አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ስምንት (28)

እንደሚያፈቅራት ብትፈቅድለትና ፍቅራቸውን ለመካፈል ቢችሉ ደስ እንደሚለው ደጋግሞ ገልጾላታል ። ግን እሷ ልቧን ትጠራጠረዋለች ። በይመስለኛል ስሜት ተገፋፍታ ሳይሆንላት ቢቀር ፒተርን ማስቀየም
ይሆናል ። ይህንን ደግሞ ፈፅሞ አትፈልገውም ። ስለዚህ የፒተር ጥያቄ የኣሺታም የእምቢታም መልስ ሳያገኝ በውዝፍ ዶሴ ተይዞ ቀርቷል ። መዋደዳቸው ፤ መተሳሰባቸው ፤ ጓደኝነታቸው ግን አሌ የሚባል ነገር አይደለም ። «በጣም ናፍቀኸኝ ኖሯል ፒተር» አለች ሜሪ ። ይህን ብላ ህክምና በሚደረግላት ጊዜ እምትቀመጥበት ወንበር ላይ ተቀምጣ ሥራውን እንዲቀጥል ዝግጁ ሆነች ። ዓይኗን ገርበብ አደረገች ። ከወንበሩ ላይ ተነስቶ ትንሽ ከተመለከታት በኋላ « ዛሬ ደግሞ ለመታከም ጥድፊያ በጥድፈያ ሆነሻል » አላት በተለመደው ብርጩማው ላይ ፊት ለፊቷ ተቀመጠ፡፡ « ሁለት ዓመት ሙሉ በፋሻ ስትሸፈን ፤ ፋሻ ሲላጥልክ ብታሳልፍና የመጨረሻው ቀን ቢመጣ አንተ ራስህስ ብትሆን ያንለት ለመገላገል መቻኮልህ ይቀር ነበር ? »

«አይቀርም ፤ እንዲሁ ለማለት ያህል አልኩ እንጂ ነገሩስ ይገባኛል ። ... በደንብ ይገባኛል የኔ መቤት» እግንባሯ ላይ ያለውን ፋሻ ካነሳላት በኋላ ፤ «አሁን አይንሽን መግለጥና ፊትሽን በመስታወት ማየት ትችያለሽ ፣ ሜሪ» አለ ። ሜሪ ግን ካለችበት ላይ ንቅንቅ አላለችም ። ብዙ ዓለም አይታ መጥታለች ። ሆኖም የአዲስ እሷን ፊት ሙሉውን አታውቀውም ። አንደኛው ጐን ቢገለጥ ሌላኛው ወይ በፋሻ ተሸፍኖ ወይ ፕላስተር ተለጥፎበት ወይም ተደርቶ ነበር የምታየው። «በያ ብድግ በይና ወደ መስታወቱ ቅረቢ» አለ ፒተር ያን አዲስ ፊት ፤ ያን ናንሲ ማክአሊስተር የነበረችውን የቀድሞ እሷን ሳይሆን ሜሪ አዳምሰን የተባለችውን አዲስ እሷን ለማየት ፍርሃት ተጫናት ። ምን ያለ የማይረባ ፍርሃት ነው አለች በሐሳቧ። ፍርሃቷን እሸንፋ ተነሳች ። ፊቷን በመስታወቱ ውስጥ ስታይ ፊቷ በሳቅ ቧ ብሎ ተከፈተ ። በጉንጯ ላይ ግን እንባዋ ይጐርፍ ነበር ። ይህ የስሜት ግንፈላ ተግ እስኪልላት ድረስ አልተጠጋትም ። አላነገራትም ። ያ ጊዜ የግሏ የሆነ ማንም ሊጋራት የማይገባ ጊዜ እንደሆነ በመገንዘብ ። «ፒተር ፤ እረ የፈጣሪ ያለህ ! እንዴት ቆንጆ ነው አለች ። «አይ አንቺ ቂል ፍጡር» አለ ፒተር በለሆሳስ እየሳቀ «እንዴት ቆንጆ ነው ሳይሆን እንዴት ቆንጆ ነኝ በይ… ያቺ የምታያት ሌላ ሰው ወይ ሌላ ነገር አይደለችም ። አንቺ ነሽ ራስሽ ነሽ›› ዞራ አየችው ። የተናገረው ትክክል እንደሆነ በቃላት መግለጽ አቃታት ። ራሷን በአዎንታ ነቀነቀች ። ልክ ነው ። ሙሉ በሙሉ ተቀይራለች ። ከምታውቀው መልኳ የቀረ ቅንጣት ምልክት የለም ። አሁን ያላንዳች ማወላወል ሜሪ አዳምሰን ነኝ ስትል አመነች

«ፒተር !...» አለች ውለታ በበዛበት ድምጽ ። ሄዳ ተጠመጠመችበት ። ተቃቅፈው ብዙ ጊዜ ቆዩ ። በመጨረሻ ፊቷን ለማየት እስኪችል ድረስ በክንዶቿ ይዞ ራቅ አደረጋት ። ፈቷ በእንባ ርሷል ። በጣቶቹ ጠረገላት ። «ፒተር. . . አየህ እንባየ እንኳ ፊቱን አላሟሟውም ! » አለች ። «ያ ብቻ ሳይሆን በትንሽ በትንሹ ይሁን እንጂ ፀሐይም መሞቅ ትችያለሽ» አላት ። ከዚያ በኋላ ግን ዕድሜሽን በሙሉ የፈለግሽውን ነገር ማድረግ ትችያለሽ ። ደስ ያለሽን ብትሆኝ ምንም አደጋ አይኖርም ። በነገራችን ላይ ምን ለማድረግ ነው እቅድሽ ? »

ይህን ብላ እተሽከርካሪው ወንበር ላይ ተቀምጣ ፤ እግሯ ጉንጯን ነክቶ ከራሷ በላይ እስኪሆን ሽቅብ አንስታ ከወንበሩ ጋር መሽከርከር ጀመፎች ። «አምላኬ እስቲ ይኸን ምን ትለዋለህ ? ሴትዮዋ እቢሮዬ ውስጥ ገብታ አንድ አካሏ ቢጐድል ሰው ምን ይለኛል ። አበጀህ እንኳን ይለኝ ይሆን ?»
«አትፍራ እኔ እንደሆነ ዛሬ የመጣው ቢመጣ ጥርሴ እረገፈ ፤ እግሬ ተሰበረ ... ካሣ ምናምን እንደማልል ይግባህ ።የማከብረው እንጂ የምጨቃጨቅበት ቀን አይደለም»
«እንዲያም ከሆነ መልካም ። ይህ ቀን ዓመት ባልሽ መሆኑን መስማቴ ደሞ በጣም ደስ አስኝቶኛል » ፒተር ብቻ ሳይሆን ፍሬድም (ውሻው) በሆነው ነገር ደስ ያለው ይመስላል ። ይዘላል ፤ ይቧርቃል ፤ ጭራውን ይቆላል። የተናገርኩት ስለገባው ነው አለች ውሻውን እያሰበች ። ከዚያም ጨብጠኝ እንደማለት እጅዋን እየዘረጋችለት ፣ «አላወክም ነበር ማለት ነው ጅሎ !. ይህን ዕለት ለማክበር ለራሳችን ጢን ያለ የምሳ ግብዣ እናደርጋለን ፒተር›› አለች ። ስሙን ከጠራችው በኋላ ሙሉ በሙሉ እያየችው «ፒተር ውለታህን ልከፍልህ የምችል አይመስለኝም ። ግን ደግሞ እስከመቃብር ከልቤ አትጠፋም ። መቼም ቢሆን የትም ቢሆን አስታውስሃለሁ ። በበድን አካሌ ነፍስ የዘራህባት አንተ ነህ» አለች ።

«አ…እ… እኔ ሳልሆን ሌላ ሰው ነው» አለ ፒተር ። አዎ ማሪዮን ሂልያርድ ፤ የማይክል እናት ናት ፤ ይህ ሁሉ እንዲሆን ያደረገችው። ግን ደግሞ ሜሪ ማሪዮንን ምን ያህል እንደምትጠላት ስለሚያውቅ ስሟን ሊጠራ አልፈላገም ። ሌላ ሰው ብሎ ጠራት ።
ቀጥሎም...
«እኔ. .. እኔ በበኩሌ ግን ሜሪ… ያደረግኩልሽን ሁሉ ስላደረኩልሽ ደስ ይለኛል ። ለወደፊቱም ላደርግልሽ የምትፈልጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ» አለ ። «ነው?... ቀልድ መስሎሃል ፤ አደል ? እንዲያውም ከዛሬ እንጀምራለን ፤ ዛሬ በስድስት ሰዓት ተኩል ተገናኝተን ምሳዬን እንድታጐርሰኝ እፈልጋለሁ ። እሺ?»
«ደስ ይለኛል»
«የት እንገናኝ ? » አንድ በቅርብ የተከፈተ ምግብ ቤት ጠቀሰላትና ታውቀው እንደሆነ ጠየቃት ።
«በሚገባ !» አለች ።
«ይስማማሻል ?››
«አሳምሮ ። እንዲያውም ካሁን ጀምሬ ወደዚያው አካባቢ ሄጂ ሰዓቱ እስኪደርስ ፎቶግራፍ ሳነሳ እቆያለሁ፡፡ አይን የሚገባ ነገር ከተገኘ»
«አሁን የልቤን ምኞት ነገርሺኝ ። ገበያ ሄጄ አዲስ ልብስ ስመርጥ ወይም ሌላ ብትይኝ ኖር ይከፋኝ ነበር» ተሰነባብተው ተለያዩ ፤ እስከምሳ ሰዓት ።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በምሳ ሰዓት ሲገናኙ ልብሷን ቀይራ ሽክ ብላ አገኛት ። «በእውነት ይቺ ሴት አንቺው ራስሽ ነሽ ?»
«ባለወርቅ ጫማዋ ልዕልት እነሆኝ ፡። እንዴት ነው ፤ አምሮብኛል ?»
«አምሮብኛል !? እንደ ቅዱሳን አንፀባርቀሻል እንጂ ፤ ምንማማር ብቻ! ... እንደፈራሁት ፎቶ ግራፍ ማነሳሳቱን ትተሽ ቀሚስ መረጣ ላይ ዋልሽ ልበል?»
«ምን ይደረግ ትላለህ ። ሳስበው ለካ ይህ ቀን የሚከበር ፌስታ የሚደረግበት እንጂ የሚሠራበት አይደለም» ድንገት አቅፈህ ሳማት የሚል ሐሳብ መጣበት ፤ እምግብ ቤቱ ውስጥ ያ ሁሉ ሰው እያዬ ። ሐሳቡን ገታና እጅዋን ጥብቅ አድርጐ ያዛት ። «ውዴ ይህን ያህል ደስ ብሎሽ ስላየሁ እኔንም እጅግ ደስ አለኝ» ኣለ ። «ፒተር በጣም ደስ ብሎኛል ። የዛሬዋ ቀን ለኔ ልዩ ናት። ስለገጽታዬ ብቻ አይምሰልህ ። የዛሬ ቀን. . . ነገ የፎቶግራፍ ተርኢት የማቀርብበት ፤ ኤግዚቢሽኔ የሚከፈትበት ቀንም ስለሆነ... አዲስ ሕይወት መጀመሬም ነው።... አንተም አጠገቤ እንዳለህና ድንቅ እንደሆንክ ስለማውቅ»
👍141
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ዘጠኝ (29)

«ውዴ . . . እስኪ ዚፔን ዝጋልኝ » ብላ ውብ ጀርባዋን አዞረችለት « እኔ እንኳ ደስ የሚለኝ… ብከፍተው ነበር››
«ፒተር ! . . . እንዲህ ያለ ወሬ… » አለች በማስጠንቀቅ መልክ ተገላምጣ እያያችው ። ሁለቱም ሳቁ ። አለባበሷን ሲመለከት ፣ ውበቷን ሲያይ በአድናቆት ተዋጠ ። «በኋላ ምን ብሎ ነበር ብለሽ ናቂኝ አንድ ሰው ፎቶግራፍሽን ቢያይ ከምላሴ ጠጉር »
« ለምን?»
«የተመልካች ዓይን አንቺው ላይ ያርፋል ። እዚያ ተተክሎ ይቀራል። በቃ !»
« ያን ያህል ?» ይህን ስትል ያለውን ነገር ፈጽሞ እንዳላመነች ገባው ። ጥርጣሬዋ የመገረም ሳቅ አሳቀው ። እሱም በኤግዚብሽን መክፈቻ ላይ ሽክ ብሎ ለብሷል ። ቢጋቡ የሚያስቀኑ ባልና ሚስት ይሆናሉ። «እንዴት ነው ? ፎቶ ግራፎቹን እንደምትፈልጊው አድርገው ሰቀሉልሽ ? ጊዜው ጠፋና ይህን እንኳ ልጠይቅሽ አልቻልኩም»
«ምንም ችግር የለም ። ያዘዝኩት ሁሉ እንዳዘዝኩት ሆኖ ተፈጽሟል ። እድሜ ላንተ ፤ ፒተር ። ይኸኔ ቅር ይላትና ዋ! ብለሀቸዋል ። ወይ አንተ ወይ ጃክ ይህን ያላችሁ ይመስለኛል » ጃክ የኤግዚብሽኑ አዳራሽ ባለቤት ሲሆን የፒተር ግሬሰ? የረጂም ጊዜ ጓደኛ ነው ። « ሁሉን ነገር ሰው ይሰራዋል ። እኔ በቃ አርቲስት ብቻ ነኝ የሚል ስሜት ይሰማኝ ጀመር››
«ሊሰማሽ የሚገባ ነው። ይሀ ትርኢት ሲያልቅ የኪነጥበብ ስራሽ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ያኔ ታያለሽ ።»

እንዳለውም ሆነ ። ኤግዚብሽኑ በተከፈት ማግስት በጋዜጦች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች በአድናቆት የተሞሉ ነበሩ። ፒተርና ሜሪ ጧት ቁርሳቸውን በልተው ቡና እየጠጡ ጋዜጦችን ሲያነቡ በጣም ደስ አላቸው ። «አላልኩሽም ?» አላት ፒተር ፤ ገና የመጀመሪያውን በአድናቆት የተሞላ አስተያየት ሲያነብ « አየሽ ? ኮከብ ነሽኮ »
«አንተ ደሞ ጅል ነህ ! » አለችና ጋዜጣውን አስደገፈበት ጭኑ ላይ ዘጭ ብላ ተቀመጠችበት ። ጋዜጣው ተጨማደደ። «እስከሚቀጥሊው ሳምንት ቆይና ደሞ ሌላ ተአምር ታያለሽ ። እያንዳንዱ ፎቶግራፍ እያራባ የሚሸጥ ድርጅትና ፎቶግራፍ አሻሻጭ ከመላ ሀገሪቱ ዳር እስከዳር ስልክ እየደወለ ባያስቸግርሽ ቱ! ከምላሴ ፀጉር ! »
«በቃ አዕምሮሀን እንደመንሳት እያደረገህ ነውኮ ውዴ!» ሆኖም የፒተር ግምት ሜሪ የገመተችውን ያህል ከእውነት የራቀ አልነበረም ። በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ከተለያዩ ሰዎች የስልክ ጥሪዎች ይመጡ ጀመር። ሰኞ ዕለት ከሎስ አንጀለስ እና ከችካጐ የተለያዩ ጥሪዎች ደረሷት ። እያንዳንዱ ሰው ስልክ ደውሎ የሚያቀርብላት ጥያቄና አድናቆት አስደነቃትም ። አስደሰታትም ። ስለዚህም ስልክ በተደወለ ቁጥር አሁን ደግሞ ምን ይሉ ይሆን ? በሚል ጉጉት ስልኩን ታነሣለች ። ይህ ቀጠለ ፤ ቤን አቭሪ እስኪደውልላት ድረስ ።

ቤን አቭሪ የደወለው አንድ ማክሰኞ ቀን ወደ ማታ አካባቢ ነበር ። በዚያም ሰዓት ሜሪ ፊልሞችን ለማሳደግና ለማጣብ በማሰናዳት ላይ ነበረች ። ከተለያዩ ቦታዎች ፎቶግራፎቿን ለመግዛት የትእዛዝ ጐርፍ መጉረፍ ጀምሮ ስለነበር ከፎቶግራፍ ማጠቢያው ክፍል (ዳርክ ሩም) ለመውጣት እንኳ ጊዜ አነበራትም ። በሥራዋ ተመስጣ እያለች ስልኩ ተንጫረረ። ሥራዋን አቋርጣ እየተጣደፈች ወጣች ። ምክንያቱም ፒተር «በዚያ ሰዓት ስብሰባ ስላለብኝ ደውዬ የት እንደምንገናኝ እነግርሻለሁ » ብሏት ነበር ። ስልኩን አንሥታ «ሃሎ » አለች ። «ሚስ አዳምሰን» አለ አንድ የማታውቀው ድምጽ፡፡ «ነኝ» አለች ፒተር ስለመሰላት በገጽታዋ ላይ ፈክቶ የነበረው ፈገግታዋ እየጨለመ ። «አኦ.. ከዚህ በፊት ለገና በዓል የስጦታ ዕቃዎችን ስገዛ ሚስ አዳምሰን ከምትባል ሰው ጋር ተዋውቀን ነበር ። ከሞክሼሽ ጋር ይሁን ካንቺ ጋር እርግጠኛ አይደለሁም ። የጉዞ ሻንጣዎች ስገዛ ተገናኝተን... » ቤን ነው ማለት ነው ። አይደለሁም ልበለው? ለምን?
« ከኔ ጋር ሳይሆን አልቀረም » አለች…. መዋሸት የሚያስፈልግ አልመሰላትም ። «ማለቴ ...እኔ.. ነው ? ማለት የማውቃት ሚስ አዳምሰን ነሻ ? »
«ነኝ»
« ይህንን ማረጋገጡም አንድ ነገር ነው ። ማለት ተቀራርበን ለመነጋገር ባንችልም እንተዋወቃለን ። ብቻ አሁን የደወልኩልሽ እንኳ የያኔ ትውውቃችንን በሚመለከት አይደለም ። የፎቶግራፍሽን ኤግዚብሽን ስላየሁ አንዳንድ ነገር እንድንነጋገር ስለፈለኩ ነው ።. ...ግሩም የሆነ ሥራ ነው ሚስ አዳምሰን ። እኔም ጓደኛዬ ሚስ ታውንሴንድም ኤግዚብሽኑን ዓይተን የተሰማን ስሜት ከፍተኛ ነው » የጠራት ሴት ዕቃው የተገዛላት ሴት ትሆን ? የማወቅ ፍላጐት አደረባት ። ሆኖም መጠየቅና ማወቁ አስፈላጊ መስሎ አልተሰማትም ። ስለዚህም በረጂሙ ተንፍሳ…. «ደስ ስለተሰኛችሁ እኔም ደስ ብሎኛል ፤ ሚስተር አቭሪ›› አለች ።
« ስሜንም አልረሳሽም?»
«ስሞችና የመሳሰሉ ነገሮችን አልረሳም ። አንድ ዓይነት እነዚህን ነገሮች የማያስረሳ ተፈጥሮ አለኝ »
«መታደል ነው ። እኔ ደሞ የስም ነገር አይሳካልኝም ። ይኽ ደሞ ለሥራዬ ጥሩ ነገር አይደለም። አንጐሌ ወንፊት ቢጤ ሆኖ ሲፈጠር ጊዜ ምን ማድረግ ይቻለኛል ! ወደ ፍሬ ነገሩ ልመለስና ተገናኝተን ስለሥራዎችሽ ብንነጋገር በጣም ደስ ይለኝ ነበር ።»
« በምን መንገድ ? » አለች ። ምን የሚያነጋግረን ነገር ተፈጠረ ደግሞ ! አለች በሐሳቧ ። «እንዲህ ነው ሚስ አዳምሰን ። እዚህ ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ አንድ የሕክምና ማዕከል ሕንፃ በመሥራት ላይ እንገኛለን ። በጣም ግዙፍ የሆነ ፕሮጄክት ነው ። ፕሮጀክቱን ስንቀበል ከገባናቸው ውሎች አንዱ ሕንፃውን እስከማስዋብ ያለውን ሥራ ፈጽመን ማስረከብ እንዳለብን ይገልጸል ። ያንችን ፎቶግራፎች ስመለከት ለዚህ ተግባር በጣም ሊያገለግሉን እንደሚችሉ ተረድቻለሁ ። እንዴት አድርገን በምን ሁኔታ እንደምንጠቀምባቸው ግልጽ የሆነልን ነገር የለም ። ስለዚህም ተገናኝተን ይህንን ጭምር ብንወያይበት ደህና ገቢም ይኖረዋል ። ላንቺም ቢሆን ሥራሽን ያስተዋውቅልሻል» አለ ቤን ። ይህን ሲናገር በሙሉ ልቡ እንደነበረ ድምጹ ይናገራል፡፡ «ገባኝ።. . . ግን የትኛውን ድርጅት ወክለህ እንዳነጋገርከኝ ልትነግረኝ ትፈቅዳለህ ? » አለች ። ድርጅቱ ማን ሊሆን እንዶሚችል ስለጠረጠረች ፤ ከላይ ከላይ ሊላት ያሰበውን ትንፋሷን ቁጥር አድርጋ መጠባበቅ ጀመረች ።
«ድርጅቱ» አለ ቤን ኮራ ብሎ «የኒውዮርኩ ኮተር ሂልያርድ ነው»
«ነው... ስላሰብክልኝ አመሰግናለሁ።፤ ሚስተር አቭሪ ግን አይሆነኝም »
«አይሆነኝም ? ለምን ?» አለ የመደመም በሆነ ድምጽ
👍14
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ (30)

የጨለማውን ክፍል በር ከፍታ ገብታ መልሳ ልትዘጋው ስትል ስልኩ የጥሪ ድምጽ አሰማ። ቤን አቭሪ መሆን አለበት እንደገና የደወለው። ተናደደችና በሩን በርግዳ ወጥታ ወደ ስልኩ ሄደች። መነጋገሪያውን መንጭቃ ካነሳች በኋላ «አይሆንም ማለት አይሆንም ነው ! መልሴ አንድ ነው። ይኸን ደግሞ ቁርጥ ባለ ቃል ነግሬሃለሁ» ስትል ጮኸች፡፡ ‹‹የፈጣሪ ያለህ ምነው ምን አጠፋሁ?» አለ ለስላሳውና ልቧን የሚያበራው የፒተር ድምጽ። የፒተርን ከፊል ሳቅ ያፈነው ከፊል ድንጋጤ የበረዘው ድምጽ ስትሰማ ንዴቷ ባንዴ ቀዘቀዘ። አዕምሮዋም ርጋታን ተላበሰ። «ፒተር! አስደነገጥኩህ አደል ? ይቅርታ ። አንድ ሰው ስልክ ደውሎ የማይሆን የማይሆን ነገር ነግሮኝ አይሆንም ብዬው ነበር። እሱ መልሶ የደወለ መስሎኝኮ ነው»
«የፎቶ ግራፍ ትርኢቱን በሚመለከት ነው?»
‹‹አዎ ወደዚያው ነው»
«የአዳራሹ አስተዳደር የስልክ ቁጥርሽን ለማንም መስጠት አልነበረበትም። መልዕክት ተቀብለው ላንቺ መንገር ነበረባቸው። ያለዚያ የማንም ቦዘኔ እየተነሳ ያልሆነ ነገር ሊያደርግ ይችላል» ። የተበሳጨ መስሎ ተሰማት ። ‹‹ግን ደህና ነሽ አደለም ? »
«ደህና ነኝ» ይሀን ስትል መረሽዋን በድምጺ ስለተረዳ ደህና ነኝ ያለችውን አላመነም ። «ደግ መጣሁ ከአንድ ሰዓት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ እደርሳለሁ ። እስከዚያ ድረስ ማንም ቢደውል ስልክ ማንሳት የለም ከዚያ በኋላ የሚደውለውን ሰው እኔ እንደሚሆን አደርገዋለሁ»

ሌሎች የንግግር ልውውጦች ካደረጉ በኋላ ስልኩን ዘጋች ። ግን እንደደወለና ምን እንዳበሳጫት ለፒተር አለመንገሯን ስታስበው ጥፋት እንደሠራች ተሰማት ። ፒተር ያሰበው ቦዘኔ ቀውስ እንዳስቸገራት ነው። ቤን አቭሪ ግን ሁለቱንም አይደለም ። የሱ ጥፋት ፤ የወረወራትና የናቃት የማይክል ሂልያርድ ሰራተኛ መሆኑ ብቻ ነው ። በሌላ በኩል ደግሞ ይሀን ጉዳይ ለፒተር መንገርም ጥሩ እንዳልሆነ ገመተች ። የለም ጥሩ አይደለም አለች በሐሳቧ ። ይህን ጉዳይ ብትነግረው ፒተር ይበልጥ ይጨነቃል ።

