አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_አራት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


...አንድ ማታ ኒኮልን ከተማ ሬስቶራንት እራት ጋበዝኳትና ብዙ
ወይን እያጠጣኋት ስለልብ ወለድ መፃህፍትና ስለ ፊልሞች ጨዋታ
እስጀመርኳት። መጀመሪያ ስለምንወዳቸው ደራስያን፣ ስላየናቸው ፊልሞች፣ ስለምናውቃቸው ሰዎች እና በልብ ወለድ መፃህፍት ውስጥ ካገኘናቸው ሰዎች ጋር በምን እንደሚመሳሰሉ ማለት
ስለራሳችን ሳይሆን ስለ ሌላ ነገር ስናወራ፣ ወይን ስንጠጣ፣ ብዙ ጊዜ አሳለፍን። እየለመደችኝ ሄደች። ወይኑም እየሰራ ሄደ። አይናፋርነቷ እየረገፈ፣ እንደ ልቧ ለማውራት እየቻለች ሄደች፡፡ እኔም ፈረንሳይኛ እሷ ስትናገረው በጣም የሚጥም መሆኑን እያስተዋልኩ ሄድኩ።

ቀስ ብዩ ወሬውን ወደ ባህራም ወሰድኩት:: እንዴት ጎበዝ ሆኖ
እንደሚታየኝና፣ ምን ያህል እንደማደንቀው ከነገርኳት በኋላ፣
ባህራም ላንቺ እንዴት ሆኖ ነው የሚታይሽ? አልኳት። ደራሲ
መሆን እንደምፈልግና ስለሰዎች ማወቅ እንዳለብኝ፣ ይልቁንም
ሴቶች ወንዶችን እንዴት እንደሚያዩዋቸው ማጥናት እንደሚገባኝ ስለዚህ፣ እሷ ስለራሷ ብትነግረኝ ለኔ ትልቅ ዋጋ እንዳለው፣ በሰፊው ዘረዘርኩላት። ተቀበለችኝና ስትናገር፣ በቃላትዋ እየተንሳፈፍኩ የድምፅዋ ዜማ እየተመቸኝ አዳመጥኳት
ደራሲ ሳትሆንም ስለራሴ ብነግርህ ግድ የለኝም አለችኝ።
ባሀራም ስላንተ ብዙ ጥሩ ጥሩ ነገር ስለነገረኝ ነው መሰለኝ፣ በጣም የማውቅህ መስሎ ይሰማኛል። ደሞ እወድሀለሁ:: በጣም ተወዳጅ ልጅ ነህ። ብዙ ሴቶች ይህን ነግረውህ የለ? ተናገር፡ (ትስቃለች።እሷ የተናገረችው በንፁህ ልብ ነበር። እኔ ግን ምኞቴ ተቀሰቀሰ፡፡
እግሮቼን አጣመርኩ። የሉልሰገድንና የሷን ታሪክ ባላውቅ ኖሮ አሁን ምኞቴ ይቀሰቀስብኝ ነበር? እንጃ፡፡ ኒኮል ቀጠለችልኝ

«በአስራ ስድስት አመቴ ማርሴል ከሚባል ልጅ ፍቅር ያዘኝ
ማርሴልም ወደደኝ። ቤቶቻችን ሁለቱም ሀብታም ቡርዥም
በመሆናቸው ይከባበሩና ይዋደዱ ስለነበረ፣ በመዋደዳችን እጅግ
ተደሰቱ። እስክንጋባ ቸኮሉ፡፡ ግን
ሁለታችንም የዩኒቨርሲቲ
ትምህርታችንን እስክንጨርስ ላንጋባ ቆረጥን። ቤቶቻችንን ለማስደ ሰት ስንል ተጫጨን፡፡ በዚህ መካከል ማርሴል አየር ሀይል ገባ

«አንቷን ደ ሴንት ኤግዙፔሪን ታውቀው የለ? በኤሮፕላን
ስለመብረር፣ ስለአደጋው፣ ስለክብሩ፣ ስለጀግንነቱ የደረሳቸውን መፃህፍት፣ ማርሴል ደጋግሞ ያነባቸው ነበር፡፡ ከልቡ ሴንት ኤግዙፔሪኝ ያደንቀው ነበር፤ ያመልከው ነበር፡፡ ለዚህ ይመስለኛል አየር ሀይል የገባው፡፡ እኔ ተው አትግባ፤ እንደ ሴንት ኤግዙፔሪ በኤሮፕላን አደጋ ትሞታለህ፣ አልኩት። መሞት የት ይቀራል? አለኝ። የሰው ልጅ ተግባሩ ከሞት ለማምለጥ መጣጣር ሳይሆን፡ ሞት
እስኪመጣ ድረስ ክብር ያለው፣ ኩራት ያለው ኑሮን መኖር ነው፣
አለኝ። አለቀስኩ። እምባዬን ጠረገልኝ። አሮፕላን ነጂ ሆነ
ይህ ሁሉ ሲሆን በግብረ ስጋ ሊገናኘኝ ይሞክር ነበር፡፡ በብዙ
ይለምነኝ ነበር፡፡ ሳንጋባ አይሆንም ብዬ እምቢ አልኩት አንድ ቀን የኤሮፕላን እደጋ ደረሰበት። ሁለት ወር ሙሉ ሀኪም ቤት ተኛ። ከዚያ ወደ ቤቱ መጣ። የአየር ሀይል ኑሮ፣ የሴንት ኤግዙፔሪ አይነት ኑሮ፣ ክብር፣ አደጋና ጉብዝና የሞላበት ኑሮ፣ የጀግኖች አይነት ኑሮ በቃው:: ከአየር ሀይል አሰናበቱት።ምክንያቱም ወገቡ ተሰብሮ እግሮቹ ሽባ ሆኑ። በተሽከርካሪ ወምበር ቁጭ ብሎ፣ እኔ ወይም እናቱ እየገፋነው ነበር አየር ለመቀበል እንኳ የሚወጣው
«ካንጀቴ አዘንኩለት፡ በሀይል ወደድኩት እሱ ግን አሁንም ሽባ ሆኖ የሴንት ኤግዘፔሪን መፃህፍት
ያነብ ነበር። ስለአደጋ፣ ስለጀግንነት፣ ስለክብር ስለሞት ያነብ ነበር።አንድ ቀን ሽጉጡን ጠጥቶ ሞተ ሀዘን ጀመረኝ። ግን ሀዘን ይለመዳል። ወጣት ከሆንክማ ትንሽ ቆይቶም ይረሳል። በተለይ ያጠቃኝ ፀፀት ነበር። ፀፀት አይለመድም፣
አይረሳም፣ የማይጠግብ የማይተኛ ውስጣዊ ትል ነው፡ እድሜ ልክህን ይበላሀል። የቆጨኝ ማርሴል በግብረ ስጋ ሊገናኘኝ ሲፈልግ እምቢ ማለቴ ነው:: እወደው ነበር፡ ስጋዬን ለሱ መስጠት እንዴት አቃተኝ? በሀይል ይቆጨኝ ይሞረሙረኝ ጀመር

ነብስ አባቴ ጋ ሄድኩና ሁሉን ተናዘዝኩ፡፡ የሠራሽው ልክ
ነበር አሉኝ። እኔግን ፍፁም ስህተት እንደነበረ የበለጠ እየተገነዘብኩ ሄድኩ፡፡ ራሴን መቅጣት ጀመርኩ፡፡ ከጠየቀኝ ሁሉ መተኛት
ጀመርኩ። ደሞ ብዙዎች ይጠይቁኝ ጀመር። ርካሽ ሴት ሆንኩ

«ግን አሁንም ፀፀቱ አልተወኝም»

በካሎሪያዬን እንዳለፍኩ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት ወደ ኤክስ
መጣሁ፡፡ ቤቶቼም ማርሴልን ለመርሳት ካለአቨር ከተማ መራቅ
እንዳለብኝ ስላወቁ ሂጂ አሉኝ። ኤክስ መጥቼ በርካሽነቴ ላይ
ጠጪነት ጨመርኩበት። የፈለገኝ እንግዲህ እስክሰክር ድረስ ማጠጣት አለበት። ብዙ ሰአት ካንዱ ጋር ስጠጣ አመሻለሁ። ጧት ወደ አምስት ሰአት ላይ ስነቃ አልጋው ውስጥ ነኝ፡፡ ሲደሰትብኝ እንዳደረ ይታወቀኛል፣ ግን ምን ምን እንደሰራን እንደ ህልም'ንጂ እንደ ውን ሆኖ አይታየኝም

ካንዲት የኔ ብጤ ርካሽ ጋር ገጠምኩ፣ አብረን መጠጥና
ወንድ ስናሳድድ እናመሽ ጀመር

እንዲህ ስል አመቱ አለፈ፡ ፈተና ወደቅኩ፡ ክፍል ደገምኩ፣
ሁለተኛው አመት ተጀመረ፣ ያንኑ ኑሮዩን ቀጠልኩ

አንድ ረቡእ ጧት እንደ ልማዴ አንዱ እማላውቀው መኝታ
ቤት ነቃሁ። ሰውየው ቁርስ ያቀርባል፡፡ ልዩ ሰው ሆኖ ታየኝ።
ሳይነካኝ አድሯል፡፡ ከመስከሩ የተነሳ ሊነካኝ ባይችል ነው እንዳልል፣ ትላንት ማታ ፓርቲው ጋ ልሰክር ትንሽ ሲቀረኝ ጠጣ እንጂ»
ስለው ሁለታችንም ከሰከርንማ ማን ማንን ይደግፋል?» ሲለኝ
አስታወሰው
“አልጋ ውስጥ እንዳለሁ ቁርስ ከበላን በኋሳ፣ ሰውየው በተሰባበረ
ፈረንሳይኛ
“ እንቁላል ከተሰበረ ወድያ ምንም
እንደማይሆን ታውቂ የለ?» አለኝ፡፡ ምን እንደሚል ሳይገባኝ «አዎን”
አልኩት። ወጣትነትም አንዴ ከተሰበረ ሊጠገን አይችልም» አለኝ

«ምን ማለትህ ነው?» አልኩት

«ያንቺ ወጣትነት ገና አልተሰበረም:: ግን ሊሰበር ትንሽ ነው የቀረው። እንደዚህ አይነት ኑሮ ከቀጠልሽ ከትንሽ ጊዜ በኋላ
ይሰበራል»

ተናደድኩ «ምን አገባህ?» አልኩት
«ምን አገባህ አትበይኝ፡ ፈረንሳይ መሰልኩሽ እንዴ? እናንተ
ፈረንሳዮች ፈሪ ናችሁ፡፡ ግብዝ ናችሁ። ተግባራችሁን መፈፀም
አስቸጋሪ የሆነባችሁ እንደሆነ፣ እኔ ምን አገባኝ? Ca me regarde pas. ብላችሁ ትተዉታላችሁ፡፡ እኔ ግን እንደሱ አይደለሁም፡፡»

«እና በኔ ህይወት አንተ ምን አገባህ?»

«አንቺ አልጋዬ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ? በኔ ህይወት ውስጥ
ገባሽ ማለት አይደለም?» አለኝ። መልስ ስላጣሁ ዝም አልኩ
መጥቶ አልጋው ላይ አጠገቤ ቁጭ እለና፣ አይን አይኔን እያየኝ
«አሁን እስቲ ለሁለት ደቂቃ ፈረንሳይ መሆኑን ተይና ሰው
ሁኚ፡፡ ለሁለት ደቂቃ ብቻ፣ እሺ? አለዚያ ለመናገር አልችልም»
አለኝ፡፡ አንድ አይነት ደግ ፈገግታ አሳየኝ፡፡ ረስቼው የነበረ
አይናፋርነቴ ድንገት ተመልሶ ሽፍን አደረገኝ፡፡ ወደታች ሳይ ፊቴን
በእጆቹ ይዞ ቀና አደረገኝና ግምባሬን ሳመኝ

«አገሬ ኣንቺን የሚያካክሉ ታናናሽ እህቶች አሉኝ፡፡ አንቺ
የምታረጊውን ሲያረጉ ባያቸው ዝም አልላቸውም። ስለዚህ አንቺንም ዝም አልልሽም። ይገባሻል?»
👍28👏2
ዝም ብዬ ሳየው ቀጠለ አሁን እንግዲህ ባንቺ ቤት አደግኩ
ብለሻል። አልኮል ጠጥተሽ ስለሰከርሽና፣ የማታውቂው ሰው አልጋ ውስጥ ስላደርሽ የበሰልሽ ይመስልሻል። ግን ዋናው መብሰል ራስን ማወቅ ነው:: ራስሽን ብትመረምሪ ደሞ ርካሽ ሴት እንዳልሆንሽ ትገነዘቢያለሽ፡፡ ታድያ ርካሽ ሳትሆኚ አንደ ርካሽ ሴት መኖር ምን ይባላል? እኔ መቸስ ህፃንነት ነው እላለሁ።»
ዝም ኣልኩት። እውነትክን ነው አላልኩትም
«ትምህርት አለብኝ መሄዴ ነው:: መሄድ ካለብሽ ሂጂ፡፡ መሄድ
ከሌለብሽ ግን እዚህ ቆይኝና አብረን ምሳ እንበላለን» ብሎኝ ሄደ።ተመልሶ ለምሳ ወሰደኝ፡፡ ከተመገብን በኋላ ካፌ ገብተን ቡና ስንጠጣ ሰሙን ነገረኝ

እና ባህራም ምንሽ ነው? ብለህ ብትጠይቀኝ፣ ቀላል መልስ
ልሰጥህ አልችልም:: የስጋ ወዳጄ ነው፡ የመንፈስ ጓደኛዬ ነው፣
የህይወቴን አቅጣጫ ለበጎ ያስለወጠኝ ጠባቂዬ ነው»
የኒኮል ውበት ጉም እንደሸፈነው ተራራ ነው፤ ጉሙ በፀሀይ
ሙቀት ቀስ እያለ ሲተን፣ ተራራው መታየት ይጀምራል። በኔና
በኒኮል መካከል የነበረው እንግዳነትና አይናፋርነት እየተገፈፈ እየተዋወቅን እየተለማመድን ስንሄድ፣ ውበቷ እየተገለፀልኝ ሄደ:አይኖቿ ንፁህ ውሀ አረንጓዴ ሆነው፣ ረዣዥም ሽፋሎቿ አረንጓዴ ኩሬ ዙሪያ በተርታ የበቀሉ ሀር ጥቁር ቄጤማዎች ይመስላሉ።
አስተያየቷ ልስልስ ያለ ሆኖ፤ ሀዘን የተሞላ ይመስላል። ድምፅዋ
ውስጥ የማር ጠብታ አለ፤ ፈረንሳይኛዋ የታላላቆቹን ደራሲያን ቋንቋ ይመስላል። ይህ ውበቷ ቀስ እያደረገ፥ ሳይታወቀኝ፡ ልቤ ውስጥ ገባ፡፡ በሌለችበት አስባት ጀመር። ስትራመድ ባየኋት ቁጥር፣ ሉልሰገድ
«አልጋ ውስጥ የባለጌ መጨረሻ ናት» ያለኝን አስታውሳለሁ፡ እኔና
እሷ ባለጌ ነገር ስንሰራ ይታየኛል. .. ካለችበት ቦታ መንጭቄ ወደ ሀሳቤ ጫካ እወስዳታለሁ፤ እንደ እንሰሳ ዛፍ ስር አስጎንብሼ እስራታለሁ፤ አፏን ትከፍታለች። ጣቶቼን አፏ ውስጥ እከታለሁ፤ ትጠባቸዋለች፣ ታኝካቸዋለች. ..

ሉልሰገድ ኒኮልን ሊተዋት ሞከረ። ከልቡ ሞከረ። አልቻለም፡፡
ይታገስ ይታገስና፣ ሄዶ ይለምናታል። ጥፋ ከፊቴ ትለዋለች። እኔ ጋ መጥቶ “ካፌ ኒኮል ይወስደኝና ቡና አይነት ቢራችንን አየጠጣን ስለኒኮል ያወራልኛል። ስለአሸዋ ጡቶቿ፣ ስለወተት ጭኖቿ፣ ስለነበልባል እምሷ፣ ስለቅዱስ ብልግናዋ፣ የቃላት ቃና ይፈጥራል።
በቃላቱ ላይ እየተንሳፈፍን የኤክስን ፀሀይ እየሞቅን በሀሳባችን ኒኮል
ጭኖች መሀል ገብተን እንጨማለቃለን። ኣንድ ሽባ አይነት ደስታ ልባችን ውስጥ ይንፏቀቃል
እስካሁን እንግዲህ በጋ ኣልፎ፣ በልግ ተጋምሷል። ቅጠሎቹ
አረንጓዴ ሰልችቷቸው በቡና እይነት፣ በብጫ ብጤ፣ በቀይ መሳይ ቀለማት አሸብርቀዋል። ፀሀይዋ ከኛ እየራቀች ትሄዳለች፣ ሙቀቷ እየተቀነሰና እየጣመን ይሄዳል። ከምሳ በኋላ ኩር ሚራቦ ላይና በየመናፈሻው ውስጥ የኤክስ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች አግድም ወምበሩን ሁሉ ሰፍረውበት፣ በፀሀይ እንደ ዶሮ ያንቀላፋሉ። ህፃናቱ
እሽዋ እየሰፈሩ ወይም
ባለሶስት እግር ብስኪሌት እየነዱ
ይንጫጫሉ። እንዳንዶቹም ከእናታቸው ወይም ከአያታቸው ጋር ኳስ እየተወራወሩ ይጫወታሉ፡፡ የኤክስ አዛውንት «ቡል» የተባለውን ጨዋታ የብረት ኳስ እየወረወሩ ይውለብታል። ጎረምሶቹና ኮረዳዎቹ በየካፌው ተቀምጠው ያወራሉ፡፡ በየዛፉ ስር ሳር ላይ ተጋድመው ይሳሳማሉ፡፡ ንፁህ ውብ ሰማይ ከኤክስ ሰላይ ተዘርግቷል፤ ፀሀይዋ ብቻዋን እንደምትንሸራሸር ብጫ የእሳት ኳስ ናት ።ሊመሽ ሲል፣
ለአንድ ሰአት ያህል ፀሀይዋ እንደ ትልቅ ብርቱካን ሰማዩ ዳር ላይ
ትንጠለጠላለች፣ የኤክስ ውብ ሰማይ እንደ ልጃገረዶቹ ጉንጭ
ፅጌረዳ ቀለም ይለብሳል። ከዚያ የተንጠለጠለችው ቀይ ብርቱካን
አድማሱ ውስጥ ትገባለች የኤክስ ሰማይ ቀስ እያለ ይጠቁራል፣
ኮከቦቹ ብቅ ብቅ ይላሉ።
አንዳንድ ቀን ግን ሚስትራል» የተባለው ሀይለኛ ነፋስ ኤክስን
በጥፊ ይላታል፣ ሽማግሌዎቹና ህፃናቱ በየቤታቸው ይሸሽጋሉ፤
የልጃገረዶች ፀጉር ይበታተንና ወደአንድ በኩል ይፈሳል፤ ቀሚሳቸው ወጣት ገላቸው ላይ ይለጠፍና ቅርፃቸውን ወለል አርጐ ያሳያል። ሰዎቹ ሲሄዱ ጐምበስ ብለው፣ ፊታቸውን አጨማደው፣ የያዙትን እቃ አቅፈው፣ ከንፋሱ ጋር እየተጋፉ ነው። ሚስትራል ልክ ለሶስት፣ለስድስት፣ ወይም ለዘጠኝ ቀን ነው የሚነፍሰው ይባላል፡፡ ነፍሶ ሲሰለቸው ይሄዳል። ኤክስ ውስጥ ሰላም ይመለሳል. . .

ሲልቪ ትፅፈው የነበረው ረዥም ልብወለድ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ እምቢ አላት። ከዚህ በፊት፣ አንድ መቶ ገፅ ያሀል ከፃፈች በኋላ፣ ከደረሰችበት መቀጠል ፈልጋ ታሪኩ እምቢ ብሏት፣ እኔን በጣም አስቸግራኝ ነበር፡፡ አንዴ ማርሰይ ውሰደኝ ትለኛለች፣ አንዴ ናይት ክለብ ውሰድና እስክረኝ ትለኛለች፣ አንዴ ጫካ ውሰደኝና ፍቅር እንስራ ትለኛለች፣ አንዴ ቤት መጥተህ ቁጭ በልና እኔ ልፃፍ ትለኛለች። ይሄ ሁሉ ሲሆን፣ ድንገት ኩርፍ ኩርፍ እያለች ትእግስቴን ታስጨርሰኛለች።

በመጨረሻ፣ ከፊቴ ጥፋ፣ እኔ መጥቼ እስክፈልግህ ድረስ
ፊትህን እንዳታሳየኝ አለችኝ፡፡ እሺ አልኳት። ከስድስት ቀን በኋላ፣
መጣችና እየሳቀች «ስላስቸገርኩህ ይቅርታ አርግልኝ
አለችኝ

አሁን ደሞ መቶ ዘጠና ገፅ ላይ ካደረሰችው በኋላ፣ ታሪኩ ወደፊት አልቀጥልም እምቢ አላት። አሁንም አባረረችኝ። በሷ
ምክንያት እኔም መፃፍ እምቢ አለኝ ሉልሰገድን በበኩሉ የኒኮል እምቢታ ይጫወትበታል። ስለዚህ
ቤታችን« ካፌ ኒኮል» ሄደን ቡና አይነት ቢራ እናዛለን። ሉልሰገድ
ስለኒ ኮል ያወራልኛል። በምኞት እየጋልኩ ኣዳምጠዋለሁ

«የኒኮልን ጡት እንግዲህ እንደ ነጭ ሰማይ ልታየው ትችላለህ::
ሰማዩ መሀል ላይ ደማቅ ወይን ጠጅ ጨረቃ አለች። ወይን ጠጁን
ጨረቃ ሮዝ ቀለም ብርሀን ከቧታል:: ይታይሀል? ታድያ ያንን
ሞቃት ነጭ ሰማይ እየዳበስኩ ጨረቃዋን መጉረስ ነው የሚታየኝ

የኒኮልና የሲልቪ ጡቶች ምናቤ ውስጥ ይደሳለቃሉ፥ ሰላም
ይነሱኛል፣ ሉልሰገድ ንግግሩን ይቀጥላል። ...
በልግ ወደ ማለቂያው ተቃረበ....

