አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አርባ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ያልተኖረበት የአንድ ወር ቅድመ ክፍያ ቃል ከፍሎ የሄደ ቢሆንም እሷ የስድስት ወር ተጨማሪ ቅድመ ክፍያ ከፈለች...ይሄንን ቅድመ ክፍያ ቃል ሲኖርበት ለነበረ ክፍል ብቻ ሳይሆን ከዛ ቀጥሎ  ለነበረች አንድ ክፍል ቤትም ጭምር ነው የከፈለችው። ክፍሏን እንደአዲስ ቀለም አስቀባችው.....ሙሉ እቃ ፤ አልጋ፤አነስተኛ ፍሪጅ፤ቴሌቪዠን አንድ ጠረጰዛና ሁለት ወንበሮች አስገባችበት ...እንዲህ ያደረገችው የቃልን አባት ከመቄዶንያ አስወጥታ እቤት በማምጣት እራሷ  ልትንከባከባቸው ስለወሰነች ነው።አዎ ይሄንን ዕቅድ ካቀደችበት እለት አንስቶ  በውስጧ ደስታ እየተሠማትና ከድብርቷም በመጠኑም ቢሆን እየተላቀቀች ነው።

አሁን ሙሉ በሙሉ ዝግጅቷን ስላጠናቀቀች ወደሜቅዶኒያ ሄዳ አባትዬውን   የምታመጣበት ቀን ነው።ከመውጣቷ በፊት በሞባይሏ ያዘጋጀችውን ቤት ፎቶ ደጋግማ አነሳችው...ለመምጣት  አሻፈረኝ እንዳይሏት ምን ያህል ተጨንቃ እንዳዘጋጀችላቸው   በምን ያህል መጠን ቁርጠኛ መሆኗን  እሳቸውን ለማሳመን እንዲያግዛት አስባ ነው።በዛ ላይ በማሳመኑ ስራ ቀላል እንዲሆንላት ከእሷ በላይ የሚያውቋትንና ከልጃቸው ባልተናነሰ ያሳደጓትን ጊፍቲን ይዛ ነው የምትሄደው።

የራሷን መኪና እየነዳች እግረ መንገዷን ጊፍቲን ካለችበት አንስታ መቂዶኒያ ደረስን.... መኪናዋን አቁማ ከጊፍቲ ጋር ጎን ለጎን በዝግታ እርምጃ(ያው እርጉዝ ስለሆነች)ወደ ቃል አባት ያሉበት አካባቢ ሲደርስ ያልተለመደ ግርግር ነገር ገጠማቸው...ጊፍቲን ወደኃላ ተወችና ፈጠን ፈጠን እያለች ወደፊት ተጓዘች.... ደረሰች፡፡ ከአስር የሚበልጡ ሰዎች በቦታው ይተረማመሳሉ...አንዳንዶቹ ከንፈራቸውን ይመጣሉ...የሆነ ቀፋፊ ስሜት ሳትፈልግ በግድ ወደ ሰውነቷ ሲሰርግ ታወቃት..ወደ አንድን አዛውንት ተጠጋችና"አባባ ምን ተፈጥሮ ነው?"ስትል  ጠየቀቻቸው፡፡

"ያው ሰው ከንቱ አይደል?አንድ ጓደኛችን ሞቶ ነው"

"ወይ እግዚያብሄር ነፋሱን ይማር."አልኩኝ፡፡

‹‹ወዬኔ ጋሽ ሞገስ...በቃ ሞተ "እያለች አንድ ሴት በስሯ አለፈች፡፡

"ጋሽ ሞገስ?  ይሄን ስም የት ነው የማውቀው? ስትል እራሷን ጠየቀች ተምታባት..በዚህ ጊዜ ከኃላዋ ቀርታ የነበረችው ጊፈቲ ስሯ ደርሳ ነበር.."

"ምን ተፈጠረ ?"ስትል ጠየቀቻት፡

"ሰው ሞቶ ነው?ጋሽ ሞገስ የሚባሉ ሰውዬ ናቸው አሉ"ነገረቻት

"ሞገስ?ሞገስ ማን?"አደነጋገጧ አስፈሪ ነበር፡፡

‹‹ምነው ታውቂያቸዋለሽ እንዴ?››

"የቃልዬ አባት...."
ዠው አለባት...‹‹የተምታታብኝ ለካ ለዛ ነው?"አለች፡፡

‹‹ምንድነው እየሆነ ያለው? ማነው የነካሽው ሁሉ ወድያው ይብነን ወይ ይክሰም ብሎ የረገመኝ?።ስትል አማረረች
""""
ከጊፍቲ ጋር ሆነው የቃልና አባት ቀብር በተገቢው መንገድ አስፈፀሙ....ቅልብጭ ያለች የእብነበረድ ሀውልትም አሰራችላቸው። እሳቸው ከሞቱ በኋላ በፊት የሚሰማት  ሀዘን ብቻ አይደለም እየተሰማት ያለው ።ጉልበት የማጣትና ተስፋ የመቁረጥ ሰሜት ጭምር ውስጧን እያወደመው ነው። አሁን በዚህ ሰአት እሳቸው ሀውልት ጋር ቁጭ ብላ እየተከዘች ነው፡፡

ፊት ለፊቷ ዝርፍፍ ያለች የብሳና ዛፍ ትታታለች ...የበጋው ንዳድ እሷን ብቻ ሳይሆን ዛፏንም የጎዳት መሰላት።ቅርንጫፎቾ የተሸከሞቸው አብዛኛው ቅጠሎች ወይበዎል።አረንጎዴ ቀለማቸው ተመጦ ወደ ቢጫነት እያዘገሙ ነው።ድንገት ከወደ ምዕራብ በኩል ብዛት ያላቸውና ከእሷና ከዛፉ በተቃራኒው በውበት ያሸበረቁ ወፎች ተንጋግተው  መጥተው ሰፈሩበት ...ግማሽ የሚሆነው ቅጠሉ እየተቀነጠሰ ወደ መሬት ረገፈ...፡፡አዘነች ውስጧ እስኪሰበር ድረስ አዘነች..፡፡ያዘነችው ለዛፉ በማዘን አይደለም ለራሷ እንጂ...የእሷም ለዘመናት የገነባችው ተስፋዋ ድንገት መጥቶ ህይወቷን በነቀነቀው መከራ ልክ እንደዚህች ዛፍ ቅጠሎች ነው እርግፍ ያለው።እርግጥ ዛፍ ከጥቂጥ ሳምንታት በኃላ ክረምት ገብቶ ዝናብን ሲያርከፈክፍለት በደስታ ከድርቀቱ አገግሞ እንደሚለመልም መወየብ ታሪክ ሆኖ አረንጓዴ እንደሚለብስ ታውቃለች .‹‹.የእኔስ  ዝናብ መቼ ይሆን አስገምግሞ መጥቶ የሚያርሰኝ እና ከድርቀቴ የሚፈውሰኝ።›ስትል ጠየቀች…

ሰው ግን  በሚሊዬን ህያዋን መካከል እየኖረ ሚሊዬን ህያዋንን በመንገድ ላይ እየገፈተሩና እየገላመጡ መጥቶ እንዲህ  በድን ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ከበድን ጋር ማውራት.?››ስትል በራሷ  ድርጊት ተደመመች፡፡

"ያው የቃል አባት ስለሆኑ የእኔም አባት ኗት...ደግሞ ያው አባትም የለኝም። ምን አልባትም እንደእርሶ የሞተ ይመስለኛል..እንደዛ ከሆነም  የሁለታችሁንም ነፍስ አምላክ ይማራት።››ትንፋሽ  ወስዳ ጉሮሮዋን በምራቋ ካረጠበች በኃላ ንግግሯን አራዘመች፡፡

<<እና ይሄውሏት ቃል ጥሎኝ ከጠፍ በኃላ ለቀናት ሳዝንና ስጨነቅ ከርሜ ነበር እና ድንገት ስለእርሶ ትዝ ሲለኝ ውስጤ ተስፋ ሰነቀ...የፈለገ በእኔም ሆነ በጠቅላላ አለሙ ቢጨክን በአባቱ አይጨክንም ስል አሰበኩ፡፡በእርሶ ላጠምደው ወሰንኩ። ያው ያውቁ የለ እኛ ሴቶች ያፈቀርነውን ወንድ የራሳችን ለማድረግ የተለያዩ ስውር ዘዴዎችን እንጠቀማለን...ለምሳሌ የምናፈቅረው ወንድ አልጨበጥ ብሎ ካስቸገረን ሌሎች ወንዶች እየፈለጉንና እየተከተሉን እንደሆነ እንዲያውቅ እናደርጋለን...ቅናት ውስጥ ገብቶ ከመቀደሜ በፊት ልቅደም እንዲል እኮ ነው ።ወይም ደግሞ የተሳሳትን በማስመሰል  ልጅ እናረግዝና ውሳኔው ከባድ እንዲሆንበት እናደርጋለን ….አዎ በፍቅር ጉዳይ ሴቶች ቁማርተኞች ነን፡፡

እንደሚያውቁት እኔ ደግሞ ቃልዬ አብሮኝ ስለሌለና  የት እንዳለም ስለማላውቅ እንደዛ ማድረግ አልችልም..ስለዚህ የነበሩኝ ብቸኛ የመጫወቻ ካርዴ እርሶ ነበሩ  ። ወደቤታችን ማለቴ ወደቃል ቤት ልወስዶት ለቀናት ለፍቼ ብዙ ብዙ ነገር አዘጋጅቼ  ያማረች ክፍል አዘጋጅቼሎት ነበር...የምትንከባከቦትም ወጣት ነርስ ቀጥሬሎት ነበር..እናም ደግሞ እስከመጨረሻው ድረስ ልንከባከቧት አልሜና ወስኜ ነበር...ከአሁን በኃላ አስርና ሀያ አመት ይኖራሉ የሚል ግምት ነበረኝ...እና በዛ የጊዜ ርዝመት ውስጥ ቃል አንድ ቀን እርሷን ለማየት ሲል ብቻ  ተመልሰሶ ሊመጣ ስለሚችል አንድ ላይ ሲያገኘን ይደሰታል..እናም ምን አልባት ዳግመኛ ጥሎኝ ለመሄድ  ልቡ አሻፈረኝ ትላለች የሚል ምኞት ሰንቄ ነበር ...እንደው ያ ባይሆን እንኳን  አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል እያልኩ ነፍሴን በተስፋ ሞልቼ ህይወቴን በጥበቃ ለማስቀጠል  ወስኜ ነበረ...ግን ምን አልባት የልቤን ሀሳብ አማልዕክቱ ሰምተው መጥተው ሹክ ብለዎት መሠለኝ የሀሳቤ ተባባሪ ላለመሆን ሞተው ጠበቁኝ። ግድ የለም አሁን በሁሉ ነገር ተስፋ ቆርጬያለሁ...እሱን ለመጠበቅ ያለኝን እቅድም እርግፍ አድርጌ ትቼዋለሁ..ግን ህይወቴን እንዴት እንደምቀጥል ምንም አላውቅም..?መቼ መሳቅና መቼ ደግሞ ማልቀስ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል...በሉ ደህና ይሁኑ...አልፎ አልፎ ብቅ ብዬ አዬዎታለሁ።ቃልዬ አደራ ብሎኛል።