የማይክል ነገር እስካሁን ከልቡናዋ አልወጣም ። በጣም ጠልቆ በመግባቱም እስከመቼም ላይወጣላት ይችላል ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል ። ጥቅም የለውም ብላ ተወችው ። ያን ዕለት ቤን አቭሬ ደግሞ አልደወለም ። ይህም ተመስገን የሚያሰኝ ነበር ። ፒተር መጥቶ ከሱ ጋር ስትጨዋወት ችግሩም መሸበሩም ቀስ በቀስ ከሜሪ አዕምሮ እየደበዘዘና እየጠፋ ሄደ። ግን አልቀጠለም… በማግስቱ ጠዋት ቤን አቭሪ ደግሞ ደወለ «ሃይ ሚስ አዳምሰን ። ቤን አቭሪ ነኝ»
«ስማ ፤ ትናንት ማታ ሁሉን ነገር ተነጋግረን የጨረስን መሰለኝ ። ይሆንሻል ያልከው ሥራ አይሆነኝም፣አይስማማኝም አልኩህ በቃ፡፡»
«ግራ የገባኝኮ አልፈልግም አልሽ እንጄ ምን እንደማትፈልጊ እንኳ ያወቅሽ አይመስለኝም ። ከእኔና ከጓደኛዬ ጋር ምሳ እየበላን ለምን አንነጋገርም አይተሽኛል ሰው ነኝ ።አልበላሽ ! መነጋገር ደግሞ ምንም ጉዳት የለውም ። ወይስ መነጋገሩም ሊጐዳ ይችል ይሆን ?» ይችላል ቤን በጣም ሊጐዳ ይችላል ! አንተ አጠገብ መሆን ብዙ የተደበቀ ትዝታ ጐትቶ ያመጣል… በሐሳቧ ። «አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ ። ግን አይመቸኝም ። ሥራ ይበዛብኛል» አለች ። ሌላ መንገድ ቢሞክር ፍንክች ሳትል ቀረች ተስፋ የሌለው ነገር ነው በሚል መንገድ ዓይኑን አፍጦ እያንከባለለ ዌንዲ ታውንሴንድን ተመለከታት ። ኮተር ሂልያርድ ትልቅ ድርጅት ነው ። እንደ ሜሪ ያለች ሰውን ለማስቀየም አይችልም፡፡ ይኸ ግን በቀጥታ ከድርጅቱ ጋር ጠብ ያላት ይመስላል። ምን በደል ደረሰባት ኮተር ሂልያርድን ለምን ጠላችው ?
«ነገስ አይመችሽም ?»
«ስማ... ቤን... ሚስተር አቭሪ መቼም አይመቸኝም። ፍላጐቱም የለኝም ። ፍላጐቱ ከሌለኝ ምንም የምንነጋገርበት ነገር የለም። አሁን ነገሬ ግልጽ ነው ?»
«የምሥራች የሚባልለት አይደለም እንጂ ግልጽስ ነው» አለ።
ጸጥታ…
«ግን» አለ ቤን «ግን ትልቅ የሙያ ስህተት የሠራሽ ይመስለኛል። ጉዳይ አስፈጻሚ ወይም ወኪል ካለሽ ብታማክሪው ይህን እኔ የነገርኩሽን ነገር ደግሞ ይነግርሻል»
«ነበር ግን ወኪል ወይም ነገረ ፈጅ የለኝም ። ስለዚህም አይለኝም ። ወኪል የማያስፈልገኝ ደግሞ ከራሴ ሌላ ማንንም መስማት ስለሌለብኝ ነው»
«ከስህተቶችሽ አንዱ ይህ አስተሳሰብ መሆን አለበት በነገር ባንራራቅ ደግ ነው»
«ስላሰብክልኝ አመሰግናለሁ ። ምክንያቱም ለሌላ ሰው ማሰብ ቅንነት ነው ። ግን እንድትቸገር አያሻም ። እና እንደገና ባንደዋወል ይመረጣል»

••••••

ቤን አቭሪ ከምድር ውስጥ ባቡር ጣቢያ ወጥቶ በፓርክ አቬንዩ ወደሚገኘው ቢሮው የሚወስደውን መንገድ በእግሩ ሲፈጭ የፌብሩዋሪን (የካቲት) ቅዝቃዜ በመፍራት ኤሊ እድንጋዩዋ ውስጥ ተሰብስባ እንደምትገባ እሱ ደግሞ እካፖርቱ ውስጥ ለመደበቅ አንገቱ ትከሻውን እስኪነካ በመሰብሰብ ነበር ። ዝናብ ሊጥል አጓግቶ እንደመጣ ከአየሩ ሁኔታ ተረዳ ። ገና ለሁለት ሰዓት ጥቂት ደቂቃ ጉዳይ ቢሆንም ቸኩሏል ። የሥራ መግቢያ ሰዓት ማለትም ሦስት እስኪሞላ ሊጠብቅ አይችልም ። ብዙ ሥራ ይጠብቀዋል ። ከሳንፍራንሲስኮ የተመለሰው ትናንት ሲሆን ከኮተር ሂልያርድ ሥራ አስኪያጅ ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር አራት ሰዓት ላይ ስብሰባ እንደሚኖረው ተነግሮታል ። መልካም ነገር ይዞላት እንደሚቀርብም ይተማመናል ።

በመሥሪያ ቤቱ ማረፊያ ክፍል ውስጥ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል ። አሳንሰሮችም ጥቅጥቅ እያሉ በመሙላት ሰዎችን ወደየቢሮአቸው ማጓጓዝ ቀጥለዋል ። ገና ጥዋት ቢሆንም የንግድ ሥራው ዓለም መተራመሱን ጀምሯል ። ሕይወት ረጋ ብላ በምትፈስበት ሳንፍራንሲስኮ ቆይቶ የንግድ ዓቢይ ፈለግ ወደሆነችው ኒው ዮርክ ሲመለስ የዚችን ከተማ ትርምስ ለሚያውቃት ቤን አቭሪ እንኳ አስደንጋጭ ሆነበት ። የሱ ቢሮ ከሚገኝበት ፎቅ ደርሶ ሲመለከት ቀድሞት የገባና ሥራ የጀመረ ሰው አልነበረም ። ቢሮው ምንም እንኳ የማይክል ሂልያርድን ቢሮ ያህል የሰፋና እንደ ማይክል ቢሮም በልዩ ምርጫ የተሰናዳ ዕቃ ባይኖረውም ምቹና ያሸበረቀም ነው፡፡ ማርዮን ሂልያርድ ለኮተር ሂልያርድ ቢሮዎች ምቾትን ለመስጠት በወጭው ላይ ወደኋላ የማትል ሥራ አስኪያጅ ናት ። ካፖርቱን ካወለቀና ሰውነቱን ለማሟሟቅ ከመዳፍ ለመዳፍ ማፋጨት እስከወገብ እንቅስቃሴ ያለውን ከፈጸመ በኋላ ስለሥራው ማሰብ ጀመረ ። ሆኖም የኒውዮርክ የዝናብ ወቅት ብርድ ከሰውነቱ ሙልጭ ብሎ አልወጣም ። ቢሮው ራሱ በረዶ የተጋገረበት ያህል ቀዝቃዛ ነበር፣ መጋረጃውም ወፍራም ሕንፃውም ሙቀትን አፍኖ ለማቆየት የሚችል ሆኖ ቢሠራም እንኳ ግን ብርድ አለ ብሎ አርፎ መቀመጥ አይችልም ። የተለያዩ ጉዳዮችን የያዙ ወረቀቶችን ከቦርሳው እያወጣ እጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ ተመሳሳይ ጉዳይ ያላቸውን አንድ ላይ ማድረግ ጀመረ ።

ስለተልዕኮው አሰበ ። ሁሉም ነገር ቀና መንገድ ይዟል ። ከአንድ አነስተኛ ነገር በስተቀር ። ያ ደግሞ የሚስተካከልበት መንገድ ይገኝለት ይሆናል ። ሰዓቱን ተመለከተ ። ይሁን አይሁን የሚል ጥያቄ መጣበት ። ቢሳካም ባይሳካም አንዴ መሞከር እንዳለበት ወሰነ ። ያን ያስቸገረውን ጉዳይ አንድ መልካም እልባት ላይ አድርሶ ስብሰባውን ቢካፈል ደስ ይለው ነበር ። ቤን አቭሪ ከሜሪ አዳምሰን የፎቶግራፍ ሥራዎች ጥቂቱን ይዞ መጥቷል ። ሜሪ እነዚያን ፎቶግራፎች እንዳልሰጠችው ግልጽ ነው ። በቀጥታ ከሷ ሳይሆን ከኤግዚቢሽኑ ቦታ ነበር የገዛው ። የፎቶግራፎቹ ዋጋ ደግሞ የሆነውን ቢሆን የባከነ ገንዘብ እንደማይሆን
👍25
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አንድ (31)

ያን ድምጽ ከዚህ በፊት ሰምቶታል ? የት? ሊያስታውሰው አልቻለም ። ግን ደግሞ ያ ድምጽ አዲስ አይደለም ። እንዲያውም የአንዲት በቅርብ የሚያውቃት ሴት ድምጽ እንደሆነ ይሰማዋል። የማንን ድምጽ ነው የሚመስለው ? አሰበ ። አሰበ… ሊያስታውስ አልቻለም « ልልሀ የፈለኩትን ነገር ገና ልትረዳልኝ አልቻልክም ይሆን በሥላሴ ? › እኒህ በቁጣ የጠነከሩ ቃላት ከፍለጋው መለሱት። ወደ አሁን አመጡት ። ከሜሪ አዳምሰን ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው ። እውነቱን እንዲያይ ፤ ይህቺ ሜሪ እንጂ ማንም እንዳይደለች እንዲረዳ አደረጉት ። ባኛል ሆኖም ተስፋ ያደረግኩት »
«ተስፋ ዝባዝንኬ!... ነገርኩህ'ኮ አልፈልግም አልኩህ ፤ በዚሀ ነገር ላይ ለመነጋገር ይህን ነገር አውጥቶ አውርዶ ለማሰብ ወይም ለኔ ምኔም ስላልሆነው የሳንፍራንሲስኮ የሕክምና ማዕከል አንዲት ቃል ለመነጋገር አልፈልግም ። በሥላሴ ይዤሃለሁ ፤ ተወኝ » ይህን ተናግራ እጆሮው ላይ ደረገመችበት ። የተዘጋውን ስልክ ማነጋገሪያ በእጁ ይዞ የጅል ፈገግታ ፈገገ ። ከዚያም «ይኸው አፈነዳሁትና አረፍኩ ወንድሞቼ» አለ ።

ቤን ይህን የተናገረው ለራሱ ነበር ። በሐሳብ ስለተዋጠ የቢሮውን በር ከፍቶ መቃኑን በመዝናናት ደገፍ ብሎ የቆመው ማይክልን አላየውም ። «እንኳን ደህና መጣህ ። ለመሆኑ ምንድነው ያፈነዳኸው ?» ማይክ ይህን ጥያቄ የጠየቀው ይህን ያህል ለማወቅ በመጓጓት አልነበረም ። የጓደኛው መመለስ እንዳስደሰተው ብቻ ነበር ገጽታው የሚገልጸው ። በፊቱ ላይ ደስታው እንደጐላ ወደ ቤን ቢሮ ገብቶ በምቹው የእንግዳ መቀበያ ሶፋ ላይ ቁጭ አለ። «ከጉዞሀ ተመልሰህ ሳይህ ደስ አለኝ»
«መመለሱስ አይከፋም ነበር ። ግን ምን ዋጋ አለው ? የሳንራንሲስኮን አየር ተለማምደህ መጥተህ የኒውዮርክን ብርድ ፍጹም ሰውነትህ አይቀበለውም»
«ለስላሳው ፍጡር ሆይ ካሁን ጀምሮ ከሞቃታማዎቹ የደቡባዊ ክፍሎች እንዳትወጣ የተቻለንን ያህል እንሞክራለን» አለ በጸሎት ድምጽ ።። ከዚያ ቀጠል አድርጐ «የስልኩ ጭቅጭቅ ስለምን ነበር ?» ሲል ጠየቀው ። «እሱን አታንሳው ። በዚህ የሥራ ጉብኝት ውስጥ እሾርባዬ ውስጥ ያጋጠመኝ አንድና አስቸጋሪ የሆነ ፀጉር ! » አለ።«ማለት ሁሉ ነገር እንደከረከሙት ሁሉ እየተስተካከለ ሲመጣ… እንዳሰብነው ፣ እንደፈለግነው ሲሆን . . . ርግጠኛ ነኝ ሪፖርቱ ሲቀርብ እናትህ ተፍነክንካም አታበቃ… አንድ ነገር ግን አሻፈረኝ አለ። ርግጥ ነው ፤ አልሳካ ያለው ነገር ይህን ያህል ትልቅ ችግር የሚባል አይደለም ። የኔ ሃሳብ ግን ሙሉ ስኬትን ለመፍጠር ነበር ።»
«እንዴት ነው ፤ ነገሩ ምን ይሆን እያልኩ መጨነቅ ልጀምር ወይስ?»
«አያስፈልግም ። ተሸወድኩ ልበልህ…. እንዴት መሰለህ አንዲት አርቲስት አጋጠመችኝ። ፎቶ ግራፍ አንሺ ናት ። ማለቴ ግዙፍ ችሎታ ያላት ፍጡር…. ማይክ እንዲህ ተራ ነገር እንዳትመስልህ ። ኤግዚቢሽን ታሳይ ነበር ። ኤግዚቢሽኑን ተመለከትኩት። ባለፈው ጊዜ በሕንፃ ማስጌጡ ሥራ ላይ ፎቶግራፎችን መጠቀም እንደሚቻል ሰብሰባ ላይ የተስማማንበትን አስታወስኩ። ልቀጥራት ፈለግኩ »
« እሺ?»
« ነገርኳት ››
«‹ መልሷ!? »
«አንገቴ ይቆረጣልንጂ ያንተን ስራ አልነካውም አለችኝ ። እንነጋገርበት አልኳት ። አይሞከርም አለች »
«ምን ምክንያት ሰጠችህ?... የኪነጥበብ ስራዬን ለገንዘብና ለንግድ አላውልም ነው ወይስ ሌላ ?»
«ምኑም ምኑ ሊገባኝ አልቻለም። ገና ነገሩን ሀ ብዬ ሳነሳ ጅራቷን ሸጉጣ ወደ ኋላ ማፈግፈግ ጀመረች። ልታስጠጋኝ አልቻለችም» ማይክ ጅሎ በሚል አስተያየት እየተመለከተው ፣

«ነገሩ አይገባም አልክ? ግን ግልጽ ነው።» እምቢ ያለችህ በከንቱ አይምሰልህ ። ኮተር ሂልያርድ ምን ያህል ግዙፍ ድርጅት እንደሆነ ታውቃታለች ማለት ነው ። እምቢታዋ የሚታየው በርካታ ገንዘብ ይሰጥሻል እስክትባል ነው ። ለመሆኑ ይህን ያህል አሪፍ ናት?»
‹‹ተወዳዳሪ የላትም ስልህ ። ምን አለፋኝ እኔን ፤ ከፎቶግራፎችዋ ጥቂቶቹን ለናሙና ያህል ይዤ መጥቻለሁ አደል እንዴ ታያቸውና ራስህ ትፈርዳለህ »
«እንዲያ ከሆነ የፈለገችውን ማግኘት ትችላለች። የለም ፎቶግራፎቹን በኋላ እናያቸዋለን ። አሁን ለአንድ ጉዳይ ላነጋግርህ ፈልጌ ነው የመጣሁት » ማይክል ይህን ሲል በቁም ነገር ነበር። ነገሩን ለቤን ለመንገር ብዙ ጊዜ አስቦበታል ። «የሆነ ጥፋት ኣለ?»
«የለም… ምንም ጥፋት የለም ። እንዲያውም ይህን ጥያቄ ሳነሳብህ ምን ያህል አካባቢየን ማየት የማልችል አጋሰስ ነኝ የሚል ስሜት እየተሰማኝ ነው። ሆኖም ደህና ማለት ከዌንዲ ጋር የሆነ ግንኙነት ፈጥራችኋል?»

ለዚህ ጥያቄ መልስ ከመስጠቱ በፊት ቤን አቭሪ የማይክልን ፊት በደንብ አድርጎ መመልክት ጀመረ ። ማይክል የማወቅ ፍላጐት ያደረበት እንጂ ፈጽሞም የተቀየመ አይመስልም። ርግጥ ነው ቤን ስለማይክልና ስለዊንዲ ግንኙነት በሚገባ ያውቃል ። ግን ደግሞ ማይክል ለዌንዲ ደንታ እንዳልነበረውም ያደባባይ ምስጢር ነው። ቢሆንም አሁን ሲያስበው ፤ በተለይም ከማይክል ጋር ከዚህ በፊት በዚህ ዓይነት ተገጣጥመው ስለማያውቁ እና ማይክ ይህ መሆኑን ሲገነዘብ የሚሰማውን ስሜት መረዳት ስላዳገተው ቤን አቭሪ ተጨነቀ ። ጓደኛው የቀመሳትን ፤ ቢተዋትም የሱ የነበረችን ሴት መውሰድ መልካም እንዳይደለ ገባው። ያም ሆነ ይህ እውነቱ እውነት ነው። ዌንዲና ቤን ይፋቀራሉ። ስራቸው አንድ ላይ በመሆኑም አንድ ላይ ይጓዛሉ ። ባለፉት ወራት በሳንፍራንሲስኮና በሎስ አንጀለስ ሲሰሩ ባልና ሚስት ሆነው ነው ያሳለፉት ። እንዲያውም ቤን የጫጉላ ቤታችንን ጊዜ በማሳለፍ ላይ እንገኛለን እያለ ሲቀልድባት ነበር ። « አልመለስክልኝምኮ » አለ ማይክል ። ቤን አቭሪ ከሃሳቡ ብትት ብሎ ነቃ ። «አስቀድሜ ባለመንገሬ ጅልነቴ ተሰማኝ ። መልሱ ግን ፤ እዎ ነው ። ቅር ይልሃል ማይክ !?»
👍13
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ሁለት (32)


ለሷ ማይክል ሂልያርድ የሚባል ሰው የለም፤ ስትፈልገው ሲሸሻት በስጋ አብሯት ተቀምጦ እንኳ በመንፈሱ ሲርቃት ምን ያህል እንዳቆሰላት የታወቀ ነው ። የለም አብርው ሆነው የሚያውቁም አይመስላትም ።
«እንሂዳ ። ያላዘጋጀኸው ነገር አለ ንዴ?»
« በቂ ያህል የተዘጋጀሁ ይመስለኛል »
« ደህና »
«በነገራችን ላይ ለሜሪ አዳምሰን ፎቶግራፍ አንሺዋ ደውየላት ነበር »
« ምን አለች ? »
« ሰውዬ ባትጨቀጭቀኝ ምናለ ! አለችኝ »
« የሚገርም ነገር ነው»


በስብሰባዋ ላይ ማሪዮን ሂልያርድ ከየክፍሉና ከየፕሮጀክቶቹ የመጡትን ሠራተኞች ተራ በተራ እንዲናገሩ የክፍሉን ወይም የፕሮጀክቱን ስም እየጠራች ትጠይቅ ጀመር ። የተከናወኑ ስራዎች ባለፈው ስብሰባ ላይ የቀረቡ ችግሮችና የተሰጣቸው መፍትሔ ባሁኑ የሥራ ክንዋኔ ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ሁሉም ለስብሰባው ይልቁንም ለማሪዮ ከቀረቡ በኋላ በቂ መመሪያዎችና መፍትሔዎች ተሰጡ ። የሳንፍራንሲስኮ የህክምና ማዕከል ፕሮጀክትን በሚመለከት ቤን አቭሪና ዌንዲ እየተቀባበሉና እየተረዳዱ ራፖራቸውን አቀረቡ። ራፖሩን አቅርበው እንደጨረሱ የማሪዮን ፊት በደስታ ፈካ። በተለይም የዚህ የሳንፍራንሲስኮ ፕሮጀክት ዋና ኃላፊ ልጅዋ ማይክል ሂልያርድ በመሆኑ በዚያ ስብሰባ ላይ ከቀረቡትመ የሥራ አፈፃጸም ሪፖርቶች ሁሉ ይህ የሳንፍራንሲስኮው ፕሮጀክት ከፍተኛ ክንዋኔ እንዳደረገ ስለተረዳችና ይህም ማይክል ሂልያርድ ጠንካራ ሠራተኛና የሥራ መሪ መሆኑን ስላስገነዘባት የማርዮን ደስታ እጥፍ ድርብ ነበር። ምክንያቱም ይህ ኮተር ሂሊያርድ የተባለ ድርጅት ዞሮ ዞሮ በማይክል እጅ መግባቱ አይቀርም ። የኮተር ሂልያርድን ዋና ሥራ አስኪያጅነት ዙፋን ከመውረስ የሚተናነስ አይደለም ። የኮተር ሂልያርድ ግዝፈት ደግሞ በእድል የተገነባ ወይም ድንገት የሆነ ሳይሆን በጠንካራ ሰዎች የሌት ተቀን ጥረት ፤ ግረትና ብርታት የተገኘ ነው ። ማሪዮን ኮተር ሂልያርድን ለማስተዳደር ምን ያህል ኃይልና ፈቃደኛነት መስዋእትነትች እንደሚያስፈልግ ታውቃለች ። ማይክል ስራውን በሚገባ ሲያከናውን የተደሰተችውም ያን ጠንካራ ሰው ወልዳ ኮትኩታ አሳድጋ ስታየው ያሰበችው ሁሉ እንደሚሳካላት ስላወቀች ነው ።

«ሁሉ በወግ በወጉ ሲከናወን አንድ ትንሽ ነገር ብቻ ረበሸኝ» አሊ ቤን አቭሪ ። በማሪዮን የገረጣ ፊት ክንብል ብሎ የነበረው ቅላት ቀነሰ። ደም የመሰለው ጉንጯ ወደ ቀድሞ መልኩ ተመለሰ ። ይህን ሲያዩ በዚያ ክፍል ውስጥ የተሰበሰቡ ሁሉ ትንፋሻቸው መለስ አለ። በተለይም የቤን አቭሪ ። ስለሰአሊዋ ነገራት ።
«ይኸን ያህል ታስፈልገናለች? »
«በኔ ግምት በጣም ታስፈልገናለች ለናሙና ካነሳቻቸው ጥቂት ፎቶግራፎች ይዤ መጥቻለሁ ።»
«አላነጋግርህም አለችኝ እያልክ አልነበረም ? ታዲያ ፎቶግራፎቹን እንዴት ልትሰጥህ ቻለች?»
«እሷ ሰጥታኝ ሳይሆን ከትርኢት አዳራሽ ገዝቼ ነው ። የወጣው ገንዘብ በትክክል የወጣ ይመስለኛል ። ሆኖም ድርጅቱ ገንዘቡ የወጣበት ምክንያት በቂ አይደለም የሚል ከሆነ ገንዘቡን ከፍየ ፎቶግራፎቹን የግል ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ »
«እስኪ እንያቸው » ዌንዲ ፎቶግራፎቹዋን አመጣች ፤ ፎቶግራፎቹ ታዩ ። በጭብጥም በጊዜና በቦታ አመራረጥም የተዋጡ ነበሩ ። በፎቶግራፎቹ ላይ ዝብርቅርቅ ነገር አልነበረም ። ሌላ ሰው ቢያነሳቸው ወይ ጊዜውን ስላልጠበቀ ወይ በቦታው ላይ የሰፈሩ ነገሮች ተስማሚ ባለመሆናቸው የተነሳ ሊበላሽ ይችል ነበር ይሆን ? የሚያሰኙ ፎቶግራፎች ነበሩ ።

ማሪዮን ፎቶ ግራፎቹን በጥሞና ከተመለከተች በኋላ ቀና ብላ ቤንን ተመለከተችው ። ቤን ዝም አለ ። ቆይታ ፤ «እንዳልከው እንደምንም ልናግባባትና ልናስራት ይገባል›› አለች ። «ስለተስማማን ደስ አለኝ » አለ ቤን፡፡ «ማይክ ? » አለች ማሪዮን ሂልያርድ «ምን ይመስልሃል ?›› ማይክል ፎቶግራፎቹን ሲመለከት አንድ ዓይነት ስሜት ተሰማው ። የሚያስደነግጥ ። ወደ ኋላ የሚመልስ ስሜት ። የት እንዳየሁት እንጃ ግን አውቀዋለሁ የሚያሰኝ ስሜት በውስጡ ይመላለስ ጀምር ። ልቡን ቁልቁል ሳበው ። ጭብጣቸው ነው? ወይስ የሚነሳውን ነገር አመራረጥ ? ምኑን ነው የሚያውቀው ? ይህን ጥያቄ ሊመልስ ፈለገ ። ግን አልቻለም ። ፎቶግራፎቹን አትኩሮ በተመለከተ ቁጥር አእምሮው ላይ ጫና እየወደቀበት ሄደ። ፎቶ ግራፎቹ ጥበባዊ ኃይል እንዳላቸውም ተገነዘበ ። ስለዚህም ፤ «በጣም ድንቅ የጥበብ ሥራዎች ናቸው» አለ ። «እኔ ግሩም የጥበብ ሥራዎች ናቸው ብያለሁ ። ያን ያሀል ትልቅ ናቸው ነው እምትለኝ?» አለች ማሪዮን ፍርጥ አድርጐ እንዲነግራት እየገፋፋችው ። በቃላት ሳይሆን አንገቱን በአዎንታ ፅሙና በመነቅነቅ መለሰላት ። «ታዲያ ይችን ሴት በምን ሁኔታ ነው የኛ ልናደርጋት የምንችለው?» አለች ማሪዮን ፤«ቤን ምን ይመስልሃል?»
«የዚህን ጥያቄ መልስ ባውቀው እንዴት ደስ ባለኝ ነበር» አለ ቤን ። «ገንዘብ ነው መንገዱ ። ይህ ግልፅ የሆነ ነገር ነው» አለች ማሪዮን ። ለመሆኑ ሁኔታዋ እንደምንድነው ? ተገናኝታችሁ አይተሃታል?።»
«አይቻታለሁ። ማለት ይኸ ሁሉ ነገር ሳይሆን የገና በአል ከመዋሉ በፊት አንዳንድ የስጦታ እቃዎችን ስገዛ ድንገት ተገናኝተን ተነጋግረናል ። በጣም ቆንጆ ናት ። ማለት ቁንጅና እንዲህ እንደማንም ቁንጅና አይደለም ። እንከን አይወጣላትም ።ሙሉ በሙሉ ቆንጆ ። ደስ ባላት ቀን ከሆነ ማንንም ሰው ይሁን ልታናግረው፤ ልታጫውተው ፈቃደኛ ናት ። መልካም ሙያም አድሏታል፡፡ ቀደም ሲል ሰአሊ ነበረች የሚል ወሬ ሰምቻለሁ። የምትለብሳቸው ልብሶች በጥራትም በዋጋም በቀላል የሚገመቱ አይደሉም ። ችግር ያለበት አይመስለኝም ።