💫ይቀጥላል💫
👍251
#አንዲት_መርፌ_ስንቱን_ቀዳዳ_ትስፋው


#ሶስት(መጨረሻ)


#በአሌክስ_አብርሃም



እኔ ይሄን ስድብ በፀጋ ተቀብዬ እግር ማየቴን መቼም አላቆምም። የሴት ልጅ እግር የውበት ጥጌ
ነው። ለሰርጌ ቀን አይበለውና እግሯ የሚያምር ግን አንገቷ የተቆረጠ ሴት ጎኔ አምጥተው ሚስትህ ናት ቢሉኝ፣ “በደስታ ይሁን በሐዘን…” ብዬ ከመፈረም አልመለስም። እንዲህ የምንሰፈሰፍለት፣የምማልልለት፣ የምልከሰከስለት፣ ልክስክስክስ የምልለት የሴት ልጅ እግር እንደኔ እንደኔ በሁለት ትላልቅ ክፍል ይከፈላል፣

1ኛ የዓለም ሴቶች እግር ሁሉ በአጠቃላይ ማለት ነው።
2ኛ. የዙቤይዳ እግር ! በቃ እኔን የሚያልከሰክሰኝ፣ በምኞት አፌን የሚያስከፍተኝ፣ ሳመው ሳመው
የሚለኝ ይሄ ሁለተኛው እግር ነው። እናም ድንገት ከቀሚሷ ወጣ ብሎ ፍም የመሰለ ተረከዟ፣የሕፃን
ልጅ ጣት የመሳሰሉ ጣቶቿ፣ ውሃ የመሰሉ (መስተዋትም ይመስሉኛል) ጥፍሮቿ፣ ምንም ቀለም ሳይቀቡ ደግሞ የቁርጭምጭሚት አጥንቶቿ ብይ ብይ መስለው ጠቆር ያለው አረቢያን መጅሊስ ላይ
እንደ እሳት ሲንቀለቀሉ ሳይ ቀልቤን ሳትኩ። ዜድዬ እኮ ለእኔ ሰርክ አዲስ ነች። አይቼ አልጠግባትም ።ተንደርድሬ ሄጄ እግሮቿን ብስማቸው ደስታዬ፤ የሆነ ነገር ሂድ ሂድ እያለ ይገፋኛል።

እ.? ”አሉኝ የዜድ አባት

“እ?…” አልኳቸው እኔም፣ የተናገሩትን ባለመስማቴ አፍሬም ደንግጬም ነበር፤(ታዲያ ምን ላድርግ እኔ የብቸኝነት፣ የክህደት፣ የውሸት፣ የማስመሰል፣ የጥቅም ማሳደድ እና የዝሙት ቆፈን በሚያቆራምደው ከተማ፣ የፍቅር እሳታቸውን ወልደው እሳት ውስጥ ቆሜ እንዴት ያሉትን ልስማ…? )

“እናቴዋ…ቀልቡን ወሰድ ያደርገዋል አንዳንዴ እንደ አብዱ” አሉ የዜድ እናት (ጎበዝ ኧረ ይሄ አብዱ ማነው…?) ዙቤይዳ ቡፍ ብላ ሳቀች። እናቷም ሰውነታቸው እስኪረግፍ ሳቁ። አባቷግን ኮስተር እንዳሉ ፂማቸውን በመዳፋቸው እየዳሰሱ ዝም ብለው ቆዩ። በዝምታው ውስጥ ድምፃቸው የሚያማምር ሕፃናት ከሩቅ በስርቅርቅ ድምፃቸው ቁርዓን ሲቀሩ ይሰማል። ለምን እንደሆነ ባላውቅም የሕፃናቱ ድምፅ፣ የአባቷ ዝምታ፣ የዙቤይዳ አቀርቅራ በክሪሟ መጫወት ተዳምሮ ዜድን ላጣት ከዜድ ጋር
ልንለያይ ሴኮንዶች የቀሩ መሰለኝ። ምፅአት መሰለኝ። ድንገት ነው በቃ እንደዚህ የተሰማኝ። እንባዬ
ሁሉ ይታገለኝ ጀመረ እልህ ውስጤ ተንተከተከ።

የዜድዬ እናት ድንገት ዝምታውን ሰብረው፣ “ዘምዘም…” ብለው ተጣሩ ።

“አቤትእማማ ! ብላ የዙቤይዳ እህት ከውስጠኛው ክፍል የግቢ በር የሚያክለውን በጌጥ የተሽቆጠቆጠ ባለሁለት ተከፋች የጣውላ በር ከፍታ ገባች። ዘምዘም ቁመቷ የትየለሌ ነው። በዛ ቁመት ላይ ሙልት ያለ ሰውነቷ ተጨምሮበት ክብድ የሚል ነገር አላት። ሳሎኑ ውስጥ መጥታ ስትቆም የሆነ ረዥም ማማ
ነገር የቆመ ነበር የሚመስለው፣ አንጋጥጬ ሽቅብ ተመለከትኳት። ኮስተር አለችብኝ። አሁን የመረረው
ባላጋራ መጣ አልኩ በሆዴ። በተቻለኝ መጠን ዘምዘምን ላለማየት ወደ ዙቤይዳ ዞርኩ፤ ፈገግ አለችልኝ ወደ ዘምዘም በድፍረት ዞርኩ ቡትሌ አክላ ታየችኝ፡፡አስማተኛው የዜድ ፈገግታ እንኳን አንዲት ሴት ኪሊማንጃሮን በፊቴ ጠጠር ያሳክለዋል። ከፍቅር የሚገዝፍ ነገር የለማ !

“ምሳ አልደረሰም እንዴ? እንግዳ ጠርታችሁ በራብ ልትገሉት ነው እንዴ” አሉ እማማ። ዘምዘም
ክፉ ደግ ሳትናገር ወደ ውስጥ ተመልሳ ገባች። እኛም በዝምታችን እንደፀናን በሩ ተበረገደና የምግብ መፈክር ያነገቱ ሰላማዊ ሰልፈኞች ወደ ሳሎኑ ተግተልትለው ገቡ አራት እህትና አንዲት ሠራተኛ።
ዘሐራም ከሰልፈኞቹ አንዷ ነበረች። የያዘችውን ሰሐን በትኩረት ተመለከትኩት። “እሷ ከያዘችው ሰሐን አልበላም” አልኩ ለራሴ። ሠራተኛዋ ምንጣፉ መሐል ላይ አንድ ሰፊ ክብ ላስቲክ አነጠፈች። ከዛ የምግብ ዓይነት በሚያማምር ሰፋፊ የሸክላ ሰሀኖች ተደረደሩ። ላስቲኩ ላይ ዙሪያውን የተደረደሩትን
ነጫጭ ሰሀኖች በክብ ተደርድረው ስመለከት በፀሐይ ዙሪያ ምህዋራቸውን ተከትለው የሚሽከረከሩ ፕላኔቶች ሥዕል ትዝ አለኝ።

ሰልፈኞቹ ወጡና ሌላ ሰሐን ይዘው ተመለሱ(ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ጉድ)። ብስኩቱ፣ ጣፋጩ፣ ስሙን
የማላውቀው ነገር ሁሉ በዓይነት ተደረደረ። አንድ ነገር ውስጤን በሐዘን ሞላው። ዙቤይዳ ሱቅ ፀሐይ ልንሞቅ ስንቀመጥ የምጋብዛትን ቦንቦሊኖ ለመብላት ቁርስ ሳትበላ ትመጣ እንደነበር አስታወስኩ።እውነቴን ነው ይሄን ማዕድ ስለ ፍቅር ረግጣ፣ “አብርሽ ኧረ ርቦኛል ቦንቦሊኖ ግዛልኝ…” ትላለች።ፀሐያችንን እየሞቅን ፊት ለፊታችን ካለች ሻይ ቤት ቦንቦሊኖ አዝዘን እየተጎራረስን በሻይ እንበላለን።እንደውም አንድ ጊዜ አረፋ በዓል ሆኖ የነዙቤይዳ ሱቅ ዝግ ነበር፤ እኔ ተቀጥሬ የምሠራበት ሱቅ ደግሞ
አልተዘጋም፤ ዙቤይዳ ከቤቷ ሹልክ ብላ መጥታ በበዓሉ ቀን እዛች ሻይ ቤት ሄድንና ቦንቦሊኖ በሻይ በላን። ለረመዳን ሙሉ ቀን ዙቤይዳ ስለማትበላ እኔም ሳልበላ የምውልባቸው ቀናት ይበዙ ነበር።

የዙቤይዳ እናት “በልና ወዲህ፣ ዙቤይዳ ነቅነቅ በይ እንጂ መታጠቢያ ቤቱን አሳይው” አሉ። ዙቤይዳ እየመራች በሚያምረው በር አልፋ ወደ መታጠቢያው ወሰደችኝ። አንዳንድ ነገሮች አሉ በአክብሮት ሲደረጉ ስድብ የሚሆኑ። የነዙቤይዳ መታጠቢያ ቤት ስፋት የአባቴን መኝታ ቤት ያክላል። የመታጠቢያ
ሸክላዎቹ ንጣት፣ የቤቱ አስደሳች ጠረን አፍ አውጥቶ የሰደበኝ መሰለኝ፣ “አንተ አመዳም ደሀ ልካችንን እየው…" የሚለኝ መሰለኝ። ዙቤይዳ ፈዝዤ መቆሜን ስታይ “ታጠብ…” አለችኝና ዞር ብላ ወደ ኋላዋ
ተመልክታ ማንም አለመኖሩን ካረጋገጠች በኋላ ጉንጬን ሳመችኝ። ከንፈሯ ይሞቃል። የሆነ ርጥበቱ ጉንጩ ላይ የቀረ መሰለኝ። ስትስመኝ ድንጋጤው ይሁን ንዝረቱ አስበረገገኝ። “ብቻችንን ከሆንን አያስችለኝም ቶሎ ውጣ” አለችኝ እየሳቀች። እና ራሷ እጇን መታጠብ ጀመረች። በመስተዋቱ ውስጥ ዓይኖቿ አፍጥጠውብኝ ነበር። የመታጠቢያ ቤቱ ውበት ውበቷን አጉልቶት ነው መሰል፤ ዙቤይዳ
በጣም አማረችብኝ። ለዚህች ልጅማ አንድ ሰውና አንድ ጥይት እስኪቀር ታጥበን ወጣን።

ወደ ሳሎን ስንመለስ የዙቤይዳ እናት ኖር.. አሉኝ፣ አባቷ ግን አሁንም ፂማቸውን እያሻሹ ዝም
ብለው ተቀምጠዋል። እንደውም ከቅድሙ በላይ ፊታቸው ተቀያይሮ ቁጣ ነበር ከግንባራቸው
የሚስፈነጠረው። ወደ መታጠቢያ ቤቱ እንደገባን የዜድ እናት ጋር የሆነ ነገር እንደተነጋገሩ ገመትኩ።
እንዴት ይጨንቃሉ። ዘሐራ ጭልፉ ይዛ ስትገባ፣ እኛ ታጥበን ስንወጣ አንድ ሆነ። እንደው ይህች ልጅ
ደንቃራ ነገር ናት ልበል። በግርምት እግሬን ተመለከተችኝ። ዓይኗን ተከትዬ ወደ እግሬ ስመለከት ወደ
መታጠቢያ ቤት ስገባ ያደረግኩት የዙቤይዳን ሰንደል ጫማ ነበር። ያውም ብዙ ጊዜ ኡዱ ስታደርግ
የምትጫማውን። እሾህ ! ዓይኗ የማያየው ነገር የለም። እኔ ራሴ ጫማ ላድርግ፣ በእግሬ ልሁን ትዝ
ያለኝ አሁን ነው።

አንዲት ትንሽ ትራስ ነገር ከተሰደረው ምግብ ፊት ዙቤይዳ አመቻቸችልኝና ተቀመጥኩ። አባቷ
ከምግቡ ክምር ወዲያ፣ እኔ ወዲህ። ምግብን ድንበር አድርገን የተፋጠጥን ጠላቶች። (አንቱ ወዲያ ማዶ፣ እኔ ወዲህ ማዶ፣ አንገናኝም ወይ ተራራው ተንዶ..) መብላት አልቻልኩም። አባቷ ዓይኔን ላለማየት ሲሸሹ ምግቡ ዘጋኝ። በቤታቸው ምግብ አቅርበው ፊታቸውን ሲያጠቁሩብኝ ለልመና የመጣሁ እስኪመስለኝ አፈርኩ ተሳቀቅኩ። ዙቤይዳ ገብቷታል። ምንም ነገር ሳትፈራ ሰሀኔ ላይ እንጀራና ንጣቱ
👍19👏2
የሚገርም ነጭ ቂጣ አድርጋ ወጥ ጨለፈችልኝ። ብዙ ዓይነት ቀለም ካላቸው ሩዞች ጨመረችልኝ።
“ብላ አብርሽ…” አለችኝ። የአባቷ ማኩረፍ አስከፍቷታል። ድምፅዋ ውስጥ እልህ አለ። “ወደዳችሁ
አልወደዳችሁ ገደል ግቡ…” ዓይነት ነበር የምታሳየኝ ፊት። ግን ሕመሟ አመመኝ። እንደ ውጭ ሰው ሆኜ ሳስባት ዜድ ያፈቀረችውን ሲገፉባት የሚሰማት ውስጣዊ ስቃይ ተሰማኝ (የራሴን ስቃይ ዋጥ አድርጌያት የዜድን ስቃይ በመንፈሴ ተካፈልኳት ...)።
ከእኔ የበለጠ ማፈሯን የጉንጮቿ ቅላት ይመስክራል። የዜድ እናት በጋሽ ጀማል ኩርፊያ ግራ ተጋብተው አንዴ እኔን፣አንዴ ባላቸውን እየተመለከቱ፣ “ብላ አይዞህ..! ”ይሉኛል። ጭራሽ የዜድ አባት ሁለት ጊዜ
ጎርሰው ሰሀናቸውን አስቀመጡና እጃቸውን ሰብሰብ አድርገው ተቀመጡ። እኔም ከዛ በላይ መብላት አልቻልኩም። እናቷም ብላ ብለው ማስቸገር አልፈለጉም - ገብቷቸዋል። ወጥ የነካ ጣታቸውን አንከርፍፈው ምንጣፍ ምንጣፉን እያዩ ተከዙ።

ጋሽጀማል ከተቀመጡበት ተነሱና ክፉም ደግም ሳይናገሩ ወደ ውጭ ወጡ። ትንሽ ቆይተው ዙቤይዳን ጠሯት። በሕይወቴ ከሰማኋቸው ሰቆቃዎች ሁሉ የከፋው ሰቆቃ ከበረንዳው መጣ።

“አንች ባለጌ አሳዳጊ የበደለሽ፣ እንዴት ወንድ እየጎተትሽ ቤቴ ድረስ…”

“አባባ አንቱ አይደለሁ ጥሪው ያሉኝ ኧረ አላህን ፍሩ”

“ሰው መስሎኝ ነበራ። ደግሞ አብረሽ ማዕድ ላይ ታቀርቢኛለሽ የማንም…” ዝምታ። መኪናቸው
ሲነሳ ሰማሁ። በቃ ሔዱ። “ያውልህ ቤቱ አንተን ከማይ…” ያሉኝ መሰለኝ። የዙቤይዳ እናት እንዲህ አሉ፤ ያፅናኑኝ መስሏቸው፣ “ይሄውልህ ሥራውም ግብሩም እያበሳጫቸው አንዳንዴ እንዲህ ይሆናሉ፤ ላንተም ብቻ አይደለም አየዋ አይዞህ…”። እሳቸውም አንቱ ነው የሚሏቸው ባላቸውን።

እማማን አመስግኜ ወጣሁ። በረንዳ ላይ ዘሐራና እህቶቿ ተቀምጠዋል። የታፈነ ሳቃቸው ፊታቸው ላይ ሊፈነዳ እንዳኮበኮበ ነበረ። የሴት መዓት ጅሪ! ቁመት ብቻ፣ መልክ ብቻ፣ ቅላት ብቻ ፍቅር አይገባቸው፣ ሕይወት አይገባቸው ለነሱ ማንን አገቡ መባል እንጅ ማናቸው መባል እዚህ ግባ የሚባል ጉዳይ አይደለም። ይሄ ነው ክብር። ዙቤይዳ ሊፈነዳ የሚታገላት እንባዋን እየታገለች፣ ፊቷ ላይ ሊገልፁት የማይችሉት ስቃይ እየታየባት እህቶቿን ላለማየት አንገቷን አቀርቅራ ወደ መኪናዋ
መራችኝ። እንዴት በእህትማማቾቹ ፊት ላይ አንድ ጉዳይ እኩል ለሳቅና ለለቅሶ ምክንያት ይሆናል ?

“ዜድ ተመለሽ በእግሬ እሄዳለሁ” አልኳት።

“እሺ አብርሽ” ብላኝ በር ድረስ ሸኘችኝ። እንደ ወትሮው አንድ ላይ ሆነን ሐዘናችንን ከማሸነፍ ይልቅ
ለየብቻችን ሽንፈታችንን ልንቀበለው ፈልገናል። መሀላችን የንቀት ቦንብ አፈንድተው በታተኑን። አይዟችሁ ባይ በሌለበት ! ዜድ ቶሎ መኝታ ቤቷ መግባትና አልቅሳ ሊወጣላት፣ ስቃዩን፣ መዋረዷን በእንባ ልትሸኘው ቸኩላለች። አንድ የሆነ ነገራችንን ሰብረውታል። ተሳክቶላቸዋል።

ከትልቁ ግቢ እንደወጣሁ ከት ብዬ ሳቅኩ። እግዜር ይጠብቀኝ እንጂ እብደት ሳይጀምረኝ አልቀረም።
ካበድኩ አይቀር መንገድ ላይ ከምዋረድ እዛች መከረኛ እናቴ ጋር ሄጄ ልበድ ብዬ እርምጃዬን
አፈጠንኩት። አእምሮዬ ግን በሚያስፈራ ድምፅ ቁጣውን እያስገመገመ ነበር።

አንዳንዴ መገፋታችን ሳይሆን የተገፋንበት ሁኔታና ቦታ ያመናል። እኒህ ሰውዬ ሕዝብ የመሰከረላቸው ደግ ጨዋ ሰው ነበሩ። ደሀውን ሁሉ በሬ ጥለው የሚያበሉ። የተጣላን የሚያስታርቁ። እኔ ... አንድ
እኔ ግን ፍቅርን ተርቤ ቤታቸው ብሄድ ይሄው ገፍተውኛል። ፍቅርን ለመቀበል ደግነት ብቻውን
በቂ አይደለም። የተጣላን ማስታረቅ በፍቅር ከራስ ጋር እንደመታረቅ አይከብድም። በሬ አርደው የከተማውን ሁሉ ደሀ የሚያበሉት እኒህ ሰው፣ የልጃቸውን ፍቅር ለተራበ አንድ ደሀ ፍርዳቸው ተዛብቷል። እኔን ብቻ አይደለም ልጃቸውንም በፍቅር ረሀብ ገድለዋታል። ልቤን ሰብረውታል። እሺ ምን አደረግኳቸው። ለምን ቤታቸው ጠሩኝ። ምኔ ነው “ከሰው ያነሰ…” ሆኖ የታያቸው።

እግዚአብሔርም አብረሃምን እንዲህ አለው !ያንተንዶሮ፣ ያንተን በግ፣ያንተን'በሬ' አልፈልግህም።
ካከበርከኝ ልጅህን ሰዋልኝ። አብርሃምም ልጁን ሊሰዋ በእግዚአብሔር ፊት አጋደመው” ለፍቅር የሚሰዋው ለካ ፍቅር የሚሰማው ሰው ብቻ ነበር። ስለፍቅር ልጁን የሚሰዋ ሲጠፉ ፣ የሰው ልጅ ልብ ይንኮታኮታል። ትዳር .. ትዳር አብሮ መኖር ነው ያለው ማነው? የግራ አጥንትን ነጥሎ ሌላ ጎን ላይ ሊገጥሙ ቢሞክሩ ወይ አጥንቱን መስበር አልያም እድሜ ልኩን እንደተዟዟረ ጫማ የተወናከረ ፣ በኩርፊያ ጉንጩን የነፋትዳር ተብዬ የሁለት ሰው አሰልቺ ስብሰባ መጥራት ነው ትርፉ። የልጆቻቸውን
ፍቅር ቀምተው እየገደሉ “የልጅ ልጅ አየን…” የሚሉ ስግብግብ ራስ ወዳድ አያቶች ስንቱን ትዳር
እንደሻገተ ቲማቲም አቦሽርቀውታል። ያቻትላቸው ልጃቸው ... ስግብግብ ሁሉ !

“ማንም ከተረፈው ብር ይሰጣል ። ብርን ታች ላሉ ሰዎች ለመስጠት ደግነት ብቻ በቂው ነው። ራስን
ዝቅ አድርጎ ከታችኞቹ ጋር መዋል ግን ከባዱን የፍቅር ቀንበር መሸከምን ይጠይቃል። ማነው በፍቅር ለተጠሙ ደራሽ? የማን ሕንፃ፣ የማን ቪላ ነው የጥላቻ ፀሐይ፣ የመገፋት ሐሩር ላደረቀው ሚስኪን የፍቅር ጥላውን የሚጥል?! እኔ ለዙቤይዳ ክፉ ነኝ ? ፈጣሪ ይመለከታል፤ ዙቤይዳን ከቤተሰቦቿ የበለጠ ካልተንከባከብኳት። አንደ ወንድ ይዣት ለመጋደም አልተጣደፍኩም። አዎ ! ዙቤይዳ
ከልክላኝ አልነበረም። ተቃቅፈን ባዶ ቤት ማንም በሌለበት፣ “አብርሽ የፈለከውን ጠይቀኝ” ስትለኝ ሰማይና ምድር ሰምተዋል። ነገዋን እንዳላበላሽ፣ የናቁኝ ቤተሰቦቿን አክብሬ ጫፏን ሳልነካት ከስሜቴ ይልቅ የዙቤይዳ ክብር የገዘፈብኝ አፍቃሪዋ ነበርኩኮ።

በዚያች በተከራየኋት አንዲት ክፍል ቤት ተንበርክኬ እግሯን ሳጥባት ከሷ ምንም ፈልጌ አልነበረም።
ስለማከብራት ስለምወዳት ብቻ! ኤጭ ! ሀብታም ለልጁ ሊያወርስ የሚችለው ነገር የለም ማለት
ነው?! ቢያንስ በዚህ በዚህ ምክንያት ልጃችንን እንድታገባት አንፈልግም ቢሉኝ ምናለበት ? የልጃቸው ልብ እንዳይሰበር የእኔን ልብ እንዲህ ማንኮታኮት ነበር አላማቸው? ቤታቸው ጠርተው ማዋረድ? ከነሚያበሉት በሬ ገደል ይግቡ። ደሞ ከሳቸው ብሎ አንቱ ። “ሰው መስሎኝ ነበር” ይላሉ ሱቃቸው ሄደን ስንገዛቸው ነው ሰው የምንመስላቸው። ቤታቸው ሄደን ፍቅር አካፍሉን ስንል ይነጫነጫሉ !ከዜድ ጋር ከሳምንት በኋላ ተገናኘን። ለመሰነባበት። ዙቤይዳን ላገባትና ቤተሰቦቿን ጉዳያችሁ ልንላቸው እንችል ነበር። ዙቤይዳም አሁን ነይ ብላት ያ ትልቅ አጥር ሳያግዳት ከድምፄ ቀድማ አጠገቤ ነበረች። ግን ምናችንን በምናቸው እንዳከሸፉት እንጂ የዜድን አይን ከዛ በኋላ ማየት እንዳልችል አድርገው አኮላሽተውናል። የሆነ ነገራችን ቀምተውናል፣ ያሉንን እንድናደርግ የፈለጉትን እንድንሆን
በክፋታቸው ማርከውናል። እርስ በራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለየራሳችንም ማሰብ እንዲደክመን አድርገውናል።
ተገናኘን፤ ዜድ አላለቀሰችም። ትክ ብላ ሳታቋርጥ ፌቴን አየችኝ። ፊቷ መቀመጤን በዓይኖቿ ብቻ
ማረጋገጥ ያቃታት ይመስል በእጆቿ ፊቴን ዳሰሰችኝ። እንደ ሐውልት ዝም ብዬ በለስላሳ እጆቿ ተዳሰስኩ።
👍19
ፊቷ እንደ ወረቀት ገርጥቶ ነበር። ቀስ ብላ ስትነሳ መቆም አቅቷት ተንገዳገደች። እጆቿን ይዤ
ደገፍኳት። እስከምትረጋጋዓይኖቿን ጨፍና ቆየች። አሁን ግን አንዲት የእንባ ዘለላ ኮለል ብላ በጉንጫ
ላይ ወረደች። ዝም ተባብለን ቤቷ ድረስ ሸኘኋት። ሰፈራቸው ደርሰን ሁልጊዜ የምንለያይባት ቦታ
ላይ እኔ ስቆም ዜድ አልቆመችም። ዝም ብላ ዞራ ሳታየኝ ወደ ግቢው በር ተጓዘች። የመቃብሩ በር ተከፈተ። መጀመሪያ ግራ እግሯ ፣ከዛ ቀኝ እግሯ ወደግቢው ገባ፣ ቀሚሷ ቀስ እያለ ወደ ውስጥ ገባ
ግቢው ተዘጋ!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሥራ ለቅቄ ክፍለ ሀገር ሄድኩ ሐረር ! እዛም ኑሮ አልተመቸኝም። ሰው ኑሮ የማይመቸው አካባቢው
ስለማይመቸው አይደለም። ውስጡ የማይመቸው ነገር ሲቀመጥ እንጂ ! ዜድስ ብትሆን መች አዲስ አበባ ይመቻታል፤ የእኔ ዜድ፣ የእኔ ሩቅ። በራሴ ላይ የፈረድኩትን አመክሮ የሌለው እስራት፣ የዙቤይዳንም ሕይወት ያለመበጥበጥ መሐላ ላለማፍረስ ሦስት ዓመታት ጥርሴን ነክሼ ቆየሁ። መራር የብቸኝነት ኑሮ። ፍቅሬን ስለተቀማሁ ብቻ አይደለም ፍቅሬን ቀምተው ምርኮኛውን እኔን ለዘመናት
በሚቆጠቁጥ የንቀት በትር አድቅቀውኛል፤ እያገገምኩ ነበር ።
ስልክ የለኝም። ለእናቴ በመስመር ስልክ እደውላለሁ። ለዜድ ላለመደወል ሁሉንም አቅሜን
ተጠቅሜያለሁ። ስንት ቀን ለእናቴ ስደውል ጣቶቼ ከቁጥጥር ውጭ እየሆኑ ለዜድ ሊደውሉ ቃጣቸው፣
ስንት ቀን በባዶ ሜዳ ድምጿን የሰማሁ እየመሰለኝ ወደ ኋላዬ ዞርኩ?! ድምጿን ከሰማሁ በቀጣዩ ቀን አዲስ አበባ ነኝና ራሴን በእሳት አለንጋ እየገረፍኩ የነፍሴ ጀርባ በናፍቆት እየተተለተለ እንደምንምዐሦስት ዓመት ቆየሁ !! ሶስት አመት ሞትኩ። ካልሞቱ ትንሳኤ የለም ብዬ።
የእናቴ ለቅሶ አሳቅቆኝ ከሦስት ዓመት በኋላ አዲስ አበባ ተመለስኩ። የአዲስ አበባ መንገዶች ላይ መቆም
በባዶ እግሬ የጋለ ምጣድ ላይ ከመቆም በላይ እንደሚያንገበግበኝ ማን አወቀልኝ? የተገፋሁባት ከተማ፤
አላፊ አግዳሚው ሁሉ እንደውዳቂ የሚመለከተኝ ውዳቂ የመሆን ስሜት እንደደበተኝ ለማን ልተንፍስ ? ከተማዋ እንደሰው ጀርባዋን የሰጠችኝ እንደመሰለኝ ማን ይሄን ግፍ ይመለከታል ?

