አትሮኖስ
279K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
456 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_አንድ


#ከፍቅረ_ማርቆስ_ደስታ

...የልጃገረድ ጡት የመሰለው የሐመር ተራራ አፈዘዘው እና! ያን ማራኪ ተራራ በአይኑ ጠባው... በህሊና አኘከው... ጳ...
እኝ... ጳ... እያደረገ አጣጣመው።

hቡስካ ተራራ ላይ ሆኖ የሐመርን ምድርና ቀዬ ከአድማስ ወዲህ የአስሌንና የቡሜን ተራራ በየኮረብታው ላይ የሚታዩትን የሐመር መኖሪያ ቀዬዎች እየተጠማዘዘ ከቡስካ ተራራ ስር ጀምሮ ቁልቁል ወደ ኦሞ ወንዝ የሚጓዘውን የከስኬን ወንዝ... በአረንጓዴ
ልምላሜ የተዋበውን የሐመርን ጫካ ሲቃኝ የከብቶችን ግሣት
ሲያዳምጥ ስሜቱ ዋለለ፡፡

ደልቲ ውስጡ እንደዚያ በደስታ ቢተራመስም ውጫዊ እርጋታው ያው እንደወትሮው ነው:: ዝም!  ጅንን፡

አካባቢው በአዕዋፍ ድምፅ በሽምልማል ንፋስ ሽውሽውታ ከዛፍ እየተንጨዋለሉ በሚቦርቁት ጉሬዛና ጦጣዎች... ደምቋልዘ

ደልቲ ገልዲ ዝግባ ጥድ ግራር ካስዋበው የቡስካ ተራራ ላይ ሆኖ የአባቱን ምድር የሐመር ውብ ተፈጥሮ ሲቃኝ ቆይቶ
ከቆመበት ቦታ በስተግራ በኩል ካለችው ውብ የግራር ዛፍ ስር ሄዶ
በርኮታው ላይ ቁጭ አለ፡፡

ገሃዱ ዓለም ላይ ዋና ሥራ ጉዞ ፍቅር ጥላቻ... ይሆንና
በህሊና ቀረጢት ደግሞ ትዝታ ይከማቻል፡  ህልም ትዝታ...ማንም ከዚ ከስተት ሊያመልጥ አይችልም:: በገሃዱ የፈፀመውን
በትዝታ ምስል ያየዋል ከዚያ ይፍነከነካል ወይ ይቆዝማል! ይቅበጠበጣል ወይ ይሽማቀቃል! አልያም ይስቃል ወይ ያነባል...
ትዝታ! የተዳፈነውን እውነት እየጫረ ስሜትን ይለዋውጣል…

ደልቲም እንዲያ ከተዋበው ሥፍራ ሆኖ ዛሬን ከዛሬ ተቋድሶ ትናንትን አለማት ህልሟ  ትናንት ደግሞ የትናንት ግሣንግሷን
ይዛለት ከፊት ለፊቱ ተደቀነች፡ ጨዋታ ጭፈራ ጀግንነት ፍቅር...
አንዱ በሌላው ላይ እየተነባበረ ታየው፡፡ ገሃዱን ዓለም ከምናባዊ ትውስታው ጋር አንዳንዴ እየተጋጨ ሌላ ጊዜ እየተዋሃደ ተመለከተው የህይወት ኡደት የተፈጥሮ ባህሪ አንዱ ሌላውን እየተካ ብቅ ጥልቅ እያለ ሲያልፍ ህሊናው የትናንት ትዝታን ወደኋላ
ሲያነጠጥን ለማየት ተከተለው፡

ጦጣና ጉሬዛዎች ከዛፍ ዛፍ እየዘለሉ ሲቦርቁ አዕዋፍ ሽቅብ እየጓኑ ቁልቁል ሲወረወሩ... የደልቲ የቦዙ አይኖች የሚያዩት
ትናንትን ነው:: የትናንት ትዝታ ከሁሉም ገዝፎ በህሊናው ተንሰራፍቷል።

