አትሮኖስ
284K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
521 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹ምን ችግር አለው፡፡ አንድ ከተማዋን የሚያውቃት ጓደኛ ፈልጋ፡፡ አየህ ይሄንን የመሠለ አጓጊ ጨዋታ በአዲስ አበባ ግርግር ውስጥ መጫወት አልፈልግም፡፡በደብረዘይት ፀጥታና ውበት እየተደመምኩ ቢሆን እመርጣለሁ፡፡››

‹‹እሺ ይሁን ለጊዜው ከጓደኞቼ መሀከል ከተማዋን ማን እንደሚያውቃት ትዝ አይለኝም፡፡ ካልሆነ አንድ ሰው እቀጥራለሁ፡፡››

‹‹የግድ እኮ ወንድ ጓደኛህ መሆን የለበትም፤ሴትም ጓደኛህ ልትሆን ትችላለች...የመጨረሻ አንድ ማሳሰቢያ ሞባይል ስልኬን በመከታተል ጊዜ እዳታጠፋ...የተመዘገበው በእኔ ስም ሳይሆን እኔም በማላውቀው በሌላ ሰው ስም ነው፡፡አረብ አገር በሄደ ሰው ስም፡፡ለማንኛውም ቻው፡፡ ዝርዝር ህጎችን ቀኑን ስትወስን እንነጋገራለን፡፡ >> ሰልኩ ተዘጋ፡፡

ይቀጥላል

አሁንም ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ ቤተሰቦች ዛሬም አንድ 10 ሰው እጠብቃለው👍  አሁንም እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #አድርጉ ያሰብነው ከሞላ ነገ እንገናኝ ይሆናል። 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍57😁7🔥3
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አስራ አምስት፦ ማመን ማየት ነው!
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

ዛሬ፦ ሲያትል

የትላንትናው ውብና ብሩህ ቀን ተቃራኒ ነው:- ዛሬ። ዝናቡ አሁንም ይወርዳል፦ በዝግታ፣ ልስልስ ብሎ። ዛፎቹ ላይ የሚታየው ጉም፣ ሰማዩ ጥቅጥቅ ባለ ጭጋግ ተሸፍኖ ሳየው ቀኑ ራሱ የሚመጣውን ያየ ነው የሚመስለው፦ የዳሪክን ሞትና ስንበት። የዝናቡ አወራርድ፣ የጸሐይ ድብቀት፣ የሰማዩ ላብና የደመናው ጥቁረት ሲታይ ቀኑ ራሱ የሆነ ልብን የሚያርድ ነገር አለው። የሆነ የሚያሳዝን ውበት ፈስሶበታል፦ ቀኑ። ቀኑ ይዞት ሊመጣው ያለው ነገር፣ የዳሪክ ለሞት መታጨት አሁንም ውስጤን በሃዘን ሰብሮኝ፣ እንባዬን ላለማውጣት እየታገልኩኝ ከሳሌም ጋር ዳሪክን ማዘጋጀት ቀጠልን። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ዳሪክ ስንዱ ሆነ፦ ለማይቀረው ጉዞ።

ሳሌም አሁንም ያው ናት፦ ጸጥ፣ ረጭ፣ ርግት ያለች።

ጥቂት ሳያት ቆየሁና "...ምንም አይመስልሽም ሳሌም?...” ጠይቅኳት

“…ምኑ ሳዬ?...” መልሳ ጠየቀችኝ 

“…የዳሪክ ነገር ነዋ፣ ሃኪሞቹ ሊያደርጉት ያለው ነገር?...”

ሳሌም ቀና ብላ አየችኝ “…ያሳስበኛል። በደንብ ያሳስበኛል። ግን ደሞ ከሃሳቤ፣ ከጭንቀቴ በላይ የማምነው ነገር አለ። ከፍቅሬ የተማርኩት አንድ ነገር የምታይው ነገር ሁሉ የሚታመን አለመሆኑን ነው። ማየት ማመን ነው ይላሉ። እኔ ደሞ በተቃራኒው ነው እላለሁ። ለኔ ማመን ማየት ነው። ትዝ አይልሽም ወደ ዚህ ሃገር ስመጣ የሆነው…..የመጀመሪያውና የመጨረሻው ቀን...”

እንደዚህ ስትለኝ …ከቀናት በፊት ሳሌም የተረከችልኝ ያወራችልኝ ትዝ አለኝ።…ለአንድ አፍታ እንደገና በሃሳቤ ሄድኩኝ።

**

የመጨረሻው ቀን፦ አዲስ አበባ

…ምንም አይመስልህም የኔ መልዐክ?...” በ'ርጋታ ፊት ለፊቷ ቁጭ ያለውን ዳሪክ ጠየቀችው። “…ትንሽ እንኳን አይጨንቅህም? ከሃያ አራት ሰዐት ቡሃላ እኮ ለረጅም ጊዜ ልንለያይ ነው?  ምንም አይመስልህም?....” 

ይሄ ቀን ለሳሌም ለዳሪክ የሚለያዩበት ቀን ነው። ሳሌም በሚቀጥለው ቀን አመሻሽ ላይ ወደ አሜሪካ ትበራለች። ዳሪክ ደግሞ ከፍተኛ ነጥብ አምጥቶ ወደ ክፍለ ሃገር ዩኒቨርስቲ ገብቶ ሪፖርት የሚያደርግበት የመጨረሻው deadline የዛኑ ቀን ነው። በማለዳ ተነስቶ መሄድ አለበት። በአጭሩ ሳሌምና ዳሪክ ያላቸው ቀን ይሄ ነው። ህይወትና ኑሮ ሁለቱን ለመለያየት በትጋት ላይ ናቸው።

በዛ የመጨረሻ ቀንና ሰዐት ሳሌም ጭንቅ ላይ ሆና፣ የምታደርገው ጠፍቷት ስትዳክር ዳሪክ ግን በተቃራኒው ተረጋግቶ፣ ዝም ብሎ ቁጭ ብሏል።

“…ምንም አይመስልህም? ምንም አይጨንቅህም?...” ሳሌም እንባዋ ባ'ይኗ ሞልቶ መፈሰስ ጀመረ

“…የምወድሽ…” ዳሪክ ቀስ ብሎ እንባዋን እየጠረገ “…ማመን አለብሽ። አንለያይም። እንኳን በጊዜና በስፍራ መለያየት ቀርቶ ሌላም ነገር ቢመጣ እንኳን ፍቅራችንን እንደማይንደው፣ እንደማንፈርስ ማመን አለብሽ። የምታየውን ብቻ አትመኚ። የምታምኚውን አየዋለሁ... ብለሽ  በቃ ዝም ብልሽ ጌታን እመኚ…ማመን ማየት ነው የምወድሽ.”
 
“…ምንድን ነው የምታወራው?.. ያንተ ፍልስፍና አያልቅም?...” ሳሌም ብስጭት ብላ

ዳሪክ ተረጋግቶ ማውራቱን ቀጠለ “…አየሽ የምወድሽ ማየት ማመን ነው ይላሉ። ግን እኮ የሚታየው ነገር ሁሉ እውነት አይደለም። አሁን አዲስ የተሰራ አስፋልት ላይ ብትሄጂ  ከፊት ለፊትሽ አስፋልቱ ላይ ውሃ እንዳለ አይንሽ ያሳይሻል። ግን ውሃ የለም። ወይም ደሞ ሙሉ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ ስትሮ ብትከቺ ስትሮው የተሰበረ መስሎ ይታይሻል። ግን ስትሮው አልተሰበረም። አንድን ዛፍ ከሩቅ ብታይው ...ዛፉ ትንሽ መስሎ ይታይሻል። ስትቀርቢው ግን ዛፉ ትንሽ አይደለም። .... አሁንም በህይወታችን ላይ የሚታዩት ነገሮች ልንለያይ እንደሆነ ለአይኖቻችን ሊያሳዩን እየሞክሩ ነው። ፍቅርና እምነት ግን ከሚታየው በላይ ሄደው ያምናሉ፣ያያሉ። እምነቴ  ከማየው ነገር በላይ ነው። ያመንኩት አሁን የማየውን አይደለም። ይልቅስ ተቃራኒ ነው።  የማየው በውስጤ ያመንኩትን ነው። ለኔ ማየት ማመን አይደለም። ይልቅስ ለኔ 'ማመን ማየት ነው! የማምነው ደሞ የኔና ያንቺ ፍቅር ከመለየት በላይ መሆኑን ነው። እንለያይም የምወድሽ። ይህንንም ስላመንኩኝ በቃ …ይህንን ብቻ ነው የማየው። ያመንኩትን ብቻ ለማየት ወስኛለሁ። አንለያይም የምወድሽ። አንለያይም።…. ይህንን ነው የማምነው...ይህንን ነው የማየው።….”

ሳሌም የሚያወራው ትንሽ የገባት መሰላት። ብዙው ግን አልገባትም። እሷ የሚታያት አይኑን አፍጥጦ በሁለቱ መካከል ሊገባ ያሳፈሰፈው መለየት የሚባል ጉድ ነው። የምታውቀው ከአለም ግማሽ ርቃ፣ ውቂያኖስ ተሻግራ ከፍቅሯ ልትለይ መሆኑን ነው። መለየት ባላንጣ፣ መለየት ክፉ፣ መለየት ጨካኝ በር ላይ ቆሟል። ያስፈራራል። ይዝታል። ይፎክራል።

የዛን ለት በመለየት ጥላ ስር በወደቀ ፍቅር አብረው ብዙ ከቆዩ ቡኃላ አመሻሽ ላይ  መለያየት ባይፈልጉም… ጊዜ አይቆምምና … የሚለያቸው ጊዜ ቀረበ።

ሳሌም ታክሲ ውስጥ ገባች። ዳሪክም በተቃራኒው ጉዞውን ጀመረ።

ዳሪክ ላይ አይኗን ተክላ ከጀርባው ስታየው አይኗን የሞላው እንባ የዳሪክን ምስል ሲያደበዝዝው…. ታክሲው ጉዞ ጀመረ። ታክሲው በዝግታ መጓዝ ሲጀመር በዳሪክና በሷ መካከል ክፍተቱ እየሰፋ ሲመጣ …መለየቱ እውን ሆነ። መለያየት አሸነፍኩ አለ። ሳሌም ሲጨንቃት፣ የምታደርገው ሲጠፋት ሳምንታት አልፈዋል። አሁን ግን የጭንቁ ጫፍ ላይ ደረሰች። ዳሪክን ለወራት፣ለአመታት … ወይም እስከ መጨረሻው ላታየው እንደምትችል ስታስብ ደረቷ ላይ የሆነከባድ ነገር ቁጭ ሲል፣ ሲከብዳት  ትንፋሿን እያጣች.. ሞት አፋፍ ላይ የቆመች ያህል ሆነ።

በታክሲው ትንሽ እንደሄደች አልቻለችም “..አቁምልኝ!...ወራጅ አለ!...” ወደ ታክሲው ረዳት ዞረች።

“…ምን?....  እዚህ ጋር አይቆምም እሙ…”

" አውርደኝ ነው የምልህ!" ሳሌም አምርራ

" እሙዬ እዚህ ጋር አይቆምም እያልኩ...."ረዳቱ ሲያወራ እቐረጠችው።

“….ወራጅ አለ!... መውረድ እፈልጋልሁ!... አሁኑኑ!...” ሳሌም ጮኸች።

ተሳፋሪዎች  ዞር ብሎ ያዩ ጀመር ፦ ሳሌምን።

“…እዚህ ጋር አይቆምም… ተሻግረን…” ረዳቱ ሊያሳምናት ሲሞክር ሳሌም እሱን የምትሰማበት ጆሮ አልነበራትም …አቋረጠችው።

“…ወራጅ አለ!...  ወራጅ!...  ወራጅ !... መውረድ እፈልጋለሁ!....” ሳሌም የሚኒ ባሱን ጎን በሃይል ስትደበድብ

“….ኸረ አቁመው ባክህ ልጅቷ ትንሽ ነካ ያደርጋታል መሰለኝ….” ረዳቱ በድንጋጤ።

ታክሲው ሲቆም ሳሌም ወርዳ በፍጥነት መሮጥ ጀመረች፦ ወደ ዳሪክ። እየተደነቃቀፈች ፦ ወደ ዳሪክ። መንገደኛው እንደጉድ እያያት፦ ወደ ዳሪክ። ስሙን እየጠራች “..ዳሪክ!… ዳሪክ!… የኔ ፍቅር!... የኔ መልዐክ!...” ፦ ወደ ዳሪክ።

ዳሪክ የሳሌምን ድምጽ ሰምቶ ዞር ሲል አጠገቡ ደርሳለች። ላዩ ላይ ተጠመጠመችበት። ከዛም ዝቅ አለችና እግሩን ያዘችው “…ዳሪክ.. የኔ መልዐክ!... አትሂደብኝ፣ የትም አትሂድብኝ፣ እኔም አልሄድም….”  እንባዋን እያዘራች፣ እየተንሰቀሰቀች “…የምሞት መሰለኝ፣ ከተለየኸኝ የሚያበቃልኝ፣ ትንፋሼ የሚቆም መሰለኝ። እባክህን?... እባክህን  አትለየኝ፣ አትሂድብኝ!...” ለሚያያት ሰው ሳሌም የታመመች ነበር የምትመስለው።

ዳሪክ ሁኔታዋን ሲያይ ልቡ ተንሰፈሰፈ።  ቀስ አድርጎ ደግፎ አነሳትና እንደ ህጻን ደረቱ ላይ ደግፎ ያባብላት ጀመር “…ሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽ…” በቃ።
👍233🥰2
ሳሌም ደረቱ ላይ በልቅሶ እየተንቀጠቀጠች  " ሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽ.... የምወድሽ.....ሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽ!'

እንደዚህ ይዟት ብዙ ቆየ።

ትንሽ ስትረጋጋ  “….የምወድሽ…” ዳሪክ ጠራት

“….ወዬ...የኔ መልዐክ…”

“…እስከዛሬ ዋሽቼሽ አውቃለሁ የምወድሽ?...”

“…በጭራሽ…”

“…ቃሌን ታምኚዋለሽ የምወድሽ?...”

“…እህ…” ራሷን ደፋ ቀና አደረገች

“…ካመንሽኝ ቃሌን ስሚኝ የምወድሽ። አልለይሽም የምወድሽ። መከራ ቢመጣ፣ ችግርና ችጋር ቢያፈጥብኝ፣ በስፍራ ብትርቂኝ፣ ሞት አፋፍ ቆሜ ብገኝ … 'አትለየኝ' ካልሺኝ አልለይሽም። በቅርቡ እንደገና እንገናኛለን …ይህ ቃሌ ነው። የምነግርሽን ብቻ ቃሌን እመኚው። ቃሌን ካመንሽኝ ያመንሽውን ታይዋለሽ። ማየት ማመን ሳይሆን …ማመን ማየት ነው። አመኚኝ አልለይሽም…”

የዳሪክ 'ርጋታና ድምጹ ላይ ያለው እምነት በራሱ ሳሌምን ቀስ በቀስ ሊያረጋጋት ጀመረ።

“…አትለየኝ በይኝ የምወድሽ…”ዳሪክ ቀና እያደረጋት። 

“…አትለይኝ የኔ ፍቅር!...” ሳሌም ቀና ብላ

“…አልለየሽም የምወድሽ ...አልለየሽም ይህ ቃሌ ነው። ቃሌን ደሞ እመኚው!...” የዳሪክ ንግግር ሃይል ነበረው። እውነትንም ውስጡ ይዟል።

“…እሺ አምንሃለሁ… የኔ መልዐክ!...” ሳሌም ከልቧ ነበር።

“…ያኔ የምታምኚውን ደሞ ታዪዋለሽ …አስታውሺ ማመን ማየት ነው። አንለያየምን በአይንሽ   እይው፣ በእጅሽ ዳሺው… አንለያየም!....አንለያየም!...አንለያየም!....እሺ የምወድሽ …እሺ!...”

ሲደጋግምላት የዳሪክ ቃላቶች፣ ድምጹ ቀስ በቀስ ሳሌምን ያረጋጋትና እምነትን በውስጧ ያበቅል ጀመር … ‘አልለይሽም የምወድሽ፣..’  … ‘…አንለያየም…’…. ‘…እመኚኝ…’  ‘….ማመን ማየት ነው!...’

******* 

ዛሬ፦ ሲያትል….

  ዳሪ
ክን ካዘጋጀነው ግማሽ ሰዐት ያህል ቆይቶ ለማይቀረው ጉዞ ሂደቱን የሚፈጽሙት ሃኪሞች መጥተው ነገሮችን ያብራራሉን ጀመሩ። በክፍሉ ውስጥ ያለነው ሳሌም፣ እኔ፣ ታዴና ዳሪክ እዚህ ሃገር እንዲመጣ ከረዱት ቤተሰቦች አንድ ሰው ነው። አንደኛው ሃኪም ቀለል ባለ ሁኔታ የሚደረገውን ቅደም ተከተል አስረዳ።

በመጀመሪያ…ዳሪክ ወደ ሆስፒታሉ ታችኛው ወለል ላይ የሚገኝ አንድ ክፍል ይወሰዳል።

ከዛ ሃኪሞቹ ማሽኖቹን ሙሉ በሙሉ ያጠፋሉ፦ በዚህ ሂደት ላይ የዳሪክ ሳንባ ሙሉ በሙሉ መተንፈስ ያቆማል። ተከትሎም የልብ ትርታው ቀስ በቀስ ወርዶ ዜሮ ይገባል። ይህም መጨረሻው ነው።

ከዚህ በፊት ካላቸው ተሞክሮ ይህ ሁሉ ሲደረግ ለበሸተኞቹ ቤተሰቦች አስጨናቂ ስለሚሆን በስፍራው መገኘት ካልፈልግን አለመገኘት እንደምንችል ተነገረን። ሳሌም ከዳሪክ ጎን እንደማትሄድ ስትናገር እኔም ጭንቅ ቢሆንብኝም ሳሌም ብቻዋን መተው ስላሳዘነኝ አብሬ ለመሄድ ተስማማሁ። ታዴና ሌላው ሰው እዛ ክፍል ውስጥ እንደማይገቡ ውጪ መሆን እንደሚመርጡ ተናገሩ።

ነርሶቹ ዳሪክን ሊወስዱ ሲዘጋጁ …ሳሌም አቋረጠቻቸው “…ይቅርታ ትንሽ ጊዜ ከዳሪክ ጋር ልውሰድ?...”

"...እሺ…. የምትፈልጊውን ያህል ውሰጂ…” አንደኛው ሃኪም ነበር “…ለብቻሽ ነው መሆን የምትፈልጊው?...”

