አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ ስምንት
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ነው፡፡ የተገዛው ምግብ ጠረጳዛ ላይ ተደረደረና ሁሉም ከየክፍሉ ወጥቶ ጠረጳዛውን እንዲክብ ተደረገ…ከክቡ ጠረጳዛ ራሱን በማግለል ለብቻው ፈንጠር ብሎ ኮምፒተሩን እየጎረጎረ ያለው ካሳ ብቻ ነበር…ደክተር ሰጳራና አብዬት እቤቱ ድረሰ በጥንቃቄ ሄደው ካነገገሩት ቡኃላ ለአንድ ሳምንት አብሮቸው ሆኖ ሊያግዛቸው ተስማምቶና በስልክም ሀለቃውን የቤተሰብ ችግር እንዳጋጠመው በመግለፅ ፍቃድ ጠይቆ ከተቀላቀላቸው አራት ሰኣታት ቢያልፉም እስከአሁን ማንንም ፍቃደኛ ሆኖ አላናገረም…፡፡ዶክተሯንም ጭምር…፡፡
አብዬትም ቀድሞ ስለባህሪው በመጠኑም ቢሆን ሌሎችን እንዳያጨናንቁት ነግሯቸዋል፡፡ እራቱም በተቀመጠበት ለብቻው ቀረበለት..፡፡ኮምፒተሩን መጎርጎሩን ሳያቆርጥ መመገብ ጀመረ…፡፡የተቀሩትም ብዙም ንግግር በሌለበት ሁኔታ የመጀመሪያውን ቀን የጋራ መአድ አንድ ላይ ተመገቡ….ከምግብ ቡኃላም የሚጠጣውን ነገር ሁሉም ፊት ለፊታቸው አስቀምጠው ለቀጣዩ አለ ለተባለው ውይይት ተዘጋጁ..፡፡
በዚህ መሀል ግን ድምፁ ጠፍቶ ምስሉ ብቻ እተንቀሳቀሰ የነበረው የሳሎኑ ግዙፍ ቴሌቭዥን ላይ የዶክተሯ ምስል በጉልህ ገጭ አለ….በመጀመሪያ አብዬት ነበር የተመለከተው፡፡ ከተቀመጠበት በርግጎ በመነሳት ወደሪሞቱ ሮጠና ድምፅን ጨመረው….ሁሉም ሁኔታውን አይተው ሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ቴሌብዥኑ አደረጉ….ህፃኑ በድሉ እየዘመረ የነበረ ቢሆንም እናቱ አፉን አፍና ዝም አስባለችው….በስክሪኑ ሞልቶ ከተለቀቀው የዶክተሯ ፎቶ ስር የሚሄደው ድምፅ አስገምጋሚ ነው፡፡
የዳይመንድ ኢንተርናሺኛል ሆስፒታል መስራቾችና ባለቤቶች መካከል አንዷ የሆኑት የማህፀን እስፔሻሊስት ዶ/ር ሰጳራ ወንድይራድ በተመሳሳይ የድርጅቱ መስራችና ባለቤት የሆነውን አቶ ኤልያስ ደቻሳን ከግብረአበሮቾ ጋር በመሆን እቤቱ ድረስ በለሌት በመሄድ በአምስት ጥይት ደረቱ ላይ በመደብደብ መሰወራቸው የታወቀ ሲሆን ጥቃት የደረሰበት አቶ ኤልያስ ወዲያውኑ ህይወታቸው ባያልፍም በቤተሰቦቻቸው አማካይነት እዛው ዳይመንድ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ተውስደው ከፍተኛ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው ነፍሳቸውን ለማትረፍ እርብርብ የተደረገ ቢሆንም በስተመጨረሻ ህይወታቸው ሊያልፍ እንደተቻለ ለማወቅ ችለናል..፡
በመሀከል የፕሮፌሰሩ ምስል ገጭ አለ..ጋዜጠኛው ማይኩን ወደአፉ አስጠጋለትና….‹‹ፕሮፌሰር በሆስፒታላችሁ ስለተፈጠረው አስደንጋጭ ክስተት ምን አስተያየት አሏት?››ሲል ጠየቀው
ፕሮፌሰሩ ናፕኪን ከኪሱ አውጥቶ የአይኖቹን ጫፎች እየጠራረገ ሲቃ በረበሸው ድምፅ‹‹በእውነት የሰማነውን ነገር ማናችንም ማመን አልቻልንም፡፡ እርግጥ በሟችና ገዳይ መካከል የአክሲዬን ድርሻህን ሽጥልኝ አልሸጥም በሚል ከፋተኛ ጭቅጭቅ እንደነበረ ይታወቃል..ግን የገዛ እጮኛዬ ለገንዘብ ስትል የገዛ ጓደኛችንን ትገደላለች ብዬ በፍፅም አላስብም..አይ አይሆንም የሆነ የተሳሳተ ነገር አለ››ብሎ ከካሜራው እይታ በርግጎ አመለጠ…
.ዘጋቢው ዜናውን ቀጠለ
በአሁኑ ጊዚ ዶክተሯ ማንናታቸው ካልታወቀ ሶስት ግብረአባሮቾ ጋር መሰወራቸው ታውቆ ፖሊስ እያደናቸው ሲሆን አንዱ ግለሰብ ግን በቁጥጥር ስር ውሎ የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቶል፡፡
በቁጥጥር ስር የወላው ጳጥሮስ ዳንሳ የተባለው ወጣት እንደሰጠው ቃል ከሆነ ዶክተሯ በአቶ ኢልያስ ግድያ ተባባሪ እንዲሆን 50 ሺ ብር እንደከፈሉትና እሱም ለሊት አብሯቸው ወንጀሉን እንደሰራ ገልፆል፡፡በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ እንዳስረዳው አብረውት ነበሩትን ሌሎቸ ተባባሪዎችን አካላዊ ቁመናቸውን ካልሆነ መልካቸውን እንዳማያውቀውና ሁሉም ለሊት ስምንት ሰዓት ላይ ሞቹ ቤት አቅራቢያ ጭንብል ለብሰው እንደተገናኙ ገልፆ ዶክተሯም በወቅቱ በአካባቢው እንደነበሩ እና ወደግቢው ውስጥ ሳይገብ ተልዕኮቸውን ፈፅመው እስኪወጡ የሟቹ በራፍ ላይ መኪናቸው ውስጥ ሆነው ሲጠብቋቸው እንደነበር በግለፅ አብራርቷል›…. ከተያዘው ተጠርጣሪ መኖሪያ ቤት በተደረገው ፍተሸ….ሞቹ ከተገደለበት ሁለት ሽጉጦች መካከል አንደኛውና አራባ ዘጠኝ ሺ ሶስት መቶ ብር በጥሬው እንደተገኘና በኤግዚቢት እንደተያዘ ታውቋል፡፡
በመጨረሻም..ያለህብረተሰብ ትብብር ወንጀልን መከላከል ሆነ ወንጀለኞችን አድኖ የመያዝ ተልዕኮ አይሳካምና ማንኛውም ሀገር ወዳድ ዜጋ ዶክተሯን ሆነ ግብር አበሮቾን ካየ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲያደርግ ይጠየቃል፡፡
ቤት ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ ደንዝዞ ነበር…..ህፃኑ በድሉ እንኳን የሚካሄደው ነገር ባይገባውም ሆነ አስጨናቂ ጉዳይ እንደተፈጠረ የገባው ይመስል በዝምታ ወለሉ ላይ ተዘርፍጦ ሁሉንም በየተራ እተመለከተ ነው፡፡
‹‹ምንድነው አብዬት?የሚሉት ገባው ሰው አለ….?ምን አክሲዬን ግዚና ሽያጭ ነው?››እራሷ ዶክተር ነች ጠያቂዋ….አሁን ከላይ በቀረበው ዜና መሰረት እዚህ ቤት ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ በጥያቄ ማጣደፍ ያለበት እሷን ነበር…እሷ ግን ይሄው ተገላቢጦሽ….
ካሳ ብቻ ነው ምንም እንዳልተፈጠረ ነገር አይኖቹን የገዛ ኮምፒተሩ ላይ ሰክቶ የራሱን ስራ እየሰራ ያለው፡፡
አብዬት ቴሌቪዥኑን ሙሉ በሙሉ አጠፋና ሙሉ ትክረቱን ሰበሰበ…መናገር ጀመረ‹‹እንግዲህ ሁለችሁም አንደተመለከታችሁት ሰዎች ምን ያህል አደገኞች እንደሆኑና እስከምን ድረስ ሊሄዱ እንደሚችሉ ከዚህ በላይ ማስረጃ የለም…….
ካሳ አቆረጠው…‹‹አልቆልሻል እጅ ስጪና ተገላገይ..ቅሊንጦ ይልኩሻል እኔም እንደፈረደብኝ እዛ የኮምፒተር ባለሞያ ከፈለጉ እንዲቀጥሩኝ እጠይቃለሁ››
እሱን ችላ አለችና በጥያቄዋ ገፋች‹‹ቆይ ተያዘ ያሉትስ ሰው….?ከየት የመጣ ነው?››
‹‹እሱ ለአንቺ ሰዎች ቀላሉ ነገር ነው….ለተያዘው ሰው አንድ አምስት መቶ ሺ ብር ይከፍሉትና እስክሪፕት ፅፈው ያሰጠኑትል ከዛ እጅ እንዲሰጥ ያደርጋሉ››አብዬት ከልምድ በሚያውቀው መሰረት መለሰላት፡፡
‹እንዴ ነፍስ ማጥፋት ስንት አመት ነው ሚያስፈርደው..?ለአምስት መቶ ሺ ብር ያን ሁሉ አመት ለመታሰር ፍቃደኛ የሚሆን ሰው ከየት ነው ሚያገኙት?››
በየዋህ ጥያቄዋ ተገርመው ሳቁባት፡፡
‹‹አምስት መቶ ሺ ብር ያልኩሽ እንደው በጥድፊያ ያደረጉት ስለሆነ ይወደድባቸዋል ብዬ ነው እንጂ ቀስ ብለው ቢያደርጉት በመቶ ሺብር ሀያ አመት የሚታሰርልሽ ሰው ላገኝልሽ እችላለሁ….አንዳንዴ እኮ በነፃ ወንጀል ሰርቼያለው ብሎ የሚታሰር ሰው አለ፡፡››
‹‹ምን አገኝ ብሎ?››
ቀላል ምሳሌ ልስጥሽ..አንድ ማውቀው የጎዳና ልጅ አለ.. ሁሌ ክረምት ሲቃረብ የጎዳና ላይ ቀላል የስርቆት ወንጀል ፈፅሞ ሆነ ብሎ ፖሊስ እጅ ይወድቅና ይያዛል…ሁለት ሶስት ወር ይፈረድበታል….በዛ ክረምት በዶፍ ዝናብ ከመሰቃት ይተርፍና ምግብም መጠለያም የሚያገኝበት ቦታ አገኘ ማለት ነው…፡፡ለማንኛውም አሁን ያንቺን የተሞላቀቀ ጥያቄ በመመለስ መዳከም የለብንም… ቀድሞ ወደአቀድነው የትውውቅ ፕሮግራማችን እንግባ፡፡ ያው እስከአሁን እርስ በርስ ከመተያየት በቀር አልተዋወቅንም..ማለቴ እኔ ሁላችሁንም አውቃለሁ..
‹‹እኔን ግን አታውቀኝም..እኔም አላውቅህም…እና ደግሞ ደስ አላልከኝም››አለው ካሳ ..አብዬት ውድ ሆነ ፈገግታውን ፈገግ አለና ንግግሩን ቀተለ
እናናተ ግን አብዛኞቻችሁ እርስ በርስ አልተዋወቃችሁም….እዚህ የተገኘንበትን ምክንያት ለእያንዳንዳችሁ በዝርዝር ነግሬችሆለሁ…እዚህ የተገኛችሁት ገንዘብ ለማግኘት ብቻ አይደለም….ከገንዘብ በላይ አላማ ይዘን ነው..በጣም አደጋ ያለውና ህይወታችን ሊያስከፍል የሚችል ሚሽን ነው….
👍29
‹‹ይቅርታ››ካሳ ነው አሁንም ከቀረቀረበት ቀና ሳይል እጆቹን ከላፕቶፑ ኪቦርድ ላይ ሳያነሳ የተናገረው‹‹..ይቅርታ እኔ ለምንም አይነት ሚሽን ህይወቴን መክፈል እልፈልግም….በተለይ እሷ ከመሞቷ በፊት ቀድሜ መሞት አልፈግም…..ግን ደግሞ ከሞተችም ቡኃላ መኖር አልፈልግም…በተረፈ እኔ የማንም ነፃ አውጪ አይደለሁም…..ጨርሼያለሁ…ክቡር ሊቀመንበር ቀጥል››
አብዬት ይሄን ሰው በጣም እየወደደው ነው..እንዲህ አይነት ሀቀኛና ውስጣቸውም ሆነ ውጫቸው ተመሳሳይ የሆኑ ሰዎች ያስደስቱታል..ደግሞም ለቡድኑ መነቃቃት ይፈጥራል ብሎ ገምቷል…ሌሎቹ ግን በሰውዬው ያልተለመደ ባህሪ ግራ መገባታቸው ከሁኔታቸው መረዳት ችሏል….
ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ..‹‹ እዛ በየሜዳ ከጎዳና እየተሰረቁ ኩላሊታቸውን ለሚዘረፉ ሚስኪኖች ፍትህ ለመስጠት ስንልነው….ገንዘብ ስላላቸው ብቻ የደሀን ነፍስ እየነጠቁ በገንዘባቸው ልባቸውን እየተጠቀሙ ያሉትን ክብረ ቢስ አውሬዎችን ለመበቀል ስንል ነው…ይሄ በደል እኛ የደሀው ማህበረሰብ ልጆቻችን ፤እህቶቻችን፤ ሚስቶቻችን ከዛም አልፎ እራሳች ጋር የሚደርስ ነው…እራሳችን እንደነፃነት ታጋይ ነው የሚንቆጥረው…አካሉን የሚዘረፈውን ማህበረሰባችን ነፀ-ለማውጣት የዘመትን የፍትህ አርበኞች..እና በዚህ መሀል ማንም ቢሞት የሞተውን ወንድማችንንም ወይም እህታችንን በክብር በልባችን እንቀብርን ወደፊት ነው..እኔ ብሞት የሚቋረጥ ነገር የለም…ዶክተሯ ብትሞትም እንደዛው….
‹‹እንድታውቁት ቡኃላ አላስተነቀቀንም እንዳትሉ ..እሷ ከሞተች ቡሃላ ለማንም ደንታ የለኝም… እያንዳንዳችሁን መጥተው ፊቴ ቢበላልታችሁ እራሱ አላዝንላችሁም..እንደውም አሳልፌ ምሰጣችሁ እኔ ነኝ ..ጨርሼያለሁ››
ዶክተሯ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ አለች..ምን ነክቶኝ ነው ግን እንዲህ በህይወቱ ከሚያፈቅረኝን ሰው ጉያ ወጥቼ.. ገና ለገና ፀባዩ ግራ ነው በሚል ሰበብ ከሚያርደኝ አፈቀላጤ ጉያ ውስጥ ተንደርድሬ የበገባሁት ?ስትል..በውስጦ እራሷን ጠየቀች፡፡ፀፀት ውስጧን በላት፡፡
አብዬትም ንግግሩን እስኪጨርስ ጠብቆ ምንም መልስ ሳይሰጠው በፈገግታ ይቅርታ‹‹…በዋናነት ለዚህ ጉዳይ መነሻው ዶክተሯ ብትሆንም አሁን የሁላችንም የጋራ አላማ ሆኗል……ገንዘቡን እሷ ብታቀርብም እኛም ሙሉ ህይወታችንን ለዚህ አላማ አቅርበናል..ሞቅ ያለ ያድናቆትና የድጋፍ ጭብጨባ ቤቱን አናጋው፡፡
እንግዲህ በእኛ ላይ ነገ ወይ ተነገ ወደያ አንድ ሴት የምግብ አብሳይ ትጨመራለች ..በተረፈ ሙሉ እስኮዱ ይህ ስለሆነ እያንዳንዳችሁ በየተራ ስለራሳችሁ ከስማችሁ ጀምራችሁ ታስተዋውቁናላች ለአሁኑ..ያው ብታውቁኝም ለመግቢያ ያህል ከራሴ ልጀምር…
ስሜ አብዬት ይባላል…ለጊዜው የዚህ ቡድን ሰብሳቢ ነኝ..አላማውን ለማንም ሳይሆን አምኜበት የገባሁበት ነው….ከዶክተር እና ከካሳ በስተቀር ሁላችሁንም በተለያየ ገጠመኝ ለአመታት አውቃችሆለሁ…ከሁላችሁም ጋር በመከራም በደስታውም ያሳለፍናቸው ታሪኮች አሉ..በህይወቴ አምናችሆለው ስል በተቻለኝ መጠን ህይወታችሁን በህይወት ክፍያ ጭምር እጠብቃለሁ እያልኩ ነው፡፡እናንተም እንደዛው እንደሆናችሁ አምናለሁ፡፡አመሰግናለሁ፡፡
ይሄው ነው ዶክተር ቀጥይ
ዶክተር ሰጲራ እባላለሁ፡፡የዳይመንድ ኢንተርናሺናል ሆስፒታል የማህፀን እስፔሻሊስት እና ከባለቤቶቹ ውስጥ አንዱ ነኝ..ነበርኩ ማለት ይቀላል ፡፡በአሁኑ ሰዓት ቅድም አብዬት የዘረዘራቸውን ወንጀሎች በሆስፒታላችን ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ እንደሚሰራ ከደረስንበትና በፍጥነት ካላቆሙ እንድምናጋልጣቸው ስለነገርናቸወ ያው ጎደኛዬን ገደሉት እኔም በተአምር በአብዬት እገዛ ለጥቂት ነው የተረፍኩት..በእውነት አሁን በዜና የሰማችሁ ውስጥ አንድ እውነት ቢኖረው ኤልያስ የተባለው ጎደኛችን መሞት ብቻ ነው….አቁስለውት የገደሉት መስሎቸው ጥለውት ሲሄዱ ቀድሞ እያጣጣረ የደወለው እኔ ጋ ነው..እሱ እንዳመልጥ ባያስጠነቅቀኝ እኔም አብቅቶልኝ ነበር…ለነገሩ አሁን ዋናው የእኔ መትረፍና መገደል አይደለም..እነዚህ ሰዎች እኔን ዝም ማስባል ከቻሉ በቀጣይነት ይበልጥ ሚስጥራዊና ፈርጣማ በመሆን ለመለዋወጫ አካል ሲሉ በየቀኑ በግፍ መግደላቸውና ይቀጥላሉ…..ቢያንስ አነሱን ከዚህ ተግባራቸው ለማስቆም ስታገል መሞት ለእኔ ክብርም ከፀፀትም ሚያድነኝ ነው..እና እናንተን የመሰሉ ወንድሞቼና እህቶቼ በሙሉ ልብ አላማዬን አላማችሁ አድርጋችሁ በህይወት እራሱ ለመፋለም በመነሳታችሁ ክብርም ኩራትም ተሰምቶኛል..በተረፈ በሂደት እንተዋወቃለን…፡፡
ቀጣይ የበድሉ እናት እራሷን ማስተዋወቅ ጀመረች
እኔ ሰብለወንጌል እባላላሁ ሰብሊ በሉኝ…የምሰራው ብና ቤት ነው….ያው ዳቡዬን እየቸረቸርኩ ነው የምኖረው…ይገባችሆል አይደል….?ግን ሞያዬ እሱ ብቻ አይደለም..በካራቴና ቲካንዶ ጥቁር ቀበቶ አለኝ…እና በተለይ ወንዶቹ እንዳትሳፈጡኝ ከአሁኑ ማሳሰብ አፈልጋለሁ…….ያው እኔ በፊትንም ለልጄ ብዬ ነው እንጂ ለመሞት ሰበብ የምፈልግ ሰው ነበርኩ እንዲ አይነት ቀሽት የሆነ የምሞትለት አላማ ሳገኝ ደግሞ መታደል ነው፡፡ማለት አለማ ስላችሁ እናንተ የምታወሩትን አይነት ማለቴ አይደለም ..ማለቴ አብዬት የሆነ ነገር እንዳደርግለት ከጠየቀኝ ህይወቴን በራሴ እጅ ሁሉ ላጠፋለት እችላለሁ..ይህንም ልጅ ታያላችሁ አይደለ የእሱ ነው…
ሁሉም እርስ በርስ ደግሞ እሱን ማየት ጀመሩ..
አረ ለወሬ አትቸኩሉ ..ከእሱ ነው የወለድኩት እያልኮችሁ አይደለም፡፡ እንደዛ ቢሆንማ በምን እድሌ ከማንም እንደወለድኩት በቅጡ አላውቅም..ግን ገንዘብን ሆጭ አድርጎ ከሞት ያተረፍለኝ እሱ ነው ፡፡እሱን ብቻ ሳይሆን እኔንም ጭምር..እስከአሁንም ሲቸግረኝ ልክ እንደታላቅ ወንድሜ ወደእሱ ነው የምሮጠው ፡፡አንድ ቀን አሳፍሮኝ አያውቅም..፡፡እና ያው በዘራፋ ምናምን ኤክስፐርት ነኝ…መግደልና ማፈንም የተካንኩበት ነው..አይዞችሁ አትፍሩኝ..አመሰግለሁ፡፡
ዶክተር ሰጲራ ሴትዬዋ ተናግራ እስክትጨርስ ከሰውነቷ ብዘ ኪሎ ነው ተቦጭቆ የወደቀው በተለይ ለህፃኑ ልጅ ስነልቦና ምንም ሳትጨነቅ ስለአባቱ የመጣላትን መዘላበዶ አበሳጭቶታል….ቢሆንም ምንም መናገር አልቻለችም፡፡
ቀጠለ
ስሜ ረዢምና አደረናጋሪ ነው..ባርች ብላችሁ ብጠሩኝ ደስ ይለኛል…ሁሉም ሰው ባርች ብሎ ነው የሚጠራኝ..ከአብዬት ጋር ወታደር ቤት ሆነን ነው የምንተዋወቀው..እኔ አብዬትና አቤሎ ወታደር ቤትም ሆነ ከእዛ ከወጣን ቡኃላም ብዙ ታሪክ አሳልፈናለ፤ያው አብዬት ቅድም አልነገራችሁም ቆስሎ ቦርድ ወጥቶ ነው ከሰራዊቱ የተቀነሰው፡፡ እኔና አቤሎ ግን ያው ከዚህ ይዘን የሄድነውን ፀባይ ማረቅ ተስኖን በስተመጨረሻ በዲሲፒሊን ተቀነስን…በእውነት ይህን ሳወራ ሁሌ አፍራለሁ.ጀግኖች ከሚፈሩበት የክብር ቦታ በቀሺም ምክንያት አንገት ደፍቶ መባረር አይነፋም..ለማንኛውም ያው አብዬት አቤሎም ያውቃሉ ሶስታችን ከዚህ በፊትም አንዳችን ላንዳችን ቡዙ ጊዜ ተደባበድበናል..ቆስለናል..ታስረናልም..ለምሳሌ አብዬት ለእኔ ሲል አመት ከስድስት ወር ታስሮል….አቤሎ ብዙ ጌዜ ተፈንክቶልኛል…በጩቤም ተወግቶ ያወቅቃል..በአጠቃላይ ስለኛ ምንም አያሳስባችሁ ለማለት ነው፡፡
👍311
እኔ ያው ባርቾ አቤል እባላለሁ፡፡ይህን ብድን የተቀላቀልኩበት ተቸማ ሆነ ምክንያት አለኝ….ብቸኛ እህቴ ቆሎ ለመሸጥ ከቤት እንደወጣች ከአዲሳባ ጎዳና ተሰውራብኛለች..እሷን ስፈልግ ሶስት አመት እልፎኛል ፡፡እሬሳዋን እንኳን ምነው ባገኝ እያልኩ ሁሌ እንዳዘንኩ ነው..፡፡እና አሁን ይሄን ታሪክ ስሰማ ምን አልባት የእህቴ በድንገት መሰወር እንቆቅልሽ ከእነዚህ ሰዎች ጋር የተያያዘ ይሆናል ብዬ አሰብኩ…እና እውነታውን አብረን እናውቃለን፡፡በቃ ይሄው ነው፡፡
ቀጠል ቶሎሳ................

