#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
ቀናት ገሠገሡ። ሳምንታት አለፉ። አሮጌው ሄደ፡፡ አዲሱ መጣ፡፡ የጊዜ
ዑደት ሕግ ሥርዓቱን ጠብቆ በአንድ አቅጣጫ ወደፊት ያመራል።
ህይወት ግን በዝብርቅርቅና በውጣ ውረድ ቀለበት ውስጥ እየተዟዟረች
ትህትና ድንበሩና ሻምበል ብሩክ በላይ በከንፈር ማህተም ያፀደቁትን ቃል
ኪዳን ጠብቀዋው ስለወደፊቱ የትዳር ህይወታቸው በሰፊው መወያየቱን
ከጊዜ ጋር ትራመዳለች::
ቀጥለዋል።
ሻምበል ብሩክ በቤተሰቡ ልብ ውስጥ ዘልቆ ከገባና ዝምድናውን ካጠናከረ በኋላ ያ ቤት ድሮ የትህትና አባት መቶ አለቃ ድንበሩ እያለ የነበረውን የህይወት ሙቀት ቀስ በቀስ መላበስ ጀምሯል፡፡
ይህ አባት አከል የወደፊት የትዳር ጓደኛዋ፤ ወድቆባት የነበረውን የህይወት ሸክም አቀለለላት፤ “አለሁልሽ” እያላት ነው፡፡ ለእናቷ የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍሎ ሆስፒታል ተመልሳ እንድትገባ ያደረገ
ዕለት...
“ ለምን ሌላ ሆስፒታል አናስተኛትም ብሩኬ?” ስትለው፡፡
“የመጀመሪያው ሆስፒታል ምን አለን ትሁት?” አላት፡፡
“እሱማ ምንም አላለን፤ አማራጭ እስካለን ድረስ ለምን ሆስፒታል አንቀይርም ለማለት ፈልጌ ነው እንጂ” አለችው መልሳ።
“እንደኔ፤ እንደኔ፤ መጀመሪያ ሲከታተላቸው የቆየው ዶክተር
ቢያክማቸው ውጤቱ ያማረ ይሆናል ባይ ነኝ፡፡ አዲስ ዶክተር ማለት አዲስ ህክምናን ሀ ብሎ እንደመጀመር ነው የሚሆነው፡፡ ይሁን ካልሽም እሺ” አላት ዐይን ዐይኖቿን በፍቅር እያየ።
ከዶክተር ባይከዳኝ ሙሉ ለሙሉ ለመራቅ እንጂ፤ በህክምናው በኩል ተደናቂ ሀኪም መሆኑን ዘንግታው አልነበረም፡፡ ሻምበል ብሩክም ልክ አዜብ እንዳለቻት ሁሉ ህክምናውን የመጀመሪያው ሀኪም
እንዲቀጥል ሀሳብ ሲያቀርብላት ጥያቄዋን አነሳች፡፡
በዚህ ሰዓት ሆስፒታል በመቀየር ከምታገኘው ጥቅም ይልቅ የእናቷን ጤንነት ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲከታተል በቆየው ዶክተር ህክምናውን መቀጠሉ የሚያስገኘው ጥቅም አመዝኖ ታያትና...
“እንግዲያውስ ይሁን” በማለት ተስማማች። ዕድሜ ለሱ። ዛሬ የሰላምና የንፁህ አየር እየተነፈሰች የወደፊት የትዳር ህይወቷን ትልም በመንደፍ ላይ ነች ፤ እናቷ ተገቢውን ህክምና እንድታገኝ የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው። በሻምበል ብሩክ ከፍተኛ ምክርና ጥረት አንዱአለም
ችላ ብሎት የነበረው ትምህርቱን በሚገባ መከታተል ጀምሯል።
ይህ ውጣ ውረድ የበዛበት ህይወቷን ለማስተካከል እንድትችል ማካካሻ ያገኘችበት መልካም እድል
ሊሆንላት፤ የዶክተር ባይከዳኝና
የእንደሻው ጥላ ደግሞ በሄደችበት እየተከተላት፤ ሀሳቧን ጠቅለል አድርጋ
እንዳትተኛ እንቅፋት ከመሆን አልቀረላትም፡፡
ዶክተር ባይከዳኝ በፍቅሯ እንደተቃጠለ ነው። እንዲያውም እስከመጨረሻው የሱ ሆና እድትቀር የነበረው ምኞቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ልዩ ልዩ ስጦታዎች ያበረክትላት ጀምሯል። የዶክተር ባይከዳኝ ጥርስ የሌለው አንበሳነት፤ በህይወቷ ላይ ችግር የማያስከትል በመሆኑ እናቷ ሙሉ ለሙሉ ከበሽታዋ ድና እስከምትወጣ የተለመደውን ከልብ ያልመነጨ ፍቅር እያቀመሰችው ለመቆየት ወስናለች።
ይህንን የወሰነችው ደግሞ ብቻዋን አልነበረም፡፡ ከአዜብ ጋር በደንብ አድርገው ከተወያዩበትና ከተማመኑ በኋላ ነው።
“አዜቢና ለምን ቁርጡን አልነግረውም?” በማለት ስሜቷን ለጓደኛዋ ስትገልጽላት።
“ምን ብለሽ ትሁት?” ስትል ጠየቀቻት።
“በቃ እጮኛ እንዳለኝና እንዲተወኝ ብጠይቀውስ?”
“ሞኝ ሆንሽ እንዴ ትሁት? እንደሱ ብለሽ ብትነግሪው የሚያምንሽ ይመስልሻል? ጠልተሽው የደረብሽበት ነው የሚመስለው፡፡
በዚህ ላይ ይሄ ሁሉ የስጦታ ግርግር ፍቅር መሆኑን አትርሺ!!
ምን ቸገረሽ ለትንሽ ጊዜ ብትታገሺ? ፍቅር የያዘው ሰው ፍቅሩን ለሌላ አሳልፎ መስጠት ስለማይፈልግ ሌላ አፈቀርኩ ብለሽ ብትነግሪው ጥሩ አይመጣም፡፡ ያፈቀረ ብዙ ነገር ከማድረግም ወደኋላ አይልም፡፡ አቅሙን እንደሆነ የምታውቂው ነው፡፡ ጉዳት እስካላስከተለብሽ ድረስ ማሚ ድነው እስከሚወጡ እየሸወድሽው ብትቆዪ ምናለበት? በዚህ ላይ ታዋቂ ሀኪም ነው” ስትል አማከረቻት።
እሱን በአሁኑ ሰዓት ማጣት ጉዳት እንጂ ጥቅም ስለሌለው ከሻምበል ብሩክ ጋር ጋብቻቸውን እስከሚፈጽሙ ድረስ ግንኙነታቸው እንደነበረ እንዲቀጥል ተስማሙ።
በተቻላት መጠን ግን ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማርገብ ጥረት እንድታደርግ፤ ቀስ በቀስ የግንኙነት ገመዱን ለማላላት እየቀጠሩ መጥፋት፤ ሲገናኙ መለማመጥና ምክንያት እየሰጡ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ላለመገናኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ በዚህ
ውስጥ እንዲጠቃለሉ በስፋት ተማከሩበት። በዚሁ መሠረት ከዶክተር ባይከዳኝ ጋር ለረጅም ጊዜ ሳይገናኙ
ቀሩ። ለረጅም ጊዜ ያለመገናኘታቸው ደግሞ እንደግምታቸው ተስፋ የመቁረጥና የመረሳሳትን አዝማሚያ ከማሳየት ይልቅ ' ዶክተር በናፍቆት
ተጠብሶና፤ በፍቅር ተቃጥሎ፤ እንዲጠብቃት አደረገው፡፡ሻምበል ብሩክ አስፈላጊውን ክፍያ ሁሉ ፈጽሞ እናቷን
ሆስፒታል ባስገባችበት ዕለት ተገናኙ። እናቷ በገንዘብ እጥረት ምክንያት
ከሆስፒታል እንድትወጣ ሲደረግ! ስለገንዘብ ከሆነ አለሁልሽ ብሏት
ነበር፡፡ በክፍያ ችግር ምክንያት መሆኑን ልትገልጽለትና በሽንፈት እጇን
ስላልፈለገች... “ለገንዘቡ አይደለም ዶክተር፤ እናቴ ከሆስፒታል ወጥታ በቤት ውስጥ ለመታከም ስለፈለገች ነው
” በማለት ነበር መልስ የሰጠችው::
አሁን እናቷን ሆስፒታል መልሳ ማስተኛቷን ሲያውቅ ቶሎ ቶሎ ለመገናኘት እድል ይፈጥርለታልና በጣም ተደሰተ፡፡ እሷ ግን ይህንን አልወደደችውም።ሻምበል ብሩክ ግንኙነታቸውን እንዳይደርስበት ሰጋች።
ሆኖም እሱን ከማንኛውም ጥርጣሬ ነፃ የምታደርግበት የራሷ ማረጋገጫ
አላትና፧ ተጽናናች። ሁሌም ለእሷ ንፁህ የመሆን ማህተሙ አብሯት እስካለ ድረስ ዶክተር ባይከዳኝ የእናቷ ሀኪም ከመሆኑ ባሻገር ሌላ ጉዳይ ይኖራቸዋል ብሎ እንደማይገምት ተማምና፤ ከዶክተር ጋር ያላትን ቀዝቃዛ ግንኙነት ቀጠለች።
ይህ ሁኔታ በዚሁ ቀጥሎ ሳለ፤ አንድ ቀን ሻምበል ብሩክ በፖሊስ መምሪያ የተካሄደውን ስብሰባ ተካፍሎ፤ ምሳውን ከበላ በኋላ፤ ወደ ቢሮው ለመመለስ የያዛትን የመንግስት መኪና በሚያሽከረክርበት ወቅት አዲስ ነገር ተፈጠረ።
ከቀኑ አሥር ሰዓት ተኩል ሆኗል።
ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ነው። የትራፊክ መብራት ይዞትእንደቆመ፤ በስተቀኝ በኩል ከፊት ለፊቱ ቀደም ብላ የቆመችውን ነጭ
ኦፔል መኪና እንደዋዛ በዐይኖቹ ገረፍ አደረጋት።
በዚያች መኪና ውስጥ እንደዋዛ ያየው ነገር የትኩረት ስሜቱን ሳበውና፤ መኪናውን ቀስ ብሎ ትንሽ ወደፊት በማንቀሳቀስ ተጠጋ፡፡ፍጹም ሊሆን የማይችል ነገር ነው። አእምሮው ሊጠረጥረው የማይችለውን
ነገር በማየቱ፤ አይኖቹን ተጠራጠረ። የሚያየውን እውነታ ህሊናው በቀላሉ ሊቀበልለት ስላልቻለ፤ ቀይ መብራት በርቶ
መኪኖች ሲለቀቀቁ እንኳ አልታወቀውም ነበር። የሚያየው ነገር እውነት መሆኑን፤ አይኖቹ የሚያሳዩት የሌለ ነገር ሳይሆን፤ ያለውን ሀቅ መሆኑን፤ ሲረዳ ግን፤ ጭንቅላቱ በከባድ ነገር እንደተመታ ሁሉ፤ ክው ብሎ ደርቆ ቀረ።
በሚያየው ነገር ምክንያት ሰውነቱን ማተኮስ ስለጀመረው! የመኪናውን የበር መስታወት ወደታች ዝቅ አድርጎ ንፋስ አስገባ፡፡ በዚያች መኪና ውስጥ ያለቸው ትህትና ድንበሩ መሆኗን
ሲያረጋግጥ፤
መኪናውን የሚያሽከረክረውን ሰው ማንነት ለመለየት ፈለገና አተኩሮ
ተመለከተው፡፡ ያውቀዋል። ዶክተር ባይከዳኝ ነው።ጉድ ፈላ! ስራውን ትቶ የዚህን ተአምር ማብቂያ ሊከታተል
ወሰነ። መብራቱ አረንጓዴ በርቶ ሲለቀቁ ነጫን ኦፔል መኪና ተከትሎ ያሽከረክር ጀመር ክትትሉ እንዳይታወቅበት

🔥2👍1
#ቆንጆዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ
....ሶስና ነበረች የመለመለቻት…አንድ በአንድ ይታወሳታል... ጓደኛዋ ሶስና ነበረች የመለመለቻት፡፡
ርብቃ ሶስናን የምታውቃት በዩኒቨርስቲ ዓመቶቿ ነው፡፡ ሁለቱም የቋንቋ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ ከትምህርት ዓለም ተሰናብተው ወደ ሥራ ዓለም ሲሸጋገሩ ሶስና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ርብቃ ደግሞ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ሥራ ያዙ፡፡
የሥራ ቦታቸው መለያየት ሊለያያቸው የሚችል ቢሆንም አልተራራቁም፡፡ ቢያንስ በሣምንት አንዴ እየተገናኙ አብረው ጊዜያቸውን ያሳልፉ ነበር፡፡ በመጨረሻም የለያያቸው ሶስና በአንደኛ ፀሃፊ የሥራ መደብ ካይሮ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መሄዷ ነበር፡፡
ባለፈው ዓመት መጨረሻ ገደማ ላይ ነበር፡፡ ከሥራ ሰዓት በኋላ ዘወትር እንደሚያደርጉት ቀጠሮ ተሰጣጥተው ተገናኝተው ሲጫወቱ አመሹ፡፡ ወደ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ሶስና ድንገት ተነስታ ቀጠሮ እንዳላት ስትነግራት ርብቃ አዲስ ነገር ሆነባት።
“በዚህ ሰዓት?” አለች መምሽቱን ተመልክታ፡፡
አዎ ርብቅዬ... ማታ ማታ ነው የምንገናኘው።”
“ማነው ባክሽ?” አለች ርብቃ እየተሽኮረመመች፡፡
“ኦ! ወንድ መስሎሽ ነው እንዴ አይደለም ጓደኞቼ ናቸው፡፡”
“እኔ የማላውቃቸው ጓደኞች! ሂ! ሂ! ሂ!” ርብቃ ሳቀች ጓደኛዋ የደበቀቻት ምሥጢር እንዳለ በማመን፡፡
“ርብቃ ሙች እንዳስብሽው አይደለም፡፡ ምን መሰለሽ በእርግጥ አታውቂያቸውም፡፡ እኔም ቅርብ ጊዜ ነው የተዋወቅኋቸው.. እና አልፎ አልፎ ተገናኝተን በተለያዩ አርዕስቶች ላይ እንነጋገራለን፡፡”
“ምን ልትፈጥሩ?” “ አለች ርብቃ ጓደኛዋ የምትለው መላቅጡ ሲጠፋት፡፡
“የተሻለ ዓለም!” አለች ሶስና ጓደኛዋ ትኩር ብላ እየተመለከተቻት ምን መሰለሽ .. ” አለች የርብቃን መደናገር ስታይ፡፡ “በአንድ ርዕስ ላይ ስትከራከሪ የተለያዩ ሃሳቦችን ታገኝያለሽ፡፡ ጭንቅላትሽ ይሰፋል አስተሳሰብሽም ይዳብራል፡፡”
“እና ለመከራከር ተቀጣጥራችሁ ትገናኛላችሁ ማለት ነው?”
