አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በሕይወት_አንድ_ጥግ

ትላንትና እሁድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውየ መጣና በሩን አንኳኳ…… እኔ ፣መአዛና የመአዛ እናት ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር ! ሮዛ ጎረቤቴ አብሮ አደጌ ናት ! አስቴር ደግሞ እናቷ . . .ለእኔም እናቴ ማለት ነች ኧረ …የእኔና የሮዛ ፍቅር ለብቻው ነው ከህፃንነታችን ጀምሮ ንፁህ የሆነ ምንም ፆታዊ ክጃሎት ውል ያላለበት ፍቅር እንዳለን አገር መንደሩ ምስክር ነው … እህቴ !!
ሮዚ ዩኒቨርስቲ ቆይታ ለእረፍት መምጣቷ ነበር ፡፡ የሚገረመው እናቴና የሮዛ እናት አስቴር የመረረ ጥል ያላቸው ኩርፈኞች ናቸው ! ግን እኔም እነሮዛ ቤት ሮዛም እኛ ቤት ልጆች ነን ! ስለእናቴ አስቴር ፊት ከተነሳ …‹‹ውይ ውይ የሷን ነገር አታንሳብኝ ጋኔል ….ምን ያረጋል እንዳንተ እይነት መለአክ ወለደች ››ትለኛለች እናቴን ለእኔ ታማልኛለች ! ‹‹ ቱ ሰው አይደለችምኮ !›› ትላታለች ! በእናቴ የመጣብኝን ሰው ይቅር ብየ አላውቅም አስቱ ግን ስትረግማት እንኳን ምርቃት የሚመስለኝ ለምን እንደሆነ እንጃ !
እሮዛ እኛ ቤት ስትመጣ ደግሞ እናቴ በተራዋ ለሮዛ ስለእናቷ ክፋት ጋኔልነት ትነግራታለች ‹‹ እናትሽ ….ምን እናት ናት እች እቴ …የሰይጣን ቁራጭ ከጥላዋ የተጣላች …እኔ ለሷ እንዲህ አልነበርኩም ….›› እያለች
እኔ እና ሮዚ እናቶቻችንን ረስተን እብድ ያለ ጓደኝነታችንን ቀጥለን አለን ! የሮዚ አባት በሂወት የሉም ! ‹‹ችግር የለም አባባን እንካፈላለን ›› ትላለች አንዳንድ ቀን ስንቃለድ አባባ የምትለው የእኔን አባት ነው ! ‹‹እናቶቻችን አባባን እንዳይካፈሉ ብቻ ›› እላታለሁ ‹‹ባለጌ ስድ ›› ብላ ትግል ትጀምረኛለች ቀይ ፊቷ በሃፍረት ይቀላል ! ሮዛ ቆንጆ ናት ግን ምኗ ነው ቆንጆ ቢባል አላውቅም እንዲሁ ጠቅለል አድርገው ሲመለከቷት በጣም ቆንጆ የምታሳሳ ኑሮ ምችት ያላት ልጅ ነች ! አንዳንዴ ሰውን ስንወድ ፍቅራችን የወደድነው ሰው ላይ ጎዶሎውን ሞልቶ ያሳየናል መሰል ሮዛ ጉድለት የላትም ለእኔ ! አዎ #ፍቅር አፍንጫ ፀጉር አይን ቁመት ጥርስ ከንፈር ሳይሆን አይቀርም ! ለነገሩ የሚጠይቃት ጎረምሳ ብዛትም ለሳቢነቷ ምስክር ነው !