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍241
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ቀፎ ሰቃዮች የመድሃኒት ሥርና ቅጠል ፈላጊዎች...
ለመኝታ የሚጠቀሙበት ማማ ላይ ዳራና ደልቲ ቅጠል ጎዝጉዘው
ቅጠል ተንተርሰው የተፈጥሮ ግዴታቸውን ከተወጡ በኋላ ደልቲ
የወደቀበትን ሳያውቀው አድሮ ከተኛበት ነቃ።

ልጃገረዷ ከደስታዋ ብዛት ይመስላል ማማዋ ላይ ፈገግ እንዳለች ፊቷን ዞራ ተጋድማለች ወገቧ ተሰርጉዶ ዳሌዋ
የለበሰችውን የፍየል ቆዳ ወጥሮታል። እጅዋ ጡቷን ቢጫንም ጡቷ ግን እንደ ችካል እጅዋን ወጥሮ ይዟታል… ደልቲ ተኝቶበት ካደረው ከማማው ስር የንጋት ፀሐይ ተኮስ ስታደርገው ከተኛበት ተነስቶ
ሳዳጎራውን ባጭሩ ጠበቅ አድርጎ አስሮ ላዩ ላይ ዝናሩን እንደ ቀበቶ
ታጠቀበት።

ጉሬዛና ጦጣዎች ከዛፍ ዛፍ እየዘለሉ በቂንጥ
እየተንጨዋለሉ በመቦረቅ እንደ ህፃን ልጅ “የአላየን መሰላችሁ..."እንደሚሉ ሁሉ እያሽካኩ ይቀበጣጥራሉ። 'ፈታይ' የሚባሉት ወፎችም ክንፍና ክንፋቸውን ከአካላቸው ጋር እየጠበጠቡ ከዛፍ ዛፍ
ይበራሉ። ንስርም ሰማዩ ላይ ክንፉን አጠፍ ዘርጋ አጠፍ ዘርጋ ያደርግና አየሩ ላይ ይንሳፈፋል... አረንጓዴ የተላበሱት የግራር የጥድ... ዛፎችም የጠዋቷን የፀሐይ ሙቀት እየከመከሙ ጎንበስ ቀና ይላሉ።

የየአካባቢው ያ የጥንቱ የሐመር ቀዬ! ያ የጥንቱ ባንኪሞሮ በብብትና ብብቱ እበትና ንብ ይዞ የመጀመሪያውን የሐመር እሳት የለኮሰበት ቅዱስ ስፍራ ቡስካ ተራራ ሰው አልባነቱ ዉጦት  ሐመሮች ሜዳውን መርጠው በብዛት ቢሸሹትም ከአራስ ቤት
እንደወጣች ሴት ድንቡሽቡሽ ብሎ ያምራል።

ደልቲ ዕጽዋቱን ምድሪቱን ሰማዩን ቁልቁል
የተንጣለለውን የአባቱን አገር... ቃኝቶ ወደ ማማው ጠጋ ብሉ አየ።ማማው ላይ ያች የደም ገንቦ ዳራ ተጋድማለች። የተገጠሙ
አይኖችዋን ጉንጯን ከንፈሯን ሰርጓዳ ወገቧን ዳሌዋን አይቶ ስሜቱ ጎምዥቶ ተወራጭቶ ሊያስቸግረው ከመከጀሉ በፊት ዘወር ማለቱን መርጦ ጉዞ ሊጀምር ሲል ሻካራ እጅ ትከሻውን ያዘው።

ዘወር ብሉ አያት። ልጃገሪዷ ትስቃለች አይኖችዋ ግን
እንደተከደኑ ናቸው። ለጥቂት ጊዜ  አይን አይኗን
ሲያይ የሚንቦገቦጉት ትናንሽ አይኖችዋ ተከፈቱ። ልጃገረዷ የደልቲ ጉሮሮ
ምራቁን ሲያንጎራጉጭ ሰማችውና “አያ ደልቲ?" አለችው።

ከዚያ አይኖቹን የሰጎን ላባ የሰካባትን ጴሮ የወገኖቹ ጠላት የሆኑትን ሙርሲዎች ገሉ በአምስት ረድፍ መስመር መስመር
የተበጀበትን ሳንቃ ደረቱንና ፈርጣማ እጆቹን አየችና

“ቦርጆ ኢሜ" አለችው አመሰግናለሁ  ለማለት:: በሐመር ባህል ቦርጆ ፈጣሪ እድል የፈጣሪ ሃይል ደህንነት... ሲሆን
የእርካታ በሐመሮች የቀን ተቀን ህይወት የመልካም አጋጣሚ መግለጫ ነው። ስቃይ የተጠናወተው ወይም በሞት የተለየ ቦርጆ
ራቀው፤ እድል ጠመመችበትም ይባላል።

ዳራ ደግማ “አያ ደልቲ" ስትለው በአይኖቹ ወይ አላት እኒያ የወተት አረፋ የመሰሉ ጥርሶችዋን እያሳየችው ፍልቅልቅ
አለችና፡-

“አንተ ጀግና ነህ!  ልብህ
የብዙ ልጃገረዶችን ፍቅር
ሊያስተናግድ የሚችል ሜዳ ማዘጋጀት ሲገባው ለምን እንደ ፍየል ግንባር ጠባብና ለአንድ ሰው የተዘጋጀ መውጫ የሌለው ማማ ሆነ አለችው  ፊቷን ቅጭም አድርጋ
ጀግናው!  ተኩሶ የገደለው!  እጄን እንጂ ልቤ ግን ፈሪ
ቢሆን ይሆናላ” ብሎ ትክዝ ብሎ ቆየና “ለነገሩ ምነው ጅል ጥያቄ ጠየቅሽኝ? የማማውን መውጫ አንችስ መች አጣሽው ወጥተሽ
ተጋድመሽበት አይደል!” አላት።

የደም ገንቦዋ ደግማ ደጋግማ በሣቅ ተፍለቀለቀችና “አንተ!
አያ ደልቲ እኔንኮ ስሜን ጠርተህ ወደ ደረትህ አላስጠጋኸኝም።
"ጎይቲ" ብለህ ጎይቲን ያገኘህ መስሎህ ነው እኔን ወደ ጎዳናህ ያስገባኸኝ

እኔ ግን ስቋምጥለት የኖርሁትን መንገድ ሳገኝ ባገኘሁት ቀዳዳ እንደ እባብ እየተሳብሁ እንደ አንበሳ እየዘለለሁ ልብህ ውስጥ
ገባሁ::... ከተኛችበት ብድግ ብላ እንደ ቂብ ዶሮ እያሽካካች አካባቢውን በሣቅ አጥለቀለቀችው: በሐመር ባህል ሴት ልጅ የሣቅ ምንጭ ናታ። ፍልቅልቅ ስትል የተጠማው የhፋው ወንድ ሁሉ
ጥሙን የሚቆርጠው በሷ ፈገግታ ነው!

በዚህ መሐል ማር ጠቋሚ ወፍ አጠገባቸው ካለው ዛፍ ላይ ድንገት አርፋ ላባዋ እየተርገፈገፈ በከፍተኛ ድምፅ ማዜም ጀመረች።
ደልቲ የዛችን ወፍ ድምፅ ያውቀው ነበርና ዞር ብሎ በፈገግታ አያት: ወፏ ግን ጨኸቷን ይበልጥ ጨመረችው።

ደልቲ ወደ ልጃገረዷ ዞሮ “ዳራ?” አላት

"ዬ"  አለችው

“ደርሼ መጣሁ ብሏት መሣሪያውን ይዞ ሲንቀሳቀስ ወፏ ከተቀመጠችበ ተነስታ በረረች ተከተላት። እንደገና አርፋ እየተጣራች ጠበቀችው አጠገቧ ሲደርስ ተነስታ በረረች እሱም
ተከተላት ዳራም ወፏን የሚከተለውን ጀግናዋን
በአይኗ ተከተለችው፡ ወፏን እየተከተለ ወደ ጫካው ሲገባ የንብ ድምፅ ሰማ፡
ትልቅ : ግንድ ላይ ንቦች እየዘመሩ ይዟዟራሉ ወፏ ደልቲን እየመራች ወስዳ ንቦች ዘንድ ካደረሰችው በኋላ ፊረሱም ሜዳውም
ይኸው'' ብላ ፀጥ ብላ ዛፏ ላይ አርፋ ብብቷን በማንቁርቷ እየኮለኮለች
ተቀመጠች።

ደረቅ ያለ የዛፍ ቅርንጫፍ ዘነጠፈና ከወገቡ ላይ ጩቤውን አውጥቶ ፋቅ ፋቅ አድርጎ አሾለው: ከዚያ በአይኑ የተቆረጠ ደረቅ
ግንድ ሲያማትር ከሱ በስተቀኝ በኩል ግንዱን አዬና ግንዱን በጩቤው ትንሽ አጎድጉዶ...ደ የጠረበውን እንጨት በቀዳዳው ከለካ በኋላ ጣቶቹን በመዘርጋት በመዳፉ አጥብቆ ይዞ እያሽከረከረ ይሰብቀው ጀመር: ለጥቂት ጊዜ ሲሰብቅ እንደቆየ አንድ ነገር መርሳቱን ትዝ አለው
ደረቅ ሣር ወይም ቅጠል። ሄዶ ለማምጣት ቀና ሲል ዳራ ደረቅ ሳር
ይዛ ከፊት ለፊቱ ድቅን አለች:: ቀና ብሉ በአይኖቹ ሳቀላት: ከዚያ እሷ ሳሩን ወደ ጢሱ ቀረብ አድርጋ ስትይዘው ጢሱ ትጉልጉል አለና ነደደ:: ወዲያው ዳራ የደራረቀውን እንጨት አስግብታ እሳቱን
አያያዘች:

ይህን ጊዜ ደልቲ መሳሪያውን ግንዱ ላይ አስደግፎ ዝናሩንና
ሳዳጎራውን ፈቶ ምልምል ራቁቱን እንደሆነ ዳራ የያዘውን እንጨት
ልትሰጠው ዘወር ስትል ራቁቱን አየችው ወዲያው አይኖችዋ ቁልቁል ሽቅብ እንደገና ቁልቁል ሮጡ። ፈዛ ቆመች አይኖቿን ቡዝዝ አድርጋ አየችው ! አያት ተያዩ ጢሱ ይጤሳል: ንቦቹ
ከርቀት ይዘምራሉ። ወፏ ቸኩላለች ዳራ ከንፈሯ ቀጥቀጥ ያለባት
መሰላትና ሳቅ አለች የሳቱ ግለት ሲሰማት ከነበረችበት ነቃችና ዝቅ ብላ አየችው።

“ትሰጭኝ!" አላት ደልቲ እጆቹን ዘርግቶ ሽቅብ ወደ ንቦቹ እያየ: ፈገግታዋን ሳትቀንስ አቀበለችው ጀግናው እሳቱን እንደያዘ
ዘወር ብሎ ሳያያት ወደ ዛፉ ተገጋ እሳቱ ጠፍቷል። ጢሱ ግን እየጨመረ ነው:
ቀና ብሎ ዛፉን አይቶ በግራ እጁ እሳቱን ይዞ በቀኝ እጁ ወደ ዛፉ ቅርንጫፍ ወጣ ዛፉ ሲንቀሳቀስ የጭሱ ጠረን ሲሸታቸው ንቦች ቁልቁል መጡበት ነደፉት፡ ፊቱ ቅጭም ሲል
ዳራ አየኘው: እንደገና ተስቦ ሌላ ቅርንጫፍ ላይ ወጣ ንቦቹ እሾሃቸውን በሰውነቱ እየሰገሰጉ ተረባረቡበት
ስቃዩን ጥርሉን ነክሶ ችሎፀ ሽቅብ እየተሳበ ወጣ... ጢሱን ወደ ቀፎው ሲያስጠጋው ንቦች ጩኸታቸውን እየጨመሩ ሸሹ የድምፃቸው ቃና ተቀየረ: ኡ ኡ ኡ.." ሲሉ ደልቲ እጁን ወደ
ተፈጥሮዊ የግንድ ቀፎ ከተተ። እጁ የማር ሰፈፍ ይዞ ተመለሰ።
እንደገና ከተተው ከዚያ ሰፈፉን በዳራ የፍሬ መልቀሚያ ሾርቃ
ሞልቶ ወረደ:

ዳራ ደልቲ ከዛፉ እንደወረደ፡ “መቼም አልተረፍህም"
ፈርጠም ብላ ጠየቀችው:

“አዬ አስቀርተውኝ ነበር! እንዲያው የሞት ሞቴን…" አለ።ላመል ያህል ጉንጭና ጉንጩ ጨምድዶ ከንፈሩ ለጠጥ ጥርሉ ብልጭ ብሎ።

አይቀርም ኖሯል። የአንተን እንጃ እንጂ እኔ መቼም ማር
አላማረኝም ስትለው፡-
👍34
“ትኩስ ማር ጥሩ ነው: ጤነኛ ያረጋል! ያጠነክራል።
ሳይነደፍ ደግሞ ጥሩ ነገር አይገኝም..." ብሎ ንቦቹ የነደፉትን ቦታ ሲነካካ ዳራ ጠጋ ብላ ሰንኮፉን ትነቅልለት ጀመር።

እውነትህን ነው ትኩስ ማር ጥሩ ነው። ደግሞ" ብላ ዝቅ
ብላ ስታይ መናገር አቃታት
ዳራና ደልቲ ወደ ማማቸወ ሄደው ማራቸውን ሲውጡ
ወፏ እንደገና ተንጣጣች። ደልቲ ሾርቃውን ይዞ ወርዶ ቅጠል ላይ ማሩን አስቀምጦ ሲመለስ ማር ጠቋሚዎ ወፍ “የልፋቴ ዋጋ ነው" እያለች ቆርቆር ቆርቆር አድርጋ እያንጋጠጠች መስልቀጡን ቀጠለች:

ደልቲ በርኮታውን በሚገባ እየከረከመ ለማስተካከል ብዙ ሰዓታት ፈጀበት። ከዚያ ብዙውን ጊዜ ከባራዛፍ የሚሰራውንና በመኸር ወቅት የሚዜምበትን የትንፋሽ መሣሪያ “ወይሳ" በሶስቱ ቀዳዳዎች ላይ ሶስቱን ጣቶቹን ብድግ ቁጭ ቁጭ ብድግ እያደረገ ከምንጭ ውሃ ኩልልታ ከንፋስ ሽውሽውታ ከአባቶች ብሒል ከወፎች ዝማሬ ከከብቶች ቡረቃ... የተቀነባበረውን ቃና ሲጫወት ነፍሱ በሃሴት እየተዋጠች ያቺ የሚወዳት የሐመር ምድር እኒያ ከሐመር ህዝብ ጋር ተጣጥመው የሚኖሩት
ከብቶች ወፎች እፅዋት ንፋሱ ፀሐይዋ... የፍቅር ምንጭ የሆነችው ጨረቃ!
የአያት ቅድመ አያቶቹ ፍቅር ጀግንነት አብሮ የመኖር ልማድ... በአይነ ህሊናው እየመጣ አንዱ ሲደቀን ሌላው ሲሸሽ ያኛው ሲመጣ ይህኛው ሲሄድ. የሙዚቃው ጣዕም ሁሉንም እየሸለቀቀ ፍሬ ፍሬውን ሲያቀርብላት...

አካባቢውን እየረሳ ትዝታው እየገዘፈ ሕይወትን እያነፃፀረ ወይሳውን እያስረቀረቀ ነጎደ። ወደ ውስጡ በስሜቱ ውስጥ ያሉትን ተባዮች ሊያጠፋ የሕይወት ደስታውን ሊጎናጸፍ! የሙዚቃውን ቃና
ተከትሉ አካሉን እየከፋፈተ ገባ፡

ወይሳ ብቸኛ ሲሆኑ ይህን እንደ አሜባ ቅርፅ አልባ የሆነ የሆያ ሆዬ አለም። በትዝብት መመልከት ሲጀምሩ! የደረቀውንና ዛፍ
ላይ ንፋስ የሚያስደንሰውን አረንጓዴ ቅጠል ያላቸውን ልዩነትና አንድነት መረዳት ሲችሉ  ህያው አካል በድን
ሆኖ ምስጦች ሲርመሰመሱበት ሲያዩ... ህይወትን ለመኖር ከገሃዱ ዓለም ጋር ሲጋፈጡ ይህችን ዓለም ምሬትና ጣምናዋን መለየቱ ምን ያህል ከባድ መሆኑን። የረገፈው ትናንት ከአበባው ዛሬ  ከእንቡጡ ነገ
የሚለይበትን ሊያውቁ የሚችሉ በሙዚቃ ቃና ነው። በወይሳ በባለሦስቱ ቀዳዳ የትንፋሽ መሣሪያ…

ደልቲ ይህን የሙዚቃ መሣሪያ መለማመድ ከጀመረ ዘግየት
ቢልም “የልጅና የሴት መጫወቻ ነው" እያለ ሲንቀው ኖሮ ቀን ኦልፎ
ቀን ሲተካ ወይሳው ሽማግሌ እሱ ልጅ እየሆነ መጣ እና እሸቱን የፍቅር ዘመን በመዚቃ እርሾ እያቦካ ህሊናው ላይ ትዝታውን
እየጋገረ ረሃቡን ለማስታገስ ሲያኝክ በሙዚቃው ቃና ተመስጦ ሲጫወት ጀንበር ከርቀት ተራሮችን እየታከከች ወደቀች። ደንገዝገዝ
ብሎ አካባቢው ለአይን ያዝ ሲያደርግ ግን ሸዋ ሸዋ... የሚል ድምፅ ሰማና ቀና ብሉ ሲመለከት ዳራ ተራራው ጫፍ ካለው ጫካ ብቅ አለች:

በጀርባዋ ያዘለችውን ማየት ባይችልም በሁለቱም እጆቿ
ሁለት ዶላ ይዛለች።

ደልቲ እሷን እያዬ የሙዚቃ መሣሪያውን ጭኑ ላይ
አስቀመጠ: ዳራ ፈገግታ ተላብሳ ቀረበችውና ዶላውን አስቀምጣ በጀርባዋ የተሽከመችውን በላሻ ሁለት ሾርቃና ቶፋ አወረደች።

“ይእ! አንተ አያ ደልቲ! ጀንበር ለመውደቅ እንዲህ ምን አጣደፋት? ከአንተ ከሄድኩ ወዲህ የሰራሁትን ሳላውቀው እንዲሁ
ስደነባበር ከብቶች ከዋሉበት መጡ።

“ቡስካን ደግሞ እቃ ይዞ በጨለማ መውጣት ለጠላትህም አይበለው። እየተደነባበርሁ ፀያንና ዴርን ብቻ አልቤ ሌላውን ለእነ
በርቲ ትቺላቸው ጀንበር ሳትወድቅ ወደ አንተ ገሰገስኩ።

“...ይእ! እና አንተ ዘንድ ለመድረስ ብጣደፍ፡ ብጣደፍ እግሬ ወደ ኋላ እንጂ ወደፊት እንደማይሄድ ሁሉ መንገዱ ሊያልቅልኝ ነው.. ብላ በሳቅ ተፍለቀለቀችና ወተት የያዘውን ዶላ ስታቀብለው ክዳኑን ከፍቶ አገጩን ከፍ አድርጎ ሲያንቆረቁረው
የጉሮሮው አጥቅ ከፍ ዝቅ ሲል እያየች ቆየችና ጨርሶ ሲሰጣት ሁለተኛውን ዶላ አቀብላው “ይእ! ጥሙ አቃጥሎህ ዋልህ አይደል!''
ብላ ወደ ጫካጡ ሄደች።

መጀመሪያ የደራረቀ እንጨትና ግንድ ቀጥላ ለጉልቻ የሚሆን ሦስት ድንጋይ አቅርባ እሳት አቀጣጠለችና ውሃ የያዘውን
ቶፋ ወደ አንደ በኩል ዘንበል አድርጋ ጣደችው ከዚያ በለሻ እንዲበላ ስታቀብለው “አንችስ ብይ እንጂ ተወተቱም ጠጭ…"
አላት ጭብጦውን እያላመጠ።.....