በዚህ የትዝታ ማጥ እንደተዘፈቀ የቦዙ አይኖቹ እንግዳ ነገር ተመለከተ
አይኑ የሚንቦገቦግ ቀንዱ የሾለ ሰውነቱ
የሚያንፀባርቅ... ግን የደነበረ አውሬ ሰውነቱ የሚንቀጠቀጥ መሸሽ
ደግሞ ያቃተው አውሬ::

ደልቲ ከትዝታ ማጡ ያለ የሌለ ሃይሉን አስተባብሮ
በመውጣት የያዘውን ክላሽንኮቭ በአውሬው ግንባር ላይ አነጣጥሮ
አመልካች ጣቱን ቃታውን ከመሳቧ በፊት ስሜቱ ሲጣራ ወስፋቱ ሲጮህ ሰማው፡፡ የተጠበሰ ስጋ ወጠሌ ጥብስ ትዝ አለው  ጎመጀ።የራበው ሰው የሚበላ ሲመጣ አይገፋም፡ ያውም ካውሬም የድኩላ
ምራቁ በአፉ ሞላ፡፡

ድኩላውን ከማሰናበቱ በፊት በመሣሪያው የማነጣጠሪያ
ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከተው። ተሸብሯል! ፍርሃትም ያንዘፈዝፈዋል! “ለማምለጥ መሞከር ሲገባው ለምን ተገትሮ ቀረ?
አይኖቹስ ለምን ይማፀኑኛል?..” አለ በማይሰማ ድምፅ

ደልቲ ግራ ገባው፡፡ ቀጭኔ ጎሽ አንበሳ... ሲገል
እየተሯሯጠ አንዱ ለማምለጥ ሌላው ለማስቀረት እየተጣጣረ...
እየወደቀ.. እየተነሳ... ነበር: ዱኩላው ግን አልተንቀሳቀሰምI
አልሮጠም ታዲያ ደልቲ እንዴት ደንግጦ የቆመ እንስሳ ይገላል!
እንዴትስ ለሆዱ  ብሎ ተሸብሮ ከፊት ለፊቱ እንደ በግ ቆሞ የሚማፀነውን አውሬ ገድሎ የአባቱን የጀግንነት ባህልና ታሪኩን
ያበላሻል።

ዘገነነው! የራሱ የሆኑት ፍየሉች በጎችና, ከብቶች
ታሰቡት። የሥጋ አምሮት የአባት ባህል... እስሜትና እህሊና ትግል ውስጥ ከተቱት። ስሜቱ በሰውና ጥብስ ብላ አለው: ሀሊናው
“ፈርቶ ደንብሮ ጉያ ውስጥ የገባን አውሬ ተኩሶ መግደል የጀግና ሞያ አይደለም። የመልካም ስም የደግነት ሥራ ጠላቱ ከርስ ነው። ሆዳምነት! እና ተወው" አለው።

ደልቲ ይህን እያስበ ዓይኖቹን ከድኖ ሲከፍት ደነገጠ:: ተምታታበት ደኩላው ከፊት ለፊቱ የለም በሱ ቦታ የተተካውን
ማመን አቃተው አይኖቹን ጨፍኖ እንደገና ከፈታቸው: ለውጥ የለም: ድኩላው የለም: እሱን የተካው ግን ከፊት ለፊቱ ቆሟል።

ምን ጉድ ነው!" ደልቲ ተሸበረ። የሚያየውን ማመን
ተሳነው። አይኖቹን ደጋግሞ እየከደነ ከፈታቸው: አዎ! ቅዠት አይደለም እውነት ነው ከፊት ለፊቱ የቆመው ሰው ነው  ልጃገረድ... ያውም የደም ገንቦ ..

