አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ ሰድስት (46) ‹‹እሷማ ነግራሃለችኮ ተወኝ ብላሃለችኮ» ፒተር ረጋ ባለ ድምፅ ነበር ይህን የተናገረው… ማይክልን ፊት ለፊት በጠንካራ አስተያዬት እያየ። ማይክል ይህን ሲሰማ ደነገጠ ። ሳያስበው ወደኋላ አፈገፈገ።
ደነገጦ እንጂ በአይኑ ውስጥ ተስፋ ይነበብ ነበር ። አይኑም ገፅታውም ተስፋውን ድንጋጤውንና ግራ መጋባቱን ያሳዩ ነበር፡፡ ከሁለት አመት በኋላ ነፍስ ዘርተው ። «ግሬግሰን አትሳሳት ። ተወኝ ያለችኝ ሜሪ አዳምሰን ናት ። ናንሲ ማክአሊስተርን አላነጋገርኳትም ። ሁሉንም ከሷ መስማት እፈልጋለሁ። ያ ብቻ አይደለም ። ብዙ ምርመራም አለባት። ሁለት አመት ሙሉ ለምን አልነገረችኝም? ለምን በሕይወት መኖሯን አልገፃለፀችልኝም ? ሞተች ብለው የነገሩኝ፤ ፈቅዳላቸው ነው ወይስ ... የሌላ ሰው ሀሳብ ነው ? ይኸ ሁሉ አለ ። ትጠየቃለች ። ይኽ ሁሉ ሆኖ ግን ...› አለና ንግግሩን አቋረጠ ። ጥያቄውን ከመጠየቁ በፊት መልሱን አወቀው። ቢሆንም ርግጠኛ መሆን አለበት ስለዚህ ጠየቀው ፤ «ማነው ለህክምናው የከፈለላት ?»
«ብዙ ጥያቄዎች አቀረብክልኝ ።የሁሉንም መልስ እማውቅ አይመስለኝም ፤ ባውቅም... እንደልቤ መልስ ለመስጠት የሚያስቸግሩኝ ናቸው »
«ተው ። እንዲያ ብለህ አት ....» ማይክል ይህን ብሎ ወደ ፒተር ተንደረደረ ፤ ሊያንቀው ።
ሆኖም ፒተር ብልህ ስለሆነ በቃ የሚል ምልክትና ማረጋጊያ አሳየው ፤ መዳፉን በማንሳት ። «ለቀዶ ጥገናው ሕክምናና ለመኖሪያዋ የሚሆነውን ገንዘብ የከፈለቸው እናትህ ናት ። በጣም ከፍተኛ ልግስና አድርጋለች ›› ማይክል የፈራው መልስ ይህን ነበር። ግን ያሰበውን ያህል አላስደነገጠውም ፤ አልሰቀጠጠውም። ይህን ሁሉ ሲያስበው ካጠነጠናቸው ነገሮች ጋር ይገጥማል ። አትጠቅመውም ብላ ይሆናል፡፡ መሳሳት ልማዷ ነው ማሪዮን… ማይክልን በሚመለከት ጉዳይ ላይ አሁን ደግሞ ወደ ሜሪ የላከችው እንዲገናኙ ፈልጋ ሊሆን ይች ይህን አሰበ ማይክል ። «ያንተስ ? ማለት ያንተና የናንሲ ግንኙነት ምንድነው ግልዕ አድርገህ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ »
«ያን እነኳ አንተን የሚያገባህ አልመሰለኝም »
«ስማ ጋግርት…» እንደገና በኮሌታው እንቅ አደረገው ። ፒተር እጁን አነሳ መሸነፉን ለመግለፅ ። እና «እኔና አንተ ይህን ነገር ብንተወው ምናለበት ? ሜሪ አለች አይደለም ? መልስሀን ሁሉ ከራሷ ታገኛለህ ። ጥያቄህን ሁሉ እሷኑ ጠይቃት» አለና ተቀመጠ ። «እኔ እንደሆንኩ አባቷ እሆናለሁ ። እንደኔ እንደኔ ከኔም ካንተም እሷ የተሻለውን መርጣ ታደርጋለች»
«ምናልባት ይሆናል ። ግን ይህንም ቢሆን ከሷው መስማት ነው እምፈልገው ። እንዲያውም አሁኑኑ እጠይቃታለሁ ፤እቤቷ ድረስ ሄጄ »
«ወደ ቤቷ መሄድህ እንኳ ዋጋ የለውም»
«ለምን ?»
«የለችም ። አታገኛትም» ማይክል ግራ በመጋባት ይመለከተው ጀመር ።
«እናንተ እቢሮዬ የገባችሁት ከአየር ማረፊያ ስልክ ደውላልኝ ተነጋግረን እንደዘጋሁት ነው»
«የት ሄደች ? ወዴት ሄደች ደሞ አሁን » ፒተር ለጥቂት ጊዜ ያህል ዝም ብሎ ቆዬ ። ልንገረው አልንገረው አለ ። መንገር የለበትም። ምንም ነገር መንገር አልነበረበትም። « ወደ ቦስተን ነው የሄደችው»

ይህን ሲሰማ ማይክል ለቅፅበት ያህል አይኑን በፒተር ላይ አሳረፈ ። ፈገግታ ቢጤ ፈቱን ዳሰሰውና አለፈ ። ወደበሩ የሄደው በሩጫ ነበር ። በሩን ከፍቶ ሊወጣ አሰበና ቆመ ። ዞረ ። እንዳበባ በፈካ ፈገግታ ለፒተር ስንብቱን አቀረበ ። እና… «አመሰግንሃለሁ» አለ ።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ጐሀ ሲቀድ ከመኝታዋ ተነሳች ። ድቅስቃሱ ሁሉ ለቅቋት ሙሉ በሙሉ ሕያው ሆና ። ዝንተ ዓለም ያልተሰማት መልካም ሰሜት ተሰማት ። አሁን ነፃ ናት ። ነፃ የሆነች ያህል ነው ። ተቃርባለች ። ከሁለት ሦስት ሰዓት በኋላ ሙሉ በሙሉ ነፃ ትሆናለች ። ከታሰረችበት ትፈታለች ። ያ የልጅነት ቃል ኪዳን ያ የሕፃን ጨዋታ ይህን ያህል ጊዜ ይሠራል ! ፈቀደችለታ ። የዚያ ቃል የማሰር ኃይሉ ፤ እሷ ፈቅዳ የለጠፈችበት ኃይል ብቻ ኖሯል ለካ ። ቁርስ በመብላት እንኳ ልትዘገይ ፤ ልትቸገር አልፈለገችም ። በቁርስ ፋንታ ሁለት ሲኒ ቡና ጠጣች ። ከዚያም እተከራየችው መኪና ውስጥ ገብታ ጉዞዋን ቀጠለች ። መንገዱ ሁለት በዓት ያሀል ቢፈጅባት ነው ፤ ከቦስተን እስከ ጉዳይዋ ያለው መንገድ ። አራት ሰዓት አካባቢ ትደርሳለች ። ቀትር ላይ ተመልሳ ቦስተን ትደርሳለች ። ወዲያው ወደ አየር ማረፊያ መሄድ ነው ። ወደ ሳንፍራንሲስኮ የሚጓዝ አውሮፕላን ብታገኝ . . . መሸትሸት ሲል ሳንፍራንሲስኮ ከች ነው ። ከቀናትማ ፒተር ከቢሮው ሳይወጣም ልትደርስ ትችላለች ። ያ ከሆነ ደግሞ በቀጥታ ወደ ፒተር ቢሮ ሄዳ ሳያስበው ዱብ ብላ ልታስደምመውም ትችላለች ። ምስኪን ፒተር ፤ እሄዳለሁ ስለው እኮ በጣም ተጨንቋል ። ግን ታገሰ፡፡
👍22
መንገድ ላይ ሁሉ አሁንም ሐሳቧ ወደ ፒተር ይሄድ ነበር፡፡ ስለዚህም ከከተማው ወጥታ ገጠሩን ስትያያዘው ያለ አንድም ነገር ትዝ አይላትም ። ስለፒተር ስታስብ አሳዘናት ይወዳታል ። ብዙ ውሎላታል ። እሷ ግን ምንም አላደረገችለትም ። ብትችል ብዙ ብትውልለት ደሰ ይላት ነበር። ምናልባት ከዛሬ በኋላ ሁሉ ነገር ይለወጥ ይሆናል። ያሰበውን ለመፈጸም እችል ይሆናል ። ወይስ ከዚህ በኋላም ይህን ሐሳብ ጠላችው ። እስከ መጨረሻው ለማሰብ እንኳ ጊዜ መስጠት አያስፈልግም አለች ። ፒተርን እኮ አፈቅረዋለሁ ይኸ ጥርጥር የለውም ። ዋናው ነገር ግን ይህ አይደለም ። ወደ ውጭ ስትመለከት የኒው ኢንግላንድ የገጠር ምድር ግራጫ ጥቁር ሆኖ ታያት ። ክረምቱ ቢወጣም በረዶው ቢሟሟም ዕፅዋት ገና አልለመለሙም ፣ ሣር አልበቀለበትም ። ይህን ሁለት ዓመት እሷ ብቻ ሳትሆን የገጠሩ ምድር ውበት ተቀብሮ ያሳለፈ ይመስል ። ሪቨር ቢች አካባቢ ስትደርስ አንድ ጊዜ ባዛር ተዘጋጅቶበት የነበረውን ቦታ አየችው ። ስታስታውሰው አንድ ስሜት የሠራ አካላቷን አናወጻት ። በወደቡ ዳር ዳር የሚያስኬድ አንድ ያልተጠገነ የመኪና መንገድ ተከትላ መንገድ ጀመረች ። እምትፈልገው ቦታ ስትደርስ ከመኪናዋ ወረች ። ሁለመናዋን አንድ ነገር ጨምድዷት ነበር እንጂ ድካም አልነበረባትም ። መንፈሷም ይሸበር ፤ ይረበሽ ነበር ። አሁን ወደኋላ የለም ። ይህ ነገር መከናወን አለበት ። ማድረግ አለባት…. ያ ዛፍ ታያት ። ባለችበት ላይ ቆማ ለረጂም ጊዜ ትኩር ብላ ተመለከተችው ፣ የሚያውቃት ፣ ምሥጢሯን ሁሉ የሰማ ምስክር ይመስል ። ታሪኳን የሚያውቅና እንደምትመለስ ስለሚያውቅ እሷኑ ሊጠብቅ የቆመ ይመስል ። ቀስ እያለች ወደዚያ ዛፍ ሄደች ። ልክ አንድ የምታውቀውን የናፈቃችን ጓደኛዋን እንደምትገናኝ እየተሰማት ። ግን ያ ዛፍ ጓዶኛዋ መሆኑ ቀርቷል ።. ያኔ የወደደችውን ነገር ሁሉ ስትተው እሱም ቀርቷል ፤ ትታዋለች ። እንግዳ ነው ፤ ለሷ። ከዚያም ካለፈ በናንሲ ማክአሊስተር መቃብር ላይ ከተተከሉ ምልክቶች አንዱ ነው። እዛፉ አጠገብ ስትደርስ ቆመች ። እንደገና ተራመደች ወደ ትልቁ ድንጋይ ። ያኔ እንደነበረ አሁንም አለ ። ኦልተንቀሳቀሰም ። ሁሉም ነርገ እንዳለ ነው። ከሷና ከማይክል በስተቀር ። እሷና ማይክል ግን ወዶ ተቃራኒ አቅጣጫ ተጉዞዋል፡፡ ላይገናኙ ተለያይተዋል ። ረዘም ላለ ጊዜ እድንጋዩ አጠገብ ቆመች፡፡ ሀይል ከማጠራቀም የፈለገች ይመስል ። በመጨረሻ ጎንበስ ብላ ድንጋዩን ለማንሳት መታገል ጀመረች። ድንጋዩ ቀስ በቀስ መንቀሳቀስ ጀመረ ። የነበረበትን ቦታ በእንጨት ቶሎ ቶሎ ጫረች ። አለ ብላ ያሰበችውን እዚህ ድረስ ያመጣትን ነገር ለማግኘት ። አንድም ነዢ አልነበረም ። ድንጋዩን ለቀቀችው ። ወደ ቦታው ተመለሰ ። ተስፋ አልቆረጠችም። በእልህና ባዲስ ጉልበት ብድግ አደረገቺው ይኸኔ ግን በጣም ስላነሳችው የፈለገችው ነገር የነበረበት ቦታ ባዶ ሆኖ ታያት ። አንድ ሰው ወስዶታል ። እኒያን የአንገት ጌጥ መቁጠሪያዎች አንድ ሌላ ሰው ወስዷቸዋል ። ድንጋዩን ስትለቀውና ቦታውን ሲይዝ ሰማች ፤ ድምጹን ።

« ያንችን ያልሆነ ነገር ለመውሰድ መሞከር የለብሽም ። ጌጦቹ የሌላ ሰው ናቸው ። እኔ አፈቅራት የነበረች ልረሳት ያልተቻለኝ … የሷ ናቸው » አየችው ። ማይክል ነበር ። ዓይኖቹ በእንባ ረጥበዋል

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
30👍12😁1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አንድ


#ከፍቅረ_ማርቆስ_ደስታ

...የልጃገረድ ጡት የመሰለው የሐመር ተራራ አፈዘዘው እና! ያን ማራኪ ተራራ በአይኑ ጠባው... በህሊና አኘከው... ጳ...
እኝ... ጳ... እያደረገ አጣጣመው።

hቡስካ ተራራ ላይ ሆኖ የሐመርን ምድርና ቀዬ ከአድማስ ወዲህ የአስሌንና የቡሜን ተራራ በየኮረብታው ላይ የሚታዩትን የሐመር መኖሪያ ቀዬዎች እየተጠማዘዘ ከቡስካ ተራራ ስር ጀምሮ ቁልቁል ወደ ኦሞ ወንዝ የሚጓዘውን የከስኬን ወንዝ... በአረንጓዴ
ልምላሜ የተዋበውን የሐመርን ጫካ ሲቃኝ የከብቶችን ግሣት
ሲያዳምጥ ስሜቱ ዋለለ፡፡

ደልቲ ውስጡ እንደዚያ በደስታ ቢተራመስም ውጫዊ እርጋታው ያው እንደወትሮው ነው:: ዝም!  ጅንን፡

አካባቢው በአዕዋፍ ድምፅ በሽምልማል ንፋስ ሽውሽውታ ከዛፍ እየተንጨዋለሉ በሚቦርቁት ጉሬዛና ጦጣዎች... ደምቋልዘ

ደልቲ ገልዲ ዝግባ ጥድ ግራር ካስዋበው የቡስካ ተራራ ላይ ሆኖ የአባቱን ምድር የሐመር ውብ ተፈጥሮ ሲቃኝ ቆይቶ
ከቆመበት ቦታ በስተግራ በኩል ካለችው ውብ የግራር ዛፍ ስር ሄዶ
በርኮታው ላይ ቁጭ አለ፡፡

ገሃዱ ዓለም ላይ ዋና ሥራ ጉዞ ፍቅር ጥላቻ... ይሆንና
በህሊና ቀረጢት ደግሞ ትዝታ ይከማቻል፡  ህልም ትዝታ...ማንም ከዚ ከስተት ሊያመልጥ አይችልም:: በገሃዱ የፈፀመውን
በትዝታ ምስል ያየዋል ከዚያ ይፍነከነካል ወይ ይቆዝማል! ይቅበጠበጣል ወይ ይሽማቀቃል! አልያም ይስቃል ወይ ያነባል...
ትዝታ! የተዳፈነውን እውነት እየጫረ ስሜትን ይለዋውጣል…

ደልቲም እንዲያ ከተዋበው ሥፍራ ሆኖ ዛሬን ከዛሬ ተቋድሶ ትናንትን አለማት ህልሟ  ትናንት ደግሞ የትናንት ግሣንግሷን
ይዛለት ከፊት ለፊቱ ተደቀነች፡ ጨዋታ ጭፈራ ጀግንነት ፍቅር...
አንዱ በሌላው ላይ እየተነባበረ ታየው፡፡ ገሃዱን ዓለም ከምናባዊ ትውስታው ጋር አንዳንዴ እየተጋጨ ሌላ ጊዜ እየተዋሃደ ተመለከተው የህይወት ኡደት የተፈጥሮ ባህሪ አንዱ ሌላውን እየተካ ብቅ ጥልቅ እያለ ሲያልፍ ህሊናው የትናንት ትዝታን ወደኋላ
ሲያነጠጥን ለማየት ተከተለው፡

ጦጣና ጉሬዛዎች ከዛፍ ዛፍ እየዘለሉ ሲቦርቁ አዕዋፍ ሽቅብ እየጓኑ ቁልቁል ሲወረወሩ... የደልቲ የቦዙ አይኖች የሚያዩት
ትናንትን ነው:: የትናንት ትዝታ ከሁሉም ገዝፎ በህሊናው ተንሰራፍቷል።

በዚህ የትዝታ ማጥ እንደተዘፈቀ የቦዙ አይኖቹ እንግዳ ነገር ተመለከተ
አይኑ የሚንቦገቦግ ቀንዱ የሾለ ሰውነቱ
የሚያንፀባርቅ... ግን የደነበረ አውሬ ሰውነቱ የሚንቀጠቀጥ መሸሽ
ደግሞ ያቃተው አውሬ::

ደልቲ ከትዝታ ማጡ ያለ የሌለ ሃይሉን አስተባብሮ
በመውጣት የያዘውን ክላሽንኮቭ በአውሬው ግንባር ላይ አነጣጥሮ
አመልካች ጣቱን ቃታውን ከመሳቧ በፊት ስሜቱ ሲጣራ ወስፋቱ ሲጮህ ሰማው፡፡ የተጠበሰ ስጋ ወጠሌ ጥብስ ትዝ አለው  ጎመጀ።የራበው ሰው የሚበላ ሲመጣ አይገፋም፡ ያውም ካውሬም የድኩላ
ምራቁ በአፉ ሞላ፡፡

ድኩላውን ከማሰናበቱ በፊት በመሣሪያው የማነጣጠሪያ
ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከተው። ተሸብሯል! ፍርሃትም ያንዘፈዝፈዋል! “ለማምለጥ መሞከር ሲገባው ለምን ተገትሮ ቀረ?
አይኖቹስ ለምን ይማፀኑኛል?..” አለ በማይሰማ ድምፅ

ደልቲ ግራ ገባው፡፡ ቀጭኔ ጎሽ አንበሳ... ሲገል
እየተሯሯጠ አንዱ ለማምለጥ ሌላው ለማስቀረት እየተጣጣረ...
እየወደቀ.. እየተነሳ... ነበር: ዱኩላው ግን አልተንቀሳቀሰምI
አልሮጠም ታዲያ ደልቲ እንዴት ደንግጦ የቆመ እንስሳ ይገላል!
እንዴትስ ለሆዱ  ብሎ ተሸብሮ ከፊት ለፊቱ እንደ በግ ቆሞ የሚማፀነውን አውሬ ገድሎ የአባቱን የጀግንነት ባህልና ታሪኩን
ያበላሻል።

ዘገነነው! የራሱ የሆኑት ፍየሉች በጎችና, ከብቶች
ታሰቡት። የሥጋ አምሮት የአባት ባህል... እስሜትና እህሊና ትግል ውስጥ ከተቱት። ስሜቱ በሰውና ጥብስ ብላ አለው: ሀሊናው
“ፈርቶ ደንብሮ ጉያ ውስጥ የገባን አውሬ ተኩሶ መግደል የጀግና ሞያ አይደለም። የመልካም ስም የደግነት ሥራ ጠላቱ ከርስ ነው። ሆዳምነት! እና ተወው" አለው።

ደልቲ ይህን እያስበ ዓይኖቹን ከድኖ ሲከፍት ደነገጠ:: ተምታታበት ደኩላው ከፊት ለፊቱ የለም በሱ ቦታ የተተካውን
ማመን አቃተው አይኖቹን ጨፍኖ እንደገና ከፈታቸው: ለውጥ የለም: ድኩላው የለም: እሱን የተካው ግን ከፊት ለፊቱ ቆሟል።

ምን ጉድ ነው!" ደልቲ ተሸበረ። የሚያየውን ማመን
ተሳነው። አይኖቹን ደጋግሞ እየከደነ ከፈታቸው: አዎ! ቅዠት አይደለም እውነት ነው ከፊት ለፊቱ የቆመው ሰው ነው  ልጃገረድ... ያውም የደም ገንቦ ..