ልፍለፍዋን  ጨርሳ ከመቃብሩ ድንጋይ ላይ ተነሳች፡፡

ይቀጥላል
👍11417👎1🔥1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አርባ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ጎነኛው መቃብር ስር አንድ ሰው  እንደሀውልት ተገትሮ   ቆሟል...እዛ ያለ ይመስላል እንጂ በድኑ ብቻ እንዳለ ያስታውቃል። ሀዘኑ ሀዘኗን ቀሰበሰባት። ምኑ ይሆን የሞተበት"የማወቅ ጉጉት አደረባት።አንገቷን አሰገገችና ሀውልቱ ላይ የተፃፈውን ፁሁፍ አነበበች ወ/ሮ ቅድስት ሀምሳሉ 1980 ፡፡ 2015ዓ.ም ይላል።እድሜዋን በአእምሮዋ አሰላችው ።የሰውዬው  እድሜ ገመተች ..አርባ አመት ቢሆነው ነው በቃ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ነች ስትል አሰበች።እንዲህ ካሠበች በኋላ ለሰውዬው  ያላት ሀዘኔታ ጨመረ፡፡

ለማታውቀው ሰው በዚህ መጠን ሰታዝን ይሄ የመጀመሪያ ገጠመኞ ነው። ምን አልባት እሷ  ገና ለገና ፍቅረኛ እንዲሆናት  የፈለገችው ሰው  ጥሏት ስለተሠወረ  እንዲህ እንቅሽቅሽ ካለች እሱ ደግሞ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ለዘላለም ጥላው ሞታ ከምድር በታች አፈር ለብሳ ስትቀበር እንዴት ሊያዝን እንደሚችል አሰላችና ሰቀጠጣት...?ያው ለእሱ እያዘነች ቢመስላትም  በተዘዋዋሪ ለራሷ እያዘነች ነው። ወደኋላ  ተመለሰችና ለቃል አባት አምጥታ ሀውልቱ ላይ ካስቀመጥቻቸው አምስት የፅጌረዳ ዝንጣፊዎች መካከል ሁለቱን አነሳች ‹‹ይቅርታ በሚቀጥለው ስመጣ የእነዚህንም ፋንታ ይዤ መጣለሁ... ብድር ነው›› በማለት...ወደሰውዬው ሄደች.. አጠገቡ ቆመች...ከደቂቃዋች በኃላ ዞር ብሎ አያት አየችው.  ።

ጎንበስ አለችና አበባውን በሀውልቱ መሀከል ላይ አስቀመጠችው...፡፡ይደሰታል  ..ያመሰግነኛል ብላ ስትጠብቅ  በቅፅበታዊ ንዴት አይኖቹን አጉረጠረጠባት... ፊቱ በአንዴ ደም ለበሰ...አይኑ ውስጥ የሚንቀለቀል ከገሀነም እሳት የረገፈ ፍም ነው ያየችው..በዚህ መጠን ሰው አስፈርቷትም አስደንግጧትም አያወቅም....፡፡ጎንበስ አለና ያስቀመጠችውን አበባች አነሳና ብጥቅጥቅ አድርጓ ቆራረጣቸው፤ ተበታትነው መሬት ከመርገፍ የዳኑትን ወደ አፍ ከቶ  እያኘከና እየበጣጠቀ መትፍት ጀመረ…፡፡አንድ አምስት እርምጃ ወደ ኃላ ሸሸት አለችው...

‹‹እሷ አበባ ፈፅሞ አይገባትም.››."አሁን ይሄን መቃብር ብንከፍተው ስጋዋን እንዳለነው የምናገኘው..አፈር አይበላትም߹ ከበላትም ለአፈሩ አውዳሚ  አሲድ ነው የምትሆንበት ፤ምስጦችም አይበሏትም ከበሏትም ሰውነታቸው ተመርዞ ያልቃሉ"አላትና ጥሏት ሄደ...በህይወቷ በሞተ ሰው ላይ ሲሰነዘር የሰማችው በጣም መራርና አስከፊው  ወቀሳ ነው ፡፡በመሄዱ እፎይ አለች ..እዛ ከእሷና እሱ ውጭ  ሰው በሌለበት የቀብር ስፍራ  ሲጥ አድርጎ የሚገላግላት መስሏት በፍራቻ መንቀጥቀጥ ጀምራ ነበር ።አይ የሠው ልጅ ከደቂቃዎች በፊት   ለመኖር ያላት ጉጉት ተሟጦ አልቋል ስትል ነበር ..አሁን ደግሞ ህይወቷ ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እየሠጋች ነው።እራሷን አረጋጋችና ኩስ ኩስ እያለች ከኋላ  ተከተለችው፡፡

ከመቃብር ቅጥር ጊቢ  ወጥቶ አስፓልት ጠርዝ ላይ ሲደርስ  እርምጃዋን ከእሱ እርምጃ ጋር ማስተካከል ቻለች....ዝም ብሎ መራመድን ቀጥሏል"ማኪያቶ ልጋብዝህ›› አለችው ..ሀሳብ ድንገት ነው የመጣላት፡፡

"አይ  ማኪያቶ አልወድም...አሁን  ጂን  ነው ምጠጣው"

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው.. እንደውም እኔም እሱን ብጠጣ ጥሩ ይመስለኛል።››

"ጥሩ"
"መኪናዬን ግን  ፊታችን ያለው ሆቴል ነው ያቆምኩት… እዛ ብንጠጣ ቅር ይልሀል..?."ዝም ብሎ አቅጣጫውን ወደነገረችው ሆቴል አስተካከለ።ያ ማለት በሀሳቧ መስማማቱን ማሳያ አድራጋ ወሰደችውና ተከተለችው፡፡እንደዛው ጎን ለጎን እየተራመዱ ምንም ሳያነጋገሩ  ሆቴል ደረሱ..  በፅድ ተክሎች የተከበች ከለል ያለች ቦታ መርጠው ተቀመጡ የሚቀመጡበትንም ቦታ የመረጠችው እሷ ነች..)እሱ ለመጠጡ እንጂ ለቦታው ግድም ያለው አይመስልም፡፡

"ስለደረሰብህ ሀዘን በጣም አዝናለሁ››አለችው ፈራ ተባ እያለች፡፡

የእሷን አስተያየት ችላ አለና"አባትሽ ናቸው?"ሲል ጠየቃት…ደነገጠች

"ምን? ማን?"

"ቀብሩን ነው ያልኩሽ"

"እ...የእጮኛዬ አባት ናቸው...ማለቴ የፍቅረኛዬ...   ማለቴ የማፈቀረው ልጅ አባት"

"በአንድ ፅኚ እንጂ..የምን መወነባበድ ነው?"

"ወድጄ ይመስልሀል"

"የት ነው"

"ማ ?"
"እሱ...የምታፈቅሪው ልጅ"

"ገዳም ገባ"

መልሷን ከሰማ በኃላ ያዝንልኝና  ያፅናናኛል ብላ ስትጠብቅ

‹‹ተገላገለ" ብሎ እርፍ።

"እንዴት እንደዛ ልትል ቻልክ?"

"ያው አንድ ቀን ልቡን ሰብረሺው  ስቃይ ውስጥ ከሚገባ እንዲ በደህናው ጊዜ ገዳም መግባቱ ይሻለዋል"

"እንዴት ልቡን ልሰበር እችላለሁ ከራሴ በላይ እኮ ነው የማፈቅረው"

"እዛ የተኛችው ማለት ቅድም አበባ  የሠጠሻት ሴትም ከአመታት በፊት እንዲሁ አንቺ ያልሺውን ቃል  መቁጠር ከምችለው ጊዜ በላይ ብላኝ ነበር"

"ታዲያ ምን ተፈጠረ?"

"ያው እንዳልኩሽ ነዋ የልብ መሠበር"

"ሁሉም ታሪኮች ፍፃሜያቸው እንደምታስበው አይደሉም"

"ናቸው..ቆይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?"

"ጠይቀኝ"

"አሁን ጥሎሽ ገዳም ከገባው ልጅ በፊት ፍቅረኛ ነበረሽ"

"አዎ ነበረኝ"

"ታፈቅሪው ነበር?"

"በወቅቱ አዎ አፈቅረው ነበር"

"ጥሩ ...እንደምታፈቅሪውስ ነግረሽው አታውቂም"

"በወቅቱማ እንዴት አልነግረው ...ፍቅረኛዬ ነበር...እንደማፈቅረው ብዙ ጊዜ ነግሬው አውቃለሁ።"

"በቃ መልሴ ተመልሶልኛል"

ድንግርግሯ ወጣ ።ምን ለማለት እንደፈለገ ምንም አልገባትም።

‹‹የምኑ መልስ?"

"ያው መጨረሻውን አየሽው߹ ከዛ ፍቅረኛሽ ጋር አሁን አብረሽ የለሽም...የሌላ ወንድ ፍቅር ፍለጋ በየመቃብር ሀውልቱ ትዞሪያለሽ ߹ያ ፍቅረኛሽ ግን ምን እየተሠማው እንደሆነ ምን ያህል እንዳዘነ ?በምን ያህል መጠን እየናፈቅሽው እንደሆነ ?ምንም ትዝ ብሎሽ አያውቅም አይደል?።"

ለወንዶች ያለው ውግንናና ለሴቶች ያለው ጥላቻ ጠርዝ የወጣ ነው ብላ ስላሰበች አበሳጫት።

"ምን እያልክ ነው..?ቺት ስላረገብኝ እኮ ነው  የተለያየነው"

"እ እንደዛ ነው?" አለና  ጅኑን አንስቶ ተጋተው
‹‹ምነው?  በቂ ምክንያት አይደለም?"

"ለወንድ አዎ .ለሴት ግን አይደለም"

"አልገባኝም?

"ሴት  መጀመሪያውኑ  ለመለየት  አቀባብለ እየጠበቀች ካልሆነ በስተቀር ፍቅረኛዋ ችት ስላደረገባት ብቻ አታባርረውም"

ዝም አለች። ይሄ  የአስፈሪው እንግዳ ሰው ንግግር ለሌሎች ሴቶች ይስራ አይስራ ባታውቅም  እሷን በተመለከተ ዝንፈት የለበትም...እናም ገፍታ ልትከራከረው አቅም  አላገኘችም።ለተወሰነ ደቂቆች በዝምታ እያሰላሠለች ጅኑን መሳብ ጀመረች።ድንዝዝ እንዲላት ፈልጋለች። ለዛሬም ቢሆን እንኳን  ሁሉን ነገር መርሳት።

"እስቲ ስለራስህ ንገረኝ...ስለእሷ...አበሳጭታህ  ስለሞተችው ሴት"

‹‹እርግጠኛ ነሽ መስማት ትፈልጊያሽ?››

‹‹አዎ በደንብ›› አለችና ለመስማት አቆብቆበች….አቀማመጧን አስተካከለች…ማውራት ጀመረ

‹‹የሶስት አመት ፍቅረኛና የአራት አመት ባለቤቴ ነች፡፡ከባለጉዳይ ጋር ስዳረቅ እና ከሀለቃዬ ጋር ስጨቃጨቅ ቆይቼ በድካም ውልቅልቅ ብዬ ወደ ቤቴ ስመጣ  በገዛ አልጋዬ ላይ ከገዛ ጓደኛዬ ጋር ተኝታ ደረስኩ።ከመተኛቷ በላይ ያበሳጨኝ ከእኔ ጋር ስትተኛ ሰምቼው የማላውቀውን በደስታ የመቃተት ድምፅ መስማቴ ነው። የወሲብ ፊልም አክተሮች እራሱ እሷ እያለከለከች እንዳለው አያለከልኩም። ለማንኛውም በአፍላ ስሜት ነቅናቂ ሙዚቃ በታጀበ ተራክቦ ላይ እያሉ ደረስኩባቸው።

እሱ በመስኮት ዘሎ ፈረጠጠ..እሷን ያዝኳት..።
👍846😁2👏1
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

አንቺ ወደሬሳ ማቆያው ቀድመሽ ሂጂና ሁኔታውን አመቻቺ… እኔ ቀስ ብዬ በጓሮ በኩል  ሄጂ የግቢውን መብራት አጠፋለሁ…ጄኔሬተሩንም አቶማቲኩን ስላበላሸሁት ሄደው አስተካክለው እስከሚያበሩት 10 ደቂቃ ይኖረናል..በዛ ጊዜ ውስጥ ይዘነው እንሄዳለን››

‹‹እሺ ግን ተጠንቀቅ…. ሰው እንዳያይህ››

‹‹እጠነቀቃለሁ..እንቺ ልክ መብራቱ እደጠፋልሽ ቶሎ አዘጋጂውና ከጋሽ ተካ ጋር ይዛችሁት በጎሮ በኩል መኪና መቆሚያው ድረስ ይዛችሁት ኑ..እኔ የመኪናዬን  ሞተር አስነስቼ ዝግጁ ሆኜ እጠብቃችኋለው…››

ተስማምተው እሱ ወደጎሮ  መብራቱን ሊያቆርጥ እና ግቢውን በጨለማ እንዲዋጥ ሊያደርግ እሷ ደግሞ በሽተኛውን ልትረከብ ወደሬሳ ማቆያ ክፍል ሄደች
መብራቱም ጠፍቶ እነሱም ሬሳውን(በሽተኛውን ) ይዘው  በመምጣት በመኪና ውስጥ አድርገው የውጭ ጥበቃዎችን በጥበብ አልፈው ግቢውን ለቀው ለመውጣት 8 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀባቸው..