“አዎ አንድ ርዕስ እንመርጥና እንዘጋጅበታለን፡፡ ለምሳሌ ስነጽሁፍ …ወይ…ኋላቀርነት ወይ አፍሪካ በቃ እንድ ርዕስ ከዛ በርዕሱ ላይ እያንዳንዳችን እንዘጋጅና ተገናኝተን የሰበሰብነውን
እንለዋወጣለን! እንከራከራለን፡፡” .
“ጥሩ ነው ሃሳቡ፡፡” አለች ርብቃ ቦርሳዋን እያነሳች:: “በይ ከሄድሽ ቶሎ እንሂድ፡፡ እንዳይመሽብሽ፡፡”
“ለምን አብረን አንሄድም?”
“የት?!” አለች ርብቃ ጓደኛዋ ላይ አፍጥጣ፡፡
“አሁን ያልኩሽ ቦታ ነዋ::”
“አበድሽ እንዴ? ደግሞ እኔ ምንድነኝ? አንቺኮ ጓደኞችሽ ስለሆነ…”
“አይደለም. አይደለም:: ባይገርምሽ አብዛኛዎቻችን የተዋወቅነው
እዛው ነው:: እየሽ እያንዳንዱ አባል ብስለት አለው የሚለውን ሰው መጋበዝ
ይችላል፡፡እና ተጋባዥ እንድ ፕሮግራም ይካፈልና ከጣመው አባል ይሆናል፡፡”
“ሌላ ጊዜ።” አለች ርብቃ የጓደኛዋን ክንድ ይዛ ከነበሩበት ቡና ቤት እየወጡ፡፡
ለምን? ነይና እይው፡፡ ምንም መናገር አያስፈልግሽም፡፡ ዝም ብለሽ ተቀምጠሽ እኛ ስንወያይ ታዳምጫለሽ፡፡ እንዳልኩሽ ፕሮግራሙ የሚጠቅምሽ ከመሰለሽ… እያየሽ ትቀጥያለሽ፡፡ ማን ያውቃል ብዙ ነገር ታስተምሪን ይሆናል፡፡ ጋዜጠኛ መሆንሽን ሲያውቁማ ወጥረው ነው የሚይዙሽ፡፡” ሶስና ገፋፋቻት፡፡
“ጋዜጠኛ ለፍላፊ ነው ለማለት ነው ብሽቅ!” አለች ርብቃ ጓደኛዋ
የወትሮውን ብሽሽቅ የጀመረች መስሏት፡፡
“አይደለም... አየሽ ጋዜጠኞች በተለያዩ አርዕስቶች ላይ ስለምትስሩ ከተራው ሰው የተሻለና ሰፋ ያለ እውቀት ይኖራችኋል፡፡ ይህ ደግሞ የሚያከራክር አይደለም፡፡ የኛ ጋዜጠኞች ደግሞ ዋዛዎች አይደላችሁም፡፡
“እ…እ”
“ሙች ሙች ከምሬ ነው:: ሌላውን ብንተወው እንኳን… ለየግላችሁ ያላችሁ ዕውቀት የሚናቅ አይመስለኝም:: ብቻ እስቲ ነይና እይው።”
“እረ በናትሽ ሳይጠሩኝ ሰተት ብዬ ቤታቸው ስሄድ ምን ይለኛል?
“በደስታ የሚፈነድቁት ርብቃ ሙች! አዲስ ሰው በመጣ ጊዜ ምን ያህል እንደምንደሰት ብታውቂ… አዲስ አስተያየት፤ አዲስ አመለካከት ማለት ነው!”
“ግን ታመሹ እንደሆነ?”
“ምንም ችግር የለም። መኪና የሚይዙ ስላሉ ሁላችንን በየቤታችን የሚጥሉን እነሱ ናቸው፡፡ እሱ አያሳስብሽ…እሺ በቃ እንሂድ… እሺ?” ውጥር አድርጋ ያዘቻት፡፡
“ግን… እንጄ.…” እያለች ነበር ርብቃ ለመሄድ የተስማማችው::
ታክሲ ተሳፍረው በንፋስ ስልክ መስመር ወደ ጎተራ አቅጣጫ አመሩ፡፡ መሃል ላይ ሶስና “እዚህጋ ይበቃናል፡፡” ብላ ታክሲውን አስቁማ ሲወርዱ ሊጨልም ዳድቶት ነበር፡፡ አንድ ሰዓት ከአሥር፡፡
“አርፍደናል፤ከአንድ ሰዓት በፊት መገኘት ነበረብን፡፡” አለች ሶስና ከዋናው መንገድ በስተግራ ተገንጥሎ ሽቅብ ወደሚወጣ መንገድ እያመራች።
ጎን ለጎን እየተራመዱ በዝምታ ቀጠሉ። ከአንድ ግራጫ ቀለም ከተቀባ
የብረት በር አጠገብ ሲደርሱ ሶስና ጠጋ ብላ መጥሪያውን ተጫነችው።
አራት ማዕዘን ቅርፅ ያላት ትንሽ የስርቆሽ በር ተከፈተችና አንድ ሰው አጮልቆ ተመለከታቸው። ሶስና ምንም ሳትናገር ጠጋ ብላ ፊቷን አሳየችው፡፡ የስርቆሽ በር ተዘጋችና ዋናው የብረት በር ተከፈተላቸው፡፡ ገቡ፡፡
ርብቃ ከማታውቀው ቤት ሳትጠራ በመምጣቷ እፍረት ቢሰማትም
ውስጥ ገብታ ጉዷን እስክታየው ቸኮለች። ከፊት ለፊት ያለው ቤት ትልቅ ሳይሆን ቀልብጭ ብሎ በጥሩ ሁኔታ የተያዘ ይመስላል፡፡ ምናልባት በቅርብ
ጊዜ የተሰራ ስለሆነም ሊሆን ይችላል፡፡ ከፊት ለፊት የሚታዩት ሁለት
መስኮቶች ተዘግተዋል፤በግቢው ውስጥ ከጥግ እስከጥግ እንደምንጣፍ
የተነጠፈው አስፋልት መሐል የሚታይ የአትክልት ዘር የለም፡፡ ቤቱ
ሕይወት ያለበት አይመስልም፡፡
የገዛ ቤቷ እንደሆነ ሁሉ ሶስና ነይ፡፡ አይዞሽ አትፍሪ” እያለች የዋናውን ቤት የፊት በር ከፍታ ገቡ፡፡ ከውስጥ የተቀበሳቸው ጨለማ ነበር፡፡
በጠባቧ መተላለፈያ ውስጥ ባለው ደብዘዝ ያለ ብርሃን ሦስት የተዘጉ በሮች
ይታያሉ፡፡ ስልክ የተቀመጠበት ትንሽ ጠረጴዛና ወንበር ጥግ ይዘዋል፡፡
በተረፈ ምንም የለም:: ድንገት የታፈነ የሚመስል ድምፅ በስተቀኝ በኩል
ካለው በር ጀርባ መጣ፡፡ ሰዎች የሚነጋገሩ ይመስላል በለሆሳስ፡፡
ነይ እንጅ…” አለች ሶስና በስተቀኝ ወዳለው በር እያመራች፡፡ ርብቃ
ከተል አለቻት፡፡
ከውስጥ የተቀበላቸው ክፍል ከመተላለፊያው የተሻለ ብርሃን ያለበት
ቢሆንም እዚያም ያለው ጨለማ ለአይን የሚከብድ ነበር፡፡ እራቅ ካለ ማዕዘን
የቆመው ባለ ረጅም ቋሚ መብራት ድብዝዝ ያለ ብርሃን ይተፋል፡፡ ከቋሚ
መብራቱ ቀይ ጨርቅ የሚፈሰው ብርሃን ቤቱን ፍም አስመስሎታል፡፡
“ይቅርታ ስላረፈድን፡፡ አንደምን ዋላችሁ።” አለች ሶስና በደፈናው፡፡
በሳሎኑ ክፍሉ ውስጥ ሰዎች ተቀምጠዋል፡፡ ወዲያ ማዶ የተዳፈነው
ቀይ ብርሃን አጠቃላይ ቁመናቸውን እንጅ ገፅታቸውን ጥርት አድርጎ አያሳይም።
“ዛሬ አዲስ እንግዳ ይዤ ነው የመጣሁት።” አለች ሶስና የርብቃን
እጅ ይዛ ወደ ሳሎኑ እየተጠጋች፡፡
ማናቸውም ድምፅ አላሰሙም፡፡ በተቀመጡበት “ጭንቅላታቸውን
እያነቃነቁ ስምምነታቸውን ሲገልፁ ርብቃ በጨለማ ውስጥ ሸንጎ የተቀመጡ
አማልክት መሰሏት።
ሶስና ከማናቸውም ጋር አላስተዋወቀቻትም::የርብቃን ስም አልተ
ናገረችም፡፡ አንድ ፎቴ ላይ እንድትቀመጥ ካመለከተቻት በኋላ ከወደጥግ ካለ
ጠረጴዛ ላይ ወደ ተቀመጠች አነስተኛ ማቀዝቀዣ ሄዳ ከፈተቻት፡፡ ለአንድ
አፍታ ከማቀዝቀዣዋ ውስጥ የወጣው ብርሃን በሳሉን ክፍል ውስጥ ሲናኝ
ርብቃ ከፊት ለፊቷ የተቀመጡትን ሦስት ሰዎች ተመለከተቻቸው… ሁለቱ
ወንዶች ሲሆኑ በስተቀኝ ዳር ያለችው ሴት ነች… በስተግራዋ

#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
.....አኔም በሩ ከተዘጋ በኋላ ይዛው የነበረውን እምባዋን ለቅቃ እየተንሰቀሰቀች ማልቀስ ጀመረች::
ወደ ታችኛው የከተማው ክፍል በ10ኛው ጓዳና ላይ መኪናዋን የምታሽከረክረው ኒኪ ሆዷ ድረስ ዘልቆ የሚሰማ የንዴት እና የሀዘን ስሜት ውስጥ ትገኛለች። አለ
አይደል በደም ሥሯ ደም ሳይሆን እርጎ
የሚዘዋወርባት ይመስል ሁለመናዋን የሚስማት የሚቆመጥጥ ነገር ብቻ
ነው። አንዴ ለእሷ ታዝናለች፤ ደግሞ የተዋረደች ይመስላታል፡፡ ደግሞ
ንዴት እና ፀፀት ተቀላቅሎ ይሰማታል።
ስለ አኔ ባል ለአኔ የነገረቻት ነገር ትክክል ነው። ባሏ ምንም ያህል ለጋስ እና አማላይ ቢሆንም ያው ደካማን የሚያጠቃ በጥባጭ ነገር ነው። በጥባጭ
ሰው ደግሞ መቼም አይለወጥም። ይህንን ነገር ለአኔ ብትነግራት አሁን ላይ
እንደማትሰማት ይገባታል። ምክንያቱም ከአሁን በኋላ አኔ ኒኪን እንደ ሀኪሟ አይደለም የምታያት። አኔ ኒኪን እንዴት ነው የምታያት? ብላ ራሷን ጠየቀች፡፡ “እንደ ጓደኛዋ? ምናልባት እንደ ፍቅረኛዋ? ምናልባት ከባሏ ልትነጥላት ቆርጣ እንደተነሳች ሴት?”
አኔን በዚህ መልኩ ማናገር አልነበረባትም።
ይሄው አኔ በግልፅ ባይሆንም ኒኪ ቀድማ ብዙ ስለቀረበቻት ይህንን ተናግራት አይደል “አንቺ እንደ ቴራፒስት አይደለም ለእኔ ደንታ ያለሽ፡፡ ይሄንን ደግሞ ሁለታችንም እናውቀዋለን!” ብላታለች። ግን የዶውግን ከትዳር ውጪ ስላለው ግንኙነት እንዴት ልታውቅ ቻለች? አኔ እንዴት ስለ እዚህ ጉዳይ ማወቅ ቻለች? ይህንን ጉዳይ የሚያውቁት ደግሞ ጓደኛዋ ግሬቸን እና ዶፎ ናቸው፡፡ እነርሱ ደግሞ በፍፁም ይህንን ነገር ለማንም እንደማያወሩት ታውቃለች፡፡
የሚሰማት የሚያስጠላ ስሜት ሲጨምር በመኪናው መስኮት ወደ ውጪ ተመለከተች፡፡ አራት ቤት አልባ የሆኑ ሰዎች ከቲያትር ቤቱ መግቢያ በር
ላይ ተደርድረው ቁጭ ብለዋል፡፡ ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ባዶ እና ተስፋ አልባ
ስሜት ውስጥ ሆኖ ወደ እሷ አይኑን ጎልጉሎ ይመለከታታል። በሱስ ናውዟል፤ ያስታውቃል፡፡ የሆነ የሀዘኔታ ስሜት እንዲሰማት ጠበቀች። የለም፡፡ ይሄንን ስሜቷን ያቺ ሸርሙጣ የሟች ባሏ ሩሲያዊቷ ውሽማ አጥፍታባታለች፡፡
የሆነ ልቧ ውስጥ ያለውን ያቺን የዋህዋን
ኒኪን ይህቺ ሴት ገድላባታለች። ወይንም ይሄ ነገሯ አልሞተም፤ በቃ ነዳጅ ምናምን አልቆበት ነው። ምናልባት አንድ ቀን የፍቅር እና ለሰዎች ያላት የመልካም ስሜቷ ነዳጇ መልሶ ሙሉ ሲሆን የሀዘኔታ ስሜቷን መልሳ ታገኘው ይሆናል።
ምናልባት!