ድኵላ. ልጃገረድ… ድኩላ ልጃገረድ… ህሊናው እውነቱን ለማጣራት ሞከረ።

"ለምን መጣች? ምን ጉዳይ ይኖራት ይሆን ድኩላውስ
ለምን ቆመ? ለምን ደነገጠ? የትስ ሄደ ?  ለምን በሱ ቦታ እሷ ተተካች..." ራሱን ለማሳመን ማጠፊው አጠረበት።
ልጃገረዷን  የደም ገንቦዋን አውቋታል: የወሮ መንደር
ቆንጆ ናት ግን እሷ ስለመሆኗ ማን ማረጋገጫ ይስጠው: በህሊናው
መልስ አልባ ጥያቄዎች ተደረደሩ'

“ይእ! ከመሞት እንደሁ የሚያመልጥ የለ። ነገ ወይንም ተዚያ በኋላ በወባ ሞተች... የከስኬ ውሃ በላት… ከብት ወግቷት
ሞተች... ከምባል ደልቲ ገደላት I አፍቅራው ሄዳ ፍቅሯን ሳይረዳ
ጭንቀቷን ሳይካፈላት ራቧን ሳይራብ ሙቀቷን ሳይጋራት...ጀግናው ገደላት ቢባል ምናለ!" ልጃገረዷ ከቆመችበት ሳትንቀሳቀስ
አጉተመተመች።

እሏ ያስደነበረችው ድኩላ እሷን ፈርቶ ሮጦ ደልቲን ሲያይ ከፊት ለፊቱ ቆመ: እሷም የስንት ጎረምሳ ልብ ተነጥፎላት እየረጋገጠች አልፋ በፍቅር ልቡ ርሷል ለተባለው ጀግና ፍቅሯን
ልታበረከትለት ከደስታ ፈጣሪ ደረቱ ላይ ለመጋደም ተራራውን ወጥታ ከፊት ለፊቱ ተገተረች።

“ ደልቲ ድኩላውን ለምን ሳይገለው ቀረ? የቆመ
የተሽበረ አልገልም ብሎ እንጂ ከሰማይ ወፍ የሚያወርድ ጀግና ነው፡፡
ይእ እንዲህ ነው እንጂ ጎበዝ! ምግባሩን ለአባቱ ለባንኪሞሮ ትዕዛዝ
ያስገዛ  ለሆዱ ያላደረ... ለዚህ ጀግና ፍቅር ተራራ ቢወጡ እንደ ቅንቡርስ መሬት ለመሬት ቢልወሰወሱ እንደ ኩይሳ ከፊት ለፊቱ
ተገትረው ቢኖሩ ነፍስና ስጋን ቢሰጡት ምን ይቆረቁራል

“አይ እርጋታ! ደሞ ዛሬ እንደ አንበሳ ግርማ ሞገሱ እንዴት ያምራል? እውነት ከእሱ እቅፍ ገብታ ዓለሟን ያየች ሴት ጨረቃና
ከዋክብት በሌሉበት ድቅድቅ ጨለማ ብትጓዝ ትደናቀፍ ይሆን!"ፍቅሩ ውስጧን እያመሳት ቀባጠረች

ደልቲ ከንፈሯ ሲንቀላቀስ አይቷል። የምትለውን ግን
አልሰማም፡ ልጃገረዷ አንገቷ ላይ ከደረደረቻቸው ጨሌዎች ሦስቱን
አወጣች፡፡ ትንባሆ የያዘ ትንሽ የፍየል ቀንድ በቆዳዋ ጫፍ ቋጠረችበት ፈታች። ደልቲ በትዕግሥት ይመለከታታል፡

ልጃገረዷ አይኖችዋን ሳትሰብር በፍቅር አይን አይኑን እያየች ስትመጣ ደልቲ ትዝታው እንደአውሎ ነፋስ ወደ ኋላው ነጥቆት
ነጎደ። ወደ ትናንት ወደ ድሮ: ያኔ የትናንቱ ድሮ ጎይቲ አንተነና እሱ መጀመሪያ ከዲመካ ገበያ ተያይተው በአይን ተጠቃቅስው
በልቦናቸው ተስማምተው በፍቅር መሪነት ጫካ ገብተው ያ ያዜመችለት የወንዶች አውራ ጭን ላይ ቁጭ ብላ አእዋፍና ነፋሱ
እያጀቧት የድምጿን ቅኝት
👍663
በሚጥመው ድምጽ ቃኝታ
በሚስረቀረቀው ድምጿ ስታሞካሸው ምርጫዋ ተፈቃሪው በትክክል
እሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ከጭኖቹ ላይ ተነስታ ከፊት ለፊቱ ቆማ ስትመለከተው! እሱም በፍቅር እመቤቱ ትዝታን እንደሚጫወት
አዝማሪ ኩሩው ዳሌዋን በጉንጮቹ ተንተርሶ የአንባር ማስገቢያ የመሰለ ወገቧን አቅፎ በተፈጥሮ መኝታ ቤት ተያይዘው ላይና ታች
ሲሆኑ በዝነ ህሊናው እንደገና እየተጓዘ ውበቷን እየበረቃቀሰ ሲጎመጅ ... ጎይቲ ደግሞ ያ ጎሽን የሰበረ አንበሳ ያ ቀጭኔን
የቀለመጠው አይበገሬ አጓርቶ የተወረወረን አንበሳ ያንበረከከውዐየሐመር አንበሳ እሷንም የፍቅር አከርካሪዋን አድቅቆ ለፍቅሩ
ያልወሰወሳት ጀግናና ቀብራራው ደልቲ መሆኑን አረጋግጣ የፍቅር ምሷን ወስዳ አምሮቷን ለመወጣት የቀለጠ ልቧን ወደ ደልቲ ገላ ለማፍሰስ ወደ ከንፈሮቹ ዝቅ ስትል... እያዬ ያን ደግ ትናንት ሲያልም እንግዳዋ ልጃገረድ በእጆችዋ የያዘችውን ጨሌ ሽልማት
በአንገቱ አጥልቃ ትምባሆውን ልታቀብለው ስትጠጋ ጎይቲን እንዳገኘ
ሁሉ በሰመመን ወደ እሱ ሳባት፡፡

ልጃገረዷ የደስታ እንባ
አይኖችዋን ሞላው፡፡ለካ
የተመኙትን ለማግኘት አስፈላጊው የቡስካ ተራራን መውጣት ነው:"
ልቧ እየደለቀ ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያሉ ከደልቲ ጠንካራ ጣቶች ከመሸሽ ይልቅ ወደ ጎመጀችለት ገላ ቀድማ በሃሣቧ ወደቀች። እቅፉ ሞቃት ደረቱ እንደ ኦሞ ደለል ተመቻት ገላው ደላት በደስታ ሰከረች፡

“ጎይቲ…” ብሎ  ደልቲ በቅዠት ዓለም እንደ ሰመጠ
ልጃገረዷን ወደ እሱ ይበልጥ ሳባት ልጃገረዷም በስሟ እንዳልጠራት
በሰመመን ውስጥ ሆና ብትሰማውም አካሏን ዘና አድርጋ ወደ እሱ ጉዞዋን አጣደፈች።

“ይእ! ባሻው ስም ይጥራኝ እኔ ምን ተዳዬ! ይልቅ ይኸዋ እንደ ትኩስ ወተት የሚያውደው የጀግናው ጠረን አወደኝ እቅፉ ውስጥ ገባሁ ከእንግዲህ ከዚህ ሰው ምን የምደብቀው ሚስጥር አለኝ? ምንስ የምነፍገው ነገር ይኖረኛል። ሁሉንም ይንካው እንደ
አባቴ ቁርበት አንጥፎ ይንከባላልብኝ... እንደ ጭሮሽ ወሃ የማመነጭለትን ፍቅር በእፍኙ እያፈሰ ይጠጣው" ብላ ከአካሉ ተጣበቀች።

የወፎች ድሪያ ተጀመረ: ጡቷ ደረቱን ነክሶ ያወ እጆችዋ አንገቱ ላይ እንደ ሃረግ ተጠመጠሙ የጋራ ሙቀታቸው እንደ እቶን የሚንቀለቀል እሳት ፈጠረ... ደልቲ ስርጓዳ ወገቧን እንደ ችቦ ጨምቆ ሲስባት እየተለጠጠች ወደሱ ስትጓዝ ቀንዱ ወጋት ያኔ
ከእግር እስከ ራሷ ነዘራት  ከማፈግፈግ ይልቅ…..

“አዎ! ከዚህ ደስታ በኋላ ሺ ሞት ይምጣ! የመጨረሻዋ ቀኔ ዛሬ ትሁን የአባቴ ጨረቃና ከዋክባት ብርሃናቸው ይጥፉ
የሚመስሰኝ መንገድ ሰውና ከብት የማይጓዝበት ገደል ይሁን..."እያለች ተጓች።

ነፋሱ ያገኘውን እየጠራረገ ሽቅብ ያጓነ እፅዋትን ጎንበስ
ቀና እያደረገ... ይነፍሳል። የፍቅራቸው እሳት ግን ወደ እነሱ ሊያስጠጋው አልቻለም።

ቡስካ ላይ በዚያ ለዘመናት በተገተረ ጥድ ስር... ፍቅር
ተተክሎ አደገ። አበባ ሆኖ ከመቅፅበት አፈራ ንቦች ከአባው ሊቀስሙ ወፎች ከፍሬው ሊለቅሙ አንዣበቡ ... ልባዊ የፍቅር
ጨዋታው አካባቢውን በመልካም መዓዛው አወደው: በመዓዛው አራዊት ቦረቁ አዕዋፍ ድምፃቸውን  ከፍ አድርገው ማህሌት ዜማቸውን አንቆረቆሩ ፀሐይ ዳመና ውስጥ ገብታ ሙቀቷን ቀነስች ዛፏ ጥላዋን አሰፋች... ለፍቅር ሊባል ሁሉም የየአቅሙን አደረገ።...

💫ይቀጥላል💫
👍5014🔥5🥰2👎1
አትሮኖስ pinned «#ኢቫንጋዲ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #ከፍቅረ_ማርቆስ_ደስታ ...የልጃገረድ ጡት የመሰለው የሐመር ተራራ አፈዘዘው እና! ያን ማራኪ ተራራ በአይኑ ጠባው... በህሊና አኘከው... ጳ... እኝ... ጳ... እያደረገ አጣጣመው። hቡስካ ተራራ ላይ ሆኖ የሐመርን ምድርና ቀዬ ከአድማስ ወዲህ የአስሌንና የቡሜን ተራራ በየኮረብታው ላይ የሚታዩትን የሐመር መኖሪያ ቀዬዎች እየተጠማዘዘ ከቡስካ ተራራ ስር ጀምሮ…»
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ


ሰማዩ እንባውን አንዠቅዥቆ ወጣለት: ጀንበር ግን እሷ
እየነደደች ጮራዋን እንደገና በሐመር ተራሮች አሾልካ ፈነጠቀች ዳመናዎችም እንደገና ተበታትነው ለዓመፅ ምክር ይዘዋል  በድጋሚ
ሰማዩን ለማስለቀስ ምድሯን ለማጨቅየት...

ወፎች እጅብ ይሉና ቁልቁል ደሞ ሽቅብ ይጎኑና ቀስ በቀስ ሰማዩ ውስጥ ገብተው ይጠፋሉ።

“እምቡዋ...እምቡዋ… የሚያማምሩትና
ቆዳቸው የሚያብለጨልጨው
እንበሶች ቃጭላቸውን እያቅጨለጨሉ ልብ
በሚበላ ልጅነትን በሚያስታውስ ዜማ ይጣራሉ: ጎይቲ የነሱን
ድምፅ ስትሰማ ተብረከረከች።

የተወለደችው ከጥጃ ጋጥ ጎን የተንቦራቸችው ከነሱ ፍግ ላይ የመቦረቂያ ዜማዋ የነሱ ድምፅ ጣፋጩ የልጃገረድነት ድሪያ
ከነሱ ፊት ... ያ ተመልሰው የማያገኙት የልጅነት ዘመን ያለፈው ከእነሱ ጋር... ጎይቲ ከእንስሳት ሁሉ ጥጆችን ከወንዶች ሁሉ ያን ልቧን እያዳመጠ የሚያባዝታትን ፈትሉ ፍቅር የሚያለብላትን
ነፍሷን በሐሴት የሚያንበሸብሻትን ደልቲን ይናፍቃል::

ሲያቀብጣት ከሐመር ቀዬ ከጭፍራው ቦታ ከተፈጥሮ
መኝታ ቤቷ ከምትንተራሰው የደልቲ ክንድ ርቃ የጨረቃና
ከዋክብት ውበት ከማይታይበት የዱር ፍሬ ለቅመው ከማይበሉበት
የእንስሳት ቡረቃ
ከማይታይበት እየሳቁ እየተጫወቱ
ቡና ከማይጠጣበት. አገር ቆይታ እንደ ውሃ የራባትን የአባቷን ባህል
ደልቲን ለማየት ቀን ተሌት አልማ ስትመጣ ሁሉንም እንደነበረ ስታገኘው ጀግናዋን አጣችው ያኔ የሐመር ጫካ የከስኬ አሸዋ
የቡስካ የአስሌ ተራራ ባዶ ሆነባት::

"...በሉ ተዉኝ! እኔማ ተናግሬያለሁ! ጀግና እድሜ
የለውም የጀግና ልብ ቶሎ ይቀየማል  ጀግናም ምድሪቱን ታፈቅረዋለች መከታነቱን ትፈልገዋለች'  ብዬም አልነበር!
ሳልሰናበተው አያ ደልቲ' ብዬ ስንቅ የሚሆነውን ፍቅሬን ጉያው ውስጥ ሳልወሽቅለት ፍቅሬን በአስተቃቀፌ ጥንካሬ ሳላሳየው ምርቃቱንና የፍቅር ስንቄን ሳልቀበለው ነፍሴን ባስደስታት ደረቱ
ላይ ራሴን ደገፍ ሳላደርግ! ሳብ ገፍተር በሚያደርገኝ ልቡ እንደ ቂጠማ ጎንበስ ቀና ሳልል እሱ አየሩን ሲቀዝፍ እኔ ዳሌዬን
እያሽከረከርኩ ዳንኪራ  ሳልረግጥ አምሮቴ ሳይወጣልኝ የፍቅሩ
ጣዕም ዝንተ ዓለም ከጉሮሮዬ የማይጠፋውን የፍቅሬን ጌታ  ላልሰናበተው.

