#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ዋጋው እርካሽ ተመጣጣኝ ወይም ውድ ሊሆን ይችላል እንጂ በነፃ የሚገኝ ነገር በዕድሜ ዘመኔ አላጋጠመኝም፡፡
ቢሾፍቱ አፋፍ ሆቴል ከተቀመጡ ከአንድ ሠዓት በላይ ቢያልፋቸውም ድምፅ ግን አልተሠማም፡፡ ሁሴን በማከታተል ከትካዜና ብስጭት ጋር ውስኪውን ያንደቀድቃል፡፡ ትንግርት ቀይ ወይኗን እየተጎነጨች በመስተወቱ አሻግራ አይኖቿን በጨለማ የተሸፈነውን የቢሾፍቱ ሐይቅ ላይ አተኩራ ትቆዝማለች፤ጨንቋታል አጠገቧ ሠው ተቀምጦ ዝም ሲላት ትፈራለች፡፡
‹‹የሆቴሉ መብራት ነፀብራቅ ጨለማው ሀይቅ ላይ ሲያርፍ የሚፈጥረው ውበት አያስደንቅም?›› ለንግግር መክፈቻም ጭምር ነበር ሀሳቧን የሠነዘረችው፡፡
ቀና ብሎ አያትና ‹‹ለመሆኑ ስታየኝ በዚህ ሠዓት የተፈጥሮን ውበት ለማድነቅ ዝግጁ እመስልሻለሁ?››
‹‹እርግጥ አትመስለኝም፤ ግን ዝግጁ መሆን ነበረብህ፤ አየህ የተፈጥሮን ውበት ማድነቅ ስትጀምር ልብህ በፍቅር ይቀልጣል... ስሜትህን ለፈጠራ ይነሳሳል..… ሕይወትም በስኬት ያሸበርቃል፡፡ አሁን ያለኸው ፍቅርን ፍለጋ ላይ ነህ፡፡ ፍቅርን ስትፈልግ ደግሞ ዘና ብለህ በደስታ ውስጥ ሆነህ መሆን አለበት፡፡ በብስጭትና ንዴት ፍቅርን እንዴት ወደራስህ መሳብ ትችላለህ፡፡ የተፈጥሮ ህግም አይፈቅድልህም፤ በሕይወት ተስፋ ስትቆርጥ ምድር ጨለማ ትለብሳለች ዕድል ካንተ ትርቃለች፡፡ ነፍስህም በእጦት ትጠወልጋለች፡፡››
‹‹ያልተነካ ግልግል ያውቃል አሉ፡፡››
‹‹አይምሰልህ ....እያልኩህ ያለሁት ማድረግ ያለብህን ነገር በብስጭትና ተስፋ በቆረጠ ስሜት ሳይሆን በመረጋጋት መንፈስ ከውናቸው እያልኩህ ነው፡፡ አየህ ዋጋው እርካሽ ተመጣጣኝ ወይም ውድ ሊሆን ይችላል እንጂ በነፃ የሚገኝ ነገር በዕድሜዬ አላጋጠመኝም፡፡››
‹‹እንደዚህ ውድ እና ግራ የገባው መስዋዕትነት የሚጠይቅ ነገር ገጥሞኝ አያውቅማ››
‹‹አውቃለሁ ግን አሁንም ልልህ የምፈልገው ተረጋጋ ነው፡፡ ቅድም እንዳልከኝ እኔ ለሊት ተነስቼ እሄዳለሁ፡፡ ከዛ በፊት ግን መረጋጋትህን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ››
ትኩር ብሎ አያትና ‹‹ለምን ለጊዜውም ቢሆን ርዕሳችንን አንቀይርም?››
‹‹ይመቸኛል፡፡ ርዕሰ ፍጠራ ስለምን ብናወራ ይመችሃል?››
‹‹ስለ አንቺ!››
‹‹ስለ እኔ ምን?›› እንደ መደንገጥም እንደመባነንም ብላ፡፡
‹‹ስለ አንቺ ማንኛውንም ነገር አንቺን በተመለከተ ያልተመለሱልኝ ብዙ ጥያቄዎች አዕምሮዬ ይጉላላሉ፡፡ መልሳቸውን ዛሬ ባውቅ አይከፋኝም፡፡››
‹‹ምን ችግር ...ተራ በተራ ጠይቀኝ፡፡››
‹‹ዛሬማ አንድ ጥያቄ ብቻ ነው እንድትመልሽልን የምፈልገው፡፡››
‹‹እሺ ቀጥል፡፡››
‹‹አፍቅረሽ ታውቂያለሽ?››
‹‹ምን ዓይነት ቀሽም ጥያቄ ነው ?መዓት ጊዜ ነው ፤አስር ... ሃያ ... ሠላሳ.... አላውቀውም፡፡››
‹‹እንደዛ ማለቴ አይደለም፡፡ መሠረት ያለው ከውስጥ ከስሜትሽ የመነጨ ፍቅር ማለቴ ነው፡፡ ልክ እኔ እንዳፈቀርኩት ፡፡›› እንደመቆዘም አለችና ለተወሠኑ ደቂቃዎች ትንፋሽ ወስዳ ከወይኑ አንዴ ከተጎነጨች በኋላ
‹‹አዋ ሦስት ጊዜ፡፡››
‹‹በቅደም ተከተል አውሪኝ፡፡››
‹‹እሺ ማወቅ ያለብህ ግን ይሄንን ታሪክ ለሌላ ለማንም ሠው አውርቼ እንደማላውቅ ነው፡፡ የመጀመሪያው ጌዲዬን ይባላል፡፡ የ 17 ዓመት ልጅ ሆኜ ነው ያፈቀርኩት፡፡ ጌዲዬን እስከዛሬ ካየኋቸው ወንዶች ሁሉ ቆንጆ ነው፡፡ በጣም ቆንጆ! ግን የቆንጆ ብልሹ! አንደኛ ከራሱ ጋር የተጣላ ሠው ነው፡፡ ተቅበዝባዥ! ያየው ሁሉ የሚያምረው፡፡ .. ይገርማል እንደውም ቃኤል ብዬ ነበር የምጠራው፤ልክ እንደ እሱ ያልተረጋጋ ሕይወት ስለነበረው እንዲያም ሆኖ በጣም አፈቅረው ነበር! ሦስት ዓመት ከቆየን በኋላ ግንኙነታችን ተቋረጠ፡፡››
‹‹እያፈቀርሽው ተውሽው?››
‹‹እኔ አይደለሁም የተውኩት እሱ ትቶኝ ሄደ፡፡ ከመጀመሪያ ፍቅረኛቸው ሲለዩ ብዙ ሠዎች ይጎዳሉ፤እኔ ግን ተቃራኒው ስሜት ነበር የተሠማኝ፡፡ ግንኙነታችን አንድ ቀን እንደሚያከትም እርግጠኛ ሆኜ ስጠብቅ ነበር፤ እናም ከሦስት ዓመት ቆይታ በኋላ ማለት አንደኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን እንዳጠናቀቅኩ አካባቢ ነበር ...ከእኔ ራቀ.... በየሜዳው ስለ እኔ ማውራት ጀመረ፡፡››
‹‹ምን እያለ ነው የሚያወራው?››
‹‹በቃ አለ አይደል... ያልበሠለ አይነት ሠው
ወሬ! አልፈልጋትም፤ ሌላ ወድጃለሁ፤ አትክዳኝ
እያለች እየለመነችኝ ነው፤እኔ ግን አልፈልጋትም>>
ብርጭቆውን አንስቶ ጨለጠና ሌላ አስቀዳ፤ የጨፈገገ ስሜቱ እየለቀቀው ነው፡፡ ጨዋታው መስጦታል ፡፡ ስለ እሷ ያለፈ ታሪክ አንድ መረጃ አገኘሁ ሲል አሠበ፡፡
‹‹ታዲያ ወሬዎቹን ስትሰሚ አልተበሳጨሽም?››
‹‹በመጠኑ ተበሳጭቼያለሁ፤ግን ብዙም አልደነቀንም፤ከእሱ የምጠብቃቸው ነገሮች ስለነበሩ ታዲያ ምን እንዳደረኩ ታውቃለህ፤ ስለሱ የሚሠማንን ሁሉ በሁለት ገፅ ወረቀት ፅፌ በደብዳቤ ላኩለት፡፡ ከዛ በኋላ አይኑን ለማየት አልፈለኩም፡፡ ተመልሶ ለመምጣት ሞክሮ ነበር... የእኔ የፍቅር በር ግን ተከርችሞ ነበር:: >>
‹‹ለመሆኑ ምን የሚል ደብዳቤ ነው የላክሽለት?››
‹‹ጌዲዬን እስከአሁን እንዳልረሳሁት የማውቀው በምን እንደሆነ ታውቃለህ? ደብዳቤውን ቃል በቃል አሁንም ማንበብ ችላለሁ፡፡ >>
ግርም አለው ‹‹አረ በፈጠረሽ አስኪ ልስማሽ!››
‹‹እርግጠኛ ነህ?››
‹‹ኧረ ከእርግጠኛም በላይ፤ ይልቅ ጊዜ አትፍጂ ቀጥይ …፡፡ >>
‹‹ጌዲዮን ከዳኋት ብለህ ታወራለህ አሉ፡፡ እኔ
ግን ከድተኸኛል ብዬ አላስብም፡፡ እርግጥ
አውቃለሁ ጥለኸኝ ሄደሃል፡፡ ነገር ግን አልከዳኸኝም ፤የምትከዳኝ እኮ መጀመሪያውኑ ባምንህ ነበር፤ እኔ ግን ከተገናኘን ሠዓት ጀምሮ አንዲት ሽራፊ ደቂቃ እንኳን አንተን በማመን አባክኜ አላውቅም፡፡እርግጥ አፈቅርህ ነበር፤ አሁንም አፈቅርሀለሁ፡፡አጠገብህ ስሆን ደስታ ውስጤን ይወረዋል፤ ስትለየኝ ግን በሃዘን አልቆራመድም፡፡ አንተ እና ለማዳ እርግብ አንድ ናችሁ ብዬ ነው የማስበው፡፡ ባሻት መንገድ በራ፤ የነፀነት አየር ስባ ስትጠግብ ወደ ማደሪያዋ በመመለስ አሳዳሪዋ ትከሻ ላይ አርፋ የፍቅር መዝሙር በጆሮው የምታንሾካሽኩለት፤ አንድ ቀን ግን በሌላ ለማዳ እርግብ ተጠልፋ ሌላ አሳዳሪ ጎጆ ተሰንቅራ እንደምትቀር አይነት ዕርግብ አንተም ተመሳሳይ እጣ እንደሚገጥምህ አስብ ነበር እና ከድቻታለሁ ብለህ አትደሰት ወይንም በፀፀት አትተክዝ፡፡ በፊቱን ተጣመርን እንጂ አልተዋሀድንም፡፡ ጥምረት ደግሞ ልክ በብሎን እንደተያያዘ ሁለት የብረት ቁራጭ ማለት ነው፡፡ ብረቶቹን ለመነጣጠል ብሎኑን መፍታት ብቻ በቂ ነው፡፡
እኔ እና አንተ በአብሮነታችን ወቅት ሁለት ነበርን፤ አሁንም ሁለት ነን፡፡ ልዩነቱ አጣምሮን የነበረውን ብሎን ሳታማክረኝ ባንቀላፋሁበት ፈተኸው እራስህን ከእኔ በማላቀቅ ከሌላ ጋር በሌላ ብሎን መጣበቅህ ነው፡፡አደራ የምልህ ግን አሁንም አዲሷን ተጣማሪህን በዛ አዚማዊ በሆነ ውበትህ አደንዝዘህ፣በዛ ለስላሳ ግን መርዝ በሚተፋ አንደበትህ አታለህ ለውህደት እንዳትጋብዛት፡፡ እሷ እንዋሀድ ብትልህ እንኳን እሺ አትበላት ለመዋሀድ እኮ መቅለጥ ያስፈልጋል፡፡ እሷ መቅለጥ ብትችል እንኳን አንተ ግን ፀሐይን እራሷን ያለችበት ድረስ ተጉዘህ ብታፈቅራት እንኳን ልታቀልጥህ አትችልም፡፡ ካልቀለጥክ ደግሞ ልትዋሀዳት ስለማትችል ሲበቃህ እሷንም አንድ ቀን እንደእኔው ከዳሁሽ ትላታለህ፡፡ የዛን ጊዜ ሞራሏ ይደቃል፣ ተስፋዋ ይሰበራል፣ የየዋህ ሠዎችን ተስፋ ማጨለም ደግሞ ንስሃ የሌለው ሀጥያት ነው፡፡ዳሩ አንተ ምንም ብታረግ አይፈረድብህም፡፡

👍94❤18😁2
ምክንያቱም የፍቅር ረሀብተኛ ነህ፡፡ ከእኔ በፊትም ብዙ ቦታ ፈልገኸው አላገኘኸውም፤ አሁንም ለማግኘት እየባዘንክ ነው፡፡
ከዚህ በፊት የነገርኩህን ዛሬም ልድገምልህ ‹ማንኛውም እንስት ላንተ ሽራፊ ፍቅር ቆንጥራ ልትሠጥህ አትችልም፡፡ እርግጥ በወሲብ ፈረስ ልታጦዝህ ትችል ይሆናል፤ ፍቅር ማለት ግን ያ ብቻ አይደለም፡፡ ፍቅርን መፈለግ ያለብህ ከእራስህ ልብ ውስጥ ነው፡፡ ምንጩ እዛ ስለሆነ! እስቲ መባከኑን ገታ አድርግና አረፍ ብለህ ውስጥህን አዳምጥ ‹በመጀመሪያ እኔ እራሴ እራሴን አፈቅረዋለሁ ወይ?› ብለህ ጠይቅ፤ በእርግጠኝነት እነግርሀለሁ፡፡ አንተ ፈጽሞ እራስህን አፍቅረህ አታውቅም፡፡ ከቀኑ አብዛኛውን ሠዓት የምታባክነው እራስህን
ስትረግምና ስትወቅስ መሆኑን በደንብ አድርጌ አውቃለሁ፡፡ እራሱን ማፍቀር የማይችል ሠው እንዴት ሌላውን ማፍቀር ይችላል? እባክህ እራስህ ላይ አትጨክንበት፡፡ በመጀመሪያ አመለካከትህን አፅዳ ቀጥሎ፤ እራስህን ለማፍቀር ሞክር፤ ከዛ በኋላ ሌላውን ሠው የማፍቀር ብቃቱና ችሎታው ይኖርሀል፡፡ በሌላውም ትፈቀራለህ፡፡ ምን ይታወቃል <ከዳኋት› የሚለውን ቃል ዘወትር እንደጀብድ ከማውራት ትገላገል ይሆናል› ይሄው ነው፡፡››
‹‹አንቺ ቆይ ማነሽ?›› ከአንደበቱ ሾልኮ የወጣውን ጥያቄ ይሄ ብቻ ቢሆንም ለማለት የፈለገው ግን ብዙ ነገር ነበር፡፡ ስለእሷ ያለው መገረምና መደነቅ ከማሠብ አቅሙ በላይ ሆነበት፡፡
‹‹እኔማ ትንግርት ነኛ!››
‹‹ትንግርት ነኝ ትላለች እንዴ ትንግርትማ ትንግርት ነሽ፡፡ ኧረ ከትንግርትም በላይ ነሽ፡፡ ይሄን ሁሉ ሀሳብ ሸምድዶ ለሠባት ዓመት ሙሉ በአዕምሮው መዝግቦ የሚያቆይ ሌላ ሠው አላውቅም፡፡ የተጨበጨበላቸው ተዋናዮች እንኳን ቢሆኑ ለመሆኑ ጌዲዬን አሁን የት እንዳለ ታውቂያለሽ?››
‹‹በደንብ አውቃለሁ›› እጇን ወደ እሱ ዘረጋች፡፡
‹‹ምንድነው?››
ብራስሌቱ ላይ ያለውን አንብብ፤የዛሬ ዓመት ገደማ ነው የላከልኝ፡፡››
በመስገብገብ እጇን ወደ እራሱ አስጠግቶ አነበበው ‹ባንቺ ምክር ለዚህ በቃሁ› ይላል፡፡
‹‹ምን ለማለት ፈልጎ ነው?››
‹‹በወቅቱ ውስጤን ለማስተንፈስ የፃፍኩለት
ደብዳቤ እራሱን እንዲመረምር አደረገውና ወደ መስመር ተመለሰ፤ እነሆ ዛሬ ከስኬት ጫፍ ላይ ተቆናጠጠ፡፡››
‹‹ትንሽ አብራሪልኝ፡፡››
‹‹ይሄ የምነግርህ ሠው በአሁኑ ሰዓት በጣም ታዋቂና ብርቅዬ የዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሆኗል፡፡››
‹‹ለጊዜው ስለ እዚህኛው በቃሽ፤ስለሁለተኛው ትነግሪኝ?››
ትንፋሿን ሆዷ እስኪወጠር ወደ ውስጥ ስባ አንጀቷ እስኪጣበቅ ወደ ውጭ ተነፈሠች፡፡
<<ምነው?>>
‹‹የሁለተኛው እንደመጀመሪያው ቀላል አይደለም፡፡ የፍቅሩ አይነት፣ ያሳደረብኝ ጠባሳና በሕይወቴ ላይ ያስከተለው ለውጥ ያልተለመደ አይነት ነው፡፡››
‹‹ምን የተለየ ነገር አለው ታዲያ? ያንቺ ነገር እኮ ሁሉም ያልተለመደ አይነት ነው፡፡››
‹‹ይሄ ግን ይለያል፡፡››
‹‹ልስማዋ፡፡››
‹‹ሁለተኛዋ ፍቅረኛዬ ሴት ነበረች፡፡››
‹‹ምን አልሽ? አልሰማሁም፡፡›› እስከ አሁን የጠጣው መጠጥ ውሃ እንደሆነ ሁሉ ውስጡ ቀዘቀዘበት፡፡
‹‹ሰምተኸኛል፤ልክ ከእሱ በተለየሁ በስድስት ወሬ ከሴት ጋር ነበር ፍቅር የጀመርኩት፡፡ በወቅቱ ስለ እንደዚህ አይነት ነገር ከወሬ ባለፈ ብዙም ግንዛቤው አልነበረኝም፡፡ ተጣማሪዬ ግን የልጅነት ዕድሜዋን ውጭ አገር ጨርሳ ወጣትነት ውስጥ ስትገባ በቤተሠብ ውሳኔ ስርዓት የለሽ ሆነች፤ ከባህሏ አፈነገጠች በሚል ሠበብ ልክ እንደ ማረሚያ ቤት ወደ አገሯ ላኳት፤ አያቷ ጋር፡፡
‹‹ካንች ጋር እንዴት ተገናኛችሁ?››
‹‹እሷም የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበረች፡፡ ከሁለተኛ ዓመት ጀምሮ አንድ ዶርም ነበር የምንጋራው ፤ቀስ በቀስ ተቀራረብን አብረን መዋል አብረን ማደር ጀመርን፤ እንደምታየው በተፈጥሮዬ አዲስ ነገር ለመሞከር ደፋርና ጉጉ ነኝ፡፡ እንደ ቀልድ አስጀመረችኝ፤ ቀስ በቀስ ሠመጥንበት፡፡
ተጣብቀን መዋል ጀመርን፡፡ ለሠዓታት መለያየት እንኳን አቃተን፤ ብዙ ነገር አሳለፍን፣ ብዙ ፍቅር ሠራን፣ ብዙ ተዝናናን፣ ብዙ ቃል ኪዳን ተለዋወጥን፡፡››
‹‹ምን ዓይነት ቃል ኪዳን?›› በመደንዘዝ ውስጥ ሆኖ ጠየቃት፡፡
‹‹በቃ እስከ ሕይወታችን ፍፃሜ ላለመለያየት፣ አንድ አካባቢ ስራ ለመቀጠር፣ አንድ ላይ ለመኖር፣ በቃ ለመጋባት፡፡››
‹‹እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆናችሁ ሁለት ሴቶች ለመጋባት?››
‹‹ምን አለበት? በይፋ መዘጋጃ ሄደን በመፈራረም እኮ አይደለም ለመጋባት የወሠነው፤ ሕጉም ባሕሉም እንደማይፈቅድልን እናውቃለን፡፡ እንደ ሁለት ሴት ጓደኛሞች ግን አንድ ቤት ለዘለዓለምም ቢሆን እንዳንኖር የሚከለክለን ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህም ነው ለመጋባት የወሰነው፡፡ በጣም
ነው ያፈቀርኳት! በጣምም ነበር ያመንኳት፤ ሁሉ ነገሬም ሆና ነበር››
‹‹ታዲያ መጨረሻው እንዴት ሆነ?››
‹‹መጨረሻውማ ተመረቅን፤ ሁለታችንም ናዝሬት አንድ ካምፓኒ ውስጥ ስራ አገኘን፤ ቤት ተከራየን፤ እኔም እሷም ከየቤታችን የሚያስፈልግንን መሠረታዊ ቁሳቁስ አሟላንና መኖር ጀመርን፡፡ እጅግ ጣፋጭ የሆነ ገነታዊ ኑሮ! ግን ለሦስት ወር ብቻ …፡፡››
የታሪኩን ፍፃሜ ለመስማት ልቡ ተንጠልጥላ ጉሮሮው ውስጥ የተወተፈች መሠለው‹‹ከዛ በኋላ ምን ተከሠተ?››
‹‹ዳግመኛ ተከዳሁ፡፡ ምንም ሳትነግረኝ ወላጆቿ ጋር አሜሪካ ተመልሳ በረረች የመጨረሻውን ሀዘን አዘንኩ፡፡ እድሜ ልኬን ማልደግመውን ለቅሶ አለቀስኩ፤ ስራዬን አቋርጬ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ …ከዛም ሁሉንም ነገር ጥዬ ሸርሙጣ ሆንኩ! እራሴን
ለመርሳት፤ኑሮዬን ለማጨመላለቅ፤ ውስጤን ለማቆሸሽ ተመቸኝ››
‹‹ያልገባኝ ነገር አንቺም ውጭ የመሄዱ እድሉ አለሽ...ቤተሠቦችሽ ጠቅላላ እዛ አይደለ ሚኖሩት?እና ለምን አብራችሁ ሳትሄዱ?››
‹‹አብሮ ለመሄድ እኮ መጀመሪያ መነጋገር መመካከር ያስፈልጋል፤ አንድም ቀን እኮ ተመልሳ ወደ ውጭ መሄድ እንደምትፈልግ ተሳስታ እንኳን ስታወራ ሠምቻት አላውቅም፡፡ እኔ እኮ እሷን ከማጣት አይደለም አሜሪካን ሲኦልም ቢሆን እንሂድ ብትለኝ ተከትያት እሄድ ነበር::>>
‹‹ታዲያ ከዛስ በኋላ ቢሆን… አድራሻዋን ፈልገሽ ለምን ለመሄድ አልሞከርሽም፡፡››
‹‹ያንማ በፍፁም አላደርገውም፡፡ የማፈቅራትን ያህል ነው የጠላኋት፡፡ ዳግመኛ ባገኛት እንደምገላት እርግጠኛ ነበርኩ...ስለዚህም
አልፈለኩም... የወሠድኩት እርምጃ እሷንም እኔንም መርሳት ነው፡፡››
‹‹ እሷን መርሳት ግን እንዳሰብሺው ተሳካልሽ?»