«የኤግዚቢሽን አዳራሹ ባለቤት እንደነገረኝ ከሆነ ወኪል ነገር አለት መሰለኝ ። አንድ በእድሜ ጠና ያለ ሀኪም ፤የታወቀ የቆዳ ቀዶ ጥገና (ፕላስቲክ ሰርጄሪ) ሀኪም ነው አሉ ። ብቻ በዚያም ተባለ በዚህ ያቀረብንላትን ጥያቄ ያልተቀበለችው ገንዘብ ለማስጨመር ብላ አይመስለኝም ። . . . የማውቀው ይህን ያህል ነው» አለ ቤን ። «ገንዘብ ካልሆነ ምን ?» አለች ማሪዮን ። ወዲያው አንድ ቀዥቃዣ ሃሳብ አእምሮዋ ውስጥ ተወራጨባት ። ደነገጠች ። የለም የለም ጭራሽ የማይሆን ቅዥት ነው አለች በሃሳቧ ። ግን ምኑ ይታወቃል ? እድሜዋ ምን ያህል ይሆናል ?» አለች ቤንን እየተመለከተች። «እንጃ ። ያኔ ከገና በፊት የተገናኘን እለት ዘርፈፍ ያለ ባርኔጣ ነበር ያደረገችው ። ፊቷን ክልሏት ስለነበር በደንብ አላየኋትም መሰለኝ ። ብቻ ከሃያ አራት ከሃያ አምስት ግፋ ቢል ከሃያ ስድስት ዓመት የሚበልጣት አይመስለኝም። ግን እድሜዋ ምን ያደርግልናል ?››

«እንዲሁ ነው ፤ ለማወቅ ያህል ። ይልቅ ስማኝ ቤን ። አንተና ዌንዲ የሚቻላችሁን ያህል ጥረት አድርጋችኋል። ድርጅቱ የሚፈልገውን ያህል ሰርታችኋል ። ልትመሰገኑ ይገባል ። ስለልጅቷም ቢሆን በናንተ በኩል ያለው አልቋል ። በሚቀጥለው ሣምንት ወደ ሳንፍራንሲስኮ መሄዴ ስለማይቀር እግረ መንገዴን ላነጋግራት እሞክራለሁ ። ምናልባት ከወጣቶች ይልቅ የአንዲት ባልቴት ነገር ሊከብዳት ይችላል››
👍21
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ሶስት (33)

‹‹እንግዲያውስ…. አንቺና ጆርጅ ተጋብታችሁ… ሥራውን ለቀሽ ማለት ነው፡፡ ለምን እየተደጋገፋችሁ ፤ ደስ እየተሰኛችሁ አትኖሩም ?! እግረ መንገዱን አዲስ አይነት ኑሮም ይሆንላችኋል » አለ ማይክ ። ማይክል ስለጆርጅ እና ስለ ማሪዮን ሂልያርድ ግንኙነት በግልፅ ሲናገር ይህ የመጀመሪያው ነበር ። ስለዚህ ጆርጅ ይህን ሲሰማ አፈረ ። ፊቱ ቀላ ። ሆኖም የመከፋት ስሜት አልታየበትም።
«ማይክል!» አለች ማሪዮን ። ያ ይህን አድርግ ፤ ይህን አታድርግ የሚለው ድምጽዋ እየተመለሰ «ማይክል እስበህ ተናገር። ሌላው ቢቀር ጆርጅን እስበው ። እንዴት እንዳስደነገጥከው ይታይሀል ? ያም ተባለ ይህ ሥራ ለመተው አልደረስኩም ። አመመኝም ቀረም ለመሥራት ጉልበት አላነሰኝም»
«እሱ እንዳልሽው ይሁን ፤እሺ ልበል። ምንም ማድረግ ልችልም። ግን ሥራ ቀንሺ። ማለት ለምሳሌ በሚቀጥለው ሳምንት ሳንፍራንሲስኮ መሄድሽ አስፈላጊ አይደለም ። እኔ ልሄድና ጉዳዩን ልፈፅም እችላለሁ ። እዚህ እዋናው መሥሪያ ቤት ቁጭ ብለሽ ይህን ያን አድርጉ ብትይን ልንረዳሽ እንችላለን ። በቃ፣ይህን ያህል እሺ በይኝ» ሳቀች እንጂ ሌላ መልስ አልሰጠችውም ። ከዚያም ብድግ ብላ ወደ መደበኛ የቢሮ መቀመጫዋ ሄደችና ተቀመጠች ። ስጋዋ እንደደከመ ይታያል ። መንፈሷ ግን ወደ ዱሮ ቦታው ተመልሷል ። ሁሉንም ካየች በኋላ ፡፡ «አሁን በከንፈር መጠጣና በአዘንልሽ አትጫኑኝ ። ሁላችሁም ማለቴ ነው ። ሂዱልኝ ። እናንተ ሥራ ከሌላችሁ… እንዲያ ይመስለኛል ሳያችሁ… እኔ ሥራ አለብኝ ፤ ልሥራበት»
«እማዬ ፤ ቤት አድርሼሽ ልምጣ።እስኪ አንዳንድ ቀን ሰው የሚልሽን እሺ በይ !» አለ ማይክል ቆጣና ኮረፍ ብሎ። «ማይክል የማይቻል ነገር አታውራ ። አሁን ቀጥ ብለህ ወደ ሥራህ ሂድ። ያለዚያ ጆርጅን እየገፈተርክ አስወጣልኝ እንዳልለው» ጆርጅ ፈገግ አለ… የነገሩ መታሰብ አስገርሞት ። «ባይሆን ሰዓት ደረሰ አልደረሰ ሳልል ለመሄድ እሞክራለሁ እንጄ አሁን አይሆንም ። በተረፈ ስለመልካም አስተሳሰብህና ስለሌላው እመሰግናለሁ ። በቃ ። ሩት ያን በር ክፈች» ጸሐፊዋ በሩን ከፍታ እንዲወጡ መጠባበቅ ጀመረች ። ማይክልና ቤን ወጡ ። ጆርጅ እደረጃው ላይ ቆሞ ፤
«ማሪዮን» አለ።
«እሀ»
«ወደ ቤት መሄድ አለብሽኮ »
«ትንሽ ቆየት ብዬ»
«ደግ። ከግማሽ ሰዓት በኋላ እመለሳለሁ» ወጣ። ፈገግ አለች ። ሆኖም ወደራሷ ሀሳብ ስትመለስ ገና በሩ አልተዘጋም ።

የዛሬው ህመሟ የተነሳበት ምክንያት በሚገባ ታውቋታል ። ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ አለባት ። በሌላው ሌላ ምክንያት እየተነሳ እረፍት አሳጥቷታል ህመሙ። ሌላ መነሻ ሲጨመር ዝም ብላ ማየት አትችልም ። ለምን እንደሆነ አይግባት እንጂ ቤን አቭሪ ስለሜሪ አዳምሰን ሲናገር ሜሪ ማን እንደሆነች አውቃለች ። በርግጥ ናንሲ ማክአሊስተር ናት ብላለች ። ቅድም እስብሰባው ላይ በግልጥ እንደተናገረችው ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትሄድ ሜሪን ለማየትም ፤ ለማነጋገርም ወስናለች ። ግን ታውቃት ይሆን? ምናልባት የተደረገላት የቀዶ ጥገና ህክምና (ፕላስቲክ ሰርጀሪ) ፈጽሞ ለውጧት ሊሆን ይችላል ። ያስ ባይሆን ናንሲን በሚገባ ታስታውሳታለች እንዴ ? አይታወቅም ። ቤን አቭሪ የሰጣትን የሜሪ አዳምሰን አድራሻ አውጥታ ስልክ ደወለች። ስልኩ ሶስቴ ይሁን አራቴ ሲጮህ ተሰማት ። ተነሳ። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አቅሏን ስታ ወድቃ የነበረችው ማሪዮን ሂልያርድ መሆኗን ማንም ሊያምን በማይችልበት ደረጃ ረጋ ባለና ስልጣን በተሞላበት ድምጽ፤ «ሚስ አዳምሰን ። ማሪዮን ሂልያርድ ነኝ ፤ ከኒወዮርክ » ስትል ተናገረች ።

ንግግራቸው በጣም አጭር ፤ ተዝቃዛና በመደነጋገር የተሞላ ነበር። ማሪዮን ሂልያርድ ስለሜሪ አዳምሰን በተጨማሪ ያገኘችው እውቀትም አልነበረም ። ይሁን ። ልክ የዛሬ ሶስት ሳምንት ማወቅ የሚገባትን ሁሉ ታውታለች ። ሊገናኙ ተቀጣጥረዋል ። ማሪዮን ቀጠሮውን አጀንዳዋ ላይ ካሰፈረች በኋላ የወንበሯን መከዳ ደገፍ ብላ ወደ ኋላዋ ተለጠጠች ። አይኖቿን ዘጋች ።

ከሜሪ አዳምሰን ጋር ከተገናኙም በኋላ ምንም ጠቃሚ ነገር ላታገኝ ትችላለች ። ሁሉም እንዳሰበችው ላይሆን ይችላል ። ወይም ሜሪ ምንም ነገር ላለመናገር ትወስን ይሆናል... ሆናም ያን ቀን ትፈልገዋለች ። ልትናገራቸው ያውጠነጠነቻቸው ጥቂት ነገሮች አሉ ። ብቻ. . . ብቻ ከዚያ ወዲህ ክፉ ነገር እንዳያጋጥማት። ትልቁ ምኞቷ ይህ ብቻ ነው።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ሶስት ሣምንት ሲደርስ አጭር ጊዜ ነው፡፡ ሲያስቡት ይርዘም እንጂ፤ የማሪዮን ሂልያርድና የሜሪ አዳምሰን ቀጠሮ ደረሰ ከሶስት ሣምንት በኋላ እለተ ሰሉስ ።

ማሪዮን ሂልያርድ ፌይርሞንት በተባለው ሆቴል በተከራየችው የልዩ ማዕረግ ማረፊያዋ ሳሎን ውስጥ ተቀምጣለች ። እዚያ ክፍል ውስጥ አረፍ ብሎ ወደ ውጭ ለተመለከተ ሰው ደንቅ የሆነው ወደብና ከዚያ አልፎ የሚገኘው የማሪን ካውንቲ ውበት በእጅጉ ያስደምመዋል ። ከሌላ ሀሳብም ያወጣዋል ። ማሪዮን ሂልያርድ ግን ይህን ትእይንት ለማየት ፍላጐት አልነበራትም ። ስለዚያች ልጅ በማሰብ ላይ ነበረች ። ምን ሆና ይሆን? ምን ትመስል ይሆን? ግሬግሰን (ፒተር) ከሁለት ዓመት በፊት ታምር አሳይሻለሁ ብሎ አንደፎከረ ተሳክቶለት ታምር በርቶ ይሆን? ቤን አቭሪ ሜሪ አዳምሰንን ሲያያት የሚያውቃት ሴት እንዳልሆነችበት ግልፅ ነው… ማይክልም ቢያያት አያስታውሳትም ይሆን? እሷስ እንዴት ነው ይሆን የምትኖረው ? ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅር ይዞአት ይሆን ወይስ እንደማይክል ሁሉን ነገር ትታ አንገቷን ደፍታ ውስጧ እየበገነ መኖር ቀጥላ ይሆን ? ማሪዮን ሂልያርድ የቀጠሮው ሰዓት እስኪደርስ ስለ ናንሲ ማክአሊስተር ስታስብ ልጅዋ በመሀል ገባ። እሱም ፍቅር ያውቅ ነበር ። አፍቅሮ ነበር ። እንዲያውም አሁን እምትጠብቀው ማይክል ሂልያርድ በጣም ይወዳት የነበረችዋን ልጅ ነው። ግን…. እሷ ባትሆንስ ? ካልሆነች . . . ካልሆነች ምንም ለውጥ አያመጣም። እሷ ካልሆነች አንዲት የዚሁ አካባቢ ተወላጅ የሆነች ፎቶ አንሺ ናት ማለት ነው ቤን አቭሪ አይኑን የጣለባት ፎቶግራፍ አንሺ። በቃ። ሊሆን ይችላል ። ያወጣሁት ያወረድኩት ፤ አስቤ የቀመርኩት ፤እውነት ብዬ ያሰብኩት ነገር ሁሉ መሰረተ ቢስ ፤ አጉል ሀሳብ ሊሆን ይችላል አለች በሀሳቧ።

ምናልባት. . . ምናልባት
👍17
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አራት (34)

«ምን… ከኔ ጋር ? አዎ» አለች ማሪዮን ። ሁለቱም ፀጥ አሉ፣ ረጂም ለመሰለ ጊዜ ። በመጨረሻ «እንተዋወቃለን ናንሲ ። ፒተርን አውቀዋለሁ ። ላንች ያደረገልሽ ህክምናም እጅግ የሚደነቅ ነው» አለች ማሪዮን ።
«ትንሽ ስህተት ሳይፈጠር አልቀረም መሰለኝ ። እኔ ናንሲ ሳልሆን ሜሪ…» ንግግሯን አልጨረሰችም ። ጉልበቷ ተሟጦ ሲወጣ ተሰማት፡፡ ባዶ ሆነች። አጥንት አልባ የሆነች ይመስል ተልፈሰፈሰች ። እንባ አነቃት ። እንደምንም ብላ ተነሳች ። ወደ መስኮቱ ሄዳ ጀርባዋን ለማሪዮን ሰጥታ ቆመች ። እና «ማን . . . እንዴት ልታውቂኝ ቻልሽ ?» አለች ። የተሰበረ ድምፅ ነበር ። ማሪዮን ርግጠኛ ሆነች ። የዛሬ ሁለት አመት የሰማችው የናንሲ ማክአሊስተር ድምፅ ብቅ አለ። «ማን ነገረሽ ? » አለች ሜሪ ደግማ በሚያስገድድ ድምፅ ። «ማንም አልነገረኝም ። ገመትኩ ። ግምቱ ለምን እንደመጣብኝም አላውቅም ። ሆኖም ገመትኩ ። ገና ቤን ስለሁኔታሽ መግለፅ ሲጀምር እሷ ናት? የሚል ጥያቄ መጣብኝ ። የነገረን ነገር ሁሉ ስለአንቺ ከማውቀው ጋር ሙሉ በሙሉ ሲመሳሰል ጊዜ ነው መሰል »
«እንዲያ ከሆነ ... » አለችና ዝም አለች፡፡ ማይክልም ያውቃል ማለት ነዋ! ልትል ነበር ። የተረገመ ልብ መቼ ነው ተስፋ እሚቆርጠው! መቼ ነው መጥላት የሚገባውን የሚጠላው ? «አሁንስ ለምን እዚህ ድረስ መጣሽ ? መኖሬን ስታውቂ ጊዜ ፈራሽ? ውል እማፈርስ መሰለሽ ? እና ውሉ ያልፈረሰ መሆኑን ልታስታውሺኝ ፈለግሽ ? »
«አይደለም ። በዚያ በኩል አልጠረጥርሽም ። ቃልሽን ማክበር እንደምትችይ አረጋግጫለሁ» አለች ማሪዮን ፤ እጅግ ያረጀሰው በመሰለ ድክም ባለና ደግነት በተሞላ ድምፅ «ላይሽ ነው የመጣሁ ። ላነጋግርሽ ምን እንደመሰልሽ ፤ ይመችሽ ፤ይክፋሽ ... ላይሽ ነው የመጣሁ። ላያት የመጣኋት ልጅ አንች ነሽ ማለት ከደፈርኩ ። ሌላውን ምክንያት እኔም በቅጡ አላውቀው»
«ለምን ? ይህን ያህል አመት ትዝ ሳልልሽ ቆይቼ ድንገት ምን አዲስ ስሜት ተፈጠረ ?» የሜሪ ድምፅ የሚናደፍ መርዛም ነበር ። ማሪዮን ምንም አልመለሰችም ።

«ድንገት ምን ነገር ተፈጠረ ሚስ ሂልያርድ? ወይስ የግሬግሰንን ሥራ ተመልክቶ ማድነቅ ስላማረሽ ይሆን ? እንዲያ ከሆነ ... እንዴት ነው በአራት መቶ ሺ ዶላር ክፍያ ያሰራሻት አሻንጉሊት እምታምር አትመስልሽም? አራት መቶ ሺ ዶላር ቢወጣም አይቆጭ! የሚያሰኝ ነው?. . . የሚያሰኝ ነው ወይ ? ምነው ጭጭ አልሽ ? ጥያቄየን መልሺልኝ እንጂ… ደስ አለሽ ወይስ ከፋሽ?» ደስ ቢለኝ ኖሮ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር ! አለች ማሪዮን በሀሳቧ ። ድንገት ደስ ቢለኝ የሚል ምኞት አደረባት ። ግን የሰራችው ነገር ውጤት መጥፎ ፤ ያደረገችው ነገር አስቀያሚ እንደሆነ ወለል ብሎ ታያት። ለዚህ ገጽታ ሁሉም ብዙ እንደከፈሉ ግን ያ ሁሉ ከንቱ እንደነበረ ተገነዘበች ። ይህ ፀፀት ነው። ፀፀት ግን ዋጋ የለውም ። ሁሉም ነገር ካለፈ ፤ ምንጩ ከነጠፈ በኋላ ቢፀፀቱት ምን ፋይዳ አለው? ማይክልን አሰበች ። ናንሲን ተመለከተች ። እሷን ራሷንም ። አንዳቸውም እንደነበሩ አይደሉም። ሁሉም ሌላ ሆነዋል ። ማይክልና ናንሲ። ሁሉም ነገር ሩቅ ከሩቅ ፤ የራቀ ሩቅ ሆኗል ። ለነሱም ። አንዳቸው ላንዳቸው ይሆኑ ዘንድ የማይቻል ነው ። ህልማቸውን በግል ሲያባርሩ ፤ ሊያገኙት ከቻሉ ሌላ ቦታ ቢፈልጉት ይሻላል ። «ናንሲ በጣም ቆንጆ ልጅ ሆነሻል ኮ» አለች ማሪዮን ፤ ወንድ አይጠፋም ለማለት ያህል ። «ቆንጆ ስላልሺኝ አመሰግናለሁ ይገባኛል ። ፒተር ውብ የእጅ ሥራ ቀርጾአል ። ግን ይህን ለማድረግ የገባሁበት ውል…. ከሰይጣን ጋር እንደመዋዋል የሚቆጠር ነው ። ቆንጆ ፊት ለማግኘት ሕይወትን መሰዋእት ማቅረብ ። ሌላ ትርጉም የለውም»

«ሰይጣኒቷም እኔ እንደሆንኩ አውቃለሁ» አለች ማሪዮን በሀዘን በተሰበረ ድምፅ «ምንም እንኳ ዛሬ ይህን ላንች መንገር ርኩስ ተግባር እንደሆነ ቢገባኝም ፡ ያኔ ናንሲ ፣ያኔ ቃል እንድ ትገቢልኝ ሳግባባሽ ፤ ሊሆን የሚገባውን ነገር ያደረግኩ መስሎኝ ነበር»
«አሁንስ ? አሁንስ ምን ይመስልሻል ? » አለች ፊት ለፊት በድፍረት እየተፋጠጠቻት «አሁንስ ምን ይሰማሻል ፤ሚስ ሂልያርድ ? ለመሆኑ ማይክል ደስተኛ ነው? እኔን እንደ አሮጌ ዕቃ ወርውረሸ ከጣልሽለት በኋላ ደስ ብሎት መኖር ጀመረ? ተልእኮሽ ሰመረልሽ ? » ስሜት ተናነቃት ። በጥፊ ልታልሳት ፈለገች ። ይህን የወይዛዝርት ልብሷን እንደተጎናፀፈች ገፍትሬ ጥዬ መሬት ለመሬች ብጎትታት ! ስትል ተመኘች ። «የለም የለም አንዱም ነገር አልተሳካልኝም ። ማይክል ደስተኛ አይደለም ። ከጊዜ ጊዜ ሁሉን ነገር ይረሳል ፤ ሀዘኑ ይሽራል በሚል ተስፋ ስጽናና ቆየሁ ። ግን አልሆነም ። አንችም እንዲያ እንደምትሆኝ ተስፋ ነበረኝ ።ግን ሳይሽ ነሽ ሀዘንሽ አልሻረም ምንም ነገር አልተረሳሽም ። ወይስ የተሻለ መንገድ መርጠሻል? ብዬ እጠይቅሽ ነበር ። ሆኖም መብት ያለኝ አይመስለኝም »
«ልክ ነሽ። ያን ጥያቄ ለማቅረብ ምንም መብት የለሽም ማይክል ሚስት አገባ ወይስ ?»
«አግብቷል» አለች ማሪዮን ። ሜሪ ክው ብላ ደነገጠች ። ኡኡ ! ብላ ለመጮህ ፈለገች ። ድምጹን አፍና አስቀረችው ። ያ ድምፅ ከጉሮሮዋ ሳይወጣ ሟሟ። «አዎን ፤ ሜሪ ። አግብቷል ። ሥራውን አግብቶ ትዳር መስርቷል ። የሚበላው የሚጠጣው የሚተኛው እሥራው ላይ ሆኗል። ትንፋሹ ሳይቀር ሥራው ሆኗል ።» ሜሪ ትንፋሽዋ መለስ አለ። «ከሥራው ላይ ንቅንቅ አይልም ። በሥራው ውስጥ ሰምጦ ዘለአለም አለሙን ሊያሳልፍ የፈለገ እስኪመስል ። አብረን እንኖራለን ይባላል እንጂ መልኩን የማየው ከዝንተ አለም አንድ ጊዜ ነው»

የት አባሽ አንች ውሻ !እንኳን ! አለች ሜሪ በሀሳቧ «እንዲያ ካልሽ ፤ ስህተት መስራትሽን ተገንዝበሻል ማለት ነው። ማለት በአለም ላይ ካለው ሀብትና ማንኛውም ድንቅ ነገር አብልጨ እወደው እንደነበር ታውቂያለሽ ? » ይህን ብላ ስታበቃ በኃሳቧ ከዚህ ፊቴ በስተቀር…. ከፊቴ በስተቀር ! አምላኬ ምናልኩህ «በስተቀር» እንድል አደረግከኝ! «አውቃለሁ ። አውቅ ነበር ። ግን ፍቅር ነውና ያልፋል ብዬ ገመትኩ»
«ሆነ ? ግምቱ ትክክል ነበር ? ረሳኝ ? »
«እንጃ ። ምናልባት አልፎለት ይሆናል ። ስምሽን አንስቶ አያውቅም መቼም»
«በመጀመሪያ ወይም መቼም ቢሆን የት እንዳለሁ ለማወቅ ሙከራ አድርጎ ነበር ?» ማሪዮን በአሉታ ራሷን እየነቀነቀች «እልሞከረም» አለች ። ይህን ትበላት እንጂ ለማይክል ናንሲ ሞታለች እንዳለችው አልነገረቻትም ። «ያ ከሆነ ታዲያ ለምን ጠራሽኝ? እኔን የማየት ጉጉትሽ እንዲረካ ? ….. ፎቶግራፎች እንዳሳይሽ?. . . ለምን ?»
«እኔም ለምን እንደፈለግኩሽ አላውቅም ፤ ናንሲ ። ይቅርታ... ሜሪ ። ቅድም እንደነገርኩሽ ነው ። አላውቀውም።... በግድ እዘኑልኝ ማለት ፤ ወይም ሆደባሻነት ይመስላል እንጂ ደኅና አይደለሁም ። መሞቻዬ ሩቅ አይደለም ። እመቃብሬ አፋፍ ላይ የቆምኩ ይመስለኛል»
👍15
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ አምስት (35) በሆስፒታሉ ኮሪደር ውስጥ እየተጣደፈ ሲሄድ የጫማው ድምፅ ጎልቶ ይሰማ ነበር። ምን ብታስብ ነው ወደ ሳንፍራንሲስኮ ስትመጣ ብቻየን ነው የምሄድ ብላ ድርቅ ያለችው ? ይህን ያህል አመት ስትኖር ረዳት አያስፈልገኝም ፤ሁሉንም ነገር ብቻየን ልወጣው እፈልጋለሁ የምትለው ለምንድነው ? ይህን እያሰበ በሩን አንኳኳ ። አንዲት በገጺ ላይ ምን ይፈልጋሉ ? የሚል ጥያቄ የተሳለባት ነርስ በሩን ከፈተችለት ። «ማሪዮን ሂልያርድ የተኛችው እዚህ ክፍል ነው ?» ሲል ጠየቃት ። በነርሷ ገፅታ ላይ የተሳለው ጥያቄ አልተነሳም ነበረና «ጆርጅ ኮሎዌ እባላለሁ» ሲል ጨመረ ። ድካም ፡ እርጅናና ያለመረጋጋት ስሜት በፊቱ ላይ ጎልተው ይታያሉ ። እነዚህ ስሜቶች በሠራ አካላቱ ተሰራጭተው ይሰሙትም ነበር ። የለም እንዲህ አይነቱ ርባና ቢስ ነገር አሁንስ ስልችት አለኝ ። ማሪዮን በዚሀ ሁኔታ ልትቀጥል አትችልም። ዛሬ ሁሉንም ግልጥልጥ አድርጌ መንገር አለብኝ ሲል አሰበ ። እንዳገኛት ይነግራታል ። ገና ከኒውዮርክ ከመነሳቱ በፊት ይህን ውሳኔ ለማይክል ሂልያርድም ነግሮታል ።