ጎይቲን ሳግ ተናነቃት አይኖችዋን ከድና ስትከፍታቸው እንባዋ ቁልቁል ወረደ እንደ ምንጭ ውሃ ኮለል ብሎ የጠራ
እውነተኛ ፍቅር የተጠመቀ ንፁህ እንባዋ ጠይም ቆዳዋን እየሸረሸረው ቁልቁል ፈሰሰ

ጎይቲ እንደ ውቅያኖስ ከአድማስ አድማስ የተንጣለለው የፍቅር ዘመን መተንፈሻ አሳጥቶ እንደ ውጋት አስቃተታት: አይኗን
ብትከድን ምድር ምድር ሰማይ ሰማይ ብታይ ለውጥ የለም! ሁሉም ቦታ የሚታያት ጮርቃወ ፍቅሯና የፍቅር ጀግናዋ ነው:
ስለዚህ ጎይቲ መድረሻ ጠፋት:: አንበሳዋ ሐመርን ለቆ ጠፋ ጫካ ውስጥ ሆኖ ማግሣቱን አቆመ፡

“.ኧረ ተቃጠልሁ... ኧረ የት ሆኜ ልጥራህ... አያ ደልቲ
አንተ እኔን ብለህ ለአደን ስትሄድ እኔ በምን አቅሜ መንገዱን ይዤ ጢሻውን ጥሼ ጫካ ልግባ." ጎያቲ ወደ ሐመር ተራራ ወደ ቡስካ ፊቷን አዞራ ጮከች! አያ ደልቲ የት ነህ?... ጥቀሰኝ መፋቂያህን
እንደጎረስህ ጥራኝ... የፍቅር ጦርህን ሰብቀህ የተኛ አካሌን ወጋጋው..." ብላ ወደ ሰማይ አንጋጣ ተጣራች፡ ሰማዩ ግን ድምጿን ዋጠው ደልቲን ዋጠው ፍቅሯን ዋጠው….
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከሎ ሆራ በህምታ የምትቆዝመውን ጎይቲ ሲያይ ግራ ገባውና

“ጎይቲ” አላት

"ዩ” አለችው ከንፈሯን እያሸሸች ችምችም ብለው
የሚያንፀባርቁ ጥርሶችዋን እያሳየችው።

.እውነት ይህች ፀባዬ ሸጋ ልጅ የተሸከመችው የውበት
መዓት የኔ ነው? አላት እጁን ትከሻዋ ላይ ደገፍ አድርጎ።" እሷም የእጅ ጣቶቹን በሁለት እጆችዋ እየደባበሰች ቀና ብላ የሚያንፀባርቁ
ጥርሶችዋን እያሳየችው “ይአ!  አሁንማ የሰራ አካላቴ ሁሉ የአንተ ነው የኔ ጌታ!
ከኔ በላይ የኔ ባለቤት ነህ። ከእንግዲህ ከልቤ
የማልበው የፍቅር ወተት የአንተን ጥም ቆራጭ ነው..." ብላ ሐዘን
የተቀላቀለበት ፈገግታዋን አሳየችው።

ከሎ ሆራ! “አሁንማ የስራ አካላቴ በሙሉ የአንተ ነው..." ያለችው አባባል ከነከነው፡ ጎይቲ በዚያ የነፃነት ዘመን በሐመር
ወግና ባህል የእሱ ከመሆኗ በፊት እንደ ንብ እየዘመረች በቀሰመችው የአበባ ዘመኗ በምታደርገው  ድሪያ  የፍቅር ወለላ  እየቀመመች
ጣፋጩን ስሜት በጋራ ልሣ በእርካታ የምትንበሽበሽበት ዘመን እሸቱን ፍቅሯን እያሸች ያቃመችው ስው ሌላ ነው። ከሎም ይህን
በሚገባ ያውቃል በሥልጣኔና በተፈጥሮ ህይወት መካከል
የተከፋፈለው ህሊናው ግን የትናንቱን ድርጊት እንዲሰረዝ አሊያም
እንዲደበቅ ይፈልጋል:
የፍርፋሪ ስልጣኔ ያስተማረው የሚፈልጉትን ለማግኘት ስሜትን በረጋግዶ እጅን መዘርጋት! ችግር ሲያጋጥም ደግሞ እጅን መሰብሰብ! ስሜት ሲያስቸግር መከተል፤ ስሜት እንደ እሳተ ገሞራ
ፈንድቶ ሲፈስ መፈርጠጥ መዋሸት ፊት ማዞር... ስሜትን ከህሊናው መስተጋብር ውጭ ማድረግን ነው ያስተማረው  ከሎን።

ጎይቲ ግን ከሚካል አልባውን የከስኬን ውሃ ጠጥታ ማዳበሪያ ያልነው አፈር ያበቀለውን ማሽላ በቆሎ... በልታ ያደገች
አያት ቅድመ አያቶችዋ በተጓዙበት መንገድ በልበ ሙሉነት የምትራመድ ናትና ትናንትን በትናንትነቱ ዛሬን ደግሞ በዛሬነቱ
በሐቅ መዘከር ትመርጣለች። ስለዚህ በህሊናዋ ጓዳ የተቋጠረውን ትዝታ “አካፍይን" ካሏት ካለ ይሉኝታ እየፈታች ታሳያለች:: ሆኖ ያለፈ የደስታና የሃዘን ትውስታ በውስጧ ተከማችቶ እያስደመማት
እያስቃሰታት... እንዳልሆነ እንዳልነበረ ሁሉ የትናንትን ሁሉ  የትናንትን ትውስታ በምላሷ ጫፍ ለማጥፋት መሞከር ሞቷ ነው፡፡
ቅጥፈት ነውር ነዋ! በአባቷ ባህል።

ከሎ “...አሁንማ...”ብላ የተከዘችበት ምክንያት
አልጠፋውም፡ እንደ ወይን ታሽጎ የተቀመጠና በዋለ በሰነበተ ቁጥር ጣምናው እየጨመረ የሚመጣበት የደልቲ ፍቅር እንደሆነ ያውቃል ግን እንደ አዲስ ይጠይቃታል። ያኔም

“ጎይቲ?” አላት

“ዬ!'' አለችው።

“...አሁንማ የሰራ አካላቴ በሙሉ የአንተ ነው... ያለሽኝ ድሮስ ፍቅርሽን ለማን ነበር አልበሽ የምትሰጭው?” አላት:

“ይእ! ኧረ እዩልኝ! አንተ ሰው'' ብላ ከንፈሯ እየተለጠጠ ሲሸሽ እኒያ በረዶ የመሰሉ ጥርሶችዋ ከፊት ለፊቱ ተገጠገጡና
እንደገና ተመልሰው ተሸፈኑ፡፡
አሁን ይህን እውነት አጥተኸው ነው ድሮ ፍቅርሽን የምትሰጭው?!
ያልከኝ! ድፍን ዓለም
የሚያውቀውን! የፍቅሬን እንገር በአገሬ ጫካ እንደ እንቦሳ የጋትሁት
ለአያ ደልቲ መሆኑ እውነት አሁን ጠፍቶህ ነው። እንጥፍጣፊ ሳላስቀር ፍቅሬን ሳጠባውና ጀግናዬ ግዳዩን እንደ ባልጩት ድንጋይ በለሰለሰው ጭኑ ላይ አስቀምጦኝ ሲያገሳ ነፍሴ በደስታ ትበራለች:
ከዚያ አይኑ ላይ የተሰካውን አይኔን ሳልነቅል ቁልቁል
እንሽራተታለሁ..." ብላ የጎይቲ አይኖች ቡዝዝ ሲሉ ከሉ ሆራ እሷን የራሱ ለማድረግ በሐመር ባህል መሰረት ጫካ ለጫካ ሲዞር ግራር ዛፍ ስር ደልቲና እሷ መርፌና ክር ሆነው ሲወዛወዙ ከወገቡ
በስሜት እየተናጠ ምራቁን እያንጎራጎጨ ግንድ አቅፎ የተሻሸበትን ጊዜ አስታወሰና ቅናት ውስጡን እያተራመሰው፡-

“ከተንሽራተትሽ በኋላስ?” አላት ሳያስበው፡
👍403🥰2
“ይእ! ከዚያማ ጨረቃ ከቡሜ ተራራ ግርጌ  እንደወደቀችው ፀሐይ እኔና አያ ደልቲን ሳታዳላ ታሞቀናለች። እና አብረን እንፈላለን. ቱግ ቱግ እንላለን። ፍቅራችንን በአንድ ሾርቃ ተካፍለን እንጠጣለን ከዚያ ደግሞ አብረን እንሰክናለን፤ ጨረቃዋም
ወደ ዳመናው ትገሰግሳለች ያን ጊዜ ጨለማው ሳይመጣ ነፍሴን ሳላውቀው አሽዋው ውስጥ ሰርጎ እንደሚጓዝ የከስኬ ወንዝ ወደ አያ ደልቲ ልብ ደስ እያለኝ እስርጋለሁ" አለችና ጎይቲ የሚንሰፈሰፍ
አንጀቷን በሁለት እጆችዋ ጭምድድ አድርጋ ተንፍሳ፡-

“ያ ህይወት ግን አሁን ጉም ነው አይንን ጨፍነው የሚያዩት የስራ አካልን የሚያምስ ከመተኛት ይልቅ የሚያቃዥ..." ብላ ቀና
ስትል አይን ለአይን ተጋጩ፡ የዛሬና የትናንት ፍቅር ተጋጭቶ የፍቅር ፍላፃ ፈጠረ....

💫ይቀጥላል💫
24👍14👎2🥰2
😘  #ቃል  😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ ሰባት (47)

ሁሉም ነርገ እንዳለ ነው። ከሷና ከማይክል በስተቀር ። እሷና ማይክል ግን ወዶ ተቃራኒ አቅጣጫ ተጉዞዋል፡፡ ላይገናኙ ተለያይተዋል ። ረዘም ላለ ጊዜ እድንጋዩ አጠገብ ቆመች፡፡ ሀይል ከማጠራቀም የፈለገች ይመስል ። በመጨረሻ ጎንበስ ብላ ድንጋዩን ለማንሳት መታገል ጀመረች። ድንጋዩ ቀስ በቀስ መንቀሳቀስ ጀመረ ። የነበረበትን ቦታ በእንጨት ቶሎ ቶሎ ጫረች ። አለ ብላ ያሰበችውን እዚህ ድረስ ያመጣትን ነገር ለማግኘት ። አንድም ነዢ አልነበረም ። ድንጋዩን ለቀቀችው ። ወደ ቦታው ተመለሰ ። ተስፋ አልቆረጠችም። በእልህና ባዲስ ጉልበት ብድግ አደረገቺው ይኸኔ ግን በጣም ስላነሳችው የፈለገችው ነገር የነበረበት ቦታ ባዶ ሆኖ ታያት ። አንድ ሰው ወስዶታል ። እኒያን የአንገት ጌጥ መቁጠሪያዎች አንድ ሌላ ሰው ወስዷቸዋል ። ድንጋዩን ስትለቀውና ቦታውን ሲይዝ ሰማች ፤ ድምጹን ።

« ያንችን ያልሆነ ነገር ለመውሰድ መሞከር የለብሽም ። ጌጦቹ የሌላ ሰው ናቸው ። እኔ አፈቅራት የነበረች ልረሳት ያልተቻለኝ … የሷ ናቸው » አየችው ። ማይክል ነበር ። ዓይኖቹ በእንባ ረጥበዋል

እኩለ ሌሊት ላይ ነው እዚህ ቦታ የደረሰው ። በሌሲት ልትመጣ ትችላለች ብሎ ስላሰበ ሲጠብቃት አደረ ። የምታደርገውን ነገር ስላወቀ ጊዜ አልሰጠውም ። ከሳንፍራንሲስኮ ወደ ቦስትን የበረረው አውሮፕላን በግሉ ተከራይቶ ነው ። ያን ማድረግ ባይችልም ክንፍ አውጥቶ ቢበር እንጂ አይቀርም ነበር ። እጁን ዘርግቶ የጨበጠውን ነገር አሳያት ። ያንገት ጌጦቹ ነበሩ ። ከነአሸዋቸው ። ይህን ስታይ እንባዋ ዓይኗን ሞላው ። ‹‹ተለያይተናል ላልል ። ላልሰናበት ቃል ገብቼ ነበር ። አላደረግኩትም » አለ ማይክል ።
‹‹የት ነች ብለህ እልፈለግከኝም››
« ሞተች ብለው ቢነግሩኝ ምን ላድርግ »
«አለሁ ልልህ አልቻልኩም ››
« ለምን ?››
«የተጐዳውን ፊቴን ከለወጡልኝ መኖሬን ላልገልጥልህ... ቃል ገብቼ ነበር !! ... ደፍሬ ቃሌን ሰጠሁ ። ምክንያቱም አንተ ይህን ውል እንደማትቀበል ተማመንኩብህ ። ትተወኛለሀ አላልኩም »
«ባውቅ እመጣ ነበር ። የገባሽልኝን ቃል ታስታውሻለሽ? ›› ዓይኖቿን ጨፍና ራሷን አቅንታ በፀሎት ፅሙና ማይክል ካገኛት ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በናንሲ ማክኣሊስተር ድምፅ ተናገረች ። የማይክል ልብ በፍቅር ሲቃ ዘለለ ። በደስታ ተሞላ። «እዚህ አለት ሥር የተቀበረውን ነገር እስከዘላለም ላልረሳ ቃል ገብቻለሁ ። ወይም ተምሳሌት የሆነውን ነገር» አለች። « ረሳሽው ላትረሺው ቃል የገባሽለትን ? » ይህን የጠየቃት እንባ እያነቀው ነበር ። ስለፒተር ግሬግሰንና ይህን ሁለት ዓመት ስላሳለፈችው ጊዜም እያሰበ ። «ሞከርኩ። በጣም በጣም ምከርኩ ። ግን አልሆነልኝም» አለች ናንሲ ። « አሁንስ ናንሲ ? አሁን ቃልሽን ለማስታወስ አትፈልጊም? ቃልሽን አስታውሺ... .» ከዚሀ በላይ ንግግሩን መቀጠል አልቻለም ። አንድ ነገር ወደሷ ገፋው ። ተንደርድሮ ሄዶ እቅፍ አደረጋት ። አጥብቆ አቀፋት ። «ናንሲ! ኡሁ! ናንሲ በጣም እወድሻለሁ። ሁልጊዜም እወድሻለሁ ። መሞትሽን ስሰማ እኔም የምሞት መስሎኝ ነበር ። ሞተች ብዬ ሳስብ። እኔም ሞትኩ ። ልክ እንደሰማሁ ሞትኩ» አለ ጥብቅ አድርጎ እንደያዛት ። መልስ አልሰጠችውም ። ያሳለፈችውን የስቃይ ጊዜ አስባ፤ ይመጣል ብላ ስትጠብቀው ያሳለፈቻቸውን ወሮች ፤ ሳምንቶች ቀኖች ፤ ሰአቶች ፣ ደቅቃና ሴኮንዶች አስታውሳ ፤ ተስፋ የቆረጠችባቸው ቅፅበቶች ትዝ ብለዋት የዛሬ ደስታዋም ተደባልቆ ስሜቷን ገፍቷት ስቅስቅ ብላ ታለቅስ ነበር። እያለቀሰችም ጥብቅ አድጋ ያዘችዉ ህጻን ልጅ አሻንዱኪቱን አጥብቆ እንደሚይዝ ልውሰድብህ ቢሉት በጄ እንደማይል፤ እንደማይለቅ።

ብዙ ቆዩ ። በመጨረሻ ትንፋሸዋን እንደምንም ተቆጣጥራ ‹‹እኔም አወድሀለሁ። የፈለገውን ብልም አንድ ቀን እንደምትመጣ፤ እንደምትፈልገኝ ኣስብ ነበር» አለች። «ናንሲ…ሜሪ .. ስምሽ የፈለገው ይሁን» አለ ማይክል። ሁለቱም እያነቡ ሳቁ፤ እንደ ህፃን።

«በለቤቴ በመሆን የመጨረሻውን አክብሮት እንድታጎናፅፊኝ ልለምንሽ? እንዳለፈው ሳይሆን፤ በወግ በማእረግ እንድንጋባ። በሙዚቃ በድግስ..»

ፀጥታ። እናቱን አስታወሰ ። ሰርጓን፣ ከዚያም ገረመው። ይህን ሁሉ ያደረገች እሷ (ማሪዮን) ሆና ሳለ አልተቆጣባትም፤ ቂም አልያዘባትም ። ለምን? ገባው። ዛሬ ሁሉን ይቅር የሚልበት ቀን ነው። ናንሲን አገኘ። በቃው ። ጎንበስ ብሎ አያት ። አቅፏት እደረቱ ላይ ተለጥፋ። «እሺ?» አለ ። እራሷን በአሉታ ነቀነቀች ፤ በጣም ። «አይቻልም ፤ አይሆንም? ሙዚቃ ፤ ድግስ፣ ዳንስ !... ይኽ ሁሉ እስኪዘጋጅ መጠበቅ አለብን እንዴ!...»
«እሺ?» ሲል« ታገቢኛለሽ?» ማለቱ መሆኑ ሲገባት « አዎና ለምን አላገባህም? አሁኑኑ እንጋባ ። መቆየት አልፈልግም ። በመዘግዬት አልተማመንም ። እያንዳንዷ ደቂቃ ታስፈራኛለች ። ባለፈው የሆነው ተመልሶ የሚሆን እየመሰለኝ እሰጋለሁ ። አንተ ትመስለኛለህ የምትጎዳው . . . አንጠብቅም »

በፀጥታ ተቀበላት ። በመላ አከላቱ መስማማቱን ገለፀላት ። አንድ ጀልባ በዝግታ እየተንሳፈፈ ቀስ ብሎ ወደ ወደቡ ተጠጋ ። ደካማይቱ ፀሐይ በስተምሥራቅ በኩል ሰማዩን በስሱ ከሸፈነው ደመና ውስጥ ለውስጥ ጉዞዋን ቀጠለች ።
ሁሉም ነገር ገባው።

ተ ፈ ፀ መ ።

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
22👍14😱3🤔2
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››