‹‹የፈረደባት ልቤ ሦስተኛ ሠው ወደ ጓዳዋ ጎትታ እስክታስገባ ድረስ እራሴንም እሷንም እረስቼ ነበር መሠለኝ፡፡››
‹‹ሦስተኛው ደግሞ ምን ዓይነት ይሆን?››
‹‹ስለ ሦስተኛው እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ውስጤ ግን በጣም እየፈራ ነው፡፡ስለ ፍፃሜው ሳስብ ከሁለተኛውም የከፋ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ይሠውረን ነዋ! ለማንኛውም እስቲ
«አጫውችኝ...::>>
<<ሌላ ቀን።>>
‹‹በእንጥልጥልማ አታቋርጭም፡፡››
‹‹አትልፋ ዛሬ አልነግርህም፡፡ ይልቅ ሂሳብ ዝጋና ተነስ እንተኛ፡፡›› አስተናጋጁን ጠራና ሂሳቡን ሠጥቶት ተጨማሪ መጠጥ መኝታ ቤታቸው እንዲያመጣላቸው አዞት መቀመጫውን ለቆ ተነሳ፤ ተከተለችው፤ ጎን ለጎን ነው የያዙት፡፡ ቀድማ ክፍሏን ከፍታ ገባች ፤ተከትሏት ገባ፡፡
‹‹ትንሽ ማውራት ብዙ መጠጣት እፈልጋለሁ፡፡ የጠጣሁትን ሁሉ ወሬሽ አርክሶብኛል፡፡››

👍81👎13❤9😱3🔥2
‹‹ከሚገባው በላይ አወራን፤ አሁን መተኛት ነው ያሠኘኝ፡፡ መጠጣት ከፈለክ ክፍልህ ግባና በራፍህን ዘግተህ አስነካው፤ ብቻ ልብህ እንዳትፈነዳ፤ ለማንኛውም ለሊት ከመሄዴ በፊት ሠላም ማደርህን ማረጋገጡን አልረሳም፡፡››
‹‹ቁርጤን ሳላውቅማ ሜዳ ላይ ብቻዬን ጥለሺኝ አትመለሺም፡፡›› በማለት አልፏት ሄዶ አልጋው ጎን ያለው ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ እሷም ምንም እንኳን ብቻዋን ሆና አልጋዋ ውስጥ ገብታ ስላወራችለት ነገር ዳግመኛ ማሰላሰል ብትፈልግም በግድ ግን ወደ ክፍሉ ልታባርረው አቅሙን አላገኘችም፡፡ አስተናጋጁ የታዘዘውን መጠጥ አምጥቶ በራፉን ዘግቶ ተመልሶ ሄደ፡፡
✨ይቀጥላል✨
አሁንም ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍59❤17👎8😱8
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
✍ አሌክስ አብርሃም
ክፍል ሁለት
መጀመሪያ ስለ ሰውነቷ...
ስለ እርሷ ባሰብኩ ቁጥር ደጋግሜ የማስበው ይኼንን ነው፤ እንደ አለት የጠነከረ ጅልነቴ ጋር በላባ መንፈሷ ስትፋለም የኖረች ምስኪን ነበረች፡፡ ምስኪን ነበረች እልና አንዳንዴ አይ! ጀግና ናት፣ እላለሁ፤ ወይስ ጀግኖች ምስኪኖች፤ ምስኪኖችም ጀግኖች ናቸው?!
ለአራት ዓመታት “በፍቅር”” ቆዬን፡፡ ከልጅነት መፍለቅለቅ ወደ አዋቂነት መብሰልሰል ያለፈችው በእኔ ላይ እየፈሰሰች ነበር፡፡ እኔ ፀሐይ እንዳቃጠለው ደረቅ ምድር ነበርኩ፤ እሷ እንደ ወንዝ በእኔ ላይ ፈሰሰች፤ አነሳሷ የበዛ ኃይል የነበረው የክረምት ጎርፍ ዓይነት ነበር። የበዛ ተስፋዋ፣ ሳቋ፣ ፍቅሯና የዋኅነቷ እኔ ውስጥ ሰርጎ የደከመ የበጋ ምንጭ አከለች፡፡ እሷ እና እኔ - እኔና የእሷ ሰውነት አራት ዓመት አብረን ቆይተናል፡፡ያውም አራት ወራት የሚመስሉ አራት ዓመታት። አራት ዓመት ብዙ ነው፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት ተወልደው በየልሳናቼው መናገር ጀምረዋል፤ መናገር መጀመር ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ለቅሶም ቢሆን፤ መጥቻለሁ የሚል መልዕክት ባለው ለቅሶ ነው መቼስ ወደዚህች ዓለም የተቀላቀልነው፡፡ ዓለም ብዙ ሚሊዮን ድምፅ ጨምራለች፡፡ ስንትና ስንት አገር የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጎርፍ፣ አውሎ ነፋስ፣ ወረርሽኝ እና ጦርነት ተነስቶ ብዙ ሺዎች አልቀዋል፡፡ ይህች ቻይ መሬት ከተፈጠረች ጀምሮ፣ ባዶ የነበሩ ሜዳዎች ሰማይ በቀል ፎቆች አብቅለዉባቼዋል፡፡ አገራት ተጣልተዋል - አገራት ታርቀዋል፡፡ አራት ዓመት ብዙ ነው። ባዶ የነበሩ የወጣት ወንዶች አገጭ ላይ ፂም አቆጥቁጧል፤ ሕፃናት- ወጣት፣ ወጣቶች- እናትና አባት ሆነዋል፡፡ ችምችም ያሉ ጎፈሬ ራሶች፣ ወደ መላጣነት እዝግመዋል፡፡ ሚሊዬኖች በዝምታ ይችን ዓለም ለቀው ሄደዋል፡፡ እንደ እኩለ ቀን ጥላ ስብስብ ያሉ ውብ የቆነጃጅት ጡቶች፣ እንደ ምሽት ጥላ ረዝመው ወርደዋል፡፡ ብዙ ውበት በዕድሜ ፈራርሷል፡፡ አንዳንዱ ውበት በሚያፈቅረው ልብ እንደ ጽላት ተጽፎ ትውስታ፣ በፎቶም ምሥል ቀዝቃዛ ትዝታ ሆኗል፡፡ አንዳንዱም
እንዳልተፈጠረ- እንዳልነበረ ሁሉ ካለመታሰቢያ ትቢያ ሆኖ ጠፍቷል፡፡ አራት ዓመት ብዙ ነው!! የሰዓት መቁጠሪያ እጄታዎች ዞረው የተነሱበት ቦታ ላይ እያረፉ ጊዜን ቢቆጥሩም? ጊዜ ግን ዞሮ አይመለስም፤ እንደ ጅራታም ኮከብ ከሆነ ጨለማ ተነስቶ፣ ወደ ሆነ ጨለማ- ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ የሚምዘገዘግ፣ መጨረሻም መጀመሪያም የሌለው ግትልትል ፍርጎ ነው። የትኛው ዘመን ላይ ነበርን?! ስንል የትኛው ፍርጎ ላይ ነበርን?! እንደ ማለት። እኔና እሷ በፍቅር ቆዬን ማለት አሻሚ ነገር አለው፡፡ ፍቅር በሙሉ ልብ ሁለንተናን የመውደድ እና የመቀበል የነፍስ ስሜት ከሆነ፣ በአራት ዓመት ቆይታችን ለአንዲት ደቂቃ እንኳን እንደዚያ ዓይነት ስሜት የተሰማብኝን ጊዜ አላስታውስም። አፈቅርሻለሁ ያልኩባትም ጊዜ ትዝ አይለኝም። አላፈቅራትም ነበር? ወይስ የፍቅር ብያኔ አልገባኝም? እንጃ!! የሆነ ሆኖ እንዲሁ አብሮ _ መቆዬታችንን “ፍቅር” ልበለውና ለማንም መፋቀራችንን እዩልን አላልንም፡፡ እዬተጓተትን የጓደኞች መንጋ ውስጥ አልተገኘንም፡፡ ወይኔ ስታምሩ! አብሮ ያቆያችሁ፣ ውለዱ፣ ክበዱ የሚል የዐንገት በላይ ምርቃት ፍለጋ አብረን ፎቶ እየተነሳን አላሳዬንም፡፡ ይኼ ሕዝብ ምርቃቱ የርግማን ገበር አብሮት የተሰፋ ስለሚመስለኝ፣ ምርቃቱን ሲያለብስ ርግማኑንም አብሮ ያከናንባል እያልኩ እፈራ ነበር፡፡ ምርቃት እና ርግማን ሰም እና ወርቅ ናቸዉ። የሚበዛው ምርቃት ሰሙን እንደ አቧራ እፍ ብለን ካዬነው ወርቁ ርግማን ሳይሆን ይቀራል!? እናም ምርቃቱ እውነት አይመስለኝም፡፡ ምርቃታችን ቢሠራ ኖሮ እንደ እኛ የተመራረቀ ሕዝብ የት አገር ይገኛል? ርግማናችንም ቢሆን ስልብ ነገር ይመስለኛል፤ የረገምናቼው እንዳማረባቼው አሉ። ርግማንህም- ምርቃትህም አይያዝልህ ብሎ ሕዝቤን የረገመው ይኖር ይሆን? ወይስ እንደ ሒሳብ ስሌት ምርቃታችን በእርግማናችን እየተጣፋ ባለንበት የሚያስረግጥ የዜሮ ድምር ሕይወት እየኖርን ነው?
እሷ ጋር አብረን የተነሳነው አንድም ፎቶ አልነበረንም። በአራት ዓመት ቆይታችን አንድም የእርሷ ፎቶ አልነበረኝም ብል ማን ያምነኛል? ሁሉም ትዝታ በጋለ ብረት ቆዳ ላይ እንደተተኮሱት ጠባሳ ለዘላለም ላይጠፋ፣ ቼልተኛ አእምሮዬና አፍቃሪ ልቧ ላይ ታትሟል። ዓይነቱ ቢለያይም በሕይወት እስካለን ይኽን ማኀተም ስናዬው፣ አልያም ጠባሳ ነውና በአንዳንድ የሕይወት ብርዳማ ቀናት ሲጠዘጥዘን፣ በትካዜ “ጆሯችንን የተበሳን፣ በጋለ ብረት የተተኮስን የፍቅር እና የውበት ባሪያ ነበርን'' እንላለን፡፡ ባርነትም እንደ ነፃነት የሚናፍቅበት ጊዜ እንዳለ ማን ያውቃል?! ምኗን ትወድላት ነበር? ብባል ሁለት ጊዜ ሳላሰብ፣ ሰውነቷን እና ስሟን እላለሁ፤ ማኅደረሰላም ትባላለች፡፡ ሰዎች “ማኅደረ ሰላም ምን ዓይነት ስም ነው!?'' ሲሏት፣ ፈገግ ብላ “ትንሽ ረዘመ አይደል? ያውም የአባቴን ቀንሸላችሁ ነው'' ትላለች፡፡ ስትስቅ የታችኞቹ ጥርሶቿ አይታዩም፡፡ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም ፈገግታዋ የሚያልቅ ዓይነት አልነበረም፤ ሁልጊዜ የሆነ የቀረ የተደበቀ ቀሪ ፈገግታ ያላት ያስመስላታል፡፡ ሙሉ ስሟን ብወደውም፣ መቼ እንደጀመርኩት ትዝ በማይለኝ ማቆላመጥ ማሂሰላም ነበር _የምላት። “ማሂሰላም'' ስላት በእነዚያ ዓይኖቿ በጥልቀት እያዬችኝ “ ማንም እንደዚህ ጠርቶኝ አያውቅም'' ትለኛለች፡፡ እንዴት እንደተዋወቅን አሁን ላይ ትዝ አይለኝም ብል ማን ያምናል!? ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀጣጥረን የተገናኜንበትን ቅጽበት ግን አስታውሳለሁ፡፡እሷን ሳስታውስ ያንን ቅጽበት አልረሳዉም። ግን ከመቀጣጠር በፊት መተዋወቅ ይኖራል መቼም፣ እንዴት ነው የተዋወቅነው? ሁልጊዜ የማስበው ጥያቄ ነው፡፡ ይኼን ጠይቂያት አላውቅም፡፡ ያስቀይማት ይሆናል በሚል ፍርኃት (ማነው ከፍቅረኛው ጋር የተዋወቀበትን ቀን የሚረሳ? ጅል ወይም የማስታወስ ችግር ያለበት ሰው ካልሆነ በስተቀር) ያ! መተዋወቅ ነው፣ እንዴት እንደ ነበር ትዝ የማይለኝ፡፡ የዚያ ሰሞን ብዙ ሴቶች አውቅ ስለነበር ተቀላቅሎብኝም እንደሆነ እንጃ! በአንድ ፀሐያማ ቀን (ቅዳሜ መሆን አለበት...ያኔ በአንድ የግል ድርጅት ተቀጥሬ እሠራ ስለነበር ሰው የምቀጥረው ቅዳሜ ቀን ነበር) ከሜክሲኮ ወደ ቄራ
በሚወስደው መንገድ፣ ከገነት ሆቴል ከፍ ብሎ የሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ ነበር ቀጠሯችን። የሕንፃው ሁለተኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው ሬስቶራንት ስገባ ቀድማኝ ደርሳ አገኘኋት፡፡ ስስ፣ ነጭ መጋረጃ በተጋረደበትና እንዱን ግድግዳ ሙሉ ለሙሉ በያዘው ሰፊ መስኮት በኩል፣ ጀርባዋን ለመስኮቱ ሰጥታና እጇን ደረቷ ላይ አነባብራ ተቀምጣለች። ከእርሷ በስተቀር በመስኮቱ በኩል የተቀመጡት ሰዎች በሙሉ ፊታቼው ወደ መስኮቱ ዞሮ፣ የቄራ ሜክሲኮን የመኪና እና የሰው ትርምስ ማዬት በሚችሉበት አቅጣጫ ነበር አቀማመጣቼው። ምንም ቁም ነገር ባይኖረውም ትርምሱ ትኩረት ይስባል። ለትርምሱ ጀርባዋን ሰጥታ ነበር መጀመሪያ ሳገኛት። ከንፈሯ ሬስቶራንቱ ውስጥ ከተከፈተው ዘፈን ጋር አብሮ ይንቀሳቀስ ስለነበር፣ አብራ እየዘፈነች መሆኗ ያስታውቃል፡፡ የብራ ቀን ሰማይ የመሰለ ስስ ውሃ ሰሚያዊ ሹራብ ለብሳለች፣ሰላም ያለው ሰማያዊ። ሹራቡ መካከለኛ ክብ ጡቶቿን ቀድመው እንዲታዩ አድርጓቼዋል፡፡ እጅጌውን ሰብሰብ ስላደረገችው፣ ጠይም ግራ እጇ አንጓ ላይ የምታበራ ቀጭን ወርቃማ 'ብራዝሌት' ትታያለች፡፡ በጥቁረትና ግራጫነት መኻል የሚዋልል ቀለም ያለውን ረዥም ጸጉሯን ወደ ኋላ ሰብስባ በማስያዝ

👍49❤2😁2👏1
ለቀዋለች፡፡እንደ እሷ ለጸጉሯ ግድ የሌላት ሴት ዓይቼ አላውቅም፡፡ የለበሰችው ጥቁር ጅንስ ሱሪ፣ የሰውነቷን ውብ አወራረድ አጉልቶ ያሳጣል፡፡ ቀላል ፈዘዝ ያለ ሰማያዊ 'ፍላት' የቆዳ ጫማ ተጫምታለች፡፡ እስከ መጨረሻው ሳውቃት አለባበሷ እንዲህ ቀለል ያለ ነበር፡፡ ተረከዘ ረጅም ጫማ ላይ ቆማ ሁለት ርምጃ መራመድ አትችልም፡፡ ለውበት ግዴለሽ ናት፡፡ ውበት ግን ችላ እንዳሉት አፍቃሪ በእልኅ እንደተከተላት ነበር፡፡ ፊት ለፊቷ፣ ግማሹ ወደ ብርጭቆ የተጋባ የሚሪንዳ ጠርሙዝ እና ሽንጣም _ ብርጭቆ በሚያምር ብርቱካናማ ቀለም ተሞልቶ ተቀምጧል... ከጎኑ፣ ትንሽ ከቆዳ የተሠራች ሰማያዊ የእጅ ቦርሳ... ቦርሳዋ ከጫማዋ በተረፈው ቆዳ የተሠራች ነበር የምትመስለው። ...ይኼንኑ ነው የማስታውሰው፡፡
በዚያ ርቀት ያዬሁት ያ ምሥሏ ልክ እንደ ፎቶ እስከ አሁን በውስጤ ተቀምጧል፡፡ በተለይ ብርጭቆ ዉስጥ የነበረው የሚሪንዳ ቀለም ትዝ ባለኝ ቁጥር ምን እንደዚያ አደመቀው? እላለሁ፡፡ ምናልባት በመስኮቱ የገባው ብርሃን? ገና ሰላም ተባብለን እንደተቀመጥን የ'ሷን ብርጭቆ አንስቼ፣ ሚሪንዳውን ቀመስኩት- ፈገግ አለችና “ውጩ ይሞቃል አይደል?'' አለችኝ፡፡ ከእኔ ብርጭቆ መጎንጨትህ ልክ ነው በሚመስል ድምፅ፡፡ አሁን ላይ ሳስበው በመጀመሪያ ቀጠሮ ከሰው ብርጭቆ መጎንጨት ትንሽ ብልግና ይሆንብኛል፡፡ እሷ ግን ስለዚያ አጋጣሚ ስታወራ”ቀለል አድርገህ ስለቀረብከኝ ያኔውኑ ነው የወደድኩህ'” ትላለች፡፡ እንደ ትልቅ ነገር ደጋግማ ነበር የምትነግረኝ... ሌላም ነገር አስታውሳለሁ፡፡ መጀመሪያ እንዳዬኋት፣ ገና ሰላም ሳልላት፣ ሳልቀመጥ፣ የተሰማኝ ትንሽ የሚያሳፍር ዓይነት የወሲብ ስሜት ነበር፡፡በዚያ ፍጥነት በዚያ የብልጭታ ያኽል በፈጠነ ዕይታ እንዴት ይኼ ስሜት ተሰማኝ? እሷ የመጀመሪያዬ አልነበረችም፡፡ እንዲያውም ስንተኛዋ የሴት ጓደኛዬ እንደነበረችም እንጃ፡፡ በሴት የተለከፍኩ ነበርኩ፡፡ ከአንዷ ሸሽቼ ልቤ እስኪፈነዳ ር ^ና፣ መድረሻዬ ሌላኛዋ ነበረች፡፡ ምድር ላይ ሴቶች ብቻ የሚኖሩ እስኪመስሉኝ ዕጣ ፋንታዬ ሄዶ ሄዶ የሚያርፈው ሴት ላይ ነዉ። ትንሽ እንኳን የአየር ማስገቢያ ክፍተት በሌለው ሁኔታ ዙሪያዬን በሴት የተከበብኩ ነበርኩ፡፡ ባይከቡኝም ራሴን ወስጄ ክበቡ መኻል የማስቀምጥ ሰው ነበርኩ። ጓደኛ፣ ዘመድ ወይም የሥራ ባልደረቦቼ ጋር ተገናኝቼ ወሬ ሲጀመር “ባለፈው ከሆነች ልጅ ጋር የሆነ ካፌ አይቼህ፣ ባለፈው ታክሲ ላይ አይቼህ- ከሆነች ልጅ ጋር፣ ትላንት ከሆነች ልጅ ጋር መንገድ ላይ አዬሁህ ልበል? ነው? አይደለም? እያልኩ... አጅሬው መልአክ የመሰለች ልጅ ጋር ሜክሲኮ ታይተኻል...ፓ! ቆንጆዎቹን በትእዛዝ የምታስመጣቼው'ኮ ነው የሚመስሉት፣ የትላንቷ ደግሞ ልዩ ናት...ሃሃሃሃሃ! ደግሞ ምን የምታኽለው ጋር ገጠምክ?.... ተርፈህ አይኻለሁ አላልኩም ነበር፤ ተራራ የምታኽል ልጅ... እዚያ ታክሲ ፌርማታው ጋ አዬሁህ- በፈጠረህ ዘመዴ ነች በለኝ!... በስማም ጥላህን የመሰለች ጥቁር ልጅ ጋር አዬሁህ ወዘተ፡፡ እንደዚያ ነበር ምስሌ፡፡