«ሚስተር ኮሎዌ ?» አለች ነርሷ ስሙን ስትሰማ በገዝፅዋ ላይ የተሳለው ጥያቄ ወደ ፈገግታ እየተለወጠ «ስንጠባበቅ ነበር » ማሪዮን እዚህ ሆስፒታል የገባችው ምሽቱ ላይ ፤አሥራ ሁለት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ጆርጅ ከኒውዮርክ ተነስቶ እዚያ የደረሰው ከምሽቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር ።ይሀ ደግሞ ከኒውዮርክ ሳንፍራንሲስኮ ለመድረስ የመጨረሻው ፈጣን ጉዞ ሳይሆን አይቀርም ። ነርሷን አልፎ ገባ። ማሪዮን የጆርጅን መምጣት አይታ ፈገግ ስትል ነርሷ ከክፍሉ ውስጥ ወጥታ ወደ ሠራተኞች ማረፊያ አዳራሽ ሄደች ።

«ሄሎ ጆርጅ »
«ሄሎ ማሪዮን ፤ ተሻለሽ ?»
«ከድካሙ በስተቀር አደጋውን አልፌዋለሁ ። ማለት ሀኪሞቹ የነገሩኝ እንዲያ ብለው ነው ። ኃይለኛ አልነበረም አያያዙ»
«ዛሬስ እንዲያ ሆነ ግን ለወደፊቱስ? ወደፊት›› ጀርጅ ይህን ተናግሮ በክፍሉ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሲንጎራደድ እርምጃው ሁሉ የአንበሳ ይመስል ነበር። ቁጣውም ለማሪዮን ግፅል ሆኖ ታያት ። ይህን ያየችው ማሪዮን ሁኔታው አስገረማት። እንደሁልጊዜው አልሰማትም ።። ብዙ ነገር ሲነግራት አስቧል ማለት ነው ። «ለወደፊቱ ፣ ወደፊት ሲሆን ይታሰብበታል ። ላሁኑ አረፍ በልና ሰውነትህን ዘና አድርገው ። እኔን ጭምር እየረበሽከኝኮ ነው። የሚበላ ነገር ይቅረብልህ ? አንድ ሣንዱች እንዲያስቀምጡልህ ለነርሶቹ ነግሬአቸዋለሁ »
«መብላት አልችልም»
«አይ አሁን አበዛኸው ። ደሞ የምን አዲስ ጠባይ ነው? ይህን ያህል ዘመን ስንኖር እንዲህ ስትሆን አይቼህ አላውቅም። በሽታው ያን ያህል ከባድ መስሎህ ነው? አልነበረም ። እና በስላሴ ይዣሀለሁ እኔን ጨምረህ አትረብሸኝ››
«የለም የለም ፤ አትምከሪኝ ። አልፈልግም ፤ አትምከሪኝ ማሪዮን ሂልያርድ። እንደፈለኩት ልሁን ስትይ እሽ ስል ምን መጣ ይኸዋ በሽታ ላይ ወድቀሽ አረፍሽው ። አሁን በዛብኝ በቃኝ። አልቻልኩም »
«በቃ ተስፋ ቆረጥክ?» አለች የፌዝ ፈገግታ ፈግጋ ተስፉ ከቆረጥክ ፤ ከሰለቸህ ለምን ሥራውን ለቀህ አረፍ አትልም›› የጆርጅ ሁኔታ የቀልድ ያህል አስደነቃት ሆኖም ፊቱን ወደሷ ሲመልስና ከጀመረው ሀሳብ ወደኋላ እንደማይል የሚገልፅ ገፅታውን ስታይ የቀልድ እድናቆቷ ወደ እውነተኛ አድናቆትና ድንጋጤ ተለወጠ ።

«ሥራ ልቀቅ አልሺኝ ፣ ማሪዮን ? እኔም አስቤ እሰላስዬ የወሰንኩት እሱን ነበር ። እኔም አንችም ሥራውን ለቀን በጡረታችን መኖር አለብን» ይቀልዳል ?... የለም ከልቡ ነው ፤ አለች በሀሳቧ ። «አትቀልድ» አለች ። ሆኖም ድምጺ የተለመደው ጥንካሬ ይጎድለው ነበር ። «ቀልድ ? ቀልድ የለም ። እንዲያውም በዚህ አብረን በኖርንበት ሃያ አመት ውስጥ እንዲሀ አይነት ጠንካራ ውሣኔ ወስኘ አላውቅም ። ሁለታችንም ከሥራ እንሰናበታለን ። ለማይክልም ይህንኑ ነግሬዋለሁ ። እግዜር ይስጠው አውሮፕላን ማረፊያ ያደረሰኝ እሱ ነበር ። ልመጣ ስላልቻልኩ በጣም አዝናለሁ ። በሥራ ተወጥሬ ነው ብሏል ። እና ተስማምተናል ። አንች ይህን አልሽ ያን አሁን ዋጋ የለውም ። ተወስኖአል ፤ያበቃ ነገር ነው»
«አበድክ ልበል ?» አለችና ከተጋደመችበት ተነስታ ቁጭ አለች ። አፈጠጠችበት ፤ በደብዛዛው ብርሃን «ልስማህና ሥራውን ትቼ ልቀመጥ እንበል ግን ምን ሳደርግ ልዋል ? ሹራብ ስሠራ ወይስ መጽሐፍ ሳነብ ?»
«ሹራብ ሥሪ ወይም መፅሐፍ አንብቢ ። የፈለገሽውን ብታደርጊ ከተስማማሽ ጥሩ ነው። ሥራውን ከተውን በኋላ ግን ወዲያውኑ የምናደርገው ነገር አለ ። እኔና አንቺ እንጋባለን ። ከዚያ በኋላ እንዳፈቀደሽ መሆን ትችያለሽ ። ግልፅ ነው?››
«እንዴት ያለ ነገር ነው ባካችሁ? ቢያንስ ቢያንስ እንድንጋባ ፈቃደኛ ነሽ ወይስ አይደለሽም ተብዬ አልጠየቅም ? ወይሰ ይኸም ከዋናው ሥራ አስኪያጅ ከማይክል የመጣ ትዕዛዝ ነው» ኣለች ማሪዮን ። ሆኖም ድምጺ የቃላቱን ያህል መከፋትም ቁጣም አልነበረበትም። ስላሰቡላት ልቧ ተነካ ። ሸክሙ ቀለል አላት ። እውነትም ይበቃታል ። ብዙ ነገር አድርጋለች መጥፎም ጥሩም ፣ እኩል በኩል ። ይህን ደግሞ ተገንዝባዋለች ። አውቃዋለች ።

ከሜሪ ኣዳምሰን (ናንሲ ማክአሊስተር ) ጋር ያንለት ያደረገችው ንግግር ይህን ጉዳይ ግልፅ አድርጎላታል ፣የዕድሜ ልክ ተግባሯን ተመልሳ እንድታይ አድርጓታል ። ደግም ከፋትም ሠርታለች ። «የማይክልን ምርቃትም አግኝተናል» አለ ጆርጅ ። ይህን ብሎ ወደ አልጋው ሄደና እጅዋን ጨብጦ «ታገቢኛለሽ፤ማሪዮን !?» ሲል እየፈራ ጠየቀ ። ይህን ያሀል ዘመን አብረው ኖረው ሲያፍራት ገረመው ። እንዲያውም ማይክል «ይገባል ። ፍቅራችሁን ልታከብሩት ይገባል» አይነት ነገር ባይለውና ምንም ትርጉሙ ግልፅ ሆኖ ለጊዜው ባይታየው «ለጋብቻው አበረታታት» ባይለው ኖሮ ላይጠይቃትም ይችል ነበር ። «ንገሪኝ እንጂ» ይህን ብሎ እጅዋን ጠበቅ አደረጋት ።
👍27🥰2
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ስድስት (36) ትዝ ካለህ ያንለት ልክ እንተ ስትገባ እሱ ወጥቶ አልሄደም ? እየተቆጣ ? ያንለት የመጣው ልጅቷን እንደሚያገባት ሊነግረኝ ነበር ። እኔ ደግሞ ስለቤተሰቧ ያሠራሁትን ሪፖርት ሰጠሁት » ልትቀጥል አልቻለችም ። የለም ጆርጅ በሀሳቡ ። ምንም ደህና አይደለችም ፤ አለ «ማሪዮን ውዴ ፤ ታዲያኮ ያችን ልጅ ዛሬ ልታገኛት አይልሽም ። ማለት ልጅቷ እኮ ያኔ ነው... ያለፈችው»
«አይ ጆርጅ ። ሞኝ ነህ ። ብዙ እማታውቀው ነገር አለ ፣ ስለኔም ስለብዙ ነገርም ። አልሞተችም እኔ ነኝ ሞተች ብዬ የነገርኳችሁ ። አደጋው ደረሰ ። ፊቷ ብቻ ሲጎዳ ፣ ሲበላሽ ልበልህ ? ሌላው አካሏ ምንም አልሆነም ነበር….. ፊቷ ግን ከአይኗ በቀር አልነበረም» ጆርጅ ማዳመጥ ጀመረ ። ማሪዮን የሆነውን ከዳር እስከዳር ገለፀችለት ። «ማይክልን ለማግኘት ካልሞከረች ፊቷን በፕላስቲክ ሰርጄሪ ለማስጠገን ገንዘቡን እንደምከፍልላት ቃል ገባሁላት» አለች ማሪዮን ።
«ተስማማች?»
«ተስማማች»
«እንዲያ ከሆነ ማይክልን አትወደውም ነበር ማለት ነው። ስለዚህ ለህክምናው ስለከፈልሽላት እንዲያውም በጎ አድራጊ እንጂ ክፉ አይደለሽም ። እንዲያውም እሱም ያን ያሀል ቢወዳት እሷም ያን ያህል ብትወደው በዚህ ጉዳይ ተስማምተው ቁጭ አይሉም ነበር»
«የለም የለም ። ያልገባህ ነገር አለ ፤ ጆርጅ ። አየህ ዋሽቻቸዋለሁ ። እሷ የተስማማችበት ምክንያት ፤ ምን ተባለ ምን ማይክል የሷንና የኔን ስምምነት እንደማይቀበል ፤ መኖሯን እንዳወቀ የፈለገውን ነገር ጥሶ እንደሚያገባት በመገመት ነው ። ለማይክል ደሞ ሞታለች ብለን ነግረነዋል ። የሚያውቀው መሞቷን ነው።

ባይሆን ኖሮ ደሞ ርግጠኛ ነኝ ማይክል የፈለገው ቢሆን ውርስ ብነሳው እንኳ ትቶልኝ እሷን ያገባ እንደነበር ቁልጭ ብሎ ይታየኛል » ጆርጅ ይህን ሲሰማ አዘነ ። ማሪዮን የዓለም ሰው መሆኗን ያውቃል ። ምንም አይነት ውሣኔ የምትወስነው ለሷ ቅርብ የሆነውን ነገር ለማዳን ነው። ይህን ሁሉ ያደረገችው ደግሞ በልጅቷ ላይ ክፉ ለማድረግ ሳይሆን የማይክልን ክብር ለመጠበቅ ስትል እንደሆነ ይገባዋል ። ሆኖም ነገሩ ማይክልን እንዳልጠቀመው ግልፅ ነው። በህይወቱ የመጣ ነገር ነበረና ብዙ ጎድቶታል። ይህ ደግሞ ለማሪዮን የማይሽር ቁስል ሆኗል ። ነገርን ቢያባብሱት ዋጋ የለውም ። ይልቅ ቁስሏ ይሽር እንደሆነ የሚቀባ መድሐኒት መሞከር ይሻላል አለና አሰበ ። እና… «ግን ይህ ስለሆነ ማይክል ምንም ያህል አልተጎዳም። ወደ መጀመሪያው ላይ በርግጥ… !» ሲል አቋርጣው «የለም ፣ ዛሬም የማይክል ቁስል አልሻረም ። ርግጥ ነው ማይክል እንደመጀመሪያው ሲያዝን ፡ ሲተክዝ ፤ ሲበሳጭ ፡ ሲጠጣ አይታይም ። ያን ያህል እኔም ሳልገነዘብ አልቀረሁም ሆኖም እንዳየኽው ሌት ተቀን ሥራ ሥራ ሥራ ነው። በሥራ ተጠምዶ ይውላል ፤ በዚያው ያድራል ። በሱ እድሜ እንደሚገኝ ወጣት አይደሰትም ። የሱን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው እኩዮቹ አይጨፍርም ። ሽሽት ነው። ይኸ ሁሉ ኑሮን መተው ነው። ቁስሉ ውስጥ ውስጡን እያሰቃየው. . . የሱ ኑሮ ይሄ ነው። ከማንም ሰው ይበልጥ ይህን እማውቅለት እኔ ነኝ። እናቱ ነኝ። ግን….» አለች።

«ግንኮ ይህን ያህል ጊዜ ተለያይተዋል ማሪዮን ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ደሞ ሁለቱም ተለውጠዋል ። ስለዚህ ዛሬ ቢገናኙ እንኳ ፍቅራቸው እንደዚያ ጊዜው ላይሆን ይችላል ። ላይፈቃቀዱ ይችላሉ» አለ ጆርጅ ቁስሏን የማከም ሙከራውን በመቀጠል ። «ይገባኛል ። አሁን ያልከውንም አስቤዋለሁ ። ግን እንጃ ማይክ ሁሉን ማድረግ ሲችል ሁሉን ትቶ ሥራ፣ ሥራ እያለ ከመኖር ሸሽቶ ኑሮውን ይገፋል። እሷም ብትሆን…. እሷም የሷም…» ንግግሯን አቋርጣ በሀሳብ ጭልጥ ብላ ጠፋች ። በአይነ ኅሊናዋ ሜሪን በማየት ላይ ነበረች ። «እሷም» አለች በሀሳብ እንደሰመጠች «በርግጥ ቆንጆ ሆናለች ። አለባበሷ አቋሟ ይኽ ቀረሽ የማትባል ቆንጆ ሆናለች ። ናትግን ቁጡ ፤መራራ ስሜት ያላትና በጥላቻ የተሞላች ሰው እንደወጣትም በግልፅ አይቻለሁ ። ቢጋቡ እንዴት አይነት ድንቅ ባልና ሚስት ይወጣቸው ነበር»
«አሁን ያ ሁሉ እንዳይሆን መሰናክሏ እኔ ነኝ ነው እምትይው ?»
«ይህን ሁሉ ከነገርኩህ ፤ይህን ያህል ስለሁኔታው ካወቅህ በኋላ አንተስ ቢሆን ጥፋተኛ ናት ቢሉህ እትስማማም?...›› «
‹‹... ጆርጅ እውነቱን መሸሽ አያሻም ። ጥፋተኛ ነኝ ። በሁለት ፍቅረኞች መካከል መግባት አልነበረብኝም ። »
«ሳይታሰብ በደል ተፈፅሟል እንበል ። ግን ደግሞ የሁለቱ ነገር የሚሆን ከሆነ አሁንም ነገሩ የሚስተካከልበት መንገድ ይኖር ይሆናል ። ከተስተካከለ ደግሞ ያ ባይሳካ እንኳ ለልጅቷ የዋልሽላት ውለታ ቀላል አይደለም። ገላዋን መልሰሽላታል እኮ... ምናልባትም የተሻለ ኑሮ እንድትኖርም ረድተሻታል»
«ይህን ሁሉ አደረግሺልኝ አላለችም ፤ እሷ እንዲያውም በጣም ትጠላኛለች»
«ይህን እያወቀች የምትጠላሽ ከሆነ ዋጋ የላትም ። ጅል ናት ማለት ነው»
«የለም ጆርጅ ጅል አይደለችም ። መጥላቷም ትክክል ነው። ልብ ቢኖረኝ ኖሮ ደሞ ለማይክል እነግረው ነበር የሆነውን ሁሉ።»
«አሁንማ መንገር ምን ዋጋ አለው? አሁንስ ባትነግሪው ይመረጣል ውዴ» አለ ጆርጅ የማይክልን ቁጣ እያሰበ ።«አትንገሪው እሺ ?»
«አይዞህ ፣፤ ጀርጅ» አለች ማሪዮን በሀዘን ፈገግ ብላ «ያን ያህል ደፋር አልምሰልህ። ይህን ለሱ ለመንገር ያህል ልብ የለ። ሆኖም ማወቁ አይቀርም ። ጊዜ ይወስዳል እንጂ ማወቁ የማይቀር ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ እኔም እረዳዋለሁ ጥፋቴን ለመዘርዘር አቅምም ድፍረትም የለኝም ። ከተገናኙ በኋላ እሚስማሙ ከሆነ እሷው ትንገረው ። ያኔ ምናልባት ይቅርታ ያደርግልኝ ይሆናል»
«ተወኝ ብላ እምታስብ ከሆነ እሺ ብላ እምትቀበለው ይመስልሻል ?››
«እሱን እንጃ ፤እሱ እኔንም ያጠራጥረኛል ። ግን እኔ የተቻለኝን ያሀል እንዲገናኙ ማድረግ አለብኝ»
«እንዴት ያለው ጣጣ ...»
«እዎ እንደተበተብኩት ማፍታታት አላብኝ ። ውሉ ላይገኝ ያሰብኩት ላይሳካ ይችላል ። ቢሆንም መሞከር አለብኝ»
«ይገርማል።... ይህን ያሀል ጊዜ ሁለት አመት መሆኑ ነው... ይህን ያሀል ጊዜ በሆነ መንገድ ከልጅቷ ጋር ግንኙነት ታደርጊ ነበር ?»
«እንዲያ በፋሻ ተደግልላ ካነጋገርኳት በኋላ አይቻት እላውቅም ነበር ። ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋት ዛሬ ነው»
«ገባኝ ፤ ዛሬስ እንዴት ልትገናኙ ቻላችሁ ?››
«የቀጠርኳትም እንድንነጋገር ያቀድኩትም ራሴ ነበርኩ ። ቤን ስለፎቶግራፍ አንሺዋ አርቲስት ሲነግረኝ ልቤ ጠረጠረ ። ጥርጣሬ እንጂ ርግጠኛንኳ አልነበርኩም»
«አብራችሁ ያሳለፋችሁት ጊዜ ጭንቅ የበዛበት ሳይሆን እይቀርም»
«ከዚያ የባሰ ሊሆንም ይችል ነበር» አለች ድምጺ በሀዘን ለስልሶና አይኗ ላይ እንባዋ ተንቀርዝዞ «የባሰ ነገር ሊመጣም ይችል ነበር ግን እልሆነም ። ምን ያህል እንደትሳሳትኩ ፤ ሁለት ህይወት እንዳበላሸሁ ፤ ወንጀለኛ እንደሆንኩ ብቻ ነው የተረዳሁት ። ያ ብቻ ነው...»
👍17
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ሰባት (37) «ማሪዮን» አለ። አየችው ፤ አቤት እንደማለት ። «ማሪዮን ያለፈው ኣልፏል ። ላሁኑ ሁለቱ የሚገናኙበትን መንገድ ቀይሺ ። የሚቻልሽን ሞክሪ ። ከዚያ በኋላ የሁለቱ ጉዳይ ነው። አንቺ ምንም ማድረግ አትችይም ። እኔና አንቺ ብዙ እድሜ አልትረፈንም ። ያችኮ ያለችዋን የተቻለንን ያህል እንድንደሰትባት እፈልጋለሁ እንጋባ ። አንድ ላይ እንኑር ፤ በሰላም ። እኔም እስከ ዛሬ የናፈቅሁት ፣ አንቺም ሠራሁት በምትይው ሀጢአት እስከ ዛሬ የተቀጣሽው በቂ ነው ። እኛም'ኮ በደስታ የመኖር ድርሻ አለን» አለ ጆርጅ ። ‹‹ድርሻው ይሁን ፣ ግን እኔ የመደሰት መብት ያለኝ ይመሰልሀል ጆርጅ ?» አለች ማሪዮን ቅዝዝ ብላ ፤ ከልቧ። ይህን ስትል ቅዝዝ እንዳለች ቁልቁል ሲያያት ገና ለግላጋ ወጣት ሆና ታየችው ፤ ለጆርጅ ኮሎዌ ። «በደንብ ነዋ |» አላት «የመኖር መብትሽን ማን ሊነሳሽ ፍቅሬ ?» ከዚያም ፀፀቷን ሁሉ እንድትረሳ ፤ ሀጢአት የምትለው ነገር ከንቱ ሀሳብ መሆኑንና ለወደፊቱ የሚቻለውን ካደረገች በኋላ ደስታቸውን እየተላበሱ በሰላም መኖር እንዳለባቸው ደግሞ ነገራት። ቀጥሎም… «ላሁኑ ግን ማረፍ አለብሽ ለጥ በቃ ። ለእንደዚህ ያለው በሽታ መድሐኒቱ እረፍት ነው። እሺ ?» አለ ወደ ላይ እያየችው ፍንድቅ ብላ ሳቀችና «ጆርጅ ኮሎዌ እወድሀለሁ» አለችው፡፡ «መውደድሽ ደግ ሆነ ። ምክንያቱም ወደድሽም ጠላሽ አንችኑ ማግባቴ አይቀርም ነበር ። የመጣው ቢመጣ። ገባሽ?»
«አዎና» ሁለቱም በደስታ ግለው በፈገግታ ይንቦገቦጉ ጀመር።

አንድ ነርስ በሩን ቀስ ብላ ከፍታ ሀኪሙ ለማሪዮን በደንብ መተኛት እንዳለባት መግለፃቸውንና ሌሊቱ እየተገባደደ መሆኑን እስክትነግራቸው ሁሉንም ረስተው በፍቅር ተተብትበው አንድ ላይ ቆዩ ። ጆርጅ ኮሎዌ እንደወጣ ማሪዮን ሂልያርድ ወደ ኒው ዮርክ ስልክ ደወለች… ከሳንፍራንሲስኮ ማለት ነው ። ጊዜው (ኒውዮርክ ውስጥ) አነጋጉ ላይ ቢሆንም ማይክል ስልኩን ቶሎ አላነሳውም ። ጠበቀች ፤ ማሪዮን። «ሃሎ?» አለ ፤እንቅልፍ የተጫጫነው የማይክል ድምፅ «የኔ ሸጋ ፤እኔ ነኝ » አለች ማሪዮን። «እማዬ ነሽ ? ደህና ነሽ ? ተሻለሽ? » ጥያቄውን አዥጎደጎደው። «ደህና ነኝ ። አይዞህ አትስጋ ። ይልቅስ አንድ ነገር ልነግርህ ስለፈለኩ ነው የደወልኩልህ »
« ገባኝ ። ጆርጅ ነግሮኛል » አለ እያዛጋ «እንዴት ነው እሺታ ወይስ እምቢታ?»
«እምቢታ የለም ። ሁሉንም ተቀብያለሁ » አለች ። «አሁን የጠራሁህ ለሌላ ጉዳይ ነበር» አለች ። መልስ አልሰጣትም ። ትንሽ እንደማጉረምረም ብቻ አለ ። «ስለዚያች ልጅ ጉዳይ» አለች ማሪዮን ። «የቷ ልጅ?» ማይክ እየተደናገረ ጠየቀ ። «ፎቶግራፍ አንሺዋ... ማይክል ገና አልነቃህም”ንዴ
«ገባኝ። እሺ።ምን ትሁን!»
«ታስፈልገናለች»
«ያን ያህል››
«በጣም ። ሆኖም እንደምታውቀው እንግዲህ እኔ የጆርጅ ሰው ነኝ። ልጀቷን ማደኑ ያንተ ሥራ መሆኑ ነው»
«ትቀልጃለሽ እማዬ ? እኔ ያለብኝን የሥራ ውጥረት እያወቅሺው ። ቤን ይከታተል የሷን ጉዳይ»
‹‹ቤንንማ አፍንጫህን ላስ አለችውኮ ። ይልቅ ስማ ። ልጅቷ ዘመናዊ ከመሆኗም በላይ የታረመችና በእውቀቷም የምትተማመን ሰው ናት ። ከማንም ኩታራ ጋር ለመነጋገር የምትፈቅድ አይመስለኝም… ከተቀጣሪዎች ጋር ማለቴ ነው»
«ገባኝ ። ግን የመቀመጫ እሾህ መስላ ነው ለኔ የታየችኝ››
«እሷ ሳትሆን አንተ ነህ እንዲያ የሆንክብኝ ። በምን መንገድ ልታግባባት እንደምትሞክር አላውቅም ። በሆነው ፣ በመሰለህ ሁሉ ብትቀርባት ደንታዬ አይደለም ። ግን እንፈልጋታለን። ለኔ ስትልም ቢሆን ይህን ነገር ዳር እንድታደርገው እፈልጋለሁ››
«የለም ፤ የለም ዛሬ ደህና አይደለሽም ። ጊዜ እንደሌለኝ እያወቅሽ እንዲህ ስትይ» አለ። «ይልቅ ይህን ጉዳይ ብቻ አንቺ ጨርሺ በቃ።»
«አላደርገውም ማይክ ፤ ደግሞ ይህን ጉዳይ አልፈፅምም የምትል ከሆነ ገና እኮ ነው ፤ሥራውን አልለቀኩምኮ !››
«ይህን ካላደረግክ አንደኛ ሥራዬን አልለቅም ፤ እዚያው እቢሮዬ ውስጥ እሞታለሁ ። ሁለተኛ…»
«በቃ በቃ!» አለ ማይክል አቋርጧት «እንዳልሽው ይሆናል »
«ልባርግ ! ቀልድ አይደለም ። ቃል ፤ ቃል ነው ። ቃልህን ከሻርክ ቃሌን እሽራለሁ ።»
« አረ በእግዜር |! እሺ አልኩሽኮ አሁን ትተኛለሽ ወይስ ?»
«እተኛለሁ ግን ይኸ ጉዳይ ነገ ዛሬ እንደሌለው እወቅ ። ገባህ?»
«ገባኝ ስሟን ማን ነበር ያልሺኝ ››
‹‹ሜሪ አዳምሰን»
«ሜሪ አዳምሰን ። በቃ ከነገ ጀምሮ የማገኝበትን መንገድ እፈልጋለሁ»
«ደግ... እግዜር ያክብርህ የኔ ቆንጆ»
«ደህና ደሪ የኔ አሮጊት ።... ቆይ... ቆይ እንኳን ለፍጥምጥሙ አበቃን ። ወሬውን ላናፍሰው ? ሙሽራው ማን እንደሆነ ልናገር ?»
«ምን ይጠየቃል ? ከጆርጅ የተሻለ ማንን ላገኝ ? አላፍርበትም» ሁለቱም ዘጉ ።