ምዕራፍ አምስት

ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


‹‹ባክህ የመጣው ይምጣ…ፌዴራል ፖሊስ ሄጄ ከሳቸዋለሁ…››
‹‹አዎ ጥሩ ውሳኔ ነው…..ግን እዛ ድርስ ምን አለፋሽ ..ከዚህ ከእኔ ቤት ትንሽ ራቅ በይና ቀጥታ ለእጮኛሽ ደውይለት….››
‹‹ለምን?››
‹‹ለመሞት እዛ ፌዴራል ፖሊስ ድረስ ታክሲ ተሳፍረሽ ከምትሄጄ እነሱው ባለሽበት መጥተው ይግደሉሻል››
‹‹እና…አንተ ዝም ብለህ ታየኛለህ ?አትረዳኝም..?››
አፍጥጦ አያት….‹‹በሽተኛ ነሽ እንዴ? ለምን ብዬ እረዳሻለሁ….?አንቺን የመርዳት ምንም አይነት ቅንጣት ፍላጎት የለኝም››
‹‹በቃ?››
‹‹አዎ በቃ …ግን ደግሞ ያን እጮኛሽንና ግብረአበሮቹን እበቀላቸዋለሁ..እነሱን ከስራቸው ገንድሼ ሳልጥል እንቅልፍ አልተኛም››
‹‹እኮ እኔስ ምን አልኩህ..እነሱን መበቀል የምትፈልግ ከሆነ እኔ በጣም እረዳሀለው….እኔ እንድረዳህ ደግሞ በህይወት መቆየት አለብኝ ..?ለዛ ነው የምታግዘኝ፡፡››
‹‹አንቺ ከእነሱ የማፊያ ስራ ውስጥ ፍጽም እጅሽ እንደሌለበት በምን እርግጠኛ እሆናለሁ..?አብራችሁ ስትገድሉ እና ስትዘርፉ ኖራችሁ በጥቅም ተጣልታችሁ አሁን ለመገዳደል ሰየፍ የተማዘዛችሁ ከሆነስ…?››
‹‹ቀላል ነው…ነገ ተነገወዲያ ስለሁላችንም ሆነ ስለሆስፒታላችን ታሪክ በዝርዝር ስታጠና እና ስታውቅ እውነቱን ትደርስበታለህ..ከዛ እኔም ለአንድ ቀን እንኳን በዚህ አሻጥር ካለሁበት በቃ ከእነሱ ቀድመህ ታጠፋኛለህ…››
‹‹እንግዲያው እቅድ እናውጣ››
ፊቷ ሁሉ በራ ..ለመጀመሪያ ጊዜ የመትረፍ ተስፋ በውስጧ ሲራወጥ ታወቃት‹‹ተስማማን ማለት ነው?››ጠየቀችው
‹‹ቢያንስ ለጊዜው አብረን እንድንሰራ የሚያስችል የጋራ ፍላጎት አለን…..አሁን ለመጀመሪያ ማድረግ ያለብን ባንክ ያለሽን ብር በፍጥነት ማውጣት ነው››
‹‹ምን ያህል?››
ፈገግ አለ‹‹እንደእኔ የተወሰኑ ሺ ብሮች ያለሽ መስሎኝ እኮ ነው..ባንክ ያለሽን ብር ሁሉ እንድታወጪ የጠየቅኩሽ..አንቺ ለካ ሚኒዬነር ነሽ››
‹‹እሱን ተውና ምን ያህል ብር ላውጣ…?››
‹‹እንግዲህ እኔ ይህን ያህል አልልሽም..ግን የሆስፒታሉን ደህንነት የሚፈታተን ወንጀል ሰርተሸ እንደተሰወርሽ ፍርድ ቤቱን በማሳመን በተገኘሽበት እንድታዳኚ እና እስከዛው ባንክ ያለሽን ሂሳብ ጨምሮ ጠቅላላ ንብረትሽ እንዲታገድ እንዲያደርግ ለጠበቃቸው ነግረውት እንቅስቃሴ ጀምሯል…ምን አልባት ይሄንን ለማድረግ አንድ ወይም ሁለት ቀን ብቻ ይሆናል የሚፈጅበት….ከዛ ቡኃላ አተላዬችሽን ማሸነፍ እስክትቺይ ቢሳ ቢስቲ አይኖርሽም…እና አሁን የነገርኩሽን ከግምት በማስገባት ይበቃኛል ያልሽውን ብር አውጪ…››
‹‹ምን.. አንድ አስር መሊዬን ላውጣ…››
‹‹እንዴ? ሰራዊት ነው እንዴ የምናቋቁመው….ደግሞ አስር ሚሊዬን አውጥተሸ በኩንታል አድርገሽ በመኪና ይዘሽ ልትዞሪ ነው? ወይስ የት ልትሄጂ፡፡››
‹‹የት ሄዳለሁ? እዚሁ አንተ ቤት ነዋ፡፡››
‹‹አንገትሽን ቀንጥሼ ብሩን የግሌ እንደማላደርገው በምን እርግጠኛ ሆንሽ?፡፡››
‹‹ከዛሬ ቡኃላ በህይወት ውስጥ ባለ በምንም ነገር እርግጠኛ አልሆንም..››
‹‹እና?››
‹‹እናማ ያልከሀውን ብታደርገው ያው አደረከው ማለት ነው፡፡››
‹‹እንግዲያው አሁን የለበሽውን የባለቤቴን ቀሚስ በክብር አውልቀሽ ያገኘሽበት ቦታ መልሺና ፔስታል ውስጥ ያመጣውትን አልባሳት ሞክሪያቸው….››
ከተቀመጠችበት የአልጋ ጠርዝ ለቃ ሲገባ በራፉ አካባቢ ጣል ወደአደረገው ፔስታል ሄደችና አነሳችው፡፡ ከፈተችው..ውስጡ ያለውን ነገር እዛው ወለሉ ላይ በርከክ ብላ ዘረገፈችው….
ረዘም ያለው ቀይ ቀለም የተቀባ በጭንቅላት ጥልቅ የሚደረግ አርቴ ፊሻላ ፀጉር….
የሚሰካ ቅንድብ..ጥቁር መነፅር፤ ሶስት የሚሆኑ ሊፒስተክ ብልቃጦች… ሁለት የተለያየ ቀለም ያላቸው ቀሚሶች..ሁለት የአንገት ልብሶች…››
‹‹ምነው ፓንትና ጡት ማስያዣ ረሳህ?››አለችው …ይህንን ያለችው የገዛላት ሁሉ ከግምቷ ውጭ በመሆኑ ተገርማና ተደስታ ጥቂት ለመቀለድ ነው
‹‹ያው ሁለቱንም ትናንት እላይሽ ላይ ስላላየዋቸው የመጠቀም ልመድ የለሽም ብዬ አስቤ ነው….››
‹‹አንተ..ትናንት ያላደረኩት እኮ ድንገት ተጣድፌ ከቤት ስለወጣሁ ነው እንጂ የመጠቀም ልምድ ስለሌለኝ አይደለም፡፡››
‹‹መጀመሪያውኑስ ለምን አውልቀሽ ነው ?››
ፈተኝ ጥያቄ ጠየቃት‹‹ውይ አንተ ለካ እንዲህ ነገረኛ ነህ?››
ፀጉሩን አነሳችን አስተካክ አጠለቀች…ቅንድቦቹን ሰካካች….
‹‹እስኪ ፊትህን ወደእዛ አዙር ..ቀሚሱን ልቀይር ››
‹‹ምነው ከማታው የተቀየረ ነገር አለ እንዴ?›;ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ በቀልድ መለሰላት
‹‹አረ አታሳፍረኝ..››አለችው እንደ18 አመት ታዳጊው ወጣት እየተሸኮረመመች፡፡
‹‹እሺ በረንዳ ላይ እሆናለው ቶሎ በይ ››ብሎ ክፍሉን ለቆ መወጣና በራፉን ዘጋላት
ከላይ የለበሰችውን ልብስ ተራ በተራ አወለቀችና ካመጣላት ቀሚስ አንድን አነሳችና ለበሰች……ሊፒስቲካን ተቀባች…ጥቁር መነፅሯን ሰካችና..መጨረሷን ስታረጋግጥ ‹‹ግባ ጨርሼለሁ›› አለችው..ቀስ አለና በራፉን ከፍቶ ገባ….ዝም ብሎ ተሰጥኦዋን ለመዳኘት እንደተሰየመ የፋሽን ሾ ዳኛ በትኩረት ከላይ እስከ ታች ተመለከታት
‹‹መስታወት የት ጋር ነው ያለህ?››ጠየቀችው
‹‹ፊት የሌለው ሰው መስታወት ምን ያደርግለታል?››አለት
‹‹ምን ማለት ነው?››
‹‹ገብቶሻል››አለና ወለላ ላይ ካሉት እስካርፕ አንድን በማንሳት በአንገቷ ዙሪያ ጠመጠመላትና ‹‹አሁን ማንም አይለሽም…ተከተይኝ››
‹‹አንተማ የት ታውቀኘና ትለየኛለህ….ከአመታት በላይ አብረውኝ የኖሩ ሰዎች እጠፋቸዋለው ብለህ ታስባለህ›.
‹‹ፕሮፈሰርሽም መንገድ ላይ ገጭቶሽ እንደሚያልፍ እርግጠኛ ሁኚ››ተከታትለው ወጡ፡፡
ቀድማ ወደ ውጩ በራፍ ሄደችና ልትወጣ ስትል
‹‹ወዴት ነው?›› አላት ግቢው መሀል ላይ ቆሞ
‹‹እንዴ እየሄድን ነዋ….ምነው ቆምክ?››
‹‹በመኪና አይሻልም..?››አላት ግቢው ውስጥ ወደቆመችውና እስካአሁን ልብ ያላለቻትን አይጣማ ቪታራ መኪና በእጁ እየጠቆማት፡፡
ፈገግ አለችና ወደኃላ ተመለሰችና መኪናዋ ውስጥ ቀድማው ገባች ..እሱ ደግሞ በተራው ወደፊት ሄደና የመኪናውን በር ሙሉ በሙሉ ከፈተው.. ወደመኪናው በመመለስ ሞተሩን አስነስቶ ወጣ…..መኪውን አቁሞ ተመልሷ የከፈተውን በራፍ ይዘጋዋል ብላ ብትጠብቅም እሱ ግን ትዝም ያለው አይመስልም፡
‹‹እንዴ የከፈትከውን በራፍ እኮ አልዘጋህም?››የረሳው መስሎት ማስታወሷ ነበር፡፡
‹‹አውቄያለሁ››
‹‹አከራዬችህ ዝም ይሉሀል?››
‹‹እንዴት?››
‹‹እንዳያስወጡህ ብዬ ነዋ››
"ሌባና ማጅራት መቺን ደፍሮ ከቤቱ የሚያስወጣ አከራይ እምብዛም የለም"አለት ኮስተር ብሎ
"እሱስ እውነትህን ነው ..መጀመሪያውን አለማከራየት እንጂ ካከራዩ ብኃላማ እንዳልከው ጣጣው ብዙ ነው።"
"አሁን ገብቶሻል...በይ ወደቁም ነገሩ እንመለስና የት ባንክ ነው የምውስድሽ .?"
"..መጀመሪያ ንግድ ባንክ"
"እሺ"
"ያው እንደውም ንግድ ባንክ...ቦታ ፈልግና አቁም አለችው" በሚሄድበት መንገድ ሀምሳ ሜትር ርቀት ላይ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አይታ ። እሱ ግን ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን ዝም ብሎ ነዳው።
"አልሰማሀኝም?"
"ሰምቼሻለሁ ግን በሀሳብሽ አልተስማማሁም...ሂሳብሽን ባንቀሳቀሽ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ የትኛው ቅርንጫፍ እንደነበርሽ መረጃው ይደርሳቸዋል ..ከዛ አካባቢውን ማሰስ ይጀምራሉ።ይሄ አካባቢ ደግሞ ከእኔ ቤት ቅርብ ነው ።አንድ ወረዳ ብቻ ሳይሆን ተመሳሳይ ቀበሌ ውስጥ ነው..."
"ስለዚህ ክፍለ ከተማ እንቀይር እያልክ ነው።››
👍29🔥31
"አዎ በትክክል ...ካለንበት ጋር የማይዋሰን"
ቀጥታ መርካቶ ነው ይዞት የሄደው።እንደዛ ያደረገው አንድም ከእሱ መኖሪያ አካባቢ ስለሚራራቅ ሁለትም ግርግር ያለበትና በሰው የተሞላ በመሆኑ ድንገት ቢመጡባቸው እንኳን በሰው አጀብ ተከልለው ለማምለጥ የተሻለ እድል የሚሠጥ ቦታ በመሆኑ።ሲደርስ ከባንኩ 50 ሜትር ርቀት ላይ አቆመና...አሁን በግር እንሄድ ብሎ ጎን ለጎን መሄድ ጀመሩ ..በራፍ አካባቢ ሲደርሱ" እንቺ ይሄን ስልክ ያዢ ..እላዩ ላይ አንድ ቁጥር ብቻ ነው ያለው እሱም የእኔ ነው ..የሆነ ችግር ወይም አጠራጣሪ ነገር ካየሽ ወዲያው ደውይልኝ።"
"የሆነ የሞሳድ ወይም የኬጂቢ ሰላይ የሆንኩ ነው የመሠለኝ"
"ብትሆኚ ነው የሚሻልሽ"
"እሺ የባንክ ቁጥርህን ስጠኝ?"
"እርግጠኛ ነሽ...?"
"ባክህ ጊዜዬን አትብላው።"
ከኪሱ ወረቀትና እስኪሪብቶ አወጣና ጫር ጫር አደረገና አቀበላት"
አቢዬት እንደልብ
100002385....
አነበበችና ፈገግ አለች
"ምነው ?"
‹‹ምንም አይደል አቢዬት ››ብላው በፈገግታ እንደተሞላች ወደውሰጥ ገባች

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
15👍8😱1
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ፀጥታውን አዳመጠው፡ ይንጫጫል: ስልቱ ግን ጣፈጠው።እንደገና ጆሮውን አቁሞ ሰማ... “በዚህ ትርምስ በሞላበት ዓለም
ምናለ ፀጥታም በካሴት ታትሞ ቢሸጥ?“ ተፈላሰፈ።

ኤርቦሬ ማሕበረሰብ ውስጥ እያለ ህይወቱ ቀለል ያለ
ይመስላል። በእርግጥ ይበላል: ልብስ ግን አልነበረውም:

...ይህን ግዙልኝ መጫወቻ አምጡልኝ ኬክ ቤት
ውሰዱኝ..." ብሎ አላስቸገረም ወይንም አልተቸገረም:: እራሱን
ከጓደኞቹ ጋር በዚያ የእንቦቀቅላነት ዘመኑ አላወዳደረም: ሕይወት
ተመሳሳይ ነበረች። ራቁት ሆኖ አፈር ረጭቶ አቧራ አቡኖ ከበግና ፍየል ግልገሉች ጋር ሮጦ ነበር የኖረው።

“ተማር ህይወትህን ለውጥ ለወገንሀ ጠቃሚ ዜጋ ሁን..." ብለው ከባሕሩ አስወጡት: ያኔ እንደ ዓሣ ጨነቀው:: ግን መኖር ቻለ አዲስ ንድፈ ሃሳብን አወቀ።
አወቀ።ህልሙ ግን እውነት
አልሆነለትም ማወቅና መተግበር አራምባና ቆቦ ' መሆናቸውን ተረዳ። ተቀምጦ ታሪክ በሚያወራ ተማርሁ' ብሎ ብርጭቆ
ጨብጦ የካምፓስ ሕይወት" እያለ ከሚቦተልከው ራሱን አርቆ
ለሃገሩ ለአፍሪካ ለዓለም ለዚች ፕላኔት ቤዛ የመሆን ህልሙ አስኳሉ እንደወጣ እንቁላል ኮፈኑ ብቻ ቀረ። ኮፈኑ ይለብሳል ኮፈኑ
ያጌጣል ኮፈኑ ያዝናናል... ህሊናው ግን አፍሮ ተደብቋል።

የልመና እጆች ሲበራከቱ ማጣት ሲንሰራፋ ጥላቻና በቀል ለዚህ ማዳበሪያ እየሆነ አለመግባባትን ሲያበቅሉ እያዬ ሀዝቡን
እሚያስተምረው ስለ አተሞች በአይን ስለማይታዩት ሕዋሳት ነው::
የወገኑን ህይወት ለማይቀይረው ትምህርት ለዘመናት ባዘነ  ትምህርት ግን ማውራትን እንጂ ጥጃ መጠበቅን በጦር መሬት
ወግቶ በቆሉ መዝራትን አስረሳው። እውቀት ፈጠራ የነጮቹ ወሬ መናቆር የእኛ መሆኑን አምኖ እነሱ ሰርተው ላመጡት ግኝት ዜማ ይሰጡትና ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ እያጨበጨበ እንዲዘምር ይነግሩታል።
እና! የወር ደመወዝ የሚያገኝበትን ሲዘምር ይውላል። ከዚያ ብርጭቆ
ውስጥ ተጠቅልሉ ያመሻል። ሲሞቀው እንደ ህፃን እየተወለጋገደ
ሲኮላተፍ ይተኛል።

ነገ ግን ያው ነች:: እሱም ነገን ለውጥ እንደሌላት ያውቃል፡ በትናንት የተዘራ በዛሬ የተኮተኮተ... የለም፡ እና ከነገ እንዴት ፍሬ
ይጠበቅ!

በእርግጥ በህፃንነት ዘመኑ ማንም ሳያስተምረው ያወቀው ማልቀስን ነው: ከዚያ መሰል ተፈጥሯዊ ክስተቶች ተጨማሪ ግን
ሁሉንም ነገር ለማወቅ ህሊናው ሲፈልግ እጆቹ ሲወራጩ እግሩ ሲኳትን... የእንቦቀቅላነት ዘመኑን ያሳለፈው በደስታ ነበር። ከሁለት በላይ በሆነ ባህል ውስጥ ተሰንቅሮ ይህን አትይ ያንን አትንካ እንደዚህ አትናገር ያ መጥፎ ነው ያስቀጣል ያሳስራል... እየተባለ በአዳዲስ ሃሣቦች ሲኮረኮም ሲገሰፅ ሲቆነጠጥ ኖረ:

ህሊናን የሚያዞር የህይወት ፈተና! የመፈቀርና የመጠላት እጣ የማግኘትና የማጣት የተንኮልና የጥላቻ... አንዱ እያጣደፈ
ሲያስቀምጠው ሌላው ሲያስኮፍሰው እንደ ፊኛ ሲነፋ ቱሽ ተደርጎ ሲጎድል ሕይወት ስትጥመው ስትመረው ያዝኩሽ ሲላት
ስትርቀው ራቅሽ ሲላት ቅርብ ነኝ እያለች ስትሸነግለው ኖረ።
ዛሬና ትናንት እንዲሁ በተስፋና ቅዠት አለፉ። ነገ ደግሞ አካሉ ያረጃል መንፈሱ ይደክማል ውበቱ ይረግፋል... ያኔ ይቆዝማል
ህይወት ግን ማዕበል አሳሯን እንደሚያሳያት ጀልባ እየዋዠቀች እንኳ የምትጥም ትሆንበታለች ህሊናው ሁሉም ያልፋል በሚል እምነት ቢታጨቅም የሚተማመንበት ያጣል መኖሩን ማሪጋገጥ
አይችልም ልቡ በፍቅር ቢጠማም ጥም መቁረጫውን አያገኝም።
መስታዋት የማያ ሰበቡ ይጠፋል... ከስዎች ጋር እንዳልናረ ሁሉ ያለፈ ህይወቱን ሲከልሰው ብቻውን ጡል ጡል እያለ መኖሩን ይረዳል። ይህን ሲያስብ ያሳላፈው ህይወት ጣምናው ይጠፋዋል።
ስለዚህ “መጥኔ... አይ ህይወት...” እያለ እየተትከነከነ ወደዚያ አቀበት
ይኳትናል  ወደ ሞት ሲረግጣት የኖረችው ምድር ስትውጠው እስትንፋሉ ሲቆም. ያኔ “...ይብላኝ ለቋሚ ( ሟችስ ጣጣውን ጨርሶ ወደ እውነተኛው ዓለም ሄዴ.. ተገላገለ” ይባላል። ይህም ግን
“ይባላል" ነው። ተዚያ ወዲያ ሕይወት የግል ሚስጥር ነች ለተጓዦች!