ደ/ር እስክንድር ቀጥታ የነዳው ለዚሁ ጉዳይ ታስቦ ወደተዘጋጀ  ዛሬ ጥዋት ወደተከራዩት አፓርታማ ነበር….ይህን ቤት የተከራዩበት ዋና ምክንያት የሰሚርን ቤት የበሽተኛው ዘመዶች ያውቁታል..እሱ ቤት እንደይወስዱት ደግሞ ከቤተሰቦቹ ጋር ነው የሚኖረው…. በዚህ ምክንያት የግድ   ማንም የማያውቀው እና ሰወር ያለ ቦታ ቤት መከራየት ነበረባቸው….
እንደደረሱ….ያው እንደሬሳ ድርቅርቅ ያለውን በሽተኛ ለሁለት እንደምንም ተጋግዘው ከመኪናው አወረዱትና ከሆስፒታል ባመጡት ተሸከርካሪ ጋሪ እየገፉ ወደቤት  አስገቡትና  …መኝታ ቤት የሚገኝ  አልጋ ላይ  ዘረሩት….

ይሄንን ሁሉ እስኪያደርጉ በመካከላቸው በስሜት ከመግባባት እና በምልክት መልእክት ከመለዋወጥ ውጭ ቃላት አልወጣቸውም ነበር….ሁለቱም በተመሳሳይ ሁኔታ በድን ሆነዋል

‹‹በይ ቶሎ መድሀኒቶቹን አምጪልኝ…››ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ዓ.ነገር ነበር

ሮጣ ሄደችና ካስቀመጠችለት በማምጣ ፊቱ ያለው ጠረጵዛ ላይ ዘረገፈችለት…

ሁለት መድሀኒቶችን ቀላቅሎ በመርፌ ክንዱ ላይ ወጋው….እና ከጎን ያለ ወንበር  ሳብ በማድረግ አልጋውን ተጠግቶ በመቀመጥ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመረ..ሰሚራ ተገትራ  አይኖቾን የተዘረረው ሬሳ ላይ እንደሰካች ነው…ዶክተርም  ቁና ቁና እየተነፈሰ በየሰከንዶች ልዩነት ሰዓቱን እያየ ይቁነጠነጣል..ሰዓቱ ደግሞ መንቀርፈፉ….

‹‹ምነው ዝም አለ…..?››ሰሚራ ጠየቀች

‹‹እኔ እንጃ …መድሀኒቱ በመላ ሰውነቱ እስኪሰራጭና እስኪሰራ 5 ደቂቃ ይወስድበታል››

‹‹ታዲያ ከሰጠሀው እኮ ቆየ…..?››
‹‹መስሎሽ ነው …ገና ሁለት ደቂቃ ነው››

‹‹ሁፍ!!! ሁለት ደቂቃ ማለት ግን ስንት ነው…..?››

‹‹ሁለት ደቂቃ ማለትማ  ያው ሁለት ደቂቃ ነው..ግን አንዳንዴ  እንደዚህ ይበረክታል››አላት በደመነፍስ

…አይደርስ የለ 5 ደቂቃ ሞላ በሽተኛው ንቅንቅ አልል አለ….

‹‹ምን ይሻላል..…..?የሆነ ምልክት ማሳየት ነበረበት››ደ/ር እስክንድር ነው ግራ በመጋባት ለራሱ ይሁን ለሰሚራ በማያስታውቅ ስሜት ያወራው

‹‹አረ የሆነ ነገር አድርግ..ወይኔ ተዋረድን››

‹‹ቆይ እስቲ ተረጋጊ …ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ..››አለና ፊት ለፊቱ ካለ ጠራጴዛ ላይ ከተዘረገፉት መድሀኒቶች ውስጥ አንዱን መርጦ በፊት  ከወጋው በተቃራኒ ባለው ክንዱ ላይ ወጋውና በተመሳሳይ ሁኔታ ውጤቱን መጠበቅ ጀመረ….
አንድ ደቂቃ..ሁለት ደቂቃ…ሶስት ደቂቃ…ምንም የለም..በድን ሬሳ…

‹‹ወይኔ ተበልተናል…ምንድነው የተሸወድኩት…..?››

‹‹እኔ ምን አውቃለሁ…መድሀኒቱ አስተማማኝ ነው …አውቀዋለሁ ብለህኝ ነበር…..?››

‹‹አዎ ብዬሽ ነበር..ግን  አልሆነም››

‹‹ግን አልሆንም ትለኛለህ እንዴ……?ስለሰው ህይወት እኮ ነው እያወራን ያለነው..ገና አለምን በቅጡ መኖር ስላልጀመረ ወጣት››

‹‹መቼስ ይሄ እንዲሆን ፈልገን አይደለም..እንደውም በተቃራኒው የእሱን ህይወት ለማትረፍ ነው እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የገባነው..ሞክረናል  ግን አልቻልንም››

‹‹መቻል ነበረብን …››ከ20 ደቂቃ በላይ ተገትራ ከቆመችበት ቦታ ተነቃነቀችና ወደእሱ ቀረበች ….እሱም ምን ሊፈጠር ነው በሚል ስጋት ከተቀመጠበት ተነሳና ፊት ለፊቷ ቆመ
እንባዋን እያዘራች….‹‹ልታድነው ይገባ ነበር …መሞት አልነበረበትም…ከባድ  ስህተት ነው የፈፀምነው…››ደረቱን እየመታች  በመንሰቅሰቅ እቅፉ ውስጥ ገባች፡

‹‹አንቺ ምን አደረግሽ..…..?ከምትችይው በላይ ልትረጂው እየሞከርሽ ነበር›››

‹‹አይ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነበር መሄድ የነበረብኝ…የማይሆን  ነገር ነው የሞከርኩት …..››

‹‹የት ነው ያለሁት…..?››ያልታሰበ ከሩቅ የሚመስል ድምጽ ተሰማ…. ሁለቱም በድንጋጤ ፈዘው  ወደአልጋው መመልከት ጀመሩ ....መላኩ በተኛበት እልጋ ላይ አይኖቹን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገ ዙሪያ ገባውን ሲቃኝና በጥያቄ አስተያየት ሲያይ ተመለከቱት

‹‹ወይኔ በአላህ ነቃ ..አደረከው ..አደረከው..››ደ/ር ላይ ተጠመጠመችበት….ለቅሶዋን ማቋረጥ አልቻለችም….ከሳቅ ጋር የተቀላቀለ የደስታ እንባ

‹‹የት ነው ያለሁት…..?››በሽተኛው ጥያቄውን ደገመው

‹‹አይዞህ… እኔ ሲስተር ሰሚራ እባላለሁ…እሱ ደግሞ ጎደኛዬ ነው ዶ/ር እስክንድር ይባላል…ያንተን ጤንነት የምንከታተለው እኛ ነን››

‹‹ምን ሆኜ ነው…..?››

‹‹አይዞህ ጥቂት ጉዳት ደርሶብህ ነበር.. አሁን ተርፈሀል….››

‹‹ሰላሜስ…..?ሰላምን ጥሪልኝ..››
‹‹አይዞህ ጠራታለሁ .አሁን ራስህን አታድክም .››

‹‹ጥሩ…ልኝ..››እያለ ወደ እንቅልፍ አለም ገባ 

‹‹መተኛቱ ጥሩ ነው….ይገርማል የሰጠነው መድሀኒት ከሞት ብቻም ሳይሆን ሰሞኑንም ከነበረበት ኮማ ጭምር ነው መንጭቆ ያወጣው….እንዲህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር….ግን አሁን መልሶ ከእንቅልፉ ሲነቃ  ስለፍቅረኛው እና  ስለወንድሙ እንዴት ታስረጂዋለሽ…..?››

‹‹አታስብ ዋናው ወደ ህይወት መመለሱ ነው… ሌላው እዳው ገብስ ነው… የሆነ ዘዴ አላጣም..አንተ ግን ድንቅ ሰው ነህ››

‹‹አረ ድንቅነት በአፍንጫዬ ይውጣ ..ሁለተኛ እንዲህ አይነት ቅብጠት አይዳዳኝም …እንዴ ነፍሴ በአፍንጫዬ ልትወጣ እኮ ነበር››

‹‹ይቅርታ አጨናነቅኩህ አይደል…..?››

‹‹አጨናነቅኩህ ብቻ..ልትውጪኝ እኮ ነበር…ይሄ ልጅማ እንዲህ በቃላሉ ከዚህ ቤት የሚወጣ አይመስለኝም››

‹‹ምን ማለት ነው…..?››

‹‹እኔ እንጃ አይነ ውሀሽ አላማረኝም…ለማንኛውም በየስድስት ሰዓት ልዩነት ይሄንን መድሀኒት ስጭው…ችግር ካለ ደውይልኝ አሁን እኩለ ለሊት ከማለፉ በፊት ወደቤቴ ልሒድ››

‹‹ስላደረክልኝ ነገር በጣም አመሰግናለሁ..ና ልሸኝህ››

‹‹አረ ግድ የለም….ነገ መቼስ ስራ አትመጪም››

‹‹አረ የዓመት ፍቃድ እጠይቃለሁ..እስኪሻለው  ለማን ጥዬው እሔዳለሁ…?››

…ፈገግ ብሎ እየሳቀባት ቤቱን ለቆላት ሄደ 

.በደንብ እስኪሻለው 15 ቀን ፈጀበት..የሆነውን ነገር እና ፍቅረኛውና ወንድሙ ምን እንዳደረጉት የነገረችው እቤቷ በወሰደችው በ3ተኛ ቀን ነበር..የመከዳቱን ነገር ከሰማ በኋላ ለቀጣዬቹ ሶስት ቀናት ህመሙ አገርሽቶበት ለምን ነገርኩት…..? ብላ እስከምትፀፀት ድረስ ነበር እንዲቆጫት ያደረገት..በኋላ ግን ቀስ በቀስ እያገገመ መጣ ..ሲቆይ በእሷ እንክብካቤ እና ማበረታታት ተሻለው….
👍9218🥰5😁4
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

በ25ኛው ቀን ጥዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ

‹‹ዛሬማታ ልሄድ ነው››

‹‹የት ነው የምትሄደው…..?››ደንገጥ ብላ ጠየቀችው ሰሚራ

‹‹ከከተማ ወጣ ብዬ  ትንሽ ራቅ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰብ እፈልጋለሁ….››