“…አዎ…” ሳሌም መለሰች “…ለብቻው!.... ከአምስት እስከ አስር ደቂቃ ብወስድ ነው….” ሁኔታዋ የሆነ ነገር ያስታወሰች ነበር የምትመስለው።

የሳሌምን ጥያቄ አክብረን ሁላችንም ክፍሉ ውስጥ ሳሌምንና ዳሪክ ጥለን ወጣን። ሁላችንም ወጥተን የዳሪክ የሆስፒታል ክፍል በሩ ተዘግቶ ሳየው ሳሌም ምን እያደረገች፣ ምን እያለች ይሆን ብዬ ማሰቤ አልቀረም።

ሳሌም ግን ብዙም አልቆየችም።የምታደርገውን ነገር ጨርሳ ነርሶቹን ጠራቻቸው።  ከደቂቃዎች ቡሃላ ነርሶቹ ዳሪክን ከነአልጋውና ከማሽኖቹ ጋር እየገፉ ሲወስዱት፣ እኛም ከሃኪሞቹ ጋር ከኋላ እየተከተልን አጅበነው መጓዝ ጀመረን። በሰላማዊ እንቅልፍ ውስጥ ያለው ዳሪክ ሲያዩት ወደ ዘላለማዊ ጉዞው የሚሄድ ሳይሆን ለእረፍትና ለጉብኝት ወደ ሌላ ሃገር የሚሄድ፣ በአውሮፕላን የመጀመሪያ ማዕረግ…እየሄደ ያለ በጥልቅ እንቅልፍ ላይ ያለ ቱሪስት ነው የሚመስለው።

*********

የመጨረሻው ቀን፦ አዲስ አበባ


    ወደ ኢትዮጲያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር …እንኳን በደህና መጡ!.... ይህ በረራ ከአዲስ አበባ… ሮም…. ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚበር …. የምንበርበት ከፍታ 35000 ጫማ ሲሆን ባሁን ሰዐት በምዕራባዊ ሱዳን የአየር ክልል ውስጥ እንገኛለን። …ሳሌም በአውሮፕላኑ የድምጽ ማጉያ ከሚወጣው የአብራሪው ድምጽ የሰማችው በሱዳን የአየር ክልል ውስጥ የሚለውን ብቻ ነው። …ከሀገር ለመውጣት የሚፈጀው ይህን ያህል ጊዜ ብቻ ነው? አቤት ፍጥነቱ? ተወልዳ ያደገችበትን፣ ሁሉን ያየችበትን፣ የፍቅርን “…ሀ…ሁ…” የቆጠረችበትን ምድር እንዲህ በደቂቃዎች ለቃ ስትወጣ እንደገና ልቧ በሃዘን መወጋቱ አልቀረም። እንባዋ እንዸገና በአይኗ ሊመጣ ሲዳዳው ….ትላንት ሌሊቱንና ዛሬ ቀኑን በልቧ እያሰላሰለች ስትጽናናበት የነበረውን የዳሪክ ቃላቶች ማሰብ ጀመረች። “…አንለያየም!... የኔን መልዐክ አምነዋለሁ!... አየለየኝም!… በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን ሞትም ቢመጣ አይለየኝም!... የኔ ፍቅር አይለየኝም!...” የዳሪክን ቃላቶች ስታስብ፣ ድምጹን ስታሰላስል …. ነፍሷ በውስጧ ሲሰክን፣ ስትረጋጋ ታወቃት።

አጠገቧ ያለውን አነስተኛ የጉዞ ብርድልብስ ስትለብስ… ትራስ አውጥታ ደገፍ ስትል…ዳሪክ ያላትን፣ የነገራትን ስታስብ… ከሰሞኑን ከነበረባት ድካም የተነሳ እንቅልፍ ሲወስዳት ደቂቃዎች አልፈጀም። ትላንት ጆ ካሮሎስ ሬይስን እስር ቤት አይተን ስንመጣ ባስ ውስጥ ስንገባ የወስዳትን አይነት ሰላማዊና ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥም እር.....................ፍ ብላ ገባች።

“…የሚበላ ነገር ምን ይፈልጋሉ? ቺክን ወይስ ሳንድዊች?...”

ቆይቶ ከጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ የቀሰቀሳት የአስተናጋጇ ድምጽ ነበር።

ከገባችበት ጠሊቅ እንቅልፍ የተነሳ ...ሳሌም ከእንቅልፏ ለመንቃትና ያለችበትን ለማወቅ ትንሽ ጊዜ ወሰደባት።  ምግብ የተደረደረበትን አነስተኛ ካርት (ጋሪ)  እየገፋች ያለችውን ቆንጆ የበረራ አስተናጋጅ ስታይ ግን በረራ ላይ መሆኗን አስታወሰች።

“…የሚበላ ነገር ምን ላቅርብሎት?...” የበረራ አስተናጋጇ በፈገግታ

ሳሌም አንቱ ተብላ ስትጠራ ሰምታ ሰለማታውቅ እሷም ፈገግ አለች።

“… ምን ያህል ጊዜ ሆነን? የት ነው ያለነው?....” ሳሌም ጠየቃቻት

“…አሁን ከሮም ወደ ዲሲ  እየበርርን ነው... ምግብ ይፈልጋሉ?...”

“…አልፈልግም!...” ሳሌም መሰለች “…ምንም መብላት አልፈልግም። ካለስቸገርኩሽ ዲሲ እስክንደርስ ባትቀሰቀሺኝ መተኛች ብቻ ነው የምፈልገው።…”

“…ችግር የለም አንቀሰቅሶትም!....” አስተናጋጇ ወደፊት መሄድ ቀጠለች።

ሳሌም አይኗን ጨፈነችና ማሰብ ጀመረች። “….ፍቅሬን አምነዋለሁ!... የኔ መልዐክ አይለየኝም!... አምነዋለሁ!... ያመንኩትን ደግሞ  አየዋለሁ!... ማመን ማየት ነው!...”   ይህንኑ ስታስብ፣ ስታሰላስል እንደገና ያው የቅድመ አይነት ሰላማዊ እንቅልፍ ወሰዳት።

********
ዛሬ፦ ሲያትል….

በረጅም ኮሪደር አልፈን፣
በአሳንሰር ውስጥ ወደታች ወርደን በመጨረሻ አንዲት የሆስፒታሉ  አነስተኛ ክፍል ውስጥ ደርሰን ቆመናል፦ሁለቱ ሃኪሞች፣ ሳሌምና እኔ።
👍286
“….ይህ የምናደርገው ነገር ደስ የሚል ነገር አይደለም። አስጨናቂ ነው።…” ሃኪሙ ሁለታችንንም እያየ  “…እርግጠኞች ናችሁ እዚህ ሆናችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ?...”

“…እኔ እርግጠኛ ነኝ!...የትም አልሄድም!...”  ሳሌም በሙሉ ልብ መለሰች “…ሳዬ አንቺ ከፈልግሽ መሄድ ትችያለሽ….”

ፈርቻለሁ። መፍራት ብቻ ሳይሆን ተርበትብቻለሁ። ግን ደሞ ሳሌምን ብቻዋን ትቻት መሄድ ፈጽሞ አልፈልግኩም። “…ችግር የለም እዚህ እሆናለሁ….” የሳሌም እጅ ጥብቅ አድርጌ ይዤ ቆምኩኝ።

ሲያወራን የነበረው ሃኪም “…እንግዲህ መጀመራችን ነው…” ብሎ ለሌኛው ሃኪም ምልክት ሲሰጠው ሃኪም …ዳሪክ ከአደጋው ቀን ጀምሮ ሲተነፍስበት የነበረውን ማሽን ሄዶ መነካካት ጀመረ። አንድ ነገር በነካ ቁጥር የዳሪክ ደረት በጭንቅ ወደ ላይ መነሳት፣ ለመተንፈስ መታገል ጀመረ። ደረቱ ወደ ላይ ከፍ ዝቅ እያለ…ትንፋሹ እየተቆረራጠ ለመተንፈስ ሲታገል… እጅግ ያሳዝናል። ትንሽ ቆይቶ ሃኪሙ ማሽኑን ሙሉ በሙሉ ሲያጠፉ… ሌላኛው ሃኪም ደግሞ በዳሪክ ጉሮሮ ወደ መተንፈሻ ቱቦው የገባውን ቀጭን ቱቦ ማውጣት ጀመረ። በዚህ ጊዜ ዳሪክ በከፍተኛ ጭንቅ ማሳል ….ያለማቋረጥ ሳል፣ ሳል፣ ሳል…ከአንገቱ ጭንቅላቱ እየተነሳ ሳል…ሳል… እንደመንፈራገጥ እያለ ሳል…. ከሳሉ ቀጥሎ የታነቀ በሚመስል ሁኔታ ሲያስል፣ ትንፋሽ ለማግኘት ሲጣጣር፣ ሲታገል ከዚህ በላይ ማየት ስላልቻልኩኝ እየተንቀጠቅጥኩኝ፣ እንባዬ እየወረደ …በተቃራኒው ወደ ግድግዳው ዞርኩኝ። ሳሌም በድን ሆና ቆማ ታያለች። ስዞር ደሞ አላመለጥኩም... ሌላ ነገር.... የዳሪክን የልብ ትርታ ከሚያሳየው ማሽን ላይ የልብ ትርታው ቁጥር ፊት ለፊት ማየት…. 
120 …
130….
143….
156…..ወደ ላይ እየወጣ ነው።

ከዛ ደሞ በፍጥነት ወደ ታች መውረድ ጀመረ።

145…
131…
117…
96…
78…..
55….
43…..
28….

 
ቁጥሮቹ …ቁጥሮች ብቻ አልነበሩም። የዳሪክን ዘላለማዊ ጉዞ የሚያውጁ የስንብት አሃዞች ነበሩ። ዳሪክ እየሄደ ነው….ዳሪክ ወደ ፍጻሜው እየመጣ ነው።

************

የመጀመሪያ ቀን፦ ሲያትል

ካ‘ዲስ አበባ - ዲሲ ተኝታ
እንደገና ከዲሲ - ሲያትል ‘ስክትደርስ እንዲሁ ስታንቀላፋ፣ ስተተኛ ነው የመጣችው፦ሳሌም።... ድክም፣ ድብር፣ ክፍት ብሏታል፦ሳሌም። ሲያትል ደርሳ ከአውሮፕላኑ ወርዳ ትንሿን ኬሪ ኦን እየጎተተች …በኤርፖርቱ ውስጥ ጥቂት እንደሄደች አበባ ይዞ የሚጠብቃት አባቷና አጃቢዎቹን ስታይ ወደ ‘ነሱ ማምራት ጀመረች። ጥቂት ርምጃዎች ተራምዳ በተቃራኒው አቅጣጫ ስታይ ግን በአይኗ ሊሆን ይችላል ብላ ያልጠበቅችው ነገር ተመለከተች።

************
ዛሬ፦ ሲያትል….

የዳሪክ የልብ ትርታ መውረድ ቀጠለ 2
7…
26…
25… .
.
.
.
.
25 ሲደርስ ግን ወደ ታች መውረዱን አቆመ።

25….ቀጥ
 
25…አትነቃነቅ የተባለ ይመስል አሁንም ዝም ብሎ ቆመ።

“…ምንድን ነው? ምን እየሆነ ነው?...” አንደኛው ሃኪም ጠየቀ

“….እኔ አላውቅም….” ሌላውም መለሰ

የልብ ምቱንና ሂደቱን የሚቆጣጣረው ማሽን “…ቲን!.. ቲን!...ቲን!...” እያለ 25… ላይ ረጅም ጊዜ ቆመ።
ሁላችንም ተገርመን፣ ተደንቀን ስናይ የልብ ትርታው ቆይቶ … 26
ቆይቶ 27.....
ቆይቶ 28…..ወደ ላይ መውጣት ጀመረ።

ትንሽ ቆይቶ 36…
ከዛ 51…..
64…ወደ ላይ መውጣት......።
72…ላይ ቆመ።

ሁለቱም ሃኪሞች እየሆነ ያለው ነገር ግራ አጋብቷቸው ወደ ዳሪክ ተጠግተው ምርመራ ጀመሩ። አንደኛው በስቴስስኮፕ ሳንባውንና ልቡን ካዳመጠ ቡሃላ “….በጣም ይገርማል!.... ሊታመን የማይችል ነገር..”… ወደ እኛ ዞረ “….የሚገርም ነው ...በራሱ… በሳንባው እየተነፈሰ ነው!...”

**********

የመጀመሪያ ቀን፦ ሲያትል

“…ኦ ማይ ጋድ
!…ኦ ማይ …ኦ ማይ ጋድ!…”  ሳሌም ያየችውን አላመነችም። ህልም ነው? እውነት ነው? የምታየው ነገር ምንድን ነው? ዳሪክ!...ዳሪክ!... ዳሪክ!... ፊት ለፊቷ ከሁለት ፈረንጆች ጋር ቆሟል። እሱም አበባ ይዞ። በትከሻዋ የያዘችው ቦርሳ ወደቀ። ኬሪ ኦን መሬት ተንከባላለ። ሳሌም ሮጠች። ሰውን ሁሉ እየገፈታተረች። ከሁለት አመት በፊት ያየችው አባቷ ጋር ሳይሆን ከሁለት ቀናት በፊት ያየችው ዳሪክ ጋር ሮጠች። ሮጠች።  ሮጣ ሄዳ ስትጠመጠምበት ዳሪክም ወደ ላይ ከፍ አድርጎ አነሳት። ለብዙ ደቂቃዎች ቤተሰብ ከቧት ዳሪክን ጥብቅ አድርጋ ይዛ በደስታ፣ባለማመን እንባዋ ወረደ…ተጠመጠመችበት። ።

“…እንዴት ሊሆን ይችላል? የኔ መልዐክ እንዴት?...”

“….አልለይሽም እመኚን ብዬሽ አልነበር የምወድሽ?...” ዳሪክም እንባው ባይኑ ሞልቶ

“…አዎ…” ብለኸኝ ነበር። “…አዎ…የኔ ቆንጆ!... የኔ ፍቅር!...” ቃላት ያጣች ይመስል

“…አሁን አመንሽኝ የምወድሽ?...”

“…አዎ…”

“… የምወድሽ ...አስታውሺ እሺ ማመን ማየት ነው።.. እመኚ ምንም ቢሆን፣ ሞት እንኳን ቢመጣ አልለየሽም።…”

“…አምናለሁ የኔ መልዐክ። የማየውን ብቻ አላምንም። ይልቅስ …የማምነውን ነው የማየው!...”

ከዳሪክ ጋር ከመጡት ፈረንጆች አንዱ ተጠግቶ ታዴን ጠየቀው “ what are they saying to eachother ( ምንድን ነው የሚባባሉት?)

ታዴ ልጁንና ዳሪክን እያየ  “…Believing is seeing (ማመን ማየት ነው)… የሚባባሉት...”

"...Seeing is believing! (ማየት ማመን ነው) ማለትህ ነው?..." ፈረንጁ ለማረጋገጥ ጠየቀ

“ …አይደለም  Believing is seeing! …ማመን ማየት ነው!... ማመን ማየት ነው!... የሚባባሉት። ...." ታዴ ደጋገመው።

ዙሪያቸውን የከበቡት ሁሉ ….ሁሉም ተገርመው ሁለቱን ከማየት ውጪ ሳሌምና ዳሪክ የሚያወሩት...የሚባባሉት...የገባው ወይም የተረዳ ሰው አልነበረም።

********
ዛሬ፦ ሲያትል….

“….ምን ማለት ነ
ው በሳንባው ይተነፍሳል ማለት…. አይሞትም ማለት ነው?...” በደስታ ጠይቅኩኝ

“…አዎ… እንደዛ ማለት ነው…” ገራ ከገባቸው ሃኪሞች አንዱ መለሰ

የምለው ጠፍቶኝ…በደስታ ሲቃ ይዞኝ…ወደ ሳሌም ዞርኩኝ። “….ሴለም!... ሲሊ! ...አይሞትም!... ዳሪክ አይሞትም!...”

በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ዝም ያለችው ሳሌም፣ ርግት ያለችው ሳሌም፣ ጸጥ ያለችው ሳሌም በትላልቅ አይኖቿ እንባ ሲሞላ ያየሁ መስለኝ። ባለችበት በጉልበቷ ተንበረከከችና እጇን ወደ ላይ አነሳች “…ህይወትን የምትሰጥ…ስታንፋስን የምታረዝም ጌታ ሰለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ።…”

ከዛም ከተንበረከከችበት ተነሳችና ወደ ዳሪክ ቀረብ ብላ እንደገና እንባ በሙሉ አይኖቿ ዳሪክን ተመለከተችው።  በ‘ርጋታ፣ ቀስ እያለ ይተነፍሳል.. በራሱ፣…በሳንባዎቹ... ሳሌም እጆቹን ጥብቅ አድርጋ ያዘቻቸው፣ ቀጥላም እጆቹን ለቀቀችና በተኛበት ጥብቅ አድርጋ አቀፈችው። ከዛም መናገር ጀመረች “…የኔ መልዐክ!… የኔ ቆንጆ!… የኔ ፍቅር!  ቃልህን ስለጠበቅክ፣ አልለየሽም እንዳልከኝ እንዲሁ ስላልተልየኸኝ አመሰግናለሁ። ማመን ማየት ነው። ዛሬ አምኛለሁ። ያመንኩትንም አይቼዋለሁ። ...ካሁን ቡሃላም ... አልፈራም ...
👍354
አምናለሁ።  ገና የማምነውን ብዙ ነገር አያለሁ። ማየት ማመን አይደለም ይልቅስ 'ማመን ማየት ነው! ” ሳሌም እንባ በሞሉ አይኖች….ግን ደሞ በደስታ በስሱ ፈገግ ብላ።

“ ..What is she saying to him (ምን እያለችው ነው?)” በሁኔታዋ ልቡ የተነካው ሃኪም ጠየቀኝ

“..Believing is seeing (ማመን ማየት ነው!) እያለችው ነው….” በደስታ ከእንባዬ ጋር እየታገልኩ

“…Seeing is believing! (ማየት ማመን ነው!) ማለትሽ ነው?....” ሃኪሙ ግራ ገብቶት

“…አይደለም… እያለችው ያለችው …believing is seeing (ማመን ማየት ነው!)…” አረጋገጥኩለት።

ይህንንም ለሃኪሙ እየነገርኩትም እዚህ ስፍራ ላይ እሰማዋለሁ ብዬ ፈጽሞ ያልሰማሁትን ድምጽ ሰማሁ.......ተዐምር!!!!!!
*
*
ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

(…የዚህ ክፍል የታሪክ ግርጌ ማስታወሻ፦ የዳሪክ ወደ አሜሪካ መምጣት ራሱ ተአምር ሲሆን የረዱትም በዚህ ሃገር የሚኖሩትና በርዳታ ድርጅቱ በኩል ስፕንስር ያደረጉት መልካም ሰዎች ናቸው። ከወራት በፊት ሳሌም አሜሪካን ልትሄድ መሆኑን ልትነግረው ስትል እኔም የምነግርሽ ነገር አለ ብሏት ነበር። ዳሪክ ለሳሌም ሊነግራት የነበረው ወደ አሜሪካ ሲያትል ሊሄድ እንደነበረ ነው።  ሁለቱም ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ሲያውቅ ለምን ስርፕራይዝ አላደርጋትም ብሎ አሰበ። የሚያመጡትም ቤተሰቦች ተስማሙ። ሁሉም ነገር ተዘጋጀ። ዳሪክ አንድ ቀን ሲቀረው የሄደው ወደ አሜሪካ ነው እንጂ ወደ ኮሌጅ አልነበረም። ሰርፕራይዝ…ሰርፕራይዝ….)
👍3913
የፍቅር ‘ርግቦች
ክፍል አስራ ስድስት፦ የፈውስ መንገድ!
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር

“ የ… ምወድሽ!” የሰማሁትም የአምስት ፊደላት ውህደት ውጤት የሆነውን ይህንን አንድ ቃል ነው። “የ…ምወድሽ!”