ዙቤይዳ ማግባቷንና አሁንም እዛው ሱቅ እንደምትሠራ፤ መንታ ልጆች ወልዳ አንድኛው ልጅ
እንደሞተባት ሰማሁ። ባለቤቷ ሀብታም ነው አሉ፤ ብዙውን ጊዜ ውጭ ስለሚኖር ዙቤይዳ ቤተሰቦቿ ጋር ነው የምትኖረው። እንደው ዝም ብዬ ሳስብ ቤተሰቦቿ ደስ እንዲላቸው ያገባች ግን ደግሞ ባሏ አጠገቧ እንዳይኖር ሆነ ብላ ይህን ሰው ያገባችው መሰለኝ። ደግሞም ሌላኛው ሐሳቤ ቅሬታ ዘራብኝ፣
እኔ ነኝ የምሰቃየው፣ ዙቤይዳ ከባሏ ጋር በፍቅር ከንፋ ረስታኝ ዓለሟን ስትቀጭ ነው የኖረችው” የሚል ቁስሌ ላይ በርበሬ እንደመነስነስ ያለ ሐሳብ…!

አዲስ አበባ መጥቼ ምን እንደምሰራ ምን እንደማደርግ ግራ ተጋብቼ ቆየሁ። የአዲስ አበባ አየር አፈነኝ። መንገዱ ሁሉ የትዝታ አሜኬላ የተዘራበት ክፉ መሬት መሰለኝ። በተቻለኝ ሁሉ ዘቤዳ ጋር
ላለመገናኘት አብረን የረገጥነውን መንገድ ላለመርገጥ ስጠነቀቅ ኖሬ አንድ ቀን አረፋ በዓል ሆኖ ሕዝበ ሙስሊሙ አምሮና ተውቦ ወደ ሶላት ሲተም አንድ ነገር ውስጤን ገፋፍቶት በንፋስ እንደሚገፉ ፌስታል
እየተወዘወዝኩ መንገድ ገባሁ። ሰው አእምሮውን ማዘዝ የሚችልበት፣ መቆጣጠር የሚችልበት ልክ አለ፤ አሁን የዙቤይዳ ናፍቆት ግድቡን ጣሰ። ላያት ፈለግኩ፣ ዓይኔ ፈለጋት። አይኔ ራባት፣ እግሬ ወደ
ቄራ ተጓዘ…

እኔና ዜድ ውብ የፍቅር ጊዜያት ያሳለፍንበት ሰፈር፣ የዙቤይዳ መኪና ብቅ ስትል ልቤ በደስታ
የሚፍለቀለቅበት ሰፈር … ኡፍፍፍገና ጠዋት ነበር …መንገዱን ተሻግሮ እኔና ዜድ ቦንቦሊኖ የምንበላባት ሻይ ቤት እንዳለች አለች። ገና በጧቱ ተከፍታ ደንበኞቿን እያስተናገደች ነበር። አዳዲስ አስተናጋጆች
ወዲያ ወዲህ እየተሯሯጡ ደንበኞቻቸውን ያስተናግዳሉ። መንገዱን ተሻግሮ የዜድ ሱቅ ተዘግቶ ይታየኛል። ቀጥ ብዬ ወደ ሻይ ቤቷ ገባሁና እንደ ፅጌሬዳ አበባ ሽታ የሻይ ቤቷን መዓዛ በአፍንጫዬ ስስበው ዜድን ያገኘኋት ያህል ውስጤ በአንዳች እርካታ ተሞላ።

“ምን ልታዘዝ?” አለችኝ አስተናጋጁ።

“ቦንቦሊኖ በሻይ” አልኳት ክፍሏን በዓይኔ እየተመለከትኩ። ሕይወት ግን ምን ዓይነት ጨምላቃ ነገር
ናት ? ቦንቦሊኖው በባለ ወንፊት ሰሀን ቀረበልኝ። በፍቅር ገመጥኩት። ለምን እንደሆነ ባይገባኝም አቅለሸለሸኝ። ምንም ሰላም አልሰማ አለኝ። ተረበሽኩ። ዝም ብዬ ተቀመጥኩ። አንድ በእጁ ሰርቪስ ትሪ የያዘ አስተናጋጅ ከውጭ እየተጣደፈ ገባና ጮክ ብሎ እንዲህ አለ፣ “አንድ ቦንቦሊኖ ሽሻይ ዙቤይዳ ሱቅ” አስተናጋጇ በግርምት እንዲህ አለችው፣ “ዛሬ አረፋ አይደል እንዴ ዙቤይዳ እንዴት ገባች ?”

“እንጃ ! ምን የሷ ነገር ነካ ያደርጋታል” አለ አስተናጋጁ። ዙቤይዳን እኮ ነው አይገርምም ? ..ነካ
ያደርጋታል ? መግቢያዬ ጠፋኝ። ተጨነቅኩ። እንደውም እጄ ሲንቀጠቀጥ ተሰማኝ። ራሴን ስቼ
የምወድቅ መሰለኝ፡፡ ሒሳቤን ከፍዬ ቀስ ብዬ ወጣሁ። እንደ ምንም ዓይኔን ወደ ዙቤይዳ ሱቅ ላክኩት ዙቤይዳ ! የኔ ዜድ ... ጀርባዋን ለመንገዱ ሰጥታ ፀሐይ የምንሞቅበት ቦታ ላይ ተቀምጣለች - እኔ እሠራበት የነበረው ሱቅ በር ላይ። ፀሐይ የለም ! ክረምት ስለሆነ ደመና አንዣብቦ ነበር። የዜድ ሱቅ
በደንብ አልተከፈተም፣ ከሁለቱ ተካፋች በሮች አንዱ ብቻ ነበር ገርበብ ያለው። ቀስ ብዬ ሽቅብ ወደ ሜክሲኮ በእግሬ መንገዴን ተያያዝኩት። አንዳንች ነገር ወደዜድ እየጎተተኝ ነፍሴ እንደድር ከከበባት ስበት እየታገለች …የህልም ሩጫ በሚመስል እግር መጎተት… ሽቅብ ወደላይ መንገዴን ቀጠልኩ።
እኔና ዙቤይዳ ስክር እብድ የሚያደርግ ፍቅር ውስጥ የወደቅነው ድንገት ነበር። ዛሬም የዙቤይዳን ስም ሳነሳ ሰውነቴ በሆነ ኃይል ይሞላል…ደስታ በመላው አካላቴ እንደ ዥረት ሲፈስ ይሰማኛል ማን ያምነኛል ብናገረው ? ከተለያየን ከሦስት ዓመት በኋላ እንኳን ጠረኗ አጠገቤ ያለች ያህል ይሸተኛል።
ድምጽዋ ይሰማኛል፣ የልብሷ ቱማታ ሳይቀር ይሰማኛል። ነፍሰ ጡሮች አማረን እንደሚሉት ዙቤይዳ ክፉኛ ታምረኛለች፣ ድምጿ ያምረኛል፣ ዓይኖቿ ያምሩኛል። እኔስ የማይወለድ ፍቅር ያውም የጨነገፈ
ግን ከውስጥ የማይወጣ ፅንስ ፀንሼ የለ ከነፍሰ ጡር ምኑን ተሻልኩት። ድፍን አገሩ በአንድም
በሌላም ብሶት ያረገዘው ብዙ ብሶት ውል የሚልበትም እልፍ አምሮት አለው!! ማን ማንን ያፅናናል? አምሮታችን እንዳማረን ወደ መቃብራችን እግራችንን እንጎትታለን።

ድንገት ገነት ሆቴል ስደርስ ወደ አፍሪካ ኅብረት ታጠፍኩ። ፀጥ ባለው መንገድ ግራና ቀኝ በተሰለፉት የዘንባባ ዛፎች መሐል እየተጓዝኩ ረዥሙ የአፍሪካ ሕብረት ሕንፃ ከፊቴ ተጋረጠ። አፍሪካዊ ነኝ፣ እኔ አፍሪካ ነኝ፤ በአረንጓዴ ምድር የፍቅር ችግር አድርቆኝ ውስጤ ምድረ በዳ የሆነ የአፍሪካ ልጅ ነኝ፤አፍሪካ፣ አፍሪካ፣ አፍሪካ “ስደት” የሚል ቃል አእምሮዬ ውስጥ ፈነዳ !! አዲስ አበባ የእኔ አይደለችም።

አለቀ
👍2711🔥1
አትሮኖስ pinned «#አንዲት_መርፌ_ስንቱን_ቀዳዳ_ትስፋው ፡ ፡ #ሶስት(መጨረሻ) ፡ ፡ #በአሌክስ_አብርሃም እኔ ይሄን ስድብ በፀጋ ተቀብዬ እግር ማየቴን መቼም አላቆምም። የሴት ልጅ እግር የውበት ጥጌ ነው። ለሰርጌ ቀን አይበለውና እግሯ የሚያምር ግን አንገቷ የተቆረጠ ሴት ጎኔ አምጥተው ሚስትህ ናት ቢሉኝ፣ “በደስታ ይሁን በሐዘን…” ብዬ ከመፈረም አልመለስም። እንዲህ የምንሰፈሰፍለት፣የምማልልለት፣ የምልከሰከስለት፣…»
#በሕይወት_አንድ_ጥግ


#በአሌክስ_አብርሃም


ትላንትና እሑድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውዬ መጣና በሩን አንኳኳ። እኔ፣ ሮዛና የሮዛ እናት ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር። ሮዛ አብሮ አደግ ጎረቤቴ ናት። አስቴር ደግሞ እናቷ። ለእኔም እናቴ ማለት ነች
ኧረ። የእኔና የሮዛ ፍቅር ለብቻው ነው። ከሕፃንነታችን ጀምሮ ንጹህ የሆነ፣ ምንም ፆታዊ ክጃሎት ውል
ያላለበት ፍቅር እንዳለን አገር መንደሩ ምስክር ነው። እህቴ ሮዚ ነው የምላት ። ታዲያ ዩኒቨርስቲ ቆይታ ለእረፍት መምጣቷ ነበር። የሚገረመው እናቴና የሮዛ እናት አስቴር የመረረ ጥል ያላቸው ኩርፈኞች ናቸው። ግን እኔም የእነሮዛ ቤት፣ ሮዛም የእኛ ቤት ልጆች ነን። ስለእናቴ አስቴር ፊት ከተነሳ፣ “ውይ! ውይ! የሷን ነገር አታንሳብኝ፤ ጋኔል…! ምን ያረጋል እንዳንተ ዓይነት መልአክ ወለደች፤” ትለኛለች።
እናቴን ለእኔ ታማልኛለች። “ቱ…! ሰው አይደለችምኮ!” ትላታለች ደጋግማ። በእናቴ የመጣብኝን ሰው ይቅር ብዬ አላውቅም። አስቱ ግን ስትረግማት እንኳን ምርቃት የሚመስለኝ ለምን እንደሆነ እንጃ።

ሮዛ እኛ ቤት ስትመጣ ደግሞ እናቴ በተራዋ ለሮዛ ስለእናቷ ክፋት፣ ጋኔልነት ትነግራታለች። “እናትሽ ምን እናት ናት! እች እቴ… የሰይጣን ቁራጭ! ከጥላዋ የተጣላች! ..እኔ ለሷ እንዲህ አልነበርኩም….”እያለችም ። እኔና ሮዚ እናቶቻችንን ረስተን እብድ ያለ ጓደኝነታችንን ቀጥለን አለን። የሮዚ አባት በሕይወት የሉም። ችግር የለም አባባን እንካፈላለን” ትላለች አንዳንድ ቀን ስንቃለድ። አባባ የምትለው የእኔን አባት ነው። እናቶቻችን አባባን እንዳይካፈሉ ብቻ” እላታለሁ ለሮዚ፤ “ባለጌ.! ስድ!” ብላ ትግል ትጀምረኛለች። ቀይ ፊቷ በሐፍረት ይቀላል።

ሮዛ ቆንጆ ናት፤ ግን ምኗ ነው ቆንጆ ቢባል አላውቅም። እንዲሁ ጠቅለል አድርገው ሲመለከቷት
በጣም ቆንጆ፣ የምታሳሳ፣ ኑሮ ምችት ያላት ልጅ ነች። አንዳንዴ ሰውን ስንወድ ፍቅራችን የወደድነው ሰው ላይ ጎዶሎውን ሞልቶ ያሳየናል መሰል ሮዛ ለእኔ ጉድለት የላትም። አዎ ፍቅር በራሱ ሰልካካ አፍንጫ፣ ሃር ፀጉር፣ አሎሎ ዓይን፣ መቃቁመት፣ በረዶ ጥርስ፣ …ከንፈር ሳይሆን አይቀርም። ለነገሩ ሮዚን የሚጠይቃት ጎረምሳ ብዛትም ለሳቢነቷ ተጨማሪ ምስክር ነው።

ሮዛን የጠየቁትን ጎረምሶች እኔና ሮዚ የዕለት ውሎ መመዝገቢያችን ላይ እንመዘግብ ነበር። የሚገርመው ዳይሪያችን አንድ ነበረች፣ ሁለታችንም ውሏችንን የምንመዘግብባት። ለሮዛ የሚላክ የፍቅር ደብዳቤን አብረን ነው የምናነበው። እኔም ለሴት የምልከውን አብረን ጽፈን እናውቃለን። ታዲያ ሮዛ ብትሞት
ለፍቅር አትሸነፍም፤ ትምሕርቷ ላይ አትደራደርም፤ ልቧ የገባም ወንድ የለም። “ወንዶች ጅል
ይመስሉኛል…” ትላለች በተደጋጋሚ።

አባቷ እናቷ ላይ ያደረሰው በደል ሁሉ (ነፍሱን ይማረውና) መጥፎ ጠባሳ ጥሎባታል። አባቷ ሲበዛ
መልከመልካም ሽቅርቅር ሰው ነበር። በዛ ላይ አይጠጣ፣ አያጨስ በጊዜ ነው ቤቱ የሚገባው ፤ በጊዜ ገብቶ ታዲያ ዋና ስራው እናቷን አስቴርን መደብደብ ነበር። እነሮዚ ቤት አባቷ ካመሸ ደስታ ነበር
።እንዴ!የአስቴርን ጥርሷን ሁሉ አውልቆት ወርቅ ጥርስ አስተክሎላታል። ሮዛ ልብ ውስጥ የነበረውን ወንድን የመሻት ተፈጥሯዊ ስሜት ግን ነቅሎ ባዶውን ትቶታል። (አሁንም ነፍሱን ይማረውና፤ የሚምረው እንኳን አይመስለኝም...)

እና…ትላንትና እሑድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውዬ መጣና በሩን አንኳኳ። ቡና ተፈልቶ ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር። እንዳጋጣሚ ለበሩ የምቀርበው እኔ ስለነበርኩ ተነስቼ በሩን ከፈትኩ። ከተወለደ
ጀምሮ ዛሬ ገና የዘነጠ የሚመስል፣ ሙሉ ግራጫ ልብስ የለበሰ፣ ቀጫጫና ረዥም ሰውዬ በሩ ላይ እየተሽቆጠቆጠ ቆሟል። ሰውዬው ሙሉ ልብስ ቢለብስም ለምን እንደሆነ እንጃ ሙሉ ልብስ የለበሰ አይመስልም። መቼም ሕይወት በሰዎች ዓይን ፊት ስታጎልህ እንኳን ሙሉ ልብስ፣ ሙሉ ብርጌድ አሰልፈህ ብትመጣ ግርማ ሞገስ የሚባል ነገር አይጠጋህም። ቅልል ትላለህ። “ቀትረ ቀላል” ትሆናለህ።

ሰላም አልኩት። እየተሽቆጠቆጠና ዳማከሴ እንደሚያሽ ሰው እጆቹን እርስ በእርስ እያፋተገ ሰላምታዬን
ከወገቡ ጎብጦ መለሰልኝ። ከርዝመቱ እና ከእንቅስቃሴው ፍጥነት የተነሳ ለሰላምታ ከወገቡ ሲታጠፍ ከላይ ተምዘግዝጎ የመጣ የሆነ ወገቡ ላይ ተሰብሮ የሚወድቅ ባሕር ዛፍ ነበር የሚመስለው።

“ይ…ሄ የነሮዛ ቤት ነው አይደል…?” አለና፣ ራሱ መልሱን መለሰው። “አዎ ነው አውቀዋለሁ።” አነጋገሩ
የሚርበተበትና ከአፉ የሚወጡት ቃላት በጠባብ በር እንደሚወጣ ብዙ ሕዝብ የሚገፋፉና የሚተሻሹ
ይመስላሉ፤ ዝም ብዬ ስመለከተው።

እ… የሮዛ እናት ይኖራሉ ወይም አባቷ?” አለና መልሶ ለራሱ፣ “አውቃለሁ አባቷ እንኳን በሕይወት የሉም…ግን እናቷ” ተርበተበተ።

"እናቷ አለች” አልኩት።

ልግባ ?” ሲል ገነት በር ላይ የቆምኩ መልአክ የሆንኩ እስኪመስለኝ ወደ ቤቱ ውስጥ በጉጉት ዓይኖቹን ልኮ ለማየት እየሞከረ ለመነኝ።

“ግባ…” ብዬ በሩን ለቀቅኩለት፤ ገባ። አረማመዱ የሆነ የሚጮኽ ዓይነት ነው። የሚራመድ ሳይሆን
በአንድ እግሩ ብቻ የሚዘል ዓይነት ላይ ታች ያረገርጋል። እድሜው ሠላሳ አምስት ቢሆን ነው። የሮዛን
እናት በሁለት እጁ ሰላም ብሎ ወደ ሮዛ ዞረ። ርሷንም በሁለት እጁ ሰላም አላት። ሲመለስ የእኔን እግር ረገጠና ተንገዳግዶ ጠረጴዛው ጫፍ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ባዶ ሲኒ ከነበለው። ሲኒው ስር ቀርቶ የነበረው የረጋ የቡና ዝቃጭ ምንጣፉ ላይ ጥቁር ደም መስሎ ተረጨ። ይሄ ሰው መርዶ ይዞ ነው እንዴ የመጣው? ምን ያደናብረዋል…?

ከአስቱ ፊት ለፊት ተቀመጠ። ሁላችንም ምን እንደሚል ለመስማት ዓይን ዓይኑን እናየው ጀመር።

እ ….ሰላም ነዎት ታዲያ እትዬ ..አስቴር?” አለ።

እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ።” ፊቷ ላይ የት ይሆን የሚያውቀኝ የሚል ግርታ ይታያል።በፈገግታ ልትሸፍነው ብትሞክርም አልተሳካላትም።

“ልጆች ሰላም ናቸው ? ማለቴ ልጅዎት? አዎ አንድ ልጅ ብቻ ነች ያለችዎ አለ ወደ ሮዛ አየት
አድርጎ መልሶ እየተሸቆጠቆጠ ወደሚያፍተለትለው መዳፉ አቀረቀረ። ላቡ ቅንድቡ ላይ ችፍፍ ብሎ በግልፅ ይታያል ሲጨንቅ። ደግሞ ያጠናውን ነበር የሚናገረው፤ ያስታውቃል። ላቡን በመዳፉ አንዴ ሞዥቀውና መዳፉን አየት አድርጎ በኮቱ እጅጌ እንደገና ግንባሩን ጠረገው።

“ደህና ናት” አለች አስቱ፤ እናም ኮስተር ብላ አየችኝ። ትከሻዬን በቀስታ ወደ ላይ ሰበቅኩት። ያየችኝ ማነው…?” ማለቷ ሲሆን እኔም በትከሻዬ ምላስ እኔ 'ጃ” አልኳት። ለትንሽ ደቂቃ እንግዳውም አቀርቅሮ፣ እኛም እንግዳው ላይ አፍጥጠን እንደቆየን እንግዳው ተናገረ።

አንተ አብርሃም ነህ … እዚህ ጎረቤት ያለኸው ልጅ አይደለህም እንዴ…?” አለኝ።

“…አዎ”

“ያው ለሮዛ ወንድሟ ማለት ነህ ..፤ ማዘርም ጋር ትቀራረባለህ ያው ልጃቸው ማለት እኮ ነህ…።

“አዎ ያው ልጅ ማለት ነው!” አለችው አስቱ።

“ጥሩ!ያው የቤተሰብ ጉዳይ ስለምናወራ ላረጋግጥ ብዬ ነው።” አለ ወደ አስቱ በፈገግታ እየተመለከተ።ፈገግታው ይጨንቃል። ከንፈሮቹ ወይ በደንብ አይከፈቱ፣ ወይ አይገጠሙ፣ እንዲሁ ሄድ መለስ እያሉ
ይንቀጠቀጣሉ። በማጭድ የተጋጠ የሚመስል ፂሙ ቅሪቱን አጥንታም ጉንጩ ላይ ዘርቶት በሽተኛ አስመስሎታል። ጥላሸት የተዘራበት አጥንታም ጉንጭ !ደግሞ እኮ ሲያደርጉ አይቶ ኦ' ቅርፅ!! አፉ በፂሙ ተከብቦ ሲታይ በኮሸሽላ ዙሪያውን የታጠረ የደረቀ የውኃ ጉድጓድ ይመስላል። ወቸ ጉድ! ምን ሊል ይሆን…? ጭንቀት ገደለኝ።
👍22
“የመጣሁት ሌላ የሚመጣልኝ ሰው ስለሌለ ነው። ላቀው እባላለሁ…” አለና ድንገት ቆሞ አስቱን እጇን ጨበጣት። እኔንና ሮዛን ግን ረሳን። “…እ…ያው የመጣሁት መጥቼ መናገር ስላለብኝ እና …” ስልኩ ጮኸች።ልክ እንደ አይጥ ነበር ፂው ፂው እያለች የጮኸችው…። ገና ሳያወጣት ስልኳን “ቀድረ
ቀላል” መሆኗን አውቄያታለሁ። እጁን እስከከንዱ ሱሪው ኪስ ውስጥ ከተተና ዙሪያዋን በፕላስተር መቀነት የተተበተበች ቀይ ስልክ አወጣ (ይሄው እንዳልኳት ናት፤ ካልኳትም ትብሳለች)። ስልኳን ከኪሱ ሲያወጣት ጩኸቷ ተቋረጠ። የሆነ ነገሯ ኪሱ ውስጥ ስለቀረ እንደገና ኪሱን ፈትሾ ክዳኗንና ባትሪዋን አወጣ። ተበታትና ነበር የወጣችው። በጥንቃቄ ገጣጠመና ኮቱ ኪስ ውስጥ አስቀምጦ ወሬውን ቀጠለ።

“…እና የመጣሁት መጥቼ እርስዎን ለማግኘት ነበር። ያው አግኝቼዎታለሁ” ብሎ ፈገግ አለ። አስቱን እንዳገኛት ለራሱ አላመነም መሰል።

“አዎ አግኝተኸኛል፣ ከየት ነው ግን የመጣኸው? እንደው ዘነጋሁህ መሰል፣ አላወቅኩህም።” አለች
በጨዋነት።

“አይ አልዘነጉኝም ...። ድሮም አያውቁኝምኮ” አለ።

“ኧረ… እንደዛ ነው? ..እምምም ታዲያ እኔን እንዴት አወቅከኝ?”