ሶራም ይህን ተራራ መውጣቱን ተያይዞታል: ጫፉ ዳመና  ውስጥ የገባው ተራራ ግን መንገድ አልባ እሾህ የበዛበት
የሚያንሸራትተው የበረከተ... አስፈሪ ነው:: ያለፉበትን ሲያዩት ያስፈራል
ገና የሚወጡት ደግሞ ከማስፈራራትም ያስጨንቃል: በዚያ ላይ የሚፈራረቀው ብርሐንና ጨለማ ቆፈንና ሙቀት. ያታከታል።

መፅናኛው ግን ብዙ ነው: ጠኔ ያስቸገረው አካለ ስንኩሉ የእለት ጉርሱ ያጣው በሽተኛው ያን ሲያዘይ የሙከራ ጥረቱ
ይጨምራል... ካሰበው ቦታ ስለመድረሱ ግን ማረጋገጫ ያለው የለም።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ህሊናው አካሉን እየቧጨረ እየታገለ... እረፍት ሲነሳው
እንደቆየ የቤቱ በር ተንኳኳ።

“ይግቡ...” አለ በታከተ ድምፅ ቅላፄ። ደሞ ማን ይሆን እንደ መርዶ ነጋሪ በጠዋቱ የመጣብኝ' እያለ በር በሩን እያዬ በሩ በዝግታ ሲጢጥ…” ብሉ ሲከፈት ተረከዘ ሎሚ ከበሩ ግርጌ
ተመለከተ።

ማናት...?” አለ ግራ እየገባው ከዚያ ከተጋደመበት ቀና
ብሎ አይኑን እንደ አበያ በሬ አፍጥጦ ጆሮውን እንደ ጥንቸል ቀሰረ:

ግቢ... ማን ልበል?"  ያላሰበውን ዓረፍተ  ነገር ከራሱ አንደበት ሲወጣ ተስማው። እንግዳዋ ረጋ ብላ ወደ ውስጥ ዘለቀች።

“ይቅርታ!... ካለቀጠሮ በመምጣቴ...” አለችው የቤቱ ብርሃን ደብዘዝ ስላለባት አይኖችዋን ፈጠጥ አድርጋ፡

"ምንም አይደለም” ብሎ ፈገግ አለ፡ ማንነቷን ለማወቅ ህሊናውን ውለዳት ቢለውም ሊያገኛት ሊያውቃት አልቻለም።
ከመቀመጫው ተነሳና ወንበር ቀረብ አድርጎላት! “እዚህ ላይ አረፍ በያ! እያለ እሁንም ሊያስታውሳት ሞከረ: መልኳን ከዚህ በፊት
ያየው መሰለው። የት ነው የማውቃት?' ጠየቀ ራሱን።

"ካለቀጠሮ በመምጣቴ ይቅርታ" አለችውና አንገቷን ደፋች፡፡ “ለነገሩ  ቀጠሮ  አስፈላጊ ነበር ለማለትም ይከብደኛል" ቀና ብላ
አይታው አሁንም ሃሳቧን ገታችበት።
በሃሳቡ! ቀጠሮ የምን ቀጠሮ?' ብሎ እንዳሰበ በመላምት ህሊናውን አገለባበጠና ሃሳቡን ማጠቃለያ ላይ ለጊዜው ደረሰ: ልቡን ደስ አለው፡ ሴት ልጅ አፈቀርሁህ ብላው አታውቅም እሱ ግን ብዙ
ሌሊት ኮርኒሱን በአይኑ ሲቧጥጥ ቀን ላይ እንደ ክምር ፈጅ ገመሬ
ዝንጀሮ በአይኑ መሬት ሲያርስ ኖሯል፡

“ለጊዜው የኔም ቤት  የተከራየሁት ማለቴ ነው ከዚህ ብዙም አይቀርም። የማልኮራበትም ስራ አለኝ አለችና አሁንም በስርቆሽ ተመለከተችው።

ላቡ ግንባሩ ላይ ተንቸረፈፈ: ተቀጥቶ አፍህን ያዝ
እንደተባለ ህፃንም የፍርሃቱ ሳግ ላይ ላይ ሲያቃትተው

“ምን ነካኝ?” ብሎ
ተወራጨ። እግሮቹን እየቀያየረ አነባበራቸው፡ እጆቹን እንደ ሙሾ አውራጅ አወዛወዛቸው:

“ተናኘ... ተናኘ ወርቅ
እባላለሁ። ቶምም ይሉኛል
የሚቀርቡኝ:: ብዙ ጊዜ እንደ ቶማስ ሳላይ አላምንም ስለምል: ስለ ቶማስ ታውቃለህ መቼም? ቀና ብላ አየችው:

“አዎ! እየሱስ ሞትን ነስቶ ወደ ደቀመዝሙሮቹ መጥቶ
“እኔ ነኝ' ሲላቸው ካላየሁ አላምንም' ያለውን ነው" አላት። ፈገግ ብላ ትክክል መሆኑን አረጋገጠችለት “ሻይ ቡና” ምርጫ አቀረበላት:

“ኡፍ አንተም የሞቀ ውሃ ሰጥተህ የሚተናነቀኝን ቁልቁል ልታወርደው ትፈልጋለህ?" ነብር ሆነችበት አራስ ነብር::
👍26😁3
“ይቅርታ!  እሽ ወንበሩ የተመቸሽ አይመስለኝም” ድምፁ ተቋረጠ የሚተናነቀኝን  ቁልቁል ልታወርደው ትፈልጋለህ?'
እንደገና ደስ አለው። ትዕግስት ፍሬዋ ጣፋጭ ነው' የት ነበር ይህን
ጥቅስ ያየሁት የጥቅሶች ሁሉ ጉልላት ማለት እሱ ነው፡ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ስንቱ በፍቅር ህሊናውን እየዘረጠጠ ተቀጨ። እኔ ግን ይሄው በትዕግሥቴ ከማፍቀር ወደ መፈቀር ማማ ልወጣ ነው“ ብሎ
እንዳሰበ ሌላ ሃሳብ ደግሞ ተግተልትሎ መጣበት። ሊሸሸው ሞከረ አቃተው ሃሳቡ እንደውሻ ዘሎ ተከመረበት።

የማልኮራበትም ስራ አለኝ... ይህማ ሊሆን አይችልም:: መሆንም የለበትም። ግን እኮ የተከራየሁት ቤት ከአንተ ቤት ብዙ አይርቅም ብላዋለች። ጠረጠራት። እድሜዋ ግን ለጋ ነው፡ ጡቶቿ እንኳ አልወደቁም። ጉንጯ እንደሚጎመራ ብርቱካን ገና በመቅላት
ላይ ነው... ተምታታበት

“በእርግጥ ሴት ነኝ: በእድሜ ልጅ በተግባር ግን ሴት ሙሉ ሴት᎓ ትምህርት ቤት ናት ይባል የለ ህይወት።" የፊቱ መቀያየር ወንድነቱን ሲፈታተነው የሚያገሳው የስሜት ግሣት
ከረፋት።

"ሴት የወንድን በር አንኳኩታ ስትገባ ሁሌም መንፈሷና
አካሏ ለድሪያ ቢቋምጥ ነው መባሉ አይቀር አይደል! እና አንተም አመጣጤን በለምድከው የወሲብ ፍች ፈታኸው: አራሷ  ነብር
ተቅበጠበጠች:

“ሴትን ልጅ አይቆረቁራትም አይከፋትም እንደማዕበል
ህሊናዋ ውስጥ የሚቀሰቅስ ሃሳብ የለም ወሲብ የራባት ብቻ ናት...
ብለህ ታምን ይሆን?  እባክህ እንደዚያ እንደሚያስቡት አታስብ።
ህሊና አለን! የእድሜ ጓደኞቻችን ከሆኑ ወንዶች ይልቅ ሴትነታችን ጠልቀን እንድናውቅ ረድቶናል" አለችና ፍርሃቷ አካሏን
ሲያንገጫግጨው ከንፈሯ ሳይቀር ተንቀጠቀጠ።

“..እዚች ድህነትን በንቦቀቅላነት በምታወርስ ሀገር ለምን ተወለድሁ? ልትመልስልኝ ትችላለህ?" በጥያቄ አፈጠጠችው።

እድላችን ነው: አሁን መነሳት ያለበት ጥያቂ አይደለም።
መልሉ የተሰጠ ጥያቄ ጥያቂ ሊሆን አይችልም
ይልቅስ ሁሉንም በፀጋ ተቀብሎ መኖር ነው" ለምን በምን. ላይ ያተኮረ
ሃሳብ  ሃሳብ እንዳላት ሊገባው  አልቻለም  ስለዚህ ደስታው እየኮለመነ ግራ መጋባቱ እያየለ ሄደ።....

💫ይቀጥላል💫
👍27
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ ስድስት
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