ሮዛን የጠየቁትን ጎረምሶች እኔ እና ሮዚ የእለት ውሎ መመዝገቢያችን ላይ እንመዘግብ ነበር ! የሚገርመው ‹‹ዳይሪያችን›› አንድ ነበረች ሁለታችንም ውሏችንን ምንመዘግብባት ! ለሮዛ የሚላክ የፍቅር ደብዳቤ አብረን ነው የምናነበው እኔም ለሴት የምልከው አብረን ፅፈን እናውቃለን ! ታዲያ ሮዛ ብትሞት ለፍቅር አትሸነፍም ትምህርቷ ላይ አትደራደርም . . . ልቧ የገባም ወንድ የለም ‹‹ወንዶች ጅል ይመስሉኛል›› ትላለች አባቷ እናቷ ላይ ያደረሰው በደል ሁሉ (ነብሱን ይማረውና ) መጥፎ ጠባሳ ጥሎባታል ! አባቷ አይጠጣ አያጨስ ግን እናቷን መቀጠቀጥ ሱስ የሆነበት ሰው ነበር ጥርሷን ሁሉ አውልቆት ወርቅ ጥርስ አስተክሎላታል ! ሮዛ ልብ ውስጥ የነበረውን ወንድን የመሻት ተፈጥሯዊ ስሜትም ነቅሎ ባዶውን ትቶታል !
(አሁንም ነብሱን ይማረውና ግን የሚምረው አይመስለኝም )
እና ……ትላንትና እሁድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውየ መጣና በሩን አንኳኳ…… እኔ ፣መአዛና የመአዛ እናት ቡና ተፈልቶ ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር ! እንዳጋጣሚ ለበሩ የምቀርበው እኔ ስለነበርኩ ተነስቼ በሩን ከፈትኩ ! ከተወለደ ጀምሮ ዛሬ ገና የዘነጠ የሚመስል ሙሉ ግራጫ ልብስ የለበሰ ቀጫጫና ረዥም ሰውየ በሩ ላይ እየተሸቆጠቆጠ ቁሟል ! ሰውየው ሙሉ ልብስ ቢለብስም ለምን እንደሆነ እንጃ ሙሉ ልብስ የለበሰ አይመስልም . . . መቼም ሕይወት በሰወች አይን ፊት ስታጎለህ እንኳን ሙሉ ልብስ ሙሉ ብርጌድ አሰልፈህ ብትመጣ ግርማ ሞገስ የሚባል ነገር አይጠጋህም ! ቅልል ትላለህ ! እማማ ሩቅያ እንደሚሉት ‹‹ቀድረ ቀላል ›› ትሆናለህ !
ሰላም አልኩት … እየተሸቆጠቆጠና ዳማከሴ እንደሚያሽ ሰው እጆቹን አርሰ በእርስ እያፋተገ ሰላምታየን ከወገቡ ጎብጦ መለሰልኝ ! ከርዝመቱ እና ከእንቅስቃሴው ፍጥነት የተነሳ ለሰላምታ ከወገቡ ሲታጠፍ ከላይ ተምዘግዝጎ የመጣ የሆነ ወገቡ ላይ ተሰብሮ የሚወድቅ ባህር ዛፍ ነበር የሚመስለው !
‹‹ይ….ሄ የነሮዛ ቤት ነው አይደል …›› አለና እራሱ መልሱን መለሰው ‹‹አዎ ነው አውቀዋለሁ ›› አነጋገሩ የሚርበተበትና ከአፉ የሚወጡት ቃላት በጠባብ በር እንደሚወጣ ብዙ ህዝብ የሚገፋፉ የሚተሸሹ ይመስላሉ ዝም ብየ ስመለከተው ‹‹ እ. … የሮዛ እናት ይኖራሉ ወይም አባቷ ›› አለና መልሶ ለራሱ ‹‹ አውቃለሁ አባቷ እንኳን በህይወት የሉም …ግን እናቷ . . . ›› ተርበተበተ
‹‹እናቷ አለች ›› አልኩት
‹‹ልግባ ? ›› ሲል ገነት በር ላይ የቆምኩ መልአክ የሆንኩ እስኪመስለኝ ወደቤቱ ውስጥ በጉጉት አይኖቹን ልኮ ለማየት እየሞከረ ለመነኝ (ምን የተቀመጠ መስሎት ይሆን እነዲህ የጓጓው )