‹‹ስለምንድነው የምታስበው..…..?ክፉ ነገር አይደለም አይደል…..?››

‹‹እኔ እንጃ …ለጊዜው ምንም የመጣልኝ ነገረ የለም..እንደገደሉኝ ልግደላቸው…ወይስ ይቅር ልበላቸው …..?የማውቀው ነገር የለም…ገንዘቤን ግን ልጅነቴን የሰዋሁበትና ብዙ ፈተና ያየሁበት ስለሆነ ሰባራ ሳንቲም እንደማልተውላቸው እርግጠኛ ነኝ..ምን አልባት እስከዛው በደንብ ቢደሰቱበት  ጥሩ ነው››

‹‹እንዴት አድርገህ ታስመልሳቸዋለህ……..?አሁን እኮ ንብረትህ በእነሱ እጅ ነው..በህይወት መኖርህን ካወቁ ባለ በሌለ  ኃይላቸው ነው አሳደው የሚያስገድሉህ››

‹‹አይዞሽ አታስቢ… እጠነቀቃለሁ….ለዛም ነው ከዚህ ከተማ ራቅ ብዬ በጽሞና ምን ማድረግ እንደምችል ማሰብ አለብኝ የምልሽ››

‹‹ካልክ እሺ ..ቆይ መጣሁ›› ብላ ከነበሩበት ሳሎን ተነስታ ወደመኝታ ቤቷ ከሄደች ከ5 ደቂቃ በኃላ ተመልሳ መጣችና ቼክ እጁ ላይ አስቀመጠችለት፣..ግራ ገብቶት አንዴ የሰጠችውን ቼክ አንዴ ደግሞ እሷን በማፈራረቅና በመገረም ሲያያት  ከቆየ በኃላ

‹‹ምንድነው ይሄ…..?››ጠየቃት

‹‹የራስህ ብር ነው..አንተን እንድገድልላቸው የከፈሉኝ ነው…ሁኔታዎችን እስቲስተካከሉልህ ለመንቀሳቀሻ ይሆንሀል››

‹እንዴ ምን አይነት ሰው ነሽ….?እንዲህ አይነት ሰው እኮ በዚህ ጊዜ አይገኝም››

‹‹አይ እንደምታስበኝ ደግ ሴት ሆኜ አይደለም..ለአንተ ብቻ ነው እንዲህ የሆንኩት..››

በንግግሯ ውስጡ ተነካና‹‹ለእኔ ለምን…..?››ጠየቃት

‹‹እኔ እንጃ….. ›አለችው
..ከተቀመጠበት ተነሳና ስሯ ተንበረከከ..ደነገጠች፡፡ አቀፋት …አንገቷ ሰር ገብቶ ሳማት…. ውርርር አደረጋት፣..አላቆመም… ወደታች አስጎንብሶ ግንባሯን …አይኖቾን… ጉንጮቾን በመጨረሻ ከንፈሯ ላይ ተጣበቀባት…አይኗን ከመጨፈን እና ከንፎሯን ከማነቃነቅ ውጭ ምንም ተቃውሞ አላሰማችም…ደስ የሚሉ እልፍ መሰል ሁለት ደቂቆች አለፉ….

የሚያደርገውን አድርጎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲቆም እሷ አፍራ  አቀረቀረች…
የሰጠችውን ቼክ መልሶ ጉልበቷ ላይ እያስቀመጠላት..ይሄ ምን አልባት እኔን ለገደልሽበት ቢከፍሉሽም.. አንቺ ግን እኔን ለማዳን ለህክምና ይሄን ቤት ለመከራየት ላወጣሽው ወጪ መሸፈኛ ይሁንሽ…ውለታሽ ግን በዚህ ብር የሚመለስ ወይም የሚጣጣ ፍጽም አይደለም…በሕወቴም ጭምር ከፍዬ አልጨርሰውም››

‹‹ህይወትህን ስፈልግ ያኔ  ትከፍለኛለህ …አሁን ግን ከእኔ ይልቅ አንተ ነህ ችግር ላይ ያለህው …  ደግሞ ከራሴ ገንዘብ ምንም ያወጣሁት ነገር የለም…ከዚህ በተጫማሪ መቶ ሺ ብር ቦነስ ብለው ሰጥተውኝ ነበር…እርግጥ ከላዩ ላይ አንተን ለማሸሽ እና የሬሳ ሳጥኑን ቀይረው ለሰጡኝ አቶ ተካ 50 ሺ ብር ከፍያለሁ..ሌላውን 50 ሺብር   ደግሞ እስከአሁን እየተጠቀምኩበት ነው ፡፡››

‹‹አይዞሽ ለእኔ አትስቢ አልኩሽ እኮ …እነሱም ሆነ ማንም የማያውቀው 5 ሚሊዬን ብር ባንክ አለኝ…..በዛ እጠቀማለሁ፡፡››

‹‹ግን ባረብሽህ ምትሄድበት ይዘህኝ ብትሄድ …..?››

‹‹አረ ደስ ይለኛል..ስራሽን ብዬ እኮ ነው…..?››

‹‹ስራው ይደርሳል››

‹‹በያ ተዘጋጂ….መኪና እንከራይ ››

‹‹ወደየት ነው ግን ምንሄደው…..?››

‹‹እግራችን ወደመራን….››

ይቀጥላል
👍11210👎5👏2
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


//
የጊቢዋ አጸድ ውስጥ ባለ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ የወፎችን ዝማሬ እና የዛፎችን ሽውሽውታ እየታዘበች በሀሳብ እየናወዘች ነው፡፡ያው በህይወቷ አዲስ ክስተት ተከስቷል … አንድ ሰው ላይ ለቀናቶች ሀሳቧ እንደተጣበቀ ነው….ያ ባሪያ ልጅ ልቧን ቅልጥ ሀሰቧን ውስውስ ነው ያደረገባት፡፡ሰሚራ ከምትባለው ፍቀረኛው ጋር ያለውን ታሪክ እና የፍቅር ትስሰር  ሙሉውን ታሪክ ለመጨረስ እራሱ አቅም አነሳት...ስለሱ ከማሰብ የሚያሰንፋት መስሎ እየተሰማት ነው….‹‹ለማንኛውም እስቲ  ታሪኩን ልጨርስ›› ብላ ተቀመጠች …ግን ታሪኩን ለመጨረስ  ንስሯ ያስፈልጋታል..እንደምታየው ደግሞ አሁን ጊቢ ውስጥ  ንስሯ አይታያትም …ብዙም ሳያስጠብቃት ከሄደበት ተመልሶ መጣ 

ቀጥታ ወደዛ ወደተለከፈችበት ታሪክ አመራች …አእምሯዋን ከንስሯ አዕምሮ ጋር በተለመደው መንገድ አቆራኘችው..አዎ አገኘዋቸው…ከከተማ እንውጣ ብለው ላንጋኖ ነው የሄድት …በሀይቁ ዳር በታነፀ ላውንጅ  የተዘጋ መኝታ ክፍል ውስጥ ናቸው፡፡
//////
ህይወት ልክ እንደካርታ ጫወታ ነች…ይበወዝና ተጫዋች ለሆኑት  ኗዋሪዎቾ የሚታደል ዕጣ ፋንታ በሚሉት ምናባዊ ሀዲድ  የምትሸረብ…አጋጣሚ በተባለ የህይወት ሰንሰለታማ  ጉዞ ላይ በትክክለኛው ቦታ በትክክለኛው ጊዜ አንዱ ካንዱ በመገጣጠም መላተም እና በሌላ ገጽ ላይ  በሰከንድ ሽርፍራፊ ሰከንድ መዘግየት ተፈጥሮ ተፈላልጎም ሳይገናኙ  መተላለፍን በውስጧ የያዘች….

በጣርነው መጠን ማናገኝባት…ባመረትነው መጠን ማንሰበስብባት…በተመኘነው መንገድ ማንጓዝበት..እንደሎተሪ ዕጣ ብዙዎቻችን የምንከስርባት…የተወሰነው በማስተዛዘኛ የምንፅናናባት..ጥቂቶች ደግሞ እንደው ጠብታ  ላባቸውን በአልማዝ ተመንዝሮ እጃቸው ላይ የሚቀመጥላቸው …ውጥናቸውን አለም ጠቅላላ ተረባርቦ ከግብ የሚያደርስልቸው ከእርጥብ እድል ጋር የተፈጠሩ…ንግግራቸውን በደቂቃ አለም የሚያደምጥላቸው…እነሱ ለተከዙት አለም ተንሰቅስቆ የሚያለቅስላቸው …እንዲሁ መርቆ የፈጠራቸው አሉ፡፡ … እና ህይወት የካርታ ጫወታ ነች…የጫወታውን ህግ ግን ተፈጥሮዊ ብቻ አይደለም..ሰው ሰራሽም ጭምር ነው … 
ይሄንን ሀሳብ ያሰበችው ሰሚራ ነች ..ፍቅረኛዋ  መላኩ ደረት ላይ ጋደም ብላ እያሰላሰለች የምትገኘው፡፡እንዴት እንዲህ ልሆን ቻልኩ....?እንዴት ከበሽተኛዬ ጋር ፍቅር ውስጥ ገባሁ…...?አጋጣሚው ነው ወደዛ የገፋኝ ወይስ እራሴ ነኝ ፈቅጄ እና አስቤ ወደዚህ ደረቱ ላይ ወደተጋደምኩት ልጅ ልብ ውስጥ የገባሁት…...?

‹‹ምን እያሰብሽ ነው..?››ድንገት በጠየቃት ጥያቄ ለውስጥ ጥያቄዋ መልስ ሳታገኝ  አቋረጠችው፡፡

‹‹መቼ ጥለህኝ እንደምትሄድ እያሰብኩ ነው››አለችው…ለምን እንደዛ እንዳለችው ለራሷም አልተገለጸላትም… ..ምክንያም እያሰበች ያለችው ያንን እንዳልሆነ እሷና እግዚያብሄር ያውቃሉ….ሳታስብ ከንፈሯ ላይ የመጣላት ድንገታዊ መልስ የእውነት ስጋቷ አይደለም ማለት ግን አይቻልም…

‹‹የት ነው ጥዬሽ የምሄደው..?››

‹‹ወደኑሮህ ነዋ››

‹‹ኑሮ ማለት እኮ  የህይወት ደስታሽ የሚመረትበት ቦታ ነው….ማንም ሰው በህይወቱ የሚባክነው ያንን ቦታ ፍለጋ ነው…የደስታው ምንጭ የሚፈልቅበትን ጥግ ለማግኘት …የሰው ልጅ ስኬትም የሚለካው በዚህ ነው…እና እኔ እድለኛ ነኝ .ብዙም ሳለፋ በተዐምራዊ አጋጣሚ አንቺን አግኝቼያለሁ….እንዳገኘውሽ ያወቅኩት ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በቃ ስትስቂ ልቤ ትቀልጣለች…ትንፋሽሽን ወደውስጤ ስስበው በሰውነቴ ውስጥ በስብሰው  ያበቃላቸው ሴሎቼ እንኳን መልሰው ህይወት ሲዘሩ ራሱ ይታወቀኛል…..ከጎኔ መኖርሽን ሳይ ዓለም ጠቅላላ ተሰብስባ ከእጄ የገባች ይመስለኝና ልቤ በኩራት አብጣ ልትፈነዳ ትደርሳለች..እና ከአንቺ ተለይቼ መሄድ ማለት ወደባዶነት ሸለቆ ተወርውሮ መከስከስ ማለት እንደሆነ ሚጠፋኝ ይመስልሻል …...?አሁን ባለሁበት ሁኔታ ከንቺ ውጭ ኑሮ ማለት ሲም ካርድ የሌለው ባዶ የሞባይል ቀፎ መሆን ማለት ነው…..››