የዳይመንድ ኢንተርናሺናል ሆስፒታል ከፍተኛ ባለአክሲዬኖች ሼክ ጠሀ ቤት በሚገኝ ምድር ቤት ውስጥ ስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡በስብሰባው ላይ የተሳተፉት አራት ሰዎች ናቸው፡፡ፓሮፌሰር ይሳሀቅ፤አቶ ሙሉ እና ሼክ ጠሀ ሲሆኑ በተጨማሪ የጋንግስተሮች ዋና ሀላፊ ዶዬ የሚባለው ወጠምሻ ተገኝቶል፡፡
አራቱ ሰዎች ጠረጵዛውን ከበው ተቀምጠዋል፡፡ፕሮፌሰሩ ስብሰባውን አጠር ባለ ንግግር ከፈተ …..እንግዲህ ለምን እንደተገናኘን ከመካከላችን የማያውቅ ሰው አለ ብዬ አላስብም ፡፡ካለም ያው ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጧል ማለት ነው፡፡
አሁን ዶክተሯ ተገኝታ አፎን እንድትዘጋ እሰከልተደረገች ድረስ ከፍተኛ አደጋ ላይ ነን….ሴትዬዋ ለሆነ ከእኛ ሰርክል ውጭ ላለ አንድ አካል የምታውቀውን ነገር ተናገረች ማለት የወንጀሉ አይነት ሆነ በወንጀሉ የተጨመላለቁት ሰዎች ብዛት ተግተልትሎ የሚያልቅ አይሆንም….እንደው እሷ ባትናገር እንኳን አሁን የተፈጠረውን ነገር ከእኛ ጋር የሚሰሩት ትላልቆቹ ባለስልጣን ጆሮ ቢደርስ ለራሳቸው ደህንነት ሲሉ ቅድመው ሊያጠፉን ይችላሉ…
‹‹እና ምን እንዳርግ?፡፡››ሼኪው በለዘብተኛ ንግግር ጠየቁ
‹‹አቶ ሙሉ በከፍተኛ ብስጭት እድል እስኪሰጠው እንኳን ሳይጠብቅ መናገር ጀመረ…‹‹ይህ ግልፅ ነው…ያለ የሌለ አቅማችንን አሞጠን እሷን አግኝቶ ማስወገድ ነው ከዚህ መአት መውጫ ብቻኛ መንገዳችን፡፡..ጠቅላላ አዲስ አበባን በርብረን መፈለግ አለብን ;;በየወሩ በመቶ ሺ ብሮች ወደካዝናቸው የሚከቱት እነ ዶዬ ይሄንን ማድረግ ካቃተቸው ጥቅማቸው ምንድነው….?ደግሞ ከሀገር እንዳትወጣ አየር መንገድ አካባቢም ክትትል ማድረግ አለብን…ዘመዶችም ክፍለ ሀገር ካሏት ከውስጥ አዋቂ ጠይቀን ልትሄድ ትችላለች በተባለ ከተማ ወይም መንደር ክትትል ማድረግ አለብን፡፡..ጨርሼያለው››
ፕሮፌሰሩ ተቀብሎት መናገር ጀመረ..‹‹አቶ ሙሉ አሁን የተናገርከው ሁሉ እያደረግን ያለነው ነገር ነው…..እና ደግሞ ስትናገር እንደወንድ በቀጥታ ብታደርገውና አሽሙር ባትቀላለቅልበት ጥሩ ነው….ውስጥ አዋቂ ማለት ምን ለማለት ነው? እኔን ለመንካት ነው?ደግሞ አሁን የተገናኘነው አዲስና የተለየ ሀሳቦችን ለመስማት ነው…ለምሳሌ ሴትዬዋ ከእጃችን አምልጣ እሷን ማሳደድ ከጀመርን ከለሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ እስከ አሁን ….አሁን ስንት ሰዓት ነው?እጁ ላይ ከሰረው ሰዓቱ ሰዓት አየና ‹‹አምስት ሰዓት..እስከአሁን ቢያንስ ከሶስትና ከአራት ሰዎች ጋር ተገናኝታ ሚስጥራችንንም ተናግራ ሊሆን ይችላል እና የሚያበሳቸው ደግሞ አሁን ባለው ሁኔታ ባገኘናት ቦታ ደፍተናት ዞር ማለት አንችልም …››
‹‹ለምን?›› አሉ አዛውንቱ ሼክ ጠሀ ……ጭል ጭል በምትል አይናቸው በትዝብትና በጥርጣሬ አጨንቁረው እያዩ
‹‹አሁን የምንችለው እንዳገኘናት ከእነ ህይወቷ አፍነናት ወደሰዋራ ማቆያ ቦታ መውሰድ ነው፡፡ ከዛ ቡኃላ…ከማን ጋር እንደተገናኘች ..?ምን መረጃ እጆ ላይ እንደለ ካጣራን ቡኃላ ነው እርምጃ መውሰድ ምንችለው››
‹‹እሺ ብላ ትነግረናለች?››
‹‹እሷ ትገኝ እንጂ እሱ የእነዶዬ ስራ ነው..ከፈለጉ ገርፈው ከለበለዛም ሰውነቷን እየቆራረጡ በአእምሮዋ የሰወረችውንም ሆነ በሆዶ የቀበረችውን የምታውቀውን ሚስጥር ሁሉ እንድትናዘዝ ማድረግ አለባቸው ››
‹‹እሱ አያሳስባችሁ….እኔ እራሴ አናዝዛታለሁ….አስር ደቂቃም እትቋቋመኝም››በልበ መሉነት ማረጋገጫ ሰጠ፡፡
‹‹ግን በእውነት ልታገባት የወሰንካት ፍቅረኛህ ነበረች?›ገርሞቸው የጠየቁት ሼክ ጠሀ ናቸው
‹‹አዎ …አሁን እዚህ ጋር እያወራን ያለነው ግን ስለ ፍቅር ጉዳይ አይደለንም..የህልውና ፊልሚያ ላይ ነን››አለ ኮስተር ብሎ፡፡
‹‹ይሁን…ሌላው እሷን ማሳደዱ እንዳለ ሆኖ ነገሮች መስመር ይዘው ወደቀድሞ ቦታቸው እስኪመለሱ ድረስ ከሆስፒታሉ ከሚሰጡ መደበኛ ህክምናዎች በስተቀር ሌሎች ሙሉ በሙሉ ይቁሙ…..ለተለዩ ተግባራት የሚንገለገልባቸውን መሳሪያዎችም ከሆስፒታሉ ልዩ ክፍሎች ዛሬውኑ ወጥተው በጣም አስተማማኝ ወደሆነ ቦታ ሄደው ይቀመጡ…ፕሮፌሰር ከአንተ ጋር የሚሰሩትም ረዳቶች ከጥሩ ጉርሻ ጋር አረፍት ቢወጡ መልካምይመስለኛል፡፡››
‹‹ሼኪ በጣም ወሳኝ ነገር ተናግረዋል….ስለአሉት ነገር ቀድሜ ሳስብበት ነበር….ዛሬ ለሊት ሙሉ በሙሉ የሆስፒታሉ ሚስጥራዊ የህክምና ክፍል ንፅህ ይሆናል….ሶሰቱ ረዳቶቼም ቢሆኑ ለ15 ቀን እረፍት በሆስፒሉ ወጪ ድበይ ሄደው ተዝናንተው እንዲመጡ እንደተወሰነ ነግሬቸዋለሁ…የጉዞ ሰነዳቸው እንዲያመቻቹላቸው ለሚመለከታቸው የሆሰፒታል ሰዎች መመሪያ አስተላልፌያለሁ…እርግጠኛ ነኝ ከነገ ወዲያ ይሄንን ሀገር ለቀው ይበራሉ፡፡››
‹‹ጎበዝ ለዚህ እኮ ነው ካንተ ጋ መስራት ደስ የሚለኝ››ሼኪው ተደሰቱ
‹‹እሺ ዶዬ የምትለን የተለየ ነገር አለ፡፡?››ሲል ጠየቀው ፕሮፌሰሩ… የሚለውን ለመስማት ሁሉም አይናቸውን እሱ ላይ ተከሉ
‹‹ደረቱን ነፋ አድርጎ ልክ እንደሚደባደብ ሰው እጆቹን እንደክንፍ በመዘርጋት በጎረነነ ድምፅ መናገር ጀመረ…..‹‹እንግዲህ እንደምታውቁት ከለሊት ጀምሮ ከመካከላችን የተኛ ሰው የለም…ልጆቼ ሁሉም ከተማዋን እየበረበሩ ነው….እንደምታውቋት አዲስ አበባ ወደጎን መንቦርቀቋ ብቻ ሳይሆን ወደ ላይም ተመንድጋለች….በዛ ላይ የሀገሪቱ ግማሹ ህዝብ በውስጧ ሚኖር ነው የሚመስለው… ጉንዳን በሉት…ዝም ብሎ ይርመሰመሳል….ይሄ ሁሉ ሰው ግን በልቶ ያድራል.....?››
ዶዬ …..በልቶ ስለማደሩ ራሱ ሰውዬው ካልሆነም መንግስት ይጨነቅበት..አሁን ወደ ነጥብህ ግባ ››ፕሮፌሰሩ በረዘመ ማብራሪው ተሰላቸና ጣልቃ ገባበት፡፡
‹‹….እና ለማለት የፈለኩት ፍለጋው እንዲህ እንደምታስቡት ቀላል እንዳይመስላችሁ…ይሁን አንጂ በተቻለን መጠን ተግተን እየሰራን ነው….አንዳንድ የእኛ የቅርብ የሆኑ በየፖሊስ ጣቢያው ያሉ ፖሊሶችም ቀጥታ በፍለጋው በመሰማራትም ሆነ መረጃ በማቀበል እያገዙን ነው….ከዚህ በላይ ተጨማሪ አዲስ ሰዎችን በፍለጋው ላይ ማሰማራት ብንፈልግም ከእናንተ በኩል ሚስጥር ይባክናል ስለተባለ ያንን ማድረግ አልቻልንም…ሌላው…››
ንግግሩን ሳይቋጭ ስልኩ ተንጫረረ…ንግግሩን ገታ አድርጎ ከኪሱ አወጣና ተመለከተው‹‹…ማንሳት አለብኝ…ከንግድ ባንክ ዋናው ቢሮ ያለ የእኛ ሰው ነው የደወለልኝ››
ሁሉም በህብረት የሆነ የምስራች ለመስማት በመቋመጥ ስሜት ‹‹አንሳው ..አንሳው›› አሉት …ከተቀመጠበት ተነሳና አነሳው..ሁሉም ከመቀመጫቸው ተነስተው እሱን እየተከተሉ መንጎራደድ ጀመሩ
‹‹እሺ እንዴት ነው ..?አዲስ ነገር አለ?››
‹‹አዎ….5.5 ሚሊዬን ብር ከደብተሯ ላይ ወጪ አድርጋለች፡፡
‹‹ምን አለ?..
‹‹ ምን አለ?››በጥያቄ አጣደፉት.
ስልኩን ከጆሮው አላቀቀና…‹‹5.5 ሚሊዬን ብር ወጪ አድርጋለች ነው የሚለኝ››
‹‹ላውድ ላይ አድርገውና ከየትኛው ቅርንጫፍ እንደሆነ ጠይቀው››
እንዳሉት ስልኩን ላውድ ላይ አድርጎ ‹‹ከየት ቅርንጫፍ ነው?››ሲል ጠየቀው
‹‹ከመርካቶ ሱማሌ ተራ ቅርንጫፍ››
‹‹መርካቶ››
‹‹አዎ››
‹‹መች ነው? ቆይታለች?››
‹‹አይ አስር ደቂቃ ቢሆነ ነው..እርግጠኛ ነኝ አሁንም እዛው አካባቢ ነው የምትሆነው››
‹‹እሺ ለማንኛውም ቸው ..አመስግናለው..ቡኃላ ደውልልሀለው..››ስልኩን ዘጋውና ፤ሌላ ቦታ ደወለ
‹‹ስማኝ…መርካቶ አካባቢ ሰው አለን?››ጠየቀ
👍281
‹‹ሰባተኛ….በል እኔም አሁን ወደዛ እየሄድኩ ነው፡፡ ሰባተኛ ያለውን ሰው ቶሎ መርካቶ ወደ ሱማሌ ተራ እንዲንቀሳቀስ አሁኑኑ ንገረው..ንግድ ባንክ ብር እያወጣች መሆኑን አውቀናል ..በነፍስ ነው የምትፈለገው ..በነፍስ…ይሄንን ለሁሉም ንገራቸው…እና አንተም ወደእዛው ተንቀሳቀስ መጣሁ››ስልኩን ዘጋው
‹‹ልሄድ ነው…››
‹‹ሂድ ፍጠኑ.. የደረስክበትን ነገር በየጊዜው አሳውቀኝ››አለው ፕሮፌሰሩ ስለእሷ አንድ ነገር በመስማቱ የተወሰነ ተስፋ በፊቱ ላይ እየታየ፡፡
‹‹እሺ በቃ ሄድኩ….››እየነጠረ በችኮላ ወጥቶ ሄደ፡፡
ሼኩ ‹‹አሁን ፈራሁ››አሉ..በቀሙበት ከዘራቸውን ተደግፈው እየተከዙ
‹‹ምነው ሼኪ እንደውም የሆነ ቦታ መታየቷ እኮ አሪፍ ነገር ነው››አቶ ሙሉ ነው ተናጋሪው
‹‹አይ አይደለም….5.5 ሚሊዬነ ብር ለምን በአንዴ ልታወጣ ቻለች..?ምን አስባ ነው….?ከሀገር ልትወጣ…?እኛን የሚያስወግድ ነፍሰ ገዳይ ልትቀጥርበት..?በእኛ ላይ ምርምር ለሚከፍት የህግ ሰው ጉቦ ለመስጠት ?ብዙ ብዙ ነገር ያሳስባል፡፡››
ፕሮፌሰሩም ‹‹እሱስ እውነቶትን ነው ያሳስባል…››አለና ስልኩን አውጥቶ ደወለ..
‹‹እሺ ጠበቃው ምን ላይ ደረስክ?››
‹‹ዳኛውን ለማሳመን እየሞከርኩ ነው››
‹‹ለመሞከር እኮ አይደለም ያንን ረብጣ ብር የተፃፈበትን ቼክ እስይዤ የላኩህ..አንተ ስትንቀረፈፍ እሷ አንተን መግዛት የሚችል ብር ከባንክ ደብተሯ ማውጣቷን አሁን ከባንክ ሪፖርት ደርሶናል…..ዛሬ እገዳውን ሳትጨርስ ወደመኝታህ እንዳትሄድ..በኤልያስ ግድያ ላይ ቀጥታ እጇ እንዳለበት የሰጠውህን መራጃ ተጠቀምበት…እና ጭንቅላትህንም አሰራው…ቸው››ጆሮው ላይ ዘጋበት፡፡
በሉ ሁላችሁም ወደመቀመጫችሁ ተመለሱና ስለቀረው ነገር እንነጋገር››አለ ፕሮፌሰር ቀድሞ ወደለቀቀው ወንበር ሄዶ በመቀመጥ
ሁለቱም ወደለቀቁት መቀመጫቸው ተመለሱና ቁጭ አሉ..ሴኪው የመናገሩን ቅድሚያ ወሰዱ፡፡‹‹አሁን ስልክ ስታወራ ትዝ አለኝ የኤልያስን ጉዳይ እንዴት አደረጋችው፡፡
‹‹አልቋል..አስተካክዬዋለሁ››አለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ፡፡
‹‹ሆስፒታል መግባቱን እንደሳማ ለሊቱን 10 ሰዓት አካባቢ ነበር ሆስፒታል የሄደው..ሲደርስ ዶክተሮቹ ቀዶ ጥገናውን በስኬት አጠናቀው ውስጡ ተቀርቅሮ የቀረውን ሁለት ጥይት አውጥተውለት ጨርሰው ነበር…ልክ ሲደርስ የኤልያስ ሚስትም ሆነች ሁለት ልጆለት እላዩ ላይ ተጠምጥመው እያለቀሱ …አባታቸውን እንዲያድንላቸውና ገዳዩንም እንዲያዝ እንዲያደርግ ተማፀኑት ..እሱም ጥልቅ ሀዘኑን በከፍተኛ የትወና ብቃት እያሳየቸው ቃል ገባላቸውና ገብቶ ሁኔታውን አየው…ከዛ ወደቢሮው ተመለሰና ከተሰካለት መድሀኒት ጋር የሚቃላቀል ገዳይ ግን ስውር መድሀኒት አዘጋጅቶ ተመለሰ…ቼክ እንደሚያደርገው ማንኛውም የሚመለከተው ዶክተር በቀላሉ ገባና ቀላቀለው….ከዛ ሚስቱን ሆነ ልጆቹን አረጋግቶና አፅናነቶ ..ችግር ካለ እንዲደውሉለት እሱ ግን እስከዛ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ስለገዳዩ ማንነት ከፖሊሶች ጋር መነጋር እንዳለበት አብራርቶላቸው ሹልክ ብሎ የሆስፒታሉን ቅጥር ጊቢ ለቆ ዶክተር ሰጵራን ወደመከታተል ስራው ተመለሰ…
እንደነገራቸውም ከሁለት ሰዓት ቡኃላ ደወሉለት…‹‹ባለቤቴን ሰረቁኝ….ኤልያስ ሞተ..››ብላ ከታላቅ ሲቃ ጋር ደውላ መሞቱን ያረዳችው ሚስቱ ነበረች፡፡
እንደሚሞት እርግጠኛ ቢሆንም መሞቱን በሰማበት ሰከንድ ግን ክፉኛ ደንግጦ ነበር፡፡ፕሮፌሰሩ የሰው ልጅ ነፍስ አቅዶና አስቦ ሲያጠፋ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ገጠመኙ አይደለም…ግን ደግሞ በኤልያስ ልክ ቅርቡ የሆነን ጓደኛውን ገድሎ ግን አያውቅም..እና ልቡ ላይ ጨለማ ቋጥኝ ሲከመር ታውቆታል…በቀጣይ ደግሞ የገዛ እጮኛውን ሲጨምርበት ከዚህን ቡኃላ ህልሙ እንደሆረር ፊልም ስቃይ የተሞላ እንደሚሆን ከወዲሁ እርግጠኛ ሆነ…..‹‹አዎ በቀሪ ህይወቴ ሙሉ ዋጋ እከፍልበታለሁ..ቢሆንም ምርጫ አልነበረኝም››ብሎ ነበር እራሱን ያፅናናው፡፡
‹‹ፕሮፌሰር››ሼኪው ናቸው ከሀሳቡ ያባነኑት፡፡
‹‹ከሞተ ታዲያ ይሄን ያህል ምን ሀሳብ ውስጥ ሰነቀረህ?››
‹‹አይ እንዲሁ ነው….ያው ምንም ቢሆን ጓደኛዬ አልበረ››
‹‹እንግዲህ ቻለው ..እኛም እንችለዋለን..ግን በእቤቱ ዙሪያ በጣም ንቁ ሰው መመደብ አለብህ?››
‹‹ለምን?››
‹‹እንዴ …እጃችን እስካልገባች ድረስ እኮ ምን እንደምታደርግ መገመት አይቻልም..ሄዳ አንዳቸውን አግኝታ የሆነ ነገር ብትላቸውስ ጥርጣሬ ላይ ወድቀው የሆነ ነገር ማዛባታቸው ይቀራል?››
‹‹አዎ ነገሮች በዙብኝ መሰለኝ ይህንን ፈፅሞ አላሰብኩበትም ነበር..አሁን መድባለሁ››
‹‹አቶ ሙሉ ቀጠለ….‹‹ቆይ በስልክ ደውላ ብትነግራቸውስ…?››
‹‹አይ እንደዛ የምትሞክር አይመስለኝም….እኛ ያለችበትን አካባቢ በስልኳ አማካይነት ለማግኘት እንደምንሞክር ስለምታውቅ ፈፅሞ አትከፍተውም..››ፕሮፌሰር ግምቱን ተናገረ፡፡
‹‹ለማንኛውም አዋጩ ዘዴ መከላከል የምንችለውን አደጋ ሁሉ በሙሉ አቅማችን እየተከላከልን..እሷን ደግሞ ብዙ ጉዳት ሳታደርስ አግኝቶ መጨፍለቅ ነው››ሼኪው ናቸው ተናጋሪው፡፡
‹‹ትክክል ብለዋል..አሁን እዚህ ላይ ይብቃን …መሰራት ያለባቸው ብዙ ጉዳዬች ስላሉ እንንቀሳቀስ››
‹‹እሺ››
ተስማሙና ተያይዘው ወጡ
..



ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍311
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ

እድላችን ነው: አሁን መነሳት ያለበት ጥያቂ አይደለም።
መልሉ የተሰጠ ጥያቄ ጥያቂ ሊሆን አይችልም
ይልቅስ ሁሉንም በፀጋ ተቀብሎ መኖር ነው" ለምን በምን. ላይ ያተኮረ
ሃሳብ  ሃሳብ እንዳላት ሊገባው  አልቻለም  ስለዚህ ደስታው እየኮለመነ ግራ መጋባቱ እያየለ ሄደ።

“ልታነጋግሪኝ የፈለግሽው ምንድን ነው? ፈገግ ለማለት
እየሞከረ በጥሞና ጠየቃት:

“...እንደውሻ ቢያላዝኑ ሰሚ በሌለባት ምድር ለምን
ተወለድሁ! መወለዴን ሳስበው ይቆጨኛል! መሞቴም ያበሽቀኛል፤
ለምን ተወለድኩና ለምንስ ደግሞ እሞታለሁ። ስወለድም ለሞት
የምኖረውም ለሞት... አይኖችዋ ድንገት በእንባ ተጥለቀለቁና ቁልቁል ተደፋ: ያን ጊዜ ጨነቀው፡
የሚለበልበው እንባዋ
የማያውቃት ልጅ ድንገት እቤቱ መምጣቷ ብቻ አንሷት እንደበደላት ሁሉ ስታለቅስበት የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፋው።

“የኔ እህት የሶራ ገልቻ ቤት የብሶት መወጫ የበደል
ማራገፊያ ነው ያለሽ ማን ነው?... ደግሞስ እንዲህ ስታለቅሺ ሰው ቢመጣ ምን ይላል? ልቅሶ ካማረሽ ብሶትሽን ማካፈል ከፈለግሽ...”ብሎ በውስጡ የተፈጠረውን ሃሳብ በአእምሮ አዘጋጅቶ ከመቋጨቱ በፊት አናጠባቸው:

“ወኔ ቢስ! ይህን ስትል አታፍርም አይደል! እልህ
ውስጥህ አይንጠውም አይደል!  እዚች ሃገር መወለዴ እድሌ መሆኑ ጠፍቶኝ የጠየቅህ ይመስልሃል?  እንዴት ያስጨነቀኝ ጥያቂ መለስህልኝ ባክህ ጅል!" ብላ በእልክ እያለቀሰች በስርዓት የተጠቀለለ ፀጉሯን ነጨችው።

“ቆይ እስኪ እንዴ
እኔ አልበደልኩሽ የኔ እህት: አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ እንዲሉ ካለበደሌ..."

ዝም በል! ደሞ አልበደልኩሽ ይላል”  በለባጣ ሳቅ ተፍለቀለቀች። ጥርሶችዋ ያምራሉ! እያለቀሰች እንኳን አይኖችዋ
ያንፀባርቃሉ በጣቶችዋ
የምትበትነውኀፀጉሯም ውበቷን አላጎደለውም:

“ጤነኛ ነሽ? ለመሆኑ ከማን ጋር ለምን እንደምትነጋገሪ
ታውቂያለሽ?" አላት ትንሽ መረር ኮስተር ብሎ።

እሷ ግን “እብድ  መሰልኩህ? እልኸኛ በመሆኔ በማስመሰያ ግብረገባዊነት በውስጤ የሚንተከተከውን ሃሳቤን ሳላፍን እንደ እሳተ ጎሞራ ፈንድቶ ሲወጣ እየለበለበኝ የሚፈሰው እንባዬን,
ስሜቴን በማካፈሌ እብድ በለኛ! ለነገሩ ማን መርምሮኝ ጤንነቴን
አውቀዋለሁ። አመመኝ ስል አውልቂ እባላለሁ... በሽታዬ ይገኛል እፈወሳለሁ ስል ጭኖቼ ተበርግደው ቆሻሻ ይደፉብኛል”  ብላ
በትዝብትና ጥላቻ አየችው።

ከሴት ልጅ የምትፈልጉት ይህን ነው አይደል?!" ቀሚሷን ወደ ላይ ገለበችው:: ፈጣን አይኑ በለስላሳ ጭኖችዋ አልፎ
በለበሰችው ስስ ፓንት ያለውን ነገር ተመለከተ:

“...ይህን እንካ ብልህ እብድ ነሽ! አትለኝም ነበር። ከሃሣቤ ይልቅ ሳያስረዱህ የምታውቀው የስሜት ለሃጭህን የምታዝረከርከው
የሴት ልጅ ጭን ስታይ ነው አይደል!... ብሽቅ! አለችውና
ጭንቅላቷን ያዘች

“..እኔ ምንህም አይደለሁም. የአንተ እህት ግን ጓደኛዬ ናት። እንደ ሎሚ ተመጣ የምትጣል! ጭኖችዋን ለስሜት ሳይሆን ለገንዘብ የምትከፍት! የማታውቀውን ጠረን የምትታጠን... ለመሆኑ ስለእሷና ስለጓደኞችዋ አስበህ አዝነህ... ታውቃለህ? እህትህ ለተጠማው ወንድ ሁሉ በገንዘብ ተገዝታ የምትጠጣ መጠጥ
ተመልሳ ደግሞ እንደ ሽንት ቆሻሻ ላይ የምትሸና ጉድፍ መሆኗን ታውቃለህ?"

እህትህ' ስትል ነደደውና
ሶራ በጥሞና ሲያዳምጣት እንዳልቆዬ ሁሉ እህትህ
“የማን እህት?... የኔ... የኔ እህት?…" አፈጠጠባት: በንቀት እያየችው ቆየችና ረጋ ብላ፦

“ጠባብ በአብራh ክፋይ የምታምን ቂል. ሸርሙጣ እህት የለኝም እያልክ ያን የበከተ እምነትህን በመግለፅ ልትኮፈስ ይሆናል።''

“የኔ እህት ልትሰድቢኝ'ኮ…"

“ዝም በል  አንተ?” ባረቀችበት።

“የተማርከው! እንደ ባንዲራ እየዘመራችሁ ወደላይ ስቀሉኝና አየሩ ላይ ልውለብለብ ንፁህ አየር ነፍሴን ያስደስታት የነዳያንን
ጩኸት ወደማልሰማበት ፉከታቸውን ወደማላይበት! ወደላይ ሽቅብ ልውጣ... ባይ ነህ አይደል! እንደ ብዙዎቹ ምስኪን ያገራችን
ምሁራን፡

“የኛ መማር ከድሃው Uዝብ በተለየ ደሴት ውስጥ ለመኖር ነው። የተማርነውን
ንድፈ ሃሳብ ኮሯጆችን ውስጥ ከተን አንጨምርበት አኝከን አንትፋው ስንውጠው አንታይ!... ብቻ
ተሸክመነው እላይ ወጥተን መውለብለብ  ንግግሯን ገታ አድርጋ አየችው አያት፡ ተያዩ ምን እንደሚላት ጠፋው: ውጭልኝ ለማለትም ወኔ አጣ: እሷ ግን ቤቱን ደግማ አማተረች:: አይኗ
ከምኝታው ራስጌ ካለው ኮመዲኖ ባለው የሚማርh ፍሬም ላይ አረፈ።

“ምንድን ነው ይሄ?” ብላ ፈገግ እያለች በንቀት አየችው:

“የቱ?” አላት ወደራስጌው እየተመለከተ

"ዲግሪ ስትቀበል የተነሳኸው ፎቶ! አለችና ሳቀችበት።

“አያምርም! አየ አስተያየት አየ መልክ... አቤት ኩራት!
አሁንም የምፀት ሣቋን ለቀቀችው።

“...ምን ሰራሁበት ብለህ ነው ከራስጌህ ያስቀመጥከው?
መካኒክ የመካኒክነት ሙያ ንድፈ ሃሳብ በመማሩ መፍቻዎቹን ደረቱ
ላይ ደርድሮ ፎቶ ቢነሳ ምንድነው ትርጉሙ?  ጉራ ብቻ! ሥራበት አዲስ ቅርፅ አዲስ ምርት አምርትበት  ጠቅመህ ተጠቀምበት
የተባለውን መፍቻ እንደሰራው ሁሉ ደረቱ ላይ ደርድሮ ፎቶውን ገጭ አድርጎ ግድግዳው ላይ ቢሰቅለው ወይንም እንዳንተ ኮሚዲኖው ላይ ቢያስቀምጠው ፍችው ምንድነው?