ይህ ቃል የወጣውም ከሳሌም በስተቀር ሁሉም ተስፋ በቆረጠበት፣ ከቀናት በፊት ሊሞት ከተወሰነበትና ወደ ዘላለማዊ ጉዞው ሊሄድ እዚህ ክፍል ውስጥ በትንሽ የሆስፒታል አልጋ በነርሶች እየተገፋ ከመጣው፣ ከጠይሙ፣ ክርዳዳ ጸጉር ካለው፣ ከሳቂታው፣ ከሳሌም ‘ጠባቂ መልዐክ’፣ ከ ‘ብቸኛው ቅርንጫፍ’፣ ብዙ ጊዜ አልሞትም ብሎ ከታገለው ከ ‘ትንሹ ተዐምር’፣ ፍቅሩን ሳሌምን ‘የምወድሽ’ ብሎ ከማይጠግበው ከዳሪክ አንደበት ነበር።

ሳሌም ዳሪክን አቅፋ ተኝታበት ከነበረው ደረቱ ላይ ቀና ስትል እኔም አይኖቼ በድንጋጤ ይሁን በደስታ የሆነ በማላውቀው ስሜት ተከፍተው አንድ እርምጃ ወደፊት ቀርብኩና ተለመከትኩ። ምን ተመለከትኩ? ተ-ዐ-ም-ር!! የሳሌምን ትላልቅ ውብ አይኖች የሚያዩትን ከሰመመንና ከጥልቅ እንቅልፍ የወጡ፣የተከፈቱትን የዳሪክ አይኖች፦ ተዐምር!!

((((እነዚህ አራት አይኖች እንዴት ነበር የሚተያዩት?  እንደዚህ ነው … ዝም ብለው ይተያያሉ።  ዳሪክ የሳሌም አይን፣ ሳሌም ደሞ የዳሪክን አይን በስስት ይመለከታሉ። ያያታል፣ ያያታል ደሞ አሁንም ያያታል። አይኗን አልፎ፣ ውስጧን ሰርስሮ፣ በዐጥንቶቿና በጅማቶቿ ላይ ተንሸራቶ፣ በልቧ ትርታዎች ላይ ተሰፈንጠሮ ፦ አዎ ነፍሷ ላይ፣ ነፍሷ ላይ የሚደርስ ‘ስኪመስል ያያታል።

   …ታየዋለች፣ታየዋለች፣ አሁንም ደግማ ታየዋለች። አይኑ ውስጥ የማያቋርጥ ውብ ትዕይንት እንዳለ፣ አይኑ የበጋ ላይ የውቂያኖስ ውብ ውሃ፣የአይኑ ብሌን በውቂያኖሱ ላይ የምትጠልቀውን ቆንጆ ጸሀይ እስኪመስለኝ ድረስ ታየዋለች።))))

ድምጹን ስትሰማና የተከፈቱትን የዳሪክ አይኖች ስታይ፣ ሳሌም የዳሪክን የቀኝ እጅ በሁለት እጆቿ ጥብቅ አድርጋ እንደያዘች ቀስ ብላ ተነሳችና የአልጋው ጠርዝ ደገፍ ብላ ቆመች።

ሳሌም በፍርሃት አልሮጠችም!
ሳሌም ድንጋጤ አይታይባትም!
ሳሌም መገረምም መደነቅም አልሞላባትም!
ሳሌም አሁንም በፍጹም እርጋታ ውስጥ ናት!
ሳሌም ሌላ ክፍል ውስጥ የሚጠብቃት ዳሪክ ጋር ክፍል የገባች ነው የምትመስለው!
ሳሌም በቃ በልቧ ውስጥ በየቀኑ ያየችውን ነገር መልሳ ያየች ነው የምትመስለው!

በፍጹም እርጋታ  የአልጋ ጠርዝ ተጠግታ.. ቆማ… ዳሪክን በተኛበት ወደታች… የተከፈቱ አይኖቹን እያየች ፍዝዝ፣ዝም ብላ ቆመች!!! ስታየው ….ዝም ብላ ስታየው…ሾክ ውስጥ የገባች፣ መናገር የተሳናት… የምትለው የጠፋት፣ አንደበቷ የተሳሰረ ትመስል ነበር።

ወዲያው ደሞ …በትላልቅ አይኖቿ ውስጥ ግን እንባ ሲሞላ ይታየኛል። ይህን ጊዜም ከዶክተሮቹ አንዱ ወጥቶ የጠራቸው ታዴና ሌላው ፈረንጅ ተከታትለው ክፍሉ ውስጥ ገብተው እነሱም ይህንን ‘ተዐምር’ ይመለከቱ ጀመር፦ አይኖቻችውንና አፎቻችውን በሰፊው ከፍተው።

ዳሪክ ያልያዘችውን እጁን ዘረጋላትና “…የምወድሽ...” እንደገና ድካም በያዘው ድምጽ ጠራት።

እንደገና ድምጹን ስትሰማ አልቻለችም። አልጋው ላይ ቁጭ አለችና “…ወ…….ይዬ የኔ መልዐክ!!! …ወ.…ይዬ የኔ ፍቅር!!! ” ቃላት የትግሏን ከምላሷ ወጡ።

ዳሪክ እጆቿን ጥብቅ አድርጎ ይዞ፣ አይን አይኗን እያየ ያወራት ጀመር። “…የምወድሽ እሰማሽ ነበር። …ተኝቼ፣ በለምለም መስክ ላይ በሰመመን ውስጥ ሆኜ ሁሌም እሰማሽ ነበር የ..…ምወድሽ! መጽሀፍ ስታነቢልኝና ስትተርኪልኝ እሰማሽ ነበር የ…..ምወድሽ!! ስትጸልይልኝ እሰማሽ ነበር የ…ምወድሽ!! የቀኑን ውሎሽን ስታወሪልኝ በደንብ እሰማሽ ነበር የ…..ምወድሽ!!  ‘ጥዬሽ አልሄድም ብለህ ቃል ገብተህልኛል አትሂድብኝ’ እያልሽ ቃል ኪዳኔን ስታስታውሺኝ ጥርት ብሎ ይሰማኝ ነበር የ…..ምወድሽ!!! እኔ ‘ተስፋ አልቆርጥም፣ አምናለሁ’ ስትይ፣ ‘ማመን ማየት ነው!’ እያልሽ ስትነግረኝ እሰማሽ ነበር የ…..ምወድሽ። አባቴ ‘ፍቅሬን አትቀማኝ፣ አትወሰድብኝ’ እያልሽ ስትማጸኚ እሰማሽ ነበር የ..…ምወድሽ! ስለ ማንስቺተር ኳስ ጨዋታ ስትነግሪኝ እሰማሽ ነበር…የ…ምወድሽ! በማለዳ ፊቴን ስትዳሺኝ፣ ጸጉሬን ስታበጥሪልኝ፣ እጆቼን ይዘሽ ሙቪ ስታይ፣ ሰውነቴ ላይ ከኤሌትሪክ ንዝረት በላይ ይታወቀኝ ነበር የ……ምወድሽ!!! ካ’ጠገቤ በየቀኑ ስታድሪ፣ ‘ጥዬህ አልሄድም’ ስትይ ይሰማኝ ነበር የ…ምወድሽ። እሰማሽ ነበር… የምወድሽ። በደንብ እሰማሽ ነበር …የ…ምወድሽ …ሁሌም እ……..ሰማሽ ነ..በ…ር የ…ምወድሽ።…” ዳሪክ እዚህ ጋር ድምጹ በሳግና በለቅሶ ተቆራረጠበት።

ሳሌም እንባዋ ባ’ይኗ ሲሞላ አይቼ አውቃለሁ። እንባ ሲታገላት ጥቂት ጊዜ አስታውሳለሁ። በሙላት ስታለቅስ ግን በጭራሽ አላየሁም። ዛሬ ግን አልቻለችም። የጸና ፍቅሯን፣የጠንካራ እምነቷንና የፍጹም ይቅርታዋን ፍሬ ስትመለከት በቃ አልቻለችም። ሁላችንም ተስፋ ቆርጠን እንደ ሞኝ በተመለከትናት ጊዜ ሳሌም ከጸና ፍቅር፣እምነትና የይቅርታ አለት ተራራ ላይ አልወርድም አለች። የዚህ ሁሉ ውጤት ይህ ነው፦ የዳነው ዳሪክ። የዚህ ሁሉ ፍሬ ይህ ነው፦ የተፈወሰው ዳሪክ። ፍቅር፣ እምነትና ይቅርታ አንድ መንገድ አላቸው። ይህም መንገድ የፈውስ ጎዳና ይባላል፦ የፈውስ መንገድ!!! ሁላችንም ማየት አልቻልንም እንጂ ሳሌ ፍቅር፣እምነትና ይቅርታ በሚባል ‘የፈውስ መንገድ’ ላይ ነበረች፦ ዳሪክንም በዛ የፈውስ መንገድ ላይ ተጉዛ መልሳ አመጣችው።

የዳሪክን አንገት ጥብቅ አደርጋ ይዛ አቅፋ፣ እንባዋ ከትላልቅ አይኖቹ መንታ መንታ ሆኖ እየወረደ፣ ከልቧ እየተንቀጠቀጠች ታለቅስ ጀመር። በመጀመሪያችቹ ጥቂት ደቂቃዎችም እራሷን የገለጸችበት መንገድ ይህ ነበር። 
  
“…አ..…ውቃለሁ የኔ መልዐክ!... አ..…ውቃለሁ የኔ ፍቅር!....አ…..ውቃለሁ ትሰማኝ እንደነበር በደንብ አሳምሬ አውቃለሁ…!...” እንባዋ እየወረደ ከልቅሶ ጋር እየታገለች እቅፍ አድርጋ ይዛው።

እሱም ጥብቅ አድርጎ ያዛት።

መተቃቀፋቸው፦እውነተኛ ፍቅር ነው። መያያዛቸው፦ ናፍቆት ነው ። የተጠላለፉ እጆቻችው፦ የዋሃት መውደድ ነው።

ሊያላቅቃቸው የሚሞክር ወየውለት!

ተቃቅፈው ሳሌም እያነባች ዳሪክ እያባባላት ለረዥም ጊዜ ቆዩ።

“…የምወድሽ ታስታውሺያለሽ?.. ምን ያህል ትወደኛለህ?.. ብለሽ ስትጠይቂኝ …ፍቅሬ መለኪያ የለውም ስልሽ…” እንደተቃቀፉ ጠየቃት

“…አዎ በትክክል አስታውሳለሁ የኔ ውድ… የኔ መልዐክ!...” ቀና ብላ እያየየችው።

“….የምወድሽ ተሳስቼ ነበር። ፍቅሬ መለኪያ አለው። የፍቅሬ መለኪያ ያንቺ ልብ ነው። ያንቺን ልብ ያህል ነው የማፈቅርሽ …የምወድሽ። ልብሽ እጅግ ትልቅ ፣ ሰፊና ብርቱ ነው…የምወድሽ። የተሞላው ደሞ በፍቅር፣በእምነትና በየዋህነት ነው…የምወድሽ።…እኔም የማፈቅረሽ የልብሽን ያህል ነው። የፍቅሬ መጠን…የፍቅርሽን ስፋት፣ የእምነትሽ ከፍታና የየዋህነትሽ ጥልቀት ድረስ ነው… የምወድሽ።….የፍቅሬ መለኪያው መልካሙ ልብሽ ነው…የምወድሽ።”

እንደገና ላይላቀቁ ጥብቅ ተደራርገው መተቃቀፍ፦ ዳሪክና ሳሌም።

የሁለቱን ልጆች…በተለይ የሳሌምን ሁኔታ….ያየ በደስታ አለማልቀስ አይቻለውም። እንባዬ በምን ይቁም? የኔም። ቀና ብዬ ሳይ ታዴና የሚያወሩትን ያልተረዱት ሃኪሞችና ፈረንጁም ሳይቀር  እንባቸውን ከአይኖቻቸው በጣቶቻቸው ይጠራርጋሉ።

ወዲያውም ማንም ሳይጠብቀው ታዴ እያለቀሰ መጥቶ ተንበረከከና የሳሌምን ጉልበት ያዘ “ማ…ሪኝ ልጄ! ይ.…ቅር በይኝ ሴሊና በፍቅርሽ ላይ በ.…መጨከኔ …ማ..ሪኝ …ይ…ቅር…”
👍3610
“አባቴ! የ..መወድህና የማከብርህ አባቴ” ሳሌም አቋረጠችውና ከተንበረከከበት ታዴን አነሳችው “ አባቴ መቼም ቢሆን መቼም አንተ ላይ ቂም አልይዝም። በጭራሽ እሺ!” ሳሌም አረጋገጠችለች “ መቼም!.…በጭራሽ!” ጥብቅ አድርጋ አቀፈችው።

የዳሪክና የሳሌም ፍቅር …ጥላቻን፣ቂምን፣ ይቅር አለማለትን እየጠረገ ሊያጠፋ ከዚሁ ክፍል የጀመረ መሰለኝ።
*
*
ለሚቀጥሉት ብዙ ደቂቃዎችም ዳሪክና ሳሌም እንደገና ሳይላቀቁ… አንዴ ሲተያዩ፣ አንዴ ሲተቃቀፉ…እኛም በዙርያቸው አጃቢዎችና ምስክሮን ሆነን ቆየን።  በመጨረሻም ሃኪሞች የተለያየ ምርመራ ለዳሪክ መደረግ እንዳለበት ነግረውን ከምድር ቤቱ ወደ ላይኛው የሆስፒታሉ ክፍል ሁለት ነርሶች እየገፉ ሲወስዱት በሆስፒታሉ ኮሪደሮች ላይ ነርሶች፣ ሃኪሞችና ለሌሎች የሆስፒታሉ ሰራተኞች በጭብጨባ፣ በደስታ ጩኸትና በፉጨት ተቀበሉን። ትዕይንቱ እጅግ በጣም ደስ የሚል ነበር። ግማሹ ከዳሪክ ጋር ሰልፊ ይነሳል፣ ሌሎች ደሞ በስልኮቻቸው ፎቶና ቪዲዮ ይቀርጻሉ።

ግርግሩና ፌሽታው አልቆ፣ ዳሪክም ለምርመራው ገብቶ ሳሌምና እኔ አብረን በእንግዳ መቀበያ ውስጥ ቁጭ ብለን

“…ሴለም…” ሳሌምን ጠራኻዋት

“…ወዬ ሳዬ…”

“….ትዝ ይልሻል ቅድም ዳሪክን ሃኪሞቹ ሊወስዱት ሲሉ ማሽኖቹን ሊነቃቅሉ…?”

“…እህ…. እንዴት እረሳዋለሁ ሳዬ…”

“…ከመሄዳችን በፊት ለብቻሽ ሆነሽ ከዳሪክ ጋር ምን እያደረግሽ ነበር? ምን እያልሽው ነበር?...”

ሳሌም የምወደውን ስስ ፈገግታዋን መገበችኝ። “..ሳዬ…”

“…ወዬ…”

“…በቃ ምንም አያመልጥሽም አይደል?...” እየሳቀች

“….ምንም አያመልጠኝም…” አብሬ እየሳቅኩ

ሳቃችንን ተከትሎ … ነገረችኝ።

የዳሪክ ማሽኖች ሊነቀሉ፣ ዳሪክን ወደ ሞት ልናሰናብት ጊዜው ሲቃረብ ...ሁላችንም ከወጣን ቡሃላ ሳሌም ዳሪክ አጠገብ ሄዳ እጆቹን ያዘች። የተከደኑ አይኖቹን አየች። ከዛም ነገረችው። ነገረችው …እንዲህ ብላ

“….የኔ መልዐክ አባቴን ለመንኩት። ፍቅሬን አትውሰደብኝ አልኩት። ግን አልሰማኝም። ሃኪሞቹን ለመንኳቸው። መልዐኬን አትቀሙኝ አልኳቸው…ግን አልሰሙኝም። አሁን የቀሩኝ፣ የሚሰሙኝና የማምናቸው ሁለት ብቻ ናቸው፦ ጌታና አንተ። ጌታን ጠይቄዋለሁ። እንደሚሰማኝ በሙሉ ልቤ አምናለሁ። ሃኪሞቹ ድምጽ አይሰማም ቢሉኝም እኔ ግን እንደምትሰማኝ አምናለሁ። ስለዚህ ….አንተን እጠይቅሃለሁ፣ እለምንሃለሁ፣ ‘…አትሂድብኝ፣ አትለየኝ የኔ መልዐክ!...  ካስታወስክ ‘..አትለየኝ…’ ካልሽኝ ‘…አልለይሽም…’ ብለኸኛል። ስለዚህ እልሃለሁ ‘…አትለየኝ!...’ ….አባቴ ከጥቂት ቀናት በፊት ጥያቄ ጠይቆኝ ነበር ‘…  ከዳሪክ ብትለይ ምን ትሆኚያለሽ?   ...’  ብሎ ….ካንተ ብለይ የምሆነው ይህን ነው። ብትለየኝ የምለየው በሚያስገርምና በየደቂቃው በሚያድግ ፍቅር ከሚወደኝ ልጅ ነው ….የምለየው። ብትለየኝ የምለየው ..በሚገርም ሁኔታ ሴትነቴን፣ እኔነቴን ከሚያከበር …የአርዲን እድሜ እንኳን ቢሆን እጠብቅሻለሁ ካለኝ ልጅ ነው …የምለየው።…. ብትለየኝ የምለየው ሁለቱን ፍርሃቶቼ በደቂቃ ከልቤ ካባረረው ልጅ ነው የምለየው። …ስለዚህ ከተለየኸኝ ሶስት ነገር ይሆናል። ..ከተለየኸኝ ፍቅር በውስጤ ይሞታል። የሴትነት ክብሬ ይወድቃል። ከአውሮራ ድልድይ ላይም ወደ ታች …ወደ ፍርሃቶቼ እወድቃለሁ። የሚሆነው ይህ ነው የኔ ቆንጆ። ይህ ነው የሚሆነው የኔ መልዐክ…. ስለዚህ እባክህን አትለየኝ፣ አትሂድብኝ።…”

በነዛ ደቂቃዎች ሁላችንም ውጪ ሆነን ድምጿን አውጥታ ሳሌም ለዳሪክ የነገረችው ይህንን ነው። ….ሳሌም ይህንን ነው ያለችው። ዳሪክም ያለችውን ሰምቷል። አለተለያትም።

የሳሌምና የዳሪክ ፍቅር፣ መተማመንና የነፍስ ትስስር ለሰው ልጅ አእምሮ የማይገባና ግራ የሚያጋባ ነበር።

እንግዲህ እንዲህ ሆነ!

