አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አንዲት_መርፌ_ስንቱን_ቀዳዳ_ትስፋው


#ሶስት(መጨረሻ)


#በአሌክስ_አብርሃም



እኔ ይሄን ስድብ በፀጋ ተቀብዬ እግር ማየቴን መቼም አላቆምም። የሴት ልጅ እግር የውበት ጥጌ
ነው። ለሰርጌ ቀን አይበለውና እግሯ የሚያምር ግን አንገቷ የተቆረጠ ሴት ጎኔ አምጥተው ሚስትህ ናት ቢሉኝ፣ “በደስታ ይሁን በሐዘን…” ብዬ ከመፈረም አልመለስም። እንዲህ የምንሰፈሰፍለት፣የምማልልለት፣ የምልከሰከስለት፣ ልክስክስክስ የምልለት የሴት ልጅ እግር እንደኔ እንደኔ በሁለት ትላልቅ ክፍል ይከፈላል፣

1ኛ የዓለም ሴቶች እግር ሁሉ በአጠቃላይ ማለት ነው።
2ኛ. የዙቤይዳ እግር ! በቃ እኔን የሚያልከሰክሰኝ፣ በምኞት አፌን የሚያስከፍተኝ፣ ሳመው ሳመው
የሚለኝ ይሄ ሁለተኛው እግር ነው። እናም ድንገት ከቀሚሷ ወጣ ብሎ ፍም የመሰለ ተረከዟ፣የሕፃን
ልጅ ጣት የመሳሰሉ ጣቶቿ፣ ውሃ የመሰሉ (መስተዋትም ይመስሉኛል) ጥፍሮቿ፣ ምንም ቀለም ሳይቀቡ ደግሞ የቁርጭምጭሚት አጥንቶቿ ብይ ብይ መስለው ጠቆር ያለው አረቢያን መጅሊስ ላይ
እንደ እሳት ሲንቀለቀሉ ሳይ ቀልቤን ሳትኩ። ዜድዬ እኮ ለእኔ ሰርክ አዲስ ነች። አይቼ አልጠግባትም ።ተንደርድሬ ሄጄ እግሮቿን ብስማቸው ደስታዬ፤ የሆነ ነገር ሂድ ሂድ እያለ ይገፋኛል።

እ.? ”አሉኝ የዜድ አባት

“እ?…” አልኳቸው እኔም፣ የተናገሩትን ባለመስማቴ አፍሬም ደንግጬም ነበር፤(ታዲያ ምን ላድርግ እኔ የብቸኝነት፣ የክህደት፣ የውሸት፣ የማስመሰል፣ የጥቅም ማሳደድ እና የዝሙት ቆፈን በሚያቆራምደው ከተማ፣ የፍቅር እሳታቸውን ወልደው እሳት ውስጥ ቆሜ እንዴት ያሉትን ልስማ…? )

“እናቴዋ…ቀልቡን ወሰድ ያደርገዋል አንዳንዴ እንደ አብዱ” አሉ የዜድ እናት (ጎበዝ ኧረ ይሄ አብዱ ማነው…?) ዙቤይዳ ቡፍ ብላ ሳቀች። እናቷም ሰውነታቸው እስኪረግፍ ሳቁ። አባቷግን ኮስተር እንዳሉ ፂማቸውን በመዳፋቸው እየዳሰሱ ዝም ብለው ቆዩ። በዝምታው ውስጥ ድምፃቸው የሚያማምር ሕፃናት ከሩቅ በስርቅርቅ ድምፃቸው ቁርዓን ሲቀሩ ይሰማል። ለምን እንደሆነ ባላውቅም የሕፃናቱ ድምፅ፣ የአባቷ ዝምታ፣ የዙቤይዳ አቀርቅራ በክሪሟ መጫወት ተዳምሮ ዜድን ላጣት ከዜድ ጋር
ልንለያይ ሴኮንዶች የቀሩ መሰለኝ። ምፅአት መሰለኝ። ድንገት ነው በቃ እንደዚህ የተሰማኝ። እንባዬ
ሁሉ ይታገለኝ ጀመረ እልህ ውስጤ ተንተከተከ።