‹‹ግባ ›› ብየ በሩን ለቀኩለት ገባ !! አረማመዱ የሆነ የሚጮህ አይነት ነው የሚራመድ ሳይሆን በአንድ እግሩ ብቻ የሚዘል አይነት ላይ ታች ያረገርጋል …. እድሜው ሰላሰ አምስት ቢሆን ነው ! የሮዛን እናት ( አስቱ ነው የምንላት) በሁለት እጁ ሰላም ብሎ ወደሮዛ ዞረ እርሷንም በሁለት እጁ ሰላም አላት ! ሲመለስ የእኔን እግር ረገጠና ተንገዳግዶ ጠረንጴዛ ጫፍ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ባዶ ስኒ ከነበለው ! ስኒው ስር ቀርቶ የነበረው የረጋ የቡና ዝቃጭ ምንጣፉ ላይ ጥቁር ደብ መስሎ ተረጨ ! (ይሄ ሰው መርዶ ይዞ ነው እንዴ የመጣው ምን ያደናብረዋል )
ከ አስቱ ፊት ለፊት ተቀመጠ ! ሁላችንም ምን እንደሚል ለመስማት አይን አይኑን እናየው ጀመረ ‹‹ እ …ሰላም ነዎት ታዲያ እትየ ….አስቴር ›› አለ
‹‹እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ ›› ፊቷ ላይ ‹‹የት ይሆን የሚያውቀኝ ›› የሚል ግርታ ይታያል በፈገግታ ልትሸፍነው ብትሞክርም አልተሳካላት !
‹‹ልጆች ሰላም ናቸው ….ማለቴ ልጅዎት …አዎ አንድ ልጅ ብቻ ነች ያለችዎ ›› አለ ወደሮዛ አየት አድርጎ ያጠናውን ነበር የሚናገረው ያስታውቃል …..ፊቱን አልቦት ነው መሰል በመዳፉ አንዴ ሞዠቀው እና መዳፉን አየት አድርጎ በኮቱ እጅጌ እንደገና ግንባሩን ጠረገው !
‹‹ደህና ናት ›› አለች አስቱ እናም ኮስተር ብላ አየችኝ ! ትካሻየን በቀስታ ወደላይ ሰበኩት … እርሷ ያየችኝ ‹‹ማነው›› ማለቷ ሲሆን እኔም በትካሻየ ምላስ ‹‹እኔጃ ›› አልኳት ለትንሽ ደይቃ እንግዳውም አቀርቅሮ አኛም እንግዳው ላይ አፍጥጠን እንደቆየን እንግዳው ተናገረ
‹‹አንተ አብርሃም ነህ …እዚህ ጎረቤት ያለከው ልጅ አይደለም እንዴ ›› አለኝ
‹‹አ . . .አዎ ››
‹‹ያው ለሮዛ ወንድሟ ማለት ነህ …ማዘርም ጋር ትቀራረባለህ ያው ልጃቸው ማለት እኮ ነህ ››
‹‹አዎ ያው ልጀ ማለት ነው ›› አለችው አስቱ
‹‹ጥሩ ያው የቤተሰብ ጉዳይ ስለምናወራ ላረጋግጥ ብየ ነው ›› አለ ወደአስቱ በፈገግታ እየተመለከተ . . .ፈገግታው ይጨንቃል ከንፈሮቹ ወይ በደንብ አይከፈቱ ወይ አይገጠሙ ሄድ መለስ እያሉ ይንቀጠቀጣሉ ! በማጭድ የተጋጠጠ የሚመስል ፂሙ ቅሪቱን ጉንጩ ላይ ዘርቶት በሽተኛ አስመስሎታል … ጥላሸት የተዘራበት አጥንታም ጉንጭ ! ደግሞ እኮ ሲያረጉ አይቶ ‹ኦ › ቅርፅ ! አፉ በፂሙ ተከቦ ሲታይ በኮሸሽላ ዙሪያውን የታጠረ የደረቀ የውሃ ጉድጓድ ይመስላል ! ወቸ ጉድ ምን ሊል ይሆን . . .ጭንቀት ገደለኝ
‹‹ የመጣሁት ሌላ የሚመጣልኝ ሰው ስለሌለ ነው .ላቀው እባላለሁ .›› አለና ድንገት ቁሞ አስቱን ሰላም አላት እኔንም ሮዛን ግን ረሳን ….‹‹ እ….ያው የመጣሁት መጥቼ መናገር ስላለብኝ እና
👍3🔥1
#በሕይወት_አንድ_ጥግ