ከሁለት መቶ አርባ ቀናት ቡኃላ…

ከአምስት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ሰዓታት ቡኃላ…

ከሶስት መቶ አርባ እምስት ሺህ ስድስት መቶ ደቂቃዎች ቡኃላ.…

ሰመመን ውስጥ ከገባ ስምንት ወራት ሊሞሉት ጥቂት ቀናት ሲቀሩት…

የዳሪክ አይኖች ተከፈቱ።

በዙሪያቸው ሆነን ላየነውም ተዐምር፣ ለሚሰማውና ለሚያነበውም ሁሉ ደስታናን ሃሴትን ማዕበል ሊሰጥ… ከዛች የሆስፒታል ትንሽ ክፍል ውስጥ ጀመረ።
*
*

ከሁለት ሳምንታት ቡኃላ

ጥንካሬው የተመለሰለት ዳሪክና ሳሌም በሲያትል ሰሜናዊ ክፍል የሚገኝ አንድ ሌላ ትንሽ የስታርባክስ ትንሽ ካፌ ውስጥ መጡ።

እንግዲህ ዳሪክና ሳሌም መጡ፦ ከምሽቱ አስር ሰዐት አካባቢ። ከየት መጡ?እንዴት መጡ? ማንም አያውቅም። መጥተው በካፌው ውስጥ በአንድ ጥግ ባሉት ወንበሮች ላይ ተቀመጡ።

ሳሌም ሻይ አዘዘች።

ዳሪክ ካርሜል ማኪያቶ።

ለሚቀጥሉት ብዙ ወራትም እዛ ካፌ ውስጥ መጥተው ይሄዳሉ።  በብዙ መጥተው በብዙ ይሄዳሉ።

   የፍቅር ወፎች ናቸው ፦ ዳሪክና ሳሌም። የማይለያዩ… በአየር ላይ፣  ከደመናት በላይ ተንሳፈው ማንም በማይደርስበት አየር ክልል የሚበሩ ወፎች። አሁን በአየር ላይ ያሉት እነሱ ብቻ ናቸው። ዙሪያችውን አያዩም። አካባቢውን አይሰሙም። እሱ እሷን ያያል። እሷ እሱን ታያለች። እሱ እሷን ይሰማል። እሷ እሱን ትሰማለች።  ካፌው ውስጥ ተስተናጋጅ ቢጣላ (ቢንጫጫ)፣ ብርጭቆ ቢከሰከስ፣ ወንበር ቢሰባበር፣ ማንኪያ ወድቆ ቢንኳኳ (ኳኳኳኳ…ኳኳ...ኳ.ኳ.ኳ.ኳ…ኳ) እያለ  መሬት ለይ ቢሄድ) እነሱ ግን በራሳቸው አለም ውስጥ ናቸው።

  ደሞ የፍቅር ከዋክብቶች ናቸው፦ ዳሪክና ሳሌም። ሰፊ በሆነው የፍቅር ህዋ ውስጥ ከተለያዩ ‘ጋላክሲዎች’… የተገናኙ በራሪ የመዋደድ ከዋክብቶች። ሁለቱም ሲበሩ አንድ ቀን ተገናኙ።  …ተገናኙ …. ተያዩ … መተያየታቸውንም ሊያቆም የሚችል ነገር ጠፋ። እሷ… እሱን … እሱ…. እሷን ብቻ ለማየት የተፈጠሩ ይመስል ይተያያሉ። አሁን በህዋ ውስጥ ያሉት እነሱ ብቻ ናቸው። ሰው ቢሮጥ፣መኪና ቢበር፣ባቡር በድምጹ ቢያንባርቅ፣ የፖሊስ መኪና ሳይረን (ኡኡኡ…ኡኡኡኡኡ..ኡኡኡ….ኡኡ……) እያለ ቢከንፍ አይሰሙም፣ አያዩም።

…የእነሱ አለም ሶስት ማዕዘን ነው።

አንደኛ ጎን፦ ዳሪክ

ሁለተኛ ጎን ፦ ሳሌም

ሶስተኛ ጎን፦ አምስተኛው ጎዳና

…ደሞ ሌላ ሶስት ማዕዘን ነው።

ካፌው ፦ የፍቅራቸው መቅደስ

ጥግ ያሉት ወንበሮች፦ የፍቅራቸው ቅድስት

ሻይና ማኪያቶ፦ የፍቅራቸው ቅመም ነው

…ደሞ ሌላ ሶስት ማዕዘን ነው።

የዳሪክ አይኖች፦ ሳሌምን ያያሉ

የሳሌም አይኖች፦ ዳሪክን ያያሉ

የሌሎች አይኖች፦  ደሞ ሁለቱን ያያሉ

የፍቅር ዋኖሶች፣ የፍቅር የዋህ ርግቦች የተለየ ነገር አላቸው። የበራ፣ የጠራ፣ የነጠረ አፍላ ፍቅር።

   ካፌው ውስጥ አንዳቸው ቀድመው ደርሰው … ከዛ ሲገናኙ ማየት ነው፦ የፍቅር ዋኖሶችን። ሳይገናኙ በፊት ክረምት ነው፦ በሁለቱም ፊት ላይ። ዶፍ ዝናብ የሚዘንብበት፣ በረዶና ጠል የሚወርድበት፣ ቅዝቃዜው ጆሮን የሚቆርጥበት፦ ድቅድቅ ክረምት። ሳይገናኙ ለሁለቱም ጨለማ ሃምሌ ነው። ሲገናኙ ጸሐይ በፊታቸው ላይ ትወጣለች። የፊታቸው ሰማይ ጭጋጉ ይጠፋል። ይጠራል። ሰማያዊ ይሆናል። ሲተያዩ ጸሐይ ነው፦ ብርሃን፣ ደስ የሚል የፍቅር ብርሃን በሁለቱም ፊት ላይ ያለማቋረጥ ይወርዳል።

የፍቅር ዋኖሶቹ ፍቅር ሲገላለጹ ንጹህ ናቸው። በዚህ “ፍቅር” የሚለው ቃል ትርጉም ሚዛኑ ተንጋዶ በራስ ወዳድነትና በእኔነት በሚገለጽበት አለም ላይ እንዴት እነሱ በታላቅ ንጽህና መዋደዳቸውን አሳዩ? እኔ አንጃ። እኔ አላውቅም።

አንዳንድ ቀን …
👍294🥰2
ዳሪክ ያወራታል ሳሌምን። ሳሌም ትስቃለች። አይኗ፣ ፊቷ፣ጥርሷ ይስቃል። በሳቋ የሚያምሩት የእጆቿ ጣቶች አብረው የሚደንሱ፣ እግርቿ የሚያጅቡ ይመስላሉ። እንባዋ እስኪፈስ ትስቃለች። ስትስቅ ጸጥ ያለው ፊቷ የበለጠ ይበራል። ጸጥ ያለ ውቂያኖስ ላይ ጸሐይ በማለዳ ብቅ ስትል የምትሰጠውን ውበት ያህል ፊቷ ይውባል፣ ይበራል።
 
ዳሪክ ፈርዶበት ሳቂታ ነው። ሳሌም ስትስቅ ደግሞ  የዳሪክ ሳቅ ሞልቶ፣ በዝቶ ይትረፈረፋል። መናገር የፈለገውን ነገር መናገር ስኪያቅተው ድረስ ይስቃል፣…. ይስቃል። ከርግቦቹ ንጹህ ፍቅር የሚፈሰው የደስታ ዝናብ  በሳቆቻቸው ድምጽ ተሳፍሮ ለኛም ልብ ካፊያው ይደርሳል። የነሱ ደስታና ሳቅ በዙሪያችን ያለነውን የእኛን ነፍስ ሳይቀር ፍስሃ ይሆንላታል። .ሳያውቀው ልባችን ጮቤ ይርግጣል። ሳናውቀው ጥርሶቻችን ከከናፍርቶቻችን መሃል ብቅ ይላሉ ይላሉ … ፈገግ።

አንዳንድ ቀን…

ዝም ይላሉ። በቃ ዝም ብለው ይተያያሉ። ሰው ዝም ብሎ፣ ቃል ሳያወጣ ይነጋገራል? አዎ። ዳሪክ የሳሌም አይን፣ ሳሌም ደሞ የዳሪክን አይን በስስት ይመለከታሉ። ያያታል፣ ያያታል ደሞ አሁንም ያያታል። አይኗን አልፎ፣ ውስጧን ሰርስሮ፣ በዐጥንቶቿና በጅማቶቿ ላይ ተንሸራቶ፣ በልቧ ትርታዎች ላይ ተሰፈንጠሮ ፦ አዎ ነፍሷ ላይ፣ ነፍሷ ላይ የሚደርስ ‘ስኪመስል ያያታል።

   …ታየዋለች፣ታየዋለች፣ አሁንም ደግማ ታየዋለች። አይኑ ውስጥ የማያቋርጥ ውብ ትዕይንት እንዳለ፣ አይኑ የበጋ ላይ የውቂያኖስ ውብ ውሃ፣የአይኑ ብሌን በውቂያኖሱ ላይ የምትጠልቀውን ቆንጆ ጸሀይ እስኪመስለኝ ድረስ ታየዋለች። ሻይና ማኪያቶ ይረሳል። ይቀዘቅዛል። የፍቅር ዋኖሶች በመተያየት ያወራሉ፣ በመተያየት ይጫወታሉ፣ በመተያየት ይግባባሉ።

አንዳንድ ቀን…

ዳሪክ እጁን ዘርግቶ ሳሌምን ይዳስሳታል፣እጇን ይዞ በዝግታ እየደሳሰ ጣቶቿን በታላቅ ቀስታ ይንካካቸዋል። አደሳሱ፣ አነካኩ አዲስ ሙዝቃን አዲስ በተገኘ ፒያኖ የሚጫወትን ዘማሪ ያህል ነው። እኛ ደሞ ታዳሚዎች ነን።

….ሳሌም በተመሳሳይ እጁን ትነካካዋለች፦ በዝምታ፣ በስሱ ። ውብ ጣቶቿን በአይበሉባው፣ በቆዳው ላይ በርጋታ ስታስኬድ.. ከአልማዝ፣ ከእንቁና ከሩቢ ውህድ የተሰራ በአለም ያለታየ አዲስ የከበረ ድንጋይ ያህል (…የኔ ብቻ እጅ… የኔ ብቻ…) እያለች የምትነካካው የምታየው ይመስለኛል።

ረጅሙ መንገድ!....

   ረጅሙ መንገድ….ለሁለቱ የፍቅር ርግቦች ረጅሙ መንገድ የትኛው ነው? ምን ያህል ነው? ከሃምሳ ሜትር የሚበለጥ አይመስለኝም። ከካፌው እስከ አውቶቢስ ፌርማታው ያለው ነው። ሃምሳ ሜትር ለ‘ነሱ ሃምሳ ጊዜ የምድርን ክበብ የመዞር ያህል ነው። ርግቦቹ የአለምን ግማሽ ያህል የሚሄዱ ይመስል ያዘግማሉ። በብዙ ግፊያ ውስጥ የሚሄዱ ይመስል እርምጃቸውን ይቆጥራሉ። በጫማቸው ልክ ይራመዳሉ። እጅ ለእጅ ተያይዘው ይቆማሉ፣ ደሞ ዝግ ብለው (…ኤሊን “…ደሞ ከኔ የባሳም አለ እንዴ?...” ) ብላ በሚያስደምማት አይነት ጉዞ ይጓዛሉ። ለምን? እንዳይለያዩ እኮ ነው።

አይደረስ የለም ባስ ፌርማታው ላይ ሲደርሱ ደሞ ይቆማሉ።

በመስመሩ ላይ የሚመጣው አንድ አውቶቢስ ነው። ባስ መጥቶ ይቆማል። ሹፌሩ ያያቸዋል።

የሚሄዱ ይመስላሉ። ትንሽ በትዕግስት ይጠብቃል። ።

“…ትሄዳላችሁ?...” ሹፌሩ ይጠይቃል

ዳሪክና ሳሌም አይሰሙም። ቆመው ያወራሉ። ወይም ዝም ብለው ቆመው ይተያያሉ። አንዳንድ ጊዜ ሳስበው ወሬ የሚመጠላቸው፣ በጥልቅ መተያየት የሚፈልጉት በዚህ በመለያያቸው አስራ አንደኛ ሰአት ላይ ይመስላል።

ጥሏቸው ይሄዳል። ሌላ ባስ ይመጣል። ይሄዳል። ሌላ ይመጣና ይሄዳል። ደሞ ሌላ ይመጣል።

ሳሌም ወደ ባሱ መንገድ ትጀምርና ዳሪክ ደሞ ሊያወራት ይጀምራል። ትመለሳለች። ደሞ እንደገና ተያይዘው፣ ቆመው ወሬ ይጀምራሉ። ተለያዩ ሲባል፣ ሲሳሳቡ፣ ሲያወሩ ረዥም ጊዜ አልፎ በመጨረሻ ሳሌም አውቶብሱ ውስጥ ገብታ ጉዞ ይጀምራል።

ዳሪክ ቆሞ ሳሌም የገባችበትን ባስ ያያል። ህጻን ልጇን ላይመለስ እንደተወሰደበት ወላጅ፣ ለመጨረሻ ጊዜ እንደምትታይ መቼም ተመልሳ እንደማትመጣ የጸህይ ጥልቀት ቆሞ ያያል። ባሱ ከዐይን እስኪሰወር አሻግሮ ይመለከታል። ከዛ በተቃራኒው አቅጣጭ ቀስ እያለ መጓዝ ይጀምራል። ቀኑ መሽቷል። ጸሐይም ጠልቃለች።

ረጅሙ ጊዜ!...

ረጅሙ ጊዜ የትኛው ነው? ፍቅሮቹ ተለያይተው እስከሚገናኙ ድረስ ያለው ነው።
 
  …ሲለያዩ ሰአታት ይቆጠራሉ፣ ደቂቃዎች ይመነዘራሉ፣ ሰኮንዶች ይሸራረፋሉ። የናፍቆት ምጥ ይጀምራል። በሚቀጥለው ቀጠሮ የሚገናኙበትን ጊዜ ዋኖሶቹ መራብ ይጀምራሉ። አሁን ሲለያዩ
ሰኔ ነው። እሱ ጸደይ ነው፦ እሷ ደሞ አበባ። ጸደይ አበባን፣ አበባም ጸደይን እንደሚናፍቁ የዋኖሶቹም ናፍቆት እንዲሁ ነው። አሁን ሲለያዩ ጥቅምት ነው። እሱ መስከረም ነው ፦እሷ ደሞ የመስቀል ወፍ። መስከረም የመስቀል ወፍን፣ የመስቀል ወፍም መስከረምን እንዲናፍቁ የእነሱም ናፍቆት እንዲህ ነው።
*
*
*

የ’ነዚህ ሁለት ታዳጊዎች የፍቅር ታሪክ… ማዕበል ነው። በየስፍራው በምቾት ተቀምጦ ላለው ጥላቻ የድንጋጤ ማዕበል ነው፦ይህ ፍቅር ። ይህም ፍቅር በደረሰበት አካባቢ ሁሉ ጥላቻ ፈርቶ ይሮጣል። የሁለቱ ‘ርግቦች የጸና የፍቅር ታሪክ ጥላቻ ለተባለው ወረርሽኝ  ፍቱን ክትባት ነው። በነዋይ፣በስሜትና በሚታይ ነገር ላይ ነገሶ ዳንኪራ ለሚጨፍረው የውሸት ፍቅር ማምከኛ ነው፦ ይህ ፍቅር።

አንድ ቀን ታዳጊ ወጣቶች እንዲህ እያሉ ሲያወሩ ታየኝ።

“…እውነተኛ ፍቅር የለም ለምን ትይኛለሽ?  ሳሌም ትዝ አትልሽም።…”

“…ፍቅር የለም፣ጠፍቷልስ ለምን ትለኛለህ? ዳሪክን አታስታውሰውም።…”

“…ትዝ አይልህም …ሳሌም ስርቻ ውስጥ ገብታ ታሞ የተኛውን ዳሪክ ስታነሳው…”

“…አታስታውሺም…ዳሪክስ ሳሌምን  ‘የምወድሽ ከከፍታሽ አትውረጂ’… ሲላት…”

“…ትዝ አይልህም …ሳሌምስ በየቀኑ ከአልጋው አጠገብ አልሄድም ብላ ዳሪክን ስትንከባከብ…”

“…አታስታውሺም…ዳሪክስ ግጥሞች ሲጽፍላት፣ ሺ ጊዜ ‘..የምወድሽ..’ ሲላት …‘ማመን ማየት ነው! የምወድሽ…’.…  እያለ …”

“…ሳሌምስ .… ጆ ካርሎስን ‘ይቅር ብዬሃለሁ፣ እወድሃለሁ’… ስትለውስ…”

“…ዳሪክስ … ‘የምወድሽ የአርዲን እድሜ እንኳን እጠብቅሻለሁ’… ሲላት...”