ወይም ደግሞ ጨርሶም ላይመጣ ይችላል።
የመንገዱ እግረኛ ማቋረጫ ላይም አንዲት በመሀከለኛ ዕድሜ ላይ
የምትገኝ ሌላ ሴትን ተመለከተች፡፡ ይህቺ ሴትም ያኔ ዶፎ ቬኒስ ውስጥ የሚገኘውን ክሊኒክ ሲያስጎበኛት እንዳየቻቸው ሁለቱ ጎረምሶች አጥንቷ ገጥጦ ወጥቷል፡፡ መልካም አረንጓዴ ነው። ዶፎ ክሮክዳይል ይባላል። አዲስ የመጣ አደንዛዥ ዕፅ ነው ብሎ የነገራትን ነገር አስታወሰች፡፡
ያኔ ክሊኒኩ ውስጥ ላየቻቸው ሁለቱ ጎረምሶች ሀዘኔታ ተሰምቷት ነበር፡፡
አሁን ግን ይሄው ባዶ ናት፤ ምንም ነገር አይሰማትም። ምናልባት ከአኔ ጋር
ስታወራ የተቀበለችው ውርደት ይህንን ውስጧ የቀረውን እንጥፍጣፊ
የሀዘኔታ ስሜትን አጥፍቶባት ይሆን?
ምንም ነገር ማሰብ አቆመች እና ዝም ብላ ወደ ቤቷ አቅጣጫ መኪናዋን
ማሽከርከር ጀመረች። ቤቷ ስትደርስ ደጃፏ ላይ ሁለት ፖሊሶች የፖሊስ
መኪና ውስጥ ተቀምጠው አገኘቻቸው። ፖሊሶቹ ትላንትና ማታ መርማሪ
ፖሊስ ጉድማን የእሷን እምቢታ ሳይቀበል ቀርቶ እንዲጠብቋት የመደበላት
ፖሊሶች ናቸው፡፡
ትላንትና ማታ የእሱ መኪና ውስጥ ቁጭ ብለው እጁን ታፋዋ ላይ አድርጎ “ጥበቃ ያስፈልግሻል” ብሏት ነበር።
“ምንም አይነት ጥበቃ አልፈልግም”
“ኒኪ ጥበቃውን አንቺ ስለፈለግሽው ሳይሆን የምመድብልሽ ሥራዬ
ስለሆነ ነው እሺ” ብሎ ሲናገራት ውስጧን ደስ የሚል ነገር ተሰምቷት
ነበር።
“እኔ ያንተን ጥበቃ ባልፈልግስ?” ብላው ነበር። የእሷን እጅ የት አድርጋ ፀታወራው እንደነበር አስታውሳም።
እንደርሱ ከሆነማ እተውሻለሁ ዶክተር” ብሏት ነበር ጉድማን ማዕረጓን ልክ እንደ ስድብ የተጠቀመበት።
የፖሊሶቹ ቤቷ አጠገብ መገኘት ጉድማን ትላንትና ማታ እሷን ለማማለል ሳይሆን ስለ ጥበቃ ያወራው ነገር የእውነቱን መሆኑን እንድትረዳ አደረጋት። ግትርነት የምትወዳቸው የወንዶች ፀባይ ነው መሰለኝ ግትር ወንዶች ደስ ይሏታል። ምንም እንኳን መጨረሻቸው ባልጠበቀችው መልኩ ቢያበቃም ባሏ ዶውግም እንደዚያ ነበር።
አይኗ በእምባ ሲሞላ ኒኪ ተናደደች እና እምባዋን ውጣ፣ መኪናዋንም አቁማ ወደ ቤቷ ገባች። የቤቷን መብራት አብርታ እና ጫማዋን ወርውራ አውልቃ ወደ ማብሰያ ክፍሏ አመራች። አዲስ የገዛችውን ቦርሳዋን ከማብሰያው ክፍል ባልኮኒ ላይ አስቀመጠች። የማታው የዞረ ድምር እስከ አሁን ባይለቃትም ፍሪጂ ውስጥ ያስቀመጠችውን ቨርጅን ሜሪ መጠጥ
ብርጭቆዋን ሞላች። የባልኮኒው ወንበር ላይ ቁጭ እንዳለችም ላፕቶፕዋን
ከፈተች እና ኢ ሜይሏን ተመለከተች፡፡
ምናልባት አኔ ኢ ሜይል ልካ ከሆነ ብላ ነበር ለፕቶፕዋን የከፈተችው።
ከአኔ ግን ምንም የተላከ ኢ ሜይል አላገኘችም።
ሌላ የተላከላት ኢ ሜይል ስለበነረም ከፈተችው። የማታውቀው ኢ ሜይሉን የላከላት ግለሰብ 'ትላንትና ማታ አይቼሻለሁ! በሚል ርዕስ ሥር
ትላንትና ማታ ከጉድማን ጋር አብረው የነበሩበት የዳን ታና ሬስቶራንት ፎቶ
ለጥፏል። ከሆቴሉ ሥር ያለው ሁለተኛው ፎቶ ደግሞ የእሷን ከአንገት በላይ
ያላ ፎቶን ከአንዲት ራቁቷን ከምትወዛወዝ የካርቶን ቪዲዩ ላይ በፎቶ ሾን አያይዞታል። ከፎቶውም በታች “አንቺ ሸርሙጣ እገድልሻለሁ!” የሚል
ማስፈራሪያ ተፅፎበታል።
ኒኪ ይህንን ካየች በኋላ ድንገተኛ ድንጋጤ እና ፍርሃት ወረራት፡፡
በመቀጠልም ድንዝዝ ያለ ስሜት ውስጥ ገብታ ቁጭ አለች።
ስሜቷ ደንዝዞ ብትቀመጥም ጎበዙ አዕምሮዋ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ይወተውታት ጀመረ። ይሄ ቀልድ አይደለም። ይሄ የግድያ ዛቻ ነው፡፡ ለዚያውም የእሷን እያንዳንዱን እንቅስቃሴዎቿን ከሚያውቅ ሰው
ትላንትና ማታ ዳና ሬስቶራንት ውስጥ ከማን ጋር እንደነበረች ሁሉ
ከሚያውቅ ሰው ነው ማስፈራሪያው የተላከላት። ስለዚህ ነገሩን ለፖሊስ
ማሳወቅ ይኖርባታል። አሊያም ደግሞ ለጉድማን ልትነግረው ይገባል።
ግን ደግሞ ትንሽ አመነታች፡ ለመልከመልካሙ መርማሪ ፖሊስ
ጉድማን ነገሩን ማሳወቅ እሱን ይበልጥ ወደ እሷ ህይወት እንዲገባ ማድረግ
አይሆንምን?
ልጠብቅሽ ነው በሚል ሀሳብ ከእሷ ጋር እንዲጣበቅ ምክንያት ማቀበል
አይሆንም?
ግማሽ እሷነቷ ለመርማሪው ነገሩን አሳውቂ ሲላት፣ ግማሽ እና ብልሁ
ሌላኛው እሷነቷ ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ ነገራት።
ጉድማን መልካም ሰው ነው፤ ችግሩን ለመፍታት አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ ያደርጋል። ግን ደግሞ ባልደረባው የሰይጣን ቁራጩ ጆንሰን አብሮት
የሚሰራ አጋሩ እስከሆነ ድረስ ሁለቱም የግድ የእሷን ጉዳይ ይመለከቱታል
ማለት ነው። ይሄ የእሱ አጋርነት ደግሞ የሊዛን እና የትሬይን ገዳይ እንዲሁም ደግሞ እሷን ጭምር በመኪና ሊገድላት የሞከረ ሰውን ይዞ ለፍርድ ማቅረብ ያቃተው እንደሆነ እያየችው ነው።
ለማንኛውም ህይወቷ አደጋ ላይ ነው፣ ኒኪ ጥበቃ ያስፈልጋታል።ከጥበቃው በላይ ደግሞ መልስ ትፈልጋለች፡፡ የምትፈልገው መልስ ደግሞ ስለ ግድያዎቹ ብቻ አይደለም። የዶውግን ክህደት ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ
በዋናነት የእሷን ህይወትን መርዞባት እስከ አሁን ድረስ ውስጧን ለሚያደማት

👍2❤1
#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
...እንደ ረጂም ነጭ ጭራ የዕንጨት ሽበት ያንጠለጠሉ ዛፎች በብዛት ይታያሉ፡፡ የማዶውን ትቼ አጠገቤ ስመለከት ትልልቅ ጐለጐሎች የሞተች
የእባብ ራስ (ትል) ጉማጅ አግኝተው ከፊትና ከኋላ በመተጋገዝ እያንከባለሉና
እየገፉ ሲወስዷት አየሁ። ሕይወት እና ኑሮ የከባድ ትግል ውጤት ናቸው::የቦታው ቁልቁለታማ ስበት ከጉልበታቸው በላይ በማየሉ አምልጣቸው ተንከባለለች፡፡ የት እንዳረፈችና እንደገባች ስላጧት ተቅነዘነዙ። እንደ ፈሪ መርዶ ነጋሪ ዙሪያውን ዞሩ። በፍለጋ ብዛት አገኟት፡፡
ተፈጥሮ ለታካች ከማዕዷ አታጎርስምና እንደገና በትግል ይዘዋት መንገድ ቀጠሉ ፍጻሜያቸውን ለማወቅ በዐይኖቼ ተከተልኳቸው:: በአንዲት ሰፊ ደረቅ ቅጠል ሥር ከነግዳያቸው ተሸጎጡ፡፡ የእንሱ ጉዳይ በዚያው አከተመ።
የየወዲያነሽ አእምሮ ምን እንደሚያስብና እንደሚያሰላስል ባላውቅም አካባቢውን በፈገግታ ትመለከተዋለች። ድንገት ሳታስበው ክንዷን ሳብ አድርጌ
«የወዲያ! ይኸ አካባቢ ደስ አይልም እንዴ? አልኳት፡፡ በአድናቂ ስሜት ፈገገ
አለች።
ሻንጣውን ከጐኗ ሳብ አድርጋ ትውስብሳቢውን ተረተረችው:: አምስት
ብርቱካኖች አውጥታ እንደ ምፅዋት መቀበያ ሰጣ በተን ባለው ነጠላዋ ላይ
አስቀመጠች:: እናት ነች የልብ ከውቃ:: መላጥ ጀመርኩ፡፡ እሷም ተያያዘችው:: እርሷ ገና ልጣ ሳታጋምስ እኔ ለእሷ ሦስት ጊዜ ለራሴ ሁለቴ ጎረስኩ፡፡ አንዷን የብርቱካን ፍንካች አፌ ውስጥ እያንከላወስኩ «የወዲያ ደስ አላለሽም መሰል ይህ አካባቢ?» ብዬ እንደገና ጠየቅኋት። በጠይሙ ፊቷ ላይ
ፈገግታዋ እየተዘናከተ «እንዴት ብዬ ልንገርህ?» ብላ በእጅዋ የያዘቻትን
ፍንካች ሰለከከች። እኔ ሁለተኛዬን በልቼ ልጨርስ ስል እርሷ ሁለተኛይቱን
ልጣ ፈረካከሰቻት። «እንካ እስኪ ይቺን ቅመሳት ጌትዬ?» አለችኝ።
“አ!” ብዬ ተቀበልኳት። ከእጅዋ ላይ ተጨማሪ ጣዕም ፈልቆ ብርቱካኑ ውስጥ የገባ ይመስል ያጎረሰችኝ ጣፈጠኝ። ስውጥ አይታ ደገመችኝ። ቁልቁል ሸኘኋት፡፡ በድጋሚ ስትዘረጋ «ተይ ተይ በቃኝ! አንቺ ጉረሻት» አልኳት። እጅዋን እንደ ዘረጋች «ይቺን ብቻ ጌትዬ ስሞትልህ?» ስትለኝ ካንገት በላይ እየተግደረደርኩ ተቀበልኳት። ሆዴ ብቻ ሳይሆን ሕሊናዬም ጠገበች፡፡ ደመናኑን በረጅም መጥረጊያ ሙልጭ አድርገው የጠረጉት ይመስል ሰማዩ ጸጥ ያለ ባሕር መስሏል። ምንም እንኳ በሰማዩ ላይ ደመና ባይታይ ፀሐይዋን ለማየት የቻልነው ገላጣው ቦታ ላይ በመቀመጣችን ነበር፡፡
እኩለ ቀን ሊሞላ አንድ ሰዓት ብቻ ቀርቶታል። ኃይለኛውን የበጋ ሐሩር የቀነሰልን ግን ከአካባቢው የሚነፍሰው የለስላሳ አየር ሽውታ ነበር፡፡
ከነበርንበት ሥፍራ ተነሥተን ጥቂት ርምጃዎች ወደ ጎን አለፍ ብለን ከአንድ
ቁጥቋጦ ሥር ተቀመጥን፡፡ የቁጥቋጦው ቅጠል የላይ ገጽ በጣም ደማቅ አረንጓዴ ሆኖ ወበቅ እንዳቃጠለው የከበርቴ ፊት
በስተጀርባው ግን ግርጣት ያይልባታል።
ወዛም እንደ ቀድሞ ገዳይ ጎፈሬ የተቸመቸመው ድፍን አረንጓዴ ቅጠሏና
ደርበብ ያለው ቁመቷ ታይቶ የማይጠገብ የውበት ፀጋ አልብሷታል፡፡
የወዲያነሽ አንዷን ጎበጥ ብላ መሬት ለመንካት አንድ ክንድ ያህል የማይቀራትን ቅርንጫፍ እንደ ተቀመጠች ተንጠራርታ ሳበቻትና ለጋ ጫፉን ቀለጠመቻት፡፡ በቀኝ እጅዋ ይዛ ግራ እጅዋ ላይ ስትጠበጥባት ጥቂት ቅጠሎች ረገፉ፡፡
አንዷን በጥቃ ተስተካክለው በሰቀሉት ጥርሶቿ እየነካከሰች በሳቻት።
ቅጠሊቱን ከእጅዋ ላይ መንጭቄ ወረወርኩና «ምን ዐይነቷ ናት እባካችሁ?