መታፈኔ አማርሮኝ(ልክ ያልፈለግሁት ይመስል) ከዚህ አዙሪት ለመሸሽ ስወራጭ? የሴቶች ዳና ነፍሴ ላይ እንደ መርግ ከብዶ ስንዝር አላራምድ ይለኛል። ልተንፍስ ብል የምተነፍሰው እነሱን ነው። እማረራለሁ፤ ግን እዚያው ነኝ፡፡ ከሴቶች መራቅ አለብኝ እላለሁ፤ ግን እዚያው ነኝ፡፡ ልክፍት ነው እላለሁ ለራሴ፣ ዕድል ነው ይላሉ ሌሎች። የሴት ልጅ ሳቅ ወጥመዴ ነው፣ ስለ ጥርሷ ውበት ግድ የለኝም፡፡ የሴት ኩርፊያ ገሃነም ነው የሚሆንብኝ፡፡ ኩርፊያ አልወድም፤ ግን አኩራፊ ሴት የሆነ ነገሯ ይስበኛል፡፡ የሴት ልጅ ዕንባ ልቤን ያስጨንቃታል፤ ቀርባኝ ያላለቀሰች ሴት ግን የለችም፡፡ የሴት ዕንባ ጥሩ አይደለም፣ አጉል ቦታ ይጥልኻል የሚሉትን ሟርት ክፉኛ አምናለሁ። ባለቀሱብኝ ቁጥር የሰማይ መልአክት ሁሉ ዶማና አካፋ ይዘው የነገ መንገዴን ቆፋፍረው ሊያበላሹ፣ በዕንባዋ ወንዝ ላይ እየቀዘፉ የሚፈጥኑ ይመስለኛል ። ሴቶች ሲያለቅሱብኝ፣ ዕንባቼውን የማስቆምበት መንገድ የሚመስለኝ አብሮ መተኛት ነበር። ስቃልኝ አብሪያት ያልተኛኋት ሴት የለችም፡፡ አልቅሳብኝ አብሪያት ያልተኛኋት ሴት የለችም፡፡ አኩርፋኝ አብሪያት ያልተኛኋት ሴት የለችም። ሳትስቅም፣ ሳታለቅስም፣ በውብ ዓይኖቿ በቁም ነገር ስታዬኝም ያልተኛኋት ሴት የለችም፡፡ ለእኔ ብቻ የተለዬ የመሬት ስበት የተሠራ ይመስል ለመውደቅ ቅርብ ነበርኩ፡፡ ተሳስቼ አንዷን _ በሌላዋ _ ስም የጠራሁበት ጊዜ ብዛቱ! እንግዲህ ለእያንዳንዷ ሴት በመታወቂያ ስሟ ማኅደር አላዘጋጅ ነገር። “አንተ ምን አለብህ! ሰው አንድ አጥቷል አንተ ታተራምሰዋለህ” የሚሉኝ ወንድ ጓደኞቼ ፊት ላይ የማዬው ቅናትና የማስተውለው አድናቆት ገብቶኝ አያውቅም። ሴቶቹ እንደ ዕቃ እኔ ብቻ ቁልፉን የያዝኩት መጋዘን ውስጥ አይደለም የሚኖሩት፤ ሁላችንም አንድ ዓለም፣ አንድ አገር፣ አንድ _ ከተማ ነን፡፡ ለምን ማተራመስ የሚያስቀና ከሆነ አያተራምሱም? ጨዋ ነን ከሆነ ቅናቱን ምን አመጣው!? እኔ አተራምሼ፣እነሱ ተመኝተው እኩል ሲኦል መነዳታችን አይቀር!! ያዬ በልቡም
የተመኜ፣ አመነዘረ አይደል የሚለው ቃሉ!? (“ሰይጣን ላመሉ መጽሐፍ ቅዱስ Μή" )... ያኔ የዘወትር ጥያቄዬ፣ ሰዎች እንዴት አንድ ሰው አፍቅረው ይኖራሉ? የሚል ነበር፡፡ እንዴት ለዓመታት አንድ ሰው በታማኝነት ይጠብቃሉ? ያውም በዙሪያቼው ከሚጠብቁት ሰው የተሻሉ ብዙዎች እያሉ? ይመስለኛል፣ ወይ አንድ ሰው እንዲያፈቅሩ ተረግመዋል፤ ወይም ማንንም እንዳያፈቅሩ ተረግመዋል፡፡ ግራህንም ዘረጋህ ቀኝህን፣ ጣቶችህ የሚነኩት ርግማንን ከሆነ የተሻለውን ርግማን መምረጥ የተሻለ ነው፡፡ እሱም ርግማንህን ከብዙዎች ጋር መካፈል፤ አምሳ ርግማን ለአንድ ሰው ሸክሙ ለአምሳ ሰው ...እንጃ! እነዚያ ሁሉ ሴቶች ጋር ፍቅሬን ሳይሆን ርግማኔን ስካፈል የኖርኩ ይመስለኛል፡፡ ስለ እሷ ሌላ ምን አስታውሳለሁ? ምንም! ከዚያ ቀጥሎ ያለኝ ትዝታ፣ ልክ ራሱን ስቶ በሌላ ቀን ሆስፒታል አልጋ ላይ እንደነቃ ሰው... የሆነ ቀን ሁለታችንም ራቁታችንን እኔ ቤት አልጋዬ ላይ መገኜታችንን ብቻ ነው፡፡ ጠይምነቷ አልጋዬ ላይ፣ ምንጣፌ ላይ፣ ሶፋዬ ላይ፣ በእርጋታ ተጥለቅልቆ... ጠይም ውቂያኖስ ሆኖ። ሰውነቷ ይገርመኛል፡፡ ለማንም የሚገርም ዓይነት ጠይም ሰውነት ነበራት። ከእግሯ እስከ ፊቷ ትንሽ እንኳ የቀለም ልዩነት የሌለው ጥይምና። ጡቶቿ ጫፎች ላይ ግራ እና ቀኝ እንደ ዓይን ብሌን በክብ ከተሳሉ ጠይም ጥቁረቶች በስተቀር አንድ ዓይነት፡፡ ብዙ... ብዙ የሴት ሰውነት ዓይቻለሁ፣ ማን ናት የፊቷ ቀለም ከሰውነቷ ጋር አንድ ዓይነት የነበረው? አላጋጠመኝም፡፡ ወይ ጉልበቷ ይጠቁራል- አልያም _ እንዲህ ለመናገር የሚከብድ የሰውነቷ ክፍል ላይ ይዥጎረጎራል፡፡ የእርሷ ግን ይለይ ነበር፡፡ ፈጥሮ ከጨረሳት በኋላ ጠይም ቀለም ውስጥ በቀስታ ነክሮ ያወጣት ነበር የምትመስለው፡፡ ጠይምነቷ፣ በቀስታ ከላይ ከጸጉሯ ሥር ወደ ታች፣ ወደ እግሯ ጣቶች የሚፈስ ዓይነት ነው፡፡ የእጄን አውራ ጣት ሰውነቷ ላይ አጥቅሼ ወረቀት ላይ ባሳርፈው ጠይም አሻራ የማገኝ ይመስለኛል፡፡ ለዘላለም ከትውስታ የማይጠፋ ጠይምነት፡፡

👍35❤7
ያ ነቁጥ እንኳን የሌለው ንጹህ ጠይም ገላዋ የልቧም ምሳሌ ነበር፡፡ ከእኔ በፊት ማንም በፍቅር ያልታሰበበት፣ የማንም አሻራ ያላረፈበት፣ ንጹህ ልብ፣ ንጹህ ገላ፣ ንጹህ መንፈስ፣ ያውም በዚያ ዕድሜ፡፡ የውበትም የንጽህናም ጉልላት ነበረች። እንዲህ ግን ብያት አላውቅም፡፡ በማላውቀው ምክንያት ቃል አውጥቼ ለማድነቅ እፈራ ነበር። ከእኔ የሚወረወር የቃል ጠጠር የሚሰብራት፣ ስስ ነበረች፡፡ ሙገሳዬ ፍቅር _ ቢመስላትስ እያልኩ ሲበዛ ቁጥብ ነበርኩ፡፡ ከዚያ ሰውነቷ ጋር በፍቅር የወደቅሁ ፍጡር ነበርኩ፡፡ አንድ በአንድ የማውቃቼውን ሴቶች እየተውኩ ለአራት ዓመታት አብሪያት የቆዬሁት፣ በሰውነቷ ፍቅር ነው፡፡ ስንት ሴቶች አውቅ ነበር? ብዙ...ብዙ። የማስታውሳቼውን ልዘርዝር ብል ...ያቺ የግል ኮሌጅ ትማር የነበረችዉ- ፋሲካ የምትባል ልጅ- ወገቧ ችቦ አይሞላም የተባለላት፤ እሷም ይኼን አውቃ ስትራመድ ወገቧን ለማሳዬት የምትንጠራራ፣ በጥፍሯ ልትቆም የሚዳዳት፡፡ ያቺ ጥቁር አንበሳ በቀጣዩ ዓመት ተመርቃ ሐኪም ልትሆን ስትደክም የነበረች (በኋላም ሐኪም ሆና የጋብቻ ቀለበት አድርጋ ያዬኋት) ኪያ: በብዙ ንባብ የዛለ ሰውነቷን እየጎተተች የምታገኘኝ ምስኪን...
ያቺ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ መሸጫ ውስጥ የምትሠራ‐ ከተሰቀሉት አምፖሎች እንደ አንዱ የሚያበራ ቅላት የነበራት፣ ቢነኳት የምትፈርጥ የምትመስል፣ ርጋታዋ የሚያረጋጋ ራውዳ። ያቺ የጴንጤ ዘማሪ የሆነች፤ ኢየሱስን እየሰበከችኝ... እየሰበከችኝ... እዬሰበከችኝ...የገነትን መንገድ ስተን ወደ አልጋ የሄድን ሩሃማ... ስንተቃቀፍ... ኦ! ጅሰስ... ውይይ... ጅሰስዬ.... እያለች የምትቃትት.... ነገራችንን ከፈጻጸምን በኋላ በኃፍረት ዓይኔን ማዬት የምትፈራ፣አንዳንዴም ረከስኩ እያለች የምታለቅስ፡፡ ...ያቺ ...ያቺ...ከአስመራ የመጣች፣ በድፍን ኢትዮጵያ ሽሮና ቡና የምትችል ሴት የሌለች እስኪመስለኝ “ብታገባኝ የምሠራልህ ሽሮ፣ የማፈላልህ ቡና፤ እኔ እንደ ሐበሻ ሴት እንዳልመስልህ" የምትል፡፡ ...ያቺ ከመቐሌ የመጣች- ቅናቷ የሚያስፈራኝ ባለ ጥቁር ረዥም ጸጉር ልጅ “አንድ ቢራ ብትጠጣ ትሞታለህ?'' የምትል፤ ባለመጠጣቴ ክፉኛ የምትበሳጭ “ ቢራ” ስትል ፊደሎችን
ስለምታጠብቃቸው “ቢራቢሮ” የሚለውን ቃል ለሁለት ከፍላ ቢሮን የተወችው ነበር የሚመስለኝ። ያቺ...ከወለጋ የተጓዘች "ከረቫት" ካላሰርክ እያለች ቤቴን በ'ከራቫት' ስጦታ የሞላች(ምን ነክቷት ነበር ግን?!)...ያቺ የአርባ ምንጭ ልጅ፣ የደቡብ ጭፈራ ካላለማመድኩህ ብላ የደከመች፤ ስልጠናው አልሆን ሲለኝ አንተ እንኳን ጭፈራ ጭብጨባም አይሆንልህ ያለችኝ... ሌሎችም ክተት ታውጆ የተጠሩ ይመስል ዘር እና ሃይማኖት ሳይለያያቼው በጠላት እንደተወረረ የአገራቼው መሬት፣ እኔ ገላ ላይ ዘመቱ፤ እኔም ሳላዳላ በእነሱ ላይ ዘመትኩ። . . .መጨረሻ ላይ ግን ልቤ በአድሎ አዘነበለ፤ ሁሉንም ተራ በተራ ትቼ ማሂሰላም ጋር ተሰበሰብኩ፡፡ ልክ እንደ ትዳር እሷ ጋር ብቻ፤ ለድፍን አራት ዓመታት፡፡ ግን አላፈቅራትም ነበር።ይኼ ታዲያ ተአምር አይደለም!? ትንፋሽ እስኪያጥረኝ በጉጉት የምጠብቀው ትዕይንት ቢኖር ማሂሰላም ልብሷን ስታወልቅ ማዬት ነበር፡፡ሁልጊዜ ሳያት እንደ ሽንኩርት የተደራረበ ጠይምነት ለብሳ የምትኖር ይመስለኛል፤ ማታ ማታ ከላይ የዋለችበትን ጥይምና ስትልጠው ከውስጥ አዲስ የሚወጣ፤ የማሂሰላም ሰውነት ይለያል፤ እጅ ላይ ብቻ ሳይሆን ዓይን ላይ የሚለሰልስ ሰውነት ነው ያላት። የተቀቀለ ዕንቁላል፣ በሥርዓት ቅርፊቱ ሲነሳ የሚኖረው ጥራትና ልስላሴ ዓይነት ነበር ሙሉ ሰውነቷ። በክረምት ማለዳ መነሳቴ ላይቀር ከሞቀ አልጋዬ ውስጥ መውጣት እንደሚከብደኝ፤ መለያዬታችን ላይቀር ሰውነቷ በሚሰጠኝ ምቾት ሰንፌ አራት ዓመት አብሪያት ቆዬሁ። አራት ዓመት እንዲህ አጭር ነው?! የምታወራውን ነገር ነገሬ ብዬ ሰምቻት አላውቅም፡፡ _ አፈቅርሃለሁ ትበለኝ- እጠለሃለሁ፣ ትመርቀኝ- ትርገመኝ፣ ታልቅስ- ትሳቅ፣ጉዳዬ አልነበረም፡፡ ብዙ ቀናት አብረን ስቀናል፤ በምን እንደሳቅን ዛሬ ላይ ትዝ አይለኝም፡፡ሰውነቷ ብቻ ነበር ምስልም ድምፅም ያለው ሕያው ነገር። ምን የሚሉት ፍቅር ነው ይኼ ሰውነትን ከሰው ለይቶ በፍቅር መውደቅ?
“በሳለፋችሁት አራት ዓመታት ከተናገረቻቼው ነገሮች ሙሉ ለሙሉ የምታስታውሰው ምንድን ነው?'' ብባል፤ ከብዙ ብዙ ወሬዋ በላይ ሰውነቷ ናፍቆሻ ስደውልላት “ ወይዬ አብርሽ! ...እሺ እመጣለሁ'' የሚል ለስላሳ ድምጿን ነበር፡፡ ሳምንት ቆይቼ ስደውል፣ አንድ ወር ጠፍቼ ስደውል፣ ሦስት ወራት ጠፍቼ ስደውል፣ የድምፅዋ ልስላሴ ሳይቀዬር “ ወይዬ አብርሽ! ...እሺ እመጣለሁ" ሰው ከምን ከምን ነበር የተዋቀረው ያሉን!? ከሥጋ፣ ከነፍስ እና ከመንፈስ...እሷስ? ከአፍቃሪ ሰውነት፣ ሰላም ካለው ሰውነት እና ከጠይም ሰውነት። ፍቅር ነፍሷ ...ሰላም መንፈሷ ...ጠይምነት ሥጋዋ ... ዝም ብለን ከነፍሳችን ተዋደድን፤ እሷ እኔን እኔ እሷን ....
እቤቴ ትመጣለች፡፡ በሰጠኋት ቁልፍ በሬን እየተጣደፈች ትከፍትና ልክ ከኋላዋ የሚያሳድዳት ሰው ያለ ይመስል በፍጥነት በሩን ትዘጋለች፡፡ “በቃ በር ማንኳኳት ቀረ?'' እላታለሁ፤ ልቀበላት እዬተነሳሁ፡፡ “ለምን አንኳኳለሁ? ውጭ ያለሁ እኔ ውስጥም ያለሁ እኔ" ትል እና ፈገግታዋ ያጥለቀልቀኛል፡፡ እጆቼን እንደክንፍ እዘረጋለሁ፣ ተንደርድራ መጥታ በእጆቿ ወገቤ ላይ ትጠመጠማለች፤ ሳቅፋት ልጥፍ ትልብኛለች። አለጣጠፏ ሁሉን ነገሯን ለእኔ መስጠት ነበር፡፡ አፈቃቀሯ፣በምድር ላይ ሌላ የሰው ዘር የሌለና እኔና እሷ ብቻ የምንኖር እስኪመስል የእኔ ብቻ የመሆን ነበር፡፡ ትንፋሽ እስከሚያጥረን እንሳሳማለን፤ ድንገት ገፋ ታደርገኝና ከእቅፌ ወጥታ “ሙዚቃ! ሙዚቃ! ሙዚቃ!" እያለች ትጮኻለች፡፡ በደስታ እየተፍለቀለቀች ጥግ ላይ ወደተቀመጠው 'ሲዲ ፕሌየር' ራመድ ብላ በየጊዜው እያመጣች ከከመረቻቼው የዘፈን ሲዲዎች አንዱን መርጣ ትከፍታለች፡፡ ብርሃን እንዲገባ ከፋፍቼ የምተወውን የመስኮት መጋረጃ ከግራና ቀኝ እየጎተተች ትጋርደውና መብራት ታበራለች። ቤቴ በሙዚቃ፣ በእርሷ ጠይምነት እና ፈገግታ ይሞላል፡፡ ማሂ ሰላም ፊቷ በእርካታ ይጥለቀለቃል፡፡
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍70❤3😢2
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
እሁድ ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት
ሁሴን ከነጋ ከትንግርት ጋር አልተያዩም፡፡ ማታ ሲጠጡና ሲጫወቱ እስከ ስምንት ሠዓት ነበር የቆዩት፡፡ ከዛ በኋላ ነው ብቻውን መሆን እንደሚፈልግ የተናገረው ነገር ከምሩ ሳይሆን በወቅቱ ተበሳጭቶ ስለነበር ገልፆላት ይቅርታ እንድታደርግለት ከለመናት በኋላ የመጨረሻ ዕድሉን የመሞከሪያ ቀኑንም አብራው እንድትሆን አሳምኗት ሊተኛ ወደ መኝታ ክፍሉ እየተንገዳገደ የሄደው፡፡
ከእንቅልፉ ሲነቃ ሠባት ሠዓት ሆኖ ነበር፡፡ በርግጎ በመነሳት ከክፍሉ ወጥቶ የትንግርትን ክፍል ሲያይ እሷም አልተነሳችም፡፡ ከዛ ያደረገው ነገር ቢኖር አስተናጋጁን ጠርቶ ምግብ እና የምትጠጣው ነገር ክፍሏ ድረስ እንዲወስዱላት ማድረግ ነበር፡፡ እሱም ለራሱ ሻወር ከወሠደ በኋላ ምሳውን በልቶ ወደ ከተማ ወጣና ዞር ዞር ብሎ ሲመለስ ትንግርት እንደተኛች አገኛት፡፡ ክፍሉ ገብቶ የተዝረከረኩና የተበታተኑ የግል ዕቃዎቹን ሠብስቦ በሻንጣው ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ወደ ሆቴሉ እንግዳ መቀበያ ክፍልም ሄዶ ያለበትን ሂሳብ ዘጋ፡፡ ዛሬ ከበፊት ቀናት ይልቅ የመዝናናት የደስታ ስሜት እየተሠማው ነው፡፡ ሠዓቱን ተመለከተ፤ ዘጠኝ ተኩል ሆኗል፡፡
በመካከለኛ ኃይል የትንግርትን በር አንኳኳ፡
ኳ..ኳ..ኳ..ኳ..ኳ
‹‹ማነው?"
‹‹በሕይወት አለሽ? የበከትሽ መስሎኝ ነበር፡፡››
‹‹አንተም አልበከትክ .. ጠብቀኝ መጣሁ፡፡››
ከውጭ እንደተገተረ የተወሠኑ ደቂቃዎች አስጠበቀችው፡፡በዝግታ በሩ ተከፈተና ‹‹ግባ›› አለችው፡፡ ገባ፡፡ መልሳ በራፉን ዘጋችው፡፡ ከሻወር ነው የምትወጣው፡፡ገና ልብሷን
አለበሰችም፡፡ መሀከላዊ ሠውነቷን በፎጣ ጠቅልላዋለች፡፡አብዛኛው የላይና የታች አካሏ እንደተራቆተ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ቀን ያያት ይመስል ዓይኖቹን ተከለባት፡፡ ከእሷ ጋር ያሳለፋቸው የፍቅር ጊዜያቶች፣የቆዳዋ ልስላሴ፣የሠውነቷ ጠረን፣የከናፍሮቿ ጣዕም፣ጠቅላላ ትዝታው የፍቅር ረሃቡን ቀሠቀሱበት፡፡ የቡና ቤት ሕይወቷን ካቋረጠች ስምንት ወር ሞላት ያ ማለት ከእሱ ጋርም ጾታዊ ግንኙነት ማድረግ ካቆሙ ስምንት ወር አለፏቸዋል ማለት ነው፡፡ያ የሆነው ደግሞ እሷም ፊት ስለነሳችው እሱም ስለፈራት ነው!፡፡
‹‹ምነው አትናገርም እንዴ?››
‹‹እንዲህ ቆንጆ ሆነሽ አይቼሽ አላውቅም..›› አላት አስቦበት አይደለም በድንገት ነው ቃላቶቹ ከአንደበቱ ተስፈንጥረው የወጡት ፡፡
ተንጨፍርሮ ውሃ የቋጠረ ፀጉሯን በፎጣ እያደረቀች‹‹ምን አልባት ያየኸኝም ዛሬ ገና ብቻ ሳይሆን አይቀርም!!›› መለሠችለት ፡፡
‹‹አይደለም፤ካገኘሁሽ ቀን ጀምሮ በጥልቀት አይሻለሁ፤ ቆንጆ እንደሆንሽም
አውቃለሁ፤አሁን ለማለት የፈለኩት ግን የተለየሽ ሆነሻል ማለቴ ነው፡፡ዞማ ፀጉርሽ ተንጨፍርሮ ወዲህና ወዲያ መዘበራረቁ፤የአይኖችሽ ቅንድቦች አበጥ…
አበጥ ማለታቸው፣የፊትሽ ወዝ ጥራቱ፣ደረትሽ
ላይ ያለው ሀብል፣የጡቶችሽ
መቀሰር፣ያገለደምሽው ፎጣ፣ ወጣ ወጣ ያሉ
ዳሌዎችሽ፣በትንሹ የተጋለጠው ባትሽ፣ የእግሮችሽ ጣቶች፣በቃ እነዚህ ሁሉ በአንድ ላይ በግልፅ ሳያቸው ምን ዓይነት ስሜት እንደፈጠሩብኝ ታውቂያለሽ? ምነው
ሠዓሊ በሆንኩ ነው ያሰኘኝ፡፡›› ያለ ምንም
ፍራቻና መሳቀቅ ፊት ለፊቱ ልብሶቿን እየለበሠች ንግግሯን ቀጠለች
<<አቶ ጋዜጠኛው! እነዚህን የመሰሉ ውብ የፍቅር
ዓረፍተ ነገሮች ያለቦታቸው አታባክናቸው፡፡ ነው
ወይንስ በኋላ እሷን ስታገኛት ምን ማለት
እንዳለብህ እየተለማመድክብኝ ነው? >>
‹‹ካገኘኋትማ አትበይ! ለምን እንደዚህ ደስ ያለኝ ይመስልሻል፤ ዘጠና ዘጠኝ ፐርሠንት ያቺ ጠይም አንባቢ የእኔዋ ምስጢር እንደሆነች እርግጠኛ ነኝ፡፡ ግን አመንሽም አላመንሽም ስለ አንቺ የተናገርኩት ከምሬ ነው››
ቀሚሷን ከስር አጥልቃ ዳሌዋን ካለበሰች በኋላ ከላይ ያለውን ፎጣ አንስታ አልጋ ላይ ወረወረችና በገረሜታ ቆሞ የሚያወራትን ሁሴንን ተመለከተችው፤እናም ከወገቧ በላይ እንደተራቆተች አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለችና እሱንም ስባ ከጎኗ አስቀመጠችው፡፡ ግራ በመጋባት ዝም ብሎ ተጎተተላት፡፡
‹‹እስቲ ንገረኝ... ቆይ እኔ ላንተ ምንህ ነኝ?››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹ብዙ ጊዜ የእኔ ነገር በቀላሉ እንደማይገባህ አውቃለሁ፡፡ ለማለት የፈለግኩት እኔ ላንተ የድሮ የቡና ቤት የወሲብ ደንበኛህ ነኝ? ... የድሮ ፍቅረኛህ ነኝ? ... ወይስ ጓደኛህ ነኝ?...