ከትከት ብላ ሳቀች..ኪ…ኪ..ኪ…እንዴ ‹‹ነገሩን ሁሉ እኮ ስነጽሁፋዊ አደረከው…ከእኔ ከመገናኘትህ በፊት ነጋዴ ነበርኩ ብለሀኝ አልነበር እንዴ..?››

‹‹አዎ በጣም ጎበዝ ነጋዴ ነበርኩ…ምን ተፈጠረ..?››

‹‹አይ ንግግርህ የደራሲ እንጂ የነጋዴ አልመሰለኝ አለኛ…..››

‹‹አታውቂም እንዴ..? ፍቅር እና ችግር ያፈላስፋሉ እኮ….!!!››

‹‹አይ ጥሩ….ለማንኛውም የቀልድህንም ቢሆን በሰማሁት ነገር ደስ ብሎኛል….ምነው በተናገረው መጠን ሊያፈቅረኝ በቻለም ብዬ ተመኝቼያለሁ››

ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ አነሳትና እሱም ከተጋደመበት ቀና ብሎ ተቀመጠ… ወደእሷ ዞሮ አይን ዓይኗን እያየ‹‹አላመንሺኝም እንዴ ..? የምሬን ነው የተናገርኩት….በጣም ነው ያፈቀርኩሽ ..ወደፊት ማግባት የምፈልገው አንቺን ነው….የልጆቼ እናት ላደርግሽም እፈልጋለሁ….. ››
አንገቷን ወደእሱ ዘንበል አድርጋ እጆቾን በመዘርጋት ተጠመጠመችበት ..‹‹በጣም ነው የማፈቅርህ አንተን ስላገኘው እድለኛ ነኝ››
…..
‹‹እሺ አሁን ወጣ ብለን  ቢች ዳር ዘና እንበል…..››አላት በሀሳቡ ተስማማችና ተያይዘው ወጡ…
ላንጋኖ ሀይቅ ላይ ያረፈችው የማታዋ ጀንበር ልዩ ህብረቀለም እየረጨች ስትታይ ለአካባቢው ልዩ ውበት አልብሳዋለች…. ቢች ዳር ኳስ የሚጫወቱ አሉ..ሀይቅ ውስጥ ገብተው የሚዋኙን የሚንቦጫረቁም ጥቂት አይደሉም…… በአካባቢው ደስታ ተመርቶ የሚታደል ወይንም ከንፋሱ ጋር ተቀላቅሎ አየሩን እየሞላው በስፍራው ያለው ሰው ሁሉ እየማገው የሚፈግና የሚደሰት ይመስላል፡፡

‹‹ትዋኚያለሽ …..?››

‹‹አረ ይቅርብኝ …ዝምብለን እዚህ ሳሩ ላይ ቁጭ እንበልና  በማየት እንደሰት..ባይሆን ቆይቶ ከነሸጠኝ አብረን እንገባለን›› አለችውና ቁጭ አለች ..ተከትሎት ከጎኗ ቁጭ አለ…….

ይቀጥላል
👍12915👎15👏6😁2🔥1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
ሁለቱ ፍቅረኛሞች ከአካባቢው ተነስተው የተንቀሳቀሱት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ነበር…እያመሩ ያሉት ወደመኝታ ቤት ነበር..ልብስ ቀይረው ራት ለመብላት እና ምሽቱን ዘና ብለው ለማሳለፍ ወደ ሬስቶራንት ለመሄድ..ግን  መንገድ ላይ ያላሰቡት ሰው በዛፎችና በጭለማ የተሸፈነውን  ጠባብ  የእግር መንገድ ዘግቶ ሽጉጥ ደቅኖ ጠበቃቸው… መላኩ ቶሎ ብሎ የሰሚራን ክንድ ጨምድዶ ያዘና ጎትቶ ከጀርባው በማድረግ አሱ የግንብ ግድግዳ ሆኖ ከፊቷ ተገተረ…..

‹‹አይ አይ ….ካንተ በፊትማ እሷን ነው መግደል  የምፈልገው››

‹‹አይ እንደጀመርከኝ እኔኑ ጨርሰኝ….››

‹‹አይ መጀመሪያማ እንደህጻን ያታለለቺኝን ይቺን ጊንጥ ፊትህ ደፋትና አንተን አስከትላለሁ..››

‹‹ለመሆኑ እዚህ ድረስ እንዴት ተከትለኸን መጣህ..?››መላኩ  ነው ድንጋጤውን እንደምንም   ተቆጣጥሮ  በጣም የገረመውን እና ያልጠበቀው ነገር እንዴት ሊሆን እንደቻለ ለማወቅ የጠየቀው፡፡

‹‹እግዜር ነው እጄ ላይ የጣላችሁ..እኔማ ሀገር ሰላም ነው ብዬ ልዝናና ነበር እዚህ የመጣሁት
…ግን ሞቶ አልቅሼ በእጄ አፈር
አልብሼ ቀብሬዋለሁ ያልኩት ወንድሜ እዚህ ዘና ብሎ አለሙን ሲቀጭ አገኘሁት…..ለዛውም ገደልኩልህ ብላ 6መቶ ሺ ብሬን ቅርጥፍ አድርጋ ከበላች ቀጣፊ ሴት ጋር…››መለሰለት ሰሎሞን
መላኩ እየተንቀጠቀጠ መናገር ጀመረ‹‹ገራሚ ነህ …አንደኛ በዚህ አፍህ የእግዜያብሄርን ስም ማንሳትህ ትልቅ ድፍረት ነው..እግዚያብሄር እኮ ፍትህ ነው..እግዚያብሄር ፍቅር ነው..እግዜያብሄር የበጎነት የመጨረሻው ጥግ ነው…ታዲያ በምን ስሌት  እግዚያብሄር አንትን ረድቶህ እኛን አንተ እጅ ላይ ይጥለናል ብለህ ታስባለህ …..?ማይሆነውን…..!!!ደግሞ ገንዘቤን የምትለው…ገንዘቡ እኮ የእኔው ነው…ደግሞ እሷ እንደአንተ እና እንደዛች ሴት ከንቱ አትምሰልህ….ገንዘቡን የእኔ መሆኑን በመረዳት ሳትሰስት ሰታኛለች…››
‹‹በቃ ከዚህ በላይ ልፍለፋህን ልስማ  አልፈልግም …..አሁን አይኔ እያየ ሁለታችሁም በአንድ ሳጥን ተዳብላችሁ ትቀበራላችሁ..እዚህ የጀመራችሁት ፍቅር እዛ ያለከልካይ ትኮመኩሙታላችሁ…››ብሎ ወደነሱ የቀሰረውን ሽጉጡን ቀጭ ቀጭ አድርጎ አቀባበለ….ይሄ ቅጭልጭልታ ቀድሞ የተሰማው ለሰሚራ ጆሮ ነበር..ያው ሴት ከወንድ በላይ ንቁ አይደለች….ከሰማችው ድምጽ ጋር እኩል ተሸከርክራ መላኩን  ገፍታር ከፊቱ ተደቀነች.. ሞቱን ቀድማ ልትሞትለት….ተሳካላት…..በዛ ቅፅበት   ዶ..ዶ..የሚል አደንቋሪ ድምጽ ተሰማ  …ወዲያው የብዙ ሰው ጩኸት እና  የሚሮጡ የሰው ኮቴ …ከዛ ሰሚራ ዝልፍልፍ ብላ መላኩ  እጁ ላይ ገንደስ ስትል ይዟት ወደመሬት ሲወርድ ..ሁሉ ነገር የሚሆነው በደመነፍስ ነበር….
////
…ሰሚራ ድንገተኛ እና ያልታሰበ ከነበረው ከዛ አደጋ ከወራት  ህክምና በኃላ ዳነች…መላኩም ወንድሙንና  እና የበፊት ሚስቱን በግድያ ሙከራ እና በእምነት ማጉደል ከሶ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ  ወህኒ እንዲወረወር አድርጎ ንብረቱን መልሶ ተቆጣጥሯል….አዎ እዚህ ድረስ ያሉ ነገሮች ጥሩና መልካም የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ…እንግዲህ ይህ  ድርጊት የተከወነው ከአምስት አመት በፊት ነበር…

በመላኩ ወንድም በሰለሞን  ሽጉጥ ተተኩሶባት ፍቅረኛዋን ቀድማ በተመታችበት ወቅት ከተተኮሱባት ሁለት ሽጉጦች መካከል አንዱ ሽጉጥ በደረቷ ሌላው ደግሞ በጭነቅላቷ ነበር የገባባት…እና በወቅቱ በደረቷ የገባቸውን የጥይት ቀላሀ በቀላሉ ማውጣት ቢቻልም የጭንቅላቷን ማውጣት ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ ነበር…፡፡
አስቸጋሪነቱ ጭንቅላቷን ቀዶ ጥይቷን  መዞ ማውጣቱ አይደለም….የከበደው ጥይቷ የተቀረቀረችበት ቦታ እንጂ… ጥይቷ ከወጣች የሰሚራ የጤና ሁኔታ በቋሚነት እንደሚበላሽ ….ትውስታዋ ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ከዛም አልፎ የማሰብ አቅሞንም እንደሚጎዳው ከፍተኛ ስጋት ስለጣለባቸው….ለጊዜው  ባለበት እንዲቆይ… በየጊዜው የቅርብ የህክምና ክትትል እንድታደርግና በሂደት የሚሆነውን ለማድረግ ተወሰኖ ነበር..
ለአንድ አመት  በየወሩ እየተማመላለሰች ህክምናዋ በመከታል በጥንቃቄ  ካሳለፈች በኃላ ምንም የሚሰማት እና የሚለወጥ ነገር ስላልነበረ ቀስ በቀስ እየተዘናጋችና ምንም አይፈጠረም በሚል እምነት ክትትሉን አቆመች ….
በዛን የጊዜ ክፍተት ውስጥ…መላኩ በንግዱ አለም ከበፊቱ የበለጠ ተሳክቶለት ከሰሚራ ጋር ያየነበረው የፍቅር ትስስር ይበልጥ እየጎመራ ሄዶ ወደጋብቻ ሊሸጋገር ወራቶች ሲቀሩት….ግን ከሁለት አመት ቆይታ በኃላ ድንገት ወድቃ  ሀኪም  ቤት ዳግመኛ ለመግባት ተገደደች…  ምርመራ ባደረገችበት ጊዜ በጭንቅላቷ መሀከላዊ ስፍራ የተቀረቀረችው ጥይት ብቻ ሳትሆን በፊት ያልነበረ ጎን ላይ  አስደንጋጭ እጢ ተፈጥሮ  ታየ..ሀኪሞቹ ተደናገጡ ..ተስፋ እንደሌላት እና ማድረግ የሚችሉት ብዙም ነገር እንደሌለ ለመላኩ ሲነግሩት አንጠልጥሎ ወደውጭ ሀገር ይዞት ሄደ….ግን የረፈደ ውሳኔ ነበር…ጥይቷ እንዲወጣላት ማድረግ ተቻለ ..እጢውም በጨረር ህክምና እንዲሞሞ ማድረግ ብዙም ከባድ አልነበረም…ይ ሁሉ ቢሆን ግን በህይወት ልትቆይ የምትችለው በዛ ቢባል ለቀጣዩ አንድ ወይም ሁለት አመት እንደሆነ አስምረው ነገረዋቸዋል…ከዛ በኃላ ወይ ትሞታለች ወይ ደግሞ በድን ሆና በህይወት እና በሞት መካከል ተንጠልጥላ ለአመታት ትኖራለች…..ሚሻለው ግን ወዲያው ብትሞት ነው…. የሀኪሞቹ ምክር ነበር፡፡ …የምርመራው ወጤቱ ለሁለቱም  ሰቅጣጭ ነበር…