#በአሌክስ_አብርሃም


ትላንትና እሑድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውዬ መጣና በሩን አንኳኳ። እኔ፣ ሮዛና የሮዛ እናት ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር። ሮዛ አብሮ አደግ ጎረቤቴ ናት። አስቴር ደግሞ እናቷ። ለእኔም እናቴ ማለት ነች
ኧረ። የእኔና የሮዛ ፍቅር ለብቻው ነው። ከሕፃንነታችን ጀምሮ ንጹህ የሆነ፣ ምንም ፆታዊ ክጃሎት ውል
ያላለበት ፍቅር እንዳለን አገር መንደሩ ምስክር ነው። እህቴ ሮዚ ነው የምላት ። ታዲያ ዩኒቨርስቲ ቆይታ ለእረፍት መምጣቷ ነበር። የሚገረመው እናቴና የሮዛ እናት አስቴር የመረረ ጥል ያላቸው ኩርፈኞች ናቸው። ግን እኔም የእነሮዛ ቤት፣ ሮዛም የእኛ ቤት ልጆች ነን። ስለእናቴ አስቴር ፊት ከተነሳ፣ “ውይ! ውይ! የሷን ነገር አታንሳብኝ፤ ጋኔል…! ምን ያረጋል እንዳንተ ዓይነት መልአክ ወለደች፤” ትለኛለች።
እናቴን ለእኔ ታማልኛለች። “ቱ…! ሰው አይደለችምኮ!” ትላታለች ደጋግማ። በእናቴ የመጣብኝን ሰው ይቅር ብዬ አላውቅም። አስቱ ግን ስትረግማት እንኳን ምርቃት የሚመስለኝ ለምን እንደሆነ እንጃ።

ሮዛ እኛ ቤት ስትመጣ ደግሞ እናቴ በተራዋ ለሮዛ ስለእናቷ ክፋት፣ ጋኔልነት ትነግራታለች። “እናትሽ ምን እናት ናት! እች እቴ… የሰይጣን ቁራጭ! ከጥላዋ የተጣላች! ..እኔ ለሷ እንዲህ አልነበርኩም….”እያለችም ። እኔና ሮዚ እናቶቻችንን ረስተን እብድ ያለ ጓደኝነታችንን ቀጥለን አለን። የሮዚ አባት በሕይወት የሉም። ችግር የለም አባባን እንካፈላለን” ትላለች አንዳንድ ቀን ስንቃለድ። አባባ የምትለው የእኔን አባት ነው። እናቶቻችን አባባን እንዳይካፈሉ ብቻ” እላታለሁ ለሮዚ፤ “ባለጌ.! ስድ!” ብላ ትግል ትጀምረኛለች። ቀይ ፊቷ በሐፍረት ይቀላል።

ሮዛ ቆንጆ ናት፤ ግን ምኗ ነው ቆንጆ ቢባል አላውቅም። እንዲሁ ጠቅለል አድርገው ሲመለከቷት
በጣም ቆንጆ፣ የምታሳሳ፣ ኑሮ ምችት ያላት ልጅ ነች። አንዳንዴ ሰውን ስንወድ ፍቅራችን የወደድነው ሰው ላይ ጎዶሎውን ሞልቶ ያሳየናል መሰል ሮዛ ለእኔ ጉድለት የላትም። አዎ ፍቅር በራሱ ሰልካካ አፍንጫ፣ ሃር ፀጉር፣ አሎሎ ዓይን፣ መቃቁመት፣ በረዶ ጥርስ፣ …ከንፈር ሳይሆን አይቀርም። ለነገሩ ሮዚን የሚጠይቃት ጎረምሳ ብዛትም ለሳቢነቷ ተጨማሪ ምስክር ነው።

ሮዛን የጠየቁትን ጎረምሶች እኔና ሮዚ የዕለት ውሎ መመዝገቢያችን ላይ እንመዘግብ ነበር። የሚገርመው ዳይሪያችን አንድ ነበረች፣ ሁለታችንም ውሏችንን የምንመዘግብባት። ለሮዛ የሚላክ የፍቅር ደብዳቤን አብረን ነው የምናነበው። እኔም ለሴት የምልከውን አብረን ጽፈን እናውቃለን። ታዲያ ሮዛ ብትሞት
ለፍቅር አትሸነፍም፤ ትምሕርቷ ላይ አትደራደርም፤ ልቧ የገባም ወንድ የለም። “ወንዶች ጅል
ይመስሉኛል…” ትላለች በተደጋጋሚ።

አባቷ እናቷ ላይ ያደረሰው በደል ሁሉ (ነፍሱን ይማረውና) መጥፎ ጠባሳ ጥሎባታል። አባቷ ሲበዛ
መልከመልካም ሽቅርቅር ሰው ነበር። በዛ ላይ አይጠጣ፣ አያጨስ በጊዜ ነው ቤቱ የሚገባው ፤ በጊዜ ገብቶ ታዲያ ዋና ስራው እናቷን አስቴርን መደብደብ ነበር። እነሮዚ ቤት አባቷ ካመሸ ደስታ ነበር
።እንዴ!የአስቴርን ጥርሷን ሁሉ አውልቆት ወርቅ ጥርስ አስተክሎላታል። ሮዛ ልብ ውስጥ የነበረውን ወንድን የመሻት ተፈጥሯዊ ስሜት ግን ነቅሎ ባዶውን ትቶታል። (አሁንም ነፍሱን ይማረውና፤ የሚምረው እንኳን አይመስለኝም...)

እና…ትላንትና እሑድ እነሮዛ ቤት አንድ ሰውዬ መጣና በሩን አንኳኳ። ቡና ተፈልቶ ተመስጠን ፊልም እያየን ነበር። እንዳጋጣሚ ለበሩ የምቀርበው እኔ ስለነበርኩ ተነስቼ በሩን ከፈትኩ። ከተወለደ
ጀምሮ ዛሬ ገና የዘነጠ የሚመስል፣ ሙሉ ግራጫ ልብስ የለበሰ፣ ቀጫጫና ረዥም ሰውዬ በሩ ላይ እየተሽቆጠቆጠ ቆሟል። ሰውዬው ሙሉ ልብስ ቢለብስም ለምን እንደሆነ እንጃ ሙሉ ልብስ የለበሰ አይመስልም። መቼም ሕይወት በሰዎች ዓይን ፊት ስታጎልህ እንኳን ሙሉ ልብስ፣ ሙሉ ብርጌድ አሰልፈህ ብትመጣ ግርማ ሞገስ የሚባል ነገር አይጠጋህም። ቅልል ትላለህ። “ቀትረ ቀላል” ትሆናለህ።

ሰላም አልኩት። እየተሽቆጠቆጠና ዳማከሴ እንደሚያሽ ሰው እጆቹን እርስ በእርስ እያፋተገ ሰላምታዬን
ከወገቡ ጎብጦ መለሰልኝ። ከርዝመቱ እና ከእንቅስቃሴው ፍጥነት የተነሳ ለሰላምታ ከወገቡ ሲታጠፍ ከላይ ተምዘግዝጎ የመጣ የሆነ ወገቡ ላይ ተሰብሮ የሚወድቅ ባሕር ዛፍ ነበር የሚመስለው።

“ይ…ሄ የነሮዛ ቤት ነው አይደል…?” አለና፣ ራሱ መልሱን መለሰው። “አዎ ነው አውቀዋለሁ።” አነጋገሩ
የሚርበተበትና ከአፉ የሚወጡት ቃላት በጠባብ በር እንደሚወጣ ብዙ ሕዝብ የሚገፋፉና የሚተሻሹ
ይመስላሉ፤ ዝም ብዬ ስመለከተው።

እ… የሮዛ እናት ይኖራሉ ወይም አባቷ?” አለና መልሶ ለራሱ፣ “አውቃለሁ አባቷ እንኳን በሕይወት የሉም…ግን እናቷ” ተርበተበተ።

"እናቷ አለች” አልኩት።

ልግባ ?” ሲል ገነት በር ላይ የቆምኩ መልአክ የሆንኩ እስኪመስለኝ ወደ ቤቱ ውስጥ በጉጉት ዓይኖቹን ልኮ ለማየት እየሞከረ ለመነኝ።

“ግባ…” ብዬ በሩን ለቀቅኩለት፤ ገባ። አረማመዱ የሆነ የሚጮኽ ዓይነት ነው። የሚራመድ ሳይሆን
በአንድ እግሩ ብቻ የሚዘል ዓይነት ላይ ታች ያረገርጋል። እድሜው ሠላሳ አምስት ቢሆን ነው። የሮዛን
እናት በሁለት እጁ ሰላም ብሎ ወደ ሮዛ ዞረ። ርሷንም በሁለት እጁ ሰላም አላት። ሲመለስ የእኔን እግር ረገጠና ተንገዳግዶ ጠረጴዛው ጫፍ ላይ ተቀምጦ የነበረውን ባዶ ሲኒ ከነበለው። ሲኒው ስር ቀርቶ የነበረው የረጋ የቡና ዝቃጭ ምንጣፉ ላይ ጥቁር ደም መስሎ ተረጨ። ይሄ ሰው መርዶ ይዞ ነው እንዴ የመጣው? ምን ያደናብረዋል…?

ከአስቱ ፊት ለፊት ተቀመጠ። ሁላችንም ምን እንደሚል ለመስማት ዓይን ዓይኑን እናየው ጀመር።

እ ….ሰላም ነዎት ታዲያ እትዬ ..አስቴር?” አለ።

እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ።” ፊቷ ላይ የት ይሆን የሚያውቀኝ የሚል ግርታ ይታያል።በፈገግታ ልትሸፍነው ብትሞክርም አልተሳካላትም።

“ልጆች ሰላም ናቸው ? ማለቴ ልጅዎት? አዎ አንድ ልጅ ብቻ ነች ያለችዎ አለ ወደ ሮዛ አየት
አድርጎ መልሶ እየተሸቆጠቆጠ ወደሚያፍተለትለው መዳፉ አቀረቀረ። ላቡ ቅንድቡ ላይ ችፍፍ ብሎ በግልፅ ይታያል ሲጨንቅ። ደግሞ ያጠናውን ነበር የሚናገረው፤ ያስታውቃል። ላቡን በመዳፉ አንዴ ሞዥቀውና መዳፉን አየት አድርጎ በኮቱ እጅጌ እንደገና ግንባሩን ጠረገው።

“ደህና ናት” አለች አስቱ፤ እናም ኮስተር ብላ አየችኝ። ትከሻዬን በቀስታ ወደ ላይ ሰበቅኩት። ያየችኝ ማነው…?” ማለቷ ሲሆን እኔም በትከሻዬ ምላስ እኔ 'ጃ” አልኳት። ለትንሽ ደቂቃ እንግዳውም አቀርቅሮ፣ እኛም እንግዳው ላይ አፍጥጠን እንደቆየን እንግዳው ተናገረ።

አንተ አብርሃም ነህ … እዚህ ጎረቤት ያለኸው ልጅ አይደለህም እንዴ…?” አለኝ።

“…አዎ”

“ያው ለሮዛ ወንድሟ ማለት ነህ ..፤ ማዘርም ጋር ትቀራረባለህ ያው ልጃቸው ማለት እኮ ነህ…።

“አዎ ያው ልጅ ማለት ነው!” አለችው አስቱ።

“ጥሩ!ያው የቤተሰብ ጉዳይ ስለምናወራ ላረጋግጥ ብዬ ነው።” አለ ወደ አስቱ በፈገግታ እየተመለከተ።ፈገግታው ይጨንቃል። ከንፈሮቹ ወይ በደንብ አይከፈቱ፣ ወይ አይገጠሙ፣ እንዲሁ ሄድ መለስ እያሉ
ይንቀጠቀጣሉ። በማጭድ የተጋጠ የሚመስል ፂሙ ቅሪቱን አጥንታም ጉንጩ ላይ ዘርቶት በሽተኛ አስመስሎታል። ጥላሸት የተዘራበት አጥንታም ጉንጭ !ደግሞ እኮ ሲያደርጉ አይቶ ኦ' ቅርፅ!! አፉ በፂሙ ተከብቦ ሲታይ በኮሸሽላ ዙሪያውን የታጠረ የደረቀ የውኃ ጉድጓድ ይመስላል። ወቸ ጉድ! ምን ሊል ይሆን…? ጭንቀት ገደለኝ።
👍22