ወይንስ በቃ ዝም ብሎ በሆነ አጋጣሚ የምታውቀኝ አንድ ተራ ግለሠብ ነኝ?››
ዝም ብሎ የጎንዬሽ ተመለከታት፡፡ በመጀመሪያ ጥያቄዎቿ እንደወትሮው የቀልድና የሽሙጥ መስለውት ነበር፡፡ አይኖቿን ሲያነባቸው ግን ትናንትና ማታ ስላለፈ የፍቅር ሕይወቷ ስትተርክለት ያስተዋለውን አይነት ስቃይ አነበባቸው እናም ጥያቄዎቿን በጥሞና አጤናቸው፡፡
‹‹ትክክለኛ መልስ ነው የምትፈልጊው?››
‹‹ለስሜቴ ቅንጣትም ሳትጨነቅ ትክክለኛ የሚሠማህን››
ለደቂቃዎች እንደመቆዘም አለና መናገር ጀመረ፡፡ ‹‹እንግዲያው እውነቱን ንገረኝ ካልሽ አንቺ ምኔ እንደሆንሽ ከአሁን በፊት አስቤው አላውቅም፡፡ ግን በእርግጠኝነት የማውቀው አንድ ነገር ቢኖር ዘወትር ካንቺ ጎን መሆን መፈለጌን ነው፡፡ሁል ጊዜ ስበሳጭ፣በሕይወቴ
የሆነ ነገር ሲመሠቃቀልብኝና ማደርገው ነገር ግራ ሲገባኝ፣መጨፈር ወይም ማልቀስ ሲያሠኘኝ፣አጠገቤ ማግኘት የምፈልገው ብቸኛዋ ሠው አንቺ መሆንሽን በእርግጠኝነት አውቃለሁ፡፡ይሄ ስሜቴና ፍላጎቴ የጓደኝነት ይሁን የፍቅር ... ብቻ ትክክለኛ ስሜቱን አላውቅም፡፡ በቃ ይሄው ነው፡፡›› በማለት ንግግሩን ጨርሶ ቀና ሲል ከሚንከባለሉ ዓይኖቿ እንባዋ እየተንጠባጠበ ደረቷ ላይ አርፎ በጡቶቿ መሃከል ሲንኳለል ተመለከተ፡፡
‹‹ምን ያስለቅስሻል ... ምን የሚያስለቅስ ነገር ተናገርኩ?›› በማለት ይበልጥ ተጠጋትና ቀኝ እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ሊያባብላት ፈለገ፡፡
‹‹ምንም ክፉ ነገር አልተናገርክም፡፡ እንደውም በተቃራኒው መስማት የምፈልገውን ነገር ስለነገርከኝ ደስ ብሎኝ ነው ያለቀስኩት፡፡ እኔም ስላንተ የሚሠማኝን ነገር ሁሉ ዝርግፍ አድርጌ ብነግርህ ደስ ይለኝ ነበር ...ግን አልችልም በፍፁም አልችልም›› ሠዓቷን ተመለከተች ፡፡
ዘጠኝ ሠዓት ሆኗል፡፡
‹‹ይሄውልህ አሁን ዘጠኝ ሠዓት ነው፡፡ ወደ ቀጠሮህ ቦታ ለመሄድ የቀረን አንድ ሠዓት ብቻ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ነገሮች ሁሉ መልካቸውን ይቀይራሉ ፤እንዳልከው እሷ ሆና ካገኘሀት እንደዚህ እንደዛሬው አንድ ቤርጎ ጎን ለጎን ለዛውም ግማሽ እርቃን ሆኜ ማውራት ይቅርና በአደባባይና በካፌ እንኳን የመገናኘት ዕድላችን በእሷ በጎ ፍቃደኝነት የሚወሰን ይሆናል፡፡ ባታገኛትም የተለየ ታሪክ አይኖረውም፤ምክንያቱም እኔ ከዚህ በፊት ደጋግሜ በፍቅር እጦት እንደተሠባበርኩ አንተም ትሠበራለህ፤ከዛ በኃላ አንተ ትጠፋና በድንህ ብቻ ይቀር ይሆናል፤ከበድንህ ጋር
ደግሞ እንደከዚህ ቀደሙ ያለ ግንኙነት ሊቀጥል አይችልም ...>>
‹‹ምን እያወራሽ ነው?የሲኦል ፍራቻ በልቤ ውስጤ እየበተንሽ እኮ ነው
‹‹እኔም በጣም ስለፈራሁ ነዋ፡፡ ከፍራቻዬ ጥልቀት የተነሳ እየተንቀጠቀጥኩ አይታይህም?››
‹‹መንቀጥቀጥሽ ይሠማኛል፤ግን ተረጋጊ በእኛ ግንኙነት መካከል ምንም የሚቀየር ነገር አይኖርም፡፡›› እርግጠኛ ባይሆንም በወቅቱ ማለት የሚችለው እንደዚህ ነበር፡፡
‹‹እንድረጋጋ...ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ.... ማለት ከዛሬ ወዲህ መቼም የማይደገም… በቃ...መሠናበቻ ...›› ንግግሯን መጨረስ አልቻም ሳግ አቋረጣት፡፡
‹‹የመሠናበቻ ምን? ... ንገሪኝ፡፡››

👍110❤11😁1🤔1🎉1
‹‹የመሠናበቻ እንድትስመኝ እፈልጋለሁ፡፡››
ቀኝ እጁን በአንገቷ ዙሪያ ጠምጥሞ መላ እሷነቷን ቀስ ብሎ ወደ ደረቱ አስጠጋት፡፡ ዓይኖቿን ጨፍና በዝግታ ተሳበችለት፡፡ ከናፍሮቻቸው ተዋሃዱ፤ ኃይል በተቀላቀለበት አሳሳም ይመጣት ጀመር፡፡ እሷም እየቃተተች...
መጠመጠችው፤እርቧት ነበር፤የስድስት ወር እረሃብ፤ ደግሞም ለዝንተዓለም እንደማታገኘው ተሠምቷታል፡፡ ይበልጥ ሠውነቱ ላይ ተጣበቀችበት፡፡እሱም በፈረጠመ ጡንቻው ጨመቃት፤ከደረቱ ጋር አጣብቆ ጡቶቿን አፍረጠረጣቸው፡፡
ከሠላሳ ደቂቃ በኋላ ሲነቁ አልጋ ላይ ሳይሆን ወለሉ ላይ እርቃናቸውን ጎን ለጎን ተዘርረዋል፡፡ ምን ጊዜ የለበሠችውን ጉርድ መልሳ እንዳወለቀች ምን ሠዓት የእሱ ልብሶች እንደወላለቁ በእርግጠኝነት የሚያውቅ የለም፡፡
‹‹አመሠግናለሁ፡፡›› አለችው፤ ከተኛችበት ወለል ተነስታ ተመልሳ ወደ ሻወር ቤቱ እያመራች፡፡
‹‹እኔ ነኝ እንጂ ማመስገን ያለብኝ፤ምን ያህል አጥቼሽ እንደነበር ያወኩት አሁን መልሼ ሳገኝሽ ነው ::>>
ሻወር በራፍ ላይ ከደረሠች በኋላ ቆም አለችና ፊቷን ወደ እሱ አዙራ ‹‹ሳገኝሽ ሳይሆን ስሠናበትሽ በል፤ቃል ቃል ነው ይሄ የመጨረሻችን ነው›› በማለት ወደ ሻወሩ ገብታ ውሀውን ለቀቀችው፡፡ እሱም ከተጋደመበት በዝግታ ተነሳና ተከትሏት ሻወር ገባ፡፡ ሳሙናውን ከእጇ ተቀበለና አንገቷ እስከ እግር ጥፍሯ ድረስ ሠውነቷን በአረፋው አዳረሠው፤ እሷም ተቀበለችውና የእሱን ሠውነት በተመሳሳይ ሁለቴ በአረፋው ሸፈነችው፤ ውሀውን እስከ መጨረሻ ከፍተው ተራ በተራ እየተሻሹ መታጠብ ቀጠሉ፡፡ በመሀከል የእሱ እጆች ሁለት ጡቶቿ አካባቢ ሲደርሱ አንዳቸው ከአንዳቸው ወደ ኋላ ማፈግፈግ አልተቻላቸውም፡፡ያልታወቀው ኃይል ሁለቱንም አንድ ላይ አጣብቆ ጨምቆ ያዛቸው፤ ቀና ብላ በፍንጥርጣሪ ውሃዎች መሀከል አፈጠጠችበት፡፡ የተቃውሞም ሆነ የትብብር ስሜት አልታየባትም ፤ ወደ ራሱ ሳባትና አፉን አፏ ላይ ዳግመኛ ከደነ፡፡ የመጨረሻው መጨረሻ የሆነውን ጣፋጭና
አይረሴ ፍቅር ሠሩና ሠውነታቸውን ተለቃልቀው መታጠቢያ ቤቱን ለቀው ወጡ፡፡ ወለሉ ላይ የተዝረከረከ ሱሪውን አነሳና ከኪሱ ውስጥ ሞባይሉን አወጣ፤ ሠዓቱን ተመለከተ...10፡10 ይላል፡፡ ‹‹ኧረ ሠዓቱ ሄዷል›› በማለት በጥድፊያ ልብሶቹን ከተጣሉበት እየለቃቀመ መልበስ ጀመረ፡፡ ትንግርትም ቅድም ልትለብሰው የነበረውን ጉርድ ቀሚስ ወለሉ ላይ ስለተረጋገጠባት ሌላ ደማቅ ቀይ ሙሉ ቀሚስ ከሻንጣዋ አውጥታ መልበስ ጀመረች፡፡
<< ቶሎ በይ... በአስር ደቂቃ ውስጥ ሻንጣሽን
‹‹ለምን ከዛ ስንመለስ አናዘጋጅም?››
‹‹አይቻልም፤ወደዚህ መመለስ አልፈልግም፤ በዛው ነው የምንሄደው፡፡››
‹‹በቃ ያቺ ጠይም ወጣት ምስጢር እንደሆነች እርግጠኛ ሆነሀል ማለት ነው?በዛው ይዘሃት ወደ አዲስ አበባ ልትበር ቸኩለሃል..!!!››
‹‹አዋ! ለማንኛውም እስክትዘጋጂ የእኔን ሻንጣ መኪና ላይ ልጫን›› በማለት በራፉን ከፍቶ ወጣና ወደ ራሱ ክፍል ገባ፡፡

👍140❤30👏8
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
✍ አሌክስ አብርሃም
ክፍል ሶስት
ሁሉን ነገሯን ስትሰጠኝ፣ ሁሉንም ተቀብያት አላውቅም፤ እመርጣለሁ፡፡ ቸልተኛ ነፍሴ መርጦ በጣቱ የሚያነሳው የዘረጋችለትን ሁሉ አልነበረም...ጊዜዋን፣ ልቧን፣ ቃሏን፣ ዕምነቷን፣ ሕይወቷን... ያላትን ሁሉ ለራሷ ሳታስቀር ነበር የሰጠችኝ፡፡ ለእኔ ግን ሰውነት ነበረች። ውብ ሰውነት፣ለስላሳና እንደ እቶን የሚፋጅ ጠይም ገላ፤ ሳይሰስት ራሱን የሚሰጥ፣ እንደፈለግሁ በፈለግሁት ሰዓት የማገኜው ውብ ገላ፤ የወጣትነት የታመቀ እቶን! ጠይም እቶን፡፡ በቀስታ እየተነሳ የሚወድቅ ጠይም እሳተ ገሞራ፡፡ ደረታቼውን የነፉ ትዕቢተኛ እና ቀዝቃዛ ተራሮች በሞሉባት አገር፣ ሲበዛ ዝቅ ብሎ ወላፈን የሚተፋ የእሳት ኩሬ፡፡ እዚያ ነበርኩ አራት ዓመት፡፡ በእኔ በኩል ከልባችን በላይ ሥጋችን የተዋኻደ ነበር፤ ጠረኗ ያሰክረኛል፡፡ ከንፈሯ ከንፈሬን ደርቆ ውሃን እንደተራበ መሬት ይናፍቀዋል፤ የዓይኖቿ ብሌኖች በመሐፀን እንዳለ ሕፃን በፈሳሽ የተከበቡ ናቸው። መቼ ነው የምታለቅሰው? የሚያስብሉ፤ ቸልተኝነቴ አጥንቷ ድረስ ዘልቆ እንደሚያማት ይገባኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ዕንባ በዓይኖቿ ሲሞላ ታዝቢያለሁ፡፡ ግን አታለቅስም ነበር፣ ዕልኸኛ ናት፡፡ ዕልዃን እወደዋለሁ፡፡ ሲበዛባት አለቀሰች፤ ዕንባዋ እንደ ጠበል ከተጠናወተኝ የጅልነት መንፈስ የሚፈውሰኝ መስሏት። ሐዘኗ ውስጤን ያመኝ ነበር፡፡ ተገናኝተን በተለያዬን ቁጥር፣ ካላፈቀርኳት ለምን ጊዜዋን አባክናለሁ? እል ነበር ለራሴ... ያ ሐሳቤ ግን ከከንፈሬ አልፎ አያውቅም፡፡ ዛሬ ላይ ግን ቅጥ ያጣ ራስ ወዳድነት ነበረ እላለሁ። ለሴት ልጅ ሰውነት በፍቅር መውደቅ፣ ማንነትን ከማፍቀርም በላይ ኃያል እና አደገኛ ነገር ነው፡፡ ብዙዎች ሰውነትን እና ሰውን በማፍቀር መካከል ያለውን ከጸጉር የቀጠነ መስመር መመልከት ተስኗቼው ሲወድቁ አይቻለሁ፡፡ ትዳር ሲፈራርስ፣ ልጆች ሲበተኑ ተመልክቻለሁ፡፡ ይመርመር ቢባል “የፍቅር” ተብለው የተገጠሙ ግጥሞቻችን እና የተዘፈኑ ዘፈኖቻችን የቆንጆዎችን ቆዳ ማለፍ የተሳናቼው የገላ አምልኮዎች ሳይሆኑ አይቀሩም፤እንደ ንቅሳት ቆዳ ላይ የተሳሉ ቆዳ ሲጨማደድ አብረው የሚኮማተሩ። ያቺን ቀጭን መስመር _ ማዬት የሚቻለው፣ እውነተኛ የፍቅር መነፅር ካጠለቅን፣ አልያም ከራስ ወዳድነት ሕመም ከተፈወስን ወይም
ደግሞ ጸጉር ሰንጣቂ ነፍስ ካለን ብቻ ነው፤ ይቻላል ወይ? ይላሉ ብዙዎች፣ ካልቻላችሁ መጭውን ቻሉት ከማለት ሌላ ምን ይባላል?! ቁጣ ያልቀላቀለ እልኅ ያዬሁት ማሂሰላም ላይ ነው፡፡ ዕንባዋ የሚፈሰው ፈገግታ ሆኖ በውብ ጥርሶቿ በኩል ይሆን? ፍቅር ድንኳኑን ተክሎ የሚሰፍረው በለቅሶና በሳቅ መካከል ባለው ድንበር ላይ ሳይሆን አይቀርም፡፡….እልኅ ጥርስን ሳያሳዩ መሳቅ ዕንባንም ሳያሳዩ ማልቀስ መሆኑ የገባኝ ያኔ ነው፡ ፡ ግንኙነታችን አንድ ዓይነት ዑደት ነበረው፡፡ አሰልች የሚመስል ግን ለአራት ዓመት ሳይሰለቼን ያደረግነው። ድንገት ትዝ ትለኛለች፤ እንደ ፍቅረኛ ማሰብ ሳይሆን፣ እንደሆነ አስቀምጠው እንደረሱት ምግብ፤ ሲርብ ትዝ እንደሚል ትዝ ትለኛለች. እደውልላታለሁ፤ በሥራ ምክንያት ከከተማ ካልወጣች በስተቀር በተቻላት ፍጥነት ሁሉ ቤቴ ትመጣለች፡፡ እሷ የናፈቀችዉ እኔን፣ እኔ የናፈቀኝ ሰውነቷን አግኝተናልና ሁሉ ነገራችን እብደት ይሆናል፡፡ በተገናኜን ቁጥር የሚበዛውን ጊዜ የምናሳልፈው አልጋዬ ውስጥ ነበር፡፡ እንደ ፍቅረኛ ቲአትር ቤት ገብተን ወይም ከከተማ ወጣ ብለን አናውቅም፡፡ አንድ ሁለት ጊዜ የሙዚቃ ዝግጅቶች እንድንሄድ ጋብዛኝ፣ ግብዣዋን አልተቀበልኩም፡፡ ከማውቃቼው ሴቶች ሁሉ ቤቴ የወሰድኳቼው ሁለቱን ብቻ ነበር፡፡ የመጀመሪዋ ደግሞ እሷ ነበረች፡፡ ተያይዘን እንወጣና ጸጥ ያለ ቦታ (ብዙ ጊዜ መጀመሪያ የተገናኜንበት ሬስቶራንት) ተቀምጠን የምትወደውን ፒዛ እናዛለን፡፡ ፒዛ ትወዳለች፤ ብዙ ጊዜ ፒዛ ሲያምራት ትደውልልኛለች፣እንቀጣጠርና ቀድሚያት እደርሳለሁ፡፡ እስከምትመጣ ምንም ነገር አላዝም፡፡ ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በፊት ሴት ቀጥሬ እዚያ ቤት ከሄድኩ እና ቀድሜ ከደረስኩ፣ የቀጠርኳት ሴት እስከምትመጠ ምንም ነገር አላዝ'ም። አስተናጋጆቹም ስለሚያውቁ አያስቸግሩኝም፤ ቢበዛ፣ ውሃ በብርጭቆ ፊቴ አቅርበውልኝ ይሄዳሉ፡፡
ፊቴ ተቀምጣ በፈገግታ እያዬችኝ ፒዛዋን በቀስታ ስታጣጥም ቡናዬን እየጠጣሁ፣ በትኩረት እያታለሁ። ጠይምነቷ እንደ አዲስ ያስገርመኛል፡፡ ልክ እንደ ሕፃን ልጅ ደስ ብሏት ስትበላ አያታለሁ። ፒዛ አልወድም። የሆነ ጡረታ የወጣ ጣሊያናዊ ምግብ አብሳይ፣ ሥራ ሲፈታ ቤቱ ውስጥ ያለውን የምግብና ቅመማ ቅመም ዘር የደፋበት መከረኛ ቂጣ ይመስለኛል፡፡ እሷ ቡና አትወድም፡፡ ለምን እንደማትወድ ነግራኛለች፤ ግን ምክንያቷን ረስቼዋለሁ፡፡ አበላሏ የተለዬ ኪነት አለው፡፡አበላሏን የሚያሳምረው የከንፈሯ ውበት ይመስለኛል፡፡ ጋብዘኝ ብላ ጠርታ ካልከፈልኩ ብላ አምባጓሮ ታስነሳለች፣ ደግሞ ከልቧ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ ትከፍላለች፤ አንዳንዴ እንደምንም በክርክሩ አሸንፌ ስከፍል ደስ አይላትም፡፡ ውጭ ስንገናኝ፣ ሳታቋርጥ ታወራኛለች፡፡ ያን ያኽል፣ ዝምተኛ የምባል ሰው አይደለሁም፤ ግን ማሂሰላም ጋር ብዙ አላወራም፤ ማሂሰላም የሚያውቋት ሁሉ እንደሚናገሩት ሲበዛ ዝምተኛ ልጅ ነበረች፤ እኔ ጋር ግን ሳታቋርጥ ታወራለች፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም አውርታኝ- አውርታኝ "ኡፍ ደከመኝ!" ብላ ትስቃለች፡፡ ስለ ሥራዋ ታወራኛለች። (“ኦዲተር' ናት። ፊልድ የሚወጡበት ክፍለ ሐገር ብዛት... የመንግሥት ካሽ በደረሰበት ገጠር ሁሉ፣ ከኋላ እየተከተለች ሙሰኞች ከተኛበት ካዝና እንዳይቀሰቅሱት፣ በሰላም መተኛቱን ማረጋገጥ... የመንግሥት ሳንቲሞች እየተቅጨለጨሉ በየክልሉ ሥርቻ በወደቁ ቁጥር፣ በስንጥር የት እንደ ወደቁ መፈለግ፣ከብዙ ያዬቻቼዉና የሰማቻቼው የሌብነት ታሪኮች ጋር፡፡ ለሥራዋ ታማኝ ነበረች፤ ብትሞት “ኦዲት' ያደረገችውን መሥሪያቤትም ይሁን ግለሰብ ነግራኝ አታውቅም፡፡ ግድ ባይኖረኝም ሳይገርመኝ አልቀረም፡፡ ያን ሁሉ አሰቃቂ የሌብነት ታሪክ፣ ያለ ገጸ – ባሕሪ የመጻፍ ያኽል ነበር ነገሩ)... ስለ ሴት ጓደኞቿ ታወራኛለች (ሰርግ፣ ልደት፣ ቀለበት፣ ለቅሶ፣ ማርገዝ እና መውለድ የማይታክታቼው ሀልቆ መሳፍርት ጓደኞች ነበሯት)፣ ስለ ታናሽ ወንድሟ ሕፃን ልጅ ታወራኛለች (ብዙ ጊዜ የምታወራበት ርዕስ ገና በሁለት ዓመት ከምናምኑ፣ በወጉ አፉን ሳይፈታ “ቻርሊቻፕሊንን" የተካ የሚመስላት ማቲ)፣ ስለ ጓደኞቿ “ቦይ ፍሬንዶች' ታወራኛለች (የሚበዙት በአስገራሚ መንገድ ሴት ጓደኞቿን ለጋብቻ