እስኪ አሁን ምኑን አውቀሽው ነው? ምናልባትስ መርዘኛ ቅጠል ቢሆን?»
አልኩና ከአንጀት ያልመጣ ቁጣ ተቆጣሁ፡፡ ሣቅ ብላ ትንሿን ጣቴን ያዘችና
«መጥፎ ቅጠል መሰለህ እንዴ? እኔ እኮ ዱሮውንም ቢሆን አውቀዋለሁ፡፡
አንተ አታውቀውም መስል? ደደሆ እኮ ነው:: ምን ያደርጋታል ብለህ ነው?
አለችኝ።
አለማወቄን ለመሰወር ያህል ነው እንዴ? እኔ እኮ ከረሳሁት ቆይቻለሁ» አልኳት ቀድሞዉንም ቢሆን የማላውቀውን ቅጠል፡፡ እንደማላውቀው አውቃብኛለች፡፡ አሁንም ያንኑ ቅጠል በጥሳ በጥርሷ
ወጋጋችው። እኔም ለመቅመስ ያህል አራት አምስቱን ቅጠል አጎርኩት።
ምራቄ ከአፌ ውስጥ በመዘውር ተቀድቶ የተወሰደ ይመስል አፌ ኩበት ሆነ፡፡
ምላሴ ደረቀች። ላንቃዬ እንደ ተወቀረ ወፍጮ ሞዠቀኝ። ውስጥ ውስጡን
ጉዴ ፈላ፡፡ እንዳይታወቅብኝ ወሬም የለ ምንም የለ፣ ዝም አልኩ፡፡ዳግመኛ ሌላ ቅርንጫፍ ጎትቼ እመጣለሁ ብላ ስትንጠራራ ጠርዙ ጉልበቷ ላይ ያደረው ቀሚሷ እስከ ጭኗ ተስቦ አሻቀበ፡፡ የወንድነት ንቁ ፍላጎቴ በጠይሙ ውብ ገላዋ ዙሪያ ተንከራተተ፡፡ እጄን ዘርግቼ ለስላሳ ገላዋን ዳበስኩት፡፡ መላ ሰውነቴ ብው ብሎ ጋለ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነሣሁ የወዲያነሽንም አፈፍ ኣድርጌ አስነሣኋት። እኔ ወደ ምዕራብ እርሷ ወደ
ምሥራቅ እያየን ፊት ለፊት ቆምን፡፡ ትከሻዋን ይዤ ደረቴን ወደ ደረቷ
አስጠጋሁት። አቀፈችኝ፡፡ አቀፍኳት። ከልብ ተሳሳምን።
ነፋስ እንደ መነጫጨረው የድርቆሽ ክምር ጸጉሯን በታተንኩት፡፡ ያ ከጥቂት ወራት በፊት አንገቷ ላይ ደርሶ የነበረው ጸጉሯ አድጎ ትከሻዋን ያስሳል፡፡ ጫፍ ጫፉ ተቆልምሞ በመጥመዝመዝ እጆቹን ሽቅብ እንደ ዘረጋ ባሕታዊ ወደ ላይ አንጋጧል። ከከንፈሯ ወረድ ብዩ ያን ካፊያ እንደ መታው ጓሚያ እንኮይ የተውለከለከውን አንገቷን ባፍና በአገጬ አድፈጠፈጥኩት።
እጅ ለእጅ ተያይዘን ከቁጥቋጦይቱ ውስጥ ወጣን፡፡ አካባቢውን ለማየት ስለ ፈለግን አንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ወጥተን መንገድ ፈለግን፡፡ የወዲያነሽ የለበሰችው ገብስማ ቀሚስና የደረበችው ቢጫ ሹራብ፣ የአካባቢው ዕፅዋት ልምላሜ፣ ምግብ የያዝንበት ቀይ ሻንጣ፣ የታጠቅሁት ሰማያዊ ሱሪና የለበስኩት ሽንብራማ ኮት፣ ባንድነት ሆነው የውበት ሽማ በመዘርጋት በቅልቅል ኀብረ ቀለማቸው አእምሮዬን ስላረኩት ታላቅ ሰብኣዊ ኩራት ተሰማኝ፡፡ ሹራቧንና ነጠላዋን አጣጥፌ ሻንጣ ውስጥ ከጨመርኩ በኋላ ቁልቁለቱን ተያያዝነው:: በጫካው ውስጥ ለውስጥ የሚያስኬደው መንገድ ቡችሎች እንደ ጎተቱት አንጀት የተጥመዘመዘ በመሆኑ በረጂሙ አግድም እንሔድና እንደ ገና ደግሞ ተመልሰን ከነበርንበት ቦታ ግርጌ እንደርሳለን፡፡ልዩነቱ ትንሽ ዝቅ ማለታችን ብቻ ነበር። አንዲት አፈመለከት ቅርፅ ያላት ትንሽ ቢጫ የሐረግ አበባ አገኘሁና ቀጥፌ ዘረጋሁላት፡፡ እጅዋ በድካም እንደ
መዝለፍለፍ እየቃጣው ተቀበለችኝ። መለስ ብዪ «የወዲያ! ያቺ ፀሐይና ይኸ
ቁልቁለት አዛሉሽ መሰል?» አልኳት። «ብዙ ሄጄ ስለማላውቅ ነው መሰል»
ብላ ደማ ፈገግታ አሳየች፡፡
ጥቂት ዝቅ እንዳልን ጆሮዎቼ የመልካም ተስፋ ድምፅ ሰሙ:: ለእኔም ለእርሷም አንጀት የሚያርስ እፎይታ ነበር። ከፊት ለፊታችን ከወደ ጋራው ጥግ ካሉት ትላልቅ የድንጋይ ቋጥኞች ሥር በከፍተኛ ፍጥነት እየተውዘገዘገች የምትወርድ ፏፏቴ ኣየን፡፡
በፏፏቴው ዳርና ዳር ያለው አለት በጥቁርና ጓያ መስል መልኩ
በጣም ይማርካል። ከወንዚቱ ዳርቻ የበቀሉት ዛፎች ቅርንጫፎቻቸው እንደ
ደጋን ጎብጦ ቅጠሎቻቸው ወራጅዋ ውሃ ውስጥ ተዘፍቆ በውሃይቱ ግፊት
ከወዲያ ወዲሀ ይነቃነቃሉ፡፡ ከሸለቆው ውስጥ የትኛው ቦታ ላይ እንደምትመነጭ አይታይም። ኩልል ብሎ የጠራው ውሃ የድንጋዩን መልክ ተጋርቶታል። ወራጂቱ ውሃ ድምፅ ሳታሰማ ጥቂት አግድመት ታገድምና ጥግ ይዞ ጠርብ የመሰለ ድንጋይ ሲያጋጥማት ፏፏቴ ቢጤ ፈጥራ ትፈጠረቃለች።
በፏፏቴው ማረፊያ ዙሪያ የእንዶድ አሪፋ የመሰሉ ነጭ የውሃ ንፍሥሪ ኳሶች ይንሳፈፋሉ፡፡ የጥበትና የስፋታቸው መጠን የተለያየ ቢሆንም

👍4❤2😁1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....ጎንቻ ቦሩ የዘረፋቸውን ከብቶች በርካሽ ዋጋ ከቸበቸባቸው በኋላ ጫካ ገባ፡፡ የሟቹ ወንድሞች ከየአገሩ ተሰባስበው መምጣታቸውንና ገዳዩን ገድለው ለመበቀል ከፍተኛ እልህና ቁጭት ሲተናነቃቸው መክረሙን የሚገልፅ መልዕክትም ደረሰው፡፡ መልዕክቱን የላከችለት ዓለሚቱ ነበረች።
ልቡ በየቀኑ ወደ ዓለሚቱ ይበርራል። ይከንፋል። ጠረኗ፣ሰውነቷ ሁለመናዋ በዐይኑ ላይ ይንከራተትበታል፡፡ ዐይኖቹን ጨፍኖ ጨክኖ ሄዶ እንዳይጎበኛት ደግሞ አደጋ ውስጥ እወድቃለሁ ብሎ ይፈራል። ጎንቻ ላውንብድና ስራው የሚያገለግለው አንድ አጭር ምንሽር ከገዛ በኋላ በጫካ
ውስጥ እንደ አውሬ እየኖረ ለሊት ለሊት ብቻ ሊጎበኛት ወስኗል።
ጎንቻ የጫካውን ኑሮ እየተለማመደው፣ አውሬነት እየተዋሀደው ሄደና ከተራ ሌብነት ወደ ሽፍታነት አመራ። ፀጉሩን ገመደና ሹሩባ አሰራው።ሁለት ጀሌዎችንም ማስከተል ቻለ። በሱ አዛዥነት የሚመራ የወንበዴ ቡድን አቋቁሞ ዘረፋውን በሰፊው ተያያዘው።
ጎንቻና ዓለሚቱ ከተገናኙ በጣም ረጅም ጊዜ ቢሆናቸውም ለአንድም ቀን ከሀሳቡ ወጥታ አታውቅም ነበር ናፍቆቷ ዐይኑን ሊያወጣው ደርሷል። በልቡ አንድ ቀን በለሊት ሂዶ ይዟት ጫካ እንደሚገባ ጥርጣሬ አልነበረውም፡፡ ዓለሚቱን ይዞ የሚጠፋው ግን ያንን ለብዙ ጊዜ የበቀል
ካራ ሲስልለት የሰነበተውን የቶላን ጉዳይ አንድ መላ ካበጀለት በኋላ እንጂ ከዚያ በፊት እንደማይሆን ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ በሱ ዘንድ ቶላ ፍፁም ምህረት ሊደረግለት የማይገባው ጥፋተኛ ሆኖ ነው የተገኘው። ልቡ ቂም አርግዟል፡፡ ጭንቅላቱ በቁጭትና በቂም ተበክሏል፡፡ ገበየሁን ከገደለ በኋላ ወንበዴነቱ ለይቶለት ልበ ደንዳና ሆኗልና በል በል ! ሂድ ግፋበት እያለው ነው፡ርህራሄ የሚባል ነገር ከውስጡ እየሟሽሽ ሄዶ የሌላ ሰው
ደም ለማፍሰስ እያቅበጠበጠው ነው፡፡ የመጀመሪያውን ፅዋ ገበየሁ ጨለጠበት እንጂ እሱ ያዘጋጀው ለቶላ ነበር። ሁልጊዜም በሀሳቡ በዚያ በገበያው መሀል በህዝብ ፊት እየወደቀ እየተነሳ የሮጠው አሯሯጥ፣ የቶላን ጩኸት ሲስማ የደነገጠው ድንጋጤ፣ እነኝያ የጎመጀባቸውን ከብቶች ሳይቸበችባቸው መቅረቱ የፈጠረበት ቁጭት ይሄ ሁሉ አሳፋሪ ትዝታ ፊቱ ላይም ድቅን እያለበት በአስቸኳይ ቶላን ተበቅሎ ያንን ውርደቱን ለማካካስ ስሜቱ ሂድ! ሂድ! እያለ ይገፋፋው ነበር፡፡ በዚሁ ዕቅዱ መሰረት ጀሌዎቹ ጊርቦ ዋዶን እና ቱሲ ቤንኪን አስከትሎ ለመሄድ ተዘጋጀ።
“ጎበዝ! ዛሬ የምንጎበኘው ሰው ደመኛ ጠላቴ ነው! ማንኛውንም ነገር
በአጭር ጊዜ ውስጥ አቀላጥፈን በቶሎ መመለስ ይኖርብናል! ጥንቃቄ
እንዳይጎድላችሁ!” ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ ሰጣቸው፡፡ ጀሌዎቹ በተጠንቀቅ ቆሙና በአለቃቸው ጠላት ላይ ጥቃት ሰንዝረው ንብረቱን ለመዝረፍ በመታደላቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገለፁለት፡፡ ትእዛዙን በሙሉ ልባቸው ተቀብለው ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋገጡለት፡፡ በዕቅዳቸው መሰረት ሲዘጋጁ አደሩና በለሊት ጉዞ ጀመሩ፡፡ ጫካ ለጫካ እየተሹለከለኩ፣ የገደሉትን አውሬ ስጋ እየበሉ ወደ ትውልድ መንደሩ ወደ ወላጆቹ ጎረቤት ወደ ቶላ ሠፈር መገስገሳቸውን ቀጠሉ...