💫ይቀጥላል💫
👍37🥰7
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ-ዘጠኝ
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
ሶስቱ የዳይመንድ ኢንተርናሺናል አክሲዬን ዋና ባለቤቶች በተለመደው የሼክ ጠሀ ሚስጥራዊ ምድር ቤት ተሰብሰብው እየተወያዩ ነው፡፡ይሄ ቤት በቅርብ ተሰርቶ ያለቀ ለኪራይ የተዘጋጀ ቪላ ቤት ቢሆንም ለጊዜው ግን ከአንድ ዘበኛ በስተቀር ማንም አይኖርበትም፡፡
እንደተለመደው የውይይቱ መሪ ፕሮፌሰሩ ነው፡፡
‹‹ያው እንግዲህ አደጋው ከተፈፀመ አራት ቀናት አለፈዋል..በእነዚህ አራት ቀናት ውስጥ ችግሩን ለማስወገድ የተለያዩ ወሳኝ የሆኑ እርምጃዎች ወስደናል…..መንግስት ውስጥ ያሉ ትላልቆቹን ባለስልጣኖችም ለጊዜው ቢበሳጩብንም ግን ደግሞ ምርጫ ስላልነበራቸው ከጎናችን ተሰልፈው ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው ፡፡ለዛም ማረጋገጫ የፌዴራል አቃቢ ህጎችንና ዳኖችን ጭምር በማሳመን የእስር ማዘዣ ዋረንት ተቆርጦ ያው ሁላችንም እንዳየነው በቴሌቪዝን ጭምር ዜና ተሰርቶ እንዲተላለፍ ማድረግ ችለናል፡፡ ይሄ ደግሞ በእኛ ስር ያሉ ፖሊሶችም ሆኑ ጠቅላላ ሌሎች የመዲናይቱ ፖሊሶች በፍለጋው እንዲሰማሩ ምክንያት ሆኖል …ደግሞም ፖሊሶችንም ብቻ ሳይሆን ለቀበሌ ሚኒሻና ፤ታጣቂዎች፤ ለደንብ አስጠበባቂዎች ሳይቀር ፎቶዋ እንዲበተን ማድረግ ችለናል፡፡
‹‹ጥሩ ነው…እንደነገርከን በጣም ብዙ ስራ ተሰርቶል፡፡ ብዙ እርቀትም ሄደናል..ዋናው ግን እስከአሁን ምን ውጤት አገኘን ሚለው ነው?፡፡››ሼኪው ናቸው ፍፅም ደስታ በማይነበብበት እና በተሰላቸ ድምፅ አስተያየት አዘል ጥያቄ የሰነዘሩት፡፡
እንግዲህ እስከአሁን በጠፋች ማግስቱ ባንክ ቤት ታየች ከሚለው ዜና ውጭ የገባችበት አይታወቅም..ይሄም ሊሆን የቻለበት ምክንያት በወንጀልና መሰል ጉዳዬች አደገኛ ልምድ ያለው አብዬት የሚባል የቄራ ሰፈር ታዋቂ ማፊያ እየረዳት በመሆኑ እንደሆነ አውቀናል››
‹‹ያንን እንዴት ልትደርሱበት ቻላችሁ?››ሼኪው በጥያቄያቸው ገፉበት፡፡
ባንክ በጥሬው ካወጣችው 500 ሺ ብር ውጭ ወደእሱ አካውንት 5 ሚሊዬን ብር አዘዋውራለች….ያ ደግሞ እንዲያግዛት የከፈለችው ብር ካልሆነ ሌላ ምን ይሆናል?››
እኔ ግን ያልገባኝ አለ አቶ ሙሉ …ይሄን ጉዳይ ከሰማ የቆየ ቢሆንም እስከአሁንም አልተዋጠለትም‹‹እኔ ግን ያልገባኝ ምን ያህል ርቀት እረዳሻለሁ ቢላት ነው ይሄን ሁሉ ብር በአንዴ አውጥታ የሰጠችው..?››
ፕሮፌሰሩ መመለስ ከመጀመሩ በፊት ሼኪው ሌላ ጥያቄ አስከተሉ‹‹እንዴት ነው ልጁንስ ማግኘት አልቻላችሁም?በፊት ታውቀዋለች ማለት ነው…?.ማለቴ ይገባሀል አይደል ውሽማ ምናምኗ እንዳይሆን?››
ፕሮፌሰሩ በጣም ተበሳጨ…‹‹እንደምንም ከእዚህ ማጥ ልውጣ እንጂ ጊዜው ሲደርስ እኚን ሽማግሌ በገዛ እጄ ነው ሲጥ አድርጌ ምገላግላቸው ››ሲል በውስጡ ዛተ…‹‹ምን ነካዎት ሼኪ? ምንም ቢሆን እኮ የእኔ እጮኛ ነበረች..በእኔ ላይ ሌላ ሰው እንዴት ትደርብብኛለች ብለው ያስባሉ…?ለዛውም ብደርብስ እንዴት አንድ የሰፈር ዱርዬ ይሆንል….?››
‹‹እሱን እንኳን ተወው?››
‹‹ተወው ሲሉ?››
‹‹የሴትን ልብ መቼም ልትቆጣጠረው አትችልም…..ማረፊያውንም አታውቅም ለማለት ነው..ካስከፋውህ ይቅርታ……ደግሞ አንተ አፍቅረሀት አይደል ልታገባት የነበረው››
እንደማሰብ አለና ንዴቱን ለመቆጣጠር መከረ…አዎ ከእኒህ እድሜያቸው ያከተመላቸው ሽማግሌ ጋር የመላተሚያ ጊዜው አሁን አይደለም››አለና ድምፅን አርግቦ መናገር ጀመረ‹‹እርግጥ እኔ ሴት ለማፍቀር ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም…ግን ልጅ መውለድ በጣም ነው ምፈልገው...ከወለዱኩ አይቀር ደግሞ ከምትጠቅም ሴት መሆን አለበት ብዬ ነው..ማለት ሀብት ካላት …ይሄው ነው….ያ ማለት ግን ከእኔ ጋር ሆና እንደትንዘላዘል እፈቅድላት ነበር ማለት አይደለም……እና ልጁን ከዚህ በፊት እንደማታውቀው እርግጠኛ ነኝ..ያልገባኝ አሁን በዚህ ውጥረትና ግርግር መሀል እንዴት ልታገኘው እንደቻለች ነው፡፡››
‹‹እሺ ገባን ..አሁን ስለልጁ ጉዳይ ንገረን?››
‹‹ስለልጁ እንደደረስንብት ወዲያው ነበር ለመከታተል የሞከርነው..ግን ቀድሞን ተሰወረብን…አሁንም ድረስ እቤቱ አካባቢ ሰው መድበናል››
‹‹እንደነገርከን ከእዚሀ በፊት ከልጁ ጋ ግንኙነት ከሌላቸው..ቆይ ይሄ ስው ብሩን ካዘዋወረችለት ቡኃለ ….ተፈላጊ ወንጀለኛ መሆኗን በቴሌቪዥንና በየሚዲያው ወሬው ስለተዘራ ይሰማል መቼስ……እዛው ገሎ ወዲያ ቢገላገላት ማንም የሚጠይቀው የለም….ቆይ እንደዛ የሚያደርግ አይመስላችሁም? እኔ ይመስለኛል››
‹‹አይ ሼኪ እኔም እንደዛ አይነት የሚስጎመዤ ምኞት ነበረኝ..ግን ስለልጁ ቆይቼ ሳጣራ አደርጋለሁ ያለውን ነገር ከማድረግ ወደኃላ እንደማይል እና ለቃሉ በጣም ታማኝ ሰው እንደሆነ ነው፡፡››
"ተው በአንተ ደረጃ ያለ ሰው ታማኝ ሳይሆን እንዴት የእሱ አይነት ሰው …? እባክህ ገንዘብ የማይቀይረው ሰው የለም።"
"አሽሙሮትን ለጊዜው ልለፈውና .. የልጅን ፀባይ ከሌላ ሰው ሳይሆን ከራሱ ከዶዬ ነው የሰማሁት...በደንብ ያውቀዋል...አብረውም ስራ ሰርው ያውቃሉ።"
"እንደዛ ከሆነ አሪፈ ነዎ...እነሱ የሚያውቁት ከሆነ ፈልገው ለማግኘት ቀላል ነው በለኛ...እሱን ካገኘን ደግሞ ..በግድም ሆነ በገንዘብ ድርድር እሷን እንዲያስረክበን ወይም እዛው እንዲጨርስልን ማድረግ እንችላለን።››አሉ በሰሙት ዜና መርቅበው
"አይ እንደዛ ቀላል አይመስለኝም..ዶዬ እንደሚለው ከሆነ ልጅ የእውነት እየረዳት ከሆነ ነገረሩ በጣም ከባድ እና የተወሳሰበ እንደሚሆንብን ነው?"
ዝም ብሎ የቆየው አቶ ሙሉ የተሰማውን አስተያት ሰነዘረ"ይህ ደግሞ ምን ማለት ነው?የእነሱን አመል አንተ አታውቅም ..እርግጥ እኔም ሳወራቸው እንደዛ ብለውኛል….ግን እኔ የተረዳሁት ተጨማሪ ክፍያ ለመጠየቅ ፈልገው እንደሆነ ነው...መቼም እነሱ የሚጠረቁ አይደሉም...የፈለጉት ያህል ተከፍሏቸው ነገሩን ያቅልሉት።"
"ትክክል ነህ አቶ ሙሉ..እኔም የጠየቁት ተከፍሎቸው. ከዚህ መአት በፍጥነት እንድንወጣ ነው››ሽማግሌው ድጋፋቸውን ሰጡ፡፡
‹‹ ..እኔም አስቤበታለሁ...ክፍያው እንዳለ ሆኖ የተናገሩትም ግን አሳምኖኛል።ልጅ ወታደር ነበረ...እስከ መቶ እልቅና የደረሰ ማዕረግም የነበረው ኩማንዶ...አዲሳአበባን እንደእኔና እንደእናንተ ሳይሆን ጓዲያ ጓድጓዳዋን በርብሮ ያውቃታል...የእነዶዬን አሰራር ብቻ ሳይሆን ፖሊሶችም እንዴት እንደሚያስቡ እና አቅማቸውስ እስከምን እንደሆነ በደንብ ያውቃል….በተጨማሪ ደግሞ ያላቸውን የሚያደርጉለት መአት ተከታዬች እንዳለው ነው የሠማሁት"
"ታዲያ ሻንጣችሁን አዘጋጅ ..ፓስፓርታችሁንም በኪሳችሁ ይዛችሁ ዙሩ አትለንም...››አለ አቶ ሙሉ
"እናንተስ እሺ ጉልበታችሁ አልዛለም...እኔ በዚህ እድሜዬ ወዴት ሄዳለሁ?"
"አይ የሆነ ችግር ገፍቶ ከመጣ እርሷ እዚህ ውስጥ መኖር የለቧትም"
"እሳቸው ብቻ ለምን እኔስ?"አቶ ሙሉ በድንጋጤና በብስጭት አንቧረቀ…
"አይ አንተማ ከእኔ እኩል የተጨማለቅክበት ነው።እኔ ቀጥታ የሠዎቹን አካል ቀድጄ ልባቸውንም፤ አይናቸውንም ሆነ ኩላሊታቸውን ባወጣም ያንን ተደራድረህ እንዲሸጥ የምታደርገው አንተ ነህ ..ከባለስልጣኖቹ ጋር ግንኙነት ያለህ አንተ ነህ….ከውጭ ደላሎች ጋርም ምትገናኘው አንተ ነህ...እእ ...አንተማ እንኳን እኛ ዳቢሎስም ነፃ ሊያወጣህ አይችልም....እና እንዳልከው ፓስፓርትህም ሻንጣህም ዝግጁ ይሁን።
ትንፋሽ ወሰደና ንግግሩን ቀጠለ‹‹…ሼኪ ደግሞ ምን አልባት ችግር ከተፈጠረ ሁለታችን ይዘን የምንሄደው በቂ ዶላርና ዩሮ ያዘጋጅልን።››
"እሱ ችግር የለውም እቤት በቂ ይኖራል"
👍381
ፕሮፌሰሩም ይሄን በሁለቱም ባለደረቦቹ ላይ የተነዛውን ፍርሀት በጥበብ በመጠቀም ሊፈፅም ያሰበው ሀይለኛ እቅድ አለው…..በተለይ ዶክተሯ ተገኝታ ከተወገደች በእርግጠኝነት የሆስፒታሉ ትልቁ ባለድርሻ የእሱ እንደሚሆን አቅዶ ጨርሷል፡፡‹‹…አዎ እነዚህን ንፍጥ ጭንቅላቶችን በብልሀቴና በጥበብ ከዚህ ጉድ ካወጣዋቸው ለዛ ተገቢውን ክፍያ አስከፍላቸዋለሁ…..ቢያንስ እያንዳንዳቸው ካለቸው የሆስፒታል ድርሻ ግማሹን መልቀቅ አለባችሁ፣አሱን ለማድረግ የሚያግዘኝን ፕላን ደግሞ ጨርሼለሁ…በሂደት ደግሞ በቅርብ አመት ሙሉ በሙሉ ያ ሆስፒታል የእኔ ይሆናል››በማለት በውስጡ የነበረውን ስውር እቅድ በክለሳ በማሰብ ፈገግ አለ፡፡
‹‹ፕሮፈሰር ምን ጥሩ ነገር ሰማህ ?ፊትህ ፈካ እኮ››አቶ ሙሉ ነው በሁኔታው ተገርሞ የጠየቀው፡፡
‹‹አይ ዝም ብዬ ነው… ለማንኛውም ብሩ እቤት ካለ ጥሩ ...ከዛሬ ብኃላ ግን እርሷ ብዙም ከእኛ ጋር አይገናኙም...እርሷንና ሆስፒታላችንን ማትረፍ አለብን።››
"ወንጀለኛ መሆናችን ከተረጋገጠ እኮ ሆስፒታሉን ማትረፍ ቢቻል እንኳን የአክሲዬን ድርሻችን ሊወረስብን ይችላል…አንተስ በደህና ጊዜ ጥሩ ትምህርትና ሞያ አለህ..በዛ ላይ በሀምሳ አመትህ ወንደላጤ ነህ…የሆነ ሀገር ብትሰደድም ሰርተህ ትበላለህ፡፡እኔ ግን ያን ሁሉ ቤተሰብ ችግር ላይ መጣሌ እኮ ነው….ታውቃላችሁ እኔ እንደ ሼኪ እዚህም አዛም ድርጅት የለኝም… ያለኝ ጠቅላላ ሀብት ሆስፒታሉ ላይ የፈሰሰ ነው"አቶ ሙሉ ነው ስጋቱን የተናገረው፡፡
‹‹አዎ ስጋትህ ትክክል ነው…ያ ከመሆኑ በፊት ግን ቀድመን የሆነ ነገር እናደርጋለን...እስከመጨረሻ መጀመሪያ ጠበቃችንን ላማክረው.....
"በዚህ ጊዜ የሼኪው ስልክ ደጋግሞ ጠራ...አንድን ሲዘጉት ሌላው ይጠራል።..አራት ልጆቻቸው ናቸው በየተራ የደወሉት።
"ምንድነው ሼኪ አንሱት እንጂ..››
"አረ ልጆቼ ናቸው...የሆነ ነገር ሳይከሰት አይቀርም?"
ፕሮፌሰሩ"ምነው ተከበን ይሆን እንዴ?››አለ፡፡
ሴኪው ለእሱ መልስ ሳይመልሱ የመጨረሻ ልጃቸውን ስልክ አነሱ
"ጀማል ምንድነው አባታችሁን ምታስቸግሩት?"
"አረ ስለሆስፒታሉ ፌስብክ ላይ የማይሆን ወሬ እየተወራ ነው"
"ያው መቼስ ሰሞኑን ያለንበትን ሁኔታ ታውቃለችሁ .. ግን አይዞችሁ ገዳዬ ዶክተር ስትያዝ ወሬውም አብሮ ይከስማል"
‹‹አረ እንደዛ አይደለም.. እሷ በፌስብክ አልገደልኩም የሚል መልዕክት ነገር ለቃለች...በምስልም በፁህፍም እየተቀባበሉት ነው...አባዬ ምንድነው እየተፈጠረ ያለው.?..››
"በል ቸው ደውልሀለሁ"በንዴት ስልኩን ጠረቀሙና ሙሉ በሙሉ አጠፈት፡፡
‹‹ምንድነው የተፈጠረው? ››ሁለቱም በአንድነት ጠየቋቸው...ሴትዬህ ከተደበቀችበት ጉድጓድ ሆና የመጀመሪያ ሚሳዬሎን ተኩሳለች እናም ባይገድለንም በደንብ የሚያቆስለን ይመስለኛል?ያ አላህ ያ ረቢ በስተመጨረሻ ቅሌት"
"ሼኪ የሆነውን በቀጥታ ለምን አይነግሩንም?"
‹‹ፌስብክ ነው ምን የምትሉት..ይሄ የምትጎረጉሩት ነገር መሰለኝ…በዛ ላይ የሆነ ነገር ተናግራ ለቃለች ነው የሚሉት...››
ሁለቱም ስልካቸውን አውጥተው ፌስብክ ከፈቱ… ፕሮፌሰሩ በሚሴጅ ሊንክ ተልኮለታል።
‹‹የተሠባበሩ ነፋሶች ››የሚል የፌስ ብክ ገፅ ነው።ከተከፈተ ገና ሁለት ቀኑ ቢሆንም ከአንድ ሺ ሁለት መቶ በላይ ተከታይ አለው።
ምስሎ ከፁሁፉ ስር ገጭ ብሎል አዲስ የተነሳችው ፎቶ መሆኑን እርግጠኛ ነው፡፡ በዚህ አይነት አለባበስ አያውቃትም።
ትንሽ ከሳ ያለች ቢመስልም የመጎሳቆል ሁኔታ አይታይባትም።የለበሰችው ልብስ የተመረጠ፤ ያለችበት አካባቢ የፀዳ..ሁኔታዎ የተረጋጋ ነው..ፁሁፉን ተወና ሊንኩን ተጫነው… ወደሺዲዬ መራው.. ትግስት አጥቶ ሁሉም እንዲሰማው ድምፅን ከፍ አድርጎ ከፈተው...
///
እኔ ዶ/ር ሰጲራ እባላለሁ። አብዛኞቻችሁ የት ነው የምናውቃት እያላችሁ እራሳችሁን በማስጨነቅ ላይ እንዳላችሁ እገምታለሁ።ግን አትጨነቁ ሰሞኑን በየቴሌቨዠን ጣቢያውና በየሬዴዬ በተገኘችበት ትያዝ የሚል አዋጅ ተላልፎብኛል።ምክንያታቸው ጓደኛሽን ገድለሻል ነው..፡፡እኔን ግን ከሞት ያዳነኝ ያ ገድለሽዋል የተባልኩት ወዳጄ ኤልያስ ነው።እሱን እቤቱ ሄደው ካጠቁት ቡኃላ የገደሉት መስሏቸው ወጥተው ወደእኔ ሲመጡ ቀጥታ በህይትና በሞት መካከል ሆኖ የደወለልኝ ሞቹ ኤልያስ ነው.. ቀድቼዋለው አድምጡት...
‹‹ሄሎ...ማን ል...በል?"
"ዶ/ር አምልጪ...ሊ...ገድ..ሉሽ ...እየ...መጡ ..ነው"
"ኤልያስ..?"
"እባ...ክሽ ፍጠ..ኚ"
‹‹ኤልያስ አንተ ደህና ነህ..?ጎድተውሀል እንዴ?"
////
እንግዲህ እንዲህ ነበር የሆነው…ድምፁ የእሱ መሆኑን ደግሞ ቤተሰቦቹና የምታውቁት ሰዎች ምስክር መሆን ትችላላችሁ።
እንግዲ ለምን ኤልያስ ተገደለ .?.እኔስ እንዴት ተረፍኩ? ገዳዬቻችን ማን ናቸው ..?ምክንያታቸው ምንድነው...?እንደ አስፈላነቱ የጓደኞቼ ገዳዬች እና የእኔ አሳዳጆች ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ በተከታታይ የማቀርብላችሁ ይሆናል….እስከዛው ለፍትህ ስትሉ ..ለተገፉና ለተሰባበረ ነፋስ ያላቸው ዜጎች ስትሉ …ይሄንን ገፅ ሼርና ላይክ እያደረጋችሁ ጠብቁ ...አመሰግናለሁ።
ወደፌስብኩ ፁሁፉ ተመልሶ አየው ..ሲጀምር 1200 የነበረው ተከታይ 1653 ደርሶል…..ከ70 በላይ ሰው ሼር አድርጎታል…እርግጠኛ ነው… ከአንድ ሰዓት ቡኃላ ከመቶ በላይ ዩቲዩበሮች ዜና ሰርተውበት በመላው አለም ይበትኑታል፡፡….ከአስር አመት በላይ ትቶት የነበረው ጨጎራው ተነሳበት……
‹‹የተረገመች››ጠረጰዛውን በቡጡ ነረተው
‹‹ቀስ ጠረጰዛውን ሳይሆን እሳኑ አግኝቶ ነው እንዲህ መነረት››አሉ ሼኪ…አሁን እየደከማቸው ነው….ይህቺን ሴት እንደምንም ብገላገል እራሱ እፎይታ አይሰማኝም››አሉ በውስጣቸው..እንደህ ሊሉ የቻሉት ፕሮፌሰሩ ላይ ባላቸው ትልቅ ፍራቻ ነው..በህይወት ጉዞቸው ፊታቸው የተጋረዱ ብዙ ግለሰቦችን በቀላሉ ዞር አድርገው መንገዳቸውን በመቀጠል በሰላም ዛሬ ላይ ደርሰዋል..ይሄ ፊታቸው የተቀመጠው ፕሮፌሰር ግን በቀላሉ የማይገፉት ቆጥኝ ነው የሆነባቸው…አሁን አሁን በጣም ነው ሚጠሉት.. በጣምም ነው የሚፈሩት፡፡
ፕሮፌሰር ስልኩና አወጣና ደወለ
‹‹ሄሎ ዶዩ››
‹‹አቤት››
‹‹ሰዎችህ ጎንደር ደረሱ እንዴ››
‹‹አዎ ደርሰዋል፣የእናቷን ቤትም አግኝተዋል….ግን እሷን እስከአሁን ሊያገኞት እልቻሉም..››
‹‹እሷ እዚሁ ነች…እሷን መፈለግ ያቁሙ..አሁን እናትዬውን በአይነ ቁራኛ ይከታተሉ..በስንት ሰዓት ይገባሉ? በስንት ሰዓት ይወጣሉ? አብሮቸው ማን ይኖራል…?እሱን ብቻ ይስሩ››
‹‹እሺ ነግራቸዋለሁ›››
‹‹እና ደግሞ አንተም አሁን ተነስና እዛው ገብተህ አንድታድር…አንድ ሁለት ሰው ይዘህ ሂድ በቂ ገንዘብና መሳሪያም ያዝ…..››
‹‹ምንድነው ጦርነት ልንከፍት ነው እንዴ?›.
በዶዬ የቀልድ የሚመስል ንግግር ተበሳጨበት‹‹አንተ ምን አይነት ሰው ነህ ?ከዚህ በላ ጦርነት አለ…?የዚህች ሴት ሁኔታ ለመቋጨት አንድ ሚሊዬን ብር ተመድቦላችሆል..አሁን ወደ ሂሳብህ ሁለት መቶ ሺ ብር አዘዋውርልሀለው…››.
‹‹አመሰግናለው..እንዳልክ እደርጋለሁ..ግን እዛ ሄጄ ማደርገውን ማለቴ ተልዕኮችንን አልነገርከኝም››
‹‹ለጊዜው ያልኩህን ብቻ አድርግ.. እዛ እንደደረስክ ደውልልኝ…ምን እንደምታደርጉ ነግርሀለው….ታዲያ ተሳስተህ እንኳን በኦፊሺያለ ስልኬ እንዳትደውል..እንደውም አሁኑኑ ከስልክ ላይ አጥፋው…ስትፈልገኝ በዚህ አሁን እየደወልኩልህ ባለውት የሚስጥር ቁጥሬ ነው››
‹‹ገብቶኛል እሺ›
ስልኩን ተዘጋ..ሁለቱም አፍጥተው እያወራ ስላለው ነገር እንዲያብራራለች እየጠበቁት ነው፡፡
👍243
‹‹እንግዲህ አይጦን ከጎሬዋ ለማውጣት ወጥመድ ማጥመድ ብቻ በቂ አይደለም..ወጥመዱ ጫፍ ላይ ምትወደውን ምግብ ማንጠልጠል የግድ ይላል…››
››እና አማችህን ልታፍን ነው ማለት እንዳይሆን…?››ሼኪው ፈገግ እያሉ ጠየቁት፡፡
‹‹የእናትዬው በቂ ካልሆነ አሉ የተበሉ ጠቅላላ ዘመዶቾ ነው አፍኜ የምጨርስላት››
‹‹አንድ ታሪክ ለልንገርህ››
‹‹ይቀጥሉ..››
‹‹የዛሬ 10 አመት ለመጀመሪያ ጊዜ ስተዋወቅህና ስለዚህ ሆሲፒታል ስራ እቅድ ስታወራኝ በጣም ተደምሜብህ ይሄ ጥበበኛ ሙሁር ቢሰልምና አንዶን ልጄን ብድርለት ብዬ ተመኝቼ ነበር..ትዝ ላይልህ ይችላል..የተወሰነ ቀንም ሀይማኖት ላይ ስላለህ አቋም በሰበብ አስባብ ጠይቄህ ነበር….እንኳንም ጥሩ መልስ አልመለስክልኝ…በገዛ እጄ ግዙፍ አውሬ በውስጡ ያሰረ ሰው አማች አድረጌ አቤቴ አስገብቼ መጥፊያዬን አመቻችቼ ነበር››
አቶ ሙሉ በንግግሩ ሳቀ..
‹‹መቼስ ሁለታችሁም ውስጥ ያለው ሴይጣን እኔ ውስጥ ካለው ሰይጣን አይተናነስም››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው ..ልዩነቱ ግን አንተ ውስጥ ያለው ያው ከአንተ ጋር ስለተማረ የተለየ ነው …ተንኮል በትምህርት ሲታገዝ ደግሞ ትክክለኛው ማሳያ ሆኗል….ያው ነው ልዩነቱ፡፡