አላወቅኮትም… ያው ልተዋወቅዎት ነው የመጣሁት።”
እልሄን ነበር ያስጨረሰኝ፣ “…ኤጭጭ ወደዚያ! ማን እንደሆንክ ተናገር” ማለት አምሮኝ ነበር። እግዜር ይይለት መንዛዛቱን ቀጠለው።

“ሰው እኮ ደፍሮ ካልተዋወቀ መቼስ…”

“ልክ ነው” አለች አስቱ እንዲናገር ለማደፋፈር እንጂ ያላለቀ ዓረፍተ ነገር መቼም ቢሆን ልክ ሆኖ
አያውቅም።

“የመጣሁት … ለዚህ ነው እኔም”

“ለምን?” አለች አስቱ ገርሟት።

“ያው ለመተዋወቅና ከተዋወቅን በኋላ አንዳንድ ቤተሰባዊ ጉዳዮችን ለመነጋገር።”

“ይሄው ተዋወቅን !እስቲ የመጣህበትን ንገረኝ” አስቱ ትንሽ ኮስተር ያለች መሰለኝ።

“የመጣሁት ያው ሮዛን ... ማለቴ ልጅዎትን ሮዛን ላገባት ስለፈለግኩ እርስዎ እንዲፈቅዱልኝ ነው…እባክዎትን እማማ አስቴር…” ብሎ ተንደርድሮ አስቱ እግር ስር ተደፋ። ቀስ ብዬ ወደ ሮዛ ዞርኩ። ሶፋ ላይ ሳይሆን ኤሌክትሪክ ወንበር ላይ እንዳስቀመጡት የሞት ፍርደኛ ደርቃ ቀርታለች። ሙልት ያሉ
ቀይ ጉንጮቿ ገረጥተው ዓይኗ ባዶ ጠርሙስ መስሏል።

“ኧረ ተነስ! ተነስ የኔ ልጅ! ” አለች አስቱ ምኑም ምኑም እንዳልጣማት ታስታውቃለች። ልጁ ተነስቶ ቆመና፣ እሺ አሉኝ ማዘር…?” ሲል በጉጉት ጠየቀ።

አክብረኸኝ ስለመጣህ ተባረክ! ግን አሁን ዘመኑ ሰልጥኗል… ማነህ...”

“ላቀው!” አለ።

“ራሳችሁ ተነጋገሩ እዛው” ብላ ሮዚን አጋፈጠቻት።

ሮዚ በርግጋ ተነሳች፤ ከዛም “ምናይነቱ ነው!” ብላ ወደ ጓዳ ገባች።

አስቱ ግራ ተጋብታ እንዲህ አለችው፣ “እንደው ወጉም ባሕሉም እንዲህ አልነበረም። ቢጠፋ ቢጠፋ ያንተ ቢጤ እንኳን አንድ ሁለት ሰው ይላካል። ሰተት ተብሎ ነውር እኮ ነው…እ.።”

አስቤ ነበር…” አለ አንገቱን ደፍቶ፣ “ግን ሰው አጣሁ። ዘመድም የለኝም፤ እና ደግሞ የምነግራቸው
ሰዎች ሁሉ ለራስህ ሳትሆን ሚስት…፣ ጠግበህ ሳትበላ ሌላ እዳ መጨመር' እያሉ አሸማቀቁኝ::አስቤ ነበር፤ ሰው የለኝም። እንጅማ አስቤ ነበር ... ሮዛን ስለወደድኳት ነው፤ እንደው እሺ ቢሉኝም ቀጥሎ ምን አባቴ አደርግ እንደነበር እንጃ። ራሴ እሷን በማሰብ ከሚፈነዳ እንዲህ ነገሩን አፈንድቼው ይለይለት ብዬ ነው። ሮዛን እወዳታለሁ። ሮዛ ቀይ ቆንጆ ልጅ ናት፤ ሰው ለራሱ ሽማግሌ ቢሆን አልኩ…፤ ትክክለኛው ሽማግሌ እኔ ነኝ። የሮዛን ፍቅር ምን ያህል እንዳለምኩት የሚያውቅ ሽማግሌ
ማን አለ? በማድርባት የፈራረሰች ቤት ብርሃን የዘራችው ማናት? ሮዛ ናት…፤ ሮዛ የእርስዎ ልጅ።
ማንም እንደ ሰው በማያየኝ አገር፣ እንደ ጥራጊ በተጣልኩበት መንደር ሰው መሆኔን ለልቤ የነገረው የሮዛ ፍቅር ነው…፤ ሮዛ የእርስዎ ልጅ….” ወደ በሩ መንገድ ጀመረ። አነጋገሩ ተረጋግቶ ነበር - ፍርሐቱ ሁሉ ጠፍቶ።

“…መቼስ የፈጣሪ ትልቅነት፣ ይሄን ፍቅር ሰው እንኳን ቀና ብዬ የማላይ ትንሽ ሰው ላይ ጥሎት ሰው ፊት አቆመኝ። እንደው ሰው ልሁን ብዬ እንጂ እሱስ እሺ ቢሉኝም ሮዛን የት እንደምወስዳት እንጃ…።ሮዛ እኮ…! አራት ዓመት ከልጅነቷ ጀምሮ፣ አስራ ሁለተኛ ክፍል እስክትሆን፣ ዩኒቨርስቲ እስክትገባ ስወዳት፣ ስወዳት፣ ስወዳት፣ ከረምኩ። አልተማርኩም፣ እንደው የእግዜር ነገር እኔ ላይ ይሄን ፍቅር ቢጥለው እኔው ሽማግሌ ሆንኩ። ሆድህን ሳትሞላ ይላሉ ፍቅር ከሆድ በተረፈ ነገር ይመጣ ይመስል
..ይሄው ሆድህ አልሞላም ብሎ መቼ ተወኝ ። ለራስህ ሳትሆን ይላሉ ምንድነው እኔ እኔ ማለት…? ለራስ ከሆኑ በኋላ በተረፈውይፈቀራል እንዴ…? ራስን ጥሎ እንጂ ለሌላውመኖር…! ሮዛን…! የእርስዎን ልጅ ወድጄ ስንት ዓመት ሙሉ…! ዘመድ የለኝም…! ሮዛን እያሰብኩ ሺ እልፍ ሆኜ ኖርኩ…። ማንም አይደለሁም ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ይባል እንጂ ቅሉ፣ ስለራሴ አብዝቼም አሳንሼም የምቆርሰው
የሌለኝ፣ ኑሮ ቆራርሶ እዚህ ያደረሰኝ ከንቱ ነኝ። ሮዛ የአንቱ ልጅ ግን በሕይወቴ ውስጥ ትልቋ ቁራሽ፣ ትልቅ ድርሻዬ ነበረች ! ሮዛ የአንቱ ልጅ…

“ሳያት እኮልቤ ውስጥ ገነት ይፈጠራል። ፍቅሯ እንደ እግዜር የገነቱ አስተዳዳሪ… መንገዱ ምንድነው የሚነጠፍበት…? ሮዛ ስታልፍ ቢጫ ይሆናል፤ ሮዛ ስትስቅ በደስታ አለቅሳለሁ…፤ እጆቿ እንደሩቅ አገር ህልም ናቸው፤ እግሮቿ፤ “ደህና ዋልሽ?” አልኳት አንድ ቀን፤ … አየት አድርጋኝ በዝምታ አለፈች….
አየችኝ ... ዓይኖቿ አዩኝ ... ቢያንስ የምታይ ሰው ነኝ፤ በክፉም ይሁን በደግ መታየት መኖርን ነው
የሚገልፀው። ሮዛ አየችኝ። ዓይኖቿ ካለመኖር ፈውሰውኝ ይሄው አለሁ…” አለና በሐሴት ፈገግ አለ።ከንፈሮቹ አልተንቀጠቀጡም በነፃነት ፈገገ!!
ከተቀመጠበት ተነሳና ከቤት ወጣ። ሲወጣ የበሩ ጉበን አናቱን ገጨው። ደህና ዋሉም አላለ።ተከትዬው ወጣሁና በሩ ላይ ቆሜ በግርምት አየሁት። የማይሰማ ነገር እያነበነበ፣ በጣም የሰፋው ሱሪው፣ እጅግ
በጣም የሰፋው ኮቱ እየተርገበገቡ፣እየተውለበለቡ ሆድ የባሰው አገር ባንዲራ መስለው፣ ወደ ታች ወረደ፤ እየተጣደፈ። ከሩቅ ሳየው አሳዘነኝ። ከዛ በኋላ እስከ ማታ እኔም፣ ሮዛም፣ አስቱም ስለዚህ
ጉዳይ አንዲትም ነገር ትንፍሽ አላልንም። በየፊናችን እያሰብነው እንደነበር ግን አያጠያይቅም።

ማታ ወደ ቤቴ ስሄድ ሮዚ ሸኘችኝ። እንደሁል ጊዜው እኛ ግቢ በር ላይ ቆመን ከላይ ጨረቃ ከታች
የነፍሳት ሲርሲርታ እና የንፋሱ ፉጨት ባየለበት ጨለማ ውስጥ ሮዛ ለስለስ ባለ ድምፅ እንዲህ አለችኝ፣ አብርሽ የቅድሙ ሰውዬ አሳዘነኝ፤ ሙሉ ቀን ሌላ ነገር ማሰብ አልቻልኩም…”

"እኔስ ብትይ!”

“ግን እዚህ ሰፈር አይተኸው ታውቃለህ እንዴ?”

"እኔጃ አላስታወስኩትም”

ዝምምምምምምምምምምምም ዛፎች ይንኮሻኮሻሉ፣ ነፍሳት ሲር ሲር ፂው ፂው ይላሉ፤ ጨረቃ እንደ ትልቅ የቅቤ እንክብክብ ወዛም ብርሃኗ በእኛ ላይ እየቀለጠ ፍስስስ ይላል፤ የጨለማ ድርቀቱን እያረሰረሰ…

“ቁመቱ ደግሞ ሲያምር!” አለች ሮዛ ልስልስ ባለ እንደ ጨረቃ በሚቀልጥ ድምፅ። ለመጀመሪያ ጊዜ ወንድ ስታደንቅ ሰማሁ።

አለቀ
👍273👏1
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_አምስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

ባህራም
ሞት

ያን ሰሞን ጀምሺድ ታሞ ተኛ፡፡ ልጠይቀው ወደ ቤቱ ሄድኩ።
ሌሎቹ በሚጠይቁት ሰአት ብሄድ ምንም አልጠቅመውም በማለት፣
በትምህርት ሰአት ሄድኩ። ፎቁን ወጥቼ በሩን ብሞክረው ተቆልፏል። ደወሉን ተጫንኩት፣ ውስጥ ሲደውል ተሰማኝ፡፡ ቆየሁ
የጀምሺድ ቤት ሳይሆን፣ በግራ በኩል ያለው የጎረቤቱ በር
ተከፈተ። መነፅር ያደረገ መላጣ ሽማግሌ ሀኪም አንገቱን ብቅ ከርጎ አየኝ፡፡ አየሁት። ከበሩ ወጣ፡፡ ነጭ የሀኪም ኮቱ በጣም ንፁህ ነው፡፡በእጁ መርፌ ይዟል። ጀምሺድ የነገረኝን ታሪክ አስታወስኩ ሀኪሙ ዙሪያውን ተገላመጠና ሲያበቃ፣ ማንም እንደሌለ ካረጋገጠ በኋላ፣ በሹክሹክታ

«ይምጡ ልውጋዎት» አለኝ
ዝም ብዬ አየሁት
ካልፈለጉ ላስገድድዎት አልችልም፡፡ ነፃነትሳ? ዳሩ፤ ለኔ ያው ነው፡፡ ደሞ ደንታ የለኝም እንጂ» እያለ ለራሱ እያጉረመረመ ወደ ጀምሺድ ተኝቷል መሰለኝ ብዬ ደረጃውን መውረድ ስጀምር
በሩ ተከፈተ። ዘወር ስል ኒኮል ነች
“ይቅርታህን። አስጠበቅኩህ? ሽንት ቤት ነበርኩ» አለችኝ::
አመዳም ፀጉሯ ተሞነጫጭሯል። ሸሚዟ በአንድ በኩል ከጉርዷ
ወጥቷል። ገባኝ፡፡ ጀምሺድ አልጋው ውስጥ ትራስ ተደግፎ
እንደተቀመጠ፣ እየሳቀ
ዶክተር ሽቫይትዘር መርፌ ይውጉህ?» አለኝ፡፡ የሱም ፀጉር
ተሞነጫጭሯል ግምባሩ ላይ ወድቋል፡፡ ግን ፈፅሞ የታመመ
አይመስልም።
ኒኮልና ጀምሺድ እየተሻሙ ስለዶክተሩ ነገሩኝ። ሰውን
የማይጎዳ ሰላማዊ እብድ ነው፡፡ የመጣውን ሁሉ መርፌ ልውጋዎት? እያለ ይጠይቃል፣ አሉኝ። አነጋገራቸው አንድ ነገር ለመደበቅ የፈለገ ሰው አነጋገር ይመስላል

ትንሽ ቆይታ ኒኮል ከፍል አለብኝ ብላ ሄደች፡፡ ጀምሺድ
ስለጎረቤቱ ዶክተር ኮሚክ ወሬ እያወራ ሲያስቀኝ ቆየና ተነስቶ ወደ ሽንት ቤት ገባ
በፍጥነት በፀጥታ ተነስቼ የራስጌውን ፍራሽ አነሳሁ፡፡ አልጋው ሽቦ ላይ አንድ ጥቁር የሴት ሙታንቲ፡፡ ሙታንቲው ኣጠገብ አንድ አምስት የተጨማደደ ለስላሳ ክሊኔክስ ወረቀት ወረቀቶቹ ፅጌረዳ አይነት ስለሆኑ ርጥበታቸው ለአይን ያስታውቃል። ጎምበስ
ብዬ ወረቀቶቹን አሸተትኩ፡፡ የግብረ ስጋ ሽታ። ያለጥርጥር፡፡
ተመልሼ ወምበሬ ላይ ከተቀመጥኩ በኋላ፣ ተነስቼ የሰው ጉድ ሳሽት ታየኝና፣ ለራሴ ሸርሎክ ሆምዝ!» ብዬ በሀይል መሳቅ
ጀመርኩ ጀምሺድ ከሽንት ቤቱ «ለምን መሳቅ?» አለኝ
«መርፌ መውጋት» አልኩትና ሳቄን ቀጠልኩ
ሉልሰገድ ስለኒኮል ባይነግረኝ ኖሮ፣ ኒኮልንና ጀምሺድን እጠረጥር ነበር? አይመስለኝም
በጀምስድ አገር ደምብ የሚያፈላው ሻይ በጣም ይጣፍጣል።
እሱን እየጠጣን ወሬ ጀመርን
ጀምሺድ እንደሚለው ከሆነ፣ በቁማር መክበር አይቻልም።
በቁማር የሚከብር ቁማር ቤቱ ብቻ ነው፡፡ ምንም ያህል ብትበላ
ያችን የበላ ሀትን ተመልሰህ እስክታስበላ ያቁነጠንጥሀል። በቁማር ለመክሰር እንጂ ለመክበር አይቻልም። እንዲህ ከሆነ ጀምሺድ ለምን
ቁማር ይጫወታል? ... ሰካራሙ ለምን ይጠጣል?ለጀምሺድ እንደሚታየው፣ ኑሮ ጨቅጫቃ ሚስት ናት፡ ና ምግብ ብላ፣ ና ተኛ፣ ና ሽንት ቤት ሂድ፣ ና ትምህርት ተማር፣ ና ይህን አድርግ፣ ና ያንን ፈፅም፣ እያለች መነዝነዝ ነው ስራዋ፡፡ ታድያ የሰው ልጅ ከዚህ ሁሉ ጭቅጭቅ ለመሸሽ አንዳንድ ጊዜ ቢሰክር ይፈረድበታል?

ጀምሺድ ዮኑሮን ችኮነት ሊረሳ የሚችለው ቁማር ቤት የሄደ
እንደሆነ ነው። ቁማር ቤት ውስጥ ያለችው ኑሮ፣ ነዝናዛ ችኮ ሚስት
ሳትሆን፣ የማትጠገብ፣ ለዛዋ ሁልጊዜ የሚታደስ ውሽማ ናት። ኮት የምታስሽጥ ውብ ውሽማ!

«እኔ ቁማር ስጫወት መኖሬን እረሳለሁ፡፡ መኖሬን ሲረሳ፣ ያን
ጊዜ ኑሮን ኖርኳት ነኝ ማለት ነው:: ሌላ ጊዜ ኑሮን ሲኖራት፣ እኔን
እያታለልኩ ነው ችኮ ናት ደስታ የለም፡፡ ቁማር ጊዜ ግን፣ ቁማር
ፈፅሞ ሲውጠኝ ሳለ። ኑሮ መሀል ውስጥ እገባ፣ ከንቱ አይደለች፣
እላያትም እኖራታለሁ ማለት»

ጀምሺድ ስለቁማር ሲያወራ አይኖቹ አይስቁም

እንስሳ ኑሮ አይሰለቸውም (ይሄ የጀምሺድ አስተሳሰብ ነው)
ምክንያቱም እንሰሳ ይኖራል እንጂ መኖሩን አያውቅም። ስለዚህ ኑሮ
አይመረውምም አይሰለቸውምም። ስለዚህ ነው እንሰሳ ራሱን የማይገለው። «በሬ ወይም አህያ ወይም አይጥ ወይም ውሻ ወይም ሌላ፣ ራሱ ገደለ እሱ ሰምተሀቸዋል ታውቃለህ?» ሰውን ከእንሰሳ
የሚለየው ማሰቡ አይደለም፡፡ በመጠኑ ይሁን እንጂ እንሰሳም
ያስባል። ሰው ከእንሰሳ የሚለየው በመሳቁ አይደለም። ዝንጀሮም
ይስቃል። ሰው ከእንሰሳ የሚለየው፣ ህይወቱን እየኖራት እንደሚኖራት በማወቁ፣ ከህይወት በኋላ ሞት መከተሉን በማወቁ፤ እነዚህም እውቀቶች ለሰው ልጅ ኑሮን ከንቱ፣ ሞትን መራራ በማድረጋቸው በዚህ ነው ሰው ከእንሰሳ የሚለየው

በመሰረቱ ህይወት ግሩም ስጦታ ናት። ኑሮ ግን ይሰለቻል።
ሀዘን ሞልቶበታል፡፡ ብስጭት ይበዛበታል፡፡ በሽታ ወሮታል። ሞት
ደሞ ይቆያል እንጂ አይቀርም። ስለዚህ መሞት ላይቀር፣
ብስጭት ሊበዛ፣ ለምን አሁኑኑ
አንሞትም? ለምን ራሳችንን አንገድልም? ችኮ የሆነ ሀዘን፣ ብስጭት የወረሰው እውቀት ምኑ ይወደዳል? ራሳችንን የማንገድለው ሞትን
ስለምንፈራ ብቻ ነው። ፈሪ ነን በቃ፡፡ ይኸው ነው ስለዚህ፤ ልናደንቀው የሚገባ ሰው ማን ነው? ራሱን ለመግደል የደፈረ ሰው ነው፡፡ እሱ ብቻ ነው። እኛሳ ዋናው አላማችን ምን መሆን አለበት? ይህን የመሰልቸት ቀሚስ አውልቀን ወዲያ መጣል
በተቻለ ፍጥነት ራሳችንን መግደል
«እኔ ራሴ ለመግደል ዋና ምኞት፡፡ ግን እስካሁን ድፍረት የለም፡፡ አንድ ቀን ግን ለመድፈር ተስፋ! ያን ጊዜ እኔ ሰው::እውነተኛ ሰው፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን ከንቱ ቁማርተኛ።»

ጀምሺድ ራስን ስለመግደል ሲያወራ አይኖቹ አይስቁም

በልግ ከዛፎቹ ላይ ቡናማ፣ ቀይና ወርቃማ ቀለማቱን ሰብስቦ
የሙቀትና የውበት ጓዙን ጠቅሎ ኤክስን ለቆ ሊሄድ ተነሳ የኤክስ አየር መብረድ ጀመረ። ሽማግሌዎቹ፣ አሮጊቶቹና
ጥቁሮቹ፣ ሹራብ መደረብ ካፖርት መልበስ ጀመርን። ወጣቶቹ
ፈረንጆች ግን ገና ብርዱ ሊሰማቸው አልጀመረም
ሉልሰገድን ኒኮል እምቢ ስትለው እኔጋ መጥቶ «ካፌ ኒኮል»
ይወስደኝና፣ እየቀረበን በመጣው የክረምት ብርድ ምክንያት፣ ቤት
ውስጥ ገብተን ቁጭ ብለን ስለኒኮል ያወራልኛል። የጭገሯ ፀጉር እንደራሷ ፀጉር አመዳም ሳይሆን፣ ንፁህ ወርቅ ቀለም የተቀባ ነው፤ወተት የመሰለው ነጭ ቆዳዋ ላይ ረዣዥም የተጠላለፈ ውብ ወርቃማ ሀረግ መስሎ በቅሏል። ታዲያ እምሷ ዳር የበቀሉት ፀጉሮች፣ ውሀ ዳር እንደበቀለ ቄጠማ ናቸው፤ አንዳንዶቹ ከሁለቱ ከናፍር ተንጠራርተው ተጠላልፈው፣ ጎምበስ ብለው እምሷ ውስጥ
የፍቅር ውሀ ይጠጣሉ. .. ወዘተርፈ

አንድ ቀን ግን፡ ስለሷ ያወራልኛል ብዬ ስጠብቅ ስለጀምሺድ
ሊነግረኝ ጀመረ፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ሆነዋል። ጀምሺድ ቁማር
ለመጫወት ካዚኖ ሲሄድ ሉልሰገድን ይዞት ይሄዳል። ከዚህም በላይ ሉልሰገድ የጀምሺድ ሻይ ሱስ ይዞታል። ሁለቱም ሻይውን የሚጠ
ጡት በኢራን አገር ወግ ነው። በፊት ከአራት ማእዘኑ ስኳር ላይ
ይገምጡና፣ ቀጥሎ ሻይ ፉት ይሉበታል፣ እንጂ ስኳሩን ሻይው
ውስጥ አይጨምሩትም
👍232
ትላንት ማታ ጀምሺድ ሻይ ላጠጣህ ብሎ ወሰደኝ» አለ
ሉልሰገድ። (ይህ የሚሆነው ጀምሺድ ድኖ ከተነሳ በኋላ ነው።)
ጀምሺድ በተገማመደ ፈረንሳይኛው ኮሚክ ወሬ እያወራ
ሻይውን ጨርሰው ሲያበቁ
«አንድ ነገር ሊያሳይህ?» አለው
«አሳየኝ» ሲለው፣ ከጠረጴዛው ኪስ ውስጥ ሽጉጥ አወጣ፡፡
ጥይቶችም አወጣና አጎረሰ። አንድ ቃል ሳይናገር ሽጉጡን አቀባበለ
«አሁን መተኮስ ብቻ፡፡ አንዲት ጣት። እንደዚህ» አለና ሽጉጡን
ሉልሰገድ ደረት ላይ አነጣጠረው
ሉልሰገድ ለመሳቅ እየሞከረ፣ ግን ላቡ ግምባሩ ላይ ብቅ ብቅ
እያለ ተው እንጂ። ይባርቃል» አለ፡፡ ድምፁ የሌላ ሰው ሆኖ
ተሰማው ጀምሺድ ሽጉጡን እንዳነጣጠረ
«አይባርቅ። እኔ የፈለግኩ ይባርቅ፡፡ እኔ ሳልፈለግኩ አይባርቅ» አለ። ፊቱ ላይ ዝምተኛ አይነት ቁጣ ሰፍሯል፤ አይኖቹ ውስጥ ምህረት የማያውቅ ጭካኔ አድፍጧል
ሉልሰገድ በድንጋጤና በፍርሀት ውሀ ሆኗል፡፡ ላቡ ከግምባሩ
ወደ ጐን ይወርዳል። መሀረቡን አወጣና ግምባሩን ጠረገ። እጁንም ጠረገ፡፡ አጁ ይንቀጠቀጣል። ጀምሺድ አሁን ቢተኩስስ?
ጀምሺድ ሽጉጡን ወደ ሉልሰገድ ግምባር አነጣጠረ
«አሁን እተኩስ፣ ጥይት አይኖችህ መሀል» አለ
“ምን አረግኩህ?»
«ምንም»
«እንግዲያው ሽጉጡን ወደዚያ በለዋ»
«ቆይ አንድ ነገር ሊነግርህ»
“እሱን ወደዚያ በለውና ትነግረኛለህ»
«የለም፡፡ እኔ ሲነግርህ፤ ሽጉጥ አይኖችህ መህል። ያን ጊዜ ጥሩ
ሉልሰገድ እንደገና ግምባሩን እያደረቀ እሺ ንገረኝ» አለ
“ኒኮል። ተው። በቃህ ኒኮል ቤት መሄድ የለም፡፡ ኒኮል
ስትሄድ በትልልቅ አይን ማየት የኒኮል ቂጥ በአይን መብዳት
የለም፡፡ አለዚያ ጥይት! በአይንህ መሀል! እሺ?»
«አሁን ተነሳ፡፡ ሂድ፡፡ ደህና እደር፡፡
ደህና እደር» ብሎ ሉልሰገድ ተነስቶ ወጣ። ባቡር መንገድ
ሲደርስ አስታወከው:: ብርድ ብርድ አለው
ቤቴ ሄዶ ገላውን ታጥቦ ጥርሱን ቦርሾ ወደ ከተማ ተመለሰና
አንድ ቢራ ጠጣ፡፡ ይህን ጊዜ ስድስት ሰአት ይሆናል
«አሁን የምነግርህ በሙሉ የሆነ ነገር ነው» አለኝ ሉልሰገድ ግን
እኔ ራሴ በፈቃዴ የሰራሁት አይደለም። የማደርገውን ሁሉ፥
ከማድረጌ በፊት አንድ ደቂቃ አስቀድመህ አሁን ምን ልታደርግ
ነው? ብትለኝ እንጃ ነበር የምልህ፡፡ ምክንያቱም፣ አላውቀውም
ነበር። እኔ አይደለሁማ ያደረግኩት! ውስጤ አንድ ባእድ መንፈስ ወይም አጋንንት ገብቶ ነው የሰራው፣ ሳላውቀው ይታወቀኛል የሆነ ሆኖ ምን ሰራህ?» አልኩት።