ማይክልንና ሜሪን ካገናኘች ፤ሁለቱ ተዋውቀው አንድ ነገር ከመሰረቱ አእምሮዋ ሰላም ያገኛል ። ማይክ የሠራችውን ሁሉ ሲሰማ ምን ይላት ? ሆኖም ፍቅሩን የማግኘቱ ደስታ ለሷ የሚኖረውን ጥላቻ ሊቀንሰው ይችላል። በኋላ ተፀፅታ የሠራችውን ሲያይ ይቅር ይላታል ። እንቅልፍ እያንሸራተተ……

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
14👍11
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ስምንት (38) ጆርጅ ኮሎዌ በፍቅር ሲስማት ለስላሳው ሙዚቃ እንደገና ጀመረ ። የሠርጉ ሥነ ሥርዓት የተከናወነው በማሪዮን ሂልያርድ ቤት ሲሆን እሷም ለዚሁ የሠርጓ ቀን ሶስት ሙዚቀኞች ቀጥራ ነበር ። ለሠርጉ የታደሙት አንድ ሰባ የሚሆኑ ሰዎች ሲሆኑ ፤ የምግብ ቤቱ ክፍልም እንደ የዳንስ አዳራሽ ሆኖ ተዘጋጅቷል ። የቡፌ ግብዣው የሚከናወነው ደግሞ በዚሁ መኖሪያ ቤተ መፃሕፍት ውስጥ ነው ። ዝግጅቱ የተከናወነ ፤ቀኑም ተስማሚ ነበር። የየካቲት የመጨረሻው ቀን ። ይህ ቀን ጥርት ያለ ፤ ነፋሻና ሳንካ አልባ የሆነ የኒውዮርክ ቀን ሆኗል ። ማሪዮን ሳንፍራንሲስኮ የደረሰባትን ነገር እንደመርሳት ያለች ይመስላል ። ደሟ ግጥም ብሎ ሞልቷል ። ጆርጅ በደስታ ፈነድቋል፡፡

ጋዜጠኞችም በዚሁ ሠርግ ላይ ተገኝተዋል ። ታይም የተባለው ታዋቂ መጽሔት ፎቶ አንሺ ማይክልንና ማሪዮንን ፤ ባሏ ጆርጅን ፎቶ አነሳቸው። ማሪዮን በባለቤቷና በልጅዋ ታጅባ ነበር የተነሳችው ። ማይክል ሂልያርድ እናቱን ዳረ ። ማሪዮን ሂልያርድ ካሁን ጀምሮ ፤ ማሪዮን ኮሎዊ ትባላለች ፤ የጆርጅ ኮሎዌ ባለቤት ። ማይክል ሂልያርድ ከዚህ ጊዜ ጄምሮ የኮተር ሂልያርድ ባለቤት ነው ። የአንድ ግዙፍ ድርጅት (የኮተር ሂልያርድን ያክል ግዙፍ ድርጅት) ፕሬዚዳንት መሆን ! ለማይክል የተሰማው ስሜት . . . ሆኖም ይህም ስሜት ቢሰማውም . . . ይህን ስሜቱን ደግሞ ማይክል ሊደብቅ አይሻም ። ፕሬዚዳንት ፣ በዚህ እድሜው ባለቤት ! በማግስቱ ታይም የተባለው በመላው ዓለም የሚሰራጭ መጽሔት የማይክልን ፎቶ በሽፋኑ ይዞ ወጣ ። ድንቅ ተባል ። በዚህ እድሜ የኮተር ሂልያርድ ፕሬዚዳንት !. . የማሪዮንና የጆርጅ ኮሎዌ ሠርግ እለት የዛ ለት ማይክል ወደእናቱ ቀረብ ብሎ፣ «ሚስዝ ኮሎዌ ! » አለ አዲሱን የጋብቻ ስሟን እየተጠቀመና ለቀሰስተኛው ዳንስ እየጋበዛት ። «አዲሱን ስም እናክብረው ጋብቻውን እናክብረው» አለ ። አዲሱን ስም እናክብረው ሲል ናንሲ ትዝ አለችው ። እንዳለው ሆነ ። አከበሩት ፤ ጆርጅና ማሪዮን ኩሎዌ በጋብቻ ተሳሰሩ ። ሁለቱም ለረጅም ጊዜ ተሰቃይተዋል ። ደስ ይበላቸው ፤ ደስታ ይገባቸዋል ። ደስታ ያስፈልጋቸዋል ። ጋብቻቸውን ምክንያት በማድረግ ወደ አውሮፓ ሔደው ሽርሽር ይላሉ። ደስ ይሰኛሉ ። « በጣም ቆንጆ ነህ የኔ ሸጋ » አለች ማሪዮን ፡ ማይክልን በፍቅር እየተመለከተች ። «ያንቺን አላየሽ ። አሸብርቀሻል ፤ ተውበሻል » አለ ማይክ ከልቡ። «ቤቱ ሳይቀር እንደ አዲስ ያበራል ፤ አምሯል » እለ ። «በጣም አሸብርቋል አደል ? » አለች ማሪዮን ። ማይክ ከልቡ ተደስቶ ማሪዮንን ተመለከታት ። እናቱ ነችኮ። ይህቺ ሙሽሪት እናቱ ነች ። ሙሽራ ትመስላለች ፤ የእውነት ሁኔታዋ ሁሉ የሙሽራ . . . የልጃገረድ ሙሽራ ሆኖ ታየው ። «ሚስተር ሂልያርድ » የሚል ድምዕ ቀሰቀሰው ። « ማይክል ሂልያርድ በጣም ደስ ያለህ ትመስላለህ ዛሬ » ዌንዲ ነበረች ። ሲያያት እንደወትሮው አላፈረም ። ዓይኑ አልሸሻትም ። ይህ ቀርቷል። ዛሬ ቤን አቭሪና ዌንዲ ሊጋቡ ተጫጭተዋል ። የማጫ ቀለበቷ (ዕንቁ ያለበት ቀለበቷ ) እቀለበት ጣቷ ላይ ያበራል ። ሊጋቡ ወስነዋል ። ማይክል ሂልያርድም ዋና ሚዜ ሆኖ ተመርጧል ። ተስማምቷልም ።

«ደስ አትልም?» አለ ማይክ እናቱን ለዌንዲ እያሳያት ዌንዲ አንገቷን በአዎንታ ነቅንቃ በደስታ ፈገግ አሰች ። ደስ ብሎት ስላየችው ደስ እላት ። እንዲህ ደስ የሚለው መስሏት አያውቅም ። ብቻ ነገሩ ሁሉ አይገባትም ። ገባት አልገባት ደሞ ደንታዋ አይደለም ። ለሷ እንደሆነ ቤን አለላት ። የቤንን ያህል በፍቅር ደስ ያሰኛት ወንድ የለም ። «እንቺም በሚቀጥለው በጋ እንዲህ ቆንጆ ሆነሽ ማየት አለብኝ ። ሙሽራ ቁንጅት ሲል የሠራ አከላቴ በደስታ ይሞላል » አለ ማይክል ዊንዲን በደስታ እያየ ። ደስ አላት ። ዛሬ ጓደኛዋ ነው። ትወደዋለች ። አትመኘውም ለጓደኛ የሚገባውን ሁሉ ግን ትመኝለታለች ። «አሀ የኛ ጀግና ፤ የሰው እጮኛ ለማማገጥ ነዋ ?» ቤን አቭሪ ነበር እንዲህ ያለው ። ቤን ሶስት መለኪያ ሻምፓኝ ይዞ ነበር የመጣው ። «በሉ ተቀመጡ። ይኸው ! ሁለት መለኪያ የናንተ ነው አንሱና ጠጡ» አለ ቤን በደስታ ፈክቶ ። ቀጥሎም ፣ «በነገራችን ላይ ማይክ ምን እንደሚሻለኝ እንጃ እንጂ ፍቅር ይዞኛል ፤ ከማሪዮን ጋር » አለ ። «ቀለጥክ… ዛሬ ጠዋት ላንድ ጎረምሳ ዳርኳት» አለ ማይክ ። ቤን ወይኔ በሚል ሁኔታ ጣትና ጣቱን አጩሆ ደንግጦ ቀረ። በዚህም ነገር ሶስቱም ከልባቸው ሳቁ። ሙዚቃው የተጀመረው ገና ስቀው ሳያበቁ ነበር ። በዚህ ጊዜ ማይክ « ሙዚቃው ጀመረ። መሔድና እናቴን ለዳንስ መጋበዝ አለብኝ ። ደንቡ እንደሚለው እኔና እሷ ዳንሱን እንከፍታለን ። ጆርጅ ይቅርታ ጠይቆ ይነጥቀኛል።» ይህን ብሎ ወደ ዳንሱ አዳራሽ ከገባ በኋላ ነበር እናቱን ባዲሱ የጋብቻ ስሟ ጠርቶ የጋበዛት ።

« ዛሬ በጣም ደስ ያለው ይመስላል » አለች ዌንዲ ማይክ እንደተለያቸው ። «እንዲህ አንዳንድ ቀን እንኳ ደስ ብሎት እንየው እንጂ » አለ ቤን ፊቱ በተመስጦ ተሞልቶ። ከዚያም ድንገት ተመስጦን ነጥቆ ወጥቶና ከልቡ ፈገግ ብሎ «አንቺም ዛሬ በጣም ደስ ብሎሻል » አላት «ደሞ እኔ መቼ ከፍቶኝ ያውቃል? ዕድሜ ላንተ እንጂ›› አለች ከልቧ ። ለጥቂት ጊዜ ፀጥታ ሆነ ። ከዚያ በኋላ « በነገራችን ላይ ፤ እጠይቅሀለሁ እያልኩ እየረሳሁት «ያችን ፍቶ ግራፍ አንሺ አነጋገርካት ወይስ እንዴት አደረግክ?» ስትል ጠየቀችው ፡፡ «አላነጋገርኳትም » አለ ቤን ራሱን በአሉታ እየነቀነቀ «ማይክ ሊያነጋግራት አስቧል » አልመስልሽ አላት « ማይክ ጊዜ አግኝቶ ? » አለች ጥያቄዋ መደነቅም ነበር ። «ጊዜ እንኳን የለውም ። ግን ማይክ ለሥራ ጊዜ ያጣል ብለሽ ነው እንደምንም ያብቃቃዋል ።. ለዚህም ለሌላ ሌላ ሺህ ጉዳይም በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ሳንፍራንሲስኮ ይሔዳል » አለ ቤን ። ፀጥታ ሆነ ። ዌንዲ ማሰብ ቀጠለች ።
👍15
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰላሳ ዘጠኝ (39) «ሄሎ» አለች ሶስት እራቴ ስልኩ ከጮኸ በኋላ ። «እንደምን አመሸሸ ሚሰ አዳምስን። ማይክል ሂልያርድ እባላለሁ» አለ ። ባለችበት ላይ ደንዝዛ ቀረች ። ልትጮህ ቃጣት…..
። ሆኖም እንደምንም ብላ ተቆጣጠረቸው ። ትንፋሽዋንም ዋጥ አደረገች ። ይህን ሁሉ ካደረገች በኋላ «ነው? ሳንፍራንሲስኮ መጥተሃል ማለት ነው" አለች፡፡ ይህን የተናገረችው በመጠኑ በሚቆራረጥና በጎረና ድምፅ ነበር ። ያን ድምፅ የሰማው ማይክል የተቆጣች መሰለው ። ምን አስቆጣት ? አለ በሀሳቡ ። ምናልባት በሌላ ነገር ትበሳጭታ ይሆናል ። ወይም እቤቷ ሲደውሉላት አትወድ ይሆናል ። ብቻ የሰው ጠባይ ብዙ ነው ። ያም ሆነ ያ ማይክል ደንታው አይደልም ። «አዎ። ሳንፍራንሲስኮ ነው ያለሁት ። እና ተገናኝቶን አንዳንድ ነገር ብንወያይ ብዬ ነበር» አለ ማይክ «የለም የለም ። ምንም የምንነጋገረው ነገር የለም ። ለእናትህ ግልጹን የተናገርኩ መስሎኝ ነበርኮ» አለች። አልቅሺ አላት። ሰውነቷ በመላ ተንቀጠቀጠ ፤ የስልኩን እጀታ እንደያዘች ። «አልነገረችኝም ። ምናልባትም ረስታው ይሆናል» አለ ። የሱም ድምፅ እንደ እሷ ድምዕ ሙጥረት ይሰማበት ጀመረ። «ካንች ጋር እንደተለያያችው ቅለል ያለ የልብ ድካም በሽታ ስለተነሳባት ከህመሙ በኋላ ረሰታው ይሆናል ፣ ያው ልትረጂው እንደምትችይ…››

‹‹አመሣት ?» አለችና ዝም አለች « ግን ወዲያው… «አሁንስ እንዴት ነው ተሻላት?» ስትል ጠየቀች። «አሁን ደህና ናት ። ከዚያም አልፎ ባለፈው ሳምንት ባል አግብታ አሁን ማጆርካ ውስጥ ትገኛለች» አለ ማይክ ። አንድ ነገር መጥቶ እጉሮሮዋ ላይ ተሰነቅረ ። ውሻ! የኔን ሕይወት ብልሽትሽቱን አውጥታ ስታበቃ እሷ ተሰርጋ ትምነሽነሽ እንጂ ! እለች ፤ በሀሳቧ ። ጥርሷን ማንቀራጨጭም አማራት ። ስልኩን እጆሮው ላይ ድርግም ማድረግም አሰኛት። «ይህ እንኳ ከቁም ነገራችን ውጭ ነው» ኣለ የማይክል ድምዕ «እና መቼ እንገናኝ ትያለሽ ? »
«አንችልም ብዬ ነገርኩህኮ » ይህን ያለችው በፍጥነት ነበር ፤እንትፍ ያለችበትን ያህል ። ጉዳዩ አስደንግጦት ወይም አስገርሞት ኣይኑን ገርበብ አደረገ ግን ብዙም አልተጨነቀም ። ጉልበት አልነበረውም፤ ደክሞት ነበረና ። «እሺ ይሁን፤ተሸነፍኩ ። ላሁኑ ማለቴ ነው። ምናልባት ሀሳብሽን ከቆየርሽ ፌይርሞንት ሆቴል ነኝ። ደውይልኝ»
«አልደውልም»
«ደግ»
«ደህና ደር፤ ሚስተር ሂልያርድ»
«ደህና ደሪ፤ ሜሪ አዳምሰን» እንዴት ባንዴ ነገሩን ቁርጥ አደረገው! ደሞም ፈፅሞ ማይክልን የመሰለ ነገር የለውም! የደከመ፤ ሁሉ ነገር ገደል ይግባ ብሎ የተወ ይመስላል ። በነዚህ ሁለት ዓመታት ውስጥ ምን ደርሶበት ይሆን? ምን አጋጥሞት ይሆን? ስልኩን ከዘጋች በኋላ ለረጂም ጊዜ ስለማይክል ብዙ ጥያቄዎች ጠየቶች። ስለማይክል ባያሌው ኣሰበች።

•••••••••••••••••••••••••

«ውዴ ዛሬ በጣም ፀጥ ብለሻል። ቅር የተሰኘሽበት ነገር አለ ?› አለ ፒተር ግሬግሰን ምሳ የሚበሉበትን ጠረጴዛ አሻግሮ እያየ ። ሜሪ ምንም አልሆንኩም በሚል መንገድ ራሷን ነቅንቃ ወይን የተቀዳበትን መለኪያ እያሽከረከረች «ምንም አልሆንኩም» አለች «ምንም አልሆንኩም ። ቅር ያለኝ ነገርም የለም ። እያሰብኩ ነው… ስለምጀምረው አዲስ ስራ። አዲስ ፕሮጀክት ሳስብ ሁሌም እንዲህ ያደርገኛል ። ከአእምሮዬ ማውጣት አልችልም » ይህን ያለችው ስታብል ነበር ።ይህን ደግሞ እሷም ታውቅዋለቸ፤ ፒተርም ያውቀዋል ። ነገሩ ሌላ ነበር። ከትናንት በስቲያ ምሽት ማይክል ከደወለ ጊዜ ጀምሮ ናንሲ ዛሬን መኖር አልቻለችም ወደ ትናንት እየተጠለፈች ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት የሆነውን ሁሉ ታሰባለች ። የምታስበው ሁሉ የመጨረሻዋን ቀን ነበር።... ቢስክሌቶቻቸውን ሲነዱ፤ ወደ ባዛሩ ሲገቡ ፎቶ ግራፍ ሲነሱ ካንዲ ፍሎስ ስትልስ… ሰማያዊዎቹን መቁጠሪያዎች በባህሩ ዳርቻ ላይ ስትቀብራቸው፡፤ የገቡት ቃል... ያን ለት ማታ የለበሰችው ቀሚስ፤ማይክልን ልታገባ ስትወጣ እና .. እና በመጨረሻ የማይክል እናት ድምፅ . . እሷ በፋሻ ትደግልላ ያነጋገረቻት ።

ይኸ ሁሉ ልክ እንደፊልም ባይኗ ላይ ጎልቶ ይታያት ነበር። ስንቴ ሌላ ነገር ልታስብ ሞከረች ግን አልቻለችም ። ከዚህ ሀሳብ ልታመልጥ ከቶ አልቻለችም ። «ውዴ ግን. .ግን . . ደህና ነሽ?» አለ ፒተር በመጨነቅ ። «ምን ትሆናለች ብለህ ነው? አይዞህ አትጨነቅ ። ደህና ነኝ በእውነት ደህና ነኝ ። ይቅርታ ዛሬ መቼም አሰጨነቅኩህ ። ምናልባትም ደክሞኝ ይሆናል ፤ በቃ» አለች ሆኖም አላመናትም ። አይቷላ የተጠናወተው የሚመስል ገፅታዋን ። የተከፋ ፈቷን ፤ በዓይኖቹዋ መካከል የተቋጠረ ግንባሩዋን አይቷል ። «ከፌ ጋር በቅርብ ተገናኝታችሁ ነበር?» አለ ፒተር። «አልተገናኘንም ። አንድ ቀን ምሳ እጋብዛታለሁ እያልኩ አልቻልኩም። ኤግዚብሽኑ ከተከፈተ ወዲህ ስራ በዛ» አለች ። ኤግዚብሽኑን ሰታነሳ ውለታውን በሚነግር ድምፅ ነበር የተናገረችው ፈገግ ብላ ። ከዚያም አከታትላ «ምን! እንደምታየው ከፎቶ ግራፍ ማጠቢያ ክፍል ወጥቼ አላውቅም» አለች። «እንዲህ በጓደኝነት ማለቴ ሳይሆን እንደሐኪም አነጋግራሽ ታውቃለች ወይ? ማለቴ ነበር» ኣለ ። «እንዲያውም ። አልነገርኩህም እንዴ ከገና በአል በፊት ያን ጉዳይ ጨረሰን ብዬ?»
«ግን እኮ ማን እንደሆነ ውሣኔውን የሰጠው አልነገርሽኝም ። አንቺ ትሆኝ ፤እሷ »
«የወሰንኩት እኔ ነኝ ። ግን ስነግራት አልተቃወመችም »። አለች

ፒተር የአእምሮ ሕክምና እንደሚያስፈልጋት በመጠቆሙ ናንሲ ትንሽ ቅር አላት ። ስለዚህም ሕክምናው እንደማያስፈልጋት በተዘዋዋሪ እንዲህ ስትል ልትነግረው ሞከረች ። «ፒተር ምንም የመረበሽ ስሜት የለብኝም ። ድካም ብቻ ነው። ደሞ እሱ ይለቀኛል »
«ይሆናል ። ግን ልቤ ይጠራጠራል ምክንያቱም አየሽ እፊትሽ ላይ የሆነ ነገር ይታየኛል ። . . . ማለት ከሁለት ዓመት በፈት የነበረው ነገር የሆነው ሁሉ እየመጣ የሚያስጨንቅሽ ይመስለኛል » ይህን ሲል እየተጨነቀና ሁኔታዋን እያጤነ ነበር ። ሰምታው ሽምቅቅ ስትል ሲያይ ደነገጠ ። ራሱን ጠላ ። «የምን ያለፈ ነገር?» አለች ሜሪ « የማይረባ ነገር አታምጣ››
👍17
😘  #ቃል  😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ (40)


ለማይክ ያላትን ፍቅር ደግሞ ምንስ ብላ እንዴትስ አድርጋ ልትረሳው ትችላለች? ማይክ ስልክ እንደደወለላት፣ ድምጹን ስትሰማ እቅፍ አድርጋ ልትስመው ምን ያህል እንደጓጓች እንዴት አድርጋ ትንገረው ለፒተር ? ቢያቅፋት የተመኘችውን ፣ማይክን ያለመችውን ምን ጉልበት አግኝታ ብታስረዳው ይገባዋል ? እንጃ… እንጃ…..

«እሺ ፒተር አስብበታለሁ» አለች ፌን ማነጋገር አለብሽ አላት ። «እንደሱ ነው የሚሻለው ። አሁን እንዴት ነው እቤትሽ ባደርስሽ አይሻልም ? » አለ ። ተሰማማች ። አደረሳት ። ከመኪናው ስትወርድ ፣ «ቤት ላስገባሽ ? » ሲል ጠየቃት። «አይ ተወው ። እራሴ እገባለሁ» አለች ። ጉንጩን ሳመችው። ዞር ብላ ሳታይ ወደ ህንፃው ገባች ። እቤቷ እንደገባች በቀጥታ ወደ አልጋዋ አመራች ። ፍሬድ (ውሻዋ) ይዘል ጭራውን ይቆላ ምላሱን ያንቀላብጥ ነበር። አልጋዋ ላይ ተዘረረች ። ዘሎ አልጋው ላይ ወጣ ። ግን ጨዋታ አላሰኛትም ነበረና ገፍታ አስወረደችው። አልተመለስም በጀርባዋ ተዘርራ ኮርኒሱን እየተመለከተች ለረጂም ጊዜ ባሀሳብ ተውጣ ቆየች ። ብዙ ብዙ አሰበች። ሀሳቧም እግር እጅ እልነበረውም ። በመጨረሻ ስልኩ ተንጫረረ ። ፒተር ይሆን? አለች በሀሳቧ ማንም ይሁን ደክሞኛል ፤ወሰነች ። አላነሳውም አለች ስልኩ መንጫረሩን ቀጠለ ። ፒተር ነው። ደህንነቷን ሊጠይቅ መሆን አለበት ። ላንሳው ይሆን? አዎ ማንሳት አለብኝ አለች። ስልኩ አላቋረጠም ። ተነሳች አነሳችው ።
«ሃሎ» አለች።
«ሚስ አዳምሰን?» አለ ደዋዩ። አምላኬ ምን አልኩሀ ?ፒተር አይደለም ። ራሱ ነው። አንድ ነገር የሰራ አካላቷን ገዘፋት ። ረጅም ትንፋሽ ከሰራ አካላቷ ወጣ። እንደምንም ብላ «በስላሴ ይዥሀለሁ ማይክ ፤ ተወኝ ! እባክሀ ተወኝ !» ብላ ዘጋች ስልኩን። ማይክል ግራ ተጋብቶ መነጋገሪያውን በአትኩሮት ተመለከተው። ምንድነው? ምንነካት?... ‹‹ደሞስ ለምን ማይክ አለችኝ?..»