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍26😢6😁31
#እውር_ድንብር

ሽማግሌ ሲልክ እራሱን አልቻለ
እሷም የሱ ቢጤ ራሷን ያልቻለች



አለመቻል በአንድ ላይ ሲኖሩ
ሲኖሩ-------ሲኖሩ



የወለዱትን ልጅ
መቻል ብለው ጠሩ።

🔘ግዛቱ አማረ🔘
👍39😁22🥰3🎉3
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ-አስር
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
////
ሰዓቱ ከምሽቱ አራት ሰዓት ነው፡፡ ፕሮፌሰሩ ከዶዬ ጋር በስልክ እያወራ ነው…ዶዬ እንደታዘው ጎንደር ገብቶ ቀድመው እዛ ገብተው ተልዕኮ ላይ ከተሰማሩት የራሱ ሰዎች ጋር ተቀላቅሏል….ሆኗል
‹‹….እሺ ፕሮፌሰር አሁን ያለነው አሮጊቷ ቤት ፊት ለፊት ነው››
‹‹ጥሩ…አብሮት ቤት ውስጥ ስንት ሰው አለ?››
‹‹… ብቻቸውን ነበሩ አሁን ከመሸ ግን አንድ ሴት ከ8 ዓመት ልጆ ጋር መጥታ ተቀላቅላቸዋለች…..እህቷ እንደሆነች አረጋግጠናል…እስከአሁን ስላልወጣች በእርግጠኝነት አብራቸው ነው የምታድረው ማለት ነው››
‹‹እንግዲህ ዛሬ ማድረግ አንችለም ማለት ነው››
‹‹እና እንዴት እናርግ?››
‹‹ምንም አታድርጉ ዝም ብላችሁ አሁን እያደረጋችሁት እንዳለ ተከታተሉ….ምን አልባት ሴቲቱ ወጥታ ምትሄድ ከሆነ ደውሉልኝ….ሴትዬዋም ፈፅሞ ከአይናችሁ ሊሰወሩ አይገባም››
‹‹እሺ ሀለቃ›
‹‹በቃ ቸው አዲስ ነገር ካለ በማንኛውም ሰዓት ደውልልኝ›› አለና ስልኩና ዘግቶ ወደኪሱ በመክተት ትኩረቱን ፊት ለፊቱ ወዳለው ሰው መለሰ፡፡
‹‹እሺ አቶ ሙሉ.››
‹‹‹አለው›› ፊት ለፊቱ የተቀመጠውን አቶ ሙሉ መለሰ....በዚህ ሰዓት ሁለቱም ወደቤታቸው አልገቡም.ቦሌ አካባቢ የሚገኝ ቪ.አይ ፒ ክፍል ያለው ውስኪ ቤት ጎን ለጎን ተቀምጠው እየዶለቱ ናቸው፡፡
‹‹አሁን እናቷን አገትናቸው እንበል ከዛስ?››ሁኔታው ሙሉ በሙሉ ግልፅ ያልሆነለት አቶ ሙሉ ጠየቀ
‹‹ከዛ ማለት?››
‹‹እንዴት እሷን አግኝተን ወደእኛ መጥተ እጆን እንድትሰጥ አናስፈራራታለን..?ስልኳ እንደሆነ አይሰራም››
‹‹ለእሱ አታስብ….አድራሻዋን እኮ ሰጥታኛለች›
‹‹እንዴት? መቼ? በሚስጥር ማውራት ጀመረችህ አንዴ?››አቶ ሙሉ ድንገተኛ የጥርጣሬ ሀሳብ በአእምሮው ተሰነቀረ፡፡
‹‹ባክህ አተበርግግ….ባለፈው መልዕክቱን ስትለቅ ያየንበት ‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች›› የሚል የፌስ ቡክ ገፅ አለ አይደል? ወይ ቀጥታ የእሷ ነው ካልሆነም ደግሞ የሚረዳት ሰው የሚቆጣጠረው ነው ሚሆነው….በዚህም አለ በዛ ገፅ ላይ መልዕክቱን ኢንቦክስ እናደርግላታለን .ከዛ እየተክለፈለፈች እቤቴ ድረስ ትመጣለች…፡፡
‹‹እሷ ከተያዘች ቡኃላ እናትዬውን እንለቃቸዋለን አይደል?.››
‹‹እስከአሁን አላሰብኩበም …ግን አሁን ያ ምን ያሳስባል?››
‹‹አይ እንዲሁ ዝም ብዬ ነው…አሁን ቀለል እለኝ …እንደው ይሄንን ጭንቅላትህን ተጠቅመህ ከዚህ መአት ካወጣሀን የዘላለም ባለውለታዬ ነው .››
‹‹አትጠራጠር….ለሽልማቱ ብቻ ተዘጋጅ…..አሁን እንሂድ…›ሂሳብ ከፍለው ተያይዘወ ወጡና ሁለቱም በየራሳቸው መኪና ገብተው በተለያየ አቅጣጫ ወደ የቤታቸው አመሩ…
.//////
እቤቱ ውስጥ አብዬት ካሱ ህፃኑ በድሉ እና አዲስ የተቀላቀለቻቸው የዶክተሯ ተመላላሽ የቤት ሰራተኛ የነበረችው ምግብ አብሳዬ ክብነሽ ብቻ ነው ያሉት፡፡ሶስቱ ወንዶችና የበድሉ እናት ሰብለ ለተልዕኮ ተሰማርተዋል፡፡
ክብነሽ ህፃኑ በድሉ ስለተኛ ምን አልባት ድገት ሲባንን እንዳይደነግጥ እሱን ለመጠበቅ እላይ መኝታ ክፍሏ ነው ያለቸው …..የተቀሩት ግን ሶስቱም ሳሎን ተቀምጠው ስራ እየሰሩ ነው….
ካሳ ኮምፒተሩን አዘጋጅቶ ካሜራውን ደቅኖ ማይክሮፎኑን ደቅኖ የዶክተር ሰጵራን ዝግጁ መሆን እየጠበቀ ነው…
‹‹እንዴት ነኝ….አምሮብኛል እንዴ…?.ተጎሳቁዬ መታየት አልፈልግም››አለች፡፡
‹‹አሪፍ ነሽ… ምን አትይም›› አላት አብዬት፡፡
ካሱ አብዬት ላይ አፈጠጠበት
‹‹ምነው የተሳሳተ ነገር ተናገርኩ እንዴ ?.››አለ .አብዬት.. ከንግግሩ መካከል የትኛው ካሱን እንዳበሳቸው ስላልገባው፡
‹እንዴት ምንም አትይም ትላታለህ ?እኔን ስሚኝ ልጄ ፊትሽ የውበት ሸማ ለብሷል…በዛ ላይ ከግንባርሽ የሚፈልቅ የማር ወለላ ይንጠባጠብበታል..እርግጥ ወለላውን እኔ ከሩቁ እየታየኝ ቢሆንም ይሄ አጠገብሽ ያለው ማይረብ ሰውዬ ግን የማየት ብቃት የለውም..አይቶ የማድነቅ ብቃት ከሌለው ደግሞ የማፍቀርም ብቃት እንደሌለው እግረመንገድሽን ማረጋገጥ ትቺያለሽ…. ይሄ ደግሞ ያበሳጫል፡፡ቢሆንም ዋናው ለእኔ ወላላው ሲንጠባጠብና ፊቴሽን ሲያለብሰው ማየቴ ነው፡፡እንደውም ከፊትሽ ላይ ትንሽ በጣቴ ጠቀስ አድርጌ ለዚህ የድሮ ወታደር ላቅምሰው እንዴ ?አዎ ምን አልባት በዛን ጊዜ ልዩና ድንቅ የውበት ቀንዲል ነች ብሎ ለመመሰክር ይገደድ ይሆናል››
አብዬት ሌላ ሰው እንዲህ ተናግሮት ቢሆን ይሄኔ በዛ እንደሼሴ ግዙፍ በሆነ ክንዱ አድቆት ነበር..ካሱን ግን በጣም ስለተረዳው እንደውም በሚናገረው ማንኛውም ነገር እየተዝናና ነው፡፡
ዶክተር ፈግግ አለች…‹‹ዋናው አንተ ቆንጆ መሆኔን ከመሰከርክ ይበቃል…እንደዛ ከሆነ እንቀጥል›› አለችው….የእሷ ውበት የመነታረኪያ ርእስ ሆኖ እንዲቀጥል ስላልፈለገች›
ገሮሮዋን አፀዳዳችን… ዝግጁ ሆነች…..ምልክት ሲሰጣት አይኖቾን ካሜራው ላይ አፍጥጥ የተዘጋጀችበትን ማውራት ጀመረች፡፡
///
ዛሬ እንግዲህ ዘርዘር ያለ ነገር ነግራችሆለው…ዳይመንድ ኢንተርናሺናል ሆስፒታል ሲመሰረት ለትርፍ ብቻ የተቋቋመ ድርጅት አልነበረም….ቢያንስ በግልፅ ስንነጋገር እና ሆስፒታሉን አለማና ግብ ዘርዝረን እና በፕሮፖዛልም አዘጋጅተን ስንወያይ ሀገራችንን ረድተን እኛም ጥቂት ለመጠቀም. ነበር፡፡ህዝባችንን ከበሽታና ስቃይ እየፈወስን በሂደት በውጭ ሄዶ መታከም ያለባቸውን እንደ ኩላሊት ንቅለ ተከላ…የልብ ኬዞችን የመሳሰሉትን ተገቢውን መሳሪዎቹን በማስገባት ሰው ከሀገር ሀገር ሳይንከራተት በተመጣጣኝ ክፍያ መታከም እንዲችል ለማድረግ ነበር፡፡ከሀገራችንንም አልፈን ለምስራቅ አፍሪካ ተመራጭና የህክምና መአከል ገንብተን ጎረቤት ሀገሮች ሀገራችን እየመጡ ሚታከሙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነበር እቅዳችን…፡፡ብዙ ብዙ ሩቅ አሳቢ እቅድ በማንገብ ሆስፒታሉን ገንብተን ነበረ፡፡ በዛም ከ8 አመት በላይ እድገቱን የጠበቀ የምታቁትን አይነት ገናና ሆስፒታል መገንባት ችለናል….ግን የሚገርመው ከመሀከላችን ሆነው ከመጀመሪያው ጀምሮ ስውር ሀሳብና እኩይ እቅድ የነበራቸው ሰዎች ነበሩ
…ሰሞንኑ እንዳሰመማሁት አሁን በተፈጠርው ችግር ምክንያት ሆስፒታሉ ላይ የተለያዩ ሀሚቶችና እየተወሩ እንደሆነ በየማህበረዊ ሚዲያው አንብቤያለሁ…ችግሩ ቀጥታ ከሆስፒታሉ ጋር ሚገናኝ አይደለም፡፡ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ ዶክተሮችን ነርሶችና ሌሎች ባለሞያዎች በጣም ድንቆች በስነ-ምግባር የሚሰሩና በጣም የምኮራባቸው የሀገር አለኝታ ናቸው…
👍16😁31
ችግሩ እጮኛዬ የነበረው ፕሮፌሰር የተመለከተ ነው….በእውነት እሱን እጮኛዬ ብዬም ሆነ ፕሮፌሰር ብዬ መጥራት አፍራለሁ…..እስኪ ፖሊሶች ስራችሁን በሀቀኝነት የምትሰሩ ከሆነ ፕሮፌሰሩን በሆስፒታሉ ሽፋን ከጥቂት የሆስፒታሉ ባለቤቶች ጋር በመመሳጠር ምን ይሰራ እንደነበረ አጣሩ….?ሲሆን ሲሆን ፕሮፌሰሩ እራሱ ነገ በጥዋቱ በቅርብ ካለ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ እያንዳንዱ የሰራቸውን ወንጀሎችንና ቀፋፊ ሀጥያቶችን እንዲናዝ ምክር እሰጠዋለው….ይሄ ምን አልባት በፍረድ አደባባይ መሰቀል ሲገባው በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ የቅጣት ማቅለያ ሆኖ ይታሰብለት ይሆናል….ካልሆነም እንዳልኩት ፖሊሶች እኔን ማሳድዱን ለጊዜው ገታ አድርገው ምርመረቸውን በእሱ ዙሪያ ቢያደርጉ ስለኤልዬስ ግድያ ማንነት ሆነ ሌሎች ለመስማት የሚሰቀጥጡ ወንጀሎችን በርብሮ ለማውጣት ወደትክክለኛው አቅጣጫ ይመራቸዋል.. አሁን እኔም እየተሳደድኩ ያለሁት ጓደኛዬ ኤልያስም ሊገደል ያቻለው እነዚህ በፕሮፌስሩ የሚመሩ ማፍያ ብድኖችን እየሰሩ ያሉትን ለጆሮ ሰቅጣች ወንጀል ደርሰን ልናስቆማቸው እንቅስቃሴ ሰለጀመርን ነው….አውቃለሁ አሁን ፖሊሶች ፕሮፌሰሩ እና ከኃላው ያሉ ሰዎች ላይ ምመርመር ለመክፈት ቀላል አይሆንላቸውም…..ምክንያቱም ከፕሮፌሰሩና ወንጀሎቹ ጀርባ ከርሳም የሆኑ ትላልቅ ባለስልጠኖች ጥቂትም ቢሆኑ የፖሊስ አዛዦች አሉበት ….
ለማንኛም ሶስት ቀን ሰጥቻችሆለው…ከሶስት ቀን ቡኃላ የፕሮፌሰሩ ወንጃሎችን በዝርዝር እመለስባቸዋለሁ…በነገራችን ላይ ጎበዝ የምርምር ጋዜጠኛ የሚኖር ከሆነ በፌስቡክ ገፅችና በውስጥ መስመር ቢያናግረኝ መነሻ ሚሆኑትን ተጨባጭ መራዎች ለመስጠት ፍቃደኛ ነኝ….ከጎኔ ለሆናች ፍትህ አፍቃሪ ሁሉ አመሰግናለሁ፡..ከሶስት ቀን ቡኃላ በሌላ አዲስ መረጃ እመለሳለሁ..እስከዛው ሁላችሁም በየእምነታችሁ ፀልዩልኝ››
ጨረሰችና ከካሜራ ፊት ወንበሮን ዞር አርጋ ተቀመጠች‹‹እንዴት ነበርኩ.?ስትል አስተያታቸውን ጠየቀች
‹‹አሪፍ ነው…ለፖሊሶቹም ለወንጀለኞቹም እንዲሁም ለህዝቡ ጥሩ የቤት ስራ ነው የሰጠሻቸው››አላት ከፊቷ የቆመው አብዬት ፊቱ ላይ የተጋደመውን መስመር በእጆቹ እየዳበሰ፡
ካሳ ካሜራውን ከኮምፒተር እያገናኘ መናገር ጀመረ‹‹ከሶስት ቀን ሰጥቻችሆለው ስትይ ትገርሚያለሽ?›አለላት
‹‹ለምን ገርማለሁ?››
‹‹አሁን እስከሶስት ቀን እነሱ ያለሽበትን አግኝተው ጉሮሮሽን እንደማያንቁሽና እንደማይገላግሉሽ ብምን እርግጠኛ ሆንሽ;…በአብዬትሽና በጎደኞቹ ተማምነሽ ብቻ እንዳይሆን?›
‹‹አዎ በእነሱ ብቻ ሳይሆን በአንተም ጭምር ነው የምተማመነው›
‹‹እኔ ግን ብተድኝም ቢይዙሽም ችግር ለብኝም››
ደነገጠች‹‹ምን ማለት ነው…?ከአንተ በላይ ለእኔ የሚጨነቅ ሰው ይኖራል እንዴ..?ከገኙን እንደሚገድሉኝ አታውቅም..››
‹‹አውቃለሁ..ግን አንቺን ብቻ ገድለው እንደማይሄዱ አውቃለሁ… እዚህ ቤት ያገኙትን ሁሉ አንድላይ ጨፍጭፈው ነው የሚሄዱት..››
‹‹እና ይሄ ይበልጥ አያስፈራህም.?›አለው አብዬት ተገርሞ
‹‹እንዴ ትቀልዳለህ ምን አልባት እዛ ስንሄድ እኔም ጸባዬን አሻሽል ይሆናል… እሷም እኔን እንድሮዋ ወደማፍቀር ትመጣ ይሆናል….አዎ ቶሎ ሄጄ የሰማይ ቤቱን ኑሮ መሞከር ፈልጋለው››
‹‹አሀ እዚህ ያልተሳካልህን እዛ ልትሞክር ?››
‹‹አዎ››
‹‹ግን እዚሁ እሷም በህይወት ቆይታ አንተም ሳላም ሆነህ ሁለተኛ እድል ለማግኘት መሞከሩ አይሻልም.?››አለው
‹እዚህማ በየት….ይህቺ አለም የቀሺሞችና የደደቦች ነች…ለእንደእኔ አይነት ጂኒዬስ ቦታ የላትም….በፊት ያን ስገግብግብ የስም ፕሮፌሰር ከፊቴ ተጋርደ ነበር….አሁን ደግሞ›አለ የዶክተሯን ንግግር ኮምፒተሩ ላይ ኤዲት እያደረገ
‹‹አሁን ደግሞ ምን?›› አብዬት በገረሜታ ጠየቀው
‹‹አሁን ደግሞ ያው አንተ እኔና እሷ መካከል ተጋርጠሀል….››
እውነትም የቆመው መሀከላቸው ነበርና ዞር ብሎ ወደ መቀመጫው ሄዶ ተቀመጠ
‹‹አይ ጭንቅላት..አሁን ከቆምክበት ወደ መቀመጫ ሄደህ ስለተቀመጥክ ከመሀከላችን ዞር አልክ ማለት ነው፡፡››
‹‹ጥሩ ጭቅላት አለህ..ግን አብዛኛው ክፍሉ በቅዠት የተሞላ ነው…››አለወ አብዬት ኮስተር ብሎ፡፡
‹‹እና ዶክተሯ ላይ አይኔን አልጣልኩም እያልክ ነው…?››አፈጣጠው….ዶክተሯና አብዬት በእፍረት ተሸማቀው እርስ በርስ ተያዩ…..
‹‹በሉ አናንተ ቀልድ አያልቅባችሁም…ልብሴን ቀይሬ ቢጃማ ነገር ለብሼ ልምጣ…..›› ብላ ወደ መኝታ ቤቷ ስትንቀሳቀስ
‹‹ደግሞ ቢጃማው ሰውነትሽነ የሚያሳይ እንዳይሆን የሰው አይን አንደሚያሳክክ ታውቂያለሽ አይደል?››
አላት ካሱ
‹‹አውቃለሁ አታስብ›› አለችው፡፡
አብዬት ሳቀ….አሁን ሁለቱ ብቻ ቀሩ..ካሳ እና አብዬት ብቻ
አብዬት‹‹አሁንም ታፈቅራታለህ አይደል?››ሲል ጠየቀው በሀዘኔታ
‹‹አሁንም ስትል..ነፍስ ከአወቅኩበት ጊዜ አንስቶ እሷን ማፍቀር መች አቁሜ አውቅና››
‹‹እና እንዴት የተለያያችሁ ይመስለሀል…?››
‹‹እሷ ተለየቺኝ እንጂ እኔ ተለይቼያት አላውቅም››
‹‹እሺ እሷ እንዴት ተለየችህ?››
‹‹እኔ እጃ ጓደኞቼ ማፍቀር አልቻልክበትም ይሉኛል ..ለምሳሌ አንድ ጊዜ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለን የራሷ ጓደኛ መጣችና‹‹ ለምን በስርአት አታፈቅራትም ?››አለቺኝ፡፡
ፍቅርና ስርአትን ምን እንደሚያገናኛቸው ስላልተገለፀልኝ‹‹..እንዴት ?ማለት እያፈቀርኳት አይደለም ወይ ››ብዬ ተሟገትኳት
‹‹ፍቅር እንደዚህ አይደለም..ትቀጥራታለህ ..አይን አይኗን አይተህ ትሸኛታለህ..የእውነት የምታፈቅራት ከሆነ ይህ በቂ አይደለም›› አለችኝ
‹‹እሺ ምን ማድረግ እንዳብኝ ወይ አሳይኝ ወይ ንገሪኝ አልኳት..››
" ብቻችሁን ስትሆኑ እቀፍትና ከንፈሯን ሳማት ..አልፎ አልፎ ማታ ይዘሀት ውጣና አዝናናት አልጋ ያዙና ይዘሀት ግባ… ወሰድና ጡቶቾን ዳብስላት...ከዛ ሁኔታውን እያየህ ትቀጥላለህ›› አለቺኝ ፡፡
"እኔ እኮ እሷን ካፌ ቀጥሬ ፊት ለፊቴ አስቀምጪ ሳወራት…..ወይም ላይብረሪ ፊት ለፊቷ ቁጭ ብዬ እንኳን ሳጠና ከንፈሬ ከከንፈሯ አይነሳም...ፊት ለፊቴ ተቀምጣ ከለበሰችው ልብስ ሳይሆን እርቃን ገላዎ ነው የሚታየኝ።የጡት ማያዣዋ አይደለም ፓንቶን እራሱ እላዬ ላይ አላስቀርም...እና ማፍቀሬ ማረጋገጫ አንቺ እንደምትይው ከሆነም በጣም ጥሩ ስራ እየሰራሁ ነው…ፊት ለፊቴ ኖረችም አልኖረችም በልቤ ውስጥ እርቃኖን ስትንገዋለል አይደል የምትውለው።በየቀኑ በውኔም በህልሜም እንደሳምኳትና እንደተዋሰብኮት ነው…..ይሄንን ማታውቅ ከሆነ ጓደኛዋ ስለሆንሺ ሂጂና ንገሪያት›› ብዬ ሸኘዋት…
‹‹ከዛ እንዴት ሆነ?››ሲል ጠየቀው ሳቁ እንዳያመልጠው ለመቆጣጠር እተሰቃየ፡፡
‹ሁለቱም ከወር በላይ አኮረፉኝ….እውነቱን ነው ተናገርኩት… ምን አጠፋው?››
‹ያለፈው አልፎል አሁን ግን እድሉ አለህ …እንዳታባክነው››
‹‹አቤት ሰው ሰውን መምከር ሲወድ….እስኪ መጀመሪያ ለራስህ እወቅ››
‹‹‹እኔ ደግሞ ምን ሆንኩ?››
‹‹አላወቅክም እንዴ…ልብህ አልነገረህም…አፍቅረሀታል እኮ…….እኔ እንደውም የዚህን ታሪክ መጨረሻ ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት ላይ ነኝ…አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ አንተ ይዘሀት ሄደህ በሌላ ሰው ተነጥቄ አጣትለው ወይስ የፕሮፌሰሩን በቀል ጭምር አንተን በማሸነፍ እበቀላለሁ?ልብ አንጠልጣይ ነው አይደል…?››
‹‹አንተ ምትገርም ሰው ነህ…ደግነቱ በደህና ጊዜ ያበድክ እድለኛ ሰው ነህ…››ሲል ዶክተሯ ከላይ ከደረጃው የእግር ኮቴ ተሰማና ሁለቱም አይናቸውን ወደላይ አንጋጠጡ … ሙሉ ሰማያዊ ቀለም ሱሪና ጃኬት ያለው ቢጃማ ለብሳ ከታች ነጭ ሲልፐር ጫማ ተጫማታ ወደታች እየወረደች ነው፡፡
👍361🔥1
‹‹አሁን ኤዲት አድርጌ ጨርሼያሁ ልለቀው ነው››
‹‹ልቀቀው ››
‹‹ለሰውዬሽ ሊንኩን ልላክለታ ››
‹‹አድርገው››፡