እንግዲህ እነዚህ ፍቅረኛሞች …ሳቃቸው ከእንባ የተቀላቀለ፤ደስታቸው ከፍራቻ የተጋባ፤ተስፋቸው ጨለማ የገደበው ከሆነ እና በዚህ ሰቀቀን ውስጥ መኖር ከጀመሩ አመት አልፏቸዋል እና ንስሯ ባመጣላት ታሪክ መሰረት በቀደም የዋና ገንዳ ውስጥ ያገኘችው ፤የፈተነችው እና የፎከረችበት ወጣት ታሪክ እንደዚህ ነው…ታማኝ የሚሆነውም ለዚህች ፍቅረኛው ነው…..አግቢኝ እና ውለጂልኝም የሚላት ይችኑ በጀርመናዊዎቹና በአሜሪካኖቹ ሀኪሞች የ አመት ጊዜ ብቻ የተቆረጠላትን ወጣት  ነው….
ኬድሮን አሰበች‹‹እና ምን ላድርግ ….?እንዳለች ልተዋት….? ትውለድለትና ትሙት…. ከዛ እኔ ለእሱ ሚስት ለልጁ ደግሞ እናት ልሁን…..?ነው ወይስ ላድናት……..?›ከህሊናዋ ጋር ከባድ ፈተና ገባች፡፡በእርግጠኝነት   ንስሯ ከረዳት ለእሷ መዳኛ የሚሆን መድሀኒት ሌላ የአለም ጥግ ማሰስ ሳያስፈልጋት …ከዚህችው ከቅድስቲቷ የኢትዬጵያ ምድር  ቆፍር ቆፈር አድርጋ  ስር ማስ ማስ ፤ ቅጠል በጠስ በጠስ በማድረግ  ልታድናት ትችላለች..፡፡ግን  ለምን ታደርገዋለች…..?ለማንኛወም ጊዜ ወስዳ ልታሰብበት ከራሷ ጋር ተስማማች….

ይቀጥላል….
👍12821👎4😁2🔥1👏1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


////
እየሄደች ነው… ልታናግረው…፡፡ ለምን እሱን ማናገር እንደፈለገች አታውቅም፡፡ ምን አልባት ዳግመኛ አጠገቡ ልትቆምና ያንን ወንዳወንድ ቁመናው እና ቆንጅዬ ባሪያ የሆነ መልኩን በቅርበት ለማየት ፈልጋ ሊሆን ይችላል….ናፍቋትም ሊሆን ይችላል፡፡ 

ንስሯ የት እዳለ በነገራት መሰረት ቀጥታ ቤቱ ነው የሄደችው..የውጩን የጊቢ በር መጥሪያ ስትጫን ዘበኛው ነበር የከፈተላት…‹‹ከመላኩ ጋ ቀጠሮ ነበረኝ ቤት እየጠበኩሽ ነው ብሎ ደውሎልኝ ነበር..?››ብላ ቀላመደች… ዘበኛው ያልተለመደ ነገር ሆኖበት .. ግራ እንደመጋባት አለና በመጠኑ ካቅማማ በኃላ እንድትገባ  ፈቀደላት…
ቀጥታ ቤተኛ እንደሆነ ሰው የተንጣለለውን ግቢ ሰንጥቃ ባለአንድ ፎቅ ከሆነው ዘመናዊ መኖሪያ ቤት  በረንዳው ላይ ደረሰች… የሳሎኑን በር ገፋ ስታደርገው ተከፈተ…የቀኝ እግሯን አስቀድማ ግራዋን አስከትላ ወደውስጥ ከገባች በኃላ  ወደኃላ ዞሯ በራፉን አንኳኳችው…
‹ከገቡ በኃላ ማንኳኳት ከገደሉ በኃላ ማዘን አይነት አይደለም እንዴ…..?››እራሷው በራሷ ነው የጠየቀችው
መላኩ የሳሎኑ መአከላዊ ስፍራ ላይ  ካለችበት ወደውስጥ 4 ወይም 5 ሜትር ያህል ርቆ በመገረም አፍጥጦ እያያት ነበር….
ማንኳኳቷን ስትቀጥል

‹‹አቤት››የሚል ድምጽ አሰማ

‹‹መግባት ይቻላል..?››

‹‹ገብተሻል እኮ ››

‹‹እሺ ካልክ›› ብላ ቀጥታ የሳሎኑን በር መልሳ ዘግታ ወደእሱ አቅጣጫ አመራች ….በተገተረበት ስለማንነቷ በመመራመር ይመስለል ፈዞ እንደቆመ በስሩ አልፋ ልክ እንደቤተኛ ሶፋው ላይ ዘና ብላ ተቀመጠች….መጣና ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ

‹‹አውቅሻለሁ ልበል..?››

‹‹እኔን የመሰለች ቆንጆ ልጅ እንዴት ልትረሳ ትችላለህ..?››

‹‹ማለት..?››

‹‹ጎበዝ የዋና ተማሪህ ነበርኩ ብዬ ነዋ››

…ድንገት እንደበራለት ሰው በመደነቅ ‹‹እንዴ አንቺ እብድ ..እቤቴን ደግሞ ማን አሳየሽ..?›› አለት ‹‹ቀላል ሰው  አይደለሁም ብዬህ ነበርኮ..?››

‹‹አረባክሽ.. ፉከራሽን እኮ አየነው..እኔማ አንተን ማሳሳት ካቀተኝ እንጠለጠላለው ብለሽ ስለነበረ..በቃ ይቺ ልጅ አልሆንላት ሲል እራሷን አጥፍትለች ማለት ነው..ምን አይነት ለቃሏ ታማኝ ልጅ ነች ብዬ ሳደንቅሽ ነበር የሰነበትኩት፤ለካ ዝም ብለሽ ጉረኛ ነገር ነሽ..?››

‹‹አንተን ማውጣት አቅቶኝ ሳይሆን አሳዝነኸኝ ነው የተውኩህ ››

ግድግዳውን ሰንጥቆ በመውጣት ውጭ ድረስ ለመሰማት ኃይል ባለው አይነት አንቧራቂ ሳቅ ሳቀ‹‹አሳዘንኩሽ…..?ቀልደኛ ነሽ››

‹‹ቀልድ አይደለም…የዛን ቀን የሄደክው ከፍቅረኛህ ጋር ወደሆቴል አልነበር…..?ስለ ጋብቻ ስታወሩ አልነበር....?እንድታገባህ ስትለምናት አልነበር…..?እሷ መጋባቱ ቀርቶባችሁ እስክትሞት ድረስ የቀራትን ህይወት እንደዚሁ እንድታሳልፉ ስትለምንህ አልነበር…..?ከመሞቷ በፊት ካላገባችህ እና መጽናኝ የሚሆን ልጅም ካልወለደችልህ በሞተች ቀን አብረሀት እንደምትሞት እየነገርካት ስትላቀሱ አልነበር……..?››

ይሄንን ስትነግረው እነዛ የኮከብ ክፋይ የሚመስሉ  ደማቅ አይኖቹን ከወዲህ ወዲያ በመገረም እያሽከረከራቸው ነበር…..

‹‹አንቺ ክፍል ውስጥ ተደብቀሽ ስታዳምጪኝ ነበር እንዴ..?››በንዴት ጡንቻው ውጥርጥር ሲልና … ልነቃት አልነቃት እያለ ከውስጡ ጋር ሙግት እንደገተመ ከሁኔታው ያስታውቃል….

‹‹አይደለም …ክፍል ውስጥ አልነበርኩም…ግን በአካል ባይሆንም ክፍል ውስጥ ገብቼ  እናንተን ምታዘብበት ሌላ ዘዴ ነበረኝ››

‹‹ምን ..?ካሜራ ..?››
‹‹አይደለም…ምንነቱን ቀስ ብዬ ነግርሀለሁ…አሁን ወደመጣሁበት ጉዳይ እንግባ››

‹‹ወደመጣሁበት ጉዳይ .. ..?በይ ሳትዋረጄ በመጣሽበት እግርሽ ሹልክ ብለሽ ቤቴን ለቀሽ ውጪ..››ከመቀመጨው ቀድሞ ተነሳ…

‹‹ሁለተኛ እንኳን እቤቴ እኔ ባለሁበት አካባቢ  በድንገት ባገኝሽ እወነቴን ነው አጠፋሻለሁ…ሲጥ አድርጌ ነው የምገልሽ….››

ዘና ብላ እንደተቀመጠች መልስ መመለሷን ቀጠለች  ‹‹ዝም ብለህ አትፎክር…በቁጣ እያንቧረቁ መናገር እና ፊትን ማጨማደድ የምትለውን አይነት ጭካኔ እንዲኖርህ አያግዝህም››

‹‹ምን ማለት ነው..?››

‹‹እንኳን እኔን ምንህም  ላይ ያልደረስኩትን ልጅ ይቅርና ሰላምን እንኳን እንደዛ በድላህ ፍቅህን ረግጣ የገዛ ወንድምህን በማግባት ስታወድምህ   ለህግ አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ምንም ልታደርጋት  አቅም አላገኘህም፡፡››
ተንደርድሮ ወደእሷ ቀረበና  ተንበርክኮ አንገቷን በማነቅ እያረገፈገፋ‹‹ማነሽ …....?አንቺን ማነው የላከብኝ....?ማነው ንገሪኝ..?››

‹‹ማንም …ምን አልባት የምታመልከው አምላክ ሊታረቅህ ፈልጎ ይሆናል…ምን አልባት እስዛሬ የፀለይከው ፀሎት አምላክ መንበር ደርሶ መልስ የማግኛህ ጊዜ ደርሶም ሊሆን ይችላል…››
፣እጁን ከአንገቷ ላይ መንጭቃ በማላቀቅ ገፈተረችውና …ዝርፍጥ ብሎ ወለሉ ላይ በቂጡ ቁጭ አለ …እዛው ባለበት አፍጦ እሷን ከማየት በስተቀር ለመነሳት አልሞከረም

‹‹ሰሚራን ባድንልህ ምን  ታደርግልኛለህ..?››

‹‹ምን  እየቀባጠርሽ ነው…...?ደግሞ በእሷ ልትቀልጂብኝ ነው..?››

‹‹አይደለም ..ካዳንኩልህ ምን ታደርግልኝለህ..?››

‹‹ቅጠል አሽተሸ በመቀባት የምታድኚው ቁስል… ምች መድሀኒት ወይንም ጅንጅብል ጨቅጭቀሽ ከሻይ ጋር አፍልቶ በመጋት  የምታድኚው  ጉንፋን በሽታ  ያመማት መሰለሽ  እንዴ..?››
‹‹አውቃለሁ…ለአመታት በጭንቅላቷ ቆይቶ የነበረው ጥይት እና የጭንቅላት እጢ ተከትሎ…….››
አላስጨረሳትም ‹‹…በፈጠረሽ ማን ነሽ ?ምንድነው ምትፈልጊው....?ይሄን ሁሉ ገበናችኝን ስንት አመት ብትሰልይን ነው ማወቅ የቻልሺው..?››