ቢራዬን ከጠጣሁ በኋላ ሰአቴን አየሁ። ስድስት ከሃያ። በቀጥታ
ኒኮል ቤት ሄድኩና አንኳኳሁ፡፡ ክፈች፣ የምነግርሽ አለኝ» አልኳት፡፡
ከፈተች። ገባሁና ወደ አንድ በኩል ገፍቻት በሩን ቆለፍኩት።
ረዥም ስስ የሌሊት ቀሚሷን ለብሳ፣ ላይዋ ላይ ከፎጣ የተሰራ የቤት ውስጥ ካፖርት ደርባለች
«ሂጂ ውሀ አምጪልኝ ጠምቶኛል» አልኳት። ስታመነታ
ገፈተርኳት። ቃል ሳትናገር ወደ ወጥ ቤቷ ሄደች፡፡ ወደ መኝታ
ገባሁና በፍጥነት ልብሴን ማውለቅ ጀመርኩ፡፡ ለምን? ብለህ ብትጠይቀኝ በጭራሽ አላውቀውም፡፡ ጋኔን ሰፍሮብኛል ብዬሀለሁ። ውሀውን ይዛ እንግዳ ቤት ስትገባ አጣችኝ፣ የት ነህ?» አለች
«ነይ ወዲህ አልኳት። ገባች፡፡ በሩ አጠገብ እንደቆመች
ቀረች። ወለሉ መሀል እጆቼን ወገቤ ላይ አድርጌ ቆሚያለሁ፣
ራቁቴን ነኝ ቁላዬ ግትር ብሎ ቆሞ፣ ትር! ትር ትር! አያለ
ዳንኪራ ይረግጣል። አስታውስ፣ ይህን የምሰራው አሁን የማወራልህ ሉልሰገድ እንዳልመስልህ። ሌላ ሰው ነኝ
«አውልቂ!» አልኳት፡፡ አቤት ድምፄ ውስጥ ያለው ትእዛዝ!
ምርጫ አልነበራትም፡፡ የውሀውን ብርጭቆ ኮሞዲኖው ላይ አስቀመጠችና፣ የፎጣ ካፖርቷንና የሌሊት ቀሚሷን አውልቃ እዚያው ወለሉ ላይ ጣለችው:: ዝም ብዬ ሳፈጥባት ጡት መያዣዋንና ሙታንቲዋን አወለቀች
«ነይ ወዲህ!» አልኳት፡፡ መጣች። ፊቴ ተምበረከከች።
አቀፈችኝ። ከዚያ በኋላ ያለውን እንዳልነግርህ : እንግዲህ መናገር የሚገባ አይመስለኝም፡፡ አየህ፣ ራቁታም ባለጌ ከመሆኗ የተነሳ ቅዱስ ምስጢር ይሆናል። እና ብናገረው ቃላቱ ያረክሱታል፡፡ ብቻ፣
ከተፈጠርኩ እንደ ትላንት ያለች ሌሊት አሳልፌ አላውቅም። እኔ
እምለው፣ እንደ ኒኮል ያለች ሴት እየበዱ ሁለት አመት ኖረው
ቢሞቱ ምን አለበት?

ጧት ወደ አምስት ሰአት ላይ ነቃሁ። ኒኮል ተኝታለች፡፡
እንዳልቀሰቅሳት ቀስ ብዬ ልብሴን ለብሼ ወጣሁ አሁንም የትላንት ሊሊቱ መንፈስ እየነዳ ጀምሺድ ቤት ወሰደኝ ገባሁና ጀምሺድን «ሻይ አፍላልኝ» አልኩት። ለምን
እንደመጣሁ ግራ ገብቶታል። ሻይውን ከጠጣን በኋላ ተነሳሁና
ቆምኩ። አይን አይኑን እያየሁ
«ትላንት ማታ የሽጉጥህን ቀዳዳ አይቼ ቆመብኝ አልኩት
እየሳቀ እና?» አለኝ
“እና እምስ አስፈለገኝ። እና ሄጀ ኒኮልን በዳኋት» ሳቁ ጠፋ፡፡ አይኖቹ ውስጥ የትላንቱ ጭካኔ ብቅ አለ። ተነሳ።
አቤት አይኖቹ ሲያስፈሩ እዚህ ጀርባዬ ውስጥ ብርድ ተሰማኝ፡፡
ተነሳና እጁን ትከሻዬ ላይ እያሳረፈ በጨካኝ አይኖቹ እያየኝ
«ጎበዝ ነህ፡፡ በጣም ጎበዝ፡፡ አንድ ቀን እገድልሀለሁ፡፡ ሂድ»
አለኝ። ትቼው ሄድኩ፡፡ አይኖቹን ሳስታውስ አሁንም ጀርባዬን
ይበርደኛል (አለኝ ሉልሰገድ ከዚህ ከሽጉጥ ፍጥጫ በኋላ ጀምሺድና ሉልሰገድ ብዙ ጊዜ፤ብዙ ቦታ አብረው ይታዩ ጀመር፡፡ ማታ ሁለቱ በጀምሺድ መኪና ይሄዱና፣ ኒስ፣ ካን ወይም ሞንቴካርሎ ቁማር ሲጫወቱ ሰንብተው ሰኞ ጧት ይመለሳሉ። ከውጭ ለሚያየው ሰው ጓደኝነታቸው እየጠበቀ ሄዴ


💫ይቀጥላል💫
👍241
#ድንቡጮ_ለምን_ለምን_ሞተ?


#አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

ሰፈራችን ውስጥ መክብብ ግሮሰሪ የምትባል አለች። ማታ ማታ ፀሐይ ሲያዘቀዝቅ ትልልቅ ሰዎች በረንዳዋ ላይ ተሰባስበው እያወሩ ጅን የሚባል መጠጥ ድርፍጭ ባሉ ብርጭቆዎች የሚጠጡባት።በግሮሰሪዋ ሁሉም ዓይነት መጠጥ ቢኖርም በረንዳ ላይ የሚቀመጡት ሽማግሌና ጎልማሶች ግን ልክ ዕድሜ ይቀጥል ይመስል ጅን ብቻ ነበር የሚጠጡት። በሯ ላይ በግራ በኩል እንደ ኤሊ ፍርግርግ
ድንጋይ የለበሰ የሚመስል ግንድ ያለው የዘንባባ ዛፍ የግሮሰሪዋ ግርማ ሞገስ ነው። ይህች የዘንባባ ዛፍ ለጥምቀት ሰፈራችንን አቋርጠዉ የሚያልፉት ሁለት ታቦታት ከመለያየታቸው በፊት የሚቆሙባት የታቦት መቆሚያ ነበረች። ባለቤቱ አባባ መክብብ ይባላሉ።አጭር፣ ሙሉ ፀጉራቸውን ነጭ ሽበት
የወረሰው፣ ከባድ ሌንስ ያለው መነፅር የሚያደርጉ ሰውዬ ናቸው።

አባባ መክብብን ባየኋቸው ቁጥር የሚገርሙኝ ሁለት ነገሮች አሉ። የመጀመሪያው ግርምቴ አፋቸው
ውስጥ ምግብ ኖረም አልኖረም በባዶው ያላምጣሉ። አፋቸው አያርፍም፤ ዝም ብሎ ያላምጣል። በፊት በፊት ማስቲካ የሚያላምጡ ይመስለኝ ነበር። ታዲያ ትልልቅ ሰዎች ማስቲካ ብዙም ስለማያላምጡ አባባ መክብብ ዘመናዊ ሽማግሌ ይመስሉኝ ነበር። በኋላ ከፍ ስል ግን እንደው ልማድ ኾኖባቸው ነው…. ሲባል ሰማሁ። ሲያወሩ ሁሉ በየመሀሉ ባዶ አፋቸውን እንደሚያላምጥ ሰው እያንቀሳቀሱ አየር ያኝካሉ። ሁልጊዜ ሙልጭ ተደርጋ የምትላጭ ትንሽ አገጫቸው ላይና ታች ከፍ ዝቅ ስትል ነው
የምትውለው። ታዲያ አንዳንዴ ሊልኩኝ ፈልገው ወይም ለሆነ ጉዳይ በባዶው በሚያኝኩት አፋቸው “አብራም” ሲሉኝ ስሜን አላምጠው የተፉት ይመስለኛል። በዛ እድሜዬ የሚመስለኝ ነገር ይበዛ ነበር።

ሁለተኛው ከአባባ መክብብ የሚገርመኝ ሱሪያቸው ነው። ሱሪያቸው ከታች እስከላይ ይገርመኛል።ከግርጌው እንደዣንጥላ ጨርቅ ወደ አንድ በኩል ተጠምዝዞ ይጠቀለልና ካልሲያቸው ውስጥ ይጠቀጠቃል። በእርግጥ የእኔም አባት እንደዛ ያደርጋል። ግን አባባ እንደዛ የሚያደርገው ዝናብ ጥሎ
መሬቱ ሲጨቀይ ብቻ ነው። አባባ መክብብ ግን ሁልጊዜም ነው የሚያጭቁት። ከላይ ደግሞ ጥቁር የቆዳ ቀበቷቸው ወገባቸው ላይ ሳይሆን ከእንብርታቸው ከፍ ብሎ ከልባቸው ሥር ... እዛ ላይ ነው ቅብትር ተደርጎ የሚታሰረው። ከነተረቱ ሰፈራችን ውስጥ የሆነ ሰው ሱሪውን ከፍ አድርጎ ከታጠቀ
“ምነው እንደአባባ መክብብ ሱሪህን ደረትህ ላይ ሰቀልከው ?” ይባላል።

ሌላም የረሳሁት ሦስተኛ አስገራሚ ነገር አለ። አባባ መክብብ ደንበኞቻቸውን እያስተናገዱ (ሁሉም ደንበኞቻቸው በርሳቸው ዕድሜ ስለሆኑ ከደንበኛ ይልቅ ጓደኞቻቸው ይመስሉኛል) ከመኪና ላይ ቢራ እያስወረዱ ወይም ግሮሰሪው በር ላይ በጉርድ የብረት በርሚል የተሞላ ፉርሽካ ተዘርግፎላቸው የሚበሉትን ሦስት ሙክት በጎቻቸውን እየተመለከቱ የሚሠሯት አንዲት ነገር አለች፤ ከእጃቸው በማትለየውና የቀንድ እጀታ ባላት የጢም መላጫቸው በደረቁ ጉንጫቸውን፣ አገጫቸውንና የአገጫቸውን ሥር ይፈገፍጋሉ ሁልጊዜ። እንደውም ሰው ሰላም ሲሉ የጢም መላጫቸውን በቀኝ እጃቸው ስለሚይዙ ለመጨበጥ አይመቻቸውም። እናም እንደጨበጧት አይበሉባቸውን
አዙረው ሰላም ወደሚሉት ሰው እጅ ይዘረጉና ነካ አድርገውት እጃቸውን ይመልሳሉ። ታዲያ የጢም መላጫቸውን የበረንዳዋ መከለያ ብረት ላይ ኳ ኳ አድርገው ያራግፏታል ! ድምፁ እስካሁን ጆሮዬ ላይ አለ።

አባባ መክብብ በመንደሩ ሰው በሙሉ “ደግ ሰው ናቸው…” ነው የሚባሉት። ግሮሰሪው በር ላይ
ለበጎቻቸው ፉርሽካ ከሚቀመጥበት ጎራዳ በርሚል ራቅ ብሎ ሰማያዊ የፕላስቲክ በርሚል በውኃ ተሞልቶ ይቀመጣል። በርሚሉ ጋር በረዶ በመሰለች የኤሌክትሪክ ገመድ ጫፏ ተበስቶ የታሰረ ቢጫ
የቲማቲም ሥዕል ያለባት የመርቲ ጣሳ አለች ... በርሚሉና ጣሳው ከድሮ ጀምሮ ስለማይነጣጠሉ
በኤሌክትሪክ ገመድ እትብት የተያያዙ እናትና ልጅ ይመስሉ ነበር። እንግዲህ አላፊ አግዳሚ የኔ ቢጤ ውኃ ከጠማው ከዛ በርሚል በጣሳዋ እየጠለቀ ይጠጣል። ትንሽ ልጆች እንደነበርን ውኃው የተለየ
ነገር ስለሚመስለን እኛም እየተደበቅን እንጠጣ ነበር። በኋላ ግን ወላጆቻችን “ማንም በሚጠጣበት እየጠጡ ኮሌራ ሊያመጡብን…” እያሉ ሲቆጡን አቆምን !

ምንጊዜም የቡሄ በዓል ሲሆን የሰፈር ልጆች ተሰባስበን አንደኛ የምንሄደው አባባ መክብብ ግሮሰሪ ነበር። ፈንታው ድንቡጮ የሚባል ጓደኛችን አውራጅ ይሆናል። አባባ መክብብ ፈንታውን በጣም ነው የሚወዱት። ጉንጩ ድንቡጭ ያለ ስለሆነ ነው መሰል 'ድንቡጮ' እያሉ ነው የሚጠሩት። በዚሁ ሰበብ ጓደኛችን ፈንታው ፈንታው ድንቡጮ ተብሎ ቀረ። ግሮሰሪዋ በር የዘንባባውን ግንድ ተገን አድርጎ
የተቀመጠ ትልቅ ድንጋይ ላይ ካርቶን ጣል አድርጎ እንደ ወንበር በመጠቀም ሊስትሮ ይሠራል።
ጫማውን የሚያስጠርገው ደንበኛ ድንጋዩ ላይ ተቀምጦ የዘንባባውን ግንድ ደገፍ ይልና ከድንጋዩ ሥር
ብሩሹን ይዞ ለሚጠብቀው ፈንታው እግሩን ያቀብለዋል። ታዲያ ያች ድንጋይ የፈንታው ድንቡጮ ድንጋይ' ነው የምትባለው። የእኛ ሰፈር አክሱም ናት. የእኛ ሰፈር ላሊበላ ናት... የእኛ ሰፈር ውቅር የሊስትሮ ወንበር ናት ... የእኛ ሰፈር አፈ ታሪክም ናት!

“በድሮ ጊዜ እግዜር ለቅዱስ ድንቡጮ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፣ 'ልጄ ድንቡጮ ሆይ፣ ምድር የእግሬ መርገጫ መሆኑን ሰምተሃል.. እንግዲህ እግሬ ምድር ላይ ሲያርፍ የወርቅ ጫማዬን ትቦርሽ ዘንድ የእግሬን ማረፊያ ድንጋይ በዚህ አስቀምጥ .. የሚል ራዕይ ተገልጦለት ከእንጦጦ ድረስ ይቺን ድንጋይ በኤኔትሬ መኪና አስጭኖ ወደዚህ ሰፈር አመጣት .…”

ታዲያ የሰፈሩ ልጆች ለቡሄ አባባ መክብብ ግሮሰሪ በር ላይ እንሄድና ጭፈራውን እናወርደዋለን።እሳቸውም በጢም መላጫቸው ግራ ቀኝ ጉንጫቸውን በደረቁ እየፈገፈጉና ብረቱ ላይ
ኳኳ አድርገው እያራገፉ ግጥማችንን በጥሞና ያዳምጣሉ፤

“እዛ ማዶ…
ሆ!
አንድ ሞተር
ሆ!
እዚህ ማዶ!
ሆ!
አንድ ሞተር!
ሆ!
የኔ አባባ መከብብ!
ሆ!
ባለ ዲሞፍተር!
"ሂዱ ወዲያ ! የምን ዲሞፍተር ነው …” ይሉና ይቆጣሉ። ረስተነው ነው እንጂ አባባ መክብብ የጦር
መሣሪያ አይወዱም። እንደውም መሣሪያ ታጥቆ ወደ ግሮሰሪያቸው የሚሄድ ደንበኛ ያስወጣሉ
እየተባለ ይወራ ነበር። ታዲያ ይችን አመላቸውን ስለምናውቅ በቁጣቸው አንደነግጥም። ፈንታው ድንቡጮ ወዲያው ግጥሙን ይቀይረዋል … እሳቸውም ወዳቋረጡት ጢም መላጨታቸው ተመልሰው
አንጋጥጠው የአገጫቸውን ሥር እየፈገፈጉ ዓይኖቻቸውን ጨረር እንዳይወጋቸው ጨፍነው
ይሰሙናል ...

“እዛ ማዶ!አንድ አፍንጮ፣
የኔ አባባ መክብብ ባለ ወፍጮ…!
እዛ ማዶ!አንድ በሬ፣
የኔ አባባ መክብብ ጀግና ገበሬ..”

ሃሃሃሃ እንደሱ ነው የሚባለው እደጉ! እደጉ! ድንቡጮ! ... ና ወዲህ …” ይሉና የጢም
መላጫቸውን ወደ ግራ እጃቸው አዘዋውረው በቀኝ እጃቸው አጭሯን የሥራ ገዋን ወደ ቀኝ ገልበው ሱሪያቸው ኪስ ውስጥ እጃቸውን ካስገቡ በኋላ በጣም ብዙ ተዘበራርቆ የተቀመጠ ብር (ድፍን የመቶና የሃምሳ ብር ኖቶች የሚበዙበት) ዘግነው ያወጣሉ። ከዝግኑ መሃል መርጠው ድፍን አምስት ብር ከለዩ
በኋላ (ይሄ ድርጊታቸው ቀልባችንን ስለሚወስደው ጭፈራችን ቀዝቀዝ ይላል…) ሌላውን ብር ወደ ኪሳቸው መልሰው ሲያበቁ ብሩ ላይ ትፍ ትፍ ብለው ድንቡጮ ግንባር ላይ ይለጥፉታል (እንደውም
ግንባሩ ለሽልማት ይመቻል) ..እኛም ሞቅ ይለናል ፤ ጭፈራውን በአዲስ ጉልበት ምርቃቱንም ለየት ባለ ፍቅር እናዥጎደጉደዋለን።
👍25🔥31
“የመክብብን ቤት!
ድገምና !!
ዓመት
ድገምነ !!
ወርቅ ይፍሰስበት!!
ድገመና !!
ዓመት .….!” አባባ መክብብ ደስ በሚል ፈገግታ በተዋበ ፊት እያዩን ይቆዩና…፣

“ወይ እነዚህ ልጆች ምርቃቱን ከየት ከየት ነው የሚያመጡት? እትየ ንግሥትን ሄዳችሁ እንኳን
አደረሰሽ' በሏት እንዳትረሱ……” ይሉናል። እትየ ንግሥትኮ ሚስታቸው ናቸው። አይገርምም?
ሲጠሯቸው እትየ ንግሥት እያሉ ነው። የእትየ ንግሥት ስም ሲነሳ ምን የመሰለ ሲነኩት ትሙክ ትሙክ የሚል ነጭ የድፎ ቁራሽ ትዝ ይለናል። የአባባ መክብብ መኖርያ ቤት ከግሮሰሪው ብዙ አይርቅም።በአስቻለው ወፍጮ ቤትጋ ወደ ግራ እጥፍ ሲባል ያለው ትልቁ ግቢ ቤት ነው።
ስንደርስ ልክ እንደራሳችን ቤት የግቢውን በር አልፈን እንገባለን። ለማዳው ውሻቸው 'አሲምባ' እንደ
እንቦሳ በዙሪያችን እየፈነጠዘ ይቀበለናል። የውሻው ስም አሲምባ ነው። ይሄ ውሻ በሁሉም የመንደሩ ነዋሪ እንደ አንድ የመንደሩ ነዋሪ ነው የሚታየው። ሥጋ ተቀቅሎ ጨው ካልተነሰነሰበት እና ሁልጊዜ
በአጃክስ ታጥቦ የሚቀመጥ ወጨት ላይ ቀርቦ ካልተሰጠው ንክች አያደርግም። እንደውም አንድ ቀን እማማ ንግሥት እኛ ቤት መጡና እናቴን እንዲህ አሏት….

“የጊወርጊስ ጠበል አለሽ እንዴ? እስቲ በእቋ ቆንጥረሽ ስጭኝ”

“ምነው ማን ታመመ እማማ ንግሥት…?” አለቻቸው ጠበሉን መቀነሻ እቃ እየፈለገች።

“ኧረ አልተሞሞም… አንድ ዉሻ ዘው ቡሎ ጎትቶ የአሲምባን ዎጩት ለከፈበት” እናቴ በሳቅ ወደቀች።እንግዲህ አንድ የመንደሩ ውሻ የእማማ ንግሥትን ውሻ እቃ “ስለለከፈው” ፀበል ረጭተው ሊቀድሱለት ነበር። እዚህ ድረስ የሚታሰብለት ውሻ ነበር።

በዛ ላይ ግዝፈቱ እና ቀይ ቆዳው ላይ አልፎ አልፎ ጣል ጣል ያደረገበት ነጭ ቡራቡሬ ቀለሙ ልዩ ውበት ያላብሰዋል።

በረንዳው ላይ የተነጠፈውን ሴራሚክ ብትራችንን እያንኳኳን እማማ ንግሥትን እናሞግሳለን…፤
የብትሩ ኳኳታ ጭፈራችንን ያደምቅልናል!

“የኔ እማማ ንግሥት የሰጠችኝ ሙክት፣

አልችለው ብየ እመንገድ ጣልኩት…”

እማማ ንግሥት በወርቅ የተሽቆጠቆጠ ተራራ የሚያህል ሹርባቸው ላይ ነጠላቸውን ጣል አድርገው
(ነጠላ የለበሰ ጉብታ) ነጭ ባለጥልፍ የሐገር ባህል ቀሚስ ደረቱ ላይ ትልቅ መስቀል የተጠለፈበት ቀሚስ ለብሰው ከቤት ብቅ ይላሉ። ባዷቸውን አይደለም፤ ጋሻ የሚያክል፣ ከስፖንጅ ፍራሽ ላይ
የተቆረጠ ትልቅ ቁራጭ ስፖንጅ የመሰለ ድፎ ከፍ አድርገው ይዘው፤ በዜማችን እየተውረገረጉ
ዳቦውን እንደዋንጫ ከፍ አድርገው እያስጨፈሩት ከሚፍለቀለቅ ፈገግታቸው ጋ ብቅ ይላሉ።አቤት ደስታችን! ምራቃችን በአፋችን ይሞላል። ዳቦውን እንደ ጎበዝ ጎል ጠባቂ የዳንቴል መረቡን በተጠንቀቅ ዘርግቶ ለቆመው አለባቸው ይሰጡታል። በዳንቴሉ ተቀብሎ ጥቅልል ያደርግና ደረቱ ላይ ለጥፎ ያቅፈዋል። ፍጥነቱን ለተመለከተው መልሰው እንዳይቀሙት የፈራ እኮ ነው የሚመስለው !

“ዓመት አውዳመት!
ድገምና!
ዓመት!
ድገምና!
የንግሥትን ቤት!
ድገመና!!
ዓመት!
ድገመና!
ወርቅ ይፍሰስበት ….”