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍252
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ-11
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
////
ፕሮፌሰሩ ከመጠጥ ቤት ወጥቶ ወደቤቱ እየነዳ ሳለ በእስፖኪዬ ድንገት ወደኃላው ሲመለከት የሆነ የሚያጠራጥ ነገር ተመለከተ…..ከፊት ለፊቱ አደባባይ አለ ዞረና ወደግራ ታጠፈ….. ከኃላ ተመልክቷት የነበረችው ነጭ ቲዬታ መኪና እሱ እንዳደረገው አደረገች…..ምን እየተካሄደ ነው…..ፍጥነቱን ቀዝቀዝ ሲያደርግ መኪናዋም ቀዝቀዝ አለች…እጁን ወደእጀርባው ልኮ ጎኑ ሽጦ የነበረውን ሽጉጥ አወጣና ፊት ለፊት አስቀመጠውና ዝም ብሎ ወደፊት ነዳ….ብርሀኒ አደሬ ሞል ጋር ሲደርስ ወደቀኝ ታተፈና ወደውስጥ የሚያስጋባ ቀጭን መንገድ ውስጥ ገባ…..ከኃላ ምን ም አይታየውም..አዎ ሸወድኮቸው ማለት ነው ብሎ አስቦ ሳይቸርስ መኪናዋን አያት ወደግራ ታጠፈና ውስጥ ለውስጥ ተሱለክልኮ በቀነኒሳ ሆቴል በኩል ወጣና ዋናውን ወደቦሌ አየር ማረፊያ የሚወስደውን መንገድ ያዘ…. አሁንም እየተከተሉት ነው …ከመገናኛ ወደቃሊት የሚወስደው መንገድ ጋር ሲደርስ ወደቀኝ ታጠፈ እና ቀጥታ መንዳት ጀመረ……በዚህ መንገድ ለምን እንደመጣ አያውቅም…እርግጥ የቤቱን መስመር ይዞል ግን የተሻለ እንደዚህ ጭር ያላለ መንገድ መጠቀም ይችል ነበር..‹‹ማናቸው ከኃላ ሚከታተሉኝ….››እራሱን ጠየቀ…
ባለስልጣኖቹ እያሳደዱት እንደሆነ ገባው…ከፍራቻቸው አንፃር ወይ ምን እየሰራ እንደሆነ ሊከታተሉት ካልሆነም ሊያስገድሉት እየሞከሩ ይሆናል….ስልኩን አወጣን ደወለ…››
‹‹ሄሎ ሙሉ …››
‹‹እሺ ፕሮፌሰር እቤት ገባህ እንዴ?››
‹‹ምን ገባለሁ… የሆኑ ሰዎች እየተከታተሉኝ ነው…››
‹‹ምን ..?ምን አይነት ሰዎች….?››
‹‹አላውቅም የሆነች ነጭ ቲዮታ መኪና ነች ..ወስጧ ሁለት ሰዎች ያሉ ይመስለኛል……››
‹‹እርግጠኛ ነህ ግን?››
‹‹እርግጠኛ ሳልሆን ደውልልሀለው..ያላወቅኩት እንደዚህ የሚያደርጉት እነማን ናቸው ?ምን ለማድረው ፈልገው ነው ?የሚለው ነው፡፡››
‹‹ለምን አታናግራቸውም…?››
‹‹ሰውዬ ስካር ላይ ነህ እንዴ?ለምን ፈጥናችሁ አትገሉኝም ብዬ ነው አቁሜ ማናግራቸው…?.››
‹‹ግራ ገብቶኝ ነው እኮ ነው… ለፖሊስ ልደውል እንዴ? ››
‹‹አይ ቆይ እስኪ ትንሽ ላጣራ..ምን አልባት እንዛ ባለስልጣን ወዳጆችህ ክፉ ነገር አስበው ይሆን እንዴ..?እንሱ ከሆኑ አሁኑኑ ደውልና እንዳያደርጉት ንገራቸው…አንድ ነገር ከሆንኩ አያንዳንዱን ወንጀልና ወንጀለኝ በዝርዝር ለሚመለከተው አካል ሆነ ለሚዲያ እንዲበተን ከአምስት የበለጡ ወዳጆቼ ጋር በትኜያለሁ..…እኔን በማስወገድ ከወንጀል ነፃ መሆንን ፈፅሞ አይታሰብም..ይሄ ለሁላችሁም ይታሰራል..››
‹‹ለሁላችሁም ስትል?››
‹‹ለአንተና ለሼኪውም ጭምር››
‹‹በስመአብ በል..አሁን እኔን እንዴት ነው በእንደእዚህ አይነት ሁኔታ የምትጠራጠረኝ?››
‹‹አሁን ጊዜ የለኝም …ስማኝ እቤቴ አካባቢ እየደረሰኩ ነው ሰዎቹም ከኃላዬ አሉ..አሁኑኑ ለባለስልጣኖቹ ቢያንስ ለዋናው ደውልና አስጠንቅቅልኝ….አሁኑኑ››ስልኩን ዘጋው፡፡
ወደቤቱ በሚያስገባው ቅያስ ሲታጠፍ ቲዬታዋ ተጠፈችና ፊቷን ወደመጣችበት አዙራ ተመልሳ ወደመጣችበት በረረች፡፡
ተንፈስ አለ ..እቤቱ ደርሶ ክላክሱን ሲያስጮህ ዘበኛው ከፈተለት….ወደውስጥ ገባና መኪናዋን በቦታዋ አቆመ…..
እቤቱ በሰላም መግቱን አላመነም….የመኪናውን ሞተር አጠፋና ከመኪናው ወርዶ ወደቤቱ ገባ….በዚህ ነፋሻማ ምሽት ከጭንቅላቱ ላብ እየተንጠባጠበ ነው፡፡
‹‹አዎ ….አሁን ይኄ እንደውም ለእኔ ጥሩ ማንቂያ ነው…››.ሲል አሰበ….መኝታ ቤቱ ገባና ልብሱን አወላልቆ ቢጃማ ቀየረ… ወደሳሎን ተመለሰ….የውስኪውና ጠርሙስ ከፈተና በብርጭቆ ቀድቶ ሶፋው ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠ….
..በእጁ የያዘውን ስልክ ደወለ….ከረጅም ጥሪ ቡሃላ ተነሳ
‹‹ከእንቅልፍ እንዳልቀሰቀስኮት ተስፋ አለኝ››
‹‹አይ ዝም ብዬ እየተገላበጥኩ ነበር….እንቅልፍ አሻፈረኝ ከላኝ ቆየ..እድሜ ለዛች ተወዳጅ እጮኛህ››
‹‹ወንጀላችንን ህዝብ ጆሮ ከደረሰ ምን እንደሚውጠን በደንብ ማሰብ ጥሩ ነው፡፡አዎ በደንብ አስቡ››አላቸው እንዳበሳጪት ሊያበሳቻቸው ስለፈለገ፡፡
‹‹ፕሮፌሰር እኔ እኮ የግማሽ ህዝብ አባት ነኝ..አምስት ሚስቶች አሉኝ ፡፡ከአምስቱ ሚስቶቼ 42 ልጆችን ወልጄያለው….ከ42 ልጆቼ መካከል 35 ቱ አግብተው53 ልጆችን ወልደዋል….ከ53 የልጅ ልጆቼ መካከል 12 አገብተው 29 ልጆችን ወልደው ቅርም አያት አድርገውኛል፡፡ኢድ ወይም አረፋ ሲሆን እኔ ግቢ ብትመጣ እቤቱ ሳይሆን ግቢው እራሱ ሞልቶ ይተርፋል…ሰው ድል ያለ የሰርግ ድግስ ተደግሶ የከተማው ግማስ ህዝብ የተጠራ ነው የሚመስለው፣ግን የሚገርመው ያው ሁሉ ልጆቼ ፤የልጅ ልጆቼና ሚስቶቻቸው ናቸው…አሁን አሁን እማ ማናቸው መጥተው እንደዘየሩኝ የትኛቸው ደግሞ የራሱ ጉዳይ ብለው ወይም ትርምሱ አስጠልቷቸው በቤታቸው እንደቀሩ ሁሉ መለየት ማልችልበት ደረጃ ደርሼያለው….ታዲያ ህዝብ ህዝብ እያልክ ብታስፈራራኝ የምሰማህ ይመስልሀል…እኔ እራሴ ህዝብ ሆኜያለው እኮ..ከመንግስት ጋር ብቀያየም እራሱ እነዚህን ቤተሰቤትን አሰልፌ በቤተመንግስት መንገድ ብበትናቸው…አለም አቀፍ ጣቢያወች ሳይቀሩ ያለምንም ማቅማማት የአዲስ አበባ ኑዋሪ በነቂስ ወጥቶ በመንግስት ላይ ያለውን ቅሬታ በሰላማዊ ሰልፍ ገለፀ› ብለው እኮ ነው የሚዘግቡት…..እና ህዝብ እያልክ እኔን ለምን ታስፈራራኛለህ…?፡፡እና ቀድመው የሚቦጫጭቁኝ ልጆቼና የልጅ ልጆቼ ናቸው..የራሴ ህዝቦች፡፡››
ያወሩትን ዝባዝንኪ ወሬ ጭላ ብሎ ‹‹ሰው እንዲከታተለኝ መድበው ነበር እንዴ?››ሲል ጠየቃቸው
‹‹ምን እንዲያደርግልኝ?››
‹‹እኔ እንጃ አላውቅም?››
‹‹ከምን ተነስተህ ይሄን ጥያቄ ልጠይቀኝ ቻልክ?››
‹‹አሁን ከአቶ ሙሉ ጋር አምሽተን ወደቤት ስገባ ከቦሌ ጀምሮ የሆኑ ሰዎች ከኃላ እየተከተሉኝ እቤቴ አከባቢ ስደርስ ነው ትተውኝ ወደኃላ የተመለሱት፡፡››
‹‹እኔ አላደረኩትም..እኔ ባደርገው እንኳን በዚህ ሰዓት የማደርገው ደህንነትህን ለመጠበቅ ነው የሚሆነው….ከዚህ መአት ለመውጣት እኮ ተስፋዬ አንተ ነህ››
‹‹ግራ ገብቶኝ ነው እኮ››
‹‹ይሄን ነገር በቀላሉ ማየት የለብንም..ከነገ ጀምሮ አንድ ሁለት ጠባቂ ይዘህ መንቀሳቀስ አለብህ….ለመሆኑ አንተ ማንን ተጠራጠርክ….?ማለቴ ከእኔ በተጨማሪ››
‹‹እኔ ትልቁ ጥርጣሬዬ ባለስልጣኖቹ ላይ ነው…..እነሱ ሲበረግጉ የፈሪ ዱላ መወርወር ልማዳቸው ነው….››
‹‹ግን እንሱ ቢሆኑ እኮ ከአንተ ቀድመው ሙሉን ነበር የሚያስወግዱት..››
‹‹አሁንም ሊሆን ይችላል…ሙሉን መግቢያና መውጫውን ቀድውንም የውቁት ይሆናል…እና የማያውቁት የእኔን ስለሆነ አሁን እያጠኑ ነው…እና ሁለታችንንም በአንድ ቀን ካስወገዱ ወደእነሱ የሚወስደውን የወንጀል መስመር በጠሱት ማለት ነው..አዎ እንደውም እነሱ ናቸው፡፡
‹‹እና ለተወሰነ ቀን እራስህን ሰውረህ በስልክ ብቻ ነገሮችን ብትከታተል ምን ይመስልሀል…ያው ታውቃለህ ያ ስብሰባ የምንሰበስብበት ቤቴ አሁንም አላከራየሁትም.. ሁሉ ነገር ሙሉ ነው፡፡››
‹‹እስኪ ላስብበትና ነገ አንድ ነገር አደርጋለሁ..አሁን ልዘጋው ነው..ሙሉ እየደወለ ነው፡፡››
ስልኩን ዘጋውና እየተደወለ ያለውን አነሳው..
‹‹እሺ አገኘሀቸው፡፡››
‹‹አይ የሁሉም ስልክ አይነሳም…መልዕክት ግን ልኬላቸዋለሁ››
‹‹ጥሩ ለጊዜው እቤቴ አካባቢ ድረስ ከተከተሉኝ ብኃላ ዝም ብለው ሄደዋል…..ነገ ተነጋግረን የሆነ ነገር እናደርጋለን..እና አንተም ተጠንቀቅ….ስትንቀሳቀስ ዙሪያ ገባህን እየተመለከትን››
👍241
‹‹እሺ..ግን እኔን እንኳን ማን ይተናኮለኛል ብለህ ነው?››
‹‹አረ…እራስህን ፃድቅ ፃድቅ የምታጫውተው ነገር ነው የማይገባኝ …ባለስልጣኖቹ ከሆኑ እኮ ከእኔ ቀድመው የሚያጠፉት አንተን ነው…ቀጥታ ከእነሱ ጋር የምትገናኛቸው አንተ ነህ..ሚስጥራቸውን ከእኔ በላይ ታውቀለህ..ታዲያ እኔን ብቻ ስላጠፉ የሰላም እንቅልፍ የሚተኙ ይመስልሀል?››
‹‹እና ታዲያ ምን እናድርግ?››
‹‹ለጊዜው ስልካቸው እንደሰራና ይደወሉልህ ይሆናል… ያልኩህን ንገራቸው…ከዛ ምን ማድረግ እንዳለብን እዳልኩህ ነገ እንወስናለን፡፡››
ዘጋው፡፡ ከጠረጵዛው ላይ ብርጭቆውን አነሳና አንዴ በደንብ አድርጎ ተጎነጨለትና መልሶ አስቀመጠው››ስልኩን አነሳና ፌስቡክ ከፈተ …..
ያው ፌስብክ ከገባ በመጀመሪያ ቼክ የሚደርገው ‹የተሰባበሩ ነፍሶች› የሚለውን ገፅ ከሆነ ከራርሟል…ሰርች ላይ ገብቶ ሊፈልገው ሲል ሚሴጅ ቦክስ ውስጥ መልእክት እንዳለው አየ..ከፍቶ ሲገባ እንደበቀደምለታው ሊንክ ተቀምጦለታል፡፡፣..በርግጎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ… ተመልሶ ተቀመጠ…ሊንኩን ከፈተው …ቀጥታ ወደ ገፅ መራው..፡፡ገፅ 10 ሺ በላይ ተከታታዬች አፍርቷል…፡፡.ከ15 ደቂቃ በፊት የተለቀቀ ቪዲዬ አለ…..ቶሎ ብሎ ከፈተው….በቀደም ለታ ከለበሰችው አለባበስ የተለየ አለባሰበስ ለብሳ አምሮባታል….፡፡.‹‹በቅርብ መሞትሽ ላይቀር እንዲህ መሽቀርቀር ምን ሊረባሽ አለ?፡፡››ሲል አጉረመረመ፡፡
ማድመጥ ጀመረ…..እንደፈዘዘ ጨረሰው፡፡
ወደኮመንቶቹ ሲልክ ከዋናው መልዕክት በላይ አስፈሪ የሆኑ መረጃዎች እየተለቀቁ ነው
በኮመንት ከተፃፉጽ መካከል ፅቂጾቹ
……የሆኑ ደላሎች ኩላሊትህን በ500 ሺ ብር እንሽጥልህ በለውኝ ነበር…ከዚህ ጉዳይ ጋር ይያያዝ ይሆን እንዴ;
……ለምን በአንዴ ፍርጥርጥ አታደርጊውም….በቁርጠት ልንሞት እኮ ነው››
…ጤነኛ ወንድሜ በትንሽ ህመም እዛ ሆስፒታል ገብቶ ሞቶብኛል..እስከዛሬ ለምን እያልኩ በጥያቄ ስሰቃይ ነበር…ከአንቺ መልስ አገኛለሁ ብዬ ጠብቃለሁ››
……ከጎንሽ ነን….ፖሊሶች ስራችሁን ስሩ
……የሄ ከርሳምና ሙሰኛ መንግስት ነው እንደዚህ አይነት ሆዳሞችን በጉያው አቅፎ ሚጫወትብን…በርቺ
…….ጀግናችን ነሽ…..ፍትህ ነፃ ታወጣለች፡፡
እያለ ይቀጥላል ፡፡ ስልኩን ዘግቶ ኪሱ ውስጥ ከተተና መጠጡን እየተጋተ ቤቱ ውስጥ ከክፍል ከፍል መንጎራደድ ጀመረ…
‹‹.ነገሮች ከእጄ እየሾለኩ ነው››አለ….
‹‹ግን እንደዚህ አይነት ውስብስብ ጭንቅላ ያላት ሰው ነበረች እንዴ ?ሲል ጠየቀና
..‹‹አይ ይሄ ሁሉ እቅድና አሰራር የእሷ ሊሆን አይችልም… እያግዛት ያለው ሰው ነው እየተጫወተብኝ ያለው ..እውነትም የተለየ ወንጀል ነክ እውቀት ያለው ሰው ነው››ሲል አመነ….
ተፋላሚዎቹ ባላሰበው እና ባልተዘጋጀበት የጦር ሜዳ ነው እየገጠሙት ያለው….በፍጥነት አግኝቶ እዛው ባለቸብት ጉድጎድ ውስጥ እስከነግብራበሯ አፍኖ ካላስወገዳት በቀናት ውስጥ እንደሚያበቃለት እርግጠኛ ሆነ፡፡
አሁን ጊዜ ሳያጠፋ እራሱን መሰወር እንዳለበት ወሰነ…..‹‹ምርጫ የለኝም›› አለ..ለጊዜው እሱን ስም በድፍኑ ነው የጠቀሰችው…እንደፎከረችው ከሶስት ቀን ቡኃላ ደግሞ ምን እንደምታደርግ አሁን መገመት አይቻልም…ከአሁን ቡኃላ መንገዱን ከፍታለች..እሷምንም ባትል እራሱ ቁርጥራጭ መራጃ የሚያውቁ ሁሉ ያሚያውቁትን ይፋ ሲያደርጉ ህዝቡ እና የሚመለከተው አካል እንዛን ገጣጥሞ አንድ ምስል ይይዛል…..
ወደመኝታ ቤቱ ሄደና መቀየሪያ ልብሶችን ጌጣጌቶችና ብሮችን …ጠቃሚ ሰነዶችን በመካከለኛ ሻንጣ እያጣጠፈና እየስታካከል መክተት ጀመረ….ጨጨርአልጋው ላይ ተቀመጠና ከሞባዩሉ ሰዓቱን አየ 5፤40 ሆኖል….መፍጠን አለብኝ ››ሲል ወሰነ ..ስልኩን አወጠናና ደወለ…..ዶዬ ጋር››
‹‹ሄሎ ሀለቃ››
‹‹ገብተህ እንዳልተኛህ እርግጠኛ ነኝ…››
‹‹አረ ልጆቹ ጋር ነኝ››
‹‹የተቀየረ ነገር አለ…ልጅቷ ሌላ መረጃ ለቃለች….››
‹‹አዎ አሁን እሱን እያየሁ ነበር››
‹‹ስለዚህ አፈናውን አሁን ማድረግ አለብን››
‹‹አሁን ማለት?››
‹‹ዛሩውን …ከመንጋቱ በፊት ››
‹‹እናቷን ብቻ መነጠሉ ይከብዳል››ዶዬ ስጋቱን ተናገረ፡፡
‹‹ምን አጨናነቀህ ..እቤት ውስጥ ያሉትን ሁሉ አግቷቸው.. ሶስት አይደሉ..?››
‹‹አዎ ሶስት ናቸው ..ማለቴ ሁለት አዋቂ ሴትና አንድ ህፃን ልጅ››
‹‹በቃ አድርጉት››
‹‹እሺ..እናደርገዋለን››
‹‹ዶዬ አሁን ገንዘብ ለማግኘት ብቻ አይደለም…እራሳችሁንም ለማትረፍ ጭምር እያሰባችሁ ስሩ…እያንዳንዱ ወንጀል በተጋለጠ ቁጥር ከጀርባው በአስፈፃሚነት የእናንተ እጅ እንዳለበት ግልፅ ነው…እና እኛን ለማትረፍ ብቻ ሳይሆን እራሳችሁንም ለማትረፍ ስሩ፡፡››