ጥያቄውን ችላ በማለት  የራሷን ጥያቄ ደግማ ጠየቀችው

‹‹ካዳንኩልህ ምን ታርግልኛለህ..?››

‹‹ እኮ እንዴት ነው የምታዲኚያት…..?የጀርመንና አሜሪካ ጠበብቶች ያቃታቸውን አንቺ እንዴት ብለሽ..?››

‹‹እኔ የተለየ መንፈሳዊ ስጦታ አለኝ …››

‹‹አላምንሽም››

‹‹እንድታምነኝ…አንድ አንተ ብቻ የምታውቀው ታሪክ ልንገርህ…እንደውም ለምን ዛሬ ያየኸውን ህልም አልነግረህም ..…››

ንገሪኝም ተይው ማለት አቅቶት በግራ መጋባት ስሜት እየዋለለ ዝም ብሎ እንዳፈጠጠባት ፈዞ ቀረ…

ጣና ሀይቅ መሀል ላይ ያለች ትንሽ ደሴት ትመስልሀለች….እሷን ከብዙ የሀገሪቷ ሀብታሞች ጋር ተወዳደረህ በጫረታ በማሸነፍ ትገዛና …በጣም ውብ የሆነ በባህላዊ መንገድ እጽብ ድንቅ ተደርጎ የታነፀ ቤት ትሰራበታለህ…በዛች ደሴት ላይ አንተ ከሰራሀት ቤት ውጭ ምንም አይነት ሌላ ቤት የለም፤ደሴቱ ሙሉውን በቡና ተክል፣በሙዝ፣በብርቱካን፣በመንደሪን፣በአፕል እና  በመሰሰሉት የሚበሉ ፍራፍሬዋች የተሞላች ነች…አዕዋፍት እና የዱር እንስሳትም  ከደኑ ጋር ስመም ፈጥረው ተፈጥሮን አድምቀው እና በተፈጥሮም ደምቅው የሚኖርበት ቦታ በመሆኑ ልዩ ድስታ ተሰምቶህ ይሄንን ስጦታ ላዘጋጀህላት ለሰሚራ ትሰጣታለህ…

‹‹ሰሚርዬ ቀሪ ህይወትሽን ምንም እንኳን አጭር ብትሆንም በደስታ የተሞላች እድትሆን ፈልጋለሁ…በዛ ላይ እዚህ ከእኔ እና ከተፈጥሮ ውጭ ምንም አይነት የሰው ልጅ ወደ ሌለበትና ወደማይኖርበት ቦታ ሳመጣሽ ቀሪ ዘመንሽን የብቻዬ ብቻ እንድትሆኚ በመፈለግ እና በመሰሰት ነው…ይቺ ስፍራ የእኔ እና የአንቺ ገነት ነች››ትላታለህ፡
👍767😁3🥰2
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
‹‹ግን ምን አይነት ዳቢሎስ ነሽ..?››ሙትት ባለ ድምጽ

‹‹ዳቢሎስ እንኳን አይደለሁም…. ምን አልባት የዳቢሎስ ልጅ ልሆን እችላለሁ…ግን የምትወዳትን ልጅ ላድንልህ እኮ ነው እያልኩህ ያለሁት .. ..?እንደዚህ አይነት በጎ ተግባር  ዳቢሎስ ያሰኛል እንዴ..?››

‹‹አዎ ዳቢሎስ ፍቅር አያውቅም..ፍቅር የማያውቅ ደግሞ ምንም ነገር በነፃ መስጠት አይችልበትም፤ለሰጠሸ ጥሩ የሚመስል ነገር ሁሉ ተመጣጣኝ የሆነ መከራና ስቃይ ያስከፍሉሻል…››

‹‹አልገባኝም..?››

‹‹ለምሳሌ …ያለፋሽበትን ገንዘብ ተመኝተሸ ስጠኝ ብትይው በደስታ ነው የሚሰጥሽ፤የገንዘብን ባለቤት ግደይና ነጥቀሺው ውስጂ ብሎ መንገድን እና ብልሀቱን ያሳይሻል…ከዛ ትገድይና ገንዘብን ታገኚያለሽ ሀብታም እና በፀፀት የሚሰቃይ ሰው ትሆኚያለሽ፡፡አንቺም ፍቅረኛህን ላድንልህ..እና ልንጠቅህ እያልሺኝ ነው…፡፡ያው እኮ ነው በስጋ ከመሞት ታድኛታለሽ ከዛ ፍቅርን በመንጠቅ በመንፈስ ትገያታለሽ…እኔንም እንደዛው፤ታዲያ አንቺ ዳቢሎስ ካልሆንሽ ማን ይሆናል....?››አላት ምርር ባለ የመጠየፍ ንግግር፡

‹‹እሺ እንግዲያው ይቅርብህ…ሁለተኛ አረብሽህም፤ደህና ሁን››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና እንደ አመጣጧ ሳሎኑን ሰንጥቃ  በርፍን ከፍታ ወጣች እና መልሳ ዘግታ መንገዶን ቀጠለች…የግቢው አማካይ ስፍራ ስትደርስ   ነበር የበር መከፈት እና ‹‹ማን ነበር ስምሽ..?››የሚል  ከሙታን  መንፈስ የወጣ የሚመስል ድምጽ  ከጀርባዋ የተሰማው

እርምጃዋን ገታችና ቀኝ ኋላ ዞራ ‹‹ሶፊያ››ስትል መለሰችለት
‹‹ከቻልሽ አድርጊው..አድኚልኝ ፤ተስማም..ቼ…ያ….ለሁ››አላትና ከእሷ ምንም አይነት መልስ ሳይጠብቅ ፊቱን መልሶ ወደውስጥ በመግባት  በራፉን በመዝጋት ከእይታዋ ተሰወረ ..

‹‹እውነትም ዳቢሎስ ነገር ነኝ እንዴ..?….ምን እያረግኩ ነው…...?››ስትል አሰበች፡፡ቅድም እዚህ እሱ ጋር ስትመጣ ይሄንን ለማድረግ አልነበረም…ዝም ብላ ፍቅረኛው እደምታድንለት ልትነግረው እና በተስፋ ልታስፈነጥዘው ብቻ ነበር ፍላጎቷ…ያደረገችው ግን ተቃራኒውን ነው..በደስታ እና ሀዘን መካከል ነፍሱ ተንጠልጥላ እዲሰቃይ ፈረደችበት …

‹‹የእውነት ግን ያልኩትን አደርገዋለሁ…..?እሷን አድኜ እሱን ነጥቄያት አገባዋለሁ…..?.ማግባትስ በእውነት እኔ የምፈልገው ነገር ነው....?ወይስ በስቃዩ ለመደሰት…..?››ብላ ተደራራቢ ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡

ለማንኛውም ዛሬ ማታ ከንስሯ ጋር ለመብረር አቅዳለች….ለልጅቷ የሚሆን መድሀኒት የት እደሚገኝ ፍንጩን አግኝታለች ….ቦረና ባሌ መካከል መዳ ወላቡ አካባቢ ነው ለሰሚራ ፈውስ የሚሆነው መድሀኒት ሚገኘው….፡፡ 
የየትኛውም ሀገር አቨዬሽን  የማይቆጣጠረው በረራ ላይ ነች፡፡ግን ደህንነቱ ፍፅም የተረጋገጠ በረራ ….ከየትኛውም አይሮፕላን ጋር እጋጫለሁ ወይም አሞራና ወፎች ተላትመውብን አቅጣጫ ያስቀይሩናል…ነዳጅ አልቆ ወይም ሞተር ጠፍቶ ችግር ላይ እንወድቃለን  ብላ የማትሰጋበት ዥዋዝዌ የመጫወት ያህል ዘና የሚያደርግ በረራ…. ይሄን አይነት በረራ ሳታካሂድ ሶስት ወራት ስላለፋት ናፍቆት ነበር…
እየሄድ ያለው ከአዲስ አበባ ወደ መዳወላቡ ነው ፡፡መዳወላቡ የት እንደምትኝ መገመት ካቃታችሁ..ኬንያ ድንበር አካባቢ ብትሉት አካባውን ለመገመት ይቀላችኋል ፡፡እየበረሩን ያለነው ከንስሯ ጋር ነው…፡፡እሱ ክንፎች  መሀከል ዘና ብሎ ቁጭ ብላለች….
ከመሬት ያሉበትንን ከፍታ ገምታ ለመናገር አትችልም ..…ግን ትንሽ ግልፅ ለማድረግ  ምሳሌ ለመስጠት ያህል በዚህ ሰዓት ( ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ነው) ሻሸመኔ ከተማ አካባቢ ደርሰዋል..እላይ ባሉበት ከፍታ ላይ ሆነው ከተማዋ ቁልቁል ስያዮት ከእሷ ቤት ጊቢ ብዙም ሰፍታ አይታያትም….ጭልጭል የሚሉ አንድ ቦታ የተሰበሰቡ መብራቶች ናቸው እንደምልክት የሚታዩት..
የሚፈልገበት ቦታ ላይ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው የደረሱት…ከአውሬ ድምጽ እና ከጥቅጥቅ ጨለማ በተጨማሪ ብዙ ድምጽ ይሰማል..የደረቁ ቅጠሎች በንፋስ ተገፍተው ከዛፍ ሲወድቁ ይሰማል…..ካረፍበት ተራራ ወገብ ላይ እየፈለቀ ቁልቁል ወደ ታች እየተምዘገዘገ የሚወርድው  አረፋ ደፋቂ ፏፏቴ ድምጽ በጣም ይሰማል…የብዙ አውሬዎች መጣራራት እና ማስካካተ ድምጽ ይሰማል…. ….

‹‹የቱ ነው መድሀኒቱ….?››ጠየቀችው ንስሯን 
አንድ ከእሷ ቁመት ብዙም የማትበልጥ ቋጥኝ ላይ ዘና ብሎ ቁጭ በማለት ዝም አለት
የሚያስበውን ማወቅ ስለፈለገች..‹‹አዕመሮህን ክፈትልኝ…..….?››ስትል ጠየቀችው… ቁልፍ አደረገና ችላ አለት ..አንዳንዴ እንዲህ ግግም ብሎ ያስቸግራታል..

‹‹ምን እያሰብክ ነው… ….?ለሊቱን እዚሁ ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር እናሳልፍ እንዴ…….?››ጠየቀችው
አዕምሮው ውስጥ ሰርስሯ እንዳትገባ እንደከረቸመባት በሹፈት መልክ አንገቱን አሸከረከረባትና ጀርባውን ሰጣት…በቃ ምንም ማድረግ አልችለችም …እስኪለቀው ድረስ መጠበቅ እንዳለባት ስለተረዳች እራሷን አረጋጋች..የሆነ የሚጠብቀው ወይም ለጊዜው ያልጣመው ነገር አለ ማለት ነው ስትል አሰበች..ተወችውና አካባቢውን በመቃኘት ዘና ማለት ጀመረች..
ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ ስታይ.. በአካባቢው በቅርብ ርቀት  ከሚገኙ የገጠር መንደሮች ጭል ጭል የሚሉትን  የኩራዝና የፍኖስ መብራቶችን  ..ወደ ላይ አንጋጣ የዘወትር አጫዋቾን ጨረቃን ስትመለከት ሰዓቱ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሆነ …ንስሯ ፀባይ ላይ ምንም የተለወጠ ነገር የለም …አሁንም የነበረበት ቋጥኝ  ላይ በተመስጦ… አረ እንደውም የፀሎት በሚመስል ሁኔታ ያለእንቅስቃሴ አንገቱን ወደጨረቃዋ አንጋጦ ተደምሟል ..
የተቀመጠችበት የወደቀ የግንድ ጉማጅ ቂጧን ስላሳመመት ተነሳችና ቀስ እያለች እሾህ እንዳይቧጭራ እና አውሬ ጉድጋድ ውስጥ ተንሸራታ እንዳትገባ እየተጠነቀቀች ወደ ፏፏቴው ተራመደች… እንደደረሰች ሙሉ ልብሷን ፓንቷንም ሳታስቀር ውልቅልቅ አድርጋ ገባችበት… ፏፏቴው ከላይ ከአለቱ እየተላተመ መቶ ጭንቅላቷ ላይ ሲያርፍ ያለውን ኃይል መቋቋም አቅቶት ልትወድቅ ነበር.. ለጥቂት ነው በአቅራቢያዋ የጋጠማትን የግንድ ቅርንጫፍ ይዛ የተረፈችው‹‹..ደግሞ ውሀው እንዴት አባቱ ይሞቃል…….?››አለችና ድክም እስኪላት ድረስ ሰውነቷን እየተገለባበጠች አስመታችውና ወጥታ ልብሷን ለብሳ ወደ ንስሯ ተመለሰች፡፡
ስሩ እንደደረሰች  ከፊት ለፊቱ ቆማ በትኩረት አየችው…መልኩ ተለየባት… የሆነ አመድ ላይ የተንከባለለ አህያ መስሏል..እንዴ ምን ላይ ተንከባሎ ነው….?..እዚህ ሰውነት ላይ ነው እንዴ ተጭኜ የመጣሁት…….?ነው ወይስ እኔ ውሀ ውስጥ  ሳለው የሆነ ነገር ከሰማይ አመድ ነፋበት..….?አረ አመድ ብቻ አይደለምል  አንገቱንም መሸከም አቅቶታል…››ስለንስሷ ቴና ሀሳ ገብቷት መነብሰልሰል ጀመረች