አዲሱ የወጣቶች ንግግር ይህ ሲሆን በምናቤ ታየኝ።

በመጨረሻ ፍቅር አሸነፈ።

ፈገግ አልኩኝ፦ ፈ…………………………......ገግ!!!!!!!!!!!!!!!!!
*
*
*
የ'ነዚህ ሁለት የፍቅር 'ርግቦች ጽኑ ፍቅር ተራኪ እኔ ሳዬ እባላለሁ። ጸሃፊ ፈጸሞ አይደለሁም። ደራሲ? በጭራሽ ። ነገር ግን ስለ መወደድና ማመን መጻፍ እወዳለሁ። እኔ ሳዬ ነኝ!… እውነተኛ ፍቅር የሚታይበት አካባቢ፣ የእውነትና የፍቅር ውህደት የሚያመጣው መልካም ሽታ ያለበት ስፍራ ላይ እገኛለሁ! ስለ ፍቅርና እምነትም መጻፌን እቀጥላለሁ፦ ሳላቋርጥ።
*
*
ተፈፀመ።

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
43👍25😢2
ድህረ-ታሪክ ማስታወሻ፦
የዳሪክ መንቃት ለህክምናው አለም ትልቅ ተዐምር ነው። ሀኪሞች ሊያብራሩት አልቻሉም። ለወራት ኮማ ውስጥ የነበረና ይሞታል የተባለው ልጅ እንዴት ተመልሶ እንደመጣ ለማወቅ ዳሪክ ላይ ብዙ ጥናት ተሰርቷል። ነገር ግን ይህ ነው የሚባል አሳማኝ ምክንያት ሊገኝ አልቻለም። ከጥናቶቹ አንዱ ያለው ሃኪሞቹ የመተንፋሻ ትቦውን ከዳሪክ ውስጥ ሲያወጡ ዳሪክ ማእከላዊ የነርቭ ሲስተም ላይ የፈጠረው stress (ጫና) የተኛውን የዳሪክ አእምሮ ክፍል እንዲነቃ አስተዋጾ አድርጓል የሚል ነው።

ሃኪሞች ይህንንና ያን ቢሉም .…እኔ ግን የሆነው ትንሽ ገብቶኛል። የዳሪክን ህይወት ያራዘመው ፍጹም ፍቅር ነው። ከሞት የታደገው በጌታ ላይ እምነት ነው። ፈውስን የሰጠው ደሞ ፍጹም ይቅርታ ነው። ሳሌም ፍቅር፣ እምነትና ይቅርታን መረጠች። አብሪያት በነበርኩበት ጊዜ ሁሉ እነዚህ ሶስቱም በሳሌም ውስጥ ያለመከልከል ይፈሱ ነበር። የፍቅር ሃይል ህይወት ነው። በጌታ መታመንም ከሞት ድ’ነት ነው። በፍጹም ይቅርታ ውስጥ መኖርም ፈውስ ነው!....የፈውስ መንገድ።
👍5317👏4
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹የግድ እኮ ወንድ ጓደኛህ መሆን የለበትም፤ሴትም ጓደኛህ ልትሆን ትችላለች...የመጨረሻ አንድ ማሳሰቢያ ሞባይል ስልኬን በመከታተል ጊዜ እዳታጠፋ...የተመዘገበው በእኔ ስም ሳይሆን እኔም በማላውቀው በሌላ ሰው ስም ነው፡፡አረብ አገር በሄደ ሰው ስም፡፡ለማንኛውም ቻው፡፡ ዝርዝር ህጎችን ቀኑን ስትወስን እንነጋገራለን፡፡ >> ሰልኩ ተዘጋ፡፡

ቀኑ አርብ ነው፡፡ የመጀመሪያ ዕድሉን የሚሞክርበት ቀን ነው፡፡ ቢሾፍቱ ሆራ ሀይቅ የእሬቻ በዓል የሚከበርበት ቦታ ላይ ከትንግርት ጋር ቆሞ በተመስጦ ይቃኛል፡፡ ከትንግርት ጋር ሊመጣ የቻለበት ምክንያት አካባቢውን የሚያውቅና ብቸኝነቱን የሚጋራው ሠው ይዞ እንዲመጣ ከምስጢር ጋር በተነጋገሩበት መሠረት ነው፡፡ከጓደኞቹ መካከል ደግሞ ቢሾፍቱን በጥሩ ሁኔታ የሚያውቃት ሰው አልተገኘም.… ከትንግርት በስተቀር፡፡

በመጀመሪያ ሁኔታውን ሲነግራትና አብራው እንድትሄድ ሲጠይቃት በመገረምና ብስጭት በተቀላቀለበት ስሜት አንገራግራበት ነበር፡፡ በኋላ ግን ተስማምታ እንሆ በዚህ ሠዓት ከጎኑ ትገኛለች፡፡

አሁን የሚገኙት ቢሾፍቱ ከተማ የኦሮሞ ማህበረሠብ ባህላዊ እምነት ማለት የኢሬቻ በዓል በሚከበርበት በሆራ ሀይቅ አካባቢ

ነው፡፡ እምነቱ በዓመት አንድ ጊዜ በታላቅ ክብረ በዓል በመስከረም ወር ከመስቀል ቀጥሎ ባለው እሁድ ቀን ይከበራል፡፡ ከተወሠኑ ዓመታት ወዲህ የእምነቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ አገር ቱሪስቶች የበዓሉ ተካፋይ እየሆኑ ስለመጡና መንግስትም ቱኩረት ስለሰጠው የታዳሚዎች ቁጥር በሚሊዬኖች ሆኗል ፡፡ ይህም ቁጥር ከዓመት ዓመት ዕድገት እያሳየ ነው ፡
በተጨማሪም በዚህ ቦታ በግለሠብና በግሩፕ በመሆን የተለያየ አምልኮ ስርዓቶችን ይከናወኑበታል፡፡ አካባቢው በትላልቅ ዛፎች የተከበበ ነው፡፡ከረጅም ጉብኝት በኋላ አካባቢውን ለቀው የመጀመሪያ ዕድሉን ለመሞከር ከምስጢር ጋር ወደ ተቀጣጠሩበት በቅርብ እርቀት ላይ ወደሚገኘው መኰንኖች ቁጥር ሁለት ሆቴል ሄዱ፡፡መኰንኖች ደርሠው ወንበር ይዘው ሲቀመጡ አስር ሠዓት ሊሆን አስራ አምስት ደቂቃ ነበር የሚቀረው፡፡

የሆቴሉ አፀድ ሆራ ሀይቅንና ዙሪያውን የከበቡትን ተራሮች በጽሞና ለማየት እንዲያመች ተደርጎ ነው የታነፀው፡፡ የተስተናጋጆች መቀመጫ በሦስት ደረጃ የተከፈለ ነው፡፡ከሦስቱ ደረጃዎች በተጨማሪ ሀይቁን ተጠግቶ ለመቃኘትና ፎቶዎችን ለመነሳት ሃያ አራት የሚሆኑ ደረጃዎችን ወደ ታች ተንደርድረው ከጨረሱ በኋላ እንደ መድረክ ሀይቁ ላይ በብረት ወለል የተሠራ ዙሪያውን 1.5 ሜትር ቁመት ባላቸው ነጭ ቀለም ተቀብቶ በተለያዩ ዲዛይን ባላቸው ባለብረት መከለያ ዘንጎች ተከልሏል፡ ደረጃው አካባቢ ዕድሜ ጠገብ የሚመስል ትልቅ የሾላ ዛፍ አካባቢውን በጥላ አልብሶት ልዩ ድባብ ፈጥሮበታል፡፡ ግቢው ዙሪያውን ግራና ቀኝ በተለያዩ ትላልቅና መካከለኛ መጠን ባላቸው አረንጓዴ ዛፎች የተሞላ ነው፡፡ ግቢው ብቻ ሳይሆን ሀይቁ ዙሪያውን የተደረደሩት ተራሮች አረንጓዴ የለበሱ ስለሆነ ከሀይቁ ጋር በማበር ልብን ስልብ ያደርጋሉ፡፡ሁሴንና ትንግርት

ሁሉንም ነገር በግልፅ ለማየት እንዲያመቻቸው ከላይ ነው የተቀመጡት፡፡

አስተናጋጁ መጣና ‹‹ምን ልታዘዝ?›› አላቸው፡፡

ሁሴን ስፕራይት ሲያዝ ትንግርት ቢራ አዘዘች፡፡

‹‹ምነው ስፕራይት...ጠጪ አይደለሁም ብለህ ዋሽተሀታል እንዴ?›› የአሽሙር ንግግር አሠማች፡፡

በመጠኑ ፈገግ አለ <<ባክሽ በደመነፍስ ነው ያዘዝኩት፤ችግሬ መች የመጠጥ አይነት ሆነና::>>

‹‹አሁን ካሉት ሠዎች እሷን የሚመስል ሠው አላጋጠመህም?››

‹‹ቆይ እስቲ አታጣድፊኝ፤ እያየሁ ነው፡፡ ለነገሩ ሠዓቱም አስር ደቂቃ ይቀረዋል፡፡›› በማለት አይኖቹን እነሱ በተቀመጡበት መስመር ወደ ኋላው አዙሮ አየ፡፡ ሴት የሚባል የለም፡፡ አንድ ስልሳ ዓመት የሚጠጋቸው ሽበታም ጥቁር ሠውዬ ቢራቸውን ከፊት ለፊታቸው አስቀምጠው ሲጋራቸውን ያቦናሉ፡፡

በቀኝ በኩል ዞሮ ተመለከተ፡፡ሁለት ወንበሮች የተያዙ አሉ፡፡ አንዱ ወንበር በሁለት ጎልማሳ ሲያዝ ሌላኛው በሁለት ጥንዶች ተይዞል፡፡ ዓይኖቹን ወደ ታች ላከ ወደ ሁለተኛው ዝቅታ ላይ ወደሚገኙት ተስተናጋጆች ሦስት ሴቶች የሚዝናኑበት ወንበር ከስድስት በላይ ወንድና ሴት የውጭ ዜጎች የተቀመጡበት ጠረጴዛም ታየው፡፡ ዳር ላይ አንድ ብቻዋን የተቀመጠች ሴት ሲያይ ልቡ ብትን አለበት፡፡ ዕድሜዋ በግምት ወደ ሠላሳ ይጠጋል፤ጠይም ነች፤ቆንጆም አስቀያሚም የምትባል አይደለችም፤ ጠረጴዛዋ ባዶውን ነው፤ ሞባይሏ ላይ አፍጥጣ ትጐረጉራለች፡፡

ምልከታውን ለሀይቁ ቅርብ ወደሆነው ሦስተኛው ዝቅታ አሸጋገረ፡፡ አብዛኞቹ ፍቅረኞች የሚመስሉ ጥንዶችና ነጠላ ወንዶች ይበዙበታል፡፡ ሀይቁ ላይ የተሠተረው መድረክም ባዶ ነው፡፡ ዓይኖቹን ወዳለበት
ሲመልስ ያዘዙት መጠጥ ቀርቧል፡፡ ትንግርት በአትኩሮት እያስተዋለችው መጎንጨት ጀምራለች፡፡ እሱም ፊት ለፊቱ ተከፍቶ የተቀመጠለትን ስፕራይት አነሳና አንዴ ገርገጭ በማድረግ ሊደርቅ የፈለገውን ጉሮሮውን አረጠበበት ፤ መልሶ አስቀምጦ ወደ ግራው ዞር ሲል ቅድም ያልነበረች አርባ አመት የሚዘላት አጭር ወፍራም ደማቅ ቀይ ሴት ከሽማግሌው ቀጥሎ ባለው ጠረጴዛ ላይ ተቀምጣ አያት፡፡

‹‹እንዴት ነው?›› አለችው ትንግርት፡፡

‹‹እኔ እንጃ፤እስካሁን ሁለት ሴቶች ብቻ ናቸው እዚህ ግቢ ውስጥ የሚታዩት፡፡››

‹‹የቷ እና የቷ?››

‹‹አንደኛዋ በስተግራችን ከሽማግሌው ቀጥሎ የተቀመጠችው፡፡››

ዞር ብላ አየችና ‹‹እሺ ትንሽ አሮጊት ትመስላለች፡፡››

<<ሁለተኛዋስ?>>

‹‹ሁለተኛዋ ትታይሻለች? እዛ ... >> ንግግሩን አልጨረሰም፡፡

«እዛ የት..?>>

‹‹ተይው በቃ አሁን ደግሞ ብቻዋን አይደለችም፤የሆነ ወንድ መጥቶላታል፡፡››
ከት ብላ ሳቀችና ‹‹ቆይ ግን ብቻዬን ነው የምመጣው ብላ ነግራሀለች?››

‹‹ታዲያ ከማን ጋር ትመጣለች?››

‹‹ለምሳሌ ከሴት ጓደኛዋ ጋር .. ወይም ልክ አንተ እኔን ይዘህ እንደመጣህ ፤ እሷም አንድ የድሮ ወንድ ጓደኛዋን ...>>

<የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል› አለ ያገሬ ሠው፡፡ እንደዛ ከሆነማ ጉድ ፈላብህ በይኝ፡፡ ምን አልባት ከሴት ጓደኛዋ ጋር ልትመጣ ትችል ይሆናል፤ከወንድ ጓደኛዋ ጋር ግን አታደርገውም፤ምክንያቱም አንድ ከወንድ ጋር ያለች ሴት እሷ መስላኝ በስህተት አበባ ባስታቅፋት እንዴት አይነት ችግር ውስጥ እንደምገባ መረዳት አያቅታትም፡፡››

‹‹ይሁንልህ፤እስቲ ቀስ ብለህ እያት ይህቺ ቦርጫሟ፡፡ ዝም ብላ ታይሀለች፤አይኖቿን በሽማግሌው አሻግራ እዚህ ነው የተከለቻቸው፡፡››

‹‹እየቀለድሽ ነው አይደል? .. ብሎ አይኑን ወደ ተባለችው ሴት ሲልክ እውነትም ዓይን ለዓይን

‹‹እውነትም አንቺ .. ይህቺ ግን አትሆንም››

‹‹እንዴት አትሆንም ..?››

‹‹እንደዛ አይነት ማራኪ ድምፅማ ከዚህች ወፍራም ሴት አይወጣም፡፡››

‹‹ባክህ እራስህን አትደልል፤ስንት ከዚህች እጥፍ የሚሠፉ ግን ደግሞ ልብን የሚሠልብ
ድምፅና ያነጋገር ለዛ የታደላቸው ብዙ ሠዎች እኔም አንተም እናውቃለን፡፡››

‹‹እሱስ ትክክል ነሽ›
👍879👎2
ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አንድ ለጋ ወጣት ቁመቷ ሜትር ከሠባ የሚዘል የወገቧ ቅጥነትና የዳሌዋ ቅርፅ አፍ የሚያስከፍት ጠይም ወዟ የሚያብረቀርቅ ይህ ቀረሽ የማትባል ሠማያዊ ቀለም ያለው ከጉልበቷ ትንሽ ከፍ የሚል ጉርድ ቀሚስ ከሚማርክ ሮዝ ቀለም ካለው ከግማሸ ጡቷ እስከ እንብርቷ ከሚሸፍን አላባሽ ጋር ለብሳ በአጠገባቸው አለፈች፡፡ የሁለቱም ዓይን ተከተላት፡፡ በእጇ አንድ መፀሐፍ ይዛለች፡፡ ሁሴን ዞሮ ወደ መግቢያው ቃኘ፡፡ የተከተላት ሰው እንዳለ ለማረጋገጥ ነበር፡፡

ወደ ሁለተኛው ዝቅታ ሄዳ ፊቷን ወደ እነሱ አቅጠጫ አዙራ ተቀመጠች፡፡‹‹ዋው! ይህቺ ከሆነችማ .. እንኳን አንተ እኔም ሳላፈቅራት
አልቀርም፡፡››

‹‹እንኳን ልብ ድካም አልኖረብኝ፡፡›› ሁሴን ነበር፡፡ልጅቷ አስተናጋጅ ታዘዛት .. ወይን ቀረበላት .. እየተጎነጨች መፅሀፉን ማንበብ ጀመረች፡፡

‹‹መፅሀፉን አየኸው?›› ትንግርት ነበረች::

<<ምነው?>>

‹‹የሚሥጥር መፅሐፍ እኮ ነው!››

« አዎ አንቺ... !>>

‹‹በቃ እሷ ነች ማለት ነው>>

‹‹እስቲ አትቸኩይ ገና አስራ አንድ ሠዓት እንኳን አልሆነም...እስከ አስራሁለት ሠዓት ዕድሌን ተረጋግቼ መሞከር እችላለሁ፡፡››

‹‹ይህቺኛዋ ግን ያዘዘችውን ምግብ እንኳን መብላት አልቻለችም፤ አይኖቿ እኛው ላይ እንደተቅበዘበዙ ናቸው፡፡››

‹‹አሁን ባለው ሁኔታ ያለን ምርጫ ሁለት ናቸው ግን እስኪ እንጠብቅ ምን አልባት ሠዓቱ ከመገባደዱ በፊት ከሁለት አንዷ ተነስታ ትሄድ ያሆናል፤ያ ከሆነ ደግሞ ምርጫችን አንዷ ላይ ብቻ ያርፋል ማለት ነው፡፡››

አስራ ሁለት ከሃያ ሲል ምርጫው ከሁለት ወደ
አንድ ዝቅ ከማለት ይልቅ ወደ አራት ከፍ አለ፡፡
ሦስተኛው ዝቅታ ላይ ምግብ ፈፅሞ በአፏ
ገብቶ የማያውቅ ይመስል የአፍንጫዋ ትልቅነት ከፊቷ ስፋት ጋር የማይመጣጠን
የፀጉሯ እርዝመት ሾጣጣ መቀመጫዋን ሊነካ
ጥቂት የቀረው ቀይ ወጣት ልጅ ፊት ለፊቷ ሚሪንዳ አስቀምጣ አይኖቿን ሀይቁ ላይ ተክላ ተክዛለች፡፡

ሌላኛዋ ደንዳና ሠውነት ያላት መቀመጫዋን የለበሠችው ጥቁር ጅንስ ሱሪ ወጥሮ ሊተረትር የሚመስል ፈገግታዋ ከሩቅ
የሚጣራ ደረቷ ወደ ፊት ትንሽ ፈጠጥ ያለ ጡቶቿ ተራራ ላይ እንደታነፀ ቤተክርስቲያን ከሩቅ አይን የሚገቡ ፣ጎረድ ያለ አፍንጫ ያላት ወጣት ትታያለች፡፡ይህቺኛዋ አልተቀመጠችም ቀጥታ ወደ ሀይቁ ነው
የወረደችው፡፡ መድረኩ ላይ ያለውን የብረት ከለላ ተደግፋ ሀይቁን ትቃኛለች፣ተራራውን ታማትራለች፣ በሞባይሏ ትቀርፃለች፡፡ ዞራ ደግሞ ወደነ ሁሴን አማትራ ፈገግታዋን ትረጫለች፤መልሳ ደግሞ ፊቷን ወደ ሀይቁ ትመልሳለች፡፡

‹‹እሺ ጌታው ሠዓትህ እያለቀ ነው ወስና፡፡››

‹‹እንዴት ልወስን፤ አራት እኮ ሆነዋል!››

‹‹ነፍስህ ታውቃት የለ፤ከአራቱ እሷ የትኛዋ እንደሆነች ለያ..፡።››

‹‹ለተቀማጭ ሠማይ ቅርቡ ነው፡፡አሉ.. መች እንደዚህ ቀላል ሆነና››

‹‹አይ ምን አልባት የሥነ ልቦና ምሁር ስለሆንክ ብዬ ነዋ፡፡››

‹‹በናትሽ በአሽሙርሽ አትረብሸኝ፡፡››

‹‹ኦኬ ! ይቅርታ ትቼዋለሁ፤እራስህን አረጋጋና ስራህን ቀጥል፡፡››

‹‹ይሄውልሽ ይህቺን ወፍራሟን ቀልቤ አልወደዳትም ሠርዤያታለሁ››

‹‹ሦስት ቀረህ፡፡››

‹‹ያቺ ቆንጆዋ አንባቢ ምንም እንኳን የምታነበው የእሷን መጽሀፍ ቢሆንም ይሄ ያጋጣሚ ጉዳይ ይመስለኛል፤እሷ እንዲህ ግልፅ የሆነ መረጃ አትሠጠኝም፡፡ ስለዚህ ሠረዝኳት፡፡››