በማግስቱ ጧት ሜሪ ከድንክዬ ውሻዋ ከፍሬድ ጋር ወደ ጋለሪው (የኢግዚብሽን አዳራሹ ) ስትገባ ደካክሟት ነበር ። ከፒተር ግሬግሰን ጋር ያጋጠማት አስደንጋጭ ነገር ትናንትን ደግማ እንድትኖረው አስገደዳት። ኬማይክል ሂልያርድ ጋር ለመኖር መጨረሻ የሆነችዋን ቀን በዚያች ሌሊት ከሀ እስከ ፐ አስታወሰቻት። ያንለት እሷና ማይክል ከሀርቫርድ ተነስተው በቢስክሌት ያደረጉት ጉዞ የላሱት የቀመሱት . . . ሁሉንም እንደገና አደረገችው ። የገቡትንም ቃል ... እስከ መቼም አልረሳህም ... እስከ መቼም አልረሳሽም ... ያችን ቀን ሺህ ዓመትም ብትኖር አትረሳትም ። መቶ ዓመት የኖረች ያህል ድክምክም ብሏታል ። እንቅልፍ ባይኗ ዘወር ሳይል ወገግ ነበር ያለው።

ይህም ስለሆነ የአዳራሹ ባለቤት የሆነው ጃክ ፤ልክ እንዳያት «ሌት ተቀን ሥራ ምንም ረፍት ያገኘሽ አትመስይምኮ የኔ መቤት» አላት «ወይስ ከውድ ዳይሬክተራችን ጋር ፓርቲ ቢጤ ወጥታችሁ አመሻችሁ!» ቡና ቀዳና ሰጣት ፤ከተቀመጠች በኋላ ። ጃክ የፒተር ግሬግሰን የቆዬ ወዳጅ ሲሆን ከናንሲ ጋር ከተዋወቁ ወዲህ እሷንም እየወደዳት መጥተዋል ። «ሥራ ያልከው ይሻላል እንጂ ፓርቲ አልነበረም። ደስም አይለኝም አለች » ሜሪ ፈገግ እያለችና የቀዳላትን ወፍራም ቡና ፉት እያለች ። ጃክ ሁሉ ነገር ከፈረንሳይ የመጣ ቢሆን ደስ ይለዋል « ልብሱ፤ ጫማው፤ ባርኔጣው ። ይህ የሚጠጡት ቡና ሳይቀር የፈረንሳይ የተፈጨ ቡና አዘጋጅ የቀመመው ነው። «ጅል የሆንሽ ልጅ »አለ ጃክ « አንችን መሰል ልጅ በዚህ እድሜው መጨፈር እንዳለበት ለምን ትረሻለሽ !»
‹‹ሁሉም ቀስ እያለ ይደረስበታል ። አሁን እስኪ ስራዬን ልጥገበው » ይህን ብላ ለወደፊቱ ልትሰራቸው ስላለመቻቸው ነገሮች መግለጽ ጀመረች ። በተለይ የቅርብ እቅዷ « የሳንፍራንሲስኮ የበረንዳ ሕይወት » የሚል እንደሚሆን ገልፃለት ነገሩን በእርካታ ተቀብለው እንዲህ ሲል « በጣም ግሩም የሆነ ሀሳብ ነው ። ከእንግዲህ ነገ ዛሬ ሳትይ እንደምትጀምሪ ተስፋ አለኝ »

ይህን አለና ቀና ብሎ ካያት በኋላ ጉዳዩን እንድታብራራለት ሊጠይቃት ሲል ፀሐፊው የቢሮውን በር ከፍታ አረ ዝም በሉ ጉድ-ነው ! የሚል የጣት ማስጠንቀቂያ አሳየቻቸው ። «ጉዳችን ! ምናልባት አንዷ የከንፈር ወዳጅህ መጥታ ይሆን?» አለች ናንሲ ፤ የውሸት እየደነገጠችና እያሾፈች ። «ይሆን ይሆን ?» አለ በውሸት ድንጋጤ። ከዚያም ወደ ፀሐፊዋ ሄዶ እየተንሾካሾኩ ማውራት ቀጠሉ ። ናንሲ ጃክን ስታይ ጉዳዩ ምን ይሆን ስትል አሰበች ። ምከንያቱም በጃክ ገፅታ ላይ የእውነተኛ አድናቆትና ደስታ ቅይጥ ጎልቶ ይታይ ነበር ። «አዎና እንዴታ !» አላት በመጨረሻ ለፀሐፊው ። ወጣች ፀሐፊዋ ጃክ እወንበሩ ላይ ከተቀመጠ በኋላ «የሚደንቅ ነገር ነው ። ትልቅ የምሥራች ይዥልሻለሁ ። ኣለ ጃክ ፤ ይህን ጊዜ የቢሮው በር ተንኳኳ ። «አንድ በጣም በጣም ታላቅ የሆነ ሰው ፎቶግራፎችኾን እንደሚፈልጋቸው በመጠቆም ሊፈልግሽ መጥቷል » አለ ጃክ ነገሩን ለማጤን ጊዜ አልነበራትም ። በሩ ተከፈቶ ገባ አየችው ማይክል ሂልያርድ ነበር። ማይክል ጠቆር ያለ ሰማያዊ ቀለም ያለው ኮትና ሱሬ ሲለብስ፤ በረዶ የመሰለ ነጭ ሸሚዝና ጠቆር ያለ ክራባት አድርጓል። ገና ሲያዩት ትልቅ ቱጃር መሆኑ ይታወቃል ። እንዲያ ሆኖ ሲገባ ስታየው ነፍሷ ምንጥቅ ብላ የወጣች መስሎ ተሰማት ። የያዘችው ትኩስ ቡና በእጅዋ ላይ ሊደፋ ምንም ያህል አልቀረውም ። ማይክል ሊጨብጣት እጁን እንደዘረጋ ስታይ በቀኝ እጅዋ የያዘችውን ሲኒ እቢሮ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጣ ጨበጠችው ። እንዴት ስሜቷን እንደተቆጣጠረች ለሷም ግልፅ አልሆነላትም እንጂ የጨበጠችው ረጋ ፤ ኮራ ብላ ነበር ። እሰው ቢሮ ውስጥ እንዲያ ተዝናንታ ተቀምጣ ሲያያት ማይክል በልበ ሙሉነቷ ተደነቀ ። ትናንት ማታ ስልክ ሲደውልላት ምናልባት ብትተወኝና ሰላም ብትሰጠኝ ያለችው ልጅ ይቺ ልትሆን እንደማትችል ገመተ ። መሆኑንስ ናት ግን ምን ነክቷት ነበር ይሆን ? በኔ ሳይሆን በአንድ ነገር ተበሳጭታ ይሆናል ። ይኸኔ አንድ ወንድ ይሆናል ያበሳጫታል ሲል አሰበ ። ወይስ ሰክራ ነበር ? ሰክራ ሊሆን ይችላል ። የጥበብ ሰዎች ሲባሉ ምናቸውም አይታወቅ ፤። ሀሳቡን ቀጠለ ። ማይክል ይህን ሁሉ ያስብ እንጂ ሀሳቡ በገጽታውም ላይ አይታይም ነበር ፤ የሷ መሸበርም እንዳልታየ ። « በመጨረሻ ተገናኘን ። በጣም ደስ አለኝ። እንዴት አድርገሽ አለፋሽኝ መሰለሽ ሚስ አዳምሰን አራወጥሽኝ እንጂ። የሆነ ሆኖ ይህን ችሎታ ይዘሻልና ልትኮሪ ይገባል እላለሁ » አለ ማይክል የደስ ደስ ያለው ፈገግታ እየለገሳት ። ሜሪ ከጠረጴዛው ማዶ ቆሞ ማይክልን ለመጨበጥ እጁን ወደ ዘረጋው ጃክ ተመለከተች ። ጃክ የኮተር ሂልያርድ ድርጅት የሜሪን ሥራ በመፈለጉ እጅግ ተደንቆ ተደስቶ ነበር ። ስለዚህም ማይክል ስላልጨበጠው ፤ ስለረሳው አልተናደደም የሱ ሀሳብ ፀሐፊዋ አነጋገረችው ነገር ላይ ነበር አሁን ሜሪ፡፡ ይቺ ኩሩዋና የመጣው ቢመጣ የማትደነቀዋ ሜሪ ሳትቀር በትንሹም ቢሆን በደስታ ሳትፈለቀቅ አትቀርም ሲል አሰበ አያት ። እሷ ያው ነበረች ፤ ፀጥ እንዳለች ። የገመተውን ያህል ቀርቶ በመጠኑ እንኳ ደስታ ፀጥታዋን አልገሰሰውም። «በቀጥታ ወደ መጣሁበት ቁም ነገር ልግባና ጉዳዩን ላስረዳችሁ ? » ሲል ጠየቀ ማይክል ። «እንዴታ » አለ ጃክ ማይክልን ተከትላ ገብታ እቢሮው ውስጥ የቆመችውን ፀሐፊ ለማይክል ቡና
👍22
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ አንድ (41) «ቢያንስ ምክንያቱን . . . ማለት የማትፈልጊበትን ምክንያት ልትገልጭልኝ ትችያለሽ?። አለ ማይክል በለሰሰሰ ድምፅ። እዚህ ድምፅ ውስጥ አዲስ ነገር ተሰማት ።
እዚህ ድምፅ ውስጥ ማይክል ያለውን ሥልጣን የሚያውቅ ሰው እንደሆነ ተገነዘበች። ይህን በራሱ ላይ ያለውን መተማመን ትወደዋለች ናፈቃት ። በዚህም ተናደደች ። ይህ ንዴት ግን የሙውደድም ሆነ የናፍቆት ስሜቷን ከልቧ ሊያወጣው አልቻለም ። «ለምን?» አለ ማይክል ደግሞ ። «ምናልባት ቅብጥብጥ ሰው ብሆን ይሆናል ። ቅጥየለሽ የጥበብ ሰው ብለህ ጥራኝ ብትፈልግ ። የፈለገውን ብትለኝም፣ ምክንያት ብነግርህ ባልነግርሀም መልሴ አንድ ነው .... አልችልም » አለች ።

ይህን ብላ ቡናዋን ጨልጣ ሲኒዋን ካስቀመጠች በኋሳ ከተቀመጠችበት ተነስታ እዚያው ቆማ ላፍታ ሁለቱን ሰዎች ተራ በተራ እየቻቸው ። ከዚያም እጅዋን ዘረጋች ። ማይክልን ስትጨብጥ በፅሞና ጨበጠችና « የፎቶግራፍ ሥራዎቼን ስለወደዳችሁልኝ አመሰግናለሁ ። ለስራችሁ መቃናት ደሞ ችግር አይኖርም ። የተሻለ ሰው ልታገኙ ትችላላችሁ እንዲያውም በዚህ አዳራሽ ሥራዎቻቸውን የሚያሳዩ ኢያሌ ሠዓሊዎችና ፎተግራፍ አንሺዎች ስላሉ በጃክ በኩል በቀላሉ ልትገናኙዋቸው ትችላላችሁ » አለች፡፡ «ሌላ ሳይሆን አንችን ነው እምንፈልገው » አለ ማይክል።

ማይክል ይህን ሲል ግትር እንደማለት ብሎ መሆኑ በድምጹ ይታወቅ ነበር። ቅሬታም ይሰማበት ነበርና ጃክ በይቅርታ አድርግልን አስተያየት አየው ። ሜሪ ግን ፍንክች አላለችም ። ከዚህ በፊት ያጠፋችው በቂ ነው ። በጥቅሟ ደሰታዋን ሸጣለች ። ዳግም? አይለምዳትም ። ስለዚሀም ፤ «ይህ እንኳ አጉል ነገር መሰለኝ ፤ ሚስተር ሂልያርድ ። የልጅ ነገር ሆነ ልበል። እኔ አይሆንም ካንተ ጋር አልሰራም ብያለሁ ። ስለዚህ ሌላ ሰው መፈለጉ ይሻላል ። ከዚህ የቀለለ ምንም ነገር ያለ አይመስለኝም » አለች ። «እኔን ተይኝ፤ ለድርጅቱ ከሌላ ሰው ጋርም ለመሥራት ፈቃደኛ አይደለሽም ? » በአሉታ ራሷን ነቅንቃ ወደ በሩ አመራች ። « ባይሆን አስቢበት ። አስበሽበት እንኳ ልትነግሪኝ አትሞክሪም» ይሀን ሲናገር እበሩ ዘንድ ደርሳ ነበር። ጥያቄውን ስትሰማ ፊቷን ወደነሱ ሳታዞር ቆመች ። የምታስብ ትመስላለች ። ካፍታ በኋላ ራሷን በአሉታ ነቅንቃ በሩን ከፍታ ስትወጣ «አይሆንም አልኩ » የሚለውን ቃል ሰሙ ። ፍሬድ (ውሻዋ) አብሯት ወጣ ።

ማይክል ጊዜ አላጠፋም ። ጃክን ሳይሰናበት ከመቀመጫው ብድግ ብሎ ተከትሏት እየተጣደፈ ወጣ። ጃክ ነገሩ ሁሉ መላቅጥ የጠፋው ሆኖበት ባለበት ላይ እንደተቀመጠ ቀረ ። « አንዴ….. ጠብቂኝ » አለ ማይክ ፤ ከአዳራሹ እንደወጣ ሜሪን እየጠራ ። ለምን እንዲህ እንደሚያደርግ ራሱን አልጠየቀም ። ይሀን ያህል መለማመጥ ይኖርብኛል ? አላለም ። ተከተላት ደረሰባት እና ጎን ጎኗን እየሔደ፤ « አብሬሽ በእግሬ ትንሽ መጓዝ ይፈቀድልኛል? » አላት፡፡ «ትርፉ ድካም ነው እንጂ ትችላለህ » አለችው ። አንዴም ዞር ብላ አላየችውም ። ቀጥታ ፊት ለፈቷን እየተመለከተች ጉዞዋን ቀጠለች ፤ እሱም በጎን በጎንዋ ። «ለምንድነው እንዲህ ክርር ብለሽ እምቢ ያልሽው ? የተቀየምሽበት ጉዳይ አለ ? በኔ ወይስ በሌላ ሰው ? ወይስ የሰማሽው ነገር አለ? ስለድርጅቱ ? ወይም ስለኔ » አለ ማይክል ። « ሰማሁ አልሰማሁ ፤ ተቀየምኩ ቀረ ልዩነት አያመጣም »
« ለምን አያመጣም ? ያመጣል ። በደምብ አድርጎ ልዩነት ያመጣል » አለና ፊት ለፊቷ ቆመ ። አቆማት ። ያዛትና፤ « ንገሪኝ ፤ መንገር አለብሽ ። የማወቅ መብት አለኝ። ። «መብት አለህ? » አለችው፡፡ ሁለቱም ፊት ለፊት ተፋጠው ቆሙ ። ለዘለዓለም አለም በዚህ ሁኔታ የቆሙ ያህል ነበር ። ከዚህ በኋላ ንዴቷ ጋብ አለ። ‹‹ነገሩ ምስጢር ነው » አለች ። «ደግ ፤ ግን ንክ እንዳይደለሽ ይገባኛል » ይህን ስትሰማ ከት ብላ ሳቀችና «እንደሆንኩስ ማን ያውቃል ? » አለች ። « ንክ ናት ብዬ ባምን ነገሩ ቀለል ይለኝ ነበር ።ግን መስለሽ አልታየሽም አይደለሽም ። የሚታየኝ ነገር ወይ እኔን ትጠያለሽ ወይ ኮተር ሂልያርድን » አለ ። በልቡ የማይረባ ሀሳብኮ ነው ። እኔንስ ምን አድርጌያት አውቄያት ? ኮተር- ሂልያርድስ ምን አድርጐ ? ኮተር ሂልያርድ ስሙን ጠብቆ ሸርና ማጭበርበር ካለበት ውል ተጠብቆ የሚኖር ድርጅት ነው ሲል አሰበ ። በመቀጠልም ይህ ፈፅሞ ሊሆን አይችልም ። ምናልባት፣ አዎ ምናልባት ካንድ የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ባልደረባ ከሆነ ሰው ጋር ኣንድ ግንኙ ፈጥራ በዚያ ቂም ይዛ ይሆናል ። እንዲያውም እንዲያ ቢሆን ነው አለ አሁንም በልቡ ። « አንተን አልጠላሁም ሚስተር ሂልያርድ » አለች ቆይታ። ጉዞ ጀምረው ነበር ይህን ስትለው ።

‹‹ግን እንዴት ያለሽ ተዋናይ ነሽ እባክሽ » አላት ፊቱ በፈገግታ ተሞልቶ ። ከተገናኙ ጊዜ ጀምሮ ይህን ማይክል አላየችዉም ይህ ያ ማይክል ነው ። ማይክል ፤ ያ የዱሮው፤ እሷ አፓርታማ ውስጥ ወይም እሌላ ቦታ ከቤን አቭሪ ጋር ነቃብህ የሚጫወቱት የጫዋታ ሸር የሚችለው ማይክል ነው... ይህኑ ያለፈ ጊዜ ነገር ስታስብ ልቧ ተሸነፈ ። ማይክልን ላለማየት ወዲያ ማየት ጀመረች ። « ቡና ልግዛልሽ ? » አላት ። አልችልም ልትለው አሰበች ። ግን ዶግሞ ሀሳቧን ለወጠች። ሁልጊዜ ከምሰቃይ ዛሬውኑ ተስፋ ላስቆርጠው ዳግም በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር የለብንም ስትል አሰበች ። ይህን አሳብም «ና ይቻላል » ስትል መለሰችለት ።

ወደ አንዲት ኤስፕሬሰ ሄዱ ። ወፍራምና ለየት ያለ ቡና የሚጠጣባት ቤት ። ሁለቱም ቡና አዘዙ ። ቡናው ሲመጣ ለሷ ከጨመረች በኋላ ሁለት አንኳር ስኳር የያዘውን ማቅረቢያ ሰጠችው ። ሳታስበው ሁልጊዜ ሁለት አንኳር እንደሚጨምር ታውቃለች ። እሱ ግን እንዴት አወቀች የሚለውን ጥያቄ አላሰበም ። ምክንያቱም ሀሳቡ እሷን በማሸነፍ ላይ ነበረና ትዝ ሳይለው ቀረ ። ስሩን ስለሰጠችው አመስግኖ ማስቀመጫውን እጠረጴዛው ላይ አኖረው በናውን እያማሰለ ወሬ ቀጠለ ። «ፎቶግራፎችሽን ሳይ አንድ ነገር ይሰማኛል ። ምን እንደሆኑ ሊገባኝ አልቻለም። ማለት ይኸ ነው ይኸ ልልሽ አልችልም አንድ የማይገባኝ ስሜት ግን እንዳለ እርግጠኛ ነኝ ምንድነው? እላለሁ ። አላገኘውም ፤ እንደ ጥንውት ቆጠሪው ። ምን ማለቴ ነው? አዲስ አይሆንብኝም ። ከዚህ በፊት ያየኋቸው በደንብ የማውቃቸው ይመስለኛል ። ልትይው የፈለግሽው የሚገባኝ ፤ ያየሽው የሚታየኝ ይመስለኛል ። ምን ማለት ነው ይኸ? የሆነ ትርጉም አለው ?»

አዎን ማይክል ። ደንበኛ ትርጉም አለው። ለሥዕል እመርጣቸው የነበሩ ሀሳቦችን ነው ለፎቶግራፍም የምመርጣቸው ። ሥዕሎቹ ደሞ እንዳንተ የሚገቡት ሰው አልነበረም ፤ አለች በሀሳቧ ።
👍22👎1
😘  #ቃል  😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ ሁለት (42)

ልክ እወደቡ ደርሳ የካሜራ መትከያውን ባለሶስት እግር  መቋሚያ እንዳስተካከለች አንድ ሰዉ ቀጥ ብሎ ወደ እሷ ሲመጣ ታያት ። አማመዱ ወደሷ መሆኑ አጠያየቃት፡፡  ማን እንደሆ አወቀች፤ ቆይታ ።
ማይክል !ጣጣ ነው ፤አለች በሀሳቧ።
«አንድ ነገር ልነግርሽ ነው የመጣሁት» አለ እፊቷ ተገትሮ። «መስማት አልፈልግም» አለችው ቀና ሳትል። «እሱ እንኳ ያስቸግራል ። ምክንያቱም ፈቀድሽም ቀረ እነግርሻለሁ ። እና ብታስቢበት ይሻላል ስለግል ሕይወቴ የሆነ ያልሆነ ነገር እየጎረጎርሽ ሀሳብ የመስጠት መብት የለሽም ። እንዲህ ያለህ ሰው ነህ እንዲህ አይነት ፍጡር ነህ ልትይኝ አትችይም። አታውቂኝም ፤ አላውቅሽም ። ይህን ለማለት ምን መብት አለሽ !?» አለ።

ትናንት የተናገረችው ቃል ሌሊቱን ሙሉ እንደጥርስ ህመም ሲጠዘጥዘው ነው ያደረው። «ስለኔ ስነምግባር አስተያየትም ሆነ ፍርድ ለመስጠት የሾመሽ ማን ይሆን ? የኛ ዳኛ ምን መብትስ አለሽ» ጦፈ ። «ምንም» አለች ረጋ እንዳለች ። « ግን ደግሞ የማየው ነገር ደስ አላለኝም » ይህን ስትል ቀና ብላ አላየችውም ። የካሜራ ሌንስ ትቀይር ነበር ። «ያየሽው ነገር ምን ይሆን እባክሽ ?»
«ዛጎል ። ቀንዳውጣው የሞተ በድን ቅርፊት ። ልቡ ፍቅርን የተራቆተ፤ ስራ ስራ ብቻ የሚል ሰው። ስለማንም ደንታ የሌለው ማንንም የማይወድ፤ ምንም የማይሰጥ ፤ ምንም ያልሆነ ባዶ ሰዉ ይህንን ነው ያየሁት ። »
«አንች ውሻ |! አንች ማን ሆነሽ፤ ምን አውቀሽ ነው ደሞ ስለኔ የውስጥ ስሜት ይህን ያህል እምታወሪው ! ለመሆኑ አንችን ሁሉን አዋቂ ያደረገሽ ማነው በይ!» አለ። ዝም ብላ ካሜራዋን አዙራ የአሸዋ ኮረብታ ላይ አነጣጠረች። «አንችን እኮ ነው እማናግረው! ሰሚኝ !» አለ ካሜራዋን ሊይዝ እየሞከረ ። ቀደም ብላ ፊት ለፊቱ ቆመችና አፈጠጠችበት። ከዚያም እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ «ለምን አትተወኝም ። ለምን እሰው ኑሮ ውስጥ ገብተህ የሰው ሰላም ትነሳለህ ?» አለችው ። «ማ ? እኔ ? እኔ አንች ኑሮ ውስጥ አልገባሁም ። እኔ ጥቂት ፎቶግራፎችን መግዛት ብቻ ነው እምፈልገው በቃ ። በተረፈ ያንቺን ኑሮም ፤ያንችን አስተያዬት አልሻም ። ፎቶግራፍ ! በቃ!» በንዴት መንቀጥቀጥ ጀመረ። እሷ ግን አልመለሰችለትም ። እንደቆመ ትታው ሄደች። አንድ ብርድ ልብስ ላይ የተቀመጠ የወረቀት መያዣ ቦርሳ አነሳች ፤ ዚፑን ከፍታ ከውስጡ አንድ የታጠበ ፎቶግራፍ አወጣች እና ፎቶ ግራፍ ነው የምትፈልገው አደል? ይኽውልህ ። ይኽን ወስደህ የፈለገህን ነገር አድርገው ። እኔን ግን ተወት አርገኝ። እሺ» ብላ ሰጠችው ። ተቀበላት ። አላነጋገራትም ። ሄደ ዞራ አላየችውም። ስራዋን ቀጠለች። ስራ ፤ ስራ ፤ሰራ። ጸሐይ ብርሃኗን ስትነሳ ካሜራው መስራት ሲሳነው ስራዋን አቆመች።

እቤቷ እንደደረሰች እንቁላል ጠብሳ በልታ ቡና አፍልታ ጠጣች በኋላ ወደ ፎቶግራፍ ማጠቢያ ክፍሏ ገባች። ያንለት የተኛችው ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ሲሆን ነበር ። ጧት በሁለት ሰዓት ለመነሳት ወስና ባለዶወል ሰዓቷን አስተካክላ ተኛች። ባለችው ሰዓት ነቃች። ደወሉ ቀሰቀሳት ። ሰውነቷን ታጥባ ፣ ልብሷን ለባብሳ፤ ቡናዋን እየጠጣች ጋዜጣዋን እንብባ ከቤቷ ስትወጣ ልክ ማታ ባቀደችው መሰረት ለሶስት ሰዓት ጥቂት ደቂቃ ይቀር ነበር ። ደረጃውን ስትወርድ ሁሉ የምታስበው ስለቀኑ ስራዋ ነበር። ፍሬድ ኋላ ኋላዋ ቱስ ቱስ እያለ እሷ እያሰበች ከቤት ወጡ፡፡ የውጪውን ደረጃ በመውረድ ላይ እንዳለች አንድ ደረጃ ሲቅራት ቀና ብላ ተመለከተች ። ከመንገድ ማዶ ማይክል ሂልያርድን ቆሞ አየችው። እጁን አውለበለበላት ። አጠገቡ ባለው የጭነት መኪና ላይ በትልቅ ሰሌዳ የተለጠፈ ስእል አየች ። ተመለከተችው ። ትናንት ጧት የሰጠችው ፎቶ ግራፍ ነበር ። ወስዶ በትልቁ ኦጉልቶ አሳጥቦ አንዳች በሚያህል ሰሌዳ ላይ ለጥፎ ይዞት መጥቷል ። ድንገት ሳቋ መጣ ። እደረጃው ላይ ቁጭ ብላ ትንከተከት ጀመር ። ፊቱ በፈገግታ በርቶ ሰውነቱ በደስታ ተሞልቶ ወደ ተቀመጠችበት መጣ፡። አጠገቧ ሲደርስ በፈገግታ እንደበራ በደስታ እንደተሞላ እደረጃው ላይ እጎኗ ተቀመጠ። «ቆንጆ ነው? ወደደሺው ?» ሲል ጠየቃት። «አንተ ግን የምትገርም ሰው ነህ!» አለችው ። «ልክ ብለሻል ። ግን እንዴት ነው? ደስ አይልም?» ሲል አሁንም ደግሞ ጠየቃት። ደስ ይላል ብትለው እንዴት አድርጎ ይደሰት። «እይው እስኪ፤ አሪፍ አሪፎቹን ፎቶግራፎች መርጠን ከፊሉን እንዲህ በትልቁ አሳጥበን እህክምና ማእከሉ አናት ላይ ብንሰቅላቸው ጉድ አይደለም ? » አላት ። ጉድስ ራስህ ነህ… ስትል አሰበች።፡ ደስ እንዳላት ሲያይ በጣም ደስ አለው ። ስለዚህም ነፃ ሆነ «አሁን እዚህ ምን ጎለተን? ተነሺና አንድ ቦታ ሄደን ቁርሳችንን እንብላ» አላት ።