በመጠየቅ ታሪክ የሠሩ፣ በዚህም ጉሮ ወሸባዬ የሚዘመርላቼው) ዋናው ርዕሷ ስለ አባቷ (ያለ እናት ያሳደጓት፣ የልጅ ልጅ እንድታሳያቼው በምድር ላይ ላሉ አማልዕክት ሁሉ የተሳሉ አባቷ) ለዚያም ነው መሰል ከምሰማው ይልቅ ሳልሰማ የማልፈው ወሬዋ የሚበዛው ... አልሰለቻትም፤ ግን አልሰማትም፡፡ ከዚህ ሁሉ ወሬዋ በኋላ፣ ማሳረጊያው በእነዚያ መላ ሰውነቴን በሚያሞቁ ውብና በምኞት በሚንቀለቀሉ ዓይኖቿ እያዬችኝ “ውይ እንዴት ንፍቅ እንዳልከኝ!'' የሚል ነበር። እዚህ ላይ ጆሮዬ፣ የባለቤቱ መኪና ጡሩምባ እንዳንባረቀበት የግቢ በር፣ በሰፊው ይከፈታል፡፡ ነፍሷ ሲያወራ ይደብተኛል ...ሥጋዋ መናገር ሲጀምር ሥጋዬ ይነቃል፡፡ ለእኔ ሰውነት ነበረች፡፡ ብዙውን ነገር በቁም ነገር አዳምጫት አላውቅም። ምንም ታውራ ምን፣ ጆሮዬ እንደ በር ከውስጥ የሚቆለፈው ነገር ነበር፡፡ በደፈናው አለመስማት አልኩት እንጂ ስሜቱ ለራሴም አይገባኝም፡፡ ወሬዎቿ የተለመዱ ስለሆኑ እንደ

👍51❤6👎1
ሰውነቷ ሰርክ አዲስ አይሆኑብኝም፡፡ ለምሳሌ፣ አንዲት ጓደኛዋ ወንድ ልጅ ወለደች፣ ወንዱ ልጅ አባቱን ይመስላል፡፡ ሌላ ቀን ሌላ ጓደኛዋ ሴት ልጅ ትወልዳለች፣ ልጅቱ እናቷን ትመስላለች። ሌላ ጊዜ አንዷን ጓደኛዋን አንዱ አግቢኝ ብሎ ሽማግሌ ላከ፣ እሺ ተባለ፡፡ ሌላ ቀን፣ ሌላው-ሌላዋን.... ከምንም በላይ የሚገርመኝ እነዚህን ወሬዎች ስታወራ፣ የምትሰጠው ትኩረት ነው፡፡ አንዳንዴ ከማውራቷ በፊት፣ ግራ ቀኝ ተገላምጣና ድምፅዋን ቀንሳ ስለምታወራ፣ የሆነ ከባድ የአገር ጉዳይ ላይ የሚፈጸም ሤራ ታስመስለዋለች... አለ አይደል መፈንቅለ መንግሥት ነገ እንደምንፈጽም ወይም ወደሆነ አገር የሚበር አውሮፕላን እንደምንጠልፍ... ዓይነት ነገር፡፡ ይኼ፣ ቀላል ለሆኑ ወሬዎች ከፍ ያለ ትኩረት መስጠቷ (አስባውም ባይሆን) እኔን፣ በእርሷ ልክ _ ለነገሩ ስሜት ኖሮኝ መሳተፍ እንዳልችል ያደርገኝ ነበር፡፡
ራሴ ወሬ እንዳልጀምር፣ የተወሰኑ ጊዜዎች እንደሞከርኩት በጉጉት ብታዳምጠኝም፣ ስለማወራው ነገር ምንም መረጃ የላትም ነበር፡፡ ጉዳዩ የዕውቀት ማነስና መብለጥ ነገር አልነበረም፣ ውሏችን አራምባና ቆቦ ስለነበር እንጂ፡፡ ስለ ዘፋኞች ታወራኛለች፤ እንደ ዘፈን የምትወደው ነገር መኖሩን እንጃ፡፡ ስለ ድሮ ዘፈኖች (ሳትወለድ በፊት ስለተዘፈኑ) ስለዘፋኞች ምንም የማውቀው ነገር የለም፡፡ ነገሬ ብዬ ዘፈን የሰማሁበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ በአስቴር አወቀና በጥላሁን ገሰሰ መካከል ስላለው ልዩነት ብጠየቅ፣ መልሴ ጾታቼው የሚል ብቻ ሳይሆን አይቀርም። ክፋቱ ሬስቶራንቱ ውስጥ በየጥጋጥጉ የተሰቀሉት “ስፒከሮች' እንደ ሰይጣን ምላስ የማያቋርጥ የዘፈን ርዕስ ያውሷታል፡፡ አንዳንዴ አብራ ስታንጎራጉር፣ ይኼን ሁሉ ግጥም በየትኛው ጊዜዋ አጠናችው? እላለሁ! ወይንስ “ኦዲተሮች' ከአገራችን ዘፈኖች ግጥም ላይ ቃል እንዳይጎድል በየወሩ “ኦዲት' ያደርጋሉ!? ዘፈን የቀን መቁጠሪያዋ ነው። “መቼ ነው የተመረቅሽው ...?'' “የማንትስ የመጨረሻው አልበም ሲወጣ ...'' “ልደትሽ መቼ ነው ...?' “የእኔና ማንትስ የምትባለዋ ዘፋኝ ልደት አንድ ቀን ነው'' ከዚህ አልፋ በዘፈኖቹ ውስጥ የሚሰሙ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ሳይቀር በስም እየጠቀሰች ትነግረኛለች “ይኼን “ቤዝ ጊታር' አዳምጠው'ማ. . .ኦ! እዚህ ዘፈን ላይ ያለው 'ፍሉት'...ቆንጆ ሙዚቃ ነበር፤ ግን ምንትሱ ይረብሻል'' እያለች። እሷ ጋር እስክንገናኝ ድረስ፣ ዘፈን በዚህ ልክ ሱስ ይሆናል ብለው ቢነግሩኝ አላምንም ነበር፡፡ አንድ ቀን ቤት ስትመጣ ፊቷ በደስታ ተጥለቅልቆ፣ ካለወትሮዋ ጉንጨን በስሱ ስማኝ አለፈችኝና ከቦርሳዋ ውስጥ “ሲዲ' አወጣች፡፡ ከፍ አድርጋ አሳይታኝ “ይኼን ሲዲ ለማግኜት እንዴት እንደደከምኩ አትጠይቀኝ'' አለች፡፡እንቅስቃሴዋ ፈጣን ስለነበር “ሲዲው' ላይ ያለውን ስምም ሆነ ምሥል ለማዬት ዕድሉ
አልነበረኝም፡፡ አንድም ቀን ነገሬ ብዬ ተጠቅሜበት የማላውቀው፣ ከተገዛ አምስት ዓመት? ያለፈው ትልቅ “ ሲዲ ማጫወቻ'' አለኝ፡፡ ኮንዶሚኒዬም ቤቴን በተከራዬሁ ሰሞን ኦና ሆኖ የተመለከተ ሊቢያ ኤምባሲ በአስተርጓሚነት ይሠራ የነበረ ጓደኛዬ ነው በግድ ያስገዛኝ። ኤምባሲው በየዓመቱ እቃ ሲቀይር ትልቅ የኤሌክትሪክ ምድጃ ጋር አብሮ አምጥቶ ቤቴ አስቀመጠውና ሳልወድ በግዴ ከፈልኩ፡፡ “አንድ ቀን መሸጥ ብትፈልግ እጅህን ስሞ በእጥፍ የሚገዛህ ሞልቷል!'' ብሎ፣ ማጋነን የማይወድ ጥሩ ልጅ ስለሆነ አመንኩት። በተለይ “ ሲዲ ፕሌየሩ'' ካሰብኩት በላይ ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ በአራት ካርቱኖች ታሽጎ ሲመጠ ማመን አልቻልኩም ነበር፡፡ አንዱን የሳሎኑን ግድግዳ ሙሉ ለሙሉ ተንሰራፍቶ የያዘው ይኼው ሲዲ ማጫወቻ ነበር፡፡ አንዳንድ ቀን አንዱ 'ስፒከር ላይ ተቀምጨ በመስኮት ወደ ውጪ አላፊ አግዳሚ እመለከታለሁ፡፡ ማሂሰላም ቤቴ ውስጥ ስትመጣ፣ ከእኔ ቀጥሎ አብዝታ የምትነካካው ያንን “ሲዲ' ማጫወቻ _ ነበር፡፡ እሷ ካልመጣች ነገሬ ብዬ ከፍቼው አላውቅም። በጣም ብዙ የሚነካኩ ነገሮችና የተለያዩ ቀለማት ያላቼው መብራቶች ስላሉት የአውሮፕላን “ኩክፒት' ይመስላል፡፡ ፊት ለፊቱ ቁጭ ብላ፣ በቁም ነገር አንዱን ስታበራ፣ አንዱን ስታጠፋ የሆነ ዘፈን የምትከፍት ሳይሆን “ፓይለት' ነበር የምትመስለኝ፡፡ እናም የዚያን ቀን ያመጣችውን “ሲዲ' አስገብታ ከፈተችው፡፡ሁለት አረንጓዴ መስመሮ˘ እንደ ጅራታም ኮከብ ከግራ ወደ ቀኝ ተወነጭፉና ...የሙዚቃው ድምፅ ቤቱን ሞላው። ይህንን “ሲዲ ፕሌር' በከፈተች ቁጥር “ ኡፍ ይኼ “ፕሌየርሀኮ' ትናንት እናቱ የሞተችበት ሐዘንተኛ ሳይቀር ለዳንስ ይወሰውሳል" ትለኛለች፡፡ ዘፈኑ እስከሚጀምር እኔም ትንፋሼን ውጨ ጠበቅሁ...
"ይላል ዶጁ... ይላል ዶጁ.... ፏፏ ይላል ዶጁ..."
ተገርሜ አዬኋት፤ በደስታ ፍንክንክ ብላ እንደመደነስ እያደረጋት አብራ መዝፈን ጀምራ ነበር፡፡ ድምፅዋ ውብ ነው! ማሂሰላምን እኔ ሰውነቷ ጋር በፍቅር እንደወደኩ
እንዱ ሙዚቃ ወዳድ ከድምፅዋ ፍቅር ቢይዘው አልፈርድበትም፡፡ ይኼን ዘፈን የታላቄ ታላቅ... ሕፃን ልጅ ሆኜ፣ አሮጌ የመኪና ጎማዎች ላይ በተቀመጠ ሳፋ ልብስ እያጠበች ስትዘፍነው ከሰማሁት በኋላ ገና አሁን እንደገና መስማቴ ነበር፤ ከዬት አመጣችው!?...እንዴት አመጣቸው!? በየቀኑ ሙዚቃ እንደ አሸን በሚፈላበት ዘመን፣ ስልሳ ይሁን ሰባዎቹ ውስጥ የተዘፈነ ዘፈን በምን ትዝ አላት!?እያልኩ ሳስብ... ዞር ብላ፣ መገረሜን ዓይታ መሰለኝ፣ ወገቧን ይዛ እየሳቀች የሆነ ነገር ልትነግረኝ ጀምራ ተወችውና (ሐሳቧን ቀይራ መሆን አለበት) “በቃ አንተ ወደ ፊትም ወደ ኋላም መሄድ አትችልም አብርሽ?" ብላ እየሳቀች መጥታ እቅፌ ላይ ወደቀች፡፡ ከንፈሮቿ ከንፈሬ ላይ አረፉ፡፡ ልብሶቻችን እዚያው በቆምንበት አውሎ ንፋስ እንዳጋጠመው የቤት ክዳን ቆርቆሮ በየአቅጣጫው ተግለበለቡ፤ ጠይምነት ቤቱን ሞላው... እብደት ቤቱን ሞላው፤ ከልስላሴዋ እኩል...ከእብደታችን...ከጠረኗ እኩል ይላል ዶጁ... በመላ ደም ሥሬ ያኔ የገባ እስከዛሬ ባጋጣሚ ዘፈኑን ስሰማው፣ ጠረኗ ከነጠይም ልስላሴዋ፣ ከነሚቆራረጥ ትኩስ ትንፋሽዋ፣ አሁን እየሆነ ያለ ያኽል ትዝታው ቁልጭ ብሎ ይታዬኛል፡፡ ያ ንግግሯም ዛሬም ድረስ አይረሳኝም “በቃ አንተ ወደ ፊትም ወደ ኋላም መሄድ አትችልም አብርሽ?'' ሌላው የጅልነት ገጽታ ይኼ ነው። ጅል ወደፊትም ወደኋላም መሄድ አይችልም። ጅልነት መሄድም መመለስም ለሚፈልጉ ሰዎች መንገድ ዘግቶ መኻል ላይ እንደ ጅብራ የሚቆም መንፈስ…ተገስፆ የማይለቅ ጥንውት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የምታወራውን ወሬ ልሰማት ታግያለሁ፣ የሆነ ወሬ ጀምራ እያዳመጥኳት በመኻል ሐሳቤ ይበታተናል፡፡ የብዙዎቹ ወሬዎቿ መጨረሻ ምን ላይ እንዳረፈ አላስታውስም፡፡ ይኼ ነገር ከጊዜ በኋላ ሳይገባት አልቀረም፤ እሷም ቀስ በቀስ ወደ ዝምታዋ ተመለሰች፤ ብዙው ጊዚያችን በዝምታ ነበር የሚያልፈው፡፡ ይኼን ዝምታ ለማካካስ በሚመስል ሁኔታ፣ እጆቼ ጠረጴዛውን ተሻግረው እጆቿን እንደያዙ ናቸው፤ ወይም ጎን ለጎን ተቀምጠን ትከሻዬ ላይ ተደግፋ እጆቿ አንዴ ጸጉሬን፣ አንዴ ጉንጨን እየነካኩ በዝምታ ረዥም ጊዜ እናሳልፋለን፡፡

👍44❤3🥰3
ሴት አስተናጋጆች የማይወዱት፣ ወንድ አስተናጋጆች ከመሬት ተነስተው የሚሽ ኮረመሙበት፣ ነገራችን ይኼ ነበር፡፡ ፈገግ ይበሉም፣ ኮስተር አስተናጋጆቹ ፊት ላይ “ምን ይዳሩብናል እዚህ! ቤታቼው አልጋ የለም?'' የሚል አስተያየት የተጻፈ ይመስል ነበር፡፡ በወጣትነት ትኩሳት ለሚቃጠል ወጣትና በፍቅር ልብሷን ለጣለች ምስኪን፣ ካሉበት ቦታ አልጋ ድረስ ያለው ርቀት‘ፕላቶ' ከሚባለው ፕላኔት ርቀት ጋር እኩል ነው፡፡ ሰዎች ይኽን አይረዱትም 'ፊዚክስ' ነው፡፡ ለተመልካች የማይገባ መንገደኛው ብቻ የሚያውቀው የ'ፊዚክስ' ቀመር... ከዚህ እስከ አልጋ በብርሃን ዓመት የሚለካ ሩቅ....!
አትሸኟትም ወይ መሄዷ አይደለም ወይ!
አንድ ቀን ይኼ ሁሉ ሰለቻት፡፡ የሰለቻት አብሮነታችን አልነበረም፡፡ አብሮነታችን መጨረሻው ምን ይሆን ብሎ መስጋት እንጂ...ጥበቃ ይሰለቻል፡፡ ከረዢም ሕንፃ ላይ ቁልቁል ራሱን የወረወረ ሰው ዝም ብሎ ለዓመታት መሬት ሳይነካ እየወረደ ቢኖር “ልትረፍ አልያም ልፈጥፈጥ ብቻ ልረፍ'' ማለቱ ይቀራል? እንደዚያ ነበር በትክክል ስሜቷ፤ ውጤቱን ሳይሆን፣ ምንም ይሁን መጨረሻውን መናፈቅ፡፡ አንድ ቅዳሜ፣ እንደ ልማዴ _ አርፍጄ ምሳ ሰዓት አካባቢ ከእንቅልፌ ስነቃ አስታወስኳት፤ ያው አስታወስኳት ማለት ጠይም ገላዋን ሰውነቴ ፈለገ ማለት ነው፡፡ ለሁለት ሳምንት አልደወልኩላትም _ ነበር። ደውላም _ ስልኳን _ አላነሳሁም፡፡ ደወልኩላት፣እስክትመጣ ከአልጋዬ ሳልወጣ ልጠብቃት ነበር ያሰብኩት፡፡ ስልኳን ስታነሳ ከተለመደው ለዬት ባለ ድምፅ... “አብርሽ ዛሬ ውጭ እንገናኝ!'' አለችኝ፡- “ነይና አብረን እንወጣለን፡፡'' “ስማኝ እንጂ አብርሽ!” አነጋገሯ ጠንከር ስላለብኝ፣ ምኞቴ ብን ብሎ ጠፍቶ ብርድልብሱን ከላዬ ላይ ገፍፌ እየተነሳሁ፡፡
“ደህና ነሽ ግን?'' አልኳት::
"ደና ነኝ ... ፒዛ ጋብዘኝ "
“ለዚህ ነው?... በቃ መጠሁ እዚያው ጠብቂኝ''
“እዚያ አይደለም! ሌላ ቦታ...ሁልጊዜ አንድ ቦታ አይሰለችህም እንዴ?''
“እሺ! የፈለግሽበት ምረጭ አልኳት የትም ቢሆን ግድ አልነበረኝም!'' ቦሌ አካባቢ ሰምቼው የማላውቀው ሬስቶራንት ነገረችኝ፡፡ ስንገናኝ እንደልማዷ ቀለል ባለ አለባበስ፣ አንዱ ጥግ ተቀምጣ አገኜኋት። ቤቱ በቂ ብርሃን የሌለው አጉል ባህላዊ ካልሆንኩ በሚል ትግል ካፍ እስከገደፉ በኮተት የተሞላ ቤት ነበር። አንዱ ጥግ ሲያዩት የሚኮሰኮስ የሳር ክፈፍ የደፋ የጎጆ ቤት ቅርፅ ቆሟል፡፡ “ኮንክሪት” ሕንፃ ውስጥ ጎጆ። በጎጆው በር አልፎ መታጠቢያና መጸዳጃ ቤቱ አለ (ለምን የእውነት ገጠር እንዲመስል ከጓሮ ዛፍ ተክለው ደንበኞቻቸው ጫካ ውስጥ አይጸዳዱም!? እላለሁ በውስጤ) ...በሌላኛው ጥግ የቅልና እንስራ መዓት ተደርድሯል፣ ከዚያ አለፍ ብሎ ሞፈር ከእነ ቀምበሩ ተጋድሟል፣ አጠገቡ ያለ ጠረጴዛ ላይ አንዲት “ሚኒስከርት” የለበሰች እግሯ የሚያምር ወፍራም ሴትና መላጣ ሰዉዬ፣ ጭሱ እንደ ባንዲራ የሚውለበለብ የሸክላ ጥብስ አቅርበው ትኩሱን ይበላሉ (እስኪበርድ ምን አጣደፋቼው!?) አጠገባቼው ሞፈርና ቀንበር _አጋድመው ጥብስ ሲበሉ፣ የአንዱን ደሃ አርሶ አደር የእርሻ በሬ ነጥቀው ያረዱበት ሽፍቶች ነበር የሚመስሉት፡፡ ጥሎብኝ ከተሜ ባህላዊ ልሁን ብሎ እንደ ገጠር ሲሠራው ደስ አይለኝም፡፡ እንደ ባህል ምግብ ቤቶች የምጠላው ነገር የለም፡፡ንግድ ፈቃዳቼው ላይ የባህል ምግብ ቤት ሳይሆን፣ ደካማ ቲያትር ቤት ተብሎ የተጻፈ ነው የሚመስለለኝ፡፡ ማሂሰላም ጋር የባጥ የቆጡን እያወራን ትንሽ እንደቆዬን፣ ፒዛ ካላቼው ላዝዝላት፣ አስተናገጁን በምልክት ስጠራው፣ አልፈልግም ብላ ቀድማ ያዘዘችውን ሚሪንዳ ወደ ብርጭቆ ቀዳች። ሚሪንዳው ጠጅ ይመስላል፤ የቤቱ ብርሃን መሰለኝ፡፡ ቡና አዘዝኩ፤
ጥድፍ ያለው አስተናጋጅ በሚጣደፍ ድምፅ “ትኩስ ነገር የለንም!" አለኝ (ቡና የሌለበት የባህል ቤት) አባባሉ ድምፁ ለቡናና ሚሪንዳ ቦታ አትያዙብን የሚል ንቄት ነበረው፡፡ በዚያ ላይ እኛን እያናገረ ዓይኑ የሚያዬው ወደ ሌላ ደንበኞች ነበር፡፡ የቦሌ ስልጣኔ ያስጠላኛል፤ በር ላይ እንደተነጠፈ የእግር መጥረጊያ፣ ገቢ ወጭው በጫማው ሶል ይዞ የሚመጠውን ፍርፋሪ ዘመናዊነት ትቶላት የሚሄድ ቦሌ፤ ርጋፊ ዘመናዊነትን ሰብስባ ሌላው አዲስ አበቤ ላይ ካላራገፍኩ የምትለው ነገር አለ፡፡ የአስተናጋጁን መቆናጠር ችላ ብዬ ወደማሂሰላም ዞርኩ፡፡
"ደህና ነሽ?”
በረዥሙ ተነፈሰች...በዝምታ እንዳቀረቀረች ምንም ሳትጨምር ሳትቀንስ “አብርሽ አግባኝ!"አለችኝ.....

👍57❤4👎2
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
አስር ሠዓት ከሃያ ሲሆን ሻንጣቸውን ጭነው ሆቴሉን ተሠናብተው ወጡ፡፡ ቁልቁለታማውን ኮረኮንች መንገድ ጨርሰው ዋናው አስፓልት መንገድ ሊገቡ ሃምሳ ሜትር ገደማ ሲቀራቸው ወደ ገበሬዎች ሆቴል አጥር መኪናውን ጥግ አሲይዞ አቆመና ተንቀሳቃሽ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ መደወል ጀመረ፡፡
‹‹ሄሎ ፎዚ››
‹‹ደህና ነኝ››
<<እ .. ምን አልሺኝ?››
‹‹አግኝቻታለሁ...ዝርዝር ሁኔታውን ማታ ስመጣ አወራሻለሁ፡፡ አሁን የደወልኩት እንደምንም ብለሽ ለአስር ሠው የሚበቃ እራት ማዘጋጀት ትቺይ እንደሆነ ልጠይቅሽ ነው?››
‹‹ጎሽ... ብር የሚያንስሽ ከሆነ ከሰሎሞን ውሰጂ ፤ደውዬ እነግረዋለሁ››
‹‹ቻው... ሁለት ሠዓት አካባቢ እንደርሳለን፡፡››
በተቀመጠችበት ደንዝዛ በፍራቻና በሀዘኔታ የሚሠራውን ታስተውላለች፡፡ አዝማሚያው አላማራትም፡፡ እንዲህ የጓጓለትን ነገር ሲያጣ ተስፋ በመቁረጥ አንድ ነገር እንዳይሆን ፈራች፡፡ እሱ አንድ ነገር ከሆነ ደግሞ እሷ እራሷን ይቅር ማለት እንደማትችልና የከፋ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ ሲታሠባት ሠውነቷ ተንቀጠቀጠ፡፡ ሁሴን ሁለተኛ ስልኩን እያናገረ ነው …፡፡
‹‹አንተ ቦርጫም አመንክም አላመንክም ሁለት ሠዓት ላይ እቤቴ ይዣት ከች ነው፡፡››
‹‹ግዴለህም በእርግጠኝነት ማንነቷን ለይቼዋለሁ፤ ከአስር ደቂቃ በኋላ በእጄ ነች፡፡››
‹‹ኡፍ ... አሁን ክርክሩን ተውና ቤት ሄደህ ፎዚያን አግዛት፤ ባዶ ቤት ይዣት መምጣት አልፈልግም፤ እሺ ካለች ለኤደንም ንገራት ፤ሁለት ሠዓት ቤት እንድትገኝ፤ ቅር ካላለህ የውብዳርንም ደውዬ ብጠራት፡፡››
<< ... በቃ በቃ ትቼዋለሁ ..ቻው በቃ በሠዓቱ እንገናኝ፡፡››
ስልኩን አናግሮ ሲጨርስ መልሶ ኪሱ ከተተና መኪናውን አስነስቶ ወደ አስፓልቱ ገባና ወደ ግራ ታጥፎ አዲስ አበባ መውጫ ላይ ወደሚገኘው ፒራሚድ ሆቴል አመራ፡፡ምንም ሳይነጋገሩ ነበር ሆቴሉ ደርሠው ከመኪና በመውረድ የግቢውን ውስጥ ጠቅላላ ማየት የሚቻልበት ቦታ መርጠው የተቀመጡት፡፡ ትንግርት ደመነፍሷ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው፤ አዕምሮዋ ራሱ ማሠብ ያቆመ መስሎ ተሰማት፡፡
ሁሴን‹‹አየሻት አይደል?›› አላት በፈገግታ እንደተሞላ ፡፡
‹‹ማን..ን?›› አለችው ከደነዘዘችበት ባና፡፡
‹‹ማንን ነው ለማየት የመጣነው? ሚሥጥርን ነዋ፡፡ ከፊት ለፊትሽ አትታይሽም?››
በመከራ አንገቷን ካቀረቀረችበት አቅንታ አይኖቿን ወደ ጠቆማት አቅጣጫ ወረወረች፡፡ እውነትም ጠይሟ ወጣት በተመሳሳይ ሁኔታ ወይኗን እየተጎነጨች መጽሀፏን ታነባለች፡፡ ትንግርት እሷን በምታይበት ሠዓት እሷም አማትራ እነሱን ተመለከተችና እጇ ላይ ያሠረችውን ሠዓት በማየት ወደ ንባቧ ተመለሠች፡፡
‹‹ሠዓቷን እያየች ነው፤በማርፈድህ ቅር ሳይላት አይቀርም፡፡››
‹‹ዋናው አለመቅረቴ ነው ...>> አስተናጋጁ አቋረጣቸው... ሁለቱም ጭማቂ አዘዙና መጣላቸው፡፡
‹‹አበባውን ይዘሻል አይደል?››በዝምታ ቦርሳዋን ከፈተችና የመጨረሻው ዕድል መግለጫ የሆነችውን አበባ ሠጠችው፡፡ ‹‹ከበስተጀርባህ አሮጊቷ እንዳለች እንዳትዘነጋ፡፡›› አለችው፡፡
ቀስ ብሎ ወደ ጀርባው ሲገላመጥ እውነትም
ዛሬም ያን ቦርጯን ወደ ፊት አንገፍጥጣ አይኗን ጀርባው ላይ ተክላለች፡፡ሁሴን ፈጎ የዋለ ፊቱን በመጠኑ ቋጠረው ‹‹ይህቺ ክምርማ
እኔን አታጭበረብረኝም፡፡››
‹‹አጭበርባሪዋ የትኛዋ እንደሆነች በምን አወክ? ምን አልባት ይህቺ ጠይሞም ሚሥጥር ላትሆን ትችላለች፡፡ ምን አልባት ሁለቱም አጭበርባሪ ይሆናሉ፡፡››
‹‹እንግዲያው ሁለቱም አጭበርባሪዎች ከሆኑ ትክክለኛዋ ሚሥጥር አንቺ ነሽ ማለት ነው?››
ልትጠጣ ያለችው የጁስ ብርጭቆ ከእጇ ተንሸራቶ አመለጣት… እሱ በፍጥነት ባይቀልበው ኖሮ መሬት ወድቆ ተከስክሶ ነበር
‹‹ምን ነካሽ እያንቀላፋሽ ነው እንዴ? አየሽ ዛሬ ማዳመጥ የምፈልገው ስሜቴን ነው፤ስሜቴ ደግሞ ይህቺ ጠይም ወጣት ትክክለኛዋ የእኔዋ ሚሥጥር መሆኗን ነግሮኛል፡፡››
‹‹ታዲያ እርግጠኛ ከሆንክ ምን ትጠብቃለህ ተነስና አበባውን ስጣት፤ ሀብሉን አንገትህ ላይ ታጥልቅልህ፤ አንተም ቀለበቱን በጣቷ ላይ ሠካላት… እንደውም ጣቶቿ በጣም ያምራሉ››
‹‹ምን አስቸኮለሽ፤ ገና አንድ ሠዓት አለኝ፡፡ ልክ አስር ደቂቃ ሲቀረው ነው አበባውን የምሠጣት እስከዛ እኔ በጉጉት እንዳተሠቃየሁ እሷም ትንሽ ትሠቃይ፡፡››
‹‹እስከዛ ደንዝዘን ቁጭ እንበል?›› አለችው ትንግርት ተስፋው በተሟጠጠ ድምፅ፡፡
‹‹እኔ ለሠላሳ ደቂቃ ያህል የነገሮችን አጀማመርና አሁን ያሉበትን ሁኔታ ወደ ኃላ ተመልሼ ማሠብ እፈልጋለሁ፡፡ አስር ደቂቃ ሲቀረው አስታውሺኝ›› በማለት አይኖቹን ሠማይ ላይ ተክሎ እግሮቹን አንፈራጦ ሀሳብ ውስጥ ገባ፤ ከሚሥጥር እንዴት ፍቅር እንደያዘው፤ ከእሷ ጋር የተለዋወጣቸው የስልክ ምልልሶች፤ እሷን ለማግኘት
የተጋፈጣቸው ውጣ ውረዶች፤አንድ በአንድ
በቅደም ተከተል ማሠላሠል ጀመረ፡፡
በመሀከል ዓይኖቹን ወደ ጠይሟ አንባቢ ወጣት ይወረውራቸዋል መልሶ ወደ ሀሳብ ይገባል፡፡ሙሉ በሙሉ ከሀሳብ ተጎትቶ የወጣው ትንግርት ትከሻውን ስትነቀንቀው ነበር፡፡ ‹‹ሠዓቱ ደርሷል›› አለችው
በሚርገበገብ ድምፅ፡፡ሠዓቱን ተመለከተ፡፡
በእጁ የያዘውን ቀይ የፈነዳ አበባም አስተዋለ፤
እላዩ ላይ የተለጠፈውን እንቆቅልሽ የሚል ፅሁፍም ለመቶኛ ጊዜ ደግሞ ተመለከተ …፡፡
‹‹አጨበጨበና አስተናጋጁን ጠራ.... ያቺ የምታነበው ልጅ ትታይሀለች የእሷን እና ከጀርባዋ የተቀመጠችውን ወፍራም ሴትዬ ሂሳብ ስንት ነው፡፡ የእኛንም ጨምረህ ቢል አሠራ፡፡›› አስተናጋጁ ወደ ዋናው ሆቴል
እየተጣዳፈ ሄዶ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ቢል ይዞለት መጣ፡፡
መቶ ሠማንያ ስምንት ብር ከሃማሳ ሳንቲም ....ሁለት መቶ ብር አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ ወረወረና ወደ ትንግርት ዞሮ‹‹ቦርሳሽን ያዥና ተነሽ›› አላት፡፡
በድንጋጤ አንጋጣ አየችው፡፡
‹‹ተነሽ እኮ ነው የምልሽ፡፡›› ግራ እጇን ይዞ እየተጣደፈ ግቢው ውስጥ ወደ ቆመችው መኪናው ይዟት ገባ፡፡ መኪናውን ከግቢው አውጥቶ ፊቷን ወደ አዲስ አበባ በማዞር ወደ ዋናው አስፓልት ገብቶ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ በኋላ ማሳያ ስፖኪዬው ሲመለከት ጠይሟ ወጣት እና አሮጊቷ ጎን ለጎን ቆመው አይናቸውን እሱ መኪና ላይ ተክለው በመገረም ሲመለከቱት አያቸው፡፡
ትንግርትም በድንጋጤና በሠመመን ውስጥ ሆና ያለ ምንም እንቅስቃሴና ንግግር
ደንዝዛለች፡፡ ዓኖቿ ፊት ለፊት ያለው አስፓልት ላይ ተተክለዋል፡፡ ጥያቄም ሆነ አስተያየት መሠንዘር አልቻለችም፡፡ መኪናዋን
በመጨረሻው ፍጥነት እያስፈተለከ ነው፡፡
ያበደም መሰላት፤ ‹‹ሁለታችንንም ወደ ግብዓተ መሬታችን ይዞን እየተጓዘ ነው እንዴ?››ስትል አሰበች…በጣም ፈራች፡፡...

👍107❤103🔥3👏3🤔2😁1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹዋቤ
ሁሴን ትንግርትን እንደያዘ ቤቱ ሲገባ የገጠመው ከገመተው በላይ የሆነ ዝግጅት ነው፡፡ ለወር ያህል የታሠበበት ይመስል ሁሉ
ነገር ደምቋል፡፡ ሳሎኑ በዲኮሬሽን አሸብርቋል፡፡
ቤቱ ውስጥ ያሉ ሠዎች የጎደሉ ነገሮችን ለሟሟላት ከወዲህ ወዲያ ውር ውር ይላሉ፡፡
የሳሎኑን በር ዘልቀው ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ግን የቤቱ ድባብ ሙሉ በሙሉ ነበር የተቀየረው፡፡ ሁሉም በያለበት ደንዝዘው ቆሙ፡፡ ፎዚያ፣ ኤደን፣ ሠሎሞን፣ የሠለሞን ሁለት መንታ ልጆች፣ አንድ የጎረቤት አሮጊት፣ እቤቱ ውስጥ የጠበቁት ሠዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ፈዞ እንደቆመ ሁሴን የትንግርትን እጆቿን ይዞ
እየጎተተ ወደ ሶፋው ወስዶ አስቀመጣትና ወደ መኝታ ክፍሉ አመራ፡፡
‹‹አልተሳካም ማለት ነው?›› ሠሎሞን ነበር ከደብረ ዘይት ጀምሮ አንደበቷን ተቆልፎ የደነዘዘችውን ትንግርትን የጠየቃት፡፡ሌሎችም መልሱን ለመስማት ወደ እሷ ተጠግተው ቆመዋል፡፡
‹‹ምን ነካችሁ? ምን ተፈጠረ?›› መልስ ስታጣ ዳግመኛ የጠየቀችው ፎዚያ ነች፡፡ከድንዛዜዋ ሳትወጣ ‹‹ባካችሁ ተውኝ እሱኑ ጠይቁት፤ እኔ ምንም አላውቅም፡፡››ብላ መለሰችላቸው፡፡
‹‹አብረሽው አልነበርሽ እንዴ?›› ኤደን ነች ጣልቃ የገባችው፡፡ ትንግርት ቀና ብላ አየቻት፡፡ እስከአሁን መኖሯን አላወቀችም ነበር፡፡
‹‹ነበርኩ.. ግን ለምን እራሱን አትጠይቁትም›› ተበሳጨች፡፡
‹‹ተዋት በቃ.... ለማንኛውም ተረጋጉ መጣሁ፡፡›› በማለት ወደ መኝታ ክፍል ፈራ ተባ እያለ አመራ፤ሰሎሞን፡፡ ዘልቆ ሲገባ ያልጠበቀው ነገር ነው ያየው፡፡ሁሴን በፈገግታ ተጥለቅልቆ.. ለብሶ የመጣውን ልብስ አውልቆ
ቡኒ ከለር ያለውን የጣሊያን ሱፉን እየለበሠ ነበር::
‹‹ምን እየተከናወነ ነው?›› ሠሎሞን በገረሜታ ጠየቀው፡፡
‹‹ሙሽራ አይደለሁ… እየተዘጋጀሁ ነዋ!!››
‹‹አግኝተሀታል ማለት ነው?››
<አግኝቻታለሁ ግን ይዣት አልመጣሁም .. አላናገርኳትም፤ እዛው ጥያት ነው የመጣሁት፡፡
‹‹አንተ ሠውዬ ጭራሽ ለይቶልሀል ማለት ነው?›› ይሄን ሁሉ ጊዜ ቁም ስቅላችንን ስታሳየን ከርመህ አንተም ይሄን ያህል ተሠቃይተህ ካገኘሀት በኋላ ጥያት መጣሁ ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››
‹‹ባክህ አትነጫነጭ .. ድግሳችሁ አይከስርም አንድ እቅድ አለኝ ሂድና ንገራቸው.. ሁሉም ለእራት ዝግጁ ይሁኑ፤ አስር ደቂቃ አይፈጅብኝም መጣሁ፡፡››
‹‹ለነገሩ እውነትህን ነው... የለፋንበትን እራትማ መሬት ላይ ደፍተን አንሄድም፡፡ ሁለተኛ ግን ካንተ ጋር አብሮ የሚያብድ ሠው የምታገኝ አይምሰልህ፡፡ደግሞ ልጆቼን አንከርፍፌ መምጣቴ፡፡›› በማለት እየተበሳጨ ወደ ሳሎን ተመለሠ፡፡
ሁሉም መቀመጫቸውን ይዘው የእራት ድግሱን ለመቋደስ ሲዘጋጁ ሠዓቱ ሁለት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ እንዳንዱ ቤት ውስጥ ካሉት መጠጦች የሚስማማውን እየመረጠ ይዟል፡፡ የሁሴን ፊት በፈገግታ መጥለቅለቅ የቤቱን የቀድሞ ድባብ በተወሠነ ደረጃም ቢሆን አሻሽሎታል፡፡ ትንግርት ግን አሁንም እንደደነዘዘች ነው፡፡
ከጎኑ ብትቀመጥም ሩቅ ኪሎ ሜትሮች በሀሳብ ርቃ ሄዳለች፡፡ ፎዚያ ወደ እራት ዝግጅቱ ለማምራት ፈራ ተባ በምትልበት ቅጽበት ሁሴን እጁን በማጨብጨብ መናገር የሚፈልገው ነገር እንዳለ ሲናገር ሁሉም
በታላቅ ፀጥታ ውስጥ ገባ፡፡ ፎዚያም ክፍት ወንበር ፈልጋ ተቀመጠች፡፡ ሁሉም በአዕምሮአቸው የሚያጉላሉትን ጥያቄዎች መልስ ከንግግሩ ለማግኘት ጓጉቷል፡፡
‹‹ወደ እራት ፕሮግራሙ እንደዚህ በተጨናነቀና በታፈነ ድባብ እንድንገባ አልፈለኩም፡፡ በመጀመሪያ ኤደን ምን አልባት ጥሪዬን አትቀበይም ብዬ አስቤ ነበር ስለተገኘሽ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ መንታዎቹ ዕፀ - ህይወት እና ዕፀ - ፍቅርም ስለተገኛችሁ በጣም አስደስታችሁኛል፡፡ እናታችሁ ብትመጣም ደስ ይለኝ ነበር ግን ምንም አይደል…›› ንግግሩን ገታ አደረገና እጁን ወደ ኪሱ ከቶ አበባ እና ቀለበት ይዞ መጥቶ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው፡፡
‹‹እንግዲህ የሦስት ቀን ተልዕኮዬን አጠናቅቄ መጥቻለሁ፤ እናንተም ይሄንን በማስመልከት በሞቀ ዝግጅት ተቀብላችሁኛል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ የጠበቃችሁት ነገር ማለት የፈለጋችሁት ሠው ለማየት አልቻላችሁም፡፡ የዚህንም
ምክንያት እንዳብራራላችሁ የምትፈልጉ ይመስለኛል፡፡መቶ ፐርሰንት እርግጠኛ ባልሆንም ለሁለት ዓመታት በማይጨበጥ ፍቅር ያሠቃየችኝን ደራሲ ዛሬ ያገኘኋት መስሎኛል ፤ነገር ግን ላናግራት ወይንም በተስማማነው መሠረት ይሄንን እንቡጥ አበባ ላበረክትላት፤ ይሄንን ቀለበትም ላጠልቅላት አልቻልኩም፡፡ እንዲህ ስላችሁ የማትሆን ሴት ሆና ስላገኘኋት እንዳይመስላችሁ ፤እንዳውም ከጠበኳት በላይ ቆንጆ፤ ከአሠብኳት በላይ ውብ ነች፡፡ ጠይም የሆነ ኢትዮጵያዊ የቆዳ ቀለም፤ሞዴሊስት ለመሆን የሚያስችላት የሠውነት ቅርጽ፤ገና ያልተነካ እንቡጥ ወጣትነት፤በቃ አሟልቶ የፈጠራት የምትባል ዓይነት ነበረች፡፡››
‹‹እና መጨረሻው ምን ሆነ?›› ትዕግስት አጥታ ጣልቃ የገባችው ኤደን ነበረች፡፡ ከስምንት ወር በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ከእሱ ጋር ስትቀመጥ ዛሬ የመጀመሪያዋ ነው፡፡አሁንም ታፈቅረዋለች፤ግን በበፊቱ መልክ አይደለም፡፡ ከእሱ ጋር የነበራትን አብሮነት ሙሉ በሙሉ በጥሳዋለች፡፡ሌላ ሕይወት ሌላ የፍቅር መንገድ ውስጥ ገብታለች፡፡ እንዲያም ሆና ታፈቅረዋለች፡፡ስለምታፈቅረውም… ያፈቀራትን፤ለረጅም ጊዜ የተጎዳባትን፤ከእሷ ጋርም የተለያየባትን ልጅ አግኝቶ ጥሩ የፍቅር ስኬት ቢያጋጥመው በዚህን ወቅት ደስተኛ ትሆን ነበር፡፡ አሁን ግን ምኞቷ ሁሉ በመክሸፉ ግራ መጋባት ውስጥ ገብታለች፡፡
ሁሴን ንግግሩን ቀጠለ <<....መጨረሻም ሀሳቤን ቀየርኩ፡፡ ሳስበውና ውስጤን በጥልቀት ሳዳምጠው፤ ከእሷ በላይ ማጣት ማልፈልጋት፤ ከእሷ በላይ የማፈቅራት ልጅ ልቤ ውስጥ አገኘሁ፡፡››
‹‹ማነች?›› ከሦስት ሠው አፍ ነበር የወጣው፡፡
ሠሎሞን፣ ፎዚያ እና ኤደን፤ እንደተማከረ ሠው
በአንዴ አፋቸውን ከፈቱ፡፡ ትንግርት በመጠኑ
እንደመነቃቃት ብላ አይኖቿን አፍጣ
ታስተውለው ጀመር፡፡
ምን እየተካሄደ እንደሆነ ብዙም ያልገባቸው ከጎረቤት የተገኙት አሮጊትና መንታዎቹ የሠሎሞን ልጆች በዝምታ ይቁለጨለጫሉ፡፡
‹‹ማንነቷን ልነግራችሁ አይደል…፡፡›› አበባውን አነሳ ፊቱን ከጎኑ ወደ ተቀመጠችው ትንግርት አዞረ ...‹‹እነሆ ይሄ የሦስተኛና የመጨረሻ ዕድሌን የምሞክርበት የፍቅር መግለጫ አበባ ነው፡፡ ትንግርት አንቺን ከምስጢር በላይ እንደማፈቅርሽ ዛሬ በደንብ ነው የገባኝ፡፡ ዛሬውኑ ላገባሽ እፈልጋለሁ፤ እባክሽ አታሳፍሪኝ፡፡››
የቤቱ ሠው ሁሉ የሚካሄደውን ትዕይንት ማመን አልቻለም፡፡ አንደ ትንግርት ግን ሁሉም ነገር ቅዠት የሆነበት የለም፡፡ ሁሴን አበባውን እንድትቀበለው እጆቹን ለልመና እንደዘረጋ ነው፡፡ እሷ ግን መንቀሳቀስ አልቻለችም፤ ወንበሩን ወደ ኋላ አንፏቆ ክፍት ቦታ ካገኘ በኋላ በጉልበቱ ተንበረከከና አንገቱን በትህትና ወደ መሬት ደፍቶ ‹‹እባክሽ ተቀበይኝ፡፡›› አላት፡፡
‹‹ተቀበይው›› ሠሎሞን ነበር፡፡
<ተቀበይው ተቀበይው ሁሉም...» በመቀባበል ጮኹባት፡፡በደመነፍስ እጇን ዘርግታ ተቀበለችው፡፡ እቤቱ በጭብጨባ ደመቀ፡፡ በማስከተልም ጠረጴዛ ላይ ያለውን ቀለበት አንስቶ ጣቷ ላይ አጠለቀላት፡፡ዳግመኛ ደማቅ ጭብጨባ በቤቱ ተስተጋባ፡፡ የትንግር፦ ጉንጮች በእንባ ራሱ…፡፡ ቀስ ብላ አጠገቧ ያለውን ቦርሳዋን አነሳችና የጎን ኪሱን ከፈተችው፡፡ እጇን ሠደደችና የልብ ቅርፅ ኖሮት መሀከሉ የእሱ ስም የመጀመሪያ ፊደል ያለበት ሀብል መዛ አወጣችና አንገቱ ላይ አጠለቀችለት፡፡ አሁን ደግሞ ግራ

👍106❤14👎2👏1
የመጋባትና የመደንዘዙ ተራ የሁሴን ሆነ፡፡ በዝግታ ከተቀመጠበት ተነሳ ...