‹‹ጎበዝ ሁለቱ ቀሩ .. ያቺ ቀጫጫ ብቻ እንዳትሆን?፡፡››

‹‹እሱን አስር ደቂቃ ታገሺኝ፡፡ ወደ ታች ልወርድ ነው፡፡››

‹‹ይቅናህ .. እኔ አራተኛውን ቢራዬን አዛለሁ፡፡››

‹‹እንደፈለግሽ››በማለት ከመቀመጫው ተነሳና ወደ ታች በመሄድ ከብረት ወደተሠራው ወለል ወርዶ መደገፊያውን ተደግፎ ‹‹ሀይ›› አላት፡፡

ባለትላልቅ ጡቷ ከሱ ሦስት ሜትር ያህል እርቃ በሀይቁ ውስጥ የምትዋኘውን አንድ ፈረንጅ እያየች ትፈነድቃለች፡፡ ፊቱን ወደ ቀጭኗ ሴት አዞረ ሲጋራ እያጨሰች ነው፡፡ አካሏ እንጂ መንፈሷ እዚህ ያለ አይመስልም፡፡ አስተውሎ አያት ኧረ እንደውም እያለቀሰች ነው፡፡ይህቺ የምታፈቅረው ከድቷት ልቧ ተሠብሮ የስብራቱን ጥዝጣዜ እያንገበገባት ያለች ነች፡፡›› በማለት ጎኑ ወዳለችው ሀሳቡን ሰበሰበ፡፡ ቀስ ብሎ ወደ እሷ ቀረበ፡፡

‹‹እሷ ስትዋኝ አይተሽ ከምትፈነጥዢ ለምን እራስሽ ገብተሸ ደስታውን አታጣጥሚም?››

‹‹የእኔ ቆንጆ ለምክርህ አመሠግናለሁ፡፡ ነገር ግን ሠውነቴን እንኳን የምታጠበው እንዳልንፈራገጥ በሠንሠለት ታስሬ ነው፡፡››

‹‹እንዴ ይህን ያህል ውሃ ትፈሪያለሽ?››

‹‹ከመፍራት በላይ..፡፡››

<<ለመሆኑ የየት አገር ልጅ ነሽ?››

‹‹ምነው መልኬ... ፈገግታዬ ቆንጅዬ ኢትዮጲያዊ አልመስል አለህ?››

‹‹እንደዛ ማለቴ ሳይሆን .. ለምሳሌ የደብረ ዘይት፣ የአዲስ አበባ፣ የናዝሬት ... ወዘተ እንድትይኝ ፈልጌ ነው፡፡››

‹‹እነሱ ብጥስጣሽ የማንነት መገለጫዎች ናቸው፤ ሙሉው ማንነቴን ከፈለክ እንዳንተው ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡››

‹‹አንቺ አትቻይም፡፡››

‹‹መች ሞከርከኝና፡፡››

‹‹ይሄው ዳር ዳር እያልኩ አይደል?››

‹‹ዳር ዳር ባዬቹማ ብዙዎች ናቸው…ወደ መሀል ሚዘልቅ ደፋር ጠፋ እንጂ፡፡››

‹‹ይህቺማ እራሷ ነች፡፡›› ሲል ደመደመ፡፡ እንዲወስን ካገዙት አቢይ ምክንያቶች አንዱ በንግግሯ ያስተዋለው ብስለት፣ የድምፅዋ ለዛ እና ቶሎ መግባበት መቻላቸው ሲሆን ሁለተኛው አንገቷ ላይ ሀብል ማጥለቋ ነው፡፡ አበባውን ስትሰጠኝ እኔ ሀብል አጠልቅልሃለሁ ነበር ያለችው፡፡ እሱ ደግሞ ሀብልሽ አንገቴ ውስጥ እንደገባ እኔ ደግሞ ቀለበት እጣትሽ ላይ በክብር ሠካለሁ... ስምምነታቸው በምናብ ከለሰው…፡፡

‹‹ምነው ተከዝክ...ወደ መሀል መዝለቅ ፈራህ እንዴ?››

‹‹በፍፁም፤ ቆይ አንድ ጊዜ መጣሁ፡፡›› በማለት ወደ ላይ ወጣ ... ወደ ትንግርት

‹‹አበባውን ስጪኝ፡፡››

‹‹ወሠንክ፡፡›› አለችው፡፡ከቦርሳዋ እንቆቅልሽ የሚል ፁሁፍ የሚነበብበት ቁራጭ ወረቀት የተለጠፈበት ቀይ አበባ አውጥታ እየሠጠችው፡፡

‹‹አዋ እራሷ ነች፡፡›› እንዳመጣጡ እየተንደረደረ
ተመለሠ፡፡ በቀኝ እጁ አበባውን በግራ እጁ
ጃኬት ኪስ ውስጥ ያለውን ቀለበት በጉጉትና በጋለ ስሜት እያፍተለተለ፡፡ስሯ ሲደርስ በሚያምረው ፈገግታዋ ትላልቅ አይኖቿን
አፍጥጣ በአድናቆት ትመለከተው ጀመር፡፡

‹‹በመጀመሪያው ቀን ስለለየኋት በጣም ተደንቃብኛለች ማለት ነው፡፡›› ሲል በውስጡ እያሰበ ከአንገቱ ትንሽ ጎንበስ ብሎ አበባውን እንድትቀበለው ወደ እሷ በመዘርጋት ...‹‹እነሆ ወደ መሀል መግባት እፈልጋለሁ፡፡›› አላት፡፡ ተቀበለችውና ወደ አፍንጫዋ አስጠግታ በስሜት አሸተተችው፡፡

ወረቀቱን ገንጥላ አነበበችና <<እውነትም እንቆቅልሽ››


‹‹በመጨረሻም አገኘሁሽ አይደል?››

‹‹ሳታገኘኝ አትቀርም››

ቀለበቱን አወጣና መልሶ ከተተው፡፡ ቅድሚያ የእሷ ሀብል መቅደም አለበት፡፡ እጆቿን ወደ አንገቷ ወይም ወደ ቦርሳዋ እስካሁን አላከችም፡፡ በሁኔታው የተደመመች ትመስላለች፡፡ሊያስታውሳት ፈለገ፡፡ ‹‹ሀብሉ››

‹‹ምን ሆነ?››ፓፓዬ መስለው ባሞለሞሉ ሁለት ጡቶቿ ስንጥቅ መካከል ተኝቶ ወደ ተደበቀው ሀብል አፍጥጣ ተመለከተች፡፡ ቀስ ብላ እየመዘዘች አወጣችና ከላይ ደረቷ ላይ ለቀቀችው፤ክው ብሎ ደነገጠ፡፡ የልብ ቅርፅ አይደለም፤የመስቀል ቅርፅ ነው፡፡ የእሱም የመጀመሪያ ፊደል አይታይበትም፡፡

ይቀጥላል

ከተች ያለው #YouTube ቻናል ነው  #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ያስብነው ስላልሞላ ብዙ ቆየን ዛሬ ሐሳባችንን ሙሉትና በቅርብ እንገናኝ።
👍126😁16🔥43
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍14
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ‹‹የግድ እኮ ወንድ ጓደኛህ መሆን የለበትም፤ሴትም ጓደኛህ ልትሆን ትችላለች...የመጨረሻ አንድ ማሳሰቢያ ሞባይል ስልኬን በመከታተል ጊዜ እዳታጠፋ...የተመዘገበው በእኔ ስም ሳይሆን እኔም በማላውቀው በሌላ ሰው ስም ነው፡፡አረብ አገር በሄደ ሰው ስም፡፡ለማንኛውም ቻው፡፡ ዝርዝር ህጎችን ቀኑን ስትወስን እንነጋገራለን፡፡ >> ሰልኩ ተዘጋ፡፡…»
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ዕለተ ቅዳሜ 9፡45 ቢሾፍቱ ድሪምላንድ ሆቴል ሁለተኛ ዕድሉን ለመሞከር ከትንግርት ጋር ጎን ለጎን ተቀምጠዋል፡፡ ዛሬ እንደ ትላንቱ ጉጉት ሳይሆን ፍራቻም ጭምር ስሜቱን ቀፍድዶ ይዞታል፡፡

‹‹ዛሬ የማገኛት ይመስልሻል?›› ትንግርትን ነበር የጭንቀት ጥያቄ የጠየቃት፡፡

‹‹በምን አውቃለሁ ብለህ ነው?››

‹‹እንዴት ምን አውቃለሁ? አማካሪዬ እንድትሆኚ ነው እኮ ይዤሽ የመጣሁት፡፡››

‹‹ትልቁ ስህተትህ እሱ ነው፡፡››

<እንዴት?>>

‹‹እንዴት ልታምነኝ ቻልክ ?>>

‹‹እንዴት አላምንሽም ጓደኛዬ አይደለሽ ...?

‹‹ ምክር ብለግስህ እንኳን ጠቃሚ ምክር ይሆናል ብለህ እንዴት ታስባለህ? እርግጥ ጓደኛህ ነኝ፤በተጨማሪም ፍቅረኛህ፤ይቅርታ ማለቴ የድሮ የወሲብ ደንበኛህ፡፡ ስለዚህ የሆነ የሚሠማኝ ነገር ያለ አይመስልህም?ቅናት

በአግራሞት ‹‹እውነትሽን ነው?››ጠየቃት፡፡

<<አዎ::>>

‹‹እኔ ግን ፍፁም እንደዚህ ይሠማሻል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡ቅናት የሚባለውን ቃል እራሱ የምታውቂው አይመስለኝም፡፡ እርግጥ ጥሩ የወሲብ ጥምረት እንደነበረን አልክድም ቢሆንም እኔ እንደማፈቅርሽ እንጂ አንቺ ታፈቅሪኛለሽ ብዬ በፍፁም አስቤ አላውቅም ፤ግንኙነታችን ከፍቅረኝነት ይልቅ የጓደኝነት ቃናው እንደሚያይል ነው የምረዳው፡፡››

‹‹እንደዚህ የተሠማህ እያስከፈልኩህ ስለምወጣልህ ይሆን?››

‹‹የክፍያው ጉዳይማ ድራማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ አድርገሽዋል፡፡››

‹‹እንግዲያው ስለሴቶች ገና ብዙ ያልገቡህ ነገሮች አሉ ማለት ነው፡፡ለማንኛውም ይሄ ያከተመለት ጉዳይ ነው ፤ እርሳውና ወደ ስራህ ተመለስ ሠዓቱ ደርሶልሀል፡፡››

የእጁን ሠዓት ተመለከተ፤ እውነትም 11፡05 ሆኗል፤ ዙሪያውን ቃኘ፡፡ ሴት የሚባል አስተናጋጅ የለም፡፡አንድ ሦስት የሚሆኑ ወንዶች ፈንጠርጠር ብለው ይታያሉ፡፡ ዓይኑን ዙሪያውን በተራራዎች ተከቦ ክብ ቅርፅ ኖሮት ገደል ውስጥ የሚገኘውን አስፈሪና አስደማሚ እይታ ያለውን የቢሾፍቱ ሀይቅ ላይ ተክሎ ከትንግርት ጋር ስለተለዋወጡት ቃለ ምልልስ ያሠላስል ጀመር፡፡ ትንግርት ማለት ለእሱ ሊያጣት የማይፈልግት በጣም የቅርብ ሠው ነች፡፡ ሁሉ ነገሯ ይመቸዋል፡፡ በአሁኑ ማንነቷ ውስጥ ሲገመግማት ብቻ ሳይሆን በሽርሙጥና ስራዋ ላይ እያለችም ስለእሷ ለራሱም የሚገርመው አይነት ስሜት ነው የሚሠማው፡፡ ባለፈው አመት አንድ ወርክሾፕ ላይ ለመሳተፍ ጀርመን ለሦስት ወር ሄዶ ነበር፡፡ በወቅቱ ጓደኞቹ... ስራው... ቤቱ ወይንም አገሩ አልነበረም በአይኑ ላይ የሚበሩት ትንግርት እንጂ ...ሀሳቡን ሳይቋጭ ትንግርት ከኋለው ጎንተል አድርጋ አቋረጠችው፤ እንደመባነን ብሎ ‹‹እ .. እ ... ምነው?››

‹‹እይ ከጀርባህ፡፡››

ዛሬም መፅሀፉን ይዛለች፡፡አለባበሷን ግን ከትላንቱ ተቀይሮል፡፡ በቀሚስ ፋንታ ከሠውነቷ ተጣብቆ ቅርፅን አጉልቶ የሚያሳይ ወደ ቡኒ የሚያደላ የጨርቅ ሱሪ ለብሳለች፡፡ ከላይ የለበሠችው እጅጌ ሙሉ ሠማያዊ ቲሸርት ሲሆን ፀጉሯን ትከሻዋ ላይ ለቃዋለች፡፡ ያ ጠይም ፊቷ ከትላንትናው ይበልጥ ወዝቷል፡፡ ግን ዛሬም መፅሀፍ ላይ እንዳቀረቀረች ነው፡፡ ውስጡን ብርድ ብርድ አለው፡፡ ደስታ ይሁን ፍራቻ መለየት አልቻለም፡፡

‹‹ምን ትላለህ?››

‹‹ምን እላለሁ እሷ ትሆን እንዴ?››

‹‹ያንተን አላውቅም እኔ ግን ሳትሆን አትቀርም እላለሁ፡፡››

‹‹ምን አልባት አጋጣሚ ቢሆን ዛሬም እዚህ የተገኘችው፡፡››ጥርጣሬውን ገለፀላት፡፡

‹‹እንዲህ አይነት አጋጣሚ እንዴት ይኖራል? ሳትቀጣጠር በተከታታይ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የተለያየ ቦታ መገናኘት ይቻላል?››

‹‹በደንብ ይቻላል፡፡›› አለ በአግራሞት አይኑን በቀኝ በኩል ካለ መቀመጫ ላይ ተክሎ፡፡

‹‹አልገባኝም›› ትንግርት ነች፡፡

‹‹በደንብ እንዲገባሽ ወደ ጀርባሽ ዙሪ››

ቀስ ብላ ዞረች

አገጯን በአግራሞት ደግፋ‹‹አጃኢቭ ነው›› አለች፡፡

‹‹ምን እየተካሄደ ነው?›› መልሳ ጠየቀችው፡፡

ከትላንትናዎቹ ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለተኛዋን ነበር የተመለከቱት፡፡ ዕድሜ ጠና ያለችውን፡፡ አለባበሷም ሆነ ጠቅላላ ሁኔታዋ ልክ እንደትላንቱ ነው፡፡ ዛሬም አይኖቿን እሱ ላይ ከመትከል አልቦዘነችም፡፡

<<የሆነ ነገር የገባኝ መሠለኝ፡፡››

<<ምን?>>

‹‹ይህቺ እርጉም የዋዛ አይደለችም፡፡ ከሲ.አ.ይ.ኤ ተባራ የመጣች ሳትሆን አትቀርም፡፡እንዲያደናግሩኝ አራትና አምስት ሴት አሠማርታብኛለች፡፡ ከትላንትናዎቹ መካከል የቀሩት አሁን ይመጣሉ፡፡›› ተናግሮ ሳይጨርስ ትናንት ሲጋራ እያጨሠች ስትነፈርቅ የነበረችው ከሲታ ወጣት በተንቀዠቀዠ አረማመድ አልፋቸው ፊት ለፊታቸው ካለ ወንበር ጀርባዋን ሠጥታቸው ፊቷን ወደ ሀይቁ አዙራ ተቀመጠች፡፡አስተናጋጅ ቀረባት፡፡ ጭማቂ አዘዘችው፡፡

ትንግርት ከት ብላ ሳቀች፡፡ ‹‹ኪኪ . ኪ . ኪ››

‹‹ምን ያስቅሻል?››

‹‹እንዴት ምን ያስቅሻል? ከማሳቅም በላይ ነው እንጂ፡፡ ቀድማ ብትነግረን እኮ የፊልም ዳይሬክተርና ካሜራማን አዘጋጅተን እያንዳንዷን ድርጊት እናስቀርፀው ነበር፡፡ህዝብ በወረፋ ለማየት የሚራኮትበት ልብ አንጠልጣይ ድንቅ ፊልም እንደሚወጣው አይታይህም፡፡ ጉድ ሠራችን፡፡ የቢዝነስ ሠው አይደለችም ማለት ነው፡፡ ግን አያት ያሳደጋት ልጅ ሳትሆን አትቀርም፡፡

‹‹አልገባኝም››

‹‹አየህ አያቶች ሲያሳድጉ እንቆቅልሽና ተረት እየጋቱ ነው፡፡ ይህቺም ያንተዋ ሴት እንዲህ ሰራዋ ሁሉ እንቆቅልሽ የሆነው በዛ የተነሳ ይሆናል ብዬ ነዋ፡፡››

‹‹የእኔን ችግር ለመፍታት የሚበጅ መፍትሄ ባይኖረውም፤ጥሩ ግምት ነው፡፡›› አለ ተስፋው በሰለለ ድምፅ ፡፡

ሠዓቱ 11፡ዐዐ ሞልቷዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ተስተናጋጆች ወጣቶች ናቸው፡፡ በመጠኑ ጠና ያሉም ይገኙበታል፡፡ የእሱ ትኩረት ግን ትናንት ያያቸው ሦስት ሴቶች ላይ ብቻ ነው፡፡

‹‹እንግዲህ ከሦስቱ አንዷ ነች ማለት ነው›› ሁሴን ነው፡፡

‹‹ከአራቱ በል እንጂ››

‹‹አራተኛዋ ደግሞ የቷ ነች?›› በብስጭት ጠየቃት፡፡

‹‹እንደውም አምስት ናቸው፡፡››

‹‹አሹፊብኝ ...አንቺ ምን አለብሽ?››

‹‹ምን አሾፍብሀለሁ ... ያቺን ከፈረንጆቹ ቀጥሎ የተቀመጠችውን ልጅ አየኋት?››

ወደ ጠቆመችው አቅጣጫ ፊቱን ላከ፡፡ ፊታቸው የተሸበሸቡ ሁለት ያረጁ ሴት ፈረንጆች ተመለከተ፡፡ በዚህ ዕድሜያቸው ሠው አገር ምን እንደሚያንከራትታቸው አሠብ አደረገና ተወው፡፡ ከነሱ ቀጥሎ አንድ ወጣት ሴት አለች፡፡ ከፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ ፋንታ ከነጠርሙሱ ቁጭ ብሏል፡፡ አሁን በአትኩሮት ሲቃኛት አበሻ መሆኗን ለየ፡፡ ወደ ነጭነት ያደላ ቅላት አላት፡፡ ድቅልም መሠለችው፡፡ ታምራለች ፀጉሯ በአገራችን ያልተለመደ አይነት ነው፡፡ ቡኒ ቀለም አለው፡፡ ያብረቀርቃል፡፡