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍315
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ

መጀመሪያ የደራረቀ እንጨትና ግንድ ቀጥላ ለጉልቻ የሚሆን ሦስት ድንጋይ አቅርባ እሳት አቀጣጠለችና ውሃ የያዘውን
ቶፋ ወደ አንደ በኩል ዘንበል አድርጋ ጣደችው ከዚያ በለሻ እንዲበላ ስታቀብለው “አንችስ ብይ እንጂ ተወተቱም ጠጭ…"
አላት ጭብጦውን እያላመጠ።

ይእ! ይልቅ አታስቀምጠው ጠጣው። የኔ በኋላ ይደርሳል“ ብላ በጨንዋዛ ቅጠል የተቋጠረውን ሽፈሮ ቡና ፈታ በሚቆለቆሰው
እሳት በመቅጃው የቅል ጭልፋ ዙሪያ ትጉልጉል የሚለውን እንፋሉት እንዳያቃጥላት ተጠንቅቃ የቡና ገለባውን ጨመረች:

ሰማዩ ላይ እንደ ጨሌና ዛጎል ከዋክብት ሆጨጭ ብለዋል። በስተ ሰሜን በኩል ደግሞ ብናኝ ዳመና አቅፎ የያቸው ከዋክብት
ብልጭ ድርግም... ይላሉ: የምሽት በራሪዎች የሌሊት ወፍ ጉጉት የማታ ተረኞች ሆነው ወዲህ ወዲያ ይበራሉ: ጅብ ይጮሃል
አንበሳው ያገሳል... ጦጣና ዝንጀሮ ፀጥ ብለዋል: ጉሬዛዎች ግን እንደ ዶሮ ሰዓት እየጠበቁ “ጉርር ጉርር. ጉርርርር..." እየተቀባበሉ ያውካኩና ጸጥ እረጭ ይላሉ።

ዳራና ደልቲ በሚነደው የሳት ወላፈን እሷ አንድ ጉልበቷን
አጥፋ መሬት ላይ አጋድማ፧ ሌላውን ጉልበቷን አጥፋ አቁማ አልፎ አልፎ እንጨቱን ቆስቆስ እያደረገች አይኖችዋን ጨለማው ውስጥ ተክላለች።

ደልቲ በርኮታው ላይ ቁጭ ብሎ የአባቱን ከዋክብት እንደ እሳት እየተንቦገቦጉ ቁልቁል ተወርውረው የሚጠፉትን “ሚቲዎሮች”
እያየ ያስባል።

በሁለቱ መካከል ንግግር የለም:: ፀጥታ ሆኗል: በሐመር ባህል የቡና ሥነሥርዓት እርጋታና ፀጥታ የሰፈነበት ነው:: ህፃናት
እንኳን ይህን ስለሚያውቁ  ቡረቃቸውን ገተው ያደፍጣሉ። ሴቷ ወንዱ ሽማግሌው ከራሳቸው
ጋር የሚነጋገሩበት ራሳቸውን የሚመዝኑበት አደብ የሚገዙበት በጎና እኩይ ተግባራቸውን የሚፈትሹበት... ነው የቡና ሥነ ሥርዓት ለሐመሮችሽማግሌ
ትናንትን የሚያደንቅበት ዛሬን የሚያመሰግንበት ነገን በተስፋ የሚጠባበቅበት ግለሰቡ ለማህበረሰቡ ደህንነት ሰላምን፡ ጥጋብን የሚመኝበት የአባት የአያት ደንብ ወደ ልጅ የሚሸጋገርበት ጠላትና ወዳጅ ጠንቅቆ የሚታወቅበት ምላስ አጥራ ህሊና ገዝፎ መግባባት የሚመጣበት ነው የቡና ሥነ ሥርዓት። ይህ የቡና ሥነሥርዓት ለህፃን ለወጣት ለአዋቂ ለሽማግሌ ለእንግዳ ክፍት ነው። ያሻው ሁሉ ይሳተፋል እድሜና ደረጃውን ጠብቆ ይዳረሳል። የሐመር በር መዝጊያ የለውም። የሐመር ሕይወት ጓዳ የለውም፡ የሐመር ማህበረሰብ “ከሌላው ኪስ ወስደህ የኔን ኪስ ሙላ በሚል ስግብግብነት ምኞት ላይ አልተመሰረተም።

ደስታ ችግር ጦርነት... የጋራ ነው: የአንዱ ምርኩዝ ሌላው ነው: ግለሰብ ህብረተሰብን አይረሳም። ህብረተሰቡም ግለሰቡን
አይጥልም ያሳድገዋል ሃብት ያካፍለዋል ይድረዋል ለጀግንነቱም
ያሞግሰዋል...

ስሰዚህ ደልቲና ዳራ ምንም እንኳ ጫካ መሃል ብቻቸውን ቢሆኑም ህሊናቸውና አካላቸው ግን በባህላቸው ደንብና ሥርዓት
የተገነባ ነው: ፀጥታው ተጠብቆ ዝምታው ሰፍኖ እሱም ሆነ እሷ ትናንትን ቃኝተው ዛሬን አስታውሰው ነገን ሲያልሙ በሐሳብ
ተውጠው ቆዩ።

ከዚያ ዳራ ሾርቃውን ጠረግ ጠረግ አረገችና የቅል ማንኪያውን አንስታ ቶፋው ውስጥ ጨምራ ከቡናው ሁለቴ ቀድታ ሰጠችው ደልቲ ቡናውን ለማብረድ ግራና ቀኝ ጎለል አደረገና ፉት ብሎ “ፕስስ ፕስስ.." እያለ ወደ ምስራቅ ምዕራብና ወደ መሬት የሸፈሮ ቡናውን አርከፍክፎ- “የአባቴ ሰማይ ዝናብ ይጣል በሽታዎች ከሐመር ምድር ይጥፉ፤ ከብቶች  ፍየሎች በጎች
አያገሱ  በሰላም ይግቡ ይውጡ..." ብሎ መረቀና ወደ  ዳራ ዞሮ ቡናውን ፉት ብሎ “ፕስስ..” አለና ሽፈሮ ቡናውን አርከፈከፈባት፡

ዳራ ደንገጥም አፈርም ሳትል አይኗን ከወረወረችበት
ሳትመልስ በሃሣብ እንደሰመጠች
“..ተባረኪ... ዘርሽን ያብዛው የአባትሽ የሐመር ምድር የልጆችሽ መቦረቂያ ይሁን... የባልሽ ጥገት ይብዛ" ብሎ መረቃትና ቡናውን በፀጥታ መጠጣት ጀመረ።

ሰረቅ አድርጋ አየችው: በውስጧ እንደ ህፃን የሚላወሰው እሱ ነው ከፊት ለፊቷም የተቀመጠው እሱ ነው፡ ፍቅር የሰጣት የመረቃት እሱ ነው። ስለሱ ያላትን ስሜት አሁንም በእርግጠኝነት አጤነች ስለ ጀግናው የሚባለውንም አስታወሰች።

ጥጃና ፍየል ስትጠብቅ ወንዶች የድሜ ጓደኞችዋ እነሱ ጠመንጃ እያሉ እንጨት ቆርጠው እየተሸከሙ እንደ ጥይት ዳውላ እየወረወሩ ይሄ ከብት የኔ ያ እርሻ የኔ... እየተባባሉ ሲጫወቱ። እሷም የእድሜ እኩዮችዋ ከሆኑት ልጃገረዶች ጋር ከከስኬ ወንዝ
የጭሮሽ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየለቀሙ, ልጅ እያቀፉ... ሲጫወቱ
ይቆዩና ጫካው መሃል ሚስትና ባል ሲባባሉ ቆይተው ዘፈን ሲጀምሩ
ስለ ሐመር ተራራ ስለ  ሐመር ሰማይና ምድር... ስለከብቶች ሲያዜሙ ይቆዩና የሐመር ጀግኖችን ህፃናቱ ሲያወድሱ የደልቲ ስም የደልቲ ጀግንነት... ይነሳል። ወንዶች ህፃናት “እኔ ነኝ እሱ እኔ ነኝ
ሲባባሉ እሷም ከሌሎች የእድሜ ጓደኞችዋ ጋር “ደልቲን የሆነውን ወንድ እኔ ነኝ የማገባው ! እኔ ነኝ የማገባው" ሲባባሉ አንዳንዴ ሁለት አንዳንዴ ሦስት እየሆኑ ሲያገቡት የነበረው የልጅነት ዘመኗ
ታወሳት። እንዲህ ዳሌዋ ሰፍቶ ጡቶችዋ አጎጥጉጠው ሰውነቷ
አምሮ ባለበት የቡረቃ ዘመኗ ያ ስም አብሯት አደገ:: የዚያ ጀግና መግነጢሳዊ የፍቅር ሃይል በውስጧ እየተገለባበጠ  ሲያስጨንቃት ኖረ።

ገበያ ስታየው ትንፋሽዋ ቁርጥ ያለባት ሲመስላት  ስሙ ሲነሳ እንደ አውሬ  ስትደነብር  ፍትወት ሲያስቸግራት ከልቧ
አውጥታ ጉያዋ ውስጥ በሰመመን ስታስገባው፤ በፍቅሩ ወዲያ ወዲህ
ስትንገላታ ኖረች: ነገ ነገን ሲተካ የሷ አምሮትም ከቀን ወደ ቀን ሲጨምር ከስኬ ወንዝ አሸዋ ጭራ ጭሮሽ ውሃ ስትቀዳ ያ በውስጧ
አብሯት ያደገው ጀግና ድንገት ሽቅብ ወደ ቡስካ ተራራ ሲወጣ አየችው ደነገጠች! ግራ ገባት: “አያ ደልቲ! እሱ ኮ ነው…..የኔው.." ብላ ቀባጠረች። ጓደኞችዋ ሳቁባት አላየቻቸውም።
አልሰማቻቸውም እሱም የለም: ጫካው ሰወረው። እሷ ግን ታየዋለች።አካሉ ቢሄድ እሱ ልቧ አለ፡ አወጣችው አየችው ወደደችው! አቀፈችው...

ይእ!  እሰይ እሱንም ከውስጤ ያለውንም አየሁት..." ቀና ብላ ፀሐይን ሰማዩን... ቦርጆን አመሰገነች።

“እይ! እሽ ምን ልሁን! እሽ ምን ላርገው.." ጓደኞቿ እንደገና ሳቁባት። ጆሮዋ ግን አይሰማም አይኗ አያይም... ሁሉም ጀግናዋን ሊዳብሱ ሄደዋል። ውስጧ ያለው የፍቅር ሃይል ለፍንዳታ ተዘጋጀ ተቀባበለ። ሃይሉ ናጣት ወዘወዛት, አሻት... አዞራት አሽከረከራት... ዛፍ ጥላ ስር በደመ ነፍስ ሄዳ አረፈች መረጋጋት ስትጀምር ቡስካ ተራራን ቀና ብላ አየችው: ነይ" አላት። ወሰነች
ለመሄድ ጀግናዋን ጫካ መሃል ለመፈለግ  ቆረጠች። ሄደች “አቅጣጫ ያላት ጀልባ ንፋሱም ይረዳታል ይባል የለ አገኘችው::

ደልቲ ዳራ የቀዳችለትን ሸፈሮ ቡና አራት ጊዜ እየተቀበለ ጠጣና  ሾርቃውን ከፊት ለፊቱ አስቀመጠው: በሐመር ደንብ የጠጡበትን እቃ ማቀበል ጨምሩልኝ ሲሆን ማስቀመጥ ግን በቃኝ ማለት ነው:: ዳራ ለራሷ መጠጣት ጀመረች። በሐመር ባሀል ወንድ በሐመር ባሀል ወንድ
አንበሳ ነው ሴቷ አንበሳ መጀመሪያ ግዳይ ትጥላለች: ወንዱ ጎፈር
አንበሳ ግን ቀድሞ ይባርካል ይበላል፤ ይጠግባል፤ ተንጎማሉ ሄዶ
ለመከታነቱ ተዘጋጅቶ ይጋደማል። ሴቷ አንበሳና ደባሎችዋ የጎፈር
አንበሳው ግሣት ደህንነታቸው ህልውናቸው ነው... እሱ ሲጠግብ
እሱ ሲጠነክር ይረካሉ። ዳራም አንበሳዋ ከጠገበ በኋላ ጭብጦዋን በላች ቡናዋን ጠጣች ከዚያ እቃውን ሸካከፈች።
👍37👎1
ደልቲ መሳሪያውን ይዞ ጫካ ገባ፡ ዳራ ግን እርጥብ ቅጠል ቆራርጣ ማማው ላይ አነጣጠፈችና ጨረቃን ቀና ብላ አየቻት:
“አለሁ! ደስ ይበልሽ! ፍቅርሽን ስጭው፤ እርካታሽን ሳትሰንፊ
አጣጥሚው። እሱን አይደል የጠየቅሽኝ! እሱ አይደል በውስጥሽ ሲዋኝ የኖረው! ጊዜ አትጠብቂ! እኔ እያለሁ ተዳሩ እኔ እያለሁ ጨፍሩ! ከሄድኩ በኋላ እስክመለስ ሰዓቱ ብዙ ነው። ለምን ናፍቆት ይጥበስሽ  ስለዚህ እሳትሽን አታዳፍኚው። ብቻሽን አትቃጠይ፡
አካፍይው ስጭው፤ የሱንም ውሰጅ ያኔ ጥሩ እንቅልፍ ይወስድሻል"ያለቻት መሰላት ጨረቃ።
ወዲያው ከማማው ወርዳ ጡርንባዋን እየነፋች ዳሌዋን እያወዛወዘች ሄድ መለስ ስትል ቆየችና፡-

“ጨረቃ መስክሪ ብትሆኝም ብቸኛ
አይደለም ምኞቴ ለመዋል ከጀግና፡
እናንት ከዋክብትስ ምነው ማኩረፋችሁ!
ደስታዬ ደስታችሁ እንዳይሆን ጠላችሁ

ከዋክብት ቦግ ብልጭ ቦግ ብልጭ ሲሉ። እነሱም አይዞሽ!! ሲሏት አየቻቸው።

እንግዲያማ  እንግዲያማ!
በሏ!  ዘምሩልን የፍቅር ዝማሬ
ጨፍሩ እንጨፍር፧ ደስ ይበለን ዛሬ:
ጀግናው ሲንጎማለል እንደ ኮርማ በሬ...”

ዳራ ጡሩንባዋን እየነፋች እየዘፈነች እየፎከረች ሳለ ደልቲ ከጫካው ብቅ አለ ዳራ ትዘፍናለች ጥሩንባው ይጮሃል: ወኔው
ተናነቀው። ጭፈራም አማረው: ለግላጋነቷ ቁመናዋ ሳበው ለሱ
ያላትን አክብሮት ወደደው: ስለዚህ የጀግንነቱን ውሉ አስታወሰው፡

ጡሩንባዋን እየነፋች ወደ እሱ አቅጣጫ መጣችና በግራና ቀኝ እጆችዋ የደረደረችውን አንባር እያፋጨች ከፊት ለፊቱ ስትደንስ እጆቹን እንደ መፎከሪያ በሬው ዘርግ ቀንድ አቁሞ ወዲያ ወዲህ
እየተንቀሳቀሰ ዘፈኑን ያቀልጠው ጀመር።

"...ተናገር ሰማዩ ተናገሪ መሬቱ ምን እንደ ተሰራ

ይናገር ተራራው ይመስክር ደን ጫካው የዋልሁበት  ሥፍራ

ባልዳምሜ ላሎምቤ ጋልታምቤ...

ጓደኞቼ ሁሉ እስኪ ተናገሩ

የባንኪሞሮ ህግ ተሽሯል ወይ ቃሉ!