ድኵላ. ልጃገረድ… ድኩላ ልጃገረድ… ህሊናው እውነቱን ለማጣራት ሞከረ።

"ለምን መጣች? ምን ጉዳይ ይኖራት ይሆን ድኩላውስ
ለምን ቆመ? ለምን ደነገጠ? የትስ ሄደ ?  ለምን በሱ ቦታ እሷ ተተካች..." ራሱን ለማሳመን ማጠፊው አጠረበት።
ልጃገረዷን  የደም ገንቦዋን አውቋታል: የወሮ መንደር
ቆንጆ ናት ግን እሷ ስለመሆኗ ማን ማረጋገጫ ይስጠው: በህሊናው
መልስ አልባ ጥያቄዎች ተደረደሩ'

“ይእ! ከመሞት እንደሁ የሚያመልጥ የለ። ነገ ወይንም ተዚያ በኋላ በወባ ሞተች... የከስኬ ውሃ በላት… ከብት ወግቷት
ሞተች... ከምባል ደልቲ ገደላት I አፍቅራው ሄዳ ፍቅሯን ሳይረዳ
ጭንቀቷን ሳይካፈላት ራቧን ሳይራብ ሙቀቷን ሳይጋራት...ጀግናው ገደላት ቢባል ምናለ!" ልጃገረዷ ከቆመችበት ሳትንቀሳቀስ
አጉተመተመች።

እሏ ያስደነበረችው ድኩላ እሷን ፈርቶ ሮጦ ደልቲን ሲያይ ከፊት ለፊቱ ቆመ: እሷም የስንት ጎረምሳ ልብ ተነጥፎላት እየረጋገጠች አልፋ በፍቅር ልቡ ርሷል ለተባለው ጀግና ፍቅሯን
ልታበረከትለት ከደስታ ፈጣሪ ደረቱ ላይ ለመጋደም ተራራውን ወጥታ ከፊት ለፊቱ ተገተረች።

“ ደልቲ ድኩላውን ለምን ሳይገለው ቀረ? የቆመ
የተሽበረ አልገልም ብሎ እንጂ ከሰማይ ወፍ የሚያወርድ ጀግና ነው፡፡
ይእ እንዲህ ነው እንጂ ጎበዝ! ምግባሩን ለአባቱ ለባንኪሞሮ ትዕዛዝ
ያስገዛ  ለሆዱ ያላደረ... ለዚህ ጀግና ፍቅር ተራራ ቢወጡ እንደ ቅንቡርስ መሬት ለመሬት ቢልወሰወሱ እንደ ኩይሳ ከፊት ለፊቱ
ተገትረው ቢኖሩ ነፍስና ስጋን ቢሰጡት ምን ይቆረቁራል

“አይ እርጋታ! ደሞ ዛሬ እንደ አንበሳ ግርማ ሞገሱ እንዴት ያምራል? እውነት ከእሱ እቅፍ ገብታ ዓለሟን ያየች ሴት ጨረቃና
ከዋክብት በሌሉበት ድቅድቅ ጨለማ ብትጓዝ ትደናቀፍ ይሆን!"ፍቅሩ ውስጧን እያመሳት ቀባጠረች

ደልቲ ከንፈሯ ሲንቀላቀስ አይቷል። የምትለውን ግን
አልሰማም፡ ልጃገረዷ አንገቷ ላይ ከደረደረቻቸው ጨሌዎች ሦስቱን
አወጣች፡፡ ትንባሆ የያዘ ትንሽ የፍየል ቀንድ በቆዳዋ ጫፍ ቋጠረችበት ፈታች። ደልቲ በትዕግሥት ይመለከታታል፡

ልጃገረዷ አይኖችዋን ሳትሰብር በፍቅር አይን አይኑን እያየች ስትመጣ ደልቲ ትዝታው እንደአውሎ ነፋስ ወደ ኋላው ነጥቆት
ነጎደ። ወደ ትናንት ወደ ድሮ: ያኔ የትናንቱ ድሮ ጎይቲ አንተነና እሱ መጀመሪያ ከዲመካ ገበያ ተያይተው በአይን ተጠቃቅስው
በልቦናቸው ተስማምተው በፍቅር መሪነት ጫካ ገብተው ያ ያዜመችለት የወንዶች አውራ ጭን ላይ ቁጭ ብላ አእዋፍና ነፋሱ
እያጀቧት የድምጿን ቅኝት
👍663