‹‹እንዴት እሷ ትሆናለች ብለሽ ገመትሽ?››

‹‹እሷም ትናንት እዛ ስለነበረች ነዋ፡፡››

‹‹በፍፁም አልነበረችም›› የድምፁ መጠን ለእሷ ሳይሆን ለተስተናጋጆች ሁሉ እንዲሠማ ያሠበ ይመስላል፡፡

ትንግርት ግራና ቀኟን እያየች፡፡‹‹ቀስ ብለህ አውራ፡፡›› አለችው፡፡

‹‹ይሄውልህ ትያት አትያት አላውቅም እንጂ ይህቺ ልጅ ትናንትና እዛ ነበረች፡፡ ሌላው ቢቀር ያንን ፀጉሯን እንዴት እረሳዋለሁ?››

‹‹የት ጋር ነበር የተቀመጠችው››

‹‹ዋናው ቡና ቤት በረንዳ ላይ››

‹‹ለዛ ነዋ ያላየኋት፡፡ ለምን ታዲያ አላሳየሽኝም?››

‹‹በወቅቱ ትያት አትያት እርግጠኛ አልነበርኩም፤ ደግሞም ምርጫዎችህ በዝተው እንድትደናገር አልፈለኩም ነበር፡፡››

‹‹እሺ አምስተኛዋስ የትኛዋ ነች››
👍8311👏1
‹‹አምስተኛዋ እኔ ነኝ፤አላየኸኝም እንዴ? እኔም እኮ ትናንት እዛ ነበርኩ››ፈገግ አለ፡፡

‹‹እኔ እንጃ፡፡ነበርሽ እንዴ? ምን አልባት በጣም ተጠግተሸኝ ተቀምጠሸ ከሆነ ‹ሎንግ ሳይት› በሽታ ስላለብኝ ቅርቤ ያለውን ነገር አጥርቼ ማየት ይቸግረኛል›› ሲል ተረቧን በተረብ መለሰ፡፡ ‹‹አስራ አምስት ደቂቃ ብቻ ነው የቀረህ››

‹‹እንደ እኔ ግን ሴትዮህ አሮጊቷ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ለደቂቃ እንኳን አይኗ ካንተ አይነቀልም፡፡አንተ ስትኮሳተር ፊቷን ታጠወልገዋለች፣ፈገግ ስትል ትገለፍጣለች፡፡ ምራቋን የዋጠች የሠከነች ሚስት እንደሚወጣት እርግጠኛ ነኝ፡፡››

‹‹እሷን እርሻት ባክሽ፡፡አታያትም ጥርሷ እራሱ እንዴት እንደሚገጥ፡፡››

‹‹ምን ሁኚ ምንም አፈቅርሻለሁ... አልተውሽም ብለሀታል፤እረሳኸው እንዴ?››

‹‹አረሳሁም፡፡ ግን እንዲህ አይነት ትሁን ማለቴ አይደለም፡፡ ቦርጯን እስቲ እይው? ከሠሎሞን እኮ አትተናነስም፡፡››

‹‹ያቺ ቀጫጫዋስ? ዛሬ ደግሞ ከትናንቱ በተቃራኒ ፈነዲሻ ሆናለች፡፡››

‹‹እሷ እንኳን ምንም አትል ግን ማደናገሪያ ትመስለኛለች፡፡ ስሜቴ እንደዛ ነው የሚነግረኝ፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ ይህቺ አንባቢዋ ሳትሆን አትቀርም፡፡››

‹‹ትናንት እኮ እሷ ልትሆን አትችልም ብለኸኝ ነበር፡፡ እሷ ብትሆን የራሷን መፅሃፍ በማንበብ ግልፅ የሆነ ምልክት እንዴት ልታሳጥህ ትችላለች?»

‹‹ታዲያ ምን ላድርግ፤እሺ ንገሪኝ የትኛዋ ነች?>>

«ያቺ ቀዮስ?»

ፊቱን አዞረ፡፡ ሠርቃ ስታየው ተመለከታት‹‹አምጪ አበባውን ..…ታፍኜ አልፈነዳ››

ከቦርሳዋ አውጥታ ሠጠችው፡፡ እጁን ወደ ኪሱ ከተተና ቀለበቱ መኖሩን አረጋጠ፡፡ ከመቀመጫው ተነስቶ በተንቀረፈፈ እርምጃ ወደ ልጅቷ አመራ፡፡

‹‹ሠው አለው?›› ከፊት ለፊቷ ወዳለው ወንበር በጣቱ እያመለከተ፡፡

‹‹የለውም... ከዛ አባረረችህ እንዴ?››

ምንም ሳይመልስላት ተቀመጠ፡፡በዛው ቅፅበት በጨረፍታ ሲመለከት ጠይሟ ወጣት መጽሀፏን ዘግታ ከመቀመጫዋ ለቃ ወደ መውጫው ስታመራ ተመለከታት፡፡ በጥርጣሬ ታፍኖ በአይኑ ሸኛት፡፡ አሮጊቷም አምስት እርምጃ በማይሆን ርቀት ከኃላዋ አንገቷን ደፍታ ተከትላታለች፡፡ ግቢውን ለቀው ወጡ፡፡ አይኑን ሲመልስ ወርቃማ ፀጉሯን በቀጫጭን ጣቶቿ ወደኃላ እየላገች አፍጣ በመገረም ታየው ነበር፡፡

እንደመርበትበት አለና አይኖቹን ከአይኖቿ አሸሸ፡፡

‹‹የያዝከው አበባ ያምራል፤ የሚቀበልህ አጣህ እንዴ?>>

‹‹አበባውን የሚቀበለኝ ሳይሆን ክራይቴሪያውን የሚያሟላ ነው ያጣሁት፡፡››

‹‹ስላላፈቀርክ ነዋ፡፡››

<<እንዴት?>>

‹‹ክራይቴሪያ የሚኖረው እኮ ከፍቅር በፊት ነው፡፡ ካፈቀርክ ግን የክራይቴሪያ ዘረ ማንዘሮች ተጠራርገው እንጦሮጦስ ይገባሉ፡፡ ምክንያቱም ፍቅር ጉድለቶችን ሁሉ አይቶ የማለፍ ብቃት አለውና፡፡››

‹‹እንደመልክሽ ንግግርሽም ጣፋጭ ነው››

‹‹አመሠግናለሁ፡፡ ግን ያቺን የመሠለች ቆንጆ ብቻዋን አስቀምጠህ እዚህ የመጣኸው ልትጀነጅነኝ እንዳይሆን?››

‹‹ብጀነጅንሽ ምን አለበት?››

‹‹ምንም የለበትም፡፡ ክፋቱ ዛሬ መጀንጀን አላሠኘኝም፤ ለማንኛውም አበባውን ግን እቀበልሀለሁ ፤ልትሠጠኝ ከፈለክ ማለቴ ነው፡፡››

አበባ የያዘ እጁን ወደ እሷ ዘረጋ፡፡ተቀበለችው፡፡ ለደቂቃም በፅሞና ተመለከተችው፡፡ እላዩ ላይ የተለጠፈውን ቁራጭ ወረቀት አነበበች፡፡ ‹‹እንቆቅልሽ›› ጮክ ብላ አነበበችው፡፡ በዝግታ ከጎኗ ያስቀመጠችውን ቦርሳ አነሳችና ጭኗ ላይ አስቀምጣ መክፈት ጀመረች፡፡የሁሴንም ልብ አብሮ መከፈት ጀምሯል፡፡እጇን ቦርሳ ውስጥ ከታ ታተረማምሳለች፡፡

‹‹ቀስ ብለሽ ፈልጊው›› አላት ሳያስበው፡፡

ቀና ብላ አየችውና ፈገግ ብላ ወደ ፍለጋዋ ተመለሠች፡፡ እሱም እጁን ወደ ኪሱ ከቶ ቀለበቱን ባለበት ያፍተለትል ጀመር፡፡ዳግመኛ እጇ ከቦርሳዋ ሲወጣ ግን ይዛ የወጣችው የጓጓለትን ሀብል ሳይሆን ቢዝነስ ካርድ ነው፡፡ ፊት ለፊቷ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችለትና፡፡ ከወንበሯ ተነሳች፡፡ ቦርሳዋን ትከሻዋ ላይ አድርጋ አበባውን በቀኝ እጇ እንደያዘች <<የኔ ማር ዛሬ ሙዴ ስላልሆነ ነው ፤ያው አድራሻዬ፤ ሌላ ቀን ብትደውልልኝ መገናኘት እንችላለን፡፡ እስከዛው አበባህን ውሃ እያጠጣሁ እንከባከባታለሁ›› በማለት ጎንበስ ብላ ጉንጩን ሳመችውና እየተውረገረገች ግቢውን ለቃ ወጣች፡፡ ሁሴን ባለበት ደነዘዘ፡፡ ምንም መናገር አልቻለም፡፡ ምራቁ መረረው፡፡ ትንግርት መጥታ ከጎኑ በመቀመጥ ብታናግረውም አልሠማትም፡፡ትከሻውን እያርገፈገፈች ለማናገር ሙከራዋን ቀጠለች፡፡

‹‹ስማ ነገሮች እኮ አላከተሙም፡፡ ሌላ አንድ እድል እኮ ይቀርሃል፡፡››

‹‹ተይኝ ባክሽ እንዲያውም አንቺ ነሽ›› አንቧረቀባት፡፡

‹‹ደግሞ እኔ ምን አደረግሁ?››

<<አሳሳትሽኛ፡፡ እኔ አሁን ይህቺን ዲቃላ መች አየኋት፡፡ አንቺ ነሽ የጠቆምሽኝ፡፡ ደግሞ አውቀሽ እንድሳሳት ፈልገሽ ነው፡፡››

‹‹እንዴት እንድትሳሳት እፈልጋለሁ?››

‹‹ከእሷ ጋር እንድንገናኝ እንደማትፈልጊ እኮ ከቅድሙ ንግግርሽ ተረድቼያለሁ፡፡ ደግነቱ አሁን ማን እንደሆነች አውቄያታለሁ ነገ ብቻ ይንጋ፡፡ ወደ ኃላ መመለስ አቃተኝ እንጂ ልክ እኔ ወደዚህ ስመጣ ነው እሷ ተበሳጭታ ስትወጣ ያየኋት፡፡››

‹‹እሷ ብቻ እኮ አይደለችም ተበሳጭታ የወጣችው እንዲያውም የእሷን ብስጭት አልተከታተልኩም፡፡ አሮጊቷ ግን አንገቷን ደፍታ ነበር እያዘነች የወጣችው፡፡››

‹‹በቃ ከአሁን በኋላ በራሴ መንገድ መሄድ ነው የምፈልገው ምክርም አልፈልግም፡፡ እንደውም ጥዋት እሸኝሻለሁ፡፡ የመጨረሻውን ፈተና ብቻዬን መጋፈጥ እፈልጋለሁ፡፡ አሁን ተነሽ ወደ ሆቴላችን እንሂድ..… በጣም መጠጣት አምሮኛል፡፡›› በማለት መቀመጫውን ለቆ ውጪ ወደቆመው መኪና አመራ፡፡ ከኋላው ተከተለችው፡፡ ቀጥታ ያመሩት አልጋ ወደያዙበት ቢሾፍቱ አፋፍ ሆቴል ነበር፡፡

ይቀጥላል

ቀጣዩ ክፍል ማታ #ሁለት #ሰዓት ይለቀቃል እስከዛው በብዛት ዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ
ጠብቁኝ ቤተሰቦች 😘
 
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍104🥰13🔥65
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስምንት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ዕለተ ቅዳሜ 9፡45 ቢሾፍቱ ድሪምላንድ ሆቴል ሁለተኛ ዕድሉን ለመሞከር ከትንግርት ጋር ጎን ለጎን ተቀምጠዋል፡፡ ዛሬ እንደ ትላንቱ ጉጉት ሳይሆን ፍራቻም ጭምር ስሜቱን ቀፍድዶ ይዞታል፡፡ ‹‹ዛሬ የማገኛት ይመስልሻል?›› ትንግርትን ነበር የጭንቀት ጥያቄ የጠየቃት፡፡ ‹‹በምን አውቃለሁ ብለህ ነው?›› ‹‹እንዴት ምን አውቃለሁ?…»
#ትንግርት


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹በጊዜ ነበር እኮ መምጣት የፈለኩት ለሆነች ጉዳይ ከአንድ መስሪያ ቤት ወደ ሌላው ስሯሯጥ መሸብኝ›› ሠሎሞን ነው፡፡

‹‹ምንም አይደል ዋናው መምጣትህ ነው›› ፎዚያ መለሠችለት ከፍሪጅ ያወጣችውን ቀዝቃዛ ቢራ ከፍታ ፊት ለፊቱ እያስቀመጠች፡፡

‹‹ወድጄ መሠለሽ ፤ ያ እብድ ሳታያት እንዳታድር ብሎ ስላስገደደኝ ነው የመጣሁት፡፡››

‹‹ሁሴን እያት ባይልህ አትመጣም ነበር ማለት ነው?›› አለችው ትንሽ እንደማኩረፍ ብላ፡፡

‹‹አይደለም፤ እንዲሁ ነገፀሩን አልኩ እንጂ መምጣቱንማ እኔም እፈልገው ነበር ምነው ቆመሽ ቀረሽ አንቺም ያዥና ቁጭ በያ ::

ፍሪጁን ከፍታ ሚሪንዳ አውጥታ ከፍታ ፊት ለፊቱ ቁጭ አለች፡፡

‹‹አይ ይሄማ አይሆንም.ቢራ ከሌለ ወጣ ብዬ ገዝቼ እመጣለሁ ካለበለዚያ ግን እኔን አልኮል እየጋትሽ አንቺ ለስላሳ እንዳትከፍቺ››

‹‹እንዴ! አረ እኔ አልጠጣም ።.››

‹‹ይቅርታ እንደዛ ፓጋን መስለሺኝ ነው፡፡

‹‹እዚህ ጋር ወራጅ አለ…እኔ ፊት እሱን መተቸት ክልክል ነው፡፡.››

‹‹ተቀብያለሁ...ለመሆኑ ዛሬ ደውሎልሻል?››

‹‹አልደወለልኝም ትናንት ነው የደወለልኝ ፣እንደውልለት እንዴ?››

‹‹አይ ተይው አሁን ከሀያ ደቂቃ በፊት አናግሬዋለሁ፡፡.››

‹‹እንዴት ነው ተሳካለት?›› በጉጉት ጠየቀችው፡፡

‹‹አልተሳካለትም፡፡ዛሬማ ሊያብድ ደርሷል፡፡እኔ በበኩሌ ምን እንደሚሻለው ግራ ግብት ብሎኛል፡፡.››

‹‹ምን አንተ ብቻ ኧረ እኔም የማደርገው ጠፍቶኝ እንዴት እንደተጨነቅኩ ብታይ! ወይኔ ወንድሜን ምን አይነት ምትሀተኛ ልጅ ገጠመው?

‹‹ያን ያህል ትወጂዋለሽ ማለት ነው?››

‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው የምትጠይቀኝ? እሱ እኮ ለእኔ ወንድሜም፣አባቴም፣ መላ ቤተሠቤ ማለት ነው፡፡መውደድ የሚለው ቃል ብቻ ይገልፀዋል፡፡.››>

ሠሎሞን በስሜት እየተንዘረዘረ ስታወራው በአንክሮ እየተመለከታት ውስጡ ቅናት ነገር ብልጭ አለበት‹‹እኔን ይሄን ያህል ከልብ የሚወደኝ ሠው ይኖር ይሆን? >> ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ ቢያስብ ቢያስብ ከልጆቹ በስተቀር ማንም ትዝ ሊለው አልቻለም፡፡ የቀረውን ቢራ
ጨለጠና እርሱ ተነስቶ ፍሪጁን ከፍቶ ድጋሚ ቢራ አውጥቶ ከፈተው፡፡

‹‹እኔ የሚገርመኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ?›› ፎዚያ ነች ንግግሯን የጀመረችው፡፡

‹‹ካልነገርሽኝ አላውቅም፡፡››

‹‹የትንግርት ነገር!››

‹‹የእሷ ነገር ስትይ?››

‹‹አብራው መንከራተቷ ነዋ፡፡ ምንም ቢሆን መቼስ አንሶላ መጋፈፋቸው አልቀረ፡፡ ያፈቀርኳትን ሴት አፋልጊኝ ሲላት እሺ ብላው አብራ መሄዷ፡፡

‹‹ምን ታድርግ! መቼስ የሚያፈቅሩት ሠው ሲያብድ ወይ በሠንሠለት አስሮ ህክምና መውሠድ አልያም ደግሞ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በሄደበት እየሄዱ ባደረበት እያደሩ ደህንነቱን መከታተል ነው.…እሷም እያረገች ያለችው እንደዚሁ ነው፡፡››

‹‹በፊት ለእሷ ያለኝ ስሜት የቀዘቀዘ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን እየወደድኳት መጣሁ፡፡››

‹‹በደንብ ውስጧን ብታውቂ ደግሞ ይበልጥ ታፈቅሪያታለሽ፡፡ ልዩ ሠው ነች፡፡ ምን እንዳደረገባት አላውቅም እንጂ እኔ እሱን ብሆን ዓይኔ ከእሷ ውጭ ሌላ ሠው አያይም ነበር፡፡ በስብዕናዋ፣በጥበብ አፍቃሪነቷ፣ በአስደሳች ገፅታዋ፣በምሁራዊ ምልከታዋ፣የሕይወትን ውስጠ ምሥጢር አብጠርጥራ በማወቋ በቃ በሁሉም ነገሯ ለእሱ የምትገባ ሴት ነበረች፡፡እንዴ! ትንግርት ማለት እኮ አንድ ሴት ሳትሆን አስር ሴት ነች፡፡››