“እደጉ ልጆቸ እድእግ በሉ !! ወርቅ ይፍሶስቦት ሟለት ትልቅ በረከት ነውኮ…፤ ከወርቅ በሏይ ሙን
አለ…? ቡዙ ተብዛዙ ቁም ነገር ያቡቋችሁ..! አቡነ አረጋዊ ጭንቅላታቹሁን ይከፋፍተውና ትሙሩቱ ይግባዓባችሁ…” ብለው ይመርቁናል። አፋቸው ይጣፍጣል። እማማ ንግሥት ኤርትራዊት ናቸው። ታዲያ በአማርኛ ሲያወሩ አንደበታቸው አይጠገብም። ጥርስ የማያስከድኑ ተጨዋች ናቸው። ሲቆጡም በዚያው ልክ ነው ይባላል ሲቆጡ አይተናቸው አናውቅም......

ይቀጥላል
👍136
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

....ከዚሀ ከሽጉጥ ፍጥጫ በኋላ ጀምሺድና ሉልሰገድ ብዙ ጊዜ፤
ብዙ ቦታ አብረው ይታዩ ጀመር፡፡ ማታ ሁለቱ በጀምሺድ መኪና
ይሄዱና፣ ኒስ፣ ካን ወይም ሞንቴካርሎ ቁማር ሲጫወቱ ሰንብተው ሰኞ ጧት ይመለሳሉ። ከውጭ ለሚያየው ሰው ጓደኝነታቸው እየጠበቀ ሄዴ..

ክረምት እየተንፏቀቀ መጣና፣ ከወርቃማው በልግ ጋር ተቃቅፋ
የነበረችውን የኤክስ ከተማ እንደ ቀናተኛ ሌላ ውሽማ በብርድ
ይገርፋት ጀመር፡፡ ሽማግሌዎቹንና አሮጊቶቹን ከየመንገዱና
ከየመናፈሻው አባረሯቸው። ልጃገረዶቹ ቆንጆ ስስ ቀሚሳቸውን
ትተው ወፍራም ሱፍ ቀሚስ፣ ሱሪና ወፍራም ሹራብ፣ ካፖርት
እየለበሱ፣ ውብ ቅርፃቸውን ከክረምቱ አይን እየሽሽጉ በበጋ ቀያይ ወይም ብር መሳይ የጥፍር ቀለም ተቀብተው ሲውለበለቡ የነበሩትን ጣቶቻቸውን በወፍራም ጓንቲ ውስጥ እየደበቁ፤ ከክፍል ወደ ምግብ ቤት፣ ከምግብ ቤት ወደ መኝታ ቤት በፍጥነት ኩስ ኩስ ይሉ ጀመር። ውብ ዳሊያቸውን እያወዛወዙ በዝግታ መራመድ፣ ፅጌረዳ ጉንጫቸውን እያሳዩ፣ በቀያይ ከንፈራቸው እየሳቁ፣ በተኳላ አይን
ጎረምሳውን መቃኘት ቀረ፡፡ (ኩሉንና የከንፈር ቀለሙን ብርድ
ስለሚሰነጣጥቀው ለአይን ደስ አይልም።) ደም የሽሽውን ነጭ
ጉንጫቸውን ግራጫ ብጤ የጎሽ ፀጉር ወረረው በየመንገዱ ዳር በተርታ የተተከሉት ዛፎች ራቁታቸውን ቆመው
የኤክስን ንፁህ ሰማይ በጭራሮዋቸው ይቧጥጡታል። ቅጠሎቹ በሙሉ ረግፈው የባቡር መንገዱን ዳርና የሰው መተላለፊያውን ሞልተውታል። ሰው በፍጥነት ሲራመድ በቡት ጫማው ይፈጫቸዋል

አንዳንድ ቀን በረዶው እንደ ጥጥ በዝግታ ይወርድና ኤክስን
በንፁህ ነጭ ሻሽ ይገንዛታል። በሱፍ የተከናነቡት ልጃገረዶችና
ጎረምሶች ሜዳ ወጥተው በረዶውን እያድቦለቦሉ ይፈነካከታሉ ይሳሳቃሉ። ትንፋሻቸው እንደ ጉም ከአፋቸው ቡልቅ ቡልቅ! ሲል ይታያል። ጥቁሮቹ በረዶው ላይ እየሆኑ ፎቶግራፍ ይነሳሉ የኤክስ ሰማይ አብዛኛውን ጊዜ ብሩህ ሰማያዊ ነው። አንዳንድ ጊዜ ውሀ አረንጓዴ ይሆናል፣ ወደ ማታ ሰአት እንደ ልጃገረዶች ጉንጭ ይቀላል። የኤክስ ሰማይ ደመና አይለብስም፡ ሁልጊዜ ራቁቱን ነው፣ ሁልጊዜ ውብ ነው፤ ሁልጊዚ ሰሳማዊ ነው። ማታ ማታ የአልማዝ ከዋክብትና የፀጥታ ሰላም ይለብሳል

ክረምት ሲሆን ሌሊቶቹ ይረዝማሉ፣ ቀኖቹ ያጥራሉ፤ ፀሀይዋ ጧት ወደ አንድ ሰአት ተኩል ላይ ትወጣና ከሰአት በኋላ ወደ አስር ተኩል ላይ መጥለቅ ትጀምራለች፤ በሽታ እንደያዘው እየማቀቀች እየደከመች ትሄዳለች። ሩቅ፣ ሩቅ ሩቅ በጣም ሩቅ ሆና ኮሳሳ ብርሀን ትልካለች። እቺ ፀሀይ በበጋው የሙቀት ምንጭ ነበረች፡ለኤክስ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች የህይወት ተስፋ ነበረች፣ አሁን ግን
ሰማዩ ተበስቶ ከውጭ የብርድ ጮራዎች የሚያስገባ ይመስላል

ብርዱ መላውን ፍጥረት ጨብጦ ያዘ፡፡ የሁላችንም ህይወት
በክረምቱ ብርድ ታሰረ፣ በቆፈን ተቋጠረ፡፡ ፀደይና ፀሀይ መጥተው
እስኪያስፈቱንና እስክንንቀሳቀስ ድረስ፣ የህይወታችን ታሪክ በያለበት ረጋ:: ተካና ጀርመኗ እኔ የማላውቀውን ግንኙነታቸውን ቀጠሉ፡፡ጀምሺድና ሉልሰገድ በኒኮል የፍትወት ገመድ ተሳስረው መለያየት አቅቷቸው፣ ጤና የለሽ ጓደኝነታቸውን ቀጠሉ፤ ለገና እረፍት ባህራም ወደ ኤክስ ሲመለስ ጊዜ፤ ኒኮልን ትተውለት ሁለቱ ተያይዘው ወደ ሞንቴ ካርሎ ሽሹ። እኔና ሲልቪ አልፎ አልፎ
እየተገናኘን፣ የቀረውን ጊዜ ስንፅፍ እንሰነብት ነበር በብርዱ ምክንያት የህይወታችን ታሪክ መፍሰሱን መለዋወጡን ትቶ፣ በያለበት ረጋ
አዳሞ የተባለው ዘፋኝ
"Tombe la neige
Tu ne viendras pas ce soir
Tombe la neige
Me crie mon desespoir..."
(በረዶው ይወርዳል
እንግዲህ ዛሬ ማታ አትመጪም
በረዶው ይወርዳል
ተስፋ መቁረጤ ይነግረኛል .. .»)
እያለ የክረምት እንጉርጉሮውን ያዜማል ..
ፀሀይዋ ቀስ በቀስ የሸሸችንን ያህል ቀስ በቀስ ትጠጋን
ጀመር። አየተቀነሰ የሚሄደው ብርድ፣ ቀጥሎም እየበረታ የሚሄደው ሙቀት፣ ረግቶ የነበረውን የፍጥረት ደም ቀስ በቀስ ያፍታታው ጀመር። መጀመሪያ አንዳንዷ ደፋር ቅጠል ብርዱን አሽንፋ አንገቷን
ብቅ ታደርጋለች፣ ራቁታቸውን የከረሙት ጭራሮ ቅርንጫፎች ላይ ስትታይ ታስደንቃለች፡ ታስደስታለች፤ የድል አድራጊው ህይወት ፊታውራሪ ነች፡ ምስጢራዊ ተአምር ነች። እንግዲህ ሌሎቹ ቅጠሎች
ይከተሉዋታል፡ የኤክስ ዛፎች በራቁት ጭራሮዋቸው ሰማዩን
መቧጨር ትተው፣ በለምለም አረንጓዴ ልብሳቸው ይወለውሉታል፣ ያፀዱታል። የኤክስ ጎረምሶችና ኮረዳዎች መጀመሪያ ካፖርትና
ጓንቲያቸውን አወለቁ፤ ቀጥሎ ሹራባቸውን አውልቀው መሳሳቅ
ጀመሩ። አንዳንድ ደፋር አሮጊት ወይም ሽማግሌ ካፖርቱን
እንደለበሰ መንገድ ላይ ይታይ ጀመር፡፡ ክረምቱ አለፈ ..

ፀደይ መጣ፡፡ የኤስ ልጃገረዶች ከባድ የክረምት ልብሳቸውን ገፈው ጥላው፣ ክረምቱ አልብሷቸው የነበረውን
አስቀያሚ ነጭ ጎሽ ፀጉር ኣራግፈው፤ የተፈጥሮ ውበታቸውን
መልበስ አመጡ፡፡ ፀጉራቸው ጭንቅላታቸው ላይ ተቆልሎ ወይም ወደ ኋላቸው እየፈሰሰ፣ ቆዳቸው ልስልስ ብሎ የፅጌረዳ ቀለም እየለበሰ፣ በቀይ ከንፈራቸው የተከበበ ጥርሳቸው በፈገግታ እያብለጨለጨ፡ ተሸሽጎ የከረመው ወጣት ቅርፃቸው እየፋፋ፣ ሹል ጡታቸው
ከፊት እየተንቀጠቀጠ፣ ያበጠ ዳሌያቸው ከኋላ እየተወዛወዘ፣ ይሄ ሁሉ ፀጋ የፀደይን መልካም ብርሀን ለብሶ በየመንገዱ እየተዘዋወረ፣ የኤክስን ጎረምሶች ምራቃቸውን ያስውጣቸው ጀመር። በብርድ ተኮራምተው የከረሙት ኮረዳዎች አሁን በሙቀት ተዝናኑ፤ እየተጯጯሁ በሳሩ ሜዳ ይፈነጩ
ይንከባለሉ ጀመር። ከጎረምሶቹ ጋር ልፊያና መተቃቀፍ ተጀመረ

ሽማግሌዎቹና አሮጊቶቹ እየወጡ የኩር ሚራሶንና የመናፈሻውን
አግዳሚ ወምበሮች ሰፈሩባቸው። እርጅና ከወጣትነት ጋር እየታከከ
የኤክስን መንገዶች በጎባጣ ጨምዳዳ እርምጃው ይንፏቀቅባቸው ጀመር የክረምቱ ብርድ ገድቦ ይዞት የነበረው ታሪካችን አሁን በፀደይ
ውቀት እንደገና መፍሰስ ጀመረ

ፀደይ ለኤክስ ብርሀንና ሙቀት ከአረንጓዴ ቀሚስ ጋር ይዞላት
ሲመጣ፤ ለተካ ችግር ይዞለት
መጣ። ባለውስታሿ ጀርመን
ታስቸግረው ጀመር። ከአንድ ያገሯ ልጅ ጋር መውጣት አመጣች፡፡
ታዛ ምን ትሽረሙ@ያለሽ? አላት። መሸርሞጥ አይደለም ማማረጥ ነው» አለችው:: እና የትኛችን ይሻላል?» አላት::በአንዳንድ ነገር እሱ ይሻላል፤ በሌላ ደሞ አንተ ትሻላለህ»አለችው። ተካን ቅናት ይሞረሙረው ጀመር

ጥፍሩን እየነከሰ «አሁን ምን ማድረግ ይሻለኛል እባክህን?»
አለኝ

«ትወዳታለህ?» አልኩት
«አዎን። ብዙ ነገር ይገባታል፡»
እሷስ ትወድሀለች?»
«አዎን»
«እንግዲያው አግባታ»
“አብደሀል? ነጭ ሚስት ይዤ ብመለስ አባቴ አይታነቅም?»
«እንግዲያው ተዋት»
እንዴት አድርጌ ልተዋት? በፊት እንኳ ቢሆን ልተዋት እችል
ነበር። አሁን ግን፣ ከዚያ ከንፍጣም ጀርመን ጋር መውጣት
ከጀመረች ወዲህ፡ ከምተዋት ብገድላት እመርጣለሁ፡፡»
«የሀበሻ ምቀኝነት ነው?» አልኩት
«አይደለም፡፡»
«ታድያስ?»
«እህ! ስለቅናት አታውቅም እንዴ? እንግዲያው ልንገርህ፡፡
አየህ፣ ስትቀና ልጅቷን በሀይል ትጠላታለህ። ብትገድላት ፈቃድህ
ነው፡፡ ግን በዚህ አለም ላይ ምን ትፈልጋለህ ቢሉህ፤ እሷን ነው
ምትፈልገው ሁሉ ነገር ይቅር ብቻ እሷ ትምጣ፡፡ ገባህ የምልህ?
ለምሳሌ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሱ ጋር የወጣች ጊዜ፣ ቤቷ ወሰድኳትና አንድ ጥፊ አላስኳት፡፡ ወዳ እስክትጠላ ልደበድባት ቆርጬ ኮቴን አወለቅኩ። ታዲያ ዳግማዊ ጥፊ ላወርድባት ስል
👍162
“Sauvage! ኣፍሪቃ ውስጥ ያለህ መሰለህ እንዴ?» አለችኝ።እንደቃጣው ቀረሁ
ዳግማዊውን ጥፊ እንደማውረድ አቅፌ ሳምኳት። ስትፍጨረጨር በጉልበት ሙታንታዋን ቀድጄ በታተንኩባት፡፡ ወደ አልጋው እንኳ እስክወስዳት አላስቻለኝም። እዚያው ምንጣፍ ላይ በዳኋት፡፡ እንደጨረስኩ ታድያ በሀይል ቀፈፈችኝ::እዚያው ወለል ላይ እንደተጋደመች ትቻት ወጥቼ ሄድኩ

«ይሄ ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ እንግዲህ የኔ
ኑሮ መቃጠል ሆኗል።»

«ሰውየውን ተይው አልካት?» አልኩት

«አዎን። 'እንዴት እተወዋለሁ? ላንተ ብዪ እንዴት እሱን
ልተወው? አንተ ልትተኛኝ ነው የምትፈልገው፡፡ እሱ ግን ሊያገባኝ
ነው ሚፈልገው:: ባይሆን ለሱ ስል አንተን እተውሀለሁ እንጂ፣
እሱንስ አልተወውም አለችኝ፡፡»
«ምን አልካት?»
«አንድ ሁለት ጥፊ አላስኳት፡፡ ስታለቅስ በግድ በዳኋት፡፡»
«እንዲህ ከቀጠልክ ትተውሀለች» አልኩት
“ተሳስተሀል፡፡ በጥፊ መትቼ በጉልበት ስደፍራት በሀይል ነው
ፍቅሬ የሚጥማት፡፡»
«እንዴት ታውቃለህ?»
«ከሁኔታዋ ያስታውቃል»
«ዋ! ጥፊው ቢቀር ይሻለሀል» አልኩት “አይገባህም። ቅናት ገና አላጋጠመህም» አለኝ
ግን አንድ ነገር ገብቶኛል፡፡ ልጅቷ ልታገባው ታጥቃ ተነስታለች

ክረምት አልፎ ፀደይ እንደገባ በፋሺስቶችና በኮሙኒስቶች
መካከል ትልቅ አምባጓሮ ተነሳ፡፡ አምስት ስድስት ፋሺስቶች ይሆኑና አንዱን ኮሙኒስት ይዘው ይደበድቡት ጀመር፡፡ ኮሙኒስቶቹ
ተማሪዎች፣ እጃቸውን ወይም ራሳቸውን በፋሻ ጠምጥመው ይታይ ጀመር። ፋሺስቶቹ ወንድ ቤት ሳይሉ ያገኙትን ኮሙኒስት
መደብደብ ሆነ። አንዷን ልጅ አራት ጎረምሶች ተጋግዘው ደበደቧትና የአፍንጫዋን አጥንት ሰበሩት። ሆስፒታል ተኛች ኮሙኒስቶቹ ከባድ የብረት መሳሪያ፣ አጭር የብረት ዱላ፣ ወይም ይህን የመሳሰለ ነገር እጅጌያቸው ውስጥ እየደበቁ ሶስት
አራት እየሆኑ መዞር ግድ ሆነባቸው። ጩቤ ወይም ሽጉጥ እየያዙ የሚዞሩም ነበሩ
ባህራምን ልጠይቀው ትምህርት ቤቱ ሄድኩና የሆነውን ሁሉ
አጫወትኩት። አብሮኝ ወደ ኤክስ መጣ፡፡ «የነገርኩህ ወሬ ደስ
ያሰኘህ ይመስላል» አልኩት

«ለኮሙኒስቶቹ እዝንላቸዋለሁ። ግን ጥሩ ነው፤ ይጠቅማቸዋል።
ለአምባጓሮ በቂ ዝግጅት የላችሁም፣ አያልኩ እጨቀጭቃቸው ነበር።
ፈረንሳይ አገር ኣምባጓሮ አይስራም፡፡ በፅሁፍና በንግግር የሰውን ሀሳብ ማናወጥ ማነቃነቅ ነው የሚያስፈልገው፤ ሲሉኝ ነበር። ብቻ የራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡ የፈረንሳይ ህዝብ ወሬ ያበዛል። ስራ፣ ጀብዱ (Action) ስትለው በቄንጠኛ ሰዋሰው ስለ አርት ሊያወራልህ ይጀምራል። ተዋቸው እነሱን። እኔን ያስደሰተኝ ሌላ ነገር ነው::»

«ምንድነው?»

ረብሻ ውስጥ ከገባሁ አመታት አለፉ። ናፍቆኛል» በተጨበጠ ቀኝ እጁ ግራ መዳፉን እየወቀጠ ረብሻ ናፍቆኛል» አለ

እንግዲህ ኤክስ ውስጥ ኮሙኒስቶቹ የሚያዘወትሩት አንድ ካፌ አላቸው። ሮያሊስቶቹ አንድ ሌላ ካፌ ያዘወትራሉ (ሮያሊስቶቹ
ፈረንሳይ ውስጥ ንጉስ ለማንገስ የሚፈልጉ ናቸው) ወንድ ለወንድ
የሚዋደዱት አንድ ካፌ አላቸው፡፡ ፋሺስቶቹም የራሳቸው ካፈ
አላቸው ኤክስ እንደገባን ባህራም ፋሺስቶቹ ካፌ ወሰደኝ። ቢራ፣ ቡና
እየጠጡ በየጠረጴዛው ያወራሉ። አብዛኛዎቹ ፂማቸውን በቄንጥ
ያስተካከሉ ወጣቶች ናቸው:: በጣም ያምራሉ

እኔና ባህራም መውጫው በር አጠገብ ያለችው ጠረጴዛ ጋ
ቁጭ ብለን ቢራ ጠጥተን ሂሳቡን ከከፈልን በኋላ፣ ባህራም
ምንም ቢመጣ ምንም፣ ከተቀመጥክበት እንዳትነሳም አለኝ
“ምን ልታረግ ነው?» ስለው

«ታያለህ» አለኝ....

💫ይቀጥላል💫
👍22👏1
#ድንቡጮ_ለምን_ለምን_ሞተ


#ሁለት(መጨረሻ)


#በአሌክስ_አብርሃም


...“እደጉ ልጆቸ እድግ በሉ !! ወርቅ ይፍሶስቦት ሟለት ትልቅ በረከት ነውኮ…፤ ከወርቅ በሏይ ሙን አለ…? ቡዙ ተብዛዙ ቁም ነገር ያቡቋችሁ..! አቡነ አረጋዊ ጭንቅላታቹሁን ይከፋፍተውና ትሙሩቱ ይግባዓባችሁ…” ብለው ይመርቁናል። አፋቸው ይጣፍጣል። እማማ ንግሥት ኤርትራዊት ናቸው። ታዲያ በአማርኛ ሲያወሩ አንደበታቸው አይጠገብም። ጥርስ የማያስከድኑ ተጨዋች ናቸው። ሲቆጡም በዚያው ልክ ነው ይባላል ሲቆጡ አይተናቸው አናውቅም እንጂ…!! አባባ መክብብ ታዲያ ሚስታቸውን ሲወዷቸው ልክ የላቸውም። አንድ ቀን እትየ ንግሥት ታመው (የደም ግፊት የሚባል ነገር ነው አሉ) አንቡላንስ ተጠርቶ ጎረቤቱ ሁሉ ሲሯሯጥ አባባ መክብብ እንደ ሕፃን ልጅ በሁለት እጆቻቸው ጭንቅላታቸውን ይዘው ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ እና ሲጮሁ አይቻቸዋለሁ ! ሰው ሁሉ እያባበላቸው!

“እትየ ንግሥት ... እናቴ፣ እህቴ፣ ጓደኛዬ ሜዳ ላይ እኔን ጥለሽ ..” እያሉ…

ባልና ሚስቱ አንዲት ልጅ አለቻቸው፤ ህደጋ የምትባል፣ ፈረንጅ አግብታ ውጭ አገር የምትኖር።በየሦስት ዓመቱ እናትና አባቷን ልትጠይቅ ስትመጣ ከታች ሰፈር ጀምሮ እስከላይ ሰፈር ድረስ
ሁሉም ቤት እየገባች ጎረቤቱን ሁሉ ትስምና ሃምሳ ሃምሳ ብር ትሰጣለች። ለትልልቅ ሰዎች ብቻ
ነው የምትሰጠው። ከእኛ መካከል የሃምሳ ብር እጣ የሚወደቅለት ፈንታው ድንቡጮ ብቻ ነበር።
የፈንታው እናት ሚስኪን ናት፤ በሽተኛ ስለሆነች ከአልጋ ላይ አትነሳም። ፈንታው አባባ መክብብ
ግሮሰሪ በረንዳ ሥር ጫማ እየጠረገ እና እየተላላከ ነው እናቱን የሚያስታምመው። አባቱ በደርግ ጊዜ ዘምቶ ይሙት ይትረፍ ሳይታወቅ በዛው ቀልጦ ቀርቷል። ያው የህደጋ ሃምሳ ብር ፈንታው ድንቡጮን የሚያካትተው ለዚህ ሳይሆን አይቀርም !

አንድ ቀን ታዲያ የስፖርት ትጥቅ ለመግዛት ከመንደርተኛው ሳንቲም እንለምናለን። በአጋጣሚ ፊት
ለፊታችን ህደጋ አሻንጉሊት የመሰለ ልጇን በደረቷ አቅፋ ስትመጣ ተገጣጠምን። ሌላውን መንደርተኛ ሳንቲም ውለድ እያልን ምናስቆም እኛ፣ ህደጋን ለምን እንደፈራናት እንጃ፤ ብቻ ገለል ብለን አሳለፍናት።
በቀጣዩ ቀን ታዲያ አስጠራችንና እንኳን በእውናችን በህልማችንም አስበነው የማናውቀውን የስፖርት
ትጥቅ ከነኳሱ ገዛችልን።

አቤ…ት! እንዴት እንደተደሰትን…! ለስንት ዓመት ታሪክ ሆኖ በመንደራችን ተወራ ! “ኳሱ የት
ይቀመጥ” በሚል በመካከላችን ከባድ ክርክር ተደርጎ እኔጋ እንዲቀመጥ ተወሰነ። የተሰማኝ ደስታ ወደር አልነበረውም። ግን ምን ያደርጋል አንድ ቀን ያ ለብዙ ሕፃናት ህልም የነበረ ኳስ ምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ጠፋ። የጠፋው ከእኛ ቤት ስለነበር በቡድኑ አባላት ዘንድ ክፉኛ አስተችቶኛል።ለረዥም ጊዜ ያኮረፉኝ የሰፈር ልጆችም ነበሩ። በእግር በፈረስ በሰፈራችን ስርቻ ሁሉ ኳሱን ፈልገን ስናጣው በቃ ወደ ጨርቅ ኳሳችን ተመለስን። አሁን ካደግን በኋላ ሳይቀር የኳሱ ነገር ሲነሳ እወቀሳለሁ።
እንደውም አሁን ካደግን በኋላ እድሜያችን ሃያዎቹ ውስጥ ገብቶ ተፈሪ የሚባለው የሰፈራችን ልጅ
(አሁን አዉስትራሊያ የሚኖር) ኢ-ሜይል ሲያደርግልኝ ስለ ኳሱ ጉዳይ አንስቶ እንዲህ ብሎኛል፣
“አቡቹ እዚህ የፈረንጅ ሕፃናት ኳሶች ይዘው ሲጫወቱ ሳይ ያች ህደጋ የገዛችልን የጣልክብን ኳስ ትዘ እያለችኝ ይቆጨኛል ሃሃሃ” አንረሳም እኮ አንዳንዴ !
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ድንገት ነበር ነገሮች የተገለባበጡት፤ ልክ እንደ መሬት መንቀጥቀጥ፣ እንደጎርፍ መጥለቅለቅ ሰፈራችን ውስጥ በአብሮ መኖር የፍቅር ቆሌ የሆኑ ነዋሪዎችን ከሥራቸው እየመነገለ ድራሻቸውን ያጠፋ ድንገቴ
ነውጥ። እንዴት ነው ሰው ድንገት ተነስቶ ትላንት አለፍኩት ወዳለው አረንቋ መልሶ የሚዘፈቀው…?
“ሲደርሱብን ምን እናድርግ” ብሎ ነገር ...