‹‹ሚስጢር ማለት አንቺ ነሽ?››
‹‹አዎ፡፡ ሚስጢር ትንግርትም እኔው ነኝ፡፡››
‹‹ታዲያ ያቺ ጠይም ማን ነች? አሮጊቷስ?››
‹‹በተደጋጋሚ ቀን ያየሀቸው አምስቱም ሴት እኔ ያሠማራኋቸው ጓደኞቼ ናቸው››ጎትቶ ከተቀመጠችበት አስነሳትና ጭምቅ አድርጎ አቀፋት፤ ከንፈሯን... ጉንጯን....ግንባሯን…. እያፈራረቀ ሳማት፤ እሷም አፀፋውን መለሠችለት፡፡
ወደ ጆሮው ተጠግታ በሹክሹክታ‹‹ትናንት ጀምሬ ያልጨረስኩልህ ሦስተኛው የፍቅር ታሪኬ ይሄ ነው፡፡›› አለችው ፡፡
‹‹ሦስተኛው ብቻ ሳይሆን የመጨረሻም ይሆናል፡፡››ብሎ መለሠላት፡፡
እረጅም የእፎይታና የእርካታ ትንፋሽ እየተነፈሰች << አሜን ያድርግልኝ ፡፡›› አለች፡፡....
✨ይቀጥላል✨
አሁንም ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
‹‹ሚስጢር ማለት አንቺ ነሽ?››
‹‹አዎ፡፡ ሚስጢር ትንግርትም እኔው ነኝ፡፡››
‹‹ታዲያ ያቺ ጠይም ማን ነች? አሮጊቷስ?››
‹‹በተደጋጋሚ ቀን ያየሀቸው አምስቱም ሴት እኔ ያሠማራኋቸው ጓደኞቼ ናቸው››ጎትቶ ከተቀመጠችበት አስነሳትና ጭምቅ አድርጎ አቀፋት፤ ከንፈሯን... ጉንጯን....ግንባሯን…. እያፈራረቀ ሳማት፤ እሷም አፀፋውን መለሠችለት፡፡
ወደ ጆሮው ተጠግታ በሹክሹክታ‹‹ትናንት ጀምሬ ያልጨረስኩልህ ሦስተኛው የፍቅር ታሪኬ ይሄ ነው፡፡›› አለችው ፡፡
‹‹ሦስተኛው ብቻ ሳይሆን የመጨረሻም ይሆናል፡፡››ብሎ መለሠላት፡፡
እረጅም የእፎይታና የእርካታ ትንፋሽ እየተነፈሰች << አሜን ያድርግልኝ ፡፡›› አለች፡፡....
✨ይቀጥላል✨
አሁንም ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏83❤35👍29🤩9🥰1😁1🎉1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
✍ አሌክስ አብርሃም
ክፍል አራት
በረዥሙ ተነፈሰች...በዝምታ እንዳቀረቀረች ምንም ሳትጨምር ሳትቀንስ “አብርሽ አግባኝ!"አለችኝ፡፡ አባባሏ አላስደነገጠኝም፣ አላስገረመኝም...ትከሻዬን ወደ ላይ ሰብቄ “እሺ!” አልኳት። ትንሽ እንኳን አላሰብኩም፡፡ _ በትክክል የሰመኋት አልመሰላትም፡፡ ዓይኔን በዓይኗ ፈልጋ፣ ቀና ብላ ትክ ብላ አዬችኝና ከንፈሯን ሳትከፍት ትከሻዋን ብቻ ወደ ላይ በፍጥነት ሰብቃ (ማይክሮ ሰከንድ የፈጄ እስክስታ) ስቅታ የምትመስል አጭር ሳቅ ሳቀች። ከዚያም ምንም ሳትናገር አቀርቅራ የሚሪንዳ ጠርሙሱ ጋር መጫዎት ጀመረች፡፡ የእሺታዬ ፍጥነት ጥያቄው ከእኔ የመጣ እስኪመስል አስገራሚ ነበር “ልናገረው ስል ከአፌ ላይ ቀደምሽኝ'' ዓይነት! በረዥሙ ተንፍሳ እጇን እጄ ላይ ጫነች፡፡ አልያዘችኝም ጣል ብቻ፤ የተነባበሩ እጆቻችንን ፍዝዝ ብላ እያዬች በለስላሳ ድምፅ፣ “እቤት እንሂድ!” አለችኝ፡፡ ቀድሚያት ስነሳ ወደ ጠረጴዛው ሥር አጎንብሳ የሆነ ነገር መፈለግ ጀመረች፡፡ “ምን ወደቀብሽ?'' “ጫማዬ ጠፋኝ'' አለች በሚነጫነጭ ድምፅ፣ ማሂሰላም ሁልጊዜ ካፌም ይሁን ሌላ ቦታ ስትቀመጥ የአንድ እግሯን ጫማ የምታወልቀው ነገር ነበራት... እንዲሁ
ልምድ፤ ጫማዋን ከተቀመጠችበት ወንበር ኋላ አገኜሁላት፡፡ ብዙ አልቆዬንም ከዚያ የተንኳተተ ቤት ወጥተን በ “ኮንትራት” ታክሲ ወደ እኔ ቤት ሄድን፡፡ የዚያን ቀን ለስላሳ እጆቿ እንደ ሐረግ ተጠመጠሙብኝ፣ ጡቶቿ ደረቴን በስተው ከልቤ ደም አጠቀሱ፤ እናም የነፍሴ ሌጣ ወረቀት ላይ በአንዱ እንዲህ ብለው ጻፉ “አውቃለሁ አታገባኝም ግን ሌላ ወንድ ሰውነቴን እንዳይነካው የመሰናበቻ እስክሞት ሳመኝ፣ እስክሞት እቀፈኝ” ተቀላቀልን... ተደባለቅን ...ፈሰስን፡፡ ጅረት ጎርፍ ሆንን፡፡ የውሃ ጎርፍ ሳይሆን የቀለጠ አለት ገሞራ ... ፈረሰኛ... የሚንተከተክ የእቶን ፈረሰኛ፤ ለምን እንጋባ አልሽኝ? አላልኳትም፤ _ እስከአሁንም የሚገርመኝ ለምን የዚያን ቀን፣ ከዚያ ጊዜ በፊትም፣ ከዚያ በኋላም፣ ከአፏ ወጥቶ የማያውቀውን “የአግባኝ” ጥያቄ እንደጠዬቀችኝ ነበር፡፡ ትዕቢት በቀላቀለ ጅልነት ተጠምቄ ነበርና ይኽን ያሰብኩት ከዓመታት በኋላ ነበር፡፡ ጅል ጥያቄውን የሚያቀርበው መላሹ ከሄደ በኋላ ነው፡፡ አግባኝ ካለችኝ በኋላ ሳንጋባ አንድ ዓመት ቆዬን፤ ጸባይዋ አልተቀየረም፡፡ ዳግመኛም ስለ ጋብቻ አላነሳችም። እኔ _ እንዳነሳው ጠብቃ ይሆናል፤ ወይም ሳልነግራት እየተዘጋጄሁ መስሏትም ይሆናል...ብቻ ደግማ አላነሳችውም፡፡ ካወራነው ይልቅ የተሳሳምነው፣ የተቃቀፍነው፣ በስሜት ያበድነው ይበዛ ነበር... ምንም የተለወጠ ነገር አልነበረም፡፡ አንድ ቅዳሜ፣ ደውዬላት ቤቴ መጥታ ሰፊ አልጋዬ ላይ እንደተቃቀፍን ...በስሜት እየቃተተች “በደንብ አባልገኝ" አለችኝ! ቃሉ ቀፈፈኝ... አባልገኝ!...ፈጽሞ ከእሷ አንደበት የወጣ ቃል አይመስልም፤ የእሷ ቃላት ጠያይሞች ናቸው፡፡ ይኼኛው የተቃጠለ የመኪና ዘይት የመሰለ ጥቁር የከተማ ቃል ነበር፡፡ “እንደዚያ አትበይ ማሂ” አልኳት፡፡
"ለምን?"
“ይደብራል!” "ይደብርሀ! አባልገኝ!!” ዝም አልኳት። ከብዙ ግርምት ጋር፡፡ በአራት ዓመት ቆይታችን አልጋ ላይ ከሥሬ ተኝታ ከሚቆራረጥ ትንፋሽዋ ውጭ እንድ ቃል ስትተነፍስ ሰምቻት አላውቅም ነበር፤ የዚያን ቀን ግን ምርር ባለ ድምፅ ብዙ ብዙ ነገር አለች ...አልሰማም ብል እንኳ አስገድዶ በጆሮዬ የሚፈስ ነገር ... “እንደማታገባኝ እያወቅሁ አብሬህ መተኛቴ ብልግና ነው ... ርካሽነትም ነው፤ ራሴን መናቅ ነው። የምመጠው እንድታባልገኝ ስፈልግ ነው ለመባለግ፣ ለመርከስ ፈቅጄ ነው ...ይኼ ፍቅር አይደለም፤ አባልገኝ! ... ሳሎንህ ውስጥ አባልገኝ፣ ስፋሀ ላይ አባልገኝ፣ ምንጣፍህ ላይ አባልገኝ፣ ኩሽናህ ውስጥ አባልገኝ..." "ማሂ" ብዬ ጩኽኩባትና ከላይዋ ላይ ልወርድ ስል፣ አጥብቃ አቀፈችኝ። የአስተቃቀፏ ጥንካሬ ያቺ የማውቃት ለስላሳ ከሥሬ እንደማር የምትቀልጥ ልጅ ናት ወይ? ያስብል ነበር። “...አታቋርጥ አባልገኝ... ልትሸኜኝ በገባንበት የሰፈሬ ጨለማ ውስጥ ሰው አዬን አላየን ብለህ አባልገኝ... የት ቀረ...? ታክሲ ውስጥ ወይም ቢሮዬ መጥተህ... የትም እምቢ አልልኽም፣ አእምሮዬ ቢነጫነጭም ሰውነቴ ባሪያህ ነው... ሰውነቴን እጠላዋለሁ፡፡ እስከምሞት እያዋረድክ አባልገኝ... የምትፈልገው ይኼንን ነው አይደል? ያውልኽ ሰውነቴ! አባልገኝ" ይኽን ያለችኝ ቀን አለቀሰች፡፡ እያለቀሰች ጥፍሯ ጀርባዬን ይቧጥጠኝ ነበር፡፡ ብዙ መስመሮች ጀርባዬ ላይ ደም አርግዘው ተሰመሩ፤ ሁሉም ቀስ በቀስ ጠፍተው የአንዱ ምልክት ብቻ እስከ አሁን በፈዛዛው ጀርባዬ ላይ አለ፡፡ ምን ሆነሽ ነው? አላልኳትም።እንዲያውም ቁጣው በእኔ ብሶ ተበሳጭቼ ነበር፡፡ ወደ ቤቷ ስሸኛት ምንም እላወራንም። ሁልጊዜ ስሸኛት፣ የምንለያይበት ቦታ ላይ፣ ቆይ ትንሽ አውራኝና ትሄዳለህ የምትልብኝ ቦታ ላይ፣ እንደገና የምንገናኘው መቼ ነው ! የምትልብኝ ቦታ ላይ፣ ሰው አዬን አላዬን ብላ በፍጥነት ጉንጨን ስማኝ
የምትለይብኝ ቦታ ላይ ደርሰን ለመቆም ፍጥነቴን ስቀንስ፣ ልክ ብቻውን እንደመጣ ሰው በመጣችበት ፍጥነት ቻው እንኳን ሳትለኝ የቆምኩበት ትታኝ እንዳቀረቀረች ወደ ቤቷ ገባች፡፡ ከቆምኩበት ራቅ ብሎ ከሚገኜው ጋራዥ የሚወጣ አሰቃቂ ድምፅና የመበዬጃ ጨረር፣ ጨለማውን እንደመብረቅ እየሰነጠቀ ቤታቸው ግድግዳ ላይ ሲያርፍ፣ ማሂሰላምን ሁለተኛ እንዳላገኛት ፈጣሪ ቤቷን በአስፈሪ እሳት ማጠር የጀመረ አስመስሎት ነበር። ከጅልነት ብዙ ገጽታዎች ሌላኛው “አባልገኝ'' ማለትን እንደፈቃድ ወስዶ ማባለግ ነው፡፡ መተቃቀፍ፣ ፍቅር መሥራት “ ሴክስ ማድረግ'' ፣ መርፌና ክር መሆን፣ አንሶላ መጋፈፍ...የሚሉ ገራገር ዓይንአፋር ዘወርዋራ ቃላት በአድራጊው በራሱ “ መበለግ'' ወደሚል ቀፋፊ ቃል ሲቀዬሩ ጅል አይደነግጥም።ጥቁር ቃላት የሕይወት ደመናዎች መሆናቼውን አይረዳም፡፡ ጅል የሚነቃው ሲዘንብ ነው። ያኔ ይበሰብሳል እንጂ መጠለያ _ አያገኝም። የሚወዱን ሰዎች በፍቅር እንደ ዣንጥላ ከበላያችን የሚዘረጉበት ዘመን አለ፤ ከብቼኝነት ዶፍ ከመልከስከስ ንዳድም ጠባቂዎቻችን የሚሆኑበት። ሁልጊዜ ግን እንደዚያ አይቀጥልም፣ አንድ ቀን ግፋችን ከብዷቼው ቸልተኝነታችን አድክሟቼው እንደ ዣንጥላ ይታጠፋሉ፡፡ ወይም አያያዛችንን ዓይቶ ጠንካራ ነፋስ ከእጃችን ይነጥቃቼዋል፡፡ ዶፍ ውስጥ ካለመጠለያ የመቆሚያ ዘመን አለ፡፡ ጅል ግን ይኼን ቀድሞ አይረዳም፡፡ ጅል ከጅልነቱ ይፈወስ ዘንድ፤ በመከራ መጠመቅ አለበት። በመከራ ያልተፈወሰ ጅል፤ ሞት ብቻ ነው የሚገላግለው፡፡ እብደታችን መባለግ ሳይሆን በፊት፣በዚያ ድንጋይን እንደ ቅቤ በሚያቀልጥ የግንቦት ነበልባል ፀሐይ ስደውልላት፣ ጠይም ፊቷ ላይ ላቧ ችፍፍ ብሎ ቤቴ እየመጣች፣ የወጣትነት ሙቀትና ትኩሳታችን ተደምሮ አልጋዬ ገነትን የሚያስንቅ ሲኦል ይሆን ነበር፡፡ ጠረኗ ለቀናት ከአልጋዬ አይጠፋም! ተያይዘን ጠባቧ መታጠቢያ ቤቴ ውስጥ ቀዝቃዛ ውሃ ሲወርድብን፣ ገና አሁን እንደተዋወቁ ፍቅረኞች ምኞታችን “ሀ” ብሎ ይጀምራል፡፡ ቀዝቃዛ ውሃ አትወድም፤ እኔ ጋር ስትሆን ግን ሳታንገራግር ትገባለች... ከረዥም ውይይይይይይይይ! ጋር፡፡ እንደ ማር ረጋ ብሎ የሚፈስ የሚመስል ለስላሳ ጠይም

👍49❤9👎2
ሰውነቷ ላይ የሰፈሩትን የውሃ ጤዛዎች በተለይም ከክብ ውብ ጡቶቿ ላይ በከንፈሬ መጥጫቼዋለሁ... እንዴት ነበር በዚህ ሁሉ ውስጥ ፍቅር ያልነበረው? ሥጋዬ እና ሥጋዋ ብቻውን እንደዚያ ይሆናል? ሰው የሰውነቱን ባለቤት አግልሎ ለሰውነት ብቻ ከአምልኮ በማይተናነስ ፍቅር ይወድቃል? ሰው የሰውን ድምፅ ላለመስማት ጆሮውን ደፍኖ በዓይኑ ብቻ ሰውነትን ያፈቅራል? በዳበሳ ብቻ ፍቅር አለ? ከአምስቱ የስሜት ሕዋሳት ለፍቅር ያነሰ አስተዋጽኦ ያለው የትኛው ነው!... ዓይኖቼ ጠይምነቷን አላዩም?...እጆቼ ልስላሴዋን አላረጋገጡም? ጆሮዎቼ ምን ነካቼው?... ስለምን የምትለውን መስማት አይፈልጉም ነበር? ጆሮ ያልተሳተፈበት ፍቅር ምን 小さか?! ሰውነት የሚያኮማትር ብርድ ጋር ከባድ ዶፍ ዝናብ በሚወርድባቼው : የክረምት ቀናት፤ ማሂ ሰላም _ ዝናብ ፈርታ አልቀረችም፡፡ ጎርፍ ለብሰው ጎርፍ ጎርሰው የሚደነፉ የአዲስ አበባ መንገዶች አላገዷትም፤ ነይ ስላት ጉልበቷ ድረስ በጭቃ ተነክራ ዓይኖቿ በቅዝቃዜ ውሃ ሞልተው፣ ከውብ ጸጉሯ ጫፎች ላይ ጤዛ እየረገፈ፣ በሬን አንኳኩታለች፡፡ የሞቀ ቤቴ ውስጥ በሚሞቅ የጥጥ ፒጃማዬ ተጀቡኜ፣ ትኩስ ሻይ እየጠጣሁ፣ ሞቄ ጠብቂያታለሁ፡፡ “ በዝናብ የበሰበሰ ልብሷ ፍቅርና ናፍቆት ባጋለው የሰውነቷ ሙቀት እየጨሰ ስስ ደመና የመሰለ እንፋሎት፣ እንደ ብርሃን አምድ ከቧት ፊቴ እንደቆመች፣ በብርድ በሚንቀጫቀጩ _ ጥርሶቿ _ መኻል፣ በብርድ ከቀሉ ውብ _ ከንፈሮቿ _ “እንዴት እንደናፈቅኸኝ!" ከሚል ቃል ውጭ ምን ትናገር ነበር? እነዚያ የሚያማምሩ ጠያይም እግሮቿ በጭቃ ከተሸፈነ ቡትስ ጫማዋ ተመዘው ሲወጡ ከሰገባው እንደወጣ ሰይፍ ነበሩ፤ ጠያይም ሰይፎች፤ ያኔም መታጠቢያ ቤቴ ውስጥ፣ ሙቅ ውሃ እየወረደብን በእንፋሎት ታፍነን፣ በሰመመን ለሰዓታት ስንቆይ፣ በማሕፀን ያሉ መንታ ነፍሶች እንመስል ነበር!! እንዴት በዚያ ውስጥ ፍቅር ሳይኖር ቀረ? እንደገና እንዳገባት አልጠዬቀችኝም _ “እየባለግን'' ሄደች፡፡ እያባለኳት ሸኜኋት። አካሄዷ አስገራሚ ነበር... አብራኝ ከመኖሯ በላይ አካሄዷ ሲደንቀኝ ይኖራል፡፡
እንድ ቀን ከመበለጋችን በአንዱ... ሰፊ አልጋዬ ላይ በስሜት ስንጦፍ በመኻል подзеム予... “አብርሽ!" "A...!" “ላገባ ነው!" ለአፍታ በስስት ከምስመው አንገቷ ቀና ብዬ ፊቷን አዬኋት። ዓይኖቿን ጨፍና ዕንባዋ በጠይም ጉንጮቿ ላይ ግራና ቀኝ ወደ _ ጆሮዋ እየፈሰሰ ነበር። ፊቷን ሳምኳት፣ ግንባሯን፣ ዓይኖቿን፣ ከንፈሯን...የዕንባ ዘለላወቿ አፌን ጨው ጨው በሚል ጎምዛዛ ጣዕም ሞሉት፡፡ አስተቃቀፏ፣ በእነዚያ ውብና ቀጫጭን እጆቿ ያቀፈችኝ እስከማይመስለኝ ድረስ፤ ትንፋሽ የሚያሳጣ ጥንካሬ ነበረው፡፡ ደረቷ ላይ አጣብቃ አቀፈችኝ...ጡቶቿ እስኪጨፈለቁ፤ ምንም አላልኳትም፡፡ የሆነ ገደል ውስጥ የወደቀ ሰው፣ ገደሉ ጫፍ ላይ አንዳች ነገር ይዞ ላለመውደቅ የሚታገለው ዓይነት ስቃይ ውስጥ ነበረች፡፡ ምንም አልጠየቅኋትም፡፡ በየጄርባችን እንደተኛን ...ወደ እኔ ዞራ አንገቴ ሥር ተጣብቃ አቀፈችኝ... ለረዥም ሰዓት በዝምታ ተቃቅፈን ቆዬን፤ ዕንባዋ ሳያቋርጥ እየፈሰሰ ነበር፤ ጠይም መስክ እንደሚያቋርጥ ወንዝ፣ ራሷን ይዞ እየሄደ ነበር ዕንባዋ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ ብዙ ብዙ ነገር አሰብኩ፡፡ የሚበዛው፣ ማንን ነው የምታገባው? የሚል ነበር፡፡ ውስጤ ከእኔ መውጣት ያልቻለው የመለያዬት ጥያቄ፣ ከእሷ በመምጣቱ እረፍት ቢሰማኝም፤ ማንን ነው የምታገባው? ...አብረን ሆነን እሱ ጋር ሌላ ነገር መጀመር እንዴት ቻለች? ከጀመረች እኔ ጋር ለምን መጣች? ...ምክንያቱም የእሷ ፀባይ አልነበረም፡፡ የመጀመሪያዋ ወንድ ነኝ፡፡ በዚያ ዕድሜ እግዜር እንደፈጠራት ሳገኛት፣ ከመደንገጤ የተነሳ ቃል አጥሮኝ ነበር፡፡ ምናልባት ቀድማ ብትነግረኝ፣ ወደዚህ ነገር ውስጥ መግባቴን ዛሬ ላይ
እጠራጠራለሁ። ምንም እንኳን ብዙ ሴቶች ጋር ብሄድም፤ እንዲህ ዓይነቱ ጉዳይ ይጨንቀኝ ነበር፡፡ ሰው ይኼን ሁሉ ዘመን ከመጀመሪያ ድግሪ አልፎ ሁለተኛ ድግሪ እስኪይዝ፣ ካለነገሩ ጉልበቱን እቅፎ አይተኛም። ሴትነቷን ያስቀመጠችለት የምኞት ሰው ይኖር ይሆናል፡፡ ያ ሰው አንተ ነህ ብትል እንኳን፤ እንዳይደለሁ አውቃለሁና አልሞክረውም ነበር፡፡ ያስችለኝ ነበር ወይ?...አዎ! አጋጥሞኝ ያውቃል፡፡ እኔ ትዳር የሚባል ነገር አልፈልግም፤ ቢያንስ በብዙ ፈተና ያቆየሽውን ክብርሽን ለመቀበል ብቁ አይደለሁም፣ ብዬ የሸኜኋት ሴት አለች። እስከዛሬ ጥሩ ወዳጅ ነን፡፡ ጨዋነቴ አይደለም፡፡ ማንም ልቤ ውስጥ እንዲቀር እንደማልፈልገው፤ማንም ልብ ውስጥ በደግም በክፉም የመቀመጥ ፍላጎት የለኝም፡፡ የማገኜውን ደስታ ያኽል አብረውኝ የሚሆኑ ሴቶችም፣ አግኝተው ሲበቃን ያለምንም ቀሪ የሕይወት ሒሳብ መሰነባበት ብቼኛ ፍላጎቴ ነበር፡፡ ማሂ ሰላም ላይ ግን ይኼ ፍልስፍናዬ ሳይሠራ ቀረና የመጀመሪያዋ ወንድ ሆንኩ፡፡ የዚያን ቀን ብስጭቴ ከአንዲት ድንግል ሴት ጋር የተኛሁ ሳይሆን፣ ድንግልናዋን ክፉኛ ጠብቆ ካገባት ሚስቱ፣ የጠበቀውን ነገር ያላገኜ የገጠር ሙሽራ ነበር የምመስለው፡፡ “ምን ሆነኻል? ደስ ያለህ አትመስልም'' “ለምን አልነገርሽኝም?''
"ምኑን"?
“የመጀመሪያሽ መሆኑን!''
“ለምን እነግርኻለሁ?
...ቀድመህ ለጋዜጠኞች ትደውል ነበር? ወይስ በቀይ ምንጣፍ ልትቀበለኝ?'' ብላ አቀፈችኝና ሳቀች፡፡ ፍጹም ደስተኛ ነበረች። ሌላ ቀን ሳልደውልላት፣ ድንገት መጣች፡፡ እንደዚህ አድርጋ አታውቅም። ተቻኩላ ነበር ፣ብዙ እቃ ይዛለች፤ በፌስታል የተቆጣጠረ፣ በወረቀት ከረጢቶች የተከተተ ....
“ምንድነው ይኼ ሁሉ ደግሞ?'' አልኳት እያቀፍኳት፡፡ “ቸኩያለሁ፣ እግረመንገዴን ላይህ ነው የመጣሁት" ከያዘቻቼው ፌስታሎች ሥር፣ በትልቅ ባለ ዚፕ ላስቲክ ተሸፍኖ፣ በልብስ መስቀያ ያንጠለጠለችውን ልብስ አዬት አድርጋ “ቬሎ ነው'' ካለችኝ በኋላ፣ ሶፋው ላይ ጣል አድርጋ አቀፈችኝ፡፡ መሳሳም ጀመርን ... እያገባች ነበር፡፡ ወደ ትዳር እየሄደች... ቬሎዋን ይዛ ቤቴ መጣች ቢባል ማን ያምናል?....እየሳመችኝ ታለቅሳለች፡፡ “መቼ ነው?”...አልኳት የሞት ሞቴን ዓይኗን ላለማዬት እየሞከርኩ፡፡ ራሷ ወደ መኝታ ቤት እየጎተተች ወሰደችኝ እና ልብሷን አወላልቃ አቀፈችኝ ጠይም ስቃይ ...በስሜት እየቃተተች፣ ቅድም ሳሎን የጠየኳትን ጥያቄ፤ መኝታ ቤት መለሰችልኝ፡፡ “ከሁለት ሳምንት በኋላ አገባለሁ'' አሁን አላለቀሰችም፡፡ግን ሲበዛ ኮስተር ብላ ነበር፡፡ አጥብቃ አቀፈችኝ፡፡ ከአንድ ሰዓት በኋላ ምንም እንዳልተፈጠረ፣ የተኛሁበት ትታኝ ተነስታ ልብሷን በፍጥነት ለበሰች፣ ጸጉሯን አስተካከለች ቆም ብላ አዬችኝ እና ወጥታ ሄደች፡፡ በሩ ሲዘጋ ከውጭ ይሰማኛል፡፡ አዘጋጉ ኃይለኛ ነበር፤ ግድግዳዎቹ እስኪነቃነቁ። ሙሉ ቀን ከአልጋዬ አልተነሳሁም፡፡ ሐዘን አይደለም፣ ምንም አይደለም...ሰው አያምንም እንጂ፣ የዚያን ቀን ለሦስት ወይም ለአራት ሰዓታት ሞቼ- ከሞት ተነስቻለሁ፡፡ ማሰብም፣ በራስ ሰውነትም ይሁን ስሜት ማዘዝ አለመቻል፣ ሞት ካልሆነ ምን ነበር ታዲያ? ምን _ እያደረገች ነው? ለማስቀናት እየሞከረች ነው?...እኔ ማድረግ ያልፈለኩትን፣ ሌላ ወንድ እያደረገው መሆኑን ለማሳዬት ነው?... ወይስ እልኅ አስገብታ ባለቀ ሰዓት እዚሁ እንዳስቀራት? ...ምንድን ነው ፍላጎቷ!?...ያኔ እንደዚያ ነው ያልኩት ፍቅር የአፍቃሪ ነፍስ መሆኑን አላወቅሁም ነበርና ግቢ ነፍስ ውጭ ነፍስ ሲቃዋን መረዳት አልቻልኩም፡፡

👍34❤8
ለአንድ ሳምንት አልደወልኩላትም፡፡ በርግጥ በየቀኑ አስባት ነበር፡፡ እንደዚያ ሳላቋርጥ ስለ እሷ ያሰብኩበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ ለመደወል በየቀኑ ስልኬን አነሳና፣ ሐሳቤን እየቀዬርኩ እተወዋለሁ፡፡ ግን ደውዬ ምን ልላት እችላለሁ? .. በቃ አታግቢ እኔ አገባሸለሁ? እና ያ ድፍረት ከሌለኝ ሌላው ሁሉ ምንድን ነው? ከራሲ እየተማጎትኩ ከመደወል አረፈድኩ፤ ከሕይወቷ አረፈድኩ፤ ከሁሉም ነገር አረፈድኩ ያውም እዚያው በሯ ላይ ቆሜ። ከሁለት ሳምንት በኋላ (በትክክል ሁለት ሳምንት አይመስለኝም) ከሰዓት በኋላ ደወለችልኝና “ እየመጣሁ ነው እቤት ነህ?'' አለችኝ፡፡ እዚያው አካባቢ ስለነበርኩ ቤት ሄጄ ጠበቅኋት፡፡ መጣች፡፡ ጸጉሯ በትልቅ ሻሽ ተጠቅልሎ፣ መላ ሰውነቷ ሻንፖና ኮንዲሽነር፣ እንዲሁም የተቃጠለ ጸጉር ዓይነት ይሸታል። ጠይም ፊቷ ጉንጩና ጉንጯ ላይ ቀልቷል- ጠይም ቅላት (ጸጉር ማድረቂያ ውስጥ ስትቆይ እንደዚያ እንደሚሆን አውቃለሁ) ጥፍሮቿ፣ ረዣዥም ጥፍሮች ተቀጥሎባቼው፣ ነጭ የሚያብረቀርቅ የጥፍር ቀለም ተቀብተዋል፡፡ “ከጸጉር ቤት ነው የመጣሁት፣ ሚዜዎቼን መጣሁ ብያቼው በ 'ኮንትራት' ታክሲ!" ብላኝ ወገቧን ይዛ ቤቴን እንደ አዲስ በዓይኗ ቃኜችውና ቅሬታ በረበበት ፊት ድምፅ የሌለው ሳቅ ሳቀች፡፡ የሠራችውን ለራሷም ማመን የቸገራት ትመስል ነበር፡፡ ግራና ቀኝ ዳሌዋ ላይ ያረፉ መዳፎቿ፣ ከረዣዥም ጥፍሮቻቼው ጋር ተዳምረው፣ ቀጥሎ ዘላ የምትበጫጭቀዉ ነገር የምትፈልግ አስመስለዋታል፡፡ እኔ ቤት መገኜቷ ለራሷም ግራ የገባት ይመስላል። እና ሁለት እጆቿን እንደ ክንፍ በሰፊው ግራና ቀኝ ዘርግታ ቆመች፤ተጠግቼ አቀፍኳት፡፡ ፈርቻት ነበር፡፡ እየሄደች ነው እየተለያዬን ... እና ደግሞ ጠረኗ... ተሳሳምን ...አልጋዬ ላይ ወደቅን፣ ሻሽዋ ተፈቶ የተፈሸነ ጸጉሯ ትራሱን ሞልቶ እየተንሸራተተ ሲገማሸር ማዕበል ይመስል ነበር ...ጥቁር መዓበል... የተቆጣ ጥቁር መዓበል፡፡ ደግሞ ሽታው እንዴት ደስ ይላል፡፡ ሰውነቷ በሙሉ በሽቶ ተነክሮ ነበር፡፡ ከንፈሬ ደም አርግዞ ሕመሙ እስኪጠዘጥዘኝ በመንከስና በመሳም መካከል በሆነ ስሜት ሳመችኝ... እያለቀሰች ነበር...በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ሳሎን ትታው
የመጠቸው ስልኳ ያለማቋረጥ አሁንም አሁንም ይጠራል.. እዬሳመችኝና እያለቀሰች... ስልኳ ይጠራል... ማንን ነው የምታገቢው? አላልኳትም፡፡ ስልኳ ይጠራል... ልብሷን በፍጥነት ለባብሳ ሻሽዋን ስታስር ለራሷ በሚመስል ቀሰስተኛ ድምፅ “ ምን ዓይነት መርከስ ነው ይኼ!?'' አለች፡፡ በኃፍረት መሬት መሬት ነበር የምትመለከተው... ስልኳ ይጠራል፣ የሚረብሽ የድምፅ፣ የምስል፣ የስሜት ረብሻ ነበር፡፡የሆነ የተቀናበረ ረብሻ፡፡ ማሂ ሰላም ስልክ አትወድም። ቤቴ ስትመጣ፣ ሰላም ተከትሏት የሚመጠ ልጅ ነበረች፡፡ “ማሂ ሰላም...” ጠራኋት ፡፡ ልክ የሆነ ነገር ወድቆ እንደተሰበረ ዓይነት ደንግጣ ቀና አለች፣ “ጥሩ ልጅ ነሺ!” አልኳት፣ “ነኝ ....!?" አለች፣ መልሳ እያቀረቀረችና ልብሷን እያስተካከለች፡፡ ድምፅዋ ውስጥ ዛሬ ገና ተገለጠልህ? የሚል ብስጭት ነበር። ስልኳ ይጠራል፤ እናም ዞራ ሳታዬኝ እየተጣደፈች ከመኝታ ቤት ወጣች፡፡ በሩን በቀስታ ዘግታ ስትወጣ፣ በርግጌ ተነሳሁና ራቁቴን ወደሳሎን ሮጥኩ፡፡ ትልቁ 'ስፒከር' ላይ ተቀምጨና እጆቼን የመስኮቱ ደፍ ላይ አስደግፌ፣ የኮንዶሚኒዬሙን የመኪና ማቆሚያ ሜዳ አቋርጣ፣ ከዋናው ግቢ ስትወጣ ከኋላዋ አዬኋት።እረማመዷ የማውቀው ዓይነት አልነበረም ፈጣን ነበር፤ ስልክ ታወራለች ...ረጋ ያለች ነበረች ሳውቃት፣ ከየት መጣ ይኼ ፍጥነት? አብረን ስንሄድ እንኳን ከፈጠንኩባት “ኧረ! ቀስ አብርሽ ልቤ በአፌ ልትወጣ ነው'' የምትል፡፡ ከግቢው ውጭ አንዲት ሰማያዊ ላዳ ታክሲ ቆማ እየጠበቀቻት ነበር ...ገብታ ሄደች
በቃ
ሰማያዊ ቀለም የመለያዬት ባንዲራ ይመስለኛል- እስከዛሬ፡፡ የሰው ልጅ የታሪክ ምዕራፍ እንዲህ ይዘጋል ግን ? ተገረምኩ፡፡ በመለያዬታችንም በተፈጠረውም ነገር ሳይሆን በነገሩ ፍጥነት፡፡ የምጠብቀው ቢሆንም አራት ዓመት ሙሉ፣ ሕፃን ልጅ በጥርሱና በእጁ ይዞ እነደለጠጠው ማስቲካ ሲቀጥን... ሲቀጥን የነበረ አብሮነታችን የሆነ ጊዜ እንደሚበጠስ ባውቅም፣ ይኼ ግን ገረመኝ፡፡ የእርምጃዋ ፍጥነት፣ ታክሲ
ውስጥ የገባችበት ፈጣን እንቅስቃሴ፣ ከማትፈልገው ትዳር ለማምለጥ ወደሰርጳ በፍጥነት መሮጥ አይገርምም!? .. ወደምንሸሸው ነገር እየሮጥን መሸሽ፡፡ እና ከዚያ ያላስጣልኳት እኔን፤ በዚያች ቅጽበት፣ በቀለም፣ በብሩሽ ምናምን ሳይሆን፣ በተረት ለመሣል ቢሞከር “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም'' ይሉት አባባል ፎቶዬ ሆኖ ዕድሜ ልክ ግድግዳዬ ላይ በተሰቀለ ነበር፡፡ እዚያው መስኮት ላይ ረዥም ጊዜ ተቀምጨ ቆዬሁ፤ ለምን ሰው አሰቃያለሁ? .. ለምን ውስጤ ቅጥል አለ!? በሽተኛ! ብዬ ጮኽኩ፡፡ ራሴን ነበር! ምን አደረገችን አንዲት ሚስኪን ናት! ምንድን ናት? ጠላቴ ናት? ...ሰው ለመሆን ዕድሜ ልኳን የደከመች፣ ጥርሷን ነክሳ ተምራ ሰው የሆነች ...ያለ እናት ብቼኛ አባቷ ጋር ጉድለቷን ችላ፣ ሕመሟን አፍና ያለፈች ሚስኪን ነች!...አፈቀርኩ ብቻ ነው ያለችው ...አፍቅራኛለች፣ አላፈቀርኳትም!... ሥር ሳይሰድ በጊዜ የምንለያይበት ሌላ ጨዋ መንገድ አልነበረም??? ...ምን አደረገች ...? ለራሴ የሥጋ ደስታ ስል እዚህ ድረስ መጓዝ ነበረብኝ...? ለምንድን ነው ያላፈቀርኳት? ፍቅር መላመድ ነው የሚሉት ነገር የት ሄደ?....ወይንስ አራት ዓመት ሙሉ የማይለምድ፣ሥጋን ብቻ እየነጠቀ የሚሮጥ፣ ከሆነ ዓለም የመጣሁ ክፉ አውሬ ነኝ? ምንም መልስ ላገኝ አልቻልኩም... ለምንድን ነው ማፍቀር ያቃተኝ?... ደውዬ ነይ ስላት፣ እንደ _ አምቡላንስ እየተንቀለቀለች ቤቴ በመምጣቷ? ልክ እንደ አምቡላንስ፣ ፈገግታዋ ቀይ መብራት፣ ሳቋ ሳይነር፣ ሆኖ ፀሐይ ዝናብ ሳትል መምጣቷ?... የታመመችው ግን እሷ ነበረች። ሳቅፋት የምትፈወስ ዓይነት! አቤት እቅፌ ውስጥ ስትወድቅ እንዴት እንደምትረጋጋ፣ ከሚያሳድዳት አውሬ ያስመለጥኳት ያኽል! ለምንድን ነው ያላፈቀርኳት...? ይላል ዶጁ ምናምን የሚል ዘፈን በዚህ ዘመን በመውደዷ? ምኗ ነበር የሰለቼኝ? ቆይ ባላፈቅራትስ፣ ዝም ብዬ ባገባት ምን እሆን ነበር ?...ፕላኔቶች ምህዋራቼውን ስተው ይጋጩ ነበር? ካናዳ፣ እንግሊዝ ምናምን አንድ ኢትዮጵያዊ የማያፈቅራትን ሴት ስላገባ ስንዴ አንረዳም ይሉ ነበር? ይኼው እሷ
የማታፈቅረውን ሰው ልታገባ አይደል? ብታፈቅረው ሰርጓ ሁለት ቀናት ቀርተውት እኔ አልጋ ላይ ትገኝ ነበር!? ከተቀመጥኩበት ስነሳ፣ ከኋላዬ መኸል መንገድ ላይ ተንሸራቶ፣ መሬት ላይ ወድቆ የነበረውን የሰፋ ትራስ በብስጭት በእግሬ ጠለዝኩት፡፡ በአየር ላይ ተንሳፎ፣ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረ የግድግዳ ሰዓት ጋር ተላተመ፡፡ ሰዓቱ ወርዶ ምንጣፉ ላይ ወደቀና በአፉ ተደፋ... ከሚጎርሳቼው ሁለት ባትሪዎች አንዱ ወደ ሆነ ቦታ ተስፈንጥሮ ጠፋ፣ በትሪውን የመፈለግ ፍላጎቱ አልነበረኝም፡፡ ዝም ብዬ የነበረበት ስሰቅለው ልክ 11፡59 ላይ መቁጠሩን አቆሞ ነበር! ወደ መታጠቢያ ቤት ሄጄ፣ በቀዝቃዛ ውሃ ሰውነቴን ታጠብኩና፣ ወደ መኝታ ቤቴ ተመልሼ ምንጣፉ ላይ የወደቀውን የፒጃማዬን ሱሪ አንስቼ ለበስኩ፡፡ ከላይ አላባሹ ጠፋኝ፣ ሁልጊዜ እሷ ጋር አብረን ከተኛን በኋላ ልብሴ የሚጠፋኝ ለምንድን ነው?... አልጋው ተተረማምሷል፡፡ የተመሰቃቀለውን ብርድ ልብስና አንሶላ እያነሳሁ ፒጃማዬን ስፈልግ ያስደነገጠኝን ነገር አገኜሁ...

👍39❤8
የማሂሰላም 'ፖንት'፡፡ ትናንሽ እንጉዳይ የመሳሰሉ ቀያይ አበቦች ያሉባት ነጭ ፓንት... ረስታው ነው? አውቃ ትታው ነው? ግራ ገብኝ። ልደውልላት ቃጥቶኝ ነበር...በሥርዓት አጣጥፌ፣ ቁም ሳጥኔ ላይ ካሉት ትናንሽ መሳቢያዎች አንዱ ውስጥ አስቀመጥኩት፡፡ ልክ እንደመደበቅ ነበር ...ከማን ነው የምደብቀው? ከወገቤ በላይ ራቁቴን እንደሆንኩ ወደ ሳሎን ተመለስኩና ያንን ትልቅ “ሲዲ" ማጫዎቻ ለመክፈት መጎርጎር ጀመርኩ፤ ምንም ይዝፈን፣ የሆነ ዘፈን መክፈት ፈልጌ ነበር፡፡ እዚህ ሲዲ' ማጫዎቻ ላይ ብዙ ሺህ ጠይም አሻራዎች ያሉ ይመስለኛል፤ የሚስኪን ማሂ-ዘፈኑን መክፈቱን ትቼ ዝም ብዬ ቆምኩ:: ብዛት ያላቸው ሲዲዎች እዚያና እዚህ በሥርዓት ተደርድረዋል፡፡ ዘፈን፣ ዘፈን፣ ዘፈን ...ሁሉም የማሂ ሰላም ናቸው። ዘፋኝ ይሆን እንዴ የምታገባው ሰው?!
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍33🤔11❤2