‹‹ምን ሆንክ….?››
አዕምሮውን ቀስ እያለ ከፈተላት፡፡እሷም እንደምንም እራሷን ለማረጋጋት ሞከረችና ወደአዕምሮው ገባች…አዎ መድሀኒቷን አየቻት …እሷ ካለችበት በ5 ሜትር ያህል ርቀት ላይ ትገኛለች…የተለየች አይነት ልዩ ተክል ነች ….?የአንድ ሰው የማህል ጣትን ነው የምታክለው…የበቀለችው ሌላ ትልቅ የብሳና ዛፍ ላይ ጥገኛ ሆና ነው….የሆነ ሀመራዊ አይነት የተለየ ብርሀን  ትረጫለች…
👍7113😁1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////

‹‹የአባትሽ ዘመዶች ነው ያልከው….?››

‹‹አዎ የአባትሽ ወገኖች … ይሄንን ተክል በምድር ላይ  እንዲበቅል አድርገው ሲበትኑት ለመድሀኒትነት እንዲሆን አስበው አይደለም…››

‹‹እና ለምድነው….?››

‹‹አንቺን ለማግኘት….››ብሎ ጭራሽ ግራ አጋባት

‹‹እንዴት አድርገው ነው እኔን የሚያገኑኝ…….?ደግሞ የት ናቸው….?››

‹‹የት እንዳሉማ ታውቂለሽ….››

‹‹እና እንዴት ነው የሚያገኙኝ ….?››

‹‹ልክ  ያቺን ተክል ስትቀነጥሺ ቀጥታ መልእክቱ እነሱ ጋር ይደርሳል››

‹‹እወነትህን ነው….?››ውስጧ ፈነጠዘች..አባቷ የማግኘት ምኞት ሳታስበው አዘለላት..የእናቷን እውነት የማረጋጋጥ ፍላጎት…

‹‹እና አሪፍ ነዋ..ያለሁበትን ካወቁ ይመጣሉ አይደለ..….?አባቴም ይመጣል አይደል….?››ጠየቀችው

‹‹አይ አባትሽ በጥብቅ እስር ላይ ስላላ መምጣት አይችልም.. ወደዚህ ምድር በመጣ ጊዜ ሳይፈቀድለት  ከሰው ጋር በፍቅር በመቆራኘትና አንቺን ስለወለደ ይሄው ባንቺ እድሜ ሙሉ እንደታሰረ ነው››አንጀቷ ተላወሰ..በምድር ላይ ታስሮ ቢሆን ኖሮ  የፈጀውን ያህል   ይፍጅ  እንጂ   መንግስትንም ገልብጣ ቢሆን አባቷን ታስፈታው ነበር

‹‹እና ታዲያ ዘመዶቹም ቢሆን ይምጡ ምን  ችግር አለው….?››

‹‹ሚመጡት  አንቺን ለመውሰድ ነው››

ደስ አለት..ደነገጠችም ‹‹ወዴየት ነው የሚወስድኝ….?››

‹‹ወደራሳቸው አለም….››

‹‹እኔ መሄድ ካልፈለኩስ….?››
‹‹ፈለግሽም አልፈለግሽም ይወስዱሻል …ምንም አይነት ምደራዊ ኃይል አንቺን ከመውሰድ አያግዳቸውም….››

ለአምስት ደቂቃ በትካዜ  ውስጥ ገባች…ሌላ አለም የማየት ፍላጎት… አባቷን እና ዘመዶቹን የማወቅ ፍላጎት..ደግሞ ይህቺን ምድርስ….?

‹‹ቆይ ሄጄ ሁሉን ነገር ካየሁ በኃላ ተመልሼ ወደምድር መምጣት አልችልም….?››

‹‹አይመስለኝም… ብትመለሺም እንደዚህ ሆነሽ አይደለም…ሙሉ በሙሉ ተቀይረሽ.. ሙሉ በሙሉ እነሱን ሆነሽ..የእነሱን ተልዕኮ ለማስፈፀም ነው ሚሆነው.ያ በእነሱ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ነው.ከፈለጉ እስከወዲያኛው ዳግመኛ ምድርን ላትረግጪ ትችያለሽ፡፡››

‹‹በቃ ይሁን.. ለእኛም እዛ መኖር ይሻለናል..የተለየ ዓለም  እኮ አሪፍ ነው..ይቺን ዓለም እንደሆነ በተቻለ መጠን በርብረናታል…ምን ይቀርብናል….?››

‹‹እና ወሰንሽ››

‹‹አዎ ባክህ እንደውም አሪፍ እድል ነው››
እንግዲያው ተዘጋጂ… ከአምስት ደቂቃ በኃላ ሄደሽ መቀንጠስ ትችያለሽ..ከቀነጠስሽ በኃላ ግን አንድ ሳምንት ብቻ ነው በምድር የመቆየት እድል የሚኖርሽ… ልክ የዛሬ ሳምንት በዚህን ሰዓት ካለሽበት ቦታ መጥተው ይዘውሽ ይፈተለካሉ››

‹‹አንድ ሰምንት..አንድ ሳምንት ፈጠነ..ግን ቢሆንም ቀላል ቀን አይደለም….ብዙ ነገር እንሰራበታለን…እናቴን ሄደን እንሰናበታለን..የልጅነት ጎደኞቼን እሰናበታለሁ… አሪፍ ነው..አንድ ሳምንት ይበቃናል..››አለችና ወደተክሏ ተራመደች..
ደረሰችና ልክ ድፍን  6 ሰዓት ሲሆን  ከብሳናው ዛፍ ቅርንጫፎች መካከል  እጇን ዘረጋችውና ጨበጠችው… ቀነጥሰዋለሁ ስትል በእጇ ሟሞና እንደቅባት ተሙለጭልጮ ወደሰውነቷ ሲገባ ታወቀት… ደነገጠች የቀነጠስችው መስሏት ነበር… እጇ ላይ ግን ምንም ነገር የለም… እጇ  የተለየ ቀለም እያመጣ ነው ..ሀመራዊ እሳት መሰል ቀለም… በመላ ሰውነቷ እየተራወጣ ከተዳረሰ በኃላ አንዘርዝሮና አንቀጥቅጦት በአፏ የቴንስ መጫወቻ የምታክል ድብልብል እሳት ብልቅ ብሎ በመውጣት እንደሮኬት ተተኩሶ ወደሰማይ ተምዘገዘገ ..እያየችው  አየሩን ሰንጥቆ ተሰወረ..ግራ ጋባት …እንደምንም ለመረጋጋት እየሞከረች ወደንሰሯ አዕምሮ ተመለስችና ‹‹ምን እየሆነ ነው….?››ጠየቀችው
‹‹በቃ ጨርሰናል እንሄድ››
‹‹እንዴ መቀንጠስ አልቻልኩም እኮ ..እጄ ላይ ምንም የለም….?››
‹‹እጅሽ ላይ ምን ያደርግልሻል …ተክሉ እኮ በመላ ሰውነትሽ ገብቶ ተዋሀደሽ..አሁን መዳኒቱ ተክሉ ሳይሆን አንቺ ራስሽ ነሽ..በዚህ የሳምንት ጊዚ ውስጥ የፈለግሽውን ማዳንም የፈለከግሽውን መግደልም  ትችያለሽ..››

‹‹ደስ ሲል ››

‹‹ደስ አይልም…››አለና ከመጣ ጀምሮ ተዘፍዝፎበት ከነበረው ቋጥኝ ላይ ክንፉን አርገፍግፎ ተነሳን ማጅራቷን ይዞ ወደሰማይ ተምዘገዘገ  ….ወደጀርባዋ ዞረና ተጣበቀባት…  ወደ አዲስአባ ተመልሰው እቤታችን ሲደርሱ ከምሽቱ 8 ሰዓት አልፎ ነበር… …

‹‹ወይኔ ድክም ብሎኛል..ግን መድሀኒቱን ስላገኘን ከአባቴ ወገኖችም ጋር ልንገናኝ ስለሆነ ደስ ብሎኛል…አንተስ ደስ አላላህም….?››ለመተኛት ወደ አልጋዋ እያመራች ነበር ምትናገረው

‹‹በጣም ከፍቶኛል››አላት ንስሯ

ደነገጠች‹‹ለምን….?››

‹‹ከንቺ ጋር የምኖረው ..በህይወትም የምቆየው ለሳምንት ብቻ ስለሆነ››

በህይወቷ እንደዚህ አይነት ድንጋጤ ደንግጣ አታውቅም.‹‹.እንዴ የእኔ ንስር ሟች ፍጡር ነው እንዴ…….?›ብላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰበችብት ጊዜ ነው

‹‹ጥዬህ የምሄድ መስሎህ ነው..አብረን እኮ ነው የምንሄደው››

‹‹ይዘሺኝ መሄድ አትቺይም››

‹‹ለምን….?››

‹‹እኔ መጀመሪያም ከዛ ነው የመጣሁት…ለአባትሽ ብዬ እና አሁን ተመልሼ ለመሄድ ፍፅም አይፈቀድልኝም፡፡››

‹‹በቃ ይቀራላ ..እስከዛሬ ካንተ  ጋር እንጂ ከእነሱ ጋር አልኖርኩ.. ምን  ያደርጉልናል እነሱ መቅረት ይችላሉ››

‹‹እሱማ ጊዜው አለፈ..ቅድም ከአፍሽ የወጣችው እሳት አነሱ ጋር መልዕክት ይዛ የምትሄድ ነች…ወደድሽም ጠላሽም አንቺን ይወስዱሻል..እኔ ደግሞ ካለአንቺ ህይወት የለኝም …ተነጥለሺኝ እንደሄድሽ ወዲያው በዛኑ ሰዓት እሞታለሁ..››

‹‹እንዴ  እሞታለሁ ማለት ምን ማለት ነው….?ይሄንን ታዲያ ተክሉን ከመቀንጠሴ በፊት ለምን አልነገርከኝም….?››

‹‹ውሳኔሽ በእኔ ላይ እንዲመሰረት ስላልፈለኩ ››

‹‹ያምሀል እንዴ . ….?.ካንተ ሚበልጥብኝ ነገር አለ…….?

ህይወቴ እኮ ነህ..››አበደች ጮህች ፕሮፌሰሩ ከእንቅልፋቸው ባነው በራፏን እስኪያንኮኩ ድረስ ግቢውን አተረማመችው …፡፡

ይቀጥላል….

#አደራ በዛውም YouTube ቻናሌን subscribe እያደረጋቹ እያደረጋቹ አይደለም አያስከፍልም እባካቹ እያረጋቹ ለሚለቀቁት ታሪኮች እንደክፍያ ቁጠሩት👇
https://www.youtube.com/@atronose

#ቻናሉንም ይቀላቀሉ ለሌላም ያጋሩ👇
https://xn--r1a.website/atronosee
👍112😢3120🔥5👏5🥰4