የዜድዬ እናት ድንገት ዝምታውን ሰብረው፣ “ዘምዘም…” ብለው ተጣሩ ።

“አቤትእማማ ! ብላ የዙቤይዳ እህት ከውስጠኛው ክፍል የግቢ በር የሚያክለውን በጌጥ የተሽቆጠቆጠ ባለሁለት ተከፋች የጣውላ በር ከፍታ ገባች። ዘምዘም ቁመቷ የትየለሌ ነው። በዛ ቁመት ላይ ሙልት ያለ ሰውነቷ ተጨምሮበት ክብድ የሚል ነገር አላት። ሳሎኑ ውስጥ መጥታ ስትቆም የሆነ ረዥም ማማ
ነገር የቆመ ነበር የሚመስለው፣ አንጋጥጬ ሽቅብ ተመለከትኳት። ኮስተር አለችብኝ። አሁን የመረረው
ባላጋራ መጣ አልኩ በሆዴ። በተቻለኝ መጠን ዘምዘምን ላለማየት ወደ ዙቤይዳ ዞርኩ፤ ፈገግ አለችልኝ ወደ ዘምዘም በድፍረት ዞርኩ ቡትሌ አክላ ታየችኝ፡፡አስማተኛው የዜድ ፈገግታ እንኳን አንዲት ሴት ኪሊማንጃሮን በፊቴ ጠጠር ያሳክለዋል። ከፍቅር የሚገዝፍ ነገር የለማ !

“ምሳ አልደረሰም እንዴ? እንግዳ ጠርታችሁ በራብ ልትገሉት ነው እንዴ” አሉ እማማ። ዘምዘም
ክፉ ደግ ሳትናገር ወደ ውስጥ ተመልሳ ገባች። እኛም በዝምታችን እንደፀናን በሩ ተበረገደና የምግብ መፈክር ያነገቱ ሰላማዊ ሰልፈኞች ወደ ሳሎኑ ተግተልትለው ገቡ አራት እህትና አንዲት ሠራተኛ።
ዘሐራም ከሰልፈኞቹ አንዷ ነበረች። የያዘችውን ሰሐን በትኩረት ተመለከትኩት። “እሷ ከያዘችው ሰሐን አልበላም” አልኩ ለራሴ። ሠራተኛዋ ምንጣፉ መሐል ላይ አንድ ሰፊ ክብ ላስቲክ አነጠፈች። ከዛ የምግብ ዓይነት በሚያማምር ሰፋፊ የሸክላ ሰሀኖች ተደረደሩ። ላስቲኩ ላይ ዙሪያውን የተደረደሩትን
ነጫጭ ሰሀኖች በክብ ተደርድረው ስመለከት በፀሐይ ዙሪያ ምህዋራቸውን ተከትለው የሚሽከረከሩ ፕላኔቶች ሥዕል ትዝ አለኝ።

ሰልፈኞቹ ወጡና ሌላ ሰሐን ይዘው ተመለሱ(ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ጉድ)። ብስኩቱ፣ ጣፋጩ፣ ስሙን
የማላውቀው ነገር ሁሉ በዓይነት ተደረደረ። አንድ ነገር ውስጤን በሐዘን ሞላው። ዙቤይዳ ሱቅ ፀሐይ ልንሞቅ ስንቀመጥ የምጋብዛትን ቦንቦሊኖ ለመብላት ቁርስ ሳትበላ ትመጣ እንደነበር አስታወስኩ።እውነቴን ነው ይሄን ማዕድ ስለ ፍቅር ረግጣ፣ “አብርሽ ኧረ ርቦኛል ቦንቦሊኖ ግዛልኝ…” ትላለች።ፀሐያችንን እየሞቅን ፊት ለፊታችን ካለች ሻይ ቤት ቦንቦሊኖ አዝዘን እየተጎራረስን በሻይ እንበላለን።እንደውም አንድ ጊዜ አረፋ በዓል ሆኖ የነዙቤይዳ ሱቅ ዝግ ነበር፤ እኔ ተቀጥሬ የምሠራበት ሱቅ ደግሞ
አልተዘጋም፤ ዙቤይዳ ከቤቷ ሹልክ ብላ መጥታ በበዓሉ ቀን እዛች ሻይ ቤት ሄድንና ቦንቦሊኖ በሻይ በላን። ለረመዳን ሙሉ ቀን ዙቤይዳ ስለማትበላ እኔም ሳልበላ የምውልባቸው ቀናት ይበዙ ነበር።

የዙቤይዳ እናት “በልና ወዲህ፣ ዙቤይዳ ነቅነቅ በይ እንጂ መታጠቢያ ቤቱን አሳይው” አሉ። ዙቤይዳ እየመራች በሚያምረው በር አልፋ ወደ መታጠቢያው ወሰደችኝ። አንዳንድ ነገሮች አሉ በአክብሮት ሲደረጉ ስድብ የሚሆኑ። የነዙቤይዳ መታጠቢያ ቤት ስፋት የአባቴን መኝታ ቤት ያክላል። የመታጠቢያ
ሸክላዎቹ ንጣት፣ የቤቱ አስደሳች ጠረን አፍ አውጥቶ የሰደበኝ መሰለኝ፣ “አንተ አመዳም ደሀ ልካችንን እየው…" የሚለኝ መሰለኝ። ዙቤይዳ ፈዝዤ መቆሜን ስታይ “ታጠብ…” አለችኝና ዞር ብላ ወደ ኋላዋ
ተመልክታ ማንም አለመኖሩን ካረጋገጠች በኋላ ጉንጬን ሳመችኝ። ከንፈሯ ይሞቃል። የሆነ ርጥበቱ ጉንጩ ላይ የቀረ መሰለኝ። ስትስመኝ ድንጋጤው ይሁን ንዝረቱ አስበረገገኝ። “ብቻችንን ከሆንን አያስችለኝም ቶሎ ውጣ” አለችኝ እየሳቀች። እና ራሷ እጇን መታጠብ ጀመረች። በመስተዋቱ ውስጥ ዓይኖቿ አፍጥጠውብኝ ነበር። የመታጠቢያ ቤቱ ውበት ውበቷን አጉልቶት ነው መሰል፤ ዙቤይዳ
በጣም አማረችብኝ። ለዚህች ልጅማ አንድ ሰውና አንድ ጥይት እስኪቀር ታጥበን ወጣን።

ወደ ሳሎን ስንመለስ የዙቤይዳ እናት ኖር.. አሉኝ፣ አባቷ ግን አሁንም ፂማቸውን እያሻሹ ዝም
ብለው ተቀምጠዋል። እንደውም ከቅድሙ በላይ ፊታቸው ተቀያይሮ ቁጣ ነበር ከግንባራቸው
የሚስፈነጠረው። ወደ መታጠቢያ ቤቱ እንደገባን የዜድ እናት ጋር የሆነ ነገር እንደተነጋገሩ ገመትኩ።
እንዴት ይጨንቃሉ። ዘሐራ ጭልፉ ይዛ ስትገባ፣ እኛ ታጥበን ስንወጣ አንድ ሆነ። እንደው ይህች ልጅ
ደንቃራ ነገር ናት ልበል። በግርምት እግሬን ተመለከተችኝ። ዓይኗን ተከትዬ ወደ እግሬ ስመለከት ወደ
መታጠቢያ ቤት ስገባ ያደረግኩት የዙቤይዳን ሰንደል ጫማ ነበር። ያውም ብዙ ጊዜ ኡዱ ስታደርግ
የምትጫማውን። እሾህ ! ዓይኗ የማያየው ነገር የለም። እኔ ራሴ ጫማ ላድርግ፣ በእግሬ ልሁን ትዝ
ያለኝ አሁን ነው።

አንዲት ትንሽ ትራስ ነገር ከተሰደረው ምግብ ፊት ዙቤይዳ አመቻቸችልኝና ተቀመጥኩ። አባቷ
ከምግቡ ክምር ወዲያ፣ እኔ ወዲህ። ምግብን ድንበር አድርገን የተፋጠጥን ጠላቶች። (አንቱ ወዲያ ማዶ፣ እኔ ወዲህ ማዶ፣ አንገናኝም ወይ ተራራው ተንዶ..) መብላት አልቻልኩም። አባቷ ዓይኔን ላለማየት ሲሸሹ ምግቡ ዘጋኝ። በቤታቸው ምግብ አቅርበው ፊታቸውን ሲያጠቁሩብኝ ለልመና የመጣሁ እስኪመስለኝ አፈርኩ ተሳቀቅኩ። ዙቤይዳ ገብቷታል። ምንም ነገር ሳትፈራ ሰሀኔ ላይ እንጀራና ንጣቱ
👍19👏2