በድቅድቅ ጨለማ እየወደቁና እየተነሱ ሲሮጡ ለተመለከተታቸው ወገንን
ከጥፋት ለመታደግ እንጂ የአንድ ሰላማዊ ገበሬን ህይወትን ለመቅጠፍ
ያስፈሰፉ ወንጀለኞች አይመስሉም ነበር፡፡ እርኩስ ዓላማቸውን ለማሳካት እንቅልፋቸውን አጥተው በጨለማ ሲጓዙ ካደሩ በኋላ ወደ መንደሪቱ ተጠጉ፡፡ ቶላና ቤተሰቦቹ ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። ጀሌዎቹ አለቃቸው የሚሰጣቸውን የቃልና የምልክት ትዕዛዝ ተግባራዊ ለማድረግ በተጠንቀቅ ቆሙ:: ውሾቹ ትንሽ “ዋይ! ዋይ” በማለት ሊያስቸግሩ ሞከሩ፡፡ ጎንቻ ቀደም ብሎ የተዘጋጀበት ጉዳይ ነበረና በኪሱ ውስጥ ይዞት የነበረውን ትኩስ የአውሬ ሥጋ አውጥቶ ወረወረላቸው፡፡ በዚህ ላይ የጀሌዎቹን እንጂ አንዳንዶቹ ውሾች ጠረኑን ስለሚያውቁት በጥቂት ጊዜ
ውስጥ ሰላም ሰፈነ። ቀሪው ተግባር የጎንቻን ፈጣን ርምጃ የሚጠብቅ
ነበር።
ቶላ ከባለቤቱና ከአንዲት ሴት ልጁ ጋር በሞቀች የሳር ጎጆው ውስጥ
አገር ሰላም ነው ብለው ድብን ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። ሀሳባቸውን ጣል አድርገው ስፊውን የእንቅልፍ ዓለም በሚጎበኙበት ምሽት፣ በጣፋጭ እንቅልፍ ውስጥ ሆነው በስራ የደከመ ጎናቸውን ባሳረፉበት በዚያ ውድቅት ለሊት ይህ ነው በማይባል ኃይል የተበረገደችው የእንጨት በር ተስፈንጥራ ከመሀል ምሰሶው ጋር ተላጋች፡፡ በዚያው ቅፅበት
ጎንቻ እንደ ፀሀይ የሚያበራ ጩቤውን በቶላ አንገት ላይ ደቀነበት፡፡ ከእንቅልፉ እንደዚያ በድንገት ለባነነ ሰው የጎንቻ ሁኔታ እጅግ የሚያስፈራ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበር፡፡ የተጎነጎነ ጎፈሬውን ቁልቁል አንዠርጎ፣ ምንሽሩን በትከሻው ላይ አጋድሞ፣ በወገቡ ዙሪያ ዝናር ታጥቆ ሰይፍ የሚያክል ረዥም ጩቤውን አገልድሞ ሲታይ“እባክህ አምላኬ በኪነ ጥበብህ ህይወቴን እንዲጠብቅ የተላከ መልአክ አድርግልኝ” የሚያሰኝ ነበር፡፡
ጎንቻ ግን በመልአከ ሚካኤል ተመስሎ የቶላን ህይወት ከክፉ ሊታደጋት የመጣ የነፍሱ ጠባቂ ሳይሆን ጉሮሮውን ለመበጠስ የመጣ አረመኔ ነበር፡፡እናትና ልጅ አፋቸው ታፍኖ ከአልጋው እግር ጋር እንዲታሰሩ ትዕዛዝ ሰጠ። ትእዛዙን ሲፈፅሙ ተናግሮ አልጨረሰም ነበር፡፡ እጅግ ፈጣኖች ናቸው። እሱ ደግሞ ቶላን ርቃነ ሥጋውን አስነስቶ ከጎጆዋ መሃል ከቆመው ምሰሶ ጋር በመጫኛ ተበተበውና በአፉ ውስጥ ጨርቅ
ጎስጎሰበት። ቤቱ በሶስት ወሮበሎች እየተበረበረ ምስቅልቅሉ ይወጣ
- ጀመር፡፡ በፍተሻው መሰረት አንድ መለስተኛ ገንቦ ቅቤ፣ በጮጮ የተሞላ
ነጭ ወለላ ማር ተገኘ፡፡ ከዚህ ሁሉ የበለጠ ቶላን ያስደስተው ሳጥኑ
ነበር፡፡ በሣጥኑ ውስጥ የተገኘው ጥሬ ብር ሲቆጥረው አራት መቶ ሃያ
ሆነ፡ ልዩ ልዩ ከመዳብ የተሰሩ ጌጣጌጦች በዚህ ላይ ደግሞ አንድ አሮጊ ፊሊፕስ ሬዲዮም ተገኘ፡፡ ከቶላ ይህንን ሁሉ ቁምነገር ያልጠበቀው ጎንቻ
በጣም ተደሰተ፡በአጠቃላይ በቤቱ ውስጥ በጥሪትነት የተገኘው ነገር ሁሉ
ተበዘበዘና አንዱ ተሸካሚ ሌላው አሸካሚ ሆኑ። ምንም ነገር ያልተረፈ መሆኑን ሲያረጋግጡ ጎንቻ ከቤት ውስጥ እንዳለ ጊርቦ አካባቢውን ለመሰለል ወጣ ገባ አለ፡፡ ፀጥ እረጭ... ያለ ነበር። ጊርቦ መለስ ብሎ ወደ ጎንቻ ጆሮ ተጠጋና “እንሂዳ ጌታዬ ከእንግዲህ ምን እንጠብቃለን? የምታደርገውን አድርግና ፈጠን ብለን እንውጣ፡፡ እንዳይነጋብን” አለው፡፡
ጎንቻ ከቶላ የዘረፈው ንብረት ያልጠበቀው በመሆኑ ደስተኛ ቢሆንም በእልህና በቁጭት ትኩር ብሎ ተመለከተውና ፊቱ ላይ ተፋበት፡፡
ቶላ እንዳይጮህ፣ እንዳይናገር፣ እንዳይሳደብና በአጠቃላይ ምሬቱን
ተንፍሶ እንዳይወጣለት አፉ ተወትፏል። በሚያየው ድርጊት አእምሮውን
እስከሚስት ድረስ ውስጡ በግኖና ፊቱ ጥላሸት መስሎ ዐይኖቹ እንደፈጠጡ ቁና ቁና ይተነፍሳል። በደፈረሱት ዐይኖቹ ጎንቻን በጥልቀት አስተዋለው፡፡ ያሳደገው ውርጋጥ በሱና በቤተሰቡ ላይ ስብዕናቸውን የሚያዋርድ አፀያፊ ተግባር ፈፅሞባቸው ሲሄድ ከማየት ይልቅ ሞቱን መረጠ፡፡በቤቱ ውስጥ ያንን የመሰለ ወራዳ ድርጊት ከፈፀመ በኋላ ደግሞ እነዚያን ባለፈው ጊዜ አተረፍኳቸው ብሎ በደስታ የሰከረባቸው ከብቶቹን ነድቶ
መሄዱ የማይቀር ነው። ተቃጠለ። ጢስ የማይወጣው እሳት በላዩ ላይ ነደደበት፡፡ ነፍስ አንድ ጊዜ ብትወጣ ምን ነበረበት? ግልግል ነበር። ጎንቻ ግን በሚያደርጋቸው ድርጊቶች ሁሉ ቶላን ቀስ በቀስ እየገደለው ነበር።ከሞት ሁሉ ሞት በባለቤቱ እና በትንሽ ልጁ ፊት ራቁቱን ከምሰሶ ጋር አስሮ ምራቁን ሲተፋበት፣

👍3
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...እኔም የሀገሬን ጥሪ በደስታ የምቀበለው ሁለታችሁን ለመለያየት ሁለታችሁን ለመለያየት የክተት ጥሪ ነጋሪት የተጎሰመ እንደሆነ ብቻ ነው። ይኼኛውን ግን አልቀበለውም።» አለ ዓይኑን በባርናባስ ላይ ፍጥጥ እንዳደረገ
መቀበል ያለ መቀበሉ ጉዳይ የአንተ ነው፡፡ ነገር ግን ደብዳቤው በአድራሻህ የተጻፈና የመዝገብ ቁጥር የያዘ ስለሆነ አንተው ጋር ይቀመጥ፡፡» አለና በርናባስ
ደብዳቤውን መልሶ ወደ አስቻለው ዘረጋ፣
አስቻለው ደብዳቤውን የንጥቂያ ያህል ከባርናባስ እጅ ላይ ምንጭቅ እያረገ
«አምጣው! ለታሪክ ይቀመጣል፡፡» ብሎት ወደ ኋላው ተመልሶ ከቢሮው ወጣና በሩን ድርግም አድርጎ ዘግቶ እዚያው በኮሪደሩ ላይ በመቆም ያንኑ ደብዳቤ እንደገና ያነብበው ጀመር፡፡ ግን የደብዳቤው መልዕክት አሁንም ያው ነው፡፡ አስቻለው በንዴት
ስሜቱ ተለዋወጠና ለጊዜው ምን ማድረግ እንዳለበት ቅጡ ጠፋው:: ግን በስተቀኝ
አቅጣጫ በሚገኝው የኮሪደሩ መወጫ በኩል ጅው ብሎ ሄደና ከህንጻው ውስጥ ወጣ፡፡ በዚያው በመውጫው ዳር የግድግዳ ጥግ ተደግፍ እንደገና ያነብበው ጀመር::
በዚህ ጊዜ ግን «ኪኪኪኪ …. ብሎ ሳቀ፡፡ የንዴት ሳቅ አሁንም «ኪኪኪኪ በዚያችው ቅፅበት እዚያችው ቦታ ላይ እንደ ቆመ በሀሳብ ከብዙ ቦታ ረገጠ: ሔዋንን አስታወሳት ሸዋዬንም እንዲሁ፡፡ የሸዋዬንና የባርናባስን ግንኙነት
እንዲሁም ከሁለቱ ጋር ተለጥፎ ሒዋንን በማስቸገር ላይ ያለው በድሉ ኣሸናፊ ጭምር ታዩት: በእጁ የያዘው ደብዳቤ ይዘትም ከእነዚህ ሰዎች ግንኙነትና ፍላጎት
የመነጨ ስለመሆኑ ሳይጠራጠር አመነበት።
ወዲያው አንድ ነገር ብቻ ማድረግ ታየው፡፡ በዚያ ሆስፒታል ውስጥ
ያስቀመጠው ልብስም ሆን ማስታወሻ ምንም ሳይታሰበው ጋወን ስለ መልበሱ እንኳ ሳይታወቀው ከዚያ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ለመውጣት ወሰነ፡፡ በልቡ ውስጥ ያለው መድረሻ ደግሞ የአውራጃው ግብርና ፅህፈት ቤት።
ከዲላ ሆስፒታል አስከ ግብርና ጽህፈት ቤት በአማካይ ሠላሳ ደቂቃ የሚወስደው የእግር መንገድ ለአስቻለው ሃያ ደቂቃ እንኳ አልፈጀበትም፡፡ የቆፌን
ኮረኮንች መንገድ እየነጠረ ተረማምዶ፣ ዲላ ከተማን ለምስራቅና ለምዕራብ ለሁለት
በሚሰነጥቃት አስፋልት መንገድ ላይ ገስግሶ ወደ ዲላ ሰሜናዊ ጫፍ አቅራቢያ ሲደርስ ቀኙን በመያዝ ጥቂት ዳገታማ የሆነውን አባሯማ መንገድ ረምርሞ ከበልሁ
ቢሮ በር አጠገብ ደረሰ
«ኳ..ኳ..ኳ..ኳ....»
አንዴ ይጠብቁኝ አለ በልሁ ከውስጥ፡ በዚያ ሰዓት ከሁላት ባለ ጉዳዮች ጋር እየተነጋገረ ነበር፡ አስቻለው ዛሬስ አላስቻለውም። በሩን በርግዶት ገባና የበሩን እጀታ እንደያዘ በልሁን በተቀመጠበት አሻግሮ ተመለከተው።
በልሁ አስቻለው መሆኑን ሲያውቅና አጠቃላይ የፊቱን ገፅታ
ሲመለከት በድንጋጤ ፊቱ ኩምትርትር አለና «እንዴ» «ምነው አስቻለው?» አለው ፍጥጥ ብሎ እየተመለከተው። አስቻለው መልስ አልሰጠውም። ዝም ብሎ ወደውስጥ ገብቶ ሳይጋበዝ በእንግዳ ወንበር ላይ ቁጭ አለ።በረጅም ረጅም እየተነፈሰ ጣርያ ጣርያ ያይ ጀመር። በአስቻለው ሁኔታ የተገረመውና ምናልባትም ደንገጥ ያሉ የበልሁ እንግዶች በልሁን አየት አየት አደረጉት።
«እስቲ ወንድሞቼ! አንዴ ወጭ ሆናችሁ ጠብቁኝ»ሲል በትህትና
ጠየቃቸው። ሰዎቹ አላመነቱም ወዲያው ብድግ ብለው ተከታትለው ወጡ።
«አስቻለው!» ሲል ጠራው በልሁ በሁኔታው መለዋወጥ ሆዱ እያዘነ
«ወይ»አለው አስቻለው አሁንም አይኑን ከኮርኒሱ ላይ ሳይነቅል።
«ምነው? ምን ሆንክ?»
አስቻለው የሆነውን ነገር ከመናገር ይልቅ ያን የያዝውን ደብዳቤ ለበልሁ እየዘረጋ «እንካ አንብበው» አለና ሰጠው
በልሁና ልክ እንደ አስቻለው ቶሎ ወደ ሀሳቡ አልገባም፡፡ደብዳቤውን
ቅርጽ በቅድሚያ ቃኘው። ፕሮቶኮል የጨበጠ ደብዳቤ ነው፡፡ ፊሪሚው ባርናባስ ቲተሩም የሱ ነው ከዚያ በኋላ ወደ ዝርዝር ሁኔታ ገብቶ አንብቦ ከጨረሰ በኋላ
ድንግጥ ባለ አኳኋን «ከየት አመጣኸው?”» ሲል ጠየቀው።
ሰጡኝ እኔማ ከየት አመጣዋለሁ?» አለና አስቻለው ጉንጮቹን ነፋ አድርጎ «እሁሁ» ቡሎ በረጅሙ ተነፈሰና አንገቱን ወደ መሬት ደፋ።
በልሁ ለጊዜው ምንም ማለት አልቻለም፡፡ አስቻለውን ግን አከታትሎ ተመለከተው። የደብዳቤው ይዘትና መልዕክት በወስጡ ሊፈጥርበት የሚችለውን
ስሜት ያውቃልና እሱም ሆዱ እያዘነ «እስቲ ወጣ እንበልና ሻይ እየጠጣን እንነጋገር» አለ በልሁ የአስቼሐውን ምላሽ በአይኑም በጆሮውም እየጠበቀ። አስቻለው እሺ ወይም እምቢ ብሎ ቃል አልተናገረም ብቻ ዝም ብሎ ብድግ አለና ቸከታትለው ወጡ።
ለበልሁ መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የሻይ ፍላጎት እማራጩ ሁለት ነው፡፡በዚያው በመስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በምትገኝ የሻይ ክበብ በከሰል የተፈላ ሻይ ቡና መጠጣት አለበለዚያ ከግቢ ወቶ በአንደኛ መንገድ ላይ ከሚገኙ ሆቴሎች ድረስ በመሄድ
የማሽን ሻይ ቡና መጠቀም፡፡ በዚያን ዕለት ግን በልሁ ስለ አስቻለው ጉዳይ ጊዜ ወስዶ መነጋገር ስለ አሰበ በቀጥታ ወደ ከተማ ወረዱ፡፡ ወደ አንደኛ
መንገድ ከተዳረሰ በኋላ አስቻለው አንድ ሀሳብ አመጣ።
«ለምን ወደ ታፈሡ ጋ እንሄድም?» አለና በልሁን አየት እደረገው፡፡
በእርግጥ በልሁም ትዝ ስላላለው ነው እንጂ ያ ጉዳይ ወደ ታፈሡ ቤት የሚያሮጥ ነውና ሀሳቡን ተቀበለው።
ከበልሁ መስሪያ ቤት እስከ ታፈሡ ቤት ድረስ እስከ አሥራ አምስት ደቂቃ ሚወስደውን መንገድ በዝምታ ጨርሰው በሯ ላይ ሲደርሱ ታፈሡ የቤት ልብሷን
እንደለበሰች አገኟት፡፡
«አለሽ ታፈሥ?» አላት በልሁ ቀድሞ፡፡
እንዴ! ምን ዓይነት አመጣጥ ነው?» አለች ታፈሡ ድንግጥ ብላ፡፡ ከሰአቱ አጉልነት በተጨማሪ የአስቻለው ጋውን መልበስ ግራ አጋባት፡፡ አስቻለውና በልሁ
ፊታቸውን ክፍት እንዳላቸው ስላም እያሏት ወደ ሶፋ አለፍ እያሉ ተቀመጡ።
«እናንተ!» አለች ታፈሡ አሁንም ዓይኗን በሁለቱም ላይ እያንከራተቱተች።
«እስቲ ቁጭ በይ ታፈሥ» አላት በልሁ በተዳከመ ስሜት።
ታፈሡ ቁጭ አለችና ምን ሆናችኋል?» ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
በልሁ የያዛትን ወረቀት ከርቀት አቶከረችባት።
«አይዞሽ! ብዙም" አትደንግጭ!» አላት በልሁ::
«ትንሽም ቢሆን ንገሩኝ»
«መምህርት ሸዋዬ ገና ዛሬ ሳታሸንፈን አልቀረችም፡፡» አላት በልሁ በደፈረቁ ፈገግ ብሎ እያያት፡፡
«እንዴት አድርጋ?»
«ያን ባርናባስ የተባለ ሽማግሌዋን ተጠቅማ::»
«ማለት?»
«እንቺ ይኸን ወረቀት አንብቢው፡፡» አለና በልሁ ደብዳቤውን ለታፈሡ ዘረጋላት፡፡ ታፈሡ ያን ደብዳቤ ከበልሁ እጅ ላይ በችኮላ ተቀብላ ሁለመናውን አየችው።ቀንና ቁጥር የራስጌና የግርጌ መሀተም እንዲሁም የበርናባስ ፊርማና ቲተር ያለበት ደብዳቤ ነው፡፡ ማንበብ ጀመረች።
«ለጓድ አስቻለው ፍስሀ
ዲላ
ጉዳዩ ፡ የእናት ሀገር ጥሪን ይመለከታል፡
«እንደሚታወቀው ሁሉ በስሜኑ የሀገራችን ክፍል ጥቂት ተገንጣይ
ቡድኖችና ሌሎች ጎጠኞች በመተባበር የሀገራችንን ሉዓላዊነት በመፈታተን ላይ
ናቸው። የእነዚህኑ ተገንጣይ ቡድኖችና የውጭ ደጋፊዎቻቸውን ቅስም ለመስበር ጀግናው ሠራዊታችን ከውጭና ከውስጥ ጠላቶቻችን ጋር አንገት ለአንገት

👍9
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
....ከስብሰባው እንደወጣች የክተት አዋጅ ጃን ተከል ላይ በሊጋባው አማካኝነት አስነገረች። ጐንደር አካባቢ ያለው ሠራዊት በአጣዳፊ እንዲሰለፍ አደረገች። ከሰዐት በኋላ፣ ጐንደር ያለ ሠራዊት ተሰበሰበ። ኩርዓት ሥርዐቱ መጥቶ ሠራዊቱ ለዘውዱ ሲል መሐላ እንዲገባ ጠየቀች። ሠራዊቱም፣ “አብረን ባንቆም፣ አብረን ባንታገል፣ እዝጊሃር
ይደምስሰን፤ ኸቴጌይቱና ኸንጉሡ በረከት አያሳትፈን” እያለ ማለ።
ምንትዋብ፣ ምግብ በተፋጠነ ሁኔታ ከቤተመንግሥት ቀህ በር
ለተሰበሰበው ሠራዊት እንዲታደል አደረገች። በቤተመንግሥቱ ዙርያ
ያሉት የዋርካ ቅርንጫፎች ተቆረጡ። የገባም እንዳይወጣ የወጣም እንዳይገባ አስራ ሁለቱም የቤተመንግሥት በሮች ተዘጉ።
በሁሉም በሮች መኳንንት ሠራዊት ይዘው እንዲቆሙ አስደረገች።
በተለይም ደግሞ ለጠላት መግቢያ ይሆናሉ ብላ በገመተቻቸው በሮች ላይ ጀግና የምትላቸውን መኳንንትና የጦር አበጋዞች አሰለፈች። የጦር
አበጋዞቹም ከቋራ፣ ከወገራ፣ ከከምከምና ከቃሮዳ በየቀኑ የሚገባውን ሠራዊት በሁሉም በሮች እንዲያስቆሙ አደረገች።
ልጇን ይዛ ከባለሟሎች ጋር በተዘክሮ በር ስትቆም፣ ታቦታትም
ከእነሱ ጎን ቆሙ። በጀግንነታቸውና በብልህነታቸው የተመሰገኑት ጦረኞች የዮልያና ልጅ ደጃዝማች አርከሌድስ፣ ብላቴን ጌታ ኤፍሬም፣
ፊታውራሪ ጎለም የመሳሰሉት ከጎኗ ተሰለፉ። ደጃዝማች ወልደልዑል ለውጊያ እንዲመቹ በየበሮቹ ላይ መስኮት መውጣት አለበት ብሎ በማሳሰቡ በሁሉም በሮች መስኮቶች ተከፈቱ።
የወህኒ ጠባቂው ቄርሎስ ከእነተንሴ ማሞ ጋር ተዋውሎና ለእነምንትዋብ የገባውን መሐላ ክዶ “ኢያሱ ሙቷል። መኳንንት ተመካክረው ሕዝቅያስ
ወረኛን አምጣ ተብያለሁ” ብሎ፣ ሕዝቅያስ ወረኛ የተባለውን የነጋሢ
ወገን ከወህኒ አውጥቶ፣ ለእነተንሴ ማሞ መስጠቱን ምንትዋብ ሰማች።ተንሴ ማሞ ሕዝቅያስን ይዞና በርካታ ጦር አስከትሎ በፍጥነት ጐንደር
መድረሱና ሠራዊቱ ቀሀ ወንዝ አጠገብ የጥምቀተ ባሕር ግቢ ውስጥ የመስፈሩ ዜና ደረሳት።
በቅርቡ ተሾመው የነበሩትና አፄ በካፋ በሞቱ ጊዜ ምንትዋብ
ለምክክር የጠራቻቸው እንደ እነቢትወደድ ላፍቶና ባሻ ኤልያስ
የመሳሰሉ መኳንንት ከተንሴ ማሞ ጋር ወገኑ። ምንትዋብ ስትሰማ
አዘነች። ወልደልዑል፣ “ሲሾሙና ሲሸለሙ፣ ጉልት ሲጎለቱ፣ ርስት
ሲተከሉ፣ ባረቄና በጠጅ ጉሮሯቸውን ሲያጥቡ የከረሙ ሁሉ ጊዜ አይተው መክዳታቸው አይቀርም” ያለውን አስታወሰች።
ትምህርት ተማረች።
የቀድሞው መኰንን ተንሴ ማሞ ጃን ተከል ወጥቶ፣ “ሕዝቅያስ
ነግሣል” ብሎ አሳወጀ። ሕዝቡ፣ መኳንንትና ወይዛዝርት ሳይቀሩ ከፍራቻ የተነሳ ለዐዲሱ ንጉሥ ለሕዝቅያስ እየወጡ ሰገዱ። ምንትዋብ ስትሰማ ወንድሟ ወልደልዑል፣ “ሰዉም ቢሆን ጦር ሲያነሱበት ኃይለኛው ጋር
ነው ሚወግን። ስለሚፈራ ለሱ ይነጠፋል” ያላት ትዝ አላትና ገረማት።
ካህናቱም ዐዲሱን ንጉሥ በማሕሌት ተቀበሉ።
ሠራዊቱንም ተከትለው እነምንትዋብ ባሉበት በተዘክሮ በር መጡ። ጦሩን አደራጅቶ
በተጠንቀቅ ይጠብቅ የነበረው ወልደልዑል የመጣውን ጦር በውጊያ አሸነፈ። በሌሎች በሮችም እንደዚሁ በተደረገው ውጊያ የምንትዋብ ጦር አሸነፈ።
እነተንሴ ማሞ ግን የበለጠ እየተጠናከሩ መጡ። በየበሩ እየተመለሱ ውጊያውን አፋፋሙት። በተዘክሮና በአደናግር በሮች በተለይ ውጊያ ተጧጧፈ። ደጃዝማች አርከሌድስ በሚዋጋበት በር ስለተሸነፈ፣ ዐማጽያን በሩን ሰብረው ገቡ። ያገኙትን መዘበሩ። ወርቅ ሰቀላን፣ አደናግርን፣ ርግብና ዙፋን ቤቶችን አቃጠሉ። አረቄና ጠላ እየጠጡ ተሳክረው በየቦታው ወድቀው ተሸነፉና፣ ከግቢ ተባረሩ።
ከውጭ ሴቶች ከማጀት ወጥተው እነተንሴ ማሞን ወግነው ለውጊያ
ታጠቁ። ወንዶቹንም በዜማና በፉከራ አነሳሱ። አዝማሪዎችም
አንተ ሰው
አንተ ሰው
ግንቡን ጣሰው፣ እያሉ የእነተንሴ ማሞን ሠራዊት አበረታቱ።
ለጊዜውም ቢሆን የጦርነቱ ዕጣና አቅጣጫ ወዴት እንደሚያዘነብል
ለማወቅ አስቸገረ።
የተንሴ ማሞ ሠራዊት እነምንትዋብን ለመግደል ተዘክሮ በርን ሰብሮ ሲገባ፣ የእነምንትዋብ ሠራዊት ሲሸበር ወልደልዑል ተበሳጨ። “የት ትሸሻለህ? ባለህበት ቁም” አላቸው፣ መሬቱን በሌባ ጣቱ እየጠቆመ።
ወደጎን፣ ወደፊት፣ ወደኋላ እየተንጎራደደ፣ እጁን እያወናጨፈ፣ “ቃል ለሰማይ ቃል ለምድር ይሁንብኝ። አንቺ ኸእግሬ ስር ኻልሸሸሽ እኔ አልሸሽም” አለ፣ መሬቱን እያየ። ፊት ለፊት፣ ጠመንጃ ለጠመንጃ፤
ሠይፍ ለሠይፍ፣ ጦር ለጦር፣ ጋሻ ለጋሻ ጠላቶቹን ገጠመ።
ተዘክሮ በር ድብልቅልቁ ወጣ። የስቃይ ጩኸት በቤተመንግሥት
ዙርያ አስተጋባ። ክፉኛ የቆሰለ ጓደኛውን፣ ወንድሙንና አጋሩን
ትከሻው ላይ አንጠልጥሎ ሊሸሽ ሲሞክር ከኋላው በጦር ሲወጋ ወይንም ሠይፍ ሲሻጥበት ከተሸከመው ጋር አብሮ ሲወድቅ፣ አካባቢው ደም ለበሰ፤ ሬሳ በሬሳ ሆነ፤ ቀውጢ ሆነ።
የሰው ልጅ ጭካኔ፣ በውስጡ ያለ ያልተገራ ፍጥረቱ ይፋ ወጣ ::
በጩቤ የተወጋው፣ በሠይፍ እጁ ወይ እግሩ የተጎመደው እጁን ወደ
ሰማይ ሰቅሎ “ድረሱልኝ!” “አድኑኝ!” “ልጅን ዐደራ! “ምሽቴን ዕደራ!”