“ኤርትራ ወረረችን…” ተባለ።
“ምናባቷ ቆርጧት ይች የእናት ጡት ነካሽ!” የሚሉ ደምፍላታም ሰዎች ሰፈሩን ሞሉት። ከየት አመጡት አማርኛውን…? መቸስ ታንክ ቢሆን፣ መትረየስ፣ ቦንብ ምናምን ገዙት ይባላል፣ ወይ በእርዳታ አገኙት፤ ስድብ ከየት ተፈበረከ ... ዛቻ መቼ ተረግዞ ነው በዜማ የተወለደው…? ትላንት እንደ ቦብ ማርሌ “ፀበኞች ካልታረቁ!” እያለ ሲያቀነቅን የነበረ ድምፃዊ “ፍለጠው ቁረጠው!” ዘፈኑን ከየት መዝርጦ ቴሌቪዥኑን ሞላው፤ ወይስ ሁሉም ዘፋኝ ለክፉ ጊዜ ያስቀመጠው ዘፈን አለው? ለጦርነት ግጥምና ዜማ መፍጠር ከፍቅር ዘፈን ይቀላል? ከቀበሌ ኪነት ቡድን እስከ አገር አቀፍ ታላላቅ ዘፋኞች ዘፈናቸው አይሄድ አይመጣ አንድ - “በለው ፍለጠው ቁረጠው !!”

በዓይን ርግብግቢት ፍጥነት 'ለደኅንነታችሁ' ብለው ደህና ሰዎች ብለን ያመንናቸውን፣ ስንጣላ አስታራቂ፣ ስንቸገር ደራሽ የነበሩት ጎረቤቶቻችንን ሁሉ በአውቶብስ እየጫኑ አባረሯቸው። እማማ ንግሥትን ጨምሮ። ከመወለዳችን በፊት ኤርትራ የሄዱ የማናውቃቸው ብዙ እማማዎች ከዛም ተባርረው መጡ። ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ። ለካስ የመንግሥታት ፍርሃት እንደጅብ ያነክሳል አገርንም ያስነክሳል። አሁን እማማንግሥት ምናቸው ነው ለደህንነት የሚያሰጋው? በሹሩባቸው ውስጥ ቦምብ
እንዳይቀብሩ ነው? ወይስ በድፏቸው ውስጥ ጥይት እንዳይደብቁ ...። እማማ ንግሥት (ለደህንነት ስጋት ናቸው ተብለው የተባረሩ ቀን ማታ ህልም አለምኩ….

ቀኑ ቡሄ ይመስለኛል። የሰፈር ልጆች እንደልማዳችን ተሰባስበን እማማ ንግሥት በር ላይ ቆመን
እንጨፍራለን።

“እዛ ማዶ አንድ በረዶ!

እዚህ ማዶ አንድ በረዶ!

የኔ እማማ ንግሥት!
ፓራ ኮማንዶ ….”

የእማማ ንግሥት በር ድንገት ብርግድ ብሎ ተከፈተና፣ በወርቅና በሐገር ባህል ቀሚስ የምናውቃቸው እማማ ንግሥት፣ የወታደር ልብስና ከስክስ ጫማ ለብሰው አናታቸውም ላይ የብረት ቆብ ደፍተው ድፎ ሳይሆን ዝናሩ የተንዠረገገ መትረየስ ጠመንጃ ደግነው፣ “ አንች ዲቃላ ሁሉ … በሬ ላይ ሙናባሽ ትናጫጫለሽ አቡነ አረጋዊ ድራሽ አባትሽን ያጥፉት!” ብለው ታታታታታታታታታታታታታ
ሲያደርጉብን በተለይ እኔ ሰውነቴ ተበሳስቶ ወንፊት የሆነ ይመስለኛል…፤ እየጮህኩ ከህልሜ ባነንኩ…፤ እናቴ ከትራስጌ በኩል ቆማ “አቡቹ በስማም በል ቅዠት ነው…” ትላለች።

ያየሁትን ህልም ለማሚ ስነግራት ግን ተቆጣች…

“ምን እንደው የዛሬ ልጅ የነገሯችሁን ይዛችሁ ትጋደማላችሁ፣ ቅዠት ይተርፋችኋል ፤ በል አርፈህ
ተኛ”

አባባ መክብብ እትዬ ንግሥት ወደ ኤርትራ ከተባረሩበት ጊዜ ጀምሮ ግራ እግራቸውን ሰብስቦ
ያዛቸው፤ በከዘራ ድጋፍ ሆነ የሚራመዱት። የጢም መላጫቸውም ከእጃቸው ጠፋች። ነጭና ጥቁር ቡራቡሬ ፂም ትንሽ አገጫቸውን ሸፈነው…፤ ተዘናጉ፤ ሰፈሩ ተዘናጋ …። አንድ ቀን በግሮሰሪዋ በኩል ሳልፍ አባባ መክብብ ከዘራው እጀታ ላይ የተነባበረ እጃቸው ላይ አገጫቸውን አሳርፈው አፋቸው
ባዶ ነገር እያኘከ ትክዝ ብለው ተቀምጠዋል በቀስታ ወደ ፊትና ኋላ እየተወዛወዙ። ላልፍ ስል የውሃ ማጠራቀሚያው በርሚል ላይ ዓይኔ አረፈ፤ የሆነ ነገር ቅር አለኝ …፤ በትኩረት በርሚሉን አየሁት፤ ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ ከበርሚሉ ተነጥላ የማታውቀው የመርቲ ጣሳ በቦታዋ የለችም። ጣሳዋ ትታሰርባት የነበረችው የኤሌክትሪክ ገመድ ባዶዋን ተንጠልጥላ ነፋስ በቀስታ ያወዘውዛታል !
👍21🔥1
ከበርሚሉ ራቅ ብሎ …. የፈንታው ድንቡጭ የሊስትሮ ድንጋይ ከዘንባባዋ ሥር ባዶዋን ትታያለች።
ፈንታው ድንቡጭ“ለአገሩ ዘመተ….” መባሉን ሰምቻለሁ። ፈንታው ጋር ካደግን በኋላ ብዙም ፋታ ኖሮን አንገናኝም ነበር። ቢሆንም አንዳንዴ በዛ ሳልፍ ሰላም እንባባላለን። ጫማዬንም ይቦርሽልኛል።
እንደውም ወደ ወታደር ቤት ሊሄድ አካባቢ ጫማዬን እየቦረሸልኝ ድንገት የሐፍረት ፈገግታ ፊቱን
አጅቦት እንዲህ አለኝ (በወሬ ወሬ ተነስቶ ሳይሆን እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ..)

“አብርሽ የዛን ጊዜ ህደጋ የገዛችልን ኳስ ታስታውሳታለህ ?”

እንዴ ታዲያ ያችን ኳስ ማን ይረሳል…፣” ተሳሳቅን። ፈንታው ጫማዬን መቦረሹን ገታ አድርጎ መሬት መሬት እየተመለከተ እንዲህ አለኝ፣

“ያኔ ኳሷን ከግቢ የወሰድኳት እኔ ነበርኩ፤ እማማ ብር ፈልጋ እጄ ላይ ሳንቲም ስላልነበረኝ ለሆኑ
ልጆች ሠላሳ ብር ሸጥኩላቸው።”። ነገሩ አስደነገጠኝ። ፈንታውም ቅሬታ ባረበበት እኔም ግራ በተጋባ
ፊት ተሳሳቅን፣ እናም ሁለታችንም ወደ ጥልቅ ዝምታ ገባን። ለምን እንደነገረኝ አልገባኝም ነበር።
ፈንታው ኳሷን ወስዶ ይሸጣታል ብሎ የጠረጠረ ያኔ ማንም አልነበረም፤ ማንም !! አሁን ራሱ
ቢነገረው ማን ያምናል! ፈንታው ድንቡጮ ፊቱ ወርቅ ቢዘራ ቅንጣት የማይነካ ንፁህ ደሃ ነው።
ጫማዬን አስቦርሼ ስነሳ እንዲህ አለኝ፣ “አብርሽ ይቅርታ…”
“ኧረ አታካብድ ይሄ እኮ ተራ ነገር ነው፣” አልኩት፤ ግን ለምን እንደሆነ እንጃ ቶሎ ከአካባቢው መራቅ ፈልጌ ነበር።

ወሬው ሁሉ ጦርነት ሆነ ... ሽለላው፣ ቀረርቶው፣ መፈክሩ። እንደ ቀልድ ቃል ጥላቻ ለበሰ። ጥይትና ቦንብ ለብሶ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ላይ አደረ። ገና እሳቱ ሳይጠፋ…፣ ገና ወጣቶች እየጨፈሩ ወደ ድንበር ሊፋለሙ በጭነት መኪና ጨፈቃ መስለው ተጭነው ሲሄዱ…፣ ገና በጠዋቱ ወደፊት መንደራችን ሁነኛ ሰው መርዶ ይዞ መጣና እንደ መርፌ የሚወጋ ቀፋፊ ጤዛ መንደራችን ላይ ዘራ ...

"ፈንታው ድንቡጮ ሞተ….”

ከመጀመሪያዎቹ ዘማቾች መሐል ነበር ፈንታው ድንቡጮ..
አብሮ አደጋችን ፈንታው ሞተ።
ከአባባ መክብብ ግሮሰሪ በረንዳ ሥር ዛሬም የፈንታው ድንቡጮ ድንጋይ አለች !
ታዲያ መንደርተኛው ተሰባሰበና ለፈንታው አለቀሰ። እዛው አባባ መክብብ በረንዳ ሥር የፈንታ
ድንጋይ ላይ አለቀሰ ጎረቤቱ። አባባ መክብብ ከዘራቸውን አገጫቸው ሥር አስደግፈው ግራ ቀኝ እየተወዘወዙ እንጉርጉሮ የመሰለ ዜማ ያወጣሉ። አያለቅሱም፤ ማንንም አይመለከቱም፤ ዝም ብላ
መወዝወዝ። ሰዉ ተበታትኖ ወደየቤቱ ገብቶ እንኳን መወዛወዛቸውን አላቆሙም እስከማታ በተቀመጡበት ... እእእእእእእእእእእእእ እያሉ !

ቀበሌያችን ግቢ ውስጥ ለዘመቻ የተመለመሉ ወጣቶች የሽኝት ፕሮግራም ነበር። ሰንጋ ተጥሎ፣ ብዙ በግ ታርዶ፣ ሰዉ ቢራ እየተራጨ፣ ጀግንነታችን እየተወሳ ... አድዋ፣ ማይጨው እየተገረበ፣ አባቶች ለዘማች ወጣቶች ባንዲራ እያስረከቡ፣ ወጣቶቹ ተንበርክከው ባንዲራውን እየተረከቡ፣ እናቶች እልል
እያሉ፣ ዘፋኞች ስለአጥንት መከስከስ፣ ስለደም መፍሰስ እየዘፈኑ… “አዝማቹ ሕዝብ፣ ዘማች ልጆቹን ሂዱና ጠላቶቻችሁን አደባዩ!” ብሎ እየላካቸው ...
በቀበሌው አጥር አጠገብ እጆቼን ኪስና ኪሴ አስገብቼ ወደ ቤቴ እያዘገምኩ ነበር ወደ አስራ ሁለት
ሰዓት አካባቢ ይሆናል ማታ። ታዲያ አንድ ውሻ አጥሩ ጥግ የወደቀ የበግ አንጀት እየጎተተ በአጠገቤ አለፈ፤ ማመን አልቻልኩም፤ የእማማ ንግሥት ውሻ “አሲምባ…”

“ዘመቻ ፀሐይ ግባት በድል ተጠናቀቀ!” አለ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን። ወጣቶቹ በደስታ አገር ጠበበን። በየመንገዱ የደስታ ፌሽታና ጭፈራ ሆነ። የመኪና ጡሩምባ ጩኸት፣ የእናቶች እልልታ፣ የአባቶች ዘራፌዋ ..! የሴቶች ጉሮ ወሸባዬ ... የዘንባባ ዝንጣፊና ባንዲራ የያዙ ወጣቶች የመኪናዎች እቃ መጫኛ
ላይ እንደንብ ሰፍረው ይጨፍራሉ፣ በደስታ ይጮሃሉ። ቴሌቪዥኑ ደጋግሞ የምሥራቹን ያበስራል።

ቃለ መጠይቅ በሬዲዮ ለጀግና ወታደሮች ... ለጀግና የጦር መሪዎች፣

“እስኪ የጦር ውሎዎትን ይንገሩን…

“ሻእቢያ እንደ ፍልፈል ጉድጓድ ቆፍሮ ተደብቆ የነበረ ቢሆንም፣ ከጉድጓዱ በጀግና ልጆቻችን አውጥተን ቀብረነዋል …።” ሕዝቡ በጀግኖቹ ኮራ!! አባባ መክብብ ግሮሰሪያቸው ውስጥ በስልክ እያወሩ ነበር።ጭፈራው ያደከመን የሰፈር ልጆች ግሮሰሪዋ በረንዳ ላይ ተሰባስበን፣ የሰማነውን ጀብዱ በቴሌቪዥን ያሳዩንን የጀግኖች ውሎ ለመቶኛ ጊዜ ከአፋችን እየተነጣጠቅን እያወራን ... ያዘዝነውን ቀዝቃዛ ኮካ እንጎነጫለን።

አባባ መክብብ እያዘገሙ ወጡና አጠገባችን የበረንዳውን የብረት ደፍ ደገፍ ብለው ቆሙ። ዞር ብለው ተመለከቱንና እንደ እብድ ከት ከት ብለው ሳቁ ...ሰውነታቸው እየተርገፈገፈ ሳቁ ... ግራ ተጋብተን አየናቸው። አባባ መክብብ ሚስታቸው እትዬ ንግሥት ከሄዱ በኋላ እንኳን ሲስቁ ይቅርና የተቋጠረ ፊታቸው ሲፈታ አይተን አናውቅም ነበር።

“ሰማችሁ ልጆቼ!! ልጄ ህደጋ ከአሜሪካ ደውላ ያለችኝን ሰማችሁ...” አሉን በግርምት ተራ በተራ እየተመለከቱን…።

“ምን አለች አባባ መክብብ?” በጉጉት ጠየቅናቸው።

“አሁን እናቷ ጋር ኤርትራ ደውላ አናግራት፣ እኔንም ሰላም ልትል ነበር የደወለችው
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃም ብለው ሳቁ። አእምሯቸው የተናጋ መስሎን ፈራን። እንደ ምንም ሳቃቸውን ገቱና ፊታቸውን በምሬት ኩምትር አድርገው፣

“አስመራም ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ጉሮ ወሸባዬ እየተጨፈረ ነው እኮ ነው የምትለኝ !! ሆሆ ይች አገር እንደ ካሴት ሆነች… በዚህም ዘፈን ..፣ ስትገለበጥም ዘፈን ... ታዲያ ለድንቡጮ ማን ያልቅስ …? እኮ ድንቡጮ ለምን ሞተ …?” ብለው አንድ በአንድ ተመለከቱን። ከእኛ መልስ ሲያጡ ወደ ፈንታው ድንቡጮ ድንጋይ ዞረው በትካዜ ጭልጥ አሉ።
የፈንታው ድንቡጮ ቦታ ላይ አንድ ትንሽ ልጅ አዲስ የሊስትሮ ሳጥን ይዞ ተቀምጧል። ቀና ብዬ
ግሮሰሪው በር ላይ በግራ በኩል የቆመችውን የዘንባባ ዛፍ ተመለከትኳት፤ ለጭፈራው ቅጠሎቿን ዘንጥፈናቸው መለመላዋን ቆማለች፤ ብቻዋን የቆመች ዘንባባ ፤ ከአስመራ ዘንባባዎች መሐል አምልጣ
የመጣች መሰለችኝ፣ እዛም ጭፈራ! እዚህም ጭፈራ…” ብላ። ዘንባባዎቹ ሁሉ ወደ አስመራ ሲጫኑ በሆነ ተአምር የቀረችም መሰለኝ።

ሄደችም መጣችም ከዘንባባ ጫካዋ የተገነጠለች አብዮተኛ ዘንባባ !!

አለቀ
👍108
#ትኩሳት


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር

...እኔና ባህራም መውጫው በር አጠገብ ያለችው ጠረጴዛ ጋ
ቁጭ ብለን ቢራ ጠጥተን ሂሳቡን ከከፈልን በኋላ፣ ባህራም
ምንም ቢመጣ ምንም፣ ከተቀመጥክበት እንዳትነሳም አለኝ
“ምን ልታረግ ነው?» ስለው

«ታያለህ» አለኝ.

ተነሳና ወደ ሽንት ቤት በኩል መራመድ ጀመረ። አንዱ
ጎረምሳ ፋሺስት ከዚያው ሲመለስ ነበር ባህራምን የገጨው፡፡ ፋሺስቴ ሳያስብበት በልማድ “Pardon” ብሎት ሲያልፍ፣ ባህራም

«አንተ!» ብሎ ጮኸበት። ፋሺስቶቹ ወሬያቸውን አቆሙ::
ካፌው በሙሉ በፀጥታ ባህራምን ማየት ጀመረ። የገጨው ፋሺስት
ወደ ባህራም ዞሯል ባህራም

«ለምን ገጨኸኝ?» አለው

ፋሺስቱ «አንተ ነህ እንጂ የገጨኸኝ አለው

«ውሽታም ፋሺስት! ውሻ ፋሺስት! ፈሪ ፋሺስት! ወንድ ከሆንክ ተከላከል። ልገርፍህ ነው» አለና ዘሎ ትግል ያዘው። የፋሺስቱ ጀርባ ወደኔ ስለነበረ፣ ባህራም ምን እንዳደረገው ለማየት
አልቻልኩም፡፡ ብቻ ምንም ያህል ሳይታገሉ ፋሺስቱ ፍስስ ብሎ ወደ
መሬት ወደቀ፡፡ ባህራም ከበላዩ እንደቆመ ዙሪያውን ተመለከተ፡፡
ከፋሺስቶቹ ማንም አልተነሳም
ባህራም ፋሺስቶቹን እያየ «ማንም ፋሽስት እንዲገጨኝ አልፈቅድለትም፡፡ ከንግዲህ ሌላ ፋሺስት የገጨኝ እንደሆነ፣ ፂሙን
ነው ምላጭለት አለና የወደቀውን ፋሺስት ተሻግሮ ወደኔ መጣ፡፡
አብረን ወጣን
(ፋሺስቶቹ እኔን ሌላ ጊዜ ቢያገኙኝ ይደበድቡኝ ይሆን? ብዬ
ትንሽ ፈራሁ፡፡ ግን ደፍረው ጥቁር ተማሪ የሚደበድቡ አልመሰለኝም፡፡ ምክንያቱም እኛ የፈረንሳይ መንግስት እንግዶች
ማለት ነን፡፡)
ባህራም ኤክስ ውስጥ አራት ቀን ቆየ፡፡ ቀን ቀን ኮሙኒስቶቹን
ሲመካክራቸው፣ እንዴት አድርገው መከላከል ፅሁፎቻቸውን እንዴት ቢያሰራጩ እንደሚሻል፣ እና ይህን የመሳሰለ ነገር ሲነግራቸው ይውላል። ማታ ማታ ፋሺስቶቹን በየጠባቡ መንገድ ሲደበድባቸው ያመሻል፡፡ በአምስተኛው ቀን ትምህርት ቤቱ ድረስ ሸኘሁት፡፡ ስለአምቧጓሮው ሲነግረኝ፣ ስለኳስ ጨዋታ የሚያወራልኝ መስሎ ተሰማኝ፡፡ በደስታ እየገነፈለ፣ ማድፊጡን መዝለሉን፣ እጁን እንደ ሰይፍ አርጎ አንገት መምታቱን፣ እንደ ዳንስ አድርጎ ገለፀልኝ

"ማኑ ይህን ሁሉ ስስራ አይቶኝ ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር!
ያስተማረኝን ብልሀት በሙሉ ተጠቅሜበታለሁ» አለ

«ደህና ሁን» ብዬው ወደ ኤክስ ልመለስ ስል፣ ከኪሱ አንድ
እቃ አውጥቶ አሳየኝ። የፀጉር መቁረጫ መኪና «ቶንዶዝ»፡፡
ምንድነው? አልኩት፡፡ እየሳቀ «ፋሺስቶቹ ካፌ ሂድና እቺ ነገር
ኮሙኒስት መሆንዋን ትገነዘባለህ» ብሎኝ ተለያየን ኤክስ እንደደረስኩ ፋሺሰቶቹ ካፌ ገባሁ። ብዙዎቹ እጃቸውን ወይም ጭንቅላታቸውን በፋሻ ጠምጥመዋል፡፡ ግማሾቹ ፂማቸውን ላጭተዋል። ፂማቸውን ያልላጩት ደሞ ጥቁር «ቤሬ ቆብ
አርገዋል። ለካ ባህራም ኣንድ ፋሺስት በደበደበ ቁጥር ራሱን
ወይም ፂሙን ይላጭለት ኖሯል
(እኔና ባህራም ኣንድ ግሩም የሆነ ሀራኪሪ» የተባለ የጃፓን ፊልም አይተን ነበር። እዚያ ፊልም አንዱ ጎበዝ እየዞረ የጠላቶቹን
ፀጉር ይላጫል።)

ባሀራም በሄደ በአራተኛው ቀን፣ አንዲት ኮሙኒስት ልጅ ካፌ
ቁጭ ብዬ ሳለሁ መጣችና ወደ ኤክስ አንድ ነብሰ ገዳይ መጥቷል
አለችኝ። ምን አንደሆነ ማለቴ የቱ እንደሆነ አናውቅም። ግን መምጣቱን እናውቃለን፡፡ ፋሺስቶቹ ናቸው ከማርሰይ ያስመጡት። ባህራምን ሊደበድበው ወይም ሊገድለው ነው የመጣው::»
«ፋሺስት ነው?» አልኳት
«አይደለም። የተገዛ ነብሰ ገዳይ ነው» አለችኝ
ያን ጊዜውኑ ሲልቪ ቤት ሄድኩ። በአቶቡስ እንዳልሄድ
ምናልባት ፋሺስቶቹ ይከታተሉኛልና፡ ካንቺ ጋር ለሽርሽር የምንወጣ አስመስለን እንሂድ አልኳት።በመኪናዋ ሄድን። ለባህራም ነገርኩት።
ሲልቪ ቤቷ ወስዳን እራት በላን። ከዚያ ሶስታችንም ሄደን
ፋሺስቶቹ ካፌ ገብተን ሁለት ሰአት ያህል አሳለፍን። ይህን ሁሉ
ጊዜ ባህራምና ሲልቪ ያወሩ፣ ይቀልዱ፣ ይስቁ ነበር፡፡ እኔ ግን
ምንም ያህል አላወራሁም። ለባህራም ፈርቼለት ነበር፡፡ ሰውየው የቱ እንደሆነ ብናውቅ እንኳ ለመከላከል እንሞክር ነበር። አሁን ግን ከማንኛውም አቅጣጫ ጦር ሊወረወርበት በሚችልበት
ውስጥ፣ ባህራም ብቻውን የሚራመድ መስሎ ተሰማኝ
አብሬያቸው ባለማውራቴ፣ የኔ ፍርሀት ቀስ እያለ ወደ ሲልቫ
ተላለፈባት

“ፈራሁ። በጣም ፈራሁ» አለች

ባህራም «ምን ያስፈራሻል?» አላት፡፡ ግን ድምፁ እንደ ድሮ
ልዝብ መሆኑ ቀርቶ፣ ትንሽ እሾህም ሆኗል

«ማን እንደሆነ ወይም የት እንደሆነ አናውቅም፡፡ አንድ
ብቻውን መሆኑን እንኳ በእርግጥ አናውቅም፡፡»

«እና?»