ዛሬ ቆርጦ ተነስቷል ። እሺ ሳያስኛት ይች ቀን አታልፍም። ለዚህ ሲል ከሰዓት በፊት ያለውን ጊዜ በጠቅላላ ምንም ቀጠሮ አልያዘበትም ። እሷም ብትሆን ይህንን ውሳኔውን ከሁኔታው ተረድታለች። ውሣኔው ልቧን ነክቷታል ፤ አስደንቋታል ። በዚህም ላይ ጭቅጭቅ መፍጠሩን ስሜቷ አልተቀበለውም ። «እንሂድ» አላት ። «እምቢ ማለት ነበሪብኝ። ግን አልልህም» አለች፡፡ «ጥሩ ዘይደሻል ። አብረን እንሂድ?» ሲል ጠየቃት ። «በምን? በዚያ?» አለችው የጭነት መኪናውን እያሳየችው። ነገሩ አስቂኝ ሆነባት ። «ምናለበት ይሄዳል እኮ » አስተስማማች ።

አሳ አጥማጆች ወደሚመገቡት ሆቴል አመሩ ። መኪናውን እበሩ ላይ አቆሙት ። በዚያ አካባቢ የጭነት መኪና አዲስ አልነበረምና ማንም ጉዳዬ ብሎ አላያቸውም ። ገትረውት ወደቁርስ ገቡ። ማንም ያን ያህል ፎቶግራፍ አንስቶ ይወስዳል የሚል ፍርሀት አልነበረባቸውምና ጠባቂ አልፈለጉም ። ያንለት ቁርሱ ሳይቀር በሚያስገርም ሁኔታ ድንቅ ሆነላቸው። ቡናቸውን ጠጥተው እስኪጨርሱ ድረስ በመካከላቸፅ- ጭቅጭት አልተነሳም ። ያኔ… «አሁን ተስማማሽ አይደለም?» ሲል ጠየቀ ። ነገሩን በጥያቄ ያቅርበው እንጂ በፊቱ ላይ የሚታየው ፈገግታ ርግጠኛነትና ኩራት አረፍተ ነገሩን «አሸነፍኩሽ» የሚል ስሜት ስጥተውት ነበር ። «በፍጹም አልተስማማሁም። ሆኖም ደስ የሜል ቁርስ በላሁ ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍኩ» አለችው ። «ትንሽ ውለታ ሲውሉልኝ ውለታ አነሰ ብዬ በጥፊ የምመታ ሰው አደለሁም ። ሆኖም ያ ሙሉ መንገዴ አይደለም»
«ሙሉው ምንድ ነው? እስኪ ንገረኝ»
«አሃ! ስለኔ አንች መናገርሽን ፤ መፍረድሽን አቁመሽ እኔ ራሴ እንድናገር ፈቀድሽልኝ ማለት ነው?» ነገሩን እንደቀልድ ቢለውም በውስጡ ሽሙጥ ነበረበት ። «ባለፈው ቀን ያልሽው በመጠኑም ቢሆን እውነትነት አለው ። ለስራዬ ብዙ እጨነቃለሁ» አላት ። «ሌሳ የምታስብለት ምንም ነገር የለህም? ።»
«በእውነት ከሆነ ሌሳው ነገር ለኔ ይህን ያህልም አደለም። ምናልባትም ብዙዎቹ በኑሮ ተስተካክለዋል የምንላቸው ሰዎች ካለስራ ሌላ ሕይወት የላቸው ይሆናል ። ጊዜም ቦታም አይገኝ ?››
👍18🥰1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ ሶስት (43)


ሜሪ ስልክ በመደወል ላይ ነበረች፡፡ ለፒተር ግሬግሰን ። «መቼ አልሺኝ? ዛሬ» አለ ፒተር ግሬግሰን ‹‹ውዴ ዛሬ ስብሰባ አለብኝ »
«እንዲያ ከሆነ ስብሰባውን እንደጨረስክ እፈልግሃለሁ ። በጣም እፈልግሃለሁ ። ነገ መሄዴ ነው»
«የት ? ወዴት ? ለስንት ጊዜ!»
«ስትመጣ እነግርሃለሁ ። ዛሬውኑ ና ። ማታ»
«እሺ...ይሁን ። እሺ ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ። ግን ስብሰባውን… የቂል ሥራ መሰለኝ ። ሊዘገይ አይችልም»
«በፍጹም አይቻልም» አለች ። ሁለት ዓመት ሙሉ ቆይቷል ። ያን ያህል ጊዜ ማቆየቱም ራሱን የቻለ ቂልነት ነበር እብደት አለች በሐሳቧ ። «እሺ እንግዲህ እመጣለሁ » ዘጋ ። ወዲያው ወደ አየር መንገድ ቢሮ ደወለች ፤ቲኬት እንዲይዙላት ። ቀጥላም ወደ እንስሳት ሐኪም ደወለች ፤ ለፍሬድ ማቆያ እንዲያዘጋጅላት...

ያንለት ከሰዓት በኋላ ሜሪ ፌ አሊሰንን ለማነጋገር መደ መሥሪያ ቤቷ ሄደች ። ሜሪ ወደ ፌ መሥሪያ ቤት ከሄደች ወራት አልፈው ነበረና ወደ እንግዳ መቀበያው ክፍል ስትገባ ምንም እንዳልተቀየረና እንደ ተለመደው ምቹ እንደሆነ ተገነዘበች። እምቹው ወንበር ላይ ተቀምጣ እግሯን ፊት ለፊት ዘርግታ ጣቶቿን እየተመለከተች ቀስ በቀስ ሐሳብ ውስጥ ገባች ። ሐሳቡ ጭልጥ አድርጐ ወሰዷት ነበርና ፌ ስትግባ አልሰማቻትም ። «እንቅልፍ እየታገለሽ ነው ወይስ እጸጥታ ቁዘማ ላይ ነሽ ?» የፌ አሊሰን ድምጽ ከሐሳቧ የመለሳት ሜሪ ፈገግ ብላ ፊት ለፊቷ በሚገኘው ወንበር ላይ የምትቀመጠው ፌን በጸጥታ ተመለከተቻት ። «እንቅልፍም ቁዘማም አይደለም። ዝም ብሎ ሐሳብ ነው» አለች ሜሪ ። ፌ «ደግ» በሚል አስተያየት እያየቻት ፈገግታዋን መለሰችላት ። ሜሪ ፌን ስታይ ደስ አላት ይህንንም፡፡ «ናፍቀሽኝ ኖሯል ባክሽ ፤ ሳይሽ በጣም ደስ አለኝ» ስትል ገለጸችላት ። «ድንቅ ነገር ሆነሻል ልበልሽ ወይስ ከዚያም ከዚያም ስለምትሰሚው ሰልችቶሻል ?» አለች ፌ አሊሰን በፈገግታ በርታ። በፌ አሊሰን ፊት ላይ ያየችው ደስታ ተጋባባትና ሜሪም መሳቅ ጀመረች ። ቀጥላም «ድንቅ ነሽ መባል ምኑ ይሰለቻል ብለሽ» ስትል ተናገረች ። ይህን ስትል ደስ አላት ። ለፌ አሊሰን ባይሆን ይህን እውነት እንኳ ለመናገር አስቸጋሪ እንደነበር ታውቀዋለች ። «ዛሬ ደርሼ ዱብ ስል ለምን መጣች ? የሚል ጥያቄ እንደሚመጣብሽ መቼም የታወቀ ነው» አለች ሜሪ አዳምሰን ። «ጥያቄው ብልጭ ብሎብኝ ነበር» ፌ ግምቷን አረጋገጠችላት ። ፊት ለፊት ፤ ዓይን ለዓይን ግጥምጥም አሉ ። ቦግ ድርግም ፈገግታ ተለዋወጡ ። ከዚያም ሜሪን ሐሳብ ጠለፋትና ወደ ቁዘማዋ ገባች ። ስለተወሰነ ጊዜ ጸጥታ ሆነ ። ከዚያም ሜሪ ድንገት ቀና ብላ በቦዛዛ ድምጽ ማይክልን አገኘሁት'ኮ» ስትል ተናገረች ። «ሊፈልግሽ መጣ ? »
«መልሱ አዎም ሊሆን ይችላል አልመጣምም ሊሆን ይችላል ። ነገሩንኳ የፈለገው ያገኘውም ሜሪ አዳምሰንን ነው» ቀጥላም ማይክል ለምን እንደፈለጋት ባጭሩ ነገረቻት ። «ሦስቱም ሰዎች ይህን ያህል ለመኑሽ »
«ሽንጣቸውን ገትረው»
«ደህና ምልክት ይመስላል ። በነገራችን ላይ. . . ከሦስቱ አንዱም እንኳ ማን መሆንሽን አላጤነም'!? »
«ሁለቱ ወንዶች አላወቁም ። ማሪዮን ግን አውቃለች ። እንዲያውም ማይክልን የላከችውም አውቃ ነው የሚል ግምት አለኝ» ለተወሰነ ጊዜ ጸጥ አሉ
‹‹ስትገናኙ ምን ስሜት ተሰማሽ ? »
«ከማን ጋር ? »
«ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር»
«አስቀያሚ ፤ አስቀያሚ ስሜት ነበረ የተሰማኝ ። ልክ እንዳየኋት ያደረሰችብኝ ስቃይ ሁሉ ፍንትው ብሎ ታየኝ ። ጦላኋት››
‹‹እሺ››
«ምን ልበልሽ ? ያላሰብኩት ነገር አልነበረም የናቴ ምትክ እንድትሆን የተመኘኋት ፤ ብትወደኝ ብዬ ያለምኩዋት የማይክል ሚስት ለመሆን እምበቃ መሆኔን እንድትቀበል የጓጓሁት ። ያ ሁሉ ነገር ትዝ አለኝ»
«አሁንም የማይክል ሚስት ለመሆን አትበቂም እምትል ይመስልሻል ?»
«ያሁኑን አላውቅም ። ብቻ እንጃ ። አየሽ ያንለት እንዳየኋት ብዙው ነገሯ ተለውጦአል ። እንደመሰለኝ የፈጸመችው በደል ከብዷታል ። የተጸጸተችበት ይመስለኛል ። ለኔ ሳይሆ ለልጅዋ ይሆናል ። እንደገመትኩት ከሆነ ማይክልም የሚመስለውን ያህል ደስተኛ አይደለም»
«ደስተኛ አሊመሆኑ ሲሰማሽ ልብሽ ምን አለ ?»
«ቀለል አለኛ»

ሆኖም ለማጋነን የፈለገችውን ያህል አላጋነነላችም ቀለል ማለቱ ። እንዲያውም በኀዘን የተሰበረ ድምጽ ነበረ። ለተወሰነ ጊዜ ጸጥታ ሆነ ። «ቆይቼ ሳስበው ግን» አለች ሜሪ ጸጥታውን እየገሰሰች ፤ «ቆይቼ ሳስበው ግን ፤ እሱን ደላው ከፋው ለኔ ያው እንደሆነ ገባኝ ። የኔና የሱ ነገር ያበቃ ነገር ነው ፌ። ዛሬ እሱም አያውቀኝ እኔም አላውቀው ። ሁለታችንም በጣም ተለውጠናል ። ማን መሆኔን ቢያውቅ ሥራዬ ብሎንኳ ሊያነጋግረኝ አይፈልግ ይሆናል ። እኔ ናንሲ ማክአሊስተር ያልሆንኩትን ያህል እሱም ማይክል ሂልያርድ አይደለም »
«ያን ያህል እንደተለወጠ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ!»
«አየሁታ ! መራራ ፤ ጥድፍድፍ ሰው ሆኗል ። ልቡ ቀዝቅዞ ሰብአዊ ስሜቱ ሞቷል ።እዚሀ ሁሉ ውስጥ ምን እንዳለ እንጃ…. ያየሁት ባህርይ ግን አብዛኛው አዲስ ነው»
«የፈለጉት የማጣት ፤ ተስፋ የመቁረጥ ፤ የጥልቅ ሀዘን ስሜት አይታይበትም ?››
«የለም አልታየኝም ። ይልቅ እኔን ስለመክዳቱ ፣ ስለመምጣቱስ ምን ይሰማሻል ? ልትይኝ የፈለግሽ መሰለኝ ። ቁም ነገሩ ይህ አይመስልሽም ?››
«እኔ እንጃ ። እኔ እንኳ ይህን አላሰብኩም። ግን እስካሁን ይህ አይነቱ ስሜት አለብሽ ማለት ነው? በትለይም እንደከዳሽ ነው እሁንም የቆጠርሽው ? »
‹‹እንደከዳኝ እንጂ እንደሌላ ልቆጥረው እችላለሁ ? » አለች ከረር በለ ድምፅ « ፌ፣ ማይክልን እንዴት መሰለሽ እምጠላው ! ››
ያን የህል እጠላዋለሁ ብለሽ ካሰብሽ አሁንም ሀሳብሽ ሙሉ በሙሉ እሱ ላይ ነው ማለት ነው»

ናንሲ ይህ እውነት እንዳልሆነ ሽንጧን ገትራ ትከራከረች ። ምን ያህል እንደምትጠላው እምርራ ተናገረች ። ይህን እያደረገች ሳለችተም እንባዋ ተናነቃት ። አለቀሰች። ፌ አሊሰን ይህን ስታይ ነገሩን ለማለስለስ ፣ ሜሪን ላማፅናናት አልሞከረችም ። ይልቁንም የተነሳውን ነገር ፍርጥ ለማድረግ «ናንሲ ፤ ንገሪኝ ። ማይክልን ታፈቅሪዋለሽ ወይስ ፍቅርሽን ጨርሰሻል ? » ስትል ጠየቀቻች ። ናንሲ ብላ የጠራቻት አውቃ ነበር ። ናንሲ የፌ አሊሰንን ጥያቄ ለመመለስ ጊዜ ፈጀባት ። ስትመልስም ጣራ ጣራውን እያየች ሲሆን ድምጺም ደከም ያለ ነበረ ። « ናንሲ አሁንም ታፈቅረው ይሁናል ። መቼም የናንሲ ርዝራዥ ከውሰጧ አይጠፋም ። እሷ ትወደው ይሆናል ። ሜሪ ግን ማይክልን አትወደውም ። ሜሪ ማለት እኔ ነኝ ፣ፌ ። አዲስ ህይወት፤ አዲስ ዓለም ያለኝ ሰው ነኝ ። ልወደው አልችልም ማይክልን!»
«ለምን እትችይም ?››
«ምክንያቱም እይወደኝም ። እርሉን መርሳት ኣለብኝ፣ ፌ ፈጽሞ መርሳት አለብኝ ።ይህን ወስኛለሁ ፣ አውቀዋለሁ ። ስለዚህ ይህን ላማክርሽ ፣፡ ስለማይክል ፍቅር አንስቼ ኣንገትሽ ስር ተወሽቄ ላለቅስ አይደለም የዛሬው አመጣጤ ። የተሰማኝን ነገር ላንድ ስው መንገር እንዳለብኝ በመግመት ነው። ለፒትር ብነግረው ጥሩ ነበር፡፡ ግን ይህን ለሱ መንገር ደግሞ የማይቻል መስሎ ታየኝ ። መንፈሱን ይረብሻዋል ብዬ ገመትኩ ። ለለዚህ ቀለል እንዲለኝ ላንቺ መንገር እንዳለብኝ ገባኝ ። ሙጣሁ»
👍16
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ አራት (44)


«ሁሉን ነገር የማራገፍ ጉዳይ ። እኔና ማይክ ኣንድ ላይ በነበርንበት ጊዜ በጋራ የአደረግናቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ ። እስከዛሬ ድረስ ማይክል ይመለሳል ፣ ያስበኛል ፤፣ ይፈልገኛል እያልኩ የተውኳቸውን ነገሮች ማለቴ ነው ። ለፍቅራችን ሀውልት እንዲሆኑ ብዬ ነበር የተውኳቸው ። አሁን በቃ ። ሄጄ አንድ ነገር ላደርግ ወስኛለሁ»
«እምትችይ ይመስልሻል ?»
«በሚገባ» አለች ፌ እሊሰንን እንኳ ቆራጥ መስሎ በተሰማት ድምፅ።
«ከዚህ ሁሉ በፊት ማን እንደሆንሽ ፤ ማን እንደነበርሽ ለማይክል መንገር አትፈልጊም ? »
«ፍጹም የማይሞከር ነገር ነው» አለች እያንገፈገፋት «አለቀ ደቀቀ ፤ አልኩሽኮ በቃ ። በዚያም ላይ ይህን ባደርግ ለፒተርም መልካም አይሆንም» አለች የሀዘን ትንፋሽ በረጂሙ ተንፍሳ ። ቀጥላም… ‹‹ፌ» አለች ። «ፌ ፣! ፒተርን ላስቀይመው አልፈልግም። ፒተር ጥሩ ሰው ነው ። የዋለልኝ ውለታ ተቆጥሮ እሚያልቅ እይደለም «ያም ሆነ ያ አታፈቅሪውም» አለች ፌ አሊሰን ። «አይምሰልሽ እወደዋለሁ»
«ታዲያ ቃል ለመግባት እወድሀለሁ ብሎ ለመንገር ችግሩ ምንድነው!!?»
‹‹ማይክል ይመስለኛል ። ማይክል በመካከላችን ገብቶ ድንቅር ይል ስለነበረ ነው ብዬ አምናለሁ»
«እሱ ቀላል ነገር ነውኮ ሜሪ ። ስሜትን መሸፈኛ ካልሆነ በስተቀር እሱ ነገር አልቆለታል ብለናል ገና ዱሮ»
«ብቻ እንጃ» አለችና ንግግሯን አቋረጠች ፤ ‹‹ብቻ አንድ ነገር አለ ፤ ለፒተር ቃል እንዳልገባ የሚገረግረኝ ፤ ተይ የሚለኝ ። አንድ የጎደለ ነገር አለ ።ምናልባት... ብቻ ማይክልን ተውኩት ብልም ከልቤ አላወጣሁትም ነበር ። ከፊል ልቤ ይመጣል የሚል ተስፋ ላይ ሙጭጭ ብሎ ተጣብቆ ይሆናል... . ብቻ እንጃ አንድ ልክ ያልሆነ ነገር ቢኖር ይሆናል ። ምናልባትም እኔው ራሴ እሆናለሁ»
«ልክ ያልሆነ ነገር ይኖር ይሆናል ብለሽ እንድታስቢ የሚያደርግሽ ምን ይመስልሻል ? »
«ይህንንም በቅጡ አላውቀውም ። ምናልባት ፒተር ይወደኛል እንጂ አያውቀኝም የሟል ሀሳብ ሳይኖር አይቀርም በኔ በኩል።... ፒተር ያውቀኛል ፤እኔን ሜሪ አዳምሰንን ማለቴ ነው ግን ያለፈ ህይወቴን አያውቀውም ። ባለፈ ህይወቴ የምወዳቸውን ነገሮች አያውቅም»
«አትነግሪውም ? ማለት እንዲያውቅ ማድረግ አትችይም ?»
«ምናልባት እችል ይሆናል ። ግን ደግሞ ማወቅ እሚፈልግም ኦይመስለኝም ። መፈቀሬን እንዳውቅ ሊያደርግ ሲሞክር አየዋለሁ። ግን ደግሞ ሙሉ እኔነቴን እንዳልሆነም እጠራጠራለሁ»
«ያን ካነሳን ብዙ ነገር ሊመጣ ይችላል»
«ልክ ነሽ ።ያም ሆኖ ግን ፒተር ደህና ሰው ነው። በፈለግኩት መንገድ ብሞክር ጉዳዩ የማይሳካበት ምክንያት አይታየኝም»
«ሊሳካ የሚችለው ካፈቀርሺው ብቻ ነው»
«አፈቅረዋለሁና»
«በሱም ካመንሽበት ደህና ። ዘና ብለሽ የሚሆነው እስኪሆን ጠብቂ ። ከፈለግሺም እንዲህ እንደዛሬው ጎራ እያልሽ ልንማግከርበት እንችላለን… ወደሬት ። ለዛሬ ግን ስለማይክል ምን ፤ ምን እንደሚሰማሽ ተነጋግረን መጨረሻውን ማየቱ ነው ደጉ»
«ይህን የቦስተን ጉዞዬን ላድርግና ሁሉን ነገር ላራግፍ ። ከዚያ በኋላ ነፃ እሆናለሁ»
«መልካም ። ስትመለሺ ጎራ በይና ጠይቂኝ ። እንዲያ ማድረጉ ጥሩ አይመስልሽም ?»
«በጣም እንጂ !» ሜሪ አዳምሰን ሁሉ ነገር ቀለል ያላት ሆና ታየች ።

ፌ አሊሰን ሰዓቷን አይታ ዩኒቨርስቲ ማስተማር ስላለባት ልትለያት መሆኑን በማሰብ የመከፋት መልክ ታየባት ። ከዚያም «እንግዲህ እንዴት ነው እምናደርገው ? ከቦስተን እንደተመሽ ደውለሽ ቀጠሮ ብንይዝ አይሻልም ?» ስትል ጠየቀቻት ። ‹‹ልክ እንደደረስኩ እደውልልሻለሁ »
«መልካም ። እና ደሞ ራስሽን ጠብቂ፣ እሺ? ያለፈ ነገር እያስታወሱ በትዝታ መናበዝ አያስፈልግም ። ቦስተንም ሆነ የት ችግር ካጋጠመሸ ደውዬልኝ ።» ፌ አሊሰን ይህን ስትላት ሜሪ ተደሰተች ።እገሌ አለኝ ብሎ ማሰቡ ራሱ ትልቅ ነገር እንደሆነ ገባት ።

ያንለት ከፌ አሊሰን ጋር ተነጋግራ ስትመለስ ሰሞኑን ከብዷት የነበረው ነገር ሁሉ ቀላል ሆኖ ታያት ። ስሜቷም ፈካ ። የዛሬው የፌ አሊሰንና የሷ ንግግር የሚሰማትን ነገር ለፒተር ግሬግሰን ለመግለፅ መንገድ እንደጠረገላት ፤ ውሳኔዋንም ለመንገር ቀላል እንዳደረገላት ተገነዘበት ።
👍15
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ አምስት (45)

ጧት ወደ ቢሮው እንደገባ አውሮፕላን ጣቢያ ደውሎ ሜሪ አዳምሰንን በስልክ አነጋገራት ። መሄድ ከፈለገች መቸስ ምን ማድረግ ይቻላል በማለት እንጂ የሜሪ ወደ ቦስተን መሄድ ደስ አላሰኘውም ። እንዲያውም ምንነቱን አይወቀው እንጂ ደስ የማይል ስሜትም አሳድሮበታል ። አስጨንቆታል ። «ዶክተር ግሬግሰን» አለች ጸሐፊው «አቤት» አለ ፒተር ግሬግሰን ፤ ከሐሳቡ እየባነነ እና ቀና ብሎ እያያት ። «ማይክል ሂልያርድ እባላለሁ የሚል ሰው ቀጠሮ አለኝ ይላል ላስገባው?»
«አዎ አስገቢው»
«ሌሎች ሶስት ሰዎችም አብረውት አሉ»
«ሁሉንም አስገቢያቸው» ጸሐፊዋ ስትወጣ ፒተር ማይክል ሂልያርድን ማየት እንደሚፈልግ ተረዳ ። ገና ባይኑ ሳያየው ስለ ለማይክል ከጋዜጣ ባነበበው እና በግምት ከተረዳው በመነሳት ማይክል ገና ወጣት እንደሆነ ያውቃል ። ፒተር ሊወልደው ይችላል ። ምን ዓይነት ሐሳብ ነው ! ሜሪ ይህን የመሰለ ነገር አስባ ታውቅ ይሆን ? አራቱ እንግዶች ወዶ ፒተር ግሬግሰን ቢሮ ገቡ ። ተጨባበጡ ። ተዋወቁ ። ጊዜ አላባከኑም ። ወዲያው የመጡበትን ጉዳይ ጀመሩ ። የኮተር ሂልያርድ ግዙፍ ድርጅት በሳንፍራንሲስኮ ለሚሠራው የሕክምና ማዕከል በተለያዬ መንገድ የሚረዱትን የሕክምና ባለሙያዎችን በማስተባበር ላይ ሲገኝ ፒተር ግሬግሰንም በዚህ የባለሙያዎች ቡድን ውስጥ እንዲገባ ለመጠየቅና ሁኔታውን ለማስረዳት ነበር የመጡት ። በሳንፍራንሲስኮ ከሚገኙት በርካታ በርካታ የህክምና ባለሙያዎች መካከል ዚህ በፊት አስራ አምስቱን አነጋግረው የአዎንታ መልስ እንዳጥኙና ቡድኑም ሥራውን እንደጀመረም አስረዱት ።