‹‹ኤደንስ?››

‹‹የእሷ ትንሽ የተለየ ነው፡፡››

‹‹የተለየ ስትል?››

‹‹አየሽ ኤደን ስርዓቷም ሆነ አስተዳደጓ ለሁሴን የሚሆን አይደለም፡፡ ኤደን ማለት የተለመደች አይነት ሴት ነች፡፡ ቆንጆ ነች፣ ሃይማኖተኛ ነች፣ባህል አክባሪ ነች፣ አብዛኛው ህብረተሠብ በመኖር ላይ ያለውን ኑሮ መኖር የምትፈልግ ሴት ነች፡፡ ጋብቻ፣ ሠርግ፣ እቁብ፣ ዕድር፣ አራስ-ጥሪ፣ ክርስትና፣ ለቅሶ ... የመሳሠሉትን ማህበራዊ ሠንሠለቶችን ሳታዛንፍ መከወን የምትፈልግ ሴት ነች፡፡ ሁሴንን ተመልከተችው ከህብረተሠቡ ጋር ያለው ግንኙነት የላላ፣ ከባህሉ ጋር ያለው መስተጋብር የረገበ፣ እንዲሁም የግሌ ሃይማኖት አለኝ ብሎ የሚፈላሠፍ ግለሠብ ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ በሁለት ጽንፍ ያሉ ግለሠቦች እንዴት ይጣመራሉ? መጀመሪያ እንደውም ለምን አታገባትም ብዬ እጨቀጭቀው ነበር፤ አሁን በደንብ ቀርቤ ሳያትና ልዩነታቸውን ስገነዘብ የእሱ ውሳኔ ትክክል እንደነበር ነው የገባኝ፡፡ እሷ ባይሆን ለእንደኔ አይነቱ ተመራጭ ነች፡፡›› በፈገግታ ንግግሩን አጠናቀቀና ቢራውን አንስቶ ተጎነጨ፡፡

‹‹ለእንደኔ አይነቱ ስትል?››

‹‹አየሽ እኔም እንደ እሷ የተለመደ አይነት ኑሮ ነው የሚመቸኝ፡፡ ፍልስፍና ቅብጥርሴ ያን ያህል አይደለሁም፡፡ አብዛኛው እሷን የሚመቿት ነገሮች እኔንም ይመቹኛል፡፡ በዛ ላይ ቆንጆ ነች፡፡ ገንዘብ አባካኝ አይደለችም፣ እንደውም ጠንካራ ሠራተኛ ነች፣ ታማኝ ነች፣ እነዚህ ነገሮች ደግሞ እኔ በጣም እምፈልጋቸው ናቸው››

ከመጠጡ ጋር ወደ ውስጡ የዋጠውን ንግግሩን ስታላምጠው የሆነ ነገር ጫረባት፡፡ ‹‹ያፈቅራት ይሆን እንዴ?›› ስትል አሠበችና ማረጋገጥ ፈለገች፡፡

‹‹መጀመሪያ የሁሴን ፍቅረኛ ባትሆን ኖሮ እሷን ማግባት ትፈልግ ነበር?››

መልስ ሳይሠጣት ለደቂቃዎች በአትኩሮት ተመለከታትና መናገር ጀመረ<<አዋ እሺ ካለችኝ ለሁለተኛ ጊዜ ላገባ የምፈልገው እሷን ነው፡፡ ደግሞም እሺ የምትለኝ ይመስለኛል›

ደነገጠች፡፡ የሠከረም መሠላት ‹‹ስለ ኤደን እኮ ነው የምናወራው››

«አዎ ምነው?>

‹‹አገባታለሁ ስትል ምን ማለትህ ነው? የሁሴን ፍቅረኛ እኮ ነበረች፡፡››

‹‹ነበረች፤ አሁን ግን አይደለችም፡፡ ከተለያዩ አመት ሊደፍን ነው›

‹‹ቢሆንም የሁሴንን አምቧረቀችበት፡፡

ፈገግ አለና ‹‹ባክሽ አታካብጂ .. በመጀመሪያ ሀሳቡን ያቀረበው እርሱ ነው፡፡ ሁሴን ማን እንደሆነ አታውቂም መሠለኝ›

‹‹ይሄንን ነገር እኔ አላምንም ደግሞም ያው እሱ እብድ ነው ሊልህ ይችላል፡፡ እሷ ግን በፍፁም እሽ አትልህም፡፡››

‹‹በተወሠነ መልኩ ትክክል ነሽ፡፡ እስከ አሁን አገባሀለሁ ብላ ቃሏን አልሠጠችኝም፤ግን
የተወሠነ መንገድ ተጉዘናል፡፡››

‹‹ምን ዓይነት መንገድ?››

የሁለት ወር ጉዞ፡፡ እርግጥ የመጀመሪያ ቀን አብረን ስናድር አቅደን አይደለም፤ በተለይ እሷ በአዕምሮዋም አልነበረም፡፡

እኔ ግን ሁሴን ከፈለክ ቀጥል ካለኝ በኃላ የተወሠነ ፍላጎት በውስጤ ተጭሮ ነበር፤እናም የዛን ቀን እሷ በእሱ ተናዳ፣ እኔ በሚስቴ ተንገብግቤ ተገናኘን ጠጣን እስክንበሠብስ ሠከርን፣ አብረን አደርን፤ ማደር መቼም ምን ማለት እንደሆነ ይገባሻል፡፡

‹‹ቆይ ጥዋት በንፁህ አዕምሮዋ ስታስበው ምን አለች?››

‹‹ተቆጣች፣ አለቀሰች፣ ብዙ ተፀፀተች፣ ለአንድ ሳምንት አኮረፈችኝ ፣ ግን ቀስ በቀስ ለቀቀ እያለች መጣች ደጋግመን ማደር ጀመርን››

‹‹ታዲያ እዚህ ደረጃ ከደረሳችሁ መጋባቱም ቀላል ነው በለኛ!››

‹‹እሱ ላይ እንኳን ትንሽ ችግር አለ፣ ሁሴን አግብቶ ያየሁ ቀን በማግስቱም ቢሆን አገባለሁ ብላኛለች

‹‹የሚገርም ጉድ ነው፤ ታዲያ ይቅናው ብለህ

አትፀልይም?››

‹‹ኧረ ምን ፀሎት ብቻ አዲስ አበባ ለሚገኙት ታቦቶች በጠቅላላ ተስያለሁ››

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል  #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ ቤተሰቦች ዛሬም አንድ 10 ሰው እጠብቃለው👍  አሁንም እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #አድርጉ

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍129😁1614👎3
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ‹‹በጊዜ ነበር እኮ መምጣት የፈለኩት ለሆነች ጉዳይ ከአንድ መስሪያ ቤት ወደ ሌላው ስሯሯጥ መሸብኝ›› ሠሎሞን ነው፡፡ ‹‹ምንም አይደል ዋናው መምጣትህ ነው›› ፎዚያ መለሠችለት ከፍሪጅ ያወጣችውን ቀዝቃዛ ቢራ ከፍታ ፊት ለፊቱ እያስቀመጠች፡፡ ‹‹ወድጄ መሠለሽ ፤ ያ እብድ ሳታያት እንዳታድር ብሎ ስላስገደደኝ ነው የመጣሁት፡፡››…»
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል አንድ
“ጅል አይሙት እንዲያጫውት!”

በቅርብ እና በሩቅ “እናውቀዋለን” የሚሉ ሰዎች፣ እንደሚያስቡትና እንደሚያ ወሩት (ሳያስቡ አያዉሩ መቼስ!) ብልጣብልጥ፣ ራስ ወዳድና “ከነፋስ የፈጠንኩ አራዳ” አይደለሁም “እና ምንድን ነህ?” ብባል መልሴ “ጅል ነኝ!" የሚል ነው። ጅል ብቻ! ማንም በእኔ ምክንያት በጥቂትም ይሁን በብዙ ተጎድቶ ከሆነ፣ የጎዳሁት በክፋቴ ሳይሆን በጅልነቴ ነው። ጅልነቴ ቀላል ጅልነት አልነበረም፡፡ አራት ስለት ያለው ሰይፍ ነው (የጅል ሰይፍ ባለ አራት ስለት ነው!) በግራ ስለት፣ በቀኝ ስለት፣ ጫፉ ስለት፣ እጄታው ስለት። ሌላውን ስወጋ ራሴንም እዬወጋሁ፣ ሌላውን ስቆርጥ ራሴንም እዬቆረጥኩ ነው፡፡ ይኼንን ስል የጥፋቴን መጠን ለማሳነስ አልያም “የዋህ'ኮ ነኝ” በሚል ማስተዛዘኛ ጥፋተኝነቴን ለማለሳለስ አይደለም፡፡ እንኳን ያጠፋሁትን ይቅርና፣ ባልዋልኩበት የፈለጉትን ስም አንስተው ሲለጥፉብኝ፣ለመከላከል ሞክሬ አላውቅም፡፡ ከባድ ግዴለሽነት አለብኝ፡፡ ግዴለሽነቴ ጅልነቴን ጠብቶ የፋፋ ባሕሪዬ ነው፡፡ እንደ ዔሊ ድንጋይ ለብሼው የኖርኩት ምክር የማይበሳው ግዴለሽነት፡፡

እንግዲህ ከጎዳኋቸው ሰዎች ወይም "ጎዳን" ከሚሉት አንዳንዶቹ ይህን ጅልነቴን ከራሳቸው ብልጥነት ጋር አወዳድረው እንደሚያሸንፉ ተስፋ በማድረግ የቀረቡ ነበሩ፣ “ቆይ! እዚሀ ጅል ላይ እንሰልጥንበት” ብለው እንደ ቀልድ የመጡ፤ ነገር, ግን ያቃለሉት የጅልነቴ ወላፈን፣ እንደ ጫካ እሳት እዚያው አፍኗቼው የቀሩ፡፡ ሌሎች ከጥልቅ የጅልነት ጉድጓድ እናውጣው በሚል ቅንነት፤ ለርዳታ እጃቼውን የዘረጉልን ወደ ላይ ሊስቡኝ ሲሞክሩ፣ የጅልነቴ ክብደት አድልቶ እንጦሮጦስ የወረዱ ናቸው : ጅል ከሬሳም ይከብዳል፡፡ እንኳን ከሌሎች ጋር ከራሱ ጋር ለመተባበር የሰነፈ መንፈስ፤ ስንፍናውን ያላወቀች ነፍስ እና የነፍሱንም፣ የመንፈሱንም ጉዳይ የረሳ ሥጋ ባለቤት መሆን ነው - የተሟላ ጅልነት ማለት፡፡ የተሟላሁ ጅል ነበርኩ።

እንዳንዴ፣ ያለፍኩበትን ከንቱነት ገና ሊጀምሩት የሚራኮቱ : ጀማሪ ጅሎችን ስመለከት የሆነ የግሌ ሬዲዮ ጣቢያ መክፈትና ከጧቱ ዐሥራ ሁለት ሰዓት ላይ በጎርናና ድምፅ “ይኽ የጅሎች ድምፅ ነው! እንደምን አደራችሁ ጅሎች?” ማለት ያምረኛል። ሁሉም ከእኔ ወዲያ ብልጥ ላሳር የሚባልባት አገር ዜጋ ነኝና ማንም መልስ አይሰጥም፤ ይኼንን ዝምታ ከብልጠት ይቆጥሩታል፡፡ እኔም “ዝምተኛ ነኝ” ስልና “ዝምተኛ ነው" ስባል ነበር የኖርኩት፡፡ ጅልነት የተደላደለ መኖሪያው የዝምታ ባሕር ውስጥ መሆኑ የገባኝ ቆይቶ ነው “ጅል ዝም ቢል ብልኅ ይመስላል!” ይባል የለ። በጊዜ ፈውስ እንዳናገኝ ቂል ነፍሳችንን በዝምታ ብልኅ ስናስመስል መኖርን በተረት፣ በአሽሙር እና በዘፈን አስተማሩን (ተማማርን ማለት ይሻላል!) ዝምታና ማድበስበሱ ብልኅ ያስመሰለው የጅል አገር ዜጋ ነኝ፡፡ በአገራችን ባህል የዝምታ ትርጉም ግራ የገባው ነው፡፡ እውነት በአደባባይ ሲደፈጠጥ እያዩ አፍን መሸበብ፤ ግን ደግሞ በስሚ ስሚ ለመጣ አሉባልታ ነፍስን ጭምር መስጠት። ጮኾ የማያወራ፣ ሐሳቡን የማይገልጽ ሕዝብ የሐሜት ጫካ ነው። በየጋራና ሸንተረሩ ጥይት ከማስጮኸ የበለጠ፣ ጮኽ ብሎ ያመኑበትን መናገር የሚከብደው ሕዝብ ጀግንነቱ ከባድ ጥያቄ ውስጥ ነው፡፡ በዝም አይነቅዝም ብሒል የነቀዘ ሕይወት እንመራ ዘንድ የፈቀድን ሕዝቦች መሆናችን ሳያንስ ይኽንንም በሀል አድርገን ልንኮራበት ይዳዳናል፡፡

ይኼ ተወልጄ ያደግሁበት ሕዝብ በሹክሹክታ ያወራል፣ ጓዳ ለጓዳ ያወራል፣ እውነት ይሁን ውሸት አግበስብሶ ያወራል፣ እንደ ወረርሽኝ ወሬ በብርሃን ፍጥነት ያዛምታል፣ በአደባባይ ግን ዝምተኛን ያደንቃል- ያበረታታል። በተረቱ “ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም'' እያለ ዝንብ ፈርቶ ዝም (እንዴት ለዝንብ ዝም ይባላል? ለምን ሰፈራችሁን አጽድታችሁ እንደልባችሁ አታወሩም? የሚል የማሪያም ጠላት ነው!) መንግሥትን ፈርቶ ዝም (እንዴት ዝም በሉ ለሚል መንግሥት ዝም ይባላል አፋኝ መንግሥት እጁን ከአፋችን ላይ እንዲያነሳ መንገር የለብንም ወይ? የሚል የአገር ጠላት ነው) ይሉኝታን ፈርቶ ዝም (እንዴት በይሉኝታ እንለቅ? ብንል የባህል ጠላት መበል ይመጣል፡፡) ሁሉም ስሕተትና ፍርኃታችን እንደ ትልቅ ሐብት በእሳት ሰይፍ ተከቦ የሚጠበቅ ቅርስ ነው፤ እውነት ብቻ ነው ራቁት፡፡ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም እውነት የእብዶችና ሰካራሞች ልፈፋ ተደርጋ በየመድረኩ የምትሳለው፡፡ እብዶች እውነቱን እንዲናገሩለት “ጤነኛው" ከፍሎ ይታደማል፡፡ ይኼ ባህላችን ሲሆን ከያኒ የነፍሱን ጥሪ ጣጥሎ የጅሎች አፈቀላጤ ይሆናል፡፡ ታዲያ የዚህ ሁሉ ምክንያት ፍርኃታችን ቢሆንም፣ ይኼንንም በሰበብ ስንጀቡነው (መቼም ሰበብ አናጣ) “ዝምታችን ትዕግስት የወለደው፤ ትዕግስታችንም አምላካችንን የምንፈራ ሕዝቦች ስለሆንን የተጎናጸፍነው ጸጋ ነው'' እንላለን፡፡ እውነታው ግን አምላክን መፍራታችን ሳይሆን ፍርኃትን ማምለካችን ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ዝምታ ውስጥ የታቀፈ ጅልነት ድርጊት ሆኖ ሲፈለፈል ከግለሰብ እስከ አገር ስንት የጨነገፈ ኑሮ ፈጠረ!? ታዲያ የራሳችን ዝምታ ተጠራቅሞ ሲከብደንና አላራምድ ሲለን፤ በየዘመኑ ጊዜና ሁኔታ እየጠበቅን በጋራ እንጮኻለን፡፡ የጨረባ ተዝካር! ይኼን ዓይነቱን ጩኸት አብዮት እንለዋለን (የታዘዙትን ሁሉ እሺ! እያሉ አብዮት አለ ወይ?!) ነገሩ ልክ ውሃ ውስጥ የተነከረ ውሻ፣ ውሃውን ከላዩ ላይ ለማራገፍ በደመነፍስ እንደሚርገፈገፈው ዓይነት ነው፤ ውሃው ቢራገፍም ውሻው

ያው ውሻ ነው፡፡ አጯጯኻችን በአንድ ላይ በዬአፋችን ስለሆነ ማንም ማንንም አይሰማም፤ ማንም የማይሰማው ጩኸት ደግሞ ከዝምታ እኩል ነው። ይኼ ዝምታ፣ የጅል ባንዲራ እንጂ ጨዋነት አይደለም። ባንዲራችን ከፍ ብሎ የሚውለበለበው ለዘመናት በተከመረና በደደረ ጅልነታችን ላይ ይመስለኛል፡፡ የባንዲራችንን ቀለም እየጠቀስን የማንሰጠው ትርጉም የለም። ሁሉንም ቀለም እንደ ዳማከሴ ጨቅጭቀን ብንጨምቀው ከጀግንነታችንም በፊት፣ ከኩሩነታችንም በፊት፣ከአገር ፍቅራችንም በፊት የሚንጠባጠበው ጅልነታችን ሳይሆን ይቀራል?! እሱን እየተቀባን ስንት ጊዜ ከዘመን በሽታ ተፈወስን ብለናል?!
👍7612👎2👏1
ፈውሳችን ሐሰት ነበርና ምስክርነታችን የታተመበት ቀለም ሳይደርቅ፣ ብዙዎች በነጠላም በጅምላም የጅል በትር ሰለባ ሆነው ወደ መቃብር ወርደዋል፡፡ የተረፍነው እንዴት ተረፍን? እያልኩ ሳስብ፣ አንዳንዶች “ምሕረቱ በዝቶልን'' ቢሉም እኔ ግን ፈጣሪም ከዚህች ከኛ ምድር በተዋሰው ተረት “ጅል አይሙት እንዲያጫውት!” ብሎ ለአጫዋችነት ትቶን ይሆናል እላለሁ፡፡ አገሬ ጨዋታና ተጨዋች ይበዛታል፡፡ እንደ አገር ልጅነታችንን አልጨረስንም ይሆን? እስከምል ድረስ የአገሬ ጨዋታ ወዳድነት ያስደምመኛል፡፡ ጅልነቴ ከሕዝብ ባሕር የተቀዳ ነው ስል፣ ለጥፋቴ ሌላ የሕዝብ ክንብንብ ውስጥ መደበቄ አይደለም፤ምንስ ቢሆን ሕዝብ የሚባለው አጀብ ለሚሊዮኖች ቢሰነጣጠር አንዱ ስንጣሪ መሆኔ አይቀር፡፡ ሕዝባዊ ጀግንነት፤ ሕዝባዊ ታሪክ እንዳለ ሁሉ ከየቤታችን አዋጥተን አገራዊ ያደረግነው ሕዝባዊ ጅልነት አለመኖሩን ማን አጥንቶ ነገረን?! ጅልነት ቀለም ነው፤ ታሪካችን እኛም በግልና በጅምላ አማርን ብለን የተቀባነው - የተኳኳልነዉ ጠይም ቀለም። በዚህ ጠይምነት በኩል ስለተገለጠ ግለሰባዊ ጅልነቴ በጸጸት አወራለሁ... በጓዳዬ ለአገር ያዋጣሁት የጅልነት ድርሻ... ይኽም ከንስሓ ይቆጠር እንደሆን እንጃ...


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍432