን ከ እስር ፈታቸው። ኤ ኤን ሲ የተባለው ድርጅታቸውም እንዲንቀሳቀስ ተፈቀደለት - ማንዴላም ተመልሰው ሊቀመንበር ሆኑ።
ማንዴላና የዚያን ጊዜው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኤፍ ደብሊው ደ ክላርክ በጋራ የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማት ተሸለሙ። ይህም የሆነው ጥቁሩ ማንዴላና ነጩ ደ ክላርክ የአፓርታይድ ሥር ዓትን ለማጥፋት ቁርጠኛ ስምምነት በማድረጋቸው ነበር።
በ1994 ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን ነጻ ምርጫ አደረገችና ማንዴላ የአገሪቷ የመጀመሪያ ጥቁር ፕሬዚዳንት ሆኑ። በ1998 ማንዴላ ለሶስተኛ ጊዜ ትዳር በመያዝ ከግራሻ ሚሼል ጋር ተጣመሩ። በ1997 ከ ኤ ኤን ሲ ሊቀመንበርነት ለቀቁ። በ1999 ደግሞ ፕሬዚዳንትነት በቃኝ አሉ። በ2004 ዓ.ም ማንዴላ ከፖሊቲካው ራሳቸውን አራቁና ጡረታ መውጣታቸውን አስታወቁ። እንዲያውም ያን ጊዜ “ለማውቃችሁ ሁሉ እኔ እደውልላችኋለሁ እንጂ እናንተ እንዳትደውልሉኝ” ማለታቸው ይነገርላቸዋል። ጡረታ በወጡ በዓመቱ ትልቁ ወንድ ልጃቸው ማካቶ ማንዴላ መሞቱ ልባቸውን በሃዘን ሰበረው። በተለይ አሟሟቱ በ ኤች አይ ቪ ስለነበር፣ ማንዴላ ያንን ምክንያት አድርገው ደቡብ አፍሪካውያን ከ ኤድስ ቫይረስ እንዲጠበቁና እንደማንኛውም በሽታ ቶሎ እንዲታከሙ ጥሩ አቀረቡ። ከዚያ ወዲህ ግን በበጎ አድራጎት ሥራ ሲሳተፉ ቆይተዋል። በ2010 ደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫን እንድታዘጋጅ ትልቅ ጥረት ያደረጉትን ማንዴላ ነበሩ። በመዝጊያው በዓል ላይም በመገኘት ለውድድሩ ድምቀት ሰጥተዋል። ዕድሜያቸው እየገፋም በመሄዱ 91 ዓመት ከሞላቸው ጊዜ በኋላ፣ በተለይም ከጃንዋሪ 2011 ጀምሮ ግን ባደረባቸው የስንባ ምች እየተስቃዩ በተደጋጋሚ ሆስፒታል ሲገቡና ሲወጡ ቆይተዋል።
ኔልሰን ማንዴል በግል ህይወታቸው ሳቂታና ተጫዋች መሆናቸው ይነገርላቸዋል። ፈግግታቸው ከማንም ልብ ሰርስሮ የሚገባ ነው። በሚገርም ሁኔታ 27 ዓመት በ እስር በመቆየታቸው ምንም የሚሰማቸው ምሬት እንደሌለ ሁልጊዜ ይናገሩ ነበር። ደቡብ አፍሪካም ለክብራቸው በገንዘቧ ላይ ፎቷቸውን ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ማተም ጀምራለች። ኔልሰን ሮህሊላ ማንዴላ በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ፣ ኅዳር 26 ቀን 2006 (ዲሴምበር 5 ቀን 2013) በወዳጅ ዘመድና ቤተሰብ ተከበው አረፉ። ማንዴላ ዛሬ በህይወት የሉም፣ በሁሉም ሰው ህሊና ውስጥ ግን ታላቅ ስብዕናቸው ለዘላለም ይኖራል።

ውድ የቻናላችን ተከታታዬች በተብራራ መልኩ በኔል ሰን ማንዴላ የህይወት ታርክ ዙርያ የተፃፈውን
LONG WALK TO FREEDOM በ PDF
ቀርቦላችኋል መልካም ንባብ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
2👍1