“እናቴን ዐደራ” “ውሃ!” “አምላኬ ነፍሴን ተቀበላት!” ሲል ተማጸነ።
መሬት ላይ ወድቆ ነፍስያ የያዘውን ሁሉ ሞት እየዞረ ጎበኘ ::
በሁለቱም ወገን ብዙ ሰው አለቀ። ወልደልዑል፣ ተዘክሮን ሰብሮ
ለገባው የጠላት ጦር ክንዱን አሳየ፤ አሸነፈ። ነፍሱ የተረፈች የጠላት ጦር ፈረጠጠ። አፄ በካፋ የተከሉትን ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ግን አቃጠለ። ሌሎችን ቦታዎችንም እንዲሁ።
ጐንደር ይበልጡንም በማታ ጋየች፤ ቤቶች ተቃጠሉ። ንብረትና
ከብቶች ተዘረፉ፤ ሴቶች ተደፈሩ። እነተንሴ ማሞ ቀሀ ወንዝ አካባቢን
በመያዛቸው ውሃ ጠፋ። ጐንደር ለውሃ ጥምና ለሰቆቃ ተጋለጠች።
ሰዉ “ውሃ” እያለ ጮኸ። ሰዉም እንስሳውም እጁን ለሞት ሰጠ።
በቤተመንግሥቱ በሮች እንደገና ውጊያ አየለ። ብዙ ሰው አለቀ፤ ሬሳ
በየመንገዱ ወደቀ፤ የወደቀ ቁስለኛ የሚያነሳው አጣ። ከቤተመንግሥት ውጭ ያለውን የእህል ጉድጓድ የተንሴ ማሞ ጦር በመያዙ፣ ግቢው ውስጥ የምግብ እጥረት ተፈጠረ።
ጐንደር ፍዳዋን ኣየች።
እነተንሴ ማሞ አቡኑን፣ ዕጨጌውንና ካህናቱን ሰብስበው፣ “እቴጌንና ንጉሡን አውግዙልን፣ ኮተሊክ ቄሶች መጥተው ቤተመንግሥት ውስጥ
ኸንጉሡና ኸቴጌይቱ ጋር ተዘግቶባቸዋል” አሏቸው።
እነሱም፣ “ለቴጌይቱና ለንጉሡ እንጨት የሰበረ፣ ውሃ የቀዳ፣ የታዘዘ ሁሉ ቃለ ሐዋርያት ይሁንበት። ከንጉሡ ጎን ሁነህ ሕዝቅያስን የወጋህ ሁሉ ገዝተንሃል” ሲሉ ገዘቱ።
ሊቃውንቱ ግን ተቃወሙ። “እኼ ግዝት የሕገ ወጦች ግዝት ነው።
ወፈ ገዝት ነው” ብለው አወገዙ። ምንትዋብ ስትሰማ “የሆዳሞች ግዝት” አለችው።
የጃዊ አዛዥ ሆኖ ተሾሞ የነበረው ሻለቃ ወረኛና የሜጫው አዛዥ
ጊዮርጊስም ዘንድ “ተከበናል ፍጠኑ” ስትል መልዕክት ላከች። ተንሴ ማሞ ይህን ሲሰማ አፍዞ አደንግዞ ያስቀረው ዘንድ ሻለቃ ወረኛ ላይ አስማተኛ ላከበት። ወረኛ የመጣውን አስማተኛና ዐጃቢዎቹን በጦር አለችው።
ወግቶ ገደላቸው።
ተንሴ ማሞ ዓላማው እንዳልተሳካለት ሲሰማ ተበሳጭቶ ለወረኛ፣ እነምንትዋብ ሙተዋል። ሕዝቅያስ ነግዟል። በዚያው ባለህበት ሹመትህን አጥንተናል፤ አትምጣ። ኸጊዜው ሁን” ሲል ላከበት።
ሻለቃ ወረኛና አዛዥ ጊዮርጊስ ግን የጃዊና የሜጫን ቀስተኛ፣ ፈረሰኛ፣
ነፍጠኛ፣ እግረኛና ወንጭፈኛ ሠራዊት ይዘው ፈጥነው ጐንደር ገቡ።የተንሴ ማሞን ጦር ከበቡ። የእነምንትዋብ ጦር ሲያይል አቡኑ፣ “ስለ ንጉሡ ብላችሁ ብትሞቱ የሰማዕታት ክብር ታገኛላችሁ” ብለው ሰበኩ።

👍14🔥2
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
የቀይ ኮከብ ጥሪ
ባህራም
ባህራም እየተለወጠ ሄደ፡፡ እነ ማኦ ትዜ ቱንግ የደረሱዋቸውን
መፃህፍት ማንበብ ተወ:: ስለኮሙኒዝም ማውራት ተወ፡፡ ክፍል መግባት ተወ:: እኔንም ይሽሸኝ ጀመር። እንደቀስተ ደመና ውብ የነበረውን የሬቮሉሽን ተስፋውን በብዙ የእሳት ቃላት ይነግረኝ ስለነበረ' አሁን ቀስተ ደመናው ተሰባብሮ ወድቆ ከበሰበሰ በኋላ፣ እንደገና
ሊያነጋግረኝ አልፈቀደም፡፡ ኒኮልም ፊት ነሳችኝ፡፡የባህራምን ክንፍ እንደሰበረችው ስላወቅኩ ፊት ነሳችኝ
የኤክስን ሰማይ የሉልሰገድና የጀምሺድ መቀሰፍ አላስደነገጠውም፡ የአማንዳ ጉብዝና አላስደነቀውም፡ የኒኮል ማርገዝ አላናደደውም፡ የባህራም መታሰር አላሳዘነውም፡፡ የኤክስ ሰማይ ለዚህ ሁሉ ደንታ የለውም
የኤክስ ሰማይ አብዛኛውን ጊዜ እንደ አማንዳ አይን ብሩህ
ሰማያዊ ነው፡ አንዳንድ ጊዜ እንደ ኒኮል አይን ውሀ አረንጓዴ
ይሆናል፡ ወደ ማታ ጊዜ እንደ ሲልቪ ጉንጭ ይቀላል
የኤክስ ሰማይ ደመና አይለብስም፤ ሁልጊዜ ራቁቱን ነው! ሁልጊዜ ውብ ነው፡ ሁልጊዜ ሰላማዊ ነው። ሌሊት የአልማዝ
ከዋክብትና የሰላም ፀጥታ ለብሶ ያድራል
የኤክስ የፀደይ ፀሀይ እየበረታች ሄደች። ንፁህ ብርሀኗ ቀስ
እያለ ወደ ብጫ ሀሩር ተለወጠ፡ ለስላሳውን የፀደይ ንፋስ
አደከመው፡ የሚወብቅ የአየር ባህር አደረገው፡፡ በጋ መጥቶ ኤክስ ውስጥ እንደ ሰፊ ድካም ተንሳፈፈ። አሮጊቶቹና ሽማግሌዎቹ ጥላ ውስጥ ቁጭ ብለው በዝግታ እያለከለኩ፣ የሞትን ምህረት የሚጠብቁ
ይመስሉ ጀመር
እንዳንድ ጊዚ ባህራምንና ኒኮልን ምግብ ቤቱ ሲገቡ ወይም
ሰወጡ አያቸዋለሁ። ባህራም ከስቷል፡ አይስቅም፣ በፍጥነት
አይራመድም። ሽበቱም የበዛ መሰለኝ፡፡ ኒኮል ግን ወፈር ብላ፣
እርግዝናዋ በጣም አምሮባታል፡ በዝግታ ስትራመድ ታስጎመጃለች
ቀስ በቀስ ምግብ ቤት መምጣቱን ተዉት ተካ የኒኮልን ማርገዝ ለመሸሸግ ያሉት ነው» አለኝ፡፡ ሌላ
ነገር ነገረኝ ባህራም ማታ ማታ ኒኮልን ቤቷ ትቷት ይወጣና
ሲኒማ ይገባል ከሲኒማ ወጥቶ ካፌ 'ሰንትራ' ይሄዳል፡ እዚያው
ያድራል፤ ሲነጋ ወደ ኒኮል ቤት ይኳትናል፡ ተኝቶ ይውላል
አንድ ማታ ወደ ስድስት ሰአት ላይ ከሲኒማ ወጥቼ ወደ ቤቴ
በኩል ስራመድ፡ ከኋላዬ እንደ ፈጣን እርምጃ ሲከተለኝ ተሰማኝ።
እንዳልሰሙ መንገዴን ቀጠልኩ። ደረሰብኝ፡፡ ባህራም፡፡ ወደ ካፌ
ሰንትራ ሄደን ቢራ ካዘዝን በኋላ
ቁጭ ብለን ካወራን ብዙ ጊዜ ሆነን አለኝ፡፡ አይኖቹ እንደ
መድከም ብሏቸዋል፡ ፊቱ ላይ የአምስት አመት ያህል እድሜ
ተጨምሯል
"አንተ አትገኝም አልኩት"
በገዛ ራሴ ጥፋት በታሰርኩ' አንተ ጋ መጥቼ ባለቅስብህ ተገቢ
ማስሉ አልተሰማኝም
ጥሩ እድል አጋጥሞህ ቢሆን ኖሮ ግን መጥተህ ታጫውተኝ
ነብር፡ ደስታህን ታካፍለኝ ነበር»
አዎን። ይኸውልህ፡ ልክ ከፓሪስ እንደተመለስክ እንድንጋገርበት አቅጄ ነበር፡፡ ግን ገና ሳትመለስ ጣጣ ውስጥ ገባሁ። ስትመጣ ታድያ፤ መንፈሴ ተሸንፎ ስለነበረ ያቀድኩትን ችላ አልኩት፡፡ አሁን ፈቃደኛ ከሆንክ ብንነጋገርበት ጥሩ ይመስለኛል።»
"ጥሩ"
መጀመር አስቸገረው። ሲጋራ አቀጣጠለ።
ስለሰልቪ ጉዳይ ነው። ነግርሀለች?»
«አዎን፡፡
«ምን አለችህ?»
የነገረችኝን ባጭሩ አጫወትኩት። ዝም ብሎ ሰማኝ። ስጨርስ
«ውሸቷን ነው» አለኝ
«እንዴት?
«እኔ ነኝ የለመንኳት፡፡ እሷ እምቢ ብላኝ ነበር። ለብዙ
ተለማመጥኳት። 'አሁን አሁን ከሞት ጋር ስታገል ነበር፡ ውስጤ
በፍርሀት ተሞልቷል፡ ብቻየን ነኝ፡ የሰው ሙቀት ያስፈልገኛል፣
በጣም ያስፈልገኛል አልኳት። እሺ አለችኝ። ግን እሺ ያለችኝ ብዙ
ከተለማመጥኳት በኋላ ነው»
«ማንኛችሁን ልመን?»
«እኔን
«ለምን?»
«ውሸት አልነግርህማ»
«እሷስ ለምን ውሽት ትነግረኛለች?»
«እንዳንጣላ ብላ»
ዝም አልኩ። ንዴቱ ውስጤ ሲጠራቀም ይሰማኛል
«ከፈለግክም አገጣጥመን» አለኝ፡፡ ቁጣዬን ለመግታት ስል
መዋሽት ጀመርኩ
«ግድ የለም ይቅር። አሁን ስላንተ ንገረኝ አልኩት። ድምፁ
እንደተለወጠ ተሰማኝ
«ይቅርታ አርገህልኛል ማለት ነው?» አለኝ
«እንርሳው» አልኩት
«እፍረት ይሰማኛል። አይንህ ውስጥ ንቀት ይታየኛል»
«ንቀት አይደለም» አልኩት
«ታድያ ምንድነው?»
«ስሜቴን ልግለፅልህ?»
«አዎን»
እኔ ሳላውቀው የተጨበጠ ቀኝ እጄ በፍጥነት ሄዶ አገጩን
መታው:: ከነወምበሩ ወደኋላ ተገለበጠ። እጆቼን እንደ ጨበጥኩ ከበላዩ ቆምኩ፡፡ የተገለበጠው ወምበር አጠገብ እንደተጋደመ ወደ ላይ ያየኛል። ማንኛችንም አልተንቀሳቀስንም። ወደ ላይ እያየኝ ቀስ ብሎ መሀረቡን ከኪሱ አወጣ፡፡ መሀረቡ ውስጥ ተፋ። ደም፡ ቀና
ብሉ ቀይ ፈገግታ ሰጠኝ፡፡ እጁን ዘረጋልኝ። ጨበጥኩት፣ ወደ ላይ
ሳብኩት። በየቦታችን ተመልሰን ተቀመጥን
ካፌው ውስጥ ሌሎች ሰዎች እንዳሉና እንደሚያዩን ገና አሁን
ታወቀኝ። አፈርኩ፡፡ ግምባሬን አላበኝ፡፡ መሀረቤን አውጥቼ
ጠረግኩት። ባህራም እንደገና መሀረቡ ውስጥ ተፋ፡፡ ሳቅ እያለ
«እንደሱ እንኳ ይሻላል» አለኝ
አንድ ነገር አስታወስኩ፡፡ ባህራም ቢፈልግ ነብሴ እስኪመጣ
ሊደበድበኝ ይችል ነበር! እንደገና አላበኝ። በመሀረቤ ጠረግኩት
ከዚህ በኋላ ከባህራም ጋር እንደ ድሮው ማውራት ጀመርን።
የደረሰበትን እጫወተኝ። ኒኮል ማርገዟን ስታውቅ መበሳጨት
ጀመረች፡፡ ባህራም ከስራ ሲወጣ ብስጭቷ እየባሰባት ሄደ።
ሉልሰገድና ጀምሺድ ከሞቱ በኋላ፣ ብስጭቱ ወደ እምባ ተለወጠ፡፡
ማታ ማታ ታለቅሳለች። ባህራም ያባብላት፣ በስጋ ይገናኛትና
ያስተኛታል እሷ ስትተኛ እሱ ሲጋራ አቀጣጥሎ በጨለማው ስለ ኢራን
ያስባል። ከንቱ! ያ ሁሉ ዝግጅት ከንቱ ቀረ፡፡ ያ ሁሉ አመታት
በከንቱ አለፈ፡፡ ማኑ ያ ኢራን ሳሉ የ«ፍሬ አለቃው የነበረ
ስለአምባጓሮ ያስተማረው ውድ ጓደኛው ማኑ በሱ ቦታ ቢሆን
አሁን ምን ባደረገ ነበር? ለመሆኑ፣ ማኑ የት ይሆን? እዚያው
እንግሊዝ አገር ይሆን?