ሶራ ተቁነጠነጠ ቀዝቃዛ ላብ በጆሮ ግንዱ ስር ተንቆረቆረ: “...ሌሎች የፈጠሩትን ለማወቅህ  ሌሎች ያሉትን ለመስማትህ የተቀበልከውን መተማመኛ
የደረሰህን ለማዳረስ ቃለ መሃላ የፈፀምክበትን ጥቁር ጨርቅና ወረቀት ለሰራኸው ቁም ነገር ለፈፀምከው የስው ልጅ መልካም ተግባር እንደተሰጠህ ሁሉ ቀለሙ በሚጮህ ፍሬም ውስጥ ከተህ ለእይታ ዳረግኸው፡

“ማንነትህ እንዲታወቅ... ያልተማረ እንዳትባል... በሃሣብህ ጨቅላነት የናቀህ ፎቶህን አይቶ እንዲያከብርህ እንደ ፋሲካ ዶሮ አልጋህ ላይ ልታርዳት የምታመጣት ሴት ኧረ የተማረ ይግደለኝ
ብላ በንድፈ ሃሳብ ሞረድ በተሳለው ምላስህ ሳትፈራገጥ
እንድትታረድልህ... ነው አይደል! ዲግሪ የተቀበልክበትን ፎቶ ራስጌህ ያስቀመጥኸው:

“ስትሰራ ህዝቡን ስትረዳ.. የተነሳኸውማ ምን ማስታወሻ አለህ? ማረሻ የያዘና ባዶ እጁን የቆመ ሁለቱም አንዳች ሥራ
እስካልሰሩ ድረስ ምን ለውጥ አላቸው?

“ለመሆኑ ለምን እዚች አገር ተወለድሁ? ከኬንያ
ከታንዛንያ... ያነሰች ደሃ ተብላ በምትናቅ፤ እምትኮራበት ታሪክ
አንጂ ቤሳ ቤስቲኒ ስልጣኔ በሌለባት ሃገር ለምን ተፈጠርሁ ብለህ
ቀንተህ ታውቃለህ  ከርሳም ጀብ ድሮ ጅብ ሆዱ ከሞላ በየት አገር ነው የሚቀናው: ሆዱ ከሞላ ባገኘው የቀበሮ ጉድጓድ ገብቶ መጋደም ነው: ክርፋቱ አይሸተው ጥንብ ነው ብሎ አይጠየፍ ስለ ማደሪያው አያስብ…

“በእንዳንተና እኔ አይነት ግዴለሾች ግን ችግር ችግር
እየተከመረ ዋጠን በህሊናና እጆቻችን ሰርተን ከመጠቀም ይልቅ
የህይወት ከርፋት ውስጥ ተጠቅልለን ማልቀስ መጮህ... እጣ ፈንታችን ሆነ" አላችና በሐዘን አንገቷን አቀረቀረች᎓ እንባዋ ዱብ
ዱብ ሲል ታየው: የመጣችበት ጉዳይና የምትናገርበት ምክንያት
👍372
ባይገባውም የምትለው ግን ገብቶታል። አሞታል ቆጥቁጦታል...
“የአክሱምን ሐውልት  የላሊበላንና የጎንደርን
ውጤት የሐረርን ግንብ... ያዬ እንግዳ ይህ ትውልድስ ምን ሰራ? ቢል ምን እንመልስ ይሆን?  ምክንያት መፍጠር የናቴ ቀሚስ
አደናቀፈኝ... ከማለት በስተቀር ምን አንደበት ይኖረናል እየሰሩ
ማውራት አንችል። በኛ ዘመን አባቶች የሰሩት የዘመናት ቅርስ ሲፈርስ ከንፈር መምጠጥ ብቻ... ወሬ መጠረቅ ብቻ... ለተተበተበው ችግራችን ውሉን እንዲጠቁሙን ወደ ምዕራባውያን መቁለጭለጭ ብቻ።

“ህዝቡን ባደናጋሪ ንድፈ ሃሳብባቸው እያመሱ በችግር አለንጋ  እያስገረፉት በእኛ እናውቅልሃለን አረንቋ ውስጥ ቀርቅረው ውስኪያቸውን እየጨለጡ ከአለም ህዝብ ጭራ ያደረጉት ፤ ሰርተው
ሳያሳዩ አካልና ህሊናቸው በፈጠራና ጥረት ተጎሳቁሎ ሳይቆሽሽ እንደ ህፃን ልጅ ለሆዳቸው ብቻ እያሰቡ ለፍቶ የሚኖረውን ህዝብ እየጠሩ ቦዘኔ ያደረጉት መኖሪያ ቤቱን ባጉል ፖለቲካቸው በሳስተው በፍሳሽ ያበላሹበት ምሁር ነን ባዮች አይደሉ!”

“ህዝብ የወጋውን እሾህ እየነቀሉ የሚፈልገውን የምርት መሣሪያ በቅርቡ ሆነው ያቀበሉ ለችግሩ መፍትሔ እንደ ዶሮ
እየጫሩ አለሁልህ ያሉትማ የሣት ራት ሆነዋል! ለጉሥቁልናና ስደትም ተዳርገዋል።የማይሞቱት ሥራ ሳይሆን ወሬ የሚጠፈጥፉት ትህትና ሳይሆን እብሪት የሚጋግሩት ናቸው...
እያለ በሐሳቡ ሲትከነከን፡-

“ስማ አንተ...የአለፈ  ቂም ከተዳፈነበት እየቆሰቆስን
ከማንደድ ሌላ ዝዝቡ የተሻለ እንዲያመርት የተሻለ እንዲኖር መች
አደረግነው። ጃፓን ላይ አቶሚክ ቦንብ ጥላ ብዙ ሚሊዮን ህዝብ
የፈጀችው አሜሪካ ከጃፓን ጋር ካለመግባባቱ ይልቅ የኢኮኖሚ ትስስሩ ይበልጥብናል። ትናንት ለጠፋው ጥፋት ካሣው ዛሬም ጥፋት መሆን የለበትም፡ ዘመኑ የድመትና አይጥን ግንኙነት ለጎሪጥ
ሳይሆን በአክብሮት"
የሚያስከብርበት ዘመን ነው: በቀሉ ቁሞ ህዝቡን በኑሮ እያሻሻልን እንካሰው ሊሉ አንተ የኛው ምሁር ግን እትብትህ ከተቀበረበት
ሥፍራ ርቀህ ስለአፍሪካ መፃኢ ዕድል አስበህ ታውቃለህ?  ሰምን
ብለህ! ትምህርታችን እንደ ጋሪ ፈረስ ፊት ለፊት ብቻ እንድናይ አድርጎናል: ጭነታችንን አናየው: እየጎማመዱ ነጮች የሚፈትሉትን ጭራችንን አንመለከተው ብቻ የጫኑንን እየጎተትን ወደ ፊት
መሮጥ::

“አስፓልቱን ልቀቅ! እሽ የደረቀውን የናትክን ጡት ጋጥ እሽ ተጫን  እሽ ተሳደብ እሽ ይጢስ ይጢያጢያስ ሁከት
ይፈጠር  እሽ!... እሽ... እሽ ብቻ!” አሁንም ራሷን ለማረጋጋት ፀጥ
ስትል በተራው ማሰብ ጀመረ።

...መቻቻል! ለጥፋት ካሣው ጥፋት መሆን የለበትም'
ያለችው እውነት በህሊናው እንደ ተራራ ገዝፎ ታየው በቅርቡ ታይምስ መጽሔት ሲያነብ ከመጽሔቱ ፊት ለፊት የነበረውን
የማንዴላ ምስል ሲያይ ያስገረመው ነገር ትዝ አለው። ጭንቅላቱ
ትልቅ የእጆቹና እግሮቹ ጡንቻዎች ግን ትናንሽ ሆነው ነበር ያየው።

እነዚህ ነጮች እውነትን ለመቀበል መቻኮላቸው እንዴት ያጓጓል' ብሎም ነበር። አፍሪካ ውስጥ አዲስ መሪ መጣ ሲባል
ጭንቅላቱ ትንሽ ጡንቻዎቹ ትላልቅ፣ መሳሪያ  የጨበጠ ነበረ ምስላቸው።

የዚያን እውነተኛ የአፍሪ ልጅ ምስል ግን ተቃራኒውን
አደረጉለት: ሃያ ሰባት ዓመት በሥር በማቀቀባት፤ በዘረኞች ክንድ የጥቁር ደም በፈሰሰባት ሃገሩ ሃሳቡን ሳይወላውል፣
በፍርፋሪያቸው ሳይታለል፣ በመሰሪ ሃሳባቸው ሳይደናገጥ... አምርሮ
ታግሎ ለነፃነት ለመሪነት ሲበቃ የደበብ አፍሪካ ጥቁር ህዝብ ሆይ
ስቃይህ አክትሟል... ነጮች ለፈፀሙብህ ግፍ በሰፈሩት ቁና የምትሰፍርበት ጊዜ አሁን ነው: ጦር ያለህ ጦርህን. ይዘህ ለውጊያ
ዝመት: ጀግንነትህን አሳይ... ብሎ በቀልን አልጋበዘም። ይልቁንስ
...በእኛ ትውልድ በእኛ ዘመን ቂም በቀል መቆም አለበት... እኛ የምንፈልገው ነጮችና ጥቁሮች በሠላም አብረው የሚኖሩባትን
አዲሲቷን ደቡብ አፍሪካን መገንባት ነው... እግዚአብሔር አፍሪካን
ይባርክ! ነበር ያለው። ግፍን ለማቆም ምንን ማድረቅ...
ትክክለኛው አማራጭ ይኸው ነበር፡ ለሀዝብ ማሰብ ይሏል ይህ
ነው: ለአገር አሳቢ ይሏል ይህ ነው! ለአፍሪካ ለሰው ዘር ጥሩ አላሚ ይሏል ይህ ነው:

የኡጋንዳ የሶማሊያ... የእርስ በርስ ጦርነት ግን መንስኤው እኔ ከሞትሁ...'
ባይ ስግብግቦች ነበሩ:: በቀልን ከ ሀ ወደ ለ
በመቀየር ስልጣን የተጠሙ... ኧረ እውነት እኛስ ምን ጉዶች ነን...
እያለ ሲፈላሰፍ

“እብድ ነሽ ወይ? ብለህ ጠየቅኸኝ አይደል
እብድ ማለት በእኛ የቃል መፍቻ የተለዬ ማለት አይደል። ህዝቡ ሲያለቅስ
የሚስቅ! ሌላው ሲጨነቅ የሚደሰት፤ ሌላው ሲያቃስት እሱ ወሲብ
የሚያንቋልጥ... ማለት አይደል እብድ ማለት᎓
እንደዚያ ከሆነማ
እብድ ነና ሁላችንም። ህዝቡ የራሱን ገፅታ ሲያጣ እኛ የምሁርነት ማረጋገጫ ፎቶአችንን ራስጌያችን ላይ እናስቀምጣለን" አለችና
የምፀት ሳቋን እያስታመመች ስቃ፡-

“አንተ ወኔ ቢስ፣ እልህ የለሽ... ምስህን ልስጥሃ! ሊያዘህ ልክፍት! ምስህ እህልና ወሲብ አይደል!  ሥራና ፈጠራማ የነጮቹ
ነው: የሌሎቹ አገሮች ጥቁሮችን ፈጠራም ያ ሰንኮፋም ልብህ
አይቀበለውም።

ነጮች ሰርተው ያሉትን ስንሰማ ያኔ ከሰሩት በላይ
ወገባችንን ይዘን እየተውረገረግን ስለ ሰማነው ከሰሩት በላይ በዚያ በሚያንቋርር ድምፃችን እንደሰኩራለን: እስከዚያው ግን እንተኛ!
አሁን እሱን የለበስኸውን ቱታ አውልቅና ወሲብ እንስራ፡ የአንተ  ታሪክ  የአንተ ጀግንነትዐየአንተ
ማንነት የተጀመረውና
የሚያልቀው እሴት ጉያ
ነው አይደል! ያን እንዳንተ
ሃሳብ የሚልቆሰቆስ ብልትህን እሴቷ ብልት ከተህ ከመልወስወስ ሌላ ካንተ ምን ይጠበቃል።
ከዚያ ከእንደ እኔ አይነቷ ጅል ጋር ሳልባጅህን ለብሰህ ባህል እንደሌለው ህሊና እንደሌለው አካለ ስንኩል እንደሆን ሁሉ
የማስመሰል ትወናችንን በሚያሳፍር መልኩ ከሙያ አጋሮቻችን ጋር
እንተውናለን። ህዝቡ ግን ዘላለም በህልም እንጀራ እየተቁለጨለጨደ
ያዝናል ያፍራል..." ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።

ሃፍረት ህሊናውን አሸማቀቀው።

“...ተማርሁ አወቅሽ ተባልሁ... ሌላው ቀርቶ እራሴን እንኳ መቻል አቃተኝ: አመታት እንደ ሰንበቴ መክለፍት ተነባበሩ።
እግሬ እስኪያጥር መኳትን እንጂ የህይወት ለውጥ አጣሁ የቤተሰብ የአገር ሸክም ሆንሁ። እና! ህይወትን ከዜሮ ልጀምር
አካሌን ወደማላዝበት እንደ
ኮምፒውተር የተባልሁትን
ወደማደርግበት ከሰው መሆን ዝቅ ከመሞት ከፍ ወደምልበት አረብ አገር መሄድ ሆነ አማራጩ: እዚች አረንጓዴዋ ድርቅ
ከምትባለው ሃገሬ መኖር አቃተኝ እና! ለብልሽት የተዘጋጀን ገላ ማበላሸት መቼም ህሊናህን  አይሰቀጥጠውም... ከመብረሬ በፊት
ልስጥሃ!"

“ምኑን?” አላት ቀና ብሉ እያዬ: ቀሚሷን ወደ ላይ
ሰበሰበችው። አይኖችዋ እንባዋን በመንታ በመንታው ያወርዱታል።

“አመሰግናለሁ። እባክሽ አትሂጂ፡ ከህይወት መሸሽ ፈሪነት ነው...” ሲል

“ምናልክ! መሞትና መተኛት ምን ለውጥ አለው፤
እስካልሰሩ ድረስ? የሞተች ነፍስ ወደ መቃብሯ ስታዘግም ህያውነትን ተላብሳ እግዜር ቅባ ቅዱሳን ቀብቶ ደልቷት እንድትኖር
👍232👏1
ይላካት አይላካት ሳታውቅ በውሸት በተገነባ የሃሰት ህይወት ላይ ቆመህ ለምክር አንደበትህን ትከፍተው?
“ይልቅ በተግባር የካድናትን እውነት በሃሣብ እንኳ
ለመስማት ፣ በመቻልህ የምትመሰገን ነህ ለካ እውነትን የሚሰማ፣
እውነትን የሚጋፈጥ በትኩሳታምነት ያዙኝ ልቀቁኝ የማይልም አለና
ይህም ለኔ ለወፏ ትልቅ ተስፋ ነው። በል ሰዓቴ ደረሰ። ለመብረር መሄድ አለብኝ። ደህና ሁን" ብላው ወደ በሩ አዘገመች። እሱም
አይኖቹን በሩ ላይ ሰካ። ፈዞ ዱካዋን... የስደተኛዋን የግር ኮቴ አዳመጠ። ችግርና እውነትን ይዛ የምትሰቃየውን ነፍስ አስታወሳት  “እውን እዚች አገር ላይ የጠለቀችው ጀንበር ተመልሳ ትወጣ ይሆን! እያለ በመቆዘም አልጋው ላይ ተጋደመ….