አንድ ነገር ብትሆንስ? ብትሞትስ?» አለችው

እኔ? ትቀልጂያለሽ? የኛ ቤተሰብ”ኮ እስኪጃጅ ካላረጀ
አይሞትም፡፡ የኔ ወንድ አያት፣ ያባቴ አባት፣ በዘጠና ሰባት
አመታቸው ብቻቸውን ሜካ መዲና ደርሰው ተመልስዋል። ታድያ
እንደተመለሱ የቤታችን ጣራ ዝናብ ማስገባት ሲጀምር ጊዜ፣
ሊያበጁት በመስሳል ወጡ። አበጅተውት ሲወርዱ ከመሰላል ወደቁና እግራቸው ወለም ብሏቸው ሁለት ሳምንት ሙሉ እንዲተኙ ሀኪም አዘዛቸው:: ታድያ ሁለት ሳምንት እንዴት ይለፍ? ውሽማቸው ናፈቀቻቸው። እና ገና አንድ ሳምንት ሳይተኙ፣ ሌሊት ጠፍተው ውሽማቸው ቤት ሄዱ። መኝታ ቤቷ በመስኮት እገባለሁ ሲሉ ባልየው በጥይት ልባቸውን አፈረሰላቸው:: ስንቀብራቸው የኔ አባት
«አይ አባባ! አይ አባባ! እኛ ያረጀነው እያለን አንተ ወጣት
ተቀጨህ!» ብሎ አለቀሰ፡»
ስንስቅ ሲልቪ በጆሮዬ እኔ ፍርሀት አቁነጠነጠኝ፡፡ ሽንቴ መጣ» ብላኝ ወደ ሽንት ቤት ሄደች
ባህራምን «የጀምሺድን የሚመስል ታሪክ ከየት አመጣህ?» አልኩት
( ከጀምሺድ ነዋ!» አለኝ «ስማኝ፡፡ እንድ ነገር አርግልኝ።
እዚያው ትደር፡፡ እና ነገ በሌሊት ተነስቶ ማርሰይ እንዲወስዳትና
ለአንድ ሳምንት ያህል ተደብቀው እንዲቆዩ ንገረው::

ቀፈፈኝ። በባህራም ትእዛዝ ኒኮልን ጀምሺድ ቤት ወስጄ ለጀምሺድ ላስረክበው ለአንድ ሳምንት ሙሉ! በጣም ቀፈፈኝ፡፡ ግን
ምን ማድረግ እችላለሁ?
አንተም ይህን ሰሞን ተጠንቀቅ። ማታ ብቻህን አትውጣ»
አለኝ። ሲጋራ አቀጣጠለ። እጁ ትንሽ ትንሽ ይንቀጠቀጣል። ፍርሀት አሳደረብኝ
ሲልቪ ተመለሰች። ደህና እደሩ ብያቸው ሄድኩ ኒኮልን ቤቷ እገኘኋት። ጀምሺድ ቤት ስንሄድ አጣነው፡፡ ቤቱ ቁልፍ ነው። ካፌ ዶርቢቴል ሄደን ጠያየቅን፡፡ ተካ፣ ጀምሺድና ሉልሰገድ ኒስ ሄደዋል አሉን። ኒኮልና እኔ የመጨረሻውን የማታ አቶቡስ ተሳፍረን ማርሰይ ወረድን፡፡ አንድ ወሻቃ ቦታ ሆቴል
አገኘን። ባለ ሁለት አልጋ ክፍል ተከራየን። ሁለታችንም ለባህራም
ሰግተናል። አንቅልፋችን እንደማይመጣ ግልጽ ነው:: አንድ ቆሻሻ ብጤ ጭር ያለ ካፌ ገብተን ከልቫዶስ እየጠጣን፣ እያወራን፣
እየተያየን ሳቃችን እየመጣ፤ እየተሳሳቅን፣ ድንገት ሳቃችንን
አቋርጠን በፀጥታ እየተያየን፣ ስንተያይ ኒኮል በሚያስጐመጅ አኳኋን እየቀላች፣ እየቀላች፣ እየጠጣን እያወራን፤ ከአንድ ሰእት በላይ አሳለፍን፡ ሰከርን፡፡ የተረፈንን ግማሽ ጠርሙስ ካልቫዶስ ይዘነው ሞቃት ሰማይ መሀል
ሆቴላችን ስንደርስ፤ እንዳንተያይ መብራቱን አጥፍተን፣
👍20
ልብሳችንን አውልቀን፣ ወደየአልጋችን ገባን።
እንቅልፍ ሊወስደኝ አልቻለም። ሰክሬ፤ ኒኮል እዚሁ ክፍል
ውስጥ ተጋድማ እንዴት እንቅልፍ ይውሰደኝ? አስብ ጀመር፡፡
ሉልሰገድ ቡና አይነት ቢራ እየጠጣ ስለሷ የነገረኝ ሁሉ አሁን
ይታየኝ ጀመር፡፡ በሮዝ ቀለም የተከበበች ወይን ጠጅ ጨረቃ ነጭዐየኒኮል ጡት። ወተት ጭኖቿ መሀል በወርቃማ ጭራሮ የተከበበ ነበልባል የኒኮል ብልት። ይሄ ሁሉ ከኔ አራት እርምጃ ብቻ ርቆ አልጋ ውስጥ ተጠቅሉ «ቅዱስ ብልግናዋን ተከናንቦ ይጠብቀኛል። አሁን ቀስ ብዬ ሄጄ አልጋዋ ውስጥ ብገባ እንደማታባርረኝ እርግጠኛ ነበርኩ። የውሀ አረንጓዴ አይኖቿ ብዙ ነገር ነግረውኝ ነበር ግን መሄድ አልቻልኩም። በጓደኝነት
አላምንም። ግን ባሀራም እዚያ በሞትና በህይወት መካከል
እየተራመደ፣ እኔ የሱን ሴት ብነካበት፤ ከዚያ በኋላ ራሴን እንዴት ለማክበር እችላለሁ? ግን ያችን የመሰለች ሴት እንዴት ልልቀቃትን ይህን ሁሉ ጊዜ ስመኛት ቆይቼ፣ ዛሬ እድል አጋጥሞኝ ሳገኛት እንዴት ልልቀቃት? ደሞስ ባህራም ለኔ ምኔ ነው?

በጭለማው የምኞት ፍም እየጠበሰኝ ስገላበጥ
«ተኝተሀል?» አለችኝ
«የለም»
«እኔ ፈራሁ፡፡ ብቻዬን አዚህ ፈራሁ»
«ነይ ወዲህ»
በጭለማው መጥታ አልጋዬ ውስጥ ገባች። ስስ ውስጥ ልብሷን አልፎ ሙቀቷ ነካኝ፡፡ በሀይል ተጠጋችኝና፤ ሰውነቷ ከላይ እስከ ታች
እየተንቀጠቀጠ
«ፈራሁ፡፡ እኔ ፈራሁ» አለች
«አይዞሽ ማንም አይነካሽም፡፡»
«ለራሴ አልፈራሁም'ኮ። አንተ እያለህ ምን ያስፈራኛል? እኔ
የፈራሁት ለሱ ነው፡፡»
«ለሱ ከፈራሽ ሞኝ ነሽ፡፡ ፋሺስቶቹን እንዴት እንዳበሳጫቸው
አታስታውሺም?»
«ቢሆንም ፈራሁ»
«አይዞሽ! ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም።
ገላዋ ልስልስ ያለ ነው፡፡ ከሴቶች ይበልጥ ሴትነት የሰፈረበት፣
የግብረ ስጋ መቅደስ ያቀፍኩ መሰለኝ፡፡ ትንፋሿ አንገቴ ላይ የፍትወት ነበልባል ያቀጣጥላል። ሁለታችንም ወጣት ነን፣ ሁለታችንም ሰከረናል፣ ሁለታችንም ምስጢራዊ ጭለማ ውስጥ ተደብቀናል
ሁለታችንም የምኞት ማእበል የሚያናውፀው ሙቀት ውስጥ ተጠቅልለናል፣ የሁለታችንም ደም ፈልቷል። እጄን ከትከሻዋ ወረድ
ባደርግና የማባብላት አስመስዬ ወገቧን ጥብቅ አድርጌ ባቅፈው.
እንደዚህ! ደስ ማለቱ! .. ቀስ አድርጌ በቸልታ እጄን ወደታች
ሰደድ ባደርገውና ዳሌዋ ላይ ባሰርፈውስ? .. እንደዚህ!
የቡታቲዋ ጠርዝ ከእጄ ስር ታወቀኝ፤ ከገላዋ ሙቀት የባሰ የሙታንቲዋ ጠርዝ በምኞት ወጠረኝ። እኔ ሳላውቀው እጄ ሙታንቲዋ ውስጥ እየገባ አፌ አፏን ጎረሰው፡፡ የት እንደሆንኩና ማን እንደሆንኩ ረሳሁ። በመርሳቴ ደመና ላይ የባህራም ፈገግታ ብልጭ አለ እጄን ከሙታንታዋ እያወጣሁና አፌን ከአፏ እያላቀቅኩ፤ በሹክሹክታ
«ደግ አይደለም» አልኳት
«አዎን ደግ አይደለም» አለችኝ እሷም በሹክሹክታ
«ግን በጣም በጣም እፈልግሻለሁ፡፡ አንቺም ፈልገሽኛል፣ አይደለም?»
«አዎን»
«ምን ይሻላል?»
«እኔ እንጃ»
«እኔ በበኩሌ ልተውሽ አልችልም»
ዝም
«ደሞ ልተውሽ አልፈልግም። አንቺን መተው ራስን መኮነን
ነው።»
ዝም
«ምን ይሻል ይመስልሻል?»
«እኔ እንጃ»
«ባስገድድሽስ?»
«ማስገደድ አያስፈልግህም»
«እስከ ዛሬ ድረስ ያንቺን ያህል ያማረችኝ ሴት አጋጥሞኝ
አያውቅም። ደሞ እስከ ዛሬ ድረስ ሴት አግኝቼ ለሌላ ሰው ስል
ትቼያት አላውቅም፡፡ ዛሬ ግን እንዴት ልበልሽ
«ይገባኛል፡፡ ምንም ማድረግ አያስፈልግህም»
«አሁን ሁለታችንም የማናምንበት ነገር ብናደርግ በኋላ
ይቆጨናል፡፡ ግን እንድትለዪኝ አልፈልግም፡፡ ምን ይሻላል?»
«እኔ እንጃ። መብራቱን አብርተን የተረፈንን ካልቫዶስ እየጠጣን ብናወራስ?»
በመብራቱ ስንጠጣ ስናወራ ምን ያህል እንደቆየን አላስታውስም፡፡ እንዲያውም ከዚያ በኋላ ምን እንዳደረግን ወይም ምን እንደተባባልን የማስታውስ አይመስለኝም፡፡ ብቻ፣ ከአንድ አመት በፊት እንዳየሁት ህልም ሆኖ ትዝ የሚለኝ አንድ ነገር አለ።
ጠርሙሱ ውስጥ የቀረውን መጠጥ ከጨለጥነው በኋሳ፤ ራሴን ደረቷ ላይ እያንተራስኩ
«ይሄ ጡት መያዣሽ ይቆረቁረኛል» አልኳት
«ቆይ ላውልቅልህ» ብላ አውልቃው እንደገና ራሴን ደረቷ ላይ አንተራሰችልኝ፡፡ «ጡትሽ እንደ ሞቃት ሰማይ ነው፤ ሰማዩ ላይ
በፅጌረዳ ብርሀን የተከበበች ወይን ጠጅ ጨረቃ አለች» አልኳት
«ውሸታም! መቼ አየኸው?» አለችኝ
«ማየት የለብኝም»
«አሁን ዝም ብለህ ተኛ» አለችኝ
ከዚያ ወዲያ ምንም ኣላስታውስም
በነጋታው፣ ከሰአት በኋላ ወደ ስምንት ሰኣት ላይ ስነቃ፣ ኒኮል
ደረቴን ተንተርሳ ተኝታለች። አፌ ውስጥ የፋንድያ ጣእም ተሰማኝ።
ኒኮልን ቀሰቀስኳት
«ደህና ነሽ?» አልኳት
ደህና»
አፈርኩ
«ሳናውቅ የማንፈልገውን ነገር ሰራን 'ንዴ?» አልኳት
«የለም»
ኒኮልን ምሳ አብልቼ፣ ኣንድ ልብወለድ መፅሀፍ ገዛሁላትና
ሆቴል ክፍላችን ውስጥ ትቼያት ወደ ኤክስ ሄድኩ። ሲልቪ ቤት
ስገባ፣ አልጋዋ ውስጥ ተጋድማ ሲጋራ እያጨሰች ሙዚቃ ትሰማለች። የአይኖቿ ቆዳ እንደ መጥቆር ብሎ፣ የታችኛው ቆዳ አብጧል
«ምን ሆነሻል?» አልኳት ሌሊቱን አልተኛሁም
«ለምን? ባህራም የት ነው? ንገሪኝ»
ቆይ በደምብ ልንገርህ። አንተ እንደ ሄድክ፣ ትንሽ ቆይተን እኔና ባህራም ከካፌው ወጣን፡፡ እያወራን፣ ባህራም ኣንዳንድ ጊዜ
ገልመጥ እያለ ወደ ኋላ ይመለከታል፡፡ እኔን እንዳልገላመጥ ከለከለኝ። ጭለማው አስፈራኝ፡ የመንገድ መብራቶቹ በቂ ብርሀን
አልሰጡኝም፡፡ «አይዞሽ ይታየኛል። ምንም ሊያረገን አይችልም።
አለኝ። “ማን እንደሆነ አውቀሀል እንዴ?» አልኩት፡፡ «አዎን።
አይዞሽ» «አንድ ብቻውን ነው?» «አዎን አይዞሽ። በጭራሽ አትስጊ።
ብቻ እኔ የምልሽን ያለማመንታት አድርጊ።» «እሺ» «አይዞሽ።»
«እንግዲህ መንገዱ እዚያች ሶስት ትልልቅ ጥዶች ያሉባት ቦታ
ሊደርስ ይጠመዘዝና፣ አንድ ሀምሳ ሜትር ሄዶ እንደገና ይጠመዘዝ
የለ? መጀመሪያውን መጠምዘዣ እንደዞርን ሩጪ!» አለና በላይኛው
ክንዱ እንጠልጥሎ በሀይል አስሮጠኝ፡፡ ሁለተኛውን መጠምዘዣ እንዳለፍን ቆምን፡፡ ከመንገዱ ገለል አርጎ አቆመኝና፣ እሱ ከኪሱ ቆብ አውጥቶ ራሱ ሳይ ደፍቶ፣ ኮቱን አውልቆ ለኔ ሰጥቶኝ፣ መንገዱ መሀል ላይ ቆመ:: ወደ መጣንበት መንገድ ይመለከታል፡፡ እኔም
እመለከት ጀመር። ለብዙ አመታት እንደዚህ ቆመን የቆየን
መሰለኝ። ሰውየው ድንገት ከመጠምዘዣው ብቅ አለ። ባህራም ወደዚያው (ማለት ሰውየው ወዳለበት በኩል) ይራመድ ጀመር፡፡
እያፏጨ! ሰውዬው እጁን ኪሱ እንደከተተ ወደ ባሀራም ይመጣል።
አጠገብ ላጠገብ ሲደርሱ ባህራም
“Bon Seir!" አለው
"Bon soir" na narpa
«ጐን ለጐን ደረሱ። ሊተላለፉ ሆነ። ባህራም እንደሚደንስ ሰው
ወደ ሰውዬው በኩል ዘለለና በእጁ ሆዱን ነካው መሰለኝ። በቂ
መብራት ስላልነበረ በቅጡ አልታየኝም፡፡ ሆዱን ከነካው በኋላ፣
አንዲት ሰከንድ እንኳ ገና ሳታልፍ ዘሎ የሰውየውን ማጅራት
በሌላው እጁ መታው። ሰውዬው ወደፊት ታጠፈ። ወደቀ። ባህራም
እየጐተተ ከመንገዱ ወደ ዳር ወሰደው። ሁለቱንም ጨለማ ዋጣቸው እዚያው እንደቆምኩ ቀረሁ፡፡ ጭለማው ከቦኛል። አሁን
👍20👎2🤩1
ያየሁት አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሲጎዳው ነበር? በጭራሽ
አይመስልም፡፡ ሁለት ቅርፆች፣ ከልዩ ልዩ አቅጣጫ መጥተው
ተነካኩ፣ አንዱ ወደቀ፣ ያልወደቀው የወደቀውን እየጎተተ ወደ
ጭለማው አስገባው። በቃ፡፡
«አሁንም ለብዙ አመታት ብቻዬን እዚያ ጭለማ ውስጥ የቆምኩ
መሰለኝ
«አትፍሪ አይዞሽ» አለ ከአጠገቤ። ነጠርኩ። «አይዞሽ እኔ ነኝ»
አለኝ፡፡ ባሀራም ነው። ለምን እንደሆን እንጃ፣ በሄደበት መንገድ
ይመለሳል ብዬ ስጠብቅ ነበር፡፡ እሱ ግን በጭለማው በኩል
መጥቷል። ኮቱን ከኔ ወስዶ ለበሰና ቆቡን አውልቆ ኪሱ ከተተ።
በጭለማው ትንሽ ከተራመድን በኋላ ወደ ባቡር መንገድ ገባን፡፡
እግሬ ላይ ብርድ ተሰማኝ። ለካ ሳይታወቀኝ በፍርሀት ሽንቴ
አምልጦኝ ኖሯል
«እዚህ (ሲልቪ ቤት) ከደረስን በኋላ «ገደልከው?» አልኩት
የለም» አለኝ። ግን እንደገደለው እርግጠኛ ነኝ። በጩቤ ነው
የገደለው፡፡ እና ሌሊቱን ልተኛ አልቻልኩም።»
ሲልቪ ዝም አለች። እኔም ዝም አልኩ
«ፓሪስን በፀደይ አይተሀት ታውቃለህ?» አለችኝ
«የለም»
«በጣም ውብ ናት። ለአንድ ሳምንት ብንሄድ ምን
ይመስልሀል?»
«መቼ?»
«ዛሬ»
ዛሬ አልችልም፡፡ ምእራፍ ግማሽ ላይ ነኝ፡፡ ብትፈልጊ ከአንድ
ሳምንት በኋላ አንሂድ።
ባኞሽ ሙቅ ውሀ አለው?»
ገላዬን ታጥቤ ከባኞው ልወጣ ስል የወንድ ድምፅ ከሲልቪ ጋር
ሲነጋገር ሰማሁ። ልብሴን ለባብሼ ወደ መኝታዋ ስገባ፣ ባህራም
አልጋዋ ላይ ቁጭ ብሎ ሳንድዊች እየበላ ቀይ ወይን ይጠጣል። ሰው
የገደለ አይመስልም፡፡ ግን ሰው የገደለ ሰው ምን እንደሚመስል አላውቅም ኒኮል የት እንዳለች ነገርኩት ሲልቪ ተራዋን ልትጣጠብ ባኞ ቤት ገባች
ባህራም «ይቅርታ አርግልኝ፡፡ አንተ፣ ሲልቪ፣ ኒኮል ለአንድ
ሁለት ሳምንት ከኤክስ መጥፋት አለባችሁ። ኒኮልን ወደ ቤቶቿ
ወይም ወደ ሌላ ቦታ እልካታለሁ፡፡ አንተና ሲልቪ ተስማምታችሁ
ወደ አንድ ቦታ ብትጠፉ ጥሩ ነው። አየህ፣ ፋሺስቶቹ የበሰለ
አስተሳሰብ የላቸውም፡፡ ስለዚህ እኔን መጉዳት ሲያቅታቸው፣ በንዴት እናንተን ይጎዱዋችኋል። ስለዚህ ንዴታቸው ትንሽ እስኪበርድላቸው ከኤክስ ራቁ። እባካችሁን» አለኝ
በሹክሹክታ «ገደልከው?» አልኩት
ራሱን በመነቅነቅ «አዎን» አለኝ
«የመጀመሪያ ጊዜህ ነው ሰው ስትገድል?»
«ሶስተኛ ጊዜዬ ነው:: አንዱን በይሩት፣ ሌላውን ባግዳድ»
ይነግረኝ ይሆን? በማለት አየሁት። ዝም አለ፡፡ ዝም ሲል
የኢራንን ሻህ ይመስላል፡፡ እኔም ዝም አልኩት
«ፂምህን ብትላጭ ጥሩ ነው። ለመጠንቀቅ ያህል» አለኝ
«እሺ» አልኩት.....

💫ይቀጥላል💫
👍71
#አትተይኝ

እንደ ደራሽ ውሃ በፍጥነት ይሄዳል
እንዳለፈ ክረምት አይቆይም ይረሳል
ወቅት ሁሉ ይነጉዳል ሁሉም ነገር ያልፋል
በጠብ ያኳረፉን ደቂቃዎች ሁሉ
“እንዴት ለምን ?” በሚል የጥያቄ በትር
ደስተኛ ልቦች መትተው የሚገድሉ
ጊዚያቶችን እረሺ ውስጥሽ አይሣሉ
ሁሉንም ተያቸው እኛን አይወክሉ
በመጡበት መንገድ ዞረው ይሄዳሉ

እኔን ግን አትተይኝ...
ዝናብ ከሌለበት ከዛ ከሩቅ ሀገር
እኔ ላንች ፍቅር
ካለሽበት ድረስ ዝናብ እጠራለሁ
በዝናቡ ፈንታም
ስጦታ እንዲሆንሽ እንቁ አስዘንባለሁ
የእንቁው ጠብታ
ወርቃማ ብርሃን እንዲሆን አውቃለሁ
አትተይኝ አትተይኝ
እስከለተ ሞቴ
መሬቱን ቆፍሬ ጥልቁ መሃል ድረስ
አንችን ለመሸፈን ፍቅራችን ለማንገሥ
ሕጉ ንጹህ ፍቅር
ንጉሡ ውብ ፍቅር
አንቺ ደሞ ንግሥት የምትሆኝበት
አንጽልሻለሁ አዲስ ቤተ መንግሥት
ስሚኝ ብቻ ፍቅሬ
ማንም የማይገባው ልሳንን ፈጥሬ
በአዲስ መወድስ በአዲስ ዝማሬ
ሁሉን እነግራለሁ
ከሁለት ግዜ በላይ ስለተሳሳሙ
የሁለት ፍቅረኛሞች
ሁለት ንጹህ ልቦች
መሳጭ ውብ ታሪኮች
አወራልሻለሁ...
አንቺን ብሎ ወጥቶ
በዛው እንደቀረ ፍቅር ሳይሰምርለት
ነፍስ ይማር እያልኩኝ የንጉሡን ሕይወት
አወራልሻለሁ በቀን ሆነ በሌት
አትተይኝ አትተይኝ
እንዲህ ያለ ነገር መቸ ታይቶ ያውቃል ?
እሳተ ገሞራው ሲባል ጥንት አርጅቷል
ስላንቺ ከሆነ
እንደ አዲስ ተወልዶ እሳቱን ይተፋል
የመከነው መሬት የኖረው ሲቃጠል
ስላንቺ ከሆነ
ከመኸር የበዛ ውብ ስንዴ ያፈራል
ያመሻሽ ጨለማ የጀንበሯ ቅላት
የሰማይ ወጋገን የደመናው ጥለት
ስላንቺ ከሆነ
ይጋቡ የለም ወይ በመጥለቅያው ሰዓት
አትተይኝ
ተሸሽጌ ተደብቄ ከዚች ዓለም
ስትደንሺ አይሻለሁ አላለቅስም
በፈገግታሽ እስቃለሁ አላለቅስም
ስትዘፍኝም እሰማለሁ
ፈቀጅልኝ
ያንቺን ፍቃድ እሽዋለሁ
አትተይኝ አትተይኝ
እየተከተልኩሽ
ያጃቢሽን ጥላ የጥጃሽን ጥላ
የእጆችሽን ጥላ
የጥላሽን ጥላ
ያን ሁሉ ለመሆን
እየተከተልኩሽ እየተከተልኩኝ
አትተይኝ አትተይኝ

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍18😱1