ይህን ሁሉ ከሰማ በኋላ ፒተር ግሬግሰን አሉታዊ መልስ ሊሰጥ አዳጋች ሆነበት ። ዳሩ ሲጀመርም አሉታውን መልስ አላሰበውም ። ስብሰባውን የሚከታተለው አስቀድሞ ባሰበበት መሠረት ስለነበረ ብዙም አልተመሰጠበትም ። እሱን የመሰጠው ማይክል ሂልያርድ ነበር ።
ማይክል ሂልያርድ ።
የሚያስፈራ ጠላት አይደለም ። ወጣት ነው ። ቆንጆ ነው። በራሱ የሚተማመን ሰው መሆኑ በግልጽ ይታያል ። ግን ክፉ ሰው አይደለም ። እንደ ጠላት አያስፈራም ።
ማይክል ሂልያርድ ።
ራሷ ሜሪን ነው። ልክ ነው። ብዙ የሚመሳሰሉበት ነገር አላቸው ። ድፍረታቸው ቆራጥነታቸው በራሳቸው መተማመናቸው ቀልዳቸው አዎ ቀልዳቸው ሳይቀር ተመሳሳይ ነው ፣ አዎ። ፒተር ማሬግሰን ይህን ሲረዳ ደነገጠ ። ሁሉ ነገር ድፍንፍን አለበት ። ጸጥ ብሎ ዓይኑን እማይክል ሂልያርድ ላይ ተክሎ ተቀመጠ ። ስብሰባው… አዎ ስብሰባው በመካሄድ ላይ ነበር ግን... ግን ፒተር ግሬግሰን አዲስ ቃል አልሰማም የሁለቱን ፤ የማይክልንና የሜሪን ተመሳሳይነት ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ ቀስ እያለ ፤ ራሱን እያለማመደ ፤ ልቡን እያዋዛ እውነቱን ሊጋፈጠው ሲሸሸው የነበረውን ነገር ሁሉ ሊመረምረው ቆሪጠ ።

ቦስተን… ሜሪ ቦስተን የሄደችው ለምንድነው ? ትዝታዋን ለመቅበር ለማራገፍ ወይስ ለማክበር ለመሳለም ?... ግን እኔ ማነኝ ? ምንድነኝ?-... . አሰበ ። ልቡ ሜሪን መከጀል አልፎም ማፍቀር እስከደረሰበት ጊዜ ራሱን ጠይቆት የማያውቀውን ጥያቄ ጠየቀ ። ለመሆኑ እኔ ምንድን ነኝ? ማነኝ ?! አለ። የሆነው ሆነና በኒህ ሁለት ፍቅረኞች መካከል መግባት አለብኝ ? ፍቅራቸውን የማበላሸት መብት ማን ሰጠኝ? አለ። እንዲህ እያለ ማይክን አየው። ሜሪ… ማይክል። ማይክል ሂልያርድ የሜሪ አዳምሰን ክፋይ ነው። ሌላዋ ሜሪ ነው። ፒተር ግሬግሰን የሚያውቃት ሜሪን ነው። ያችን ሜሪ ፒተር አያውቃትም። ብቻ ያች አደጋው ከመድረሱ በፊት የነበረችው ሜሪ ፣ ሜሪ አልነበረችም ። ናንሲ ማክአሊስተር ነበረች ። ፒተር ግሬግሰን ደግሞ ናንሲ ማክአሊስተርን አያውቃትም ። ላውቃት አልፈለግኩም፤ እለ በሐሳቡ ። አዎ ፡ እሱ ሜሪን እንጂ ናንሲን ማወቅ አይፈልግም ። ሜሪ ከፊል ፍጡሩ ናት። ያችን ያለፈ ሕይወት ያላትን ያችን የሚጥም ትዝታ ፤ የሚመር ትውስታ ያላትን ናንሲን አያውቃትም። ሊያውቃት አይፈልግም ። እንኳን እሱ ሊያውቃት መፈለግ፤ እሷም እንድትረሳት፤ ሜሪም ሜሪን እንጂ ናንሲ ማክአሊስተርን እንደሌለች ፤ እንዳልነበረች እንድትቆጥራት ይፈልጋል ። ግን ይህ ሁሉ ከንቱ ነበር። ከሜሪ አዳምሰን ሌላ፤ በሜሪ ውስጥ ናንሲም ትኖራለች። ፒተር አይኑን ጨፍኖ የለችም እያለ ቢኖር እንጂ ለካ ናንሲን ሁልጊዜ ያያት ነበር… በሜሪ ውስጥ ። ናንሲን ባየ ቁጥር ፤ ናንሲ መሆኗን መመርመርን ስለሚሸሽ ለራሱ እንኳ አንዳንዴ ጠባይዋ እንቆቅልሽ ይሆናል ብሉ ነበር የሚነግረው ። እንጂ ናንሲስ ሁልጊዜም በሜሪ ውስጥ ትኖር ኖሯል ። አሁን ግልፅ ሆኖ ታየው ። ተስፋ ቆረጠ ። የማይዋጉትን ጦርነት ነበር ስዋጋ የኖርኩት ሲል አሰበ ። ሜሪን ሲፈጥራት ፒተር አንድ ነገር ሞክሯል ። ስለዚህ ሜሪ አዲስ ሰው ነበረች። ከመቃብር ሊያወጣት የፈለጋት ሴት ነበረች በመጠኑ የዚያች ሴት ደም ነበራት ። እሷ ነች እያለ እያሰባት። ሟችቷ ፍቅረኛው እየመሰለችው ።

ሊቪያ… የሊቪያን ደም ከገፅታዋ ላይ ስሎ። ምናልባትም ይህን ማድረግ አልነበረበትም ይሆናል ። ይሆን ማድረግ ተገቢ አልነበረም ይሆናል ። ከዚህ በፊት እንዲህ ልጓሙን ለቆ ሙያውን በፈለገው መንገድ የጋለበበት ጊዜ እልነበረም ። በሽተኛው እንደፈለገው ወይም የበሸተኛው ቤተሰብ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ነበር የሚሠራው ። ሜሪ ግን ... ሜሪ ግን፤ ያለሱ ያለፒተር ግሬግሰን ማንም አልነበራትም። ይህ ደግሞ የፈለገውን እንዲሆን ነፃነት ሰጠው ። የፈለገውን እንዲሆን ነፃነት ሰጥቶት ቆዬ ። አሁን ግን ያ ነፃነት ምኞት፤ ተስፋ ሆኖ ታየው።
ማይክልን ሲመለከት ...
አዎ እኔ ለካ ለሜሪ የአባት ያህል ነበርኩ ነኝ ። አባቷ ነኝ አለ፤ በሀሳቡ። ሜሪ ይህን ላታውቅ ትችላለች፡፡ ሆኖም ትደርስበታለች። ይዘገያል እንጂ ትደርስበታለች። አራቱ ሰዎች ጉዳያቸውን ፈፅመው ተነሱ። ስብሰባው ተፈፀመ ከማይክል ጋር የመጡት ሶስት ረዳቶቹ ፒተርን ተሰናብተው። ማይክል ግን ወደ ኋላ ቀርቶ ነበረና ሶስቱ ረዳቶች እንግዳ ማረፈያ ክፍል ውስጥ ሆነው ይጠብቁት ነበር ።

ማይክል ወደኋላ የቀረው የተለየ በቆይታ የሚነጋገርበት ነገር ስለነበረም አልነበረም ። ከፒተር ግሬግሰን ጋር ይበልጥ ለመግባባት እንዲረዳው ቀልዳ ቀልድ ፤ ገራ ገር ነገር ለመነጋገር ነበር፤ ሆነ። ፒተርና ማይክል ቆመው ገራገሩን ሲያወሩ፡፤ ሲሳሳቁ ሳለ ድንገት አንድ ነገር ተፈጠረ። ገራ ገሩ ቀልዳ ቀልዱ ወሬ ቀጥ ብሎ ቆመ። ይህን ያመጣው የማይክል ሂልያርድ አይን ነበር። ከፒተር ጋር እየተጨዋወቱ ሲሳቁ አይኑ በፒተር ትከሻ ዘሎ አልፎ አንድ ነገር ላይ አረፈ። አንድ ቅብ ስእል ላይ። ሁሉ ነገር ፀጥ አለ።

ያን ስእል ማይክል ያውቀዋል። የሷ ነው። የናንሲ ነው ። ስትስለው፣፤ ስትጀምረው አይቶታል ። እነዚያ ነርሶች ... ወደ ቦስተን አፓርትማዋ ሄዶ እቃዋ ሁሉ እንደተወሰደ አይቶ ሲጠይቅ ሁለት ነርሶች መጥተው የሳለቻቸውን ስእሎችና አንዳንድ እቃዎቿን እንደወሰዱ ተነግሮት ነበር ። ይህን ስእል ማይክል አይረሳውም ። በሐሳቡ « እንዴት ልርሳው ! ሰሰርግህ በስጦታ መልክ አበረክትልሀለሁ ብላኝ ነበር» አለ ። ደነዘዘ። የሚያደርገውን የሚሰራውን አያውቅም ነበር ። ስእሉ አልቋል ። ማን ጨረሰው?
👍21🥰1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ ሰድስት (46) ‹‹እሷማ ነግራሃለችኮ ተወኝ ብላሃለችኮ» ፒተር ረጋ ባለ ድምፅ ነበር ይህን የተናገረው… ማይክልን ፊት ለፊት በጠንካራ አስተያዬት እያየ። ማይክል ይህን ሲሰማ ደነገጠ ። ሳያስበው ወደኋላ አፈገፈገ።
ደነገጦ እንጂ በአይኑ ውስጥ ተስፋ ይነበብ ነበር ። አይኑም ገፅታውም ተስፋውን ድንጋጤውንና ግራ መጋባቱን ያሳዩ ነበር፡፡ ከሁለት አመት በኋላ ነፍስ ዘርተው ። «ግሬግሰን አትሳሳት ። ተወኝ ያለችኝ ሜሪ አዳምሰን ናት ። ናንሲ ማክአሊስተርን አላነጋገርኳትም ። ሁሉንም ከሷ መስማት እፈልጋለሁ። ያ ብቻ አይደለም ። ብዙ ምርመራም አለባት። ሁለት አመት ሙሉ ለምን አልነገረችኝም? ለምን በሕይወት መኖሯን አልገፃለፀችልኝም ? ሞተች ብለው የነገሩኝ፤ ፈቅዳላቸው ነው ወይስ ... የሌላ ሰው ሀሳብ ነው ? ይኸ ሁሉ አለ ። ትጠየቃለች ። ይኽ ሁሉ ሆኖ ግን ...› አለና ንግግሩን አቋረጠ ። ጥያቄውን ከመጠየቁ በፊት መልሱን አወቀው። ቢሆንም ርግጠኛ መሆን አለበት ስለዚህ ጠየቀው ፤ «ማነው ለህክምናው የከፈለላት ?»
«ብዙ ጥያቄዎች አቀረብክልኝ ።የሁሉንም መልስ እማውቅ አይመስለኝም ፤ ባውቅም... እንደልቤ መልስ ለመስጠት የሚያስቸግሩኝ ናቸው »
«ተው ። እንዲያ ብለህ አት ....» ማይክል ይህን ብሎ ወደ ፒተር ተንደረደረ ፤ ሊያንቀው ።
ሆኖም ፒተር ብልህ ስለሆነ በቃ የሚል ምልክትና ማረጋጊያ አሳየው ፤ መዳፉን በማንሳት ። «ለቀዶ ጥገናው ሕክምናና ለመኖሪያዋ የሚሆነውን ገንዘብ የከፈለቸው እናትህ ናት ። በጣም ከፍተኛ ልግስና አድርጋለች ›› ማይክል የፈራው መልስ ይህን ነበር። ግን ያሰበውን ያህል አላስደነገጠውም ፤ አልሰቀጠጠውም። ይህን ሁሉ ሲያስበው ካጠነጠናቸው ነገሮች ጋር ይገጥማል ። አትጠቅመውም ብላ ይሆናል፡፡ መሳሳት ልማዷ ነው ማሪዮን… ማይክልን በሚመለከት ጉዳይ ላይ አሁን ደግሞ ወደ ሜሪ የላከችው እንዲገናኙ ፈልጋ ሊሆን ይች ይህን አሰበ ማይክል ። «ያንተስ ? ማለት ያንተና የናንሲ ግንኙነት ምንድነው ግልዕ አድርገህ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ »
«ያን እነኳ አንተን የሚያገባህ አልመሰለኝም »
«ስማ ጋግርት…» እንደገና በኮሌታው እንቅ አደረገው ። ፒተር እጁን አነሳ መሸነፉን ለመግለፅ ። እና «እኔና አንተ ይህን ነገር ብንተወው ምናለበት ? ሜሪ አለች አይደለም ? መልስሀን ሁሉ ከራሷ ታገኛለህ ። ጥያቄህን ሁሉ እሷኑ ጠይቃት» አለና ተቀመጠ ። «እኔ እንደሆንኩ አባቷ እሆናለሁ ። እንደኔ እንደኔ ከኔም ካንተም እሷ የተሻለውን መርጣ ታደርጋለች»
«ምናልባት ይሆናል ። ግን ይህንም ቢሆን ከሷው መስማት ነው እምፈልገው ። እንዲያውም አሁኑኑ እጠይቃታለሁ ፤እቤቷ ድረስ ሄጄ »
«ወደ ቤቷ መሄድህ እንኳ ዋጋ የለውም»
«ለምን ?»
«የለችም ። አታገኛትም» ማይክል ግራ በመጋባት ይመለከተው ጀመር ።
«እናንተ እቢሮዬ የገባችሁት ከአየር ማረፊያ ስልክ ደውላልኝ ተነጋግረን እንደዘጋሁት ነው»
«የት ሄደች ? ወዴት ሄደች ደሞ አሁን » ፒተር ለጥቂት ጊዜ ያህል ዝም ብሎ ቆዬ ። ልንገረው አልንገረው አለ ። መንገር የለበትም። ምንም ነገር መንገር አልነበረበትም። « ወደ ቦስተን ነው የሄደችው»

ይህን ሲሰማ ማይክል ለቅፅበት ያህል አይኑን በፒተር ላይ አሳረፈ ። ፈገግታ ቢጤ ፈቱን ዳሰሰውና አለፈ ። ወደበሩ የሄደው በሩጫ ነበር ። በሩን ከፍቶ ሊወጣ አሰበና ቆመ ። ዞረ ። እንዳበባ በፈካ ፈገግታ ለፒተር ስንብቱን አቀረበ ። እና… «አመሰግንሃለሁ» አለ ።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

ጐሀ ሲቀድ ከመኝታዋ ተነሳች ። ድቅስቃሱ ሁሉ ለቅቋት ሙሉ በሙሉ ሕያው ሆና ። ዝንተ ዓለም ያልተሰማት መልካም ሰሜት ተሰማት ። አሁን ነፃ ናት ። ነፃ የሆነች ያህል ነው ። ተቃርባለች ። ከሁለት ሦስት ሰዓት በኋላ ሙሉ በሙሉ ነፃ ትሆናለች ። ከታሰረችበት ትፈታለች ። ያ የልጅነት ቃል ኪዳን ያ የሕፃን ጨዋታ ይህን ያህል ጊዜ ይሠራል ! ፈቀደችለታ ። የዚያ ቃል የማሰር ኃይሉ ፤ እሷ ፈቅዳ የለጠፈችበት ኃይል ብቻ ኖሯል ለካ ። ቁርስ በመብላት እንኳ ልትዘገይ ፤ ልትቸገር አልፈለገችም ። በቁርስ ፋንታ ሁለት ሲኒ ቡና ጠጣች ። ከዚያም እተከራየችው መኪና ውስጥ ገብታ ጉዞዋን ቀጠለች ። መንገዱ ሁለት በዓት ያሀል ቢፈጅባት ነው ፤ ከቦስተን እስከ ጉዳይዋ ያለው መንገድ ። አራት ሰዓት አካባቢ ትደርሳለች ። ቀትር ላይ ተመልሳ ቦስተን ትደርሳለች ። ወዲያው ወደ አየር ማረፊያ መሄድ ነው ። ወደ ሳንፍራንሲስኮ የሚጓዝ አውሮፕላን ብታገኝ . . . መሸትሸት ሲል ሳንፍራንሲስኮ ከች ነው ። ከቀናትማ ፒተር ከቢሮው ሳይወጣም ልትደርስ ትችላለች ። ያ ከሆነ ደግሞ በቀጥታ ወደ ፒተር ቢሮ ሄዳ ሳያስበው ዱብ ብላ ልታስደምመውም ትችላለች ። ምስኪን ፒተር ፤ እሄዳለሁ ስለው እኮ በጣም ተጨንቋል ። ግን ታገሰ፡፡
👍22
😘  #ቃል  😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አርባ ሰባት (47)

ሁሉም ነርገ እንዳለ ነው። ከሷና ከማይክል በስተቀር ። እሷና ማይክል ግን ወዶ ተቃራኒ አቅጣጫ ተጉዞዋል፡፡ ላይገናኙ ተለያይተዋል ። ረዘም ላለ ጊዜ እድንጋዩ አጠገብ ቆመች፡፡ ሀይል ከማጠራቀም የፈለገች ይመስል ። በመጨረሻ ጎንበስ ብላ ድንጋዩን ለማንሳት መታገል ጀመረች። ድንጋዩ ቀስ በቀስ መንቀሳቀስ ጀመረ ። የነበረበትን ቦታ በእንጨት ቶሎ ቶሎ ጫረች ። አለ ብላ ያሰበችውን እዚህ ድረስ ያመጣትን ነገር ለማግኘት ። አንድም ነዢ አልነበረም ። ድንጋዩን ለቀቀችው ። ወደ ቦታው ተመለሰ ። ተስፋ አልቆረጠችም። በእልህና ባዲስ ጉልበት ብድግ አደረገቺው ይኸኔ ግን በጣም ስላነሳችው የፈለገችው ነገር የነበረበት ቦታ ባዶ ሆኖ ታያት ። አንድ ሰው ወስዶታል ። እኒያን የአንገት ጌጥ መቁጠሪያዎች አንድ ሌላ ሰው ወስዷቸዋል ። ድንጋዩን ስትለቀውና ቦታውን ሲይዝ ሰማች ፤ ድምጹን ።

« ያንችን ያልሆነ ነገር ለመውሰድ መሞከር የለብሽም ። ጌጦቹ የሌላ ሰው ናቸው ። እኔ አፈቅራት የነበረች ልረሳት ያልተቻለኝ … የሷ ናቸው » አየችው ። ማይክል ነበር ። ዓይኖቹ በእንባ ረጥበዋል

እኩለ ሌሊት ላይ ነው እዚህ ቦታ የደረሰው ። በሌሲት ልትመጣ ትችላለች ብሎ ስላሰበ ሲጠብቃት አደረ ። የምታደርገውን ነገር ስላወቀ ጊዜ አልሰጠውም ። ከሳንፍራንሲስኮ ወደ ቦስትን የበረረው አውሮፕላን በግሉ ተከራይቶ ነው ። ያን ማድረግ ባይችልም ክንፍ አውጥቶ ቢበር እንጂ አይቀርም ነበር ። እጁን ዘርግቶ የጨበጠውን ነገር አሳያት ። ያንገት ጌጦቹ ነበሩ ። ከነአሸዋቸው ። ይህን ስታይ እንባዋ ዓይኗን ሞላው ። ‹‹ተለያይተናል ላልል ። ላልሰናበት ቃል ገብቼ ነበር ። አላደረግኩትም » አለ ማይክል ።
‹‹የት ነች ብለህ እልፈለግከኝም››
« ሞተች ብለው ቢነግሩኝ ምን ላድርግ »
«አለሁ ልልህ አልቻልኩም ››
« ለምን ?››
«የተጐዳውን ፊቴን ከለወጡልኝ መኖሬን ላልገልጥልህ... ቃል ገብቼ ነበር !! ... ደፍሬ ቃሌን ሰጠሁ ። ምክንያቱም አንተ ይህን ውል እንደማትቀበል ተማመንኩብህ ። ትተወኛለሀ አላልኩም »
«ባውቅ እመጣ ነበር ። የገባሽልኝን ቃል ታስታውሻለሽ? ›› ዓይኖቿን ጨፍና ራሷን አቅንታ በፀሎት ፅሙና ማይክል ካገኛት ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በናንሲ ማክኣሊስተር ድምፅ ተናገረች ። የማይክል ልብ በፍቅር ሲቃ ዘለለ ። በደስታ ተሞላ። «እዚህ አለት ሥር የተቀበረውን ነገር እስከዘላለም ላልረሳ ቃል ገብቻለሁ ። ወይም ተምሳሌት የሆነውን ነገር» አለች። « ረሳሽው ላትረሺው ቃል የገባሽለትን ? » ይህን የጠየቃት እንባ እያነቀው ነበር ። ስለፒተር ግሬግሰንና ይህን ሁለት ዓመት ስላሳለፈችው ጊዜም እያሰበ ። «ሞከርኩ። በጣም በጣም ምከርኩ ። ግን አልሆነልኝም» አለች ናንሲ ። « አሁንስ ናንሲ ? አሁን ቃልሽን ለማስታወስ አትፈልጊም? ቃልሽን አስታውሺ... .» ከዚሀ በላይ ንግግሩን መቀጠል አልቻለም ። አንድ ነገር ወደሷ ገፋው ። ተንደርድሮ ሄዶ እቅፍ አደረጋት ። አጥብቆ አቀፋት ። «ናንሲ! ኡሁ! ናንሲ በጣም እወድሻለሁ። ሁልጊዜም እወድሻለሁ ። መሞትሽን ስሰማ እኔም የምሞት መስሎኝ ነበር ። ሞተች ብዬ ሳስብ። እኔም ሞትኩ ። ልክ እንደሰማሁ ሞትኩ» አለ ጥብቅ አድርጎ እንደያዛት ። መልስ አልሰጠችውም ። ያሳለፈችውን የስቃይ ጊዜ አስባ፤ ይመጣል ብላ ስትጠብቀው ያሳለፈቻቸውን ወሮች ፤ ሳምንቶች ቀኖች ፤ ሰአቶች ፣ ደቅቃና ሴኮንዶች አስታውሳ ፤ ተስፋ የቆረጠችባቸው ቅፅበቶች ትዝ ብለዋት የዛሬ ደስታዋም ተደባልቆ ስሜቷን ገፍቷት ስቅስቅ ብላ ታለቅስ ነበር። እያለቀሰችም ጥብቅ አድጋ ያዘችዉ ህጻን ልጅ አሻንዱኪቱን አጥብቆ እንደሚይዝ ልውሰድብህ ቢሉት በጄ እንደማይል፤ እንደማይለቅ።

ብዙ ቆዩ ። በመጨረሻ ትንፋሸዋን እንደምንም ተቆጣጥራ ‹‹እኔም አወድሀለሁ። የፈለገውን ብልም አንድ ቀን እንደምትመጣ፤ እንደምትፈልገኝ ኣስብ ነበር» አለች። «ናንሲ…ሜሪ .. ስምሽ የፈለገው ይሁን» አለ ማይክል። ሁለቱም እያነቡ ሳቁ፤ እንደ ህፃን።

«በለቤቴ በመሆን የመጨረሻውን አክብሮት እንድታጎናፅፊኝ ልለምንሽ? እንዳለፈው ሳይሆን፤ በወግ በማእረግ እንድንጋባ። በሙዚቃ በድግስ..»

ፀጥታ። እናቱን አስታወሰ ። ሰርጓን፣ ከዚያም ገረመው። ይህን ሁሉ ያደረገች እሷ (ማሪዮን) ሆና ሳለ አልተቆጣባትም፤ ቂም አልያዘባትም ። ለምን? ገባው። ዛሬ ሁሉን ይቅር የሚልበት ቀን ነው። ናንሲን አገኘ። በቃው ። ጎንበስ ብሎ አያት ። አቅፏት እደረቱ ላይ ተለጥፋ። «እሺ?» አለ ። እራሷን በአሉታ ነቀነቀች ፤ በጣም ። «አይቻልም ፤ አይሆንም? ሙዚቃ ፤ ድግስ፣ ዳንስ !... ይኽ ሁሉ እስኪዘጋጅ መጠበቅ አለብን እንዴ!...»
«እሺ?» ሲል« ታገቢኛለሽ?» ማለቱ መሆኑ ሲገባት « አዎና ለምን አላገባህም? አሁኑኑ እንጋባ ። መቆየት አልፈልግም ። በመዘግዬት አልተማመንም ። እያንዳንዷ ደቂቃ ታስፈራኛለች ። ባለፈው የሆነው ተመልሶ የሚሆን እየመሰለኝ እሰጋለሁ ። አንተ ትመስለኛለህ የምትጎዳው . . . አንጠብቅም »

በፀጥታ ተቀበላት ። በመላ አከላቱ መስማማቱን ገለፀላት ። አንድ ጀልባ በዝግታ እየተንሳፈፈ ቀስ ብሎ ወደ ወደቡ ተጠጋ ። ደካማይቱ ፀሐይ በስተምሥራቅ በኩል ሰማዩን በስሱ ከሸፈነው ደመና ውስጥ ለውስጥ ጉዞዋን ቀጠለች ።
ሁሉም ነገር ገባው።

ተ ፈ ፀ መ ።

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
22👍14😱3🤔2