ጠላቴን አልጣልሁም
አንበሳ ቀጭኔ... ተኩሼ አልገደልሁም::

ተናገር ዘርማያ የአባቴ ስጦታ

ስደክም እየኸኝ ወይስ ስበረታ

አእዋፍም መስክሩ የትናንቱን በሉ

የአባቴ ደንብ ሥርዓት ተሽሯል ወይ ቃሉ…

ብሎ ሸለለና እጆቹን ቀስሮ ሲያገሳ ዳራ እየተቅበጠበጠች ዳሌዋን
በዳንስ እያሾረች
አንባሮችዋን እያፋጨች ሳለች ደልቲ አየሩን ሽቅብ
ቀዝፎ መሬቷን እየደለቀ ተመልሶ ሽቅብ እየተምዘገዘገ. እያኮበኮበ
ወደ ዳራ ተጠግቶ ከወገቡ ተሰብቆ ወደ ኋላ የተለጠጠውን የዳራን
ወገብ በእጆቹ ደገፍ አድርጎ ዳሌዋን ከዳሌው አላተመና እራሱን እንደሚዋጋ በሬ ወደፊት ንጦ ወደ ቦታው ተመለሰ እንደጣውላ በሚጮኸው እጁ እያጨበጨበ ሲያዜም ዳራ ድንገት ሽር ብላ መጥታ አንባሯን እያፋጨች ወደ ዳንሱ በእግሯ ጠቆም
አድርጋ ጋበዘችው።

ደልቲ አየሩን እየቀዘፈ በአየር ላይ ሰውነቱን ግራና ቀኝ እንደ አቦ ሸማኔ እያዟረ ተጠጋትና እሱ አባራሪ እሷ አቅጣጫ ቀያሪ እየሆኑ ሾሩ:

በሐመሮች ጨረቃ የጨለማ ፋኑስ ናት: በሚያምረው
የብርሃን ቀለሟ ውበትን ታፈካለች፤ ታስውባለች። ብርሃኗ አያቃጥልም: ውስጣዊ ሙቀት ግን ይሰጣል: ወንዶች ወገብ ለወገብ ተያይዘው ሲንቀሳቀሱ ሴቶች ተቃቅፈው ሲሰግሩ ጨረቃ
የልባቸውን ከበሮ እየደለቀች ታዝናናቸዋለች የወንድ ቁመናና ደረት የሴት ልጅ ጭንና ወገብ በጨረቃ ብርሃን ውስጥ ሲታይ
ፍቅርን የሚጭር ልዩ ምትሃታዊ ሃይል አለው ለስላሳዋ ጨረቃ ፍቅርን  ለማጀብ የተፈጠረች ናት ምቾት ስትፈጥር  ደስታን
ስታጎናፅፍ ከለላ ስትሰጥ የፍቅር ፍትፍቷን ሳታዳላ ስታጎርስ…..ወደር የላትም
ያም ሆኖ ግን ጨረቃ ሚስጥር ናት! ጨረቃ ሩቅ ናት…..ካላይዋት አታይም! ካልቀረቧት አትቀርብም ሳይጠሯት አትመጣም፡ ህፃናት “ጨረቃ ድምቡለቃ..." እያሉ በማዜም ሲያወድሷት
እየቦረቁ እስኪጨፍሩ ድረስ
በሚረዱት ቋንቋ እያንሾካሾከች ታስፈነጥዛቸዋሰች

ጨረቃ ለሐመር ኮረዶችና ጎረምሶች ደግሞ ልይ መስብ አላት በምሽቱ ዳንስ ሲውረገረጉ ብልት ከብልት ሲተሻሽ ሳንጃ
ከሰገባው ሲፋጭ ... የፍቅር ቅኔ ሲዘረፍ አካል በወሲብ ሲነድ የተፈጥሮ መኝታ ቤቱ ጫካው ሥራ ሲበዛበት እያየች ጨረቃ
አታሳብቅም! አታሾፍም ... ደስታዋ ለፍቅር ብርሃን መስጠትና ፍቅረኞችን በስርቅርቅ ድምጿ እያዜመች ነፍሳቸውን በደስታ ሙላት
ማጥለቅለቅ ነው።

እና! ጨረቃ የተፈጥሮ ኪነጥበባዊ ሃይል የታደላት ከያኒ ነች ስነ ግጥሟ ስእላዊ መግለጫ  ልብ
ልብ ሰላቢ ዜማዋ
ኵርሽምሽም እያደረጉ የሚበሉት ጥዑም ነው። ሁሉንም እንደ እድሜው እንደፍላጎቱ በተስፋና ትዝታ ዓለም ይዛው ትነጉዳለች።
በፈለገው አቅጣጫ። እሷ መኪና ናት ሾፌሩ ግን ወዷት የተጠጋው ሰው ነው:: አታስገድድም አትመራም... የእሷ ተግባር እርካታ
መስጠት  ማስደሰት ነው::

የሐመር ምሽት ዳንስ የጨረቃ ህይወት የጨረቃ ደስታ የጨረቃ ፍቅር የታጨቀበት የህይወት ማህደር ነው። እንደ ደልቲና
ዳራ ሁለት ሆኖ ለመጨፈር ልዩ ችሎታና ልምድ ያስፈልጋል ደልቲ ግን እንኳንስ ሌላ ሰው ተጨምሮለት ይቅርና እሱ ብቻውን አየሩን እንደ አሞራ እየቀዘፈ ምድሯን እየደለቀ ሲጨፍር ብዙ ሰው እንዳለ ሁሉ ይደምቅለታል። ዳራ ስትጋብዘው እሱ እየዘለለ
ሶምሶማ እየረገጠ በተለያየ ስልት ሲደንሱ ቆዩና የመጨረሻውና ለስሜት እርካታ ወሳኝ ወደሆነው የዳንስ ምት ተቃረበ

እንኳን ሰውን አራዊትንና እፅዋትን በቆሙበት በስሜት የሚያሰግረው ካለ ንፋስ ጎንበስ ቀና የሚያስደርገው! ያ ልብን ሰላቢ ጭፈራ ወቅቱ ደረሰ፡ ጦጣዎች ዝንጆሮዎች ጉሬዛዎች...ጉጉቶች
ዙሪያውን ተሰባሰቡ። የፍቅር ደመራው ሲለኮስ ስሜታዊ ግለት ተፋጭቶ ውስጣዊ እሳት ሲንቦገቦግ… ብርሃኑን ለማየት ሙቀቱን ለመጋራት ሁሉም አቆበቆበ።
...
ዳራ ፈገግ ብላ አንባሯን  ከርከር  ከርከር ስታደርግ
'ድድም. ድድም. ድድም' የሚለውን ስሜት ኮርኳሪ የመኸር ዘፈን ደልቲ ያንቆረቁረው ጀመር።

ከብቶች እያገሱ ንቦች እየዘመሩ ንፋሱ እየነፈሰ ቅጠሎች እያሸበሸቡ... ሲያጅቡት በአይነ ህሊናው እየታየው የቅላፄውን ቃና
እየጣፈጠ ሲዘፍን የዳራ ቀጭን ወገብ ደግሞ ከዳሌዋ ለመውጣት
ግራና ቀኝ ተሽከረከረ፤ ዳሌዋም ወገቧን ላለመልቀቅ በተቃራኒው
እየዞረ እንደቆዬ የእግር ጣቷ መሬቱን ሳይለቅ ከተረከዟ ከፍ ዝቅ በማለት ዘለል ዘለል ስትል አጥብቆ የያዛት የፍየል ቆዳዋ ግራ ቀኝ
ተወናወነ: ያጎጠጎጡ ጡቶችዋን ከታች በኩል በሁለት እጆችዋ ደገፍ አድርጋ ደልቲ ላይ ደግና አሰሌ አፈር ቅቤ እጣን ተቀብቶ ሹሩባ የተሰራው ፀጉሯ ማጅራቷ ላይ መለስ ቀና እያለ ዘፈኑን ከአቀንቃኙ እየተቀበለች ስታዜም ቆየች።

ደልቲ ወደ እሱ የተነጣጠረውን ጡት
የሚያረግደውን ዳሌ በመጎምዠት እያዬ ስሜቱ እያጨበጨበ መላ
አካሉ እያዜመ ጠበቃት።

ድድም. ድድም.. ጭፈራው ደመቀ።

ዳራ ዘለል ዘለል ዳሌዋን ደግሞ ነቅነቅ እያደረገች አንባሯን እያፋጨች ስሜቷ ሲያይል መቆየት ሲሳናት ወደ ደልቲ ገሰገሰች።ደልቲ ያች ሰዓት እንደደረሰች ተረዳ  አዎ ሰዓቷ በእርግጥም ደርሳ ነበር።

ዳራ በእግሯ ጠቆም አድርጋ ስትጋብዘው ለበረራ እያኮበኮ ሽቅብ ሽቅብ እየተምዘገገ ኩንቢውን እንዳሾለ... ቀረበና ግራ እጁን ትከሻዋ ላይ ባልጩት እግሩ ደግሞ እንያ በዳንስ ስፖርት ቀጥ መብለው በተስተካከሉትና በሚያማምሩት እግሮችዋ መሃል አስገባ።ቀኝ እጁ ወገቧን ያዘ ሙዚቃው ድድም... ድድም ሲል አፎቱ
ከሳንጃው ትግል ገጠመ። ንዝረቱ ጨመረ። ፍትጊያው ጠና።መሳሳቡ ጨመረ ያኔ ነፋሱ የእሱን ሳዳጎራ ቁልቁል የእሷን የፍየል
ቆዳ ሽቅብ ገለበው: ወዲያው አራዊት በስሜት ተውጠው አውካኩ እዕዋት ተንሽዋሹ. ድድም ድድም. ሙዚቃው ደራ!...

💫ይቀጥላል💫
👍374😁4👎2
‹‹የተሰባበሩ ነፍሶች››
ምዕራፍ-12
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
////
ሰዓቱ ከምሽቱ 7፡23 ቢሆንም አብዬትና ዶክተር ሰጳራ እሷ መኝታ ቤት ናቸው ፡፡ከጎኑ ቁጭ ብላ በስሜት እያወራችው ነው..እሱም በስጋውም በነፍሱም እያዳመጣት ነው
‹‹…ይሄውልህ ስማኝ ፤የምረግጠው ቦታ ሁሉ እየከዳኝ ነው...ደረቅ መሬት መስሎኝ በሙሉ ክብደቴ ስጫነው ያዳልጠኝና ሰማይ ደርሼ መሬት እፈርጣለሁ።መሬት ሳርፍ የእጆቼን ቆዳ ጠጠርና አሸዋው ገሽልጦ ያቆሳስላቸዋል።ወገቤ ለሁለት ይከፈላል።ቢሆንም በወደቅኩበት እየተንከባለልኩ ማላዘን አይሆንልኝም። እንደምንም እራሴን አበርትቼ እነሳለሁ ።የጀርባዬ ህመም ጥዝጣዜው እስኪያቅለሸልሸኝ ድረስ ቢያመኝም ከአቋቋሜ ሽብርክ አልልም ..ፊቴንም አልቋጥርም....ወደፊትም ከመራመድ አልሰንፍም።የራሴን ህመም ለራሴው በሚስጥር ይዘዋለሁ።እኔ እንዲህ ነኝ።ውስጤ እየተሠባበረ ውጬ ፈክቶ ከሩቅ ብርሀን የሚረጭ...የህይወቴን ስንጥቅ ነፍስ አባቴ እንኳን እንዲያዩት የማልፈቅድ ከሸክላ የተሠራሁ አልማዝ ቅብ ጉራማይሌ ሰው፤የተሰባበረ ነፍሴን ከተበታተነበት እየሰበሰብኩ በአኩፋዳ በመሸከፋ መንገዴን የምቀጥል ብርቱ መሳይ ተሰባሪ ..አዎ እኔ እንደዛ ነኝ።
ንግግሯ ልቡ ድረስ ዘልቆ ተሰምቶታል..ምን ብሎ እንደሚያፅናናት ግራ ገባው..ቢሆንም ለስለስ ባለ አንደበት የመጣለትን መናገር ጀመረ"ብቻሽን አይደለሽም… በዚህ ዘመን ያልተሰባበረ ነፍስ ያለው ሰው ማግኘት ቀላል ይመስልሻል?ልዩነቱ አንቺ በጊዜ ነቅተሸ ወደውስጥሽ ተመልክተሽ የነፍስሽን መሰባበር ማየት መቻልሽ ነው።ስለተሰባበረችው ነፍስሽ በጊዜ አይተሸ ማወቅሽ ደግሞ ራሰሽው እንዳልሽው ስብርባሪዎቹን ከወዳደቁበት እየሰበሰብሽ በአኩፋዳሽ እንድታጠራቅሚ እድል ፈጥሮልሻል፡፡ወደፊት ምን አልባት (ወደፊት የሚባል ቀን ካለ )ነፍስሽን ለመጠገን ምቹ የሆነ ብርሀናዊ ቀን ህይወት ታመቻችልሽ ይሆናል...አዎ የዛን ጊዜ አኩፋዳሽን መክፈትና ያጠረቀምሻቸውን የነፍስሽን ስብርባሪዎች በየባታቸው አስተካክለሽ በጥንቃቄ በመሰካካት አንድ ላይ እንደአዲስ ማጣበቅ ነው።…አየሽ ከእንደገና ለማገገም እድል አለሽ….››
ከቁዘማዋ ሳትወጣ መልስ መስጠት ጀመረች "ባጣብቀውስ? ስንጥቁ እንዴት ሊጠፋ ይችላል?››
አብዬት መለሰላት‹‹ስንጥቁማ ስንጥቅ ነው...ዘላለም ከአንቺ ጋር የሚኖር ህመምሽና ትዝታሽ ነው።ያንን ደግሞ አትጥይው ፡፡ሰው የመሆንሽ ማንቂያ፤ በህይወት ኖረሽ እየተነፈሰሽ መሆኑን ማስገንዘቢያ አላርትሽ ነው።››
‹‹ምን አለ አንተ ልብ ውስጥ ያለው አንፀባራቂ ተስፋ ወደእኔም ልብ ሰንጥቆ ቢገባና ለጨለማው እኔነቴ ብርሀን ቢረጭልኝ…››ብላ ደረቱ ላይ ደገፍ አለች..እሱም ቀኝ እጁን በተከሻዋ አዙሮ አቀፋት ፡፡
በዚህ ቅፅበት ነበር የመኝታ ቤቱ በራፍ የተበረገደው..ሁለቱም ደነገጡና ከተጣበቁበት ተላቀቁ..ካሳ ነው ፡፡ካምፒተሩን በእጆቹ እንዳንከረፈፈ በራፍ ላይ ቆሞ እያለከለከ ነው..
‹‹ምን ተፈጠረ?››ዶክተሯ ጠየቀችው
‹‹እናንተ እዚህ ፍቅር ፍቅር ትጫወታላችሁ ነገሮች ተመሰቃቅለዋል;;››
‹‹ምንድነው የምታወራው?››አለው አብዬት
አንተማ ምን ቸገረህ..ደረትህ ላይ አስተኝተህ አስለቅሳት….አንቺ ግን መቼ ነው ትክክለኛ ምርጫ የምትመርጪው ?አሁን ይሄ ደረት የሚታኛበት ሆኖ ነው….?ሌላው ይቅር እንዲህ እንደሰነፍ ገበሬ መሬት ዝግዛግ የታረሰው ፊቱ አያስፈራሽም?›
‹‹አሁን ስለእሱ ፊት ልታወራነው የመጣሀው ወይስ ሌላ የምትነግረኝ ነገር አለ;?››
‹‹አይ በመምጣቴ ከእሱ በላይ አንቺ የተከፋሽ መሰለኝ..በቃ ወደአቆረጣችሁት መላላስ ተመለሱ፣አለና በርግዶ የከፈተውን በራፍ ፊቱን አዙሮ በመውጣት ዘጋውንና መሄድ ጀመረ
‹በጣም እኮ ነው የሚያፈቅርሽ..ቀንቶ ነው?››አለ አብዬት በድርጌቱ ተገርሞ
‹‹ምን እሱን የሚያስቀናው ነገር ሰራን…?.ደግሞ እኔም እኮ ወደዋለው..ግን እንደምታውቀወ አሁን ስለእዛ ማሰቢያ ጊዜ ላይ …››ንግግሯን ሳትጨርስ አሁንም በራፉ ተበርግዶ ተከፈተ
‹‹አሁን ደግሞ ምንድነው?››አለችው
‹‹ልነግርሽ ያለኩትን ረስቼው ሄድኩ››
‹‹እኮ ምንድነበር..ንገረኝ››ትዕግስቷን ተፈታተነው፡፡
‹‹ያ እጮኛሽ የነበረው እኔ የምጠላው ሰውዬ መልዕክት ልኮልሻል››
‹‹ምን….?››ሁለቱም ደነገጡ
‹‹ምነው? ይህቺ ያህል ብቻ ነው እንዴ የምደነግጡት?››
‹‹ምንድነው የምትቀባጥረው?›› ከተቀመጠችበት ተነሳችና ተንደርድራ ሄዳ ላፕቶፑን ከእጁ ነጠቀችና ሊያሳያት መጣውን ነገር ማየት ጀመረች…..ዥው አለበት…..እናቷ ና እህቷና እጃቸው ወደኃላ ተጠፍሮ፤ አፋቸው በጨርቅ ታሽጎ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ ብለዋል…የእህቷ ህፃን ልጅ በፍራቻ ትናንሽ አይኖቹን እያቁለጨለጨ የታሰረች እናቱ ጉያ ውስጥ ተሸጉጧል…ሶስት ወጠምሻ ጠባቂዎች ሽጉጥና ጩቤ በእጃቸው ጨብጠው ከእናቷና ከእህቷ ግራናና ቀኝ ቆመው ይታያሉ….አጋቾቹ ጭንብል ቢለብሱም አውቀቸዋለች..እሷን ለመግደል እቤቷ ድረስ ከመጡት መካከል ናቸው፡፡፡
ዥው አለባት…እጆጆቾ ከመንቀጥቀጣቸው የተነሳ ላፕቶፑን ማያዝ አልቻለችም.. ለቀቀችው፡፡ ወደታች ሲምዘገዘግ መሬት አርፎ ከመከስከሱ በፊት አብዮት ተንደርድሮ ቀለበው…ካሳ አፋን በድንጋጤ ከፍቶ ቀረ…. ላፕቶፑ መትረፉን ሲያውቅ ከቆመበት ተንደርድሮ ሄደና ከአብዬት ላይ ነጠቀው..‹‹ላፕቶፔ ምን አደረገ..?ባገለገለሽ…?እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ..ድሮም አንቺ ከልቡ የሚያገለግልሽን ነገር እንደቀልድ ወርውረሽ መስበር ልማድሽ ነው››
አብዬት በጣም ተበሳጭቶበት‹‹ዝም በል››በማለት ከፊት ለፊቱ ገፍትሮ ገለል እንዲል አደረገና ወደእሷ ተጠግቶ ክንዶቾን በመያዝ ደገፋና ከመውደቋ በፊት አልጋዋ ላይ አስቀመጣት፡፡
ለአስር ደቂቃ በቤቱ ዝምታ ሰፈነ..አብዬት ከጎኖ ተቀምጦል….ካሳም ዝም በል እንደተባለ ኮሚፒተሩን በደረቱ እንዳቀፈ ፊት ለፊታቸው ካያለውን ወንበር በግዙፍ ሰውነቱ ሞልቶት ተቀምጦ ይተክዛል፡፡
ዋጋ ከፍዬ ለዘመናት የገነባሁትን ህይወት ምሰሶዬ ይሆናል ባልኩት ሰው ተሠረቅኩ ።እንዲህ አይነት ክደህት ልብ ያደክማል።ልብን ማድከም ብቻ አይደለም ነፍስንም ጭምር ይሰባብራል።ስጋን ብቻ ሳይሆን ነፍስንም ጭምር ባስረከብት ሰው ነፍስ ሲሰባበር ማየት ለማዘን እራሱ አይቻልም።ምን ቀረና በምን ይታዘናል?እኔንስ እሼ እንደፈለገ ያድርግ እንዴት እናቴንና እህቴን ለዛውም ከነልጆ ያግዳል…ኣናቴ መንኩሳ የመሞቻ ግዜዋን በፀሎትና በምስጋና ውስጥ ሆና የምትጠብቅ አሮጌት ነች….እህቴ ገና ህይወትን አህዱ ብላ መኖር ከጀመረች አመት አልሆናትም…እኔስ በገዛ እጄ ነወ እነሱን ለምን እዚህ ውስጥ ያስገባቸዋል››
‹‹አይዞሽ ተረጋጊ….የሚሆነውን እናደርጋለን፡፡››
‹‹በቃ አሁን ደክኛል…ልተኛ››
‹‹እሺ…ከፈለግሺኝ በማንኛውም ሰዓት ደውይልኝ››
‹‹ችግር የለም፡፡››
‹‹ለእኔ ግን ባትደውይልኝ ችግር የለውም..ስትፈልጊኝ ስለሚሰማኝ ፈጥኜ መጣለሁ››በዚህ ሁሉ ጭንቅ ውስጥ ሆና እንኳን ፈገግ አስባላት፡፡
ተያይዘው በሯን ዘግተውላት ወጡ….
አሁን መኝታዬ ላይ ተኝቼ በመነፍረቅ ምንም የማመጣው ነገር የለም ስትል አሰበች…ተነሳችና የለበሰችውን ቢጃማ አውልቃ….ጥቁር ጂንስ ሱሪ ለበሰች፡፡ ከላይ ወፈር ያለ ጥቁር ሹራብ ለበሰች ፡፡ከዛ ኮፊያ ያለው ጃኬት ደረበችበት፡፡መሳቢያዋን ከፈተችና ማስታወሻዋን አወጣችና መፃፍ ጀመረች፡፡
///
👍32
አብዬት ይሄንን ነገር ከዚህ በላይ መኝታ ቤቴ ውስጥ ዘግቼ በመቀመጥ የእናቴንና የእህቴን የግድያ መርዶ አሰስክሰማ መጠበቅ አልችልም…የእኔ ነገር ያበቃለት ነው…..፡፡ለዛ አውሬ ሄጄ እጄን እሰጣለሁ..፡፡እርግጠኛ ነኝ ደቂቃዎች ሳያባክን ያስወግደኛል….፡፡ግን ከዛ ቡኃላ ቤተሰቦቼን ምንም ስላማያደርጉለት ይለቃቸዋል የሚል ተስፋ አለኝ…እና ከአንተ አንድ ነገር እፈልጋለሁ…..የጀመርነውን ነገር ከግብ አንድታደርስ…፡፡.አዎ አነሱ መቀመቅ ገብተው የእኔ ከወንጀል ነፃ መሆን ከተረጋገጠ አና በእነሱ ወንጀል ምክንያት የጠፉ የብዙ ነፍሶች የተዳፈነ እውነት ከዋጣ.. የዛኔ እኔም አልሞቱኩም ማለት ነው..እስከዛው ድረሰ ግን ነፍሴ ወደ ሲኦልም ሆነ ወደገነት አትሄድም..ይልቅስ እዚሁ በአንተ ዙሪያ እየተንሳፈፈች እቅዳችንን ከግብ እስክታደርስ በፀሎት ታግዝሀለች….ሚሽኑ በድል በተጠናቀቀበት ቀን ደግሞ በሰላም ወደምትሄድበት አንተን አመሰግና ትሄዳለች፡፡
ደግሞ ነገሮች ከተስተካከሉ ቡኃላ ቤተሰቦቼነ አደራ ተንከባከብልኝ…ካሳንም እንደወንድምህ እየው…በነገራችን ላይ በህይወቴ ካሳን ባንተ መጠን የተረዳው ሰው አላውቅም..እኔ እንኳን እንደአንተ ልረዳው ብችል ኖሮ ምን አልባት አሁን ህይወቴ የተለየ መልክ ነበር የሚኖረው….ለማንኛውም አሁን ሁሉ ነገር አክትሞላታል፡፡ይሄው ከዚህ መስታወሻ ጋር አንድ ፍለሽና አንድ ቁልፍ ትቼልሀለው፡፡ፍላሹ ስለፕሮፌሰሩና ስለግብረአበሮቹ የማውቀውን ሁሉ መራጃ የሰፈረበት ነው..ከካሳ ጋር እየተማከራችሁ የሚሆነውን አድርጉ…ቁልፉ ፖስታ ሳጥኔ ነው….ሳሙኤል ለሚባል የፖስታ ቤቱ ምክትል ሀላፊ ንግሬዋለው…ችግር ካለ እሱ ያግዝሀል..እዛ ፓስታ ሳጥን ውስጥ ሁለት የታሸገ ፖስታ አለ…..አንዱ ዶላር ሲሆን ሌላው ፓውንድ ነው..አውጣና ተጠቀምበት ፡፡በል ቸው…ለእኔ በህይወቴ በጣም ጥሩ ከሆኑልኝ ጥቂት ሰዎች መካከል አንተ አንዱ ነህ፡፡ ብሞትም አረሳህም..፡፡ቸው…..ደግሞ ወንጀለኞችን ካጠፋህ ቡኃላ አንተም መልሰህ ወንጀለኛ እንዳማትሆን ሙሉ ተስፋ አለኝ….ካለበለዚያ የሙት መንፈሴ እየመጣ ይረብሽሀል፡፡
//
ጽፋ ከጨረሰች ቡኃላ መልሳ እንኳን ሳታናበው አልጋዋ መሀከላ አስቀመጠችና በላዩ ላይ ቁልፉን እና ፍላሹኑ አኑራበት ቀስ ብላ በራፉን ከፍታ ወጣች፡፡ኮሪደሩ በደመቀ የአምፑል ብርሀን ቦግ ያለ ቢሆንም ማንም የለም …የተጫማችው ፍላት ሸራ ጫማ ስለሆነ ድምፅ ሳያሰሙ ለመራመድ ምቹ ነው….ጥግ ላይ ወዳለች አነስተኛ ክፍል ነው ያመራችው….፡፡ቁልፉን ከኪሷ አወጣችና ወደውስጥ ገባች፣መልሳ ዘጋችውና መብራቱን አበራች….ክፍሏ ውስጥ አንድ ግዙፍ ጠረጳዛ አለ ፡፡ጠረጳዛው ሙሉ በክላሽ፤ በሽጉጥ፤ በጥይቶች በጩቤና በመሳሰሉት የጦር መሳሪያዎች የተሞላ ነው….፡፡በአይኗ ከዳር እስከዳር ካየች ቡኃላ ቀላልና በኪስ ሸጎጥ ለማድረግ የምትመች አነስተኛ ሽጉጥ አነሳች፣ ውስ ስድስት ጥይቶች አሉ….በጃኬት ኪሷ ውስጥ ከተተች፣አንድ አነስተኛ ጩቤም ከጩቤዎች መካከል አነሳችና በእጇ ያዘች…መብራቱን አጠፋችና በራፉን ዘግታ ወጣች…ወደመኝታ ክፍሎ አልተመለሰችም፡፡ፎቁ መውረጃ ደረጃ ይዛ ቁልቁል ወደታች ተንደረደረች…. መኪናውን አስነስታ መሄድ አትችልም…ሞተር ስታስነሳ ንቁ የሆነው አብዬት በደቂቃ ውስጥ ነው ወደታች ወርዶ አንቆ የሚመልሳት…ስለዚህ በእግሯ ግቢውን ለቃ ወጣች…ሞባይሏን አወጣችና ራይድ ታክሲ ጋር ደወለች..ከአስር ደቂቃ ቡኃላ መጥተው ጫኗት….የፕሮፌሰሩ ሰፈር አድርሻ ለሹፌሩ ሰጠችው፡፡በሰላሳ ደቂቃ ውስጥ አደረሳት…ለማንኛውም በማለት ራቅ ብላ ወረደች….ለሹፌሩ ሳብን ከጉርሻ ጋር ከፈለችውና ሸኘችው…ወጥታ ወደፕሮፌሰሩ ቤት አመራች፡፡ለምን እሰከአሁን እንዳስቀመጠችው ባታውቅም እስከአሁን የቤቱ ቁልፍ አላት….የውጩን በራፍ አንኳኳች..ዘበኛው ሰምቶ ይከፍትልኛል ብላ ነበር..ግን ደምፅ የሚባል ነገር ከውስጥ አይሰማም….ሰዓቱ ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ስላለፈ እንቅልፍ ጥሎት እንደሚሆን ገመተችና ቁፉን ከጃኬት ከኪሷ አወጣችና ከፈተች..ወደ ውስጥ ገባች፣፣ጩቤዋን ጎንበስ አለችና የካልሲው በውስጥ ሸጎጠችና ሽጉጧን በእጇ አስተካክላ በመደቀን የዘበኛውን ቤት እየገላመጠች ወደውስጥ ዘለቀች…የሳሎኑን በራፍ ቀስ ብላ ከፈተችና ወደውስጥ ገባች፣ሳሎኑ ባዶ ነው…..ወደመኝታ ቤት ሄደች….ማንም ሰው የለም…አልጋው አልተነጠፈም ክፍሉ ጠቅላላ እንደተዝረከረከ ነው….ካዝናው ክፍት ነው…..ወደቁምሳጥኑ ፊቷን አዞረችና ቀረበችና ከፈተችው….ግማሽ ሚሆን ልብስ ተንስቶለታል….፡፡
‹‹ብሽቅ አለች….ቦታ ቀይሮል ማለት ነው..ይሄ ፈሪ..››
ያገኘችው ወንበር ላይ ቁጭ አለችና..ስልኩን ደወለች፣፣አይሰራም…..በጣም ተበሳጨች..እና ገና እሱ እስኪያገኘኝን እጄን አጣጥፌ ልጠብቅ ነው…?የተለየ ሀሰብ መጣላት..ሞባይሏን ከእንደገና አነሳችና ፌስቡኳን ከፈተች…..የእሱን ፈለገችና
እቤትህ መጥቼ የለህም…የት ነህ..?
እኔን ውሰድና እቤተሰቦቼን ልቀቃቸው..አሁኑኑ››
ብላ በመጸፍ ላከችለት ፡፡አይኖቾን ሚሴጃ ቦክሰ ላይ ተክላ መጠበቅ ጀመረች..ከ20 ደቃቃ ጥበቃ ቡኃላ በዚህ ስልክ ደውይልኝ የሚል ቁጥር ተላከላት..ወዲያው አነሳችው...ደወለች፡፡
‹‹እሺ የእኔ ውድና ተፈቃሪ እጮኛዬ››
‹ድምፅ እንዲህ ቀፋፊ ነበር እንዴ?› ስትል በውስጧ አሰበች‹‹በጣም ነው የምታስጣላኝ››መለሰችለት፡
‹‹ተይ እንጂ የእኔ ውድ ..እኔ እኮ የወደፊት ባልሽና የልጆችሽ አባት ነኝ..ለእኔ ጥላቻ አይገባኝም;;››
‹ካንተ ጋር ማውራት እራሱ በጣም ነው የሚያቅለሸልሸኝ››
‹‹እና ተስገብግበሽ ለምን ደወልሽ…?››
‹‹የት ነህ ልምጣ….››
‹በጣም ናፍቄሻለው አይደል….እኔም በጣም ናፍቀሺኛል..አሪፍ የፍቅር ምሽት እንደምናሳልፍ እርግጠኛ ነኝ››
‹‹ቤተሰቦቼን አሁኑኑ ልቀቃቸው››
‹‹ምን አስቸኮለሽ… መጀመሪያ እንገናኝ..ከዛ አብረን ሆነን እንዲለቆቸውና ተንከባክበው ይቅርታ ጠይቀው እቤታቸው ድርስ እንዲያደርሳቸው እንነጋራቸዋለን…እና ደግሞ ከመሞተሽ በፊት ሁለት ነገሮችን እንሰራለን አንደኛውና የመጀመሪያው ጣፋጭ የሆነ የመጨረሻ ፍቅር እንሰራለን….ያው የመጨረሻ እራት እንደሚባለው ማለት ነው….ከዛ ያው እኔ ችግር አስገድገዶኝ እንጂ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ላረጋግጥልሽ ስለምፈልግ ቤተሰቦችሽ እቤታቸው መመለሳቸውን አረጋግጥልሻለው…ማለት በስልክ ታወሪያቸዋለሽ.ከዛ እስከመጨረሻው እንሰነባበታለን….››
‹‹እሺ አሁን የት ልምጣ?››
‹‹አይ የትም አትምጪ.. እዛው ጠብቂኝ ፡፡አሁን መኪናና ሰው እልካለሁ....ግን ማንንም ሰው አለማስከትልሽንና የሆነ ተንኮል አለማሰብሽን እርግጠኛ ሁኚ… ካለበለዚያ በእናትሽም ሆነ በተቀሩት ላይ ቀጥታ ቃታ ስበሽ እንደገደልሻቸው እወቂ…››
‹‹ባክህ ሁሉም ሰው እንደአንተ ሸረኛ እና ተንኮለኛ ይመስልሀል አይደል.?አንተ እኮ የዳቢሎስ የበኩር ልጅ ስለሆንክ ነው.. …በል አሽከሮችህን ላካቸው ፡፡ስልኩ ዘጋችው..ትንፋሽ አጠራት….በፍራቻ ብርድ እየተንዘፈዘፈች ወደመታረጃዋ የሚወስዳት ሰው እስኪደርስ መጠበቁን ተያያዘችው፡ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍26😢91🥰1
ለአንድ ሆድ
         መሸዋዎድ