«ይገርምሀል” አለ ባህራም ሲነግረኝ አንድ አስር ቀን ያህል
በተርታ፣ ማታ ማታ ስለማኑ ብዙ ብዙ አሰብኩ። እና አንድ ቀን
ከሱ ደብዳቤ መጣልኝ። አይገርምህም? አድራሻዬን እንዴት እንዳገኘ
«ደብዳቤው ምን ይላል?» አልኩት፡፡
ከኪሱ ሁለት በአረብ ፊደላት የተፃፉ ደብዳቤዎች አውጥቶ
አንዱን ተረጎመልኝ
«ብዙ ብዙ የምነግርህ አለኝ፡፡ ግን በደብዳቤ አይሆንም።ስንገናኝ ነው። እዚህ ለንደን ውስጥ ሶስት ሚልዮን ፓውንድና ኣንድ
ዘመናዊ ማተሚያ ቤት አለን፡፡ ገንዘቡ ከቻይና፣ ከሶቭየት ህብረትና ከሌሎች ወዳጆች የተሰጠን ነው፡፡ ብዙ ሌላ እርዳታም ተሰጥቶናል፡፡
አስራ አምስት ሺ ካላሽኒኮቭ ጭምር! እንግዲህ ጊዜው ደረሰ፡፡
ፎቶግራፍህን ላክልኝና ፓስፖርት ይዤልህ እመጣለሁ። እኔና አንተ
አገራችን እንገባለን፡፡ እዚያ ብዙ ብዙ ስራ ይጠብቀናል። ዝግጁ ነህ?እንዲያው ነው የምጠይቅህ እንጂ ዝግጁ እንደሆንክ እርግጠኛ ነኝ፡፡ይህን ሁለት አመት የት የት ነበርኩ መሰለህ? ፒኪንግ፣ ሞስኮ፣ፕራግ፣ ቡዳፔስት ብቻ ስንገናኝ እነግርሀለሁ። ቶሎ ፎቶህን ላክልኝ»
ባህራም ደብዳቤውን እጥፎ ኪሱ ከተተ። ረዥም ዝምታ ሰዎቹ ካፌው ውስጥ ያወራሉ። አንዷ ኮረዳ ከሽንት ቤት ወጥታ

👍18❤1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አምስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....ዣን ቫልዣ ለመተኛት ዓይኑን ከመጨፈኑ በፊት «ከዛሬ ጀምሮ
ከዚህ እኖራለሁ» ሲል ተናገረ:: እነዚህ ቃላት የሚስተር ፎሽለማን ጭንቅላት ሲበጠብጡ አደሩ:: ሁለቱም እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ነው ያደሩት:: ዣቬር ፍለጋውን እንደሚያጧጥፍ ዣን ቫልዣ ያውቃል፡፡ ኮዜትና ዣን ቫልዣ
ወደ ከተማ የተመለሱ እንደሆነ ይያዛል፡፡ ስለዚህ ከገዳሙ ውስጥ መቆየት እንደሚሻል ዣን ቫልዣ አመነ፡፡ ሆኖም ለመደበቅ የሚያመች ስፍራ ቢሆንም ወንድ ከዚያ ስለማይገባ አደገኛ ነው፡፡ ከገዳሙ ውስጥ መኖሩ
ከታወቀ በወንጀል ተከስሶ ይታሰራል::
ሚስተር ፎሽለማ ደግሞ ስለነገሩ ግራ ገብቷቸው ስለተጨነቁ እንቅልፍ አልወሰዳቸውም፡፡ «እንዴት ከንቲባው ከዚያ ሊገባ ቻለ? ጋዳሙ ዙሪያውን በግንብ አጥር በመታጠሩ ሰው ከዚያ ሊገባ አይችልም:: ልጅትዋን ከየት አመጣት? ማንም ቢሆን ልጅ አዝሎ ከግንብ ላይ ሊወጣ አይችልም:: ልጅትዋስ የማን ልጅ ናት? ከየት ነው የመጡት? ምናልባት ገንዘብ አጉድሎ
እየሽሽ ይሆን? ወይስ በፖለቲካ ጉዳይ እየተፈለገ ነው?» ሲሉ ሽማግሌው ራሳቸውን ጠየቁ፡፡ «ምናልባት ገዳሙን የመረጠው ጥሩ የመደበቂያ ሥፍራ
ስለሆነ ይሆን?» ሲለም አሰበ::
«መሴይ ማንደላይን ከሞት ያዳነኝ ሰው ስለሆነ አሁን የእኔ ተራ
ነው» በማለት ዣን ቫልዣን ለመርዳት ወሰኑ፡፡
«ለሕይወቱ ሳይሳሳ ያንን የሚያህል ጭነት ከጫነው ጋሪ ስር ገብቶ ነው ሕይወቴን ያዳናት! ግን እርሱን ከዚህ ማኖር ወንጀል ነው:: ብያዝ ምን እመልሳለሁ ሲሉ
ተጨነቁ
ሽማግሌው እስከዚህም ለሰው የሚጨነቁና ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰው አልነበሩም:: አሁን ግን በእድሜም እያረጁ ስለሄዱ ፣በስተእርጅና ሰው ላይ ምን አስጨከነኝ፣ የሚል ስሜት ተሰማቸው:: የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ገዳም ውስጥ ለሁለት ዓመት ስለኖሩ ስለሕይወት የነበራቸው አመለካከት
ሳይለወጥ አልቀረም:: በመጨረሻ ሕይወታቸውን ለመሴይ ማንደላይን ለመሰዋት ወሰኑ።
ሚስተር ፎሽለማ ቀስ ብለው በር ሲያንኳኩ «ይግቡ» የሚል መልስ
አገኙ:: የገዳሙ ኃላፊዎች ቢሮ ነበር፡፡ ከቢሮው እንደጎቡ ለጥ ብለው እጅ
«እርስዎ ነዎት እንዴ አባታችን፡፡›
እንደገና ለጥ ብለው እጅ ነሱ፡፡
«እኔ ነኝ ያስጠራሁዎት፡፡»
«በጥሪው መሠረት መጥቻለሁ::»
«ለምን ነበር እኔን ለማነጋገር የፈለጉት?»
«ጉዳይ ነበረኝ፡፡»
«የምን ጉዳይ?»
ሚስተር ፎሽለማ ለሁለት ዓመት ገዳሙ ውስጥ ሲኖሩ ከተማው
ውስጥ የሚነገረውን ሁሉ ይሰማሉ፡፡ ግን የሰሙትን ሁሉ የመደበቅ ችሎታ ነበራቸው:: የገዳሙ ነዋሪ እንደቂል ነበር የሚያያቸው:: ሴሮች ግን
በጣም ያከብሯቸዋል። ሽማግሌው ስለሥራቸው ስፋት ለሴሮች ኃላፊ ብዙ አወሩ። ቀኑ አልበቃ ብሏቸው ሌሊቱን ሁሉ በጨረቃ ብርሃን እንደሚሠሩም «ብዙ ለኃላፊዋ ከገለጹ በኋላ አንድ ወንድም እንዳላቸውና
እርሱም ከእርሳቸው
በእድሜ ይነስ እንጂ ልጅ አለመሆኑን አስረዱ፡፡ ወንድማቸው ከእርሳቸው ጋር እንዲኖር ቢፈቀድላቸው በሥራ ብዙ ሊረዳቸው እንደሚችል ሲናገሩ
የኃላፊዋ ሰውነት ተሸማቀቀ፡፡
ሽማግሌው ንግግራቸውን በመቀጠል ወንድማቸው ጎበዝ አትክልተኛ መሆኑን እርሱ ካልረዳቸው በእድሜ ምክንያት ሥራው ስለሚከብዳቸው
ምናልባት ሥራውን ለመልቀቅ እንደሚገደዱ ተናገሩ፡፡ በተጨማሪም ወንድማቸው ትንሽ ሴት ልጅ እንዳለውና ከእርሳቸው ጋር እንዲኖር ከተፈቀደላቸው ልጅትዋ በሃይማኖት ተኮትኩታ ልታድግ እንደምትችልገለጹ:: ምናልባት አንድ ቀን ይህቺ ልጅ መንኩሳ ቤተክርስቲያንን ልታገለግል እንደምትችልም አስረዱ፡፡
ሽማግሌው እንደጨረሱ ኃላፊዋ መነኩሲት ሥራ እንዲሠሩ
አዘዝዋቸው፡፡
«እስከ ነገ ማታ አንድ ወፍራም ብረት ሊገዙልኝ ይችላሉ?»
«ለምን ሥራ?»
«ለአንድ ሥራ!»
«ምን ገድዶኝ፣ እችላለሁ እንጂ!» ሲሉ መለሱ ሽማግሌው፡፡
ኃላፊዋ መነኩሲት ይህን ተናግረው ወጥተው ሄዱ:: ፎሽለማ ብቻቸውን ቀሩ
አንድ ሩብ ሰዓት አለፈ፡፡ ኃላፊዋ ሴር ተመልሰው ከመቀመጫቸው
ተቀመጡ፡፡ ሁለቱም አሳብ የያዛቸው መሰሉ፡፡
«አባታችን?»
«እማሆይ!»
«የጸሎት ቤቱን ያውቁታል?»
«ለቅዳሴ አልፎ አልፎ ወደዚያ ስለምሄድ አውቀዋለሁ፡፡»
«ከዚያ ይሄዳሉዋ?»
«ከአንዴም ሁለቴ፤ ከሁለቴም ሦስቴ ሄጃለሁ፡፡»
«ከዚያ የሚፈነቀል ትልቅ ድንጋይ አለ፡፡
«ከባድ ነው?»
«የሚፈነቀለው ድንጋይ ያለው ከቤተመቅደሱ አጠገብ ነው::»
«ብዙ ቦታ ከሆነ አንድ ሰው ብቻውን መፈንቀል አይችልም:: ሁለት ወንዶች ያስፈልጋሉ፡፡»
«ከመነኮሳቱ መካከል አራቱ ይረዱዎታል፡፡»
«ይኸው ነው ሥራው?»
«ዛሬ ጠዋት አንዲት ሴር እንደሞቱ ያውቃሉ?»
«የለም፤ አላወቅሁም::»
«ለሙታን የሚደረገውን ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡ ሟችዋ ሴር ቆመው ይጸልዩበት ከነበረው መሬት ስር አጽማቸው ያለሳጥን ማረፍ አለበት፡፡
ነፍሳቸው ከሥጋቸው ከመለየቱ አስቀድሞ የጠየቁት ጥያቄ ነው:: መጠየቅ ሳይሆን ያዘዙት ነገር ስለሆነ መፈጸም ይኖርበታል፡፡
«ከዚያ ጸሎት ቤት ሰው መቅበር እኮ የተከለከለ መሆኑን ያውቁ
የለ፡፡»
«ወንዶች ናቸው የከለከሉት? ፤ እግዚአብሔር ግን ይፈቅዳል፡፡
«ወሬ ቢሰማስ?»
«በእርስዎ ላይ እምነት አለኝ፡፡»
«ግን እማሆይ፤ የጤና ጥበቃ ተወካይ..»
«የሃይማኖት መሪዎች ስለቀብር የደነገጉት ሕግ አለ፡፡»
«ሆኖም የፖሊስ አዛዥ ...
«የጥንት ነገሥታት ፈቅደዋል፡፡»
«አስተዳዳሪው...»
«በእግዚአብሔር ፊት እርሱም ከቁጥር አይገባም::»
«አሁን እማሆይ?» አሉ ሽማግሌው::
«እምነት እንጣልብዎ?»
«እታዘዛለሁ::»
«በዚሁ ይለቅ፡፡»
«እማሆይ ለጠቀሱት ሥራ ሁለት ሜትር የሚሆን ወፍራም ብረት
ያስፈልገኛል፡፡»
«የት ታገኛለህ?»
«እዚሁ ግቢ ውስጥ እቃ ከምናስቀምጥበት ሥፍራ ብረት ያለ ይመስለኛል፡፡»
«ይኸው ነው እማሆይ? አሁን ስላሉት በሰዓቱ እገኛለሁ::»
««የለም፤ ሌላም ነገር አለ፡፡»
«ምን አለ?»
«የተገዛው የሬሣ ሣጥን ጉዳይ::»
ሁለቱም መልስ ሳይሰጡ ተፋጥጠው ለጥቂት ሰኮንድ ቆዩ::
«የሬሣ ሣጥኑን ምን እናደርገዋለን?» ሲሉ ኃላፊዋ ጠየቁ፡፡
«ይቀበራላ!»
«ባዶውን?»
«እማሆይ፤ እኔ ባፈር እሞላዋለሁ:: አፈር ቢሞላበት ሰው ያለው
ይመስላል፡፡»
«ልክ ነዎት፡፡ ሰውም ቢሆን እኮ ከአፈር ነው የተሠራው:: እንግዲህ
ባዶውን ሣጥን እርስዎ ያዘጋጁታል?»
«በሚገባ!» ብለው ከመለሱ በኋላ ለመሄድ ወደ በር አመሩ፡፡
«በመልዕክት አቀባበልዎ ደስ ነው ያለኝ:: ወንድምዎን ነገ ከእኔ
ዘንድ ያምጡት፡፡ ልጁንም ይዞ ይምጣ፡፡
ያን እለት ማታ ዣን ቫልዣ ኮዜትን ይዞ ወደ ኃላፊዋ ሴር ሄደ፡፡
ሴርዋ ዣን ቫልዣን ከእግር እስከ ራስ አዩት:: ኮዜትንም እንደዚሁ ከአዩዋት በኋላ
«ይህ ቤት ሳያስማማት አያቀርም» ሲሉ ተናገሩ::
ኃላፊዋ ሴር አብረዋቸው ከነበሩት ከሌሎች ሁለት ሴሮች ጋር
ጥቂት ተወያዩ:: ከዚያም ኃላፊዋ ሚስተር ፍሽለማን እያዩ፡- «አባታችን፤ ሌላ ጉልበት ላይ የሚታሰር ቃጭል ይሰጥዎታል፡፡ አሁን እንግዲህ ሁለት ወንዶች ስለምትሆኑ ሁለት ቃጭል ነው የሚያስፈልጋችሁ» አሉ፡፡
በሚቀጥሉት ቀኖች የሁለት ቃጭል ድምፅ ከአትክልቱ ውስጥ ተሰማ፡፡
ሴሮች በዚያ ባለፉ ቁጥር ሁለት አትክልተኞች ጎን ለጎን ሁነው አበባውን ሲኮተኩቱ ተመለከቱ፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ሴሮች በብዛት በዚያ አለፉ፡፡ሁለቱ አትክልተኞች ድምፅ ሳያሰሙ ይኮተኩታሉ፡፡ ፀጥታው ድንገት ደፈረሰ፡፡
«አብሮ የሚኮተኩተው ረዳት አትክልተኛ ነው» ካለ በኋላ የአባታችን የሚስተር ፎሽለማ ወንድም ነው» ሲሉ ተናገሩ፡፡

👍19👎2