💫ይቀጥላል💫
👍16
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ ሰባት
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
/
የሚፈልጉት ያህል ብር ወደ እሱም ደብተር ከማዘዋወሯም በላይ ከግማሽ ሚሊዬን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ በሁለት ኩርቱ ፔስታል ሞልተው ምንም ችግር ሳይገጥማቸውና ፤ማንም ልብ ሳይላቸው ተመልሰው የእሱ ቤት መድረስ ችለዋል፡፡
ከሆቴል የሚበላና የሚጠጣ አመጣና አብረው ከበሉ ቡኃላ ተረጋተው ፊት ለፊት ተቀምጠው መወያየት ጀመሩ
‹‹እሺ..አሁን አንድ እስቴፕ ወደፊት መጥተናል..ማለቴ ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ የምንንቀሳቀስበት የብር ችግር አይገጥመንም..››በሚል ዓ.ነገር የውይይቱን መድረኩን ከፈተው፡፡
‹‹ይመስለኛል….ግን አይዞህ ይሄ ቢያልቅ እንኳን እነሱን መቀመቅ እስክናስገባ የሚያግዘን ሌላ የብር ሶርስም አላጣም››አለችው በልበ ሙሉነት..አሁን ገንዘብ በእሷ ዘንድ ያለው ትርጉም ትናንትና ከትናንት ወዲያ ከነበረው ትርጉም ፍፁም የተለየ ሆኗል….ለዛ ነው ለሚወጣው የብር መጠን ብዙም ግድ ያልሰጣት፡፡
‹‹እሱን እንኳን አታስቢው.. ግፋ ቢል እስከነገ ቢወስድባቸው ነው ..ሙሉ በሙሉ ባንክ ውስጥ ያለሽን ብር ይጠረቅሙብሻል፡፡››
‹‹አይዞህ አታስብ እኔ ሴት ነኝ..ሴት ደግሞ እንደእናንተ ወንዶች ብዙም ዝርክርክ አይደለችም …ማንም ሊደርስበት የማይችል ማንም ሊያሳግደው ማይችል ቦታ መጠባበቂያ አለኝ፡፡››
‹‹እና ሳትሳቀቅ አጥፋው እያልሺኝ ነው?፡፡››አላት ሁኔታዋ እየገረመው፡፡
‹‹አዎ…እነሱን ለማጥፋትና ለማዋረድ ቅንጣት ታህል የሚያግዝ ነገር ከሆነ በምንም ነገር ምንም ያህል ብር ብታወጣ ችግር የለብኝም፡፡››
‹‹በእውነት ቸር ነሽ..አሁን ግን ቸርነትሽን ሳይሆን ቆራጥነትሽን ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹ቆራጥ መሆኔን ምኔን ቆርጬ ላሳይህ?››
‹‹እንደዛ ከሆነ ስሚኝ..እነዚህ ሰዎች እንደነገርሺኝ እንዲሁም እኔም ዞር ዞር ብዬ እንዳጣራሁት በጥራትም በብዛትም ከእኛ ጋር የሚመጣጠኑ አይደሉም..እኔ እና አንቺ ሆነን አይደለም ገፍትረን ወደገደል ልንጥላቸው ልናነቀንቃቸውም አንችልም፡፡››
‹‹እኔና አንተ ብቻ አይደለንም…ብሩም አብሮን አለ››
‹‹ትክክል ነሽ..፣ግን ደግሞ ከእዚህ ብር በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ብር እነሱ ጋር እንዳለ አትርሺ…እነሱ በግልፅ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የመንግስት ተቋሞችን ጭምር በማጭበርበር የሚጠቀሙ አጥቂዎች ናቸው.. እኛ ደግሞ በየስርቻው እየተሹለከለክን በዋናነት እራሳችን በመከላከል አጋጣሚውን ስናገኝ በስውር የምናጠቃ ነን ..አየሽ ልዩናታችንን››
‹‹እሱስ ትክክል ነህ..እሺ ምን እናድርግ?፡፡››
‹‹እኛም አላማችንን ከግብ እንድናደርስ ሊያግዙን የሚችሉ በጣም ታማኝ ሰዎች መመልመል አለብን››
‹‹አዎ አንተ ትክክል ነህ››
‹‹አዎ ትክክል ነኝ..አንቺ በጣም በነፍስሽ የምታምኚው ሰው አለ?››
ለተወሰነ ደቂቃዎች አሰበች
‹‹ምንም ዘመድ ምናምን የለሽም?››ደግሞ ጠየቃት፡፡
እኔ ዘመዶቼ በአጠቃላይ ጎንደር ናቸው.. የተቀሩት ደግሞ አሜሪካና አውሮፓ ናቸው..እኔም በቋሚነት እዚህ መኖር ከጀመሪኩ ሁለት አመት አልሞላኝም….ሁለት የወከባ አመት ነው ያሳለፍኩት..በአጠቃላይ በቅርብ የስጋ ዘመድ የለኝም…ቆይ ቆይ አንድ የኮምፒተር ባለሞያ ልጅ አለ…ልጅ እንኳን አይደለም ሙሉ ሰው ነው፡፡››
‹‹ግንኙነታችሁ ምንድነው ?ጓደኛሽ ነው….?››
‹‹አይ.. ከሀይስኩል ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ ከእዚህ ሀገር እስክወጣ ድረስ ፍቅረኛዬ ነበር››
‹‹እና ስትሄጂ ትቶሽ ሚስት አገባ››
‹‹አይ ነገሩ ውስብስብ ነው…ግን ያው እኔ ነኝ የተውኩት ማለት ይቻላል…ፀባዩና ጠቅላላ የህይወት እስታይሉ ዊርድ ነገር ነው..እና ሲያቀብጠኝ እሱን ተውኩና ፕሮፌሰሩን ያዝኩ ይው የእጄን…አገኘሁ››
‹‹እና እንደዛ የከዳሽውን ሰው ዛሬ በህይወት ይታመነኛል የሚል ድፍረት ከየት አመጣሽ ?በይ..እኔ ብሆን ይሄን ጥያቄ ይዘሽ እቤቴ ስትመጪ እራሴው ነኝ አንገትሽን እንደ ዶሮ ቀንጥሼ ጎርፍ መውረጃ ቱቦ ውስጥ የምከትሽ››
‹‹ጥሩው ዜና እሱ አንተን አይደለም….››
‹‹እንዴት?››
‹‹አንቺ ካለገባሺኝ ሌላ መቼም አላገባም ብሎ ዛሬም ወንደላጤ ሆኖ እየኖረ ነው..ልክ እኔ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ መኖር ስጀምር ይኖርበት ከነበረው ባህር ዳር ስራውንም ኑሮውንም ለቆ ወደእዚህ በመምጣት እየኖረ ነው..በሳምንት አንድ ቀን ተገናኝተን እናወራለን እንጫወታለን..በክፉም በደጉም እንጠያየቃለን…አሁን ከማንም በላይ በቁጥር አንድ ደረጃ የሚስጥር ጓደኛዬ ነው..እና ምንም እንኳን ሰውን ማመን ከባድ ቢሆንም በዚህ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ከሁላችሁም በላይ የማምነው ሰው እሱን ነው፡፡››
‹‹ለነገሩ ታሪኩን ስትንግሪኝ እኔም አምኜዋለሁ..እንዲህ አይነት ጅል ካልተማነ ማን ይታመናል….?ግን በምን ይጠቅመናል..አሀ የኮምፒተር ባለሞያ ነው አልሺኝ ..››
‹‹ለዛውም ኤክስፐርት ነው….አሁን አራሱ ኢንሳ ነው የሚሰራው፡፡››
‹‹እ…››
‹‹አዎ ኢንሳ ነው የሚሰራው..››
‹‹በቃ ..ወደድኩት..እሱ በጣም ያግዘናል…ሌላስ?››
‹‹ሌላ በእሱ መጠን ማምነው ሰው የለኝም.. ግን ተመላላሽ ሰራተኛዬ የምትታመን ትመስለኛለች..እናቷን አሞባት ከገጠር መጥተው ከ50 ሺ ብር በላይ አውጥቼ በማሳከም እንዲድኑ አድርጌለሁ…ሁል ጊዜ መች እና እንዴት ይሆን ውለታሽን የምመልሰው እያለች ታለቅስ ነበር››
‹‹እንግዲያው እንኳን ደስ ያለሽ አሁን እድሉን አግኝተሻል በያት››
‹‹ትጠቅመናለች ››
‹‹አዎ….አንደኛ ለብዱኑ ምግብ ታበሰላለች ..ትንከባከባለች….አንዳንዴም ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን ስንፈልግ ወደ ውጭ ትላላካለች፡፡በቃ ሌላውን እኔ አሰባስባለሁ..መጀመሪያ አሁን ልውጣና ተስማሚ ቤት ልፈልግ››
‹‹ቤት..? ይሄስ?››
‹‹አረ ባክሽ…የወላጆቼን ውርስ በላዬ ላይ እንዲያቃጥሉብኝ ፈለግሽ?››
‹‹እንዴ ቤቱ የራስህ ነው እንዴ….?.ለካ ለዛ ነው አንደፈለክ የምትመነቃቅርበት››
‹‹አዎ ግን ወደቁምነገር ስንመጣ ይሄ መሀከል ከተማ ውስጥ ስለሆነ እኔም በደንብ ስለምታወቅ እንቅስቃሴ ሲበዛ አይን እንስባለን….ከከተማ ደር የሆነ ሙሉ ጊቢ መሆን አለበት…››
‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው ፡፡ተመችቶኛል..››
‹‹በል ሂድ››
‹‹እሺ እስከዛ ከፈለግሽ ተኚ..ከፈለግሺ ፊልም እይ››
‹‹‹ልጆቹ ጋርስ ስልኬን ከፍቼ ልደውልላቸው እንዴ?››
‹‹ፍፅም ለእኔ ሳትነግሪ ስልክሽን እዳትከፍቺ..እነሱን በስልክ ሳይሆን ሁለቱንም ቀጥታ በአካል አግኝተን ነው የምናናግራቸው….. አሁን ቸው…..ከቤት እንዳትወጪ ማንንም በስልክ እንዳታናግሪ፡፡››
//
በዳላላ አፈላልገው ከኮዬ ፈጬ ኮንደሚኒዬም መንገድ ተሻግሮ ፊት ለፊት ከተነጠፉት የማህበር መኖሪያ ቤቶች መካከል አንድ ባለ ሁለት ፎቅ ቤት በ25 ሺ ብር የወር ኪራይ ለሶስት ወር ተከራይተው ገቡ…ቤቱ በጥራት ሆነ በስፋት ለእነሱ ጉዳይ ምቹ ነው ተብሎ የተሰራ ይመስላል..በእሱ ተርታም ሆነ ከፊትለፊቱ ያሉ ከሀያ በላይ ቤቶች የሆነ ቦታ ደርሰው ቆመዋል…በዙሪያው የተጀመረ እንጂ ያለቀ ቤት አንድም አይታይም…
በመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያው ወለል ላይ ጎን ለጎን የሚገኙ የየራሳቸውን አንድ አንድ ክፍል ይዘው እዛ ግዙፉ ቤት ውስጥ ሁለቱ ብቻ አደሩ…ያው ከእሱ ጋር አንድ ክፍልም ብቻ ሳይሆን አንድ አልጋ ላይ ጭምር አብራ ተኝታ ብታውቅም አሁን ግን ሌላ ሌላ ሀሳቦች በአእምሮዋ እየመጣባት መጨናነቅ ጀመረች…እዚህ ቢጮህ ማንም ሰምቶ የማይመጣበት ቦታ ቢደፍረኝስ….?ለሊት ላይ እንቅልፍ አልወስድ ብሎት እየተገላበጠች በነበረቸበት ጊዜ ወደምናቦ ጎራ ያለ የፍራቻ ጥያቄ ነበር.
👍292
‹‹መድፈር ስላልፈለገ እንጂ ሰው ባለበትስ ቦታ መች እራስሽን ማዳን ቻልሽ…?››ከውስጧ ነበር ለራሷ የማይረባ ጥያቄ በትዝብት መልስ ያገኘችው፡፡
በማገስቱ ከእሱ ሚገዝፉና ከእሱ በላይ የሚያስፈሩ ሶስት ወጣቶች እና ሌላ አንድ የሶስት አመት ወንድ ልጅ ያላት ጠረንገሎ ነገር አምጥቶ አፈሰሳቸው…
.በመጀመሪያ ስታያቸው ከሶስቱ ወንዶች መከከል አንደኛው የሴቶ ባልና የህፃኑ ልጁ አባት አንደሆኑ ነበር ያሰበችው….የትኛው ይኆን በሚል ሁሉንም በየተራ ብትገመግምም የአባትነት ጠረን ያለው ከመካከላቸው አጣች…እውነትም ትንሽ ቆይታ እንዳጣራችው ሶስቱም ሴትዬዋን ጭራሽ አያውቋትም….
…የሚያድሩበትን አልጋ ሲከፋፈሉ ሴቶ እኛ ያለንብት ወለል ላይ ከአብዬት ክፍል በስተቀኝ ያለውን ክፍል ሲሰጣት (እንግዲህ አብዬት በሁለት ሴቶቸ መካከል ሳንዲውች መሆኑን ልብ በሉልኝ)ለወንዶቹ ግን ሁሉም ከላይ ያለው ሁለተኛ ፎቅ ላይ እንዲወጡ ተደረገ ፡፡እኛ ያለንበት የመጀመሪያ ፎቅ ላይ ሚገኙ ሙሉ በሙሉ አስፈላጊው እቃ የተሞላላቸው አምስት መኝታ ቤቶች ቢኖሩም ወንዶቹን ግን እንዳለ ወደ ሁለተኛው ፎቅ ነው የሸኛቸው…ሙሉ ትዕዛዝ ሰጪው አቶ አብዬት ስለሆነ ለምን እንደዛ እንዳደረገ የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው..ግን ሁለተኛ ፎቅ ላይ ያሉ ክፍሎች ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ ያለቁ ቢሆኑም ከባዶ ፍራሽ በስተቀር ምንም እንደሌለባቸው ትናንትና አይቼያለሁ….እነሱ ግን ምንም የመሰላቸው አይመስሉም…
አብዬት ልጁን ለእኔ በማስረከብ ከሴቷ ጋር አስፈላጊ ነገሮችን ለመሸመት ተያይዞ ወጣ፡፡ጨነቀኝ እምቢም ማለት አልደፈርኩም እሺም ብዬ ኃላፊነቱን መቀበል ፈራሁ…፡፡አንድም የተቃውሞ ወይም የእሺታ ቃላት ከአንደበቴ ሳላወጣ ነው የሳሎኑን በራፋ በላያችን ላይ በመጠርቀም ወጥተው ሄዱት….ልጁ ጠይም ዱንቡሽቡሽ ያለ ፀጉሩ ደማቅ ጥቁርና ተጠቅልሎ.. ተጠቅልሎ ግንባሩ ላይ የተደፋ ነው…እይኖቹ እንደ ድምት አይን ጉልህና አንፀባራቂ ናቸው…..እናቱን በምኑም በምኑም አይመስል..‹‹እርግጥ የራሷ ልጅ ነው ወይ እንድታሳደግ ከሌላ ሰው ነጥቃ ነው እያሳደገች ያለቻ.?.አዎ ስትታይም ነጣቂና ቀሚ ነው የምትመስለው….››ይሄን ሁሉ የምታሰላስለው በውስጧ ልጅን በቆሪጥ እያየች ነው ፡፡
‹‹ስምሽ ማን ይባላል?››ጥፍጥ ባለ አንደበት ጠየቃት
ደነገጠች….ቀድሞ ሰላማዊ ጥያቄ ይጠይቃኛል ብላ ፈፅሞ አልጠበቀችም….እንደውም አንቧርቆ ያለቅስና ምን አደርገዋለሁ ብላ ስትጨናነቅ ነበር፡፡
‹‹ሰጲራ››
‹‹ሰፕላ››
‹‹አዎ…ያንተስ…?››
‹‹የእኔ በትሉ››
‹‹አሀ መድሉ ነው››
ትክክል መሆኗን በግንባሩ ንቅናቄ አረጋገጠላት፡፡
‹‹እናትህ ማነች?››የተለየ ነገር ይነግረኛል በሚል ጉጉት ጠየቀችው፡፡
‹‹እማዬ››
‹‹አሁን ከአብዬት ማለት ከሰውዬው ጋር የወጣችው ነች?››
‹‹አዎ›››
‹‹የት ነው እቤታችሁ?››
‹‹እዛ እሩቅ..አዲስአባ››በተረዳው መተን መለሰላት፡፡
‹‹አባትህ ማን ነው?››
‹‹እኔ እንጃ››
እኔ እንጃ ሲል ትከሻውንም ጭምር ከፍ ዝቅ በማድረግ ነው…ፈገግ አለች ፡፡ከመቀመጫው አነሳችና አቀፈችው
በትናንሽ ማራኪ ጣቶቹ ደረቷ ላይ የተኛውና ፀጉሯን እየዳበሰ……
‹‹ተጉርሽ ትልቅ ነው..ደስ ይላል››አላት
ደስ አሰኛት‹‹ይሄን ልጅ በጣም ወደድኩት›› አለች ››በውስጧ…..
እስከዛሬ ባለት ኤክስፒሪያንስ ከህፃናት ጋር ያላት ቅርርብ በጣም የላላ ነው…በረጂም ጊዜ ተደጋጋሚ ጥረት በሂደት ነው ትንሽ ትንሽ የሚቀርቧት…ይሄ ግን አስባ ሰትጨርስ በራፉ ተከፈተና የሄዱት መጡ…‹‹እማዬ መጣች›› ብሎ ከላዬ ላይ በመውረድ ወደእናቱ ጉያ ይሸጎጣል ብላ ብትጠብቅም ጭራሽ እራሷ ጉያ ሽጉጥ አለ፡፡አንጀቷ ተላወሰ፡፡የጋብቻ እቅዷ ቢሳካ ኖሮ እሷም በሚቀጥለው አመት በገዛ ሆዷ ተሸክማ ድምቡሽዬ ልጅ ወልዶ የመታቀፍ እቅድ ነበራት..አሁን ግን እንደሚታወቀው እንደእለተ-ምፅአት የራቀ የማይጨበጥ ተስፋ ሆነባት እንጂ..
‹‹ልጅ ላይ ጥሩ ነሽ መሰለኝ…?››አላት አብዬት ከገመተው በተሻለ ተቀራርበው በማግኘቱ ተገርሞ
‹‹አረ እኔም ገርሞኛል…ጣፋጭ ፀባይ ያለው ልጅ ነው››
‹‹ባክሽ ባባቱ ወጥቶ ነው..እሱም እንዲህ አንገቱን ደፍቶና ቅልስልስ ብሎ ሴት ጉያ በመግባት ሚወዳደረው የለም….ወንድ ያው ወንድ ነው…››
በሴትዬዋ ንግግር ክፉኛ ደነገጠችና ልጁን ወደራሷ ጭምቅ አድርጋ አቀፈችው
የገዙትን ከእየ እቃው እያወጡ ሲደረድሩ እየተመለከተች ነው፡፡ ለሁሉም የሚበቃ ምግብና መጠጥ እና ሲጋራዎችን ሌሎችም አስፈላጊ እቃዎችን ሸምተዋል ....


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍458
አትሮኖስ pinned «#ኢቫንጋዲ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ እድላችን ነው: አሁን መነሳት ያለበት ጥያቂ አይደለም። መልሉ የተሰጠ ጥያቄ ጥያቂ ሊሆን አይችልም ይልቅስ ሁሉንም በፀጋ ተቀብሎ መኖር ነው" ለምን በምን. ላይ ያተኮረ ሃሳብ  ሃሳብ እንዳላት ሊገባው  አልቻለም  ስለዚህ ደስታው እየኮለመነ ግራ መጋባቱ እያየለ ሄደ። “ልታነጋግሪኝ የፈለግሽው ምንድን ነው? ፈገግ ለማለት እየሞከረ በጥሞና…»