ለአንድ እንጀራ
                በገጀራ

ላይባርከን
          መጨካከን

ላያፀድቀን
        ጉሮሮ አንቀን
👍4216
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታሰ


ከአዲስ አበባ ፍልውሃ በታች ከማህተማ ጋንዲ መንገድ መስመር ከብሔራዊ ስታዲዬም ብዙም ሳይርቅ ከግዮን
ከኢትዮጵያ ከሒልተን
ሆቴል... ለሚመጡ እንግዶች አመች የሆነው የ“ጎጆ” ምግብ ቤት ግቢው በመኪና ተጣቧል።

ቢኤም ደብሊው መኪና በዘበኛው መሪነት ቦታዋን ይዛ እንደቆመች ሁለቱ እንግሊዛውያን ወደ ምግብ ቤቱ አመሩ። እሷ ቀደም እሱ ደግሞ ከኋላዋ ተከትሏት ሲገባ እንደ ቀልድ ቁመናዋን አስተዋለ: ፀጉሯ አጠር ከማለቱ ሌላ ስትሄድ የሚደንሰው ዳሌዋ አለ
'' የለም' »አስኝቶ የሚያወራርደው ወገቧ
ያው ነው።ስትጠመጠም እንደ ላስቲክ እየተሳሳበ በሰራ አካላቱ የሚስለከለከው አካሏ ለውጥ የለውም። ልክ እንደ ዛሬ ሁለት ዓመት ከስድስት ወሩ ነው ጥቁር ቲሽርት እንደ ወትሮው ሁሉ ጂንስ ሱሪ ለባብሳለች።ወገቧና አንገቷ ልብሷ አልደረሰበትም:

የሴት እምብርት ሲያይ ጎሮሮውን እንዳነቁት ሁሉ አይኑ የሚፈጠው ስቲቭ አጎጠጎጤ ጡቷን ደረቱ ላይ አስደግፋ ለጠጥ ብላ
ሽቅብ ተስባ ስትስመው እንደ ህፃን ልጅ በእቅፉ አልሞላ ስትለው እቅፉን ጠበቅ አድርጎ እንደ ቄጤማ አካሉ ላይ የለጠፉት ትዝ
አለው።

ገባ ብለው ክፍት ቦታ ሲያማትሩ አስተናጋጁ በስተግራ በኩል ግድግዳው ጥግ ባዶ ቦታ አሳያቸው።

የሲሊን ዲዮን ዜማ በለሆስታ ይሰማል ካርለት ድምፀ መረዋ ካናዳዊት አቀንቃኝ ስሊን ዲዮን ኒወርክ “ብራንድ ዌይ
ዳንሰሮች ጋር አይኖቿዋን እያስለመለመች, እግሮችዋን መሬት
ለመሬት እየሳበች ወለሉ ላይ እየተኛች...በለበሰችው ጃፖኒ እርቃን የሆነውን ትከሻዋን እየላሰች ስትዘፍን ስላየቻት ይበልጥ ወዳታለች::

እና! ገና "ከመግባታቸው በፊት የምትወደውን ዜማ ስትሰማ የደስታ ስሜት ተሰምቷታል።

አስተናጋጁ የምግብ ዝርዝር ይዞላቸው መጣ: ሁለቱም
ዝርዝሩን ተቀበሉና በፀጥታ አንብበው ካዘዙ በኋላ ጨዋታቸውን ሊጀምሩ ሲሉ

“የሚጠጣስ?” አይኖቹን ግራና ቀኝ እያዟዟረ  ጠየቀ
አስተናጋጁ።

“ማርቲኒ” አለችው ካርለት

“ነጭ ወይንስ ቀይ ማርቲኒ” የሾለ ፊቱን ወደ ፊት አስግጎ ጠየቃት።

ነጭ ይሁንልኝ አለችው። አስተናጋጁ ለጨዋታ
መጣደፋቸውን ተረድቶ ይቅርታ በሚጠይቅ አስተያየት ስቲቭን
እያየ አገጩን ሽቅብ ሰበቀ።

“ብሳክ ሌብል” አለው።

ካርለት ቦርሳዋን ወንበሩ ላይ አንጠልጥላ ፈገግ እያለች።

“እሺ ስቲቭ! ስትለው ስቲቭም ወንበሩ ላይ ጠረዼዛው እያስጠጋ ፈገግ ብሎ አንገቱን ወዘወዘ ደህና ነኝ ለማለት።

“…ኢንግላንድ መልም ጊዜ አሳለፍሽ?

“ከናቴ ከጓደኞቺ ጋር በመገናኘቴ ደስ ብሎኛል። ብዙዎቹ ጓደኞቼ ግን ደስተኞች አይደሉም:: ሁሉም ያለሙትን ህይወት
መኖር የቻሉ አልመሰለኝም። ከጎይቲና  ከከሎ ጋር ያሳለፍኩት ጊዜም ባመዛኙ እንግዳ ለሆነባቸው ስልጣኔ እያንዳንዷ እንደ ህፃን
ልጅ ማስረዳቱ አድካሚ ቢሆንም ወድጄዋለሁ:

“ጥናቴን በተመለከተ ማንቸስተር ያቀረብሁት ዝግጅት ለአማሪዬና ስብሰባ ተሳታፊዎቼ ጥሩ ስሜት የፈጠረ በመሆኑ ደስ ብሉኛል። ከዚህ ተጨማሪ ከማንቸስተር ዩንቨርስቲ አዳራሽ ስንወጣ ብዛት ያላቸው የ" ጋርዲያን የሄራልድ ትሪቡን…
ጋዜጠኞች ለኔ ለጎይቲና ለከሎ ያቀረቡልን ጥያቄ የሰጠነው መልስ  በቤቱ ውስጥ የነበረው የመግባባትና የማድነቅ እንድምታ ስቃይን እሚያስረሳ ነበር። “በተለይም ሴቶችን አስገድዶ መድፈርና
የወሲብ ብዝበዛ በሐመር ምድር የተወገዘና የማይፈፀም ፀያፍ ጉዳይ
መሆኑን ላስረዳቸውና ጎይቲ “ሴትን ያለፍቃዷ ማን ያስቸግራታል ደሞ." ያለችው ስሜታዊ አባባል ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው ውስጥ
ዋናው ነበር።

“በተረፈ ለአንድ ሳምንት ስፔን ለአንድ ሳምንት ደግሞ
ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሄጄ ነበር: እንደ ማይክል ጃክሰን በዚች ፕላኔት ካለው ወፈ ሰማያት ህዝብ መሀከል የማደንቀው ሁለት ሰው ነው:: ማንዴላንና ማር ትሬዛን ብዬ ባልደመድምም በደረጃ ከማይክል አስተያየት የማላርቀውን ማንዴላንና የሱን አመራር
በቅርብ ለማየት እድል ለማግኘቴ የተደሰተሁ ሲሆን በጆሀንስበርግ ሰሜን ማዕክል ብራምፎንቴን በሚገኘው ዊትስ ዩንቨርስቲ የአባቴ ስራዎች በመታሰቢያነት ሲቀርቡ ንግግር ማድረግ መቻሌሞ ጥሩ አባት ሞቶም የደስታ ምንጭ እንደሚሆን ለማመን ችያለሁ።

የነፃነት ረጅም ጉዞ በሚል
ርዕስ በ1994 ዓ.ም
በማክዶናልድ አሳታሚ ኩባንያ በኔልስን ማንዴላ የታተመው የ ባለ 617 ገጽ መጽሐፍም በመርፌ ቀዳዳ የሚታይን ብርሃን ተከትሎ
ከፀሐይ አካል መድረስ መቻሉን የተማርኩበት ነበረ።

“የፍቅር ህይወቴን በተመለከተ ግን እግሮቼ ሁለት መሰላል ላይ ናቸው:: ባል የማግቢያዬ ልጅ የመውለጃዬ ጊዜ እያለፈ
መሆኑን ሳስብ አንጀቴ በሃዘን መኮራመቱ ባይቀርም የሰለጠነው
ዓለም ለፍቅር ቀረቤታ ያለው አነስተኛ ግምት የመመዘኛ ዝባንዝንኬው በተፈጥሮው ዓለም ደግሞ ህይወቱን ላልኖረው ሰው
ያለው አስቸጋሪነትና የፍቅር  አለመጣጣም... ለጊዜው መምረጥ ከሚያስቸግር ሁኔታ ላይ እንደጣለኝ ነው የምረዳው።

“እዚህ  ላይ ግን ልገልፅልህ የምወደው እንደማንኛውም
ሰው መጭው ህይወቴ ምን መምሰል እንዳለበት ሳስብ ብዥ ብዥ እያለ የሚታየኝ ህልም አስጨናቂና አሳሳቢ ቢሆንም ከምንም በላይ
የምፈልገው በአባቴ የሰው ልጅ ሕይወት ምርምር ጎዳና መጓዝንና ለሙያዬ መሉ መስዋዕትን መክፈል ስለሆነ መፅናኛዬ ሚዛኍን
የደፋ ነው፡፡ ስለዚህ ደስተኛነቴ አሁንም ከቁጥጥሬ አልወጣም ብላ
ፈገግ አለች::

ስቲቭ ሃሣቧን ያዝኩት ሲል ወዲያ ስታላጋው ወዲህ
ስታጋጨወ ቆይታ እንደ ጥሩ ተውኔት ጨዋታውን ባላሰበው መንገድ ደመደመችበት።

ለጥቂት ጊዜ ሁለቱም በየግል ሃሣባቸው ተውጠው እንደቆዩ ፈጣኗ ካርለት ከነበረችበት የሃሣብ ግልቢያ ድንገት ልጓሟን ስባ የስቲቭን ቀኝ እጅ በቀኝ እጅዋ ቀስ ብላ ጫን አድርጋ
ሳታስደነግጠው ሳታሽብረው ሃሣቡን ሳታምታታበት ትክ ብላ
መረጋጋቱን ካስተዋለች በኋላ፡-

“ስቲቭ! አንተስ ከተለያዬን በኋላ ጥሩ ጊዜ አሳሰፍክ?"
አለችው።

ዘናና ፈገግ ብሎ  “በስራዪ ብዙም ውጥረት አልነበረኝም የዲፕሎማት ትልቁ ሥራ ግንኙነት መፍጠር፤ የአገሪቱን
ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አዝማሚያ መከታተል፤ ተስፋን መመገብ ገደብ አልባ የሆነ ቃል ኪዳን መግባት በመሆኑ በፈቀደልኝ የጉዞ ፍጥነት እያሽከረከርኩ ስራዬን ለመወጣት ሞክሬያለሁ፡ የኢትዮጵያ ኑሮ ግን ከብዶኛል" አላት

እንዴት? የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ!" አለችው ውስጡን
ጠልቃ ለመመልከት አይኖቹን እየፈለገች።

ካርለት የሰዎችን አይን በማየት ስለ ሁኔታዎች ምንነት ለማወቅ እንደሚቻል በስነ ልቦናዊ ትምህርቷ ታውቃለች። አንድ ሰው ያስጨነቀው ነገር ትዝታውን• ፍቅሩን ጥላቻውን... ሲገልፅ
የአይኖቹ ኳሶች የት እንደሚሆኑ ወዴት እንደሚዞሩ ከስነ አዕምሮ
ባለሙያዋ እናቷ ተምራለች። ሌላው ቀርቶ እውነትና ውሸት አባባልን የአይንን እንቅስቃሴ አይታ በከፊል መግለጽ ትችላለች።
ከዚህ በተጨማሪም የአንድ ሰው አመለካከቱ በመስማት ወይንም በማየት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ከአገላለፁ በመረዳት አይኑና ሃሣቡ  ከሚሰጣት ግንዛቤ ግንኙነቷን ለመመዘንና ለመለካት
አትቸገርም። ለዚህም ካርለት ስቲቭ ሲያወራት አይኖቹን ትፈልግ ነበር: ኋላ ግን አይኑን በአይኗ ያዘችው እንቅስቃሴዋንም
አስተከለችና፡-

"...የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ? አለችው ደግማ ስቲቭ
በአፍንጫው ጫን አድርጎ ተነፈሰና፡-
👍22